melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አዲሱ የአልዛይመር መድሃኒት!

ኢሳይ እና ባዮገን በተሰኙ ሁለት የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች የተሰራውን «ለካነማብ»/lecanemab/ ወይም በገበያ ስሙ ለኬምቢ /Leqembi/ በመባል የሚጠራውን ይህንን መድሃኒት ትልቅ ስኬት ነው ይሉታል። የብሪታኒያ የዴሜንሽያ ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ባርት ዲ ስትሮፐር። 

''ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት አልዛይመር በዘር የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን፤ «አሚሎይድ ቤታ» በመባል የሚታወቀው መደበኛ የአንጎል ፕሮቲን የሰዎች ዕድሜ እየገፉ ሲሄድ ብዙውን ጊዜ አሚኖፕሮቲን ወይም አሚሎይድ ወደሚባሉ ጎጂ ቅሪቶች ይቀየር እና በአንጎል ውስጥ ይከማቻሉ። ይህ የጎጂ ህዋሳት ክምችት የነርቭ ህዋሳትን በመግደል እና የአንጎልን ስራ በማደናቀፍ የማስታወስ እና የማገናዘብ ችሎታን ያሳጣል። የአዲሱ መድሃኒት ስራም ሰውነት እነዚህን ንጣፎች እንዲያጸዳ መርዳት ነው።'' -ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ (አዲክሽን ሳይካትሪስት)

https://p.dw.com/p/4MNsd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ደስታን ከየት ነው ምናገኘው?

የወደፊት ማንነታችን የተሻለ እና ደስተኛ አና ሕይወታችን ጣዕም እንዲኖረው ግዜአችንን እና ጉልበታችንን ምን ላይ ብንሰራ የተሻለ ይሆናል?
የሚሉት ከዘመን ዘመን ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ጥያቄዎች በጥናት ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል።

ከወደ ምዕራቡ ከእውቁ ሀርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተጠናው ጥናት እና ምርምር ምናልባትም በግል በሰው ሕይወት ዙሪያ ላይ ከተሰሩ ጥናቶች በአለም ደረጃ ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ ከተከወኑት ውስጥ በመሪነት የተቀመጠ ነው፡፡ ይህ ጥናት በ724 ሰዎች ላይ ከወጣትነት ማለትም ከአስራዎቹ እድሜ ክልል ጀምሮ እስከ ጎልማሳነት እና እርጅና እድሜአቸው የቀጠለ ጥናት ነው፡፡ ጥናቱም ለሰባ አምስት (75) አመታት የዘለቀ ከመሆኑም በላይ አሁንም ጥናቱ እንደቀጠለ ነው።

ታዲያ ከዚህ አንድ ምዕተ አመት ሊሞላ ጥቂት እድሜ ከቀረው ጥናት ምን ተገኘ? በተሳታፊዎቹ ሙሉ የሕይወት ሂደታቸው ውስጥ ከወጣትነት እስከ እርጅና ድረስ በሳይንሳዊ ዘዴ ከተቀዳው ምንስ ያስተምረናል?

ከዚህ ከ75 ዓመት በላይ በፈጀ ጥናት የተገኘው ቁልጭ እና ግልጥ ያለው መልስ ጤናማና ደስተኛ አርጎ የሚያቆየን ጥሩ ግንኙነት (Good relationship) ነው፡፡ ከምን ጋር አትሉም? ትልልቅ ሶስት አንኳር ነጥቦችን አስቀምጧል፡፡

1ኛው፦ ግንኙነታችን ከማህበራዊ ጋር ያለው መስተጋብር ሲሆን ከተሳታፊዎቹ ከተሰበሰበው መረጃ ውስጥ ጥሩ የሚባል ማህበራዊ ግንኙነት ሕይወት ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ደስተኞች ከመሆናቸውም በላይ በተጨማሪ በአካል፣ በጤንነት እና ከተመዘገበው የእድሜ ጣሪያ በመኖር የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

በአንጻሩ ግለኛ እና ብቸኛ ሆነው ከተመዘገቡት ተሳታፊዎች በሕይወታቸው የሚያጣጥሙት ደስታ እጅግ ያነሰ ነበር፡፡ ከዚያም በላይ ግን በተለይ ወደ ጎልማሳነት እድሜዎቹ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት የአካላዊ ጤናቸው ላይ እና የአንጎል ስርአተ መስተጋብር ላይም አሉታዊ ተፅኖ አሳድረዋል፡፡
እንግዲህ ከሚያሳዝነው ነገር እንደ ዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት በቅርቡ ካወጣው መረጃ ውስጥ በአለማችን ከ5 ሰው ውስጥ አንድ ብቸኛነትን ሪፓርት አድርግዋል ይላል፡፡

2ኛው፦ አንኩዋር ነጥብ ከጥናቱ የተገኘውም በብዙ ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ስላለን ወይም ታማኝ የትዳር አጋር ስላለን ሳይሆን ትልቁ ቁም ነገር ያለው በመሀከላችን ያለው የግንኙነቶችን ጥራት (relationship quality) ላይ የወደቀ ነው፡፡ ስለዚህም በአብዛኛው በግጭቶች እና ባለመግባባቶች በስራ፣ በትዳር፣ በትምህርት በሌሎችም ከተከበበ የሚታወከው ሳይኮሎጂካል ጤናችን ብቻ ሳይሆን አካላዊ ጤንነትም ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያድርበታል ማለት ነው፡፡

ይህንን ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ከተጠቀሙት የምርምር ዘዴዎች መካከል፡-

በጥናቱ ሙሉ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል በሰማንያ እድሜ ክልል ውስጥ የደረሱትን መረጃ በመያዝ እነዚሁ ሰዎች በጎልማሳነት (ከ 45 በላይ) እድሜ በነበሩበት ሲመሳከር የወደፊት ጤንነታቸውን በተሻለ የተነብይ የነበረው በደማቸው ውስጥ ያለው ኮሌስትሮል አልነበረም፡፡ የሆነው ግን በቀጥታ ተያያዥ ሆኖ የተገኘው ግን የነበራቸው የግንኙነት ጥራት (relationship quality) ነበር፡፡ 

ከተመዛገቡት መረጃዎቹ ውስጥ አንዱ ደስተኛ ከተባሉት ውስጥ በሰማንያ እድሜ ክልል ውስጥ ከገቡ በኋላ አካላዊ ህመም በሚሰማቸው ወቅት ያሉበት የደስታ መጠን ሲለካ የነበረበት ላይ ወይም ለውጥ ሳያሳይ እዛው ደስታ ደረጃ ላይ ነበሩ፡፡ በተፃራሪው ደስተኛ ካልነበሩት ውስጥ በተመሳሳይ እድሜ (80ዎቹ) ውስጥ ሆነው አካላዊ ሕመም ሲያጋጥማቸው በተጋነነ መልኩ ስሜታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ አድርጎ ታይቷል፡፡

