melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እኛ እራሳችንን እና ሌሎች እኛን ምን ያህል ያውቁናል?

አንዳንድ ግዜ ሰዎች እኔ እራሴን በደንብ አውቀዋለሁ ወይም እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን የስነ-ባህሪ አጥኚዎች ሰው ራሱንም እንዲሁም ሌሎችን ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ እንደሚከተለው ያስረዱናል።

4ቱ ማንነቶቻችን፦

1. Open- ግልፅ ሆኖ የሚታየው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን እና ሌሎች እኛን የሚያውቁት ግልፅ የሆነው ማንነት ክፍል ነው።

2. Hidden- ድብቅ የሆነው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን የምናውቅው ሌሎች ግን ስለእኛ የማያውቁት ክፍል ነው።

3. Blind- ሰዎች ስለኛ የሚያውቁት እኛ ግን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።

4. Unknown- ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እኛ ራሳችን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።

ስለዚህ ከሰዎች ጋር መልካም እና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከላይ የተዘረዘሩትን የማንነት ክፍሎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

ካልሆነ ግን እከሌን አውቀዋለሁ ብለው ሲያስቡ አንድ ቀን ድብቁ/ የማያውቁት ማንነት ሲገለጥ ሊጎዱ ይችላሉ። እንዲሁም ራስዎትን ራሴን በደንብ አውቀዋለሁ በማለት ሌሎች ከሚሰጥዎት ምክር ባለመማር ራስዎትን ከማሳደግ እና ከማሻሻል እንዳይገደቡ ጥንንቃቄ ያድርጉ።

በ መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እራስን ካለፉ መጥፎ ክስተቶች እስር ነፃ ማውጣት!

ህይወትህ ውስጥ በተፈጠረ አንድ አሉታዊ ክስተት ምክንያት፣ በአዕምሮህ አሁንም እየተመላለሰ የሚያስቸግርህ ሃሳብ አለ? ይህ ሃሳብ ስሜቱ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ እንዴት አድርጌ ልርሳው ወይም ከትውስታዬ ልፋቀው ብለህ ታውቃለህ? 

አዕምሮህን እንደትልቅ ላይብረሪ ተረዳው። ከልጅነት እስከ እውቀት አንተ ጋር የተከናወኑ ነገሮች ሁሉ በትውስታ መልክ በውስጡ እንደመጽሃፍት ተሰድረውበት ይገኛሉ። ከእነዚህ ትውስታዎች አንዳንዶቹ  መልካም (አውንታዊ) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መልካም ያልሆኑ (አሉታዊ) ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ትውስታዎች ቢያልፉም እንደተገነዘብናቸው መጠን ዛሬም ድረስ ውስጣችን አውንታዊ ወይም አሉታዊ  ስሜት ይፈጥራሉ።

በተለይ የአሉታዊ ክስተቶች ተፅዕኖ አሉታዊ ስሜት ውስጣችን በመፍጠር ብቻ የሚቆም አይደለም። ብዙ ግዜ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ውስጥ ዛሬም ጣልቃ እየገቡ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳንወስን ሊከለክሉንም ይችላሉ። ከዚያም ሲያልፍ ጉዳዩ በተፈጠረበት ወቅት ከደረስንባቸው መረዳቶችና ድምዳሜዎች የተነሳ፣ ወደፊት መፍጠር ከምንፈልገው ህይወት አንጻር የማይጠቅም እይታ (አመለካከት) እንድናዳብርም ያደርጋሉ።

የሚገርመው ብዙ ግዜ አሉታዊ ስሜት የሚፈጥሩትን ትውስታዎች በቀላሉ ማስታወስ፣ እንዲያውም እነዚህ ትውስታዎች ውስጥ ለረጅም ግዜ በመቆየት ራሳችንን ቶርቸር ማድረግ ለብዙዎቻችን ቀላል ነው። ምናልባት እነዚህ የምናስታውሳቸው ክስተቶች ያለፉና የማይደገሙ እንደሆኑ ብናውቅም አዕምሯችን ግን  ክስተቶቹ አሁን በዚህ ቅጽበት እየተከናወኑ ያሉ እስከሚመስል ድረስ በጠንካራ አሉታዊ ስሜት ውስጥ እንድንዘፈቅ ያደርገናል። ታዲያ እነዚህ ያለፉ፣ የማይደገሙ ክስተቶች አሁን እየፈጠሩብን ካለው አሉታዊ ስሜት፣ የውሳኔ ውስንነትና፣ ጎታች አመለካከት ተፅዕኖዎች ራሳችንን እንዴት ማላቀቅ እንችላለን?

ይህን ጥያቄ ስናነሳ ብዙዎች “እርሳው ባክህ”፣ ወይም “ለበጎ ነው” ወዘተ የሚል ምላሽ ይሰጡናል። ነገርግን “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” ነውና እኛ ነገሩን ማስታወስ ፈልገን ሳይሆን አዕምሯችን ከኛ እውቅና ውጪ እያሳሰበን እንደሆነ ማን ይንገርልን?

እነዚህ በውስጣችን ተሰድረው ማለፋቸው ሳያንስ አሁንም ህይወታችንን ካመሰቃቀሉ ትውስታዎችን ለመፋታት የሚከተሉትን ማድረግ እንችላለን፦

1. እነዚህን ክስተቶች ከንደገና በማስታወስ ልንማርባቸው የምንችላቸው ነገሮች ካሉ ወረቀት ላይ በጽሁፍ ማስፈር።

2. እነዚህን ክስተቶች ከንደገና በማስታወስ ጉዳቱን የፈጠሩ ሰዎች ካሉ፣ በወቅቱ የነበረባቸውን የባህርይ፣ ስሜት እና የውሳኔ ውስንነት እንደገና አሁን ባለን መረዳት መመልከት። እነዚህ ውስንነቶች ባይኖሩባቸው ምን ሊያደርጉ ይችሉ እንደነበር ማሰብ፤ እነሱ የነበሩባቸውን ውስንነቶች እኛም ሳናውቅ እያንጸባረቅን እንዳልሆነ ማረጋገጥ።

3. የሚፈጥሩብን ስሜት ከባድ ከሆነና ከላይ ባደረግናቸው ልምምዶች ስሜቶቹንና ግንዛቤያችንን መለወጥ ካቃተን የባለሙያ ርዳታ እንፈልግ።

ዳንኤል አያሌው (Certified NLP Practitioner)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “እንደ ህብረተሰብ የስነልቦና ቁስልን መገንዘብ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የአሃ ሳይኮሎጂካል አገልግሎት መስራች እና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ ገ/ማሪያም ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️

https://forms.gle/Y8iPkGRELLR2cFW86

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የውድድር ስነ-ልቦና!

የውድድር ስነ ልቦና እንደዘርፉ ባለሙያዎች ትንታኔ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡

ውድድር ሰዎች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማነሳሳት እንደሚረዳና አውጥተውም እንዲያሳዩበት እድል የሚፈጥር መሆኑ ይነገራል፡፡

ሆኖም የውድድር መንፈስ እንደጥቅሙ ሁሉ በትክክል መያዝ ካልተቻለ ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ ጤናማ ያልሆነ ውድድርም የተለያዩ የጤና እክሎችን እንደሚያስከትልም ነው የሚነገረው፡፡

የውድድር ስነ-ልቦና ሰዎች በህይወታቸው ያልተመለከቱትን አቅጣጫ የሚመለከቱበት ነው። በተጨማሪም በተለያዩ መንገዶች የተሻለ ለመሆን እገዛ የሚያደርግ ነው።

ውድድር አሸናፊና ተሸናፊዎች ያሉበትና ሽንፈትን ፈጽሞ አለመቀበል ራስን አላስፈላጊ ጭንቀት ውስጥ ሲከት ይታያል፡፡ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኛ አልያም በስራ አካባቢ የበዛ የውድድር መንፈስ ሲታይ ተመልክተው ይሆናል፡፡

ይህ የውድድርና የአሸናፊነት ጥማት የሌሎችን ስኬት ዕውቅና ከመንፈግ ጀምሮ የራስን ማንነት አለመቀበል ሊያስከትል እንደሚችልም ይገለጻል፡፡

ይህም ሰዎችን መዋሸት፣ ጫናዎች፣ ጭንቀት፣ የበታችነት ስሜት መሰማትና በቂ ነገር የለኝም በማለት ያሉበትን ቦታ አለመውደድ እና የማንነት ቀውስ ውስጥ ያስገባል።

ያለአግባብ የውድድር መንፈስ በራስ መተማመን የሚያመጣው ስሜት ነው፥ የራሴ ነገር በቂ አይደለም በሚል ሃሳብ ሌሎችን ለመምሰል ይሞክራሉ፡፡ ይህ ስሜት እየቆየ ሲሄድም ቁጣ፣ ንዴት፣ ቅናት እና መሰል ስሜቶች መገለጥ ይጀምራሉ፡፡

ይህ ስሜት ከየት እንደመነጨ ማስተዋል፣ የሰዎችን ስኬት መቀበል፣ የውድድሩ ፍላጎት ራስን ከማሳደግ የመነጨ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው የሚለውን መለየት ችግሩን በወቅቱ ለመፍታት እንደሚያግዝም ይነገራል፡፡

ባርኮት ጌቱ (የስነ-ልቦና አማካሪ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የእነዚህ ሁለት ምስሎች ትርጉም ጥልቅ ነው።

ምስል 1

ውጫዊ ገጽታው በፈገግታ የታጀበ ቢመስልም ውስጡ ግን ጥልቅ ሃዘን አለ::

ለዚያም ነው የቅርብ ሰዎቻችንን በፈገግታቸው ለክተን ውስጣዊ ህመማቸውን ሳናይላቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ሲሞክሩ/ሲያጠፋ 'እኮ እንዴት' ብለን ስንገረም የምንስተዋለው።

ምስል 2

ይህ የፊት ገጽታ ለረጅም ጊዜ በድባቴ ስሜት ውስጥ ያለፋ ሰዎች ላይ የሚታይ የፊት ገጽታ ነው።

- Veraguth's fold (የአይን ቆዳቸው ቅጭም ማለት)
- Omega sign (የግንባር ቆዳቸው ኦሜጋ የምትባለዋን ፊደል የመስራት ያህል መሸብሸብ) ያመላክታል።

እና ምን ለማለት ነው የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም። የውስጥ ስሜት ሁሌም ፊት ላይ ላይነበብ ይችላልና!

የድብርት ህመም ውጤታማ የስነልቦና እና የመድሃኒት ህክምና አለው!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “ራስን የማጥፋት” ስሜትን መረዳት'' የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የሆኑት ገጣሚ ዶ/ር ፌበን ፋንጮ (ሳይካትሪ ሬዚደንት) ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️

https://forms.gle/uSWkjQdTrLmgLXVn9

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በልጅነት የእድሜ ክልል ውስጥ ያለፉ የህይወት መጥፎ አጋጣሚዎች በሰዎች የወደፊት ህይወት ላይ ጣልቃ በመግባት ይረብሻሉ። 

ወላጆችን በተለያዩ ምክንያት ማጣት፣  ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎች መሠል ችግሮች ሲያጋጥሙ ሰዎች ለሱሰኝነት፣ ለድብርት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይዳረጋሉ ይህም ደግሞ ለጸጸት እንደሚዳርጋቸውም ይገለጻል፡፡

የምንተገብራቸው ጉዳዮችን ጥቅም እና ጉዳት ላይ ጊዜ ወስዶ አገናዝቦ አለመወሰን፣ ምክንያታዊ ሆኖ አለመወሰን፣ በሰዎች ላይ ጸጸትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

የደስታ፣ የብስጭት እንዲሁም የሀዘን ስሜት በሰዎች ላይ የሚስተዋል ቢሆንም፦

- ስሜታዊ ሆኖ ማሰብ፣
- የጓደኛ/ አቻ ግፊት 
- አልኮል መጠጣት
- የአደንዛዥ እጽ መጠቀም ለጸጸት እንደ መነሻ ምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ለምን አደረኩ ብሎ እራስን መውቀስ ጠቃሚ ቢሆንም ትናንት ላይ ከመኖር ይልቅ ስለ ነገ መልካም ነገሮች ማሰብ ይጠቅማል። ለዚህም ከትናንት መጥፎ  የህይወት ገጠመኞች ትምህርትን በመውሰድ ለነገ አዲስ ህይወት መዘጋጀት በሰዎች ዘንድ ሊለመድ ይገባል።

አንዳንዶች ትናንት በገጠማቸው የህይወት መጥፎም ሆነ ጥሩ  ገጠመኞች ተምረው ያልፋሉ። ነገር ግን አሁንም ድረስ ባለፈ የህይወት ታሪካቸው ተሸፍነው የሚኖሩም አሉ።

የሚጸጸቱ ሰዎች ላይ፦

- የመበሳጨት፣
- ያለመረጋጋት
- የመጨነቅ ምልክቶች ይስተዋላሉ።

ከሚጸጽታቸው ጉዳይ ወይም በተደጋጋሚ አእምሯቸው ላይ እየተመላለሰ የሚረብሻቸውን ጉዳይ ጊዜ በመውሰድ ሊረዱት አልያም በጉዳዩ ላይ የባለሞያን ምክር ማግኘት አለባቸው።

ከመጥፎ ስሜቶች ለመውጣት እንደየሰው ጥንካሬ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በቅድሚያ ግን እራስን ከመውቀስ ይልቅ ለእራስ ይቅርታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ብሩክ ዩሃንስ (የስነ ልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Yetena Weg Clubhouse Discussion!

ከዶ/ር አስናቀ ልመነህ ጋር "የአዕምሮ ጤና ሰብአዊ መብት ነው" በሚለው የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን መሪ ቃል ላይ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉ።

🗓ጥቅምት 18 (እሁድ)
⏰ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)

ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ! ⬇️

https://www.clubhouse.com/invite/tA8LVpvi

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ራቆቱን የሮጠ ብቻ አይደለም የአእምሮ ታማሚ፣ የአእምሮ ጤና ሰፊ መገለጫ ያለው ውስብስብ ጉዳይ ነው። ከ3 ሰዎች 1 ሰው የአእምሮ ጤናው ላይ እክል እንዳለበት ጥናቶች ያሳያሉ። ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጠው ስውር ህመም፣ ድብቅ ወረርሽኝ ነው። ያለ አእምሮ ጤና ግን ሰላምም፣ ለውጥም፣ እድገትም የለም።

ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ
(የሥነ-አእምሮ ስፔሻሊስትና ሥነ-ልቦና አማካሪ)

(For any questions) 0912806077)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ራሳችሁን አትሰሩ!

ሰዎች ምን ይሉኛል እያላቹ ብቻ የምትኖሩ ከሆነ፣ ጥረታቹ ሁሉ ሰዎችን impress ለማድረግ ከሆነ፣ ጥሩ ስሜት የሚሰማቹ ሰዎች ሲያደንቋችሁና ሲፈልጓቹ ከሆነ፣ ሁሌም ተቀባይነት ለማግኘት ብቻ የምትኖሩ ከሆነ፣ በሰዎች ጥፋት ራሳችሁን የምትወቅሱ ከሆነ፣ እመኑኝ እስር ቤት ውስጥ ናችሁ።

ሰዎች ሁለንተናችንን እንዲቆጣጠሩት አንፍቀድ። ሰዎች ምን ይላሉ ከሚለው በላይ ምን መሆን አለበት ብለን እንጠይቅ። ዋጋችን ራሳችን ውስጥ እንጂ ሰዎች ውስጥ እንደሌለ አንርሳ። ሰዎችን ብቻ ስንከተል ራሳችንን እንዳናጣ እንጠንቀቅ።

ኤርሚያስ ኪሮስ
(ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወላጆች ተነጣጥለው የሚያሳድጓቸው ልጆች ምን አይነት ስነ-ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል?

አንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች የነገይቷን ኢትዮጵያ ተረካቢ ናቸው።

ደስተኛ፣ የሚከባበር እና ፍቅር የሰፈነበት ቤተሰብ መመስረት እና ልጆችን በዚያ ውስጥ ማሳደግ ለታዳጊዎቹ ቀላል የማይባል የሥነልቦናዊ ጥንካሬን ይሰጣቸዋል።

ከዚህ በተቃራኒው ወላጆች ተነጣጥለው የሚያሳድጓቸው ልጆች ምን ዓይነት ጫና ይደርስባቸዋል?

ወላጆች በልጆች አስተዳደግ ላይ በርካታ ሚና ያላቸው ቢሆንም፣ በዋናነት ግን መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት እና ቁጥጥር ወይም ጥበቃ ማድረግ የሚጠቀሱት ናቸው።

በተናጠል ቤተሰብ የሚያድጉ ልጆች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ወላጆች ሲለያዩ ልጆች ቀድሞ የነበራቸው የዕለት ተዕለት እቅስቃሴያቸው ወይም አካባቢ ሲቀይሩ የሚለወጥ ሲሆን፣ ለዚህም የትምህርት ቤት እና የመኖሪያ ቤት ሌሎችም ሊቀየሩ ይችላሉ።

ይህም የለመዱትን አከባቢ ትተው ሄደው ሌላ ለመላመድ መሞከሩ ግርታ ውስጥ ያስገባቸዋል።

ወላጆች በሚለያዩበት ጊዜ ደግሞ ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል።

ልጆች በወላጆች መለያየት የሚያሳዩት የስሜት እና የባህሪ ለውጥ ይኖራቸዋል በዚህም ምክንያት፦

- የባህሪ መቀየር ለምሳሌ መነጫነጭ፣ መበሳጨት፣ ኃይለኛነት
- ጭንቀት ውስጥ መግባት
- የትምህርት ውጤት መቀነስ
- ነገሮች ላይ ትኩረት ማጣት ሊከሰት ይችላል።

በዚህ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን ስንመለከት ልጆች እኔ የፍቺ ምክንያት ነኝ የሚል እሳቤ ውስጥ እንደሚገቡ ይጠቁማሉ ከዚህም በተጨማሪ ቶሎ የማደግ እና ይህ ነገር ከሚሰጣቸው ስሜት ለመውጣት እጅግ በመፈለጋቸው ላልተገባ ጭንቀት ይዳርጋቸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን በተነጣጠሉት ወላጆች መካከል የሚኖረው የተለያየ የአስተዳደግ ሥርዓት ልጆቹን ግራ መጋባት ውስጥ ይከታል።

በተጨማሪም በተነጣጠለ ቤተሰብ ውስጥ የሚያልፉ ልጆች ለሱስ ተጋላጭነታቸው የሰፋ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ::

ይህ ነገር ከፍ እያለ ሲሄድ እራስን እስከ ማጥፋት (suicidal attempt) እንደሚያጋልጥም ገልጸዋል።

በዚህ ሁኔታ ያደጉ ልጆች ለወደፊት የቤተሰብ ምስረታ ላይ የሚኖረቻው ምልከታ የጠራ አይሆንም።

ማጠቃለያ

ወላጆች ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠማቸው በስተቀር መለያየትን እንደ መፍትሄ ባይወሰዱ መልካም ነው።

ኖህ ውብሸት (የሥነልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

“ያላመናችሁብኝን ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ!”

የሰሞኑን US Open በመባል የታወቀውን የመሬት ላይ ቴኒስ ጨዋታ በማሸነፍ ዋንጫን የተረከበችው የመጀመሪያዋ የ19 ዓመት ወጣት ኮኮ (Coco Gauff) ነች፡፡ ይህን ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ተከታትየዋለሁ፡፡ ይህች ወጣት አስገራሚ ብቃቷን የገለጸችበት ጨዋታ ነበር፡፡ ከሁሉም ነገር አስራሚ ሆኖ ያገኘሁት ግን ጨዋታውን ካሸነፈች በኋላ በነበራት ቃለ-መጠይቀ ላይ ባደረገችው ንግግር ላይ የሰነዘረችው አንድ ሃሳብ ነው፡፡

“ይህንን ውድድር እንደማሸንፍ ያላመናችሁብኝን ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ” አለች በንግግሯ መካከል፡፡ ይህንን ያለችው እነሱ አትችልም ብለው ስላሰቡና እንደምታሸንፍ ያለማመናቸው ሁኔታ የበለጠ ውስጧን እንዳነሳሳውና ለማሸነፍ ቁርጠኛ እንድትሆን እንዳበረታት ለመግለጽ ነው፡፡

በማንነታችሁና በችሎታችሁ ያላመኑባችሁ ሰዎች አትችሉም በማለት የሚያወሩትን ወሬ ለመድከም ሳይሆን ለመበርታት፣ ለማቆም ሳይሆን ለመቀጠል፣ ለመሸነፍ ሳይሆን ለማሸነፍ፣ ወደኋላ ለመቅረት ሳይሆን ወደፊት ለመገስገስ . . . ተጠቅማችሁ ያሰባችሁበት ጋር ስትደርሱ ዛሬ ያላመኑባችሁን ሰዎች ለማመስገን ያብቃችሁ!!!

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ግንዛቤ!

ዓለምን ባለበት ሁኔታ ሳይሆን፤ ዓለምን እኛ እንዳለንበት ሁኔታ ነው የምናስተዉለው ይለናል። ዕውቁ መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ። 

ግንዛቤአችን የሕይወት መነጽራችን ነው።

ግንዛቤአችን ለነገሮች ካለን መረዳትና ትርጓሜ ጋር ባንድም ሆነ በሌላ በኩል ይያያዛል።

ስለራሳችን፣ ስለሌሎች ብሎም ስለ አለም ያለን ግንዛቤ በህይወት መንገድ ላይ ለሆነብንና ከሆኑት ክስተቶችና ሁነቶች ላይ በመነሳት የምንሰጠው ትርጉምና መረዳት ነው።

ለነገሮች የምንሰጠውን ትርጉምና ያለንን መረዳት ምን ያህሎቻችን በተለያየ መንገድና አቅጣጫ መርምረነው በጠራና በተሻለ መንገድ ተረድተነዋል?

አንድን ነገር ከባድም ቀላልም የሚያደርገው ነገሩን የምናይበት ሁኔታ ነው ሌላ ነገር የለዉም።

በተለያየ አቅጣጫና መንገድ ነገሮችን ለማየትና ለመረዳት የሚሞክሩ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በተሻለ ሁኔታ አንድን ነገር የመረዳትና የመገንዘብ እድል አላቸው።                                                                  
ዳንኤል አያሌው (Certified NLP Practitioner)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ትናንት ሞክረናቸው ያልሰመሩልን የህይወት ውጥኖችን ተስፋ ባለመቁረጥ በአዲስ ሞራልና ወኔ እንደገና እንሞክረው፡፡

በህይወታችን ውስጥ በአዲስ መልክ መጀመር ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው?

ትዳራችን እንዴት ነው?

አንቺ ትብሽ እኔ እብስ ተብሎ የተጀመረ ነገር ሁሉ በጊዜ እርጅና ይፈዛል አልፎ ትርፎም ቀለሙ ይወይባል፡፡ ትናንትና የነበረው ፍቅር፤ መረዳዳት፤ መከባበር፤ መደማመጥና ትዕግስት በጊዜ ሂደት ጠፍቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጣማሪዎቹ መካከል አንደኛው ወይም ሁለቱም የመጠቃት ስሜት እየተሰማቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ የቀደመውን ጊዜ ፍቅርና መልካምነት በማሰብ የዛሬ መጠቃትንና የመገፋት ስሜትን ለአንድ አፍታ በመተው ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደ ገና በአዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ሞክሩት፡፡ በትዝታ ብቻ የቀረው ፍቅራችሁና የትዳራችሁ መልካምነት ወደ ቀደሞ ክብሩ ይመለሳል፡፡ ግድ የላችሁም ከቻላችሁ ሁለታችሁም ይህ የማይቻል ከሆነ አንዳችሁ በመጀመሪያ ኃላፊነት በመውሰድ ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደገና ስሩት፤ በውጤቱ ትደነቃላችሁ፡፡

ማኅበራዊ ህይወታችሁ?

ማኅበራዊ ህይወት መልካም እንደሆነ ሁሉ አንዳንዴ ባልተፈለገና ባልተጠበቀ አቅጣጫ ያመራና ከወዳችነት መንፈስ ወደ ጠላትነት የመሸጋገር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ አንዱ በዳይ ሌላኛው ደግሞ ተበዳይ ሆኖ በአንጀት መቆሳሰል የግንኙነት ሰንሰለቱ ተበጣጥሶ ይሆናል፡፡ የተራራቃችሁትና የተቆራረጣችሁት ሰው ምንም እንኳን ቢያጠፋና ቢበድል በህይወታችሁ አስፈላጊ ነው ብላችሁ የምታምኑት ዓይነት ሰው ከሆነ እስቲ አንድ ዕድል ስጡትና ማኅበራዊ ህይወታችሁን በማደስ እንደገና ሞክሩት፡፡

ስራችሁስ?

በግልም ይሁን ተቀጥራችሁ በምትሰሩት ስራ ውጤታማና ተሸላሚ ለመሆን ብዙ ርቀት ተጉዛችሁ ፤ ለፍታችሁ፤ ወዛችሁን አሟጣችሁ በስተመጨረሻም የልፋታችሁ ውጤት ሲታይ ትርፍና ኪሳራው እንደማይታወቅ ነጋዴ ዓይነት ሆኖባችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ ቆም በሉና ሌሎቹ ሲሳካላቸው እኔ ያልተሳካልኝ ምክንያት ምንድን ነው ብላችሁ በመጠየቅ በአዲስ መንፈስና ወኔ ጀምሩት፡፡ እስቲ በትናንትናው ጅምርና ልምድ ሳይሆን በሌላ አተያይ ችግራችሁ ምን እንደነበር ለመፈልፈል ጥረት አድርጉ፡፡ ከዚያ በአዲስ መልክ ስራችሁን ጀምሩ በእርግጠኝነት ይሳካላችዋል፡፡

አመለካከታችሁ?

ለዘመናት ሰው ለምን ይጠላኛል ብላችሁ እራሳችሁን በሃዘን፤ በትካዜ እንዲሁም እራስን ከማኅበራዊ ህይወት እስከ ማግለል ደርሳችሁ በብቸኝነት ስሜት እየተገረፋችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ግድ የለም ሰው ለምን ይጠላኛል ሳይሆን የሚጠላብኝ ነገር ምንድን ነው ብላችሁ እራሳችሁን ፈትሹ፡፡ አንዳንዴም ሌላው ሰው ምንም ሳይለን እኛው እራሳችን በምንፈጥረው ምክንያት የለሽ አስተሳሰብ ሌሎች እንደሚጠሉን ልናስብ እንችላለን፡፡ አእምሮአችሁን በአወንታዊ አስተሳብ በመገንባት ስለእራሳችሁ ጥሩ ምልከታ ይኑራችሁ፡፡ ከዚያ ሁኔታዎችን እንደ አመጣጣቸው በአዲስ መልክ ለመመለስ ሞክሩ ፤ ደስታንም ታገኛላችሁ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ይታይባችዋል?

ሁሉም ነገር በእናንተ ተቃራኒ የሚሄድ ከሆነ እናንተ እራሳችሁ የተሳሳታችሁት ነገር ሊኖር ስለሚችል ቆም ብላችሁ እራሳችሁን መርምሩ፡፡ ትናንት ብትወድቁና ባይሳካላችሁ ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው እንደገና ሞክሩት፡፡ ከአይሳካልኝም፤ ይሳካልኛል፤ ከአልችልም እችላለሁ፤ ሁሉም ነገር ጨለማ ነው ብሎ ከማሰብ ከጨለማው በኋላ ጽልመቱ በብርሃን ጸዳል ይገፈፋል ብሎ ማሰብና አዲስ ተስፋ መሰነቅ፡፡ ህይወት ሎተሪ ናት ደጋግመህ ሞክራት ይባል የለ፤ ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዞአችሁን አንድ በማለት እንደገና ጀምሩት፡፡

ሱሰኝነት?

አዲስ ዓመትና አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ከሱስ ለመገላገል ለእራስችሁ ቃል በመግባትና ምሎ በመገዘት ጥራችሁ ጥራችሁ ወደ ምትጠሉት ወጥመድ ትብታብ ውስጥ ወድቃችሁ ይሆናል፡፡ ትናንትና ሱስን ለመተው በመጀመሪያ አእምሮአችሁን ሳታሳምኑ ቀጥታ ድርጊቱን በመተው ጀምራችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ግን መጀመሪያ እንደምትችሉ  አእምሮችሁን አሳምኑ ከዚያ ድርጊቱን በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለመተው በአዲስ አስተሳሰብና መንገድ ጀምሩት፡፡ በእርግጠኝነት መድረስ ወደ የምትፈልጉበት ቦታ ላይ እንዳትደርሱ እንቅፋት ሆኖ የሚይዛችሁ ነገር የለም፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቁርጠኛ መሆን ብቻ ነው፡፡

በአጠቃላይ በህይወት መንገድ ሁሌ ወደ ፊት ብቻ መሄድ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ከተነሱበት የህይወት አቅጣጫ እራስን ዞር ብሎ በመመልከት እንደገና እንደ አዲስ የሚጀመሩ ምዕራፎች አሉ፡፡ ስለዚህ በህይወቴ ይህንና ያንን አጥቻለው ብላችሁ የምታምኑትንና እንደገና ለማግኘት የምትመኙት ነገር ካለ ያለማቅማማት ህይወትን በአዲስ መልክ ጀምሯት ይሳካላችዋል፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ምዕናባዊ ኦቲዝም፤ የዲጅታል ዘመን ልጆች ስጋት

ባለሙያዎች እንደሚሉት በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በታብሌት፣ በቴሌቪዝን እና በሌሎች ዲጅታል መሳሪያዎች ላይ ረዘም ያለ ጊዜ የሚያሳልፉ ልጆች ለጭንቀት እና ለመረበሽ፣ ለትኩረት ማጣት፣ ለንግግር እና ለቋንቋ መዘግየት እንዲሁም ለግንዛቤ እድገት ውሱንነት ይዳረጋሉ። የሰዎችን ስሜት የመረዳት እና የመግባባት ችሎታቸውንም ይቀንሳል።

በዚህ ዙሪያ #DW ያዘጋጀውን ፅሁፍ ያንብቡ ⬇️

https://p.dw.com/p/4erN2?maca=amh-Facebook-dw

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጤናማ ህይወትን መምራት እንዴት ይቻላል?

ጤናማ መሆን ማለት በአዕምሮ፣ በአካልና በስሜት ሙሉ ጤንነት ሲሰማን ማለት ነው፡፡

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል በበሽታ እንዳንጠቃ ከማገዙም በላይ ጤናችን ስንጠብቅ ለራሳችን ያለን ግምት መልካም እንደሚሆን የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ደስተኛ፣ የተረጋጋና ስኬታማ ህይወት እንድንኖር ይረዳናል፡፡

ምንም እንኳን የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ሁኔታዎች ጤናማ ህይወትን ለመምራት አሉታዊ ተጽዕኖ ቢፈጥሩም አኗኗራችንን እና ልማዶቻችንን በመቀየር ጤናማ ህይወት መኖር እንደሚቻል ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት።

ጤናማ ህይወት ለመኖር የሰው ልጅ የተለያዩ የህይወት ዘይቤዎችን ይተገብራል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፦

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
• ክብደትን መለካትና መቆጣጠር፣
• በቂ ውሃ መጠጣት፣
• ለረዥም ጊዜ ያለመቀመጥና ኮምፒውተርና ሌሎች ስክሪን ላይ የምናጠፋውን ጊዜ መቀነስ፣
• በቂ እንቅልፍ መተኛት፣
• ከመጠን ያለፈ አልኮል ያለመውሰድ፣
• ቁጣና መሰል ስሜቶችን መቆጣጠር፣
• ጭንቀትን ማስወገድ፣
•የጤና ክትትል ማድረግና መሰል የጤናማ አኗኗር ዘይቤዎች ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም ከሰዎች ጋር ያለንን ማህበራዊ ግንኙነት በትኩረት መመልከት ያስፈልጋል። ከጓደኞች፣ ከቤተሰብና ጎረቤት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን የዕለት ተዕለት ግንኙነት ማሻሻልና መልካም ማድረግ ለጤናማ ህይወት አስፈላጊ እንደሆነ የሜዲሲን ኔት መረጃ ያመላክታል፡፡
 
@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና፦

- የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።

- በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::

አጋላጮች፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።

- በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።

ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም *በህይወት መቆየት አለመፈልግ

የባህሪ ችግሮች፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር

የአመጋገብ ችግር፦
➡ ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው።

የስነ-ልቦና ቀውስ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድርበታል።

- ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ  በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።

#WHO #TikvahEthiopia

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓም በብይነ መረብ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::

በዕለቱ በአእምሮ ጤና ዙሪያ የሚያጠነጥነው “የሁሉ” የልብወለድ መፅሃፍ ላይ ከዶ/ር አዜብ አሳምነው ከዶ/ር ዮናስ ላቀው እንዲሁም ከደራሲው ከዶ/ር ዳዊት አሰፋ ጋር የኦንላይን ውይይት ይደረጋል፡፡

በዕለቱ ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ ⬇️

https://meet.google.com/gsd-iztg-rop

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ራስን ማጥፋት (suicide)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገር በስፋት የምንሰማው ራስን የማጥፋት (suicide) ተግባር በሀገራችን በተለይም አንዲት እንስት 'ብንሄድ ይሻላል' ብላ Facebook ከለጠፈች እና ራሷን ካጠፋች ብኋላ በሀገራችን በተለይም በወጣቱ ዘንድ እንደተስፋፋ ግልፅ ነው።

ከዚህ ቀደም በሚዲያ አንሰማው ይሆናል እንጂ ይህ ራስን የማጥፋት ድርጊት በዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ የትምህርት እና ስራ ቦታዎች ላይ ሲከሰት ነበር።

ምናልባትም ይህንን በራሳችን ላይ ለመፈፀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፍን ልንኖር እንችላለን። ሰው ነፍሱን በራሱ ለማጥፋት ምክንያት የሚሆኑ በጥቂቱ ብንጠቅስ፦

ሕይወት ፊቷን ስታዞር እና ቀን ሲጨልምበት፣ በሚያመነው ሰው ሲከዳ እና ተስፋውን ሲያጣ፣ የኑሮ ፈተና ሲበዛ እና መውጫ መንገድ ሲጠፋበት፣ በሚያሰበው ልክ ነገሮች ሳይከናወኑለት ሲቀሩ፣ በሚያየው ሁሉ ነገን ኣሻግሮ ማየት ሲያቅተው፣ በቤቱ፣ በትዳሩ ክብርን እና ተቀባይነት ሲነፈግ ወ.ዘ.ተ ናቸው።

በርግጥ በግለሰቡ ሁኔታ እና ጫማ ውስጥ ሆነን ነገሩን መመልከት እስካልቻልን ድረስ ስለዚህ ሁኔታ በድፍረት መናገር አንችልም።

የራስን ማጥፋት ውሳኔ ቅፅበታዊ ነው። ጥቂት ሰከንዶች ሺህ ዘመን መስለው ይታያሉ። ስቃይ እና ፈተና ዘላለማዊ ይመስልና አዕምሯችን ለውሳኔ እንድንጣደፍ ሆርሞኖችን ይቀሰቅሳል። ከዚያ ነገሮች ያበቃሉ። ሰዎች የሰዎችን ሁኔታ አያዩም እንጂ በርካቶች ለተመሳሳይ ወጥመድ ተጋልጠው በተዓምር ይሁን በራሳቸው ብርታት አምልጠዋል። ለዚህ ምስክሮችን መጥራት አያስፈልግም።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እንዳናገኝ እነዚህ ነገሮችን ብንተገብር መልካም ነው ብዬ አስባለው።

1. ከእምነት ተቋማት አለመራቅ። ሀይማኖታዊነትን መላበስ በራሱ የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጣል ብዬ አምናለው።

2. Multi-Professional-Friends ሊኖሩን ይገባል። በአንድ ሙያ መስክ ብቻ የተሰማሩ ጓደኞች አይኑሯችሁ። ሕይወትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሊያስመለክቱ የሚችሉ ወዳጆችን መፍጠር ያስፈልጋል።

3. በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ - Counselling and Guidance Service ተቋማትን መጎብኘት ያስፈልጋል። በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ እነዚህ ተቋማት በመሰል ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ቦታዎች በየከተማው ላይ መስፋፋት አለባቸው።

ራሳቸውን ላጠፉ ፈጣሪ እዝነቱን ያድርግላቸው!

Credit: Workineh Gebeyehu Gomera

#EliasMeseret

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የጭንቀት መነሻዎችና መፍትሄዎች!

የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ 2019 ባደረገው ጥናት በዓለም ዙሪያ 301 ሚሊየን ሰዎች በጭንቀት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 58 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት እና ወጣቶች መሆናቸውንም ነው የገለጸው።

የአዕምሮ በሽታ ተብለው ከሚጠቀሱና በማህበረሰቡ በስፋት ከሚስተዋሉት መካከል ጭንቀት አንዱ ሲሆን፥ ከራስ ጋር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖር ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጫናን ሊፈጥር ብሎም የስራ ምርታማነትን እና ወደ ስኬት የሚደረገው ጉዞ ላይ እክል ሊፈጥር ይችላል፡፡

ይህም የተወሰነ የእድሜ ክልልን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍልን የሚያጠቃ ነው፡፡

ያለበቂ ምክንያት ወይም ሊያስጨንቅዎት የሚገባው ነገር ካለፈ በኋላ ስሜቱ ሲቀጥል ጭንቀት ይባላል።

በአሁኑ ወቅት መረጃ ከመጠን በላይ መገኘት፣ ያለአግባብ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ራስን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር፣ ጤና፣ ገንዘብ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የልጅነት ገጠመኞች፣ ከባድ አጋጣሚዎች፣ ለነገሩ የሚሰጡት ክብደት መጨመሩ እና ሌሎች የጭንቀት መንስዔዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አብዛኞቹ የአዕምሮ በሽታዎች ያሉበት ደረጃ ባሕርያትና ሁኔታ ከሰውሰው ይለያያሉ፥ አንዳንዶቹ ላይ ቀለል ያለ ሌሎች ላይ ደግሞ ከባድ ወይም ውስብስብ ምልክቶችን ያሳያሉ።

የባህሪ መቀያየር እስከ ማህበራዊ ህይወት መገለል ያሉ ምልክቶችም ይታያሉ።

በተጨማሪም የእጅ መንቀጥቀጥ፣ ላብ ላብ ማለት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የድካም ስሜት፣ የራስ ምታት፣ የተወሰኑ ነገሮች ላይ ደጋግሞ ማሰብ፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ደስታ ወይም ፍላጎት ማጣት ምልክቶች ናቸው፡፡

በአብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሰዎች የሥነ-አዕምሮ በሽታ ተጠቂዎች እንደሆኑ አምነው ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ መታከም አልተለመደም፤ ይህንን ተከትሎም በሽታው ከነበረበት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በመድረስ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

የአዕምሮ ጤና ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ ወደሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል ይላሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፡፡

በአካባቢና በህይወትዎ የሚፈጠሩ ክስተቶች በአግባቡ ካልተቆጣጠሩት እና ራስዎ ላይ ትኩረት አድርገው ካልሰሩ የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ ሊከትል ይችላል፡፡

አልፎ አልፎ ጭንቀትን በተለመደው የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ሊያጋጥም ይችላል። ሆኖም በጭንቀት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በራሳቸው ጥረትና በህክምና ባለሙያዎች እገዛ ተደርጎላቸው መዳን ይችላሉ፡፡

በዚህም ለራስ ጊዜ በመስጠት (በጥሞና) ነገሮችን ማሰላሰል፣ ተረጋግቶ የራስን ህይወት በትኩረት ማየት፣ አስተሳሰብ ላይ ረዘም ያለ ጊዜ በመውሰድ ፍተሻ ማድረግ፣ ለነገሮች የሚሰጡትን አመክንዮ እና ራስ ላይ በማተኮር መፍትሄ መስጠት ይቻላል፡፡

ከዚህ ባስ ካለ ወይም የባለሙያ እገዛ ካስፈለግዎ ሃኪምን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

ቴዎድሮስ ድልነሳው (የሥነ-ልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፀፀትን እንዴት ከራስዎ ያርቃሉ?

ሰዎች የሚሰማቸው የሃዘን፣ የቁጭት እና የመረበሽ ስሜት ድምር ፀፀት ይባላል፡፡

ፀፀት የተሻለ ስራን ለመስራት ወኔ ቢፈጥርም ከልክ ካለፈ ግን ቀላል የማይባል ተጽዕኖን ይፈጥራል፡፡

ለፀፀት የሚዳርጉ ምክንያቶች፦

- ሥህተት መስራት እና
- እንከን የለሽ ሆኖ ማደግ፦ በልጅነት ጊዜያቸው ፍጹም በመሆን ተጽዕኖ ውስጥ ያለፉ መሆን

ፀፀት በርካታ ጉዳቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፦

– የመስራት አቅምን ይነጥቃል
– የበታችነት ስሜት ይፈጥራል
– ተስፋ መቁረጥ
– ኢኮኖሚ ችግር እና
– ማህበራዊ ችግር

ፀፀት የከፍተኛ ጭንቀትና ድባቴ ውስጥ ከሚከቱ የስሜት መዘበራረቆች መካከል አንዱ ሲሆን፥ ይህ ከተባባሰ የአካልና የአዕምሮ እክልን ያስከትላል ይላሉ ባለሙያው፡፡

ፀፀት ውስጥ እንዳይገቡ መፍትሄው ምንድን ነው?

– ስህተትን አምኖ መቀበል
– የሚታረም ከሆነ በቻሉት አቅም ለማረም ጥረት ማድረግ
– አካባቢን መቀየር
– ሥር የሰደደ እና ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ማግኘትና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
 
ሔኖክ ሃ/ማርያም (የሥነ-ልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለራስ ማድረግ መቻል!

ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ፣ ለሌሎች ሰዎች ብዙ የምናደርጋቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ያህል እናስብላቸዋለን፣ እንጋብዛቸዋለን፣ እናዳምጣቸዋለን፣ ደስተኛ እንዲሆኑ የቻልነውን እንሞክራለን።

ለኛ ለራሳችንስ ምን አድርገን እናውቃለን?

ራሴን መቼ ነው የጋበዝኩት?
ራሴን መቼ ነው ያዳመጥኩት?
ራሴን መቼ ነው ያሰብኩለት?
ራሴን መቼ ነው የተንከባከብኩት? ወዘተ

በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የሚያስችሉንን ነገሮች ሁሉ እናደርጋለን። ነገር ግን መቅደም ያለበት እራሳችንን መቀበል ነው ወይንስ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው?

ከእኔ ውጪ ላሉ ነገሮች ሁሉ መትረፍ የምችለው እኔ በጥሩ ሁኔታ መኖር ከቻልኩ ብቻ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ለራሴ ብለን የምናደርጋቸው ነገሮች ሊኖሩን ይገባል።

ይህ ራስ ወዳድ መሆን አይደለም። እኔነቴን መንከባከብ፣ ማፍቀርና ፍሬያማ ማድረግ እንጂ።

ተመስገን አብይ (የስነ-ልቦና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ትኩረት መነፈግና ተጽዕኖው!

የሰዎችን ትኩረት ማጣት ጭንቀትና ከፍተኛ የሆነ ድባቴ እንዲሁም ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሰዎች በተለይም ህጻናት ከሚገባው በታች ትኩረት ሲያገኙ የወደፊት ህይዎታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያደርስ ይችላል፡፡

አንድ ሰው የሚገባውን ያህል ትኩረት ካላገኘ ምንም ያሕል አቅም ቢኖረውም እንኳን አቅሙን አውጥቶ ሊጠቀምበት የሚችልበት ዕድል አናሳ ነው፡፡

ግለሰቡ ‘’ሰው አይቀበለኝም፤ ልክ ላልሆን እችላለሁ’’ ብሎ ስለሚያስብ ያለውን አቅም ለሕብረተሰቡ ሳያንጸበርቅ ሊቀር ይችላል፡፡

ከሰው መሸሽ፣ ለራስ ዝቅተኛ የሆነ ስሜት መኖር፣ ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማብዛት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ሊመጡ ይችላሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ሕመሙ ሲባባስ ሕክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ይህ ጉዳይ አብዛኛውን ጊዜ ችላ ይባላል። ‘’አመሏ/ሉ ነው፤ ብቻው/ዋን መሆን ትወዳለች/ይወዳል’’ በማለት የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ።

ይህም ሣይታወቅ ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ ችግር ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል ማወቅ ይገባል፡፡

መፍትሄው ምንድነው?

- ከቤተሰብ ጋር ማውራትና ችግሮችን መፍታት፣
- ከተለያዩ ሰዎች ጋር ሃሳብ መለዋወጥ ካለባቸው ድባቴ ወይንም ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲወጡ ያግዛል፡፡

አበበ አምባው (የተቀናጀ የአዕምሮ ጤና ስፔሻሊስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ጤንነትን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?

- ሁልጊዜ እራስን ደስተኛ ማድረግ
- ከሰዎች ጋር ጊዜዎትን ማሳለፍ፣ ብቻ አለመሆን
- ዘላቂነት ያለው አስተሳሰብ መኖር
- የተሰጠንን ነገር ደጋግመን ማሰብ
- የበጎፋቃድ ተግባሮችን ማድረግ
- በራስ የመተማመን ስሜትን መላመድ 
- የፈጠራ ችሎታዎን ማዳበር
- ጤናማ እንቅልፍ ማግኘት
- ጤናማ የአመጋገብ ስርአት መከተል
- በራሳችን መድኃኒቶችን አለመውሰድ
- ጭንቀትን ማስወገድ
- ስሜታዊ/ብስጩ አለመሆን
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

የአእምሮ ሀኪም ጋር መሄድ ያለብን መቼ ነው?

- በእለት ተለት እንቅስቃሴያችን በሚያጋጥሙን ምክኒያቶች ልንናደድ ወይም ልንጨነቅ እንችላለን ነገር ግን ምንም ምክኒያት ሳይኖረን የምንጨነቅ፣ የምንረበሽ እና ከልክ ያለፈ ፍርሃት የሚሰማን ከሆነ።
- ምክኒያቱ ያልተረዳነው ጭንቀት እና መረበሽ በስራችን፣ በትምህርታችን፣ በውጤታማነታችን እና በማህበራዊ ግንኙነታችን ላይ ተፅእኖ ካመጣ።
- የመረበሽ እና የመጨነቅ ስሜቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየ።
- በዙሪያችን ያሉ የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛ እና የትዳር አጋር የምናሳየውን አዲስ ስሜት አይተው ሁኔታህ ጥሩ አይመስልም ምንሆነሃል/ሻል ብለው እስኪጠይቁ የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ከደረስን።
- የሚሰማዎት ጭንቀት ከልክ በላይ ሆኖ እርሱን ለመርሳት የአልኮል መጠጥ እና የእንቅልፍ መድሃኒቶችን መፈለግ ከጀመሩ።
- ከሚሰማዎት ጭንቀት ብዛት "አሁንስ ብሞት ይሻላል" የሚል ሀሳብ ከጀመሮት። 
- ያልተለመደ ሃሳብ ማለትም ሰዎችን መጠራጠር እና ያልተለመዱ ድምፆችን መስማት ከጀመሩ በግዜ የስነ-ልቦና አማካሪ/ የስነ-አዕምሮ ሐኪም ጋር በመሄድ የንግግር ወይም የመድሃኒት ህክምና ያግኙ።

#WorldMentalHealthDay
October 10, 2023

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አለም አቀፍ የአእምሮ ጤና ቀን በየዓመቱ መስከረም ወር መጨረሻ ይከበራል!

ሜንታል ሄልዝ አዲስም ይህን አስመልክቶ በዚህ ወር “የአእምሮ ጤና ሰብዓዊ መብት ነው!” በሚል ርዕስ በበይነ መረብ (online) የሚቀርብ የፓናል ውይይት አዘጋጅቷል፡፡

ቀን፦ ቅዳሜ መስከረም 26/ 2016
ሰዓት፦ 10፡00 (ከሰዓት)

በዕለቱ ይህን መስፈንጠሪያ ተጭነው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ⬇️

https://meet.google.com/gsd-iztg-rop

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጭንቅላትህን አፅዳው!

….ጭንቅላትን (አዕምሮን) ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡ የቆሸሸ ደግሞ ይጣላል እንጂ አይጠቅምም፡፡

አዕምሮውን የጣለ ልብሱን ከጣለ የባሰ ነው፡፡ ልብስ ያጣ እፍረተ ስጋውን በቅጠል ሊሸፍን ይችላል፡፡ አዕምሮውን የጣለ ግን ገበናውን በምን ሊሸፍነው ይችላል? በምንም!

ወዳጄ ሆይ…. ራስህን ጠብቅ! ራስህን ጠብቅ ማለት አለባበስህን አልያም አበላልህን ማለቴ ብቻ አይደለም፡፡ ራስህን ጠብቅ የምለው አስተሳሰብህንም ጭምር ነው፡፡

ምን ዘንካታ ብትሆንና አለባበስህ ቢያምር ጭንቅላትህ (ሕሊናህ) ከቆሸሸ በሚያምር ንፁህ ቤት ውስጥ ቆሻሻ መከመር ነው የሚሆነው፡፡

ራስህን ጠብቅ ማለት ጭንቅላትህን አፅዳው (ተንከባከበው)፤ ልቦናህን አጥራው፣ አስተሳሰብህን አስላው፣ ስሜትህን ግራው፣ ሃሳብህን ተቆጣጠረው፣ ሕሊናህን ዘወትር በአዲስና በበጎ ሃሳብ ሞርደው፣ ምክንያታዊነትህን እየጨማመርክ አሳድገው ማለቴ ነው፡፡

አዎ ራስህን ያልተፈለገ ቦታ ከመጣልህ በፊት አስብ! ማሰብህ ራስህን ከመጣል ያድንሃል፡፡ ጠቃሚ እንጂ ጎጂ አትሆንም፡፡ አንዳንድ ሰው ራሱን ከመጣል አልፎ ለሐገርም ስጋት፤ ለወገኖቹም ጎጂ ይሆናል፡፡

ራስህን ከምትጥል ገንዘብህን ብትጥል ይሻላል!

ራስ ማለት ጭንቅላት ነው! ራስ ማለት ምክንያታዊነት ነው! ራስ ማለት ሰውነት ነው!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አዎንታዊ ስነልቦና (Positive Psychology)

አዎንታዊ ስነልቦና ህይወትን ለመኖር ብቁ ስለሚያደርጋት ነገርና እና የሰዎችን የመኖር አዎንታዊ ፍላጎት ምንጭ ምንነት የሚመረምር የሳይንስ ዓይነት ነው፡፡

አዎንታዊ ስነልቦና ከሌሎች የሳይኮሎጂ መንገዶች በተለየ ተግዳሮቶች ላይ ሳይሆን መልካም ጎኖች ላይ የሚያተኩር የሳይንስ ዓይነት ነው፡፡ ማለትም የተፈጠሩ ችግሮች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ያሉንን ጠንካራ ጎኖች እና ወደ ፊት የሚኖሩን ብሩህ ተስፋዎች ላይ ያነጣጥራል፡፡

ይህ ሳይንስ ሌሎቹን የስነልቦና (Psychology) ሳይንሶች በማፍረስ ሳይሆን እነርሱ ላይ በመደመር ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎም ያምናል፡፡ የዚህ ሳይንስ ዋናው ሀሳብ ደህንነት ነው፡፡ ሰዎች እንዴት ደህና ይሆናሉ?

ማርቲን ሴሊግማን የአዎንታዊ ስነልቦና ሃሳብ ጠንሳሽ ከሆኑት ተመራማሪዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ስለደህንነት (well beingness) ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር ደህንነት አምስት መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው እነርሱም፡-

1. አዎንታዊ ስሜት

ሰዎች ስለነገሮች የሚኖራቸው ስሜት አዎንታዊ አሊያም አሉታዊ መሆን በአዕምሯቸው ላይም ሆነ በሰውነታቸው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ልዩነትን ሊያመጣ ይችላል፡፡

2. መጠመድ

ሰዎች በስራቸው አሊያም በሂወት ዓላማቸው በተጠመዱ ቁጥር ደህንነታቸው አስተማማኝ እየሆነ ይመጣል፡፡ የሰው ልጆች አዕምሮ ስራ መፍታትን ከሆነ ከገደብ በላይ መቀበል አይቻለውም ያም ደህንነታቸውን አስጊ ወደሆነ ደረጃ እንዲያሽቆለቁል ያረጋል፡፡

3. ግንኙነት

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ውስጣዊ ክፍተትን የመሙላት በሀሪ ስላላቸው ሰዎች እንደ ብቸኝነት እና ባይተዋርነት ያሉ አፍራሽ ስሜቶች እንዳይሰማቸው በማድረግ ለደህንነታቸው እንደ ዋስትና ያገለግላል፡፡

4. ትርጉም

ሰዎች በህይወት ለመቆየታቸው እና ለእያንዳንዷ እንቅስቃሲያቸው ትርጉም ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ ሰዎች ትርጉም አልባ ህይወት እንዳይኖሩ የሚደርጓቸውን የህይወት ትርጓሜዎች ባበጁ ቁጥር ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል፡፡

5. ማጠናቀቅ

ሰዎች ከልፋታቸው ማግስት ውጤት ከድካማቸው በኋላም ፍሬን ይፈልጋሉ። በመሆኑም የተጠመዱበትን ነገር መጨረሻ ማየት ደህንነታቸውን ያረጋግጥላቸዋል።

ምንጭ፡- PsychologyToday

ፍ/ማርያም ተስፋዬ (Psychologist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ቤተሰብ ለልጁ ሊያደርግለት የሚችለው አንዱ ትልቁ ውለታ የመማር ጉጉት (curiosity) መፍጠር ነው።

ልጆች ለትምህርት መጓጓት አለባቸው። "ትምህርት ቤት ሄጄ ማወቅ፣ መማር እፈልጋለሁ፤ አባቴ እናቴ ትምህርት ቤት እንዲሄድ ይፈልጋሉ እኔም መሄድ እፈልጋለው" የሚል ስሜት መፍጠር ያስፈልጋል።

ይሄ ለህይወት ዘመን ለልጆቻችን የምናስታጥቃቸው ትልቅ ትጥቅና ስጦታ ነው። ይህ ከሆነ ልጆቻችን ብዙ ክትትልና ድጋፍ ላያስፈልጋቸው ይችላል።

የትምህርት ጉጉት የተፈጠረለት ልጅ ከተመረቀም በኋላ ማንበብን፣ መጠየቅን ማዳመጥን እንደ ትልቅ ሙያ አድርጎ ይይዛል። ቤተሰብ በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ጉጉት ለልጆቹ መፍጠር ይጠበቅበታል።

[ዶ/ር ሰለሞን በላይ] #TM

መልካም የትምህርት ዘመን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የመፅሀፍ ጥቆማ!

"የሁሉ" የአእምሮ ጤና አንኳር ጉዳዮች ከማህበረ - ፖለቲካዊ ተግዳሮቶቻችን ጋር ተሰናስሎ የቀረበበት ልቦለድ መፅሐፍ ነው።

በጃፈር እና ሀሁ የመፅሐፍ መደብር ያገኙታል

ዶ/ር ዳዊት አሰፋ (የአእምሮ ሐኪም፡ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል)

ስልክ: 0911882934

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel