ውድቀታችን የኑረታችን መጨረሻ አይደለም!
ሁሉንም ነገር ከልብ ከፈለግነው ያደክመናል እንጂ አናጣውም። ከልቡ የፈለገ ሰው የልቡን አያጣም።
ሽንፈቶቻችን ሁሉ በጥረቶቻችን ይሸነፋሉ። ድክመቶቻችንም በጥንካሬአችን ይደመሰሳሉ። በማይቆም ጥረት ውስጥ ስንኖር ለማይቀር ድል እንታጫለን።
የምንኖረው መሆን እና አለመሆን በሚፈራረቁባት ምድር ላይ በመሆኑ ለደቂቃም ቢሆን ጥሮና ግሮ ከመኖር አንታቀብ። ብዙ ነገር ሊያጥረን ይችላል ነገር ግን የሁሉም እጥረቶች ማጥፊያ ራሱ ጥረት ብቻ መሆኑን አንርሳ።
ከተጋን እየፈካን እንኖራለን። ትጋታችን ምኞታችንን ከተረትነት ይታደገዋል። ሳንሰለች ከታገልን የፈለግነው ሁሉ እኛን ይፈልገናል።
በከፈለኝ ዘለለው ['አሞዛ']
መልካም ቀን!
@melkam_enaseb
⬆️ You are invited to join a Zoom webinar!
When: Wed, march 15, 2023 at 12:00 Pm.
Topic: Management of Schizophrenia especially on the newly imported drug Paliperidone.
Join Zoom Meeting: https://us05web.zoom.us/j/4284924927?pwd=QjV1aWhxUnV1REQrcUJqdjdrUzFXZz09
Meeting ID: 428 492 4927
Passcode: sitota
@melkam_enaseb
ስብዕና!
"ከህመሞች ሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን ከስብዕና መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሠው የገጽ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሠው እውነተኛ መልክ ነው። በየዕለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር፣ እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ሰብዕናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ሰብዕናችን ነው። የሰብዕና ስንኩልነት፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፣ አገር ይንዳሉ፣ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከም ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።
ሰብዕና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሠው ሰብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካለገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። ዕድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና።"
(''ሌላ ሰው'' መጽሐፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ)
@melkam_enaseb
"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?
እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...
እያልክ ይሆናል።
ትክክል ብለሃል። ይሁንና ጨርሰህ መርሳት የሌለብህ...
ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች። ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ።
ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።
እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።
ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።
አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
(Samuel Geda)
@melkam_enaseb
ከቀዳዳ ጀልባ ላይ ውሀ በማንኪያ!
አማኑኤል ሆስፒታል በሀገራችን ብቸኛው የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው። ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ አልጋዎች አሉት። በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ወደ አርባ ክፍሎች አሉት።
የአእምሮ ህመም ከ5 ሰው 1 ሰው ላይ ይከሰታል። በሀገራችን ያለው የአእምሮ ህመም ስርጭት (Life time prevalence) 27% ነው። የሀገራችን ህዝብ 120 ሚልየን ይገመታል። ያ ማለት 30 ሚሊዮን ህዝብ በአንድ ወይም በሌላ ወቅት የአእምሮ ህመም ያጋጥመዋል ማለት ነው። በሚያሳዝን መልኩ አብዛኞቻችን የአእምሮ ህመም የሚመስለን ልብሱን አውልቆ ጎዳና የወጣ ሰው ነው። የአእምሮ ህመም ማለት ህፃናት ላይ የሚከሰት ትኩረት ያለማድረግ ችግር (ADHD)፣ መኮላተፍ (Fluency disorders)፣ ከ5አመት በኋላ አልጋ ላይ መሽናት (enuresis)፣ በአስራዎቸ እድሜ የሚከሰቱ የስሜት መዋዠቅ፣ የድብርት ህመም (Depression)፣ ሱስ፣ የእንቅልፍ ችግር (Insomnia)፣ የወሲብ ፍላጎት አለመኖር (Hypoactive sexual desire disorder)፣ በእድሜ ማምሻ ላይ የሚከሰት የመርሳት ህመም (Dementias) .....ወዘተ ማለት ነው።
የአእምሮ ህመም በሁሉም ክልሎች ይከሰታል። ገጠርና ከተማ፣ ብሄርና ሀይማኖት አይለይም። ከአእምሮ ህመም ስርጭት አንፃር አንድ አማኑኤል የሚሰጥ አገልግሎት ከቀዳዳ ጀልባ ላይ የሞላውን ውሀ በማንኪያ እንደመድፋት ነው። ትልልቅ የአእምሮ ህክምና ተቋማት ቢቻል በየዞኑ ባይሆን በየክልሎች ያስፈልጋል። 27% ማለት ሁላችንም ቤት ያለ ጉዳይ ማለት ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
@melkam_enaseb
አዲስ ምዕራፍ በዳዊት ድሪምስ!
የ21 ቀን ፓራዳይም ሺፍት ስልጠና መጋቢት አንድ ይጀምራል።
ለመመዝገብ: +251938252525
@melkam_enaseb
ልባችን ከእድሜያችን በላይ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ?
