melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ጤናዎ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው!

ዶ/ር ደረጀ አሰፋ በላንሴት የሚገኝ እና እርስዎን ለማማከርና ለመርዳት ሁል ጊዜም ዝግጁ የሆነ የስነ-አእምሮ ስፔሻሊስት ሐኪም ነው። ይጎብኙን!

Dr. Dereje Assefa is an excellent consultant psychiatrist who is available at Lancet and always ready to help you take care of your mental health. Visit us!

የስራ ሰዓት: ሰኞ፣ ረቡዕ እና ዓርብ 4:00 ሰዓት
ቅዳሜ 8:00 ሰዓት

አድራሻ: መገናኛ አደባባይ አፈራንሲስ ህንፃ

📞 0977717171

(Lancet General Hospital)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዲፕረሽን ወንዶች ላይ!

የዲፕረሽን ምልክቶች በሴቶችም በወንዶችም ላይ ተመሳሳይ ይሁኑ እንጂ መገለጫዎቹ ይለያያሉ፡፡ የልዩነቱ መንስኤ አስተዳደግ ላይ "ወንድ አይደለህ ቆፍጠን በል!" የመሳሰሉት አባባሎች ስነ ልቦና ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ወይም ተፈጥሯዊ ልዩነት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ምክኒያት ዲፕረሽን ወንዶች ላይ ሲከሰት በቀላሉ ለመለየት ከማስቸገሩም በላይ የሀፍረት ስሜት ተከትሎት ከመጣ ጥሩ ያልሆኑ ውጤቶች ያስከትላል፡፡

በዲፕረሽን ላይ ሀፍረት ተጨምሮ ሲመጣ ከሰዎች መገለል፣ ስሜትን አውጥቶ ለመናገር አለመቻል (ለቅርብ ሰዎች እንኳ) እንዲሁም የህክምና እርዳታ አለማግኘትን ያስከትላል፡፡ እንዲሁም በዲፕረሽን ምክኒያት የሚመጣውን መከፋት ለመሸፋፈን ወይም ለመቋቋም አልኮልና እና ሌሎች ሱስ አምጪ ነገሮችን አብዝቶ መጠቀም፣ ቁማር አብዝቶ መጫወት፣ ህይወትን ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ማሽከርከር፣ ብስጩ መሆንና በቀላል ነገሮች መናደድ ያስከትላል፡፡ በተለይ ብስጩ መሆን ለቤተሰብ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡

የሚወዱትን ሰው ያጡ አንዳንድ ወንዶች 'ጠንከር እንዲሉ' እና ሀዘናቸውን እንዳይገልፁ የሚደረገው ክልከላ እርማቸውን እንዳያወጡና የተወሳሰበ ሀዘን (Complicated grief) ውስጥ እንዲገቡ ሲያደርጋቸው ያጋጥማል፡፡

አብዛኛው ዲፕረሽን ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚታከም በመሆኑ ጥሩ ስሜት ካልተሰማ ወይም የፀባይ ለውጦች ካሉ ከአእምሮ ሀኪም ወይም ከስነ ልቦና ባለሞያ ጋር በመነጋገር መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡ የአእምሮ ህመም ፆታ፣ ብሄር፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለይ ሁላችንም ላይ ሊከሰት የሚችል፤ ውጤታማ ህክምና ያለው ህመም ነው፡፡

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#አለኝታ

6388 አለኝታ ነጻ የስልክ መስመር ላይ ይደውሉና #ስነልቦናዊ ድጋፍና ሪፈራል ከበቂ ባለሙያዎች ያግኙ።

ጾታዊ ጥቃት ይቁም!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

“ስለ አዕምሮ ጤና በግልፅ መነጋገር ለሁላችንም ጤንነት ነው” - ዶ/ር ያዕቆብ ተክዔ

ያዕቆብ ተክዔ (ዶ/ር) በአሜሪካው ፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ባለሙያ ነው። ያዕቆብ በትምህርቱ ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት፣ በሥራው ቴራፒስትና የሙሉ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነው።

ያዕቆብ ተውልዶ ያደገው በኤርትራ ሲሆን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን ለመከታተል ከበቃበት ጊዜ አንስቶ የሥራ ዓለሙን እስኪቀላቀል ድረስ ኑሮው በአሜሪካ ነው።

የያዕቆብ ሥራ የሚያተኩረው በስደተኞች ላይ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከአፍሪካ፣ ከባድ አደጋ፣ የፆታ ወይም የወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን አስፈላጊውን የአዕምሮ ጤና ድጋፍ እና ክትትል ያደርግላቸዋል።

ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዳያገኙ የሚከለክሏቸው በማህበረሰባችን ሊገጥሟቸው የሚችለውን መገለል በመፍራት እንደሆነም ያስረዳል።

"ለብዙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና መሰናከል ቋሚ ችግር ይመስላቸዋል ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ሰው በተለያየ ምክንያት የአዕምሮ ጤናው ሊስተጓጎል ይችላል" በማለት ያብራራል።

የአዕምሮ ጤና መጓደል ቋሚ አይደለም የሚለው ያዕቆብ፣ "አካላዊ በሽታ ሲገጥመን ሆስፒታል/ክሊኒክ ሄደን እንደምንታከመው ሁሉ ለአዕምሯችንም ተመሳሳይ እንክብካቤ ማድረጋችን ተገቢ ነው" ሲል ይመክራል።

(ከ BBC Amharic ጋር ከነበረው ቆይታ የተወሰደ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሬናሰንት የአእምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ጀምሮል!

ሬነሰንት (Renascent) ማለት በሙሉ አቅም እንገደና መነሳት ማለት ነው።

ሬነሰንት በሀገራችን ብቸኛው የሱስ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት (Addiction Psychiatrist) ከሆኑት ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ በተጨማሪ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስቶችና የምክክር የስነ ልቦና ባለሞያዎች ይሰራሉ።

በሬናሰንት የአእምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶች፦

- የሱስ የስነ ልቦና ህክምና (Addiction counseling)
- የሱስ ተኝቶ ህክምና (In-patient detoxification)
- የጭንቀት ህመሞች፣ የድብርት ህመሞች፣ የእንቅልፍ ችግር ህክምና
- ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ህክምና
- የህፃናት የአእምሮ ህክምና ይሰጣሉ።

አድራሻ: ለገጣፎ
ስልክ: 0941776060

#Mentalwellness

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#የማለዳድምፅ

እንደ ጤና ጣፋጭ፣ እንደ ፍቅር ማዕረግ፣ እንደ ይቅርታ ድል፣ እሰው ፊት እንደ መቆም ደግሞ መራራ የለም።

#ልብ_በል!

ለመፍረድ አቅም ያገኘኸው ለማፍቀር ጉልበት ስላጣህ ነው። ሌሎችን መጥቀም ትልቅነት ነው፤ ካልሆነልህ ግን አለመጉዳትም ጨዋነት ነው።

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአልኮል መጠጥ ሱስ እና የትኩረት ማጣት!

የአልኮል መጠጦችን ማዘውተር በጭንቅላታችን ውስጥ የሚገኝንና ለነገሮች ትኩረት እንድንሰጥ የሚያደርግን ኬሚካል እንደሚያቋርጥ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

በቴክሳስ ጤና ሳይንስ ማእከል የሚገኙ ተመራማሪዎች አልኮል ተጠቃሚዎች እንዴት የትኩረት ማጣት ችግር እንደሚጋጥማቸው የተለያዩ ጥናቶችን ሲደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚህም ጠጪዎች የሚያጋጥማቸው የትኩረት ማጣት ችግር ለሰው ልጆች በነገሮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው norepinephrine የተሰኘ ኬሚካል በአልኮል ምክንያት ባለመመንጨቱ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በማእከሉ ሀኪም የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር Martin Paukert ሰዎች በነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ ስንፈልግ ወይም ከወንበራችን ተነስተን ንቁ ለመሆን ስናስብ ጭንቅላታችን አነቃቂውን ኬሚካል ይረጫል፡፡ ታዲያ በአልኮል ሱስ የተጠመድን ከሆነ ትኩረት ለማድረግ መፈለጋችንን ጭንቅላታችን እንዳይረዳው ያደርገዋል፡፡

በዚህም ምክንያት norepinephrine የተባለው ኬሚካል ስለማይመነጭ ከፍተኛ የሆነ የትኩረት ማጣት ችግር ይገጥመናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዚህ ዘገባ ሙሉ መረጃም ታህሳስ 2፣ 2020 በ Nature Communications ታትሞ የወጣ ነው።

Source: https://www.sciencedaily.com/releases/2020/12/201202085222.htm

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሐሴት የሳይኮቴራፒ እና ስልጠና ማዕከል
(Hasset Psychotherapy and Training Center)

ማዕከሉ እውቅና በተረጋገጠላቸው የስነልቦና ባለሙያዎች የማማከርና የተለያዩ የስነልቦና አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካካል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦

• የትዳርና የቤተሰብ ችግሮችን
• ውጥረት
• ጭንቀት
• ድባቴ
• ሌሎች ስነልቦናዊ ጫናዎችን የስነልቦና ድጋፍ
• የህይወት ክህሎትን የሚያሻሽሉ ስልጠናዎች።

ለተጨማሪ መረጃ፡ 0115622550/ 0938591131 ወይም በ hasetpsychotherapycenter@gmail.com ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ: ደምበል ሲቲ ሴንተር 12ተኛ ፎቅ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ!

የጌርጌሴኖን የአዕምሮ መርጃ ማህበር ከተመሰረተ አስራ አምስት አመት የሞላው ሲሆን እስካሁን ከአንድ ሺ (1000) በላይ የአዕምሮ ህሙማንን አስተናግዷል። በመቶዎች የሚሆኑት ከህመማቸው ድነው ሌሎችን እየረዱ ይገኛሉ።

ማህበሩ እስካሁን ሲጠቀምበት የቆየው 1000 ካሜ. የማይሞላ የኪራይ ቤት ሲሆን አሁን ላይ ወደ 450 ህሙማን አገልግሎት እያገኙ ይገኛሉ።

ሰኔ 5/2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለማህበሩ የ3000 ካሜ. መሬት አስረክቧል።

6860 ላይ Ok ብለው በመላክ ማህበሩን መደገፍ ይችላሉ።

#GergesenonEthiopia

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጀምሮ መጨረስ!

ሕይወት ጀምሮ የመጨረስ ሂደት ነች፡፡ የዚህች ሕይወት ጥራትና ስኬት የሚለካው ደግሞ በየጊዜው ጀምረን በብቃት በምንጨርሳቸው ነገሮች ነው፡፡ በትምህርት ዓለም፣ በፍቅርና በቤተሰብ ዓለም፣ በስራው ዓለምና በአጠቃላይ በራእያችንና በግቦቻችን ሂደት ውስጥ አንድን ነገር የመጀመር፣ የመቀጠልና በብቃት መጨረስ ያስፈልጋል።

“የዚጋርኒክ ተጽእኖ” (The "Zeigarnik Effect") በመባል በሚታወቀው የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሃሳብ መሰረት ያጠናቀካቸውን ስራዎች ከማስታወስህ ይልቅ ያላጠናቀካቸውን ስራ የማስታወስህ እድል እጅጉን የጎላ ነው፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1927 በተደረው ጥናት ብሉማ ዚጋርኒክ (Bluma Zeigarnik) የተሰኘው ሩሲያዊው የስነ-ልቦና ሊቅ የተወሰኑ ለጥናቱ የተዘጋጁ ሰዎችን አንድን ተግባር እንዲያከናውኑ ጠየቃቸው፡፡ ስራውን በመስራት ሂደት ላይ እያሉ በድንገት ስራውን ከማጠናቀቃቸው በፊት አቋረጣቸው፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ በዚያን ጊዜ ተሰጥቷቸው ስለነበረ ስራ ሲጠየቁ በስራው ሂደት ወቅት ለማጠናቀቅ ከቻሉት የስራው አካል ይልቅ ያላጠናቀቁትን ነበር ያስታወሱት፡፡

በጥናቶች እንደሚታወቀው አንጎላችን አንድን የተጀመረን ስራ ለመጨረስ የሚያበቃው ኃይል አለው፡፡ አንድን ተግባር ካላጠናቀቀ እዚያው ያልተጠናቀቀው ስራ ላይ የመቆም ባህሪይም አለው፡፡ አንድ መጠናቀቅ የነበረበት ስራ እንዳልተጠናቀቀ የሚያስታውሱን አእምሯችንን የሚያውኩ ሃሳቦች ብቅ እያሉ ገና መጠናቀቅ ያለባቸውን ስራዎች ያስታውሱናል፡፡

ስለዚህ፣ ውጣና ለአንድ ለጀመርከው ነገር ፍጻሜን ፍጠርለት፡፡ የጀመርከውን ጨርስ!

(“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው አዲሱ የ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተቀነጨበ...)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

Albert Einstein “ከትናንትና ተማር፣ ለዛሬ ኑር፣ ለነገው ደግሞ ተስፋ አድርግ” ይለናል

እውነት ነው በህይወት ውስጥ ፈተና ከበዛብህ አትዘን፣ ተስፋ አትቁረጥ፣ ታገስ። ምክንያቱም የህይወት ፈተና አንተነትህ ውስጥ ያለውን ዉበት፣ አቅም፣ ችሎታ የሚያወጣ ነውና። የጨረቃ ውበት የሚጨምረው፤ ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር እንደሆነ አትዘንጋ።

ገንዘብ ቢተጣጠፍ ወይ ቢጨማደድ ዋጋው አይቀንስም፤ እኛም በከባድ ፈተና ብንወድቅ ህይወት አሰልቺና ትርጉም አልባ ብትሆን እንኳን ዋጋችን መቼም አይቀንስም። እንደውም ወርቅ በእሳት ተፈትኖ አንፀባርቆ እንደሚወጣው ያንን ከባድ ጊዜ ስናልፍ ወርቅ የሆነ ስብዕና እንደሚኖረን መርሳት የለብንም!

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስነ-ልቦና በማምረቻ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት (Industrial - Organaizetional Psychology)

ይህ የስነ-ልቦና ዘርፍ ትኩረቱን በስራ ቦታ ምርታማነትን በመጨመር ብሎም ከዚህ ጋር በተያያዙ በሰዎች የአካል እና አእምሮ ጤናማነት ላይ በማተኮር በስነ-ልቦና ጥናት የተረጋገጡ ሀሳቦች እና መመረያዎችን በተቋማት ላይ ለመተግበር የሚሰራ የስነ-ልቦና ክፍል ነው።

በዚህ መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ሰፊ እና የተለያዩ ተግባራትን የሚፈፅሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል የሰራተኞችን አመለካከት እና ባህሪ ማጥናት፣ ተቋማቱን መገምገም፣ የአመራር ስልጠና መስጠት እና የመሳሰሉ ተግባራትን ይፈፅማሉ።

🔹የዚህ ዘርፍ አጠቃላይ ግብም በስራ ቦታ የሰዎችን ባህሪ ማጥናት እና መረዳት ነው።

Source: Psychology Today

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

“The cave you fear to enter holds the treasure you seek.” – Joseph Campbell

የምንፈራው ነገር ብዙ ጊዜ የምንመኘውና የሚበጀንን ነገር ነው። ሰዎች ከእውነተኛ ፍላጎታችን የመሸሽ ባህሪ አለን። በምክንያቶች እራሳችንን እያታለንን፤ ሊነቃ የሚታገለውን ድብቅ ምኞታችንን መልሰን እናስተኛዋለን። እንደው በየእለት ኑሮዋችን፤ የምንሸሸውንና የምንፈራውን ነገር እናስተውል....ብዙን ጊዜ በድብቅ የምንመኘው ነገር ነው፤ ወይ እንደማንችለው ስለምናስብ አልያም ለእኛ የሚገባን ስለማይመስለን።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው....ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀርም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚሉት። ፍርሃታችንን....እንከተለው፤ የፍርሃት ዱካ እውነትኛ ምኞታችንን ያሳይን ይሆናል። ያንቀላፋውን ምኞት የሚቀሰቅሰውም ይኸው ለፍርሃት የምንሰጠው ምላሽ ብቻ ነው።

Via ሚስጥረ አደራው

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ተግባቦትና የስሜት ብልሃት! (Communication& Emotional Intelligence)

የስሜት ብልህነት ማለት ስሜታችንን የማወቅ፣ የመረዳት የመምራት ችሎታ ነው፡፡ ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት (Emotional Intelligence) ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪ ምክኒያት ሰሚ ያጡ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ይኖራሉ፡፡

🔹የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት የሌላቸው ሰዎች መገለጫዎች፦

▸ የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም (በቀላሉ ይናደዳሉ፣ ይበሳጫሉ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል)
▸ ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም።
▸ በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ
▸ በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል።
▸ ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ፣ ይረበሻሉ፡፡
▸ ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ።
▸ ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው።

⬆️ ከላይ የተዘረዘሩት (የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው። በእርግጥ እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች ሳይኮሎጂካል ህክምና አላቸው፡፡

Credit: ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የእናትህ ድካም!

በዚህ ምስል የደከመችዋን እናት እና ንቅት ብሎ ሩቅ የሚያየውን ልጅ ድንገት ሳይ፣ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ። ምነኛ ብትደክም ብትዝል ነው ገና በጠዋቱ እንዲህ የሆነችው እያልኩ። ልጁስ ምን ይሆን እሩቅ አሻግሮ የሚያየው? ምን እያሰበስ ይሆን?

በማይቆመው ኑሮ፣ ግን በሚጠናቀቀው ህይወታችን፣ እንዲህ ባትለን ለልጆቻችን የምናቆያት ሀገራችን በዚህ የቅጽበት ዕይታዬና ፎቶው ብዙ እንዳስብ አድርጎኛል።

ዛሬም፣ የብዙዎቻችን ትኩረት ይህን ኑሮ ማሸነፍ ሳይሆን በምናብ እና በኢጎአችን የፈጠርናቸውን ''ጠላቶቻችንን'' ማሸነፍ ነው።

በስራ ቦታችን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሳብ በሚጽፉ ጓደኞቻችን ገፅ ላይ፣ በሰፈራችን፣ ምን ስንሰራ፣ ምን ስናስብ እና ምን ስንጽፍ ነው የምንውለው?

በዚህ ፎቶ ላይ ልባችንን የምትሰርቀውን እናት ድካም እና ኑሮ የሚያሻሽል ወይስ በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ ዓይነት የስንፍና እና የጸብ ስራ?

ብናስተውል፣ በመንገዳችን ላይ፣ ለህይወት ዘመን ትምህርት እና የመለወጥ ብልጭታ የሚሆኑ፣ ቅጽበቶችን በየቀኑ እናያለን። ዓይን ያየውን የሚያስተውል ልብ እና የሚመዝን አዕምሮአችንን ካበረታነው፣ እጅና እግርማ ወዳሰማሩት ሄዶ፣ ታላቅ የመከወን ኃይል አለው።

ፈጣሪ እንድናይ ብቻ ሳይሆን እንድናስተውልና እንድንመዝን ልብና አዕምሮአችንን ያብራልን!

#YonathanMenkir

Via Getu Temesgen

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#AndrésIniesta

"When I was struggling with depression, my most enjoyable part of the day was when I took my pill and went to sleep at night. You lose joy from life, from everything. I hugged my wife, but it felt like hugging a pillow. You feel nothing. I am still going to therapy, as I need to be at peace with myself. I like to listen to professionals talk about mental health and depression. You tell yourself: This is not me. It's your body, but you have no life, no joy, and no energy. Eventually, life teaches you that depression and mental health can affect anyone. It's not about material things. I could have had all the cars in the world and everything I wanted, and it still hard to face life's problems. You need to train your brain." - Andrés Iniesta

Source: https://twitter.com/Football__Tweet/status/1583723866677211137

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የንግግር እና ቋንቋ ህክምና (Speech and Language Therapy) የት ይገኛል?

- Mahlet Azene (Speech and language Therapist)
ስልክ: 0940103047

- Aki Speech Therapy
ስልክ: 0978806778/ 0974088763

- Addis Tebiban Health Care Consultancy
ስልክ: 0984650912/ 0929135785

- Lebeza Psychiatric Specialty Clinic
ስልክ: 0966111111/ 0116662966.

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ኮተት የመሰብሰብ እንዲሁም ያለመጣል አባዜ- Hoarding disorder

አንዳንድ ለረዥም ጊዜ የተጠቀሙበትን እቃ ወይም ብዙም አስፈላጊ ያልሆነን ነገር ለመጣል ወይም ለማስወገድ ይቸገራሉ? መልሶት አዎ ከሆነ ወይም በቅርብ የሚያውቁት ሰው ችግር ከሆነ በጥሞና ያንብቡት!

ይህ ችግር በእንግሊዝኛው አጠራር hoarding disorder የሚባል ሲሆን በአእምሮ ውስጥ በሚፈጠር የተሳሳተ ሃሳብ ነገሮችን ከአስፈላጊነታቸው በላይ የተጋነነ ዋጋ እንዲሰጥና እስከመጨረሻው ይዘናቸው እንዲንቆይ የሚገፋፋ ሃሳብ ወደ ተግባር ሲቀይር የሚፈጠር ችግር ነው።

መገለጫውም አስፈላጊነቱ እምብዛም የሆነን እቃ ሰብስቦ የማቆየትና እንዲሁም ኮተትን ሰብስቦ በመኖርያ ቤት የማከማቸት እንዲሁም ለማስወገድ በሚሞከርበት ወቅት ከፍተኛ የጭንቀት ስሜትና ውሳኔ ላይ ያለመድረስ ችግር ነው።

ብዙ ጊዜ የቆዩ የተለያዩ ወረቀቶችን፣ መጽሃፍት፣ ፖስታ፣ ሻንጣዎች እንዲሁም አሮጌ ልብሶችን ሲሆን ለተለያዩ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን እንዲሁም ለእሳት አደጋ ሊያጋልጡም ይችላሉ።

በብዛት ሰዎች ወደ ሃኪም ጋር የማይሄዱ ሲሆን ምክንያቱም እንደ ችግር ስለማያዩትና አስፈላጊነቱ ለማስረዳት ስለሚሞክሩ ነው። ህክምና ቦታ ከሄዱ በብዛት የተለያዩ የስነልቦና ህክምና እንዲሁም በጥቂቱ የመድሃኒት ህክምናም አለው።

ማጣቀሻ፡- synopsis of psychiatry 11ኛ ዕትም

በዮሴፍ ሳህለ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አሃ የስነልቦና አገልግሎት በሀዘን/መለየት በሚል ርዕስ ላይ የቡድን የምክክር ክፍለ ጊዜ ለጥቅምት 12, 2015 አዘጋጅቶል።

አላማውም፦ ስሜትን መግለጽ መቻል፣ 5ቱን የሀዘን ደረጃዎች መማር፣ ጭንቀትን የምንቆጣጠርባቸውን መንገዶች መለየት ይሆናል።

በዚህ ክፍለ ጊዜ ለመጠቀም በ 0940200454/ 0116622437 በመደወል ይመዝገቡ።

Aha Psychological Services has organized a group counseling session on grief/loss for October 22/2022. Expressing feelings, Learning the 5 stages of grief, and identifying ways to handle stress and loss are the main topics.

Call on 0940200454/ 0116622437 to book you place.

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ችግርን የመቋቋም ብቃት| Adversity Quotient (AQ)

በየእለቱ የሚያጋጥሙን ችግሮችን ለማለፍ ማለትም በስራ ላይ፣ በት/ቤት፣ በትዳር ህይወት፣ ልጆችን በማሳደግ ሂደት፣ በጓደኝነት፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና በተለይም ያልተጠበቀ ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥም ችግሩ ብዙ ሳይጎዳን ማለፍ እንድንችል የሚያስፈልገን ክህሎት ቢኖር ችግርን የመቋቋም ብቃት ነው።

በተጨማሪም ችግርን የመቋቋም ክህሎት የአንድ ሰው የስራ ስኬት እና የአእምሮ ጤናንም ይወስናል።

📌 ችግርን የመቋቋም ብቃት ያላቸው ሰዎች ባህርያት፦

- ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን የሚያምኑና አንዳንዴ ከተለመደ አሰራር ወጣ ለማለት የሚደፍሩ።

- ሊያጋጥመኝ ይችላል ብለው ላሰቡት ችግር ቀድመው መፍትሄ የሚያቅዱ።

- ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን የሚሰሩ።

- ራሳቸውን እንደነርሱ ጠንካራ ከሆነ ሰው ጋር የማያቆራኙ።

- ለሁሉም ነገር መልስ ሊኖረኝ ይገባል የማይሉ።

- ለራሳቸው ክብር ያላቸውና ተገቢውን ጥንቃቄ የሚያደርጉ።

- ሰዎችን የሚረዱ፣ ካጋጠማቸው ችግር የሚማሩ።

- ለሚፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ከመውቀስ ይልቅ መፍትሄው ላይ የሚያተኩሩ።

- ችግርን እንደመልካም አጋጣሚ የሚያዩ።

📌 ችግርን የመቋቋም ብቃት ለማሳደግ፦

1. ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት ማጎልበት።
2. ችግር ሲያጋጥም ጊዚያዊ ነው ያልፋል ብሎ ማሰብ።
3. ለሚፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን አለመውቀስና የራስ አስተዋፆ ላይ ማተኮር።
4. ሰዎች የሚሰጡትን ቀና አስተያየት መቀበል።
5. ያልተጠበቀ አዲስ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ።
6. ራስን ማወቅ፦ ምን እንደሚፈልጉና መቼ እርዳታ መጠየቅ እንዳለባቸው ማወቅ።

ችግርን የመቋቋም ብቃት በተፈጥሮ የተሰጠን ቢሆንም ልናሻሽለውና ልናዳብረው እንችላለን።

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ጠንካራዋሴት 👏

''አካል ጉዳተኝነት ጉድለት አይደለም ሰው የሚመዘነው በእውቀቱ እንጂ በአካሉ ሊሆን አይገባም!'' - ዶ/ር እድላዊት አበባው

ራሷን "ጠንካራዋ ሴት" ብላ የምትገልፀው ወጣት ቤተሰቦቿ በራስ መተማመን እንድጎናጸፍ አድርገው አሳድገውኛል ትላለች፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ካስመረቃቸው የጤናና የህክምና ሳይንስ ተመራቂዎች መካከል አንዷ የሆነችው ዶ/ር እድላዊት አበባው በተፈጥሮ አንድ እጇ ላይ ጉዳት ያለባት ሲሆን ስኬቷን በተመለከተ ስትናገር "እውቀቱና ፍላጎቱ ካለን፣ እችላለሁ ብለን ካሰብን አካል ጉዳተኝነት ከምንም አያግድም። አካል ጉዳተኝነት የአካል እንጂ የእውቀት ጉድለት አይደለም። የሰዉ ልጅ ደግሞ ሊመዘን የሚገባው በእውቀቱ እንጂ በአካሉ አይደለም" ብላለች።

ዶ/ር እድላዊት አበባው ውልደቷ በሀረር ከተማ ሲሆን፣ እድገቷ ደግሞ በድሬደዋ ከተማ ነው፡፡ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በድሬዳዋ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተከታትላለች፡፡ የሀገር አቀፍ ፈተናን ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተቀላቅላ ትምህርቷን አጠናቃለች፡፡

'እችላለሁ' ለሚለው ጠንካራ እምነቴ አስተዳደጌ፣ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ፣ አስተማሪዎቼና ሌሎች በዙሪያዬ የነበሩ ሰዎች ትልቅ ሚና አላቸው ትላለች፡፡ ማንኛውም ሰው መሆን የሚፈልገውን የማይሆንበት ምክንያት የለም፣ ነገር ግን በራስ መተማመንና ጽናትን ይጠይቃል።

ራስን በማዳመጥና የሚችሉትንና የማይችሉትን መለየት ተገቢ ነው፡፡ በተለይ የህክምና ትምህርት በጣም ብዙ ውጣውረዶች የሚበዙበትና ጽናትን የሚጠይቅ ቢሆንም በውስጤ የተገነባው የእችላለሁ መንፈሴ ስላለ በጥንካሬ ልወጣው ችያለሁ የምትለው ዶ/ር እድላዊት ለእኔ ከባድ የሚመስል የነበረው የተግባር ትምህርቱ ቢሆንም አንድም ያልሰራሁት የተግባር ስራ ግን አልነበረም፡፡ ሁሉንም የህይወት እድሎች በሚገባ እንደምትጠቀምባቸውም ነው የተናገረችው።

"የህክምና ሙያ ውስጥ የህይወትና የሞትን ምንነት ያየሁበትና ያወኩበት ነው። ሰው ደግሞ ህይወትን ለማወቅ ሞትን ማወቅ አለበት፣ ህይወት ምን እንደሆነች ሲገባው ደግሞ መልካም ነገርን ይሰራል፣ መልካም ያስባል" ስትል ሀሳቧን ገልጻለች።

የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ በተግባር ተኮር የትምህርት ቆይታ ወቅት ለማየት መቻሏን የምትናገረው ዶ/ር እድላዊት ፣ ያለው የጤና አጠባበቅ ግንዛቤ አናሳ እንደሆነና በሚገባ ሊሰራበት እንደሚገባ ሀሳቧን አካፍላለች። ታዲያ እሷም "ህክምና የእውነት ሰውን ለመርዳት የሚያስችል ሙያ ነውና ለወደፊቱም ያስተማረኝን ማህበረሰብ ሙሉ ሥነምግባር የምታከብር ትክክለኛ ሀኪም በመሆን ማገልገል ፍላጎቴ ነው፡፡" ስትል ቃል ገብታለች፡፡

Credit: Haramaya University (HU) FM 91.5 Radio FB page

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የሰው ልጆች ትልቁ ፍላጎት!
(ከ #አይቻልም መጽሐፍ)

አሜሪካዊው የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመነ የበይነ ሰብእ ሥነ ልቦና (Human Psychology) ሊቅ አብርሃም ማስሎው፣ የሰው ልጆች የማደግ እና እምቅ አቅማቸውን በተሟላ መልኩ ጥቅም ላይ የማዋል ፍላጎት፣ እጅግ ጽኑ ፍላጎት ስለ መሆኑ “Motivation and Personality” በሚለው መጽሐፉ ላይ “ሁሉም ከገዛ ራሳቸው ጋር በሰላም መኖር ምርጫቸው ከሆነ፣ ሙዚቀኞች ሙዚቃ ሊሠሩ፣ ሠዓሊዎች ሊሥሉ እንዲሁም ገጣሚዎች ሊገጥሙ ይገባል፡፡ የሰው ልጆች፣ መሆን የሚችሉትን ሁሉ መሆን አለባቸው። ለተፈጥሯቸውም መታመን ይጠበቅባቸዋል። ይኼንን ፍላጎት ነው “ራስን የማብቃት እና የማላቅ ፍላጎት–need to self-actualization የምንለው።

የሰው ልጆች ትልቁ ፍላጎት፣ ፍላጎታቸውን የማሟላት ፍላጎት እና በውስጣቸው የሚገኝን እምቅ አቅም ሙሉ በሙሉ እውን የማድረግ ጽኑ ፍላጎት እንዲሁም መሆን የሚችሉትን ነገር በሙሉ የመሆን ፍላጎት ነው» ሲል ገልጾታል፡፡

በተቃራኒው ፍላጎታችንን በማሟላት መሆን የምንፈልገውን መሆን አለመቻል ደግሞ፣ ከተቀበረ ሀብት ላይ ቁጭ ብለን በድህነት ለመኖር እንደመስማማት፣ ከደጃፋችን ላይ የሚገኘውን ዛፍ ሌላው ቆርጦ ሞፈር አድርጎ ሲጠቀምበት እያየን እንደ መቅናት፣ በእጃችን የያዝነውን ወርቅ መዳብ አድርገን እንደ መቁጠር እና መድኃኒት ባለው ሕመም እየተሰቃየን እንደ መኖር ማለት ነው፡፡

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የወራቤ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ክፍል!

"ዓለም አቀፍ ትኩረት የአእምሮ ጤናና ደህንነት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል የተከበረው የአለም ጤና ቀን በወራቤ ኮም/ስፔ/ሆስፒታል ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላት፣ የስራ ክፍል ሃላፊዎችና የአእምሮ ህመም ታካሚዎች በተገኙበት ተክብሯል።

በዚህም #ከሱስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የአዕምሮ ህክምና ማገገሚያ አገልግሎት ከሆስፒታሉ ሲኒየር ማኔጅመንት አካላት ጋር ማስጀመሪያና ማስታወቂያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity Disorder) - ADHD
.
ADHD ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው።

አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡
.
ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡
.
🔹የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች፦

► አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው
► በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ
► የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ
► የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው
► በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ
► ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው
► በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ ለመውጣት የሚታገሉ
► እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው
► ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት የሚመስላቸው
► በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡
.
ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል።

ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡
.
አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ-ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት (Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡
.
🔹ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
.
በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጥቆማ!

የኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም የልሕቀት ማዕከል ያዘጋጀው የወ/ሮ ዘሚ የኑስ ዝክር (ማስታወሻ) ፕሮግራም ዛሬ ከቀኑ 9:30 -12:30 ይካሄዳል። ማዕከሉ ባስተላለፈው መልዕክት ''የዘሚን ፈርቀዳጅነትን፣ ታታሪነትን፣ እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችንን እራስን መስጠትን በማሰብ ባለንበት ሆነን የዘሚን ሕይወት እናክብር።'' ብሏል።

#CelebratingLegend
#ZemiMemorial
#NiaFoundation
#JoyAutismCenter

ለመሳተፍ ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ⬇️

Zoom: https://zoom.us/j/95497254954?pwd=a2Y0bnZV05IM3E0eVBUUWpZUFJXdz09
Passcode: 444572

YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCViscd2sd7znrehkTLAKxvg

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና፣ ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ??

▸ ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም፤ ተበድሎ ይቅር ማለት ግን ይበልጥ ይከብዳል። በድለን መርሳቱ ላይከብደን ይችላል፤ ተበድለን መርሳት መቻል ግን ጥንካሬን ይሻል። እየተጠሉ መውደድ፤ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል።

▸ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን። ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው።

▸ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን።

🔹እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ?

(ካህሊል ጂብራን)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation!

▸ "በዚህ አለም ከላይ ስንደርስ ታች የነበርንበት ከንቱ ይሆናል፣ የጨበጥነውን እንረግጣለን፣ ክብር የሰጠነውን እናዋርዳለን፣ <ከዚህ በላይ የለም> ያልነውን ተራ ነገር እናደርገዋለን፤ አለሙ እንደዚሁ ነው። ንፋስ እንደመከተል ነው፣ የሚያረካ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም።"

▸ "ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው። የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው። እንዴት? የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የቀነስከው ነውና!"

▸ "...መጥፎ ሰው ጥሩ ባለሙያ ሊሆን አይችልም፤ መጥፎ ባለሙያም መልካም ሰው ሊሆን አይችልም። የተዋጣላችሁ ለሀገር ለወገን መከታ የምትባሉ ምሁር ባለሙያ የምትሆኑት የተስተካከለ ስብዕና ሲኖራችሁ ነው። ቅንነትን፣ ደግነትን፣ አዛኝነትን፣ ታታሪነትን ለመማር ዝግጁነትንና ፈጣሪን መፍራትን ገንዘብ አድርጉ። በጋራ መስራት እንጂ በጋራ ማሰብ አይቻልም። ብቻችሁን ሁናችሁ አስቡ ስራ ላይ ግን ተባበሩ!"

("ሰበዝ" ከሚለው የዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ መፅሐፍ የተወሰደ...)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Morning_Motivation

ተስፋ ስለዛሬ ኑሯችን ነው!

በነገ ተስፋ ውስጥ ለዛሬ ሰላምና ደስታ አለ፡፡

ተስፋ ነገ ጥሩ ይሆናል ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን ዛሬ ግራ ያጋባንን ነገር እንዴት ምላሽ ልንሰጠው እንደሚገባ ያሳየናል፡፡

ሕይወት 100% እርግጠኛ የማንሆንባት ሁሌም በመለውጥ ላይ ያለች ጉዞ ከሆነች በየቀኑ በጎ ነገር ለማየት የመፍቀድ ተስፋ ያስፈልገናል፡፡

ተስፋ የነገሮችን መስተካከል መጠበቅ ሳይሆን፤ በየትኛውም የሕይወት ጉዞ ውስጥ በጎ ነገር የማየት ፍቃድ ነው።

ንቁ ተስፋ ሕይወታችን ወደ አስደሳችና ስኬታማ መንገድ እየተጓዘ እንደሆነ ማመን ነው።

ዛሬ ሕይወትህ አስቸጋሪ፣ ከባድ፣ ፈታኝ መንገድ ላይ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ነገን ስታስብ መልካሙን የምትፈጽምበት እና የምታሳካበት እንደሚሆን ሁሌም ተመልከት፡፡

በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት
ብሩህ ቀን ይሁንልን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

- ''ተግባቦት ማለት ኪሳራ የሌለበት ሰጥቶ የመቀበል ስሌት ነው።'' - ዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ

- ''በመነጋገር የጋራ አላማን ማስጠበቅ ይቻላል''
- ''በመነጋገር የጋራ ግንዛቤ ይፈጠራል''
- ''በመነጋገር ጥርጣሬና ሐሜት ይጠፋል''

በ ዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ የተጻፈውን ''ከመደነጋገር መነጋገር'' የተሰኘውን መፅሐፍ እንድታነቡት ጋበዝናቹ።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#mentalhealth #የአዕምሮጤንነት

ደህና አለመሆን ያለ ነገር ነው! ጭንቀት፣ ከመጠን በላይ ትካዜ፣ ድብርት፣ ብቸኝነት፣ ተስፋ መቁረጥ አይነት ስሜት ሲሰማችሁ እርዳታ ጠይቁ - ከሰዎች ጋር ተነጋገሩ! ስሜታችሁን አታፍኑት፣ አትደብቁት፣ ችላም አትበሉት! አንዳአንዴ ለብቻችን ማንችላቸው ነገሮች ያጋጥሙናልና ስሜታችንን ልብ እንበለው። ተስፋ አንቁረጥ። እንደጋገፍ! እንበርታ።

It's okay to not be okay! when you're feeling very anxious, depressed, alone, hopeless, please seek help - talk to people - don't deal with it alone! some things are beyond our capacity. let's pay attention to our feelings/hearts/spirit. help each other. help yourself.

Via አርቲስት ሙኒት መስፍን

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel