[ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል]
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡
❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።
❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ አንድ ሺሕ አራት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡
ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)
❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨
[የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
/channel/menfesa_wimker
/channel/menfesa_wimker
“እናንተ እምነት የጎደላችሁ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ”
(የብጹዕ አቡነ ሽኖዳ አባታዊ ምክር)
እኛ ከእግዚአብሔር እድንርቅ ካደረጉን ነገሮች አንደኛው ጭንቀት ነው ። ጭንቀት
ማለት ስለተከሰቱና ይከሰታሉ ተብለው ስለሚታሰቡ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ
ጉዳዮች አብዝቶ በማሰብ በስጋት ተውጦ መረበሽ ማለት ነው። ዓለም በብዙ
አስጭናቂ ጉዳዮች በመሞላቷና ሰውም የሚኖረው ዓለም ላይ እንደመሆኑ
አብዛኛው ሰው ሊጨነቅ ይችላል። “ጭንቀትን የተመላ ይህ ዓለም ያልፍ ዘንድ
ይቸኩላል” ዕዝ.ሱቱ 2፥27 እንዳለ ዕዝራ። ኦክስፎርድ ጭንቀት የሚለውን
ሲተረጉመው " ከቁሣዊ ነገሮች ፍላጎት የሚመጣ ግፊት ወይም ውጥረት
ይለዋል " የተሻለው ትርጉሙ ግን አላስፈላጊ ነገሮችን ከመፈለግ የተነሣ
የአእምሮ ወይም የስሜት ድካም ፤ ውጥረት ፤ ወይም ሕመም ማለት ነው ።
ጭንቀት ለሕይወታችን ከምንፈልጋቸው ወይም አላስፈላጊ
ከሆኑ ነገሮች ፍላጎት የሚመጣ ግፊት ወይም ውጥረት ነው ። ስለሆነም
የጭንቀት መንስኤው ምንድን ነው ? ስንል # ተስፈኝነት ሆኖ እናገኝዋለን ።
በአጠገባችን ካሉ ሰዎች ቃል ከገቡልን ፤ ከሚቀርቡን ፤ ከቤተሰቦቻችን ወዘተ
የምንጠብቀው አለ ። ተስፈኝነት በሁለት መንገዶች ሊመጣ
ይችላል ። የመጀመሪያው ስለ ሰዎች ያለን ተስፈኝነት አለ ። ሌላውኛው ሰዎች
ስለ እኛ አላቸው ብለን የምናስበው ነው ።
በማንኛውም መንገድ የተጨነቀ ሰው ከገጠማችሁ ከሁለቱ በአንዱ ምክንያት
እነደሆነ ታረጋግጣላችሁ ። ሌላ ሰው ለእኛ ዝቅተኛ ግምት ሠጥቶን ሊሆን
ይችላል ። ወይም እኛ
ራሳችንን ዝቅ አድርገነው ሊሆን ይችላል ። ወይም እግዚአብሔር እንደተወን
አድርገን ልንወስድ እንችላለን ። ወይም ከእግዚአብሔር እንደራቅን ሊሠማን
ይችላል ። ጭንቀት ከእነዚህ የአንዱ ስሜት ውጤት ነው ። የቁስ እቃ ፍላጎት
እንድንጨነቅ ያደርጋል ። ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም አንዳንድ ጊዜ
አወንታዊ በሆነ መልኩ ለስሜቱ ምላሽ እንሰጣለን ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ
አሉታዊ መልስ እንሰጣለን ። ሌላ ጊዜ ደግሞ አወንታዊም አሉታዊም ሳይሆን
ይቀራል ።
ከጭንቀት ለመላቀቅ የሚረዳ ዋነኛው ዘዴ ተፈጥሮአዊ ማንነታችንን ማሰብ ነው
። ቁሣዊ ሆነን
አልተፈጠርንም ። የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አርአያ እና አምሳል ነው ።
መቅደሱ ሆነን ነው የተፈጠርነው ።
ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ነው የተፈጠርነው ። ግፊቱም ፤ ጭንቀቱም
፤ሕመሙና ፤ውጥረቱ ፤ በመጣ ጊዜ ለእግዚአብሔር አሳልፈን መስጠት
ይኖርብናል ። ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የሆነ ግፊት ወይም ውጥረት የለም ።
ስለሆነም እኔ ተሸክሜ ከምጨነቅ እግዚአብሔር እኔን ሆኖ እንዲሸከም
አደርጋለሁ ። እርሱ ጫናወቻችንን ያቀላል ።
ዮሴፍ በብዙ ጫናወች ውሰጥ ይኖር ነበር ። ወድሞቹ ጉድጓድ ላይ ሲጥሉት
ምናልባት መረዳት በማይችልበት በሕፃንነቱ ጊዜ ነበረ ። እንደገናም ለባርነት
ሸጡት ። ከቤተሰቡም ጋር ተለይቶ መኖር ጀመረ ። የንጉሱ የፈርኦን ሚስት
በሐሰት ከሰሰችው ። በዚህም የተነሳ እስር ቤት ተጣለ። በእስር ቤት እያለ
ማንም የሚያስታውሰው አልነበረም ። ይህ እንግዲህ መጠነ ሰፊ ወደ ሆነ ጫና
ውስጥ ያመጣዋል ። ሆኖም ግን ዮሴፍ እነዴት ለመፍታት ሞከረ ? ችግሩን
እነዴት ተቋቋመው ? በእያንዳንዱ ሁኔታ ዮሴፍ ራሱ ዮሴፍ ነበረ ።
አልተለወጠም ። በሁሉምሁኔታዎች ተመሣሣይ ፤ ማንነት ፤ ፍቅር ፤ እምነት ፤
ነበረው ። እግዚአብሔርን አዘውትሮ ይጠራ እና ይለምን ነበረ ። እግዚአብሔርም
ሁል ጊዜ አጠገቡ ነበረ ።
ቦኑ እንከ ኢይከውነነ ናብእ መሥዋዕተ ስብሐት በኩሉ ጊዜ ለእግዚአብሔር ፍሬ
ከናፍሪነ ከመ ነእመን በስሙ
‹‹እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ
የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ ለእርሱ እናቅርብለት።›› ዕብ 13፡15
/channel/menfesa_wimker
/channel/menfesa_wimker
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +
ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"
ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)
ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::
ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::
"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)
እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?
ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::
ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::
ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::
ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
+++ መልአኩ ነው +++
ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ልጅ ብቻ ነበር፡፡ድንገት የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳ፡፡ በሁላችን አእምሮ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ? የሚል ጥያቄ ተፈጠረ፡፡ ሠራተኛችንሮጣ ሔዳ በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡‹በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡ እስዋ ግን በእርግጠኝነትተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎአላመነም፡፡ ሁሉም ማን ሊሆን ይችላል ብሎ ሲገምት የጠረጠረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ‹‹ምናልባት ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔርየተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› አሉ ሁሉም፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!
ይህገጠመኝ ባለንበት ዘመን የተፈጸመ ነው ተብሎ ቢነገር መቼም ብዙ የሚያምን ሰው አይኖርም፡፡ በሌሊት በር ሲንኳኳ በብዙዎቻችን አእምሮውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስየሚል ነው፡፡
በሐዋርያትዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖችበዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷንተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን (ጠባቂ) መልአኩ ነው፡፡››አሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)
ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስእያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛምየመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባትምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡
ቅዱሳን መላእክት እኛን መርዳት ሳይሆን እርስ በእርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ቅዱስ ገብርኤል ስለ ቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ምስክርነት ነው፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ሦስት ሱባኤ ሙሉ እየጾመ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለትና እንዲህ ሲል ተናገረው፡፡‹ዳንኤል ሆይ ወደ አንተ ልመጣ ተልኬ ሳለሁ የፋርስ መንግሥት አለቃ (የፋርስ ነገሥታት ላይ አድሮ ክፉ የሚያሠራቸው ዲያቢሎስ)ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ› በዚህ ንግግሩ እንደምናየው በምን ምክንያት ወደ እርሱ ከመምጣት እንደዘገየ አስረዳው፡፡ በመቀጠልም መልአኩ ገብርኤል እንዴት ዲያቢሎስን መዋጋቱን ትቶ እንደመጣ ለዳንኤል ሲያብራራለት ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ፤ እኔምከፋርስ ነገሥታት አለቃ (ከዲያቢሎስ ጋር) በዚያ ተውሁት›› ብሏል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል እርሱን ሊረዳው የሚቻለው ኃያል መልአክ ማንብቻ እንደሆነ ሲገልጽም ‹‹ከአለቃችሁ (ከእስራኤል ጠባቂያችሁ ማለቱ ነው) ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም፡፡›› በማለትደምድሟል፡፡ (ዳን.10፡13፣21) የአንዱ መልአክ ረዳትነት ለሌላው መልአክ እንዲህ የሚስፈልግ ከሆነ እኛ ደካሞቹ ምን ያህል የመላእክትረዳትነት ያስፈልገን ይሆን?
በየጊዜው በየሰዓቱ ጠባቂ መላእክትን ይዘዝልን!!
የሙሴን ፊት ትኩር ብሎ ማየት ካስቸገረ እመቤታችንን ያዩ ሰዎች ምንኛ በብርሃን ተሞልተው ይሆን? ‹አሕዛብ ለፊትሽ ይማልላሉ› እንዳለው የእግዚአብሔርን እናት ያዩ ዓይኖች ምንኛ ክቡራን ናቸው! እንደ አባ ይስሐቅ ‹አርእየኒ እምከ› ‹እናትህን አሳየኝ› ሳይሉ ፤ እንደ ዮሐንስና እንድርያስ ‹ማደሪያህ ወዴት ነው?› ብለው ሳይጠይቁ እመቤታችንን ያዩ ዓይኖች ምንኛ ዕድለኞች ናቸው፡፡
ሰዎች ጠፈርን አዩ ተብሎ ዝናቸው ይነገራል፡፡ ጠፈሩንም ምድሩንም በመሃል እጁ የያዘን ጌታ በእቅፍዋ የያዘችውን እመቤት ከማየት በላይ ምን ክብር አለ፡፡ ጌታ የተወለደበትን ሥፍራ ማየት ድንቅ ነው ፤ የወለደችውን ማየት ምንኛ ታላቅ ይሆን? የእናንተን አላውቅም ፤ እኔ ግን እንደ ቅዱስ ዳዊት የአምላክን ማደሪያ አይ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ ‹መቅደሱንም እመለከት ዘንድ› (መዝ.27፡4) በሰው እጅ ከተሠራው መቅደስ ይልቅ ልዑል ራሱ የሠራትን ሕያዊት መቅደስ ድንግል ማርያምን ማየት ይበልጣል፡፡ ሰማይንና ምድርን ሙሉ ከማየት እርስዋን ማየት ይበልጣል ፤ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ነው ፤ ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አላጠባውም አላቀፈውም አላሳደገውም እርስዋ ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይላል ‹‹የሽቱ ዕቃ ሽቱው ካለቀም በኋላ መዓዛው ከዕቃው አይለይም፡፡ እመቤታችን ጌታን ከወለደችም በኋላ የመለኮቱ መዓዛ አልተለያትም››
የጌታችንን የክብሩን መጠን የተረዳ ሰው ማደሪያው የሆነች እናቱን እመቤታችንን ይወድዳል፡፡ እንኳንስ የወለደችውን እናቱን ቀርቶ የለበሰውን ልብስ ሳይቀር አክብሮ ነክቶ ይፈወሳል ፣ ያደረገውን ጫማ እንኳን ልፈታ አይገባኝም ይላል፡፡
ይህን የእመቤታችንን ፍቅር ስንረዳ በሰማያት የጌታ ማደሪያ ወላዲተ አምላክ ወዳለችበት ፣ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት አእላፍ መላእክት ማኅበር ገብተን ለማየት እንበቃለን። ከሁሉም በላይ ከተአምረ ኢየሱስ በፊት "ለላህይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ" (ውበትህን ልናይ እንወዳለን) እያልን የምንለምነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማየትም እንደርሳለን።
መጽሐፉ "በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል" ይላል። በታናሽዋ ብርሃን በድንግል ማርያም ያልታመነ ታላቁን ብርሃን ክርስቶስን እንዴት ሊያይ ይችላል? "ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ባለን" በመጥምቁ ዮሐንስ ብርሃንነት ካልታመንን ወደ "ብርሃናት አባት" እንዴት እንደርሳለን? (ዮሐ 5:35 ፣ ያዕ 1:17) ዳዊትስ "በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን" ብሎ የለ? (መዝ 36:9)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 21 2007 ዓ.ም
ኩዌት የተጻፈ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
@menfesa_wimker
+ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር+
የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል:: "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60)
በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት::
በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም:: ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል::
የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል::
በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው::
ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው::
ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም::
እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ::
እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ::
በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር::
ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው::
ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ
- በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ
- በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን
- በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች
@menfesa_wimker
ሰይጣን ፡- ሞት ሆይ ፤ እስቲ ንገረኝ አንተን የሚያገለግልህና የሚያመልክህ ማን ነው? እኔን ግን ነገሥታት ሳይቀሩ እንደ አምላክ ያመልኩኛል!
ሞት ፡- ሞታቸውን እንደ መልካም ነገር የሚናፍቁኝና የሚጠሩኝ ብዙዎች ናቸው ፤ አንተን ግን ፈልጎ የጠራህም የሚጠራህም የለም፡፡
ሰይጣን ፡- ብዙ ሰዎች በሥራቸው እንደሚጠሩኝና እጅ መንሻም እንደሚያቀርቡልኝ አላስተዋልክም እንዴ? አይ ሞት!
ሞት ፡- ስምህ እኮ የተጠላ ነው አይ ሰይጣን! ሁሉ ይረግምሃል ፤ ስምህን ልታነጻውና መጠላትህን ልትሸሽገው አትችልም፡፡
ሰይጣን ፡- ጆሮህ ሳይደፈን አይቀርም ፤ ሰዎች በአንተ ላይ ምን ያህል በምሬት እንደሚጮኹ አትሰማም እንዴ? ይልቅ ብትደበቅ ሳይሻልህ አይቀርም…››
የሞትና የሰይጣን ክርክር ረዥም ነው ፤ ክርክሩ ከሲኦልም ጋር ይቀጥላል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ከሁሉ በመጨረሻ :- ‹‹አንድ ልብ ሆነው የነበሩትን ሞትና ሰይጣንን የከፋፈላቸው እርሱ የተመሰገነ ይሁን ፤ ተከፋፍለን የነበርነውን እኛንም አንድ ልብ ያደረገን እርሱ የተመሰገነ ይሁን›› ብሎ ውብ ድርሰቱን ያጠናቅቃል፡፡
‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል› እንደሚባለው ሞት በአሟሟቱና በመዋረዱ የተነሣም እኛ ክርስቲያኖች እጅግ ንቀነው ‹መውጊያህ የታለ?› እያልን መዘበት የጀመርን ሲሆን ሰማዕታቱ ደግሞ እንኳንስ ሊፈሩት የአንገታቸውን ኮሌታ ለመታረድ እየሰበሰቡ በደስታ የሚጠጡት ጽዋ ሆነላቸው፡፡ ስንቱን እንዳላስለቀሰና በጣር እንዳላስጨነቀ ዛሬ ሙቱ ሞት ተንቆ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለፍትሐት ጸናጽልና ከበሮ ይዛ የምትዘምርበት ፣ በኀዘን ፈንታ ማኅሌት የምትቆምበት ፣ እየተደገሰ ከነዳያን ጋር የሚበላበት ክስተት ሆኖ አረፈው፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 28 2012 ዓ ም
ሕማማት - ገጽ 500
አላዛር ከሞተ 4 ቀን ሆኖት ነበር።ኢየሱስ አላዛርን ይወደው ስለነበር ወደተቀበረበት ቦታ ከእህቶቹ ጋር ሄደ።ማርታ ግን ኢየሱስን ይሸታልና ወደ መቃብሩ አትጠጋ አለችው።ማርታ የሚታያት የሙታን መንደር ነው።ተስፋ ቆርጣለች።ኢየሱስ ግን አላዛርን ከመቃብር ቀስቅሶ ለክብሩ አቆመው።
ኢየሱስ ይወዳቹሀል።ሞተ ከምትሉት ይሸታል ከምትሉት ተስፋ ከቆረጣችሁበት ነገር ውስጥ ለክብሩ የሚሆን ሰውን ሁሉ የሚያስገርም እናንተን የሚጠቅም ነገር ማውጣት ይችላል።ከዮሴፍ ባርነት ውስጥ ንግስናን ያወጣ ካረጀችው ሳራ ማህጸን ይስሐቅን ያስገኘ ጌታ ዛሬም ህያው ነው።ለእርሱ ምን ይሳነዋል?
እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ........
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
ክርስቶስ ለሳምራዊትዋ ሴት እንዲህ አላት :-
እኔ ከምሠጠው ውኃ የሚጠጣ ለዘላለም አይጠማም!
እስዋም ለመነችው :-
ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልጠጣ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ’’
ይህ ውኃ ‘የሕይወት ውኃ እኔ ነኝ’’ ያለው ክርስቶስ ራሱ ነው፡፡ ሴቲቱም እርሱ መሆኑን ስታውቅ እንስራዋን ጣለች፡፡ እርሱን ካገኘች በኋላ እንደማትጠማ እርግጠኛ ነበረች፡፡
ወዳጄ አንተስ እንደ ሳምራዊትዋ ሴት መመላለስ የሰለቸህ መንገድ የለም?
ስትጠጣው አሁንም አሁንም ጨምር የሚያሰኝህ የማይቆርጥ ጥም የለህም? ልትቀዳ የምትመላለስበት ጉድጓድስ የለም? ሁለተኛ አልሔድም ብለህ ዝተህ የምሔድበት ቦታ የለም? ሁለተኛ አልጠጣውም ብለህ የምትጠጣው ሁሌ የሚጠማህ ውኃ ምንድር ነው? መላቀቅ እየፈለግህ ያልተውከው ፣ ዞረህ የምትሔድበት ፣ ታጥቦ ጭቃ ፣ አድሮ ቃሪያ ፣ ከርሞ ጥጃ የሆንህበት ልማድ የለህም?
ሰዎች በአንተ ተስፋ ቆርጠው "እሱ ዞሮ እዛው ነው : አይረባም! መከርነው አስመከርነው ትንሽ ይተውና ተመልሶ ያው ነው ሰው አይሆንም" ብለው እስኪማረሩብህ ድረስ መተው ፈልገህ ያልተውከው ነገር የለም? እንደ ሣምራዊትዋ ሴት ሰው እስክታጣ ብቸኛ ያደረገህ : ሰው ሆነህ ተፈጥረህ ከሰው በታች የሚያደርግህ የማይቆርጥ ጥም አጣድፎ ጉድጓድ አጠገብ አልጣለህም::
ክርስቶስ ቦታውንም ውኃውንም ያውቀዋል፡፡ አንተን ፍለጋ በጠራራ ፀሐይ ጉድጓዱ ድረስ ይመጣል:: መኖር አስጠልቶህ ወደ ጥልቁም ብትወርድ እርሱ በዚያ አለ:: ቀኙ በዚያ ይመራሃል:: ክርስቶስ ነፍሳትን ለማዳን እንኳን ጉድጓድ ውስጥ ሲኦልም ድረስ ይወርዳል::
ከማይለቅህ የውኃ ጥም መገላገል ከፈለግህ እንደ ሳምራዊትዋ ሴት እንዲህ በለው፦
‘ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልጠጣ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ’’
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 28 2013 ዓ ም
ሠዓሊ :- ማራኪ ግርማ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
የቴሌግራም ቻናል :
@menfesa_wimker
ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡
ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡
+ ጸሎት +
‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ
‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!
አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡
ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡
ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"
ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 27 2013 ዓ.ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +
ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"
ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)
ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::
ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::
"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)
እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?
ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::
ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::
ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::
ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
+ባሕራን ነኝ++
በጉያኔ የያዝኩት፤ ዓላማዬ እቅዴ
የት እንደሚወስደኝ ፤ የያዝኩት መንገዴ
ከቶ አላውቀውም!
አንባቢ ነሕና ፤ እስቲ አንብብልኝ
ሞት ካገኘህበት ፤ እፍ ብለህ አጥፋልኝ
በክንፎችህ ብዕር ፤እጣዬን ጻፍልኝ
ከዓለም ባህር ውስጥ ፤ ነጥቀህ ያወጣህኝ
አንተም ሚካኤል ነህ ፤ እኔም ባሕራን ነኝ።
እንደ ባህራን በስራ በትምሕርት በተለያየ የህይወታችን ኡደት የሞት ደብዳቤያችንን ይዘን የምዞር ሁሉ ሊቀ መላዕክት በህብዕ ጣቶቹ ይደምስስልን።
(ዲያቆን ሄንክ ኃይሌ)
🙏12🕯🙏
መንፈሳዊ የህይወት ምክር እና ግጥሞች
መንፈሳዊ የህይወት ምክር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ወዳጄ ሆይ ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡ እነዚህ በርግጥ አንተ ገንዘብ አድርገሃቸው እንደ ኾነ የሚታወቀው መከራ ሲገጥምህ ነውና፡፡
ለአስተያየት ......,,,,,
/channel/menfesa_wimker
ፍቅር ቊስል ነው
እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል።
እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።
ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው
ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።
ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር።
"ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።
አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው።
ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።
ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ
"እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው።
እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።
ጸሎት መጸለይ ለምን እንደሚከብድህ ታውቃለህ?
ወንድሞች በአንድ ወቅት አባ አጋቶንን ጠየቁት፤ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት (ድካም) ይጠይቃል?”። እርሱም መለሰ “ይቅርታ አድርጉልኝ፣ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከመጸለይ የበለጠ ከባድ ሥራ ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ለመጸለይ በፈለገ ጊዜ ሁሉ፣ ጠላቶቹ አጋንንት እንዳይጸልይ ሊከለክሉት ይሻሉ፤ ከመንገዱ ሊያደናቅፉት የሚችሉት ከጸሎት እንዲርቅ ሲያደርጉት ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። ሰው ማንኛውንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠራ፣ በሥራውም ቢጸና እረፍትን ያገኛል። ጸሎት ግን እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ [እረፍት የሌለበት] ውጊያ ነው።
ስለዚህ ወዳጄ ውጊያ ከሰው ሳይሆን ከአጋንንት ነው እና ሁላችሁንም የሱን ጦር ሚያርቁልንን ጾም ጸሎት በማድረግ ሚከላከሉልንን መላእክት ማቅረብ አለብን ።
ሰናይ ቀንጸሎት መጸለይ ለምን እንደሚከብድህ ታውቃለህ?
ወንድሞች በአንድ ወቅት አባ አጋቶንን ጠየቁት፤ “ከመልካም ሥራ ሁሉ የትኛው በጎ ሥራ ከሁሉ የበለጠ ጥረት (ድካም) ይጠይቃል?”። እርሱም መለሰ “ይቅርታ አድርጉልኝ፣ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከመጸለይ የበለጠ ከባድ ሥራ ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ለመጸለይ በፈለገ ጊዜ ሁሉ፣ ጠላቶቹ አጋንንት እንዳይጸልይ ሊከለክሉት ይሻሉ፤ ከመንገዱ ሊያደናቅፉት የሚችሉት ከጸሎት እንዲርቅ ሲያደርጉት ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። ሰው ማንኛውንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠራ፣ በሥራውም ቢጸና እረፍትን ያገኛል። ጸሎት ግን እስከ መጨረሻ ህቅታ ድረስ [እረፍት የሌለበት] ውጊያ ነው።
ስለዚህ ወዳጄ ውጊያ ከሰው ሳይሆን ከአጋንንት ነው እና ሁላችሁንም የሱን ጦር ሚያርቁልንን ጾም ጸሎት በማድረግ ሚከላከሉልንን መላእክት ማቅረብ አለብን ።
ሰናይ ቀን
ቅዱሳን መላእክት ለሰዉ ልጆች ድኅነት እጅግ የሚጓጉ
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ጠባቂዎቻችን ናቸዉ። እርግጥ ነዉ፤ በመጀመሪያ እኛም እንደ መላእክት
ክብሩን ለመዉረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠርን ነበርን
ግንኙነታችንም እነርሱ ከእኛ ቀድመዉ በመፈጠራቸዉ
ታላላቅ ወንድሞቻችን ናቸዉ። ከሰዉ ልጅ ዉድቀት
በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። በእኛ የባህርይ መጎስቆል
ምክንያት ታላቅ ወንድም የታመመ ታናሹን እንደሚጠብቅ ጠባቂዎቻችን ሆኑ።
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳለዉ፦ የሰዉ ልጅ
ከመላእክት ጋር ክቡር ሆኖ ሲፈጠር፤ ጠባቂን
አይሻም ነበር፤ ሰዉ በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን
እግዚአብሔር መላእክትን ጠባቂ አደረገለት።
ምክንያቱም ዲያብሎስ ሰዉን ለማጥፋት ሁል ጊዜ
ምክንያቶችን ስለሚፈልግ ነዉ።
እነዚህ መላእክት ከጠባቂነታቸዉ ባሻገር ለሰዉ ልጅ
መዳን እጅግ የሚጓጉ ሰዉን ወዳጆች ናቸዉ። አምላክ
ሰዉ ሆኖ በተወለደበት በዚያች ምሽት ሲዘምሩ
ያደሩት በአምላክ ሰዉ መሆን የሚያገኙት ጥቅም ኖሮ
ሳይሆን ለሰዉ ልጅ መዳን ካላቸዉ ፍላጎትና ፍቅር
የተነሳ ነዉ። በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
በምድርም ሰላም የሚለዉ ዝማሬያቸዉ የእኛ ሰላም
ለእነርሱ ምስጋና ምክንያት መሆን የሚያሳይ ምስጋና
ነበር። ሉቃ 2:14
የማያገቡትና የማይጋቡት እነዚህ መላእክት በሰማይ
የሰርግ ያህል ደስ የሚሰኙት በምድር አንድ ኃጢአተኛ
ንሰሓ ሲገባ መሆኑ ምን ያህል የእኛ ወዳጆች
መሆናቸዉን ያሳያል ሉቃስ15;10።
ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የተላኩ ስላላቸዉ ለማገዝ
የሚላኩ መናፍስት አይደሉምን?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ'
/channel/menfesa_wimker
/channel/menfesa_wimker
+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡
ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ
‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7
እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡
‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31
የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24
አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]
ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18
ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡
የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
/channel/menfesa_wimker
/channel/menfesa_wimker
+ ቅዱስ አጠራር +
ቅዱስ ጳውሎስ ፦ ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም ሲል ተናገረ፡፡ /2ጢሞ 1፡9/
መጠራራትን ሁላችንም ተጠራርተን እናውቃለን፡፡ በጩኸትም በፉጨትም በእጅ ምልክትም በጥሪ ወረቀትም በስልክም ተጠራርተን እናውቃለን:: ቅዱስ አጠራር ግን እንደምን ያለ ነው? እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና እርሱ ሰውን የሚጠራበት ጥሪም የተቀደሰ ነው፡፡ ይህ ጥሪ እንደምን ያለ ነው? ቅዱስ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ጥሪ ለምን ቅዱስ አጠራር አለው?
እርሱ ራሱ ከተጠራበት አጠራር እንጀምር ይሆን? ሳውል/ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሊያስርና ሊያሰቃይ ከበላይ አካል ደብዳቤን ተቀብሎ በደስታ እየቸኮለ ሲሔድ የበላዮች በላይ ደማስቆ ላይ አስቆመውና ጠራው፡፡ ለብዙዎች ሞት ፈቃድ ተቀብሎ ተሹሞ ሲመጣ ጌታ ከመንገድ አስቁሞ ለብዙዎች መዳንን እንዲሰብክ ፈቃድ ሠጠው፡፡ የጦር ዕቃ ጭኖ እየዛተ ሲመለስ ጦርና ጋሻውን አስጥሎ ራሱን ምርጥ ዕቃ አደረገው፡፡ በቅዱስ አጠራር የጠራው እግዚአብሔር ነውና!
ስለ ጴጥሮስ አጠራርስ ምን እንናገር? የሃምሳ አምስት ዓመቱ ዓሣ አጥማጅ ጎልማሳ ፣ ሌሊቱን ሙሉ መረቡን ጥሎ የሚያድረው ትዕግሥተኛ እንዴት እንደተጠራ ልብ በሉ፡፡ ለእርሱ ብዙ ዓሣ ከመያዝ በቀር ምንም ሕልም አልነበረውም፡፡ የታንኳዎቹን ቁጥር ከማብዛት የዓሣዎቹን ገበያ ከማስፋፋት በቀር በጎልማሳ ዕድሜው አዲስ ሕልም አልነበረውም፡፡
የመጦሪያ ዘመኑን እንዴት እንደሚያሳልፍና የዕድሜ ፀሐዩ ስትጠልቅ መረቡን አጥምዶ ለመመልከት ዝግጁ ከመሆን በቀር ምንም አዲስ ዕቅድ አልነበረውም:: ጀልባው ላይ ተሳፍሮ ደግ ደጉን የሚያወራው ናዝራዊ ግን ድንገት መጥቶ ጎልማሳነቱን እንደ ንሥር አደሰው፡፡ ሕይወቱን እንደ አዲስ አሁን እንደተወለደ ሕፃን ከሃምሳ ዓምስት ዓመቱ አስጀመረው፡፡ በዚያ ዕድሜው የሦስት ዓመት መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ በእሳትና በነፋስ ታጅቦ ተመርቆ : በሰባ ሁለት ቋንቋ እንደ አዲስ አፉን ፈትቶ እንዲያወራና ዓሣ ማስገሩን እርግፍ አድርጎ ትቶ በወንጌል መረብ ሰውን አጥማጅ እንዲሆን አደረገው፡፡ በድንቅ አጠራሩ የጠራው እግዚአብሔር ነውና!
ስለ ሐዋርያው ናትናኤልስ እንናገር ይሆን? ጓደኛው ፊልጶስ "የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው" ብሎ ሲጠራው ብዙም ደስ አላለውም ነበር፡፡ የናዝሬቱ መሲሕ የሚል ቃል ሲስማ ከይሁዳ ቤተልሔም መሲህ እንደሚመጣ ከሚያውቀው ትንቢት ጋር አልገጥም ብሎት ‘ደግሞ ከናዝሬት መሲህ ይነሣል እንዴ?’ እያለ በምሁራዊ ትዝብት ተውጦ እስቲ ልየው በሚል ንቀት ሳይዋጥለት ነበር የመጣው፡፡ እስቲ ልየው ብሎ ያገኘው ናዝራዊ ግን ራሱን ልቡ ድረስ ተመለከተው፡፡ ሳያውቅ የጠቀሰውን ጥቅስ አስጥሎ የሚያውቀውን የራሱን የተሸሸገ ማንነት ሲነግረው መቋቋም አልቻለም፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ መሰከረ፡፡ እርሱ እንደመሰለው የጠራው ጓደኛው ፊልጶስ አልነበረም ፤ በቅዱስ አጠራሩ የጠራው እግዚአብሔር ነውና!
የቀሬናዊው ስምዖን አጠራር ግን ከሁሉ የባሰ ነበር ፤ እርሱ መንገደኛ ነበረ ፤ መንገድ አላፊ እንደሚጣደፍ እየተጣደፈ ነው፡፡ ሰንበት ሳይገባበት ለመጓዝ ከኢየሩሳሌም እየቸኮለ ሲወጣ አንድ ብዙ ሕዝብ አጅቦት ግማሹ በማዘን የሚጮኽለትና ግማሹ በጥላቻ የሚጮኽበት የሕማም ሰው ሲንገላታ ተመለከተ::
መንገዱን ገታ አድርጎ ትንሽ ሊመለከት እንጂ ሊቆይ ሃሳብ አልነበረውም:: ነገር ግን ወታደሮች ግድ አሉት:: ሳያስበው የጌታ የሕማሙ ተካፋይ የመስቀሉ ተከታይ ሆነ:: ዓለም የዳነበትና የጌታ ደምና ወዝ የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ተሸክሞ አንድ ምዕራፍ ተጉዋዘ:: ያገዝነው ሲመስለን የሚያግዘንን ያገለገልነው ሲመስለን የሚያከብረንን ክርስቶስን ተጠግቶ መቼም የማይገኝ ክብርን ተጎናጸፈ:: በዚያች ዕለት መስቀሉን ተሸከም ብለው የጠሩት እንደመሰለው ሮማውያን ወታደሮች አልነበሩም:: በቅዱስ አጠራር የጠራው እግዚአብሔር ነውና!
ጌታ ሆይ እኔ ባሪያህን የጠራህበት ቅዱስ አጠራር እንዴት ያለ ይሆን? ስንቴ ጠርተኸኝ እንዳልሰማ ጥዬ ሔጄ ይሆን? የአንተን ጥሪ ገፍቼ ለዓለም ጥሪ ጉዋጉቼ ስንቴ ሔጄ ይሆን? "አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ" ካልካቸው መካከል እሆን ይሆን?
እባክህን ባልሰማህም ጥራኝ : ባልመጣም ጥራኝ : ጴጥሮስ በባሕር ላይ እንደለመነህ "ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ" : እንደ አልዓዛር "ውጣ" ብለህ በቅዱስ አጠራር ጥራኝ:: እንደ ማቴዎስ ከቀራጭነት ገበታዬ ላይ : እንደ ዘኬዎስ ከዛፍ ላይ : እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰረገላዬ ላይ ብቻ ባገኘኸኝ ቦታ ጥራኝ::
ሙት በሚቀሰቅስ ማዕበል በሚገሥፅ ድምፅህ ባልሰማህም ጥራኝ : ጆሮዬ አልሰማ ካለህ እንደ ማልኮስ ጆሮ ሠጥተህ አንተን ብቻ በሚሠሙ ጆሮዎች ፈውሰኝና ጥራኝ:: ዓይኔ ዓላይ ካለህ ከአፈር በምራቅህ ለውሰህ እያየሁ እንድመጣ አድርገህም ቢሆን ጥራኝ:: አሁን በቅዱስ አጠራርህ ስትጠራኝ ካልሰማሁህ በኁዋላ ልትፈርድ ስትመጣ "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" የሚለው ቅዱስ አጠራርህንም ሳልሰማ መቅረቴ አይደል? አሁን ጥሪህን ካልሰማሁ በኁዋላ ቃለ ሕይወትን አልሰማምና እንደ ሥራዬ ሳይሆን እንደ አንተ አሳብና ጸጋ መጠን ጥራኝ!
"ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 5 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
+++ በእርሱ ቊስል እኛ ተፈወስን +++
‹‹ጲላጦስም የካህናት አለቆችንና መኳንንትን ሕዝቡንም በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው ፡- ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህንን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት ፤ እነሆም በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም፡፡ ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም ፤ ወደ እኛ መልሶታልና ፤ እነሆም ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም፡፡ እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው›› (ሉቃ. ፳፫፥፲፬‐፲፮)
ጲላጦስ የጌታችንን ንጹሕ መሆን ካወቀ በኋላ ‹ቀጥቼ እፈታዋለሁ› አለ፡፡ ንጹሕ በመሆኑ ምክንያት የተቀጣ ከጌታችን በቀር ማን አለ? ጲላጦስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ስለፈለገ ያን ሁሉ ጥያቄና መልስና ሕጋዊውን የፍርድ ሒደት ማስፈጸም ትቶ በንጹሑ ጌታ ላይ ግርፋት እንዲወርድበት ፈረደ፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ›› ብሎ እንደተናገረው ትንቢት ጲላጦስ በእርጋታ ጀምሮት የነበረውን ሕጋዊ የምርመራና የፍርድ ሒደት አሽቀንጥሮ ጥሎ (አስወግዶ) ከሕግ ውጪ በዚያች ቀን በአይሁድ እጅ የተዋረደውን ጌታ ያለ ፍትሕ እንዲገረፍ ወሰነበት፡፡ (ሐዋ. ፰፥፴፫)
ጲላጦስ ‹‹ኢየሱስን ይዞ ገረፈው›› (ዮሐ. ፲፱፥፩) የጲላጦስ አሳብ ‹በመሰቀሉ ፈንታ ግርፋት ቢገረፍ ሕይወቱን ካዳንኩለት ቢቆስል ምንም አይደለም› የሚል ነበር፡፡ አይሁድም የግርፋቱን ጽናት አይተው ይሙት ማለታቸው እንደሚቀር ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከትናንት ምሽት ጀምሮ ታስሮ ሲንገላታ ያመሸውን ፣ በሐናና ቀያፋ ግቢ ውስጥ ሲደበደብና በጡጫ ሲመታ ያደረውን ጌታ በምሕረት የለሾቹ የሮም ወታደሮች እጅ እንዲገረፍ አሳልፎ ሠጠው፡፡
የሮማውያን ግርፋት እንደ አይሁድ ግርፋት በጅራፍ ብቻ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘቂሣርያ እንደገለጠው ጅራፉ በቆዳ ከተሠራ በኋላ በላዩ ላይ ስለታማ የሆኑ የብረት ኳሶች ፣ ሾለው የተሳሉ የአጥንት ስብርባሪዎች ይደረጉበታል፡፡ በዚህ አሰቃቂ የግርፋት መሣሪያና በጨካኞቹ ወታደሮች እጅ ወድቀው ሥቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው የሞቱም ብዙዎች ናቸው፡፡
በጅራፉ ላይ የተሠሩት የብረት ኳሶችና የአጥንት ስብርባሪዎች በሚገረፈው ሰውነት ላይ ሲያርፉ ሥጋውን እየነጩ የሚነሡ ስለሆኑ ጅራፉ በሰውነት ላይ ማረፉ ብቻ ሳይሆን ከሰውነት ላይ የሚነሣበትም ቅጽበት እጅግ ለመግለጽ የሚከብድ ሥቃይ የሚያደርስ ነው፡፡ የግርፋቱ መጠን በጨመረ ቁጥር የደም ሥሮችና አጥንቶች እስከሚታዩ ድረስ የሚጎዳ ፣ የጎድን አጥንቶችን መሰባበር ፣ ከፍተኛ የሆነ ውጪያዊና ውስጣዊ የደም መፍሰስ ፣ የሳንባ መጎዳት የሚያስከትል አሰቃቂ ሒደት ነው፡፡
በዚያች ቀን ጌታችንን ለመግረፍ የተመደቡት ወታደሮች እስራኤልን በብርሃን ዓምድ በሌሊት የመራቸውን አምላክ ፣ ሙሴና አሮንን በደመና ዓምድ ያነጋገራቸውን አምላክ በድንጋይ ዓምድ ላይ ለመግረፍ ዕርቃኑን አሰሩት፡፡ የካህናት አለቆችን ደስ ለማሰኘት ሲሉም በሙሉ ኃይላቸው በታላቅ ጭካኔ እጅግ ብዙ ግርፋትን አዘነቡበት፡፡ አንድ ገጣሚ እንዳለው በሙሴ አድሮ የፈጣሪን ክብር ለማየት የለመነው የሰው ልጅ ፈጣሪ በጊዜው ‹ጀርባዬን ታያለህ› ብሎ የገባለትን ቃል ቢፈጽምለትና ጀርባውን ቢያሳየው ግርፋትን አዘነበበት፡፡ (ዘጸ. ፴፫፥፳፫) በእርግጥም ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ‹‹ከጲላጦስ ግርፋትን ይቀበልበት ዘንድ ጀርባን ፈጠረ›› እንዳለው አምላክ ሰው የሆነውና ጀርባን ለራሱ ያዘጋጀው ስለ ሁላችን ኃጢአትን ግርፋትን ሊቀበልበት ነበር፡፡
የሮማውያን ግርፋት ቅዱስ ጳውሎስ እንደተገረፈው እንደ አይሁድ ግርፋት በመጠን ተወስኖ ‹አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ› እያለ የተገረፈው ሰው በሕይወት ተርፎ እያስታወሰ የሚናገረው ዓይነት ግርፋት አይደለም፡፡ (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፬)
ቤተ ክርስቲያናችን የጌታችን ግርፋት ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጊዜ እንደሆነ ስታስተምር አምስት ሺህ ነው ፣ አራት ሺህ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህን አሰቃቂ ግርፋት በሺህ ለሚቆጠር ጊዜ መገረፉን ግን ሁሉም ሊቃውንትና የታሪክ ሰዎች ተስማምተውበታል፡፡ ጌታችን እጅግ መገረፉን የሚያሳየን መስቀሉን ባሸከሙት ጊዜ በየሥፍራው እስኪወድቅ ድረስ አቅም ማጣቱ ነው፡፡
የጌታን ግርፋቱንስ መቁጠር ቢቻልም እንኳን ሥቃዩን ግን እንዴት ልንቆጥረው እንችላለን? ቤተ ክርስቲያናችን ከሥጋው አልፎ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ ስለ ተገረፈው አምላክ በዕለተ ዓርብ የምታነበውና የምታዜመው ራሱ ክርስቶስ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት አድሮ ስለሕማሙ የተናገረው የትንቢት ቃል የሥቃዩ መጠን ጥቂትም ቢሆን ለማሰብ ያግዘናል፡-
‹‹እንደ ውኃ ፈሰስሁ … አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ …. በአንጀቴም መካከል ቀለጠ…
አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ … እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም …
አጥንቶቼ ተነዋወጡ››
(መዝ. ፳፪፥፲፬፣፲፯፤፴፩፥፲)
ቅዳሴያችን እንዲህ ይላል ‹‹የወልድን መከራውን የሚናገር ምን ዓይነት አፍ ነው? ምን ዓይነት ከንፈር ነው? ምን ዓይነት አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማቱ በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፤ ሕሊናም ይመታል ፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፤ ሥጋም ይደክማል›› በእውነትም የጌታችንን ሥቃይ ለመግለጽ ምንም ዓይነት ቋንቋ ፣ ምንም ያህል ቅኔ አቅም አይኖረውም፡፡
ቅዱስ ኤፍሬምም :-
‹‹በክርስቶስ የተወደዳችሁ ሆይ ኑ! ወዲህ ቅረቡ ፤ በዚች ዕለት በዳዊት ከተማ የሆነውን አብረን እንይ! በተስፋው ቃል ሲጠበቁ የነበሩት የተመረጡት የአብርሃም ዘሮች ዛሬ ምን እንዳደረጉ እንመልከት! ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል?›› ይላል፡፡
ይህ ሁሉ የሆነው ስለ እኛ ኃጢአት ነበር፡፡ ኦሪት የሚገረፍ ሰው ‹‹የግርፋቱም ቊጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን›› ትላለች፡፡ (ዘዳ.፳፭፥፪) ጌታችን ማንም ስለ ኃጢአቱ ሊወቅሰው የማይችል ንጹሕ ቢሆንም ‹‹እግዚአብሔር የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ›› ስለተባለ ግርፋቱም በተሸከመው የእኛ ኃጢአት መጠን ሆነ፡፡
‹‹እርሱ ስለመተላለፋችን ቈሰለ ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ ፤ የደኅንነታችንም ተግሣፅ በእርሱ ላይ ነበረ›› በአጋንንት እጅ ልትገረፍ የጸጋ ልብስዋን አውልቃ ዕርቃንዋን በሲኦል የወደቀች ነፍሳችንን ነጻ ያወጣት ዘንድ እርሱ በጨካኝ ወታደሮች እጅ ዕርቃኑን ተገረፈ፡፡
‹‹እኛን ከሚገባን ግርፋት ያድነን ዘንድ ኢየሱስ የማይገባውን ግርፋት ተገረፈ›› ‹‹የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ (ተነከሩ) ፤ ከግርፋቱ ጽናት የተነሣ ሥጋው ሁሉ አለቀ›› ሐዋርያው ጴጥሮስ ‹‹በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ›› በማለት እንደተናገረ ‹‹በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን›› (፩ጴጥ. ፪፥፳፬፤ኢሳ. ፶፫፥፭)
("ሕማማት" ከተሰኘው የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ባለ 528 ገጽ መጽሐፍ )
+++ ሙሴ ሆይ ተሸፈንልን! +++
ነቢዩ ሙሴ በብሉይ ኪዳን ለአርባ ቀንና ሌሊት ከጾሙ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ‹አርባ ቀን ሙሉ እህል በአፉ ሳይገባ እንዴት አልራበውም? እንዴትስ አስቻለው› የሚል ሰው ካለ ሙሴ ምን ሲያደርግ እንደሰነበተ ያላወቀ ሰው ነው፡፡ እነዚያን አርባ ቀናት ያሳለፈው በታላቁ የሲና ተራራ ላይ ነበር፡፡ በዚህ ቅዱስ ተራራ ራስ ላይ እንዲቆም የተነገረው ይህ ነቢይ በተራራው ጫፍ ላይ እንደደረሰ ድንገት ተራራው በደመና ተሸፈነ፡፡ ልዑል እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ወረደ ፤ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት!›› የሚል ታላቅ ግርማ ያለው ድምጽም በተራራው ላይ ተሰማ፡፡
ሙሴ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ በእግዚአብሔር ፊት ወድቆ ሰገደ፡፡ በአምላካዊ ብርሃን ውስጥ ተከብቦ ፣ በእሳት መጋረጃዎች ውስጥ እያለፈ ፣ የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔርን ድምጽ እየሰማ ለአርባ መዓልትና ሌሊቶች ከፈጣሪው ጋር ሲነጋገር ቆየ፡፡ ልብ በሉ! በእንዲህ ዓይነት መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ተውጦ የከረመ ሰው መቼ ፋታ አግኝቶ ሊርበውና ሊጠማው ይችላል? በመጠየቃችንም ራሳችንን ሳንታዘበው አንቀርም!
ከአርባ ቀናት በኋላ ሙሴ ከተራራው ሲወርድ በግራና በቀኝ ሁለቱን ጽላት ይዞ ነበር፡፡ ወደ ሕዝቡ ሲመጣ ግን ሕዝቡ ወደ ሙሴ እንዳይቀርቡ ያስፈራቸው አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ ፊቱ ያበራ ነበር፡፡ በቅዱሱ ተራራ በደመናት መካከል ቆሞ ከፈጣሪው ጋር ቃል በቃል የተነጋገረው ይህ ታላቅ ሰው አርባ ቀንና ሌሊት ሳይመገብ ቢቆይም በረሃብ ከመጠውለግ ይልቅ ከአምላካዊ ጸጋ የተነሣ የፊቱ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡ ይህንን ተአምር ያዩት እስራኤልም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፡፡ ሙሴ ግን ‹ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።›
የእግዚአብሔር ሰው ክብሩን ሌሎች ያዩለታል እንጂ ለራሱ አይታየውምና የፊቱ ክብር ለሙሴ አልታወቀውም፡፡
ይህ የሙሴ የፊቱ ማንጸባረቅ በብዙ ቅዱሳን ታሪክ ላይ የምናነበውና እግዚአብሔር ለሚወዳቸው የሚሠጠው አንዱ ክብር ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ከመቀበሉ አስቀድሞ በሸንጎ ውስጥ እያለ ‹ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ› ሰዎች ተመልክተው የነበረው ሙሴ ላይ ያበራው የእግዚአብሔር ክብር በእርሱ ላይ ስላረፈ ነበር፡፡ (ሐዋ. ፮÷፲፮)
በብዙ ቅዱሳን ገድላትም ላይ ፊታቸው ሲያበራ ሰዎች ያዩአቸው ቅዱሳን ታሪክ እናገኛለን፡፡ እንዲያውም አንድ ትሑት አባት የፊታቸው ብርሃን ለሌሎች ታይቶ ለከንቱ ውዳሴ ፈተና እንዳያጋልጣቸው ብለው ሰው እንዳያገኛቸው በጨለማ ይወጡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ክብር አለመፈለጋቸውን አይቶ በጨለማ ፊታቸውን አብርቶ ሰው ሁሉ የነጋ መስሎት ከቤቱ እንዲወጣና ክብራቸውን እንዲያውቅ አድርጎባቸዋል፡፡ ይህ ክብር ለሁሉም ጻድቃን በሰማይ ይሠጣል፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ›› (ማቴ. 13፡42) ይህ ብርሃን እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ቢያበቃን ለእኛም የተዘጋጀ ክብር ነው፡፡ ‹‹እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።›› (2ቆሮ. 3፡18)
ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፊቱ ሲያበራ ታዲያ ለማየት እስኪሳናቸው ድረስ ስላበራባቸው አሮንና የእስራኤል ልጆች ሙሴን ‹ተሸፈንልን› (ተገልበብ ለነ) ሊሉት ተገደዱ፡፡ ለጊዜው ታይቶ የተሻረውን የሙሴን የፊቱን ክብር (ብርሃን) ማየት ስላልቻሉ በጽላቱ ላይ የተጻፉትን ዐሠርቱን ትዕዛዛት ለማንበብ ሲቆም ሙሴ ሕዝቡን እንዳይቸገሩ ብሎ ፊቱን በመጋረጃ ይሸፍን ነበር፡፡ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ መሸፈኛውን ይገልጥና ወደ እነርሱ ሲመለስ ግን ይሸፍነው ነበር፡፡ (ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ "ሙሴ ፊቱ ሲያበራ በልብሱ ሸፍኖት ነበር ፣ የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን በታቦር ተራራ ፊቱ ሲያበራ በልብሱ እንዳይሸፍነው ልብሱም ያበራ ነበር" ብለው ተቀኝተዋል።)
ቅዱስ ጳውሎስ ሙሴ ትእዛዛቱን ሲያነብ የተሸፈነበትን ያንን መጋረጃ የሙሴን ፊት ብቻ ሳይሆን ብሉይ ኪዳንም ሳይቀር ለእስራኤል የተሸፈነባቸው ለመሆናቸው ማሳያ አድርጎ አቅርቦታል፡፡
‹‹ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።›› በማለት ኃጢአትን ቆጥራ ታስፈርድ በነበረችው በኩነኔ አገልግሎት (በኦሪት ፈንታ) የተተካችው አዲሲቱ የጽድቅ አገልግሎት (ወንጌል) ያልተከደነች እንደሆነችና የብሉይ ኪዳንን ምሥጢራት ሁሉ የምንረዳው ያለማወቅ መጋረጃን ወዳነሣልን ወደ ክርስቶስ ዘወር ብለን ስንመለከት መሆኑን አስረድቶናል፡፡ (2ቆሮ.3፡7-16)
የሙሴ ፊቱ ያበራው ለምን ነበር?
እስቲ ወደ ሙሴ እንመለስና እንጠይቅ! እስራኤል ለምን መሪያቸውን ትኩር ብለው መመልከት ተሳናቸው? ካህኑ አሮን እንዴት ወንድሙን መመልከት አስቸገረው? የሕዝቡ አለቆች እንደወትሮው ከሙሴ ላይ ማተኮር ለምን ተቸገሩ? ያለ ወትሮው የሙሴ ፊት ለምን አንጸባረቀ? ብለን ስንጠይቅ ሙሴ ያለማቋረጥ በደመና መካከል ከእግዚአብሔር ጋር ስለቆመና ቃል በቃል ለአርባ ቀንና ሌሊት ከአምላኩ ጋር ስለተነጋገረ ነበር፡፡ ስለተቀበለው የኦሪት ሕግ ክብር ሲባል የሙሴ ፊት በክብር አንጸባረቀ፡፡ የእግዚአብሔር ክብር በዙሪያው ስለነበር ፊቱ አንጸባረቀ ፤ ትኩር ብለው ማየት ቢሳናቸውም ዕድለኞች የነበሩት የዚያን ዘመን ሰዎች የሙሴን የሚያበራ ፊቱን ተመለከቱ፡፡
እስቲ ከፈጣሪው ጋር የተነጋገረውን የሙሴን ፊት በዓይነ ሕሊናችን ሲያንጸባርቅ እንመልከተው! በዘመኑ ባንኖርም ለአፍታ ያን ትሑት ሰው ሙሴን ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጉያዎቹ ታቅፎ ከሲና ተራራ ሲወርድ ፣ ፊቱም ሲያበራ እንመልከተው......! ዕፁብ ድንቅ ነው!
ውድ አንባቢያን! በሲና ተራራ በደመና ተሸፍኖ ፈጣሪውን ያነጋገረው ሙሴ ፊቱ እንዲህ ካበራ ‹እግዚአብሔር በብሩሕ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅጸኗ ያደረ› የድንግል ማርያም ፊትዋስ እንዴት ያበራ ይሆን? ሙሴ በእሳት መጋረጃዎች መካከል አልፎ ዐሠርቱን ቃላት በመቀበሉ ፊቱ ካንጸባረቀ ሰባቱ የእሳት መጋረጃ በሆድዋ ውስጥ ተዘርግቶ ለእግዚአብሔር ቃል ማደሪያ የሆነች የእመብርሃን ፊትዋ እንደምን ያንጸባርቅ ይሆን?
ለእኔስ ሁለቱን ጽላት ከታቀፈው ከሙሴ ፊት ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል የታቀፈችው የእመቤታችን ፊት እንደሚያበራ ይታየኛል፡፡ ሙሴ ለአንድ ወር ከዐሥር ቀን ያነጋገረውን ፈጣሪ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅጸንዋ ይዛ የወለደችው ድንግል የፊትዋ ብርሃንዋ መጠን ምን ያህል ይሆን? ሊቃውንቱ ዛሬ ሌሊት ‹ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ ወታስተርኢ እም አርእስተ አድባር› ከጠዋት ኮከብ ይልቅ ታበራለች ከተራሮችም ራስ በላይ ትታያለች ይላሉ፡፡ አክለውም ‹ፈጽማ ያማረች ፣ የጸዳች እና የምታበራ ፣ እንደ ፀሐይ የምታበራ ናት› (አዳም ወሠናይት ጽዱት ወብርህት ከመ ፀሐይ ብርህት) ሲሉ ያድራሉ፡፡ እንደ ፀሐይ ብቻ ነው ወይ የምታበራው የሚል ካለ ደግሞ ‹‹ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ›› እያልንም እናመሰግናታለን፡፡
ጌታችን ለወንበዴው <<በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ > የሚል ልመና እውነት እውነት እልሃለሁ ፤ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ብሎ ወዲያውኑ :መልስ ሰጠ በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ፧ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው ።
በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግስት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት ፡ከቁጣ የራቀ ምህረቱ የበዛው አምላክ :ክፉ ስራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል <የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል ስለዚህ ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ! ይህንን ምህረት ተስፋ አድርገን << ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንት በኃጢአት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ እያልን እንጸልያለን !
#ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +
የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::
ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::
እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::
ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::
ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::
የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"
@menfesa_wimker
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
✥ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
#ቅዱሳንን_እንወቅ
አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።
አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።
አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ
ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።
ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።
በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።
በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።
ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።
ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።
ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል።
ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛዋውሯል::
የአባታች የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን
@menfesa_wimker
ዐቢይ ጾም
ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-
ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ
ለ. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ
ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡
በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-
1. ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡
2. ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡
3. ምኩራብ
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡
4. መጻጉዕ
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡
5. ደብረ ዘይት
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡
6. ገብርኄር
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡
7. ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
8. ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡
+ የሰጠኸኝ ሴት +
እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው:: አዳምም :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ::
የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል:: ሚስቴ አላለም::
አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ
"ይህች አጥንት ከአጥንቴ
ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር::
ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር::
ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር::
አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት::
እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት::
ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ::
አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ::
የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው::
በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር
ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን::
የሠጠኸኝ ሥራ
የሠጠኸኝ ወላጆች
የሠጠኸኝ ሰፈር
የሠጠኸኝ ሀገር
የሠጠኸኝ መሪ
የሠጠኸኝ ጉዋደኞች
የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ
የሠጠኸኝ ዓይን
ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን:: የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 17 2012
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
+++ ጣዕም የሌለው ስብከት ++
ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም፡፡ በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር፡፡ ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ፡፡ የሰበከው ስብከት ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ፣ ‹ንስሓ ግቡ› የሚል አዋጅ የለውም፡፡ በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!!›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር፡፡
የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው፡፡ ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው፡፡ ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም፡፡ ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው፡፡ የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ትጠፋላችሁ› ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር፡፡
ዮናስ ወደ ከተማይቱ ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር፡፡ የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሠጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም፡፡ ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ› ብሎ አልሰበከም፡፡ መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም፡፡ ‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ጮኸ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን ‹ማን ነው የሚገለብጣት?› ‹ለምን ትገለበጣለች?› ‹ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?› ‹ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም?› አላሉም፡፡ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ››
አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል፡፡ በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል፡፡ ‹ነነዌ የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር› አላሉም ፤ ሀገር ከመቀየር ይልቅ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር፡፡ ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ፡፡
የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን› አላሉም፡፡ ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም ፣ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር ፤ የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ››
የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር፡፡ ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ፡፡ ‹‹ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር፡፡ ‹‹ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ?›› ብለው አፉን አላፈኑትም፡፡ መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ፤ ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ፡፡
ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች፡፡ ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ! ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት? ‹‹መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን? (መክ. 10፡16) መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል?
ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው› ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ያቺን ከተማ በዓይነ ሕሊናው በጎበኛት ጊዜ እንዲህ ብሏል ፡-
‹‹የንጉሥ ቤት ግብዣ ተቋረጠ ፣ ንጉሥ ማቅ ለበሰ ፤ ንጉሥ ማቅ ከለበሰ ደግሞ የጌጥ ልብስ ይለብሳል፡፡ በዚያን ጊዜ በነነዌ ወርቃችሁን ብትጥሉ ማንም አይሰርቀውም፤ ሀብታችሁ ያለበትን ቤት ክፍት ትታችሁ ብትሔዱ ማንም ዘው ብሎ አይገባም፡፡ ወንዶች ወደ ሴቶች በምኞት አይመለከቱም ፤ ሴቶችም የሚያያቸውን ለመማረክ ጌጦቻቸውን አላደረጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር አብረው ወደ መቃብር ሊወርዱ ነውና አረጋውያን በላያቸው አመድን ነሰነሱ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ጥያቄ ተጨነቁ ፤ አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ‹የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው› ሲለው የተጨነቀው ጭንቀት በነነዌ ወላጆች ተደገመ››
ሶርያዊው የበተ መንግሥቱን ሁኔታም እንዲህ ይሥለዋል፡፡
‹‹የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን፡፡የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች፡፡
ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ!!››
ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ፤ ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም፡፡ ‹‹የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ፤ ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር፡፡ ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር፡፡
ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ› አላለም ፤ በተቃራኒው ‹እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ› እስከማለት ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ነነዌን ወከሎ ነቢዩን እንዲህ ይለዋል ፡-
‹‹አንተ ዕብራዊ ሆይ ሁላችን ብንጠፋ ምን ይጠቅምሃል? አንተ ሰባኪ ሆይ በሁላችን መሞትስ ምን የተሻለ ነገር ይገኛል? የማቴ ልጅ ሆይ ወደ መቃብር በጸጥታ ብንወርድ ምን ታገኛለህ? በቃልህ ፈውሰኸን ልናመሰግንህ ስንመጣ ለምን ታዝናለህ? ዕጣህ ነነዌን ተናግሮ ያጠፋት ከመባል ይልቅ ተናግሮ ያተረፋት መባል ቢሆን አይሻልህም? መላእክት በሰማይ ሲደሰቱ አንተ ለምን ታዝናለህ? ዮናስ ሆይ ከእንግዲህ በስምህ የምትጠራ ናትና ነነዌን አመስግናት››
በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ፡፡ የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በ
ብዙ ልጆች አሉት
በ ሊቀመዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ብዙ ልጆች አሉት ለሥሙ ምሥክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃው ለእኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል
አዝ
ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል በአለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ
ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ
በባሕራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ
በጉዞ የረዳችሁ በባሕር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ ዕንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ
ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት።
@menfesa_wimker
VALENTINE'S DAY
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም።
የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ???
ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው።
የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው።
ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት።
ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው)
ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡
ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም።
እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው።
ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር።
በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል
1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗
2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗
3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው።
Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው።
እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን???
" ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6)
እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
♦♦ወድቆ መቅረት ነው ትልቁ ስሕተት♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
✥እጅግ ክፉው ነገር በኃጢአት መውደቅ አይደለም፤ በዚያ ወድቆ መቅረት እንጂ፡፡ እጅግ አሳዛኙ ነገር ከወደቁ በኋላ ድጋሜ አለመነሣት፣ በሐኬት በስንፍና ተይዞ መቀለድ እንዲሁም የምግባር ጉድለትን በተስፋ መቁረጥ ካባን መሸፈን ነው፡፡ ባደረገው ኃጢአት ተስፋ የቆረጠ ክርስቲያን እንዲህ የሚለው የፈጣሪው የረሳ ነው፦ "የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን?" /ኤር.8፥4/።
ከመቶ በጎች መካከል የጠፋ አንድ በግ ነበር፡፡ ያ በግ አስቀድሞም የተለየ በግ አልነበረም፤ እንደ ተቀሩት ዘጠና ዘጠኙ በጎች እንጂ፡፡ የኹሉም እረኛቸው አንድ ነው፡፡ ያ በግ ግን ከመንጋው ተለየ፡፡ ወደ ሩቅ ሀገር ተሰደደ፡፡ ወደ ሸለቆው ወረደ፡፡ ሣር እንደ ልብ ከሚያገኝበት፣ ውኃ እንዳሻው ከሚጎነጭበት ርቆ ሔደ፡፡ እረኛው ግን አልተወዉም፡፡ ዘጠና ዘጠኙ ይበቁኛል አላለም፡፡ ፈለገው፤ አገኘውም፡፡ ባገኘው ጊዜ ግን አልገረፈውም፤ አልተቆጣውም፤ በትከሻው ተሸክሞ ከዘጠና ዘጠኙ ጋር ደመረው እንጂ /ሉቃ.15፥4-5/፡፡ አንድ በግ የተባለው እኛው ነን፡፡ ዘጠና ዘጠኝ የተባሉት ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡ እረኛ የተባለውም እግዚአብሔር ነው፡፡ በድለን ልንርቅ እንችላለን፡፡ በድለን ልንሸሽ እንችላለን፡፡ ፈጣሪያችን ግን ይፈልገናል፡፡ ዝም ቢለን ይበልጥ እንርቃለንና፥ አንድም በክፋት ላይ ክፋት እንጨምራለንና ዘጠና ዘጠኙን ትቶ እኛን ፍለጋወይም ይመጣል፡፡ እኛም ተስፋ ባለ መቁረጥ ንስሐ ገብተን ወደ እርሱ ብንመለስ ይቀበለናል፡፡ ወደ መንጋውም ይቀላቅለናል፡፡ አልቀላቀል ካልን ግን ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በአዳኝ በአውሬ መበላት ይኾናል፡፡
ቅዱስ አባት ሆይ! ንስሐን ስለ ሠራህልን ክብር፣ ኃይልና ጌትነት ለአንተ ይኹን አሜን!
ከአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔ
+ ለምን ትቀናለህ? +
በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡
አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡
ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::
ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡
ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡
ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡
ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡
የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡
ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡
የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡
ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡
ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡
ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡
በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡
‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ
ጥር 5 2013 ዓ.ም.
መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!