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ልባችን ከእኛ ቀድሞ እንዲያረጅ የሚያደርጉ ናቸውና አስቀድመን ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል።
1. ጭንቀት
ልብን በፍጥነት ከሚያስረጁ ምክንያቶች ቀዳሚው ጭንቀት መሆኑን ጆን ሆፕኪንስ ያወጣው ጥናት ያሳያል። ጭቅጭቅ የበዛበት ትዳር ውስጥ ያሉ እና ፍቺ የተደጋገመባቸው ሰዎች ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመላከተው። በጭንቀት ጊዜ ሰውነታችን የሚለቃቸው ኬሚካሎች የደም ግፊት እና የመጥፎ ኮሊስትሮል መጠን እንዲጨምር ማድረጉም የልብ ጤናን እንዲያውክ ያደርገዋል።
2. የእንቅልፍ እጦት
በቂ የእንቅልፍ ጊዜ ማጣትም የደም ዝውውርን በማፍጠን በልብ ላይ ከፍተኛ ጫናን ያሳድራል። ይህም የልብ ጤናን በረጅም ጊዜ ክፉኛ የሚጎዳው ሲሆን ልባችን ያለጊዜው ያስረጀዋል ይላል የሲ ዲ ሲ ጥናት።
3. አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ
ማዮ ክሊኒክ በ2019 ባደረገው ጥናት የልብ እርጅናን ለመቀነስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አመላክቷል። በወር ውስጥ ለ150 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግንም የልብ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው በሚል ይመክራል።
4. ሲጋራ ማጨስ
“ሲጋራ ማጨስ ሳንባን ብቻ ይጎዳል ብላችሁ የምታስቡ ተሳስታችኋል” የሚለው ሲ ዲ ሲ፥ ማጨስ የልብ ጤና ጸር መሆኑን ይገልጻል። በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ኪሚካሎች የደም መርጋትን በማስከተል በልብ ላይ ጫና እንደሚፈጥሩ በጥናት ተረጋግጧል። እናም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ልባቸው ከእድሜያቸው በፊት ከማርጀቱ በፊት ማጨስ ያቁሙ ሲልም ያሳስባል ሲ ዲ ሲ።
በአጠቃላይ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል።
(አል-አይን)
@melkam_enaseb
"አልችልምን" መሰረዝ!
ሁላችንም እኛን ለማጥፋት ኃይል ያለውን ቃል ተሸክመን ነው የምነዞረው....ይሄውም ቃል "አልችልም." ነው።
ይህ ቃል ነፍስን ይሰብራል፣ ህልምን ያጨናግፋል።
"አልችልም" ... ብዙዎቻችን ያለንን አቅም እንዳንጠቀም የሚከለክለን ቃል ነው።
በህይወታችን ለውጥን የምንሻ ከሆነ...... "አልችልም" የሚለውን ቃል ከመጠቀም መንፃት አለብን፣ በምትኩም በተሻለ፣ ጠንካራ፣ እና ተስፋን በሚያጭር ቃል መተካት ተገቢ ነው።
"አልችልም"ን በአወንታዊ በሆኑ እንደ "የመቻል አቅም አለኝ"፣ "በሙከራዬ አሳካዋለሁ"፣ "የማሳካት አቅም አለኝ" ወ.ዘ.ተ. በመሳሰሉ ቃላት ስንቀይር..... በመንገዳችን የተጋረጡትን መሰናክሎች ጠርምሰን የማለፍ አቅምን ማካበት እንጀምራለን፣ ከዛም በተጨማሪ ተግዳሮቶችን የምንጋፈጥበትን ዘዴ በጥሞና እናስተካክላለን።
በጥቅሉ "አልችልም" የሚለው ቃል ከንግግራችን ሲጠፋ፣ በምትኩ ችግሮቹን የምንወጣበት ዘዴ የመፈለግ ተነሳሽነታችን ይጨምራል!
ጥበብ እና ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!
ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለመ አቀፉ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
መልካም ቀን!
@melkam_enaseb
እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
ክብርና ሞገስ ከወራሪ ነፃ የሆነች ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን።
@melkam_enaseb
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና ከሱስና ተያያዥ ችግሮች ጋር በተያያዘ ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ስለ ድብርት መንስዔ፣ ምልክቶች፣ ጉዳት እና ሕክምና ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ድብርት ምንድን ነው? ምልክቶቹስ?
የድብርት (ዲፕሬሽን) ሕመም በሰፊው ከሚታዩ የአዕምሮ ጤና ችግሮች አንዱ ሲሆን÷ የስሜት መውረድን ብሎም የደስታ ስሜት ማጣትን ያሳያል፡፡ እንደ ባለሙያው ገለጻ አንድ ሰው በድብርት ውስጥ ሲሆን በውስጣዊ ስሜቱ እና በውጫዊ ገጽታው እንደሚንጸባረቁ ጠቅሰው÷ ይህም ደስታ ማጣት፣ መከፋት፣ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ውስጥ መሆን ናቸው፡፡
ድብርት የስሜት በሽታ በመሆኑ ከስሜት መቃወስ ጋር ተያይዞ የሐሳብ መዛባት ያስከትላል ብለዋል፡፡ በዚህም ሰዎች ለእራሳቸው፣ ለሕይወት እና ለቀጣይ ኑሯቸው ያላቸው አመለካከት ጨለምተኛ የመሆን አዝማሚያ ይታይበታልም ነው የሚሉት።
ከድብርት መገለጫዎች መካከል፦
የስሜት መዛባት፣ በፊት ያስደስቱ በነበሩ ሁኔታዎች አለመደሰትና አለመፈለግ፣ የአስተሳሰብ (የአዕምሮ እና የአካል) ፍጥነት መቀነስ (ዘገምተኝነት)፣ የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ ይጠቀሳሉ፡፡
በአንጻሩ በአንዳድ ሰዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ምክንያቱ በግልጽ ያልታወቀ ከፍተኛ ድካም፣ እራስን በከፍተኛ ሁኔታ አሳንሶ ማየት፣ እራስን በከፍተኛ ሁኔታ መውቀስ (የተጋነነ የጥፋተኝት ስሜት)፣ የኃጢያተኝነት ስሜት፣ ሕይወትንና ኑሮን መጥላት፣ ሞትን መመኘት፣ እራስን ለማጥፋት ማሰብ ብሎም ለማጥፋት መሞከር የድብርት መገለጫዎች ናቸው፡፡
የድብርት መንስኤ ይታወቃል?
ድብርት ብዙ ጊዜ እንደማንኛውም የአዕምሮ ህመም ቁርጥ ያለ መንስኤ ባይኖረውም÷ የታወቁ ሥነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና አካላዊ አጋላጭ ሁኔታዎች አሉት ይላሉ ባለሙያው፡፡ ጾታዊ ጥቃት፣ ድንገተኛ የኢኮኖሚ ክስረት፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋን ተከትሎ የሚፈጠር ማህበራዊ መቃወስ፣ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ከፍተኛ ጫናዎች እና ከሥራ መፈናቀል ለድብርት አጋላጭ የሚባሉ ማህበራዊ ችግሮች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ከሥነ-ልቦናዊ ችግሮች መካከል የአዕምሮ ጥቃት ለድብርት አጋላጭ መሆኑ ሲጠቀስ÷ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ እና አነቃቂ ዕጾች እና ሥር የሰደዱ አካላዊ (ሥነ ሕይወታዊ) ህመሞች በድብርት አጋላጭነታቸው ይነሳሉ፡፡
ድብርት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ስላለው በቤተሰባቸው የድብርት ህመም ታሪክ ያላቸው ሰዎች ለድብርት የመጋለጥ ዕድላቸው እንደሚጨምር ተገልጿል። ድብርት በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ሊታይ እንደሚችል ቢታመንም በተለይ በጉርምስና እና በ40ዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል ላይ በጉልህ ይታያል፡፡
ድብርት ሕክምና አለው?
ድብርት እንደ ሕመሙ ዓይነትና ክብደት በምርመራ ተለይቶ ሥነ-ልቦናዊ (ሳይኮ ቴራፒ) እና የመድኃኒት ሕክምና ይሰጣል፡፡ የድብርቱ ዓይነት ቀላል ከሆነ ሥነ-ልቦናዊ ሕክምና፣ ከባድ ከሆነ ደግሞ የመድኃኒት ሕክምና ይሰጣል።
በተጨማሪም የሕመሙ ተጠቂዎች ሆስፒታል ተኝተው ሊታከሙ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ ሕመሙ ሥር ሰዶ ምግብ መመገብ፣ መናገር ብሎም መድኃኒት ለመውሰድ ፈቃደኛ የማይሆኑበት ጊዜ ከደረሰ አንጎልን በኤሌክትሪክ የማነቃቃት ሕክምና ሊሰጥ ይችላል፡፡
ድብርት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በእጥፍ ጨምሮ የሚታይበት ሁኔታ በግልፅ ባይታወቅም መላ-ምቶች እንዳሉ ግን ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ያስቀምጣሉ፡፡ በሴቶች ላይ በተፈጥሮ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚቀያየሩ የሆርሞን ልዩነቶች (ከወሊድ በኋላ ለሚከሰት ድብርት)፣ እንዲሁም በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያሉ የተፈጥሮ ቅመሞችን ለአብነት ጠቅሰዋል። ከሥነ-ልቦና አንጻርም ሴቶች ለድብርት የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሳሉ፤ ለምሳሌ ተገዳ የተደፈረች ሴት ለድብርት የመጋለጥ ዕድሏ ሠፊ ሊሆን እንደሚችል በመጥቀስ።
በተመሳሳይ ሴቶች ላይ የቤት ውስጥ ጥቃት መበራከቱ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች በማህበራዊ አጋላጭ ምክንያቶች በአብዛኛው ለድብርት ሊጋለጡ እንደሚችሉም መላ-ምቶች መኖራቸውን ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ጠቅሰዋል፡፡
@melkam_enaseb
መጋቢት 10
የአለም አቀፍ የዳዉን ሲንድረምን ቀን ''ስለኛ ከእኛ ጋር'' በሚል መሪ ቃል አብረዉን በመጋቢት 10 በወዳጅነት ፖርክ እያከበሩ፣ ግንዛቤ ያስጨብጡ፣ አብረዉን ይስሩ።
Call +251942225838 for t-shirt orders.
(Deborah Foundation)
@melkam_enaseb
⬆️ Life Improvement Training!
13ኛ ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል!
ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና #የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡
ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
@melkam_enaseb
ስሜታዊ ምክንያት (Emotional Reasoning)
በሳይኮሎጂ ሳይንስ አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነገሮችን እንዴት እንደምንረዳና ወደ አእምሮ የሚገቡ መረጃዎች በአስተሳሰብ፣ በስሜትና በባህሪ የሚኖራቸውን ተፅእኖ መመልከት ነው።
የሰው ልጅ ጥሩ ስሜት እንዳይሰማውና ያልተገባ አስተሳሰብ እንዲያስብ ከዛም በዘለለ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያከናወን ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በእውነታ ላይ ያለ ነገርን በተዛባ አመለካከት (አስተሳሰብ) መንገድ መረዳት ነው፤ misinterpretation of reality ብንለውም ይገልፀዋል። የሳይኮሎጂ ጠበብቶች Cognitive Distortion ይሉታል።
አንድ ሰው በተደጋጋሚ ነገሮች የሚረዳበት ሁኔታ የተንሸዋረረ ከሆነ፣ አጋኖ የሚመለከት፣ በአንድ እይታ ብቻ የሚያየው ከሆነ፣ ሌላ አማራጭ የለም አይነት አረዳድ ካለው ለተለያዩ የስነልቦና ችግሮች የመጋለጥ እድሉ ሰፊ ነው።
Cognitive Distortion በአይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን እንኳን ብንጠቅስ Emotional Reasoning የሚል እናገኛለን። ስሜታችን በሚነግረን መልእክት እውነታውን ያላገናዘበ ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ነው። እየተደረገ ያለውን ነባራዊ እውነታ ትተን የስሜት መርህ መከተል የሚል አንደምታ አለው። ይህ ማለት ማሰብ ትተን በስሜት መነዳት ማለት ነው።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በውስጡ የቅናት ስሜት ስለተሰማው ብቻ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር ትማግጣለች ብሎ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ሚስቱ ለትዳሯ ታማኝ እያለች ነው።
ስለዚህ በEmotional Reasoning እሳቤ መሠረት በነገሮች ላይ የሚኖረን አስተሳሰብ፣ እምነትና አቋም የሚወሰነው በምናስበው ምክንያታዊ አስተሳሰብ ሳይሆን እውነታውን ያላገናዘበ በሚሰማን ስሜት ነው።
#zepsychologist
@melkam_enaseb
ማክሰኞን ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ የት ለማሳለፍ አስበዋል?
የአርምሞ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ ሳይኮቴራፒስት፣ የ5 መጽሐፍት ደራሲ፣ ሃይፕኖቴራፒስት እንዲሁም የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ማክሰኞ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በዳዊት ድሪምስ መድረክ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ማዕድ ሊያጋራን ተዘጋጅቷል።
ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
መግቢያ በነፃ VIP REP 200birr
ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ።
@melkam_enaseb
ዛሬ ደብሮኛል።
ትላንትም ደብሮኝ ነበር።
ከትላንት ወዲያም እንደዛው።
ያለ ምንም ምክንያት ይደብረኛል።
በምንም ምክንያት ድብርቴ አይጠፋም።
እየተዝናናሁ ይደብረኛል። እየሳቅሁ ይከፋኛል። እየተጫወትኩ ይደብተኛል። አዎ! በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ይደብረኛል።
ስራ እየሰራሁ ይደብረኛል። ሰው በእኔ ደስ እያለው እንኳን ደስታውን መጋራት አልችልም። ሰውን ማስደሰት ጥሬ ግሬ የማደርገው ነገር ነው፣ ተሳክቶልኝ እነሱ ደስ ሲላቸው፣ እኔ ግን ደስ አይለኝም።
እረፍት ስሆን ደግሞ ይብስብኛል። የምይዘው፣ የምጨብጠው አጣለሁ። ሁሉም ነገር ያስጠላኛል። ድሮ የሚጣፍጠኝ፣ አሁን ውሃ ውሃ ይለኛል። ቀድሞ ስሜት የሚሰጠኝ፣ አሁን ስሜት ይነሳኛል።
የምሰማው ነገር ከፍቼ፣ ጆሮዬ ቢሰማውም ውስጤ አይደርስም። ዝም ሲል ደግሞ፣ ውስጤ ይጮሃል። ድምፅ ይረብሸኛል፤ ፀጥታ ያስፈራኛል።
የከፋው፣ የደበረው፣ የተቸገረ ሰው ሳገኝ ደግሞ በእርሱ ቦታ ራሴን አገኘዋለሁ። እሱን ማዳመጥ፣ መርዳት፣ ማስደሰት ይጠማኛል፤ ግዴታዬ፣ አላማዬ፣ ስራዬ አደርገዋለሁ። ወጥጄ ወርጄ አሳካዋለሁ፣ እኔ ግን እዛው ድብርቴ ውስጥ እቆያለሁ።
የምፈልገው ነገር የለም። መፈለግ ራሱ ያስጠላኛል። ድሮ የፈለኩት እንኳ ሲሳካልኝ አያስደስተኝም።
መተኛት እፈልጋለሁ፣ እንቅልፍ አይወስደኝም። ከተኛሁ ደግሞ አልነቃም። የብዙ ሰዓት እንቅልፍ ተኝቼ እረፍት አይሰማኝም። አካሌም፣ አዕምሮዬም ይዝላል።
ተኝቼ አዕምሮዬ ንቁ ነው፣ ሲጨነቅ፣ ሲባዝን ያድራል። ነቅቼ ውሎዬን እየዋልኩ ደግሞ አዕምሮዬ ይተኛል፣ ይደነዝዛል፣ ይደበራል።
በቃ! ትናንት እንዲሁ ነበር፣ ዛሬም እንደዚህ ያልፋል፣ ነገም እንደዛው።
ከአልጋዬ መነሳት አልችልም።
ባልነሳ እመርጣለሁ። ግን ደግሞ ተጋድሜ ይደክመኛል። እያረፍኩ፣ እረፍቴ እረፍት ይነሳኛል። ውጣ ውጣ ይለኛል፣ መውጣት ሳስብ ደግሞ ልቤ ፍስስ ይላል፣ ቀድሞ ይደክመኛል፣ ሳስበው ያስጠላኛል።
አዕምሮዬ ብቻ አይደለም የሚረብሸኝ።
እጆቼ፣ እግሮቼ፣ ወገቤ፣ ጡንቻዎቼ ሁሉም እረፍት አጥተው፤ እረፍት ይነሱኛል። ህመም አይሉት ድካም፣ ብቻ ይረብሹኛል። እነርሱን ተከትሎ ደግሞ ራሴ ይቃጠላል፤ ያለማቋረጥ ይበላኛል። ራስ ምታት አትለው ይሄኛው ይለያል።
አብዛኛው ቀኖች እንደዚህ ያልፋሉ።
ሁሌም ትግል ውስጥ፣ ሁሌም ስቃይ ውስጥ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ጤነኛ መሆን፣ ለአንድ ቀንም እንኳን Normal መሆን ያምረኛል፣ ግን ደግሞ አልፈልግም፣ እርሱም ያስጠላኛል።
አልቅስ አልቅስ የሚል ስሜት ይወረኛል፣ ግን ደግሞ እንባ ከየት ይመጣል። ያለ ምክንያትስ እንዴት አለቅሳለሁ? ባለቅስም እንደማይወጣልኝ ደግሞ አውቃለሁ።
በዚሁ ሁሉ ግን አላማርርም፣ ካማረርኩ ደግሞ የባሰ ይጨንቀኛል፣ የበለጠ ይደብረኛል። ላማር ብልስ በምን አማርራለሁ፣ የጎደለኝ የለ፣ ሁሉ ሞልቶልኛል። ግን እንዲሁ፣ እንዲሁ ይደብረኛል።
ይህ ልብወለድ ወይም የሌላ ሰው ታሪክ አይደለም፣ የእኔ የራሴ የዕለት ተዕለት ኑሮዬ ነው።
ለምን አለቀስኩባችሁ?!
So ከአካፈልኳችሁ ስሜቶቼ መረዳት እንደምትችሉት Clinical Depression (Mood Disorder) አለብኝ።
ከዚህ ችግር ጋ መኖር ከጀመርኩ ወደ 7 አመት ሆኖኛል። ባለሙያ አማክሬ ደግሞ ችግሩ ከተነገረኝ 4 አመት ሆኖኛል። So ለእኔ ይህ አዲስ ነገር አይደለም።
እንደ እኔ አውጥቶ ባይናገረውም ከተመሳሳይ ችግር ጋር እየታገለ የሚኖር ብዙ ሰው አለ፣ እና "አይዟችሁ! ብቻችሁን አይደላችሁም!" ለማለት ስለፈለግኩ ነው።
እዚህ Facebook ላይ ሲመቸን እና ሲደላን ብቻ እየለፈለፍን ከሌላው የተሻለ ኑሮ እንደምንኖር ሰው ማሰብ የለበትም። ድካማችንንም share ብናደርግ፣ ሌላ ሰው ያግዛል ብዬ አስባለሁ።።
ያለቃቀስኩት ሰው አይዞህ እንዲለኝ ሳይሆን፣ ሰውን አይዞህ ለማለት ነው። እወዳችኋለሁ።
(ከአንድ አመት በፊት የተፃፈ)
✍ ዶ/ር ሱራፌል አየለ
Via: Hakim
@melkam_enaseb
የ CBT ስልጠና!
ለተጨማሪ መረጃ እንዲሁም ምዝገባ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ይጠቀሙ።
Certificate Course on Cognitive Behavioral Therapy!
For further details and registration, use the link below!
https://forms.gle/XBxigR7BG2EeDc3m6
(Aha Psychological Services)
@melkam_enaseb
ስኬታማ ሴት ልጆችን ለማሳደግ የወላጆች ድርሻ!
በመጀመሪያ ስኬታማ ሴት ማለት ምን ማለት ነው?
- በራሷ የምትተማመን፣ ውሳኔዎች የመወሰን አቅም ያላት፣
- ምርጫዋን የምታውቅና የሌሎችን ምርጫ የምታከብር፣
- ጊዜዋን በዋዛ ፈዛዛ የማታሳልፍ፣ ችግሮችን ለመፍታት የራሷን አስተዋፆ የምታበረክት፣
- ስሜትና ሀሳቧን የምትገልፅ፣ እችላለሁ የሚል አመለካከት ያላት፣
- ራሷን እና ሌሎችን የምታከብር፣ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ የሆነች፣
- ችግር ባጋጠማት ጊዜ ከችግሩ ይልቅ መፍትሔው ላይ የምታተኩር፣
- ለፈጣሪዋ፣ ለባሏ እና ለቤተሰቧ ታማኝ የሆነች፣
- የሴቶች የሆነውን ርህራሄ እና ደግነት ያላት፣
- ራስ በመቻል የምታምን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሌሎችን እርዳታ የምትጠይቅ፣
- ሂወትን እና ዙሪያዋን በአግባቡ የምትረዳ እና ሌሌችን ለመምሰል ጊዜ የማታባክን፣
- በጥላቻ፣ ክፋት እና ሃሜት የሚወረወርባትን ድንጋይ ለውድቀት ምክንያት ሳይሆን ወደከፍታ ለመውጣት ድልድይ የምታደርግ እና ለልጆቿ መልካም አርአያ የሆነች ናት።
ታዲያ እንዲህ አይነት ሴት ለማፍራት ሴት ልጆችን እንዴት እናሳድግ?
1. በዕለት-ተዕለት እንቅስቃሴዋ እኛ እናውቅልሻለን ብለን ለሷ ከመወሰን ይልቅ ራሷ እንድትወስን እድል እንስጣት።
2. በውስጧ ጠቃሚ ነገር እንዳለ ተረድተን እናድምጣት።
3. ብዙ የህይወት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንድትሳተፍ በማድረግ ከሚያጋጥሟት ችግሮች እንድትማር እና ከስኬቷ እችላለሁ የሚል መንፈስ እንዲኖራት እናግዛት።
4. ሴት ልጅ ማድረግ የምትችለው እና የማትችለው በማለት አንገድባት።
5. ሀላፊነቶች የመወጣት አቅሟ እንዲዳብር ሃላፊነት እንስጣት።
6. ብዙ ለውጪ አለም ሚድያ በተለይ በለጋ እድሜ አናጋልጣት ማለትም ስኬት ውበት እና የአርቲፍሻል ጋጋታ እንደሆነ ለማሳየት ስለሚሞክሩ።
7. እንደ ቤተሰብ ያላችሁን ቤተሰባዊ ባህል አስተምሯት።
8. ራሷን እንድትወድ እና እንድትቀበል እንርዳት ማለትም ውብ እና አስፈላጊ እንደሆነች በፍቅር እንግለፅላት።
9. ከሌሎች ጋር አናወዳድራት፤ ለሌሎች ቀና አመለካከት እንዲኖራት አርገን እናሳድጋት።
10. ያላት ዝንባሌ እንዲያድግ እድል እናመቻችላት።
በመጨረሻም: ችግር ሲያጋጥማት ችግሮቿን እንዴት መፍታት እንደምትችል እናሰልጥናት እንጂ ችግር አጋጠመን ማለት ወድቀናል ማለት እንዳልሆነ ይልቁንም የምንማርበት እድል እንደሆነ እንንገራት።
ሴት ልጆቻችንን እንውደዳቸው፣ እንንከባከባቸው፣ አስፈላጊውን ስልጠና እና ትምህርት እንስጣቸው ደግሞም በነሱ እንደሰት።
መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
#March8
መልካም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን!
@melkam_enaseb
#ባለውለታ
"ሰውነት አልሞተም"
በዚህ ግዜ እኛ ኢትዮጵያውያን ብሎም በአለም ላይ የሚታየው የሚሰማው ሁሉ ሰው ሰውነቱን በቃ አጣ? ዓለም ለመኖር አስፈሪ እየሆነች ይሆን? የሚያስብሉ ሰው የሰው ስጋት እየሆነ የመጣበት አስከፊ ነገሮች ተከስተዋል እየተከሰቱም ሰብዓዊነትም እየተሸረሸረ የመጣበት ጊዜ ነው።
ነገር ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ብርሃን የሆኑ እና ለመኖር እንድንጓጓ የሚያደርጉን ጥቂት የማይባሉ ለነብሳቸው ያደሩ ልበ ብሩሃን መልካም ሰዎች ዛሬም አሉ።
ለአብነት ያህል ከሰሞኑ በልበ ብሩሁ ቢኒያም አማካኝነት ለተቋቋመው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ ነገር ግን ያላለቁ የበር እና የመስኮት እንዲሁም አንዳንድ የፊኒሺንግ ስራዎች ለማጠናቀቅ የሚውል ገንዘብ አሰባስቤ ሳልጨርስ ከዚች ወንበር ንቅንቅ አልልም ብሎ ራሱን ለመልካምነት አሳልፎ የሰጠውን በበጎ ስራዎቹ የምናውቀው ኮሜድያን ዕሸቱ መለሰን መጥቀስ ይቻላል። እንደዚህ ያሉ መልካም ሰዎች ያብዛልን እያልን፤ ለዚህ በጎ ዓላማ መሳካት ከጎኑ የሆኑ ቅን ልብ ያላቸው መልካም ሰዎች ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።
የሀገር ባለውለታው ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ላደረከው፤ እያደረክ ላለኸው እና ወደፊት ለምታደርገው ሁሉ ክብር ይገባሃል!
"ሰውነት! ሰብዐዊነት አሁንም አልሞተም"
#Bookforall
@melkam_enaseb
#Dailytips
"ሳይገለፁ የቀሩ ስሜቶች አይሞቱም። በህይወት እንዳሉ ተዳፍነው ይከርሙና በአስቀያሚ መልክ ይገለፃሉ።" - ሲግመን ፍሮይድ
@melkam_enaseb
አውቃለሁ ህይወት ምን ያክል እየከበደችህ እንደሆነ። አንድ ነገር እንዲለወጥ ትፈልጋለህ ግን ምን እንደሆነ አታውቅም። ምን እየሆነክ እንደሆነ፣ በአንተ ላይ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አልገባህም፤ ብቻ ጭንቅላትህ ሊፈነዳ እንደደረሰ ይሠማሃል። በጣም ብዙ ጨለማ ሃሳቦች፣ የስሜት ለውጦች ይጎበኙሃል።
ምን አልባትም "እንደ ሌሎች ሰዎች ሆኜ አልተፈጠርኩ ይሆን?" ብለሃል።
ምንም እንኳን በሙሉ አቅምህ ብትሞክርም እዚህ ምድር ላይ "መኖርን" በራሱ መቋቋም አልቻልክም፤ ምክንያቱም ደህና እደለህም! ሁልጊዜ ህመም ውስጥ ነህ። ሁልጊዜ በህመም ውስጥ መሆን ደግሞ ያሰለቻል! ያደክማል!
ግን...ልብ ብለህ ስማኝ...ደህና አለመሆን የአንተ ጥፋት አይደለም፤ ይህ ማለት እረዳታ ያስፈልግሃል ማለት ነው። በመሆኑም በቅርብህ ላሉ ሰዎች ግልፅ በመሆን አማክራቸው። ብቻህን መታገል የለብህም! ምን አልባት በውስጥህ ያሉ ትርጉም የማይሰጡ ነገሮችን የሚጋራህ እና የሚረዳህ ሰው ታገኛለህ፤ ይህ ነገሮችን ያቀላል።
ይህን ማድረግ ከከበደህ ወደ አእምሮ ህክምና መስጫ ማዕከል በመሄድ የስነ አእምሮ ወይንም የስነ ልቦና ባለሙያዎችን አማክር።
No one is immuned for mental illness
Explore your mentality.
Fetlework abate (psychiatry nurse)
#Hakim
@melkam_enaseb
ታላቁ ጥበብ!
በህይወታቹ ውስጥ የሚገጥማችሁን ማንኛውም ችግር ወደ በጎ አጋጣሚ ልትቀይሩት ትችላላቹ።
የአለማችን ዝነኛዋ የሚዲያ ባለሙያ ኦፕራ መልክሽ ለቴሌቪዥን ሾው አይመጥንም ተብላ ከስራዋ ተባራ ነበር። እሷ ግን ያን መጥፎ አጋጣሚ ራሷን ችላ ለመቆምና ውስጧ ያለውን እምቅ ሀይል አውጥታ ለማሳየት ተጠቀመችበት።
አምፖል የኖረው ጨለማ ስላለ እንደሆነ አስታውሱ። አውሮፕላን የተፈጠረው አቀበትና ርቀት እንዲሁም ብዙ ከልካይ ነገሮች ስላሉ እንደሆነ አትርሱ።
ስለዚህ ዋናው ቁም ነገር የችግሮች መኖር አይደለም። ይልቁኑ እነዚህን ችግሮች ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር ዝግጁ ናችሁ ወይ የሚለው ነው።
እስኪ ቆም በሉና አሁን ላይ የምትማረሩባቸውን ችግሮች አስቡ። በነዚህ ችግሮች ውስጥ መልካም አጋጣሚም አብሮ እንዳለ ልነግራቹ እወዳለው። እስከ ሕይወታቹ ፍጻሜ ድረስ የተሻለ ህይወት የመኖር እድል አላቹ። ተግዳሮቶቻችን ሊቆሙ አለመቻላቸው ቢያሳዝንም ተግዳሮቶችን ለከፍታችን ልንጠቀምባቸው መቻላችን ደሞ ደስ ያሰኛል።
የሚደርስባችሁን ነገር መምረጥ ባትችሉ የምትሰጡትን ምላሽ ግን መምረጥ ትችላላችሁ።
አስቡ ደግማቹ አስቡ!
ኤርሚያስ ኪሮስ
(Counseling Psychologist)
@melkam_enaseb
⬆️ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
መጋቢት 23
ሲ ኤፍ ኤስ ኢትዮጵያ ከስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን የዓለም ኦቲዝም ቀንን ለማክበር ቅዳሜ መጋቢት 23፤ 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቅጥር ግቢ ይገኙ።
መርሐ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ እስከ መጋቢት 15፤ 2015 ዓ/ም ድረስ በ +251-911-619018 የእርስዎን እና የሚጋብዟቸውን እንግዶች ስም ይላኩ!
አድራሻ፡ ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ በሚገኘው ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቅጥር ግቢ።
ስለ ኦቲዝም ማህበረሰባዊ ግንዛቤ በጋራ እንፍጠር!
@melkam_enaseb
Join us for the first episode of our mental health series. You can register through the link below.
Topic: Pathways into a Career in Mental Health.
Date and time: March 04, 2023, 3:00 PM Nairobi Time
Registration link: https://forms.gle/cTS7dLaSdoUkyTuW6
#EMA
@melkam_enaseb
መልካም ዜና!
የዛሬ አመት አካባቢ በማህበራዊ ሚዲያ ሶስት የአእምሮ ታማሚ ወንድማማቾች በአንድ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው የሚል ዜና አይተን ነበር። ታዲያ አሁን ላይ ከሶስቱ ወንድማማቾች አንዱ ተሸሎት ተሞሽራል!
የተማረ ነው… ድግሪን በጣጥሷታል፡፡ ያውም በማዕረግ፡፡ መምህር ሆኖ ትውልድን በትምህርት ወልዶ፣ አሳድጎ ለቁም ነገር ያበቃ ተወዳጅ መምህር፡፡ ግን…. ህመም ማንን ሊፈራ? ታመመ፡፡ ንቁ አእምሮው እውኑን እና ምዕናቡን መለየት እስኪያቅጠው ድረስ ታመመ፡፡
አስታማሚ በሌለበት ታመመ፡፡ ራሱን ከማስታመም በላይ ከሱ የባሰ ታመው ከምሰሶ ጋር ለታሰሩ ወንድሞቹ ሀለፊነት መውሰድ ነበረበት፡፡ ረዳት በሌለበት... በባዶ ቤት ውስጥ… ተስፋን ብቻ ይዘው።
ከ10 ዓመት በኋላ… ከዕለታት በአንድ ልዩ ቀን… አንዲት የተባረከች ጋዜጠኛ ብርሀን በሚገባበት በር ገብታ ከፊታቸው ቆመች-- ከአእምሮ ህመም ጋር ለሚታገሉ የተሰጠ “ስጦታን'' ይዛ፡፡
ስጦታ የአእምሮ ህክምና እና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ሶስቱን ወንድማማቾች ተቀበለ፡፡ ጤናቸውን ስጦታ አድርጎ ሊመልስላቸው፡፡
እነሆ ባለ ምጡቅ አእምሮ መምህር አብዱልቃድር ሰይድ ይኸው ተሞሸረ፡፡
እንኳን ደስ አለህ!
የአእምሮ ታማሚዎች ታክመው ውጤታማ ሂወት መቀጠል እንደሚችሉ ይህ ማሳያ ነው።
@melkam_enaseb
የተሰበረው ገጽህ!
አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሁል ጊዜ ስትከፍተው የሚከፈተው እዚያ የተሰበረው ገጽ ላይ ነው፡፡
አንድን መጽሐፍ አንሳና አንድ ገጽ ላይ ከፍተህ ግራና ቀኙን ይዘህ ወደ ኋላ በመለመጥ እዚያ የተከፈተው ገጽ ጋር እስኪላቀቅ ግፊት በማድረግ ስበረው፡፡
በሌላ ጊዜ መጽሐፉን ስታነሳው መጀመሪያ ራሱን ከፍቶ የሚቆይህ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡
በሕይወትህ አንድ ደጋግሞ የተሰበረ ክፍል ካለህ ምንም ነገር ሲከናወን የሚከፈትብህ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡
አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሌላ ገጽ ላይ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ቢሞከር እንኳን ማንም ሳይጠይቀው ወደዚያ ገጽ የመከፈት ዝንባሌ አለው፡፡ ሕይወትም እንዲሁ ነች፡፡ ደጋግመን የተሰበርንባቸው የሕይወታችን “ገጾች” በሆነ ባልሆነ የመከፈት ባህሪይ አላቸው፡፡
ደጋግመህ የተሰበርክበትን የሕይወት “ገጽ” ቀድመህ ካላስተካከልካቸው በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ውስጥ እየተከፈተ ያስቸግርሃል፡፡
በተለይ እነዚህን ስብራቶች ይዘህ ወደ ጓደኝነት፣ ወደ ፍቅር ሕይወት ወይም ወደ ትዳር፣ ወደ ስራ ወደ መሳሰሉት ማሕበራዊ ስምሪቶችህ ስትገባ ገጹ እየተከፈተ ያስቸግርሃል።
ምንም ነገር ውስጥ ከመግባትህ በፊት በመጀመሪያ የተሰበረውን “ገጽህን” ጠግን!!!
(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
መልካም ቀን!
@melkam_enaseb
#Dailytips
''ለአእምሮ ጤናህ መልካም የሆኑ እና ሰላም እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ግዜህን አሳልፍ''
'ሁለት ነገሮች ብልህ ያደርጉናል። የምናነባቸው መፅሀፎች እና በህይወት መንገድ ላይ የሚገጥሙን ሰዎች።'
ለራስህ የምትነግራቸው ነገሮች ስነ ልቦናህን ይገነባሉ ወይም ይሰብራሉ።
ትግል ዋጋ አለው። በህይወት ትግል ውስጥ የሚፈልጉትን ነገር ያገኛሉ። ካልታገሉ ለመማር እና ለማደግ ጠቃሚ እድሎች ያመልጦታል።
ሁኔታው የቱንም ያህል መጥፎ ቢመስልም ያልፋል።
እራስዎን ጨምሮ ሌሎች ላይ መፍረድ በእጅጉ ይቀንሱ። መፍረድ ቀላሉ ነገር ነው። በሰው ጫማ ሆኖ ደግሞ ነገሮችን ማየት ከባዱ ነገር ስለሆነ።
ስራ በዝቶቦታል ማለት ውጤታማ ኖት ማለት አይደለም። ወደ ግቦችዎ የሚያንቀሳቅሱ ትክክለኛ ተግባራትን ማከናወን ነው የበለጠ አስፈላጊው ነገር።
''የሰው ልጅ ስለሚፈልጋቸው ነገሮች በራሱ አእምሮ መወሰን ካልቻለ ለሰዎች አላማ መዳረሻ ይሆናል። ህይወትህንና ፍላጎትህን ሌሎች ሰዎች እንዲሾፍሩት በጭራሽ አትፍቀድ።''
በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!
@melkam_enaseb
ሱስ የሌለባችሁ ሰዎች እስቲ እጃችሁን አውጡ!
ብዙ ሰዎች ሱስ የሚጠቀሙ ሰዎችን እንደ ሰነፍ፣ ዱርዬ፣ የሞራል ውድቀት ውስጥ እንዳሉ አድርገው ሲፈርጁ ይታያል። ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደግሞ ፍረጃውን በመፍራት ወይም ሀፍረት ስለሚሰማቸው ወደ አእምሮ ህክምና ለመምጣት ያንገራግራሉ። አንዳንዶቹ ሼም ስለሚይዛቸው "ከፈለግኩኝ እኮ ማቆም እችላለሁ።" ቢሉም ተመሳሳይ እሽክርክሪት ውስጥ ለአመታት ይቆያሉ። ሱስ ውስብስብ ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊና ማህበራዊ ሂደት ነው። ማን ሱስ ውስጥ እንደሚገባ ማወቅ አይቻልም።
ዶ/ር ጋቦር ማቴ የሱስን ፍቺ ሲያስቀምጥ "ማንኛውም ለጊዜያዊ ደስታ ተብሎ የሚወሰድ (የሚደረግ) እና 'አምጣ፣ አምጣ' የሚል ወስዋስ (Craving) የሚፈጥር እና በዘለቄታው ግን በግለሰቡ ወይም በግለሰቡ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትል ለመተው የሚያስቸግር ድርጊት ነው" ብሏል።
በዚህ ትርጓሜ መሰረት የተለያየ ሱስ አምጪ እፆች መጠቀም፣ ፖርኖግራፊ መመልከት፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለብዙ ሰአት መጠቀም፣ ከሚገባ መጠን በላይ መመገብ፣ ቁማር መጫወት...ወዘተ ሁሉም በተመሳሳይነት ሱሶች ናቸው።
ሰዎችን "ሱሰኛ" ብሎ ከመፈረጅና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት በፊት "ምንም አይነት ሱስ የለብኝም!" የምትሉ ሰዎች እስቲ እጃሁን አውጡ!
ሱሶች ሁሉ የሚያስከትሉት ጉዳት እኩል ነው እያልኩ አይደለም። ሆኖም ሁሉም ሱሶች ተመሳሳይ ሂደት እንዳላቸውና ማንም ሰው ላይ ሊከሰት እንደሚችል እንድንረዳ ነው። ከፍረጃ ይልቅ ርህራሄ፣ አናት ላይ ቆሞ ከመምከር ይልቅ አጠገብ ተቀምጦ ማገዝ ብንችል ብዙ ሰዎች ከሱስ እንዲወጡ ማገዝ እንችላለን።
ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው። ዘውዲቱ፣ ጳውሎስ ወይም አማኑኤል የሱስ ህክምና ይሰጣል። ጥሩ የግል ህክምና አማራጮችም አሉ።
(ዶ/ር ዮናስ ላቀው)
@melkam_enaseb
በሐዋሳ እና በአከባቢዋ ለምትገኙ!
ዘፀአት የአዕምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት በማንኛውም የአዕምሮ ጤና እክል እንዲሁም የሂዎት ተግዳሮቶች ሙያዊ የሆነ የማማከር እና ህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ።
አድራሻ፦ ሐዋሳ ከቲቲሲ ወደ ሪፈራል በሚወስደው መንገድ ኮሜሳ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ።
ስልክ: 0943007007
@melkam_enaseb
ልማድ/Habit
ለማድ የምንለው አንድ ተግባር፣ አስተሳሰብ፣ ስሜት ወይም በጠቅላላው ባህርይ ሆን ብለን ወይም ሳናስበው በተለያዩ ምክንያቶች በመደጋገማችን ጭንቅላታችን ውስጥ ተቀርጾ ሲቀር እና ከኛ መገለጫዎች አንዱ ሲሆን ነው። ይህ ከሆነ በኃላ አዕምሮአችን ያለ ምንም ግፊት ይህን ተግባር፣ አስተሳሰብ፣ ስሜት ወይም ባህሪይ እንድናደርግ ማዘዝ ይጀምራል። ይህን ልማድ የምናዳብረው ያስቀመጥነው ግብ ላይ ለመድረስ ሊሆን ይችላል። በተቃራኒው ካስቀመጥነው ግብ የሚያርቁን ልማዶችን ልናዳብርም እንችላለን።
ልማድን ስናዳብር አዕምሮአችን የሚከተሉት ሂደቶች አሉት፦ እነዚህም በዋነኝነት Cue, Craving, Response እና Reward ብለን እንከፍላቸዋለን።
Cue የምንላቸው አዕምሮአችን ውስጥ እንደ የተቀረፀን ተግባር እንድናስታውስ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ናቸው። እነዚህም ከልማዱ ጋር የተያያዘ ቦታ፣ ሽታ፣ ሰዓት የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ። እነኚህን ስናገኝ ቀጣይ ወደሆነው ክፍል Craving እናመራለን። ይህ ደግሞ አምሮት ብለን በአጭሩ ልንገልጸው የምንችል ሲሆን ከልማዱ በምናገኘው የአዕምሮ የሽልማት ኬሚካል መመንጨት ምክንያት የሚዳብር ነው።
ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ሂደቶች ሲያጋጥሙን ተግባሩን ወደመፈጸም ወይም Response ወደምንለው ደረጃ እንሻገራለን። ልማዳችን ተግባር ብቻ ሳይሆን ሀሳብም ሆነ ማንኛውም ተመሳሳይ ምላሽ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ስናደርግ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ደረጃዎች መንስኤ ወደሆነው እና Response ስንሰጥ በመቀጠል ወደሚመጣው Reward (ሽልማት) ደረጃ እንገባለን። ይህ የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን ልማድን ስንፈፅም አዕምሮአችን ውስጥ በሚመነጭ ኬሚካል የተነሳ የሚፈጠር የደስታ እንዲሁም የመረጋጋት ስሜት ነው።
(Aha Psychological Services)
@melkam_enaseb
#የመጽሐፍጥቆማ
"DISABILITY IN ETHIOPIA
issue, insights and implication" የተሰኘው የፕሮፌሰር ጥሩሰው ጣሰው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉን ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ያገኙታል! አድራሻ: ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር።
@melkam_enaseb