melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ከአዲስ ዘመን ጋር ካደረጉት ቆይታ የተቀነጨበ...

አዲስ ዘመን፡- የአእምሮ ጤና ችግር በአገራችን አለ?

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ፡- አዎ፣ በትክክል አለ። ይሄንን እኛ በሙያው የተሰማራንና የጥናትና ምርምር ስራዎችን የምናከናውን ሰዎች ሁልጊዜ የምናየው ነው። በአለም ላይ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ከ250 በላይ ናቸው። አብዛኞቹ የአዕምሮ ህመሞች አገራችን ውስጥ ይታያሉ።

አዲስ ዘመን፡- በአካባቢ ይገለፃል?

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ፡- አይ፣ ችግሩ አለም አቀፍ ነው። እኛን በተመለከተ በአካባቢ የሚገለፅ አይደለም። ችግሩ አገር አቀፍ ነው። በሁሉም አካባቢዎች፤ በሁሉም ክልሎች አለ። ብዙ አጋላጭ ምክንያቶች አሉ፤ ከእነዚህ አንዱና በአገራችን በአሳሳቢ ሆኔታ እየጨመረ የመጣው የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች እና አደንዛዥ አነቃቂ እጾችና መድኃኒቶችን መጠቀም ነው። አሳሳቢው ደግሞ ችግሩ ወደ ታች፣ ተጋላጭ ወደ ሆነው ክፍል (አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ጭምር) ድረስ እየወረደ መሆኑ ነው። በመሆኑም የሁሉንም የተባበረ ጥረት የሚጠይቅ ነው።

አዲስ ዘመን፡- የአዕምሮ ጤና መታወክ መነሻው ምንድን ነው፤ መፍትሄውስ?

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ፡- አዕምሮ እንደ ማንኛውም የጤና አካል ከአንጎላችን የሚመነጭ ማንነታችን ነው። በመሆኑም፣ የአእምሮ ጤና እንደማንኛውም የአካል ክፍል ጤና የሚታይ ነው። የልብ፣ የኩላሊት፣ ወዘተ . . . የጤና እክል እንዳለው ሁሉ አዕምሮም የጤና እክል ያጋጥመዋል። ሊታወክ፣ ሊታመም ይችላል። ምክንያቶቹ ደግሞ ሰው ሰራሽም፣ ተፈጥሯዊም፤ ውጫዊም ውስጣዊም ሊሆኑ ይችላሉ።

ለምሳሌ- ጦርነት፣ የሰላም ማጣት፣ በውጊያ አካባቢ መገኘት፣ የገዳይ መሳሪያ ድምፅ መስማት፣ ጭንቀት፣ ሱሰኝነት፣ አስጨናቂ ክስተቶች፣ አስገድዶ መደፈር፣ ድህነት፣ የኢኮኖሚ ድቀት፣ የመሰረታዊ ፍላጎቶች አለመሟላት፣ የአካል ጥቃት፣ የተጎሳቆለ የአኗኗር ዘይቤ፣ የጤና ችግሮች ወዘተ. . . እነዚህ ሁሉ የአዕምሮ ጤና ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

መፍትሄዎቹ ደግሞ፦ በተቻለ መጠን እነዚህ አጋላጭ ነገሮች እንዳይኖሩ ማድረግና ከእነዚህም መራቅ ነው። ከባድ የአዕምሮ ህመም የሚባሉት ደግሞ በዘር የመተላለፍ እድልም አላቸው።
እንዲሁም፣ አንድ ሰው እንደ ሌሎች የአካል ክፍሎቹ ሁሉ የአእምሮውንም ጤና ሊጠብቅ፤ ሊንከባከብ ይገባዋል። ጭንቀትን በመቀነስ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማድረግ፣ አቅም በፈቀደ መጠን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፤ እንዲሁም፣ ጤናማ የአኗኗር ዘዴን በመከተል፤ አልኮልን፣ አደንዛዥ እፆችን ባለመጠቀም የአእምሮ ጤናን መጠበቅ ይቻላል። ችግሩ በሚፈጠርበት ጊዜ ፈጥኖ ወደ ባለሙያ በመሄድ ድጋፍና እርዳታን ማግኘት ይገባል።

(አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22ቀን 2015 ዓ.ም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጭንቀት

አንዳንድ ሰዎች በየምክንያቱ ይጨናነቃሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ የምንጨነቅባቸው ነገሮች ቀድሞውኑ መሰረት የሌላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌነት የሚከተለውን የአንድ ጥናት ውጤት እንመልከት፡፡ የምንጨነቅባቸው ነገሮች . . .

1. 40% በፍጹም ለማይደርስብን ነገር

2. 30% ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር

3. 12% ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት

4. 10% ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ)

5. 8% ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ

በፍጹም ለማይደርስብን ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ምክንያታዊነትን ማዳበር ነው፡፡ ሁኔታው ሊደርስብንና ላይደርስብን የሚችልበትን የእድል መጠን አመዛዝነን ያለመድረሱ ሁኔታ ካመዘነ፣ መጨናነቅን የማቆምን ሂደት መጀመርና እየተዉ መሄድ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን እንዲሁ ምክንያት ፈልገው የመጨነቅ “ሱስ” አለባቸው፡፡  ይህ ዝንባሌ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ በአጣብቂኝ ሁኔታ ከማሳለፍና ስሜታችን የጭንቀት ሰለባ ሆኖ ከመክረሙም የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፍጹም የማይደርስ ነገር ተለይቶ ሊታወቅና ከስሜታችን የደም ዝውውር ውስጥ ሊወገድ ይገባዋል፡፡ 

ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ፈጽሞ አንዴ የሆነ ነገር መሆኑንና ምንም ብናደርግ ልንለውጠው እንደማንችል በመቀበል አእምሮን በአዳዲስ ነገሮች መሙላት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለግን ግን እስቲ አንዴ የሆነውንና ያለፈውን ነገር ለመለወጥ የአንድ ወር ጊዜ እንስጠውና የምንችለውን ያህል እንሞክርና ካልቻልን ነገሩን ለመተው ለራሳችን እድል እንስጠው፡፡

ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ መቆጣጠር የማንችለውን የሰውን ባህሪይ ለመቆጣጠር ከመጦዝ ይልቅ መቆጣጠር የምንችለውን የራሳችንን በሆነ ባልሆነው የመጨነቅ ዝንባሌ ለመቆጣጠር መስራቱ ይመረጣል፡፡ ሰዎች ስለአንተና በአንተ ላይ የሚሉት ነገር አንተ ካልፈቀድክለት በስተቀር ምንም ሊያደርግህም እንደማይችል አትዘንጋ፡፡ ብትችል ወሬው አንተ ጋር የማይደርስበትን መንገድ ፍጠር፡፡ ካልቻልክ ደግሞ ወሬው ወደ ስሜትህ የማይደርስበትን ጥንካሬ አዳብር፡፡

ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ ስለጤነታችን የሚያሳስበን ሁኔታ ካለ ያንን ለማስቀረት ወይም ለመቀልበስ የምንችለውን ያህል መሞከር ነው፡፡ ጭንቀታችን ግን “ምናልባት እታመም ይሆን” የሚል ከሆነ፣ ይህ የራስ በራስ ትንበያ እንደሚፈጸም አትጠራጠር፡፡ ጭንቀት በሽታን የመሳብ ባህሪይ አለውና፡፡ 

ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ ከተጨነቅን . . . ያለን አማራጭ በቅድሚያ፣ ሁኔታው በትክክልም የሚያሳስብና በቅጡ ካልያዝነውም የሚስጨንቅ ጉዳይ ስለሆነ ማሰባችንና በመጠኑም ቢሆን መጨነቃችን ትክክለኛው መሆኑን አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቀጥል ያሳሰበንን ሁኔታ በምን መልኩ ብንጋፈጠው ልናሸንፈው እንደምንችል በሚገባ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ አእምሮን በጭንቀት ከመሙላት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በማሰብ መሙላት በብዙ እጥፍ ይመረጣል፡፡ በጉዳዩም ላይ ሰውን ማማከሩም አንዱ መንገድ ነው፡፡

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ውጥረት (Stress) እና ሱስ ያላቸው ግንኙነት!

ውጥረት የሚከሰተው አንድ ሰው ማቅረብ ወይም መስራት የሚጠበቅበት (demand የሚደረገው) ካለው አቅም ወይም መስራት ከሚችለው (ካለው resource, capacity) በልጦ ሲገኝ ነው። ውጥረት ሲከሰት ያስጨንቃል፤ ይህም አዕምሮን የሚለውጡ ኬሚካሎችን (ለምሳሌ፦ አልኮል፣ አደንዛዥና አነቃቂ እፆችን) ለመጠቀም ይዳርጋል። ምክንያቱ ወይ ተጨማሪ ጉልበት ለማግኘት፣ የአዕምሮ ፍጥነትን ለመጨመር ወይም ችግሩን ለመርሳት ነው። ይህ ሁኔታ ጊዜያዊ መፍትሄ የሰጠ ቢመስልም ድግግሞሽ ውስጥ በመክተት ሳያስቡት ለሱሰኝነት ይዳርጋል።

ለምሳሌ:- ተማሪዎች ከስር ከስር ማጥናት ሲገባቸው ፈተና እስኪደርስ ይጠብቁና ማጥናት የሚገባቸው ካላቸው ጊዜ ጋር የማይመጣጠን ይሆንና ውጥረት ውስጥ ይገባሉ፤ በዚህ ጊዜ አዕምሮን የሚያነቃቃ ነገር (ጫት) ወደ መጠቀም ይገባሉ፤ ይህ ነገር ሲደጋገም ለሱሰኝነት ይዳርጋል። ስለዚህ፤ በተቻለ መጠን ውጥረት የሚቀንሱ ተግባራትን መፈፀም፤

ለምሳሌ፦ ተማሪዎች ፈተና እስከሚደርስ ሳይጠብቁ ከስር ከስር ማጥናት፣ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ መከላከል፣ ጤናማ የአቅም መጨመሪያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ ችግሮችን የመፍታት ክህሎትን ማዳበር፣ እንዲሁም ውጥረት ለመቀነስ የሚረዱ ዘዴዎችን መጠቀም (የአተነፋፈስ ስርአትን በመጠቀም፣ በሜዲቴሽን ወይም ፀሎት ራስን ማረጋጋት፣ ጤናማ የመዝናኛ አማራጮችን መጠቀም እንዲሁም የሌሎችን እገዛ መጠየቅ) ውጥረትን ለመቀነስ ይረዳል። ውጥረት አቅማችንን እንዳንጠቀም ሊያደርገን ይችላል። ውጥረት ሲደጋገም እና እየቆየ ሲሄድ ለአዕምሮ ህመም ይዳርጋል። ውጥረትን መከላከል ሱስ እንዳይከሰት ከመከላከያ መንገዶች አንዱ ነው።

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እነዚህን 7ቱን አድርግ!

1. የሌሎችን ልብ ከመጉዳት ተቆጠብ። የህመሙ መርዝ ወደ አንተ ይመለሳል።

2. ሁልጊዜ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን።

3. ራስህን ሚዛናዊ አድርግ። የአንተ አእምሯዊ እራስህ፣ መንፈሳዊ እራስህ፣ ስሜታዊ እራስህ እና አካላዊ እራስህ - ሁሉም ጠንካራ፣ ንጹህ እና ጤናማ መሆን አለባቸው።

4. ማን እንደሆንክ እና ምን ምላሽ እንደምትሰጥ በማስተዋል ውሳኔ አድርግ። ለድርጊትህ ተጠያቂ ሁን።

5. የሌሎችን ግላዊነት እና የግል ቦታ አክብር።

6. መጀመሪያ ለራስህ ታማኝ ሁን። መጀመሪያ እራስህን ማሳደግ እና መርዳት ካልቻልክ ሌሎችን መንከባከብ እና መርዳት አትችልም።

7. መልካም እድልህን ለሌሎች አካፍል። በበጎ አድራጎት ውስጥ ተሳተፍ።

(በራስ መተማመን መጽሐፍ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ይቻላል!

የይቻላል አዎንታዊ አስተሳሰብን ማዳበር ይቻላል፡፡ የ Positive psychology ባለሙያዎች ይህንን ሂደት “Learned Optimism” የሚል ስያሜ ሰጥተውታል፡፡

ያለፈ ጊዜያችን መጪውን ጊዜ እንዳይወስን መወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ ውድቀታችሁ የወደፊት ስኬታችሁን እንዳይወስን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ “ምን እባክህ ከዚህ በፊትም እኮ ሞክሬ አልሆነልኝም! አሁን ምን የተለየ ነገር ይኖራል ብለህ ነው?” የምትሉ ከሆነ ያለፈ ውድቃታችሁ እስር ቤት ውስጥ አሁንም በገዛ ፈቃዳችሁ ለመኖር ወስናችኋል ማለት ነው፡፡

ጥቂት እውን መሆን ያላቻሉ ህልሞቻችሁን ብቻ መሠረት አድርጋችሁ ዓላማ ያለው ሕይወት ከመጓዝ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ ዓለም በብዙ አዳጋች ሁኔታዎች የተሞላች ነች፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች መንገድ ላይ ሲያጋጥሟችሁ ወድቃችሁ አትቅሩ፡፡ በክረምት ወራት ጭቃ በየቦታው ይኖራል፡፡ አንድ እና ሁለት ቀን ወድቃችሁ ስለቆሸሻችሁ ወይም ስለተጎዳችሁ ወይም ሰው ስለሳቀባችሁ “ከዚህ በኋላ ከቤቴ ንቅንቅ አልልም” አትሉም መቼም፡፡ ቁም ነገሩ ከዚህ በፊት የወደቃችሁበትን ምክንያት ማወቅ እና ዳግመኛ ላለመውደቅ ጥንቃቄ አድርጎ ጉዞን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡

ሴሊግማን አዎንታዊ መሆንም ሆነ አዎንታዊ የሆኑ ነገሮችን ማግኘት ሕይወትን ከምንረዳበት ዘዴ (Explanatory Style) ጋር የተያያዘ ነው ይላል፡፡ ይህ ዘዴ ራሳችንን እና ዓለምን አእምሮአችን ውስጥ የምንተረጉምበት መንገድ ነው፡፡ ይህንን እይታችንን፣ አረዳዳችንን፣ አተረጓጎማችንን አወንታዊ ማድረግ መቻል በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን አንድ የስኬት መንደርደሪያ ነው፡፡

ነጋሽ አበበ (ሳይኮሎጂስት እና ፀኃፊ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የለውጥ ሂደቶች!

ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች ያልፋሉ። ለውጥ በአንድ ጀምበር አይመጣም ሂደት ነው። ብዙ መውደቅና መነሳቶች፣ ብዙ ተስፋ ሰጪና ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያቶች ታልፈው ነው ስኬት ላይ የሚደረሰው። ምናልባት አንዳንዶቹ እድል፣ ብርታት ወይንም ብልጠት በታከለበት ሁኔታ ነገሮች ቶሎ ተፈጽመውላቸው ይሆናል።

እንደ Prochaska እና DiClemente እይታ ከሆነ መለወጥ በሽክርክሪት ይመሰላል።

ለዛሬ ለዚህ ጽንሰ ሃሳብ አስረጂ እንዲሆነን ሱስ የማቆም ሂደትን እንመለከታለን፦

Pre-contemplation/ቅድመ ውጥን:-

በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለችግሮቻቸው ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ነው።

ብዙ ሱስ አስያዥ እጾችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች፣ ሱሱ በሚታይ ሁኔታ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው ቢሆን እንኳን፡ ችግሩን አምኖ ከመቀበል ይልቅ፡ ምንም ችግር እንዳልተከሰተባቸው በመካድ (denial) እና ሱሰኛ እንዳልሆኑና ማቆም ከፈለጉ በየትኛውም ጊዜ ማቆም እንደሚችሉ ሲናገሩ ይስተዋላል። በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና እነዚህን ጉዳቶች እንዲያስተውሏቸው (impact assessment) እጽ ተጠቃሚ መሆናቸው የጠቀማቸውንና የጎዳቸውን ነገር (pros and cons) እንዲዘረዝሩ በማድረግ ነገሮችን እንዲያሰላስሉ መፍቀድ ይሆናል።

Contemplation/ውጥን-

በዚህ የለውጥ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ስለ ችግሩ እውቅና ይኖራቸዋል። ንግግሮቻቸው በመለወጥና ባለመለወጥ ሃሳቦች መሃል ይዋልላሉ።

'እጹን መጠቀሜ ከባለቤቴ ጋር እንዳጋጨኝ አውቃለሁ: ግን ደሞ ጓደኞቼን ሳገኝ መጠቀሜ አይቀርም: የክፋ ቀን ወዳጆቼን ማጣት ደሞ አልፈልግም' አይነት ንግግሮች ይስተዋላሉ።

ብዙዎቹ የዕጽ ተጠቃሚዎች እዚህኛው ደረጃ ሲደርሱ ወደ ባለሙያ እርዳታን ለማግኘት የማቅናት እድላቸው ይጨምራል።

በዚህ ወቅት የባለሙያው ሚና ወደ መለወጥ ሃሳቦች እንዲዘነብሉ ማበረታታት ይሆናል።

የችግሩን ግዝፈት እንዲረዱ እና ለውጥ ለማምጣት ብቁ እንደሆኑ እንዲገነዘቡ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሻገር ይቻላል።

Preparation/ የዝግጅት ምዕራፍ

በዚህ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የመለወጥ ውጥናቸው ሚዛን መድፋት ይጀምራል።

Action/ ተግባራዊ የመለወጥ ስራዎች

የለውጥ ስራዎቻቸው መታየት ይጀምራሉ። የሚጠቀሙትን ሱስ መጠን ሲቀንሱ: ከፍ ሲልም ሲያቆሙት ይስተዋላል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉ ሰዎች: የለውጥ ሂደቱን የሚያሳልጡ መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ ይደረጋል።

Maintenance/ ለውጥን ማስቀጠል

በዚህ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች: የቀድሞ ባህርያቸው እንዳያገረሽ ስራን ይፈልጋል።

Relapse/ ወደ ቀደመ ባህርይ መመለስ

ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደቀደመ ባህርያቸው ሊመለሱ ይችላሉ። እነዚህ ምክንያቶችን መለየትና መስራት መቋቋምያ መንገዶችን መፈለግ ያሻል።

የሱስ ማቆም ህክምናዎች እነዚህን የለውጥ ሂደቶቾን መሰረት አድርገው ይካሄዳሉ።

- በግል ወይንም በቡድን ሊሰጡ ይችላሉ።
- የሱስ ማቆም ህክምናን ለማግኘት የተለያዩ የህክምና ተቋም አማራጮች በመዲናችን ይገኛሉ።

Reference
- Curriculum based motivational group by Ann Fields and Internet

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው
(የአእምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

April 2: አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች እንድናውቅላቸው የሚፈልጓቸው 10 ነገሮች፦

1. ካለብኝ ኦቲዝም ይልቅ ትኩረታችሁ እንደማንኛውም ልጅ/ሰው መሆኔ ላይ ይሁን።

2. በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የማገኛቸው መረጃዎች ከአብዛኛዎቻችሁ በተለየ ሊረብሹኝ ይችላሉ።

3. አንዳንድ ነገሮች እንደተነገሩኝ ወዲያውኑ ላልረዳቸው እና ምላሽ ላልሰጥ እችላለሁ።

4. በየእለቱ በድግግሞሽ የሚደረጉ ነገሮችን መረዳት ይቀለኛል። ድግግሞሽ የምማርበት መንገድ መሆኑን እወቁልኝ።

5. ከሌሎች ልጆች ጋር አታነፃፅሩኝ።

6. እጃችሁን እየጎተትኩ የምፈልገውን የማሳያችሁ በቃላት ሀሳብን እንዴት እንደምገልፅ ስለማላውቅ ነው።

7. ስታስተምሩኝ በቃላት ብቻ ከምትነግሩኝ ይልቅ ብታሳዩኝ እና ብታስነኩኝ በቀላሉ ነገሮችን መረዳት እችላለሁ።

8. ከሚያቅተኝ ነገር ይልቅ የምችለው ላይ አተኩሩ።

9. ከሌሎች ጋር መሆን እፈልጋለሁ ግን እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ አስተምሩኝ።

10. ያለምክንያት ውደዱኝ ይገባኛልና።

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

April 2: አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አማራጭ የአእምሮ ህክምና ተቋም- ሴሬኒቲ የአእምሮ ጤና!

ዶ/ር ቢንያም እና ዶ/ር እንግዳ የስነ ልቦና ህክምና ላይ የሚያተኩሩ (Psychologically inclined) የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስቶች ናቸው።

በሴሬኒቲ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ማእከል የሚሰጠው የስነ ልቦና ህክምና ሰዎች የተሻለ የአእምሮ ጤንነት እንዲኖራቸው ከማገዝ ባሻገር ትርጉም ያለው እና ደስተኛ ህይወት እንዲመሩ ያግዛል።

በሴሬኒቲ የሚሰጡት አገልግሎቶች፦

- የአእምሮ ምርመራ (Diagnostic evaluation)
- የአስተሳሰብ መግራት ህክምና (Cognitive Behavioural Therapy)
- በስልክ የሚሰጥ የማማከር አገልግሎት (Tele psychiatry)
- በአእምሮ ጤና ዙሪያ ለድርጅቶች የማማከር አገልግሎት (Mental health Consultancy)

አድራሻ: ሽመክት የገበያ ማእከል 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ብስራተ ገብርኤል።

ስልክ ቁጥር፡ +251946841200

#Mentalwellness

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

"ጥራት ያለው አካቶ ትምህርት ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ሁሉም ህፃናት እና ወጣቶች"

16ተኛው ዓለምአቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን በድምቀት ይከበራል! ቀኑ በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ በጆይ ኦቲዝም ማዕከል ይከበራል።

ቀን፦ እሁድ መጋቢት 24፥ 2015 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3:00- 8፡30 ድረስ፣
ቦታ፦ ሳፋሪ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው ጆይ ኦቲዝሞ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ።

ስለ ኦቲዝም ያገባኛል!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የጤናወግ በክለብሐውስ!

የአልኮል መጠጦች በጤና ላይ የሚያመጡትን ችግሮች ያውቃሉ?

እሁድ (መጋቢት 17) በ Clubhouse ላይ  የአልኮል መጠጦች በጤና ላይ ስለሚያስከትሉት ችግሮች በምናደርገው ውይይት ይቀላቀሉን።

ተጋባዥ እንግዶች፡

ዶ/ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ (የጨጓራ አንጀት እና የጉበት ህክምና ስፔሻሊስት)

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)


⏰ ከምሽቱ 12:00 - 2:00 ሰዓት

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ

ክለብሐውስ ከሌሎዎት ለማውረድ እዚህ ይጫኑ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዳውን ሲንድረም (Down Syndrome) ምንድነው?

March 21: የአለም የዳውን ሲንድርም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው።

በአለም ላይ ከሚወለዱ 800 ህፃናት በአንዱ ህፃን ላይ ዳውን ሲንድረም ሊከሰት ይችላል።

ማንኛዉም ሰዉ ገና በማህፀን ዉስጥ ሲፀነስ 23 ዘረመል ከእናቱ 23 ዘረመል ከአባቱ ወስዶ ሰዉ እንደሚሆን ያውቃሉ?

በሰውነታችን ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ ህዋሶች 23 ዘረመል ከእናት ተጨማሪ 23 ዘረመል ከአባት ወስደው ይሰራሉ። ስለዚህ ባጠቃላይ አንድ ሰዉ 46 ዘረመሎች በእያንዳንዱ ህዋስ ዉስጥ አሉት ማለት ነው።

ሆኖም አልፎ አልፎ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት በተለያየ ምክንያት ሳይሳካ ሲቀር አንደኛ ዘረመል ቦታ (ላይ ሁለት ከመሆን ይልቅ ሶስት ዘረመሎች ይሆናሉ።

ከ 46ቱ ዘረመሎች በ 21ኛው ዘረመል ቦታ ላይ ሁለት ዘረመል መሆን የነበረበት ቦታ ላይ ሶስት ዘረመል ሆኖ ሲገኝ ዳውን ሲንድሮም (Down syndrome) ያለው ልጅ ሊፈጠር ይቺላል።

ስለዚህ በ አጭሩ ዳውን ሲንድረም ማለት የዘረመል አፈጣጠር ችግር ሲሆን ዘላቂ የሆነ የተለያዩ የጤና እክሎች ሊያመጣ የሚቺል ተፈጥሮ ነው።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እሰከ ከባድ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ፦

- የአይምሮ የእድገት ዉስንነት
- የአየር ቱቦ እና አተነፋፈስ ችግር
- የልብ አፈጣጠር ችግር
- የሆርሞን ችግሮች
- የደም ችግሮች
- የአንጀት ችግሮች

Down syndrome ምልክቶቹ ምንድናችው?

ዳውን ሲንድረም ያለበት/ባት ህፃን የሚከተሉት አካላዊ ምልክቶች ይታዩባቸዋል። ለምሳሌ፦

- ጠፍጣፋ እና ለየት ያለ የፊት ገፅታ
- ከፈት ያለ አፍ እና ተለቅ ብሎ የሚታይ ምላስ
- አጭር አንገት
- ዝቅ ያለ ጆሮ
- የአይን ቅድ (አከፋፈት) አቀማመጥ ወደ ላይ ከፍ ማለት
- የአይን ሽፋሺፍት ቆዳ መብዛት
- ደካማ/የላላ ሰውነት ጡንቻ
- አጭር እና ትንሽ መዳፍ
- አጫጭር ጣቶች
- አንድ ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመር እና የመሳሰሉት ሊኖሩት ይችላሉ።

አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ባህሪ!

''ባህሪ ሁሉም ሰው የራሱን ምስል የሚያሳይበት መስታወት ነው'' ይለናል ታዋቂው ጀርመናዊው ደራሲና ጸሓፊ ጆሃን ዎልፍ ጋንግ ቮን ጎተ

ከፍላጎቶቻችን አንጻር ምን አይነት ባህሪ ነው በተለያየ ጊዜና ቦታ የምናሳየው?

ባህሪያችን ለሚሰሙን ስሜቶች፣ ለምናስባቸው ሃሳቦች እንዲሁም በአካባቢያችን ለሚፈጠሩ ነገሮችና ሁነቶች በምንሰጠው ምላሽ የተነሳ በዕውን የሚታይና የተገልፀ ማንነታችን ነው።

ታዲያ በሕይወት መንገዳችን ከግቦቻችንና ከዓላማዎቻችን አንጻር ምን አይነት ባህሪ እናሳያለን፣ እናጸባርቃለን?

ግቦቻችንንና ዓላማዎቻችንን ለማሳካት በልበሙሉነት መተግበር የሚገባንን ተግባር መተግበር፣ መክፈል ያለብንን መሰዋትነት በመክፈል ወደ ከፍታው ወደ ግባችን እየተጠጋን ነው ወይስ ከግባችንንና ከዓላማዎቻችን ተቃራኒ የሆኑ ባህሪያትን በማሳየት ፍላጎቶቻችንን እንዳይሳኩ ባለማስተዋል እያጨናገፍናቸው ነው?

ማናችንም ብንሆን በህይወት ሂደት ውስጥ ማሳካት የምንፈልጋቸውን ግቦች ብቻ ማስቀመጥ በቂ አይደለም።

ልናሳካቸው የምንፈልጋቸውን ግቦችና ፍላጎቶች እውን እንዲሆኑ በሂደቱ ላይ የምናሳያቸው ባህሪያት ወሳኝና መሰረታዊ ናቸው።

(ዳንኤል አያሌው)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ነጻነት ያለው አእምሯችን ውስጥ ነው!

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፍርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣ ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው። 

እናም ልክ ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና... «ይቅር ብዬሃለሁ» ....ብሎ አቀፈው። 

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ:-

«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»

ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አእምሯችሁ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!

ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ብዙ ጠርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!

ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው። ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል። 

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር፣ ቀናነትን መዝራት፣ ህይወትን ማደስ ነው። #Abrsh

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከአምስቱ የስብዕና ሞዴሎች (The Big Five Model) ከሚባሉት የትኛው አይነት ስብዕና ነው ያሎት?

#OCEAN

የመጀመሪያው ተቀባይነት (Openness) የምንለው ነው። ይህ መገለጫ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ለአዲስ ሀሳብም ሆነ ክስተቶችን ለመጋፈጥ ያለንን ተቀባይነት ነው። ይህን ስብዕና ለመለካት አንድ ሰው አዲስ ቦታ ላይ በሚሆንበት ጊዜ የሚያሳየውን ምላሽ እና የአዕምሮ አቀባበል ተመልክተን መወሰን እንችላለን።

ጥንቁቅነት (Conscientiousness) የምንለው ሌላኛው የስብዕና አይነት ሲሆን በዋነኝነት ጥንቃቄን ይገልፅልናል። ይህ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ድንገታዊ ውሳኔዎችን እና ሀሳቦችን የመቆጣጠር ችሎታ ሲሆን ይህን አድርጎ ምክንያታዊ የሆነ እርምጃን የመውሰድ እና ለስራ ሀላፊነትን የመውሰድ ችሎታን ያመላክታል።

Extraversion የምንለው የአንድን ሰው ከውጫዊው አለም ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት መንገድ እና መጠን የምንገልጽበት ሌላኛው የስብዕና አይነት ነው። ከሰዎች ጋር የመቀላቀል ችሎታን እንዲሁም ፍላጎትን እና ከውጪው አለም ጋር ለመገናኘት ያለን ተነሳሽነት በመመልከት ይህን መገለጫ ልናስቀምጥ እንችላለን።

አራተኛው የስብዕና አይነት ተስማሚነት (Agreeableness) የምንለው ነው። ይህ መገለጫ ሌላን ሰው ለመረዳትም ሆነ ለሰዎች ከምናሳየው አክብሮት አንፃር የሚብራራ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሰውን የማመን አቅማችን እና ርህራሄን አጠቃሎ የሚይዝ ነው።

የመጨረሻው የስብዕና አይነት Neuroticism የምንለው ሲሆን እስካሁን ከተነሱት በተለየ መልኩ
አሉታዊ የሆነን ስብዕና የሚያሳይ ነው። ይህን የባህሪ አይነት የተላበሱ ሰዎች እንደ ጭንቀት እና ድባቴ ያሉ አዕምሮን የሚረብሹ ስሜቶች በቀላሉ እና ከፍ ባለ መጠን ይሰሟቸዋል። #APS

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዝግጅታችን ላይ በአክብሮት ጋብዘንዋታል!

ዓብርሆት ስፔሻላይዝድ የሳይኮሎጂ ማዕከል የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በማስመልከት የመዝግያ ፕሮግራም አዘጋጅተናል በዝግጅቱ ወላጆች፣ መምህራኖች፣ የሳይኮሎጂ እና የህፃናት ህክምና ባለሙያዎች ይገናኛሉ።

ሚያዚያ 27፣ 2015 ከቀኑ 8:30

ለመመዝገብ ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ: https://bit.ly/3ViKKQc

ለተጨማሪ መረጃ: +251989737372  

ድረገፅ: http://www.abrihot.com/

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሜንታል ሄልዝ አዲስ ሚያዚያ 28/2015 ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዶር አዲስ ሆቴል "እውን የአዕምሮ ህመም መርገምት ነው?! በዘርስ ይተላለፋል?" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብን ጋብዟል፡፡

መግቢያ:- ነፃ
ለመታደም: በ0933616212 ሙሉ ስሞትን ይላኩ ወይንም በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ: https://docs.google.com/forms/d/1JcXN5wU_CItM93fUVZgpFNXUq7xK0ZjBWa1ddxwfEww/edit?usp=drivesdk

የሆቴሉን አድራሻ በዚህ መስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል: https://goo.gl/maps/SG2wDmdyAz52bPL2A

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ YETENA WEG CLUBHOUSE DISCUSSION!

Topic: Work place Mental Health!

Sunday| April 30
6:00-2:00 (EAT)

Here is the Clubhouse link to join ⬇️

https://www.clubhouse.com/house/yetena-weg-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%8B%88%E1%8C%8D

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስነ አዕምሮ ህክምና መስጫ መምሪያ አስመረቀ።
  
ሆስፒታሉ ለሁለት ዓመታት በዘርፉ የተሰማሩ ታዋቂ የስነ አዕምሮ ባለሙያዎችን በማቀናጀትና በማስተባበር ሲያዘጋጅ የቆየውን የስነ አዕምሮ የህክምና መስጫ መምሪያ (Standard Treatment Guideline for Psychiatric Disorders) የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል።

የዚህ መምሪያ ዝግጅት አላማው በስነ-አእምሮ ህክምና ዘርፍ የሚስተዋለውን የእውቀትና ክህሎት ክፍተት ለማረምና የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

#AMSH

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የስራ እና ድርጅታዊ ሳይኮሎጂ ስልጠና!

Certificate Course on Work and Organizational Psychology!

For further details and registration, use the link below! ⬇️

https://forms.gle/L8ghqgECiBp6nQeS9

+25111662437/ +251940200454

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የጆሀሪ መስኮቶች: የማንነታችን አራቱ ክፍሎች!

የጆሀሪ መስኮቶች ከሰው ጋር እንዲሁም ከራሳችን ጋር ያለንን ግንኙነት በተሻለ ለመረደት የሚያግዝ ንድፍ ነው፡፡ ጆሀሪ ስያሜውን ያገኘው ንድፉን በጋራ ከፈጠሩት የስነ ልቦና ባለሞያዎቹ ጆሴፍ ለፍት እና ሀሪንግተን ኢንግሀምን ስም በማቀናጀት ነው፡፡ ማንነታችን በአራት ሊከፈል ይችላል፦ ግልፅ፣ ድብቅ፣ የተሰወረ እና ጨለማ፡፡

ግልፁ ማንነት፦

ይሄኛው ስለራሳችን እኛም ሌላውም ሰው የሚያውቀው ሲሆን ድርጊቶችን፣ እውቀትን፣ ክህሎትን ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህኛው ማንነታችን ከሰዎች ጋር ለመነጋገር ችግር የለብንም በተጨማሪም ሰዎች ስለዚህ የማንነታችን ክፍል በሚሰጡት አስተያየት በብዛት እንስማማለን፡፡

ድብቁ ማንነት፦

ይህ ማንነት ራሳችን የምናውቀው ሲሆን ከሌሎች የተደበቀ ነው፡፡ በዚህ መስኮት ውስጥ ያሉ ማንነቶቻችንን ስለምናፍርባቸው ወይም የግል ህይወታችን ስለሆኑ ተጋላጭ እንዳንሆን ከሌሎች እንደብቃቸዋለን፡፡ በተመሳሳይ በትህትና ምክኒያት ሰዎች እንዲያውቁ የማንፈልጋቸው ችሎታዎቻችን እውቀታችንንም ያካትታል፡፡

የተሰወረ ማንነት፦

ይሄኛው ሌሎች ሰዎች የሚያዩት ከኛ ግን የተሰወረው ማንነት ነው፡፡ ምክኒያታዊ እንደሆንን እናስብ ይሆናል ሰዎች ግን ግትር እንደሆንን ነው የሚያውቁት፡፡ ወይም ራሳችንን 'ምንም እንደማያውቅ' ልናስብ እንችላለን ሰዎች ግን በጣም ብልህና አስተዋይ እንደሆንን ሊረዱ ይችላሉ፡፡ በዚህ መስኮት ውስጥ ነው ሰዎች ቃላችን እና ድርጊታችን እንደሚለያይ የሚያስተውሉት፡፡

ጨለማ (የማይታወቀው) ማንነት፦

ይህ ማንነት በራሳችንም ሆነ በሌሎች የማይታወቅ ክፍል ነው፡፡ ጥሩም ጥሩ ያልሆኑ ሀሳቦች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡

በአጠቃላይ የ ጆሀሪ መስኮቶቸ ራሳችንን ለመረዳት ከዚያም ለማገጎልበት እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት ለማሻሻል የሚያግዝ ንድፍ ነው፡፡

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር
(Autism Spectrum Disorder)

የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የአንድን ሰው ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት እና ባህሪ የሚጎዳ እክል ነው።

እነዚህ እክሎች መለስተኛ፣ ከባድ፣ ወይም መካከለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር የቡድን ስም ሲሆን በውስጡ አምስት እክሎችን የያዘ ነው።

እስከ ቅርብ ጊዜ ባለሙያዎች የሚጠቅሷቸው የኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር አይነቶች አሉ። እነዚህም፦

1.አስፐርገርስ ሲንድሮም (Asperger's Syndrome)
2.ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder)
3.ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder)
4.ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder)
5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome) ናቸው።

1. አስፐርገርስ ሲንድሮም
(Asperger's Syndrome)


ይህ የኦቲዝም አይነት ቀለል ያለ የሚባለው ነው። አስፐርገርስ የሆኑ ልጆች በጣም አስተዋይ እና የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡

- እነርሱ በሚወዷቸው ወይም በተሳቡባቸው ነገሮች ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።
 
- እነዚህ ልጆች ማኅበራዊ ክህሎታቸው ላይ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል።

- በተጨማሪም የንግግር እና ቋንቋ ክህሎታቸው ላይ እምብዛም እክል አይታይባቸውም።
 
2. ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር (Pervasive developmental Disorder)

- ይህ እክል ከአስፐርገርስ ሲንድሮም ካጋጠማቸው ልጆች የከፋ ሲሆን ነገር ግን ኦቲስቲክ ዲስኦርደር ካላቸው ልጆች የከፋ አይደለም፡፡

3. ኦቲስቲክ ዲስኦርደር (Autistic Disorder)

- ይህ የቆየ ቃል ያለው ከአስፐርገርስ እና ፐርቫሲቭ ዴቨሎፕመንታል ዲስኦርደር የበለጠ እክል ነው፡፡

- ይህም ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶችን ያጠቃልላል ግን በጣም ኃይለኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል።

- ይህም የልጆችን ማህበራዊ መስተጋብር፣ ተግባቦት፣ ባህርይ፣ ስሜት እና ጨዋታ የሚጎዳ እክል ነው።

4. ቻይልድሁድ ዲስኢንተግሬቲቭ ዲስኦርደር (childhood disintergrative disorder)

ይህ እክል እጅግ በጣም ከባዱ እና እጅግ የከፋው የስፔክትረም ክፍል እንደሆነ ይገለፃል።

- ይህ እክል ያጋጠማቸው ልጆች በመደበኛነት የሚያድጉ እና ከዚያም ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 4 ባለው መካከል ሲሆን ብዙ ማህበራዊ፣ ቋንቋ እና አእምሯዊ ክህሎቶችን በፍጥነት የሚያጡ ልጆች ናቸው።

- አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ልጆች የሚጥል ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል።

5. ሬት ሲንድሮም (Rett syndrome)
 
ሬት ሲንድሮም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ነው?

ሬት ሲንድሮም ያለባቸው ሕፃናት ብዙውን ጊዜ ከአቲዝም ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ባሕሪዎች አሏቸው። ባለሙያዎቹም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር መካከል ካሉት ቡድኖች ውስጥ ይመድቡት ነበር፤ አሁን ግን በጄኔቲክ ሚውቴሽን ምክንያት እንደሚከሰት ስለታወቀ በማለት እንደ ASD አይቆጠርም፡፡

በማሕሌት አዘነ
(Speech & Language Therapist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል!

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ፖል ሪቻርድ አሌክሳንደር ይባላል። የተወለደው በ1946 ሲሆን በ6 አመቱ በፖሊዮ በሽታ ይያዛል። እንደ ፈረንሳዮች ከ 1952 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በ "ብረት ሳንባ" ማሽን ውስጥ ይኖራል።

ከአንገቱ የላይኛው ክፍል በስተቀር መላ ሰውነቱ ፓራላይዝድ ነዉ። በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የመተንፈሻ ማሽን ውስጥ ከገባ ዛሬ 71 አመት ሆኖታል። በዚህ ማሽን ምክንያት ነው በሕይወት ያለው። ከዚያ ለደቂቃ ከወጣ መተንፈስ ስለማይችል በህይወት አይቆይም። የሚያስገርመዉ ግን የህግ ትምህርትን ከታወቀ ዩንቨርስቲ ተመርቆ በህግ ሙያ ያስተምራል።

አንዳንድ ጊዜ የጤንነታችንን እና የሰላማችንን ዋጋ አንረዳዉም። እጅ እግር እያለን በሚረባዉ እና በማይረባዉ ነገር እናማርራለን። ይህ ሰዉ ግን ሁሌም በህይወት በመኖሩ ያመሰግናል።

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል እና ሁሌም በህይወት በመኖራችን እናመስግን።

(ዶ/ር ኃይለልዑል)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከመናገርህ በፊት ሁለቴ አስብ!

ምላስ አጥንት የላትም አጥንት ትሰብራለች የሚለው ንግግር እውነት ነው። ሁሌም ቢሆን ከመናገርህ በፊት አስብ። የምትናገራቸው ቃላት ከድንጋይ በላይ ሰዎችን የማቁሰል አቅም አላቸው። በመናገርህ ተጸጽተህ ይቅርታ ብትጠይቅ ህመማቸውን ትቀንሰዋለህ እንጂ ጠባሳውን አታጠፋውም።

ስለዚህ፦

1ኛ. ስሜታዊ ስትሆን ላለመናገር ሞክር፦

ምክንያቱም ስሜታዊ ስትሆን ምክንያታዊ መሆን አትችልም። ይሄ የአዕምሮህ አሰራር (function) ነው። ስለዚህ ስሜታዊ ስትሆን ለብቻህ ጊዜ ለመውሰድና ራስህን ለማረጋጋት ሞክር። የምትናገረውን ነገር ብታዘገየው የሚፈጠር ተአምር የለም። ከተረጋጋህ በኃላ በችግሩ ላይ ታወራለህ።

2ኛ. የመሰለህ ሁሉ እውነት እንደሆነ አታስብ፦

ስሜት ሀሳባችን የሚፈጥረው ነገር ነው። ሰዎች የበደሉህ ስለመሰለህ በድለውሀል፣ ያጠፋ ስለመሰለህ አጥፍተዋል ማለት አይደለም። ስለዚህ የመሰለህ ሁሉ እውነት እንደሆነ ደምድመህ ከሰዎች ጋር ካወራህ ስሜታዊ ትሆናለህ። ስለዚህ ሁሌም ልክ ነኝ ከሚል መርህ ውጣና ልክ ላልሆን እችላለሁ ብለህ እያሰብክ በመረጋጋት እውነቱን ለማወቅ በሚፈልግ ልብ ጥያቄ ለመጠየቅና ሰዎችን ለመረዳት ሞክር።

ስሜታዊ አለመሆን አትችል ይሆናል። ከስሜት ተነስተህ አለመመለስ (react አለማድረግ) ግን ትችላለህ። ከስሜት ተነስቶ መመለስ ጊዜያዊ ሲሆን መዘዙ ግን የረጅም ጊዜ ነው። አስብበት።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጥልቅ ግንኙነት!

ከሰዎች ጋር ብሎም ከ አካባቢያችን ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል?

ውጤታማ በሆኑና ውጤታማ ባልሆኑ ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲፈጠር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ከሰዎች ብሎም ከ አካባቢያችን ጋር ያለን ግንኙነት ነው።

የውጤታማ ሰዎች መገለጫዎችና መታወቂያዎች ከሆኑት ነገሮች መካከል ጥልቅ ግንኙነት አንዱና ዋንኛው ነው።

ውጤታማ የሆኑ ሰዎች በግል ህይወታቸው፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እንዲሁም በስራ ቦታቸው ሰዎችንና አካባቢያቸውን በተሻለ ሁኔታ የመረዳትና የማወቅ አቅምና ጥልቅ መሻት ያላቸው ናቸው።

በዚህም የተነሳ በቀላሉ ከሰዎች ጋር የሚግባቡና የተሻለ ምቹ፣ መተማመን የሞላበት የስራ ሁኔታን በስራ ቦታ እንዲሁም ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነቶችን መፍጠር የሚችሉ ናቸው።

ብሎም በግል ህይወታቸው ማሳካትና ማድረግ የሚፈልጓቸውን ነገሮች በቀላሉ እንዲሳኩና ዕውን እንዲሆን በሚደረገው ሂደት ላይ አካባቢያቸውና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ደጋፊዎቻቸውና አጋዦቻቸው  ይሆናሉ።

ታዲያ በዙሪአያችን ካሉ ቤተሰቦች ጋር፣ ከስራ ቦታ ባልደረቦቻችን ብሎም በማህበራዊ ህይወታችን ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል?

(ዳንኤል አያሌው)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ይቅርታ እንዴት እንጠይቅ?

ምን ያህሎቻችን ነን ይቅርታ ባለማረግ እና ይቅርታ ባለመጠየቅ ደስታችንን እየቀነስን ያለን?

ይቅርታ እንዴት እንጠይቃለን በሚለው ዙሪያ ትንሽ ለማለት ዳዳው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሌላውን ሰው አስቀይመው ወይም ጥፋት አጥፍተው ይጸጸታሉ፡፡ ነገር ግን መጸጸትና ይቅርታ መጠየቅ ይለያያሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይቅርታቸውን ከአንገት በላይ ያደርጉና ተበዳዩን አዛኝ መስለው በከንፈር መጠጣ (lips service) ይሸነግሉታል፡፡ አልያም መልሰው እንደሚያጠፉ እርግጠኛ እየሆኑ እንኳን የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡

ሺህ ግዜ እያጠፋ ከስህተቱ ለማይማር ሰው ይቅርታ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲሁም ይቅርታን ለጥፋቱ መሸሸጊያ የመጨረሻ ምሽግ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሌላውን ሰው ልብ ያደማል፡፡ ይቅርታው በተግባር ለውጥ ስለማይታጀብ ከአፍ አይዘልም፡፡ የዚህ ስሜት በእራሳችን ደርሶ ካላየነው በስተቀር ህመሙ አይሰማንም፡፡ ታዲያ አሳማኝ ይቅርታ እንዴት መጠየቅ ይቻላል?

አንድሪያ ብራንድ የተባለች ሳይኮሎጂስት የሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ይቅርታን ለመጠየቅ ጠቃሚዎች ናቸው በማለት ትመክራለች፡-

1. ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ፡- 

የተበዳይ የመንፈስ ስብራት እኛም በግለሰቡ ቦታ ብንሆን ምን ያህል እንደሚሰማን በማሰብ ከውስጥ በመነጨ ስሜት ይቅርታን መጠየቅ፡፡

2. ስለበደሉት ነገር ዕውቅና መስጠትና ዳግመኛ ላለመበደል ኃላፊነትን መውሰድ፡- 

ስለአጠፉት ጥፋት እቅጩን መናገር “አውቃለሁ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም፤ እኔ በእንተ ቦታ ብሆን ምን ያህል እንደሚሰማኝ እረዳለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ!” በማለት ጥፋትን ለማረም ዝግጁ መሆንን ማሳየት፡፡

3. ዳግመኛ ላለመበደል ቁርጠኛ መሆን፡- 

የበደላችሁት ሰው ከጥፋታችሁ እንደተማራችሁ እንዲያውቅ ማድረግ፡፡ ይህንንም ዕለት ተዕለት በሚደረግ አግባቦትና ተግባር በግልጽ ማሳየትና ምንም ለውጥ ያላሳየን እንደሆን ወዳጆቻችን በግልጽ ቅሬታቸውን እንዲገልጹ ማድረግ፡፡

4. ይቅርታ የምትጠይቁት ሰው ለእናንተ ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ፡-

ከበደላችሁት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በማድነቅ መግለጽ፡፡

5. ይቅርታ መጠየቅ፡- 

ይቅርታ መጠየቅ በሁለታችሁ መሃል ስላለው ግንኙነት አስፈላጊነት የሚያስረዳ ሲሆን፤ በምላሹ ተበዳይ ይቅርታ ለማድረግ ጊዜን ይፈልግ ይሆናል እንደ ጉዳቱ መጠን፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሁኔታዎች ይቅር የሚባሉ ነገር ግን በደሉ ሊረሳ የማይችል ስለሚሆን፡፡ “Forgiven but never forgotten” እንዲል የባህር ማዶ ሰው፡፡

6. ለውጥን በተግባር ማሳየት፡-

“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ”  እንደሚባለው በአገረኛው ዘይቤ፤ ያጠፉትን ጥፋት ዳግመኛ ላለመተግበር ለእራስ ቃል ታማኝ መሆን፡፡ ይህም የአእምሮ ደውል በመውስጣችን በማቃጨል “እንዲህ ላለማድረግ እኮ እንዲህ ብለህ ቃል ገብተሃል” በተግባር ቃልህን አሳይ ማለት፡፡

በደል ያቆስላል ልብንም ይሰብራል፤ ይቅርታ ግን ቁስልን ይሽራል የተሰበረ ልብንም ይጠግናል፡፡ ይቅርታ እንታረቅ!

መልካም ጊዜ!

(አንቶኒዮ ሙላቱ)
#zepsychologist

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

World Down Syndrome Day| March 21

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

💥ስለ ዳውን ሲንድሮም ማወቅ ይፈልጋሉ?

👉 ዳውን ሲንድሮም ምን ማለት ነው?
👉 ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
👉 ተጠቂዎቹን እንዴት መደገፍ እንችላለን?


🗓 በዛሬው እለት ቅዳሜ መጋቢት 9/2015 ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በዳውን ሲንድሮም ላይ በ Clubhouse የምናደርገውን ውይይት ይከታተሉ።

እንግዶቻችን፦
- ዶ/ር ኤርሚያስ ደመቀ
- ዶ/ር ዮሃንስ ግዛው


"ለእኛ ሳይሆን ከእኛ ጋር"

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ

ክለብሐውስ ከሌሎዎት ለማውረድ👉 እዚህ ይጫኑ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

ለምንስ ስለ አዕምር ጤና መነጋገር ያስፈልጋል?

አቅራቢ: ፕሮፌሰር አታላይ አለም (MD, PHD)

መቼ: ቅዳሜ መጋቢት 23፣ 2015፣ ከሰዓት 10:00-12:00
የት: አዶር አዲስ ሆቴል

ቦታ ለመያዝ ስምዎትን በጽሁፍ ምልዕክት ይላኩ: 0933616212

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የማይቀርበት ድንቅ ፕሮግራም!

መጋቢት 9/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በካፒታል ሆቴል 'እንዴት ይቅር ልበል' በሚል ርዕስ ተግባራዊ የይቅርታ ህይወት ላይ ያተኮረ ዝግጅት ተዘጋጅቷል::

የእለቱ እንግዶች፦

ዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ
አቶ በኃይሉ ገብረመድኀን
ዶ/ር ተወልደ ገብረእግዚአብሔር (በልጃቸው ሮማን ተወልደ በኩል)

መግቢያ 2ዐዐ ብር

🎯 ዳግማዊ አሰፋ

ስልክ: +251-909-888857

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel