ውድ የሜዲካል ኢንፎ ተከታታዮች ዛሬ ይዘንላችው የቀረብነው ኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ ነው ተከታተሉን፡፡
♦♦ኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ♦♦
************************************
ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ ፡- በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Cesarean
section) ፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት?
👉በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት?
1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት
2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ
3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ
4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው
5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር
6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና
7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት
👉 ጥቅሙ፡-
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል።
👉ጉዳቱ፡-
1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም።
2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ።
3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል።
4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው።
5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ .ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡
👌👌👌 ሜዲካል ኢንፎ ምርጫዎ ያድርጉ # የጤና ችግር # ላይ አስቀድሞ # ምክሮችን የሚለግስ # የሚያስተምር # ተቀዳሚ # የጤናዎ # አጋር !! ይመረጡት # ይጠቀሙበታል !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
♦♦ችላ ሊባሉ የማይገቡ ሰውነታችን ለውጦች♦♦
********************************
የሰው አካል የራሱ የአሰራር ዘዴ አለው እና በሰውነታችን ውስጥ በተመሳሳይ ሰዓት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነገሮች ይከናወናሉ፡፡ ሰውነታችን ችግር በሚያጋጥመው ጊዜ እንድናውቀው ያደርገናል።ነገር ግን እነዚህን ምልክቶች ችላ በማለት የከፋ ደረጃ እንስከሚደርሱ እንጠብቃቸዋለን፡፡ ስለዚህ እነዚህን የማስጠንቀቂያ ምልክቶች በማወቅ በጊዜ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
1. የእንቅልፍ ችግር፣ መሸማቀቅ እና ግልፍተኝነት ፡-ይህ ምልክት ማለት ማግኒዢየም እና ፖታሲየም በሰውነታችን ውስጥ ዝቅተኛ ናቸው፡፡ ለውዝ፣ ሱፍ እና ተልባ ይመገቡ ለፖታሲየም ደግሞ ስኳር ድንች፣ አረንጓዴ እና ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፣ ስፒናች ጎመን፣ የስዊዝ ቆስጣ
2. ጨው የበዛበት ምግብ መውደድ፡-ይህ የሰውነት መጉረብረብ ፣መመረዝ ወይም የመራቢያ አካል ኢንፌክሽን ሊሆን ይችላል፡፡
3. የቆዳ መድረቅ ፡-የቫይታሚን ኢ እጥረት በሚኖርበት ጊዜ የሚከሰት ሲሆን የአሳ ዘይት፣ ለውዝ እና የአትክልት ዘይት ይመገቡ፡፡
4. ጣፋጭ ነገሮችን መውደድ ወይም መፈለግ ፡-ይህ የሚያሳየው መጨነቅ፣ መርበድበድ እና ድካም ነው፡፡ ስለዚህ ግሉኮስ ፈጣን እረፍት ይሰጠናል ብለን እናስባለን ነገር ግን በምትኩ ማር እና ደረቅ ቸኮሌት ይውሰዱ፡፡
5. የድድ መድማት ፡-ይህ የቫይታሚን ሲ እጥረት ነው ስለዚህ ሻይ ይጠጡ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ይመገቡ፡፡
6. ጥሬ ምግቦችን መውደድ ወይም መፈለግ ፡-ከጨጓራ ወይም ከጉበት ጋር የተያያዘ ሲሆን ጥሬ ምግቦች የሆድ መነፋት እና ቁርጠትን ያስታግሳሉ፡፡
7. የክርን ቆዳ መድረቅ ፡-የቫይታሚን ኤ እና ሲ እጥረት ሲሆን ካሮት፣ ብርቱካን፣ አትክልትና ፍራፍሬ ይመገቡ
8. የባህር ውስጥ ምግቦችን በጉጉት መፈለግ ፡-የባህር ውስጥ ምግቦችን ለመመገብ በጣም የሚጓጉ ከሆነ የአዮዲን እጥረት አለብዎት ማለት ነው።
9. ለመራራ ምግቦች ከፍ ያለ ጉጉት መኖር ፡-መራራ ምግቦችን ለጉበት እና የሃሞት ከረጢት ተግባር/ ሥራ ያስፈልገናል ስለዚህ ሎሚና ክሬይንቤሪ ይመገቡ፡፡
10. የፀጉር እና ጥፍር መሰባበር ፡-ሰውነትዎ የካልሲየም እና ቫይታሚን ቢ እጥረት በሚኖርነት ጊዜ ይህን ምልክት እናስተውላልን ስለዚህ ወተት፣ ድንች፣ ጥራጥሬ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ እና ስንዴ ይመገቡ፡፡
👌👌👌 ሜዲካል # ኢንፎ # ምርጫዎ ያድርጉ # የጤና ችግር # ላይ አስቀድሞ # ምክሮችን የሚለግስ # የሚያስተምር # ተቀዳሚ # የጤናዎ # አጋር !! ይመረጡት # ይጠቀሙበታል !!!
@mediccalinfo
@mediccalinfo
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
plsss join us🙏
👇👇👇👇
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንቀርባለን
❕❕❕❕❕❕❕
ዛሬ ፆም የመፆም የጤና ጥቅሞች ይዘን እንቀርባለን።
❕❕❕❕❕❕❕
እንዲለቀቅ like አርጉልን እና አብሮነታችሁን አሳዩን
Like Like🙏
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንቀርባለን
❕❕❕❕❕❕❕
ዛሬ ስለ ራስ ምታት
ይዘን እንቀርባለን።
❕❕❕❕❕❕❕
እንዲለቀቅ like አርጉልን እና አብሮነታችሁን አሳዩን
Like Like🙏
ውድ የሜዲካል ኢንፍ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንቀርባለን
❕❕❕❕❕❕❕
ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች መመገብ ያለባቸው እና የሌለባቸው ነገሮች
❕❕❕❕❕❕❕
ዛሬ post ይደረጋል like
👇👇👇
ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንቀርባለን
❕❕❕❕❕❕❕
ጠዋት ሲነሱ ሊያሰተውሏቸው የሚገቡ የጤና ሁኔታዎች ይዘን እንቀርባለን።
❕❕❕❕❕❕❕
እንዲለቀቅ like አርጉልን እና አብሮነታችሁን አሳዩን
Like Like🙏
ውድ 😍የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንመጣለን።
ዛሬ የሎሚ ጭማቂ የጤና ጥቅሞች ይዘን እንመጣለን።
ላይክ በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን እንዲለቀቅ Like Like
🙏🙏
MEDICAL INFO
ውድ 😍የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ስለ....
«ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት»
የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ።
- ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ
- የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት
- ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ
- የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ
- የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል
በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት
በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ።
መድሃኒቱን በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት፦
• አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ
• አራት የሻይ ማንኪያ ማር
• አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል
አዘገጃጀት
• ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት
• በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ
• ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት
• ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት
ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል።
MEDICAL INFO ምርጫዎ ያድርጉን ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ፦
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ስለ👇
♦♦ጤንነቶን የሚጠብቁበት ዘዴዎች♦♦
*********************************ይዘን እንቀርባለን
1. በቀን ለ10 ደቂቃዎች የእግር ጉዞ ማድረግ
2. አነስተኛ ክብደትን ለማንሳት መሞከር ጡንቻን ያጠነክራል
3. በቀን ከሚመገቡት ምግብ ጋር ፍራፍሬ ለማከል ይሞክሩ
4. ከለት ተእለት ምግቦት ውስጥ ስኳር ያላቸውን ነገሮች ያስወግዱ
5. ኦቾሎኒ የመመገብ ልምድ ይኑሮት
6. አሳ አዘውትረው ለመመገብ ይሞክሩ
7. ሁልጊዜ እጆትን በንጽህና ይያዙ
8. መልካም አስተሳሰብ ይኑሮት
9. አልኮል መጠጥን አያዘውትሩ
10. ጭንቀትን ይቀንሱ
ሜዲካል ኢንፎ ማንኛውም የጤና ችግሮች ካጋጠመዎት ምርጫዎ ያድርጉን !!! ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
☝️☝️
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ እንጠቀም ፡፡ አዕምሮአችንን በክፉ ዜናና በጠባብ አስተሳሰብ ሳይሆን በገንቢ ዕውቀትና መልካም ሃሳብ እንሙላ፡፡
መልካም ጊዜ!!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ፦
👇👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
የሥራ ማስታወቂያ
New job vacancy
Vacancy Announcement
• position:— Gp Doctor
• experience:— 3yrs
• workplace:— Gurague/ Wolkite area
• salary:— 20,000birr/month
Any one who fulfils and intersted can contact with: 0983848760
ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንመጣለን።
ዛሬ ስለ የሽንት ባንባ ኢንፌክሽን እናቀርባለን።
እንዲለቀቅ like አርጉልን እና አብሮነታችሁን አሳዩን
Like Like🙏🙏
MEDICAL INFO
ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንመጣለን።
በየቀኑ የምናደርጋቸው ለካንሰር የሚያጋልጡን ነገሮች።
እንዲለቀቅ like አርጉልን እና አብሮነታችሁን አሳዩን
Like Like🙏🙏
MEDICAL INFO
እንኳን አደረሳችሁ ፤ እንኳን አደረሰን !!
በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የይቅርታ ይሆን ዘንድ እንመኛለን !
መልካም በዓል !
MEDICAL INFO
✝@mediccalinfo✝
✝@mediccalinfo✝
Pharmacology Update::
Topic :: Antidotes for Anticancer drugs Associated Toxicity::
Hand Foot Syndrome :: PYRIDOXINE
Methotrexate Associated Mucositis and Bone Marrow Suppression :: Leucovorin ( Folinic Acid) or Folicacid
Pemetrexed Associated Mucositis and Bone Marrow Suppression :: Leucovorin ( Folinicacid ) or Folicacid with Vitamin B12
Anthracyclines Induced Cardiotoxicity and Vesication :: Dexrazoxane...
Cyclophosphamide and Ifosfamide induced Heamorrhagic Cystitis :: MESNA
Hyperuricemia due to Tumour Lysis Syndrome:: Allopurinol / Rasburicase
Mucositis Associated with Chemotherapy :: PALIFERMIN( Recombinant Keratinocyte Growth Factor)
Neutropenia :: FILGRASTIM
Thrombocytopenia :: OPRELEVKIN
Anaemia :: Epoetin Alfa / Darbopoetin Alfa
Irinotecan induced delayed diarrhoea :: High dose Loperamide
Meclorethamine associated Vesication
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
plsss join us🙏
👇👇👇👇
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
@EthiopiawinNN
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ችላ ሊባሉ የማይገቡ የሠውነታችን ለውጦች ይዘንላቹ እንቀርባለን።
❕❕❕❕❕❕❕
እንዲለቀቅ like እያረጋቹ አብሮነታችሁን አሳዩን
🙏🙏🙏
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ተከታታዮች እንዴት ዋላች እንኳን ለገና ፆም በሰላም አደረሳቸሁ !!!
@mediccalinfo
መጪው ጊዜ የገና ፆም ወቅት እንደመሆኑ የፆመኛ ትሩፋቶች ማውሳቱ መቼ የማይፃረር ወቅታዊ ተግባር ነው።
ጾም የመፆም የጤና ጥቅሞች
********************************
@mediccalinfo
1. ጾም የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዮት ጾም የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ አስተማማኝ መንገድ ነው። ለተወሰነ ወይም ለተገደበ ሠዓት መጾም ሰውነታችን ከመደበኛው ጊዜ በበለጠ ፋት ሴሎችን እንዲያቃጥል ይረዳዋል።
2. ጾም የኢንሱሊን ስሱነትን ይጨምራል
ጾም ለኢንሱሊን (Insulin) ስሱነት(ሴንሲቲቭነትነ) አሉታዊ ተጽእኖ አለው። ከማይጾሙባቸው ቀኖች በተሻለ ካርቦሃይድሬት (ስኳር) እንዲቋቋሙ ይረዳዎታል። ጥናቶች እንደሚያሳዮት ከጾም በኋል ሴሎች ግሉኮስን ከደም ውስጥ እንዲወስድ በመንገር ኢንሱሊን ውጤታማ ተግባርን እንዲወጣ ይረዳል።
3. ጾም የምግብ መፈጨትን ተግባር ይጨምራል
የሚቆራረጥ ጾም መጾም የምግብ ስልቀጣ ሥርዓት እረፍት እንዲያደርግ ይረዳዋል ይህም ሜታቦሊዝማችን በተሳካ ሁኔታ ካሎሪን እንዲያቃጥል ዕድሉን ያገኛል። የምግብ ስልቀጣዎ ደካማ ከሆነ ይህ አጋጣሚ ምግብን ሜታቦላይዝ የማድረግና ፋትን የማቃጠል ችሎታዎን ይጨምራል።
4. ጾም ዕድሜን ይጨምራል
እመኑም አትመኑም እውነታው እንዲህ ነው ትንሽ ምግብ የሚመገቡ ከሆነ ረጂም ዕድሜ የመኖር ዕድል አለዎት።
5. ጾም ረሃብን ይጨምራል
እውነተኛ ተፈጥሮአዊ ረሃብን ለማወቅ 12 ሠዓት ወይም 24 ሠዓት ሊበቃ ይችላል። ጾም በሰውነታችን ወስጥ ያሉ ሆርሞኖች እንዲረጋጉ ያደርጋል ስለዚህ ዕውነተኛ ረሃብ ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ።
6. ጾም የአመጋገብ ስርዓትዎን ያሻሽላል
ጾም ምግብ የመመገብ ችግር ላለባቸው ሰዎች ጥሩ ልምድ በመሆን ይረዳል በተጨማሪም በሥራ ወይም ሌላ ቅድሚያ በሚሰጡት ጉዳይ ምክንያት የተስተካከለ የመመገቢያ ሠዓት ለሌላቸው ሰዎች ጾም በጣም ጠቃሚ ነው።
7. ጾም የአእምሮ ሥራን/ተግባርን ያሻሽላል
ጾም የአእምሮን ተግባር ያሻሽላል ምክንያቱም ብሬን ድራይቭድ ኒውሮትሮፊክ ፋክተር (Brain Drived Neurotrophic Factor) የተባለ ፕሮቲን እንዲመረት ያበረታታል ወይም ያደርጋል።
8. ጾም በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል
የተቆራረጠ ወይም የተዘበራረቀ ጾም በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል ምክንያቱም በፍሪ ራዲካል የሚደርስን ጉዳት ይቀንሳል፣ በሰውነት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፍላሜሽንን (Inflammation) ያረጋጋል እንዲሁም የካንሰር ሴል ምርትን ያስተጓጉላል።
9. ጾም ራስን ማወቅና መግዛትን ይጨምራል
ሰዎች በሚያነቡበት፣ በሜዲቴሽንና በዮጋ (Meditation & Yoga) ስፖርት ጊዜ ከህይወት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ወይም እንዲቆራኙ በማድረግ ጾም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል።
10. ጾም ቆዳን ያነፃል ብጉርን ይከላከላል
ጾም ንጽህና የሚያምር ቆዳ እንዲኖረን ይረዳል ምክንያቱም ሰውነታችን ለጊዜውም ቢሆን ከምግብ ስልቀጣ ዕረፍት ስለሚያደርግ የቆጠበውን ጉልበት በሌሎች ስርዓት ላይ ለማዋል ዕድሉን ያገኛል
👉 መልካም የጾም ወቅት እንዲሆንሎ ሜዲካል ኢንፎ ይመኛል!!!
ሜዲካል ኢንፎ ለማንኛውም የጤና ችግሮች ካጋጠመዎት ምርጫዎ ያድርጉን !!! ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ይቀላቀሉን👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
♦♦ራስ ምታት ♦♦
**************
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ተከታታዮች እንደምን ዋላቹ እንደወትሮው ለጤናቹ ይጠቅማል ያልነውን ይዘን ቀርበናል እነሆ፡-
ራስ ምታት እንደ አይነቶቹ ምክንያታቸው እና ምልክታቸው ሊለያይ ይችላል::
የራስ ምታት አይነቶች:-
👉 የመጣጣር ወይም የመሳሳብ አይነት ስሜት ያለው ራስ ምታት(Tension headache)
ዋነኛው የራስ ምታት ነው አዋቂዎችን እና ጉርምስና እድሜ ላይ ያሉትን ያጠቃል መካከለኛ የሆነ ህመም ሲኖረው በሁኔታዎች ይመጣል ይሄዳል ሌላ ምልክቶችም አይኖራቸውም፡፡
👉 ተደጋጋሚ ከባድ ራስ ምታት(Migraine headache)
በጣም ከባድ የሆነ ህመም አለው አበዛኛውን ጊዜ ህመሙ ከ4ሰዓት እስከ 3 ቀን ይቆያል ይህም በወር 4 ጊዜ ሊከሰት ይችላል ከህመሙ ጋር አብሮ ሌሎች ምልክቶችን ያያሉ፡-ለብርሀን ስሜታዊ መሆን፣ ጫጫታ ወይም ሽታ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የጨጓራ መቆጣት ወይም የሆድ ህመም ይሄ ህመም ህፃናት ላይ ከሆነ ቆዳቸው ነጭ መሆን፣ የመደንዘዝ ስሜት እና ደብዛዛ እይታ ትኩሳት እናም የጨጓራ ህመም ይኖራቸዋል፡፡
👉 ችብችብ ያለ አይነት ስሜት(Cluster headache)
ይህኛው የራስ ምታት አይነት በጣም ሀይለኛ ስሜት ያለው ሲሆን በአንድ ዓይን በኩል የመውጋት ህመም ይህም ተከታታይነት ያለው ህመም ይሆናል፡፡
ይህ አይነቱ ራስ ምታት ያለባቸው ሰዎች የመንጎራደድ ባህሪይ ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ህመም ባለበት በኩል ዓይናቸው እንባ ሊወጣው ይችላል የዓይን ሽፋኑ ውድቅ ይላል የመቅላት የዓይናችን ጥቁሯ የመጥበብ በዛው በኩል ሙልት ብሎ ክብድ ያለ ስሜት ይኖረዋል፡፡
ይህ ህመም ያለበት ሰው ህመሙ ሲነሳበት በቀን ከ1-3 ጊዜ ሊያመው ይችላል፡፡
👉 ቋሚ የሆነ ቀን በቀን የሚከሰት ራስ ምታት
ይህ አይነቱ ራስ ምታት 15 ቀን ወይም ከ 1 ወር በላይ እስከ 3 ወር ይቆያል እንዳንዱ ከ4 ሰዓት ያነሰ ነው ይህም ከ 4ቱ የራስ ምታት አይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል
👉 የሳይነስ ራስ ምታት
ጥልቅ የሆነ እና ተከታታይነት ያለው ህመም የጉንጭ አጥንት ላይ፣ግንባራችንን ወይም የአፍንጫችን አጥንት ላይ ይሰማናል ይህ የሚሆነው ጭንቅላታችን ላይ ክፍተት ካለ ሳይነስ እንለዋለን፡፡ ህመሙ ከሌሎች የሳይነስ ምልክቶች ጋር ነው የሚመጣው የንፍጥ መዝረብረብ፣ ጆሮ አካባቢ የመደፈን ስሜት፣ ትኩሳትእና ያበጠ ፊት ይኖረዋል፡፡ትክክለኛ የሳይነስ ራስ ምታት የሚከሰተው ከሳይነስ ኢንፌክሽን ነው ይህም ቢጫ ወይንም አረንጓዴ የመሰለ ፍሳሽ ይወጣል፡፡
👉 ጉዳት ከደረሰብን በኋላ የሚከሰት ራስ ምታት
ጭንቅላታችን ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ከ 2-3 ቀን በኋላ የሚመጣ ህመም ነው
ተያይዞም፡-ደብዘዝ ያለ ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚመጣ ህመም ይኖረዋል
፡-ማዞር
፡-ጭንቅላት ቅልል የማለት ስሜት
፡-ትኩረት የማድረግ ችግር
፡-የማስታወስ ችግር
፡-ፈጣን የሆነ ድካም
፡-ብስጭት
ይህ አይነት ራስ ምታት ለትንሽ ወራት ሊቆይ ይችላል ነገር ግን በሁለት ሳምንት ውስጥ መሻሻል ከሌለ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡
👉 በሆርሞን መቀየር ምክንያት ሚከሰት ራስ ምታት
ይህ አይነቱ ራስ ምታት ሆርሞን ሲቀየር የሚከሰት ሲሆን ሆርሞን ሲስተካከል ራስ ምታቱም ይጠፋል
መንስኤ
• በእንፌክሽን ፡ትኩሳት ወይም በጣም ቅዝቃዜ ሲሰማን
• ጭንቀት
• አካባቢያችን ፡-የሲጋራ ጭስ፡ ከባድ ሽቶ
• ዘር፡-(ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ)
• ጭንቅላት ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ
• የሆርሞን መቀየር (ሴቶች ላይ)
መፍትሄው
• ሃኪም ማማከር
• የጭንቅላት ማሳጅ መጠቀም
• እረፍት መውሰድ
• ውሀ በብዛት መጠጣት
ራሳችንን እየተንከባከብን ሌሎችን እንርዳ
ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ሀሳባችንን ያጋሩ እርሶም ይጠቀሙ
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
♦♦ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች መመገብ ያለባቸው እና የሌለባቸው ነገሮች♦♦
**************************************************************
ውድ የሜዲካል ኢንፎ ተከታታዮች እንደምን ቆያችሁ ዛሬ ልናስገነዝባችሁ የወደድነው ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ምን መመገብ አለባቸው እንዲሁም የለባቸውም የሚለውን ልናስገነዝባችሁ ወደናል ተከታተሉን፡፡
👉 መመገብ ያለባቸው ነገሮች
✅ ጎመን
✅ ሰላጣ
✅ ቀይስር
✅ ቅባቱ የወጣለት ወተት
✅ እርጎ
✅ ሙዝ
✅ አሳ
✅ ጥራጥሬ
✅ ነጭ ሽንኩርት ያለበት ምግብ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
✅ የወይራ ዘይት
👉 መመገብ የሌለባቸው ነገሮች
✅ ጨው
✅ የታሸጉ ሾርባዎች
✅ የታሸጉ ቲማቲሞች
✅ ስኳር
✅ ቀይ ስጋ
✅ ቂቤ
✅ የዶሮ ቆዳ
✅ አልኮል
👉ሜዲካል ኢንፎ ማንኛውም የጤና ችግሮች ካጋጠመዎት ምርጫዎ ያድርጉን !!! ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
♦♦ ጠዋት ሲነሱ ሊያሰተውሏቸው የሚገቡ የጤና ሁኔታዎች ♦♦
*****************************
እንደምን አላችሁ ውድ የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦች ? ጠዋት ሲነሱ ሊያሰተውሏቸው የሚገቡ የጤና ሁኔታዎች እነሆ ፡-
👉 የዓይን ቀለም መቀየር
የዓይን ቀለም መቀየር የጤናዎን ሁኔታዎች ይናገራል። የአይን ቢጫቀለም መያዝ ከቢጫ ወባ ጋር
ይያያዛልየዓይን ቀለም የሚቀይረው የጉበት በሽታ ብቻ አይደለም የዓይን መቅላትም ከአይን ነርቭ
ጉዳት ጋር ሊገናኝ ይችላል ከመጠን በላይ ያለፈ የፀሃይ ብርሃን መጋለጥም ዋነኛ ምክንያት ነው.
👉 ምላስ ፡- ምላስ የጤና ሁኔታዎን ይናገራል. ምላስ ምግብን ለማጣጣም የሚረዳን ህዋስ ሲሆን የተለያዩ ምግቦቸን
እና መጠጦችን ቀለም ለትንሽ ደቂቃ ይዞ የመቆየት በሃሪ አለው ነገር ግን በጠዋት ተነስተን የምላሳችን
ቀለም ስናይ ቢጫ፣ ነጭ ወይም ብርቱካናማ ነገር ተጋግሮበት ሲያዩ የሆነ የውሰጥ ችግር እንዳለ ያመለ
ክታል.የሚከሰተውም የጨጓራ አሲድ ወደ ላይኛው የመተንፈሻ አካል ወይም ወደ ምግብ ቧንቧ እና ወደ
ምላስ በመምጣት ይጋገራል. ጠዋትም ላይ ጥሩ ያልሆነ የአፍ ሽታ እነዲኖር ያደርጋሉ።
👉 ጥፍር ፡- በጥፍር ላይ ቢጫ፣ቡናማ ወይም ነጫጭ ስትራይፕ ወይም ሰረዞችን ስናይ ተራ ምልክቶች እንዳሎኑ ይረዱ
እነዚህ ምልክቶች የቆዳ ካንሰር እየመጣ መሆኑን ያመለክታል.ምልክቶቹ በተከሰቱ ጊዜ በአፋጣኝ ወደ ጤና
ተቋም መሄድ ይኖርቦታል።
👉 የፀጉር ምሳሳት ና ፎሮፎር
ፀጉሮን በጠዋት ተነስተው ሲያበጥሩ ከማበጠሪያው ጋር አብሮ የሚወድቀው የፀጉር ብዛት እየጨመረ ከመጣ
ፀጉሩ እየሳሳ መርገፍ የሆርሞን መዛባት ችግር ነው። ነገርግን የፀጉር መሳሳትና መስባበር ሌላ ከቆዳ ጋር
የተያያዘ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ. በተጨማሪ ፎሮፎር ከማበጠሪያ አልፎ መራገፍ እና የመታየት ደረጋ
ከደረሰ አሳሳቢደረጋ ደርሱዋል ማለት ነው. ለዚህም ምክንያቱ ከመጠን ያለፈ መጨናነቅ እና ውጥረት
የበሽታ የመከላከል አቅምነ ከማዳከም አልፎ የራስ ቅልን ወዝ የመምጠጥ እና የማድረቅ ተፀዕኖም እንለው
ተደርሶበታል።
👌👌👌 ሜዲካል ኢንፎ# # በእያንዳንዳችንን # የጤና ችግር # ላይ አስቀድሞ # ምክሮችን የሚለግስ # የሚያስተምር # ተቀዳሚ # የጤናዎ # አጋር !! ይመረጡት # ይጠቀሙበታል !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
✅ ✅ join
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
ውድ 😍የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ስለ....
የሎሚ ጭማቂ ጥቅሞች
********
• ጉበትና ኩላሊትን ለማጽዳት።
• የምግብ ፍላጐትን ለመቀነስ።
• ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስን እና የጉዞ ላይ ህመምን ለመቀነስ።
• መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን ለማስወገድ።
• ከአጥንት ጋር ለሚያያዙ በሽታዎች።
• ለብጉርና ቀያይ ነጠብጣቦች።
• ኢንፌክሽንን ለመከላከል።
• ለሳል እና ጉንፋን ህመም።
• በሽታ የመከላከል አቅምን ለመጨመር።
• ለምግብ ስልቀጣ ይረዳናል።
• የልብ ችግርን ለመከላከል።
• ለፀጉር።
• ለጨረር ወይም ራዲየሽን።
• ቁስል ቶሎ እንዲያገግም ይረዳል።
• ለአስም በሽታ።
• ትኩረትን ለመጨመር።
MEDICAL INFO ምርጫዎ ያድርጉን ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ፦👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
እዚ channel ላይ ያላቹ ውድ ተከታታዮቻችንና ቤተሰቦቻችን ስለ ጤናዎ የምንወያይበት የሚጠይቁበት ግሩፓችን
ላይ የሌላቹ ይሄን link 👇
@Medicallnfo
@Medicallnfo
በመንካት ተቀላቀሉን።🙏🙏
ውድ 😍የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንመጣለን።
ዛሬ ፊታችንን ጥርት እንዲል የሚያረጉ መንገዶች ።
ላይክ በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን
እንዲለቀቅ Like Like
🙏🙏
MEDICAL INFO
ውድ 😍የሜዲካል ኢንፎ ቤተሰቦቻችን ዛሬ አዲስ የጤና መረጃ ይዘንላቹ እንመጣለን።
ዛሬ ጤንነትዎን መጠበቅ የምትችሉባቸውን 10 ቀላል መንገዶች ይዘንላቹ እንቀርባለን።
ላይክ በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን እንዲለቀቅ ሞራል ይሆነናል።
እንዲለቀቅ Like Like
🙏🙏
MEDICAL INFO
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምንድን ነው?( Urinary Tract Infections (UTIs)
*********************************************************
የብዙ ሰው ጥያቄ ስለሆነው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀረብን በያላችሁበት ተከታትሉን ሀሳብ አስተያየተዎን ያድርሱን።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ከኩላሊት እስከ ውሃ ሽንት ማስወገጃ ጫፍ ድረስ የሚከሰተ የኢንፌክሽን ዓይነት ሲሆን በማንኛውም ጾታ ላይ እና እድሜ ይከሰታል ፡፡
በአብዛኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃው የውሃ ሽንት የሚከማችበትን የሽንት ፊኛ የአካላችን ነው፡፡በሴቶች ተፈጥሮአዊ የሆነ የሽንት ቧንቧ ጫፍ ማጠር ምክንያት ከወንዶች ይልቅ ተጠቂነታቸው እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ሕመምን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ የስኳር ሕመምተኞችና እርጉዝ ሴቶች ላይም በብዛት ይከሰታል፡፡
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዴት ሊከሰት ይችላል?
⦁ በባክቴሪያ በዋነኝንት (E. coli) በተሰኘ ባክቴሪያ ያመጣዋል
⦁ በቂ ውሀ አለመጠት
⦁ የኩላሊት ጠጠር ካለ
⦁ የንጽህና ጉድለት የመሳሰሉት
⦁ የፕሮስቴት እጢ
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?
✔ የውሃ ሽንት በምንሳወግድበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መሰማት
✔ የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
✔ ከእንብርት በታች የሕመም ስሜት መሰማት
✔ ደም የቀላቀለ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት መኖር
✔ ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት መሰማት
✔ የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ ናቸው
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል ይቻላል?
⦁ በብዛት ፈሳሽ መውሰድ ባክቴሪያ በሽንት ቧንቧ ውስጥ እንዳይቀመጥ በማድረግ ይከላከላል፡፡
⦁ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እና ከተፀዳዱ በኋላ የግል ንጽሕናን መጠበቅ ተገቢ ነው፡
⦁ ሽንት አለ መቋጠር
⦁ ከተፀዳዱ በኋላ ከፊት ወደ ኋላ መታጠብ
⦁ ቶሎ ቶሎ አለመታጠብ፣ ሳሙና ቅባት ብልትን አለመቀባት
MEDICAL INFO ምርጫዎ ያድርጉን ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ይወጡ !!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ፦
Join Us👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
♦♦ በየቀኑ የምናደርጋቸው እና ለካንሰር የሚያጋልጡን ነገሮች♦♦
********************************************
ውድ😍 የMEDICAL INFO ተከታታዮች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በየቀኑ የምናደርጋቸው ግን ሳናስተዉል ለጤናችን ጠንቅ የሆኑ እና የካንሰር ህመም ሊያጋልጡን የሚችሉትን ነገሮች በማወቅ እንድትጠነቀቁ እና ጤንነትዎን እንዲጠብቁ የሚያስችል ተግባርዎ የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትልብዎ እንደሚችሉ ልናስገነዝባቹ ወደድን ይከታተሉን።
1.በጨረር የሚደረጉ ምርመራዎች፡- ለምሳሌ ራጅ፣ ሲቲ ስካን፣ማሞግራፊ ፣ራዲዮቴራፒ…… ለምርመራው ሲባል ጨረር ስለሚለቀቅ በተደጋጋሚ ምርመራወን የምናደርግ ከሆነ ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል ስለዚህ 1 ሰው የጨረር ህክምና የሚያደርግ ከሆነ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር የ6 ወር ልዩንት መኖር አለበት።
2.የላብ ማጥፊያ እና የጠረን መቀየሪያ(ዲዮድራንት)፡- ይህም የሚከሰተው በዲዮድራንት ውስጥ የሚገኘው አልሙኒየም አማካኝነት ሲሆን ይህንን በብብታችን ላይ በምንጠቀምበት ጊዜ ለጡት ካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጋል ስለዚህ በቀላሉ የሚዘጋጁ የጠረን መቀሪያ ስልቶችን መጠቀም ይቻላል ለምሳሌ ሎሚ
3.በምንመገበው ስጋ እና ወተት ውስጥ የሚጨመሩ ሆርሞኖች፦ ይህም ለከብቶች በሚሰጡ ሰው ሰራሽ ሆርሞኖች የሚከሰት ነው።
4.ሳሙናዎች፣ ሻምፑዎች እና ክሬሞች፦ ይህን በቆዳችን እና በፀጉራችን በምንጠቀምበት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል በተለይ በተሰነጠቀ ቆዳ ላይ በምንጠቀምበት ወቅት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
5.መርዛማነት ያላቸው የውብት መጠበቂያዎች፦ እነዚህ ምርቶች በፋብሪካ ውስጥ ያለፉ የውበት መጠበቂያ ምርቶች በምንጠቀምበት ወቅት በመጀመሪያ የቆዳችንን ባህሪ ማወቅ ያስፈልጋል እና በውስጣቸው ንጥረ ነገር የያዙ ስለሆኑ ቆዳን ዘልቆ የመግባት አቅም ስላላቸው ለካንሰር ተጠቂ እንድንሆን ያደርገናል እለዚህ ተፈጥሮአዊ የውበት መጠበቂያ ዘዴዎችን ቢጠቀሙ ጠቃሚ ነው።
6.ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች፦ ማጣፈጫዎችን የሚያካትቱበት ነገሮች አብዝተን የምንጠቀም ከሆነ ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጉናል ለምሳሌ ከረሜላ፣ ለስላሳ መጠጦች…….
7.ከአኩሪ አተር የሚሰሩ ምርቶች፦ ለምሳሌ ሶያ ወተት ያለው ምግብ በውስጡ ሄማግሉቲኒን እና የደም መርጋትን የሚያስከትለውን ንጥረ ነገር ይዟል እና የኢስትሮጅን መጠንን ከፍ በማድረግ ለልብ ህመም ያጋልጠናል በተጨማሪም እነዚህን ምርቶች በብዛት መጠቀም ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል።
8.ፍሎራይድ የተጨመረበት ውሃ፦ በብዛት ፍሎሪድ በውስጡ የያዘ ውሃ በምንጠቀምበት ወቅት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ማእድናትን አጥቦ በማውትጣት ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያዳክመዋል ስለዚህ ለካንሰር ተጋላጭ ያደርገናል።
9.መድሃኒቶች፦ በብዛት የምንወስዳቸው ለተለያየ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች
10.የታሸጉ ምግቦችን በብዛት መመገብ እና ሰው ሰራሽ ስኳር ማብዛት
11.ሲጋራ ማጨስ (ለሳንባ ካንሰር እንድንጋለጥ ያደርጋል)
👌 ስለዚህ እነዚህን ነገሮች መጠቀም ለካንሰር ተጋላጭ ሁኔታዎች እንደሆኑ ተረድታቹ ከእነዚህ ጉዳቶች እራሳቹን እንድትጠብቁ ሜዲካል ኢንፎ መልእክቱን ያስተላልፋል።
የእኛ የሜዲካል ኢንፎ መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!!!
👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ ቤተሰብ ይሁኑ፦
👇👇👇👇
✅ @mediccalinfo
✅ @mediccalinfo
✅@mediccalinfo
✅ @mediccalinfo
Corona VIRUS Defensiv
።።።።
በሆስፒታሎች (በለይቶ ማከሚያ ) እየተወሰዱ ያሉ መድሀኒቶች
1.ቪታሚን c 1000
2.ቪታሚን E
3.ለ 10...11 ሰአታት ለ,15ደቂቃዎች የፀሃይ ብርሃን ላይ መቀመጥ
4 እንቁላል መመገብ
5. እረፍት መውሰድ (ከ7..8 ሰአታት መተኛት )
6.1.5 ሊትር ውሃ በየቀኑ መጠጣት
7.ሁሉም ምግቦች ሞቃት መሆን አለባቸው (ቀዝቃዛ አደለም )
በሆስፒታል ውስጥ የሰውነትን የመከላከል አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ይሄ ነው።
# የኮሮና ቫይረስ ph
ከ 5.5....8.5 ድረስ ተለዋዋጭ ነው
ስለዚህም ቫይረሱን ለመግደል ከቫይረሱ አሲድነት በላይ የሆኑ የበለጠ የ አልካላይን ይዘት ያላቸውን ምግቦች መመገብ ነው
ለምሳሌ
አረንጓዴ ሎሚ....9.9 ph
ቢጫ ሎሚ......8.2 ph
አቮካዶ...15.6 ph
ጋሪክ...13.2ph
ማንጎ...8.7ph
ታንግራይን...8.5ph
ፓይን አፕል ....12.7 ph
ወተር ክረስ...22.7ph
ብርትኳን ....9.2ph
የቫይረሱ ምልክቶች
1.የጉሮሮ ማሳከክ(መቁሰል)
2.የጉሮሮ መድረቅ
3.ደረቅ ሳል
4.ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
5.ለመተንፈስ መቸገር
6.ለማሽተት መቸገር
እና ሎሚ በሞቀ ውሀ መጠጣት ቫይረሱ ገና ሲጀምር ሳንባ ጋር ሳይደርስ እንዲገለው ይረዳል ።
ይሄንን መረጃ ለራሳችሁ አታስቀሩት
ለቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁ አጋሩት።
ጥሩ ጤና እና ረጅም እድሜ እመኝላችኋለሁ።
MEDICAL INFOን ምርጫችሁ ስላደረጋቹ እናመሰግናለን🙏🙏
ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo
MNEMONIC
Hailey Hailey disease
AFB Die at High Temp
➡️A- Autosomal dominant
➡️F- Flaccid vesicles on flexures
➡️B- Benign familial chronic pemphigus
➡️Die- Decreased desmosomes
➡️High- History of multiple relapse & remissin, Family history positive
➡️Temp- Third- fourth decade (Age of presentation)
👇👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
ውድ 😍የMEDICAL INFO ተከታታዬች ዛሬ ደሞ
♦አንድ ነገር ሹክ እንበሎት♦
***************
የትኛውየም ጨለማ በተጠጋኸዉ ቁጥር ልክ ወደ ወደኋላ ያፈገፊጋል።
ወደኋላ እንዲል ወይም እንድታሸንፈዉ የምትፈልገው ነገር ምንድነዉ? ብዙ ልትዘረዝር ትችላለክ! እስኪ ጨለማን ተመልከት መንገዱን በጥቅጥቅ ጨለማ ግርግዳ ታጥሮ ታየዋለህ ከቆምክበት እስኪ ጨለማው ግርግዳ ድረስ የሚታይክ 1ሚትር ሊሆን ይችላል : : እስኪ 1ሚትር ደፍረህ ቅረበው 1 ሜትር ሸሽቶ ታየዋለህ ስለ ችግሩ ብዙ ዕውቀት ሊኖርህ ይችላል። ግን ግን ማሸነፍ አልቻልክም ።1 እርምጃ ወደ ፊት ለመጓዝ ሞክር 1 እርምጃ ወደ ኋላ ቀርቶ ታየዋለህ። የማወራህ ገብቶሀል ? ስለጨለማው ብርታት ሳይሆን ስለማየት ችሎታህ ነው።
#ከኤልዳጊ
የእኛ የ MEDICAL INFO መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!!!
👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ አሁኑኑ Join ያድርጉ፦
👇👇👇
@mediccalinfo
@mediccalinfo
@mediccalinfo