3ኛው፦ ትልቁ አንኳር ነጥብ ጥራት ያለው ግንኙነት የአካላችን ጤንነት ብቻ የጠበቀ ሳይሆን የአንጎላችንንና የእምሯችን ስርዓት-ትግበራም ላይ ጭምር ነበር፡፡ ከዚህም ውስጥ ጥራት ያለው ጥሩ ግንኙነት ውስጥ ካሉት– በችግር በሚያጋጥሟቸው ወቅት ወይም ሰው እንዲደርስልን በሚያስፈልገን ወቅት በርግጠኝነት የደርሱልናል ብለው የሚያምኑት ሰዎች አሉን ያሉት በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉት የላቀ የማስታወስ ክህሎት አስመዝግበዋል፡፡ በተቃራኒው የለንም ያሉት እጅግ ያነሰ ሆኖ ተመዝግብዋል፡፡

ይህም ጤናማ የሆነ ጥሩ ግንኙነት ማለት ከጥል ወይም ከአለመግባባት የፀዳ ብቻ ማለት ሳይሆን ስንቸገር ወይም ሰው ሲያስፈልገን የደርስልኛል ብለን አመኔታ የጣልንበት ግንኙነት መመስረት መቻላችን ነው ማለት ነው እንግዲህ፡፡

ስለዚህ የዚህ ጥናት መልዕክት ጥራት ያለው ጥሩ ግንኙነት የጤናችንና የደስታችን ብሎም የሕይወታችን የጣዕም ምንጭ ነው፡፡ ይህንንም ክህሎት ማካበት የሕይወት ትልቁ ጥበብ ነው፡፡

እናንተስ ይህን የምታነቡት ምናልባት እድሜያችሁ አንበል 18 ወይ 25 ወይ 35 ወይ 50ዎቹ የግንኙነታችን ጥራት ከስራችን ወይም ትምህርት፣ ከጓደኛ ወይም ከትዳር አጋራችን፣ ከቤተሰብ፣ ከተፈጥሮ፣ ከመንፈሳዊነት፣ ከማህበረሰቡ፣ ከራሳችን በጠቅላላ በዙርያችን ካሉ ነገሮች ጋር ያለን የግንኙነት ጥራቱ ምን ይመስላል?

ያፌት ከፈለኝ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት) አብርሆት ሳይኮሎጂካል መአከል
#የጤናወግ 

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ በተያዘው የትምህርት ዘመን በሶሻል ሳይኮሎጂ እና በዴቨሎፕመንታል ሳይኮሎጂ የሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ይጀምራል።

በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ለመማር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች እስከ ጥር 30/2015 ዓ.ም ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

አመልካቾች የሚከተሉን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-

• ሁለተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት

• ተዛማጅ የሥራ ልምድ

• ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ

• የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል

• የሁለተኛ ዲግሪ 3:00 CGPA ያለው/ያላት

• በሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፍ ውጤት ቢያንስ 'ጥሩ' ያለው/ያላት

(የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የስልጠና ማስታወቂያ!

(AMSH CPD Center)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ ራስን ማወቅ ስልጠና ጥር 13/2015 ይጀምራል!

ቆሞ ማሰቢያ፣ ብዙ ጥያቄዎችን መመለሻ፣ የንቃት መነሻ የሆነ ስልጠና በማይንድ ሞርኒንግ!

ለመመዝገብ: 0912333020/ 0935545452

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለአዕምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

የሰው ልጅ ልቡን ሲያመው አዕምሮው ልብህን አሞሃል ሃኪም ቤት ሂድ ይለዋል። ሌሎች የሰውነት ክፍሉን በአንዳች ምክንያት ጤናው የተጓደለ ሲመስለውም ለችግሩ መላ እንዲፈልግለት አዕምሮው ይወተውተዋል።

አእምሮውን ሲታመም ግን ታመሃል ብሎ የሚነግረው አይኖርም። በዚህም ምክንያት የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ይቸገራል።

ምክንያቱስ? ቢሉ የተጓደለውን ነገር ዐውቆ እና ተረድቶ የሚናገረለት አዕምሮው ራሱ ችግር ላይ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ችግሩን የሚያውቅለት እና የሚረዳለት ሌላ ወዳጅ የሆነ የሚገነዘብለት አካል ያስፈልገዋል ማለት ነው።

በአለም ጤና ድርጅት ትርጓሜ የአዕምሮ ጤናን "Mental health is a state of well-being in which an individual can realize his or her own abilities, interact positively with others, cope with the stressors of life and study, work productively and fruitfully, and  contribute to his or her family and community.” ይለዋል። ይህን ማድረግ ሲሳነው ነው የአእምሮው ጤንነት ጥያቄ ውስጥ የሚወድቀው።

በአገራችን ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሰው የአዕምሮ ህመም ተጠቂ እንደሆነ አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ። (Research Gate በኢትዮጵያ በአዋቂዎች ዘንድ 18 በመቶ በልጆች ደግሞ 15 በመቶ የአእምሮ ህመም ተጠቂ አለ ይላል)።

አንድ ወቅት ደግሞ የተጠና የ common mental Disorder ን 27 በመቶ በሚል ተጠቅሶ ነበር።

በአገራችን ስለ አዕምሮ ህመም እውቀት እና ግንዛቤ እምብዛም በመሆኑ ምክንያት ችግሩ በስፋት ሊታወቅ አልቻለም። ለዚህም ምክንያት አንዱ በዘርፉ የተሰማሩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች አለመኖር ትልቁ እንደሆነ ይታመናል።

አሁን ላይ ያሉት የባለሙያዎች ቁጥር  Psychiatrists 63 ,Psychiatric Nurses 525 ,Occupational Therapists 1, Psychologists engaged in clinical services 14 ,Social workers engaged in clinica services 3 መሆናቸውን ነው አንዳንድ ቦታ በመረጃ የተጠቀሱት።

ይህ ቁጥር የሙያተኞች ቁጥርን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይጠቁማል። ከዚህ የጨመረ እንኳን ቢሆንም ብዙ የራቀ ግን አይደለም።

አብዛኛው ህሙማን የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ እና ችግሩ ሳይታወቅላቸው የተጎዱ ራሳቸውን የሚያጠፉ ብሎም ሌላውን ስው የሚጎዱ ብዙዎች ናቸው።

ማኅበረሰቡም ታማሚውን ሰው ከማገዝ ይልቅ" ባህርይው ነው! እብድ ነው! ጨልሏል! ንክ ነው!" እያለ ችግሩን ያባብሰዋል።

እነዚህ ህሙማን ራሳቸው እርዳታ ፈላጊ ሆነው ሳለ እንደ ጤነኛ ሰው በተለያየ ሁኔታዎች ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ብቃትን የሚጠይቅ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ምክንያት ምርት እና አገልግሎት ላይም የሚያደርሱት አሉታዊ ጫና ነገሩን ከባድ ያደርገዋል።

የአእምሮ ጤና ከሌለ ጤና የለም!!!
(Kefelegn Hailu ZeBihere Sew)
#PsychAddis

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

JACK MA

በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው።

ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡- ‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።

ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው። ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት  መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!

እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል?

በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’ ይላል ጃክ ማ።

እውነት ነው እኛም አገር ያለው ነባራዊ እውነታ ይሕ ነው። ምክንያቱም ተቀጥረህ በምታገኘው የወር ደመወዝ ሀብት፣ ጥሪት፣ ቤት እና ራስህን ለውጠህ ሌላ ሰው መርዳት አትችልም። እርግጥ ነው የወር ደመወዝ ሲኖርህ የምትፈልገውን ማድረግ ባትችልም በገቢህ ልክ መኖርን ትለምደዋለህ።

ለማንኛውም በሥራ ፍለጋ ጊዜ ከማባከን በትንሹም ቢሆን የግል ስራ የምትጀምሩበትን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።

(Getu Temesgen)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከራስ ...ለራስ... የተፃፈ ደብዳቤ!

ለተከበርከው ወድ እኔ እንዴት ከረምክ?...

ዛሬ ለውጥ የምትጀምርበት ልዩ ቀንህ ነው። መጪው ምን ይዞ እንደሚመጣ አይታወቀም፣ አንተንም ምን እንደሚጠብቀህ በእርገጠኛነት አላውቅም፣ ነገር ግን ዕቅዶች አሉህ፣ ልታሳካቸው የሚገቡ ሕልሞች እና ግቦች አሉህ።

እስከዛሬ ድረስ ለነበረህ ፅናት፣ ታጋሽነት፣ አይበገሬነት እና ለፈፀምከው አኩሪ ጀብድ ከልቤ አደናቆቴ ይድረስህ።

አምናለሁ ጥሩ ተዋጊ ነበርክ!

በትግልህ ፅና ደግሞም በብርታትህ ቀጥልበት፣ ምክንያቱም ለህልምህ እውን መሆን በምታደርገው ጥረት ሳቢያ ደስታ እና ሰላም አንተ ጋር ውለው ያድራሉ።

አየኽ! ከጠነከርክ አለም የምትሰጥህን ብቻ እየተቀበልክ ከመኖር ወጥተህ አንተ የምትፈልገውን በማግኘት ትርጉም ያለው ህይወትን መምራት ትችላለህ።

ውድ እኔ!...

አየህ እንዲህ ህይወትህን በሥርዓት መምራት ስትጀምር በሌሎች ላይ መተማመንህ ይቀርና በራስህ መቆም ትጀምራለህ።

በህይወትህ የተለያዩ ሰዎች እንደሚመጡ እና እንደሚሄዱ ተምረሃል፣ በዛው ልክ ለሌሎች ፍቅርን ለመስጠት ስታስብ በመጀመሪያ እራስህን በፍቅር መሙላት እንዳለብህ እንዳትዘነጋ።

ውዴ!...

እራስህን በበቂ ሁኔታ ካልወደድክ እንደምንስ ሌሎችን መውደድ ይቻልሃልን?

በእርግጥ አንዳንዴ፣ ለራስህ በፈጠርከው ባዶ ህልም የቀን ቅዠት ውስጥ ከመስመጥ ይልቅ ነባራዊውን የገሀዱን አለም በማስተዋል ለመገንዘብ መሻት በእጅጉ ይጠቅምሃል።

አየህ ውዴ!

ላጋጠሙህ መጥፎ ገጠመኞችህ የአንተ ድርሻ የሚናቅ ባይሆንም ግን መጭው ጊዜ ለተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ራስህን ተጠያቂ በማድረግ የምትቆዝምበት ሳይሆን ለራስህ የተሻለውን ሁሉ ለማድረግ አሀዱ ብለህ የምትጀምርበት ጊዜ ነው።

ውድ እኔ !...ተመልከት

እስካሁን ባለው ትግልህ እዚህ ደርሰሀል...ነገር ግን ጥያቄው "ላንተ የሚገባው ይሄ ብቻ ነው ወይ?" ነው።

ስለዚህ ከአሁን ጀምረህ ለራስህ እወቅበት፣ ገና ብዙ ይቀርሀል እና በጭራሽ ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ ዛሬ አንድ እርምጃ ወደፊት የምትራመድበት ቀን ነው እናም በቁርጠኝነት እግርህን አንሳ፣... ማከናወንህንም ቀጥል።

አበጀህ!

ተላከ "ከትላንት የተሻለውን ህይወት ከምኖረው እኔ!"

ጥበብ እና ማስተዋል ለሰው ልጆች ሁሉ!

ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለም አቀፍ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዲፕሬሽን ቀልድ አይደለም!

ወቅቱ 2012 ዓ.ም እራሴን ከሰው መነጠል፣ ረዥም ሰአት ማልቀስ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ (ከ55ኪሎ ወደ 42 በሳምንታት የወረድኩበት) እንቅልፍ ፈፅሞ ማልተኛበት ከፍተኛ ድካም የሚሰማኝ ጊዜ ነበር።

አስታውሳለሁ ማታ ማታ መድሀኒአለምን "እባክህ ተለመነኝ ሁሉ ይቻልሃል እና ነገን አታሳየኝ" ብዬ የለመንኩት ልመና፤ አስታውሳለሁ እናቴ ምግብ አልበላም ብዬ መኝታ ቤት ሳለቅስ "ቅብጠትሽ ወሰን አጣ!" ብላ ስትማርር፤ አስታውሳለሁ የተሰማኝን ባዶነት አስታውሰዋለሁ ቅድም እንደጠጣሁት ቡና!

ዕድለኛ ነበርኩ። አባቴ፣ እህቴ ቤተል፣ ጥሩ ባልሆንላትም ሳይኮሎጂስት ማርታ ከጎኔ ነበሩ። እናቴም በኋሏ ነገሩን ስትረዳ ቅርቤም ረዳቴም ሆናለች። ብቻ ሁሉም አግዘውኝ ሳይካትሪስት አየኝ የመጀመያ ቀን ምርመራ ክፍሉ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ነው ፀጥ ረጭ ያለ፤ የሀኪም ቤት ፒጃማ የለበሱ ተኝተው የሚታከሙ ሰዎች ውር ውር ይላሉ ሀኪሜ ጋር ስገባ በባዶነት ደሞም በፍርሀት ስሜት ነበር። የአዕምሮ ህመምተኛ የሆንኩ መሠለኝ የአዕምሮ ህመም ደሞ ያስፈራል። ጨጓራ ወይም ኩላሊት እንደመታመም አይደለም ብዙ የተዛባ ነገር አለ በማህበረሰቡ...

ሀኪሜ በእንባ የታጀበ ረዥም ደቂቃ የፈጀ ገለፃዬን ከሰማ በኋሏ፤ ስለዲፕረሽን እንዲሁም ስለሚሰጠኝ ትሪትመንት ነገረኝ። መድሀኒት ሰጠኝ (የእንቅልፍ እና ሆርሞን ማስተካከያ)። ድብርት ስሜት ብቻ ሳይሆን ድባቴ ሆኖ ህመም ይሆናል። በህመም ደሞ አይቀለድም። ራሴን አመመኝ ሲባል ይቀለዳል? ከዛ ከባዱ ጊዜ ቀስ በቀስ አለፈ። ደሀ ሀገር ነው ያለነው ሳይካትሪስት ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል ቢያንስ ግን በሰው ህመም አንቀልድ፤ በሰው ቁስል እንጨት አንስደድ ትከሻ ባናውስ ቀልብ አንግፈፍ፤ ድካም ባናግዝ እንጥፍጣፊ ጥንካሬ አንንጠቅ።

(Sara Ahmed)
via: ዶ/ር ዮናስ ላቀው

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስሜ ሃኒም ይባላል በሙያ ጤና መኮንን አና የመንግስት ሰራተኛ ስሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማስተርስ እማራለው ... ነገር ግን ADHD (Attention Deficit Hyperactivity Disorder) የተባለ ችግር ተጠቂ ነኝ።

3 ጊዜ ባለሙያ ፊት ቀርቤ መዳኒት የታዘዘልኝ ቢሆንም መዳኒቱ አገር ውስጥ በጭራሽ የለም። ከውጪ ለማግኘት ብሞክርም ከአንድ አመት በላይ ባፈላልግም አላገኘውም። ከሁሉም በላይ ያሉኝ ህልሞች እንቅልፍ ይነሱኛል። ለሃገሬ ብዙ የመስራት ህልም እና ፍላጎት አለኝ... ነገር ግን በማይታይ ስውር ሰንሰለት ጥፍር አርጌ አንደታሰርኩ ይሰማኛል።

ወይ ሚታይ ነገር አይደል ነገር  ሰው አይቶ አይደርስልኝ፣ ይረዱኛል ብዬ ያወራሁዋቸው ሰዎች ራሱ የባህሪ ችግር ስልሚመስላቸው በምክርና በወቀሳ ይመልሱልኛል። ለነገሩ እኔ ራሱ ህመም መሆኑን ማመን ይከብደኛል። ስለዚም ራስን መውቀስ እና ራስን ከሊሎች ጋር እያወዳደሩ መናደድ የቀን ልምዴ ነው። 

በዚ የሩጫና የፉክክር አለም ታትሮ መስራትን እየፈለጉ በቀላሉ መስተካከል በሚችል ህመም መቸገር ያሳዝናል። ችግሬ ሳይታወቅልኝ በፈጣሪ እገዛ እዚ ብደርስም ከዚ በላይ በዙ የመስራት አቅም ነበርኝ። አሁን ግን ከብዶኛል!!!
  
የሚመለከታቸው አካላት መዳኒቱ ወደ ሀገር መግባት የሚችልበትን መንገድ ቢፈልጉ፣ እንዲሁም የግል መዳኒት አስመጪዎችም ቢያስገቡልን ትልቅ እርዳታ ነው። 

በተጨማሪም መዳኒቱን ማግኘት ምትችሉ (ከሃገር ውጪ) ያላችው ሰዎች ብታግዙን። እዚው ያላችሁም ብታካፍሉን... ከምንም በላይ ደሞ ወላጆች እና መምህራን ልጆቻችሁን በደንብ እንድትከታተሉ እና የተለየ ባህሪ ካላቸው ወደ ባልሙያ በመውሰድ እንድታማክሩ በጊዜ የታወቀ ነገር መፍትሄው ይቀላልና አደራ እላለው።

ትላልቅ ሰዎችም ብኖን ስለጤናችን መከታትልና ሃኪም ማየት ብዙ የብቻ ትግልን ይቀንሳል ብዬ አስባለው። በመጨረሻም ለብቻችሁ በተለያየ ችግር ውስጥ ያላችው ሰዎች ደፍራችው እንድቶጡ እና እርዳታ ጠይቁ .....  ለመምህራን፣ ለስራ ባልደረባ፣ ለቤተሰብ፣ ለሃኪም መናገር ወሳኝ ነገር ነው ሰዎች ከምናስበው በላይ ደግ እና ሚረዱን ናቸው። አየዞን፣ በርታ፣ ትችያለሽ፣ ጎበዝ..... መባል ራሱ ትልቅ ተስፋ ነው። የህመም ነውር የለውም፣ መቀበል ደሞ ትልቁ መፍትሄ ነው!!!

ያለ አእምሮ ጤና፣ ጤና የለም!
#ADHD #WENEEDMEDS #STIMULANTS #MOH #EFDA #MENTALWELLNES #AWARENESS #Hakim

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የማነብ ኃይል (The power of visualization)

አእምሯችን በገሃድ ዕውነታና በምናባችን ውስጥ በምንፈጥረው ዕውነታ መካከል ያለውን ልዩነት አይረዳም። ይህ ማለት አንድን ያልተፈጠረ ነገር ወይም በትውስታችን የነበረን ነገር በምናባችን ውስጥ ጥርት አድርገን ማየት ከቻልን አእምሯችን ያ ምናባዊ ዕውነት ገሃዳዊ ዕውነት እንደሆነ ያስባል።

ከዚህ የተነሳ በአእምሯችን በፈጠርነው ምናባዊ ምስል ምክንያት የሚሰሙን ስሜቶችና የምናሳያቸው ባህርያት ለዕውነተኛው ክስተት የምናሳየውን ዐይነት ይሆናሉ።

ስኬታማ ሰዎች እንዲህ ያለውን የማነብ ስልት አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት በመጠቀም የሚፈልጉትን ውጤት ያሳካሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የማይክል ፌልፕስ (Michael Phelps) የዋና አሰልጣኝ (ቦብ ቦውማን Bob Bowman) ውጤታማ የሚያደርግ የማነብ ስራ ለመስራት የመጀመሪያው ደረጃ ሰውነትን ፈፅሞ ማዝናናት (body relaxation) እንደሆነ ይናገራል።

ከዚያም ማይክል ወደፊት የሚፈልገውን የማሸነፍ ሂደትና ውጤት በአእምሮው ውስጥ በጣም ጥርት ባለና ዕውነት በሚመስል መልኩ በመመልከት በምናቡ ውስጥ እየደጋገመ ይለማመዳል።

ማይክል ይህን የማነብ ሂደት ከውድድር ቀን በፊት በየለቱ በመስራት አእምሮውን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ማንነቱና ሰውነቱን  ጥርጥር የሌለው ፍፁም የሆነ ማሸነፍ ስሜት ውስጥ ይዘፍቃል።

እንዲህ ያለ የማነብ ሂደት ለማይክል ፌልፕስ ከሃያ ስምንት በላይ የዋና ኦሎምፒክ ሜዳሊያዎችን እንዲያገኝና ሌሎች ብዙ እውቅናዎችን እንዲጎናፀፍ ረድቶታል።

ይህን በተፈጥሮ የተሰጠንን የማነብ ፀጋ እየተጠቀምንበት ነው ወይስ እሱ እየተጠቀመብን? (ልባም ሕይወት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ሊሞቱ የደረሱ ሰዎች የሚቆጫቸው 10 ነገሮች!

ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።

1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።

2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።

3) እራሴን አልተንከባከብኩም- ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።

4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው- ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?

5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም- ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።

9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም። ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።

10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።

ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል።

Via ዶ/ር ዮናስ ላቀው

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የድብርት/ድባቴ ህመም (Depressive disorders)

- ስርጭቱ ምን ይመስላል?
- ምክንያቶቹ ምንድናቸው?
- ስነ-ልቦናዊ ቀውሶቹ ምንድናቸው?
- ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ምንድናቸው?
- ምልክቶቹ ምንድናቸው?
- ህክምናው ምንድነው?

✍ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የስነ-አእምሮ ሬዚደንት ሃኪም)

ዝርዝሩን ያንብቡ: https://telegra.ph/የድብርትድባቴ-ህመም-Depressive-disorders-12-30

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለሌላው ኑር!

#ድባቴ ውስጥ ያለ ሰው እንዲህ ያስባል፡-

"በሄድኩበት ሁሉ ችግር ይገጥመኛል፣ ከዚህም ማምለጫ የለኝም፣ ወዴት እንደምጓዝ አላውቅም።"

ይህ ነው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ የሚገፋቸው። ተስፋን ይቆርጣሉ፣ ከዚህም የተሻለ ቀን እንደሚመጣ አያስቡም።

"በየትም አቅጣጫ ብዞር ማምለጫ የለኝም፣ ስቃዩን አልቻልኩትም፣ የማልረባ ነኝ ለማንም አልጠቅምም፤ ለሁሉም የሚሻለው እኔ ባልኖር ነው" ብለው ያስባሉ።

ለሌላው መኖር አንተ ምክንያት መሆን አለብህ፡፡ ለማንም አልጠቅምም የሚለውን ሰው የምታድነው አንተ ነህ፡፡ ለአንተ ጠቃሚ መሆኑን በማሳየት፣ ግራ ለገባው መንገድ በመሆን፣ ተስፋ ለቆረጠ ተስፋ በመስጠት ለሌላው መኖር ምክንያት መሆን አለብህ፡፡

ለአንተም… ምክንያት የሆንክለት እሱ አለ፡፡ ሁላችንም ተስፋን በመሰጣጠት፣ የተሻለ ቀን እንዳለ በማሳየት አንዳችን ለሌላችን መኖር አለብን፡፡

(የሕይወት ቀመሮች መጽሐፍ)
(12 RULES FOR LIFE)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዛሬ ቀንህን እንዴት ጀመርከው?                               
ዛሬ ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ደስ ብሎህ ፈጣሪህ አዲስ ቀን ስለሰጠህ አመስግነህ ዛሬ የእኔ ቀን ነው፤ እኔ ማድረግ የምፈልገውን አደርጋለው! እኔ እችላለው! እኔ ድንቅ ነኝ! እኔ ከችግሮቼ በላይ ነኝ! ብለህ ነው? ወይስ ኡፍ ደሞ ነጋ ብለህ ችግሮችህን እያሰብክ ተሰባብረህ ነው ቀንህን የጀመርከው?

ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ያለህ የስሜት ደረጃ ነው ቀንህን የሚወስነው፤ መልካም ነገሮችን አስበህ ስትነሳ መልካም ነገሮች ወደ አንተ ይመጣሉ። ስለዚህ ጠዋትህን ደስ በሚል መንፈስ ጀምረህ ቀንህን ብሩህ አድርገው። (ዳዊት ድሪምስ)
 
የደስታ ቀን ተመኘን!                                       

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ Sitota Center for Mental Health Care and Rehabilitation!

Call for CPD training on Quality Improvement (QI)

For all health professionals

To register call: 0913597672

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ወላጆች የልጃቸውን እድገት እንዴት መደገፍ ይችላሉ?

ወላጆች የልጆቻቸው እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተጨማሪም የልጆች ተግባቦትን፣ ስሜትን፣ አካላዊና የአእምሮ እድገት ላይ ትልቅ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው።

ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፦

- በራስ መተማመን እንዲኖራቸው መደገፍ እና በራስ መተማመናቸውን መገንባት፤
- ልጅዎችን አበረታችና ደጋፊ ይሁኑ ግን  አይነቅፉዋቸው፤
- ልጅዎች ችግር እንዲፈቱ እና ውጤታማ የመቋቋም ችሎታን እንዲያዳብሩ ይርዷቸው፤
- ልጅዎች ሀላፊነቶችን እንዲወስዱ እና የፈጠራ ችሎታ እንዲኖራቸው ይፍቀዱ፤
- ከውድቀት እንዲማሩ ይርዷቸው፤
- ልጅዎች ስሜቶችን እንዲያስተካክሉ እርዷቸው፤
- ልጅዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነቶች ወይም ተግባቦቶች እንዲገነቡ ያድርጓቸው፤
- የራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲወስኑ ለልጅዎች እድል ይስጧቸው፤
- ለመማር አርአያ መሆን፤
- ልጅዎች የአስተሳሰብ ሂደታቸውን እንዲገልጹ ያበረታቷቸው፤
- ሐቀኛ ይሁኑ እና ከልጅዎ ጋር ግልጽ ንግግር ያድርጉ፤
- ልጅዎ ማለት የሚፈልገውን ወይም የሚናገረውን ያዳምጡ።

Mahlet Azene (Speech and language Therapist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#Dailytips

“ማንም ሰው ሳያምንብህ ሊሳካልህ ይችላል፣ ነገር ግን #በራስህ ካላመንክ በፍጹም አይሳካልህም” (William J. H. Boetcker)

መልካም የስራ ሳምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የዘመኑ ወጣት ፈተናዎች!

በዓለም ላይ ያሉ በርካታ ለውጦች፤ ለአዲሱ ትውልድ ጥሩ እድል ብቻ ሳይሆን ጫናም ፈጥሮባቸዋል የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር እና የህፃናት እና ወጣቶች የአዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ዮናስ ባህረ-ጥበብ ናቸው።

በተለይ የዋጋ ንረት፣ ኮቪድ ጥሎት ያለፈው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን በዋናነት የሚያነሱት ዶክተር ዮናስ ወጣቱ ሰው ከሰው ከሚያደርገው ግንኙነት ይልቅ ቴክኖሎጂ ላይ ሱሰኛ መሆን እና ግኡዝ ከሆነ ነገር ጋር ያለው ግንኙነት እንደሚያመዝን ይናገራሉ።

«ወጣቱ በዚህ በዓለም ላይ ባለው የመረጃ አቢዮት ምክንያት ሁሉም መረጃ ይደርሰዋል። ጀርመን ሀገር ካለው ወጣት ጋር ተመሳሳይ መረጃ እጁ ላይ አለ። ነገር ግን መሬት ላይ ያለው እውነተኛ ነገር ስልኩ ላይ ከሚያገኘው መረጃ ጋር በጣም የተለያየ ነው። መሬት ላይ ያለው ነገር፣ በቀን አንዴ መብላት የሚቸገር ሰው ያለበት፣ መጠለያ የሌለው፣ መንገድ ላይ ድህነት ተንሰራፍቶ ያለበት እና እውነታው በጣም የተለያየ በመሆኑ የእኛን ሀገር ወጣት ጭንቀት ይፈጥርበታል።»

ወጣቱ ወደ መጠጥ እና እፅ የሚገፋፋው አንድም በዚህ ጭንቀት ምክንያት በሌላ በኩል ደግሞ በመረጃ ፍሰቱ ምክንያት ወጣቱ እየተሳበ እንደሆነ ዶክተር ዮናስ ይናገራሉ፤ «ወጣቱ በቴክኖጂ በጣም ተስቦ የበለጠ ወደ መጠጥ እና እፆች እና ሱሶች ሊሳብ ይችላል»

ወጣቱ ወደተሻለ መንገድ እንዲጓዝ የህፃናት እና ወጣቶች የአዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ዮናስ በዋናነት የሚያሳስቡት ወጣቱ ከአለም ላይ የሚያገኘውን እውቀት ተጠቅሞ የሀገሪቷን ሁኔታ ያገናዘበ ትውልድ እንዲፈጠር መሰራት እንዳለበት፣ አዲሱ ትውልድ የበለጠ ኃላፊነት ተሰጥቶት እንዲሰራ ቢደረግ እና በቡድን የሚሰራበት መንገድ ቢመቻች መልካም እንደሆነ ነው። (DW)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ፒቮታል ሪስፖንስ ትሪትመንት/ Pivotal Response Treatment (PRT)

ይህ የህክምና (የቴራፒ) አይነት ጨዋታን መሰረት ያደረገ እና በልጆች አነሳሽነት እና መሪነት የሚካሄድ ሲሆን፤ የአፕላይድ ቢሄቪየር አናላይሲስ (Applied Behavior Analysis (ABA) መርሆችን መሰረት አድርገው ከተዘጋጁት የባህሪ ህክምና አይነቶች መካከል አንዱ እና፤ በአሁኑ ጊዜ በዘርፉ በስፋት በማገልገል ላይ ያለ የባህሪ ህክምና አይነት ነው፡፡

የዚህ የባህሪ ህክምና ግቦች ናቸው ከሚባሉት ውስጥ፡-

-የተግባቦት እና የቋንቋ ክህሎትን ማሳደግ
- አዎንታዊ (positive) የሆነ ባህርይን ከፍ ማድረግ
- አላስፈላጊ የሆኑ እራስን የማነቃቂያ (self-stimulatory) ባህሪዎችን እንዲቀንሱ ማድረግ ይገኙበታል፡፡

ይህን የባህሪ ህክምና የሚሰጡ ባለሞያዎች፤ ከአንድ ልጅ ባህሪዎች መካከል አንድን ባህሪ ብቻ ነጥሎ፤ እዛ ላይ ከመስራት ይልቅ፤ ከልጆች እድገት ውስጥ “ዋና” (“pivotal”) የሆኑ ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ህክምናውን ያካሂዳሉ፡፡ እነዚህ ባለሞያዎቹ በልጆች እድገት ውስጥ አስፈላጊ ናቸው በሚሏቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፤ የሚሰጡት የ PRT የባህሪ ህክምናዎች፤ ማህበራዊ ክህሎት፣ ተግባቦት፣ ባህርይ እና የልጆች የመማር አቅም ላይ ጉልህ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡

የ PRT ዋና (አስፈላጊ) የሚባሉት ቦታዎች፡- Motivation, Response to multiple cues, Initiation of social interactions, Self-management እና Empathy ናቸው፡፡

የማነሳሻ መንገዶች (Motivation) የ PRT ዘዴ ወሳኝ ክፍሎች ናቸው፡፡ ይህ ዘዴ ተፈጥሮአዊ ማበረታቻዎችን የሚጠቀም ሲሆን ለምሳሌ፡- አንድ ኦትስቲክ ልጅ የእንስሳ መጫወቻን ለመጠየቅ ሙከራ ቢያደርግ (“ስጠኝ ቢል”)፤ ለዚህ ሙከራው፤ ሽልማቱን (ማበረታቻውን) ሌላ ተያያዥ ያልሆነ፤ እንደ ከረሜላ ያለን ነገር ከመስጠት ይልቅ፤ የጠየቀውን እንስሳ እራሱ በመስጠት ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪ ይህ ዘዴ፤ ልጆች ትክክል ባይሆኑም፤ ጥሩ ሙከራ ካደረጉ መሸለም (መበረታታት) አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡

PRT ያደገው በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲዎቹ Dr. Robert L. Koegel እና Dr. Lynn Kern Koegel ሲሆን፡፡ ከዛ በፊት Natural Language Paradigm (NLP) በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ይህ የባህርይ የህክምና ዘዴ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ግልጋሎት ላይ መዋል እንደጀመረ ይገለፃል፡፡

የስነ-ልቦና ባለሞያዎች፣ የልዩ ፍላጎት መምህራን እና የንግግር እና ቋንቋ ህክምና ባለሞያዎች፤ የPRT ህክምናን መስጠት የሚችሉ እንደሆኑ ይገለፃል፡፡

የ PRT የባህርይ ህክምና ዘዴ ምን ይመስላል?

እያንዳንዱ ፕሮግራም፤ የግለ-ሰቡን ልዩ-ፍላጎት፤ ግቦችን እና የየእለት ተእለት ክንዋኔዎችን ፍላጎት እንዲያሟሉ፤ መሰረት ተደርጎ የሚዘጋጁ ናቸው፡፡ ቋንቋ፣ ጨዋታ እና ማህበራዊ ክህሎት፤ የዚህ የባህሪ ህክምና ባለሞያዎች፤ ከልጆች ጋር በመደበኛነትም ይሁን ከመደበኛው ውጪ በሚኖራቸው ግንኙነቶች፤ ትኩረት አድርገው የሚሰሩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

የልጁን አዎንታዊ ለውጥ መሰረት አድርጎ፤ የእያንዳንዱ የህክምና ክፍለ ጊዜ (session) ትኩረት፤ ሊለዋወጥ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት፤ ይበልጥ ሰፋ ያሉ ግቦችን እና የልጁን ተጨማሪ ፍላጎቶች ለማስገባት ሲባል ነው፡፡ የባህሪ ህክምናው እየተሰጠው ባለ ልጅ ህይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ፤ ይህንን የባህሪ ህክምና፤ በልጁ ህይወት በእያንዳንዱ ክፍል በቋሚነት እንዲተገብሩት ይበረታታል፡፡

PRT ብቁ ስለመሆኑ ምንድነው ማረጋገጫው?

PRT ለኦቲዝም በደምብ የተጠና እና የተረጋገጠ የባህሪ የህክምና ዘዴ ሲሆን፡፡ ከሃያ በላይ የሚድረሱ ጥናቶች ይህ የህክምና ዘዴ ኦትስቲክ ለሆኑ ልጆች የተግባቦት ክህሎትን እንደሚያሳድግ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ ጥናቶች ህክምናውን አንድ-ለአንድ (ባለሞያው እና ልጁ) ሆኖ ሲሰጥ የተመለከቱ ሲሆን፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በቡድን በትምህርት ቤት መምህራን እና የሰለጠኑ ወላጆች፤ ቤታቸው ውስጥ ሲተገብሩት የተመለከቱ ናቸው ፡፡

በ2017 የጭንቅላት ምስል ውጤቶች ላይ የተሰራ ጥናት ባመላከተው መረጃ፤ የPRT የባህሪ የህክምና ዘዴ፤ ከተግባቦት እና ማህበራዊ ግንኙነት ጋር ተያይዞ፤ የጭንቅላት እንቅስቃሴን እንደሚያሻሽል አረጋግጧል፡፡

(Psychology For Children)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ስጦታ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል!

በምስሉ ላይ የምታዩት አንዲት ታካሚ ህክምናውን ከማግኘቷ በፊት እና ካገኘች በኋላ ያለውን ልዩነት የገለጸችበት ድንቅ ጥበብ ያሳያል።

ሙሉ ስሜትን ለመግለጽ ቃላቶች አቅም በማይኖራቸው ጊዜ።

#sitota
#Artherapy

አድራሻ: ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 9፣ በጦር ሀይሎችና በቶታል (3ቁጥር ማዞሪያ) መካከል።

ስልክ: +251 11 369 28 18
         +251 11 369 27 74

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ ባህርዳር እና አካባቢዋ ለምትገኙ!

ሐሴት የአእምሮ ሕክምና!

ዶ/ር ግዛቸው አስናቀ (የአእምሮ ስፔሻሊስት ሐኪም)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በደም ምርመራ አልዛይመር መኖሩን ለማወቅ ሊቻል ነው!

አልዛይመር የመርሳት፣ የባህሪ መቀያየር፣ የመናገር ችሎታ ላይ ችግር የሚያመጣ የአይምሮ በሽታ ነው። ቤታ አማሎይድ የሚባል ፕሮቲን በአአምሮ ውስጥ መጠባበቅ አአምሮ ውስጥ የሚተላለፈውን ሲግናል ያዳክማሉ፤ አንዲሁም የአአምሮ ሴሎችን ይገላሉ።  ከዚህ በፊት ሳይንቲስቶች ይህን ፕሮቲን መጠን ለማወቅ የሚጠቀሙት ኣንጎልን ለማየት ዘመናዊ መሳሪያዎች በመጠቀም (brain imagings) ወይንም ከአከርካሪ አጥንት ላይ ያለ ፈሳሽን በመውሰድ ነበር። አነዚህን ምርመራዎች ማድረግ ደግሞ ውድ አና በቅርቡ የምናገኛቸው ሰላልሆኑ በኣልዛይመርስ ሊጠቁ ለሚችሉ ሰዎች በቀላሉና በመደበኛ መልኩ ምርመራውን ማድረግ ይቸገራሉ።

አሁን ግን በዋሺንግተን የህከምና ዩኒቨርስቲ በተሰራ ምርምር በቶሎ የኣልዛይመር በሽታን ለማሳወቅ የሚያስችል ተስፋ ሰጪ የደም መርመራ አንዳለ ይፋ አድርገዋል። ምርምሩ ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ በስፋት ከተለያዩ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎችንም በመጨመር መቀጠል አንዳለበት አሳውቀዋል። ጥናቱ ከቀጠለ የብዙ ሰዎችን ለመመርመር ያለውን ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል። #ዘጋርዲያን

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

YETENA WEG CLUBHOUSE DISCUSSION!

Topic: EXERCISE & MENTAL HEALTH

LET'S DISCUSS THE EFFECT OF EXERCISE ON MENTAL HEALTH WITH EXPERTS ON SPORT SCIENCE AND MENTAL HEALTH.

Sunday, Jan 08 at 6:00pm - 8:00 (EAT)
ከምሽቱ 12:00 - 2:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ)

Join with this link ⬇️

https://t.co/myOtm2CETO

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም የገና በዓል!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ ስጦታ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ ማዕክል!

ስልክ: +251113692818/ +251113692774
🔗 https://sitotapsy.com
📥 sitotapsych.info@gmail.com

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዳውን ሲንድሮም ምንድነው?

ዳውን ሲንድሮም Trisomy 21 ተብሎም ይጠራል።

ዳውን ሲንድሮም አንድ ሰው ከተጨማሪ 21ኛው ክሮሞዞም ጋር የሚወለድበት ሁኔታ ነው።

ክሮሞሶም በመቶዎች አልፎ ተርፎም በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖችን ይዘዋል። ጂኖች የእርስዎን ባህሪዎች (ከወላጆችዎ የተላለፉ ባህሪዎች) የሚወስን መረጃ ይይዛሉ፡፡

የዳውን ሲንድሮም መንስኤዎች፦

- የሰው ሴሎች በተለምዶ 23 ጥንድ ክሮሞዞም ይይዛሉ፡፡ በእያንዳንዱ ጥንድ ውስጥ አንዱ ክሮሞሶም ከአባት፣ ሁለተኛው ከእናት ነው፡፡

- ዳውን ሲንድሮም የሚከሰተው 21ኛውን ክሮሞዞም በተመለከተ ያልተለመደ የሕዋስ ክፍፍል ሲከሰት ነው፡፡
- እነዚህ የሕዋስ ክፍልፋዮች ያልተለመዱ ተጨማሪ ክፍሎች ወይም ሙሉ ክሮሞዞም 21 ያስከትላሉ፡፡ ይህ ተጨማሪ ክሮሞዞም ንጥር ለዳውን ሲንድሮም ሲንድሮም ባህርይ እና የእድገት ችግሮች ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
- ሦስቱ የጄኔቲክ ወይም ዘር ልዩነቶች ዳውን ሲንድሮም መንስዔ ሊሆኑ ይችላል፦

1.Trisomy 21.

- ከ95 ከመቶው ያህል ዳውን ሲንድሮም የሚከሰተው በትሪሶሚ 21 ነው።
- ልጆች በሁሉም የሕዋሳት ክፍል ከተለመደው ሁለት ቅጂዎች ይልቅ ሶስት የክሮሞሶም 21 ቅጅዎች አሉት። ይህ የሆነው የወንድ የዘር ህዋስ ወይም የእንቁላል ህዋስ በሚፈጠርበት ጊዜ ባልተለመደ የሕዋስ ክፍል ነው።

2. የሙሴ ዳውን ሲንድሮም
(Mosaic Down syndrome)


- ከባድ ዳውን ሲንድሮም በሚባለው በዚህ ያልተለመደ ሁኔታ አንድ ሰው ክሮሞሶም 21 ተጨማሪ ቅጂ ያላቸው ሴሎች ብቻ ይኖሩታል።
- ይህ የመደበኛ እና ያልተለመዱ ሴሎች ሞዛይክ ከእርግዝና በኋላ በተለመደው ሴል ክፍፍል ምክንያት ነው።

3. ትራንስሎኬሽን ዳውን ሲንድሮም

- ዳውን ሲንድሮም እንዲሁ የክሮሞሶም 21 የተወሰነ ክፍል ወደ ሌላ ክሮሞሶም ይያያዛል ወይም ፅንስ በሚተላለፍበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡
- እነዚህ ልጆች የተለመደው ሁለት ክሮሞሶም 21 ቅጂዎች አሏቸው፣ ግን ደግሞ ክሮሞዞም 21 ከሌላው ክሮሞሶም ጋር ከተያያዘ ተጨማሪ የዘረመል ይዘት አላቸው።

ዳውን ሲንድሮም የሚያስከትሉ የታወቁ ባህሪዎች ወይም አካባቢያዊ ምክንያቶች የሉም።

ምልክቶች፦

- ዳውን ሲንድሮም ያጋጠማቸው ሰዎች የእያንዳንዳቸው ሰዎች የአዕምሮ እና የእድገት ችግሮች መለስተኛ፣ መካከለኛ ወይም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- አንዳንድ ሰዎች ጤናማ ናቸው ሌሎቹ ደግሞ እንደ ከባድ የልብ ጉድለት ያሉ የጤና ችግሮች አሉባቸው፡፡
- ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች እና ጎልማሶች የተለያዩ የፊት ገጽታዎች አሏቸው፡፡
- ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሁሉም ሰዎች ተመሳሳይ ባህሪዎች ባይሆኑም፣ በጣም የተለመዱ ባህሪዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
- ጠፍጣፋ ፊት
- ትንሽ ጭንቅላት
- አጭር አንገት
- ምላስን ያስወግዳል
- ወደ ላይ የሚያንፀባርቁ የዓይን ሽፋኖች (palpebral fissures)
- ያልተለመደ ቅርፅ ወይም ትንሽ ጆሮዎች
- ደካማ ጡንቻ
- ሰፊ፣ አጭር እጆች በአንድ መዳፍ ውስጥ 
- በአንጻራዊ ሁኔታ አጫጭር ጣቶች እና ትናንሽ እጆች እና እግሮች
- ከልክ ያለፈ ተለዋዋጭነት
- ብሩሽፊልድስ ስፖትስ በሚባሉት የዓይን ክፍል በቀለማት ክፍል (አይሪስ) ላይ ትናንሽ ነጠብጣቦች
- አጭር ቁመትና የመሣሠሉት ናቸው።
በተጨማሪ፦
- የዳውን ሲንድሮም ምርመራ ልጅዎ ዳውን ሲንድሮም ካለበት ለይቶ ማወቅ ወይም መመርመር ይችላል።

- ዳውን ሲንድሮም ያለበት እያንዳንዱ ልጅ ልዩ ስለሆነ ሕክምናው በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ነው።

- በልጅዎ ልዩ ፍላጎቶች ላይ በማተኮር የዳውን ሲንድሮም ህክምና የሚከተሉትን የተወሰኑ ባለሙያዎችን ሊያካትት ይችላል፦
- የሕፃናት የልብ ሐኪም
- የሕፃናት የጨጓራ ባለሙያ ሀኪም
- የሕፃናት ኢንዶክሪኖሎጂስት
- የሕፃናት እድገት ሐኪም
- የሕፃናት የነርቭ ሐኪም
- የሕፃናት ጆሮ, አፍንጫ እና ጉሮሮ (ENT) ስፔሻሊስት
- የሕፃናት የዓይን ሐኪም
- ኦዲዮሎጂስት
- የንግግርና ቋንቋ ፓቶሎጂስት
- የፊዚዮቴራፒስት
- የሙያ ቴራፒስት

በማሕሌት አዘነ
(Speech & Language Therapist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የራስ-እንግድነት (depersonalization) and ከባቢ-እንግድነት (derealization)

የራስ-እንግድነት (depersonalization) ለራሳችን እና አካላችን የሚሰማን የሆነ ግራ የሚያጋባ፣ ሰመመን ውሰጥ ያለን የሚመስል፤ አውነት ያለመሆን ወይም የእንግድነት ስሜት ነው፡፡

ይህ ስሜት በዙሪያችን ስላለው ነገር ከሆነ ከባቢ-እንግድነት (derealization) እንለዋለን፡፡

✍ ጋሻው አወቀ (የስነ-አእምሮ ባለሙያ) 

ያንብቡ: https://telegra.ph/የራስ-እንግድነት-depersonalization-and-ከባቢ-እንግድነት-derealization-12-29

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#አዲስጥናት

ሲጋራ ማጨስ በመካከለኛ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አጫሾች ላይ የማስታወስ ችሎታቸውን እንደሚቀንስ እና ግራ መጋባት እንደሚያስከትል አዲስ ጥናት አመላክቷል።

ኮሎምበስ በሚገኘው የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተመራው ጥናት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር በJournal of Alzheimer's Disease የታተመው።

በጥናቱ የአጫሽ ሰዎች የማስታወስ ችሎታ ከማያጨሱ ሰዎች በ1.9 እጥፍ ገደማ ያነሰ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።

ከ10 ዓመት በፊት ሲጋራ ማጨስ ያቆሙ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች 1.5 እጥፍ የማስታወስ ችሎታቸው ያነሰ መሆኑም በጥናቱ ተመላክቷል።

የጥናቱ ከፍተኛ ባለሞያ እና የኦሃዮ ዩኒቨርስቲ ኤፒዲሚዮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ጄፍሪ ዊንግ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከ45-59 ዕድሜ ክልል ውስጥ ማጨስ ቢያቆሙ የሚፈጠረውን የማስታወስ ችሎታ መቀነስ መጠን ማሳነስ ይቻላል ብለዋል፡፡

ሲጋራ ማጨስን እድሜ ከመግፋቱ በፊት ማቆም ለጤና የበለጠ ጥቅም እንደሚያስገኝም ጥናቱ መጠቆሙን ዩ.ፒ.አይ ድረገጽ አስነብቧል።

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel