melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation

ፅናት!

"በዓለም ላይ የፅናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም አይደለም። እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም። የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ ትዕይንት ነው። መማርም አይደለም። ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞላች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው። የአላማ ፅናት ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።" -ካልቬን ኮሌጅ

"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው" -ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአዕምሮ ህሙማን ወር!

“የአዕምሮ ህመምን ታክሞ ውጤታማ ኑሮ መቀጠል ይቻላል” -እሌኒ ምስጋናው

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ "ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!"

▸ ላወቀበት ሰው ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣

▸ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጂ በፍፁም አታማር፣

▸ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም፣

▸ የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም፣

▸ ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣

▸ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፣

▸ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ሕመም ስላጋጠመው ግለሰብ ማለት የማይገቡን ነገሮች፦

▸ ይሄ የቁም ቅዠት ነው
▸ እርሳው በቃ
▸ ትኩረት ለመሳብ ነው እንጂ ደህና ነህ
▸ ጭንቀት ሆነ ድብርት ያለብህ አትመስልም
▸ ይሄ ስንፍና ነው
▸ ሳታብድ አልቀረህም
▸ ሁሌ ብሶት ትወዳለህ
▸ ህይወት ቀላል ነው ያለህ ማነው?
▸ ስራ ነገርህ ሁሉ ግራ ነው
▸ አሁን ይሄ ከባድ ነገር ሆኖ ነው?
▸ ድሮም ችግር እንዳለብህ ታስታውቃለህ
▸ ማማረርህን አቁም
▸ ከዚህ የባሰ ቢገጥምህ ምን ልትሆን ነው?
▸ ከቤት ስለማትወጣ ነው
▸ ነገሮችን ማጋነንህን አቁም
▸ ምን የሚያስጨንቅ ነገር ተገኝቶ ነው?

የግንቦት ወር በአለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ወር ነው።

#May Is World Mental Health Month

#Share

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አካላዊ ገጽታ ላይ የተጋነነ ችግር ያለ መስሎ መሰማት (Body Dysmorphic Disorder)

የቦዲ ዳይስሞርፊክ ችግር ያለበቸው ሰዎች በአካላዊ ገፅታቸው የሆነ የተጋነነ ችግር እንዳለ በማሰብ የሚጨናነቁ ሲሆኑ ምንም እንኳን ለሰዎች ማራኪ ገፅታ እንዳላቸው ቢታወቅም እራሳቸውን የሚገነዘቡት አስቀያሚና አስፈሪ ገፅታ እንዳላቸው ነው፡፡

አንዳንድ የዚህ ችግር ያለባቸው ሰዎች መስታወት ላይ አካላዊ ምስላቸው በመመልከት ችግሩ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በቀን ብዙ ሰዓታትን ሊያሳልፉ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የሚያስቡትን አካላዊ ችግር ያሳየኛል ስለሚሉ መስታወት አጠገባቸው እንዲኖር አይፈልጉም አሊያም ችግሩን ይሸፍናል ብለው የሚስቡትን አልባሳት መልበስ ሊያዘወትሩ ይችላሉ፡፡ ጥቂቶችም የሚያስቡት ችግሩን ሰዎች ያዩብኛል ስለሚሉ ዉጭ ከመውጣት ተቆጥበው በቤት ውስጥ ተወስነው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡

በዚህ የስነልቦና ችግር ላይ ጥናት ያደረጉ ሙህራን በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ለህመምተኞች የህመማቸው ምልክቶች በጣም የሚያስጨንቅና የሚያሳዝን ስለሚሆን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ እራስን ስለማጥፋት አስበው እንደሚያውቁና፣ ሌሎች ደግሞ ቀላል የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እንዳካሄዱ ተናግረዋል፡፡ የፕላሲት ቀዶ ጥገናው ክፋቱ ችግሩን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ አለማቻሉ ነው፡፡

🔹በዚህ የስነልቦና ህመም ግለሰቦች ተጠቅተዋል ለማለት የሚከተሉት ሁለት መስፈርቶች ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፦

► ከሚገባው በላይ በአካላቸው ገፅታ ላይ ለሚገኝ ትንሽ ጉድፍ በጣም በመጨናነቅ ወይም በሌለ ችግር በአእምሮቸው ችግሩ እንዳለባቸው በማሰብ የሚብሰለሰሉ ከሆነ።

► የሚበሰለሰሉበት ጉዳይ በሌላ የስነልቦና ችግር ለምሳሌ በአመጋገብ ችግር በሚመጣ የሰውነት መጎሳቆል ምክንያት የማይገለፅ ከሆነ።

source: Psychology Today

@melkam_enase

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ኮሮና ጀግናችንን ነጠቀን!

የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ወንድ ልጃቸው የአዕምሮ እድገት እክል ያለበት መሆኑን ተከትሎ ስለችግሩ በጥልቀት እንዲረዱና ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች መፍትሔ ለማስገኘት በብዙ የደከሙ ሰው ነበሩ።

የኦቲዝም ታማሚ ልጃቸውን ለማሳደግ የተጋፈጡትን ከባድ ሕይወት በአደባባይ በመናገርና ለዘመናት ከህመሙ ጋር ተያይዞ የነበረውን አጉል እምነትና ዝምታ በመስበር ለብዙ ወገኖች ደራሽ እና ፋና ወጊ ነበሩ።

የጆይ ኦትስቲክ ሴንተር መስራችና ስራ አስኪያጅ በነበሩት በወ/ሮ ዘሚ የኑስ ህልፈት የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፡፡

We express our deepest condolences on the death of Mrs. Zemi Yenus, the founder and manager of the Joy Autistic Center.

ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት።
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ ማንም በምንም ሊከፍለው አይችልምና ሁሌም የሚገባትን ክብር እንስጣት።

ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የእናቶች ቀን ተጠቃሽ እመቤት ናቸው። ረጅም እድሜ ለእናታችን ይስጥልን 🙏

መልካም የእናቶች ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ከላይ በለጠፍነው ፅሁፍ ዙሪያ ስለ DID የበለጠ ለመረዳት ይሄን ድረገፅ ይጠቀሙ።
https://www.psychologytoday.com/us/conditions/dissociative-identity-disorder-multiple-personality-disorder

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

መልካምነት ለራስ ነው!

ከወራት በፊት በጅግጅጋ ከተማ አንዲት እናት ልጃቸውን ለማሳከም ብለው ከብቶችን ሽጠው የቋጠሩትን 300 ሺ ብር፤ ጉሌድ የተሰኘ ወጣት በሚያሽከረክረው ባጃጅ ውስጥ ጥለው ይወርዳሉ።

ይህንኑ በድንገት የተመለከተው ወጣቱ እናቲቱን ጠርቶ በታማኝነት ብሩን መመለሱ የቅርብ ትውስታ ነው።

በወቅቱም ከክልሉ ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ሙሀመድ ለመልካም አርአያነቱ ሽልማት አንደሚሰጠው ቃል በተገባለት መሰረት #በዛሬው እለት ዘመናዊ የህዝብ ማመላለሻ ቶዮታ መኪና መረከቡን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ አሳውቋል።

ጥሩና መልካም ሰው መሆን ከሁሉ ይልቃል!

በመልካምነት ትርፍ እንጂ ኪሳራ አይመጣም!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ፡፡

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ሚዛናዊነት!

ሚዛናዊ ህይወት መኖር የስነ ልቦናዊ ጤንነት መኖር መገለጫ ነው፡፡ ስራና ጨዋታን፣ ሳቅንና ለቅሶን፣ ስሜታዊነትንና ምክንያታዊነትን፣ ንፉግነትንና ለጋስነትን ወዘተ… ሚዛናዊ በማድረግ መኖር ጥበብም እንደሆነ ይነገራል፡፡

አርስቶትል የተባለው የግሪክ ፈላስፋ፤ “ጥበብ ያለበት ምርጫ ሁለቱን ተቃራኒ ፅንፎች ትቶ መካከለኛውን መምረጥ ነው” ይላል።

አብርሃም ማስሎውም (Abreham Maslow) ግለሰቦች ከተፃራሪ ፍላጎታቸው አንዱን ከመምረጥ ተቆጥበው ሁለቱን ማስታረቅ ይጠበቅባቸዋል ይላል፡፡

ኪነር (Kinnier) በበኩሉ፤ መካከለኛ መንገድን በመምረጥ ግጭቶቻቸውን የሚፈቱ ሰዎች ፅንፍን ከሚይዙ ሰዎች ይልቅ ደስተኞች ናቸው ይላል፡፡

የሳይኮሎጂ አባት ተብሎ የሚጠቀሰውም ፍሮይድ (Freud) በግል ፍላጎትና በማህበረሰብ ፍላጎት መካከል ከፍተኛ ልዩነት በሚፈጠርበት ጊዜ ሚዛናዊነትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ስነ ልቦናዊ ጤንነት ያላቸው ሰዎች ሚዛናዊ ናቸው፡፡

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

መልካም ጓደኛ!

▸ የጓደኛህን ስሜት ለመራዳት ሞክር፣

▸ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት፣

▸ አበረታታው፣

▸ እንደማይጠቅም አትንገረው፣

▸ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣

▸ ለስኬቱ እንጂ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን፣

▸ መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ታድለሃል። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

🔹''ዙሪያህን አዎንታዊ ነገሮችን በሚያስቡ፣ በሚናገሩ እና በሚያደርጉ እልፎም በሚደግፉህ እና መልካም አስተዋጽዖን በሚያበረክቱልህ ሰዎች ክበበው፡፡ አንተም ለእነሱ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንዳትዘነጋ፡፡''

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በ መአዛ መንክር በኦቲዝም ዙሪያ የተፃፈው 'ሁሉም በአንድ' መፅሀፍ ታትሞ ወጥቷል!

እንድታነቡት ጋበዝናቹ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሶስቱ የስብዕና ማንነት አካላት!

▸ኢድ (id)
▸ኢጎ (Ego)
▸ሱፐር-ኢጎ (Super ego)
⬇️

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ "ከአጓጉል ሀሳብና ጭንቀት ራስህን ጠብቅ!"

ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትንና፣ ሀዘንን ያስከትላል፣

ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ፣

መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር፣

የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ፣

አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄዎች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ፣

ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር።

▸ "ደግነት አይለይህ!"

ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው፣ "ያስከፍላል" ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ እናም ዘወትር ደግ ሁን፣ ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ ሰላማቸው ልክ የለውም።

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጀርመናዊው ፈላስፋ ሄግል ስለጅምላ ንግግር ሲናገር፡- ‹‹ሃሳብ ሁልጊዜ አጠቃሎ ነው፡፡ ማጠቃለያም የማሰብ ንብረት ነው፡፡ ማጠቃለል ማለት ማሰብ ነው›› ይለናል፡፡

አዎ! ስለሰው ያለን ድምዳሜ ሁሉ ስለሰውየው ያለን ዕውቀት ነው፡፡ አጠቃሏችን ከጨለመ ሃሳባችን የጨለመ ነበር ማለት ነው፡፡ ድምዳሜአችን ሁሉ የማሰብ አቅማችንን ይናገራሉ፡፡ ያለምንም በቂ አስረጂዎች አንድን ሰውም ይሁን ተቋም ጨፍልቀን ከደመደምን ጨፍላቂ አዕምሮ ይዘናል ማለት ነው፡፡ ነገሮችን እንደየሁኔታውና እንደአውዱ ቁምነገሩን እየለየን case by case መመርመር ካልቻልን አጠቃሏችን ሁሉ ከኑግ ጋር የተገኘሽ ሰሊጥ አብረሽ ተወቀጭ ይሆናል፡፡

የድምዳሜአችን ምንጭ ሃሳባችን ነው፤ የሃሳባችን ስሩ ደግሞ የምናስብበት መንገድ ነው፡፡ አስተሳሰባችን አተያያችን ነው፡፡ ድብቁ ዓይናችንን ትተን ስጋዊ ዓይናችንን ብቻ ከተጠቀምን የምናየው የላዩን እንጂ የውስጡን አይደለም፡፡ መልክን እንጂ ልብን አንመለከትም፡፡ ፊትን እንጂ አዕምሮን ለማንበብ አቅም እናጣለን፡፡

ወዳጄ ሆይ…… ሰዎችን ከመፈረጅ ይልቅ ለመረዳት ፍጠን! የአስተሳሰባቸውን መንገድ አይተህ የሃሳባቸውን አስኳል አግኝ! የተፈተኑባቸውን የሕይወታቸውን ውጣውረድ መርምረህ የኑሮ ፍልስፍናቸውን እወቅ፡፡ ቀድሞ ከመደምደም ይልቅ መመርመርን እንዲያስቀድም አዕምሮህን አለማምደው!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስነልቦና በፍትህ ስራአት ውስጥ
(forensic psychology)

ይህ የስነልቦና ዘርፍ የስነልቦና ጥናት ውጤቶችን ወደ እውነተኛ የህይወት ልምድ ከምናወርድባቸው የዘርፉ ክፍሎች አንዱ እና በትኩረቱም በፍትህ ስርአቱ ውስጥ የስነልቦና ጥናት ውጤቶችን በመጠቀም የበለጠ ፍትሀዊ እና ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ነው።

🔹የዚህ ዘርፍ ባለሙያዎች የሚከውኖቸው ስራዎች፦

▸ ከሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች መረጃ በመሰብሰብ የወንጀለኛ አጠቃላይ መረጃ (criminal profile) በማዘጋጀት ከተፈፀመው ወንጀል ሁኔታ በመነሳት ለወንጀሉ የቀረቡ ተጠርጣሪዎችን በመለየት ብሎም በምርመራው ላይ አስተዋፅኦ ማበርከት እና የታወቁ ተደጋጋሚ ወንጀለኞች ወደፊት ወንጀል ሊፈፅሙ የሚችሉበትን ሁኔታ በማገናዘብ የመከላከሉን ተግባር ይደግፍሉ።

▸ በፍትህ ስረአቱ ውስጥ በአማካሪነት በማገልገል በህግ ማስፈፀሙ ሂደት ከምርመራው ጀምረው ይሳተፋሉ።

▸ በአሁኑ ሰዓት የዚህ ዘርፍ ባለሙያዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየሰሩበት እና ውጤታማ የሆነው ተግባር ወንጀለኞችን በምክክር አገልግሎት (forensic therapy) በመጠቀም ግለሰቡ ድርጊቱን ከመፈፀሙ እና በሚፈፅም ግዜ የአእምሮ ህመም አለበት ወይስ ጤናማ ነው የሚለውን በማጣራት ችግር ካለባቸው በወንጀሉ እንዳይጠየቁ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ወደ ሚያገኙበት ይመምራት (referral) አገልግሎት ማመቻቸት።

▸ በሌላ በኩልም የወንጀል ፈፃሚወቹ ድርጊት እራስን መከላከል ነው ወይስ ማጥቃት ነው የሚለውን በመለየት የውሳኔ ሀሳብ ለህግ ተርጓሚው ማቅረብ ዋነኞቹ ናቸው።

Source: Psychology Today

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አጠቃላይ የአእምሮ ህመም ምልክቶች
(Symptoms of Mental Illness)

▸ በእለት ተለት እንቅስቃሴያችን በሚያጋጥሙን ምክንያቶች ልንናደድ ወይም ልንጨነቅ እንችላለን። ነገር ግን ምንም ምክንያት ሳይኖረን የምንጨነቅ፣ የምንረበሽ እና ከልክ ያለፈ ፍርሃት የሚሰማን ከሆነ

▸ ምክኒያቱ ያልተረዳነው ጭንቀት እና መረበሽ በስራችን፣ በትምህርታችን፣ በውጤታማነታችን እና በማህበራዊ ግንኙነታችን ላይ ተፅእኖ ካመጣ

▸ የመረበሽ እና የመጨነቅ ስሜቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየ

▸ በዙሪያችን ያሉ የቅርብ ቤተሰቦች፣ ጓደኛ እና የትዳር አጋር የምናሳየውን አዲስ ስሜት አይተው ሁኔታህ ጥሩ አይመስልም ምንሆነሃል/ሻል ብለው እስኪጠይቁ የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ከደረስን

▸ የሚሰማዎት ጭንቀት ከልክ በላይ ሆኖ እርሱን ለመርሳት የአልኮል መጠጥ እና የእንቅልፍ መድሃኒቶችን መፈለግ ከጀመሩ

▸ ከሚሰማዎት ጭንቀት ብዛት "አሁንስ ብሞት ይሻላል" የሚል ሀሳብ ከጀማመሮት እና

▸ ያልተለመደ ሃሳብ ማለትም ሰዎችን መጠራጠር እና ያልተለመዱ ድምፆችን መስማት ከጀመሩ

🔹ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩ በግዜ የአእምሮ ሀኪም ጋር በመሄድ የንግግር ወይም የመድሃኒት ህክምና ያግኙ።

በመአዛ መንክር(ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

#May Is Mental Health Month

የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ለማስፋፋት ይህንን ፅሁፍ #Share ያድርጉ።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዘሚ የኑስ- የኦቲዝሟ ''አምባሳደር'' ከተናገሩት!

''አያገባኝም ማለት ነው የሚያጠፋን....
'ማን ሊመጣልን ነው?' ብሎ ማሰብና መስራት ነው የሚያዋጣን። 'ማንስ ባይመጣልን ያቅተናል ወይ? እኛ እንበቃለን' ማለት መቻል አለብን።''

ነፍስ ይማር!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

እንዳትወድቅ እንዳትወድቂ ሚዛን ጠብቅ ጠብቂ!

የመጀመሪያውና ቅድሚያ መስጠት ያለብን ነገር የህይወት ሚዛናችንን መጠበቅ ነው፡፡ ኃይል የሚጠይቁንን እያንዳንዳቸውን የህይወታችንን ገጽታዎች በመመርመር ማመዛዘን አለብን፡፡ በዚህም ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ሃይል እንዲያገኙ ማድረግ እንችላለን፡፡

እንደ አባት ወይም እንደ እናት፣ እንደሚስት ወይም እንደባል፣ እንደሴት ልጅ ወይንም እንደ ወንድ ልጅ፣ እንደ ሰራተኛ፣ እንደአመራር፣ እንደተሳታፊ ወዘተረፈ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችለንን ሚዛን መጠበቅ አለብን። ሀይላችን ሳይዛባ ህይወታችን ማስቀጠል የምንችለውም እነዚህ እያንዳንዳቸው የሚፈልጉትን ኃይል በሚዛናዊነት ማከፋፈል ስንችል ብቻ ነው፡፡

ይህ ግን በራሱ ጊዜ የሚሆን አይደለም፡፡ የህይወት ሚዛንን መጠበቅ እያንዳንዳችን በእያንዳንዷ ሴኮንድ የምንወስነው የህይወት ምርጫ ውጤት ነው፡፡ ወይ ዝም ብለን ለመኖር አለበለዚያም ደግሞ እያንዳንዷን ደቂቃ ለህይወታችን ትርጉም ያላት ማድረግ የእኛ ምርጫ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ከእኛ ውጪ ማንም ሊያደርግልን እንደማይችል መረዳት አለብን፡፡

ማንም ለማንም አይኖርም፤ አይተነፍስም፣ አይወድም ወይም አይሞትም፡፡ ለእኛ በውስጣችን ያለን እኛው ብቻ ነን፡፡ ስንፈጠር ወንድ ወይም ሴት ከመሆን የዘለለ ስለእኛነታችን ትርጉም ያለው የአፈጣጠር ካርታም የለንም፡፡

ማን እንደሆንን፣ ምን አይነት መሆን እንዳለብን መወሰን የእኛ ድርሻ ብቻ ነው፡፡ የህይወታችንን ልዩ ልዩ ገጽታዎች ሚዛን ማስጠበቅ የእኛ ብቻ ድርሻ ነው፡፡ ይህንንም በህይወታችን መንገድ ሁሉ በምንወስናቸው ውሳኔዎች እንተገብራለን፡፡

ከ አሸናፊነት መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ...

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

''ወዳጄ የህይወት ፈተናን ተጋፈጠው፤ የምትፈልገውን ሁሉ ሞክር ከተሳካ ተሳካ፤ ካልተሳካ አንድ የማይሳካበትን መንገድ ትማራለህ።''

"የሰው ልጆ ከፈለገ ታምረኛ ካልፈለገ ሰበበኛ ነው።"

''አሸናፊዎች ሰዎች ተሸናፊ ሰዎች ማድረግ የማይፈልጉትን የማድረግ ልማድ አላቸው።''

''ትልቁን ህልምህን ስትፅፈው፤ በየቀኑ ደጋግመህ በማንበብ እንደምታሳካው በልብህ ስታምነው፤ መከፈል ያለበትን መስዋትነት ያለ ምንም ድርድር በመክፈል፤ ህልምህን በእርግጠኝነት ታሳካለህ።''

(ዳዊት ድሪምስ)

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የተከፋፈለ ማንነት መኖር ችግር (Dissociative identity disorder)

የተከፋፈለ ማንነት መኖር (DID) የስነ-ልቦና ችግር ሲሆን የአንድ ሰው ማንነት መለያ ወደ ተለያዩ ሁለት እና ከዛበላይ የስብዕና አይነት ሲከፋፈል እና እነዚህ የተለያዩ ማንነቶች እየተቀያየሩ ግለሰቡን ሲቆጣጠሩ የሚፈጠር የስነ-ልቦና ችግር ወይም የግለሰቡ የማንነት፣ ትውስታ እና የንቁነት መገለጫዎች የማቀናጀት እና በተለያየ አቅጣጫ የተዋቀረ አንድ ማንነት ያለመኖር ችግር ነው። በዚህ ችግር የሚጠቁ ሰዎች ዋናው ማንነት የግለሰቡን ከቤተሰብ የተሰጠ ስም የሚይዝ ቢሆንም በአብዛኛው በራሱ ምንም የማያደርግ፣ ጥገኛ፣ በድብርት እና የወንጀለኝነት ስሜት ይጠቃል።

ሌላኛው ማንነት ሰውየውን በሚቆጣጠር ግዜ ይሄው ክፍል የራሱ የተለየ ታሪክ፣ የራስ ምልከታ እና ማንነት ሊኖረው ሲችል በተጨማሪም የቃላት ምርጫ፣ ስምን ጨምሮ የሚገልፀው ፆታ፣ እድሜ፣ ጠቅላላ እውቀት እና አጠቃላይ ፀባይ ከዋናው ጋር የሚለያይ ሲሆን እነዚህ ለውጦች የሚመጡት ያለምንም የህክምና ሁኔታ እና ዕፅ መውሰድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

► የችግሩ ምክኒያት በህፃንነት የሚያጋጥም መጥፎ ሁኔታ (ጥቃት፣ በደል፣ አደጋ) ከዚህ የስነ-ልቦና ችግር ጋር ይያያዛል።

🔹ህክምና (therapy)

የዚህ ችግር ብቸኛ መፍትሄ የስነ-ልቦና የምክክር አገልግሎት ሲሆን አላማውን በግለሰቡ አስቸጋሪ እና ህመም የሚፈጥሩ ትዝታዎቹን እንዲገልፅ መርዳት፣ ችገሮችን የመቋቋም እና የህይወት ብቃት እንዲያሳድግ መርዳት፣ የመፈፀም አቅሙ እንዲመለስ እና የተሻሻለ ግንኙነት ኢንዲኖረው መርዳት ላይ በማተኮር እንደችግሩ ሁኔታ የሚስማማ የምክክር ስልት በመከተል የሰውየውን ማንነቶች በማገናኘት ወደ አንድ እንዲዋሃድ መርዳት ይቻላል።

Source: psychology today

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

የምትናገረው ነገር ከሌለህ ምንም ነገር አትናገር!

አንደበት የአእምሮ መስታወት ነው፡፡ ግልፅ ሃሳቦች ግልፅ ዓረፍተ ነገሮችን ይተፋሉ፡፡ የተድበሰበሱ አስተሳሰቦችም ግልፅ ያልሆነ ንግግርን ያፈልቃሉ፡፡ ችግሩ በብዙ ነገሮች ላይ ግልፅ ሃሳቦች የሉንም፡፡

አለም ውስብስብ ናትና አንዱን ነገሯን እንኳን ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ብዙ የአእምሮ ጥረት ይፈልጋል፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ እስክትደርስ ድረስ ዝም ብለህ ብትሰማ ጥሩ ነው፡፡

ማርክ ትዌይን እንዲህ ይላል፡- "የምትናገረው ነገር ከሌለህ ምንም ነገር አትናገር፡፡"

ምንጭ፦ ስለምታስበው አስብ መጽሐፍ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስሜታዊነት Vs ምክንያታዊነት

ስሜታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት የሚሰጥ ድንገተኛ ምላሽ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ምላሽ ውጤት ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ በተቃራኒው ምክንያታዊነት ማለት ለአንድ ገጠመኝ ወይም ክስተት በቂ ጊዜ ወስዶ፣ ውጤቱን አውጥቶና አውርዶ ውጤቱን ከጅማሬ አይቶ ምላሽ መስጠት ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ ስታስብ መነሻህ ስሜታዊነት ይሁን ወይስ አእምሮህ ያሰበበትና አጥጋቢ ምክንያት ያለው ተግባር ለይተህ የማወቅን ልምምድ አዳብር፡፡ ይህንን መለማመድ ዘወትር በስሜት እየተነዳህ ውሳኔና እርምጃ ውስጥ ከመግባትና ውጤቱ አፍራሽ ከሆነ ሁኔታ ይጠብቅሃል፡፡

በየእለት የሰው ለሰው ግንኙነት መካከል በሚነሱ ነገሮች ሁሉ የሚፈነዱና ቁጣ ቁጣ የሚላቸው ሰዎች፣ በትዳርና በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ በስሜት በተናገሩት ንግግር ከተቆሳሰሉ በኋላ ለመወያየት የሚሞክሩ ሰዎች፣ በማሕበራዊውና በሃገር ደረጃ አንድን ነገር ገና ከመስማታቸው ስለሁኔታው በሚገባ ሳያጠኑና የምክንያታዊነት ሂደት ሳይከተሉ ለጥፋት የሚነሳሱ ሰዎች ምክንያታዊ ሳይሆኑ ስሜታዊ ሰዎች ናቸው፡፡

አንዲት ደቂቃ በመታገስ የእለቱን የጋለ ስሜት ማሳለፍ ሲችሉ የመጣላቸውን የስሜት ንዝረት በማስተናገድ የሌላውንና የራሳቸውን ታሪክ ያበላሹ ሰዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡

ስሜታዊነት አርቆ ማሰብ ያለመቻል ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የተስፋ መቁረጥ ምልክት ነው፡፡ ስሜታዊነት የመሸነፍና አቅም የማጣት ምልክት ነው፡፡

ምክንያታዊነት የበሳሎች መንገድ ነው፡፡ ምክንያታዊነት የአዋቂዎች ምርጫ ነው፡፡ ምክንያታዊነት ሚዛናዊ በራስ የመተማመን ደረጃ የደረሱና ከፍ ያሉ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡

ምክኒያታዊ እንሁን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አልበርት ባንዱራ የተባለ ሳይኮሎጂስት እንደሚለው ሰዎች በተለይም ሕጻናት የሚማሩት በማየት ነው። በዚህም አንድን ነገር የሆነ አርአያዬ ወይም ሞዴሌ ነው ብለው የሚያስቡት ሰው ሲያደርገው በትኩረት ካዩ በኋላ ራሳቸው እንደገና ይሞክሩታል ከዚያም አዳብረውት የራሳቸው ባህርይ ያደርጉታል። ይህንንም ለማረጋገጥ በርካታ ምርምሮችን አድርጎ ተቀባይነትን አግኝቷል።

እርሱ እንደሚለው ማንኛውንም ትምህርት፣ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ሌሎችን ወይም አካባቢያችንን በማየት መማር እንችላለን። በዚህም ያየነውን አስመስለን ወይም በራሳችን ልክ አስተካክለን የተማርነውን ነገር ወደ ተግባር እንቀይረዋለን።

ታዲያ ከእርሱ በኋላ የመጡ ምሁራን ሀሳቡን የደገፉት ቢሆንም እንከን አላጡለትም። ይኸውም የሰው ልጅ ባህርይ እጅግ የረቀቀና ውስብስብ እንዲሁም በጣም ብዙ ምርምር የሚጠይቅ በመሆኑ በቀላሉ እንዲህ መግለጽ አይቻልም ይላሉ። ሁሉንም ባህርይ ሌሎችን በማየት የምንማር ከሆነ ሰዎች አሉታዊ ነገሮችን በማየት ተምረው እነሱም አሉታዊ ነገሮችን ያደርጋሉ። ለምሳሌም ድብድብ የበዛበትን ፊልም እያየ ያደገ ልጅ እርሱም ተደባዳቢ የመሆን እድሉ የሰፋ ነው። ነገር ግን ይላሉ ተቺዎቹ፣ ይህንን ሁሉም ሰዎች አያደርጉም። እንደየሰዉ ፍላጎትና ተፈጥሮ ወይም ስብዕና ይለያያል።

🔹ወደ እውነተኛ ሕይወት ስንመጣም ብዙ ሰዎች የሌሎችን ሰዎች በማየት ለማስመሰልና የነሱን ሕይወት በቀጥታ ለመኖር ሲጥሩ እናያለን። ነገር ግን ሁሉም ሰው አንድ አይነት አይደለምና ይወድቃሉ ወይም አይሳካላቸውም። ምክንያቱም ሕይወት ለሁሉም አንድ አይነት ጥያቄ የላትምና።

Source: From Personality Psychology books

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ሌሎችን መውደድ!

ስነልቦናዊ ጤንነት ያላቸው ሰዎች ሌሎችን ይወዳሉ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስም “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ነው የሚለው።

ሰው ራሱን ወድዶ ሌሎችን የማይወድ ከሆነ፣ የስነ ልቦና ጤንነቱ የተሟላ አይደለም፡፡

ስነልቦናዊ ጤንነት ያላቸው ሰዎች፤ ለሌሎች ሰዎችና ለሰው ልጅ በአጠቃላይ ደህንነት (welfare) ለመጠንቀቅ አቅምና ፍላጎት አላቸው፡፡

ባርባራ ስትሪሳንድ (Barbara Streisand) “ሰዎችን የሚፈልጉ ሰዎች በዓለም ላይ በጣም ጤናማ ሰዎች ናቸው” ይላሉ።

የአእምሮ ጤንነት ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች፤ በቤተሰብና በማህበረሰብ የመውደድ አቅም መኖር እንዲሁም ሌላውን ሰው መቅረብ፣ የስነ ልቦና ጤንነት ቅድመ ሁኔታ ነው ብለው ያምናሉ።

እርስ በርሳችን እንደጋገፍ፣ እንዋደድ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሶስቱ የስብዕና ማንነት አካላት!

በታዋቂው ሲግመንድ ፍሩድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ The Psychoanalytic Theory መሰረት የሰዎች ስብዕና ውስብስብ እና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች ነው፡፡

እነዚህ ሶስቱ የስብዕና ወይንም የማንነት አካላት ኢድ (id)፣ ኢጎ (Ego) እና ሱፐር-ኢጎ (Super ego) ተብለው ሲጠሩ ውስብስብ የሆነውን የሰዎች ባህሪ ለመፍጠር አብረው ይሰራሉ፡፡ ሶስቱም የስብዕና አካላት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡

በፍሩድ ጽንሰ-ሀሳብ መሰረት የስብዕናዎ የተወሰኑ ክፍሎች በመሰረታዊ ፍላጎቶችዎ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት ሲያደርጉ ሌሎች የስብዕናዎ ክፍሎች ደግሞ እነዚህን ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ለመግታት እና ከእውነተኛ ፍላጎቶችዎ ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ይጥራሉ።

እያንዳንዳቸው እንዴት በተናጥል እንደሚሠሩ እና እንዴት እንደሚነጋገሩ እንመልከት፡፡

1.ኢድ (id)

ከተወለደንበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ብቸኛው የስብዕናችን አካል ሲሆን፡፡ ይህ የስብዕናችን አካል ሙሉ ለሙሉ የማይታወቅ እና በደመ ነፍስ የሚመራ ባህሪያትን አካቷል፡፡ ኢድ (id) ሁሉንም ፍላጎቶች ወዲያውኑ ለማሟላት ከሚሠራው የሰውነት የመደሰት መርህ የሚመነጭ ነው፡፡ እነዚህ ፍላጎቶች ወዲያውኑ ካልተሟሉ የስብዕና ውጥረት ይፈጠራል፡፡

ለምሳሌ፦ የረሀብ ወይም የጥማት ፍላጎት ለመብላት ወይም ለመጠጣት አፋጣኝ ሙከራን እንድናደረግ ይገፋፋናል ነገር ግን እነዚህን ፍላጎቶች ወዲያውኑ ማሟላት ሁልጊዜ ተጨባጭ እና የሚቻል አይደለም፡፡ ይህ የሰውነት የመደሰት መርህ በሙሉ የሚገዛን ከሆነ፣ ሁልጊዜ የራሳችንን ፍላጎቶች ለማርካት ስንኖር አንገኛለን፡፡

እንደ ፍሩድ ገለፃ ኢድ (id) የሚፈልገውን ፍላጎትን ለማርካት የአእምሮ ምስል በመፍጠርና የመጀመሪያ ደረጃ (ስጋዊ) ስሜትን በመጠቀም የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት ይሞክራል፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ውሎ አድሮ የኢድን (id) ደመ-ነፍሳዊ ፍላጎት መቆጣጠርን ቢማሩም፣ ይህ የባህሪይ አካል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ተመሳሳይ ሆኖ ይኖራል፡፡

2.ኢጎ (Ego)

ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ከእውነታው ወይም ከገሀዱ አለም ጋር ለመገናኘት የሚየግዘን የስብዕና ክፍል ሲሆን እንደ ፍሩድ ገለጻ ኢጎ (Ego) ከ ኢድ (id) የሚዳብር ሲሆን የኢድ (id) ግፊቶች በእውነተኛው ዓለም ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲገለፁ ያደርጋል፡፡

ኢጎ የሚሠራው በእውነተኛው መርህ ላይ በመመርኮዝ ነው። ስለዚህ የኢድ (id) ፍላጎቶችን በተጨባጭና በማህበራዊ እይታ ተገቢው በሆነ መንገድ ለማርካት ይጥራል፡፡

ለምሳሌ፦ በሥራ ቦታ ረዥም ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ቆዩ እንበል፡፡ ስብሰባው እየቀጠለ ሲሄድ ረሀብዎ እየጨመረ ሲሄድ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ኢድ (id) ከመቀመጫዎ ላይ እንዲወጡ እና ለምግብ እንዲወጡ ሲገፋፋዎት ኢጎ (Ego) በጸጥታ ስብሰባው እስኪያበቃ ድረስ እንዲቀመጡ በተቃራኒው ይገፋፋዎታል፡፡

3.ሱፐር-ኢጎ (Super ego)

የመጨረሻው የሰዎች ስብዕና ክፍል ሱፐር-ኢጎ (Superego) ነው። ሱፐር-ኢጎ (Superego) ከወላጆችና ከማህበረሰብ የምናገኛቸው በውስጣችን የተቀመጡ የሥነ-ምግባር መርህና አመለካከቶችን የሚይዝ የስብዕና ክፍል ሲሆን፡፡ ሱፐር-ኢጎ ውሳኔና መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡ ሱፐር-ኢጎ (Super ego) ባህርያችንን ፍጹም እና ስልጡን ለማሳደግ ይሠራል።

🔹እንደ ፍሩድ ገለጻ ለጤነኛ ስብዕና ቁልፍ የሆነው ነገር በ ኢድ (id)፣ ኢጎ (Ego) እና ሱፐር-ኢጎ (Super ego) መካከል ያለው ሚዛናዊ መስተጋብር ነው፡፡

Source:- Best reference theories of personality (ryckman 9th ed)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስኤ አትሁን!

►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ፣

►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣

►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣

►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣

►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣

ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።

ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋር ሁን፣ አስተውል።

ፈጣሪ ለምድራችን ሰላሙን ይመልስልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ደግነት በቃላት ሲገለጽ ልበ ሙሉነትን ያመጣል!

ደግነት በኃሳብ ሲሆን የስብዕና ጥልቀት ይፈጥራል፡፡

ደግነት በመስጠት ሲሆን ፍቅር ከውስጡ ያብባል፡፡

#ቢኒ ዝና ለማግኘት፣ ትርፍ ለማግኘት አልያም ሰው እንዲያደንቀው ሰው እንዲያወራለት የሚሰራ ሰው አይደለም። እንደ ቢኒ በጎ መሆን መታደል ነው! ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ!

አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና በመሰብሰብ የላቀ ሰብዓዊነት ያለው #መቄዶንያ ‹‹ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው›› የሚል መርህ አንግቦ ዓመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ዓመታትም በርካታ አረጋውያንንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና ሕይወት መታደግ ችሎአል።

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel