Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot
መዋሸት ከአዕምሮ ጤና ችግር ጋር ምን ያገናኘዋል?
መዋሸት ከልጅነት ዕድሜ ይጀምር እና እስከ እድሜ አመሻሽ ድረስ ሊቀጥል ይችላል። ውሸት የህመም ምልክት እና የስብዕና መለያ ተደርጎ ይታሰባል፡፡
ውሸት ህመም ነው ማለት ባይቻልም ሲደጋገም ግን እንደ ህመም ባይወሰድም የህመም ምልክት ግን ሊሆን ይችላል፡፡
ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ውስጥ ሊዋሹ የሚችሉ ሲሆን፤ ጊዜ እና ቦታ እየመረጡ የሚዋሹ እና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዋሸትን የሚመርጡ በማለት በሁለት መልኩ ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡
ለመዋሸት እንደ ምክንያት የሚነገሩ መላምቶች፦
• የአእምሮ ጭንቀት
• የጤና እክል
• ዝቅተኛ በራስ መተማን
• በሰዎች ዘንድ ተፈላጊነትን ለመጨመር በማሰብ
• የናርስሲሲት ስብዕና ያላቸው ሰዎች (አፍቅሮተ ራስ)
• ከዚህ በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የሚዋሽ ሰው ካለ ህጻናት ውሸትን እየተላመዱ እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡
በመዋሸት ሌሎችን ለመጉዳት የሚሞክሩ ሰዎች ቢኖሩም ያለፈ የህይወት ታሪካቸው በሚያሳድርባቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ ሰዎች ሊዋሹ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ለምን እንደሚዋሹ ምክንያቱን ባይቁትም ፍላጎታቸው መዋሸት ብቻ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡
የመዋሸት ፍላጎታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይጨምር እና በመዋሸታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ሲናገሩም ይስተዋላል፡፡ ሰዎችን ያለ ምክንያት ማታለል፣ አመለካከታቸውን ማሳት የስብዕና እክል ተደርጎ ይታሰባል፡፡
በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች ሰዎች እንዲዋሹ እንደ ምክንያት ይነሳል ፍርኃትም ለመዋሸት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆን ብሎ መዋሸት፣ ሀላፊነትን አለመውሰድ፣ እንደ ታመሙ ማስመሰል፣ ግልፍተኛ መሆን እና የሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የሚዋሹ ሰዎች ይስተዋላሉ፡፡
እንዴት መዋሸትን ማቆም ይቻላል፤
በሰዎች እንዋሻለን የሚለው አመለካከት አለመኖሩ ለሚዋሹ ሰዎች በስነ ልቦና ባለሙያ የሚደረግላቸውን ህክምና አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
ሰዎች በቅድሚያ ስለ ውሸት እራሳቸውን መጠየቅ ይገባቸዋል፤ በንግግር ህክምና የመዋሸት ባህሪን ማከም ይቻላል፡፡ በህክምናው ሰዎች የሚዋሹበትን ምክንያት እንዲረዱ ማድረግ እና ሌሎች ተጓደኝ የአእምሮ ህመሞች ካሉ ማከምን ያካትታል።
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
የማህበራዊ ጭንቀት/ፍርሃት (Social Anxiety Disorder) or Social Phobia - ክፍል 1
በማኅበራዊ ፍርሃት/ጭንቀት የሚሰቃዩ ሰዎች በሕዝብ ፊት መቅረብ ይፈራሉ። የፍራቻቸው ዋና ጽንስ ደግሞ የሚዋርዱ ወይም የሚያሳፍር ድርጊት እንደሚፈጽሙ ማሰብ ነው።
ምንም እንኳን በህዝብ ፊት ቆሞ ንግግር ማድረግ በአብዛኞቻችን ዘንድ ምቾትን ቢነሳም፤ የ “ማህበራዊን ጭንቀት” ህመም ለይቶ ለማወቅ ከፍተኛ የሆነ የጭንቀት መጠን፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ ወይም ዘርፈ ብዙ በአካል፣ በስራ፣ በትምህርት ጉዳት ሲኖረው ነው።
ስርጭት
- ከ 5% እስከ 12% የሚሆኑ የአለማችን ህዝብ በዚህ ህመም የሰቃያሉ።
- ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ ያለው ስርጭት ከፍተኛ ነው። ሆኖም ግን ወንዶች ከሴቶች በተሻለ ወደ ህክምና ይመጣሉ። ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ ወንዶች ለማህበራዊ ተሳትፎ ከሴቶች በበለጠ ጫና ስለሚበዛባቸው እንደሆነ ስለሚገመት ነው።
- ማኅበራዊ ፍርሃት በይበልጥ የሚከሰተው በጉርምስና እድሜ ለይ ሲሆን አብዛኞቹ ተጎጂ ሰዎች ከልጅነት የጀመረ የጭንቀት ታሪክ እንዳላቸው ይገመታል።
- በቤተሰባዊ ሃረግ አለው እድሉ በ 3 እጥፍ ሊጨምር ይችላል።
ምልክቶች
1. ማኅበራዊ ጭንቀት ውስን በሆኑ ሁኔታዎች ለይ ብቻ ወይም ደግሞ አጠቃላይ የማህበራዊ ግንኙነቶችን ሊገደብ ይችላል።
ውስን ሁኔታዎች ስንል “የአፈፃፀም ጭንቀት” (“Performance anxiety”) ማለት ሲሆን እንደ ምሳሌ፦ በአደባባይ መናገር፣ መጻፍ፣ ሬስቶራንት አልያም ገላጣ ቦታ መመገብ፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤት መጠቀም፣ ወዘተ.... ያጠቃልላል።
አጠቃላይ ማህበራዊ ግንኙነቶች ስንል ደግሞ እንደ ምሳሌ፦ ከሰዎች ጋር መገናኘት፣ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ሥራ መሄድ፣ ወደ ገበያ መሄድ፣ ወዘተ.... ይይዛል።
2. በማኅበራዊ ጭንቀት የሚቸገሩ ሰዎች በሚያሳዩት የጭንቀት ምልክት ምክንያት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በአሉታዊ ሁኔታ የሚገመገሙ ይመስላቸዋል፤ ማለትም፦ የሚዋረዱ ወይም የሚያፍሩ አልያም ሌሎችን የሚያሳዝኑ)።
3. ማኅበራዊ ተሳትፎ ሁኔታዎች ሁልጊዜ በሚባል ደረጃ ፍርሃትን ወይም ጭንቀትን ያስከትላሉ።
- በልጆች ላይ ፍርሃቱ ወይም ጭንቀቱ የሚገለጸው በማልቀስ፣ በንዴት፣ ቁጣ፣ ማደንዘዝ፣ መሸማቀቅ ወይም በማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ መናገር አለመቻል ሊገለፅ ይችላል፡፡
4. ማኅበራዊ ተሳትፎዎች ሁኔታዎች ይሸሹታል፤ ግዴታ ከሆነ ደግሞ በከፍተኛ ፍርሃት ወይም በጭንቀት ያሳልፉታል።
5. ጭንቀቱ፣ ፍርሃቱ ማህበራዊ ሁኔታው ከሚፈጠረው ትክክለኛ ስጋት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም የተጋነነ ነው።
6. የማኅበራዊ ፍርሃት፣ ጭንቀት ወይም ሽሽት ቋሚ እና ከ6 ወር ወይም ከዚያ በላይ የሚቆይ ነው።
7. በማህበራዊ፣ በስራ፣ በትምህርት ወይም በሌሎች አስፈላጊ የህይወት ሂደቶች ለይ ከፍተኛ ጫና ወይም ጉዳት ያመጣል።
የማህበራዊ ጭንቀት ምልክቶች ከከፈተኛ ድንጋጤ (Panic disorder)፣ የስብዕና ችግር (Avoidant personality) እና ዓይናፋርነት (Shyness) ጋር ሊመሳሰሉ ይችላል።
ተያይዞም በሱስ አጠቃቀም ችግር፣ አልያም አካልዊ ህመምሞች እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ አለቅጥ ውፍረት፣ እሳት አደጋ፣ ወዘተ...ጋር አለመዛመዱን መመርመር አስፈላጊ ነው።
ብዙውን ጊዜ በሽታው ሥር የሰደደ ቢሆንም ምልክቶቹ በሁኔታዎች ሲለዋወጡ ይታያል፤ ትንሽ ውጥረትም ያባብሰዋል።
በቀጣይ ስለ ማኅበራዊ ጭንቀት/ ፍርሃት ህክምና እናቀርባለን፤ እስከዛው መልካም ጊዜ።
ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (ሳይካትሪስት)
@melkam_enaseb
የንግግር ህክምና
የንግግር ህክምናን በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ አረዳድ መኖሩ ይነገራል፡፡ ይህም የንግግር ህክምና የምክር አገልግሎት መስጠት ነው የሚል እሳቤ ነው፡፡
የምክር አገልግሎት ለአእምሮ እክል ወይም ህመም የሚሰጥ ቢሆንም የንግግር ህክምና ነው ማለት አለመሆኑም ይገለጻል፡፡
በንግግር ህክምና የአይምሮ እክል ያጋጠመውን ታካሚ የልጅነት ጊዜ አስተዳደግን የሚመረምር እና ያጋጠመውን ችግር ከስር ከመሰረቱ የሚያጤን ሲሆን፤ ታካሚው የችግሩን መንስኤ እንዲገነዘብ የሚረዳ የህክምና መንገድ ነው፡፡
በዚህ የህክምና ሂደት ላይ ታካሚዎች የሚሰማቸውን የውስጥ ሀዘን፣ ንዴት፣ ሃሳባቸውን እና ያለፉበትን መልካም ሆነ መጥፎ አጋጣሚዎችን በነጻነት የሚናገሩ ሲሆን፤ ባለሞያው ችግሩን በትኩረት በመረዳት የትኛው ጉዳይ በህይወታቸው ላይ ተጽዕኖን ሊያሳድር እንደሚችል እና ህመሙ ሚታከምበትን ሁኔታ የሚመረምር ይሆናል፡፡
የህክምና ሂደቱ በባለሞያው እና በታካሚው መካከል የሚካሄድ በመሆኑ የታካሚው ሚስጥር እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡
የንግግር ህክምና፦ ለጭንቀት፣ ድባቴ እና መሰል አእምሮ እክሎች የንግግር ህክምናን እንደ መጀመሪያ የህክምና ሂደት የሚሰጥ ነው። እንዲሁም ድንገተኛ ሃዘን ሲያጋጥም፣ ከአደጋ በኋላ የሚከሰት የአይምሮ እክልን፣ በትዳር ህይወት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን፣ ለሱስ ለተጋለጡ ሰዎች፣ አረዳድ እና ባህሪን ለማረቅ፣ ጠባሳ ሆነው የቀጠሉትን በልጅነት ጊዜ የተከሰቱ መጥፎ የህይወት አጋጣሚዎችን ለማከም የሚሰጥ ነው።
በልጅትነት ጊዜያት ላይ የሚያልፉ ጥሩም ሆኑ መጥፎ የህይወት ክስተቶች ለሰዎች የወደፊት ህይወት እና ስነልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራሉ፡፡
በመሆኑም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ልጆቻቸው የሚናገሩት ንግግር የተገራ፣ የሚተገብሯቸው ድርጊትች የተቆጠቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ምክንያቱም የብዙዎች የአእምሮ እክሎች በልጅነት ጊዚያት ላይ በሚፈጠሩ መጥፎ ጠባሳዎችን ተከትሎ የሚከሰቱ ናቸው።
የሰዎች አሉታዊ ንግግር በሌሎች ላይ ለበታችነት ስሜት፣ ምንም ማድረግ አልችልም ብሎ ለማሰብ እና አንዳንዴም ከልክ በላይ ለራስ ክብርን መስጠት ሊያጋልጥ በመቻሉ፤ አንደበት ሊታረም እና ለሰዎች አይምሮ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
የንግግር ህክምና ውጤታማ ነው። በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመደው የተሳሳተ አረዳደድ ሊታረም ይገባል እና ሰዎች የሚያስጨንቃቸውን እና የሚያጋጥማቸውን መጥፎ የህይወት ክስተቶችን ከባለሞያ ጋር በመነጋገር የአእምሮ ጤናቸውን መጠበቅ ይችላሉ፡፡
ህክምናው በዋናነት በልጅነት የእድሜ ክልል ያጋጠሙ ሁኔታዎችን የሚያስታውስ፣ የትኛው የህይወት ገጠመኝ የሰዎችን ስነልቦና እና የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ጫና የሚያሳድሩ መንስዔዎችን የሚመረምር በመሆኑ በወላጅ አልያም በአሳዳጊዎች ዘንድ ከታች የተዘረዘሩት ቢለመዱ ጥሩ ነው።
በተቻለ መጠን ቁጡ አለመሆን፣ የልጆች ባህሪ ላይ መስራት፣ ከቁስ በተጨማሪ ፍቅርን ለልጆች መስጠት እና ልጆች የሚተማመኑበት ወላጅ መሆን አስፈላጊ ነው፡፡
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
ጥናት!
ተመራማሪዎች በቀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችንን አቅም ለማሳገድ እንደሚረዳ አስታወቁ።
አዲስ የተሰራ የኒውሮሳይንስ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችን አዲስ መረጃ ለመውሰድና ለመያዝ እንዲዘጋጅ ያደርገዋል።
በተለይም ውሳኔ ለመስጠት፣ ጭንቀትን ለመቆጣጠርና፣ በባህሪያችን ዙሪያ የሚያቅደው የአእምሯችን ክፍል ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ነው ተመራማሪዎች ያስታወቁት።
ሌሎች አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የአዕምሮ ጤናን ለመጠበቅ እንደሚረዱ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ይህኛው ጥናት ግን የግር ጉዞ እና የአእምሮ አቅም ላይ ትኩረትን ያድረገ እንደሆነም አስታውቀዋል።
በዚህም በቀን ለ20 ደቂቃ እና ከዚያ በላይ የእግር ጉዞ ማድረግ የአእምሮን አቅም እንደሚያሳድግ እና ምንም እንቅስቃሴ ካለማድረግ የተወሰነ የእግር ጉዞ ማድረግ እንደሚሻልም ጥናቱ አመላክቷል።
የሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጥናቱን ባከናወኑበት ወቅት ተሳታፊዎች የእግር ጉዞ የሚያደርጉ እና የማያደርጉትን በመለየት ክትትል ያደረጉ ሲሆን፤ በዚህም ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ተቀምጠው ከሚውሉት የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል።
ተመራማሪዎች የአእምሮ እንቅስቃሴን በኤሌክትሮኤንሴፋሎግራፊ (ኢኢጂ) መለካት ምን እየተፈጠረ እንዳለ የተመለከቱ ሲሆን፤ በዚህም የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ ተጨባጭ እና አወንታዊ ተፅእኖዎችን አይተዋል።
Via: Alain
@melkam_enaseb
ሳይጀመር የተደመደመ ሕይወት!
Fatalistic Attitude
የሚኖሩት ኑሮ አንዴ የተወሰነና ሊለወጥ የማይችል እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ፈረንጆቹ ይህንን አመለካከት fatalistic attitude ይሉታል፡፡ ያለቀለትና ቅድመ-ድምዳሜ ተወስኖለት የተጀመረ ሕይወት እንዳለን ማመንን የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡
ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ያለውን ምንም ነገር ለመቀየር አቅሙ እንደሌላቸው ነው የሚያስቡት፡፡ የወቅቱ ኑሯቸው ሁኔታ ለእነሱ የተመደበና ምንም ቢታገሉ ሊለወጥ እንደማይችል ያስባሉ። ስለዚህም የነበረውንና ያለውን በመቀበል ያዘግማሉ፡፡
እንደዚህ አይነት ሰዎች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች በማለም፣ በመስራትና በማመን ሕይወታቸውን ሲለውጡ እያዩ እንኳን ንቅንቅ አይሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚያኞቹ በሕይወታቸው የሚያዩት ለውጥም ሳይቀር ቀድሞውኑ ለእነሱ የተወሰነላቸው እንደሆነ ስለሚስቡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ራስን ለማሻሻል ምንም አይነት መነሳሳት ስለማይኖራቸው የመጣላቸውን እየተቀበሉና ያንኑ እየኖሩ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፡፡
ሕይወት ግን እንደዚያ አይደለችም፡፡ ሕይወት የምርጫ መስክ ነች፡፡ ሕይወት የዘራነውን የምናበቅልባት መሬት ነች፡፡ ሕይወት ፈቃዳችንን፣ ጉልበታችንንና ሌሎችንም እሴቶቻችንን አስተባብረን ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ እንደመሰላል የምንወጣት የምታጓጓ መስክ ናት እንጂ ታሪካቸው ተጽፎና አልቆ ያከተመለትና ፍጻሜ የተበየነባቸው ሰዎች መተራመሻ አይደለችም።
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)
@melkam_enaseb
እኛ እራሳችንን እና ሌሎች እኛን ምን ያህል ያውቁናል?
አንዳንድ ግዜ ሰዎች እኔ እራሴን በደንብ አውቀዋለሁ ወይም እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን የስነ-ባህሪ አጥኚዎች ሰው ራሱንም እንዲሁም ሌሎችን ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ እንደሚከተለው ያስረዱናል።
4ቱ ማንነቶቻችን፦
1. Open- ግልፅ ሆኖ የሚታየው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን እና ሌሎች እኛን የሚያውቁት ግልፅ የሆነው ማንነት ክፍል ነው።
2. Hidden- ድብቅ የሆነው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን የምናውቅው ሌሎች ግን ስለእኛ የማያውቁት ክፍል ነው።
3. Blind- ሰዎች ስለኛ የሚያውቁት እኛ ግን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።
4. Unknown- ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እኛ ራሳችን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።
ስለዚህ ከሰዎች ጋር መልካም እና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከላይ የተዘረዘሩትን የማንነት ክፍሎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።
ካልሆነ ግን እከሌን አውቀዋለሁ ብለው ሲያስቡ አንድ ቀን ድብቁ/ የማያውቁት ማንነት ሲገለጥ ሊጎዱ ይችላሉ። እንዲሁም ራስዎትን ራሴን በደንብ አውቀዋለሁ በማለት ሌሎች ከሚሰጥዎት ምክር ባለመማር ራስዎትን ከማሳደግ እና ከማሻሻል እንዳይገደቡ ጥንንቃቄ ያድርጉ።
በ መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
@melkam_enaseb
እራስን ካለፉ መጥፎ ክስተቶች እስር ነፃ ማውጣት!
ህይወትህ ውስጥ በተፈጠረ አንድ አሉታዊ ክስተት ምክንያት፣ በአዕምሮህ አሁንም እየተመላለሰ የሚያስቸግርህ ሃሳብ አለ? ይህ ሃሳብ ስሜቱ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ እንዴት አድርጌ ልርሳው ወይም ከትውስታዬ ልፋቀው ብለህ ታውቃለህ?
አዕምሮህን እንደትልቅ ላይብረሪ ተረዳው። ከልጅነት እስከ እውቀት አንተ ጋር የተከናወኑ ነገሮች ሁሉ በትውስታ መልክ በውስጡ እንደመጽሃፍት ተሰድረውበት ይገኛሉ። ከእነዚህ ትውስታዎች አንዳንዶቹ መልካም (አውንታዊ) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መልካም ያልሆኑ (አሉታዊ) ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ትውስታዎች ቢያልፉም እንደተገነዘብናቸው መጠን ዛሬም ድረስ ውስጣችን አውንታዊ ወይም አሉታዊ ስሜት ይፈጥራሉ።
በተለይ የአሉታዊ ክስተቶች ተፅዕኖ አሉታዊ ስሜት ውስጣችን በመፍጠር ብቻ የሚቆም አይደለም። ብዙ ግዜ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ውስጥ ዛሬም ጣልቃ እየገቡ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳንወስን ሊከለክሉንም ይችላሉ። ከዚያም ሲያልፍ ጉዳዩ በተፈጠረበት ወቅት ከደረስንባቸው መረዳቶችና ድምዳሜዎች የተነሳ፣ ወደፊት መፍጠር ከምንፈልገው ህይወት አንጻር የማይጠቅም እይታ (አመለካከት) እንድናዳብርም ያደርጋሉ።
የሚገርመው ብዙ ግዜ አሉታዊ ስሜት የሚፈጥሩትን ትውስታዎች በቀላሉ ማስታወስ፣ እንዲያውም እነዚህ ትውስታዎች ውስጥ ለረጅም ግዜ በመቆየት ራሳችንን ቶርቸር ማድረግ ለብዙዎቻችን ቀላል ነው። ምናልባት እነዚህ የምናስታውሳቸው ክስተቶች ያለፉና የማይደገሙ እንደሆኑ ብናውቅም አዕምሯችን ግን ክስተቶቹ አሁን በዚህ ቅጽበት እየተከናወኑ ያሉ እስከሚመስል ድረስ በጠንካራ አሉታዊ ስሜት ውስጥ እንድንዘፈቅ ያደርገናል። ታዲያ እነዚህ ያለፉ፣ የማይደገሙ ክስተቶች አሁን እየፈጠሩብን ካለው አሉታዊ ስሜት፣ የውሳኔ ውስንነትና፣ ጎታች አመለካከት ተፅዕኖዎች ራሳችንን እንዴት ማላቀቅ እንችላለን?
ይህን ጥያቄ ስናነሳ ብዙዎች “እርሳው ባክህ”፣ ወይም “ለበጎ ነው” ወዘተ የሚል ምላሽ ይሰጡናል። ነገርግን “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” ነውና እኛ ነገሩን ማስታወስ ፈልገን ሳይሆን አዕምሯችን ከኛ እውቅና ውጪ እያሳሰበን እንደሆነ ማን ይንገርልን?
እነዚህ በውስጣችን ተሰድረው ማለፋቸው ሳያንስ አሁንም ህይወታችንን ካመሰቃቀሉ ትውስታዎችን ለመፋታት የሚከተሉትን ማድረግ እንችላለን፦
1. እነዚህን ክስተቶች ከንደገና በማስታወስ ልንማርባቸው የምንችላቸው ነገሮች ካሉ ወረቀት ላይ በጽሁፍ ማስፈር።
2. እነዚህን ክስተቶች ከንደገና በማስታወስ ጉዳቱን የፈጠሩ ሰዎች ካሉ፣ በወቅቱ የነበረባቸውን የባህርይ፣ ስሜት እና የውሳኔ ውስንነት እንደገና አሁን ባለን መረዳት መመልከት። እነዚህ ውስንነቶች ባይኖሩባቸው ምን ሊያደርጉ ይችሉ እንደነበር ማሰብ፤ እነሱ የነበሩባቸውን ውስንነቶች እኛም ሳናውቅ እያንጸባረቅን እንዳልሆነ ማረጋገጥ።
3. የሚፈጥሩብን ስሜት ከባድ ከሆነና ከላይ ባደረግናቸው ልምምዶች ስሜቶቹንና ግንዛቤያችንን መለወጥ ካቃተን የባለሙያ ርዳታ እንፈልግ።
ዳንኤል አያሌው (Certified NLP Practitioner)
@melkam_enaseb
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::
የዚህ ወር ርዕስም፡- “እንደ ህብረተሰብ የስነልቦና ቁስልን መገንዘብ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የአሃ ሳይኮሎጂካል አገልግሎት መስራች እና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ ገ/ማሪያም ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️
https://forms.gle/Y8iPkGRELLR2cFW86
@melkam_enaseb
የውድድር ስነ-ልቦና!
የውድድር ስነ ልቦና እንደዘርፉ ባለሙያዎች ትንታኔ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
ውድድር ሰዎች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማነሳሳት እንደሚረዳና አውጥተውም እንዲያሳዩበት እድል የሚፈጥር መሆኑ ይነገራል፡፡
ሆኖም የውድድር መንፈስ እንደጥቅሙ ሁሉ በትክክል መያዝ ካልተቻለ ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ ጤናማ ያልሆነ ውድድርም የተለያዩ የጤና እክሎችን እንደሚያስከትልም ነው የሚነገረው፡፡
የውድድር ስነ-ልቦና ሰዎች በህይወታቸው ያልተመለከቱትን አቅጣጫ የሚመለከቱበት ነው። በተጨማሪም በተለያዩ መንገዶች የተሻለ ለመሆን እገዛ የሚያደርግ ነው።
ውድድር አሸናፊና ተሸናፊዎች ያሉበትና ሽንፈትን ፈጽሞ አለመቀበል ራስን አላስፈላጊ ጭንቀት ውስጥ ሲከት ይታያል፡፡ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኛ አልያም በስራ አካባቢ የበዛ የውድድር መንፈስ ሲታይ ተመልክተው ይሆናል፡፡
ይህ የውድድርና የአሸናፊነት ጥማት የሌሎችን ስኬት ዕውቅና ከመንፈግ ጀምሮ የራስን ማንነት አለመቀበል ሊያስከትል እንደሚችልም ይገለጻል፡፡
ይህም ሰዎችን መዋሸት፣ ጫናዎች፣ ጭንቀት፣ የበታችነት ስሜት መሰማትና በቂ ነገር የለኝም በማለት ያሉበትን ቦታ አለመውደድ እና የማንነት ቀውስ ውስጥ ያስገባል።
ያለአግባብ የውድድር መንፈስ በራስ መተማመን የሚያመጣው ስሜት ነው፥ የራሴ ነገር በቂ አይደለም በሚል ሃሳብ ሌሎችን ለመምሰል ይሞክራሉ፡፡ ይህ ስሜት እየቆየ ሲሄድም ቁጣ፣ ንዴት፣ ቅናት እና መሰል ስሜቶች መገለጥ ይጀምራሉ፡፡
ይህ ስሜት ከየት እንደመነጨ ማስተዋል፣ የሰዎችን ስኬት መቀበል፣ የውድድሩ ፍላጎት ራስን ከማሳደግ የመነጨ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው የሚለውን መለየት ችግሩን በወቅቱ ለመፍታት እንደሚያግዝም ይነገራል፡፡
ባርኮት ጌቱ (የስነ-ልቦና አማካሪ)
@melkam_enaseb
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
@melkam_enaseb
⬆️ የእነዚህ ሁለት ምስሎች ትርጉም ጥልቅ ነው።
ምስል 1
ውጫዊ ገጽታው በፈገግታ የታጀበ ቢመስልም ውስጡ ግን ጥልቅ ሃዘን አለ::
ለዚያም ነው የቅርብ ሰዎቻችንን በፈገግታቸው ለክተን ውስጣዊ ህመማቸውን ሳናይላቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ሲሞክሩ/ሲያጠፋ 'እኮ እንዴት' ብለን ስንገረም የምንስተዋለው።
ምስል 2
ይህ የፊት ገጽታ ለረጅም ጊዜ በድባቴ ስሜት ውስጥ ያለፋ ሰዎች ላይ የሚታይ የፊት ገጽታ ነው።
- Veraguth's fold (የአይን ቆዳቸው ቅጭም ማለት)
- Omega sign (የግንባር ቆዳቸው ኦሜጋ የምትባለዋን ፊደል የመስራት ያህል መሸብሸብ) ያመላክታል።
እና ምን ለማለት ነው የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም። የውስጥ ስሜት ሁሌም ፊት ላይ ላይነበብ ይችላልና!
የድብርት ህመም ውጤታማ የስነልቦና እና የመድሃኒት ህክምና አለው!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ሬዚደንት ሃኪም)
@melkam_enaseb
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::
የዚህ ወር ርዕስም፡- “ራስን የማጥፋት” ስሜትን መረዳት'' የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የሆኑት ገጣሚ ዶ/ር ፌበን ፋንጮ (ሳይካትሪ ሬዚደንት) ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️
https://forms.gle/uSWkjQdTrLmgLXVn9
@melkam_enaseb
በልጅነት የእድሜ ክልል ውስጥ ያለፉ የህይወት መጥፎ አጋጣሚዎች በሰዎች የወደፊት ህይወት ላይ ጣልቃ በመግባት ይረብሻሉ።
ወላጆችን በተለያዩ ምክንያት ማጣት፣ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎች መሠል ችግሮች ሲያጋጥሙ ሰዎች ለሱሰኝነት፣ ለድብርት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይዳረጋሉ ይህም ደግሞ ለጸጸት እንደሚዳርጋቸውም ይገለጻል፡፡
የምንተገብራቸው ጉዳዮችን ጥቅም እና ጉዳት ላይ ጊዜ ወስዶ አገናዝቦ አለመወሰን፣ ምክንያታዊ ሆኖ አለመወሰን፣ በሰዎች ላይ ጸጸትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
የደስታ፣ የብስጭት እንዲሁም የሀዘን ስሜት በሰዎች ላይ የሚስተዋል ቢሆንም፦
- ስሜታዊ ሆኖ ማሰብ፣
- የጓደኛ/ አቻ ግፊት
- አልኮል መጠጣት
- የአደንዛዥ እጽ መጠቀም ለጸጸት እንደ መነሻ ምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ለምን አደረኩ ብሎ እራስን መውቀስ ጠቃሚ ቢሆንም ትናንት ላይ ከመኖር ይልቅ ስለ ነገ መልካም ነገሮች ማሰብ ይጠቅማል። ለዚህም ከትናንት መጥፎ የህይወት ገጠመኞች ትምህርትን በመውሰድ ለነገ አዲስ ህይወት መዘጋጀት በሰዎች ዘንድ ሊለመድ ይገባል።
አንዳንዶች ትናንት በገጠማቸው የህይወት መጥፎም ሆነ ጥሩ ገጠመኞች ተምረው ያልፋሉ። ነገር ግን አሁንም ድረስ ባለፈ የህይወት ታሪካቸው ተሸፍነው የሚኖሩም አሉ።
የሚጸጸቱ ሰዎች ላይ፦
- የመበሳጨት፣
- ያለመረጋጋት
- የመጨነቅ ምልክቶች ይስተዋላሉ።
ከሚጸጽታቸው ጉዳይ ወይም በተደጋጋሚ አእምሯቸው ላይ እየተመላለሰ የሚረብሻቸውን ጉዳይ ጊዜ በመውሰድ ሊረዱት አልያም በጉዳዩ ላይ የባለሞያን ምክር ማግኘት አለባቸው።
ከመጥፎ ስሜቶች ለመውጣት እንደየሰው ጥንካሬ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በቅድሚያ ግን እራስን ከመውቀስ ይልቅ ለእራስ ይቅርታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ብሩክ ዩሃንስ (የስነ ልቦና ባለሙያ)
@melkam_enaseb
Yetena Weg Clubhouse Discussion!
ከዶ/ር አስናቀ ልመነህ ጋር "የአዕምሮ ጤና ሰብአዊ መብት ነው" በሚለው የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን መሪ ቃል ላይ የምናደርገውን ውይይት ይቀላቀሉ።
🗓ጥቅምት 18 (እሁድ)
⏰ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)
ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ! ⬇️
https://www.clubhouse.com/invite/tA8LVpvi
@melkam_enaseb
ራቆቱን የሮጠ ብቻ አይደለም የአእምሮ ታማሚ፣ የአእምሮ ጤና ሰፊ መገለጫ ያለው ውስብስብ ጉዳይ ነው። ከ3 ሰዎች 1 ሰው የአእምሮ ጤናው ላይ እክል እንዳለበት ጥናቶች ያሳያሉ። ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጠው ስውር ህመም፣ ድብቅ ወረርሽኝ ነው። ያለ አእምሮ ጤና ግን ሰላምም፣ ለውጥም፣ እድገትም የለም።
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ
(የሥነ-አእምሮ ስፔሻሊስትና ሥነ-ልቦና አማካሪ)
(For any questions) 0912806077)
@melkam_enaseb
የማህበራዊ ጭንቀት/ፍርሃት (Social Anxiety Disorder) or Social Phobia - ህክምና
የማኅበራዊ ጭንቀት/ ፍርሃት ሁለት አይነት ህክምና አሉት። እንዚህም የስነ-ልቦና ህክምና እና የመድሃኒት ህክምና ናቸው። የህክምናው ምርጫ የሚወሰነው የሚከተሉትን ታሳቢ በማድረግ ነው።
- ማኅበራዊ ጭንቀቱ በተጠቂው ግለሰብ ለይ በሚፈጥረው የህይወት ጫና፣ ክብደት፣
- የታካሚ ምርጫ እና ተነሳሽነት፣
- የታካሚው በሕክምናው ውስጥ የመሳተፍ ችሎታ፣
- ተጓዳኝ የአእምሮ ሕመሞች ካሉ፣ ወዘተ...።
የስነ-ልቦና ህክምና
የኮግኒቲቭ-ቢሄቪየር ህክምና (Cognitive and behavioral Therapy) ዉጤታማ የህክምና አይነት ሲሆን፤ አስተሳሰብ እና ባህሪን በመቀየር የሚሰራ የንንግር ህክምና አይነት ነው።
ህክምናው ጊዜ የሚፈልግ እና ፍርሃትን በመጋፍጥ የሚደረግ የህክምና አይነት ነው። የግለሰቡን ተነሳሽነት የሚጠይቅ ሲሆን በደንብ ከተሰራ አመርቂ ዉጤት ያመጣል። ህክምናው በግለሰብ ወይም በቡድን ሊስጥ ይችላል።
የመድሃኒት ህክምና
የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶችን በመጠቀም የማኅበራዊ ጭንቀትን ማከም ይቻላል፤ ዉጤታማ ለውጥም ያመጣሉ። በተለይ ተጓዳኝ የአዕምሮ ችግሮች ካሉ እና በአፋጣኝ ለውጥ ካስፍለገ ይህ ህክምና ተመርጭ ይሆናል።
ስር ለሰደደ የጭንቀት ህመም የህክምና ውጤት ጊዜ የሚወስድ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። በርካታ ሳምንታት ወይም ወራቶችን በስነ-ልቦና ህክምና ሲያሳልፉ እንዲሁም ለእርስዎ ሁኔታ ትክክለኛውን መድሃኒት እስከሚገኝ ድረስ የተወሰነ የሙከራ ጊዜ ቢፈጅም፤ እምርታዊ ጉዞው በስተመጨረሻ ለውጥ ያመጣል።
ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (ሳይካትሪስት)
@melkam_enaseb
እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
መልካም በዓል!
@melkam_enaseb
ስለ አለኝታ ምን ያህል ያውቃሉ?
6388 አለኝታ ነጻ የስልክ መስመር ላይ ይደውሉና ስነልቦናዊ ድጋፍ ያግኙ።
@melkam_enaseb
የካርል ዩንግ ጥልቅ የፍልስፋና እና ሥነልቦናዊ ንግግሮች!
1. ”ባንተ በራስህ ውስጥ ያለዉን ጨለማ ማወቅ በሌሎች ጨለማ ላይ ለመስራት መንገዱን ይጠርግልሀል”
2. ”ንቁ ባልሆነዉ የአእምሮህ ክፍል ተቀምጠው ባንተ ላይ ተፅኖ የሚያደርጉትን ሀሳቦች ንቁ ወደ ሆነዉ ክፍል እስካላመጣህ ድረስ እነሱም አንተን መምራታቸው አንተም እጣፈንታዬ ነው እያልክ መኖርህ ይቀጥላል”
3. ”መልካም ነገሮችን ይዘዋል እና በህይወትህ ከባድ እና የሚገዳደሩ ነገሮችን አመስግን በእዉነታዉ ለጤናማ እድገት፣ ራስን ለመሆን እና እውነተኛው እኛነታችን ላይ ለመድረስ ተግዳሮት አስፈላጊ ነው“
4. ”የትኛዉም የምታገኘዉ ሰው አንተ የማታቀዉ የሆነ ነገር ያውቃል ስለሆነም ሁሌም ለማወቅ ጉጉት ይኑርህ ከነሱም ተማር”
5. ”እኔ ለመሆን የመረጥኩትን እንጂ በኔ ላይ የሆነብኝ ነገር ውጤት አይደለሁም”
6. “ዓለም ስለማንነትህ በሚጠይቅህ ግዜ ማን እንደሆንክ ካላወክ በምላሹ ዓለም በራሱ ስለአንተ ይነግርሀል"
7. “አንድ ሰው ይበልጥ ባወቀ ቁጥር ብቸኛ እየሆነ ይመጣል”
8. “በሌሎች ላይ አይተነው የሚያስቆጣን ነገር ሁሉ አራሳችንን እንድንረዳ መንገድ ይመራናል”
9. ”ህይወት የእውነት የሚጀመረው ከአርባ ዓመት በኃላ ነው እስከዛ በነበረው እየኖርክ ሳይሆን ጥናት እያደረግክ ነው”
10. ”አንተነትህ የሚገለፀዉ በድርጊትህ እንጂ በምታወራው አይደለም እና አድርገው”
ፍ/ማርያም ተስፋዬ (የሥነልቦና ባለሙያ )
@melkam_enaseb
የጤና ወግ ዛሬ በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት የመማር እክል በሚል ርዕስ የሚደረገው ውይይት ላይ ይቀላቀሉ።
እንግዶች:
ተባባሪ ኘሮፌሰር አበባየሁ መሰለ (የፋና የተግባቦት እና የመሰረታዊ ትምህርት ድጋፍ መስጫ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች እና ስራ አስኪያጅ)
አቶ ያፌት ከፈለኝ (የአብርሆት ሳይኮቴራፒ ማዕከል መስራች)
የመማር እክሎች የማሰብ ችሎታ ወይም ጥረት ማነስን የሚያመለክቱ አይደሉም።
የበለጠ ለመረዳት ውይይቱን በቀጥታ ይከታተሉ!
🗓 እሁድ ሚያዚያ 13, 2016
⏰ ከምሽቱ 12 ሰዓት (በኢትዮጵያ)
ውይይቱን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ ⬇️
/channel/yetenaweg?livestream
@melkam_enaseb
ምዕናባዊ ኦቲዝም፤ የዲጅታል ዘመን ልጆች ስጋት
ባለሙያዎች እንደሚሉት በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በታብሌት፣ በቴሌቪዝን እና በሌሎች ዲጅታል መሳሪያዎች ላይ ረዘም ያለ ጊዜ የሚያሳልፉ ልጆች ለጭንቀት እና ለመረበሽ፣ ለትኩረት ማጣት፣ ለንግግር እና ለቋንቋ መዘግየት እንዲሁም ለግንዛቤ እድገት ውሱንነት ይዳረጋሉ። የሰዎችን ስሜት የመረዳት እና የመግባባት ችሎታቸውንም ይቀንሳል።
በዚህ ዙሪያ #DW ያዘጋጀውን ፅሁፍ ያንብቡ ⬇️
https://p.dw.com/p/4erN2?maca=amh-Facebook-dw
@melkam_enaseb
ጤናማ ህይወትን መምራት እንዴት ይቻላል?
ጤናማ መሆን ማለት በአዕምሮ፣ በአካልና በስሜት ሙሉ ጤንነት ሲሰማን ማለት ነው፡፡
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል በበሽታ እንዳንጠቃ ከማገዙም በላይ ጤናችን ስንጠብቅ ለራሳችን ያለን ግምት መልካም እንደሚሆን የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ደስተኛ፣ የተረጋጋና ስኬታማ ህይወት እንድንኖር ይረዳናል፡፡
ምንም እንኳን የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ሁኔታዎች ጤናማ ህይወትን ለመምራት አሉታዊ ተጽዕኖ ቢፈጥሩም አኗኗራችንን እና ልማዶቻችንን በመቀየር ጤናማ ህይወት መኖር እንደሚቻል ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት።
ጤናማ ህይወት ለመኖር የሰው ልጅ የተለያዩ የህይወት ዘይቤዎችን ይተገብራል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፦
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣
• ክብደትን መለካትና መቆጣጠር፣
• በቂ ውሃ መጠጣት፣
• ለረዥም ጊዜ ያለመቀመጥና ኮምፒውተርና ሌሎች ስክሪን ላይ የምናጠፋውን ጊዜ መቀነስ፣
• በቂ እንቅልፍ መተኛት፣
• ከመጠን ያለፈ አልኮል ያለመውሰድ፣
• ቁጣና መሰል ስሜቶችን መቆጣጠር፣
• ጭንቀትን ማስወገድ፣
•የጤና ክትትል ማድረግና መሰል የጤናማ አኗኗር ዘይቤዎች ይጠቀሳሉ፡፡
በተጨማሪም ከሰዎች ጋር ያለንን ማህበራዊ ግንኙነት በትኩረት መመልከት ያስፈልጋል። ከጓደኞች፣ ከቤተሰብና ጎረቤት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን የዕለት ተዕለት ግንኙነት ማሻሻልና መልካም ማድረግ ለጤናማ ህይወት አስፈላጊ እንደሆነ የሜዲሲን ኔት መረጃ ያመላክታል፡፡
@melkam_enaseb
ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና፦
- የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።
- በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::
አጋላጮች፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።
- በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።
ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም *በህይወት መቆየት አለመፈልግ
የባህሪ ችግሮች፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር
የአመጋገብ ችግር፦
➡ ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው።
የስነ-ልቦና ቀውስ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድርበታል።
- ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።
#WHO #TikvahEthiopia
@melkam_enaseb
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓም በብይነ መረብ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል::
በዕለቱ በአእምሮ ጤና ዙሪያ የሚያጠነጥነው “የሁሉ” የልብወለድ መፅሃፍ ላይ ከዶ/ር አዜብ አሳምነው ከዶ/ር ዮናስ ላቀው እንዲሁም ከደራሲው ከዶ/ር ዳዊት አሰፋ ጋር የኦንላይን ውይይት ይደረጋል፡፡
በዕለቱ ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ ⬇️
https://meet.google.com/gsd-iztg-rop
@melkam_enaseb
ራስን ማጥፋት (suicide)
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገር በስፋት የምንሰማው ራስን የማጥፋት (suicide) ተግባር በሀገራችን በተለይም አንዲት እንስት 'ብንሄድ ይሻላል' ብላ Facebook ከለጠፈች እና ራሷን ካጠፋች ብኋላ በሀገራችን በተለይም በወጣቱ ዘንድ እንደተስፋፋ ግልፅ ነው።
ከዚህ ቀደም በሚዲያ አንሰማው ይሆናል እንጂ ይህ ራስን የማጥፋት ድርጊት በዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ የትምህርት እና ስራ ቦታዎች ላይ ሲከሰት ነበር።
ምናልባትም ይህንን በራሳችን ላይ ለመፈፀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፍን ልንኖር እንችላለን። ሰው ነፍሱን በራሱ ለማጥፋት ምክንያት የሚሆኑ በጥቂቱ ብንጠቅስ፦
ሕይወት ፊቷን ስታዞር እና ቀን ሲጨልምበት፣ በሚያመነው ሰው ሲከዳ እና ተስፋውን ሲያጣ፣ የኑሮ ፈተና ሲበዛ እና መውጫ መንገድ ሲጠፋበት፣ በሚያሰበው ልክ ነገሮች ሳይከናወኑለት ሲቀሩ፣ በሚያየው ሁሉ ነገን ኣሻግሮ ማየት ሲያቅተው፣ በቤቱ፣ በትዳሩ ክብርን እና ተቀባይነት ሲነፈግ ወ.ዘ.ተ ናቸው።
በርግጥ በግለሰቡ ሁኔታ እና ጫማ ውስጥ ሆነን ነገሩን መመልከት እስካልቻልን ድረስ ስለዚህ ሁኔታ በድፍረት መናገር አንችልም።
የራስን ማጥፋት ውሳኔ ቅፅበታዊ ነው። ጥቂት ሰከንዶች ሺህ ዘመን መስለው ይታያሉ። ስቃይ እና ፈተና ዘላለማዊ ይመስልና አዕምሯችን ለውሳኔ እንድንጣደፍ ሆርሞኖችን ይቀሰቅሳል። ከዚያ ነገሮች ያበቃሉ። ሰዎች የሰዎችን ሁኔታ አያዩም እንጂ በርካቶች ለተመሳሳይ ወጥመድ ተጋልጠው በተዓምር ይሁን በራሳቸው ብርታት አምልጠዋል። ለዚህ ምስክሮችን መጥራት አያስፈልግም።
በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እንዳናገኝ እነዚህ ነገሮችን ብንተገብር መልካም ነው ብዬ አስባለው።
1. ከእምነት ተቋማት አለመራቅ። ሀይማኖታዊነትን መላበስ በራሱ የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጣል ብዬ አምናለው።
2. Multi-Professional-Friends ሊኖሩን ይገባል። በአንድ ሙያ መስክ ብቻ የተሰማሩ ጓደኞች አይኑሯችሁ። ሕይወትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሊያስመለክቱ የሚችሉ ወዳጆችን መፍጠር ያስፈልጋል።
3. በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ - Counselling and Guidance Service ተቋማትን መጎብኘት ያስፈልጋል። በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ እነዚህ ተቋማት በመሰል ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ቦታዎች በየከተማው ላይ መስፋፋት አለባቸው።
ራሳቸውን ላጠፉ ፈጣሪ እዝነቱን ያድርግላቸው!
Credit: Workineh Gebeyehu Gomera
#EliasMeseret
@melkam_enaseb
የጭንቀት መነሻዎችና መፍትሄዎች!
የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ 2019 ባደረገው ጥናት በዓለም ዙሪያ 301 ሚሊየን ሰዎች በጭንቀት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 58 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት እና ወጣቶች መሆናቸውንም ነው የገለጸው።
የአዕምሮ በሽታ ተብለው ከሚጠቀሱና በማህበረሰቡ በስፋት ከሚስተዋሉት መካከል ጭንቀት አንዱ ሲሆን፥ ከራስ ጋር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖር ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጫናን ሊፈጥር ብሎም የስራ ምርታማነትን እና ወደ ስኬት የሚደረገው ጉዞ ላይ እክል ሊፈጥር ይችላል፡፡
ይህም የተወሰነ የእድሜ ክልልን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍልን የሚያጠቃ ነው፡፡
ያለበቂ ምክንያት ወይም ሊያስጨንቅዎት የሚገባው ነገር ካለፈ በኋላ ስሜቱ ሲቀጥል ጭንቀት ይባላል።
በአሁኑ ወቅት መረጃ ከመጠን በላይ መገኘት፣ ያለአግባብ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ራስን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር፣ ጤና፣ ገንዘብ፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ የልጅነት ገጠመኞች፣ ከባድ አጋጣሚዎች፣ ለነገሩ የሚሰጡት ክብደት መጨመሩ እና ሌሎች የጭንቀት መንስዔዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
አብዛኞቹ የአዕምሮ በሽታዎች ያሉበት ደረጃ ባሕርያትና ሁኔታ ከሰውሰው ይለያያሉ፥ አንዳንዶቹ ላይ ቀለል ያለ ሌሎች ላይ ደግሞ ከባድ ወይም ውስብስብ ምልክቶችን ያሳያሉ።
የባህሪ መቀያየር እስከ ማህበራዊ ህይወት መገለል ያሉ ምልክቶችም ይታያሉ።
በተጨማሪም የእጅ መንቀጥቀጥ፣ ላብ ላብ ማለት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የድካም ስሜት፣ የራስ ምታት፣ የተወሰኑ ነገሮች ላይ ደጋግሞ ማሰብ፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ደስታ ወይም ፍላጎት ማጣት ምልክቶች ናቸው፡፡
በአብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ሰዎች የሥነ-አዕምሮ በሽታ ተጠቂዎች እንደሆኑ አምነው ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ መታከም አልተለመደም፤ ይህንን ተከትሎም በሽታው ከነበረበት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በመድረስ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።
የአዕምሮ ጤና ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ ወደሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል ይላሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፡፡
በአካባቢና በህይወትዎ የሚፈጠሩ ክስተቶች በአግባቡ ካልተቆጣጠሩት እና ራስዎ ላይ ትኩረት አድርገው ካልሰሩ የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ ሊከትል ይችላል፡፡
አልፎ አልፎ ጭንቀትን በተለመደው የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ሊያጋጥም ይችላል። ሆኖም በጭንቀት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በራሳቸው ጥረትና በህክምና ባለሙያዎች እገዛ ተደርጎላቸው መዳን ይችላሉ፡፡
በዚህም ለራስ ጊዜ በመስጠት (በጥሞና) ነገሮችን ማሰላሰል፣ ተረጋግቶ የራስን ህይወት በትኩረት ማየት፣ አስተሳሰብ ላይ ረዘም ያለ ጊዜ በመውሰድ ፍተሻ ማድረግ፣ ለነገሮች የሚሰጡትን አመክንዮ እና ራስ ላይ በማተኮር መፍትሄ መስጠት ይቻላል፡፡
ከዚህ ባስ ካለ ወይም የባለሙያ እገዛ ካስፈለግዎ ሃኪምን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
ቴዎድሮስ ድልነሳው (የሥነ-ልቦና ባለሙያ)
@melkam_enaseb
ፀፀትን እንዴት ከራስዎ ያርቃሉ?
ሰዎች የሚሰማቸው የሃዘን፣ የቁጭት እና የመረበሽ ስሜት ድምር ፀፀት ይባላል፡፡
ፀፀት የተሻለ ስራን ለመስራት ወኔ ቢፈጥርም ከልክ ካለፈ ግን ቀላል የማይባል ተጽዕኖን ይፈጥራል፡፡
ለፀፀት የሚዳርጉ ምክንያቶች፦
- ሥህተት መስራት እና
- እንከን የለሽ ሆኖ ማደግ፦ በልጅነት ጊዜያቸው ፍጹም በመሆን ተጽዕኖ ውስጥ ያለፉ መሆን
ፀፀት በርካታ ጉዳቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፦
– የመስራት አቅምን ይነጥቃል
– የበታችነት ስሜት ይፈጥራል
– ተስፋ መቁረጥ
– ኢኮኖሚ ችግር እና
– ማህበራዊ ችግር
ፀፀት የከፍተኛ ጭንቀትና ድባቴ ውስጥ ከሚከቱ የስሜት መዘበራረቆች መካከል አንዱ ሲሆን፥ ይህ ከተባባሰ የአካልና የአዕምሮ እክልን ያስከትላል ይላሉ ባለሙያው፡፡
ፀፀት ውስጥ እንዳይገቡ መፍትሄው ምንድን ነው?
– ስህተትን አምኖ መቀበል
– የሚታረም ከሆነ በቻሉት አቅም ለማረም ጥረት ማድረግ
– አካባቢን መቀየር
– ሥር የሰደደ እና ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ማግኘትና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ሔኖክ ሃ/ማርያም (የሥነ-ልቦና ባለሙያ)
@melkam_enaseb
ለራስ ማድረግ መቻል!
ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ፣ ለሌሎች ሰዎች ብዙ የምናደርጋቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ያህል እናስብላቸዋለን፣ እንጋብዛቸዋለን፣ እናዳምጣቸዋለን፣ ደስተኛ እንዲሆኑ የቻልነውን እንሞክራለን።
ለኛ ለራሳችንስ ምን አድርገን እናውቃለን?
ራሴን መቼ ነው የጋበዝኩት?
ራሴን መቼ ነው ያዳመጥኩት?
ራሴን መቼ ነው ያሰብኩለት?
ራሴን መቼ ነው የተንከባከብኩት? ወዘተ
በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የሚያስችሉንን ነገሮች ሁሉ እናደርጋለን። ነገር ግን መቅደም ያለበት እራሳችንን መቀበል ነው ወይንስ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው?
ከእኔ ውጪ ላሉ ነገሮች ሁሉ መትረፍ የምችለው እኔ በጥሩ ሁኔታ መኖር ከቻልኩ ብቻ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ለራሴ ብለን የምናደርጋቸው ነገሮች ሊኖሩን ይገባል።
ይህ ራስ ወዳድ መሆን አይደለም። እኔነቴን መንከባከብ፣ ማፍቀርና ፍሬያማ ማድረግ እንጂ።
ተመስገን አብይ (የስነ-ልቦና ባለሙያ)
@melkam_enaseb
ትኩረት መነፈግና ተጽዕኖው!
የሰዎችን ትኩረት ማጣት ጭንቀትና ከፍተኛ የሆነ ድባቴ እንዲሁም ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያስከትል ይችላል፡፡
ሰዎች በተለይም ህጻናት ከሚገባው በታች ትኩረት ሲያገኙ የወደፊት ህይዎታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያደርስ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የሚገባውን ያህል ትኩረት ካላገኘ ምንም ያሕል አቅም ቢኖረውም እንኳን አቅሙን አውጥቶ ሊጠቀምበት የሚችልበት ዕድል አናሳ ነው፡፡
ግለሰቡ ‘’ሰው አይቀበለኝም፤ ልክ ላልሆን እችላለሁ’’ ብሎ ስለሚያስብ ያለውን አቅም ለሕብረተሰቡ ሳያንጸበርቅ ሊቀር ይችላል፡፡
ከሰው መሸሽ፣ ለራስ ዝቅተኛ የሆነ ስሜት መኖር፣ ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማብዛት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ሊመጡ ይችላሉ፡፡
ይህን ተከትሎም ሕመሙ ሲባባስ ሕክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጉዳይ አብዛኛውን ጊዜ ችላ ይባላል። ‘’አመሏ/ሉ ነው፤ ብቻው/ዋን መሆን ትወዳለች/ይወዳል’’ በማለት የተለያዩ ስሞች ይሰጣሉ።
ይህም ሣይታወቅ ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ ችግር ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል ማወቅ ይገባል፡፡
መፍትሄው ምንድነው?
- ከቤተሰብ ጋር ማውራትና ችግሮችን መፍታት፣
- ከተለያዩ ሰዎች ጋር ሃሳብ መለዋወጥ ካለባቸው ድባቴ ወይንም ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲወጡ ያግዛል፡፡
አበበ አምባው (የተቀናጀ የአዕምሮ ጤና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
የአእምሮ ጤንነትን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
- ሁልጊዜ እራስን ደስተኛ ማድረግ
- ከሰዎች ጋር ጊዜዎትን ማሳለፍ፣ ብቻ አለመሆን
- ዘላቂነት ያለው አስተሳሰብ መኖር
- የተሰጠንን ነገር ደጋግመን ማሰብ
- የበጎፋቃድ ተግባሮችን ማድረግ
- በራስ የመተማመን ስሜትን መላመድ
- የፈጠራ ችሎታዎን ማዳበር
- ጤናማ እንቅልፍ ማግኘት
- ጤናማ የአመጋገብ ስርአት መከተል
- በራሳችን መድኃኒቶችን አለመውሰድ
- ጭንቀትን ማስወገድ
- ስሜታዊ/ብስጩ አለመሆን
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
የአእምሮ ሀኪም ጋር መሄድ ያለብን መቼ ነው?
- በእለት ተለት እንቅስቃሴያችን በሚያጋጥሙን ምክኒያቶች ልንናደድ ወይም ልንጨነቅ እንችላለን ነገር ግን ምንም ምክኒያት ሳይኖረን የምንጨነቅ፣ የምንረበሽ እና ከልክ ያለፈ ፍርሃት የሚሰማን ከሆነ።
- ምክኒያቱ ያልተረዳነው ጭንቀት እና መረበሽ በስራችን፣ በትምህርታችን፣ በውጤታማነታችን እና በማህበራዊ ግንኙነታችን ላይ ተፅእኖ ካመጣ።
- የመረበሽ እና የመጨነቅ ስሜቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየ።
- በዙሪያችን ያሉ የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛ እና የትዳር አጋር የምናሳየውን አዲስ ስሜት አይተው ሁኔታህ ጥሩ አይመስልም ምንሆነሃል/ሻል ብለው እስኪጠይቁ የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ከደረስን።
- የሚሰማዎት ጭንቀት ከልክ በላይ ሆኖ እርሱን ለመርሳት የአልኮል መጠጥ እና የእንቅልፍ መድሃኒቶችን መፈለግ ከጀመሩ።
- ከሚሰማዎት ጭንቀት ብዛት "አሁንስ ብሞት ይሻላል" የሚል ሀሳብ ከጀመሮት።
- ያልተለመደ ሃሳብ ማለትም ሰዎችን መጠራጠር እና ያልተለመዱ ድምፆችን መስማት ከጀመሩ በግዜ የስነ-ልቦና አማካሪ/ የስነ-አዕምሮ ሐኪም ጋር በመሄድ የንግግር ወይም የመድሃኒት ህክምና ያግኙ።
#WorldMentalHealthDay
October 10, 2023
@melkam_enaseb