melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የባህሪያዊ ስነ-ልቦና አስተምህሮ (Behavioural Psychology)

''የሰውልጆች ባህሪ የሚመጣው ከአከባቢያችን ከምንማረው ትምህርት ነው። ስነልቦና ማጥናት ያለበት የሚታይ እና የሚለካ ባህሪን መሆን አለበት። አከባቢያችን በባህሪያችን ላይ ወሳኝ ተፅኖ ያሳድራል ነፃነት የሚባል ነገር የለም እኛ የአከባቢያችን ውጤቶች ነን።'' -B.F. Skinner

"ከፈለጋችሁ ጤናማ ሆነው የተወለዱ የተለያዩ ልጆችን ስጡኝ ለእያንዳዳቸው የራሴን የተለየ አከባቢ በመፍጠር በእጣ በመምረጥ የተፈጥሮ ብቃታቸዉ እና ችሎታቸው ሳያግደኝ የትኛውንም አይነት ባለሙያ ኢንዲሆኑ በማሰልጠን ከፈለግኩኝ የህግ ባለሙያ፣ ሀኪም፣ አርቲስት፣ ነጋዴ፣ መኮንን አዎ ከፈለኩ ደሞ ለማኝ፣ ሌባ እና ዘራፊ ላደርገው እችላለሁ" -Jhon B. Watson

''ሰዎች ከአከባቢያቸው በባህሪያቸው ውጤት ወይም ምላሽ ይማራሉ ለምሳሌ የመብራት ማብሪያ/ማጥፊያ በአጋጣሚ የነካ ህፃን ባጋጠመው አስደሳች ለውጥ የተነሳ ደጋግሞ በመንካት ስለጉዳዩ ይማራል ያውቃል በተቃራኒው የሻማ እሳት በእጁ የነካ ህፃን ባጋጠመው የማያስደስት ህመም ስለ እሳት መጥፎነት በማወቅ ደግሞ አይነካም።'' -B.F. Skinner

''ሰዎች ነገሮችን በማያያዝ ይማራሉ ከምንወደው፣ ከምንጠላው ወይም የመሳሰሉት ስሜቶች ከሚፈጥሩ ነገሮች ጋር ሌሎች ነገሮችን በማያያዝ ልንጠላ ወይም ልንወድ እንችላለን ለምሳሌ በህፃንነቱ በተደጋጋሚ ወደ ሀኪም ቤት የሄደ ህፃን እንደያ አጋጣሚው ነጩን የግድግዳ ቀለም እና የሀኪሙን ነጭ ጋውን ከመርፌው ህመም ጋር በማያያዝ ነጭነገርን ሊጠላ ይችላል በተቃራኒው የሚወደውን ነገር ያገኘ ህፃን ንፁህ እና ነጭ ነገሮችን አያይዞ ሊወድ ይችላል።'' -Ivan Pavlov

Source: From Personality Psychology books

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ቀናችንን በታላላቅ ሰዎች አባባሎች እንጀምረው!

"ያልተሰሩ ጭንቅላትቶች የተሰሩ ከተሞችን ሲያፈርሱ የተሰሩ ጭንቅላቶች የፈረሱ ከተሞችን ይገነባሉ።'' -ቤንጃሚን ፍራንክሊን

''እሆናለሁ ብለህ የምታምነውን ሰው ትሆናለህ፡፡'' - ኦፕራ ዊንፍሬይ

"መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ፣ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል ነገር ግን በፍፁም እንዳታቆም" -ማርቲን ሉተር

“ጀግንነት ማለት የፍርሃት አለመኖር ሳይሆን በፍርሃት ላይ ማሸነፍ እንደሆነ ተምሬአለሁ፡፡ ጎበዝ ሰው ማለት የማይፈራ ሰው አይደለም፣ ፍርሃቱን የሚያሸንፍ እንጂ” -ኔልሰን ማንዴላ

''የውስጥህ የሕመም መጠን የሚለካው ደባብቀሀ በያዝካቸው ጤና-ቢስ ምስጢሮችህ ልክና መጠን ነው” - ሪክ ዋረን

''የነፋሱን አቅጣጫ መለወጥ አልችልም፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም የምፈልገው ቦታ ለመድረስ እንደንፋሱ ሁኔታ የጀልባ ጉዞዬን አስተካክላለሁ፡፡'' - ጂሚ ዲን

"የራስን ስሜት መቆጣጠር አለመቻል አቅጣጫ ጠቋሚ በሌለው መርከብ እንደመጓዝ ነው።" -ማህተማ ጋንዲ

''በግልጽ ሰው የተፈጠረው ለማሰብ ነው፡፡ ይህም ሙሉ ክብሩና ግዴታው ነው፡፡ ግዴታውም እንደሚገባው ማሰብ ነው።'' - ብሌዝ ፓስካል

“ተጀምሮ ያልተጠናቀቀን ተግባር እልባት ሳይሰጡ እንደመኖር አድካሚ ነገር የለም።'' - ዊሊያም ጀምስ

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አስተሳሰባችን በስነ-ልቦና (Cognitive Psychology)

የሰዎች ባህሪ የሚመጣው ከማሰብ እና ሌሎች አእምሮአዊ ሂደቶች ሲሆን የዚህ አስተምህሮ ትኩረትም የሰው ልጅን አእምሮ ተግባራት (ትውስታ፣ ተርጉሞ መረዳት፣ ችግሮችን መፍታት፣ ውሳኔ መስጠት እና ከማሰብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን) መረዳት ነው።

"የትኛውም አጋጣሚ፣ ሁነት ወይም ሰው የትኛውንም አይነት ስሜት (ደስታ፣ ንዴት፣ ሀዘን፣ መከፋት እና የመሳሰሉት) እንዲሰማን ሊያደርገን አይችልም እንዲሰማን የሚያደርገው የራሳችን ነገሮችን የምንተረጉምበት መንገድ ነው በመሆኑም ስሜታችንም ሆነ ባህሪያችን የአስተሳሰባችን ውጤት ናቸው።"

"የአእምሮ ችግሮች የሚመጡት ልክ ወይም ምክኒያታዊ ካልሆነ አስተሳሰብ ስለሆነ እነዚህን ምክኒያታዊ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን ምክኒያታዊ በሆኑ ሀሳቦች በመተካት የአእምሮ ችግሮችን ማከም ይቻላል።" -Albert Ellis

''የአእምሮ እድገትን በተፈጥሮ ብስለት (maturation) እና ከአከባቢያችን በምናገኘው ልምድ የሚፈጠር ተራማጅ የሆነ የአእምሮ ተግባራትን ዳግም የማደራጀት ሂደት ሲሆን በዚሁ ሂደት ህፃናት አከባቢያቸውን ለመረዳት ሲሞክሩ በሚፈጠረው የሚያቁትና የሚሆነው ልዩነት ዳግም የማደራጀት ሂደት እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል።" -Jean Piaget

Source:- From Personality Psychology books & verywellmind (web)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ ''ሁሌም ካለህበት ጀምር፤ ያለህን ተጠቀምበት፤ የምትችለውን አድርግ፡፡''

▸ ከያንዳንዱ ክስተት መልካሙን ሁሉ ለማግኘት የመፈለግ ባሕል ስታዳብር ሕይወትህ የበለጠ እያማረ ነው የሚሄደው። ይህ ከታላላቆቹ የተፈጥሮ ሕግጋት አንዱ ነው። ይህም ዕውን ሊሆን የሚችለው አዕምሮን በደንብ በመጠቀም ነው።

▸ ስኬታማ ሰዎች ከንፈር ላይ ሁለት ነገር ይስተዋላል አንደኛው "ዝምታ" ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ፈገግታ" ነው።

▸ በሕይወትህ የፈለገው ነገር ቢያጋጥምህ ለጉዳዩ የምትሰጠውን ምላሽ የመምረጥ አቅም አለህ።

▸ የቁሳዊም ይሁን መንፈሳዊ ስኬት የሚጀምረው ከአዕምሮ ነው። ውጫዊው የውስጥህ ነፀብራቅ ነው።

▸ ቀስት ወደ ፊት ሊስፈነጠር የሚችለው ወደ ኋላ በተለጠጠበት መጠን ነው። ችግር ሲያጋጥምህ ደስ ይበልህ ከበፊቱ ወደ ተሻለው ልትስፈነጠር ነውና። ሁሌም ኢላማህን በመልካሙና በተሻለው ነገር ላይ ያነጣጥር!

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

🇪🇹🇪🇹🇪🇹እንኳን ደስ አለን!!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

አብዛኞቻችን እቅዳችንን የማናሳካው የወሬ እንጂ የተግባር ሰው ስላልሆንን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወሬም ሆነ ተግባር ሁለቱም የሀሳብ ውጤት መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ስለዚህ ሃሳባችንን ጠብቀን ወሬውን በተግባር ቀይረን ዉጤታማ ለመሆን መትጋት አለብን፡፡

ሁላችንም እንዲሳካልን እናስባለን፣ እንመኛለን፣ እናቅዳለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ምን ያህሎቻችን እቅዳችንንና ሀሳባችንን ለማሳካት ጠንክረን እንሰራለን የሚለው ጥያቄ ነው? ለዚህ ደግሞ ተነሳሽነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል።

መልካም የተግባር ሳምንት ይሁንልን!!!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

"ደግነት ማለት አንተ ከምትፈልገው በላይ እኔ የምፈልገውን ነገር ስትሰጠኝ አይደለም። ደግነት ማለት እኔ ከምፈልገው በላይ ለአንተ አስፈላጊ የሆነ ነገር ስሰጠኝ እንጂ።"—ካህሊል ጂብራን

የብዙዎቻችን ችግር በህይወት የምንቆይበትን ዋና አላማ አለመረዳታችን ነው፡፡ ያለምክንያት የሚገፋ ሕይወት አታካች ነው፡፡ ተግባሮቻችን እንወቅ፡፡

የደስታ ምስጢሩ ቀላለ ነው። ለመስራት የምትወደውን ነገር ለይተህ ዕውቅና ኃይሎችህን ሁሉ ያንኑ ነገር ወደምሥራት አዙራቸው።

“ሰፊው የባህር ውሃ መርከብን ማስመጥ አይችልም ውሃው ወደ መርከቦ ውስጥ ካልገባ በስተቀር በተመሳሳይ በዓለም ላይ ያሉ አሉታዊ ነገሮች በሙሉ አንተን ሊጥሉህ አይችሉም ወደ ውስጥህ እንዲገቡ ካልፈቀድክ በስተቀር።”

ግልፅ የህይወት ዓላማዎች ሲኖሩን የጊዜን ዋጋ እንረዳለን። ጊዜ የሚሰጠን አንዴ ብቻ በመሆኑና ይዘን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ባለመቻላችን ዉድ ነዉ። ራስን ለቀጣይ ዘመናት ተወዳዳሪነት የምናበቃዉ በጊዜ ነዉ። ትላንት አልፏል። ነገ ተስፋ ነዉ። ዛሬ ግን በእጃችን ስለሆነ እናዝበታለን።

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ራስህን ሁን!

የሰው ልጆች መልካምነት ላይ የሚያተኩረው የሥነልቦና ዘርፍ (humanistic psychology) በአስተምህሮው ሁሉም የሰው ልጆች በተፈጥሮአቸው ልዩ (unique) እና አውጥተው ከተጠቀሙበት መድረስ ያለባቸው ስኬት ላይ ለመድረስ የሚያስችል መቻልን (potential) ይዘው እንደሚወለዱ የሚገልፅ ሲሆን

🔹ስለራስን መሆን የተወሰኑ ጥቅሞቹ እንይ፦

► እራስን መሆን በራሳችን ልክ መሆን ስለሆነ በራስ መተማመናችንን ይጨምራል፦

"ያለን ሰዓት ውስን ስለሆነ የሌሎችን ህይዎት በመኖር ልናባክነው አይገባም" -stive jobs

► የውጥረት ስሜትን ይቀንሳል

"እንደማስበው አብዛኛው ሰው ባልተገባ መንገድ እየተመራ ነው ግለሰባዊ ልዩነታችንን ልናከብረው ልንደሰትበት እንጂ ልናፍርበት አይገባም" -joni deep

► የተሻለ ጓደኝነት እንድንመሰርት ያስችለናል፦ እራስን መሆን የራሳችንን ድክመት እና ጥንካሬ እንድንቀበል ስለሚያደርገን የሌሎችንም ደካማ ጎን ለመቀበል ቀላል ስለሚያረግልን በትንሽ በትልቁ አንቀየምም።

"እራስህን ሁንና የሚሰማህን ተናገር ምክኒያቱም በዚህ ቅር የሚላቸው አያገባቸውም የሚያገባቸው ደሞ ቅር አይላቸውም" -Bernard Baruch

► እራስን መሆን ከፍተኛ የሆነ ችሎታችንን ወደ ተግባር የመቀየር መሻትን እንድናገኝ ያደርገናል፦

"እራስን መሆን ገንዘብ ወይም ሥራ ማግኜት ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች ፍላጎት በታች የቀበርከውን በመሻት የተነቃቃ አንተነትህን ማግኘት ነው" -Kristen hannah

► ሌሎችን እንድናነቃቃ እድሉን ይሰጠናል፦

"አንተነትህን ጥሩ አርገህ ስትኖረው ለሎችንም በኑሮአቸው እራሳቸውን እንዲኖሩ ታበረታታለህ"

source: personal excellence

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

“ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች በረከቶች ናቸው ማለት እፈልጋለሁ። በጣም ንቁ እና ባለ ብሩህ አእምሮ ናቸው። ወላጆች እነዚህን ልጆች ከህብረተሰቡ ጋር ለማሳደግ እንዳይፈሩ እና እንዲያፍሩባቸው አልፈልግም። እንዲሁም ህብረተሰቡ ስለ ዳውን ሲንድረም በቂ መረጃ የለውም ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ወላጆች ስለሚያውቋቸው ነገሮች ለማህበረሰባቸው መረጃ የማካፈል ሃላፊነት አለባቸው።” -ቤተልሄም መላኩ

“I want to say that kids with Down syndrome are blessings. They are very active and smart. I want parents not to be afraid to raise them with the society and not to be ashamed of them. Also, I believe the society doesn’t have enough information about Down syndrome, for that parents have the responsibility to share information about everything they know in their community.” -Bethelhem Melaku

Source: Deborah Foundation

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዳውን ሲንድረም (Down Syndrome)

በየአመቱ March 21 - በአለም አቀፍ ደረጃ የዳውን ሲንድሮም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው።

#DownSyndrome
#DeborahFoundation
#Ethiopia

ለግንዛቤ ጥቂት ነገሮችን እንይ!
⬇️

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዳወን ሲንድሮም/Down syndrome
⬇️

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ንባብ ለአእምሮ ጤና!

በየቀኑ ወደ ጂም ስለመሄድ እና ክብደቶችን ማንሳትን አስቡ፤ ከጊዜ በኋላ ጡንቻዎቻችሁ እያደጉ እና እየጠነከሩ ይሄዳሉ።

ንባብም በአእምሮ ላይ ተመሳሳይ ውጤት አለው። በንባብ ምክንያት፤ አንጎል ቋሚ-ማነቃቂያ (Constant-Stimulation) ስለሚያገኝ ልክ ጡንቻ ለማውጣት ከሚያስፈልገው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ አስተሳሰብን የሚቆጣጠሩ እና ችሎታን የሚተነትኑ የአንጎል የተለያዩ ክፍሎችን ያጠናክራል። ንባብ፤ አእምሮ እንዲሰራ ስለሚያደርግ ጤናማ እና ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ይረዳል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ አእምሮአዊ መነቃቃት ሁኔታ ውስጥ መቆየት እንደ (Alzheimer) ትውስታን እና ሌሎች አስፈላጊ የአእምሮ ተግባራትን የሚያጠፋ በሽታ (Dementia) ያሉ በሽታዎች እድገትን ከመቀነስ አልፎ መከላከል ይቻላል።

በእርግጥ አእምሮአቸውን በንቃት ስራ ላይ የሚያሳትፉ ሰዎች፤ ጊዜያቸውን በማያነቃቃ እንቅስቃሴዎች ከሚያሳልፉ ሰዎች ይልቅ አልዛይመርን የመቋቋም እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ንባብ፤ አእምሮ እንዲሰራ ለማድረግ በጣም ጥሩ መንገድ ስለሆነ አእምሮን ለማዝናናት እና በሽታዎች እንዳያድጉ ያግዛል።

#nebebethiopia

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation

ዛሬ!

''በጊዜ ውስጥ ትናንት የትዝታ፣ ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው። ካመለጠ ትናንት ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ #ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል።

ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማይደገም ተመልሶም የማይመጣ ላንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር በትናንትና በነገ መሃል የተሸነቆረ እንቁ ነው። የዛሬ ሚስጥሩና ጉልበቱ ያለው ‘አሁን’ ላይ ነውና።

‘ቅድም’ እና ‘በኃላ’ ግን ያለቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትናና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው።''- ዶ/ር ምህረት ደበበ

ከ''ሌላ ሰው''
[ገፅ: 36_37]

ዛሬያችንን እንስራበት!

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በመጀመሪያ ግንኙነት ወይም ለስራ ቅጥር ስለእራስ ጥሩ ግምት መፍጠር!

አዲስ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ስትተዋወቁ ወይም በስራ ቅጥር ላይ ስለእናንተ የመጀመሪያ ግምት ለመስጠት ከሁለት እስከ ሶስት ሰከንድ ብቻ ቢፈጅ ነው፡፡ አቀራረባችሁ ካማረ በመልካምነት እንዲሁም የማይጥም አኳሃን ካሳያቹ በአንዲት ቅጽበት የምትፈጠረው ግምት እስከ መጨረሻው ከዚያ ሰው ጋር አብሮ የመዝለቅ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ጥሩ የመጀመሪያ ግምት መፍጠር በብዙ መልኩ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ለማኅበራዊ ህይወት፤ አዲስ ግንኑነት ለመመስረት፤ ለአዲስ ስራ ቅጥርና ለመሳሰሉ ሁኔታዎች፡፡ ጥሩ የመጀመሪያ ግምት ለመፍጠር ከዚህ የሚከተሉት ነጥቦች ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡

1. በሰዓት መገኘት፡-

ለመጀመሪያ ቀን ግንኙነት አልያም ለስራ ቅጥር ቃለ-መጠይቅ ካለዎት በፍጹም አያርፍዱ ፤ ቢቻል ከተባለው ሰዓት አንድ አስር ደቂቃ ቀድመው ይገኙ፡፡ በሰዓትዎ በመገኘት የቀጠረዎን ሰው ማስደመምና ስለእርስዎ ጥሩ ግምት በቀላሉ እንዲይዝ ማድረግ ይችላሉ፡፡

2. እራስን መሆን፡- 

ሌሎችን ለመምሰል ሳይጥሩ ትክክለኛ ማንነትዎን ይዞ መቅረብ፡፡ ይህም በራስ መተማመንዎን ይብልጥ እንዲሻሻልና እንዲጎለብት ይረዳዎታል፡፡ ሌሎችን ለመምሰል ሲጥሩ እንኳን የሌሎችን ትኩረት መሳብ ይቅርና ትዝብት ውስጥ ይገባሉ፡፡

3. እራስዎን በተገቢው መንገድ መግለጽ፡- 

ለመጀመሪያ ቀን የሚያገኝዎ ሰው ከዚህ በፊት ስለማያውቆት ስለእርስዎ የመጀመሪያ ቀን ግምት ጥሩ ስዕል እንዲኖረው ገጽታዎን አሳምረው ይሂዱ፡፡ ከፍትፍቱ ፊቱ እንደሚባለው ተዝረክርኮ መሄድ ዋጋ ሊያስከፍሎት ይችላል፡፡ በተለይ የስራ ቅጥር ላይ በፍጹም መዘናጋት የለብዎትም፡፡ ይህ ማለት ግን ሞዴል መስለው ተሽቀርቅረው ይቅረቡ ለማለት ሳይሆን እራስዎን ለዚያ ሁኔታ በሚመጥን መልኩ በማቅረብ ይግለጹ እንደ ማለት ነው፡፡ ባጭሩ አንድን ምርት ለጥሩ ገበያ እንደ ማቅረብ ማለት ነው፡፡

4. ማሸነፍ የሚችል ፈገግታን ያሳዩ፡-

ፈገግታ በሌሎች ሰዎች ላይ ተጽእኖ የመፍጠር ትልቅ ብቃት አለው፡፡ ታዲያ ፈገግታዎ የውሸት ድድን ከጥርስ ላይ ማሸሽ ብቻ አንዳይሆን ይጠንቀቁ፡፡ ሌሎች ነገሮች ተጨምረውበት ሰዎች በእርግጠኝነት በፈገግታዎ ስለእርስዎ ጥሩ ግምት እንዲይዙ ማድረግ ይችላሉ፡፡

5. ግልጽና በራስ መተማመን፡- 
የአካላዊ ንግግርና ገጽታ (nonverbal communication and gesture)

የሌሎችን ቀልብ ለመሳብ ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡ በመጀመሪያ ስትገኛኙ ሞቅ ያለ ሰላምታ እጅ በመጨባበጥ መለዋወጥ፡፡ ንግግርዎን በሚማርክ አካላዊ እንቅስቃሴ ማጀብ፡፡ ለምሳሌ “አለ አይደል…” ሲሉ አብሮ እጅዎን ማንቀሳቀስ፡፡ እንዲያ በሚያደርጉበት ወቅት ግልጽነትዎና በራስ መተማመንዎ አሳማኝና ጠንካራ እንደሆነ ግምት መፍጠር ያስችልዎታል፡፡

6. ቀስ ብሎ ማውራት፡-

ሳይፈጥኑ በጣምም ሳይዘገዩ በሚያወሩበት ወቅት የአድማጭዎን ትኩረትና ቀልብ መሳብ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ረጅም ሰዓት ወስደው ስለእራስዎ ጥሩ ግምት ለመፍጠር ሰከን ረጋ ብለው ማውራት ሲችሉ ብቻ ነው አግባቦቱን ማራዘም የሚችሉት፡፡ ክልፍልፍ ከሆኑ በሌሎች ላይ ቶሎ መሰላቸትን ስለሚያመጡ በእርጋታ ያውሩ፡፡ እርጋታ ማለት አንድ ቃል ተናግሮ ረዘም ያለ ዕረፍት መውሰድና አላስፈላጊ እንዲሁም አሰልቺ መሸጋገሪያዎችን መጠቀም አይደለም (ለምሳሌ እእእእእ……አአአአአአአ…ወዘተ)፡፡

7. አወንታዊነት፡- 

አመለካከትዎ መላ ድርጊትዎን ስለሚገዛው የሚያወሩት ነገር ስለቢዝነስም ይሁንስ ለአዲስ የስራ ቅጥር ሁኔታዎችን አስቀድሞ በመወሰን በተሳሳተ አመለካከት አግባቦትዎን አይጀምሩ፡፡ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን እራስዎን በአወንታዊ አመለካከት ቁመና አስተካክለው መቅረብ አለቦት፡፡ ይህም ጥሩ ግምት ሰዎች በእርስዎ ላይ እንዲይዙ ይረዳል፡፡

8. አድማጭና ትሁት መሆን፡-

እርስዎ ሲያወሩ ሌሎች እንዲያዳምጥዎት እንደሚፈልጉ ሁሉ እርስዎም በተራዎ ሌሎች ሲያወሩ ጥሩ አድማጭና ትሁት ተናጋሪ መሆን መቻል አለብዎት፡፡ ባለጉዳዮ ሲያወራ ሃሳቦና ትኩረትዎ ወደ ሌላ ቦታ የሚበታተን ከሆነ የቢዝነስ ሽርክናውን፤ አዲስ ግንኙነትና የስራ ቅጥሩን አሸንፈው በድል አድራጊነት መወጣት አይችሉም፡፡ ስለዚህ ጥሩ አድማጭና ትሁት መሆን የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ሲያደርጉ ጥሩ ግምት መፍጠር ቻሉ ማለትነው፡፡

#zepsychologist

ለሌሎች ሼር/SHARE ያድርጉ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation

ራስህን ሁን!

ቻርሊ ቻፕሊን፣ ዊል ሮጀርስ፣ ሜሪ ማርጋሬት፣ መክብራይድ፣ እነ ጆን ኦትሪና ሌሎችም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታላላቅ ሰዎች ራስን የመሆንን ነገር የተማሩት ከብዙ ጊዜ ጥረትና ሙከራ በኋላ ነው።

ቻርሊ ቻፕሊን ፊልም መሥራት እንደጀመረ አዘጋጁ አንድ የታወቀ የጀርመን ኮሜዲያን እያስመሰለ እንዲሠራ ደጋግሞ ይነግረው ነበር፡፡ ሆኖም ቻርሊ ቻፕሊን በራሱ መንገድ መሥራት እስኪጀምር የተሳካለት ኮሜዲያን ሊሆን አልቻለም ነበር፡፡

ቦብ ሆፕም ተመሳሳይ ችግር ደርሶበታል። ምንም እንኳን ለአያሌ አመታት በዘፋኝነትና በዳንስ ሥራ ላይ ቢቆይም ራሱን አውቆ በራሱ እስኪሰራ ድረስ ታዋቂነትን አላገኘም ነበር።

ጂን ኣትሪ ከቴክሳስ የመጣ ቢሆንም እሱ ግን የቴክሳስን የአነጋገር ቅላፄና አለባበስ ትቶ እንደ ኒው ዮርክ ሰው ለመልበስና ለመናገር ሲሞክር መሳቂያ መሳለቀያ ሆኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ባንጆ የተባለውን ክራር መሰል የሙዚቃ መሳሪያ እየመታ የቴክሳስ እረኞችን ዘፈን ሲዘፍንና ይህንንም ሥራዬ ብሎ ሲይዘው የተዋጣለትና በመላው አለም የታወቀ ዘፋኝ ሆነ፤

🔹(የፅሁፉ መልዕክት)=> በዚች ምድር ላይ አንተን የሚመስል ሰው የለም፡፡ በዚህም ደስ ሊልህ ይገባል። ተፈጥሮ ባደለችህ ጸጋ ተጠቀምበት። ሁሉም ነገር የሚወጣው ከራስህ ነውና ማዜም፣ መሳል የምትችለው ያንተ የሆነውን ብቻ ነው። አካባቢህ፣ ልምድህ፣ ከዘር የወረስከው ባህርይ ያደረጉህን ብቻ መሆን አለብህ። ለማንኛውም የራስህ የሆነውን ነገር አዳብረው።

🔹የመንፈስ ዕረፍትንና ደስታን አዳብሮ ከጭንቀት ነፃ ለመሆን የሚከተለውን ልብ በል፦

▸ ሌሎችን ለመምሰል አንሞክር
▸ ራሳችንን እንፈልግ
▸ ራሳችንን እንሁን

ከ"ጠብታ ማር" የተቀዳ የሕይወት ስንቅ

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ እንዲህ ይለናል!

“እኛ ሰዎች ድንቅ ሆነን የተፈጠርነው፣ ድንቅ ሆነን በመገኘት፣ ድንቅ ሕይወት ለመኖር ነው። ታድያ ለምንድን ነው ብዙ ሰው ድንቅ ማንነቱን ትቶ፣ ተራ ሆኖ በመገኘት ተራ ሕይወት የሚኖረው? ምክንያቱም ተራ መሆን በጣም ቀላል ስለሆነ ነው። ድንቅ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤ በነጻም አይገኝም፤ ዋጋ ያስከፍላል፤ መሥዋትነትም ይጠይቃል። ተራ ሰው ልክ እንደ ድንቅ ሰው ሁሉ ድንቅ ሕይወት መኖር ይፈልጋል። ነገር ግን ለድንቅነት የሚከፈለውን ዋጋ መክፈል አይፈልግም። ተራ ሰው፣ ድንቅ መሆን ይጀምራል፤ ከዚያም ትንሽ ከበድ ሲለው፣ ተስፋ ይቆርጣል፤ ወደ ተራ ሕይወቱም ይመለሳል።

“እንዴት አድርገህ ነው ሙሉ በሙሉ ራስህን ልትቀይር የምትችለው? ''ራሴን መቀየር አለብኝ” ብለህ ስታስብ፣ “ምንህ እንዲቀየር ነው የምትጠብቀው? ምንህስ ነው መቀየር ያለበት? የሰው ልጅ ማን ነው? ምንድንስ ነው? በምንና እንዴት ነው የሚሠራው? ራስን ለመቀየር መቀየር የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?”

⬆️እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ስትችል፣ ራስህን እንዴት አድርገህ መቀየር እንደምትችል በቀላሉ መረዳት ትችላለህ።“

የዳዊት ድሪምስ “ ትልቅ ሕልም አለኝ “ መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ...

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ፍርሃት!

በማንኛውም የሂወት መስመር ውስጥ ብናየው ፍርሃት የአስተሳሰብ ምላሽ ነው።

ፍርሃት በጊዜ ካልተወገደ ኃይልንም ያደክማል፣ የፈጠራ ችሎታህን ያጠፋል። ዋናው አለመፍራት ነው፣ ዋናው የምትፈራውን በድፍረት መተግበር፣ መጋፈጥ ነው። የፍርሃትን ምንነት በደንብ ተገንዘብ።

ፍርሃት የአንተው ፈጠራ ነው። ልክ እንደማንኛውም ክስተቶች ከአንተ ማራቅ ትችላለህ።

“ጀግንነት ማለት የፍርሃት አለመኖር ሳይሆን በፍርሃት ላይ ማሸነፍ እንደሆነ ተምሬአለሁ፡፡ ጎበዝ ሰው ማለት የማይፈራ ሰው አይደለም፣ ፍርሃቱን የሚያሸንፍ እንጂ” ይለናል -ኔልሰን ማንዴላ

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዛሬ አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

እንደ አለም ጤና ድርጅት ገለፃ በአለም ላይ ከሚወለዱ 160 ልጆች 1 ልጅ በኦቲዝም ይጠቃል። ኦቲዝም ከልጅነት ጀምሮ ወደ ጉርምስና ድረስ የመቆየት አዝማሚያ አለው።

በብዛት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ይስተዋላል።

ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች የሚያሳዩቸው ባህርያት:-

1. በእድሜያቸው የሚጠብቅባቸውን ቋንቋ አለመጠቀም፣ ምንም ቋንቋ አለመጠቀም፣ አንዳንድ ድምጾችን መጠቀም፣ ትንሽ ቃላቶች መጠቀም።

2 .ከሰዎች ጋር የአይን ትይዩ ወይም ምልክታ አለመኖር እና በዙሪያቸው የሚደረጉ ነገሮች ብዙም ትርጉም አለመስጠት

3. የጋራ እይታቸው የተገደበ መሆን

4. ስማቸው ሲጠራ መልስ አለመስጠት

5. ያልተለመዱ ባህርያት ማሳየት

6. ያልተለመዱ የጣት እንቅስቃሴ ማሳየት

7. ብቻን መጫወት መምርጥ

8 .ከሰዎች የሚሰሙትን ቃላቶችን መድገም

9 .ድግግሞሽ ያለው እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም አንድ ጨዋታ መፈለግ

10. ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ጓደኝነት መመስረት አለመቻል

🔹ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆች የሚሰጡ ህክምናዎች መካከል speech therapy, language therapy and behavioral therapy ዋነኞቹ ናቸው።

#April2 World Autism Awareness Day!

Via: speechtherapyethiopia

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ በየእድሜያችን ብዙ መልካም ጎኖች አሉን፡፡ የወጣትነት ጊዜ፣ ጤናማነት፣ ልምዶቻችንና ተሰጥዎቻችን የምንሰራባቸው በራሳችን ጊዜ ነው። በተለይ ወጣትነታችን ለህይወታችን መልካም ሙያዎችን የምናዳብርበት ወርቃማ እድሜ በመሆኑ ሳያልፍብን እንጠቀምበት፡፡

▸ ''መቼም ያንተን ህይወት ከሌሎች ጋር አታነፃፅር በፀሀይ እና ጨረቃ መካከል ንፅፅር የለም ሁለቱም የሚያንፀባርቁበት የራሳቸው ግዜ አላቸው።''

▸ ''ግብህ ጋር መድረስ ከተሳነህ መንገድህ እንጂ መድረሻህ አይቀየር፡፡ አስታውስ! ዛፎች ቅጠላቸውን እንጂ ስራቸውን አይቀይሩም፡፡''

▸ ክብደት መስጠት ባለብህ ጉዳዮች ላይ ክብደት ስጥ፡፡ ቀለል ማድረግና አንዳንዴም ማለፍ ባለብህ ጉዳዮች ላይ ጊዜህን አታባክን፡፡

▸ ''ህይወት የደስታ የሀዘን ወይም የመጥፎ ሁኔታ እና የጥሩ ሁኔታዎች አዙሪት ናት መጥፎ ሁኔታን እያሳለፍክ ከሆነ እምነት ይኑርህ መልካም ሁኔታ በቀጣይ በመንገድ ላይ ነው።''

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ እንዲህ ይለናል!

ዶ/ር ሐንስ ሴሊ የተባለው ዕውቅ የአእምሮ ሐኪም ''የሁለት ወንድማማቾች ወግ'' የተባለውን በጣም የታወቀ ወግ ለማስተማሪያነት አዝውትሮ ይጠቀም ነበር። ወጉ አንድ ዓይነት አጋጣሚ እንዴት የተለያየ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል የሚገልጽ ግሩም አብነት ነው።

ሁለት ተቃራኒ አመል ያላቸው ወንድማማቾች ነበሩ። አብረው ነው ያደጉት፤ በአንድ እናትና አባት ጉያ፤ በአንድ ቤት ውስጥ። ጠባያቸው ግን ለየቅል ነው፤ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ። አንደኛው የወጣለት ሰካራም ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፍጹም አልኮል መጠጥ የሚባል በአፉ የማይዞር ነበር። ልጅ ሳሉ አባታቸው ጠጪ እንደነበር ይነገራል። በፍጹም ሳይሰክር ወደ ቤት ገብቶ አያውቅም። ወደ ቤት ሲገባም እናታቸውን ይሰድባታል፤ አልፎ አልፎም ልጆቹን ይደበድባል።

አንደኛው ልጅ ልክ እንደ አባቱ ሰካራም ተደባዳቢ ሆነ። ሌላኛው ልጅ ግን መጠጥና ድብደባ በደረሰበት የማይደርስ ሆነ። ታዲያ እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች ስለጠባያቸው ሲጠየቁ፤ ሁለቱም አባታቸውን በምክንያትነት ይጠቅሳሉ። የአባታቸው ሰካራም መሆን አንደኛውን ስካር አስተማረ፤ ሌላኛውን ደግሞ አልኮል አምርሮ እንዲጠላ አደረገ። አንድ ዓይነት ምክንያት የተለያዩ ውጤቶችን አስገኘ። ለአንድ ዓይነት ችግር የተሰጠው ምላሽ ለየቅል ሆነ።

🔹የምንኖርበት ሕይወት በአያሌ ክሥተቶች የተሞላ ሲሆን ክሥተቶቹ አንዳንዴ ሁላችንንም በጋራ የሚነኩ ይሆናሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በግል እኛን ብቻ የሚመለከቱንና በግል የሚነኩን ሆነው ይበቅላሉ።

©የመደመር መንገድ፣ ገፅ 3-4፣ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚደረግ የመጀመሪያ እርዳታ!

ፃታዊ ጥቃት የሰዎችን አስተሳሰብ፣ ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ስሜትና ፀባይ ይለውጣል፡፡ ይሁን እንጂ የሚገባውን ያህል ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ፆታዊ ጥቃት ከደረሰ በኃላ ሌሎች ሰዎች የሚናገሯቸው ነገሮች የበለጠ የሚጎዱ የሚሆኑበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንዳንዴ ለመርዳት በማሰብም ሊሆን ይችላል፡፡ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ሊደረግ የሚገባ የመጀመሪያ እርዳታ፡፡

1. ማዳመጥ፦ ቅርብ ሆኖ ያለ ፍረጃ ማዳመጥ፡፡

2. ፍላጎትና ሀሳቧን መጠየቅ፦ የተለያዩ ፍላጎቶቿንና ስጋቷን መጠየቅ፡፡ (አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና ተግባራዊ)

3. መቀበል፦ እንደተረዳናትና እንዳመንናት ማሳየት፡፡ ጥፋተኛ እንዳልሆነች ማስረገጥ፡፡

4. ደህንነትን መጠበቅ፦ ሌላ ወይም ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስ እንዴት መከላከል እንደሚቻል መወያየት፡፡

5. ድጋፍ፦ መረጃ፣ አገልግሎት እና ማህበራዊ ድጋፍ የምታገኝበትን መንገድ ማፈላለግ፡፡

አንዳንድ ጊዜ የምናውቃቸው ሰዎች ላይ ፆታዊ ጥቃት ሲደርስ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ልንጋባ እንችላለን፡፡ በቀላሉ ልናደርግ የምንችለው የመጀመሪያ እርዳታዎች ለመነጋገር ፈቃደኛ እንድትሆን ጊዜ መስጠት፣ ስለ ፆታዊ ጥቃት መረጃ መስጠትና የስነ ልቦና ባለሞያ ወይም የአእምሮ ሀኪም ማማከር ሲሆኑ መዘንጋት የሌለብን አንድ ቁልፍ ነገር ሁሌም ፍላጎቷን ማክበር እንዳለብን ነው፡፡

ፆታዊ ጥቃት መንስኤው ሴቶችን እኩል በሆነ መልኩ ክብራቸውንና ሰብአዊነታቸውን ያለመቀበል ነው፡፡ ፆታዊ ትንኮሳ፣ አካላዊ ጥቃት፣ የቅርብ አጋር ጥቃት፣ ፆታዊ ጥቃት፣ አላግባብ የሆነ ቁጥጥር ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ናቸው፡፡

ምንጭ፦ የአለም ጤና ድርጅት ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሀኪም መመሪያ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

#ፍሬድሪክ_ኒቼ "ፍለጋ" የሱ ታላቅ ምስጢር ነው። በተለይም ራስን መፈለግ።

ኒቼ ሃሳቡን ሲያስቀምጥ "ደፋርና ታላቅ ሰው ራሱን በመፈለግ ሂደት በሚፈጠር ግጭት ውስጥ ደስታን ይፈጥራል። መከራን ስቃይንና ሽንፈትን ለማጥፋት መሞከር የአየርን ፀባይ ለመሻር ከመሞከር የማይሻል ረብ የለሽ ተግባር ነው።

በነዚህ ውስጥ ራስን አለማምዶ፣ ፈትኖና ሞርዶ ታላቁን ሰብእና መቀዳጀት ግን የስኬት ምስጢር ነው። በነዚህ የተፈተነውን ማንነት ነው 'ልዕለ ሰብ' የምንለው።" ይላል።  

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

"በእምነትን ከመውለዴ በፊት ብዙ እንቀሳቅስ ነበር፤ አሁን ግን የምኖረው ለእሱ ነው። እሱን መንከባከብ እና በየወሩ ወደ ሆስፒታል መውሰድ አለብኝ። ያለእኔ መኖር የሚችል አይመስለኝም። ወላጆች የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆቻቸውን ከማህበረሰቡ መደበቅ አለባቸው ብዬ አላምንም። ልጆቻቸውን ማህበራዊ ግንኙነት እና በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ ወደ ትምህርት ቤቶች መላክ አለባቸው።" - ወ/ሮ አሰገደች መብሬ - የህጻን በእምነት እናት
.
“I was very active before having Beminet, but I live for him now. I have to take care of him and take him to the hospital every month. I feel like he will be lost without me. And I don’t think parents should hide their intellectually disabled kids from the community. They should also send their kids to schools so that they can develop interpersonal skills and confidence.” - Mrs. Asegedech Mebre - Beminet Belayneh’s mother

Source: Deborah Foundation

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዲቦራ ፋውንዴሽን
===========
‹‹ዲቦራ ፋውንዴሽን›› - ዳውን ሲንድረም (Down Syndrome) ባለባት አራተኛ ልጃቸው ዲቦራ አባዱላ ስም በሰኔ ወር 2011 ዓ.ም. በአቶ አባዱላ አነሳሽነት የተመሠረተ ነው።

አቶ አባዱላ ገመዳ - ሺዎችን በማዳን ሕይወት እንዲኖራቸው፣ ተረጂዎች ሳይሆኑ ረጂዎች፣ የሚጨነቁ ሳይሆኑ የሚኖሩ፣ ባላቸው ጉድለት የሚያዝኑ ሳይሆኑ ዘና ብለው ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ሀገራቸውን የሚያስጠሩ እንዲሆኑ ለመሥራት፣ የዲቦራ ፋውንዴሽን ከአንድ ዓመት በፊት ተመሥርቶል፡፡

አባ ዱላ ለዲቦራ በህክምናው ረገድ ሊደረግላት የሚችለውን ሁሉ እንዲፈፀም የአባትነታቸውን ብዙ ጥረዋል።

አባዱላ በተለይም እንደ ዲቦራ የዳውን ሲንድሮም ተጠቂ ህፃናት ወላጆች እንዲሁም ኅብረተሰቡ ስለ በሽታው ግንዛቤ እንዲኖረው በሚል በሚወዷት ልጃቸው ስም "ዲቦራ" እና ዲቦራ ~ "የብርሃን ጉዞ" የሚል [ሁለት መጽሐፍት] አሳትመዋል። እንዲሁም ደግሞ የዲቦራ ፋውንዴሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ አድርገዋል።

Source: Deborah Foundation

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዳውን ሲንድረም/Down syndrome

ዳውን ሲንድሮም ማለት አንድ ልጅ ሲወለድ ሊኖረው ከሚገባ 46 ክሮሞዞም በተጨማሪ አንድ ክሮሞዞም ኖሮት 47 ክሮሞዞም ያለው ማለት ነው።

ይህ ተጨማሪ ክሮሞዞም መኖሩ በሚወለደው ልጅ የአእምሮ እና የመልክ ገፅታ እድገት ላይ ተፅእኖ እንዲኖር ያደርጋል።

🔹የዳውን ሲንድረም መከሰት ምክንያት

በርግጥኝነት ምክንያቱ የታወቀ ባይሆንም ነገር ግን የችግሩ መከሰት እድል የሚጨምሩት ልጁ ወይም ልጅቷ ስትፀነስ ምናልባት የእናት እድሜ ከ35 እና የአባት እድሜ ከ40 በላይ መሆን ወይም ከዘር ጋር የተያያዥ ማለትም ቤተሰብ ውስጥ ዳውን ሲንድሮም ያለው ሰው መኖር ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታመናል ነገር ግን በሃያዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወላጆችም አጋጥመውኝ ያውቃሉ።

ከሌሎች የአእምሮ እድገት እክሎች በተለየ አንድ ልጅ ዳውን ሲንድረም ያለው ወይም የሌለው መሆኑ በእርግዝና ወቅት በሚደረግ አምኒዬስንተሲስ የተባለ ምርመራ ማወቅ ይቻላል።

3 አይነት የዳውን ሲንድረም አይነቶች አሉ፦

1. Trisomy 21- በብዛት የሚከሰተው አይነት ነው።
2. Mosaicism- ይኼኛው አይነት በልጆቹ ላይ የሚታየው ምልክት ቀለል ያለ ነው።
3. Translocation.

አንድ ልጅ እንደተወለደ ዳውን ሲንድረም እንዳለበትና እንድሌለበት አካላዊ ገፅታውን በማየት ማወቅ ይቻለል።

ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ስለሆኑ የቅርብ ህክምና እና ክትትል ያስፈልጋቸዋል።

ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ ትምህርት የመቀበል፣ አካባቢን የመረዳት፣ የማስታወስ፣ የንግግር፣ እጅና እግርን አቀላጥፎ የመጠቀም እና እራስን የመርዳት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል።

የተቀናጀ ባህሪ እና ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ እና ደስተኛ ሂወት እንዲመሩ ያግዛቸዋል።

በየትኛውም አለም ያሉ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ሁሉ ተመሳሳይ የሆነ የፊት እና አካላዊ ገፅታ አላቸው ምናልባት ቀለማቸው ነው ሊለያይ የሚችለው።

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

🔹በየአመቱ March 21 - በአለም አቀፍ ደረጃ የዳውን ሲንድረም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

...ማንም ሰው ባለው ነገር መጠቀም አልቻለም። ያለንን ሁሉ ደግሞ መጠቀም አንችልም፡፡ ለምሳሌ ክንፍ ያላቸው ሁሉ ይበራሉ፤ ዶሮ ግን ክንፍ እያላት መብረር አትችልም፡፡ ዶሮ ክንፍ እያላት መብረር ያልቻለችው ምንአልባት ሞክራው ስለማታውቅ፤ ብትሞክረውም እወድቃለሁ የሚል ፍርሃት ይዟት ይሆናል፡፡ ከዚህም ፍርሃቷ የተነሳ መብረር አልችልም ብላ እራሷን አሳምናው ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው መንገድ ደግሞ ክንፍ ያለው ሁሉ ክንፍ ስላለው ብቻ መብረር አይችልም፡፡

▸ይህ በሰውም ላይ ይታያል፡፡ አንዳንዱ ሰው ነገርን ሁሉ አልችልም፤ አላውቅም በማለት እያወቀም ቢሆን እንደሚያውቅ እንዳይታወቅበትና መታየት ስለማይሻ እውቀቱን ይደብቃል፡፡ ሌላው ደግሞ እውቀቱ ስላለው ብቻ በሁሉም ነገር ላይ ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል አጉል ትዕቢት ይሞላል፡፡ ይህ አይነቱ ሰው የጠዋት ጤዛ ይሆናል፡፡

▸ዶሮ የተሰጣትን ክንፍ የማደሪያ ቆጧ ላይ ለመውጣት እና ለመውረድ እንዲሁም ልጆቿን ለማቀፍ እንቁላሏን ሙቀት ሰጥታ ለመፈልፈል ትጠቀማለች፡፡ ባለመብረሯ የቀረባት ነገር የለም፤ የቀረባት ነገር ቢኖር እንኳን እሷ የማታውቀው ዓለም ስለሆነ አይገባትም፡፡

🔹ቁም ነገሩ (የፅሁፉ መልዕክት)=> ማንም ሰው እውቀት፣ ችሎታና ሀብት ስላለው ብቻ ነገሮችን ይከውናል ማለት አይደለም፡፡ ሀብቱን፣ እውቀትና ችሎታውን የት፣ አንዴት፣ መቼ፣ ለምንና ለማን መጠቀም እንዳለበት ማወቅ ግድ ይላል፡፡ ስለዚህ ያለንን እውቀትና ችሎታ ባለን ልክ ለተሰጠን እና ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል አለብን፡፡

#ጠኃ_ባላደራ <ከገፅ 151-52>
(መ/ር ትምህርተ አየለ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ልጅ ፊት እንዲህ አይባልም!

ልጅ ፊት እንዲህ አይባልም፤ እንዲህ አታድርጉ ሲባል ሰምተን ይሆናል። አዎ ወላጆች ልጆቻቸው ፊት የሚያደርጓቸውን ነገሮች መጠንቀቅ አለባቸው።

ወላጆች ▸ ለንግግራቸው
▸ ለድርጊታቸው መጠንቀቅ አለባቸው።

በልጆቻቸው ፊት ሀይለ ቃላትን መናገር፣ መሣደብ፣ በልጅ ፊት ማጨስ፣ ልጆች ባሉበት ፆታዊ ግንኙነት ማድረግ እና የመሳሰሉትን፤ መከወን የለባቸውም። እነዚህን ነገሮች ልክ እንደ መድሀኒት ህፃናት ከማይደርሱበት ስፍራ ይቀመጡ/ይደረጉ። ህፃናት እኛ ከምንገምተው በላይ የምናደርጋቸውን ነገሮች ቀድተው (copy አድርገው) ሊተገብሯቸው ይችላሉ።

በቅርቡ በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ የተደረገ ጥናት የ 1አመት ከ2ወር እድሜ ያላቸው ህፃናት ለተወሰኑ ደቂቃዎች የተመለከቱትን የቴሌቪዥን ድርጊት መልሰው መላልሰው ልክ እንደተመለከቱት ሲተገብሩት ታይቷል። ይህም ህፃናት ከለጋ እድሜያቸው ጀምሮ ያዩትን ነገር አስተውለው ለመድገም እንደሚጥሩ ያሳያል።

ወላጆች ለልጆቻችን አርአያ (Role Model) በመሆን በነሱ ፊት ትህትናን፣ መልካምነትን እና ቀናውን ነገር እናድርግ።

▸ የመጀመሪያዎቹ አስተማሪዎች ወላጆች
▸ የመጀመሪያው መማሪያ ክፍልም ቤታችን መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።

(በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

"ወጣቶች ዩኒቨርስቲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ስራ ማሰብ መጀመር አለባቸው" አቶ ኤፍሬም በቀለ

ከከፍተኛ የትምህርት እና የሙያ ተቋማት እየተመረቁ የሚወጡ እጅግ ብዙ ወጣቶች በስራ ገበያው ላይ ተመጣጣኝ ስራ ሲያገኙ አይታይም፡፡

በዚም ምክንያት የተማሩ ወጣቶች በስራ ፍለጋ ከወራት እስከ ዓመት ሲጉላሉ ይስተዋላል፡፡ በአንጻሩ ቀጣሪዎችም ተወዳዳሪ የሆኑ ወጣቶች በበቂ ሁኔታ ገበያው ላይ እንደሌሉ ሲያነሱ ይሰማል፡፡

የስነልቦና ባለሞያ እና የስራ ቅጥር አማካሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም በቀለ ወጣቶች ስለ ስራ ማቀድ ያለባቸው ሲመረቁ ሳይሆን ገና ትምህርት ሲጀመሩ ነው ይላሉ፡፡

ቪኦኤ ያዘጋጀውን አጭር ዘገባ ከድምፅ ፋይሉ ያድምጡ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በብዙዎቻቹ ጥያቄ መሠረት በመጀመሪያ ግንኙነት ወይም ለስራ ቅጥር ስለእራስ ጥሩ ግምት ለመፍጠር እንሆ!

👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ተስፋ አትቁረጥ!

ተስፋ መቁረጥ ማለት ለመኖር እድል እያለ ለመጠቀም አለመፈለግ ለመኖር ትርጉም ማጣት ማለት ነው።

እውነት ነው ታላቅ የመኖር እድል ተሰጥቶናል ስለዚህ ለሕይወታችን ልዩ ማጣፈጫ ጨምረን ሕይወትን ትርጉም እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን።

ሁሌም በተስፋ የምንኖር ድንቅ ፍጡር ነን። እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ይባላል እና ወዳጄ በጭራሽ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ላንተ የተሻለ እድል አለ።

በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ትችላለህ፣ ሰዎች ላይረዱህ፣ ቦታ ላይሰጡህ፣ ስም ሊያወጡልህ፣ አልያም ሊስቁብህ ይችላሉ ግን ልብህ ቅንና ሀሳብህ መልካም ይሁን።

ህልምህን ለማሳካት ተስፋ አትቁረጥ! ጊዜ ሊወስድ፣ ዋጋ ሊይስከፍልህ ይችላል መስዋእት የምታደርጋቸው እና የምትተዋቸው ነገሮች ይኖራሉ ያሰብከውን እስክታገኝ መንገዱ ቀላል አይደለም በህልምህና ዛሬ ባለህበት ሕይወት መካከል ያለው ልዩነት ህልምህን ተራ ምኞት ቢያስመስለውም ግን በዚህ ከአንተ በቀር አንተን ሊያስቆምህ የሚችል ኃይል የለም።

ሁሉንም ነገር ያጣህ ከመሰለህ ይህን አስታውስ ዛፎች በየዓመቱ ቅጠላቸውን ቢያጡም የተሻለ ቀን እንደሚመጣ በመጠበቅ ጠንክረው ይቆማሉ ይለመልማሉ።

ተስፋ ባይኖር ሕይወት አታጓጓም ነበር ሁሉም ነገር ለበጎ ነው አንድ ቀን ነገሮች ይስተካከላሉ ከእኛ የሚጠበቀው ትዕግስት ነው።

ዛሬ አላየኸውም ዛሬ ጨልሟል ማለት ነገ የለም አይነጋም ማለት አይደለም!

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel