melkam_enaseb | Unsorted

Telegram-канал melkam_enaseb - Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

6389

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot

Subscribe to a channel

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ Training announcement!

Applied counseling techniques and skills training.

For further details and registration, use the link below! ⬇️

https://forms.gle/6qnnhj7arQZd82Dq8

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የእንቅልፍ ነገር!

እንቅልፍ ሰውነትዎ እና አዕምሮዎ በጤናማ መንገድ እንዲተገብሩ የሚያስችልዎ አስፈላጊ የህይወታችን አካል ነው። ጤናማ እንቅልፍም ሰውነት ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ እና በሽታዎችን እንዲከላከል ይረዳል። በቂ እንቅልፍ ከሌለ አንጎል በትክክል መሥራት አይችልም፣ይህም በትኩረት ለመከታተል፣ በትክክል ለማሰላሰል እና ትውስታዎችን ለማስኬድ እና ሌሎች ችሎታዎ ሊጎዳ ይችላል፡፡
 
ሰርኪድያን ሪትምስ (Circadian rhythms)

ውስጣዊ “የሰውነት ሰዓት” (body clock) የእንቅልፍዎን ዑደት ያስተካክላል፣ ሲደክሙ እና ለመተኛት ዝግጁ ሲሆኑ ወይም ሲታደስ እና ሲነቃቃ ይቆጣጠራል። ይህ ሰዓት ሰርኪድያን ሪትም ተብሎ በሚጠራው የ 24 ሰዓት ዑደት ላይ ይሠራል።
ከእንቅልፍ ከተነሱ በኋላ ቀኑን ሙሉ እየደከሙ እነዚህ ስሜቶች ምሽት ላይ እስከ መተኛ ጊዜ መድረሱን ከፍተኛ በመሆን ያመላክትልናል፡፡ የእንቅልፍ ፍላጎታችን መስረት አርጎ የሚወስነው ሳንተንኛ ወይም ንቁ ሆነን ባሳለፍነው ግዜ ውስጥ ሲሆን ለምሳሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ16  ስዓት ማለትም ክጠዋት 1ሰዓት እስከ ምሽቱ 5 ስዓት ሳንተንኛ ብንቆይ ቀሪውን 8 ሰዓት ስውነታችን እንቅልፍ ያስፈልገዋል ብሎ ይነግረናል ማለት ነው፡፡ 
 
በቂ እንቅልፍ የምንለው ምን ያህል ሰአት ብንተኛ ነው? 
 
ከ ስው ሰው ልዩነቶች ቢታዩም ብዙሃኑ ከ 5 ሰአት እስከ 8 ሰአት እንቅልፍ ይፈልጋሉ፡፡ እርግጥ እንደየ እድሜያችን የእንቅልፍ ፍላጎታችን ይለያያል ለምሳሌ ህፃናት ከ16 ሰአት በላይ ለመተንኛት የሚያስፈልጋቸው ሲሆን አዋቂዎች ከወጣትነት ዘመናቸው የእንቅልፍ ሰአት ያነሰ ፍላጎት ያሳያሉ፡፡

የእንቅልፍ ደረጃዎች

በምንተኛበት ወቅት በተለያዩ የአንቅልፍ ደረጃዎች የምናልፍ ሲሆን አንድ በቀን ወይም በምሽት የእንቅልፍ ግዜ ከ 4 እስከ 5 ደረጃዎች እናልፋለን፡፡ አንዱን የእንቅልፍ ደረጃ ዑደት (cycle) ለማለፍ እስከ 90 ደቂቃዎች ሊወስድ ይችላል። በነዚህ የደረጃ ልውውጥ ውስጥ ለጥቂት ግዜም ነቅተን ወደ እንቅልፍ ሂደቱ እንመለሳለን፡፡ ይህም ሂደት ለሰው ልጅ በእንቅልፍ ወቅት ሊደርስበት ክሚችሉ አደጋውች እራሱን ጠብቆ ዛሬ ላይ አንድንደርስ ትልቅ ግብአት ሆኖታል። እነዚህም የእንቅልፍ ደረጃዎች ሰመመን እንቅልፍ (light sleep) ጥልቅ እንቅልፍ (deep sleep) እና ፈጣን የአይን አንቅስቃሴ የሚከሰትበት እንቅልፍ (rapid eye movement)የምንላቸው ናቸው፡፡
 
ሰመመን እንቅልፍ (light sleep)- በአንድ በቀን ወይም በምሽት የእንቅልፍ ግዜ 50 በመቶውን የሚይዝ ሲሆን ብዙ ሰዎች በዚህ ደረጃ ላይ፡እንቅልፍ ወስዶናል ብለው አያምኑም ወይም አያስቡም፡፡
 
ጥልቅ እንቅልፍ (deep sleep)- ብዙ ግዜ በመጀመሪያዎቹ 2 የእንቅልፍ የደረጃ ኡደት (cycle) ውስጥ የሚከሰት ሲሆን በአንድ የእንቅልፍ ግዜያችን 20 በመቶውን የሚይዝ እና በዚህ ሂደት ውስጥ ሰውነታችን የሚያድግበት ወይም እራሱን የሚጠግንበት ወቅት ሲሆን በዚህ የአንቅልፍ ወቅት ብንነቃ ከባድ ድካም እና ግራ መጋባት ሲያጋይጥም ይስተዋላል፡፡
 
ፈጣን የአይን አንቅስቃሴ የሚከሰትበት እንቅልፍ (rapid eye movement)- ከእንቅልፍ ግዜያችን 30 በመቶውን ስይዝ፤ በዚህ፡ወቅት የአንጎላችን ክፍሎች ንቁ እየሆኑ የሚመጡበት ደረጃ በመሆኑ ትውስታዎች፣ ስሜት እና ህልሞችን የምናስተናግድበት የእንቅልፍ ደረጃ  ነው፡፡

የአንቅልፍ አክሎች 

ታድያ ይህ የእንቅልፍ ዘይቤ በቀላሉ ሊዛባ መቻሉ ለምሳሌ ቴሌቪዥን እያየን ሶፋ ላይ መተንኛት ወይም እዛው አልጋ ላይ ስልካችንን መጎርጎር ከአንቅልፍ በፊት ገላችንን መታጠብ የአንቅልፍ መድሓኒት መውሰድ እና ሌሎችም የመሳሰሉት ባህሪያት በቀላሉ የእንቅልፍ ጤናማ ስራዓተ ዘይቤያችንን እንደዋዛ እዛብተውት ጥራት ያለው እንቅልፍ እንዳናገኝ ሲፈታተኑን ይስተዋላሉ።

ብዙ ግዜ ከሚያጋጥሙት የአንቅልፍ እክሎች ውስጥ ከታች የተጠቀሱት የእንቅልፍ እጦት ወይም መታዎክ አይነቶች የተለመዱ ናቸው። 

ኢንሶሜንያ (Insomnia)- የአንቅልፍ ማጣት ወይም በእንቅልፍ ውስጥ የመቆየት ችግር ሲሆን በተደጋጋሚ ለመተኛት በምናደርገው ጥረት ውስጥ የሚከሰት ችግር ነው፡፡

ናርኮሌፕሲ (Narcolepsy)- ሰዎች በቂ ሰአት ቢተኙም በቀን ክፍለ ግዜ ውስጥ ከመጠን በላይ ድካም እንዲሰማቸው የሚያደርግ የአንቅልፍ ችግር ነው፡፡

ቅብዝብዝ እግር ሲንድሮም (Restless Legs Syndrome)- በእረፍት ላይ ያሉ እግሮችን ለማንቀሳቀስ ሃይለኛ ፍላጎት ሲሆን ከአንቅልፍ ጋር የተዛመደ የእንቅስቃሴ መዛባት አይነት ነው፡፡

4.እንቅልፍ አፕኒያ (Sleep Apnea)- የላይኛው የመተንፈሻ ቱቦን በመዝጋት ምክንያት የሚከሰት ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥነት ያለው የመተንፈስ ችግር ነው፡፡

5.በሺፍት ስራ መታወክ (shift work disorder)- በዋነኝነት የሚያጠቃው ስራውቻቸው ምሽት ላይ ወይም በማለዳ እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸውን ሰዎች ሲሆን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብዙን ግዜ በስራ ላይ ከመጠን በላይ ድካም ይሰማቸዋል አናም በተመደበላቸው የቀን እረፍት ግዜ በቂ እንቅልፍ ለማግኝት ይቸገራሉ።

6.ከመጠን በላይ መተኛት (excessive sleepiness)- የሚገለጸው ሰዎች በሚመቹ ቦታ እና ግዜ በከፍተኛ ሁኔታ አንዲተኙ የሚያስገድዳቸው የሚሰማቸው ስሜት ነው።

የአንቅልፍ እጦት ወይም መታዎክ አያሳደረብን ያለውን ጫና መረዳት

እንቅልፍ እጦት ወይም አንቅልፍ መታወክ እያሳደረብን ያለውን የጫና ደረጃ መለካት አስፈላጊ ሲሆን በተለይም አሁን ያለንበትን ደረጃ ክሚያስፈልገን የቴራፒ ቡሃላ የምናመጣውን ለውጥ ለመለካት አና ለማሳየት ይረዳናል፡፡
⬇️

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ህይወታችን ላይ ትልቅ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ 10 አመለካከቶች!

1. ራሴን ለመውደድና ለመቀበል ሰዎች እስኪወዱኝና እስኪቀበሉኝ አልጠብቅም።

2. ትክክለኛውን ነገር አደርጋለሁ እንጂ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት አልሞክርም።

3. ትችቶች እንዲያስተምሩኝ እንጂ እንዲሰብሩኝ አልፈቅድም።

4. እኔ በስህተቶቼ define አልደረገም።

5. ስህተቶቼን ከስኬቶቼ በላይ አግዝፌ አላይም።

6. ሰዎች ሁሉ እንደኔ እንዲያስቡ አልጠብቅም።

7. የማልቀይራቸውን ሀቆች እቀበላለሁ።

8. ሰዎች እንዲያማክሩኝ እንጂ እንዲወስኑልኝ አልፈቅድም።

9. በማልቀይረው ትላንት ላይ ሳይሆን ባለኝ ዛሬ ላይ አተኩራለሁ ።

10. ደስታዬን ለነገ አልቀጥርም። ባለኝ ረክቼ ዛሬ ሀሴት አደርጋለሁ።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ችግርን የመቋቋም ብቃት| Adversity Quotient (AQ)

በየእለቱ የሚያጋጥሙን ችግሮችን ለማለፍ ማለትም በስራ ላይ፣ በት/ቤት፣ በትዳር ህይወት፣ ልጆችን በማሳደግ ሂደት፣ በጓደኝነት፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና በተለይም ያልተጠበቀ ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥም ችግሩ ብዙ ሳይጎዳን ማለፍ እንድንችል የሚያስፈልገን ክህሎት ቢኖር ችግርን የመቋቋም ብቃት ነው።

በተጨማሪም ችግርን የመቋቋም ክህሎት የአንድ ሰው የስራ ስኬት እና የአእምሮ ጤናንም ይወስናል።

ችግርን የመቋቋም ብቃት ያላቸው ሰዎች ባህርያት፦

- ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን የሚያምኑና አንዳንዴ ከተለመደ አሰራር ወጣ ለማለት የሚደፍሩ።

- ሊያጋጥመኝ ይችላል ብለው ላሰቡት ችግር ቀድመው መፍትሄ የሚያቅዱ።

- ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን የሚሰሩ።

- ራሳቸውን እንደነርሱ ጠንካራ ከሆነ ሰው ጋር የማያቆራኙ።

- ለሁሉም ነገር መልስ ሊኖረኝ ይገባል የማይሉ።

- ለራሳቸው ክብር ያላቸውና ተገቢውን ጥንቃቄ የሚያደርጉ።

- ሰዎችን የሚረዱ፣ ካጋጠማቸው ችግር የሚማሩ።

- ለሚፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ከመውቀስ ይልቅ መፍትሄው ላይ የሚያተኩሩ።

- ችግርን እንደመልካም አጋጣሚ የሚያዩ።

ችግርን የመቋቋም ብቃት ለማሳደግ፦

1. ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት ማጎልበት።
2. ችግር ሲያጋጥም ጊዚያዊ ነው ያልፋል ብሎ ማሰብ።
3. ለሚፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን አለመውቀስና የራስ አስተዋፆ ላይ ማተኮር።
4. ሰዎች የሚሰጡትን ቀና አስተያየት መቀበል።
5. ያልተጠበቀ አዲስ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ።
6. ራስን ማወቅ፦ ምን እንደሚፈልጉና መቼ እርዳታ መጠየቅ እንዳለባቸው ማወቅ።

ችግርን የመቋቋም ብቃት በተፈጥሮ የተሰጠን ቢሆንም ልናሻሽለውና ልናዳብረው እንችላለን።

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በውኑ በንግግር ሰው ሊታከም ይችላልን?

- የንግግር ህክምና ምንድነው?

- በንግግር ህክምና ምን ይታከማል?
- ማንን ያግዛል?
- ምን ያህል ውጤታማ ነው?

⏰ እሁድ ምሽት 12 ሰዓት መልሶቹን እንወያይባቸዋለን።

ለመታደም በዚህ ሊንክ ይግቡ ⬇️

              http://bit.ly/3Y1N3aF

ክለብሐውስ ከሌሎዎት እዚህ ማውረድ ይችላሉ፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.clubhouse.app&hl=en&gl=US

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ከሸለብታ (Napping) ልናገኛቸው የምንችላቸው ጥቅሞች!

ከ10 ደቂቃ እስከ 30 ደቂቃ የሸለብታ ጊዜ መውሰድ ከድካም ስሜት እንዲወጡ እና የማስታወስ ችሎታ እንዲዳብር ይረዳል።

ሸለብታ ሰውነትን ዘና የማድረግ፣ ድካምን የመቀነስ፣ ንቁ እንዲሆኑ የማድረግ፣ መጥፎ ስሜትን የመቀየር፣ የፈጠራ ችሎታን የማዳበር፣ አዕምሮ በስራ እንዳይወጠር የማድረግ፣ ጤናማ እንዲሆኑ የማድረግ፣ በሽታን የመከላከል አቅምን የመጨመር፣ ጭንቀት እና ፍርሃትን የመቀነስ፣ የማስታወስ ብቃታን የማሻሻል እና ሌሎች መሰል የጤና በረከቶች አሉት፡፡

አጭር የሸለብታ ጊዜ ስናሳልፍ ንቁ እና ጤናማ ሰው ሆነን የዕለት ከዕለት ስራችን በቅልጥፍና እንድናከናውን ከማድረጉም በላይ የሸለብታ ጊዜ ከማሳለፋችን በፊት ስላከናዎናቸው ትምህርት፣ ክህሎት፣ እውቀት እና ሌሎችንም ድርጊቶች በቀላሉ ለማስታወስ ይረዳል፡፡

መጥፎ ቀን እያሳለፍን ከሆነ ሸለብታ ስሜትን ወደ ጥሩ መንፈስ የመቀየር ሀይል አለው።

ከ10 እስከ 30 ደቂቃ ባለው አጭር ጊዜ የሸለብታ ጊዜ ማሳለፍ በቂ ሲሆን የሸለብታ ጊዜው ከዚህ መርዘምም ሆነ ማጠሩ የሚገኘውን የጤና በረከት ይቀንሰዋል።

ሸለብታ ከአነቃቂ መጠጦች (ካፌን) ከሚገኘው መነቃቃት የተሻለ የመነቃቃት ሀይል እንዳለው እና የማስታወስ ችሎታችንም እንደሚያዳብር ጥናቶች ያሳያሉ።

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

“ከተሳሳታችሁ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍሩ፡፡ እንደገና ስትጀምሩ እኮ የምትጀምሩት ከዜሮ ሳይሆን ከስህተታችሁ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው''

መልካም የሥራ ሣምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#CME_Webinar_YetenaWeg & #EMA

You are invited to join a webinar.

Topic: Psychosomatic Disorders.

Presenter: Dr. Biniyam Worku

🗓  Jan 29th 2023 (This Sunday)

⏰  5:00 PM - 7:00 PM (Ethiopian Time)

Register Via the link below:

https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_1wWMVjOeSwm6ueva191B6g

After registering, you will receive a confirmation email about joining the webinar.

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

NARCOLEPSY

(በዶ/ር ኢየሩሳሌም ጌቱ)

ናርኮሌፕሲ (Narcolepsy) የመተኛትና የመንቃት ዑደቶችን የሚቆጣጠረው የአእምሮ ክፍል መዛባት ሲሆን በዚህም የተጠቁ ሰዎች ቀናቸውን በመተኛት ያሳልፍሉ፡፡

ናርኮሌፕሲ የቀን ስራ ላይ በጣም ተፅዕኖ ያሳድራል። ሰዋች ያለፍቃዳቸው ወይም ሳያስቡት እንቅልፍ ይወስዳቸዋል ይህም እየበሉ፣ እያወሩ ወይም መኪና እያሽከረከሩ ሊሆን ይችላል።

ብዙውን ጊዜ ምልክቱ በልጅነት የሚጀምር ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊጀምር ይችላል። ወንዶችንም ሆነ ሴቶችንም በእኩል መጠን ያጠቃል።

መንስኤዎች፦

ኖርኮሌፕስ ብዙ መንስኤዎች ሲኖሩት አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ሀይፓክሪቲን (hypocretin) የሚባል የኬሚካል መጠን ማነስ ነው። ይህ ኬሚካልም ለመንቃት የሚያስችል እና የእንቅልፍ መንቃት ዑደትን የሚያስተካክል ነው።

ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ መንስኤ ባይኖረውም በህክምና በተደረገ ጥናት እንደሚገልፅው ኖርኮሌፕሲ የሀይፓክሬቲን ኬሚካል እጥረትን የሚያመጡ ብዙ ምክንያቶች ውጤት ነው።

ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው የሚጠቀሱት:-

- ሀይፓክሪቲን (hypocretin) የሚያመነጩት የአእምሮ ህዋሶች መሞት (loss of Brain cells): ይህም አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው (Autoimmune Disorder) የሰውነት በሽታ መከላከያ ሲስተም እክል ሲገጥመው ነው።

- ተመሳሳይ ታሪክ በቤተሰብ መኖር

- የአንጎል መጎዳት: የተሽከርካሪ ወይም የመመታት አደጋ መኖር (Brain injuries)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ!

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

መሰረት ክንፈ ካሳተመችው ''የጥቁር እናት ነኝ'' ከተሰኘው መጽሐፍ የተገኘውን ገቢ ለተለያዩ የኦቲዝም ማዕከላት እንዲሁም ለችግሩ ተጠቂ ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰቦች አድርሳለች።

እናመሰግናለን መሲ!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#የአእምሮጤና

ታሪኳን ለአል ዐይን አማርኛ ያጋራች ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የአዕምሮ ህመምተኛ “የአዕምሮ ህመምተኛ እንደሆንኩ አላውቅም ነበር፤ ለምን ይህ አልሆነም እያልኩ አለቅስ ነበር፣ ቤተሰቦቼ አይወዱኝም ብዬም አስባለሁ፣ ለሁሉም ጥፋቴ በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ላይ አመካኝ ነበር” ትላለች።

“ባንድ ጓደኛዬ እርዳታ ከአንድ የአዕምሮ ሀኪም ጋር ተገናኝቼ ህክምናውን አገኘሁ” የምትለው ይህች ባለታሪክ” ህክምናውን ካገኘች ጊዜ ጀምሮ ደስተኛ እና አመስጋኝ መሆኗን ነግራናለች።

“ህክምናውን ባለመረዳቴ አልያም ቤተሰቦቼን ጨምሮ ብዙዎች ወደ አዕምሮ ህክምና እንድሄድ ባለማድረጋቸው ለብዙ ዓመታት ህይወቴ በስቃይ የተሞላ እንዲሆን አድርጎት ነበር፣ ባንድ ወቅት ራሴን ላጠፋ ጫፍ ላይ ደርሼ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወደ ጤናዬ ተመልሼ ስራዬን እና ህይወቴን በሚገባ እየመራሁ ነው” ብላለች።

“ይሁንና ህክምናው ውድ እና ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ለማማከር እና መድሃኒት ዋጋ በሳምንት ከ800 ብር እስከ 2ሺህ ብር እያወጣሁ ነው ይህ እጅግ እየፈተነኝ ነው” ብላናለች።

አንድ ዜጋ ማንኛውንም አይነት ህመም ተሰምቶት በቀላሉ ባቅራቢያው ወዳለ የህክምና ተቋም ሄዶ እንደሚታከመው ሁሉ የዓዕምሮ ህመም ህክምናም ሊቀል ይገባል፣ ለዚህ ደግሞ መንግስት ለሌሎች ህመሞች ትኩረት በሰጠው ልክ ለአዕምሮ ህመም ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቃለች።

ወላጆች እና ማህበረሰቡ ጋር ስለ አዕምሮ ህመም ያለው አስተሳሰብ ትክክል አለመሆኑን የምትናገረው ይህች ባለታሪክ ሰዎች የአዕምሮ ህመም ሲያጋጥማቸው ታክመው መዳን እንደሚችሉ ማመን አለባቸውም ብላለች።

ብዙዎች ሰዎች በአመለካከት እና ተስፋ በመቁረጣቸው ምክንያት ራሳቸውን የሚያጠፉ፣ ቤት ተዘግቶባቸው በጨለማ የሚኖሩ እና በየቤተ እምነቶች ከነ ስቃያቸው የሚኖሩ እንዳሉም ነግራናለች።

ቤተሰቦቼ የተማሩ የሚባሉ ቢሆንም የአዕምሮዬ ጤና ሲታወክ ሰይጣን ይዟት ነው፣ ጸባያዋ ተበላሸ እና ትታሰር ይሉ ነበር የምትለው ይህች ባለታሪክ ስለ ህመሙ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ በሰፊው ማስተማር እንደሚያስፈልግም ጠቁማለች።

በአዲስ አበባ የአዕምሮ ህክመና እና ማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት የስነ ልቦና እና የማህበረሰብ ጤና አማካሪ ሙሉ መኮንን፤ የአዕምሮ ህመም እየተስፋፋ እና በዛው ልክ ትኩረት ያልተሰጠው የማህበረሰብ ጤና እክል መሆኑን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል።

አንድ ሰው የዕለት ተዕለት ጉዳዩን መፈጸም ሳይችል ሲቀር የአዕምሮ ህመም አጋጥሞታል ይባላል የሚሉት አማካሪዋ ሰዎች እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥማቸው ሳይብስ ወደ አዕምሮ ሀኪም ጋር እንዲሄዱ አሳስበዋል።

እንደ አማካሪዋ ገለጻ በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህመምተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ብዙ አስረጂ ማስረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ጭንቀት፣ ድብርት፣ ተስፋ መቁረጥ እየተሰማቸው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ጠቁመዋል።

ይሁንና የአዕምሮ ህመም የሚፈልገው ዜጋ ቁጥር እየጨመረ የመምጣቱን ያህል በመንግስት የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኑንም አማካሪዋ ጠቁመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በጉዳዩ ዙሪያ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ በጦርነቱ እና በሌሎች የማህበራዊ ቀውሶች ምክንያት የስነ ልቦና ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአዕምሮ ህመም ጋር ተያይዞ ህክምናውን ለሚፈልጉ ዜጎች የሚውሉ መድሃኒት እጥረቶች ነበሩ የሚሉት ሚኒስትሯ አሁን ላይ ከአቅራቢዎች ጋር በተሰራው ስራ ችግሩ በመቃለል ላይ መሆኑንም አክለዋል።

የአዕምሮ ህመም በቀላሉ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በሁሉም ሆስፒታሎች የስነ ልቦና ባለሙያ ለማሟላት እየተሞከረ መሆኑን አክለዋል።

በአጠቃላይ ግን በሚሹ የጦርነት እና ግጭት አካባቢዎች በልዩ መልኩ ባለሙያ እየተደራጀ ነው የተባለ ሲሆን በሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ደግሞ ስለ አዕምሮ ህመም ምንነት፣ ህክምናው እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እንዲሟሉ ይደረጋሉም ተብሏል።

በዓለማችን ከአጠቃላይ ህዝብ ቁጥር ውስጥ 970 ሚሊዮን ያህሉ የአዕምሮ ህመምተኞች ሲሆን በየዓመቱም ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በዚሁ ህመም ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።

በየዓመቱ ህይወታቸው ከሚያልፉ አጠቃላይ ዜጎች ውስጥም 14 በመቶ ያህሉ የአዕምሮ ህመምተኞች እንደሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ከአምስት ወራት በፊት ያወጣው ሪፖርት ያስረዳል።

Via: Alain Amharic

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

“ሕይወት ብስክሌት እንደመንዳት ነው፡፡ ሚዛንህን ለመጠበቅ ካለማቋረጥ መንቀሳቀስ የግድ ነው” - Albert Einstein

መልካም የሥራ ሣምንት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#የመጽሐፍጥቆማ

"በህዝብ ፊት የመናገር ክህሎት" በሚል ርዕስ በብሩክ ወልዴ የተዘጋጀው መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ይህ መጽሐፍ በህዝብ ፊት የመናገር ጠቃሚ ክህሎት ማዳበር የምትችልባቸውን መመሪያዎች በግልጽ ያቀርብልሃል፡፡

መጽሐፉ የሚያነሳቸው ነጥቦች፦

1.በህዝብ ፊት የመናገር ክህሎት መሠረታዊያን
2.የመልዕክትን ርዕስ መምረጥ እና ግብን መቅረጽ
3.ድጋፍ ሰጪ ሃሳቦችን ማደራጀት
4.የመድረክ ንግግር ቅድመ ዝግጅት
5.መልዕክትን ማዋቀርና አስተዋጽዎ መንደፍ
6.መግቢያ እና መደምደሚያን ማዘጋጀት
7.የቋንቋ አጠቃቀም
8.አካላዊ ቋንቋን አጠቃቀም
9.የድምጽ አጠቃቀም
10.ልምምድ
11.በህዝብ ፊት የመናገር ፍርሃትን መገንዘብና መቆጣጠር
12.አስረጅ ምሳሌዎችን ስለመጠቀም
13.የፓወር ፖይንት አጠቃቀም
14.ጥያቄና መልስን በብቃት ማስተናገድ
15.የመድረክ ተናጋሪ ሥነ-ምግባር

መጽሐፉን ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ያገኙታል። አድራሻ: ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ በአዲስ አበባ ለምትገኙ ለስራ ፈላጊ የዲግሪ ምሩቃን የወጣ የምዝገባ ማሰታወቅያ!

መስፈርቶች፦

1) ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በማንኛውም የትምህርት መስክ ከ 2010 እስከ 2015 ዓ/ም ባለው ጊዜ የተመረቀ/ቀች
2) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነ/የሆነች
3) ዕድሜ ከ 18 እስከ 29
4) በማንኛውም መደበኛ የስራ መስክ ያልተቀጠረ/ች
5) ምዝገባ፡ ከዚህ ደብዳቤ ስር ተያይዞ ያለውን የ Google ቅጽ በመሙላት ወይም ከዚህ በታች ባሉት ስልክ ቁጥሮቸ መመዝገብ፡ 0902450045፣ 0947938344፣ 0929103487
የምዝገባ ጊዜ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ 15 ቀናት ውስጥ ማለትም እስከ ጥር 20፣ 2015 ዓ/ም።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeHe0BiZRwS57MeOyYWLvgqhx0mICgeRKvPPa7cZtLfCKE6Vg/viewform

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

መፍትሄዎች

እንቅልፍ መታወክ ወይም ማጣት ጋር አብሮ መኖር ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ ሰዎች እንዲተኙ እና በቀን ውስጥ የበለጠ እረፍት እንዲሰማቸው የሚያግዙ ውጤታማ ቴራፒዎች እና ህክምናዎች ይገኛሉ።

ኮግኒቲቨ የባህሪ ቴራፒ (Cognitive behavioural therapy- for insomenia) CBT-I 

ለእንቅልፍ ወታወክ ወይም ማጣት (CBT-I) ኮግኒቲቨ የባህሪ ቴራፒ እንቅልፍ ማጣት የሚያስጨንቁ ምልክቶችን ለመዋጋት አጭር ፣ የተዋቀረ እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ ነው።

CBT-I እንዴት ይሠራል?  

CBT-I በአስተሳሰባችን፣ በምናደርጋቸው ነገሮች እና በምንተኛበት መንገድ መካከል ያለውን ትስስር በመመርመር ላይ ያተኩራል።

በቴራፒ ወቅት የሰለጠነ CBT-I ቴራፒ ስለእንቅልፍ ምልክቶች አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ሀሳቦችን፣ ስሜቶችን እና ባህሪን ለመለየት ይረዳል።

ቴራፒው ብዙውን ጊዜ ከ6-8 ክፍለ–ጊዜዎች ቢወስድም፣ ምንም እንኳን ርዝመቱ እንደ ሰው ፍላጎቶች ሊለያይ ይችላል።

ምን ያህል CBT-I ውጤታማ ነው? 

CBT-I ሲጠቀሙ ከ 70% እስከ 80% የሚሆኑት የእንቅልፍ ማጣት ወይም መታወክ ችግር ካጋጠማቸው ሰዎች መሻሻልያሳያሉ። ለመተኛት ይእሚወስድብን ጊዜን መቀነስ፣ለመተኛት እና በእንቅልፍ ወቅት ከእንቅልፍ መነሳትን ያካትታሉ። ለውጦች ግን ባንዴ የሚከሰቱ ሳይሆን በሂደት የመጡ ናቸው፡፡

Acceptance & commitment therapy (ACT) 

ሥር የሰደደ እንቅልፍ ማጣት ለማሸነፍ ልዩ እና ረጋ ያለ መድኃኒት–አልባ አቀራረብን ይሰጣል።

በተለምዶ ከመተኛት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የፊዚዮሎጂ እና የስነልቦና ምቾት ሁኔታ ለማስተካከል የሰዎችን ፍላጎት ለማሳደግ ይረዳል።

ሪላክሴሽን እንቅስቃሴውች

የእንቅልፍ ባለሙያዎች እንቅልፍ ማጣት ያለባቸውን ሰዎች ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥቂት የማፍታቻ ዘዴዎችን ለይተው አውቀዋል።

እነዚህም የአተነፋፈስ ልምዶችን፣ የጡንቻዘና ማለትን እና ማሰላሰልን ያጠቃልላ። በደም ግፊትዎ፣ በአተነፋፈስ እና በልብዎመጠን እና በሌሎች መለኪያዎች ላይ ተመስርተው የተለያዩ የሰውነት ተግባራትን እንዲቆጣጠሩ ይረዳዎታል – እንዲሁም የእንቅልፍ ማጣት ምልክቶችን ለመቀነስ እና እንቅልፍን ለማሻሻል ውጤታማ ሊሆን ይችላል።

4.ለእንቅልፍ ማጣት የሚረዱ መድኃኒቶች

ለእንቅልፍ ማጣት ማንኛውንም መድሃኒትከመውሰድዎ በፊት ከሐኪምዎ ጋር መማከርዎን ያረጋግጡ፡፡ለእንቅልፍ እጦት ወይም መታወክ መድኃኒት የመጨረሻ ምርጫዎ ቢሆን ይመከራል፡፡

ምንጭ:
American Academy of Sleep Medicine. (2014). The International Classification of Sleep Disorders  
CBT Tool kit dr Claire pollard and Elaine foreman  
National sleep foundation resource center 
Siebhern, A. (2019, April 21). Cognitive Behavioral Treatment for Insomnia (CBTi) Defined. Psychology Today. 

ያፌት ከፈለኝ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ማሞ ውድነህ ስለ ሲግመን ፍሮይድ!

ብዙ ሰዎች ብዙ ህልም ያልማሉ። በህልም አለም ስንሆን እጅግ እንግዳ የሆኑ ነገሮች ልናደርግ እንችላለን። ይህን ሁሉ ህልም የምናየው ለምንድነው? በመሰረቱስ ህልም ከየት ይመጣል? ሲግመን ፍሮይድ ከሰጠው የበለጠ ሌላ አጥጋቢ መልስ የሰጠ አልተገኘም።

ፍሮይድ የተወለደው የዛሬ መቶ አመታት ግድም ነበር። (ማሞ ውድነህ መፅሀፉን ያሳተሙት በ1981 ዓ.ም. ነው።)  ፍሮይድ በሰው ባህሪ ውስጥ ያለውን ምስጢር በሚገባ አብራርቶታል። በሰው "ስውር አእምሮ" ውስጥ ያለው ምስጢር እጅግ ጥልቅና ውስብስብ የሆነ የማስታወስና የስሜት ውቅያኖስ መሆኑን የገለፀ ነው። ይህም ማለት በህፃንነታችን ወራት ያየነውንና የሰማነውን የምናስታውስበት ሁኔታ ከአደግን በኃላ ሲደርስብን ወይም በህልማችን ስናየው ነው።

ሰዎች የሚሰሩትን ለምን እንደዚያ እንደሚሰሩ ለማወቅ ከፈለግን የፍሮይድ ጥናት ውጤት በጣም ይረዳናል። በዚያ ዘመን ስለ አእምሮ ሁኔታ የሚታወቅ ምንም ስላልነበረ አንድ ሰው ሲታመም ምንም እርዳታ አይደረግለትም። "ምናልባት ሰይጣናዊ መንፈስ ሰርፆበት ይሆን? ስለፈፀመው መጥፎ ስራ እግዚያብሄር ሊቀጣው አስቦይሆን?" እየተባለ ከሚተችበት በቀር ሌላ ህክምና አልነበረም። ይህ ሁኔታ እስከዛሬ በብዙ ሀገሮች ይታያል።

ዶ/ር ፍሮይድ በምርምሩና በጥናቱ ከየአቅጣጫው በርካታ ጠላቶች አፍርቷል። ግን እጥፍ ድርብ ያላቸው ወዳጆችም አግኝቷል። ሕሙማንን በጥሞና ማዳመጥ የሚያስገኘውን ጥቅም እየዘረዘረ በማስተማሩም ስመ ጥር ሆኗል።

(ማሞ ውድነህ በዘመናችን ከታወቁ ሰዎች 1981)

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጤና በረከቶች!

በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የበሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና ጤናማ ህይወት ለመምራት ከሚያስችሉ ቀላል መንገዶች አንዱ ነው፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ከሚገኙ የጤና በረከቶች ውስጥ፦

- የማስታወስ ችሎታችን መጨመር እና የአንጎል ስራን ለማሻሻል፤
- የእንቅልፍ እጦትን ለመከላከል፤
- በጭንቀት እና ድብርት የመጠቃት እድልን ለመቀነስ፤
- ከበርካታ ከባድ በሽታዎች ራስን ለመከላከል፤
- ክብደትን በመቀነስና በመቆጣጠር ከውፍረት ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና እክሎች ለመቆጣጠር፤
- የመገጣጠሚያ አካባቢ ህመምን ለመከላከል፤
- የጡንቻ ጥንካሬን በመሳደግ ሚዛንን ለመጠበቅ፤
- የአካል ብቃት ጥንካሬን ለመጨመር ይረዳል።

ምንም እንኳን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በርካታ የጤና በረከቶች ቢኖሩትም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ባለሙያ አማክረው ቢሆን ይመረጣል፡፡

በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አልያም የእግር ጉዞ በማድረግ ጤናን መጠበቅ እንደሚቻል የሜዲካል ዌብ መረጃ ያመላክታል።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ Vacancy Announcement!

Organization: Addis Ababa City Administration Education Bureau

No of Positions:- 248

Professionals needed:-

- BSc and above in Nutrition, Public health officer, social work, sociology, #psychology, special need education, Natural science, Education planning and management, Social development, other related social science fields.

Deadline: February 9 2023

Click the link to apply ⬇️

https://docs.google.com/forms/d/19JdL4Vg99xsxOQ1y7YVlaG__uJ7bO_YoC6y2m-OfYTs/viewform?edit_requested=true

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የአእምሮ ጤና፥ የአእምሮ ጤና ተደራሽነት እና አገልግሎት - የጤና ወግ

በአያና አየለ (በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ የህክምና ተማሪ-PC 1)

አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡ ስንቶቻችሁ በአዕምሮ ህመም ተሰቃይታችኋል ወይንም በአዕምሮ ህመም የሚሰቃይ ሰው ታውቁ ይሆን? እኔ እንደምገምተው ከሆነ ሁላችንም በአእምሮ ህመም ውስጥ ያለን ወይንም በዚህ ህመም ምክንያት የሚቸግር  አንድን ሰው እናውቃለን።

ይህን ይህል ለመግቢያ አንዲሆን ከፃፍኩ አሁን ደግሞ የአእምሮ ህመም ምን ማለት አንደሆነ ላብራራው።

የአእምሮ ህመም የሚባለው በአብዛኛው ጊዜ የሚታወቁት ሁኔታዎች እንደ ጭንቀት፣ ድባቴ፣ “ስኪዞፍሬኒያ”፣ “ባይፖላር” ወዘተ እንዲሁም የአስተሳሰብ መታወክ አና የአልኮልና የተለያዩ መድሃኒቶች ሱሰኝነት ያጠቃልላል።

እነዚህ አሁን የተዘረዘሩት ህመሞች  የሚጎዱት ተመሳሳይ የአእምሮ ክፍልን ነው። በተለያየ ደረጃ እና መጠን የአእምሮ የማሰብ፣ የማሰላሰል፣ የመገንዘብ እና ስሜትን የመግዛት ስራውን በትክክል እንዳይሰራ ያደርጋሉ። ይህ የቀን ተቀን ኑሯችንን የሚያውክ ችግር ነው።

የአለም ጤና ድርጅት እንደዳስቀመጠው 20% የአለም ህዝብ በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ በአእምሮ ህመም አና ተያያዥ ጉዳዮች ይሰቃያል ይላል። ይህም ማለት ከ5 ሰዎች አንዱ ማለት ነው። ስለዚህ ሒሳቡን ብናሰላው እያንዳንዱ ሰው በአእምሮ ህመም የሚቸገር አንድን ሰው ሊያውቅ ይችላል ማለት ነው። በጥቅሉ ይህን ያህል ብዛት ያለው ሰው በአለም ዙሪያ በዚህ በሽታ ከተጠቃ በዚህ በሽታ ዙሪያ ብዙ ጥናት፣ ምርምር  አና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ  መፈጠር ይኖርበታል ማለት ነው። ግን አሁን መሬት ላይ በተግባር የሚታየው በዚህ በሽታ ዙሪያ ብዙ ምርምሮች አና ተግባሮች እንደ በሽታው ክብደት፣ መጠን እና አስከፊነት እንዳልተሰሩ ነው።

የአእምሮ ህመም መገለል አና ያላግባብ ፍረጃ ያጠቃዋል። መገለል ማለት ክብር አለመስጠት፣ መናቅ፣ ማዋረድ፣ ማሸማቀቅ አና የመሳሰሉት ናቸው። ግን ለምንድነው የአእምሮ ህመምተኞች ለመገለል እና ያላግባብ ፍርጃ የሚጋለጡት?

በአእምሮ  ህሙማን ላይ ያለውን መገለልና ትክክል ያልሆነ አመለካከት ለማሳየት አንድ ምሳሌ እንውሰድ። ለምሳሌ፦ አንተ ወይንም አንቺ ለአለቃህ/ሽ 50ኛ ዓመት የልደት በአል መልካም ምኞታችሁን እንድትገልፁ እና ንግግር እንድታደርጉ በአክብሮት ተጠራችሁ እንበል ነገር ግን በልደት በአሉ እለት ታመማችሁ አና ቀጠሮውን መሰረዝ እንዳለባችሁ ተረዳችሁ። ስለዚህ ቀጠሮውን ለመሰረዝ አንዴት ብትሉ ትመርጣላችሁ? ይቅርታ ቀጠሮውን የሰረዝኩት እራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ክፉ ድብርት (ድባቴ) ይዞኝ ነው ወይንስ እግሬን በጣም ስላመመኝ መራመድና መቆም ከብዶኝ ነው ያልመጣሁት ትላላችሁ። የመጀመሪያውን ከሁለተኛው አስበልጣችሁ ከመረጣችሁ አትጠራጠሩ አናንተ ለመገለል እና አግባብ ላልሆነ ፍረጃ ትጋለጣላችሁ።

ዶክተር ጄኤፈሪ ሊበርማን ”አሁን እኔ በየቀኑ መገለል ያጋጥመኛል እንደ አንድ የአእምሮ ሀኪም፡ ይህ እራሴን የሰጠሁለት የህክምና ስፔሻሊቲ ሙያ ከሁሉም የህክምና ስፔሻሊቲዎች በጣም የተዋረደ እና ትንሽ ቦታ የሚሰጠው ሙያ ነው።”

እስቲ የአእምሮ ህመምን አንደ ልብ ህመም አርገን እንየው እና ከዚያም ምልክቶችን ለምሳሌ ጭንቀትን እንደ ደረት ህመም፣ “አንዛይቲን” እንደ ትንፍሽ መቆራረጥ ወይንም በቀላሉ ለመተንፈስ መቸገር እንዲሁም “ሳይኮሲስን” እንደ የልብ ምት መጨመር ብናየው የመጀመሪያዎቹ ህመምዎች የሚመነጩት ከአእምሮአችን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከልብ ነው ነገር ግን አእምሮአችን ከየትኛውም አካላታችን በላይ በጣም የተወሳሰበ ነው። ልብ በመሠረታዊነት ብዙ የደም ስሮች እና 4 የደም መቀበያ ክፍሎች ያሉት 2ቢሊዮን መስል ሴሎች ያሉት የደም መርጪያ አካል ነው። በአንፃሩ ደግሞ አእምሮ 3 ፓውንድ የሚመዝን ከ100ቢሊዮን በላይ ኒውሮኖች የተገነባ እና 30 ትሪሊዮን በላይ ትስስሮች ያሉት ከመሰረታዊ እና ዋና ከሆነው ከአተነፋፈስ፣ የሰውነት ሙቀትን መቆጣጠር፣ አስከ የተቀናጀ እንቅስቃሴ መፍጠር እንዲሁም ማንነትና ባህሪን የሚያላብስ ነው። አእምሮ እራሳችንን እንድናውቅ አና አንድንነቃ እንዲሁም አዲስ ፈጠራ አንድንሰራ ትልቅ ሚና አለው። የአእምሮን ስራ በትክክል ለይቶ ለመረዳት እና ለማወቅ ከባህሪ እና ማንነት ጋር ያለውን ትስስር ለመረዳት በጣም ብዙ ጊዜ ይወሰዳል።

አሁን መገለልና አድሎ ለአእምሮ ህመም ብቻ የተሰጠ አይደለም። በሰው ልጆች ታራክ ውስጥ ብዙ በሽታዎች ታይተዋል እንደ ቲቢ፣ የስጋ ደዌ፣ ካንሰር፣ እንዲሁም እስከ አሁን መድሀኒት ያልተገኘለት ኤችአይቪ ተጠቃሽ ናቸው።

ኤችአይቪ ኤድስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከሰት ብዙ ሰው ሞተ፡ የሟቾች ቁጥርም በብዙ በእጥፍ እየጨመረ ሄደ። ነገር ግን ምክንያቱ በትክክል አይታወቅም ነበር። ብዙ ምርምሮች እና ጥናቶች ከተደረጉ በኃላ ምን እንደሆነ በምን መንገድ እንደሚተላለፍ ታወቀ። ከብዙ ጥረት በኃላም ኤችአይቪ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍበት መንገዶች በግልጽ ተለይተው ወጡ አንዳንድ ክትባቶችም ተገኙ ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላም ህዝብ ግን በኤችአይቪ የተያዙትን ከማግለል አልተቆጠበም። ኤችአይቪ ኤድስ ታማሚዎችን ማግለል ምግብ ለይቶ ለብቻቸው መስጠት፣ ከነርሱ ጋር አለማውራት፣ አለመጫወት አና የመሳሰሉት። አሁን ግን ከብዙ ግንዛቤ መፈጠር በኃላ ህዝቡ ስለ ኤችአይቪ አና ስለ ኤችአይቪ ታማሚዎች ያለው አመለካከት በተወሰነ ደረጃ ተለውጧል።

የኤችአይቪኤድስን መገለል እና ያለአግባብ ፍረጃን ከአእምሮ ህመም ጋር ስናስተያየው ብዙ የሚያመሳስሉት ነገሮች አሉ። ይህም ማለት መንግስት ትኩረት ቢሰጠው አና በጀት ተመድቦ ቢሰራበት ብዙ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን ለአእምሮ ጤና የተሰጠው ትኩረት በጣም አናሳ ነው። ብዙ ተጨማሪ ነገሮችን ከምስል እና ከአሃዝ ጋር አያይዤ ባሰፍር ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህን ፅሁፍ የፃፍኩት ከድባቴ አና መሰል የአእምሮ ህመም ጋር እየታገልኩ ነው።

አሁንም ትኩረት ለአእምሮ ጤና!
ያለ አእምሮ ጤና ጤና የለም!

ይህ ፅሁፍ በዶ/ር ሄርሞን አማረ (የስነ አዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ድህረ አደጋ ሽብረት
(Post-Traumatic Stress Disorder)


(በዶ/ር ኢየሩሳሌም ጌቱ)

በህክምናው አጠራር Post-Traumatic Stress Disorder በመባል የሚታወቀው በሰዎች አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ በጣም አሰቃቂ ሁኔታ ስላጋጠማቸው፣ ስለተመለከቱ ወይንም እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስላለፉ የሚከሰት የስነልቦና መረበሽ አይነት ነው።

ይህ ከአንድ መጥፎ አጋጣሚ በኃላ በስሜት ተቀርፆ በሚቀር ጭንቀትና ፍርሃት ወይም ስጋት አማካኝነት የሚመጣ የስሜት መዛባት በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል።

የትኛው የማህበረሰብ ክፍል ለድህረ አደጋ ሽብረት ተጋላጭ ነው?

- ከፍትኛ ለሆነ አደጋ የተጋለጡ ሰዎች (ጦርነት፣ ግርፊያ፣ የመኪና አደጋ ወይም የእሳት ቃጠሎ)
- ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው
- የሚዎዱትን ሰው በድንገተኛ ሞት ያጡ
- በልጅነታቸው አሰቃቂ ጥቃት የደረሰባቸው (አካላዊ ወይንም መንፈሳዊ)

PTSD (ድህረ አደጋ ሽብረት) ያጋጠማቸው ሰዎች ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያሉ?

- ቅዠት
- እንቅልፍ ማጣት
- ቀደም ሲል ባጋጠማቸዉ ችግር ምክንያት ስለአዪት ስቃይ በጣም ብዙ ማሰብና መጨነቅ
- በቀላሉ ድንግጥ ማለት
- የስሜት መደንዘዝ
- ይወዱዋቸዉ በነበሩ ነገሮች ላይ ደስታን ማጣት
- ራሳቸውን ከአካባቢ፣ ከሰው እና ሁኔታዎችን ከሚያስታውሳቸው ነገሮች ማራቅ

የህክምና ባለሙያን ማማከር የሚገባው መቼ ነው?

- የህይወት ትርጉም ማጣት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜቶችን ማስተናገድ ሲጀምሩ
- ምልክቶቹ በአኗኗር ዘይቤ ላይ ተፅእኖ ማስከተል ሲጀምሩ
- እራስን ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት ማሰብ ሲጀምሩ

በ ድህረ አደጋ ሽብረት የተጠቁ ሰዎች በሌላም ዓይነት የስነልቦና መረበሽ ህመም የመጠቃት እድላቸው ከፍ ያለ ስለሆነ በጊዜ የህክምና እርዳታ ቢያገኙ ይመከራል።

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

አምስት ጠቃሚ ምክሮች!

❶ ስኬት ጉዞ ነው:- ስኬት የማያቋርጥ የእድሜልክ የህይወት ጉዞ እንጂ መዳረሻ አይደለም።

❷ ያለፈው አልፏል:- ትላንት ማለፉን በመገንዘብ፣ በትላንት ስህተት እና ድክመቶች ከመቆጨት ለነገ ትምህርት መውሰድ።

❸ ዛሬ አዲስ ቀን ነው:- ትላንት አልፏል በዛሬ ግን ነገን ማስተካከል ይቻላል።

❹ ማንም ፍፁም አይደለም:- ፈተና ወይም ተግዳሮት የህይወት አንዱ አካል በመሆኑ በህይወት ጉዞ ወሰጥ መውደቅ እና መነሳት እንደሚያጋጥም በመረዳት ዝግጁ መሆን።

❺ ለበጎ ነው:- እያንዳንዱ መጥፎም ሆነ ጥሩ ክስተት ለነገ የተሻለ ውጤት እና ስኬት አስተማሪ መሆኑን መገንዘብ።

ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለመ አቀፉ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

በመኝታ ሰዓት እነኚህን ያስወግዱ!

በመኝታ ሰዓት ስማርት ስልኮችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ ታብሌቶችን እና ቲቪዎችን መጠቀም ለአእምሯችን ጤና የበለጠ አደገኛ የሚሆኑበት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ።

በመጀመሪያ: የእኛ ዲጂታል መሳሪያ ብዙውን ጊዜ የጭንቀት እና የሚያነቃ የይዘት ምንጭ ናቸው። ዜና ስንመለከት ወይም ከመተኛታችን በፊት በሰዎች ላይ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ስንበሳጭ ጭንቀትን ሊጨምር ይችላል ይህም ጥሩ እንቅልፍ እንዳንተኛ ያደርገናል (በኋላም የአዕምሮ ስራን ይጎዳል)።

በሁለተኛ ደረጃ: አንዳንድ ተመራማሪዎች በዲጂታል መሳሪያዎቻችን የሚወጣው ሰማያዊ መብራት ሜላቶኒን የእንቅልፍ ሆርሞንን ማምረት ይጎዳል ብለው ያምናሉ።

ከመተኛቶ በፊት ዲጂታል መሳሪያዎችን መጠቀም በጥልቅ እንቅልፍ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው ታይቷል።

መልካም ምሽት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ያሳዝኑኛል!

ባርኮት የ5 አመት ልጅ ነው። እናትና አባቱ በየቀኑ ይጣላሉ። ጭቅጭቃቸው ስለሚያስጨንቀው ቀኑ ሲመሽ መረበሽ ይጀምራል። አባቱ እናቱን ሲመታት የሚሰማውን ሐዘን መቋቋም ያቅተዋል። አቅም ኖሮት እናቱን መታደግ አለመቻሉ ያሳዝነዋል። በኮልታፋ አንደበቱ እናቱን "እማዬ ሳድግ አባዬን እመታልሻለው" ይላታል። ጓደኛው አቤል ዘወትር እሁድ ከእናቱና አባቱ ጋር ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ እሱ ለዚህ ነገር ለምን እንዳልታደለ ግራ ይገባዋል። ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት በራስ መተማመን የለውም።

ባርኮት ሲያድግ ምን አይነት ስብዕና ይኖረው ይሆን? ችግሮች በመወያየት መፍታት ይችል ይሆን? ጥሩ ትዳር ይመሰርት ይሆን? አላውቅም። ይሄ ታሪክ የባርኮትና የብዙ ልጆች ኑሮ ነው።

- በስነ ልቦና ሳያድጉ ልጅ በወለዱ ሐላፊነት በጎደላቸው ወላጆች ግጭት ምክንያት በጭንቀት ውስጥ የሚኖሩ ልጆች ያሳዝኑኛል።

- በቤተሰቦቻቸው ግጭት ምክንያት በልባቸው እሪታን የሚያሰሙ አድማጭ ግን የሌላቸው ህጻናት ያሳዝኑኛል።

- ትልቅ አቅም ያላቸው ነገር ግን በቤተሰቦቻቸው ግጭት ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ የሚያድጉ ህጻናት ያሳዝኑኛል።

ወላጆች ልጆች በእናንተ በኩል መጡ እንጂ ፈጣሪ በአደራ እንደሰጣቹ አስታውሱ። ልጆቻቹ ጤናማ ስነ ልቦና ይዘው እንዲያድጉ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።

ኤርሚያስ ኪሮስ (Counseling Psychologist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

⬆️ Training announcement!

Certificate course on applied counseling techniques and skills.

For further details and registration, use the link below! ⬇️

https://tinyurl.com/56tktzcj

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ግራ የተጋቡበት ጉዳይ አለ?

በሚጨነቁበት በማንኛውም ስነ ልቦናዊ ጉዳዮች ላይ ባለሙያዎቻችን ከፍቅርና ትህትና ጋር ደስተኛ ሆነው ህይወትዎን እንዲመሩ ይረዷቹሀል።

ወደ ስነ ልቦና ምክክር አገልግሎት የሚመጡ ሰዎች ደስተኛ፣ ስኬታማና ከፍተኛ ችግር የመፍታት አቅም ይኖራቸዋል።

የሚጨነቁበት ማንኛውም ስነልቦናዊ ጉዳይ መፍትሔ አለው፣ ያማክሩን!

አድራሻችን: ጀሞ ሚካኤል ቤ/ክ አጠገብ ንብ ባንክ ያለበት ህንጻ 4ኛ ፎቅ።

ስልክ: 0967678832
       +251940594855

ራዕያችን ሁለንተናዊ ስኬት ያለው ትውልድ ተፈጥሮ ማየት ነው።

(ፍካት የሥነ ልቦና ማማከር አግልግሎት)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

ዲስሌክሲያ| Dyslexia

ዲስሌክሲያ ማለት የንግግር ድምፆችን በመለየት፣ ደብዳቤዎች እና ቃላት የመማር ችግሮችንና ንባብን የሚያካትት የመማር ችግር ነው፡፡

ዲስሌክሲያ ቋንቋን በሚሠሩ የአንጎል አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ዲስሌክሲያ ያለባቸው ሰዎች መደበኛ የማሰብ ችሎታ ያላቸው እና ብዙውን ጊዜ መደበኛ የማየት ችሎታ አላቸው።

ምልክቶች፦

- የዲስሌክሲያ ምልክቶች ልጅዎ ትምህርት ቤት ከመግባቱ በፊት ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ግን አንዳንድ የመጀመሪያ ፍንጮች ችግርን ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡

- አንዴ ልጅዎ ዕድሜው ለትምህርት ከደረሰ በኋላ ይሄን ችግር ለማስተዋል የልጅዎ አስተማሪ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል፡፡

- የዲስሌክሲያ ክብደት ይለያያል፤ ነገር ግን አንድ ልጅ ማንበብ መማር ሲጀምር ሁኔታው ​​ብዙ ጊዜ ይገለጣል።

ከትምህርት ቤት በፊት

አንድ ትንሽ ልጅ ዲስሌክሲያ የመያዝ እክል ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚያሳዩት ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡

- ዘግይቶ ማውራት
- አዳዲስ ቃላትን በቀስታ መማር
- ቃላትን በትክክል የመፍጠር ችግሮች

ለምሳሌ፦ በቃላት ውስጥ ያሉ ድምፆችን መለወጥ ወይም በተመሳሳይ ድምጽ ቃላትን መተካት ችግሮች።

- ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን እና ቀለሞችን የማስታወስ ወይም የመሰየም ችግሮች።

በትምህርት ዕድሜ
 
አንዴ ልጅዎ ትምህርት ቤት ውስጥ ከገባ የዲስሌክሲያ ምልክቶች የበለጠ ግልጽ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ፦

- የሚሰማውን የመስራት እና የመረዳት ችግሮች
- ትክክለኛውን ቃል የማግኘት ችግር
- ለጥያቄዎች መልስ የመስጠት ችግር
- የነገሮችን ቅደም ተከተል የማስታወስ ችግሮች
- በፊደላት እና በቃላት ተመሳሳይነት እና ልዩነቶች የማየት አልፎ አልፎም የመስማት ችግር
- የማይታወቅ ቃል አጠራር ድምፁን ማሰማት አለመቻል
- የፊደል አፃፃፍ ችግር
- ንባብን ወይም መጻፍን የሚመለከቱ ነገሮችን ወደ ጎን መተው
- ስራዎችን ባልተለመደ ሁኔታ ረዘም ላለ ጊዜ ማሳለፍ
- ንባብን የሚያካትቱ እንቅስቃሴዎችን ማስወገድ

ወጣቶች እና ጎልማሶች

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እና በአዋቂዎች ላይ የሚከሰት ዲስሌክሲያ ምልክቶች በልጆች ላይ ካሉት ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

በአሥራዎቹ ዕድሜ እና በአዋቂዎች ውስጥ አንዳንድ የተለመዱ ዲስሌክሲያ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

- ጮክ ብሎ ማንበብን ጨምሮ የማንበብ ችግር
- ቀርፋፋ እና ጉልበት-ተኮር ንባብ እና ጽሑፍ
- የፊደል አጻጻፍ ችግሮች
- ንባብን የሚያካትቱ እንቅስቃሴዎችን ማስወገድ
- ስሞችን ወይም ቃላትን በስህተት መግለጽ ወይም ቃላትን ሰርስሮ የማውጣት ችግሮች
- ከተለዩ ቃላት (ፈሊጦች) በቀላሉ የማይገባ ትርጓሜ ያላቸውን ቀልዶች ወይም አገላለጾችን የመረዳት ችግር
- ንባብን ወይም መጻፍን የሚመለከቱ ስራዎችን ባልተለመደ ሁኔታ ረዘም ላለ ጊዜ ማሳለፍ
- ታሪክን የማጠቃለል ችግር
- የውጭ ቋንቋ መማር ላይ ችግር
- የማስታወስ ችግር
- የሂሳብ ስሌቶችን የመስራት ችግር

ዲስሌክሲያ በቤተሰብ ወይም በዘር ይሄዳል፡፡

የዲስሌክሲያ የሚያስከትሉ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

- ዲስሌክሲያ ወይም ሌላ የመማር ችግር ያለባቸው የቤተሰብ ታሪክ
- ያለጊዜው መወለድ ወይም ዝቅተኛ ክብደት
- በእርግዝና ወቅት ለኒኮቲን፣ ለአደንዛዥ ዕፅ፣ ለአልኮል ወይም ለጽንሱ የአንጎል እድገትን ሊለውጥ ለሚችል ኢንፌክሽን መጋለጥ
- ንባብን በሚያስችሉት በአንጎል ክፍሎች ውስጥ ችግሮች

ዲስሌክሌሲያ የሚከተሉትን ችግሮች ጨምሮ በርካታ ችግሮችን ያስከትላል፦

- የመማር ችግር
- ማህበራዊ ችግሮች
- የባህሪ ችግሮች

ዲስሌክሲያ ያለባቸው ልጆች በትኩረት ማነስ/ ከመጠን በላይ የመነቃቃት ችግር ADHD የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። በተቃራኒው ደግሞ ኤ.ዲ.ኤች. ዲ ዲስሌክሲያ ለማከም አስቸጋሪ እንዲሆን የሚያደርግ ትኩረትን እንዲሁም ከመጠን በላይ የመነቃቃት እና ስሜታዊነት ባህሪን የማስቀጠል ችግርን ያስከትላል፡፡

ህክምና

ዲስሌክሲያ መመርመር የሚችል አንድ ነጠላ ምርመራ የለም፡፡ የልጅዎ እድገት፣ የትምህርት ጉዳዮች እና የህክምና ታሪክ ምርመራ ውስጥ ይካተታሉ።

ዲስሌክሲያ የሚያስከትለውን መሠረታዊ የአንጎል ያልተለመደ ሁኔታ ለማስተካከል የሚታወቅ መንገድ የለም።

ዲስሌክሲያ የዕድሜ ልክ ችግር ነው፤ ሆኖም የተወሰኑ ፍላጎቶችን እና ተገቢ ህክምናን ለመወሰን ቅድመ ምርመራ እና ግምገማ ስኬታማነትን ሊያሻሽል ይችላል፡፡

የንግግር እና ቋንቋ ህክምና (Speech and Language Therapy) ባለሙያዎች ለዲስሌክሲያ ሕክምና ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

የንግግር እና ቋንቋ ህክምና ለማግኘት፦

ስልክ: 0978806778/ 0974088763

Akalu assefa (speech pathologist)

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የመንፈስ ጭንቀትን ለማስወገድ!

የመንፈስ ጭንቀት በማንኛውም ዕድሜ እና በማንኛውም ሰው ላይ ሊደርስ ይችላል። ሰዎች የመንፈስ ጭንቀትን ለማከም እንደ ፀረ-ጭንቀት ያሉ መድሃኒቶችን ይወስዳሉ፤ ነገር ግን የተለያዩ የተፈጥሮ ዘዴዎች ምልክቶቹን ለመቆጣጠር እና የወደፊት አደጋ ለመቀነስ ይረዳሉ።

እንግዲያውስ ቀጣዮቹን የባለሙያ ምክሮች ይከተሉ፦

- ትኩረት የምናደርግበትን ነገር መምረጥ፣

- የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መመጠን፣ የምንሰማውን ዜና መምረጥ፣

- በቂ የእረፍትና የመዝናኛ ጊዜ መውሰድ፣

- በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣

- አልኮል እና አደንዛዥ ዕፅ አለመጠቀም፣

- ትክክለኛውን ሰዓት የጠበቀና የተመጣጠነ አመጋገብን መከተል፣

- መጽሐፍ ማንበብ እና በቂ የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ማድረግ፣

- ጊዜንና ሰዓትን በአግባቡና በልኩ መጠቀም መልመድ፣

- መጨነቅ በማይገቡን ነገሮች አለመጨናነቅ፣

- ከችግሩ ይልቅ መፍትሔው ላይ ትኩርት ማድረግ፣

- ከቅርብ ቤተሰብና ወዳጆች ጋር በቂ ጊዜን ማሳለፍ፣

- ባለሙያ በማማከር የንግግር ሕክምና (Psychotherapy) ያግኙ።

መልካም እለተ ሰንበት!

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

#ምሉዕፋውንዴሽን

ምሉዕ ፋውንዴሽን ሀገርበቀል የበጎአድራጎት ድርጅት ሲሆን ባለትዳሮቹ ወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ እና አቶ ክንፈ ጽጌ የበኩር ልጅ በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖር ታዳጊ በመሆኑ እርሱን በማሳደግ ሂደት ያጋጠሟቸው ውጣ ውረዶችና ያካበቷቸውን ልምዶች ለሌሎች ለማጋራት በማሰብ እንዲሁም በሥራ አጋጣሚ ያካበቱትን ልምድና ዕውቀት በመጠቀም የተቀናጀ ማሕበረሰብ ለመፍጠር በማሰብ የተቋቋመ ድርጅት ነው።

ምሉዕ ፋውንዴሽን በአሁኑ ጊዜ ለማሕበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር፣ እንዲሁም ወላጆችን በማማከር፣ ለተንከባካቢዎች፣ ለትምህርት ቤቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች ስልጠና በመስጠት በተጨማሪም በማዕከሉ ቤተመጻሕፍት በማቋቋም ማህበረሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛል።

በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥም ሰፊ ጥናት በማካሄድ ለልዩ ፍላጎት ልጆችና ወላጆቻቸው የሚሆን የቴራፒ ማዕከል ለማቋቋም እየሰራ ይገኛል። የቴራፒ ማዕከሉን ለማቋቋም የሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ በመሆኑ ወጪውን ለመሸፈን ጥር 25/2015 በሸራተን ሆቴል የእርዳታ ማሰባሰቢያ የእራት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። ለዚህ ዓላማ ዕውን መሆን እያንዳንዳችን የድርሻችንን እንወጣ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል።

በስልክ ቁጥር 0906243432/ 0941024444 ይደውሉልን።

ፕሮጀክቱን ለመደገፍ: አቢሲኒያ ባንክ
አካውንት ቁጥር 75031963
ስዊፍት ኮድ ABYSETAA

#Mentalwellness

@melkam_enaseb

Читать полностью…

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

The WHO guidelines on mental health at work

The WHO guidelines on mental health at work provide evidence-based recommendations to promote mental health, prevent mental health conditions, and enable people living with mental health conditions to participate and thrive in work. The recommendations cover organizational interventions, manager training and worker training, individual interventions, return to work, and gaining employment. The guidelines on mental health at work aim to improve the implementation of evidence-based interventions for mental health at work.

@melkam_enaseb

Читать полностью…
Subscribe to a channel