የሁለት ሸንበቆ ትግል
በአንድ መንደር ሁለት ሸንበቆዎች ሰማይን ቀድመው ለመንካት ይፎካከራሉ ሁለቱም በየፊናቸው መንጠራራት ጀመሩ በዚህ ጊዜ ነፋስ ይመጣና ያወዛውዛቸዋል እነሱም በተቻላቸው መጠን በተናጥል የንፋሱን ሀይል አለፉት ከዛም እርስ በእርሳቸው አየህ እኔ እንዲህ ነኝ እያሉ ይኮፈሱም ጀመር በሌላ ቀን ነፋስ አቧራ እያገሳ እየገሰገሰ መጣ ያገኘውን ነገር ሁሉ አቧራ አለበሰ በዚህም እነዛ ሸንበቆዎች አጎንብሰው የእኔ አቧራ ከአንተ ይሻላል ይባባሉ ጀመር ዝናብም መጣ አጠባቸው አዲስም ፀሀይ በወጣ ጊዜ ፀሀይን የእኔ ናት የእኔ ናት ይባባሉ ጀመር በዚያን ሰአት አንድ ሰው የሚባል ፍጡር መጣና ቅጠላቸውን መልምሎ በአንድላይ አሰራቸው የረ ተወን ቢሉትም ሊሰማቸው አልፈቀደም ነበር ከቀናት በኋላም የአንጓቸው ስሮች ይገመዳሉ ላይለያዮ ይዋሀዱም ጀመር በዚህም ግዜ እኔ ከአንተ እወፍሪለው አንተ ከእኔ ትቀጥናለህ መባባል ጀመሩ ፉክክሩ በረታ ከማደግ ይልቅ በመገፋፋት ወደ ምድር ወደቁ ሰማዩም ራቃቸው ይህንን ያየ ሰው የተባለው ፍጡር አዲስ እንዲበቅሉ ቆረጣቸው ከመሬት ተኝተው ሳለ እሳት ወደ እነሱ ሲመጣ አዮ አይ ወንድሜ ያኔ በመልካሙ ቀን አብረን ፈተናችንን ተወጥተን ቢሆን ኖሮ ይህ እሳት ባልበላን አርጅተንም ወድቀንም ጥቅም በኖረን ነበር ተባባሉ ።
ማንስ ለብቻው መቆም ይችላል ማንስ ብቻውን መራመድ ይችላል ማንስ አላጠፋም ማንስ አልተፈተነም ማንስ ሰው አላስቀየመም አልበደለምንስ ማንስ ብቻውን ሁሉን አለፈ .....ትባረክም ጥጠበቅም ዘንድ እጆችህን ለምስጋና ለስጦታም ለይቅርታም እጆችህን ዘርጋ ፈጣሪም በእጥፍ ይባርክሀልና ። 🙏መልካም ቀን ይሁንላቹ🙏
ፀሎት የማይሽረው
:::::::::::::::::::::::::::::::
ሀገርማ አለኝ - ሁሉም የሚመኛት
በፍቅሯ ህይወቶች - የሚገበሩላት
ውብ ተፈጥሮዋ - መንፈስ የሚያረካ
በየትኛውም ሀገር - ፍፁም ማተለካ
አለቺኝ ሀገሬ - አለቺኝ ኢትዮጵያ
የቅርብን ሳይሆን - የሩቁን ማያ
በቅዱሱ መፃፍ - ስሟ የሚጠራ
ለተሰደዱትም - ልቧ የሚራራ
ሊያርዷት የሚመኙ - ልክ እንደ በሬ
እሷ ናት እናቴ - እሷ ናት ሀገሬ
ሚሊዮኖች አብረዋት - ቆመው ሚፀልዩ
ሺ ትርክት ቢነገር - የማይለያዩ
ትንሽ ሴጣኖች - እረፍት ቢነሷትም
ፀሎት የማይሽረው _ ችግር የላትም
#ዳዳ_coffee
@cokabu
ዘረኛ ከሆንክ የአለማችን እረካሹ ሰው አንተ ነህ .................... ♨ስትቀርበው ለራቀ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:- ውድ ነገር ያለቦታው ርካሽ ነውና፥
♨ሥታምነው ለከዳህ አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ታማኝ በመሆንህ አሸንፈሃልና፥
♨ሥትፈልገው ባጣኽው ነገር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-እሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህና፥
♨ሥትወደው ለጠላህ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ሥንት ምርጥ ሠዎች አንተን የሚወዱ አሉና፥
♨ሥላልሆነው ነገር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ገና ከዚህ በኋላ የሚሆኑ ነገሮች አሉና፥
♨አጣዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ብታጣ #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-አገኘዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ታገኘዋለህና፥
♨ያሠብከው ሳይሆን ቢቀር #አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ፈጣሪ ያላሠብከውን ይሠጥሃልና፥
♨ፍቅር ሥትሰጠው ፍቅር ለማይሠጥክ አትጨነቅ
#ምክንያቱም:-ምንአልባት ፈጣሪ ምርጥና ደሥ የሚል የፍቅር ታሪክ እየፃፈልክ ይሆናልና፥
*
#እናልክ__ወዳጄ__አትጨነቅ!!
🌻አንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ላንተ አልተፈጠረም!
🌻ፈጣሪ ላንተ የሚያሥፈልግክን ያውቃል ያሠብከውን አሥጥሎክ ያላሠብከውን ይሠጥካል!
*
=>ሥላለፈው ብዙም አታሠላሥል፣
=>ሥለ ወደፊቱም አብዝተህ አትጨነቅ፣
=>ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ፤
*
~~~አትጨነቅ~~~
ይችም ቀን ታልፍና #ድሮ ትባላለች!
ሠአቷ ታልቅና #ታሪክ ትባላለች!
ሥለዚህ አትጨነቅ #በደሥታ እለፋት!
ነገም ሌላ ቀን ነው፣ህይወትህ ተሥፋ አላት።
*።*።*።*
ፈጣሪ_ከጭንቀት_ይሠውረን
#አሜን
@melkam_sera
💦💦💦ያንቺ ወይም ያንተ እድግት💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡
•••
በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡
"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡ በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡ በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡ እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ።
•••
ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡
•••
ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡ የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡
•••
ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ ስህተት ይፈራል፡፡ ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡ እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል።
•••
የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ።
•••
@melkam_sera
🙏መልካም ቀን ይሁንላቹ🙏
💚 የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል ፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።
💛እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው።
ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።
❤️ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።🙏
ውብ ምሽት
💚💛❤️
ለሰው ልጅ ስብዐናው መሰረቱ ነው !!
@melkam_sera
♣♣♣ጊዜ የለኝም♣♣♣
ሰውየው በደነዘ መጥረቢያ የዛፉን ግንድ ለመቁረጥ ይታገላል፡፡ መጥረቢያው እየነጠረ ከመመለስ ውጪ የተፈጠረ ነገር የለም፡፡ ይህን ሁኔታ ያስተዋለ አንድ መንገደኛ ሰው ጠጋ ይልና ‘’ወንድሜ መጥረቢያው እኮ! ደንዟል አንድ ጊዜ ዐረፍ ብለህ ሳል ሳል ብታደርገው ጥሩ ነው ይለዋል፡፡’’ በደነዘ መጥረቢያ እየታገለ ያለው ምስኪን ሰው መንገደኛውን ዞር ብሎ አየውና ‘’እሱን የምስልበት ጊዜ የለኝም’’ በማለት በደነዘው መጥረቢያ መቁረጥ ሳይሆን መደብደቡን ቀጠለ፡፡
ጊዜን ለመቆጠብ የምናውለውን ጊዜ እንደባከነ ልንቆጥረው አይገባም፡፡ የሰውን ምክር መስማት ደግሞ ጊዜን ጉልበትን ወ.ዘ.ተ…..ለመቆጠብ እንደሚረዳን ማወቁ ተገቢ ነው፡፡ የሰውን ምክር አልቀበል እያልን መከራ እንዲመክረን ለምን እንጠብቃለን?
@melkam_sera
🙏መልካም ምሽት ተባረኩልኝ🙏
የሚከተሉትን 8 ፍሬ ሀሳቦች ዘወትር ልብ በል።
#1 እኔ ምርጥ ነኝ ብለህ ራስህን ንገረው።
#2 ያሰብከውን ነገር እሰራዋለሁ(አደርገዋለሁ) ብለህ እመን።
#3 ምንጊዜም ፈጣሪዬ ከእኔ ጋር ነው ብለህ ራስህን አበርታው።
#4 አሸናፊ እንደሆንክ ውስጥህን ንገረው
#5 ጠዋት ስትነሳ "ዛሬ ቀኑ የእኔ ነው" ብለህ በመልካም መንፈስ ቀንህን ጀምረው።
#6 መቼም ቢሆን ተስፋ አትቁረጥ ነገ ምን ይዞልህ እንደሚመጣ አታውቅምና።
#7 ብቻህን ስትሆን ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ።
#8 ከሰው ጋር ስትሆን ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ።
ምክንያቱም ንግግርህ እና አስተሳሰብህ ልክ እንደ ጦር መሳሪያ አደገኛ ሊሆን
ይችላል። የሌሎችን ስሜት ከመጉዳት ተቆጠብ።
ከዶክተር አብዱል ከላም
➥ⓈⒽⒶⓇⒺ
ይቀላቀሉ @melkam_sera
መልካም አዳር🙏❤👍
ጉድለትሕ ላይ ሥራ
✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️
ምንድነው ጉድለትሕ? በምን ጉዳዮች ላይ ነው አንተ አንሰሕ እንደተገኘሕ የሚሰማሕ በቅድሚያ ተረጋግተህ ተቀመጥና ጻፈው ምን ጋር ነው አንተ ጎድለሕ የተገኘኸው? አለመማርሕ ነው? አለመሥራትሕ ነው? ገንዘብ በአግባቡ አለመያዝሕ ነው? በራስ መተማመን አለመኖርሕ ነው? ምንድነው ጎዶሎነት የሚሰማሕ በተደጋጋሚ በሰዎች ፊት አላቀርብ ያለሕ? ጻፈው ዛሬውኑ ጻፈፈው ከዛ አንብበው ደጋግመሕ አንብበው ልክ ምንነቱን ስትረዳ ደግሞ አንዴት ልትሞላው እንደምትችል አስብ አስብ ግድ የለሕም መፍትሔው አንተው ውስጥ ነው ያለው መማር ካለብሕ ተማር መሥራት ካለብሕ ወጥረሕ ሥራ አመነኝ ጉለትሕ ይሞላል ግን ለማንም ስትል ሳይሆን ለራስሕ ስትል ሥራ ተደብቀሕ ከራስሕ እና ከእቅድሕ ጋር እየተነጋገርክ ሥራ ውጤትሕን አንተ ሳይሆን ሥራሕ ይናገረዎል ጀምር ተነስ አሁን ጻፈው ። @melkam_sera 🙏መልካም ቀን ይሁንላቹ🙏
ወዳጅ ሆይ ለህሊናህ እርፍት ለልብህ ደስታን ከፈለክ ሁልጊዜ መልካም
ሰው ሁን መልካምነት ለራስ ነው።
በልባችን መልካምነት ካለ እንኳን የተርፈን ያለችንን እንካፈላታለን
ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክኒያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ
አለውና።
ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና
መልካም ሰው መልካም ሂወትን ያገኛል
መልካም ወንድ መልካም ሚስትን ያገኛል
መልካም ሴት መልካም ባልን ታገኛለች
መልካም ሰው መልካም ልጆችን ያገኛል
መልካም ሰው ደስታን ያገኛል
መልካም ሰው ሰላምን ያገኛል
መልካም ሰው ፍቅርን ያውቃል
መልካም ሰው መልካም ነገርን ያገኛል
ታዲያ መልካም ሰው መሆንን የማይፈልግ ማነው።
@melkam_sera
🙏መልካም ቀን ይሁንላቹ🙏
ፍቅር ቊስል ነው
እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል።
እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።
ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው
ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።
ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር።
"ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።
አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው።
ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።
ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ
"እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው።
እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
ጸሐፊ: Fr Haralambos Libyos Papadopoulos
ተርጓሚ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 10 2011 ዓ ም
አዲስ አበባ
@melkam_sera
ደግ ደጉን እናስብ 🙏🙏🙏
natnim Film:
natnim Film:
#የቡናዊያን_የዘር_ሃረግ
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች ዘንድ ብዙ አስገራሚ የበጎ አድራጎት ስራዎች እና ኮረና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ ቅድመ ጥንቃቄ ግንዛቤ ማስጨበጫዎች እና ድጋፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
አንድ ሃሳብ መጣልን እስኪ #የቡናዊያን_የዘር_ሃረግ ቤተሰቦችን አስተባብረን ደግሞ በተለያየ አካባቢ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን ለ 50 ቤተሰቦች የሚሆን የ 1 ወር ቀለብ እንስጥ የሚል! ሃሳባችንን የምትደግፉ እኔ የአንድ ቤተሰብ ወይም ከዚያም በላይ እችላለሁ የምትሉ እስኪ መልክታችሁን ከታች አስቀምጡልን።
ሁላችሁም ተጋብዛችሁዋል ተሳተፉበት ማገዝ ግዴታ በገንዘብ ብቻ አይደለምና ሐሳባችሁንም ስጡበት!
.
ለተሳትፏችሁ እና ድጋፋችሁ በቅድሚያ እናመሰግናለን 🙏
👉 6 ፓስታ
👉 5 ኪሎ በሶ
👉 5 ኪሎ አሩዝ
👉 5ኪሎ መኮረኒ
👉 5ሊትር ዘይት
👉 1 ኪሎ ስኳር
👉 5 ኪሎ ሽንኩርት
👉 የንፅህና መጠበቂያ
በጠቅላላ 1100 የአንድ ቤተሰብ የሚፈጀው
👉 #1 እኛ ለኛ አሰተባባሪዎች የአንድ ቤተሰብ አስረክቦናል
👉 #2 ሰሞዲን ሀበሻ የአንድ ቤተሰብ አስረክቦናል
👉 #3 የሀንስ ክፍሌ የአንድ ቤተሰብ
አስረክቦናል
👉 #4 የቡናዊያን ዘር ሀረግ የአንድ ቤተሰብ
አስረክቦናል
👉 #5 እስክንድር ጌታቸው የአንድ ቤተሰብ
አስረክቦናል
👉 #6 ኤደን ክፍሌ የአንድ ቤተሰብ
አስረክባናለች
👉 #7 ብዙአለም ክፍሌ የአንድ ቤተሰብ
አስረክቦናል
👉 #8 ታዴ 16 ፊልም ፕሮዳክሽን የአንድ ቤተሰብ አስረክቦናል
👉 #9 ሀና የአንድ ቤተሰብ
አስረክባናለች
👉 #10......
👉 #አስተባባሪዎች
👉 የቡናዊያን ዘር ሀረግ ..0936685020
👉 #ጌች ......0911126719
👉 #ኤላ .......0913991700
👉 #ኤዱካ ....0915992756
👉 #ማሂ.....0911926384
👉 #ካሌብ....0909781167
ስብዕናችን #Humanity:
ውህደት እና ርቀት
×××××××××××
በዚህ ሰአት ከያለንበት የአስተሳሰብ ርቀት ሰብስቦ አንድ ያረገን ይህ ወቅት ነው..ይህ በሽታ ነው።
እንደ ሰው ሰው ሆነን ከክልል እና ከብሔር ቁርጥራጭ አስተሳሰብ ተላቀን ቢያንስ በሃሳብ አንድ ወደሚያደርገን መንገድ በበሽታው ሰበብ መጥተናል። እንዲህ ሆነ ብለን ደስ ብሎን ሳናበቃ በሽታው ደግሞ ሌላ ልዩነት እና ርቀት የሚፈልግ ሆኖ ቁጭ አለው....አካላዊ ርቀት። ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል እንዲሉ አበው በአካል ስንራራቅ ከልብም ተራርቀን ብንቀርስ? እንጃ ብቻ ላለመሞት ይህንኑ ትዕዛዝ እንተገብራለን።
።።።።።
ሌላው ይሄ ያሁኑ ሁኔታ ፍሪጅ ውስጥ የተቀመጠን ስጋ አስተኔ ነገር ነው የሚመስለኝ። ለምሳሌ አንድ የተቆራረጠ ወይንም የተዘለዘለ ስጋ በስሃን ነገር ፍሪጅ ውስጥ በረዶ ቤት ውስጥ ቢቀመጥ (ይቅርታ ግን በፆም ወቅት ካልጠፋ ምሳሌ ይህንን በመጠቀሜ) ያ ስጋ ተጣብቆ ድርቅ ብሎ አለቅጥ ተጠጋግቶ ይገግራል። በእርግጥ ስጋው የአንድ በሬ ስጋ ነው ወትሮም ቆራርጠነው እንጅ...ፍሪጅ ውስጥ ሲሆን ግን መልሶ በቅዝቃዜው ምክንያት ፣ በተቀመጠበት አየር ንብረት አለያም ንፍቀ ክበብ ምክንያት አንድ ውህድ ቁስ አካል ይሆናል። ይሄ ፍሪጅ ውስጥ የነበረ ስጋ ከፍሪጁ ሲያስወጡት በተለይም ደግሞ ወደ እሳት ነገር ሲያስጠጉት ...ውህደቱ ይፈርሳል ፣ የጠጠረው ይፈረካከሳል ፣ አንድነቱ ይበታተናል ከዚያም ለባለቤቱ በቀላሉ ተበይ ይሆናል....መለያየት እና መፈረካከስ ለበዮቻችን ያመቻልና።
።።።እኛም ዛሬ አሁን የምንገኝበት የአየር ንብረት ፣ አሁን የምንገኝበት ንፍቀ ክበብ ልክ የአንድን በሬ ስጋ ዘልዝለው ፍሪጅ ውስጥ እንዳስቀመጡት ሁሉ እንዲሁ የአንዲት ኢትዮጵያን ህዝቦች ሰብስቦ ፣ በብዙ ቁርጥራጭ አመለካከት የተከፋፈለ የነበረን ህዝብ ሰብስቦ በዚህ አሁን ባለንበት ከፍሪጁ በባሰ በፍርሃት በሚያንዘረዝር በሽታ ውስጥ አስቀመጠን....አሁን ቢያንስ እንደ ሃገር አንድ ላይ ውህድ ነገር መስለናል....ምናልባት ጥሩ ቀን መጥቶ ፣ ቀን አልፎ ከፍሪጁ ስንወጣ ሌላ ብራ ቀን ፣ ሌላ ሙቀት ሲነካን ልክ እንደ ስጋው እንፈረካከስ እንለያይ ይሆን? እንጃ።
ለማንኛውም ርቀታችሁን ጠብቁ ...እጃችሁን ታጠቡ።
@melkam_sera
[በጎነትን በጋራ እናቀንቅን]
✨ጠቃሚ የህይወት መርሆዎች✨
🌷ደግ ሁን🌷
የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን አትናገር፡፡ ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ሳትሰስት ለሌሎች አካፍለህ ኑር፡፡ "መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!"
💐ቀና ብለህ ተጓዝ💐
ዘወትር ቀና ብለህ ተጓዝ ምክንያቱም ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅምና፡፡
🌸ችግሮችህን አስብ🌸
የገጠሙህን ችግሮች ችላ አትበላቸው ምክንያቱም ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለምና፡፡
🍂እውቀትን የምትሻ ሁን🍂
ከሌሎች ሰዎች ለማወቅ የተዘጋጀህ ሁን ምክንያቱም የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነውና፡፡
⚜መልካም አሳቢ ሁን፡፡⚜
ሁሉም ሰው ራሱን የሚያገኘው በየእለቱ በሚፈጥረው አስተሳሰብ መሠረት ነው፡፡
መጥፎ ቀን የምንለው መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው፡፡ ስለሆነም ሁሌም መልካም ነገር እንዲገጥምህ መልካም የሆነውን ብቻ ተመልከት፡፡
🍁የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት፡፡🍁
የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት ምክንያቱም ምድር ላይ እጅግ የሚያሳፍረው ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት ነውና፡፡
🌴ለገባኸው ቃል ታመን🌴
ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁን፡፡
🌹ራስህን አሻሽል🌹🌹
"የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል"
🌱መጀመሪያ ራስህን እወቅ🌱
ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ በድክመትህ ላይ ፈጥነህ ዝመትባቸው፡፡
🌺ህሊናህን አድምጥ🌺
የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር፡፡ ሁሌም ለሕሊናህ እንጂ ለሰው አትገዛ ምክንያቱም የሰው ልጅ ዛሬ ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ነገ ሊሸሽህ ይችላል ህሊናህ ግን በፀፀት እየወቀሰህ ዘወትር አብሮህ ይኖራልና፡፡
☘አንደበተ ርቱህ ሁን☘
"ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም" ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል፡፡
💡ብልህ ሁን💡
መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት ነው፡፡ ምክንያቱም ምድር ላይ ስትኖር ለመኖር መፈተን ለማለፍ መታገስ ግድ ነውና፡፡
🌿ሁልጊዜ ራስህን ሁን🌿
ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው፡፡ ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር ማንነትህን ታጣና ህይወት ጣእሟን ታጣለች፡፡
🌸ሞራል ይኑርህ🌸
የማይዋዥቅ የህይወት ሞራል ይኑርህ ምክንያቱም ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነውና፡፡
🍃ባለህ ነገር ተደሰት🍃
ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር ይሳንሃል፡፡ ስላለህ ነገር እንጂ ስለሌለህ ነገር አታስብ ምክንያቱም ነገ የፈጣሪህ ነውና፡፡
☘እውነታን ተቀበል☘
ተፈጥሮ የቸረችህን ማንነትህን አምነህ መቀበልን ትተህ ለማማረር ወይም ለመሸማቀቅ አትሞክር ምክንያቱም በተሰጠህ ተፈጥሮሯዊ ማንነትህ ላይ ያንተ ሚና የለበትምና፡፡ በማይለወጥ አንተነትህ ተደሰት ምክንያቱም ቁርጡን ያወቀ ሰው ምርጫ ይኖረዋልና፡፡
መልካም ቀን፡፡
🍃🍃Join and share🍃🍃 @melkam_sera
በድሮ ጊዜ አንድ እንዲህ አይነት ሰዉ ነበር። ፈጣሪውን የሚፈራ፣ ለሌሎች ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ታላቁንም ሆነ ታናሹን ሰው የሚያከብር፣ እንግዳ የሚወድ፣ ለቃሉ የታመነ፣ በጓደኝነቱ የፀና፣ ለትዳሩ ፍፁም የታመነ፣ በስራው የማይቀልድ፣ በፈጣሪ ስም ለጠየቀዉ ሁሉ ነፍሱን የሚሰጥ፣ ዉሸትን አምርሮ የሚጠላ፣ ሳቁ የማይሰማና ስነስርአት ያለዉ ሰዉ ነበር። ይህንንም ሰው መልካምና ተወዳጅ ይሉት ነበር።
ዛሬ ላይ እንዲህ አይነት ሰው ካለ እንደሞኝ ይቆጠራል። ፊት ለፊታቸዉ ከሆንክ ደግሞ "በጣም መልካም ሰውኮ ነህ!" ይሉሃል። በልባቸው ግን "አምላኬ እንዲህ ከመሆን ሰዉረኝ!" እያሉ ነው። "ኖርማል" ሰዉ መሆን አሰልቺ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ግን ኖህ ብቻዉን ነበር። ሎጥ ብቻዉን ነበር። ዳንኤል ብቻዉን ነበር። የቀኙ ወንበዴም ብቻዉን ነበር። ሰዎች አፈር ነክቶታል ስላሉህ ወርቅህን ትጥላለህ?
መልካምነትህን አትጣዉ!
@melkam_sera. [በጎነትን በጋራ እናቀንቅን]
ሰው እንዲ ሲገደል ፤ ሰው እንዲህ ሲቀበር
አያሳዝንም ወይ ፤ ባዳ ሲሆን በሀገር
✍️DaDa
💚ክብሩን💛በብሄር❤️አታሳንሱ😭
@cokabu
#ዳዳ_coffee
@ilovegitem
ነህ ከተባልክ ..... በቃ ነህ!!
«ዘውድአለም ታደሰ»
መፅሃፍ ቅዱስ ሳነብ ከሚያስገርሙኝ ሰዎች መሃከል አንዱ ሐዋርያው
ጴጥሮስ ነው። ብዙዎቻችን ጴጥሮስ ሲባል የሚመጣልን ክህደቱ እንጂ
ሐዋርያቱ ሁሉ ኢየሱስን ጥለው ሲጠፉ ብቻውን በድፍረት እንደተከተለው
አይደለም። ብዙዎቻችን በባህር ላይ ሲራመድ መስጠሙን እንጂ ሐዋርያቱ
ሁሉ ጎመን በጤና ብለው ጀልባዋ ላይ መቆየትን ሲመርጡ እሱ ግን ጌታውን
አምኖ ጥቂትም ቢሆን በእምነት ውሃው ላይ መራመዱን አናስብም።
ወዳጄ ..... ሰው እንዲሁ ነው። ከተራራው ላይ መንሸራተትህን እንጂ ተራራው
ጫፍ ላይ ለመድረስ የከፈልከውን መስዋእትነት አያይም።
ኢየሱስ ግን መች እንደሰው ያያል? የሆነ ቀን “ስምኦን” አለው። "አቤት" አለ
ስምኦን ፈጠን ብሎ።
«ከእንግዲህ ስምህ ጴጥሮስ ይባላል» አለው።
ጴጥሮስ የቀድሞ ስሙ ስምኦን ነበር። የሚንሸዋሸው ቅጠል እንደማለት ነው።
(አንዳንድ ወላጅኮ ለልጁ ስም ሲያወጣ ይጨክናል )
አዲስ የወጣለት ስም ደግሞ "አለት" ማለት ነው። “ከሚንሸዋሸው ቅጠል”
ወደ “አለት” መንፈሳዊ ትራንስፎርሜሽን ይልሃል ይሄ ነው። ሃሃ
ብራዘር .... ኑሮህን በፀጥታ ኑር እንጂ ከየምኩራቡ ስም ለመሸመት አትጋፋ።
አንድዬ አይን ውስጥ የገባህ ቀን አሮጌው ስምህ ተሰርዞ አዲስ ስም
ይወጣልሃል። እግዜሩ ደግሞ ነህ ካለህ በቃ ነህ! ነፋስ በነፈሰ ቁጥር
እነደቅጠል የሚረግፈው ማንነትህ ከስምህ ጋር ተቀይሮ ወጀብና አውሎነፋስ
የማያናውጠው ፅኑእ አለት ይወጣሃል! ነህ ካለህ ነህ በቃ!
ጌዲዮን በፍርሃት ተውጦ የወይን መጥመቂያ ውስጥ እህል ሲወቃ መልአኩ
ድንገት ከች ብሎ ምን ሰማያት
«አንተ ፅኑ ሃያል ሰው!!»
ጌዲዮን ዙሪያውን ቃኘት አርጎ «እኔን ነው?» ያለ ይመስለኛል ሃሃ እግዜሩ
እንዲህ ነዋ የወይን መጥመቂያ ውስጥ እህል ሚወቃ ፈሪን ከሰማየ ሰማያት
ይመለከትና «አንተ ፅኑ ሃያል ሰው!» ብሎ ይጠራል! በዚያ ፈሪና ደካማ ሰው
ውስጥ ራሱን አስገብቶ ነዋ ሚያየው! የመጨረሻ የአለም ደካማ ሰውኮ
ከእግዜሩ ጋር ከተደመረ ፅኑና ሃያል ነው! ትንሹ ዳዊት ከእግዜር ካር ሲደመር
ጎልያድን ከፊት መትቶ ወደፊት ጥሎታል ሃሃ ኢያሱ ከግዜር ጋር ሆኖ ፀሃይን
እንደትራፊክ ገባኦን ላይ አቁሟታል! ወዘተ ...
ብራዘር እግዜር ሲሰይምህ ክንዱን ተማምኖ ነው ! ሃያል ካለህ ሃያል ነህ! ፅኑ
ካለህ ፅኑ ነህ! ሊስትሮ ሆነህ አንዱ ጫማ ስር ከተወሸቅክበት ድንገት «አንተ
ሃያል ንጉስ» የሚል ስም ሊወጣልህ ይችላል! ህልሙና ፊልሙ ተቀላቅሎብህ
ግራ ገብቶህ ስትጨናነቅ «አንተ የመፍትሄ ሰው» የሚል ስም ሊወጣልህ
ይችላል! እግዜሩ ስም ያውጣልህ አቦ! ነህ ካለህ ነሃ!
@melkam_sera
♨ ትልቁ ጀግንነት ➖➖➖ #ትእግስት
♨ትልቁ ስልጣን ➖➖➖ እራስን መግዛት
♨ትልቁ ስብእና ➖➖➖ #መልካምነት
♨ትልቁ ማንነት➖➖➖ ታማኝነት
♨ትልቁ ድህነት ➖➖➖ #እውቀት ማጣት
♨ትልቁ ድክመት ➖➖➖ለገንዘብ መገዛት
♨ትልቁ ስልጣኔ ➖➖➖#መረዳዳት
👉 ትልቁ በሽታ ➖➖➖ ሁሉንም አውቃለሁ
👉 ትልቁ ስጦታ ➖➖➖ #ፍቅር
👉 ትልቁ ሀብት ➖➖➖እምነት
👉 ትልቁ ጭንቀት ➖➖➖#ምን__ይሉኛል
@melkam_sera
ከአስተሳሰብህ ከተጣመምክ በስራህ ቀጥ ማለት አትችልም!
ቀናነት ቀና ያለ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ቅንነት በተንኮል ያልታጠፈ፣ በምቀኝነት ያልተቆለመመ፣ በራስወዳድነት ያልተንጋደደ ሃሳብና ምግባር ነው፡፡ የተንጋደደ ማንነት ቀጥ ያለ ሰውነትን አያስገኝም፡፡ ገዳዳ አስተሳሰብ ሕይወትን ያንጋድዳል፡፡ አንዴ ከአስተሳሰብህ ከተጣመምክ በስራህ መቼም ቢሆን ቀጥም ቀናም አትልም፡፡ የጎበጠ ማንነት፣ አንገት የደፋ ሕሊና ቀጥ ብሎ መቆም አይችልም፡፡ በሌሎች የሚዘወር ጭንቅላት የራሱ መሪ የለውም፡፡ በትንሹ ተፈትኖ የወደቅ በትልቁ ሊታመን አይችልም፡፡ ሲያስብ የተሳሳተ ምግባሩም ሆነ ተግባሩ የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው የዘራውን ያንኑ ነውና የሚያጭደው!
ታላቁ የጥበብ ሰው ሩሚ፡-
‹‹የመበላሸትን ወይም የመበከልን ተፈጥሮ ተረዳ፡፡ አንዴ ቁልፍህ ከተጣመመ ወይም ከታጠፈ መቼም ቢሆን ቁልፍህ አይከፍትም፡፡›› ይላል፡፡
እውነት ነው! ራስህን መረዳት ስትጀምር አካሄድህን ታጤናለህ፣ አስተሳሰብህን ትገመግማለህ፣ የምትከተለውን ትመረምራለህ፤ ከፊትህ ያለውን በደንብ ማየት ትጀምራለህ፡፡ መሪህን ትመነጥራለህ፣ ዓላማህን ቀስ ብለህ ትሾፈዋለህ፤ ግብህን ታልማለህ፡፡ መድረሻህን ገና መንገድ ሳትጀምር ወጪና ኪሳራውን ቀድመህ ታሰላዋለህ፡፡፡፡ እየተራመድክበት ያለው “የሕይወት መንገድ አዳላጭ ነው፤ ወይስ ወስዶ ወስዶ ከገደል አፋፍ የሚያደርስ ነው” የሚለውን ለማወቅ አንተነትህን፣ መንገድህንና ዓላማህን መረዳት ይጠበቅብሃል፡፡ የመንገድህን መበላሸት፣ የዓየርህን መበከል፣ የአካሄድህ ግራገብነትን የምትረዳው ራስህንና ዓለሙን ስትረዳ ነው፡፡ የመበላሸት ተፈጥሮን ማወቅ ራስን ከብልሽት ማዳን ነው፡፡ የመኪና መነፋነፍ የብልሽት ምልክት ነው፡፡ የአስተሳሰብ መዛነፍም ውድቀትን ጠቋሚ ነው፡፡ ከብልሽቱ ዓለም ለመውጣት አስተሳሰብን መጠገን ግድ ይላል፡፡ ሊሰምጥ ጫፍ የደረሰ ሰውነትን መታደግ ከምንም በላይ አኩሪና አርኪ ነው፡፡ በሃሳብ ባህር ቀዝፎ፤ በህይወት ውቅያኖስ ተንሳፎ፣ በቀና አስተሳሰቡ ታንኳ የሕይወት ወጀቡንና የኑሮ ሞገዱን የሚያልፍ እሱ በአስተሳሰቡ የጠነከረ፤ ከኑሮው ልምድ የቀሰመ ነው፡፡
ከራሱ ጋር የመነጋገር ልምድን ያዳበረ ጠማማ አስተሳሰቡን ተረድቶ ወደቀናው አስተሳሰብ ይሸጋገራል፡፡ ከራስህ ጋር ለመወቃቀስ ከራስህ ጋር መግባባት ይኖርብሃል፡፡ ወቀሳን የሚቀበል ጭንቅላት ካልፈጠርክ የራስህ ከሳሽ ራስህ ትሆናል፡፡ ከወቀሳ ይልቅ ክስ ውጤቱ ጥሩ አይደለም፡፡ ክስ በመጨረሻ ፍርድ አለው፡፡ ወቀሳ ግን ለራስህ ይቅርታ እንድታደርግለት ነጭ ነጩን ነግሮ ምክር ይለግስሃል፡፡ ወቃሹም ተወቃሹም ራስ ለራስ ነው፡፡
የሚዛናዊነት፣ የአስተዋይነትና የብልህነት ቁልፍ ከታጠፈ ደግ ነገር ሁሉ ላይከፈት ተቆልፎ ይኖራል፡፡ ልብ ከተከረቸመ ቀናነትም ይጠረቀምበታል፡፡ አዕምሮ ከተዘጋ መልካም አስተሳሰብም የተዘጋ ይሆናል፡፡ ሕሊና በምክንያት መውደድና መጥላት ካልቻለ እንደጋሪ ፈረስ በማንም ደመነፍስ ይሾፈራል፡፡ ቁልፍ የሌለው ቤት ለሌባ እንደሚመች ሁሉ ቁልፍ አስተሳሰብ የጎደለውም የማንም ግብስብስ ሃሳብ መጫወጫ ይሆናል፡፡
የሕይወት ጋኑን የሚከፍት ቁልፍ ቅን አስተሳሰብና ምክንያታዊነት ብቻ ነው፡፡ ጋኑ አዕምሮ ነው፤ ቁልፉም አስተሳሰብን ይወክላል፡፡ ብዙ ተመሳስለው የሚሠሩ ቁልፎች ወይም ሃሳቦች አሉ፡፡ የቁልፉን ጋን የሚከፍተው ግን አንዱ ቁልፍ ብቻ ነው፡፡ ያ ቁልፍ የሕይወትህን መስመር፣ የአንተነትህን ጎዳና በርግዶ የሚከፍት ነው፡፡ አዎ ቁልፉ ስሪቱ ከአመለካከትህ ነው፡፡ ጥሬ ዕቃው የበሰለ ሃሳብህ ነው፡፡ በቀላሉ በማንም የማይከፈት ቁልፍ ለማድረግ ግን ማስተር ቁልፍ ያስፈልግሃል፡፡ ስትፈልግ የምትከረችመው፤ ሲያሻህ የምትበረግደው፡፡ የአዕምሮህን ቁልፍ በቀላል ሃሳብ ካዋቀርከው የማንም ተመሳሳይ የሃሳብ ቁልፍ ይከፋፍትብሃል፡፡ አንተ የእኔ የምትለው ሃሳብ ስለሌለህ የሌሎች ሃሳብ መኖሪያና መፈንጫ ትሆናለህ፡፡ በራስህ ሃሳብ እንዳትራመድ አንቆ ይይዝሃል፡፡
ብዙዎቻችን የተቸገርንበት ጉዳይ ይሄ ይመስለኛል፡፡ የአዕምሯችንን ቁልፍ ለምናደንቃቸው፣ ለምንወዳቸው፣ ከአኛ በላይ ያውቃሉ ለምንላቸውና በግል ለምናከብራቸው ሰዎች ስላስረከብን እነሱ ሲወድቁ እኛም እንወድቃለን፣ በአመለካከታቸው ሲፍገመገሙ እኛም እንፍገመገማለን፡፡ በክፉ ሃሳባቸው ምክንያት የሃሳብ ጢሻ፣ የሃጢዓት ገደል ውስጥ ሲገቡ እኛም ገደል እንገባለን፡፡ ሲፎክሩ እንፎክራለን፣ ጃስ ሲሉን እንናከሳለን፤ ያዘው ሲሉን እናሯሩጣለን፤ በለው - ቁረጠው ሲሉን እጃችን ለመሰብሰብና አንድ ጊዜ እንኳን ለማሰብ ጊዜ የለንም፡፡ አድርጉ የተባለውን ነገር ለማድረግ አናቅማማም፡፡ ከአመክንዮ ጋር ተጋጭተን ስለምንኖር ለምን እንዴት ብለን አንጠይቅም፡፡ ለራሳችን ሃሳብ ፍሬን አላዘጋጀንለትም፡፡ ለአስተሳሰባችን ቁልፍ የለንም፡፡ ሕይወታችን የሚሽከረከረው በሌላ ነው፡፡ ፍሬኑ እንደተበጠሰ መኪና ወደፊት መብረር እንጂ የዓለምን አራቱንም አቅጣጫ አይተንና አስበን አንሄድም፤ተረጋግተን የሕይወትን መንታ መንገድና መሰናክል አንሻገርም፡፡
ወዳጄ ሆይ… የአንተነትህ ምስል የአስተሳሰብህ ስዕል ነው፡፡ እይታህ የሚወለደው ከአመለካከትህ ነው፡፡ ምግባርህና ማንነትህ የሚታወቀው በስራህ ነው፡፡ ስራህ ደግሞ ተምጦ የሚወለደው ከሃሳብህ ነው፡፡ ሃሳብህ ከተበላሸ፣ የዘራኸው ከመከነ ፍሬህ አይጎመራም፡፡
አዎ! የትዕግስትህ ቁልፍ የደስታህን በር ይከፍታል፡፡ የታጠፈ ወይም የተጣመመ የአስተሳሰብ ቁልፍህ ግን የሕይወት ጋንህን፣ የአዕምሮህን ካዝና መክፈት አይችልም፡፡ የሕይወት ቁልፍህን ቀጥ አድርገህ ትሰራ ዘንድ አስተሳሰብህን አቅና፡፡ የቀና አስተሳሰብ የአዕምሮውን በር ወለል አድርጎ ይከፍታልና፡፡
ቅንነት ለሁሉ የተከፈተ ማንነት ነው፡፡ የደግነት የትየለሌ ትርፉ ደግ ከዋልንለት የበለጠ ለራስ ነው፡፡
ቸር ቅንነት! ቸር መጣመም የሌለበት ማንነት!
@melkam_sera. 🙏መልካም ቀን ይሁንላቹ🙏
😭ህይወት😭
“ሌሎችን ዋጋ አናስከፍል”
በትልቅ ሞል ውስጥ ካለ በአንዱ ሱቅ እየተዘዋወርኩ ነበር ፡፡ የሱቁ ገንዘብ ተቀባይ ከአንድ ትንሽ ልጅ ጋር ሲከራከሩ አየሁ ፡፡ ልጁ 5 ወይም 6 ዓመት ቢሆን ነው ፡፡ ገንዘብ ተቀባዩ “አዝናለሁ ፣ ይህን አሻንጉሊት ለመግዛት በቂ ገንዘብ የለህም” አለ ፡፡ ከዛ ትንሹ ልጅ ወደ እኔ ዞሮ “አባባ ፣ እባክህ የያዝኩት ገንዘብ በቂ ሰልመሆኑ እይና እስኪ ለገንዘብ ተቀባዩ ንገርልኝ” ሲል ጠየቀኝ ፡፡
የእርሱን ገንዘብ ቆጥሬ ስጨርስ መለሰልኩለትና “የኔ ልጅ አሻንጉሊቱን ለመግዛት በቂ የሆነ ገንዘብ የለህም” አልኩት ፡፡ ትንሹ ልጅ አሁንም አሻንጉሊቱን በእጁ ይዞ ነበር ፡፡ ይህን አሻንጉሊት ለማን ገዝቶ ሊሰጥ እንደሚፈልግ ጠየቅሁት ፡፡
“እህቴ በጣም የምትወደው እና በጣም የምትፈልጋት አሻንጉሊት ናት። ለልደት ቀኗ በስጦታ ላበረክትላት ነው ፡፡ ስጦታዮን በእናቴ በኩል ለመላክ ፈልጌ ነበር ፡፡ እናቴ እንድተሰጣት ፈልጌ …” ይህን እያለ ዓይኖቹን ቅዝዝ አድርጎ በጣም አዘነ ፡፡
“እህቴ ከእግዚአብሄር ጋር ለመሆን ሄዳለች ፡፡ አባባ እማማም በጣም በቅርቡ ወደ እግዚአብሔር ትሄዳለች ብሎኛል ፡፡ አሻንጉሊቱን ይዛ ለእህቴ ልትወስድልኝ ትችላለች ብዬ አስቤ ነበር ፡፡”
የህፃኑ ልጅ ታሪክ የልቤን ምት ቀየረው ፡፡ ትንሹ ልጅ ቀና ብሎ አየኝና “ለአባቴ ፤ እማዬ ስጦታውን ሳልሰጣት እንዳትሄድ አደራ ብየው ነው ስሮጥ እዚ የመጣሁት ፡፡ ከገበያ ማዕከሉ እስክመለስ ድረስ እንድትጠብቅኝ እፈልጋለሁ ፡፡ ”
ከዛም ከኪሱ ውስጥ መላው ቤተሰብ ደስ በሚል ሳቅና ፈገግታ የተነሱትን ፎቶ አውጥቶ አሳየኝ ፡፡ “እህቴ እንዳትረሳኝ ፣ እናቴ ይህን ፎቶግራፍ አብራ ይዛ እንደትሄድ እፈልጋለሁ ፡፡ እናቴን በጣም እወዳታለሁ እና ጥላኝ እንዳትሆድ እመኛለሁ ፣ ግን አባዬ ከታናሽ እህቴ ጋር ለመሆን መሄድ አለባት ብሎኛል ፡፡ እኔ ከአባዬ ጋር እሆናለው ፡፡ ”
ከዚያ አሻንጉሊቱን በአሳዛኝ ዓይኖች እንደገና ተመለከተ ፡፡ በተስፋ መቁረጥና ሃዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ ነበር የሚያየው ፡፡ በፍጥነት ከኪስ ቦርሳዬ ውስጥ ልጁ ሳያየኝ ገንዘብ አወጣውና
“ለምን እንደገና አንቆጥረውም? ምናልባት እኮ የያዝከው ገንዘብ አሻንጉሊቱን ለመግዛት በቂ ለሆን ይችል ይሆናል” አልኩት
እሱም “እሺ ፣ በቂ ገንዘብ እንደሚኖረኝ ተስፋ አደርጋለሁ” አለ ፡፡ ከዛም ሳያየኝ በእጄ የያዝኩትን ገንዘብ በእሱ ገንዘብ ላይ አክዬው ፣ እንደገና መቁጠር ጀመርን ፡፡ ለአሻንጉሊት መግዣ የሚሆንና በቂ ገንዘብ እና የተወሰነ ትርፍ ገንዘብ ሆኖ ተገኘ ፡፡
በትንሹ ልጅ ፊት ላይ የደስታ ነፀብራቅ ወጣች “በቂ ገንዘብ ስለሰጠኸኝ አምላኬ ሆይ አመሰግንሃለሁ!” አለ ፡፡ ከዛም እኔን ተመለከተኝና “ትላንትና ማታ ከመተኛቴ በፊት አምላኬን ለእህቴ አሻንጉሊት መግዣ የሚሆን ገንዘብ እንዲሰጠኝ ጠይቄው ነበር የተኛሁት ፤ ይህው ፀሎቴን ሰማኝ፡፡ አሁን ገንዘብ ተቀባዬ ይጎላል ሲለኝ እንዴት ሊሆን ቻለ ብዬ ገርሞኝ ነበር ፡፡ ለእናቴ ነጭ ጽጌረዳ ለመግዛት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት እፈልግ ነበር ፣ ግን አምላኬን ብዙ ለማስቸገር አልደፈርኩም ነበርና ተውኩት ፡፡ ነገር ግን ይህው አሻንጉሊት እና ነጭ ጽጌረዳ እንድገዛ በቂ ገንዘብ ሰጠኝ ፡፡ እናቴ ነጭ ጽጌረዳዎችን ትወዳለች ፡፡ ” ብሎኝ በተረፈው ገንዘብ ነጭ ፅጌረዳ ገዝቶ በፍጥነት ከሱቆ ወጥቶ ሄደ ፡፡
እኔም ገበያዬን ቶሎ ጨረስኩ ፡፡ ትንሹን ልጅ ግን ከአእምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም ፡፡ ከዛም ከሁለት ቀናት በፊት የወጣ ጋዜጣ ላይ የነበረው ዜና ትዝ አለኝ ፡፡ አንድ ሰካራም የከባድ መኪና ሹፌር በትንሽ መኪና ውስጥ የነበሩትን እናትና ትንሽ ሴት ልጅ መገጨቱን መዘገቡን አስታወስኩኝ ፡፡ ትንሿ ልጅ ወዲያውኑ ስትሞት እናትየው በአስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ያትታል ፡፡
እናት ከኮማ ውስጥ መውጣትና ማገገም ስለማትችል ቤተሰቡ የህይወት ማቆያ ማሽን እንዲነቀል መወሰን ነበረባቸው ፡፡ ይህ የትንሹ ልጅ ቤተሰብ ይሆን? ብዬ እንደጠይቅ አደረገኝ ፡፡
ከትንሹ ልጅ ጋር ከተገናኘሁ ከሁለት ቀናት በኋላ ወጣቷ እናት የማረፏን ዜና ከጋዜጣው ላይ አነበብኩ ፡፡ ሃዘን ተሰማኝ በተለይ ያንን ሱቅ ውስጥ ያገኘሁትን ልጅ ሳስብ ፡፡ ቀብር መሄድ እንዳለብኝ አምኜ ብዙ ነጭ ጽጌረዳዎችን ገዝቼ ጋዜጣው ላይ በተፃፈው አድራሻ እየተመራው ወደ ቤታቸውን ሄድኩኝ ፡፡ ከቀብርዋ በፊት ሰዎች እሬሳውን ይሰናበቱ ዘንድ ሳጥኑ በግማሽ ክፍት ነበር ፡፡ የወጣቷን ሴት አስከሬን በቅርበት አየሁት ፡፡ በሬሳ ሣጥኑ ውስጥ ፣ ትንሹ ልጅ ያሳየኝ ፎቶ እና አሻንጉሊት ደረቷ አካባቢ ተቀምጠዋል ፡፡ በእጇ ደግሞ ነጭ አበባ ይዛለች ፡፡ በህይወቴ እንደዚህ ሃዘን ተሰምቶኝ አያውቀም ፡፡ በእንባ እንደተሞላው ቦታውን ለቅቄ ወጣሁ…
ትንሹ ልጅ ለእናቱ እና ለእህቱ የነበረው ፍቅር እስከ ዛሬ ድረስ ከአይምሮዬ አልጠፋም ፡፡ እና በአንድ ሰከንድ ስህተት አንድ ሰካራም ሾፌር ከልጁ ብዙ ነገር ወስዶታል…
_________
እኛ በምንሰራቸው ስህተቶች ሌሎች እንዲከፍሉ አናድርግ ። አኛ የሰራናት ትንሽ ስህተት ሌሎችን በብዙ ልታስከፍል ትችላለች እና ሁሌም ስለሎችም እናስብ ፡፡ ሁል ጊዜ የእርዳታ እጅ ይኑርዎት እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እና ለሐዘንተኞች እርዳታዎን አይንፈጉ ።
🙏መልካም ቀን🙏
😭😭😭😭😭😭
@melkam_sera
ምንም ነገር የሚያስፈራህ እስክትጀምረው ነው!!
ድፍረት ወደ ስኬት ለመጓዝ የምታደርገውን ርምጃ ማስጀመሪያ ሞተር ነው!!
አላማህን ስትጀምር መጨረሻው ሊሳካም ላይሳካም ይችላል። አንተ ግን ትኩረትህን ይሳካል የሚለው ላይ አድርግ።
መጀመሪያ በእጅህ ላይ ያሉ ነገሮችን ሳትጠቀምባቸው ሩቅ ያሉ ነገሮችን ለማምጣት አትድከም።
በሌሎች ስኬት ተደሰት። አድንቃቸው። አበረታታቸው። አንድ ቀን ያንተም ተራ ሊደርስ ይችላል።
አትችልም አይሆንልህም ሚሉህ ቦታ አትስጥ። ትችላለህ በርታ የሚሉህን እና ከጎንህ ሁነው የሚያግዙህን አድናቆት እና ክብር ስጣቸው።
የማራቶን ሩጫን ብዙዎች ይጀምራሉ። ብዙዎች መሀከል ላይ ይቆማሉ። ብዙዎች በመሃል አቋርጠው ይወጣሉ። የተወሰኑት እየወደቁ እየተነሱ ሩጫውን ይጨርሱታል። ጥቂት እና ጠንካሮች የጀመሩትን በብርታት እና በጥንካሬ ከፍፃሜ አድርሰው ርካታን ያገኛሉ።
የህይወት ሩጫም እንድሁ ነው። ጥንካሬህ የሚለካው በመጀመርህ ብቻ ሳይሆን በመጨረስህም ጭምር ነው።
➥ⓈⒽⒶⓇⒺ
@melkam_sera
መልካም ቀን ❤😍🙏
/channel/etbookstore
ይህን channel በመቀላቀል በትንሽ mb መፅሀፍት ማንበብ ይችላሉ ለወዳጆቻችን በማጋራት በጎ ነገርን እናካፍል
@melkam_sera
⏰⏰⏰
" ለሰው ልጅ ሁሉ እኩልና ያለስስት የተሰጠ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው ። ጊዜህን መጠቀም ስትችል እራስህን ትለውጥበታለህ...ራሥህን መለወጥ ሥትችል ሌሎችንም ትለውጣለህ ። ራስህን ለመለወጥ ጊዜን ካልወሰድህ ሌላን መለወጥ አትችልም ። ( Invest in your self )ራስህ ላይ ፈሰስ አድርግ መጀመርያ ራስህን ለውጥ ። አስተሳሰብህን ሞርድ ፣ እይታህን አጥራ ፣ ንግግርና እርምጃህን ገምግም ነገ የሚኖርህ ዛሬን ስትጠቀምበት ነው ። ከዛሬም ያለህ ጊዜ አሁን ነው...አሁን ደግሞ እያለፈ ነው! ጥያቄው እንዴት እያለፈ ነው የሚለው ነው ። ለዚህ ጥያቄ የምትመልሰው መልስ #ነገ በምትለው ምናባዊው ቀን ላይ ያለህን አንተነት ይወስነዋል ። "
ዛሬህን ተጠቀምበት...
⏰⏰⏰
@melkam_sera
🙏መልካም አዳር🙏
1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!
3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!
4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!
5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!
6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!
7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!
8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!
9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!
10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!
11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!
12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!
13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!
14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትልበስ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!
15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!
16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!
@melkam_sera
🙏መልካም አዳር🙏
Watch "ተዋናይት ሰላም ተስፋዬ ኑ በጋራ ወገንን እርዳ ትለናለች" on YouTube
https://youtu.be/jVfAENa_Aso
ሼር አድርገው
ዝም ባለ ቤት ውስጥ ብዙ ድምፅ አለ
ግዜው ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ተስፋ መቁረጥ በራሱ ሌላ ተስፋ ያስቆርጣል እናማ ወዳጄ ዳገት መውጣት ከባድ ነው ነገር ግን ስራ አድርገከው ሳይሆን መዝናኛ አድርገከው ተራራውን ምትወጣ ከሆነ ስራዬ ብሎ ከሚወጣው ቀድመህ ትደርሳለህ መሪ መጨበጥ ብቻ ሹፌር አያስብልም እና ስለዚህ ጎበዝ ሹፌር ለመሆን የራስክን ችሎታ እና አስተሳሰብ አስተካክል ምክንያቱም የህይወትህ ሹፌር አንተ ነህ
@melkam_sera
🙏መልካም አዳር🙏
share share share
ሰው ሆነህ የተፈጠርከው በመከራ እና በፈተና ተፈትነህ ለማለፍ ነው ስትኖር አካፍል አብላ አልብስ ደግ ሁን ያኔ ሰው ትሆናለህ
@melkam_sera
[በጎነትን በጋራ እናቀንቅን]
ምጽዋት በአበው አንደበት
"አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው።"
#ቅዱስ_ባስልዮስ
"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል።"
#ቅዱስ_አምብሮስ
"አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን።"
#ቅዱስ_አግናጥዮስ
[በጎነትን በጋራ እናቀንቅን]