ቅን መድረክ የግል ስብዕና ማበልፀጊያ ስልጠና!
በአለም ሲኒማ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 10/2015 የህይወት ክህሎት አሰልጣኝና የቢዝነስ አማካሪ ሣሙኤል ተክለየሱስ እና የግል ስብዕና አሰልጣኝ ሰመረ ነጋሽን ይዞላቹ ይቀርባል።
ሁላቹም ተጋብዛችኋል!
@melkam_enaseb
ሁለት ሰዎች ከሲጋራ ማጨስ ሲታቀቡ በዓይነ ሕሊናዎ ይመልከቱ።
ሲጋራውን ሲጋበዙ የመጀመሪያው ሰው፦
“አይ አመሰግናለሁ። እኔ ለማቆም እየሞከርኩ ነው” ይላል። ይህ ምክንያታዊ ምላሽ ይመስላል። ነገር ግን ይህ ሰው አሁንም አጫሽ እንደሆነና ሌላ አይነት ሰው ለመሆን እየሞከረ እንደሆነ ነው የሚያምነው። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተመሳሳይ እምነቶችን ይዘው ባህሪያቸው እንደሚለወጥ ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው።
ሁለተኛው ሰው “አይ አመሰግናለሁ። እኔ አጫሽ አይደለሁም” በማለት ሲጃራውን አይቀበልም። ከላይኛው ሰው ምላሽ ጋር ያለው ልዩነት ትንሽ ነው። ምላሾቻቸው ግን የማንነት ለውጣቸውን ያሳያል።
ብዙ ሰዎች ለመሻሻል ሲነሱ የማንነት ለውጥን እምብዛም አያስተውሉትም። ለድርጊቶቻቸው የሚያነሳሱ እምነቶችን ከግምት ሳያስገቡ ግቦችን ያስቀምጣሉ፤ እንዲሁም ግቦቹን ለማሳካት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ይወስናሉ። ነገር ግን እራሳቸውን የሚመለከቱበትን መንገድ በጭራሽ አይቀይሩም፤ የድሮው ማንነታቸው አዲሱን የመለወጥ ዕቅዳቸውን ሊያበላሽ እንደሚችል አይገነዘቡም።
ከራስ ጋር የማይጣጣም ባህርይ አይቆይም። ምናልባት ብዙ ገንዘብ ይፈልጉ ይሆናል፣ ግን ማንነትዎ ገንዘብን ከማፍራት ይልቅ የሚያባክን አይነት ሰው ከሆነ ከማግኘት ይልቅ ወደ ማባከን መሳብዎን ይቀጥላሉ። የተሻለ ጤንነት ይፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን ከድርጊት ይልቅ ምቾትን ማስቀደምዎን ከቀጠሉ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ ወደ ዘና ማለት ይሳባሉ። ወደ ቀድሞ ባህሪዎ የመሩዎትን መሰረታዊ እምነቶቸ ካልቀየሩ በስተቀር፣ መቼም ቢሆን ልምዶችዎን መቀየር ከባድ ነው፡፡
አዲስ ዓላማ እና አዲስ ዕቅድ ካለዎት ልክ ያልሆነውን አስተሳስብዎንና ማንነትዎን ቀድመው ይለውጡ።
(Atomic Habits ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ)
@melkam_enaseb
#መሳተፍለምትፈልጉ
Life Skill and Inspirational Training
የተገነባ ማንነት ሲኖረን ከባባድ ሁኔታዎችን ወደ ኋላ ሊያስቀሩን፣ አንገታችንን ሊያስደፉን፣ ከራዕያችን ሊያደናቅፉን የሚታገሉንን የህይወት ተግዳሮቶችን ባለመሰበር ማሸነፍና ማለፍ የሰርክ ተግባራችን ይሆናል!
ሁልጊዜ ራሴን እገነባለሁ!!!
ታዲያ በምግብ ብቻ አይደለም! በአእምሮም ጭምር እንጂ!!
ህዳር 03 ቅዳሜ ጠዋት 2:30-6:30
ቦታ: ቫምዳስ ሲኒማ
@melkam_enaseb
#የመጽሐፍግብዣ
ይሄ በዶ/ር ጁሊ የተፃፈው የግል ስብእና ማሳደጊያ መፅሃፍ 'Why Has Nobody Told Me This Before?' የሚባል ነው፡፡ ፀሃፊዋ በተለይ በቲክ ቶክ ላይ በምታቀርባቸው መልእክቶች የምትታወቅ ናት፡፡
በጣም አስቸጋሪ እና አስጨናቂ በሆኑ ጊዜያትም ቢሆን የአእምሮ ጤናችን እንዴት ማጠናከር እና መጠበቅ እንደምንችል የሚያስተምር መፅሃፍ ነው፡፡ መፅሃፉ ላይ ያሉትን የዶ/ር ጁሊ ስሚዝን የባለሙያ ምክሮች በመጠቀም ጭንቀትን መቆጣጠር፣ ትችትን መቋቋም፣ ድብርትን መቋቋም እና በራስ መተማመንን ማዳበር እንችላለን፡፡
መልካም ንባብ!
Source: ወደ ስራ የሬዲዮ ፕሮግራም
@melkam_enaseb
አልኮል እና እርግዝና!
አንዲት ሴት በእርግዝና ወቅት ወይም ለማርገዝ በምታስብበት ጊዜ የሚታወቅ አስተማማኝ የአልኮል መጠጥ መጠን የለም። በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ለመጠጣት ምንም አስተማማኝ ጊዜ የለም። ሁሉም የአልኮል ዓይነቶች ጎጂ ናቸው፣ ወይን እና ቢራንም ጨምሮ።
በእርግዝና ወቅት አንዲት ሴት አልኮል ካልጠጣች ብቻ FASDsን መከላከል ይቻላል። አልኮል አደገኛ ነው በእናት ደም ውስጥ ያለው አልኮል በእትብት በኩል ወደ ሕፃኑ ይተላለፋል። በእርግዝና ወቅት አልኮል መጠጣት የፅንስ መጨንገፍ፣ የፅንስ መሞት እና በጤና ቢወለድ እንኳን የዕድሜ ልክ አካላዊ፣ የባህሪ እና የአዕምሮ ጉድለቶች ሊያስከትል ይችላል።
እነዚህ የአካል ጉዳተኞች የፅንስ አልኮል ስፔክትራል ዲስኦርደር (Fetal Alcohol Spectrum Disorders) - FASDs በመባል ይታወቃሉ።
FASDs ያላቸው ልጆች የሚከተሉትን አካላዊ እና ባህሪዎች ሊኖራቸው ይችላል:-
▸ ትንሽ የጭንቅላት መጠን
▸ አጭር አማካይ ቁመት
▸ ዝቅተኛ የሰውነት ክብደት
▸ በሰውነት እንቅስቃሴ ደካማ ቅንጅት
▸ ተንቀዥቃዥ ባህሪ
▸ ትኩረት ለማድረግ መቸገር
▸ ደካማ የማስታወስ እና ማገናዘብ አቅም
▸ ትምህርት ቤት ውስጥ ደካማ መሆን (ዝቅተኛ IQ)
▸ ደካማ የማመዛዘን እና የፍርድ ችሎታዎች
▸ የእንቅልፍ እና የመጥባት ችግሮች
▸ የማየት ወይም የመስማት ችግሮች
▸ በልብ፣ በኩላሊት ወይም በአጥንቶች ላይ ችግሮች
በእርግዝና ወቅት የሕፃኑ አንጎል እድገት ላይ ስለሚሆን በማንኛውም ጊዜ ለአልኮል በመጋለጥ ሊጎዳ ይችላል። አንዲት ሴት መጠጣቷን ካቆመች ለልጅዋ እና ለራሷ የተሻለ ይሆናል።
(ዶ/ር ይበልጣል)
@melkam_enaseb
የሚገመት ኢ-ምክኒያታዊነትና የመደጋገም አባዜ!
አብዛኛዎቹ ሀሳቦቻችንና ድርጊቶቻችን ኢ-ምክኒያታዊ ናቸው፡፡ ኢ-ምክኒያታዊ ቢሆኑም ፀባያችን ዝብርቅርቅና በዘፈቀደ የሚፈጠር አይደለም። ኢ-ምክኒያታዊነታችን ሊገመት በሚችል መልኩ ይደጋገማል፡፡
ከሚቀጥለው ሴሚስተር ጀምሮ ትምህርት እንደተጀመረ ነው ጥናት የምጀምረው!" ብለን ይሆናል፡፡ የሚቀጥለው ሴሚስተር ሲመጣም በተለመደው መንገድ መጀመሪያ ተዘናግተን ፈተና ሲደርስ እንጨናነቃለን፡፡ ድጋሚ "በሚቀጥለው ሴሚስተር...." እንላለን። ድግግሞሹም ይቀጥላል፡፡ የገንዘብ አወጣጣችንም ደሞዝ ከወጣ በኃላ ባሉት ቀናትና ደሞዝ ሊደርስ ሲል ባሉት ቀናት ልዩነት ይኖረውና "ከአሁን በኃላ በፕሮግራም ነው የምንቀሳቀሰው!" ብለን ቃል እንገባና ተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ራሳችንን ልናገኝ እንችላለን፡፡
60 ከመቶ በላይ ሀሳቦቻችንን አንገነዘባቸውም፡፡ ሀሳባችንን ካልተገነዘብነው ኢ-ምክኒያታዊ የመሆን እድላችን ከፍ ይላል፡፡ በአፅናፈ አለም (universe) ሚሊዎን ኮከቦች መኖራቸውን አምነው የተቀበሉ ሰዎች "ግርግዳው ቀለም ተቀብቷል" ስንላቸው በእጃቸው ነክተው ካላረጋገጡ አያምኑም፡፡ አውሮፕላን ላይ "ቀበቶአችሁን እሰሩ!" ሲባል ሁሉም ሰው ሳያቅማማ ወዲያውኑ ያስራል፡፡ የመኪና "ቀበቶ እሰሩ!" ሲባል ብዙ ሰው ያንገራግራል፡፡ አያድርስና አደጋ ቢፈጠር የአውሮፕላን ቀበቶ የጎላ ጥቅም አይኖረውም፡፡ የመኪና ቀበቶ ግን በህይወትና በሞት መካከል ልዩነት ይፈጥራል፡፡
ተመሳሳይ መድሀኒት ቢሆንም ከሶስት ብር ኪኒን የሶስት መቶ ብር ኪኒን የተሻለ ውጤት ያሳያል፡፡ ምክኒያቱ ያው ሊገመት የሚችል ኢ-ምክኒያታዊ ተፈጥሮ ነው፡፡ ሰው በመሆናችን ሙሉ ለሙሉ ምክኒያታዊ ልንሆን አንችልም፡፡ ብንሆን እንኳ እጀታ እንደሌለው ስለት ጉዳት ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ሊገመት የሚችለው ኢ-ምክኒያታዊነትና የመደጋገም አባዜ ካላገናዘብነው ስራችን፣ ትምህርታችን፣ ማህበራዊና የፍቅር ግንኙነታችን ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
ሀሳባችንን መመርመር ከማንፈልገው እሽክርክሪት ለመውጣት ይረዳል፡፡
(ዶ/ር ዮናስ ላቀው)
@melkam_enaseb
አምስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ ተጀምሯል!
ውድ የልዩ ፍላጎት ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ ወላጆች፣ ባለሙያዎች እና ሞግዚቶች።
ለምዝገባ እና ማንኛውም ጥያቄ በ +251911148328/ +251911887607/ +251911735569 ይደውሉ፡፡
#CFS
@melkam_enaseb
#ነጻ_የትምህርት_ዕድል
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነጻ የትምህርት እድል ለሴቶች እና ለአካል ጉዳተኞች አዘጋጅቷል።
ሙሉ ነጻ የትምህርት ዕድሉ በ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም አምስት ሴቶች እና ሦሥት አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው
➭ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም
(መስፈርቶች እና የትምህርት ዕድሉ የተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች ከላይ ተያይዟል።)
Via: Tikvah University
@melkam_enaseb
የአእምሮ መታወክ በሴቶች እና በወንዶች ላይ በተለያየ መልኩ ሊከሰት ይችላል።
አንዳንድ የአዕምሮ ህመሞች እንደ ድብርት እና መንፈስ ጭንቀት ያሉት ሴቶች ላይ በብዛት ይታያሉ። በሴቶች ላይ ደግሞ ልዩ ወይም ሴቶች ላይ ብቻ የሚገኙ አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች አሉ።
ሴቶች በሆርሞን ለውጥ/ መዋዠቅ ወቅት የአዕምሮ መታወክ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ:- የድህረ ወሊድ ጭንቀት፣ በቅድመ የወር አበባ እና ማረጥ (menopause) ወቅት ጋር የተያያዘ የመንፈስ ጭንቀት እንደምሳሌነት ይቆጠራሉ።
የአእምሮ ሕመም መታከም የሚችል ነው። ከጤና ባለሙያዎ ጋር ከስነ-አእምሮ እና የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ያሎትን ጥያቄዎችና ሃሳቦትን በግልፅ መወያየት የእርስዎን የአእምሮአዊ ጤንነት እንክብካቤ ስለሚያሻሽል በግልፅ እንዲመካከሩና እንዲወያዩ እንመክሮታለን።
ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን።
+251 966 11 1111
+251 116 66 29 66
(Lebeza Psychiatric Specialty Clinic)
@melkam_enaseb
የእድሜ እኩሌታ ቀውስ!
የእድሜ እኩሌታ ቀውስ እድሜ ካለፈ በኃላ እንደዚህ ባደርግ ኖሮ የሚል ፀፀትና ቁጭት መሆኑን የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
የዚህ ምክንያቱ ደግሞ መስራት ባለብን ከምቾት ዞን ሳንወጣ የኖርንባቸው ዘመናት ውጤት ነው ይላሉ በጉዳዩ #ለኤፍቢሲ ሃሳባቸውን የሰጡት የስነልቦና ባለሙያ ሲሳይ ተስፋዬ፡፡
እንደ ባለሙያው ገለፃ እስከ 30፣ 40 እና 50 ዓመት ሄደው ሰዎች ለራሳቸው ማዘጋጀት ያለባቸውን ነገሮች ሳያዘጋጁ ሲቀሩ ማለትም መማር ሲኖርባቸው ሳይማሩ ሲቀሩ፣ ማግባት፣ መውለድ ሲገዳቸው ያን ሳያደርጉ ሲቀሩና የሚፈልጉትን ማግኘት አለመቻላቸውን ሲያዩ ይደነግጣሉ ይህም ከውስጥ ጥያቄ ይፈጠራል፤ ይህን መቋቋምም ከባድ ይሆናል፡፡
ሰው በጊዜው የሚያስፈልገውን አላገኘም ማለት ደግሞ ጥሩ ያልሆኑ ሃሳቦች ይፈጠርበታል፤ ቤተሰብ አካባቢም አላገባህም/ሺም፣ አልወለድክም/ ሺም እራስህን አልቻልክም/ሺም፣ አልተማርክም/ሺም የሚሉ ጥያቂዎች ይመጣሉ እንዲሁም ከእኛ ቀድመው ያሉ ጓደኞቻችንን ስናይ የሚመጡ ሌሎች ጥቄዎችም ይኖራሉ፡፡
ይህ ደግሞ የስሜት፣ የፍላጎት እና ሌሎች ጉድለቶችን ይፈጥራል በዚህ ቀውስ ውስጥ ደግሞ ከግለሰቡ አስተዋጽዖ በዘለለ ማህበረሰባዊ አገልግሎትም የራሳቸው ሚና አላቸው፡፡
በተለይም ግለሰቡ የህይወት ግቡን በትክክል እንዲረዳ፣ ምክንያታዊ ህይወት መምራት እንዲችል ንቃተ ህሊናውን በማዳበር ረገድ ስራ ከልተሰራ ግለሰቡ ዕድሜው አለአግባብ ሊባክን ይችላል፡፡
ዕድሜ ካለፈ በኋላ ለሚፈጠር ጥያቄ የተፈጠርንበት ዓላማ ማወቅ ወይም ወደ እዚህ ዓለም የመጣንበትን ምክንያት ማወቅ መልስ ይሆናል ብለዋል አቶ ሲሳይ፡፡ ያለምክንያት ወደ እዚህ ዓለም አልመጣንም፤ ድንቅ ፍጡርም ነን፣ ለምን ምድር ላይ እኖራለሁ የሚለውን መመለስ ይገባል።
#ኤፍቢሲ
@melkam_enaseb
ከጭንቀት ዘላቂ ነፃነትን እንዴት ማግኘት ይቻላል?
ጭንቀት፣ ጥርጣሬ እና ከመጠን በላይ ማሰብ የተለመዱ የህይወታችን ክፍሎች ናቸው። ስለመጪው ወይም ስለአሁኑ መጨነቅ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን "ከተለመደው" በላይ የማያቋርጥ ጭንቀት፣ አሉታዊ አስተሳሰብ እና ሁልጊዜ መጥፎውን መጠበቅ በስሜታዊ እና በአካላዊ ጤንነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው።
በተጋነነ መልኩ በጭንቀት እና ውጥረት ከተሰቃዩ ግን የሚያስጨንቁዎትን ሀሳቦች ለይቶ በማወቅ፣ ከመጨናነቁ ለመላቀቅ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች እንዳሉ ማመን ተገቢ ነው።
ይህን ጠንቅቀው ይወቁ ....ሥር የሰደደ ጭንቀት ሊሰበር የሚችል የአእምሮ ልማድ እንጂ የዘላለም ስቃይ አይደለም።
አሁን ጥያቄው "እንዴት ከጭንቀት ነፃ እንውጣ?" ነው
ጭንቀትን ማሸነፍ የሚቻልበት አንዱ መንገድ እያንዳንዱ ጣልቃ-ገብ አሉታዊ እሳቤ ለመጨነቅ ትክክለኛ ምክንያት አለመሆኑን መቀበልን መማር ነው። በቀላል አነጋገር፣ ሁሉም ሀሳቦች እውነት አይደሉም። ስለዚህ ምክኒያታዊ መሆን እና ሊያስጨንቁን የማይገቡ ሀሳቦችን ችላ ማለት ተገቢ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ጭንቀትን ለማቃለል ሊሞክሯቸው የሚችሏቸው ሌሎች ዘዴዎች እንደ #አርምሞ፣ #ማሰላሰል እና #በጥልቀት_መተንፈስ የመሳሰሉ ቴክኒኮችን መለማመድ ይቻላል።
ወጣም ወረደ ግን...የገጠሙንን ሆነ፣ የሚገጥሙንን ችግሮች በመጨነቅ ሳይሆን መፍትሔ በማበጀት ብቻ ነው ልንቀርፋቸው የምንችለው!
ሣሙኤል ተክለየሱስ
(ዓለም አቀፍ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
@melkam_enaseb
እርዳታ ጠይቅ!
የአእምሮ ጤና መጽሔት በ2017 ባካሄደው ጥናት ውስጥ በድብርትና በጭንቀት እየተሰቃዩ ያሉ ሰዎች የሌሎችን እርዳታ #እንዳይጠይቁ የሚያደርጓቸውን ምክንያቶች አጥንቷል፡፡ ከጥናቱ ከተለዩት ምክንያቶች ውስጥ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፦
- እርዳታ ስጠይቅ ሰዎች ለእኔ ያላቸው ቦታ ዝቅ ይላል፡፡
- ችግሮቼን በራሴ ማስተካከል መቻል አለብኝ፡፡
- ችግሮቼን በራሴ ነው ማስተካከል የምፈልገው፡፡
- ምን አይነት ድጋፍ ላገኝ እንደምችል አላውቅም፡፡
- ችግሮቼን በራሴ መፍታት ባለመቻሌ አፍራለሁ፡፡
- ስለ ስሜቶቼ ለሌላ ሰው ማውራት አልፈልግም፡፡
ይህ ጥናት በዋናነት ያተኮረው በድብርት እየተሰቃዩ ያሉ ወንዶች ሰዎች እርዳታ የማይጠይቁባቸው ምክንያቶች ላይ ቢሆንም፣ በጠቅላላው ግን እነዚህ ሁሉም ምክንያቶች በሌሎች ሁኔታዎች ላይ እና በሴቶችም ዘንድ ጭምር የሚሰሩ ናቸው፡፡
አንድ ነገር ግልፅ እናድርግ ሁሉም ነገር ደህና ሳይሆን ደህና እንደሆነ የምታስመስል ከሆነ ሞኝ እንጂ ጠንካራ እየሆንክ አይደለም፡፡ ነገሮችህን ዋጥ ማድረግና መደበቅ ምንም የተሻለ ነገር አያመጣም፡፡ ችግሮቻችንን የባሰ ያባብሳል እንጂ፡፡
ችግሮችን መደበቅና ከችግሮቻችን መሸሽ ምንም የሚፈታው ነገር የለም፡፡ ትብብር መጠየቅ ግን ለውጥ ለማምጣት ያግዛል፡፡
(በልኬት ወደ ስኬት መጽሐፍ የተቀነጨበ)
Via: ተክሉ ጥላሁን
@melkam_enaseb
⬆️ከትላንቱ የቀጠለ...
Neurocognitive Disorder (NCD) 3 ዋና ዋና ክፍልፋዮች አሉት፦
1.Delirium /ዲሊርየም/
2.Major neurocognitive disorders/ ከባድ ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር/
3.Mild neurocognitive disorders/ ቀላል ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር/
1.ዲሊሪየም /Delirium/
የዚህ አይነት የግንዛቤ እክል የሚከሰተው በፍጥነት (ሰዐታት-ጥቂት ቀናት) ሲሆን፣ መሰረታዊ የግንዛቤ እከል የሚስተዋለው የትኩረት (attention) ግንዛቤ መደብ ለይ ነው። የትኩረት አቅጣጫ ከመሰየም ጀምሮ፣ አተኩሮ መቆየት፣ ትኩረትን መቀየር ብሎም አካባቢን እና ጊዜን የመለየት ግንዛቤ መደብ ለይ ችግር ይስተዋላል። ተጠቂ ሰዎች ከፈተኛ መደነጋገር፣ ቅዠት አይነት ባህርይ፣ የስሜት መዋዠቅ፣ መቅበጥበጥ፣ መፍዘዝ፣ ወዘተ...ይስተዋልባቸዋል። ይህ ችግር የሚስተዋለው በሱስ አምጪ ነጥረ ነገር መመረዝ አልያም ድንገተኛ ማቆም፣ የመድሃኒት አጠቃቀም፣ ተጓዳኝ አካላዊ ህመም ጋር ተያይዞ፣ ወይም በርካታ አጋላጭ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው።
ይህ ህመም በጊዜ ካልታከመ ግለሰቡ ለይ ከፍተኛ የህይወት አደጋ ብሎም ሞት ሊያመጣ ይችላል፤ መሰረታዊ ህክምናው አጋላጩን ማከም ነው።
2.ከባድ ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር/ Major neurocognitive disorders/
ይህ የግንዛቤ እክል ዝግመታዊ ክስተት ያለው ሲሆን፣ የጊዜው መጠን የሚወሰነው በአጋላጩ በሽታ አይነት ነው። አጋላጮቹ እጅግ በርካታ ሲሆኑ፣ እንደምሳሌ የአልዛይመር በሽታ/ Alzheimer’s disease/፣ የደም ቧንቧ በሽታ/Vascular disease/፣ የጭንቅላት አደጋ/ Traumatic brain injury/፣ ኤች.አይ.ቪ/ HIV infection፣ የፓርኪንሰን በሽታ/Parkinson’s disease/፣ ወዘተ... ናቸው። ተጠቂው ግለሰብ አንድ ወይም ከዛ በላይ ባሉት የግንዛቤ ጎራዎች ውስጥ በማስረጃ የተደገፈ ከፍተኛ የግንዛቤ ማሽቆልቆል ሲኖሩት፣ እና መደበኛ የህይወት ትግባሩ ለይ የከፋ መስተጓጎል ሲፈጥር ነው። በማስረጃ የተደገፈ ስንል፣ ግለሰቡ አልያም ቤተሰቡ ወይም ደግሞ ሀኪሙ የግንዛቤ እክል እንዳለው ሲያረጋግጥ፤ እና በኒዉሮ ስይኮሎጂ መለክያ መስፈርት እከል መኖሩ ሲደገፍ ማለታችን ነው። ምልከቶቹ እንደ አጋላጩ የሚለያዩ ሲሆን የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ችግር፣ አዲስ ነገር ለመማር መቸገር፣ ንግግር መርዘም፣ ሃስብ ለመግለጽ መቸገር ፤ እንዲሁም የባህርይ ለውጥ (ግድ የለሽ፣ ጥርጣሬ፣ ቅዠት፣ ወዘተ...) እና የስነ ልቦና ለውጥ (ድብርት፣ መነጫነጭ፣ ንዴት፣ ውዘተ....) ይስተዋላሉ።
3.ቀላል ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር/ Minor neurocognitive disorders/
ይህ ከከባድ ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር /Major/ የሚለየው የህመሙ ደረጃ ማነስ ብቻ ነው። በዚህ ችግር የተጠቁ አብዛኛው ሰዎች በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎቻቸው ለይ የጎላ ለውጥ አይታይባቸውም፤ ነገር ግን የቅርብ ወዳጆቻቸው መርሳታቸውን ሊያስተውሉ ይችላሉ፤ “የእርጅና ምልክት እየታየብህ/ሽ ነው” በማለት ለግለሰቡ ሃሳብ ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። በተመሳሳይ ተጠቂው ግለሰብም ሰራው ለይ አልያም ትምህርቱ ለይ ስህተቶችን በተደጋጋሚ ማየት ሰለሚጀምር፤ የበለጠ ለመጠንቀቅ ካላንደሮች /calendar/፣ ማስታወሻዎችን /reminders/ አብዝቶ ይጠቀማል። መጠነኛ ድባቴ ካልሆነ በስተቀር ጎልቶ የሚወጣ የባህርይ ለውጥ ሲኖርም አይስተዋልም።
(በዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/ ሳይካትሪስት)
@melkam_enaseb
ADHD (Attention Deficit Hyper Active Disorder) ምንድነው?
ስንት አይነት የ ADHD አይነቶች አሉ?
Via: SNE Ethiopia
https://telegra.ph/ADHD-Attention-Deficit-Hyper-Active-Disorder-11-16
አይዞን ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሄ አለ!
ችግር/ ተግዳሮት እና መፍትሄ ልክ እንደ ብርሃንና ጥላ የማይነጣጠሉ ናቸው! የገጠመን ችግር መፍትሄው ቀላል ወይም ከባድ፤ ሩቅ አሊያም ቅርብ፤ ገንዘብ የሚጠይቅ፣ ምናልባትም የማይጠይቅ፤ አጋዥ የሚፈልግ ወይም ብቻችንን ልንጋፈጠው ግድ የሚል ሊሆን ይችላል እንጂ ከቶውኑ ያለ መክፈቻ ቁልፍ የተዘጋ አይደለም።
በእርግጥ ለነገሮች እና ለሁኔታዎች ያለንን ዕይታ እስካልተስተካከለ ድረስ በህይወታችን የሚፈጠሩ ጉዳዮች ሁሉ ችግር ሆነው ሊታዩን ይችላሉ። ምክንያቱም ሁኔታዎችን የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ያስተናግዳሉና።
ይኸውም እንዳንዶች ከችግሮቹ መልካም ዕድልን በጥረታቸው መፍጠር ሲችሉ፣ ሌሎች ደግሞ ችግሩን ችላ በማለት ሊባባስ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ።
በዚህ ልዩነት ውስጥ ግን መገንዘብ ያለብን ቁምነገር ቢኖር በህይወታችን የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን የምናይበት መንገድ ችግሩን የምንፈታበት ዘዴ ላይ በእጅጉ ተጽእኖ የሚያሳድር መሆኑ ነው። ለዚህ ደግሞ በእያንዳንዱ ሁኔታ በተፈጠሩ፣ ችግሮች ውስጥ ሆነን ምቾት እንዲሰማን ከመፈለግ ይልቅ ከተፈጠረው ችግር ባሻገር ባለው የመፍትሔ ሃሳብ ላይ ማተኮር ይኖርብናል።
ስለዚህ በችግሮቻችን አንጠመድ! ይልቅስ በተቻለ መጠን መፍትሄዎችን በማሰብ መሞከራችንን እንቀጥል። የተፈጠርነው እንዲያ ነውና ስንሞክር ደግሞ ብዙ ዋጋ ያላቸው ሃሳቦችን እናመነጫለን።
ከኛም አልፈን ቤተሰቦቻችንን፣ ጓደኞቻችንን እና በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎችን እናነቃቃለን። እናም በታጋሽነታችን እና በፅናታችን ያገኘነው የችግር መፍቻ ቁልፍ የህይወት ተሞክሮ ሆኖ ለብዙዎች ተግባራዊ ምሳሌ ይሆናል።
ወዳጆች ቀበቶአችንን ጠብቅ አናርግ፤ እጅጌያችንን እንሰብስብ፤ ትኩረታችንን እንግራ፤ የተቻለንን እንሞክር፣ ምክንያቱም መፍትሔው ያለው በጥበብ በመሞከር ውስጥ ነው!
ቀና የሙከራ ጊዜ ይሁንልን!
ሣሙኤል ተክለየሱስ (ዓለም አቀፍ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
@melkam_enaseb
Renascent Mental Health and Rehabilitation Center!
የግል የአዕምሮ ሕክምና እጅጉንም ባልተስፋፋበት ሁኔታ ውስጥ ይህንን የአዕምሮ ህክምና ማዕከል ፍሬ አፍርቶ ለዚህ በመብቃቱ የድርጅቱን መስራቾች እንዲሁም ለሁሉም የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ማኅበረሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።
በተለይ ከከባድ የአዕምሮ ህክምና ጎን ለጎን ትውልድን እየጎዳ ባለው እና ብዙ ህብረተሰቦቻችን እየተቸገሩ ላሉበት "የከባድ የሱስ ተጠቂነት ላለባቸው" ማህበረሰብ ጥራት ያለው ሳይንሳዊ ህክምና እንደሚሰጥ ተስፋ አለኝ።
የሱስ ህክምና በትዕግስት፣ ከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ተነስሽነት ከተጠቀሙት በርግጥም መፍትሄ እንዳለው የስፔሻሊቲ (ሬዚደንት ት/ት ፕሮግራም) ወቅት ምስክር በመሆን ብናገር ደስ ይለኛል።
ፕ/ር ሰለሞን ተፈራ ባለኝ መረጃ መሠረት ካልተሳሳትኩ በሃገራችን ብቸኛው የሱስ ህክምና ሰብ - ስፔሻሊስትም ጭምር ናቸው። ተማሪ በነበርኩበት ሰዓት ብዙ ነገር ከርሳቸው ለመማር ችያለው።
በመሆኑም የአገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ የሱስ ህክምናም ከመደበኛው የጠቅላላ የአዕምሮ ህክምና በተጨማሪ እንደሚያበረክቱ ተስፋ አለኝ።
መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እመኛለው!
ዶ/ር ሔኖክ ይትባረክ (የአዕምሮ ሀኪም: አማኑኤል ሆ/ል)
@melkam_enaseb
አጀስትመንት ዲሶርደር| Adjustment Disorder
✍ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የስነ-አዕምሮ ሬዚደንት ሃኪም)
https://telegra.ph/9አጀስትመንት-ዲሶርደር-Adjustment-Disorder-11-03
ራስን ስለማጥፋት
============
በሰው ልጅ ራስን በማጥፋት ሀሳብ፣ ፍላጎት፣ ሙከራ እና ተግባር ውስጥ ያለውን የስነልቦና ውጥረት ግብግብ መመልከት የቻልኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ።
የተሻለን ነገን ለማየት ከሚናፍቅ እና በተስፋ ከታጀበ የሰው ልጅ resilient ተፈጥሮ ራስ ላይ ጨክኖ ህይወትን የማቋረጥ ውሳኔ ላይ መድረስ አይደለም ሀሳቡ ከባድ ህመም አለው።
የሰው ልጅ አለመኖርን ማሰብ ሲጅምር የሚያጋጥሙት የህይወት ውጣ ውረድ የፈጠሩበትን ጫና መሸከም ከሚችለው በላይ የመሆኑ ነገር አንደኛው ነው።
በሰዉ ልጅ ህይወት ውስጥ የማይታዮ ግን የሚያልፉ ብዙ ነገሮች አሉ።
የዚህ የህይወት መንገድ ዉጤት የአዕምሮ ጤና ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ በሚያመጣው የአስተሳሰብ፣ የስሜት፣ የባህሪ ለውጦች አንድአንዴ ህይወት ሊደክመን ይችላል።
አንድአንዴ አዕምሮ ይታመማል።
አንድአንዴ አቅም ይከዳል።
አንድአንዴ ህይወት የከበደ ሰሞን አብረውን ይሆናሉ ያልናቸው ሰዎች አብረውን ላይሆኑ ይችላሉ።
አንድአንዴ መኖር አድካሚ ሊሆን ይችላል።
አንድአንዴ ነገን ማየት ሩቅ መስሎ ሊሰማን ይችላል።
ግን ህይወት የተሰኘ ይሄ ሂደት ብዙ ነገር እንደ ገና የማስጀመር እድል ይሰጣል።
There is always a little light at the end of the tunnel and let’s see hope in the hopless situations of life.
ስሜት ይታከማል። የአዕምሮ ጤና ጉዳይ መፍትሔ አለው።
ሰናይት ተመስገን
Via: Hakim
@melkam_enaseb
የሚሰሩትን ይበልጥ እንዲወዱት የሚያግዙ አምስት ጠቃሚ ነጥቦች፦
- በእቅድ መመራት
- ለፈተናዎች እራስን ማዘጋጀት
- አስደሳች የስራን አካባቢ መፍጠር
- እረፍትን በአግባቡ መጠቀም
- ስራን ወደቤት አለመውሰድ
መልካም የስራ ሳምንት!
@melkam_enaseb
#የመጽሐፍጥቆማ
ርዕሰ፦ መቋሚያ የሱስ ሳይንስ መጽሐፍ!
ከሱስ ማገገምና ምልሰተ ሱስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መንገዶች - የያዘ ድንቅ መጽሐፍ፣ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ ሊኖር የሚገባ መፅሐፍ!
ጥቂት ከመጽሃፉ፦
''አንጎል በትክክል ሲሰራ፤ በሁለንተናዊ አቅጣጫ የተሻለ ውጤት ይገኛል፤ አንጎል በትክክል ካልሰራ ደግሞ የሁለንተናዊ የሕይወት አቅጣጫችን ለአደጋ የተጋለጠ መሆኑ የማይቀር ይሆናል።
የአንጎልዎን ጤንነት ለመጠበቅ ደግሞ አንጎልን ለመንከባከብ እና ከሚጎዱት ነገር ለመጠበቅ ግንዛቤ፣ እውቀት እና አስፈላጊ የሕይወት ዘይቤዎችን መከተል ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ አንጎልን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ነገሮች አንዱ የአደገኛ እፅ ተጠቃሚነትና ሱሰኝነት ተጠቃሽ ነው፡፡''
መጽሐፉ ሚመልስልን ጥያቄዎች፦
ለመሆኑ፡- #ሱስ ምንድን ነው? #ሱስ ህመም ነው? #ስለ ሱስ ሳይንስ ምን ይለናል? #ሱሰኝነትን እንዴት መከላከል እንችላለን? #ከሱስ ማገገም ምን ማለት ነው? ስኬታማ ከሱስ የማገገም ሂደት ማለት ምን ማለት ነው?
የመጽሐፉ ፀሀፊ ኤልያስ ካልአዩ (ከሱስ የማገገም አማካሪና አስልጣኝ) ካለው ሰፊ ልምድ፣ እውቀትና በርካታ ተሞክሮ በመነሳት ለብዝዎቻችን እንቆቅልሽ የሆነብንን የግለሰብ፣ የቤተሰብ፣ የማህበረሰብና የአገር ከባድ ችግር ሱሰኝነት፤ ከሱስ የማገገም ሂደት ላይ ለመፍትሄው ሊኖረን የሚገባውን ድርሻ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ያጠቁመናል፡፡ አንብበው ራስዎን፣ ቤተሰብዎንና ማህበረሰብዎን በሚጠቅም መልኩ ይገንቡ!
Via: ጃፈር መጽሐፍት
መጽሐፉን ገዝታችሁ እንድታነቡት እንጋብዛለን!
@melkam_enaseb
ይየስብዕና መታወክ!
✍ ሳይንስ ካሳዬ (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
Via: ጋሻው አወቀ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ)
https://telegra.ph/ይየስብዕና-መታወክ-10-28-6
''በወጣቶች ላይ የመማር ፍላጎት መቀነስ፣ ተምሮ ትልቅ ቦታ ከመድረስ ይልቅ በአጭር ጊዜ ኃብትና እድገትን ያመጣሉ ወደሚባሉ ነገሮች ትኩረት ማድረግ፣ የአደገኛ እጽ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው። በአዲስ አበባ አደገኛ ዕጾችን የሚጠቀሙ ወጣቶችና አዳጊ ሕጻናት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱን ጥናቶች ይጠቁማሉ'' - አቶ ፋንታሁን ሐሰን (የስነልቦና አማካሪ)
https://p.dw.com/p/4J4gj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ምንድን ነው?
✍️ ሰለሞን ግዛቸው (የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያ)
Via: ዶ/ር አላምረዉ አለባቸዉ
https://telegra.ph/ይየስብዕና-መታወክ-10-28-5
ድንገተኛ የመረበሽ ስሜት እና ህመም - Panic attack and Panic disorder
✍ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የስነ-አእምሮ ሬዚደንት ሃኪም)
Instant View ሚለውን በመጫን ያንብቡ!
https://telegra.ph/ድንገተኛ-የመረበሽ-ስሜት-እና-ህመም---Panic-attack-and-Panic-disorder-10-29
ልጆቿን በምን መልኩ ነው ሚቀጡት?
የልጆችን ባህሪ መግራት እና ማስተማር በተለይ እድሚያቸው እስከ 6 አመት ለሆኑ
የልጆች ባህሪ ዲስፕሊን ማድረግ ማለት መግረፍ ወይም መቅጣት ማለት ሳይሆን ልጆች ያልተፈለገ እና ያልተገባ ባህሪ ሲያሳዩ እንዴት ማስተካከል እና ስሜታቸውን በተገቢው መንገድ መግለጽ እንዳለባቸው መምራት ወይም ማስተማር/ማሰልጠን ማለት ነው።
የልጆችን ባህሪ ማስተካከል ስናስብ ልናውቅ የሚገባን፦
1. በልጆች እና በወላጆች መካከል ያለው ፍቅር፣ መተማመን እና መከባበር
2. በዘር ወይም ቤተሰቡ በአጠቃላይ ስሜትን የሚገለፅበት መንገድ
3. የልጁ/የልጅቷ እድሜ እና
4. በልጆቹ መካከል ያሉ ልዩነቶችን መረዳት ያስፈልጋል
ልጆች ለምን ይረብሻሉ?
1. ትኩረት ለማግኘት
2. ሁኔታዎች እንዳልተመቻቸው ለመግለፅ
3. ብስጭት እና ቁጣን ለመግለፅ
4. ወላጆችን ለመፈተን/ አታድርግ የተባለውን ቢያደርግ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ
5. ሲሰለቹ፣ ሲርባቸው፣ ሲያማቸው እንቅልፋቸው ሲመጣ
ወላጆች እና መምህራን የልጆችን ባህሪ እንዴት እናስተካክል?
- በእያንዳንዱ የልጆች እድገት ሂደት ተያይዞ የሚመጣን ባህሪ ማወቅና መረዳት
- ባህሪ ምክኒያት እንዳለው ማወቅ እና ምክኒያቱን መረዳት
- ሁሉም የልጆች እንቅስቃሴዎችን እንደ ረብሻ አለመቁጠር ለምሳሌ፦ አካባቢያቸውን ለማወቅ እና ለመረዳት ሲነካኩ እንደ ጥፋት አለመቁጠር
- ሁሉንም ችግሮች ለማስተካከል አለመሞከር አንዳንዴ አንዳንድ ባህሪዎችን አይቶ ማለፍ
- ከእድሜያቸው በላይ ስርአት እንዲያከብሩ አለመጠበቅ
- ለአንዱ የሰራልን የባህሪ ማስተካከያ መንገድ ለሁሉም እንዲሰራ አለመጠበቅ
- መልካም ባህሪን ማድነቅ እና ማበረታታት
- ምርጫ በመስጠት በራስ መተማመንን ማሳደግ
- ማድመጥ፣ ግዜ መስጠት እና ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር
- በመጨረሻም፡ እኛ ራሳችን ምን ያህል መልካም ምሳሌ መሆናችንን መፈተሽ ማለትም ያስቀመጥናቸው ህግና ስርአቶችን መተግበራችንን ማረጋገጥ።
መአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)
@melkam_enaseb
የኢትዮጵያ ሳይኮሎጂ ባለሞያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ሔኖክ ኃይሉ፣ የሥነ አእምሮ ሐኪም ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ እንዲሁም የሥነልቦና ባለሞያ እና በሮትራክት ክለብ የሙያና አመራር ልማት ዳይሬክተር (professional and leadership development Director) የሆነችው ቃልኪዳን ኃይሉ በአእምሮ ጤና ዙሪያ ያደረጉትን ሰፋ ያለ ውይይት ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያንብቡ፣ በአዲስ ማለዳዋ ሊዲያ ተስፋዬ የተዘጋጀ።
⬇️
https://bit.ly/3TSd1ei
በ #አዲስማለዳ (22/10/2022)
@melkam_enaseb
#መሳተፍለምትፈልጉ
"እኔ ነኝ መፍትሄው የእግር ጉዞ" በዚህ ሳምንት!
እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነትና በጎነት ዘመቻ በዚህ ሳምንት ጥቅምት 19 ቅዳሜ በእንጦጦ የእግር ጉዞ ከፕሎጊንግ ኢትዮጵያ ጋር አዕምሯችን ላይ የቆሸሹ ሀሳቦችን እያፀዳን በእግር እየተጎዝን የመፍትሔ ተግባራትን እንከውናለን በሚል ይካሄዳል።
መግቢያው በነጻ ነውና መሳተፍ ትችላላችሁ!
@melkam_enaseb
የግንዛቤ እክል (Cognitive Impairment)
(በዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/ ሳይካትሪስት)
አንጎላችን ከሚያከናውነው እጅግ የተወሳሰቡ ስራዎች መካከል የግንዛቤ እና የባህርይ መድብ ተጠቃሽ ናቸው። የእንዚህ ሁለት የአንጎል መድብ መሰረታዊ ተግብር ማህበራዊ ህይወትን ለመምራት ማስቻል ነው። የግንዛቤ (Cognition) መደብ በተለምዶ የእውቀት (intellectual function) እና ከፍተኛ የአንጎል ተግባራትን (cortical function) ይሰራል።
ከፈተኛ የአንጎል ተግባሮች በስሩ ውስብስብ እና ውስን ጎራዎችን ይዟል። እነዚህም እንደሚከተሉት ናቸው፦
1. ትውስታ (Memory) እና ትምህርት (Learning) ጎራ፣
2. ቋንቋ (language) ጎራ
3. ትኩረት (attention) እና ግብ ትኮር ፈላጎት (orientation) ጎራ
4. መረዳት (Perception) እና ልማድ (praxis)
5. ማህበራዊ ግንዛቤ (social cognition)
6. ነገሮችን የመፈጸም አቅም (executive function) ማለትም እንደ ዕቅድ (planning)፣ አመክንዮ (logic)፣ ፍርድ (judgement)፣ አስተውሎ (insignt)፣ ስሌት (Calculation)፣ እና ረቂቅ አስተሳሰብን (abstract thinking) ይይዛል።
የግንዛቤ እክል (Cognitive impairment) ምን ማለት ነው?
የግንዛቤ እክል (Cognitive impairment) የሚፈጠረው በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ የገንዛቤ መደብ መድከም አልያም ስራ መዛባት ሲፈጠር ነው። አብዛኛው የግንዛቤ እክል ዝግመታዊ ሂደት የሚከተል ሆኖ ደረጃ በደረጃ የበሽታው መጠን የሚጨምር ሲሆን፤ ለውጡ ከጥቂት ወራት እስከ በርካታ አመታት ሊፈጅ የሚችልበት አጋጣሚ አለ። ነገር ግን ጥቂት የግንዛቤ እክሎች ፈጣን የበሽታ ምልክት የሚያሳዩ ሲሆን፣ ከሰዐታት እስከ ጥቂት ቀናት ሊከሰቱ ይችላል። ዝግመታዊም ሆነ ፈጣን የግንዛቤ እክል፣ በተጠቂዉ መደበኛ የእለት ተግባራት ለይ (የትምህርት፣ የሙያ እና የሥራ ችሎታዎች) በአሉታዊ መልክ ትጽእኖ ማምጣቱ አይቀርም።
የግንዛቤ እክል ትክክልኛ ህክምና አጠራር የ “ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር” “Neurocognitive Disorder (NCD)” ተብሎ ይጠራል። በሀገራችን ተቀራራቢ የሆነ ስያሜ ለማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በአብዛኛው ማህበረሰባችን “የመርሳት በሽታ” አልያም “አልዛይመር በሽታ” ብለው ሲጠሩት ይታያል። በርግጥ “የመርሳት በሽታ” አልያም “አልዛይመር በሽታ” የግንዛቤ እክል “ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር” ዉስጥ የሚመደቡ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እክል ከዚህ በላይ በርካታ የበሽታ ስብስብ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው።
በቀጣይ የ “ኒዉሮ-ኮግኒቲቭ ዲስኦርደር” (NCD)” 3 ዋና ዋና ክፍሎች እናቀርባለን።
@melkam_enaseb