melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እንደዚህ ባሉ ስሜቶች ውስጥ እራስህን አግኝተኸው ታውቃለህ? መከፋት፣ ቁጡ መሆን፣ በቀላሉ መነጫነጭ፣ ረዳት የለሽ መሆን እና የተጣልክ አይነት ስሜት፣ ፍርሀት፣ የጥፋተኝነት ስሜት?
     
ድንዛዜ እና ነገሮች ትረጉም አልሰጥህ ያሉበት ደረጃ ደርሰሀል? ለሌሎች ራስህን ማስረዳት ተራራ እንደ መውጣት ስለሚከብድህ ብቻህን መሆን መርጠሀል?
        
ምን ጭንቀት እና ድባቴ ውስጥ እንዳስገባህ ስለማታውቅ ወይንም እንዲህ ለመሆን በቂ ምክንያት የለኝም ብለህ ራስህን ጥፋተኛ ታደርጋለህ? በእራስህ ላይ ትናደዳለህ?
     
የመንፈስ ጭንቀት ምን ያክል እንደሚከብድ ከአንተ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ኣ? "ይገባኛል" ቢሉም "አይ አይገባችሁም! ይህ ከእናንተ ደባሪ ቀናት ውስጥ እንደ አንዱ አይደለም። ከዚያም በላይ...

  ....ልክ እንደዚህ:- ደስታን ማግኘት አለመቻል፣ ለመኖር ጉጉት ማጣት እመኑኝ ጠዋት ከአልጋ መነሳት፣ ፊትን መታጠብ እስኪከብዳችሁ ድረስ ህይወት አታካች ትሆናለች። ፍላጎት፣ ተነሳሽነት ሚባሉ ነገሮች የሉም በቃ አለም ላይ ምንም የሚያስገርማችሁ ነገር አይኖርም። (አስቡት!)  አሁንስ ተረዳችሁኝ?"
     
ሚገርመው ሠዎች ከዚህ የስሜት ጭንቀት እና ድባቴ እንዳትወጣ የሚያደርግህ ድክመትህ ነው ብለው ያስባሉ። "የምራችሁን ነው? ማለቴ መደበርን አልመረጥኩትም። ማንም የመንፈስ ጭንቀት ውሰጥ መግባትንም ሆነ መቆየትን አይመርጥም። በዘር፣ የእድገት ሁኔታ፣ የህይወት ውጣውረድ፣ ለአሰቃቂ አደጋ መጋለጥ ሌላም የአእምሮ ጭንቀትን ሊያመጣ ይችላል።"
   
No one is immuned for mental illness 💫
Explore your mentality ✨️

Fetlework Abate (Psychiatry nurse)

Via: Hakim

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

"አንድ ነገር ይሳካል ብለህ ስታምን አዕምሮህ ማሳካት የምትችልበትን መንገድ ይፈልጋል። በአንጻሩ ደግሞ እንደማይሳካ ስታምን አዕምሮህ ሊሳካ የማይችልባቸውን ምክንያቶች ይደረድርልሃል።"

(የሐሳብ ኃይል መጽሐፍ)

መልካም የሥራ ሳምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የስማርት ስልክ ሱሰኛ መሆንዎን በቀላሉ እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

በዚሁ አመት የተደረጉ ጥናቶችም የስማርት ስልኮች እና የተጠቃሚዎቻቸውን አስደንጋጭ አሃዛዊ ትስስር አሳይተዋል ስማርት ስልክዎ አጠገብዎ ከሌለ መተኛት ይከብድዎታል? የባትሪው መቀነስስ ጭንቀት ውስጥ ይከትዎታል? ስልክዎ ሳይጠራ የተደወለልዎ፥ መልዕክት ሳይላክልዎ መልዕክት መላኩን የሚያሳውቅ ድምጽ ሰምተው ስልክዎን ደጋግመው አይተዋል? መልስዎ አዎ ከሆነ የስማርት ስልክ ሱስ ተጠቂ ሳይሆኑ አልቀረምና ቆም ብለው ያስበቡብት።

ከተጠቃሚው ቁጥር መጨመር እኩል በስማርት ስልክ ሱስ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ቁጥርም እያደረ እየጨመረ መሆኑን ፔው የተሰኘው የጥናት ተቋም ያወጣው የዳሰሳ ጥናት ያመለክታል።

በአሜሪካ 47 ከመቶ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ስልካቸውን የሙጥኝ ያስባለ ሱስ እንደያዛቸው ያምናሉ።

71 ከመቶው የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎችም ከፍቅር ጓደኛቸው ጋር ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ለስልካቸው ጊዜ እንደሚሰጡ ነው የተናገሩት።

በጥናቱ ምላሽ ከሰጡት ህጻናት ውስጥም ሁለት ሶስተኛው በቀን ከ4 ስአታት በላይ በስልካቸው እንደሚያጠፉ ተመላክቷል።

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተሳታፊዎች ስልካቸውን ሳይዙ መንቀሳቃስ ከፍተኛ የመረበሽ ስሜትና ፍርሃት ውስጥ እንደሚከታቸው የተናገሩ ሲሆን፥ ስማርት ስልኮችን እየተጠቀሙ መንዳት ከሚደርሱ አደጋዎች 20 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።

ቀጣዮቹ አስደንጋጭ ቁጥሮችም የስማርክ ስልክ ተጠቃሚዎች ችላ ብለው ካለፏቸው በያዙት ስልክ ሱስ ተጠልፈው መውደቃቸውን ያሳያል ይላሉ ባለሙያዎች።

ስማርት ስልኮች አሰራራቸው በራሱ ሱስ
ውስጥ የሚከት ነው የሚለው የአሜሪካ አዲክሽን ሴንተር ድረገጽ፥ የየእለት እንቅስቃሴያችን ከስልካችን ጋር የተያያዘ መሆኑን ያወሳል።

መዝናኛው፣ መረጃ መሰብሰቢያው፣ ክፍያ መፈጸሚያው፣ አቅጣጫ ጠቋሚው፣ አማካሪው ስማርት ስልክ አጠቃቀሙ ገደብ ካልተበጀለት ግን ጉዳቱ እያመዘነ መሄዱ አይቀርም።

ከመጠን ያለፈና በሱስ ደረጃ የተቀመጠ የስማርት ስልክ አጠቃቀም የሰነልቦና ባለሙያዎች ከአዳዲስ ስያሜዎች ጋር እንዲያስተዋውቁን አድርጓል። ከነዚህም ውስጥ “ኖሞፎቢያ” (ስልክ የሌለበትን ሁኔታ መፍራት)፣ ቴክስታፍሪኒያ (መልዕክት ሳይገባልን ግን የተላከልን መስሎን የማየት ልማድ) እና ፋንተም ቫይብሬሽን (ስልካችን በስህተት የነዘረን መስሎን አውጥተን የምናይበት) የተሰኙት ይገኙበታል።

እናም እነዚህ ምልክቶችን ደጋግማችሁ ከተመለከታችሁ በስማርት ስልካችሁ ሱስ ውስጥ ተዘፍቃችሁ ሊሆን ስለሚችል ባለሙያዎችን አማክሩ።

የድብርት፣ እንቅልፍ እጦት እና የስራ መጥላት ባህሪ እየተላመደ መሄድም ከማህበራዊ ህይወት ከመራቅ ጋር ተዳምሮ ራስን ወደማጥፋት ሊያመራ ይችላል፤ ጥናቶችም ይህንኑ አሳይተዋል የሚሉት የስነልቦና ባለሙያዎች ጉዳዩን እንደቀላል ነገር መመልከት እንደማይገባም ያሳስባሉ።

Via: Alain Amharic

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የውልደት ቅደም ተከተልና ባህርይ| Birth order traits

✍ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው
     (የስነ-አዕምሮ ሬዚደንት ሃኪም)

Via: Hakim

https://telegra.ph/የውልደት-ቅደም-ተከተልና-ባህርይ-Birth-order-traits-12-19

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ #Psychology in general is studied in five different perspectives, each being an angle by which you look at human phenomena.

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አርቲስት ሙኒት መስፍን ስለ አእምሮ ጤና
=========================
ብዙ አስገራሚ ስራዎች ስለሰራ ወጣት አነበብኩ። ደስ የሚል ቤተሰብ አለው። ብዙ ስኬቶች አስመስግቧል። የሚገርሙ ስራዎች ይሰራ ነበር። ብዙ እቅድ ነበረው። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እራሱን አጥፍቶ ተገኘ።

ወገኖቼ ሲጨንቃችሁና ግራ ሲገባችሁ ለጓደኞቻችሁ ደውሉ። ለቤተሰብ አሳውቁ። የሀይማኖት ሰዎችን አማክሩ። ወደ ሀኪም ሂዱ። አንዳንዴ ሰዎችን ማናገር ይከብዳል። "ተጨናንቄያለሁ እርዱኝ" ማለትም ይከብዳል። ግን ለብቻ ሲሆን በብቸኝነት ሲሆን የበለጠ ከባድ ነው።

አሜሪካ ራስ የማጥፋት ሀሳብ ያላቸውና የጨነቃቸው ሰዎች የሚደውሉበት 24 ሰአት የሚሰራ ነፃ የስልክ መስመር 988 አለ። ሁሉም ሀገር ላይ እንደዚህ አይነት አገልግሎት መኖር አለበት። ምንም አይነት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ብትሆን፣ ምንም አይነት ቤተሰብ ቢኖርህ፣ ምንም አይነት ስራ ላይ ብትሰማራ አእምሮ ደህና ካልሆነ ሁሉም ነገር እያለህ ምንም እንደሌለህ ልታስብ ትችላለህ። አእምሮህ ህይወት ትርጉም አልባ እንደሆነ ሊነግርህ ይችላል።

አእምሮህ አንዳንዴ ከመጠን ያለፈ ውሸት ሊነግርህ ይችላል። በማንኛውም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ነገሮች መልካም እንደሚሆኑ ተስፋ እንደሚኖርህ እመኛለሁ። ሁልጊዜ ተስፋ አለ። የስነ ልቦና ህክምና ውስጥ ተስፋ አለ። የቤተሰብና የጓደኛ እገዛ ውስጥ ተስፋ አለ። በእምነት ውስጥ ተስፋ አለ። በጊዜ ውስጥ ተስፋ አለ።

እገዛ ሲያስፈልግህ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበል። ሳይረፍድ ቶሎ እገዛ ማግኘት ደግሞ የተሻለ ነው። እኔ የስነ ልቦና ህክምና አድርጌ ብዙ ተጠቅሜያለሁ። እገዛ የሚያስፈልጋችሁ ሰዎች የስነ ልቦና ህክምና እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ። የሚስማማኝን የስነ ልቦና ህክምና ለማግኘት ጊዜ እንደወሰደብኝ አልደብቃችሁም። ሆኖም ያስፈልገኝ ስለነበረ 'ቴራፒ' ማድረግ አልተውኩም።

ሁላችንም ብዙ የአእምሮ ጤና ጉዳዮች አሉብን። ብዙ የስነ ልቦና ጠባሳ የሚተዉ ጥቃቶች በህፃንነታችን ወይም ካደግን በኋላ ደርሶብን ይሆናል። ለብቻችን ለመቋቋም መሞከር ከባድ ነው። እገዛና ድጋፍ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበሉ። እገዛ መጠየቅ ጥንካሬ ይፈልጋል። ለራሳችሁና ለምትወዷቸው ሰዎች ስትሉ ጠንከር ብላችሁ እገዛ ጠይቁ።

ሰላምና ፍቅር ለሁላችሁም። ሁላችሁም ደህና እንድትሆኑ እመኛለሁ። ለአእምሮ ጤና ትኩረት እንስጥ!!!!

አርቲስት ሙኒት መስፍን
ትርጉም ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Thank you Munit🙏

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የስልጠና ማስታወቅያ!

በሙያ ማማከር ዙሪያ የሰርተፍኬት ኮርስ!

ለሙሉ መረጃ እና ምዝገባ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ይጠቀሙ::

Training announcement!

Vocational Guidance and Counseling Certificate course!

For full information and registration, use the link below.

https://forms.gle/g8w3teRXXjaKAwF66

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዛሬ ስብሃቲዝም የሀሳብ ውይይት!

ሐሳብ - ንባብ - ውይይት

ዛሬ ምሽት ህዳር 27 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

የእለቱ እንግዳ የስነልቦና ባለሞያው እንዳልክ አሰፍ ሲሆን  "ስነ ልቡናችን" በሚል ርዕስ እይታዎቹን ያጋራል።

12:00 ሲል ውይይቱ ይጀመራል።

ቦታው: ሃያ ሁለት ታውን ሰኩዌርሞል 8ኛ ፎቅ ሲሆን መግቢያው በጊዜ መገኘት ነው ብለዋል አዘጋጆቹ።

Via: Event Addis

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

Gender-Based Violence is violence that is directed against a person because of that person's gender.

It is also violence that affects persons of a particular gender disproportionately.

When a person experiences gender-based violence, the physical and emotional impact is lasting. It seeps into every sphere of their life.

Sexual abuse and rape survivors exhibit a variety of trauma-induced symptoms including

- Sleep and eating disturbances,
- Depression,
- Feelings of humiliation, anger, and self-blame,
- Fear of sex, and
- An inability to concentrate.

Beyond the emotional trauma, GBV can result in physical injuries,

- Contraction of sexually transmitted infections, including HIV,
- Interruptions to sexual health and reproductive abilities,
- Unwanted pregnancies and
- Even death.

During this #16Daysofactivism and beyond, let us #UNiTE in transformative activism against any and all forms of #violence.

- Protect not harm.
- Strengthen not weaken!

#EngenderHealth
#Yetenaweg

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ ዋልያ መጻሕፍት በዚህ ሳምንት!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፣ መግቢያ በነፃ!

Via: Event Addis

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ'Applied Developmental Psychology' የሁለተኛ እና የሦሥተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለማስጀመር የሥርአተ ትምህርት ግምገማ አካሂዷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ነው የሥርአተ ትምህርት ግምገማ (Curriculum Review) ያካሄደው፡፡  

የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የተገመገሙትን ፕሮግራሞች ጨምሮ 8 ፕሮግራሞች እንዳሉት ተነስቷል።

ከነዚህም ውስጥ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በክሊኒካል፣ በሶሻል፣ በካውንስሊንግ እና በዴቨሎፕመንታል ሳይኮሎጂ ፕሮግራሞች የካሪኩለም ግምገማ አካሂዶ ተማሪዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆኑን የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ዶ/ር መሰረት ጌታቸው ገልጸዋል።

Via: Tikvah University

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አዕዋፋትን መመልከትም ሆነ ድምጻቸውንና ዝማሬአቸውን መስማት ለአዕምሮ ሰላምና ደህንነት መፍትሄ እንደሚሆን ተመራማሪዎች ገለፁ፡፡

የአዕዋፋቱ ድምጽ በተለይም በተለያየ ጭንቀት ውስጥ ላሉ ሰዎች የአዕምሮ ሰላምና እረፍት እንደሚሰጥ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡

ጥናቱ የተካሄደው ለንደን በሚገኘው ኪንግስ ኮሌጅ ሲሆን በተለያየ የአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ባሉ 1300 ሰዎች ላይ በተካሄደ በዚሁ ጥናት አዕዋፋትን መመልከትም ሆና ዝማሬያቸውና ድምጻቸውን መስማት ሰላምና መረጋጋትን እንደፈጠረላቸው ተመልክቷል፡፡

የኮሌጁ ተመራማሪዎች በግለሰቦቹ ላይ ባካሄዱት ምርምር ወፎችን እንዲመለከቱ እንዲሁም ዝማሬአቸውንና ጫጫታቸውን እንዲሰሙ አድርገዋል፡፡

በዚህም ግለሰቦቹ ቀስ በቀስ ከጭንቀታቸው በመውጣት የአዕምሮ ሰላምና እረፍት ማግኘት እንደቻሉ አረጋግጠዋል፡፡

እናም ተፈጥሮን በተለይም አዕዋፋትን መንከባከብና መጠበቅ ከኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታ በዘለለ ለሰዎች አዕምሮ ደህንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ ነው።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ድህረ-አደጋ ጭንቀት/ Post-Traumatic stress Disorder (PTSD)

እንደ ልጅ በተሰጠን ፍቅር እና እንክብካቤ ምክንያት ስለ አለም እና ሰዎች ሶስት መሰረታዊ ግምቶችን እንፈጥራለን። እነሱም የአለም እና የህዝቦቿ አጠቃላይ መልካምነት፣ ዓለም ትርጉም ያለው እና ፍትሃዊ ነው እና እኔ ጥሩ ሰው ነኝ ብለን እናስባልን።

እጅግ በጣም ከባድ የሆኑ የህይወት ክስተቶች እነዚህን እምነቶች ባልተጠበቀ ሁኔታ ያበላሻሉ። እነዚህ ክስተቶች ካጋጠሙ በኋላ ያለው የስሜት ቀውስ አሰቃቂ ነው። የተለመዱ አሰቃቂ ክስተቶች ስንል እንደ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት፣ የተረበሸ ቤት ሲኖር፣ ፍቺ፣ ጉልበተኝነት፣ የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት፣ ይኖሩበት ከነበረ ስፍራ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር፣ የተሽከርካሪ አደጋዎች፣ ከባድ የጤና እክል ሲያጋጥሙ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ፣ የሽብር ጥቃቶች ሲፈፀሙ ወዘተ...ናቸው።

እንደዚህ አይነት ክስተቶች በማንኛውም የህይወት ደረጃ ላለ ሰው በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። እነዚህ ገጠመኞች መሰረታዊ ግምቶቻችንን ይሰብራሉ አቅመ ቢስ፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ስጋት፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላው ህይወት፣ አለመተማመን እና ግራ መጋባት ውስጥ እንድንግባ ያደርጉናል። የድህረ-አሰቃቂ ጭንቀት (PTSD) የምንለው ይህ ነው። የተበላሹ እምነቶችን ለመፍታት እነዚህን ስሜቶች ማስተካከል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

እንደነዚህ ያሉ ያልተፈቱ ጉዳቶች ወደ አንዳንድ የአእምሮ ጤና ስጋቶች ለምሳሌ ድብርት፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ ችግር፣ ምክንያታዊ ያልሆኑ ፍርሃቶች፣ ሱስ፣ ራስን መጉዳት ለመሳሰሉት ጉዳቶች ያግለጣሉ።

የመንፈስ ጭንቀት፡- “ዓለምና ሰዎች ጥሩ ናቸው” እና “ሁሉም ነገር ፍትሃዊ ነው” የሚለው መሰረታዊ እሳቤ ስለተበታተነ ማህበራዊ ግንኙነት ለመመስረት እና ከሰዎች ጋር ለመገናኘት አስቸጋሪ ሆኖ አናገኝዋለን። የእኛ ፍላጎት የማንኛውም ቡድን አባል መሆን (እንደ ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ የክፍል ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች፣ የጥበብ ቡድኖች፣ የስፖርት ቡድኖች፣ ወዘተ) መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት ነው። በአሰቃቂ ጉዳት ምክንያት ሌሎችን ማመን እንቸገራለን ግንኙነትን መገንባት ተሰመቶን የትም እንዳልሆንን እንዲሰማን ትተን እራሳችንን እናገላለን። ይህ የመንፈስ ጭንቀት ምልክቶች አንዱ ነው።

ጭንቀት፡- ይህ ከመንፈስ ጭንቀት ጋር ተመሳሳይ ነው። ከተሰበሩ እምነቶች የሚመጣ ነው፣ ስለዚህ ሌሎችን ማመን ቀላል አይሆንም። በዚህም ምክኒያት በሰዎች አካባቢ ጭንቀት ሊሰማዎት ይችላል እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ስለመመርመርዎ ይጨነቃሉ፣ ከሚያስቡበት የህይወት ደረጃ እንደማይረዱዎት በመፍራት። በጭንቀት ጊዜ በማያያዝ የመረበሽ ስሜት፣ ከፍተኛ ንቁ መሆን፣ ማላብ፣ መንቀጥቀጥ፣ የትንፋሽ መቆራረጥ ስሜት የተለመደ ነው።

የእንቅልፍ ችግር፡- ቅዠቶች እና ብልጭታዎች በPTSD ውስጥ የተለመዱ ናቸው። በእነዚህ ምልክቶች ምክንያት በቂ እንቅልፍ ካገኙ በኋላም ጥሩ እረፍት ላይሰማዎት ይችላል። በዚህም ምክኒያት ድካም ይሰማዎታል፣ ይህም ለጭንቀት ያጋልጠናል።

ሱስ፡- ማጨስ፣ መጠጣት እና አደንዛዥ እጾች መጠቀም ከስሜታዊ ህመም ለጊዜው ፈጣን እፎይታ ያስገኛሉ ብለው ያስቡ ይሆናል ነገር ግን እንዲህ ያሉ ንጥረ ነገሮች በብዛት መውሰዱ ህመሙን ያባብሱታል።

ራስን መጉዳት፡- ሰዎች የስሜት ሕመምን ለማስታገስ ራሳቸውን በመጉዳት እራሳችውን ከዚህ የስሜት ጉዳት የልቅ የሰውነት ጉዳት ላይ በማደርስ ህመማችውን ለመቀየር ይሞክራሉ። ያልተፈታ ድንጋጤ በአእምሮ-ደህንነትዎ ላይ ተጽዕኖ ከማድረግ በቀር ምንም አያደርግም። ስለዚህ ሰዎች ለማምለጥ እና አሉታዊ ስሜቶችን እና ሀሳቦችን ለመቋቋም ወደ ራስን መጉዳት ይመጣሉ።

ምን ሊደረግ ይችላል?

ከላይ የጠቀስናቸው ምልክቶችን ማወቅ እና መቀበል ለፈውስ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ሌሎችን ማመን ከባድ ሊሆን ቢችልም እርዳታ መጠየቅ ሂደቱን ቀላል ያደርገዋል የሥነ ልቦና ባለሙያ ወይም የሥነ አእምሮ ሐኪም ያነጋግሩ። በሰዎች ዘንድ አንድ የተለመደ አስተሳሰብ አለ የሥነ ልቦና ባለሙያን ለማየት "ማበድ" አለብዎት የሚል ነው። የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ለአስጨናቂ ሀሳቦች እና ስሜቶች ህክምና ይሰጣሉ። ስሜትዎ ጥሩ ካልሆኑ እርዳታ ለመጠየቅ ጥሩ ምክንያት ነው። ልክ ለኢንፌክሽን አንቲባዮቲክ እነደሚውሰድው ሂደቱ ከባድ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለምክር መሄድ ለአጠቃላይ የአእምሮ ደህንነትዎ ጠቃሚ ነው።

Source: i-ጤና ሳምንታዊ የጤና ጽሑፍ መረጃ

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ከመጽሐፍት

ጥረቱ ሳይኖር ውጤቱ አይመጣም!

እንዲያምር የምንፈልገው ነገር ሁሉ የሚያስመርር ትግል አለው፡፡ ካልተጋን መደሰቻ ሳይሆን መበሳጫ ቀኖቻችን ይበረክታሉ። ሒደቱን ለመሔድ ያልፈቀደ ውጤቱን ለማየት አይበቃም፡፡ ለመኖር በጣርነው ልክ ለመሞት ከማጣጣር እንተርፋለን። ጥረታችን ለውጤታችን መሰረታችን ነው። የምንከፍለው ዋጋ ካለ የሚገባንን ክፍያ አናጣም። ድላችን ሁሉ ትግላችንን መሰረት ያደርጋል። ስኬታችን የፅናታችን ውጤት ነው። በፅናታችን ከፀናን ውጤት እንደጠማን አይቀርም። ለማሳካት በወጉ መፍጋት ይጠበቅብናል። ኳሷ ሳትኖር ጎሉን አናስቆጥርም። ጥረት ሳይኖር ውጤት አይመጣም። ለክሽፈት አልተሰራንም። በጥረት ውስጥ ስንኖር ሽንፈት አያሸንፈንም።

በከፈለኝ ዘለለው [ሐዋዝ]

መልካም የስራ ሳምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የመርሃ ግብር ጥቆማ!

ህዳር 10/2015 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 “ለልዩ ፍላጎት ልጆች እና ወጣቶች ያገባናል” በሚል ርዕስ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ወላጆች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለሙያዎች ያካተተ የግማሽ ቀን መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

በዚህ መርሃ ግብር የተለያዩ ፕሮግራሞች ተካተዋል፦

ከዚህም መረሃ ግብር ውስጥ “የእኛ ልምድ እና ተሞክሮ ለሌሎች ወላጆች!” በሚል የመጽሃፍ ማደራጀት ስራ የልዩ ፍላጎት ወላጆች ልምድ እና ተሞክሮ የሚያሳይ ”አዲስ አለም” ያተሰኘ በኦቲዝም ዙሪያ የተፃፈ የመጽሃፍ ምረቃ ስነ-ስርዓት ይኖራል።

የዓለም ሕፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጲያ ልዩ ፍላጎት ሕፃናት ቀንን በመመካከር እና ግንዛቤ በመፍጠር ኑ አብረን እናክብር!

አድራሻ ጀሞ አንድ በሚገኘው ሻምፒዮን አካዳሚ ቅጥር ግቢ (ጤና ጣቢያው አጠገብ)

ስልክ: 091148328, 0911887607, 0911735569

#CFS

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ልጆቻችሁን በጥብቅ ተከታተሉ!

ለወላጆች. . .


የልጆቻችሁን ጥሩ መሆን፣ የፍቅር ልጆች መሆንና ታዛዥ መሆን በድብቅ ሊያደርጉትና ሊደረግባቸው ከሚችሉት ነገሮች ጋር በፍጹም አታምታቱ፡፡ በሌላ አገላለጽ ልጆቻችሁ ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል መልካም ባህሪያት እየገለጹ ሳለ በስውር ግን አጥፊ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚከተሉትን ሃሳቦች እንደመንደርደሪያ በመውሰድ አስቡበት፡፡ 

ልጆቻችሁ ላይ መልካምነትን፣ ፍቅርንና ታዛዥነትን እያያችሁ . . . 

1. መጥፎ ልማድ ሊያዳብሩ ይችላሉ፡፡

የፖርኖግራፊ፣ የአደንዛዥ እጽና የመሳሰሉት ነገሮችን እየተለማመዱ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ካለማቋረጥ የልጆችን ስልክ አጠቃቀም ተቆጣጠሩ፣ የባህሪይ ለውጥ ሲያሳዩ በሚገባ ተከታተሉ፣ ለብቻቸው መሆንን የመፈለግን ሁኔታ በቅርብ አጢኑ. . . ፡፡

2. በመጥፎ ጓደኛ ተጽእኖ ስር ሊወድቁ ይችላሉ፡፡

ቀስ በቀስ ባህሪያቸውን ለመጥፎ ከሚለውጡ ልጆች ጋር እያሳለፉ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ጓደኞቻቸው ማን እንደሆኑ ለይታችሁ እወቁ፣ አዲስ ጓደኛን ሲይዙ እንዲያሳውቋችሁ አድርጉ፣ ከጓደኞቻቸው የሚመጡ ግፊቶችን እንዲያሳውቋችሁ መንገድን ጥረጉ፣ አውሯቸው. . . ፡፡

3. የተለያዩ ጥቃቶች ከሰዎች ሊደርስባቸውና ላይነግሯችሁ ይችላሉ፡፡

በትምህርት ቤት ጉልበተኛ የአካል ጥቃት፣ በዘመድና በቅርብ ሰው የወሲብ-ነክ ጥቃት፣ በአስተማሪና በሌላ “ባለስልጣን” የስነ-ልቦና ጥቃትና የመሳሰሉትን እያስተናገዱ ለእናንተ ሳይነግሯችሁ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እቤት ከሰው ጋር ትታችሁ የምትወጡትን የልጆች ሁኔታ በሚገባ አስቡበት፣ ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ቦታ ሲነኳቸውም ሆነ ተገቢ የልሆነ ሃሳብ ሲያቀርቡላቸው በግልጽ መንገር እንዳለባቸው አሳስቧቸው፡፡  

በልጆቻችሁ ላይ የስነ-ልቦናም ሆነ የአካል ጥቃት አታድርሱ፡፡ መሰረታዊና አስፈላጊ ነገሮችንም በመከልከል አትጉዷቸው፡፡ ነገር ግን ተገቢ ያልሆነን ነገር እንዳያደርጉ በመከልከልና ተገቢውን ነገር እንዲያደርጉ በመጫን ብትጎዷቸው ጉዳቱ ጤናማና ለውጤት የሆነ ጉዳት እንደሆነ አስቡ፡፡

ትምህርት ቤት፣ ጓደኛም ሆነ ማሕበራዊ ሚዲያ በእነሱ ላይ ከሚያመጣው ተጽእኖ ይልቅ በበለጠ ሁኔታ እናንተ ተጽእኖን ማድረግ እንደሚገባችሁ አትዘንጉ፡፡ አለበለዚያ መቼ እንዳመለጧችሁ ሳታውቁ ታጧቸዋላችሁ፡፡

(በዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ገጽ26

የደረሰብን መከራ ባለንበት የሚያስቀረን፣ እኛ ላይ ብቻ እንደሆነ በመስበክ ነው። እኛ ብቻ ተለይተን ተጋላጮች እንደሆንን በመንገር ነው። በገጠመህ እክል ልብህ አዝኖ ጥግህን ይዘህ ቁጭ ብለህ ሳለህ በዚህ መንገድ እኮ የወደቅከው አንተ ብቻ ነህ ይልሃል።

ኩርምት ካልክበት ስፍራ ይቀርብህና ስማኝማ ይልሃል፡፡ እንደምንም ብሎ ቀልብህን እንደሳበም ጆሮህንም እንዳገኘ "ሰነፍ ነህ አትጠቅምም! ከመንገዱ ማብቂያም አትደርስም" ይልሃል። አንተም ተሽመድምደህ ባለህበት ተጣጥፈህ እስከቆየህለት ድረስ የነገረህ ሁሉ እውነት፣ አለምም ባንተ የውድቀት ዜና ዙሪያ ብቻ የምትዞር ይመስልሃል።

እውነት ነው እኮ! የወደቅ ቀን ሁሉም ጭልም ብሎ ነው የሚታይህ። ሰው ትፈራለህ፣ መዝናናትን ትፈራለህ፣ ህብረት ማድረግን ትሸሻለህ፣ ላንተ መፍትሄው ቤትህ ውስጥ መደበቅ ብቻ ይመስልሃል። ትንሽ እንኳ መስኮቴን ገርበብ አድርጌ አካባቢዬን ልይ ብትል እንኳ ዓይንህ ራሱ መርጦ የሚያይልህ ተሰብረው የቀሩትን ብቻ ነው፡፡ ጆሮህም ሳይቀር የሚሰማው ድምፅ የከሸፈ ጥይት፣ የከሸፈ ሰው ራዕይና ፅንስ ሲጨነግፍ የሚሰማውን ብቻ ነው።

በተዘጋ ክፍል ውስጥ መሆን አንድ ነገር ነው፡፡ እኔ ግን መውጫ በር እንኳ ከሌለው ጉድጓድ ውስጥ ገብቻለሁ ትላለህ።

ይህ ሁሉ ግን እመነኝ- እምቢ ብለህ ብድግ እስክትል ድረስ ብቻ ነው። ስትነሳ መንገዱን በሙሉ እየወደቁ የሚነሱ ተነስተውም የሚሮጡ ሞልተውት እንዳሉ ይታዩሃል። ወደኋላ የቀሩበትን መንገድ እንደቀስት ለመወንጨፍ የሚጠቀሙበትን ዘዴ ታስተውላለህ። ውድቀታቸውን በበጎ እይታ የሚመለከቱትንም ልብ ትላለህ።

ያኔ ማንም ያልወደቀበት ጉዞ ቢሆን እንኳ እኔን አይቶ ለመነሻ ይሆነዋል ትላለህ። የከበበህንም ጭጋግ ትበትናለህ ከአንገትህም ቀና ትላለህ።

(ዶ/ር በጸሎት ከበደ)
#Hakim

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፆታዊ ጥቃት ማለት ፆታን ማእከል ያደረገ (አንድ ሰው ሴት/ወንድ በመሆኑ ምክንያት የሚደርስ) ማንኛዉም አይነት አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ... የጥቃት ድርጊት ነው።

ብዙ ጊዜ አንዲት ሴት ፆታዊ ጥቃት ደረሰባት ሲባል አእምሯችን ውስጥ የሚመጣው አካላዊ ጥቃት ወይም ወሲባዊ ፆታዊ ጥቃት ነው።

ስነ-ልቦና ላይ የሚደርስ ጥቃት ብዙም ትኩረት ያላገኝ እንዲሁም ደግሞ በማህበረሰባችን ዘንድ ተቀባይነትን ያገኝ እና እንደችግር የማይቆጠር የጥቃት አይነት ነው።

ሴትን ልጅ ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ስሜትን በሚጎዱ ቃላት መናገር ወይም መሳደብ፣ ማዋረድ፣ እንቅስቃሴዋን ለመቆጣጠር መሞከር ስነ-ልቦናዊ ፆታዊ ጥቃት ነው።

ስነ-ልቦናዊ ፆታዊ ጥቃት አእምሮ ላይ ትልቅ ጠባሳ የሚፈጥር በመሆኑ እንደ ሌሎቹ የፆታዊ ጥቃት አይነቶች ትኩረት ሊሰጥ እና ሊወገዝ ይገባል።

የዘንድሮ የነጭ ሪቫን ቀን "ሴትን  አከብራለሁ ጥቃቷን እከላከላለው" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

ከነዓን በለጠ (የስነ-አእምሮ ሕክምና ባለሙያ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ከምጽሐፍት

"አታማር! ያለፈው ሕይወትህ አጋጣሚዎች ማከማቻ አትሁን። እናም የመጀመሪያው እርምጃህ ያለፈውን መርሳት ይሁን።

የማይረባውን ተሸክመህ አትዙር። እጅግ በጣም ወሳኙን የአእምሮህን ክፍል በእንቶፈንቶ ያለፈ ገጠመኝ አትሙላው። ሐሳቦችህ ኃይለኛ ጉልበት ያላቸው መሆናቸውን አስታውስ።

ስለዚህ በማይጠቅሙ ሰዎችና ክስተቶች አታባክናቸው። ተበድለህም ከሆነ ይቅርታ አድርግና እርሳው። አሁን ሙሉ ኃይልህን በምትፈልገው ጉዳይ ላይ ብቻና ብቻ አተኩር።"

ርዕስ፦ የሐሳብ ኃይል
አዘጋጅ፦ ከድር አሰፋ

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ብቸኝነት፡- ለህብረተሰብ ጤና ዋነኘው ተጠያቂ ነው።

በአንድ ጥላ ስር ለሚኖር ቤተሰብ ተነጣጥሎ የሚመጣ ደስታም ሆነ በረከት አይኖርም የአንዱ ደስታ ለአንዱ ይሰማል በአንዱ ሙዚቃም ሌላው ይዝናናል፡፡

ይህ ዓይነቱ ትስስር ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ፣ ተመሳሳይ የአመለካካት ውቅር እና ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እንዲኖር ያስገድዳል፡፡

ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ አሁን አሁን በከፍተኛ ሁኔታ የህብረተሰብ ጤና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ የበዛ የአልኮል አወሳሰድ፣ የታዳጊዎች በአደገኛ ሁኔታ በሱስ መጠመድ እና ረዘም ላለ ሰዓት መቀመጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሱ ሲሆን በቅርቡ የብሪገሃም ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር በሆኑት በፕሮፌሰር ጁሊያን ሆልት ለንስታንድ የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ብቸኝነት አሁን ላይ ከፍተኛውን የህብረተሰብ ጤና ስጋትን በበላይነት ይመራል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ እናዳሉት "የሰው ለሰው ግንኙነቶች ለሰው ልጅ ለመኖር እና በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የጨቅላ ህጻናት ማቆያን በተመለከተ የተደረገው ጥናት እንዳሳየው ከሆነም አጠገባቸው ሰው ከነበራቸው ጨቅላ ህፃናት ይልቅ ለብቻቸው ተነጥለው ተቀምጠው የነበሩት ለሞት የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነበር፡፡ ከዛም በላይ ሰዎችን ከህብረተሰባቸው ተነጥለው እንዲቆዩ ማድረግ የሰው ልጆች ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረ የቅጣት ዓይነት እና ፍርድም ጭምር ነው፡፡

ይህንኑ #የብቸኝነት ጣጣን በተመለከተ AARP ያወጣው ጥናት እንሚያሳየው ከሆነ በአሜሪካ እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ወደ 42ሚሊዮን የሚጠጉ ጎልማሶች በአሰቃቂ የብቸኝነት ህይወትን እየገፉ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

የፕሮፌሰሩ ጥናት አሜሪካዊያንን፣ አውሮፓዊያንን እና አሲያዊያንን ያሳተፈ የነበረ ሲሆን የጥናቱ ውጤት እንዳሳየው ከሆነ ብቸኝነት ያለእድሜ ሞትን ያስከትላል። በተጨማሪም ማህበረሳዊ ግንኙነቶች ያላቸው ሰዎች 50 በመቶ ያህል ያለእድሜ ከመሞት የማምለጥ እድል አላቸው ብሏል፡፡

በስተመጨረሻም ፕሮፌሰሩ እንደዚህ ካለው አሳሳቢ ቀውስ ለመውጣት ለተማሪዎች፣ ለህጻናት እና ለህብረተሰቡ የተለያዩ ስልጠናዎች እና ትምህርቶች መሰጠት አለበት ያሉ ሲሆን አክለውም ሀኪሞች ከበሽተኞቻቸው ጋር ቅርበት ሊኖራቸው እና ህብረተሰቡም አንዱ ከአንዱ የሚተሳሰርበት የገንዘብ ፍሰት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

N.B. ብቸኝነት እየሰፋ ሲሄድ ወደ አዕምሮ ጤና ቀውስ ያመራል። ስለሆነም እንዲህ የሚያጋጥምዎ ከሆነ ወይም የሚያጋጥመው ሰው ካዩ ይረዱት፣ ያዳምጡት። ችግሩ ከፍ ካለም ወደ ባለሙያ ይውሰዱት።

Source፡- RedOrbit

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ጤና፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት

https://www.bbc.com/amharic/articles/c5152vjxv3no

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስብዕናን ለመገንባት ቃላቶች አስፈላጊ ናቸው!!

በየቀኑ ለራሳችን የምንናገረው፤ እራሳችንን የምናይበትን መነፅር በማስተካከል ብሎም ወደ ህይወታችን የምናመጣው በረከት ላይ ጉልህ አስተዋጽዎ አለው።

ከፍቅር አጋራችን፣ ከቤተሰብ ወይም ከልብ ጓደኞቻችን ጋር ስናወራ እንደምናደርገው ሁሉ ከራስ ጋር በሚኖር ስብሰባ የድጋፍ፣ የማፅናት፣ የመተሳሰብ እና የፍቅር ቃላትን መጠቀምን ከቶዉንም ልንዘነጋዉ አይገባንም።

የምንጠቀማቸው ቃላት የመስበርም ብሎም የመጠገንም ኃይል አላቸው።

ይህን ለመረዳት ታሪክን በወጉ መቃኘት ብቻ በቂ ነው፡፡

በዓለም ላይ በአዉዳሚነቱ አቻ ያልተገኘለትን ጦርነት ያስነሳው አዶልፍ ሂትለር ምንም አይነት ምህታታዊ ኃይል አልነበረውም፤ ይልቁንስ ሃሳቡን እንዲፈፅሙለት ለጦርነት ከሚያስፈልገዉ ትጥቅና ስንቅ ዝግጅት በላይ ቃላትን ተጠቅሞ ነበር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሠራዊት ከጎኑ ማሰልፍ የቻላዉ።

እነ ማዘር ተሬዛ፣ ማህተመ ጋንዲ፣ ማንዴላ እና ማርቲን ሉተር ኪንግ የዚህችን ዓለም ጥቁር ጠባሳ ያከሙት በተአምራዊ ሀይል ሳይሆን መልካም እሳቤዎቻቸውን በቃላት በመግለጣቸው ምክንያት ነው።

ስለዚህ እኛም ለራሳችን ሆነ ለሌሎች የምንጠቀመውን ቃላት እንምረጥ ምክንያቱም ቃል ሊገነባን ወይም ሊያፈርሰን ይችላልና።

የመልካምነት ሳምንት ይሁንልን!

#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!

ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለም አቀፍ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት፤ የሬናሰንት ሪሃብ ሴንተር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ) በሱስ ዙሪያ የሰጡትን ማብራሪያ ያድምጡ።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በሃሳብ ብዛት መዋጥ/መወሰድ (Overthinking)

ማለት የትም ልንወስዳቸው የማንችላቸውን ነገሮች እየደገሙና እየደጋገሙ በማሰብ ማውጣትና ማውረድ፣ ከአስፈላጊው በላይና ከመጠን በበዛ ሁኔታ አንድን ነገር ሲያሰላስሉ መዋል ተብሎ ይገለጻል።

አንዳንድ ሰዎች አንድን ሃሳብ ከያዙ፣ አንድ መረጃ እጃቸው ከገባ፣ አንድን ነገር ከጠረጠሩ ወይም በአጠቃላይ በአንድ ጉዳይ ላይ ማሰብ ከጀመሩ ያንኑ ሃሳብ ይዘውና ሳይለቁ ሲያወጡትና ሲያወርዱት መዋልና ማደር ይቀናቸዋል፡፡

ይህ የአእምሮን ሞተር ካለልክ የሚያሰራ ሂደት በርካታ ለሆነ ክስረት ያጋልጣል፡፡

1. አእምሯችን ለቁም ነገር እንዳይውል ወጥሮ ይይዘዋል

በአንድ ሃሳብ የሚወሰዱ ሰዎች (Overthinkers) ያንን ከማድረጋቸው የተነሳ ሌላ ነገር ማሰብ ስለማይችሉ አእምሯቸውን ተጠቅመው ብዙ ማቀድና መስራት ሲችሉ መፍትሄ የሌለውን ነገር ሲያብሰለስሉ እምቅ ብቃታቸውን ያባክናሉ፡፡

2. ለጭንቀት ያጋልጣል

ሃሳብን የማይለቁ ሰዎች (Overthinkers) ራሳቸውን ለጭንቀት የማጋለጥ ሰፊ እድል አላቸው፡፡ ደጋግመው የሚያስቡት ሁኔታ ወደየት ሊሄድና ምን ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ጥጉ ድረስ ስለሚያስቡ ገና ያልሆነውንና ሊሆን የማይችለውን ሁሉ በማሰላሰል ይጨናነቃሉ፡፡

3. ለክስረት ያጋልጣል

ሃሳብን ማብሰልሰል (Overthinking) ምንም ነገር ብናደርግ መለወጥ የማንችላቸው ነገሮች ላይ እንድናተኩርና ጊዜን፣ የስነ-ልቦናና የስሜት ጉልበትን፣ እንዲሁም ገንዘብን እንድናባክን ያጋልጠናል፡፡

Overthinker መሆኔን በምን አውቃለሁ?

• አንድ ሃሳብ ላይ ከመጠመዴ የተነሳ ሌላ ነገር ማሰብ አለመቻል፤
• ፈታ፣ ዘና ለማለት አለመቻል፤
• ያለማቋረጥ መጨነቅ ወይም መጨናነቅ፤
• ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ነገር ላይ ማተኮርና እሱን ሲያስቡ ውሎ ማደር፤
• የአእምሮና የስሜት ዝለት ስሜት መጫጫን፤
• ብዙ አሉታዊ ሀሳቦች ማስተናገድ፤
• በአእምሮ ውስጥ አንድን ሁኔታ ወይም ልምምድ እየደጋገሙ ማጫወት፤
• የሁሉንም ነገር በጣም መጥፎ የሆኑ ጎኖች ማሰብ፡፡

🔹ነገርን አለመልቀቅ የለመደውን አእምሯችሁን እንደገና በማለማመድ ነገርን መልቀቅንና መተውን አስተምሩት፡፡

(በዶ/ር ኢዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆንን የመፍራት ህመም (anuptaphobia)

የፍቅር ግንኙነትን መፈለግ ተፈጥሯዊ ስሜት ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ከፍቅር ግንኙነት ውጪ ወይንም single መሆንን አጥብቀው ይፈራሉ። እንዲህ አይነቱ ህመም በሙያዊ አጠራሩ anuptaphobia ይባላል። ይሔ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ከዚህ በታች የተገለጹት ምልክቶች ይታዩባቸዋል፦

- የፍቅር ግንኙነት (relationship) ውስጥ ካልሆኑ በጣም ይጨነቃሉ። ይሄ ጭንቀት ሊቋቋሙት እስከማይችሉ ድረስ ይቆጣጠራቸዋል።

- የፍቅር አጋር አላገኝም የሚል ከፍተኛ ፍርሀት አለባቸው።

- ብቻቸውን ላለምሆን ሁሌም ቢሆን የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ። ብቸኝነትን ከመፍራታቸው የተነሳ ጤናማ ያልሆነና እንደማይቀጥል የሚያውቁትን የፍቅር ግንኙነት ይጀምራሉ።

- ጤናማ እንዳልሆነ የሚያውቁትን የፍቅር ግንኙነት ለማቋረጥ ይቸገራሉ።

- ብቸኝነታቸውን ከመፍራታቸው የተነሳ ያላቸውን የፍቅር ግንኙነት ለማቆየት ሲሉ ሊከፍሉት የማይገባውን ዋጋ ይከፍላሉ።

- የፍቅር ግንኙነታቸው ሲቋረጥ ለራሳቸው ጊዜ አይወስዱም። ይልቁኑ በጣም በፍጥነት ወደ ሌላ የፍቅር ግንኙነት ይሸጋገራሉ።

- ሁሌም ራሳቸውን ከሰዎች ጋር ያነጻጽራሉ።

የህመሙ ምክንያት

- ከልጅነት ጀምሮ የመጣ ያለመፈለግ ስሜት

- ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት

- በልጅነት ያጋጠመ የስነ ልቦና ቁስል

- ማህበራዊ ተጽዕኖ በጥቂቱ ሊገለጹ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

መፍትሄ

- ፍርሀቱና ጭንቃቱ ከየት እንደመጣ መለየት።

- የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆን ያለመፈለግ መገለጫ እንዳለሆነ መገንዘብና ለራስ ጤናማ ግምት መስጠት።

- የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆን ጤናማ የህይወት አንዱ ደረጃ እንደሆነ ማስታወስና ይሄን ጊዜ ራስን ለማሳደግ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነትንና መንፍሳዊ ህይወትን ለማበልጸግ መጠቀም።

- ከማህበረሰብ የሚሰነዘሩ ምክንያታዊ ባልሆኑ ሀሳቦች አለመሸማቀቅ።

- የስነ ልቦና ምክክር አገልግሎት መውሰድ ተጠቃሾች ናቸው።

🔹"ሰዎች የሚሉት ሳይሆን እኛ ስለራሳችን የምንለው ህይወታችንን ይወስናል።''

ለማንኛውም የስነ ልቦና ድጋፍ ይደውሉልን: 0967678832

(ፍካት የስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት)

በኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የትራማዶል መድሀኒት ሱስ

አንዳንድ ለህመም ማስታገሻ የሚታዘዙ መድሃኒቶች ሱስ የማስያዝ ባህሪ ያላቸው መሆኑን ያውቃሉ?

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ትራማዶል የተባለው የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ከፍተኛ የሆነ አላግባብ የመጠቀምና የሱስ ችግር እያስከተለ በመሆኑ በልዩ ማዘዣ በሀኪም እንዲታዘዝ ተወስኗል።

በዚህ ጉዳይ ፎርቹን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ትራማዶል በወጣቶቻችን ላይ እያደረሰ ስላለው ጉዳት ሙሉ የፊት ገፁን የሸፈነ ፊቸር ዘገባ አውጥቷል፤ የፕ/ር ሰለሞን አስተያየትም ተካቶበታል።

ሙሉ ዘገባዉን ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጠቀም ያንብቡ። ⬇️

https://t.co/sLCg6CXArg

ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት፤ የሬናሰንት ሪሃብ ሴንተር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

''አዲስ ዓለም'' ቅጽ አንድ መጽሃፍ በገበያ ላይ ዋለ!

ይህ መጽሃፍ የተጻፈው በኦቲዝም ስፔክትረም ዲሶርደር ላይ ትኩረት አድርጎ በወላጆች ተመክሮ ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ታሪክ ነው።

ለትምህርት ቤት፣ ለራስዎም ሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ ለመስጠት ከፈለጉ ይዘዙ 0911619018።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የሳይኮሎጂ ወርክሾፕ

ርዕሰ: አስተዳደግ እና የፍቅር ሕይወት

ህዳር 18, 2015 ዓ.ም ይጀምራል

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ጤና ጉዞ በኢትዮጵያ

The Mental Health Journey in Ethiopia

Sunday Nov 20, 2022

⏰ 6-8pm EAT

join and learn about the current status and how you can be part of the journey! ⬇️

https://www.clubhouse.com/join/yetena-weg-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%8B%88%E1%8C%8D/ZfJuejkN/xl4ebD6J?utm_medium=ch_invite&utm_campaign=dHk72pK_MnwV60Z47hgdzg-461102

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አንድ ሰው የአልኮል መጠጥ ሱስ እንዳለበት እንዴት እናውቃለን?

1. የሚጠጣውን መጠንና ጊዜ መቆጣጠር ያለመቻል (loss of control over drinking)

2. ከባድ የመጠጥ አምሮት (craving)

3. ሰቅዞ የሚይዝ (የሚያስጨንቅ) መጠጥ የመጠጣት ግፊት (compulsive desire to drink alcohol)

4. በመጠጥ ምክንያት የማህበራዊ፣ የጤና፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች መቃወሶች መከሰት (adverse consequences due to alcohol)

እነዚህ 4ቱ (4Cs ይባላሉ:- control, craving, compulsion, consequence) ጥሩ ጥቁምታ የሚሰጡ ሲሆኑ ችግሩን በሚገባ ለመረዳትና ተገቢውን ድጋፍ ለማግኘት ባለሙያ ያማክሩ።

የአልኮል ሱስ በህክምና የሚድን በሽታ ነው!

(Renascent Mental Health & Rehab center)

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel