Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon. ''There is no health without Mental Health.'' Contact @FikrConsultSupportbot
ስፒች ቴራፒና የባህርይ ቴራፒ!
ልጆች ትምህርት ቤት እረፍት በሚሆኑበት ጊዜ ላይ ለልጅዎ ስፒች ቴራፒና የባህርይ ቴራፒ ይፈልጋሉ?
ይደውሉና! ይመዝገቡ!
0940103047
0954999933
አድራሻ:- መገናኛ-ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ!
(ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic)
@melkam_enaseb
ከበዓል ማግስት ሚመጣ መከፋት (Post Holiday Blues)
የበዓላት ሰሞን ብዙ ጊዜ ደስታን ያመጣል፣ ነገር ግን ሲያበቃ ዝቅተኛ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል— ይህም Post Holiday Blues ይባላል።
እነዚህ ስሜቶች ብዙዎች ላይ የሚከሰቱ እና ብዙ ጊዜ ጊዜያዊ ናቸው። ከበአል ጋር በተያያዘ የስሜት ከፍታ፣ ገንዘብ ነክ ጭንቀት፣ የብቸኝነት ስሜት እንደምክኒያት ይነሳሉ።
ይህንን ስሜት ለመቋቋም የሚከተሉትን ስልቶች እንጠቀም፦
1. ወደ ተለመደው መደበኛ ሁኔታችን ቀስበቀስ መመለስ፦ ለእንቅልፍ፣ ለጤናማ አመጋገብ እና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቅድሚያ በመስጠት የዘወትር ተግባራችንን እንደገና ለማስጀመር ትናንሽ እና ሊሳኩ የሚችሉ ግቦችን ማዉጣት።
2. ለራስ ርኅራኄን ማሳየት፦ ያለፍርድ ስሜትን ለመረዳትና በዓሉ ምን ትርጉም እንደሰጠን ማሰብ።
3. አዲስ እቅድ ማውጣት፦ ለምሳሌ ከጓደኞች ጋር መገናኘት፣ አዲስ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ መንገድን መሞከር ወይም የአንድ ቀን ጉዞ ማድረግ እና አዲስ ሰፈር ወይ ከተማ መጎብኘት የመሳሰሉ የሚያጓጉ ነገሮችን ማቀድ።
4. ጤናማ የገንዘብ አጠቃቀምን መከተል፦ በጀት ማውጣት ጭንቀትን ሊያቀል ይችላል።
5. አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፦ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ ስሜትን ሊያሻሽል ይችላል። የሚያዝናኑንን እንቅስቀሴዎች መሞከር ለምሳሌ መደነስ፣ ኳስ መጫወት።
6. ከሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፦ ከጓደኛ፣ ከቤተሰብ ጋር በመገናኘት ወይም በበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ላይ ማገልገል።
7. ነገሮችን ምናይበትን መንገድ መቀየር፦ ይህንን ጊዜ አዲስ ሀሳቦችን ለማሰብ፣ ምስጋናን ለመለማመድ እና በግል እድገት ላይ ለማሰላሰል መጠቀም።
ይህም ሆኖ ስሜቶች ከቀጠሉ ወይም ከአቅም በላይ ከሆኑ ከአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር መነጋገር። አስታውሱ፣ ብቻችሁን አይደላቹም፣ ብሩህ ቀናት ወደፊት አሉ።
ለማማከር: 0704156858 ይደውሉ ወይም መልክት ያስቀምጡ!
ዶ/ር ይቅናሸዋ ሰለሞን (የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
Via: Hakim
@melkam_enaseb
ገናን ለአእምሮ ጤናማ በሆነ መንገድ ማክበር!
ደስታን ማጣጣምን፣ ጭንቀትን መቀነስን እና ግንኙነቶቻችንን ማዳበርን ያካትታል።
አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ፡-
1. እንዲሆኑ ምንመኛቸውን ነገሮች ተጨባጭነት ማረጋገጥ፦ ጭንቀትን ለመቀነስ ፍጽምናን ከመጠበቅ ይልቅ ትርጉም ባለው ጊዜ እና ቀለል ባለ መንገድ መደሰት ላይ ማተኮር።
2. ራስን መንከባከብን ማስቀደም፡- የዕረፍት ጊዜን ቅድሚያ መስጠት፣ ሚዛናዊ አመጋገብ እና የአልኮል አጠቃቀምን መቀነስ ከተቻለም ማቆም።
3. ግንኙነቶችን ማሳደግ፦ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ወይም ማህበራዊ ዝግጅቶችን መቀላቀል እና ብቸኝነት ከተሰማን ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በጋራ ለማክበር መሞከር።
4. አስቀድሞ በማቀድ በጀት ማውጣት፦ የጊዜ አጠቃቀምን አስቀድሞ ማቀድ፣ የፋይናንስ እቅድ ማዘጋጀት እና በመጨረሻው ደቂቃ ጭንቀትን እና ከመጠን በላይ ወጪን ማስወገድ።
5. አመስጋኝ መሆን እና ስጦታ መስጠትን መለማመድ፦ ምናመሰግንበትን ነገር ማሰብ ትንሽም ቢሆን፣ በደግነት ስራዎች መሳተፍ።
ጤናማ የሆነ የገና በአልን በማስተዋል፣ በህይወታችን ላሉ ሰዎች ቅድሚያ በመስጠት እና ርህራሄን ለራስ እና ለሌሎች በማሳየት እናክብር።
መልካም በአል!
ለማማከር: 0704156858 ይደውሉ ወይም መልክት ያስቀምጡ!
ዶ/ር ይቅናሸዋ ሰለሞን (የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
Via: Hakim
@melkam_enaseb
ስልጠናው ስድስት ቀን ብቻ ቀረው!
አዲስ የtelegram (online/ Live) ስልጠና- በ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
“የግል ሕይወትን ማደረጃት”/ "Organizing Personal Life"
• ሕይወታችሁ ዝብርቅር እንዳለ የሚሰማችሁ ከሆነ፣
• የየእለት ተግባራችሁን በስርአት ማደራጀት ግር የሚላችሁ ከሆነ፣
• አንድን የጀመራችሁትን ነገር እስከፍጻሜ መቀጠል የሚያታግላችሁ ከሆነ፣
• ሃሳባችሁን ማደራጀት፣ መሰብሰብ እና ወደ ተግባር መለወጥ ግራ የሚገባችሁ ከሆነ፣
• ማሕበራዊ ግኑኝነታችሁ መልክ ያጣና ግራ የሚያጋባ ከሆነ፣
• በአጭሩ ሕይወታችሁን ማደራጀት የምትፈልጉ ከሆነ፣ ይህ ስልጠና ለናንተ ነው።
የስልጠናው ቀናት፦ ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22፣ 29 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፦ አምስቱም ሀሙሶች ከምሽቱ 3:00 - 5:00 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር)
የስልጠናው ክፍያ: ለአምስቱም ሀሙሶች ጠቅላላ ክፍያ (1000) ብቻ
ለመመዝገብ፡- በ @FikrConsultSupportbot ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ!
@melkam_enaseb
Adjustment Disorder!
ህይወት በውጣ ውረድ የተሞላች ናት። ኢኮኖሚያችን ተናግቶ ኪሳችን ባዶ ሁኖብን፤ አልያም ከህግ አንጻር ትክክል ያልሆነን ነገር ፈጽመን ፍርድ ቤት የሚያስቆም ነገር ገጥሞን፤ የፍቅርና ትዳር ህይወታችን እክል ገጥሞት፤ የትምህርት ውጤታችን አሽቆልቁሎብን ተጨንቀንና ተጠብበን ይሆናል።
ብዙዎቻችን እኚህን ጊዜያት እንደአመጣጣቸው አለሳልሰን አሳልፈናቸው ይሆናል። ለእንዳንዶች ደሞ እነዚህ የህይወት ሁነቶች ለከባድ የስሜት እና ስነልቦና ቀውስ መንስኤ ሲሆኗቸው ይስተዋላል።
አጀስትመንት ዲሶርደር፦ በተፈጠሩብን አስደሳችም ሆኑ አስከፊ የጭንቅ ሁነቶች ምክንያት የሚመጣ የአእምሮ ህመም ነው።
እንደ DSM 5 ገለጻ ከሆነ አንድ ሰው አጀስትመንት ዲሶርደር አለበት ለማለት ምልክቶቹ ሁነቱ በተከሰተ በ 3 ወራት መከሰት ይኖርባቸዋል ሁነቱ በተፈታበት 6 ወራት ውስጥ ደሞ ምልክቶቹ መሻር አለባቸው ይላል።
የህመሙ ዋና ዋና ምልክቶች፦
- ድባቴ፣ የብቸኝነትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ ራስን ዝቅ የማድረግ እና ወቀሳ፣ ራስን የመነጠል፣ የመቅበጥበጥ፣ ድንጉጥ የመሆን፣ ግልፍተኝነት፣ ከልክ ያለፈ ጭንቀት
አካላዊ ምልክቶች (የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ እንቅልፍ የማጣት ህመሞች እና የመሳሰሉ)
- ራስን የማጥፋት ሃሳብ
- አደንዛዥ እጽ መጠቀም መጀመር (ምናልባትም ነገሮችን ለመቋቋም ሲባል የሚጀመር)...
- የባህርይ ለውጥ
አንዳንዶች ለህመሙ ተጋላጭነታቸው ለምን ይጨምራል?
አንድ ሰው አስጨናቂ ሁነት ሲገጥመው ነገሮቹን ለማሰናሰል የተለያዩ ሂደቶችን ያልፋል።
1. ሁነቱን የተመለከቱ መረጃዎች ለአእምሯችን ስለሚደርሱ የሁነቱን መከሰት እናገናዝባለን።
2. ሁነቱን ለመርሳት በመሞከር እና በትውስታ መሃል ሄድ መጣ እያለ ይቆያል። ከዚህ ጋርም ተያይዞ ስለ አስተሳሰባችን፣ ስነ-ባህርይ፣ ስነ-ማህበራዊ ነገሮችን በተመለከተ አእምሯችን መረጃዎችን ያጠናቅራል።
3. ሁነቱን በተመለከተ የተጠናከሩ መረጃዎችን አእምሯችን በአስተሳሰብ ማዕቀፋችን በማካተት፣ ለመላመድ መሞከር እና ትርጉም ለመስጠት ይሞክራል።
ይህ ስራ በተገቢው አኳኋን ካልተካሄደ ለስሜት መቃወስ ምልክቶች መጋለጥ ያስከትላል።
ሰዎች ለአስጨናቂ ሁነቶች ተያያዥ ስሜቶች ልምዱ ከሌላቸው፤ ለሚያጋጥማቸው ክስተት በቀላሉ ከመላመድና ወደቀደመ ህይወታቸው ቶሎ ከመመለስ ይልቅ ስለሁነቱ ራስን መውቀስ ይቀናቸዋል፣ ለሌሎች አዋይቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ብቻ ለመጋፈጥ ይጥራሉ፡፡ ይህም ለድብርት አልያም ጭንቀት እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል::
ከልክ በላይ በድሎት የኖሩ እና ሁሉንም ነገር በሰዎች እርዳታ ማለፍ የለመዱ ሰዎች ክስተቶችን በራሳቸው ለመጋፈጥ ዝግጁነት ስለሚጎላቸው፣ በሚያጋጥማቸው ውጣ ውረድ ስሜታቸው ሲጎዳ እና ለስነ ልቦና ቀውስ ሊጋለጡ ይችላሉ።
አንዳንዶች ደሞ ፈተና ያጠነክራቸዋል፡፡ Resilience ያዳብራሉ።
የህክምናው አበይት አላማዎች፦
- ምልክቶችን እና ተጓዳኝ ህመሞችን (እንደ እጽ ተጠቃሚነት ያሉ) ማከም
- የተፈጠረው አስጨናቂ ሁነትን መፍታት
- ወደ ቀደመ አቋማቸው መመለስ
ስነ ልቦናዊ ህክምና፦
- Supportive psychotherapy (ታካሚዎች ስሜታቸውን እንዲገልፁ ማድረግ፣ መመካከር፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን መዘየድ..)
- Cognitive behavioral therapy (አረዳዳችንን እና የባህርይ ማፈንገጦችን ማቃናት)
- Interpersonal therapy- የተፈጠሩ ክስተቶችን (ሃዘን/grief፡ የሚና ለውጦች/role transition፡ ብቸኝነት/interpersonal deficit፤ መቃቃር/dispute) ለይቶ መፍትሄ ማበጀት
- Meditation training (ጽሞናን እና አርምሞን መሰረት ያደረገ) እና የመሳሰሉ…
የመድሃኒት ህክምና፦
- እንደ ህመሙ ምልክቶች ደረጃ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ።
- እንቅልፍ ማጣትን፣ የጭንቀትና የድባቴ ምልክቶችን ለማከም መድሃኒት ሊሰጥ ይችላል።
ማጠቃለያ፦ በፈተና ውስጥ እያለፋ ላሉ ሰዎች ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ እዝነት ማሳየት፣ አለንላችሁ በማለት ከጎናቸው መቆም እና ያጋጠማቸውን ችግር በተመለከተ በጋራ መፍትሄ ማፈላለጉ እጅግ ወሳኝ ሚና አለው።
ቸር ይግጠመን!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
አዲስ የtelegram (online / Live) ስልጠና!
“የግል ሕይወትን ማደረጃት”/ "Organizing Personal Life"
• ሕይወታችሁ ዝብርቅር እንዳለ የሚሰማችሁ ከሆነ፣
• የየእለት ተግባራችሁን በስርአት ማደራጀት ግር የሚላችሁ ከሆነ፣
• አንድን የጀመራችሁትን ነገር እስከፍጻሜ መቀጠል የሚያታግላችሁ ከሆነ፣
• ሃሳባችሁን ማደራጀት፣ መሰብሰብ እና ወደ ተግባር መለወጥ ግራ የሚገባችሁ ከሆነ፣
• ማሕበራዊ ግንኑነታችሁ መልክ ያጣና ግራ የሚያጋባ ከሆነ፣
• በአጭሩ ሕይወታችሁን ማደራጀት የምትፈልጉ ከሆነ፣
ይህ ስልጠና ለእናንተ ነው፡፡
ለመመዝገብ፡- በ @FikrConsultSupportbot ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ!
ለበለጠ መረጃ ፖስተሩን ይመልከቱ፡፡
@melkam_enaseb
ማንነት እና ሰውነት!
ለመሆኑ Identity/Self ምንድን ነው?
ማንነት ሰፊ ጽንሰ ሃሳብ ቢሆንም እንዲህ ልንረዳው እንችላለን..'መገለጫችን የሆነ፣ ከሌሎች የምንለይበት ሲሆን፤ አካላዊ አፈጣጠራችንን፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ መዋቅራችንን ያካትታል'
አለማወቅ በተሰኘው የዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ መጽሃፍ አንድ ድንቅ ምልልስ እናገኛለን...
'ሰው መሆን የተሰጠን ወይንም ይዘነው የመጣነው ሲሆን ማንነት ግን ከዚያ በኋላ የጨመርነው ነው። ማንነት ሸክም ነው....የሚጨመር በመሆኑ የግድ ጨማሪ ያስፈልገዋል። ይህንን የሚጨምሩልን ደግሞ ከእኛ በፊት የነበሩ ሰዎች ናቸው። የቀደሙት ሰዎች የኑሮ ገጠመኞቻቸውን ከእነርሱ በኋላ ለሚመጣው ያወርሱታል።'
ዊኒኮት የተባለ የስነልቦና ሊቅ ሁለት አይነት ማንነቶች ይኖሩናል ይለናል። True እና False Self። ሁለቱን ማንነቶች አስማምቶ ማስኬዱ ለጤናማ ስነልቦና ወሳኝ ነው ይላል።
- እውነተኛው ማንነታችን፦ ማስመሰል የሌለው (Authentic)፣ በየትኛውም አውድ ውስጥ ከእውነታው አለም አንጻር ራስን የሚቀበል ማንነት ነው።
- ሃሰተኛው ማንነታችን፦ ማስመሰል ያለበት፣ ምናባዊ የሆነ (illusion)፣ ወላጆቻችን በሰፉልን ልክ እንጂ በአቅማችን ያልሆነ፣ ፍጽምናን (perfectionist) እና በሌሎች ዘንድ ሞገስ ማግኘትን የሚሻ እና ወቀሳን አብዝተን እንድንፈራ የሚያደርገን ማንነታችን ነው። (ይህን ማንነታችን ይሆን በአለማወቅ መጽሃፍ 'ማንነት ሸክም ነው' ተብሎ የተገለጸው?)
እንደ Eric Eriksson አረዳድ ከሆነ ሰዎች በተለይም በአስራዎቹ እድሜያቸው ስለ ማንነታቸው አብዝተው ይጠይቃሉ። ይህን ጊዜ 'Identity Vs role confusion' ብሎ ይሰይመዋል። ስለማንነታችን በአግባቡ መረዳት ላይ ከደረስን ጽኑ ማንነት ይኖረናል.. አልያ ግን የማንነት ቀውስ ይከተላል። ይህ የማንነት ቀውስም በራስ አለመተማመንን፣ አይናፋርነትን እና ራስን ለመግለጽ መቸገርን አለፍ ሲልም አመጸኝነትን ያስከትላል።
በእኔ አመለካከት ማንነታችን ተፈጥሮ በሰጠችን እንዲሁም በኑሮአችን በሚኖሩን ገጠመኞች (በምንኖርበት ባህል፣ ሃይማኖት፣ ማህበራዊ እሴቶች) እየተገነባ የሚሄድ ነው። የ Nature እና Nurture ድምር ውጤት።
መሆን የምንፈልገው (Ideal self) እና የሆንነው (Real self) ሳይጣጣሙ ሲቀሩ ለስነልቦና አለመረጋጋት እና ቀውስ ያጋልጣል። ብዙዎቹ ይህን ተቃርኖ መቋቋም አቅቷቸው ሲሰበሩ ይስተዋላል።
መቀየር እና ማሻሻል የምንችላቸው ማንነት ላይ መስራት፤ መቀየር የማንችለውን ደግሞ አምኖ መቀበል ያስፈልጋል።
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
ከአስደንጋጭ ገጠመኝ በኃላ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት (Post-Traumatic stress Disorder)
የህይወት ገጠመኝ የሌለው ሰው ይኖር ይሆን? ይብዛም ይነስም ሁላችንም ዛሬ እስካለንበት ድረስ ለመልካም ነገር ወይም ደግሞ ለመጥፎ ነገር ተጋልጠናል። ብዙ ሰዎች እጅግ አስደንጋጭ ነገር በራሳቸው አልያም በቤተሰቦቻቸው ላይ ገጥሟቸው ተጨንቀው፣ ተረብሸው ኑሮን በመከራ ይኖራሉ።
በአደጋ፣ በተሽከርካሪ፣ በወንጀል፣ በድብደባ፣ በስለት መወጋት፣ በጦርነት፣ በጾታዊ ትንኮሳ፣ በተፈጥሯዊ አደጋ፣ ወዘተ በኃላ የሚፈጠር የአዕምሮ ህመም ድህረ ሰቀቀን ጭንቀት (PTSD) በመባል ይታወቃል።
ስርጭት፦
ሴቶች ላይ ይበዛል። 10 በመቶ በሴቶች/ ጾታዊ ጥቃት ስለሚበዛ፣ 4 በመቶ በወንዶች/ ከግጭት ጋር በተያያዘ፣ በወታደሮች ላይ 30 በመቶ እንደሚጠጋ ጥናቶች ያሳያሉ። ወጣቶች ላይ ስርጭቱ ከፍተኛ ነው።
አጋላጮች፦
ማንም ሰው ከዚህ ችግር የተጠበቀ አይደለም። ነገር ግን ማህበራዊ ተሳትፏቸው አነስተኛ የሆኑ ሰዎች የበለጠ ሊጠቁ ይችላሉ፤ እንደ ምሳሌ ብቸኛ ሰዎች፣ ትዳር የሌላቸው/ በሞት አልያም በፍቺ ሊሆን ይችላል፣ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ ያሉ፣ የወንጀል ስለባ የሆኑ፣ አብዝቶ የሱስ ተጠቃሚዎች፣ አንዳንድ የስብእና ችግር አይነቶች፣ ተያያዥ ጭንቀቶች እንዲሁም ድባቴ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።
ምልክቶቹ፦
1. ለአሰቃቂ ነገር ተጋላጭ ከሆኑ በኋላ የሚፈጠር፦
በራሳቸው ላይ የተፈጠረ ገጠመኝ ሲሆን፣ ሌሎች ሰዎች ላይ ሲደርስ መታዘብ፣ በቤተሰብ አባል ላይ መድረሱን ሲያውቁ፣ እና ተደጋጋሚ አጋላጮች ሲኖሩ/ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች።
2. ተመላላሽ፣ ጣልቃ ገብ የሆነ የሚረብሽ ትውስታ፣ ቅዠት፣ ሰመመን ውስጥ መግባት፦
አደጋው እንደ አዲስ በእውን የሚፈጠር ይመስላቸዋል፣ ሁኔታውን እንደነበረው ይተገብሩታል፣ ፍንጭ የሚሰጡ ነገሮች ሲሰሙ፣ ሲያዩ ይረብሻቸዋል።
3. የጸና ሽሽት ውስጥ ይገባሉ፦
ስለሁኔታው ትውስታ የሚሰጣቸውን ላለመስማት፣ ላለማየት፣ ሰዎችንም ላለማግኘት በጽናት ይሸሻሉ። ትውስታውንም ለመርሳት ሱስ ይጠቀማሉ።
4. አሉታዊ አስተሳሰብ እና ስሜት ይኖራቸዋል፦
''እኔ መጥፎ ነኝ፣ ማንም ሰው አይታመንም፣ አለም ክፉ ናት'' የሚሉ አስተሳሰቦች በግለሰቡ ላይ ይነግሳሉ። እራስን መውቀስ፣ እራስን ለማጥፋት መገፋፋት፣ ሌሎችን መውቀስ እንዲሁም ለከፋ የአዕምሮ ጤና መታወክ፣ ሱሰኝነት ብሎም ክፋት ይዳርጋሉ። ፍርሃት፣ ቁጭት፣ ቁጣ መግለጫቸው ይሆናል። እነዚህ ስሜቶች ቁጥጥር ከሌላቸው ሌሎች ሰዎችን ሳያውቁት ሊጎዱ ይችላሉ።
5. ድንጉጥ እና ደንታ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፦
ቶሎ ይቆጣሉ፣ ሁሉንም ነገር በነቂስ ይከታተላሉ፣ ይበረግጋሉ፣ ይወራጫሉም። እንቅልፍ ላይ ይሰቃያሉ፣ በህይወታቸውም ደንታ ቢስ ይሆናሉ።
ህክምናው፦
የስነልቦና እንዲሁም የመድኃኒት ናቸው። ጊዜ የሚፈልግ እና ቀስ በቀስ በሂደት የሚስተካከል የህመም አይነት ስለሆነ በጊዜ ህክምና ከተገኝ ውጤታማና አመርቂ ይሆናል።
ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (MD, Psychiatrist)
@melkam_enaseb
ጃፓኖች ሁሉም ነገር ላይ እጅግ ስነ ስርዓት አላቸው ይባላል። በቀደመ ህይወቴ ጃፓናዊ ነበርኩኝ መሰለኝ እኔም ስርዓት አበዛለሁ።😄 በእርግጥ የኔ የጤና አይደለም። በፀበልም በፀሎትም የማይድን OCD (Obsessive Compulsive Disorder) አለብኝ። የችግሩ አንደኛው ምልክት ነገሮች ሁሉ በስርዓት እንዲደራጁ አለቅጥ መሻት ነው። እኔም የሚታይብኝ ይሄኛው ምልክት ነው።
የተዛነፈ ነገር ማዬት አልችልም። የማላውቀው ሰው ኮሌታ ራሱ ካልተስተካከለ እጄን ይበላኛል። የምግብም ይሁን የቡና ስፍራ አሁንም አሁንም ሳስተካከል፣ ሲኒ ሆነ ብርጭቆ በልክ ስደረድር፣ ምንጣፍ ለማንጠፍ መስመር ሳሰምር ላየኝ ድሮዊንግ ተጨንቆ እየሰራ ያለ ሲቪል ኢንጂኒየር ነው የምመስለው። የተዝረከረከ ነገር አልወድም። አልጋ ሳነጥፍ ውጥር አድርጌ ነው። መጅሊስም ይሁን ፍራሽ ሰው ተቀምጦ በተነሳ ቁጥር ነው የማስተካክለው። ጫማ ሲቀመጥ ከተንሻፈፈም ከተደራረበም ተነስቼ አስተካክላለሁ። ደርቆ የገባ ልብስ ቶሎ ካልተጣጠፈ የሆነ የተሸከምኩት ነገር ያለ እስኪመስለኝ ነው የሚከብደኝ። ያልተተኮሰ ልብስ በተዓምር አለብስም። ልብሴ ላይ ትንሽ ጠብታ ነገር አርፎ ማስወገድ ካልቻልኩ ትኩረቴ እዛ ላይ ሆኖ ይውላል። አብሮ የማይሄድ ወይም ከላይም ከታችም የተዥጎረጎረ አለባበስ ያቅለሸልሸኛል። ዲዛይነር ብሆን የሚዋጣልኝ ይመስለኛል። የብር ኖት የባንክ ሠራተኛ እንኳን እንደኔ አያስተካክሉም። ፅሁፍ ላይ ግድፈት እንዳይኖር በጣም እጠነቀቃለሁ። አለቆች ትንሽ ካወቁኝ በኋላ "መቼም አንቺ አትሳሳቺም" እያሉ ሳያነቡ መፈረም ይጀምራሉ። እምነታቸው በበሽታዬ ላይ ኃላፊነት ያሸክመኛል።🤦♀️ እንኳን ቢሮ ፌስቡክ ላይም ስፅፍ የአንዲትም ፊደል ስህተት አልፈልግም። ለአፃፃፉ ግድ የሌለው ሰው ራሱ ይገርመኛል። የቢሮ ጠረጴዛዬ ላይ አንዲት ወረቀት ያለ አግባብ አትገኝም።
ፎቶ ሳነሳ ባለሙያ ይመስል አንግል፣ ሴንተር፣ ፎከስ እላለሁ። የተጣመመ ፎቶ የማይረብሻቸው ሰዎች ታድለው። የምቀርፃቸውን የኸሚስ ቪድዮዎች ያየ አንድ ጓደኛዬ እንደውም እንቅስቃሴ ካለመኖሩ የተነሳ በስታንድ ካሜራ ነው ወይ የምትቀርጪው ብሎኛል። ለነገሮች ውበትና Details ስጨነቅ አርክቴክት ይቀናብኛል።
ሲበዛ ቀጠሮ አከብራለሁ። ሌላው ቀርቶ ፖስት ራሱ በተሸራረፈ ሰዓት መፖሰት አልወድም። 1 ሰዓት 5 ሰዓት እንደዛ። የአንድ የሁለት ደቂቃም ልዩነት አልፈልግም። በምንም ነገር ፐርፌክሽን ያስደስተኛል። ግድየለሽነት፣ ቸልተኝነት ያናድደኛል። የቱንም ያክል ቢበዛ ከቢሮ ሥራ ጨርሼ ነው የምወጣው። ካልሆነ ልቤ እዛው ተንጠልጥሎ ነው የሚያድረው። ልሠራው ያሰብኩት 5 ነገር ኖሮ አንዱ እንኳን ከጎደለ ይደብረኛል። ጓደኞቼ "ሞራልሽ የወታደር ነው!" ይሉኛል። አቡዳቢ እያለሁ ጂም ከለሊቱ 7 ሰዓት ሊዘጋ እኔ 6 ሰዓት ሄጄ አውቃለሁ። ምክንያቱም ቀድሜ አስቤዋለው።🤣 ያሰብኩትን ነገር ካልፈፀምኩ የአዕምሮዬ መንገድ ይጨናነቃል። የሰውም ጉዳይ ቢሆን ሳላሳካ መተው አልችልም። በነገራችሁ ላይ ይሄ ችግር ቀላል እንዳይመስላችሁ። በዚህ ሰበብ የፈረሱ ትዳሮች ሁሉ አሉ። ደግነቱ እኔ እየመረረኝም ቢሆን ራሴ አስተካክላለሁ እንጂ ሰው አልጫንም። ቢያመኝም ቢደክመኝም ለዚህ ሲሆን አልሰንፍም። ምናልባት ልጆች ሲኖሩኝና ቤቱን እያመሳቀሉ ጢምቢራዬን ሲያዞሩት እንደ ኩፍኝ ካልወጣልኝ በቀር ነገርዬው በዋዛ የሚተውም አይደለም። ለማንኛውም መስመር የያዘች ቅድዬ ተመኘሁላችሁ!
ፏ_ያለች_ቅድዬ!
(Atiqa Ahmed Ali)
@melkam_enaseb
⬆️ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሥነ-ልቦና ማዕከላት፤ ስልካቸውና አድራሻቸው።
#mentalhealth #addisababa #MHSUA #psychology #psychiatry
@melkam_enaseb
እንደው ለመሆኑ የተለየ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የምንሠጠው ስም/አጠራር/ስያሜ እንዴት ይኾን?
እውን ስያሜዎቻችን ጤናማ፣ ሚዛናዊ፣ ተገቢ ናቸውን?
ላሳስብዎት! ወዳጆቼ ይህ ፅሑፍ ግላዊ ዕይታ ብቻ ነው፤ ወጥ የሃሳብ ፍሰትም የለውም።
፩| በ'ኔ ጊዜያዊ አመለካከት 'አካል-ጉዳት' የሚለው ሐረግ በ 'Ontological Semantics' እና 'Pragmatical Lexicography' መነፅር ሳጤነው ተገቢ ኾኖ አላገኘሁትም፤ ይልቁንም ሐረጉ ከሚወክለው ውጪ ለሌሎች አይነት 'ልዩ-ፍላጎት' ላላቸው መጠቀም ተገቢ አይመስለኝም።
በተጨማሪም ‛አካል-ጉዳተኛ፣ አካለ-ስንኩል፣ አካለ-ጎዶሎ’ እነዚህ ሐረጎች የተለያየ ሐሳብ አላቸው ብዬ አላስብም፤ ቃላቱን በጥልቀት ብንፈትሻቸው/ብንመረምራቸው የጎላ ልዩነት አይታይባቸውም፤ ሆኖም ለቃላቱ እንደ ማኅበረሰብ የምንሠጠው ዕይታና ልማድ ልዩነትን ፈጥሯል።
ነገር-ግን በአማርኛ ቋንቋ በአንዳንድ ተናጋሪዎች ሥር-የሠደዱና የተለመዱ ቃላትና ንግግሮች፦
ደንቆሮ፣ ሽባ፣ ደደብ፣ ስንኩል፣ ዲዳ፣ አንካሳ፣ አስቀያሚ፣ አካለ ጎዶሎ፣ ቆማጣ፣ ደንባራ፣ ድውይ፣ እውር፣ እብድ፣ ዘገምተኛ ወ.ዘ.ተ
የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ
የእውር አዝማሪ የደንቆሮ ተጣሪ
የቆማጣ ፈትፋች የእውር ተሟጋች
ቆማጣን ከማከም ድንጋይ መሸከም
፪| በአዕምሮ ዕድገት ኹኔታዎች (Neurodevelopmental Conditions) ላይ በማኅበረሰባችን ጥቅም ላይ የዋሉ በርካታ ስያሜዎች አሉ። ለምሳሌም ከ6ቱ የአዕምሮ ዕድገት ኹኔታዎች መካከል አንዱ 'Intellectual Developmental Disorder' ነው።
በስፋት የምንጠቀማቸው ሁለት ስያሜዎች ሲኖሩ አንደኛው 'የአዕምሮ ዕድገት ዝግመት' ሲኾን ይህም ዘገምተኝነት ዘገም ማለት፣ ቀስ ማለትን ይገልፃል። ከሳይንሱ ብያኔ አንፃር መዝገም የሚለው ይገልፀው ይኾን? ፣ ሁለተኛው 'የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት' ነው፤ ይህም መወሰን፣ መገደብ እና ውስን ወይም ትንሽ መሆንን ያመለክታል። ከሳይንሱ ብያኔ አንፃርስ ይህ ቃል ይገልፀው ይኾን?
ብዙ-ጊዜ የምንጠቀማቸው የተለመዱ ቃላት፦
ውስንነት | ችግር | እክል | መዛባት | ጉዳት | ተጋላጭ | ፍላጎት | ተግዳሮት | ህመም | ወ.ዘ.ተ
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እና ላልተዘረዘሩት የእንግሊዝኛ ቃላት ተገቢ ትርጉም/ፍቺ ያስፈልጉናል፦
Disorder | Deficit | Impairment | Discripancy | Disturbance | Difficulties | Disability | handicap | retarded | vulnerable | syndrome | problem | Dis |e.t.c
አዎ! እንግሊዝኛውና የሀገራችን የአተረጓጎም ጉዳይ ጥናት ሊደረግበት፤ ትኩረት ሊሠጠው ይገባል!
ዋኖስ መስፍን (@WanosMesfin)
የልዩ-ፍላጎት ትምህርት ባለሞያ
@melkam_enaseb
ድብቁ የወሲብ ገበያ: ቴሌግራም ያቀጣጠለው የወሲብ አብዮት
ቴሌግራም በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰፊ ተጠቃሚዎች ካሉት መተግበሪያዎች አንዱ ነው።
ምንተስኖት ደስታ በሥነ-ሕብረተሰብ (ሶሲዮሎጂ) ከሐረማያ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በስንቅ ዩዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማናጀር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
ቴሌግራም ከሚታማባቸው ጉዳዮች አንዱ ስለሆነው ልቅ የወሲብ ገበያ ከኢትዮጵያ አንፃር የዳሰሰበትን ጹሑፍ በሐሳብ አለኝ ቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔት ላይ አስነብቦናል።
ምንተስኖት በጹሑፉ በዚህ ላይ ከሚሳተፉ፤ ይኸው ተግባር ሱስ ከሆነባቸው ወጣቶችን ቃለመጠይቅ በማድረግና እና የተለያዩ ቻናሎችን በማጥናት ጥሩ ጹሑፍ አቅርቦልናል።
በዚህም፦
- ለዲጂታል ወሲብ አገልግሎቶች ከ500 - 3000 ብር እንደሚጠየቅ፤
- የህፃናት ወሲብ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተፈላጊ ስለመሆኑ፤
- ስለባህል ህክምናና ማስታወቂያዎቹ፤
- ከመንግስት እና ከቤተሰበሰ ስለሚጠበቀው ነገር በጹሑፉ አንስቷል።
አንብቡት 👉 https://concepthub.net/article/4
Via: Concepthubeth
ትውልድን እንታደግ!
@melkam_enaseb
አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ!
Therapist
ፆታ፡ አይለይም
ብዛት:- 2
የሥራ ቦታ:- ሂል ሳይድ እና ሲ-ኤም-ሲ
የስራው አይነት:- ቤት ለቤት በሰዓት
የትምህርት ዘርፍ:- ልዩ-ፍላጎት፣ ሳይኮሎጂና ተዛማጅ
ከልጆች ጋር በመስራት ልምድ ያለው ለቦታው ቅርብ ቢሆን ይመረጣል።
በ ABA & Speech-Language ቴራፒ ስልጠና የወሰደ/ች ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
ማሳሰቢያ፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ብቻ በ @Tizaabebe CV and certification ላኩልን መደወል አይቻልም።
@melkam_enaseb
የምስራች መልካም ዜና ለድሬዳዋ እና አካባቢዋ!
ምንም እንኳን የአዕምሮ ህመም በምስራቁ ሀገራችን በብዛት ቢታይም ይህንን ያማከለ እና ለአእምሮ ህክምና ታስቦ የተዘጋጀ የህክምና ማዕከል አለመኖሩ ብዙውን የምስራቅ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዲያማትር ሲያስገድደው አስተውለናል፡፡ ይህንን መጉላላት ለመቅረፍ ቤካንሲ ልዩ የአዕምሮ ህክምና ለምስራቅ ሀረርጌ እንዲሁም ድሬዳዋ አካባቢ በተዳረጀ መልክ ብቁ ከሆኑ የአእምሮ ህክምና እና ስነልቦና ባለሞያዎች ጋር በመሆን ድሬደዋ ላይ ከትሞ ይጠብቆታል፡፡
በቤካንሲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦
- ጠቅላላ የአዕምሮ ህክምና
- ድንገተኛ የአዕምሮ ህክምና
- የተመላላሽ የአዕምሮ ህክምና
- የሱስ ማገገም እና ታሀድሶ ህክምና
- የተኝቶ ህከክምና
- የህጻናት የአዕምሮ ህክምና
- የወጣቶች እንዲሁም የአዛውንቶች የአዕምሮ ህክማኛ
- የግል እና የቡድን የንግግር ህክምና (ሳይኮራፒ)
- አጠቃላይ የአዕምሮ ጤና ምዘና
- የትዳር ማማከር አገልግሎት ህክምና
አድራሻ፡- ድሬደዋ ከኦርቢት ሆቴል ገባብሎ ማሪያም ሰፈር ት/ቤት ፊትለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 0961767778/ 0252111678
አዕምሮን መንከባከብ፣ ህይወትን መቀየር!
@melkam_enaseb
የአዋቂዎች መለያየት ጭንቀት (Adult Separation Anxiety Disorder)
የአዋቂዎች መለያየት ጭንቀት ሲባል ከቤት ወይም ከአጋር ሰው ሲለዩ የሚፈጠር የማያቋርጥ እና ከመጠን በላይ የሆነ ፍርሃት አልያም ጭንቀት ነው። ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በልጅነት የሚከሰትና በኋላም ወደ አዋቂነት የሚሸጋገር ሆኖ ይገኛል፤ መቼም መጀመርያ ወደ መዋለ ህጻናት ሲሄድ ያላለቀሰ ልጅ የለም ብዬ መናገር ባልደፍርም፣ ያለቀሱ ልጆች በኋላ ለይ ደፋር ሲሆኑ ይስተዋላል። ነገር ግን ከእነዚህ ዉስጥ ጥቂቶቹ ባያለቅሱም ከቤት አልያም ከወላጅ የመለየት ጭንቀቱ በጣም ጸንቶ በአዋቂነት ህይወታቸው ለይ ይሰርጻል። ከቤት ውጭ ወይም ያለ አጋር የሚከናወኑ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች ለይ ውስንነቶች ይስተዋላሉ።
ስርጭት፦ በአዋቂዎች ውስጥ ያለው ስርጭት ከ 1% እስከ 2% እንደሚሆን ይገመታል።
የምርመራ ምልክቶች፦
1. ከመለያየት ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የተጋነነ እና ከመጠን በላይ ፍርሃት፣ ጭንቀት ሲኖር፤ ከሚከተሉት ምልከቶች ውስጥ ቢያንስ ሶስት መኖር አለበት።
• ከቤት ርቀው ወይም ከአጋር ተለይተው መሄድን ሲያስቡ ከመጠን በላይ መጨነቅ ሲኖር።
• ከአጋራቸው በሚለያዩበት ጊዜ የማያቋርጥ እና ከመጠን በላይ ስጋት። ለምሳሌ (የሚጠፉ፣ የሚጠለፉ፣ አደጋ የሚደርስባቸው፣ የሚታመሙ፣ የሚሞቱ) ይመስላቸዋል።
• መለያየትን በመፍራት ምክንያት ከቤት ውጭ ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ ሥራ ወይም ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ፈቃደኛ አለመሆን ብሎም የማያቋርጥ እምቢተኝነት መኖር።
• ከቤት ዉጭ ወይም ካለ አጋር ሌላ ቦታ ማደር ከመጠን በላይ መፍራት ወይም አለመፈለግ።
• ከመለየት ጋር በተያያዘ የሚኖር ተደጋጋሚ የሌሊት ቅዠት መኖር።
• ከአጋር አልያም ቤት መለየት በሚጠበቅበት ጊዜ በተደጋጋሚ አካላዊ ምልክቶች ሲኖር፤ ለምሳሌ (ራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ወዘተ...)።
2. ፍርሃቱ፣ ጭንቀቱ ወይም ሽሽቱ የማያቋርጥና ቢያንስ (ለ4 ሳምንታት ለልጆች እና ለ6 ወር ለአዋቂዎች) ሲከሰት።
3. ፍርሃቱ በስራ፣ ትምህርት፣ እንዲሁም ሌሎች የህይወት መስኮች ለይ ተጽዕኖ ሲፈጥር።
ህክምና፦
ሁለት አይነት ህክምና አሉት። እንዚህም የስነ-ልቦና ህክምና እና የመድሃኒት ህክምና ናቸው። እንዚህ ህክምና አይነቶች በባለሙያ፣ በታካሚ እንዲሁም የአጋር ትብብር የሚሰጡ ሲሆኑ፤ ጊዜ እና ትዕግስትን ይፈልጋል። ነገር ግን ወደ ህክምና ከተመጣ ዉጤታማ መሆኑ አይቀርም።
ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ (MD, Psychiatrist)
@melkam_enaseb
ለድሬዳዋ፣ ሀረር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ ከተሞች ለምትገኙ ነፃ የኦንላይን ስልጠና!
የቴዲ ጎሳ የስልጠና ካውንስሊንግ እና ምርምር ማዕከል ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከአሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ለሚያከናውነው የመስራት ፕሮግራም ነፃ የኦንላይን 34 (Soft skill) እና 22 (Hard skill) ስልጠናዎች በአጠቃላይ 56 ስልጠናዎች፤ በስራ ላይ እና ከስራ ውጪ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በሰርተፍኬት የማብቃት እንዲሁም እድገታቸውን የማጠናከር ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሶ እየጠበቃችሁ ይገኛል።
በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ ይሰልጥኑ፤ ሰርቲፋይድ ይሁኑ: actacademy.et
ስልክ: 0922012854
0943274318
ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን ፋይል ይመልከቱ።
ለማህበራዊና ስነልቦናዊ ልማት እንተጋለን!
@melkam_enaseb
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
መልካም በዓል!
@melkam_enaseb
የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር| Substance use disorder!
በቅርቡ የተጠና ጥናት እንዳመለከተው በአለማችን ላይ በአመት 11.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ችግር ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ ነው፡፡
እንዲሁም 2 በመቶ የሚሆኑ የአለማችን ሰዎች የችግሩ ሰለባ እንደሚሆኑም መረጃው ያሳያል፡፡
Substance use disorder| የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር ምንድን ነው?
አንድ ሰው በተለያየ ጊዜያቶች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም እራሱን ለከፋ የጤና ሁኔታ የሚዳርግ ከሆነ Substance use disorder/ የንጥረ ነገር አጠቃቀም ችግር አለበት እንላለን፡፡
ሰዎች ይህ ችግር አለባቸው የሚባለው 3 ነገሮችን ሲያሳዩ ነው።
1. በቋሚነት የሚያደርገው ከሆነ
2. ለማቆም በሚሞክርበት ጊዜ የሚቸገር ከሆነ
3. በማቆሙ ምክንያት የሚመጡ የህመም ስሜቶች ካሉ
መንስኤው ምንድን ነው?
- የጓደኛ ተፅዕኖ
- አካባቢያችን ላይ አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ
- ብዙ ትርፍ ሰአት መኖር (ስራ ማጣት)
- አንዳንዴ ደግሞ በቤተሰብ ይሄ ችግር ካለ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- የምንጠቀመውን ነገር ሰአት ጠብቆ የፍላጎት ስሜት መሰማት
- ንጥረ ነገሩን ካልተጠቀምን የመነጫነጭ እና የድብርት ስሜት መኖር
- ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑን እየጨመሩ መሄድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
- እራስን መጠራጠር መጀመር
- ሀላፊነትን ለመቀበል መቸገር
- የቤተሰብ መረበሽ
- የኢኮኖሚ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡
ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
- ለማቆም የቆራጥነት ስሜት እንዲኖር ማድረግ
- ያለበት ደረጃ ከፍተኛ ከሆነ ንጥረ ነገሩን ከሰውነቱ እንዲወጣ ማድረግ
- በማገገሚያ ማዕከላት ለተወሰነ ጊዜ መቆየት
- የስነ ልቦና ህክምና መውሰድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ነገር ግን ለዚህ ችግር ትልቁ ህክምና የሚጀምረው ከራሱ ከግለሰቡ ነው። በመጨረሻም ሱስ እንደማንኛውም በሽታ ስለሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ተገቢውን ህክምና ማግኘት አለባቸው፡፡
አቶ ልዑል አብርሀም (የስነልቦና ባለሙያ)
Via: ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@melkam_enaseb
ጥር ወር ላይ ስፒች ቴራፒ የባህርይ ቴራፒ!
ልጆች የትምህርት ቤት እረፍት የሚሆኑበት ሰአት ላይ ለልጅዎ ስፒች ቴራፒና የባህርይ ቴራፒ ይፈልጋሉ?
እንግድያውስ ጃዚኤል (ማህሌት) ስፒች ቴራፒ ለ15 ቀን ወይም ለ1 ሳምንት በተከታታይ ቀን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ ቴራፒዎችን ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
ቴራፒያችን አንድ ለአንድ ሲሆን ቴራፒው ለወላጆች ከዛ በኃላ መቀጠል የሚችሉበትን መንገድም አመቻችተናል።
⬇️ ይደውሉና! ይመዝገቡ!
0940103047
0954999933
አድራሻ:- መገናኛ-ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ!
(ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic)
Telegram group——/channel/Jazielspeechtherapyclinic
@melkam_enaseb
የመርሃ ግብር ጥቆማ!
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።
የዚህ ወር ርዕስም፡- “ቦርደርላይን ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደርን መረዳት” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ አቶ ጴጥሮስ ሃጎስ ናቸው፡፡
ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ ⬇️
https://forms.gle/ErdfV7uCCR2Y3Lzs8
@melkam_enaseb
⬆️ 'የኦቲዝም ምስጢሮች' መፅሀፍ የምርቃት ዝግጅት ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
@melkam_enaseb
⬆️ ስለ አዕምሮ ሕመም ምን ያህል ያውቃሉ?
#AMSH
@melkam_enaseb
About Perfectionism OCD by Atiqa Ahmed Ali...⬇️
Читать полностью…የሥራ ማስታወቂያ!
ፆታ፡ ሴት (ብዛት:- 5)
የሥራ ቦታ:- ሲ-ኤም-ሲ - 1
ጦር-ሃይሎች - 3
ወይራ (ሴት አስጠኝ) 1
ስራው:- ትምህርት ቤት ላይ (Therapist)
የትምህርት ዘርፍ:- ልዩ-ፍላጎት፣ ሳይኮሎጂና ተዛማጅ
ከልጆች ጋር በመስራት ልምድ ያላት (አንድ አመት እና በላይ የሰራች) ለቦታው ቅርብ ብትሆን ይመረጣል።
ማሳሰቢያ፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ብቻ በ @Tizaabebe CV and certification ላኩልን መደወል አይቻልም።
@melkam_enaseb
Attachment styles!
ትልቆች ሆነን ስለራሳችን እንዲሁም ስለሌሎች የሚኖረን አተያይ እና ተግባቦት: በልጅታችን ከወላጅ/አሳዳጊዎቻችን: በተለይም ከእናታችን ጋር የሚኖረን ግንኙነት እና መቀራረብ መሰረት የሚቃኝ ነው።
በተለይም የመጀመርያዎቹ 3 አመታት ይህ Attachment የሚከወንበት ወሳኝ ጊዜ እንደሆነ ይነገራል። ይህ Attachment ካደግን በኋላ በሚኖሩን ግንኙነቶች ይገለጣል።
1. Anxious/Preoccupied
ስለራሳቸው አነስተኛ ግምት ያላቸው ናቸው። ከራሳቸው ይልቅ ሌሎችን አግዝፈው ያያሉ። ለራሳቸው በሚኖራቸው አነስተኛ ግምት ምክንያት: በጓደኝነት መሃል መከዳትን አብዝተው ይፈራሉ። ዘወትር ጓደኞቻቸው እንደማይከዷቸው መተማመኛን እንዲሰጧቸው ይሻሉ። ይህ ጓደኞቻቸው ላይ መታከትን ሊፈጥር ይችላል። አብዝተው Reassurance ይፈልጋሉ።
2. Avoidant/Dismissive
ለራሳቸው የተሻለ ምልከታ አላቸው። በአንጻሩ ለሌሎች አሉታዊ ምልከታ ይኖራቸዋል። ብቻቸውን መሆንና ነገሮችን በራሳቸው ማድረግን ይመርጣሉ። ከሌሎች ሰዎች ጋር መቀራረብን እንደ ጥገኝነት ሊቆጥሩት ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ጋብቻንና ሌሎች መወዳጀቶችን ሲሸሹ ይስተዋላል።
3. Disorganized
ስሜታቸውን መግራት አይችሉበትም፤
በመፈለግና አለመፈለግ መሃል ይዋልላሉ፡ ስሜትን ለማጋራት ይሰስታሉ ምክንያቱም እንጎዳለን ብለው ስለሚያስቡ። ግልፍተኝነት፣ ስሜትን ለመቆጣጠር መቸገር፣ ራሳቸው ላይ ጉዳት ማድርስ (በሰበብ አስባቡ ራስን ለማጥፋት ማንገራገር እንዲሁም መሞከር) እና የስሜት መለዋወጦችን መለያ ባህርያቸው ናቸው።
4. Secure
የተረጋጉ እና በሚኖራቸው ግንኙነቶች መተማመን ያላቸው ናቸው። ግንኙነቶቻቸው የተረጋጉ እና ሰላማዊ ናቸው። ነገሮችን ከስሜታዊነት ይልቅ በጥበብና በብልሃት ስለሚፈቷቸው የስነልቦና ልዕልናቸው ከፍ ያለ ነው።
የናንተ Attachment style የቱ ነው?
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሚገኝ ጥናት አመላክቷል!
ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ የጥናት ውጤት ጠቅሶ ባስነበበው ዘገባ ድብርት፣ ጭንቀት፣ መገለል እና ሌሎችም ከአዕምሮ ህመም ጋር የሚያያዙ በሽታዎች በወረርሽኝ ደረጃ እየተስፋፉ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የኤፒዲሚዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ኬት ፒኬት የችግሩ ስፋት በተለይም በወጣቶች ላይ በጣም አሳሳቢ ነው ሲሉ ለፋይናንሻል ታይምስ ተናግረዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ለድብርት፣ ጭንቀት እና ሌሎችም የአዕምሮ በሽታዎች መጨመር ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣ ጦርነት እና ግጭት እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጽ አጠቃቃም ቀዳሚ ምክንያት ሆነው ተጠቅሰዋል፡፡
እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአሁኑ ወቅት 280 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በድብርት የሚሰቃዩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 28 በመቶውን የሚሸፍኑት ከ18-29 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፡፡
ጭንቀትን በተመለከተ አራት በመቶ የአለም ህዝብ በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ የሚኖር ሲሆን አጠቃላይ ቁጥሩ ደግሞ ከ301 ሚሊየን እንደሚሻገር መረጃው አመላክቷል፡፡
Via: Alain
የአዕምሮ ጤንነታችንን መንከባከብ አለብን!
'ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!'
@melkam_enaseb
Mental Health Matters!
በሰዎች ተከበው ብቻቸውን የሆኑ እና ብቸኝነት የሚያሰቃያቸው ብዙ ሰዎች አሉ። በአካል አብረን ስለዋልን አብረን ስላደርን አብረን ነን ማለት አይደለም። አብረውን ካሉ ሰዎች ጋር በስነልቦናም በመንፈስም ልንገናኝ ይገባል። Spiritual and Emotional Intimacy ሊኖረን ይገባል ደስተኛ ሆነን ሰዎችን ደስተኛና ጤናማ ለመሆንም ለማድረግም።
ብዙ ነገራችን አብሮ መዋል ወይም ማደር ላይ ብቻ ስለሚመሰረት ብዙዎች የውስጣቸውን መከፋት፣ ብሶት፣ ጭንቀት እና ፍርሀት አብረዋቸው ላሉ ሰዎች ማጋራት ሳይችሉ ቀርተው በጭንቀት፣ በድብርት የሚሰቃዩ ብዙዎች ናቸው። አለፍ ሲልም ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እየተበራከቱ ነው።
ከጎናችን ላለ ሰው የአእምሮ ሁኔታ ቅድሚያ መስጠት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስሜታችንን ልንፈታተሽ ይገባል። እንዴት ነህ? ዛሬ ምን አስደሰተህ? ዛሬ ምን አስከፋሽ? ወዘተ... የሚሉት ጥያቄዎች ትንሽ ቢመስሉም ተጠይቀው ለሚመልሱት ሰዎች ግን እፎይታን ይሰጣል።
የሚሰማችሁን በውስጣችሁ አምቃችሁ አትያዙ። ንስሀ አባት የሌላችሁ የንስሀ አባት ይዛችሁ ስለመንፈሳዊ ጤናችሁ ተመካከሩ። ስነልቦናዊ እና እለታዊ ጉዳዮችን የቅርቤ ለምትሉት ሰው አጋሩ። የሚሰማችሁን አምቃችሁ አትያዙ!! ከጎናችሁ ያለን ሰው አዋሩ።
ከፍ ያለ የስሜት መረበሽ ሲገጥማችሁ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ሞክሩ። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ በፀሎት ትጉ።
ድብርት ቅብጠት አይደለም ህመም ነው።
(Rafatoel Worku)
@melkam_enaseb
Four factor model ከስነ ልቦና ህክምናዎች አንዱ የሆነው Cognitive and behavioral therapy መሰረት ካደረገባቸው ጽንሰ ሃሳቦች አንዱ ነው።
የነገር አረዳዳችን፤ ከስሜታችን፣ የሰውነት ጤና እና ባህርይ/ ክዋኔዎቻችን ጋር እንዴት እንደሚገናኝ የሚያስረዳ ምስል ነው።
ሃሳብና አረዳዳችን ሚዛናዊ በሆነ ቁጥር አዕምሯዊና አካላዊ ጤናችን የተስተካከለ ይሆናል።
የሚያጋጥሙንን ክስተቶች በጭፍን ከመደምደም ይልቅ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ ከተለያየ አቅጣጫ ለመረዳት መሞከርን መለማመድ ጥሩ ነው።
ያኔ የሚረብሹን ስሜቶች መቀነስ ይጀምራሉ። የተሻለ የመፍትሄ ሃሳብን የማፍለቅ ችሎታችን ይዳብራል።
በሂደት ሚዛናዊው እና ንቁው የአዕምሯችን ክፍል (prefrontal cortex) እየደረጀ ይመጣል።
ንቃተ ህሊናችንን እናዳብር!
Let's be consciousness!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb
Advertisement
አማራጭ የአእምሮ ህክምና ተቋም!
የአእምሮ ህክምና አገልግሎትን በተሻለ መንገድ ለማድረስ የምናደርገውን ጥረት በመቀጠል የዶ/ር ዳዊት ጤና አገልግሎትን እነሆ ብለናል።
አድራሻ፦ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ሕንፃ፣ 4ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 408 ከሲኤምሲ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ።
ቀጠሮ ለመያዝ የሚከተለውን ስልክ ይጠቀሙ፦ 0948272829
ዶ/ር ዳዊት አሰፋ (የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
በሜንታል ሄልዝ ዙሪያ የምትሰጡትን አገልግሎቶች፣ ስልጠናዎች ማስተዋወቅ የምትፈልጉ ባለሙያዎች ያናግሩን ⬇️
@FikrConsultSupportbot
@melkam_enaseb