melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የመፅሀፍ ጥቆማ!

ደራሲው በአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተቀናጀ አዕምሮ ጤና ስፔሻሊስት ሙያ ዘርፍ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም "ሰው መሆን" እና "በአያሌ ሌሊቶች" የተሰኙ ሁለት መፅፍቶችን አስነብቦናል አሁን ደግሞ "ጊዜ ሲያልፍ" የተሰኘ ልቦለድ መፅሐፍ በወርኃ ጷጉሜ ለአዲስ አመት ስጦታ ይዞልን መጥቷል።

......‹‹እውነትና ህይወት ሞት እንኳ አይሽራቸውም፤ አንዱ አልፎ ይታወሳል ሌላው ከስጋ ተላቆ ነብስ ሆኖ ይኖራል። ታዲያ ከእውነት ጋር ወደመቃብር እንዴትስ ይኬዳል? እውነት ከመቃብር በላይ ጮሆ ይናገራል። መቃብርም ወርዶ ተዳፍኖ ይኖራል። ያልተገለጠ እውነት እንዴት ልብ ይሰብራል፤ ስንቱ እውነትን ይዞ መቃብር ይኖራል። እንዳይናገሩት በእውነት አልቦች ታጥሯል። ታዲያ ከዚህ ሁሉ እውነትነት ይዞ መቃብር ይሻላል።››.....

....‹‹ዘላለም እኖራለሁ ብለህ መወለድህን አመስግን። ዘላለም ለመኖር ግን መወለድ ብቻ በቂ አይደለም። ለተወለድክበት አላማ መኖርን ተማር። የዛኔ ለተወለድክበት አላማ መኖርህንም አታስታውሰው። የሚያስታውስህ ስራህ ሆኖ ለዘላለም በምድር ትኖራለህ ማለት ነው። የሰው ልጅ ከመወለዱ በፊት ለምን እንደሚወለድ እድል ፈንታው ተፅፎለታልና፤ ሆኖም ግን የተወለደ ሁሉ ዘላለም ይኖራል ማለት ግን አይደለም። ለተወለደለት አላማ የቆመ እንጂ።››.....

በጃፈር የመፅሐፍ መደብር ያገኙታል

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በአዲሱ አመት በ2016 ከሱስ ለመላቀቅ (New Year Resolution) ለምታስቡ!

1. ውሳኔያችሁ ግልፅና የሚተገበር ይሁን፤ በፅሁፍም አስፍሩት፤

2. ለለውጥ አጋዥና አደናቃፊ ነገሮችን በዝርዝር ፃፉ፤ ለምሳሌ፣ በሱስ ከተጠቃ ጓደኛ መራቅ፤

3. የሌሎች ሰዎች እንዲሁም የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልጋችሁ እንደሆነ አስቡ፤

4. ከዚህ በፊት ሞክራችሁ ውጤት ያላገኛችሁበት መንገድ አትድገሙ፤

5. ስኬታችሁን እየተከታተላችሁ መዝግቡ፤  ብትደነቃቀፉም መጓዝን አታቋርጡ፤ ተስፋ አትቁረጡ።

መልካም የስኬት አመት ይሁንላችሁ!

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ካናቢስ እና የአዕምሮ ጤና!

አንድ ሰው ካናቢስ የመጠቀም ችግር አለበት ከሚያስብሉ ባህርያት (ምንጭ DSM-5 TR) :-

- አጠቃቀማቸውን ለመመጠን መቸገር (ለረጅም ሰአት መጠቀም፣ ካሰቡት ልክ በላይ መጠቀም፤ መጠኑን ለመቀነስ ወይንም ለማቆም እየፈለጉ አለመቻል፤ አምጡ የሚል ውስዋስ።

- በማህበራዊ ህይወት፣ በስራ፣ በቤተሰብ ጉዳዮችን ላይ ችግር ካስከተለ።

- በአደገኛ ሁኔታዎች እና ወቅቶችም መጠቀምን መቀጠል (ጡዞ ማሽከርከር፤ የጤና እክል አስከትሎም መጠቀሙ ከቀጠለ)።

- ለማቆም ሲሞክሩ የስሜትና አካላዊ ጤንነት መዛባት/Withdrawal (መነጫነጭ፣ መጨናነቅና መቅበጥበጥ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድብርት) እና በጊዜ ሂደት የሚፈልጉትን ስሜት ለማግኘት የሱሱን መጠን መጨመር ካስፈለገ።

ካናቢስና ተጓዳኝ የአእምሮ ህመሞች

- ካናቢስ ከሳይኮሲስ (ከእውነታው ማፈንገጥ/ ጥርጣሬ፣ እንግዳ የሆነ ድምጽ መስማት፣ ለሌሎች የማይታዩ ነገሮችን ማየትና የመሳሰሉ)፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት ጋር ይያያዛል::

ካናቢስ ለ ስኪዞፍሬንያ (ከባድ የሳይኮሲስ ህመም) ያጋልጣል?

🔹በዴንማርክ በተሰራ ጥናት መሰረት: በተለይም ወጣት ወንዶች የካናቢስ ተጠቃሚዎች፣ በተለይም ከ16-25 አመት ያሉት ላይ የስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ጨምሮ ታይቷል:: በጥናቱ እንደተመላከተው የካናቢስ ተጠቃሚነትን መቀነስ ቢቻል 1/5ኛ ያህል ስኪዞፍሬኒያን ማስቀረት ይቻል ነበር:: (Hjorthøj C, Compton W, Starzer M, et al.)

🔹በስዊድን ለ15 አመታት ካናቢስ የሚጠቀሙ ሰዎችን በመከታተል በተሰራ ጥናት ከ50 ጊዜ በላይ የተጠቀሙ ሰዎች በ6 እጥፍ ተጋላጭነታቸው ጨምሯል:: (https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/S0140673687926201)

🔹በተለይም ከአፍላ እድሜያቸው ጀምረው ረዘም ላለ ጊዜ የተጠቀሙ ሰዎች ለስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ይጨምራል:: በዚህ እድሜ የአእምሮ ህዋሳት የሚጎመሩበት እድሜ ነውና ሱሱ በዚህ ሂደት ላይ ተጽዕኖ ስለማያሳድር ነው::

እንደምክንያት የሚነሱ ነጥቦች:-
 
- የዶፓሚን ንጥረነገር መዛባትና የአእምሮን ስራ ማወክ
- ከሌሎች ስነህይወታዊ እና ዘረመሌዛዊ ጉዳዮች ጋር በጋራ አጋላጭነት መጨመር (Stress- vulnerability model)

ሱስ ለማቆም የሚረዱ ነጥቦች፦

- እስካሁን እንዳታቆሙ ሰበብ የሆኑባችሁን ነገሮች ከዚህ መረጃ ጋር አመዛዝኗቸውና ራሳችሁን ጠይቁ::

- የማቆም ሂደቱን የምትጠቀሙትን መጠን በመቀነስ መጀመር ይቻላል::

- ዶፓሚናችሁ በሌሎች ነገሮች እንዲመነጭ በማድረግ (በስፖርት፣ በንባብ፣ ፊልም በማየት፣ ከከተማ ወጣ ብሎ በመዝናናትና ወዘተ) የካናቢሱን አስፈላጊነት ቀስ በቀስ መግታት ይቻላል::

- በጊዜ ሂደት ካናቢሱን በመሞከር ተጀምሮ ከተለያዩ ነገሮች ጋር በማስተሳሰር መጠቀሙን እንደገፋችሁበት፣ በጊዜ ሂደት ማቆም የመጠቀም ዑደቱን ያስቀጠሉ (ደስታን መሻት/reinforcement፣ ወይንም ሲያቆሙ ጊዜ የሚፈጠሩ ደባሪ ስሜቶችን/Withdrawal symptoms ላለማስተናገድ) በመግታት ባህርይውን ማረቅ ይቻላል:: በlearning theory መሰረት ማለት ነው!

- ከባለሙያ ጋር መመካከር ደሞ እንዴት ጥሩ መሰለችሁ!

Reference: DSM-5 TR

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስሜት!

''የስሜቶቻችን ጥራት የሕይወታችን ጥራት ነው'' ይለናል ታዋቂው ቶኒ ሮቢንስ

በርግጥ ስሜት ላንተ/ላንቺ ምንድነው?

ለምንድነው የምትፈራው? ምን ላለማጣት ብለህ ነው ከመንገድህ የቆምከው? ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ላለማድረግ ምን ገደበህ?

በሕይወት መንገድ ላይ የስሜቶቻችን ድርሻ ጉልህና ቀላል የሚባል አይደለም፣ በአውንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ።

አለም ላይ የተሰጠህ እድሜ በሙሉ ያንተ ውድ ስጦታ ነው፦ እያንዳንዷን ግዜህን በፈለግከው መንገድ ልትጠቀምባት ተፈቅዶልሃል፣ የምታደርገውን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው።

ይህን ዉድ ስጦታ የሆነ ግዜአችንን  በፈለግነው መንገድ እንድንጠቀምበት ስለ ስሜቶቻችን ያለን ምልከታና ግንዛቤ ወሳኝ ነው።

ዳንኤል አያሌው (Certified NLP Practitioner)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አንድ ሰው በአልኮል፣ አደንዛዥ እና አነቃቂ ዕፆች ወይም በሌሎች የባህሪ ሱሶች መጠቃቱን ለማወቅ በአጭሩ የሚከተሉትን 4 ነጥቦች መጠቀም ይችላል፤

1. ለመቋቋም የሚከብድ በልምምዱ ውስጥ የመቆየት ከፍተኛ ጫና/ውስጣዊ ግፊት፤

2. ቁጥጥር ማጣት፤ ለማቆም እየፈለጉ ያለመቻል፤

3. ልዩ ልዩ ጉዳቶች (የጤና፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ወዘተ...) እየተከሰቱም መጠቀምን መቀጠል፤

4. መቋቋም የሚያስቸግር ከፍተኛ አምሮት፤ እንዲሁም በማይጠቀሙ ጊዜ በድብርት፣ ብስጭትና የማይመች ስሜት መጠቃት።

እነዚህ ችግሮች ከተከሰቱ ባለሙያ ማማከር እና መፍትሄ ማግኘት ያስፈልጋል።

ሱስን በህክምና እገዛ መላቀቅ ይቻላል።

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት፤ የሬናሰንት የአዕምሮ ጤና እና የሱስ ተሃድሶ ማዕከል መስራች)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ናርስሲዝማዊ የስብዕና ችግር/ አፍቅሮተ ራስ

ጤናማ የሆነ ራስን መውደድ በራስ መተማመንና ጤናማ የሆነ የውድድር መንፈስን ስለሚያላብሰን ጥሩ ነው::

ራስን መውደድ እንደችግር የሚቆጠረው መቼ ይሆን?

ይህ የስብዕና ችግር ስያሜውን ያገኘው በግሪክ አፈታሪክ ከምትታወቀው ናርሲሰስ ነው::

Diagnostic and statistical Manual አምስተኛው እትም ምልክቶቹን እንዲህ ይገልጻቸዋል

1. ከልክ ባለፈ ሁኔታ ራስን የተለዩ፣ የተመረጡ እና ያየሉ አድርጎ ማቅረብ

- ስለራሳቸው በጎነት አብዝተው ያወራሉ ወይንም ያስወራሉ እንዲወራ ይፈልጋሉ:: ራሳቸውን ሲክቡ ሌሎቹን በማጣጣል ጭምር ነው::

2. በእውን ያልሆኑትን በምናባቸው ስኬታማ፣ ተወዳጅ፣ ዝነኛ እንደሆኑ ያስባሉ::

3. የተለየን ነን ብለው እንደማሰባቸው እነሱን ሊረዱ የሚችሉቱ በነሱ ደረጃ ያሉ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያስባሉ:: አለመቻላቸውን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ሰዎች የነሱን ችሎታ ለመረዳት እቅም እንዳነሳቸው አድርገው ያቀርባሉ::

4. አድናቆትና ውዳሴን አብዝቶ መሻት

- የባዶነት ስሜታቸው እረፍት ስለሚነሳቸው የሌሎችን አድናቆት፣ የልቦናቸውን ባዶነት ለመሙላት አጥብቀው ይሻሉ::

5. የተለየ ክብካቤና አክብሮት እንደሚገባቸው ማሰብ

- ሰልፍ ላይ በተለየ ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይሻሉ አልያም ሰልፍ ጥሰው ሲገቡ ይታያሉ:: እኮ ለምን ከተባሉ መበሳጨትና ለምን ተነካሁ አካኪ ዘራፍ ማለት ይቀናቸዋል:: እነዚህ ሰዎች ውጭ ውጫቸውን አስደናቂ ባህርይ (superficial charm) ያላቸው መስለው ይታያሉ::

6. ሌሎችን ለራስ ጥቅም መበዝበዝ

- ስራ ወዳድና ታታሪ ቢመስሉም ስለሌሎች ድካምና መዛል ደንታ ስለሌላቸው ሰራተኞቻቸውን ሊበዘብዙ ይችላሉ:: ፍቅረኛቸውን እና ወዳጆቻቸውን ለግል ጥቅም ማስፈጸምያ ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል:: ሰው ምን ይሰማዋል ብሎ ነገር የለም::

7. የሰውን ስሜት ለመረዳት ይቸገራሉ

- ለፍቅረኛቸው ስሜት አልባና ቀዝቃዛዎች ናቸው::

- በታመመ ሰው ፊት ስለጤናቸው መጠበቅ ሊታበዩ ይችላሉ::

- ምናልባትም በልጅነታቸው ያጋጠሟቸው ስነልቦናዊ ቀውሶች የሰዎችን ስሜት እንዳይረዱ (impaired mentalization) አድርጓቸው ሊሆን ይችላል::

8. ቀናተኞች ናቸው /ሌሎች ይቀኑብኛል ብለውም ያስባሉ

- ሌሎች ሰዎች ሲደነቁ ማየት ይከነክናቸዋል::
- እንከን ፈላጊናዎች ናቸው::
- የተሳካላቸውን ሰዎች ያጣጥላሉ::
- በተቃራኒው የሚክቧቸው ሰዎች ይኖሯቸዋል:: እነዚህ የሚክቧቸው ሰዎች ሲነኩባቸው እነሱ የተነኩ ያህል እረፍት ይነሳቸዋል::

9. እብሪተኝነት

- የባዶነት ስሜታቸውን እና ፊት ለፊት ላለማሳየት ይጥራሉ:: ወቀሳን ለሚሰነዝርባቸው ሰው ቂምን ቋጥረው ለበቀል ሊነሳሱና ለማጥቃት ሊሸርቡ ይችላሉ::

መንስኤው ምን ይሆን?

እንደ self psychology አስተምህሮ ሰዎች ሲያድጉ self object ያስፈልጋቸዋል::
- ይህ self object በአግባቡ የሚያየን፣ የሚረዳን፣ ያየብንን አቅም በግብረመልስ መልሶ የሚያንጸባርቅልን እና ሞዴል የምናደርገው ነው::
- ይህን ፍላጎታችንን የሚያሟሉልን ወላጅ/አሳዳጊዎቻችን ናቸው::
- ይህ 'self object' በአግባቡ ኖሯቸው ያላደጉ ልጆች: ያልተቀናጀና(lack cohesiveness) እና መሰረት ያልያዘ ስብዕና ስለሚኖራቸው የማይጨበጥ አይነት ሰዎች ይሆናሉ::
- ባንድ በኩል ያጡትን ትኩረትና ስነልቦናዊ ምልአት ለመቀዳጀት በውጫዊ እሴቶች ማለትም በሃብት በቁንጅና እና በጉልበት የሚታበዩ እና እብሪተኛኞች
- በሌላ በኩል ውስጠታቸው በባዶነት ስሜት የሚናጥ እና በወቀሳዎች ተሰባሪ ሰዎች ሆነው ይገኛሉ::

ናርሲስዝማዊ ስብእና ባላቸው ወላጆች የሚያድጉ ልጆች ወላጆቻቸው የነሱ ተቀጽላ እንደሆኑ በማሰብ የልጆቻቸውን ድክመት እንደራሳቸው አድርገው ስለሚያስቡ በከባዱ ይቀጧቸዋል::
- ልጆቹም ከወላጅ/አሳዳጊያቸው ግምት ላለመውረድ ይኳትናሉ::
- አድገውም በስራና በሌሎች የህይወት መስኮቻቸው ስህተቶቻቸውን አምነው   የማይቀበሉ፣ ድብቅ ባህርይ ያላቸው (ስስ ጎናቸው እንዳይታይ) እና ግብረመልስ የማይሹ ጥፋታቸውን የሚሸፋፍኑ ይሆናሉ::

ህክምናው:-

- እነዚህ ሰዎች: ባህርያቸው ለነሱ ልክና አግባብ (egosyntonic) ሰልሆነ ወደ ህክምና እምብዛም ላይሄዱ ይችላሉ:: ከሄዱም ምናልባት ለተጎዳኝ የአእምሮ ህመሞች (ድብርት፣ ደስታን ማጣት፣ ራስን የማጥፋት ስሜት አስቸግሯቸው) ቢሆን ነው::
- ባህርይን በአንድ ጀምበር መቀየር ቢያዳግትም የተወሰኑ የስነልቦና ህክምናዎች ሊያግዙ ይችላሉ::
- በዋነኝነት የስነልቦና ህክምና (ሳይኮአናሊሲስ፣ ሃሳብና ድርጊትን መሰረት ያደረገ ህክምና/cognitive behavioral therapy፤ Mentalization based therapy..እና የመሳሰሉት ናቸው።

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአእምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሜንታል ሄልዝ አዲስ ቀጣዩን ወርሃዊውን ዝግጅቱን ይዞላችሁ መጣ።

ቅዳሜ ሀምሌ 29/2015 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአዶር አዲስ ሆቴል “የስብዕና መዛባት ምንድን ነው? እንዴስ ይታከማል?” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲናገሩ ዶ/ር ቢንያም ወርቁን ጋብዟል፡፡

መግቢያ ክፍያ:- ነፃ!!!

ለመታደም በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ=> https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8

Mental Health Addis is holding its monthly event on Saturday Aug 5/2023 (Hamle 29, 2015) at Adore Addis Hotel near Atlas at 4:00PM (10:00 local time) on the topic of "What is personality disorder and how does it get treated?

FREE OF CHARGE.

This month’s speaker is Dr Benyam Worku. Please fill out and submit this form using this link https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ባህሪያችንና የቀለም ምርጫችን!

ማንኛውንም ነገር የምንመርጠው ከእኛ ባህሪ ጋር የተገናኘ ነገር ስላለው ነው፡፡ ከባህሪያችን ጋር ግንኙነት የሌለውን ነገር ልንመርጥ አንችልም፡፡ ሌሎች ሰዎች ካልመረጡልን በስተቀር፡፡

የቀለም ምርጫችንም እንደዚሁ ከባህሪያችንን ጋር ግንኙነት አለው፡፡ እንደባህሪያችን የምንመርጠው ቀለም ይለያያል፡፡ ጥቂቶቹን እንደምሳሌ እንዘርዝር፡፡

ጥቁር፦ የብዙዎች ምርጫ ነው፡፡ በብዛት ይህንን ቀለም የሚመርጡ ሰዎች የሃላፊነት ሰዎች የሆኑና ቁርጠኛ የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በተጨማሪም በጣም ውድ ነገሮችን የሚወዱ፣ መሳሳት የማይፈልጉና ስልጣን መያዝ ወይም የበላይ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው፡፡

ቀይ፦ ይህን ቀለም የሚመርጡ ሰዎች ሁሌም ማሸነፍ የሚፈልጉ፣ በጣም ቁጡ የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በተጨማሪም ፍቅርን፣ ህይወትን፣ ወሲብን፣ አደጋን፣ ፍጥነትን የሚያመላክት ቀለም ነው፡፡ ከሌሎች ቀለሞች ሁሉ ትልቅ ተጽዕኖ በሰውነታችን ላይ በመፍጠር የመጀመሪያው ነው፡፡

ብርቱካናማ፦ ዘና ማለትን፣ ደስታን፣ ፈጠራን፣ ተነሳሽነትን፣ ስኬትን የሚያመላክት ትርጉም ያለው ቀለም ነው፡፡ እነዚህ ባህሪ ባላቸው ሰዎች ተመራጭ ነው፡፡

ቢጫ፦ ደስታን፣ ተማኝነትን፣ ጎልቶ መታየት መፈለግን፣ እውቀትንና የፀሃይን ትርጉም የያዘ ነው፡፡

አረንጓዴ፦ ተፈጥሮን፣ ውህደትን፣ መታደስን፣ ጥንካሬን፣ ጤናን፣ እድገትን፣ ገንዘብ፣ መረጋጋትንና ደህንነትን የሚያመላክት ቀለም ነው፡፡

ሰማያዊ፦ መታመንን፣ መረጋጋትን፣ እውቀትን፣ ጥልቀትን፣ እውነትን፣ በራስ መተማመንን የሚያመለክት ቀለም ነው፡፡

ነጭ፦ ንጽህናን፣ ፍፁማዊነትን፣ ደህንነትንና የፈጠራን ትርጉም የያዘ ነው፡፡

የቀለማት ትርጉም እንደምንኖርበት አካባቢ ባህልና ወግ የሚለያይ ነገር ሊኖረው ይችላል፡፡

ተመስገን አብይ (የስነ-ልቦና በላሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ብርጭቆው ከባድ ነው ወይስ ቀላል?

አንድ አሰልጣኝ እንዲህ ሲል ለሰልጣኞቹ በመጠየቅ አንዲትን ቀላል የምትመስል፣ ነገር ግን እጅግ ወሳኝ ቁምነገር አስተላለፈ፡- “አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጃችሁ ብትይዙት ከባድ ነው ወይስ ቀላል?”

ሁላችንም እንደምንጠብቀው ሰልጣኞቹ በአብዛኛው ቀላል እንደሆነ በመስማማት ገለጹ፡፡ አሰልጣኙም በመመለስ፣ “መልሳችሁ ትክክልም፣ ስህተትም ነው” በማለት ሲያብራራ፣ “ይህንን ውኃ የተሞላ ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ ከያዛችሁት ቀላል ነው፡፡ ለአንድ ሰዓት ከያዛችሁት ደግሞ እየከበዳችሁ ይሄድና እጃችሁን የሕመም ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሙሉ ከያዛችሁት እጃችሁ ይደነዝዛል፣ ይዝላል፣ እንዲያውም ብርጭቆውን ልትለቁት እስከምትደርሱ ድረስ ልትደክሙና ሊከብዳችሁ ሁሉ ትችላላችሁ”፡፡

የዚህ ብርጭቆ ክብደት ልክ በመጀመሪያ እንደነበረ፣ ከአንድ ደቂቃ በኋላ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላና፣ ከአንድ ቀን በኋላ ያው ነው፡፡ እዚህ ጋር ልዩነት ያመጣው ብርጭቆውን በእጃችን የያዝንበት የጊዜ ርዝመት ነው፡፡

መልእክቱ ይሄ ነው፡- የስሜትም ጉዳይ እንዲሁ ነው! ማንኛውም እንደ ጭንቀት፣ መረበሽና ፍርሃት የመሳሰለ ቀላል የተባለ የስሜት ሁኔታ ለጊዜው ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል፣ ሆኖም ስሜቱን ለረጅም ጊዜ ስንይዘው ግን መዛላችን፣ መድከማችን፣ መታመማችንና ሕይወት ከአቅማችን በላይ እየሆነ መምጣቱ አይቀርም፡፡

ምናልባት የመኖር ጣእም ያጣችሁ፣ ድብርት የሚጫጫናችሁና የውስጥ (የስሜት) ህመም የሚሰማችሁ አንዳንድ ስሜቶችን ለረጅም ጊዜ እየያዛችሁ ሊሆን ይችላልና አላስፈላጊ ስሜቶችን ገና በትንሽነታቸው ቶሎ ቶሎ ለማራገፍ ሞክሩ!

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ምርጫ!

''ምርጫችሁ ፍርሃታችሁን ሳይሆን ተስፋችሁን ያንጸባርቅ'' ይለናል የነፃነት ተምሳሌቱ ኔልሰን ማንዴላ


ምርጫ ምንድን ነው?

ምርጫዎቻችንን እንዴት እንደምንመርጥና እንደምንወስን ስንቶቻችን ግንዛቤዉና እውቀቱ አለን?

ምርጫ ካሉን አማራጮች ውስጥ የምንመርጠው ምላሽ ነው።

ምርጫ ቀላል፣ ወዲያውኑ የሚገኝ፣ ውጤታማና አውቶማቲክ ነው።

በሕይወት መንገዳችን ላይ በየአንዳንዱ ግዜና ሁኔታ የተለያዩ ምርጫዎችን እንመርጣለን።

አንዳንዶቹን ሆን ብለን በማሰብ ሌሎቹን ደግሞ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ እንደሆኑ እንኳን በማናውቀው መልኩ በደመነፍስ እንመርጣለን። በተለያየ ግዜ ላጋጠሙን ተመሳሳይ ሁኔታዎች ጥሩም ይሁን መጥፎ ምላሾችን እንሰጣለን።

በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሆነን አንዳችን ስንደስት ለምን ሌላችን እንናደዳለን? ሌሎቻችን ስንደፍር ሌሎቻችን ለምን እንፈራለን? አንደኛው ሰው ተመሳሳይ ሁኔታን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ  ሲጠቀም ሌሎቻችን ሳንጠቀም የምንቀረው ለምንድን ነው?

ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ምርጫዎቻችን ሆን ብለን በየግዜው የምንመርጣቸው ሳይሆኑ ካሉን ዉስጣዊ እሴቶች፣ እምነቶች እንዲሁም አመለካከቶች ጋር በደመነፍስ የሚዛመዱና ደመነፍሳዊ ናቸው።

ታዲያ ዋናውና ልናውቀው የሚገባው እውነት ምርጫዎቻችን ደመነፍሳዊ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን እኛ ከምንፈልጋቸው ግብና ዓላማ አንፃር እንዲሆኑ በንቁው አምሯችን የምንፈልጋቸውን ነገሮች ድብቁ ወይም ደመ-ነፍሳዊው አዕምሮ በሚረዳው መልኩ ሊነገረው ይገባል።  

(ዳንኤል አያሌው)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አሉታዊ ስሜቶችን እንዴት እንከላከል?

- ባለፈ ጥፋት ወይም ውድቀት ላይ በማተኮር ፀፀት ውስጥ አለመግባት፡፡ ይልቁንስ ከባለፈው ስህተት በመማርና አሁን ላይ ማተኮር፡፡

- ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ማድረግ፡፡

- ከተለያዩ እፆችና አልኮል ሱሰኝነት መቆጠብ፡፡

- ግጭቶችን ቅራኔዎችንና አለመግባባቶችን በአግባቡ መፍታት፡፡

- ውጥረትንና ጭንቀትን የሚፈጥሩብዎትን ነገሮችና ሁኔታዎችን መለየትና ከእነሱ መራቅ፡፡

- በጎ ማድረግና ምላሹን ከሰዎች አለመጠበቅ፡፡

- ጭንቀትና ድብርት ሲሰማዎ ለቅርብ ወዳጅ ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ማጋራት፡፡

- ሌሎች ሰዎች ስለእርስዎ በሚሰጡት ትችት እና አስተያየት አለመረበሽ፡፡

- የህይወትን ጥሩ ገፅታ ማየት፡፡

- በአላማና በእቅድ መኖር፤ ጊዜን በስራ ማሳለፍ፡፡

- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ንፅህናን መጠበቅ እና ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን መከተል፡፡

- ለራስ ጊዜን መስጠትና እረፍት ማድረግ፡፡

Source: www.betterhealth.vic.gov.au

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ YETENA WEG CLUBHOUSE DISCUSSION!

Be a part of our conversation with Dr.  Benyam Worku about Trauma: The effects of trauma on who we are as a person and how we experience life.

🗓Join us on May 21 (this Sunday).

⏰Timing: 6 PM - 8 PM EAT,
                  11 AM - 1 PM EST.

Join the discussion with the link below

https://www.clubhouse.com/invite/ck5oSbDg

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሁልጊዜም የውስጡ የውጪውን ይወስናል!

ወዳጆች ሕይወት ከውስጥ ነው የሚጀምረው፡፡ እኔ እናንተ፣ ሁላችንም የወጣነው ከእናታቸን ማሕፀን ውስጥ ነው፡፡ እኛም የሕይወታችንን ብሩህነትና ድቅድቅነትም የምንወስነው ከውስጣችን ከሚወጣ አቅም ነው፡፡ ብዙዎቻችን ውስጣችንን ከመስራት ይልቅ ውጪአችንን ስንሠራ ነው የምንታየው፡፡ ለደጃችን የምንጠነቀቀውን ያህል ለውስጣችን አንጨነቅም፡፡ የሠው ልጅ የቤቱን፣ የአጥር ግቢውንና የአካባቢውን አጥርና ጎዳና ያሻሽላል፤ ንፅህናውንም ለመጠበቅ ደፋ ቀና ይላል፡፡ ብዙዎቻችን ለአለባበሳችንና ለአዋዋላችን፤ እንዲሁም በኪሳችን ስለሚኖረው ነዋይ እንጨነቃለን፡፡ ነገር ግን የውስጣችንን የማንነት አጥርና የምንነታችንን ግንብ ለመስራትና የሕሊናችንን ንጽህና ለመጠበቅ ግን ስንጥርና ስንደፍር አንታይም፡፡ የሰው ልጅ ውስጣዊ ቁመናውን ለማሳመርና በኪሱ ካለው ይልቅ በልቦናውና በሕሊናው ስለሚኖረው መልካምነትና ጥበብ ሲፍጨረጨር አይታይም፡፡ በእውነት ብዙዎቻችን በታይታ ሕይወት ጠፍተናል!

ወዳጆች የዶሮዎችን ሕይወት ተመልከቱማ፡፡ ‹‹አንድ እንቁላል በውጪ ሃይል ከተሠበረ ሕይወቱ ያከትማል፡፡ ነገር ግን ዕንቁላሉ በውስጣዊ ሃይል ከተሠበረ አዲስ የጫጩት ሕይወት ይጀምራል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ትላልቅ ስኬቶች የሚጀምሩት ከውስጥ እንጂ ከውጪ አይደለምና፡፡››

ውስጣችንን አይተን፤ ራሳችንን አውቀን፤ ራሳችንን አግኝተን፤ የራሳችንን ሕይወት በራሳችን ሃሳብ እንሠራ ዘንድ እንትጋ የዛሬው መልዕክቴ ነው፡፡

የውስጡ የውጪውን ይወስናል! Inward always matters outward!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

መልካም የስራ ሳምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አስቸጋሪ ሰዎችን ለመቋቋም የሚያግዙ ሶስት ኣጫጭር ዘዴዎች!

የእለት ተዕለት ኑሯችንን ስናከናውን ይብዛም ይነስም ባህሪያቸው አስቸጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር መገናኘታችን አይቀሬ ነው። አንዳንዶቻችን እነዚህን ሰዎች በብልሃት እና በስልት ማለፍ እና ከእነሱ የምንፈልገውን ማግኘት ስንችል፣ አንዳንዶቻችን ደግሞ በድርጊታቸው ተበሳጭተን ለጭቅጭቅ እና ለንትርክ እንዳረጋለን። የሚከተሉት ሶስት አጫጭር ዘዴዎች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር የሚኖረንን አጋጣሚ ቀለል እንደሚያደርጉ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይመከራሉ።

1. ጊዜ ሰጥተው ያዳምጧቸው

በሚናገሩበት ጊዜ ሙሉ ቀልብዎን ሰጥተው ምን ለማለት አየሞከሩ እንደሆነ እና የመጡበት አቅጣጫ ምን እንደሆነ ያዳሙጧቸው፣ ተናግረው ሲጨርሱም “ከንግግርዎ የተረዳሁት ይህንን ነው” ብለው መስማትዎን ያረጋግጡላቸው። ያሉትን ማዳመጥዎን ካረጋገጡ በኋላ አቋማቸውን መለወጥ ይቻል እንደሆነ በዚያው ይመርምሩ።  
 
2. ያልተለመዱ አካሄዶችን ይጠቀሙ፦

ስላበሳጫቸው ነገር ወይም ስለነሱ ጉዳይ እንደሚጨነቁና እንደሚያስቡ ይግለፁላቸው። እርስዎን በእነርሱ ጫማ ውስጥ አስቀምጠው አመለካከታቸውን ለመረዳት ይሞክሩ። "ጉዳዩን እረዳለሁ" ብለው ይንገሯቸው። ይህ ማለት የግድ እነርሱ በፈልጉት አቅጣጫ ለመሄድ መስማማት ማለት አይደለም። ነገር ግን እነሱን ለመረዳት መሞክርዎ ብዙ ሰዎች የማያደርጉትን ያልተለመደ መልካም ሙከራ ሞክረዋልና ይህን ማድረግዎ አብዛሃኛውን ጊዜ እነዚህን ሰዎች የማለዘብ ኃይል ይኖረዋል።
 
3. ጭቅጭቁ ከመፈጠሩ በፊት ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ይምሯቸው፦

ብዙ ሰዎች ሌሎችን የሚያስተናግዱበት አካሄድ እንደተስተናጋጁ ሰው ሁኔታ ተለዋዋጭ ነው። ሰዎች ደከም ብለው ሲታዩ ብዙ ጊዜ አላግባብ የሆነ ነገር በሌሎች ይደረግባቸዋል። ስለሆነም ሰዎች ከእርስዎ ጋር ሲሰሩ እና ክንዋኔን ሲያደርጉ የማይፈልጉት ነገር እንዳይፈጠርና አግባብ በሌለው ሁኔታ እንዳያስተናግዱዎ አስቀድመው ማንነትዎን እና በግንኙነታችሁ ውስጥ ስለሚጠብቁት የንግግር አግባብ ብስለት በተሞላበት ሁኔታ ማሳወቅ እና መምራት ያስፈልጋል። ይህን በማድረግ ለሰዎች ያለዎትን አክብሮት እያረጋገጡ ነገርግን የሰዎች መጠቀሚያ ለመሆን የማይፈቅዱ እንደሆኑ ያሳያሉ፣ ብሎም ግንኙነታችሁ መከባበር በተሞላበት ሁኔታ እንዲከናወን ይረዳል። (ሰዋስው)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

MAY: የአዕምሮ ጤና የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር!

ይህ ወር የአእምሮ ጤና እና ደህንነትን አስፈላጊነት ያጎላል። ማግለልን ለመቀነስ፣ የአዕምሮ ጤናን ለማበረታታት እና የተሻለ የአእምሮ ጤና አገልግሎት እና ድጋፍ እንዲኖር ያለመ ነው።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ይህ አመት!

የአዕምሮ ደስታ፣ ሰላም፣ እረፍት የምታገኙበት፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት አመት ይሁንላችሁ፡፡

🌼መልካም አዲስ አመት!🌼

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አዲስ ዓመት አዲስ ጅማሮ!

አዲስ ዓመት የአዳዲስ ነገሮች ጅምሬ መነሻ ነው! አዲስ አመት ዳግም እንደ አዲስ እነደ መወለድ ነው። አዲሱ ዓመት ሲጀምር፣ በሕይወታችን ውስጥ ከአጉል ልምዶቻችን ለመላቀቅ፣ ለችግሮቻችን መፍተሔ ለማበጀት እና ስኬታማ ስለመሆን እናስባለን።

ብዙውን ጊዜ አዲስ ዕቅዶችን እናቅዳለን እንዲሁም አዳዲስ ውሳኔዎችን መወሰን እንጀምራለን። በአዲስ አመት የደስታ፣ የተመስጦ እና የተስፋ ስሜት ሊሰማን ይችላል፣ በዛው ልክ አንዳንድ ጊዜም ፍርሃት ያድርብናል።

በሕይወታችን ውስጥ እውነተኛ ለውጦችን ማድረግ ከፈለግን ላሰብነው አላማ እስከመጨረሻው በፅናት መታገል የግድ ነው። ትልቅ ማለም ትልቅነት ነው! ሆኖም ግን ህልማችን እውን እንዲሆን በየቀኑ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበር ተገቢ ነው።

አዲሱ ዓመት ባዶ ገጾች እንዳሉት መጽሐፍ ነው። እነዚህን ገጾችን እንዴት መሙላት እንፈልጋለን? ነው ጥያቄው አዲስ ዓመት አዳዲስ ጅማሬዎችን እንድንጀምር እና በሕይወታችን ውስጥ ለውጦችን እንድናደርግ ያነሳሳናል፣ ግን ይህ መነሳሳት ዓመቱን ሙሉ መቀጠል አለበት።

በስሜታዊነት ላይ ሳይሆን በጥበብ ላይ በመመርኮዝ በራስ ተነሳሽነት ውሳኔዎችን መወሰን ያስፈልገናል። ችግሮች እና መሰናክሎች ቢኖሩም ውሳኔዎቻችን የውስጥ ጥንካሬን እና በፈተና የመፅናት ችሎታን ያጎናፅፉናል።

በመጪው አመት መጨረሻ ውሳኔዎቻችን በመፈፀም እና ያሰብነውን በማሳካት ዓመቱ በህይወታችን ጎልቶ እንዲታይ ማድረግ እንችላለን።

አዲሱ ዓመት በህይወት መፅሀፋችን ውስጥ የምንፅፈው አዲስ ምዕራፍ ነው። የጠራ እና ግልፅ ግብ በማውጣት እና በመተግበር ይሄንን ምዕራፍ የስኬት ምዕራፍ ልናደርገው ይገባል።

ሣሙኤል ተክለየሱስ
(ዓለም አቀፍ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ነሃሴ 27/2015 ቀን አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፤

የዚህ ወር ርዕስም፡ “ስለሱስ እና ሱሰኝነት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የስነልቦና አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ናርዶስ ማሞ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️

https://forms.gle/EpY5jjAUmMpXTLjV7

The monthly Mental Health Addis’ event has come and it will be held on September 1, 2023 at Adore Addis Hotel (near Atlas) in the afternoon at 10:00 local time.

This time the topic is “Things We Need to Know about Addiction and Being Addicted.” Our guest speaker is the counseling psychologist Mrs. Nardos Mamo.

To register and attend please fill this Google form: ⬇️

https://forms.gle/EpY5jjAUmMpXTLjV7

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

መልካም ዜና!

ስጦታ የአእምሮ ህክምና እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በሰውነት ውስጥ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮች እና አደንዛዥ እጾችን መመርመሪያ በማስገባት የሱስ ምርመራ መጀመሩን በደስታ ሊያበስርዎት ይወዳል!

አድራሻ: ቶታል (3 ቁጥር ማዞሪያ)፤ ኦሜጋ ት/ቤት አጠገብ

ስልክ: +251113692818
         +251113692774

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የንዴት መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሄው!

ብዙ ሰዎች ተናዳጅና ብስጩ ቢሆኑም የንዴታቸውን መንስኤ ግን በእርግጠኝነት እንደማያውቁት ይነገራል።

ብስጭት እየጨመረ ሲመጣና ሰዎች ስሜታቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው ወደ ንዴት ያመራል። የንዴት መነሻ ምክንያቶች ውስጣዊ እና ውጫዊ በማለት የዘርፉ ባለሞያዎች በሁለት መልኩ ከፍለው ይመለከቱታል።

በእርግዝና ወቅት፣ በድህረ ወሊድ ጊዜ የሚከሰት ውጥረት፣ ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት ውስጣዊ የብስጭት ምክንያቶች ሲሆኑ፤ እውነታዎችን  መቀበል አለመቻል፣ ቅናት፣ ወቀሳና አላግባብ የሚሰነዘሩ ትችቶች ውጫዊ ምክንያቶች መሆናቸውን ባለሞያዎች ያነሳሉ፡፡

ከጤና እክሎች በተጨማሪም እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና የአይምሮ እድገት ውስንነት መሰል ስነልቦናዊ ጉዳቶች መንስኤም ሊያጋጠጥም እንደሚችልም ይናገራሉ።

ተናዳጅ እና ብስጩ የሚሆኑ ሰዎች ለእንቅልፍ እጦት፣ ለአይምሮ ህመም እና ለሌሎች የጤና እክሎች አጋላጭ ሲሆን ይስተዋላል ተብሏል፡፡

በመልህቅ የትዳር አማካሪ እና አሰልጣኝ  አቶ ጸጋዬ አሰፋ ብስጭት ተፈጥሯዊ መሆኑን በማንሳት ተደራርበው የሚመጡ ችግሮች ሰዎችን ለንዴት እንደሚዳርግ ይናገራሉ። ስሜትን መቋቋም አለመቻል  ዋነኛው ችግር  መሆኑን በማንሳት፡፡

ምልክቶች፡

በማንኛውም ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ሃሳቦችን መስጠት፣ ችኩል መሆን፣ በንግግር መሃል የድምጽ መጠን መጨመር፣ መናገር አለመቻል፣ የአካል መንቀጥቀጥ፣ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የምራቅ መድረቅ እንዲሁም የሌሎችን ሃሳብ አለመቀበል ምልክቶች መሆናቸውን ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

አሉታዊ ጎኖች፡

"መርዝ ከተድፋበት ቦታ ይልቅ የሚቀመጥበትን ቦታ የመመርዝ አቅም አለው" የሚሉት አቶ ጸጋዬ ተናዳጅ አልያም ብስጩ ሰው በመጀመሪያ እራሱን የሚጎዳ ሲሆን ለሌሎችም  የጤና እክሎች ተጋላጭነቱ  ይጨምራል ብለዋል።

ብስጩ እና ተናዳጅ መሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ጥላቻን፣ ተፈላጊነት እንዳይኖራቸው እንዲሁም ሃሳቸውን ለመናገር ፍላጎት እንዳይኖራቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡ ወላጆች ይህ አይነቱ ባህሪ ካላቸው ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት ሊረብሸው እንደሚችል ገልጸው በልጆች ላይ ፍራቻን ይፈጥራል ብለዋል።

መፍትሄዎች፡

- ያለፉ ችግሮች መለወጥ ባይቻልም እንኳን ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጉዳዮችን ማስተካከል፡፡
- የንዴት ወይም የብስጭትን መነሻ  ምክንያቶችን ለይቶ ማወቅ፣ ችግሩን  በሰአቱ ለመፍታት መሞከር፣ ቂም በቀልን በመተው ይቅርታ ለማድረግ መሞከር  ችግሩን ይቀርፋል ተብሏል፡፡

(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተጠናቀረ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የድባቴ መንስኤ፣ ምልክቶችና መከላከያ መንገዶች!

አንድ ሰው ከገባበት ሀዘን ወይም ጥሩ ያልሆነ ስሜት በቶሎ መላቀቅ ካልቻለ የድባቴ ስሜት አጋጥሞታል ማለት ይቻላል፡፡

የድባቴ ስሜት በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ችላ ከተባለ ግን የአዕምሮ ጤናን የሚያውክ ደረጃ የሚደርስ ነው።

የድባቴ ምልክቶች በሁሉም ሰው ላይ አንድ አይነት ላይሆኑ ይችላሉ፤ ደረጃ፣ ቆይታና አስከፊነት እንደየግለሰቡ የድባቴ ሁኔታ ይለያያል፡፡

ሆኖም ተከታታይ የሆነ የሃዘን፣ የንዴት፣ የብስጭት፣ የቁጣና የባዶነት ስሜት፣ የተስፋ ማጣትና ጨለምተኝነት አመለካከት፣ ራስን መውቀስ፣ ዋጋቢስና ረዳት የለሽ የመሆን ስሜት፣ በትንሽ በትልቁ መበሳጨትና ቅብጥብጥነት፣ ለወትሮው በፍቅር ለምናከናውናቸው ተግባራት ፍላጎት ማጣት፣ ድካምና ተነሳሽነት ማጣት የድባቴ ምልክቶች ናቸው፡፡

እንዲሁም አትኩሮት ማጣት፣ ዝንጉነትና ውሳኔ ለመስጠት መቸገር፣ መጫጫን፣ የእንቅልፍ መዛባት ወይም ለረዥም ጊዜ መተኛት፣ ከመጠን ያለፈ መመገብ ወይም የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ራስን ማጥፋት መፈለግና መሞከር፣ በህክምና መታገስ ያልቻለ ራስ ምታት፣ ቁርጠት፣ ቁርጥማትና የምግብ አለመፈጨት ችግር ካጋጠመ ድባቴ መኖሩን ይጠቁማል፡፡

አዕምሮን የሚረብሽ ከባድ የህይወት አጋጣሚ፣ የሚወዱት ሰው በሞት መለየት፣ ከሰዎች ጋር ያለ ሠላማዊ ግንኙነት መናጋት፣ አዕምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የሆነ ሀሳብና ሁኔታ ሲገጥም፣ ጭንቀት፣ መገለልና የሞራል ውድቀት ለድባቴ ከሌላው ሰው ይልቅ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ያመላክታል።

ድባቴን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል፣ ከአልኮል፣ ከትምባሆ እና ከአደንዛዥ እፆች መቆጠብ፣ አሉታዊ ሀሳቦችን ከአዕምሮ አስወግዶ አዎንታዊ ጎኖችን ማሰብ መለማመድ፣ በህይወት ውስጥ ለችግሮች ፍፁም የሆነ መፍትሄ እንደሌለ ማስታወስ ናቸው፡፡

እንዲሁም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ በትዕግስት ጠንክሮ መስራት፣ ለሳቅ ለጨዋታ በአጠቃላይ ለመዝናኛ ጊዜ ማበጀት፣ ለሰዎች በጎ ነገር በማድረግ መልካም ወዳጅነትን ማፍራት፣ ጭንቀትና ስጋትን ለቅርብ ሰው ማካፈልን መልመድ ይጠቀሳሉ።

ፍ/ማርያም ተስፋዬ (ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የህይወት ግቦች (goals) ማስቀመጥ የሚሰጠው ጥቅም!

በሕይወታችን የት መድረስ እንደምንፈልግ ማወቁ አስፈላጊ ሲሆን፣ ለምን መድረስ እንደፈለግን በውል ማወቅ የበለጠ አስፈላጊ ነው። አንዳንዶቹ ይህን መድረስ ከምንፈልግበት በስተጀርባ ያለውን ምክንያት እውነተኛው ግብ እያሉ ይጠሩታል። የሕይወት አጭር ወይም ረጅም ግብ (goal) ማዘጋጀት ለምን እንደሚጠቅም ባለሙያዎች እንደሚከተለው ያብራራሉ።

1. ፍላጎታችን እና ምኞታችን ይሟላል፦

በሕይወታችን አንድ ነገር ላይ መድረስ ለምን እንደምንፈልግ አስቀምጠን ስንቃኝ፣ ያስቀመጥነው ግብ በእውነትም ያንን ውጤት ሊያመጣልን እንደሚችልና እንደማይችል መመርመር እንችላለን። ስለሆነም በስሜታችን፣ በደስታችን እና በማንነታችን ላይ ለውጥ የሚያመጡ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩረን እንድንሰራ ይረዳናል።

2. በሕይወታችን ምን እንደሚያነሳሱን ብሎም እራሳችንን የበለጠ እንድናውቅ ይረዳናል፦

ግቡን አስቀምጠን የሚያመጣልንን ደስታ እና ትርፍ ስናመዛዝን በዚያ ሂደት ከሕይወታችን ምን ማግኘት እንደምንፈልግ ብሎም ደስታችን በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የበለጠ እናውቃለን። ይህም ለበለጠ የእራስ ማስተዋል እና ግምገማ ጥሩ ዕድል ይፈጥርልናል። ወደ ጥሩ የሕይወት አላማም ለመጉዋዝ ማስተካካያወች እንድናደርግ ይረዳናል።

3. ለአእምሯችን ጤንነት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፦

የሕይወት ግቦችን ማስቀመጥ እና እንደምንደርስባቸው ለራስ መንገር ለአምሯችን ሰላም መሰማት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። አእምሮአችን፣ ወደ ግባችን ለመድረስ ስንሰራ ደስታን ያገኛል፣ በዚህም የተነሳ ስለወደፊት ሕይወታችን ያለን አመለካከት ከፍ እያለ ይመጣል። በዚህም ትልቅ የአእምሮ ሰላም እናገኛለን።  (ሰዋስው)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Yetena Weg Clubhouse Discussion!

ከ ዶ/ር እንቁ ደረስ ጋር ለእምሮ ህክምና የሚውሉ መድሃኒቶች ላይ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉ።

🗓ሰኔ 18 (በዚህ እሁድ )
ከ12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ ⬇️

https://www.clubhouse.com/invite/UrVKlxDn

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሜንታል ሄልዝ አዲስ ግንቦት 26/2015 ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዶር አዲስ ሆቴል “የአዕምሮ ህመም አንዴ ከተከሰተ በኋላ ይድናል ወይ?'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ዶ/ር የፍሬዘር ገዛኸኝ (ሳይካትሪ ሬዚደንት) ጋብዟል፡፡

ለመታደም: በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ: https://forms.gle/ZsWZbFK15k8y5e9aA

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Yetena Weg Clubhouse Discussion

የልጆች አስተዳደግ በኢንተርኔት ዘመን!

ከ ዶ/ር ትዕግስት ዘሪሁን ጋር የልጆች አስተዳደግ በኢንተርኔት ዘመን ላይ በሚል ረዕስ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉ።

🗓ግንቦት 20 (ዛሬ)
⏰ ከ12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ ⬇️

https://www.clubhouse.com/house/yetena-weg-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%8B%88%E1%8C%8D

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እየተንሰራፋ የመጣው የአደንዛዥና የአነቃቂ ዕፆች ተጠቃሚነት!

በኢትዮጵያ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች እንዲሁም አደንዛዥና አነቃቂ ዕፆችን የመጠቀም ልምድ፣ በተለይም በወጣቶች ዘንድ እየጎላ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዕድሜው ከ20 ዓመት በታች የሆነ፣ እነዚህን አነቃቂና አደንዛዥ ዕፆችንና የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች መጠቀሙ፣ የአንጎል ዕድገት (ብስለትን) በቀጥታ ከመጉዳቱም በላይ፣ ዕድሜና ፆታ ለማይለዩት ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎችና ለዘላቂ ጉዳት የሚዳርግ ነው፡፡

የሬናሰንት የአዕምሮ ጤናና የሱስ ተሃድሶ ማዕከል መሥራች፣ አማካሪና የሥነ አዕምሮ ባለሙያ ሰለሞን ተረፈ (ፕሮፌሰር) እንደሚናገሩት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እጅግ አደገኛ የሆነው ኮኬይን የተባለው አደንዣዝ ዕፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር በተለይም በአዲስ አበባ እየተበራከተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለይም ወደ ደቡብ አሜሪካ በረራ ከጀመረ ወዲህ፣ በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ፍተሻ የሚያዘው የኮኬን መጠን፣ እጅግ በጣም መጨመሩን ሰለሞን (ፕሮፌሰር) ገልጸው፣ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ እየገባና በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎችም በዚህ ተጎጂ የሆኑ ሕሙማንን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያስተናገዱ መሆናቸውን አክለዋል፡፡

አደንዛዥና አነቃቂ ዕፆችና የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች ለአዕምሮ ሕመም መከሰትና መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጦርነትና ሌሎች ጫናዎች በስፋት መታየታቸውም ለአደንዛዥ ዕፆች ተጠቃሚነትና ለአዕምሮ ሕመም እንደሚዳርጉ ጠቁመዋል፡፡

ችግሮቹን ለመቅረፍ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ቢታወቅም፣ ከችግሩ መንሠራፋት አንፃር በትኩረት እየሠሩበት ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡

(ሪፖርተር)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት
(Cognitive development of child)

እንደ ስዊዝ ተወላጁ ስይኮሎጂስት ፒያዤ (Jean Piaget) መሰረት የልጆች አዕምሮ ግንዛቤ እድገት በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተለያዩ ማነቃቂያዎች (stimulus) ምላሽ በመስጠት (response) እና በመላመድ ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ (awareness) እና የባህሪ ግንባታ እንዳለው ይገልጻል። የአንድ ልጅ የባህርይ ጸባይ የሚመሰረተው ከአካባቢው ጋር ባለው ቁርኝት ሲሆን፤ ይህም በልጁ የአዕምሮ ግንዛቤ ንድፍ (Schema) ለይ የሚመሰረት ነው።

በዚህም መሰረት ልጆች 4 የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት ደረጃዎች አላቸው፦

1. ሴንሰሪሞቶር| Sensorimotor stage (ከ ተወለደ እስከ 2 አመት)

በዚህ ጊዜ ጨቅላው ልጅ ከአካባቢው ጋር የሚዛመደው በእንቅስቃሴ እና በስሜቶች ሲሆን፤ ለተለያዩ ማነቃቅያዎች እንቅስቃስያዊ ምላሽ ይሰጣል። እያደገ ሲመጣ (ወደ 2 አመቱ ሲጠጋ) የነገሮችን /ቁሶችን መኖር ይገነዘባል፤ እናም ህጻኑ የቁሶችን ምስል በአዕምሮው ጠብቆ ማቆየት ይጀምራል እና ከእይታው ውጪም ቢሆን ቁሱ እንዳለ መገንዘብ ይችላል፣ ለመፈለግም ይጥራል።

2. ፕሪ ኦፕሬሽን| Pre-operational stage (2–6 አመት)

ህፃኑ የነገሮችን፣ ቁሶችን እንዲሁም ክስተቶችን አዕምሯዊ ምስሎችን ከመፍጠር ባሻገር፤ ለሌላ ጊዜ እንዲጠቀሙበት በአእምሮ ውስጥ በማስቀመጥ ምሳሌያዊ ግንዛቤን ያዳብራል። ልጁ እንቅስቃሴ እና የቋንቋ እድገት ክህሎቶችን በማዳበር የአካባቢያዊ ተግባቦት ችሎታ ያዳብራል። የልጁ አመክንዮ ግንዛቤ (logical thinking) ገና ያልዳበረ ስለሆነ ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ለማገናዘብ አይችሉም፤ ስለዚሀ ራስ ተኮር (ego centric) እና ምትሀት ተኮር (magical thinking) አስተሳሰብ ይዘው ያድጋሉ። ሆኖም ግን በመልካም ወይም በመጥፎ ነገር ላይ በመመርኮዝ የሞራል አስተሳሰብ ግንዛቤ ማዳበር ይጀምራሉ።

3. ኮንክሪት ኦፕሬሽን| Concrete operational stage (7-11 አመት)

በዚህ እድሜ ዉስጥ የሚገኙ ልጆች አመክንዮአዊ (logical) እና ምክንያታዊ (Rational) አስተሳሰብን ያዳብራሉ። የራስ ተኮር አስተሳሰብ በእጅጉ ይቀንሳል፤ ብሎም ፅንሰ-ሀሳባዊ (conceptual) ግንዛቤዎች የጎለብታሉ፣ የሌሎችን አስተያየት መገነዘብ ይጀምራሉ። የቃላት፣ የሰውነት ተግባቦትን በደንብ ያለያሉ፤ በአጭሩ ተግባራዊ ይሆናሉ።

4. ፎርማል ኦፕሬሽን| Formal operational stage (ከ 12 አመት በኋላ)

በዚህ እድሜ ለይ ያሉ ልጆች ረቂቅ አስተሳሰብን (ሀሳቦችን መመርመር እና የንድፈ-ሀሳቦችን የማመንጨት የማስተናገድ ችሎታ)የአመክንዮ አስተሳሰብ እድገት (ከአንድ አጠቃላይ ሃስብ በመነሳት ወደ ውስን የማውረድ ችሎታ (deductive reasoning)፣ እና ፅንሰ-ሀሳባዊ አስተሳሰብ ትርጉም መስጠት ግንዛቤ ያዳብራሉ። ሃላፊነት መውሰድ የሚላማመዱበት ወቅት ነው።

ስለዚህ ወላጆች የልጆቻችሁን የአዕምሮ ግንዛቤ እድገት በዚህ መልክ መከታተል ይረዳችሁ ዘንድ እንደተጠቀሙበት እመክራለሁኝ።

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (ሳይካትሪስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከባድ የአእምሮ ህመም (Psychosis)

ሳይኮሲስ (ከባድ የአእምሮ ህመም) ማለት ሰዎች ከነባራዊ ሁኔታ (እውነታ) መውጣታቸውን ይገልፃል፡፡ በዋነኛነት የተሳሳተ ሃሳብ (delusion) መዘላበድ፤ እየተደረገ ስላለው እውነታ የተሳሳተ ግንዛቤ መኖር፤ አንድን ሰው ሌላ እንደሆነ አድርጎ ማየት፤ ሌላ ሰው የማያየውን ማየት እንዲሁም ሌላ ሰው የማይሰማውን ድምፅ መስማት (hallucination) ይታይባቸዋል፡፡

ከባድ የአእምሮ ህመም የጀመራቸው ሰዎች በአካባቢያቸው ምን እየተደረገ እንዳለ በትክክል ላያውቁ ይችላሉ ሳይኮሲስ (ከባድ የአእምሮ ህመም) በአብዛኛው የአእምሮ ህመሞች ላይ የሚታዩ ሲሆን በተጨማሪም ከታይሮይድ እጢ ጉዳት፤ ከአንጎል እብጠት፤ አንጎል ላይ በደረሰ አደጋ እና አደንዛዥ እፅ በመጠቀም ሳቢያ የሚመጡ የአእምሮ ህመሞች ጋር ይያያዛል።

ሳይኮሲስ (ከባድ የአእምሮ ህመም) የሚያሳያቸው ምልክቶች፦

1. የስሜት ህዋሳት ተግባር መዛባት (hallucination)- ከባድ የአእምሮ ህመም ውስጥ ያለ ሰው ጨርሶ የሌሉ ነገሮችን ማየት፤ መስማት፤ የመዳሰስ፤ የማሽተትና የመቅመስ ስሜት ያሳያል፡፡

2. የተሳሳተ ሃሳብ፤ እምነት መኖር (delusions)- በውስጣቸው ባለ የተሳሳተ እምነት በጣም ከማመናቸው የተነሳ በምንም አይነት መልኩ መሳሳታቸውን ቢያስረዷቸው እንኳ ሊቀበሉ ጨርሶ ፈቃደኛ አይደሉም።

3. ሊጎዱኝ ይከታተሉኛል ብሎ መጠራጠር።

4. ተለዋዋጭ ስሜት - የሰዎች ስሜት ያለምንም ምክንያት ከመሬት ተነስቶ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ የስሜት (ሙድ) መቀያየር የተለመደ ነው።

5. የባህሪ መለዋወጥ- ከተለመደው ውጭ የተለየ ባህሪ ያሳያሉ፡፡ ከመጠን በላይ ንቁ ሊሆኑ ወይም በጣም ልፍስፍስ ሊሉና ቀኑን ሙሉ አንድ ቦታ ያለምንም ስራ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡

#AMSH

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአዕምሮ ህሙማንና የሚደርስባቸው መገለል - ለችግሩም የመፍትሄ አቅጣጫ!

የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል በአለም አቀፍ ደረጃ በየትኛውም የማህበረሰብ ክፍል በስፋት የተሰራጨ ችግር ከመሆኑም ባሻገር ይሄም በጤና ባለሙያዎች ዘንድም የሚታይ አመለካከት ነው።

የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግለል በታካሚዎች ዘንድ ከማህበረሰቡ እራሳቸውን እንዲያገሉና የህክምና እርዳታ እንዳይሹ የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ይሄንንም በማህበረሰቡ የሚደርስባቸውንና እንደግለሰብ የምናደርስባቸውን ማግለል ለመከላከል ከመንቀይሰው ስልት የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:-

1. ማግለልን መቃወም

"የአዕምሮ ህመምተኞችን የማግለል ተቃውሞ ዘመቻ" ማድረገ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የሚደረገውን ማግለል ለመቀነስ ይረዳል።

2. ማስተማር

በማስተማር እያንዳንዱ ሰው ስለ አዕምሮ ህመም መንስዔ፣ የህመሙ መገለጫ ምልክቶች፣ የህክምና እርዳታና ተያያዥ ውጤቱን በማሳወቅ ሰዎች በአዕምሮ ህመምተኞች ላይ የሚያደርሱትን ማግለል መከላከል እንችላለን።

3. የአዕምሮ ህመምተኞችን ማግኘት

በተለያዩ የአዕምሮ ህክምና በሚሰጥባቸው ቦታዎችና የማገገሚያ ማዕከላት ብሎም መርጃ ማዕከላት (ሜቄዶኒያንና ጌርጌሴኖንን) እና የተለያዩ የአዕምሮ ህክምናና የሱስ ማገገሚያ ማዕከላት ሄደን ህመምተኞችን መጎብኘት ስለህመሙ ስለህመምተኞችና የሚደርስባቸውን ጫና ለመረዳት ያስችላልና የማግለል ሁኔታውን በመቀነስ የራሱን ሚና ይወጣል።

እናንተስ ስለህሙማኑ ምን አሰባችሁ?
የአዕምሮ ህሙማንን ማግለል ይቁም!

ቃልኪዳን ዮሐንስ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ልባምሕይወት

ከኖርን አይቀር የታሰበበት፣ አቅጣጫ ያለውና የምንወደውን ሕይወት ለምን አንኖርም?

በኒውሮ ሊንጉዊስቲክ ፕሮግራሚንግ (NLP) የተቃኘው የልባም ሕይወት የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና 13ኛ ዙር ምዝገባ ተጠናቆ ስልጠና ሊጀመር ነው።

ሆኖም ባሉት ቀሪ የተወሰኑ ቦታዎች ሰልጣኞችን መቀበል እንፈልጋለን። ስልጠናው ግንቦት 2 ይጀምራል።

ለአራት ሳምንታት፣ በሳምንት ሦስት ቀናት፣ ቀን ከ8:00 - 11:00 ሰዓት በሚሰጠው የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ለመመዝገብ እና ለተጨማሪ መረጃ: +251974046870

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel