+ ወርቃማዎቹ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +
"ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
ቅዱስ እንጦንዮስ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"እግዚአብሔርን ከግርማው ታላቅ የተነሣ ብቻ አትፍራው:: ከፍቅሩ ታላቅነት የተነሣ ፍራው"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው:: የጥበብ መጨረሻው እግዚአብሔርን ማፍቀር ነው:: የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስትደርስ እግዚአብሔርን ከመፍራት ወደ ፍጹም ፍቅር ትደርሳለህ:: ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላልና" ቅዱስ እንጦንዮስ ዘየዓቢ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"ለልጆችህ ስለ እግዚአብሔር ከምትነግራቸው የበለጠ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆችህ ንገረው"
አባ ኤጲፋንዮስ ዘአቴና
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"እውነተኛ እውቀት የትሕትና ፏፏቴ ነው"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"ጌታ ጴጥሮስን በባሕር ላይ ሊወድቅ ሲል በሚታይ እጁ የያዘው በየብስ ላይ በማይታይ እጁ እንደያዘው ለማስተማር ነበር" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"ክርስትና እጅግ ኃያል የሚሆነው በዓለም በተጠላ መጠን ነው" ቅዱስ አግናጥዮስ
🌺 🌺. 🌺. 🌺. 🌺. 🌺.
"ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 20 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
* ሀልወተ እግዚአብሔር *
ሀልወተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው ። እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም የሚሉ አሉና ከሱ እንጀምር ። ታዲያ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል ? ቢሉ ። 1ኛ.በስነ ፍጥረት ይታወቃል ። ም/ቱም ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለና ። ስዕል ካለ ሰዓሊው አለ ፣ ቤት ካለ አናፂ አለ ፣ ሙዚቃ ካለ ሙዚቀኛው አለ ማለት ነው ። ስለዚህ በዚ መሰረት ስናየው ይሄ ሁሉ ስነ ፍጥረት አስገኚ አካል ወይም ፈጣሪ አለው ማለት ነው ። 2ኛ. የሰው ልጆች ዝንባሌ ነው ።ይህም ማለት ግማሹ ሙስሊም ፣ ግማሹ ቡዲስት ፣ ግማሹ ክርስቲያን ፣ ግማሹ ባዕድ አምልኮ አምላኪ የሆነው ነብሱ ከውስጥ የፈጠራት አካል እንዳለ ስለምትጮህ ነው ። ስለዚ ይህም አንዱ የፈጣሪ መኖር ማስረጃ ነው ። 3ኛ.የቀናትና የወቅቶች መፈራረቅ ነው ። ይህም ለምሳሌ መብራት ሲጠፉና ሲመጣ መብራት ሀይል የሚባል አካል እንዳለ እንደምንረዳው ሁሉ ፡ የቀንና የማታ የበጋና የክረምት መፈራረቅም አምላክ እንዳለ ማስረጃ ናቸው ። ፀሀይን በቀን ጨረቃን በማታ ያሰለጠነ ቀኑን ለሰራዊት ሌሊቱን ለአራዊት ያደረገ አምላክ መሆኑን እናውቅበታለን ።የስነ ፍጥረት አይነቱ ብዛቱ ድንቅ ነው ። 1ፀሀይ ሆና ለአለም ሁሉ እንድታበራ ማን አደረጋት ? የዛፎቹ አይነት አንዳንዱ ቅጠሉ ሰፊ አንዳንዱ ቅጠሉ ቀጭን ፣ የአእዋፏቱ አይነት ፣ የአሶችና የሌሎች ባህር ውስጥ ያሉ ነብሳት መኖር ፣ ስናይ ፈጣሪ እንዳለ እንረዳበታለን ። ለውቅያኖሶች ዳርቻዎቻቸውን የወሰነላቸው ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበቦች ያስጌጠ ስራው ድንቅ የሆነ አምላክ የመኖሩ ማስረጃ ናቸው ። ሸክላና ተሽከርካሪ ፣ መርከብና አየር በራሪ ፣ ድልድይና አስፓልት ፣ መኪናና ሌሎችም ሞተር ነክ ነገሮች ፣ ታሪካውያን ህንፆዎች ፣ የሚያስገርሙ ነገሮች ሁሉ ያለ ሰሪ ፣ አትክልትና አዝርዕት ያለ መሬትና ያለ ዘሪ ፣ ልጅ ያለ እናትና አባት እንደማይገኝ ሁሉ ግዑዛንና ግዙፉን ጥቃቅንና ረቂቃን ፍጥረት ሁሉ ያለ ፈጣሪ እንዳልተገኙ እናምናለን ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚታየው ከማይታየው እንደሆነ እናምናለን" እንጂ ዳዊት በመዝሙር 13:1 "ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል" እንዳለው አምላክ የለም አንልም
“የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል” የሚለውን ቃል እንዳንሰማ እንድንተጋ እማልዳችኋለሁ፤ እማጸናችኋለሁም፤ እነዚህ አንዴ ብቻ ሰምተው ሲለወጡ እኛ ግን #በተደጋጋሚ ብንሰማም አልተለወጥንምና (ሉቃ.11፡32)፡፡ [ዳግመኛም] እነዚህ ምግባርን ኹሉ የያዙ ነበሩ፤ እኛ ግን #ምንም አልያዝንምና፡፡ እነርሱ ከተማቸው እንደምትገለበጥ ሲሰሙ ፈሩ፤ እኛ ግን ስለ #እሳተገሃነም ብንሰማም አልፈራንም፡፡ እነርሱ የነቢያትን ትምህርት አልሰሙም፤ እኛ ግን #በተጋጋሚ ተምረናል፥ ብዙ ጸጋም ተቀብለናል፡፡
🪔በእንተ #ሐውልታት፥ 20፥22🪔
የሰራሁትን ኃጢዓት ባስበው ልቦናዬ እጅግ ደነገጠብኝ። አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ። የኃጢዓቴንም ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ። አንድ ሰዓት ስንኳን ኃጢዓት ለመስራት አላቋረጥኩም።
😔😔😔😔😔
በሰውና በመላእክት ጉባኤ መካከል ራቁቴን መቆሜን አሰብኩ። በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ። ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ፤ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሰራሁት ኃጢዓት ፍዳ የተነሳ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ።
🤲🤲🤲🤲🤲
#ነገር_ግን_እኔን_ለማዳን_የምትችይውን_አንቺን_አማላጅ_አገኘሁ። #ዘወትርም_ከእኔ_እንዳትርቂ_አውቅሁ።
አርጋኖን ዘሠሉስ
🔻🔻🔻🔻🔻
🔸
+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? +
(ጊዜ ወስደው ያንብቡት አያጥር ነገር ታሪክ ሆኖ ነው)
አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡
በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡
ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦
‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡
ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡
ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡
‘’አባቴ ይባርኩኝ’
‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’
‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ
‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት
‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና
‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡
‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡
‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት
‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡
አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡
ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡
ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦
‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡
ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡
አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡
ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡
በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡
ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው
አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::
አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡
‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’
‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’
መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ው
+ ከታቦር ተራራ አትቅር +
"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/
የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው።
ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል።
የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል።
★ ★ ★
ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው።
ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ።
"ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ።
የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ?
ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም።
በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል።
ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን?
★ ★ ★
በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።
ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር።
" አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3
የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል።
ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው።
መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው።
ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ።
በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " ብሎ በገባው ቃል መሠረት ነጭ ያደርግሃል።
እርሱ ወዳለባት የቅድስት ቤተክርስቲያን ተራራ በንስሓ ከደረስክና በታቦር ያበራውን ብርሃኑን ካበራልህ ነጭ ትሆናለህ። ከዚያ "አጣቢ የማያነጻውን ያህል ትነጻለህ" ከአብ የባሕርይ ልጅ ከብርሃኑ ፀዳል ስትቀርብ አንተም በጥምቀት ያገኘኸው የጸጋ ልጅነትህ ያንጸባርቃል። ነጭ በሆንህ ጊዜ የሚያዩህ ሁሉ "በበጉ ደም ልብስህ መታጠቡን"ና ነጭ መሆኑን አይተው ይደነግጣሉ ፣ ሊሰሙህ ያልወደዱ ሁሉ ለባሕርይ ልጁ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ እንዳዘዘለት ለአንተም ጆሮ እንዲሠጡህ ያደርግልሃል።
አንተ ብቻ ከደብረ ታቦር አትቅር ፣ ካልሞትህ እንደ ኤልያስ ፈጥነህ ና ፣ በበደል ከሞትክም እንደሙሴ ተነሥተህ ና። ብቻ ወደ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ተስፋ አትቁረጥ ፣ እንደ ሙሴ ትሞታለህ እንጂ ምድረ ርስትን አታይም ብትባል ፣ እንደ ኤልያስ ትኖራለህ እንጂ ሞትን አታይም ብትባል ብቻ አንተ ከደብረ ታቦር አትቅር።
ው ነገር ግን ከአብርሃምና ከዮፍታሔ ድርጊት የተለየ ነው፡፡ እርሱ የሠዋው በጉንም ልጁንም ነው› ይላሉ ባለቅኔዎቹ አባቶቻችን፡፡
ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 27 2012 ዓ ም
(ሕማማት ገጽ 224)
አብርሃም ያያት ቀን ++
አብርሃም እግዚአብሔር ‹ወዳጄ› ብሎ የጠራው የፈጣሪ ምሥጢረኛ የሆነ ሰው ነው፡፡ በአምላኩ ትእዛዝ ሀገሩንና ዘመዶቹን ትቶ የወጣው ይህ መናኝ በድንኳን የሚኖር ምስኪን ስደተኛ ቢሆንም በድህነቱም እንግዶችን በፍቅር የሚቀበልና በዚህም አምላኩን በቤቱ ለማስተናገድ ክብር የበቃ ጻድቅ ሰው ነበር፡፡
አብርሃምና ሣራ ዘራቸው እንደሚበዛ ቃል የተገባላቸው ቢሆኑም ልጅ ያገኙት ግን ካረጁ በኋላ ነበር፡፡ ባለ ተስፋውን ልጅ ይስሐቅን ሲወልዱ ሣራ ዘጠና ዓመቷ ሲሆን አብርሃም ደግሞ መቶኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው ፡-
‹‹የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ
ወደ ሞርያም ምድር ሒድ ፣
እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ
በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው›› (ዘፍ. ፳፪፥፩)
‹የምትወደውን› ፣ ‹አንድ ልጅህን› ፣ ‹ይስሐቅን› የሚሉት ቃላት እንዴት ገላጭ ናቸው? አብርሃም ‹እንዴት ሠዋልኝ ትለኛለህ?› ብሎ ፈጣሪውን ቢጠይቅ ኖሮ እነዚህ ሦስት ቃላት መከራከሪያው በሆኑ ነበር፡፡ ‹‹እንዴት ሠዋው ትለኛለህ ፤ የምወደውን? አንድ ልጄን? ይስሐቅን? እንዴት አድርጌ?›› ብሎም በተብከነከነ ነበር፡፡
እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ቃላት በማስቀደም ሠዋልኝ ሲለው ግን አብርሃም አንዲትም ቃል አልተነፈሰም፡፡ ‹ለምን? ሀገሩን ከሞላ በግ እንዴት ልጄን እንድሠዋው ፈለግህ? ከዚህ ቀደም ልጁን የሠዋስ ማን አለ?› ብሎ አልጠየቀም፡፡ ‹‹የይስሐቅ ዘር እንደሚበዛና በምድር ላይ እንደሚያፈራ ነግረኸኝ አልነበረም? እኔ ከሠዋሁት ቃልኪዳንህ ተቋረጠ አይደለምን? ልጁንስ ካረደው በኋላ ዘሩ የበዛ ወዴት አለ?›› ሊል ይችል ነበር፡፡ ‹‹አባት ያደረግኸኝ ለዚህ ነው? የልጄ ገዳይ ልታደርገኝ ነው? መሞቱን ከፈለግህ ለምን አንተው አትወስደውም? እኔን እጅስ ስምን በደም ታቆሽሸዋለህ?›› ብሎ መሞገትም ይችል ነበር፡፡ አብርሃም ግን አንድ ጥያቄ እንኳን አልጠየቀም፡፡
‹‹አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሔደ፡፡ በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ዓይኑን አነሣና ቦታውን ከሩቅ አየ›› (ዘፍ. ፳፪፥፫-፬)
አብርሃም እግዚአብሔር ከነገረው በኋላ የአምላክን ትእዛዝ ለመፈጸም ‹በማለዳ ተነሣ›፡፡ የማለዳውን እናቆየው ፤ በእውነት አብርሃም ያ ማለዳ ከመንጋቱ በፊት የነበረችዋን ሌሊት እንዴት አሳልፏት ይሆን? ነገ ተጓዥ ነኝ ብሎ ሃሳቡን ጥሎ ተኝቶ ይሆን? መቶ ዓመት ሙሉ ጠብቆ የተሰጠውን ልጁን እንዲያርድና እንዲሠዋ ተነግሮት አብርሃም እንዴት አድሮ ይሆን? ለማንም ሳይናገር ምሥጢሩን በልቡ የያዘው ጻድቁ አብርሃም በዚያች ሌሊት እንዴት ተጨንቆ ይሆን? ዘርህንና ወገኖችህን ትተህ ውጣ ብሎት አምኖ የታዘዘለት አምላኩ አሁን በእርጅና ዘመን የሰጠውን ዘሩን ይስሐቅን ሠዋልኝ ባለው ጊዜ የአብርሃም ልብ ምን ያስብ ይሆን? በሕሊናውስ ምን ይመላለስ ይሆን?
‹እንዴት ብዬ ነው ለሣራ ልጅሽን ልሠዋው ነው ብዬ ልነግራት የምችለው? ለይስሐቅስ እንዴት ‹ልሠዋህ› ብዬ እነግረዋለሁ? ይስሐቅስ እንዴት ለመሞት ይፈቅዳል? እሱ እሺ ቢለኝ እንኳን እንዴትስ ችዬ በልጄ ላይ ቢላዋ አነሣለሁ? ሠውቼው ስመለስስ ምን እላለሁ? ሣራ ስትሰማ ምን ትለኛለች?› ብሎ ሲያስብ አድሮ ይሆን? የዚያን ጻድቅ አረጋዊ የሌሊት ቆይታ ማን ጠይቆ በነገረን! ያቺ ሌሊት ስትነጋ ግን አብርሃም በማለዳ ተነሣ፡፡ ‹መሠዋቴ ካልቀረ እስቲ ከልጄ ጋር ትንሽ የመሰናበቻ ጊዜ እንኳን ላሳልፍ ፣ የልጄን ፍቅር ልጥገብ› አላለም፡፡ ለአምላኩ ጽኑ ታዛዥ ነውና የታዘዘውን ለማድረግ ጎሕ ሲቀድ ተነሣ፡፡
የአብርሃም የሕሊና ፈተና ማልዶ ተነሥቶ ሲወጣም አላበቃም፡፡ እግዚአብሔር ‹ወደ ሞሪያም ምድር ሒድ ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው› እንዳለው ልብ እንበል፡፡ አብርሃም በሚኖርበት አካባቢ ብዙ ተራሮች ቢኖሩም ልጁን ለመሠዋት ግን የታዘዘው በሞሪያም ምድር ገና በሚነገረው ተራራ ነው፡፡ ስለዚህ እስከዚያ ድረስ አብርሃም ልጁን ይዞ ለሦስት ቀናት ያህል መጓዝ ነበረበት፡፡ እስከ ተባለው ሥፍራ እስከሚደርስ ድረስ አብርሃም ከሚወደው አንድ ልጁ ይስሐቅ ጋር ለሦስት ቀናትና ለሦስት ሌሊቶች አብሮ አሳለፈ፡፡ ልጁን አርዶ ሊሠዋ ለሚጓዘው ለአብርሃም እነዚያ ሦስት ቀናት እጅግ ረዣዥም የጭንቅ ቀናት ነበሩ፡፡ ሊሞት እንደሆነ የማያውቀው ትንሹ ይስሐቅ ከአባቱ እግር እግር እየተከተለ ሲራመድ ፣ እንደወትሮው ‹አባቴ ሆይ› እያለ በፍቅር ሲጣራ ፣ በታዛዥነት ከአባቱ ጋር ሲጓዝ ፣ ደክሞት ሲተኛ እያንዳንዱ ሒደት አብርሃም ለልጁ ያለውን ፍቅር የሚቆሰቁስና ሥቃይ የሚያስከትል ነው፡፡ ምናልባትም አብርሃም እንቅልፍ ላይወስደውና የተኛውን ልጁን ሲያይ ሊያድርም ይችላል፡፡
በሦስቱ ቀናት ጉዞ ወቅት አብርሃም ምን ያስብ ይሆን የሚለውን እኛ ከመጠየቅ በቀር እንዲህ ነው ለማለት አንችልም፡፡ ይህ ጻድቅ ሰው የልቡን ሰውሮ በዝምታ ባሳለፋቸው በእነዚያ ቀናት ፣ ልጁን በሕሊናው ውስጥ ሠውቶ በከረመበት ወቅት በልቡ ምን ያስብ እንደነበር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን እንኳን ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቧልና›› ብሎ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ነግሮናል፡፡ የእምነት ምሳሌ የሆነው አብርሃም የተስፋውን ቃል የማያጥፈው አምላክ ልጄን እንድሠዋው ቢያደርገኝም እንኳን ልጄን ከሞት አስነሥቶም ቢሆን ቃሉን ይፈጽምልኛል የሚል እምነት በልቡ ውስጥ ነበረ፡፡ (ዕብ. ፲፩፥፲፱)
ወደ ሥፍራው ሲደርሱ አብርሃም ሁለቱን ሎሌዎቹን ፡- ‹‹አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን ወደ እናንተም እንመለሳለን አላቸው›› ‹ወደ እናንተ እንመለሳለን› ያለው ጻድቁ ሰው ሎሌዎችን ለማታለል እየዋሸ ሳይሆን ልጁን ቢሠዋውም እንኳን እግዚአብሔር እንደሚስነሣለት ከነበረው ተስፋ የተነሣ ነበር፡፡
‹‹አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ይስሐቅ አሸከመው ፤እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ ሁለቱም አብረው ሔዱ፡፡ ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ፥ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ። አብርሃምም ፡- ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው፡፡ ሁለቱም አብረው ሔዱ፡፡
እግዚአብሔርም ወዳለው ቦታ ደረሱ አብርሃምም በዚያ መሠዊያ ሠራ እንጨትም ረበረበ ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው፡፡ አብርሃምም እጁን ዘረጋ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና ፡- አብርሃም አብርሃም አለው ፤ እርሱም እነሆኝ አለ፡፡ እርሱም ፡- በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ አንዳችም አታድርግበት ፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለው፡፡ አብርሃምም ዓይኑን አነሣ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ ፤ አብርሃምም ሔደ በጉንም ወሰደው በልጁም ፈንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው›› (ዘፍ. ፳፪፥፰‐፲፫)
እግዚአብሔር ይህንን ጻድቅ ሰው ስለምን ሊፈትነው ወደደ? በዚህ የሕሊና ጭንቀት ውስጥ እንዲያልፍስ ለምን አደረገው? እምነቱን ሊያውቅ ፈልጎ ነው እንዳንል እግዚአብሔር የማያውቀው ምን አለ? የአብርሃም እምነት ለሰው ይገለጥ ብሎ ካልሆነ በቀር ሳይጠይቀው በፊት መልሱ ምን እንደሚሆንም ያውቅ የለምን? ቅዱስ ያ
✝ ዓለም እኛን የሚያስደስት አንዳችም ነገር ስለሌላት በዓለም አንደሰትም!
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ብሏል ፦ " ዓለሙም ምኞቱም ያልፋል"1ኛ ዮሐ 2÷17(፪÷፲፯) ብሏል። ሁሉም ቁሳዊ ነገሮች እኛን በመንፈሳዊነት ሊያስደስቱን አይችሉም ወይም #በእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕይወታችንን ሊሞሉሉን አይችሉም። እንደነዚህ ያሉት ነገሮች የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስና #የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑትን ሰዎች ሊያስደስቷቸው አይችሉም።
ዓለሙ የእኛ የሆነውን መውሰድ ብቻ እንጅ የራሱን ስለማይሰጠን በዓለም አንደሰትም። ዓለሙ የሚሰጠን ነገር ሁሉ "ከንቱ ከንቱ የከንቱ ከንቱ "(መክ1÷2(፩÷፪) ነው። ዓለም የሚሰጠን በሙሉ የሰከነ አይደለም ዓለማዊውን ግይኙነት ጨምሮ። ከዘለዓለማዊ ሕይወት ጋር የተጣበቀችው ነፍስ ወደዚያው የሚያደርሳትን መንገድ ከዚሁ ስለ ጀመረች በዓለም ውስጥ ካሉ ነገሮች ደስታ አታገኝም።
እኛ ልናምንና ልንደሰት የሚገባን #በእግዚያብሔር ብቻ ነው።
#በእግዚአብሔር። የምንደሰተው ደስታ እውነተኛና የማያቋርጥ ደስታ ነው። አብዛኛውን ክፍል የሚወስደው #መንፈስ_ቅዱስ ስለሆነ ደስታው ነቅ የማይወጣለት ንጹሕ ደስታ ነው። ይህ ደስታ የሚጀምረው #እግዚአብሔርን ስናገኝው እርሱን ስንላመደው ምን ያህል እንደሚጥም ስንቀምሰው ስንወደውና ሌላ ምንም ሳንፈልግ ከእርሱ ፍቅር ጋር ስንኖር ነው።
መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት ለዚህ የተቀደሰ ደስታ " #እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም "(መዝ 33÷8+፴፫÷፰) እያለ ይጠራናል። #እግዚአብሔርን ስንቀምስ የተዋበውን እውነተኛ ሕይወት ስለምንመለከት ያለፈው ሕይወታችንን እንረሳዋለን። የምናስታውሰው ነገር ቢኖር #እግዚአብሔር ልባችንን አሳባችንንና መንፈሳችንን መሙላቱ ብቻ ነው።
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ ".... ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉት የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን #ኢየሱስን አግኝተንዋል. .." (ዮሐ 1÷45(፩÷፵፭) ሲለው የናትናኤል ደስታ ታላቅ ነበር። ከመሲሁ ጋር ከተዋወቀች በኋላ የሀገሯ ሰዎች ያውቁት ዘንድ የጠራቻቸው ሳምራዊት ሴት ደስታዋ እጅግ ታላቅ ነበር። "....በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ጌታየ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ (ፊል 3÷8~9(፫÷፰~፱) በማለት የመሰከረው የጠርሴሱ ሳወል ደስታም እጅግ ታላቅ ነበር።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
፨እኔ ማነኝ ? ፨
በእረኝነት ሳለሁ ጠርተህ ያከበርከኝ
መቃብሬነረ ፈንቅለህ ከሞት ያስነሳኸኝ
የተሸከመኝን አልጋ ያሸከምከኝ
ዝሙተኛ ሳለሁ በፍቅርህ ያቀፍከኝ
የኤርትራን ባህር ከፍለህ ያሻገርከኝ
ከአንበሶች መንጋጋ ከሞት አፍ ያዳንከኝ
አንገትህን ደፍተህ ቀና ያደረከኝ
አንተ እየተዋረድክ እኔን ከፍ ያከበርከኝ
ውለታህ በዛብኝ ጌታ ሆይ እኔ ማነኝ
ተናገረኝ ልስማህ ድምጽህ ያጽናናኛል
ያ ሁሉ መከራ ባንተ አልፎልኛል
ጠላቴ በፊቴ ተንበርክኮልኛል
ውስጤ አንተን ሲያስብ በሀሴት ይሞላል
የዓለም ጣጣዋ እጅግ ቢከብደኝም
ፈተና ከፊቴ ቢያደናግረኝም
በድፍረት እላለሁ ክፉውን አልፈራም
ሁሌም ከእኔ ጋር ነው ጌታ መድሃኒአለም
እሱን ተጠግቶ ያፈረ ሰው ማነው
የእጁ በረከት ልቡን ያላራሰው
እውነቱን ይናገር ይሄ ሰው ማነው
ሁሉን አሳልፎ ለዚህ ቀን ያበቃን
ከነ በደላችን በፊቱ ያቆመን
የልመናችንን ድምጽ ሰምቶ ያላሳፈረን
እንዲህ የወደደን ከቶ እኛ ማነን
ህይወቴን ልቃኘው ወደኋላ አየሁኝ
ስለኔ የሆነውን ሁሉን ተረዳሁኝ
በበደሌ ብዛት ፈጽሞ ያልተውከኝ
ኧረ ለመሆኑ ከቶ እኔ ማነኝ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
✝ ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን ።"
‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት)ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
ጾሙ ሀገራችንን ሰላም እንዲያደርግልን ምህረቱን እንዲያድለን ከክፉ ነገር እንዲጠብቀን የምንጸልይበት የበረከት ጾም ያድርግልን ። አሜን !
| መልካም የፆም ወቅት |
@menfesa_wimker
✝ ኃጥእ በደለኛ ነህን? ✝
ተስፋ አትቁረጥ! ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሓ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ የሚጠይቅህ ድካምና ጥረት እንደ ምን ያለ ነው? “በድያለሁ [ይቅር በለኝ]” ለማለት የሚጠይቅህ ዓይነት የሕይወት መንገድ ወይም እንደ ምን ያለ መከራ ነው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት ኃጥእ ነኝ ብለህ ራስህን ባትጠራ፥ ዲያብሎስ በዚህ እንደማይነቅፍህ አስበህ ነውን? በፍጹም! እንዲያውም ንስሓ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡ የከሳሽ ግብሩ ንስሓ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሓ ባልገባህበት በደልም አንተን መውቀስ ነውና ንስሓ ባትገባ ይህን ጠብቅ፡፡ ስለዚህ ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን እንዳይወቅስህ አትከለክለውም? ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም? ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡ መጽሐፍ ሲናገር፡- “ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡ ይህን ለማድረግ ድካም ጥረት አይጠይቅህም፡፡ አንደበተ ርቱዕ መኾን አያሻህም፡፡ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፡፡ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አስቀድመህ በደልህን በሰቂለ ሕሊና በነቂሐ ልቡና ኾነህ አስባትና አንዲት ቃል ተናገር፡- “በድያለሁ” ብለህ ተናዘዛት፡፡
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
ማየት ከመልአክ መቀበል ከአምላክ
++++++++++
ደጉ አባታችን ቅዱስ እንጦንስ ይህን አለም ትተው በበረሃ በምናኔ ህይወት እግዚአብሔርን ለማገልገል ተዘጋጅተው ሳለ አጋንንት በተለያየ ፈተና አስጨነቋቸው ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ ይህና ዓለም ለመቀላቀል የሚወዱትን በአታቸውን ጥለውወደ ዓለም ለመሄድ ሲነሱ መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ የሰኔል ቆብ አድርጎ የሰኔል ቀሚስ ለብሶ ያልተሰራ ሰኔል በእጁ ይዞ ያንን እየሰራ የጸሎት ጊዜ ሲደርስ እየሰገደ እና እየጸለየ የጸሎት ጊዜያት እንደዚህ እያደረገ ሁሉንም ካስተማራቸው በኋላ እንጦንስ ሆይ እንደዚህ እያደረግ ከኖርክ ከአጋንንት ፈተና ትድናለህ ብሎ አስተምሯቸዋል፡፡ቅዱስ እንጦንስም እንደዚህ በማድረግ ከመልአኩ እንደተማሩት በስራና በጸሎት አጋንንትን አሸንፈዋቸዋል፡፡ከዚህም በኋላ መነኮሳት ልጆቻቸው እንደተማሩት በስራና በጸሎት አጋንንትን ድል አድርገው የሚኖሩ ሆነዋል ያለስራና ያለ ጸሎት መነኮሳትም ሆኑ ዓለማውያን አጋንንትን ድል ማድረግ አይችልም፡፡‹ማየት ከመልአክ መቀበል ከአምላክ›እንዲሉ፡፡
በትንብልና ሳህልከ ተዘከረነ #ሚካኤል ሊቅ አበኩልነ እንዳለ ደራሲ፡፡
ለሀሳብ እና አስተያየት
@menfesa_wimker
ትህትናን ገንዘብ እናድርግ (አባ ህርያቆስ)
=====================
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ ወራት ( በሥጋ በተገለጠለት ዘመን) ስለ ትህትና ሲያስተምር እንዲህ ብሎዋል። " እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" (ሉቃ 18፥14)
ይህንን አምላካዊ ቃል ዋቢ በማድረግ ነው ታላቁ አባት አባ ህርያቆስ በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ ላይ '' ትዕቢትና መታጀርን ጌጥ አናድርግ ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ
'' ሲል የተናገረው።
አባ ዮሐንስ ሐጺርም ስለ ትህትና ሲናገር እንዲህ አለ “ዮሴፍን ማን ሸጠው?” ብሎ ጠየቀ፡፡ ከወንድሞች አንዱም “ወንድሞቹ ሸጡት” ብሎ መለሠለት፡፡
አረጋዊውም (አባ ዮሐንስም) “አይደለም፤ ትሕትናው ነው የሸጠው፡፡ ‘ወንድማቸው ነኝ’ ብሎ በመናገር እንዳይሸጥ ማድረግ ይችል ነበርና፡፡ ነገር ግን ዝምታን ስለመረጠ፤ ራሱን በትሕትናው ሸጠ፡፡ ይኸው የእርሱ ትሕትና ግን በግብጽ አለቃ አደረገው፡፡” በማለት ተናግሯል ።
" እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤" (ቆላ 3: 13)
ስለዚህ ወድ አንባቢያን ትዕቢት የዲያቢሎስ ስራ ነው! እኛ ደግሞ በጥምቀት ልጅነትን ያገኘን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ተገንዝበን ራሳችሁን የትህትና ሰው በማድረግ ትዕግስትን ገንዘብ እናድርግ።
" ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ።"
(መክ 10፥4)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን።
[ ትምህርቱን ለሌሎች ያጋሩ]
#ራስን_ድል_መንሳት
የስጋ ምኞትንና ፍላጎትን አስመልክቶ ጾምና ድንግልናን ራስን ድል የመንሳት መንገዶች ናቸው። ነፍስን አስመልክቶ የሚጠቀስም ሌላ መንገድ አለ።ራሱን የሚገዛና እርሱነቱን ወደ ዓለማዊ ደስታ ከማዘንበል የሚያግድ ሰው ብጹዕ ነው።
ማንነት ልታይ ልታይ ሲል፡ ጉራውን ሊገልጥ ሊተብት ይችላል።በዚህ ሁሉ ግን ልንቃወመው ይገባናል። ለእኛ #ከእግዚአብሔር ጋር መደሰትና መልካም የሆነው ነገር ለመጪው ህይወት ብናቆይ የሚሻለን መሆኑን ራሳችንን ልናሳምነው ይገባናል፡፡ በዚህ ዓለም ድስታን ለማግኘት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ #የመድኋኒ_ዓለም ቃል ይመሰክርባቸዋል፡- " . . . እውነት እላችኋለው፡- ዋጋቸውን ተቀብለዋል።"ማቴ6፡5፡፡
ስለዚህ በምድር ላይ ያሉ መብቶችህን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እግዚአብሔር እያንዳንዱ ዕንባህን ከዓይኖችህ ላይ የሚጠርግበት በወድያኛው ዓለም ቢሆንልህ ይሻልሃልና።
ማንነትህ ወይም ስጋህ አሁን ላለህበት ዓለም ደስታ የሚያዘም ከሆነ በርትተህ ተከላከላቸው። በራስህ ወይም በስጋህ ላይ የምይወስደው ይህ እርምጃ ጭካኔ አደለም፡ለእነርሱ ዘላለማዊ ሕይወትን ማረጋገጫ እንጂ!
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚንከባከባት ያጠፋታል። ራሱን በጥብቅ ከመቆጣጠር ችላ የሚል ሰው በእርሱ ላይ ኋይል እንዲኖረው ያደርጋል።ሰለሆነም ራሱን ለጽድቅ ከሚያለማምደውና #የእግዚአብሔር መንገድ ከሚተገብረው ሰው በተለየ ሁኔታ በመንፈሳዊ ጠባዩ ላይ እንዲያምጽ ያደርገዋል።
ራስን ድል መንሳት የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ከስጋ ደስታ ጋር እንደማይነጻጸር እርግጠኛ ሁን። ከሁሉ በጣም የሚያስደንቀው የራስ ጉራ ሙሉ ለሙሉ መጥፋት በሚገባው በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው።
#ቅድስነታቸው_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
(መንፈሳዊ ውግያዎች ከሚል መጽሓፋቸው የተወሰደ ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።)
@menfesa_wimker
++ በሰንበት መፍረስ ++
የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡
ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡
ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡
እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!
ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም.
ቪክቶሪያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! @menfesa_wimker
@menfesa_wimker
🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼 2013
አብረን እንጓዝ ! ብለን ተነስተናል በመንፈሳዊ ስራዎቻችን ውስጥ መልካም የሚባል አሻራ ለማሳረፍ እርምጃ ጀምረናል ይቀላቀሉን ይህ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ከተዋህዶ መፅሀፍት መዝገብ ስነጽሁፋዊ መፍለቂያ የሆነው የተዋህዶ Tube ነው
ይህ የተዋህዶ ቲዩብ ማዕዳችን ነው !
🌻 መንፈሳዊ መፅሀፍቶችን እየዳሰስን እምንማማርበት
🌻 ጥንካሬን ያድለን ዘንድ የቅዱሳናትን ታሪክ
🌻 የደጋግ አባቶች ተግሳፃትን የምናወሳበት
🌻 ዝማሬዎች
🌻 ስብከቶች የምናቀርብበት የ Youtube ቻናል ነው ።
© የተዋህዶ ቲዩብ ያወቅነውን ልናሳውቅ ዘንድ ለወዳጆ መልካም ሕሊናን እንፍጠር በ Youtube መተናል ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Subscribe ያርጉ ! 🔻
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCPPV0Jj4491QFJIHxs9WyJQ?subconfirmation=yes
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....
ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡
አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ለመዳን፣ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
ኃው ውስጥ ወረወርሁት፡፡
በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’
‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’
‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’
‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡
አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡
አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡
‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡
ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
✝ በምድር ላይ ስላለው ቆይታህ አስታውስ።
ነብዩ ዳዊት በጸሎቱ ውስጥ "እኔ በምድር እንግዳ ነኝና፥ትእዛዛትትህን ከእኔ አትሰውር።"(መዝ 118 ፡19)፥" እኔ በምድር ላይ እንግዳ ነኝና እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።" (መዝ 38 ፡12) እያለ በዚህ ጉዳይ ላይ በተመስጦ ይቆይ ነበር።
የመለየት ስሜት ዳዊትን ስለሞት እንድያስታውስ አድርጎታል። ነቢዩ ከማስታወስ ተጠቅሟል ማለት ነው። በመሆኑም እንዲህ እያለ ይጸልይ ነበር፡- " አቤቱ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።"(መዝ38፡4)። እንዲህ ዓይነቱ ስሜት የነበረው ነቢዩ ዳዊት ውስጥ ብቻ አልነበረም። በሁልም ቅዱሳን አባቶች ውስጥ እንጂ። ሓወርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፡-"እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ . . . እንግዶች መጻቶኞች እንዲሆኑ ታመኑ። " ፥" ………አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ።" ዕብ11፡13 እና 16። ዘላለማዊነትን ማስታወስ ኋጢአት ከመስራት ስለሚጠብቅ መናንያን አባቶች ሁሉ ሞታቸውን እያሰቡ ይኖራሉ።
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
ተኝተው አገኛቸው +
ሐሙስ ማታ ነው ፤ መከራው ከፊት ቀርቦአል፡፡ ጌታን የሚይዙት ሰዎች ሰይፍና ጦር ይዘው ሊመጡ ቀርበዋል፡፡
ጌታችን ሦስቱን ምሥጢረኞቹን ጴጥሮስን ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊያዝንና ሊተክዝ ወደደ፡፡
በታቦር ተራራ የአምላክነት ክብሩን እንዲያዩ የተጠሩት ሦስቱ ደቀ መዛሙርት አሁን ደግሞ በለበሰው ሥጋ ምክንያት የሚቀበለውን ጭንቀት እንዲያዩ ጠራቸው፡፡ በብርሃን የተሸፈነውን ፊቱንና ልብሱን ያዩት እነጴጥሮስ አሁን ደግሞ የደም ላብ ሲያልበው እንዲያዩ ጠራቸው፡፡ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን ተመልከተው ፤ አሁን ሙሴና ኤልያስ አብረውት የሉም ፤ ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ እያዘነች ነው፡፡ አሁን እናንተ በብርሃኑ የወደቃችሁለት ጌታ በፊቱ ወድቆ እየጸለየ ነው፡፡
በዚህች ምሽት እግዚአብሔር አብ እንደ ታቦር ተራራ ‘የምወደው ልጄ’ ብሎ ሲናገር አልተሰማም ፤ ክርስቶስ ‘አባት ሆይ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ’ እያለ ነው፡፡ ሁሉ ነገር በታቦር ተራራ ከሆነው በተቃራኒ እየሆነ ነው፡፡
ጌታችን በመጀመሪያ ከጸለየ በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መለስ ብሎ ሲያይ ተኝተው አገኛቸው፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡ ‘ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው’ ማለት የለ ፤ ‘ሦስት ዳስ እንሥራ’ ማለት የለ! ተኝተዋል፡፡ ጌታችን ብቻውን ነበር፡፡ ጌታችን ጴጥሮስን ‘ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳን ልትተጉ አልቻላችሁም?’ አለው፡፡ በታቦር ተራራ ባበራበት ዕለት አብረው ለመኖር ፈቃደኞች ነበሩ ፤ በመከራው ቀን ግን ለአንዲት ሰዓት እንኳን አብረውት ሊተጉ አልቻሉም፡፡ የሰው ልጅ እንዲህ ነው ፤ ፊትህ በሚያበራ ቀን አብሮህ ነው ፤ ልብስህ ነጭ በሆነ ዕለት ዳስ ልሥራልህ ይልሃል፡፡ ክፉ ቀን ሲመጣና በጭንቀት ውስጥ ስትሆን ግን ሁሉም ጥሎህ ይተኛል፡፡ ለአንድ ሰዓት እንኳን ከጎንህ የሚሆን ታጣለህ፡፡
ጌታችን አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ጸለየ ፤ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመለስ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፡፡
ጌታ ሆይ ወደ እኛስ ስንት ጊዜ ተመላልሰህ ይሆን? ስንቴስ ተኝተን አገኝተኸን ይሆን? የታቦር አጃቢዎችህ የጌቴሴማኒ እንቅልፋሞችህ ምንኛ አሳዝነንህ ይሆን? ሰይፍና ጦር ይዞ ጠላት ወደ እኛ እየመጣ ፤ እምነታችንን የሚፈትን ሦስት ጊዜ የሚያስክደን ሌሊት ከፊታችን ቀርቦ ሳለ እኛ ግን እንቅልፋችንን እያጣጣምን ነው፡፡ ግዴለህም ሳትለች ቀስቅሰን፡፡ እንኳን ከእንቅልፍ ቀርቶ አልዓዛርንስ ከሞት ቀስቅሰህ የለም ወይ? እባክህን ተነሡ በለን፡፡
ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ጸልዮ ሲመለስም ደቀ መዛሙርቱ ተኝተው አገኛቸው፡፡ አሁን ግን ተነሡ አላላቸውም፡፡ ‘ከእንግዲህስ ተኙ’ አለ፡፡ የማያስተኛ ይሁዳ ሠራዊት አሰልፎ እየመጣ ስለሆነ እሱ አያስተኛችሁምና እኔ አልቀሰቅሳችሁም ነው ነገሩ፡፡ መትጋት በምትችሉበት ሰዓት ካልተጋችሁ ሰዓቱ ስለደረሰ አሁን ተኙ፡፡ ጠላት ሲመጣ ከጸሎት ከሚያቋርጣችሁ ከእንቅልፍ ቢያቋርጣችሁ ይሻላልና በሉ ተኙ፡፡ ይህን ብሎ ሳይጨርስ ወታደሮቹ መጡ እነጴጥሮስም ደንግጠው ተነሡ፡፡
ለእኛም እንዲሁ ነው ፤ ይሁዳም ሠላሳ ብር ተቀብሏል ፤ ሮማውያንም ወታደር ልከዋል ፤ ጸሐፍትም ከፊት እየመሩ ነው ፤ ማልኮስም ጆሮውን አቁሞ እየመጣ ነው ፤ መንፈስ ተዘጋጅታለች ፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው ፤ አቤቱ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኛ ትለፍ ፤ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኛ ፈቃድ አይሁን ፤ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ!
ዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ ሲል ይጠይቃል ፡- ‹‹አብርሃምን ይፈትነው ዘንድ እግዚአብሔር ለምን ወደደ? ይህን ጻድቅ የማያውቀው ከሆነስ ስለምን ወዳጅ አደረገው?›› ብሎ ከጠየቀ በኋላ ይህንን ያደረገው ‹‹ስለ አምላካዊ ምሥጢር ነው እንጂ›› ብሎ ይደመድማል፡፡
ሊቁ በዓርብ ስቅለት ዕለት በቤተ ክርስቲያናችን በሚነበበው ድርሳኑ ይህ ምሥጢር ምንድር ነው? የሚለውን ሲገልጽ ‹‹አኮ እግዚአብሔር ፈቂዶ ወየኀሥሥ ኪያሁ ሠዊዖቶ ለይስሐቅ አላ ከመ ይኩን አርኣያ ወአምሳለ ለቅትለተ ወልደ እግዚአብሔር ዐቢይ›› ይላል ፤ ሲተረጎም ‹‹እግዚአብሔር ይስሐቅ መሠዋቱን ፈልጎ አይደለም ፤ ለታላቁ የእግዚአብሔር ልጅ መገደል አርኣያና አምሳል ይሆን ዘንድ ነው እንጂ›› ማለት ነው፡፡ (ግብረ ሕማማት ዘዓርብ መዓልት ፫)
ይህንን ከማብራራታችን በፊት ጌታችን የተናገረውን አንድ ቃል እናስታውስ፡፡ በአንድ ወቅት አይሁድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሲከራከሩ ‹‹አንተ ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህን? ብለው ጠይቀውት ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ አየም ደስም አለው›› አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት፡፡ ኢየሱስም ፡- እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው፡፡ ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሔደ›› (ዮሐ. ፰፥፶፫‐፶፱) ጌታችን ከአብርሃም በፊት ነበርሁ ያለው አሁን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆኖ የተገለጠው ቃል እርሱ በመጀመሪያው ከዓለም በፊት የነበረ መሆኑን የሚያስረዳ ስለሆነ ግልጽ ነው፡፡ ‹‹አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ ፤ አየ ደስም አለው›› የሚለው ቃል ግን ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ጌታችን ‹ቀኔ› ያለው የትኛውን ቀን ነው? አብርሃምስ ጌታችንን ያየበት ቀን መቼ ነው? አይቶት ደስ ያለውስ መቼ ነው?
የዚህ ጥያቄ መልስ ከላይ ወዳየነው ታሪክ ይመልሰናል፡፡
እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅህን ሠዋልኝ ያለበት ዋነኛው ምክንያት አብርሃም የእግዚአብሔርን ልጅ ቀን እንዲያይ ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በምሳሌ አገኘው›› እንዳለ አብርሃም በዚያ ተራራ ጌታችንን አየው ‹‹ወተፈስሐ አብርሃም በዕለተ ወልደ እግዚአብሔር ዘርእየ በአምሳለ ወልዱ›› ‹‹አብርሃምም በልጁ አምሳል ባየው በእግዚአብሔር ልጅ ቀን ደስ አለው››
አብርሃም ወደ ተራራው እስከሚደርስ ለሦስት ቀናትና ሌሊቶች በሕሊናው ውስጥ ልጁን ይስሐቅን ሠውቶ ፣ በሃሳቡ መቃብር ውስጥ ልጁን ገድሎ የሰነበተው ለካንስ ሦስት ቀንና ሌሊት ሞቶ በመቃብር የሚያድረውን የእግዚአብሔርን ልጅ ያይ ዘንድ ነበር፡፡ ልጁን በመሠዋት ከባድ ውሳኔ ውስጥ ሲሰቃይ የሰነበተው ‹አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዷል›› ተብሎ የተነገረለትን ፣ ‹ለገዛ ልጁ ያልራራለት›ን የእግዚአብሔር አብን የፍቅሩን መጠን ከሰው ሁሉ ቀድሞ እንዲረዳው ነበር፡፡ (ዮሐ. ፫፥፲፮ ፣፩ዮሐ. ፫፥፲፯) ምሥጢረ ሥላሴን በድንኳኑ የተማረው አብርሃም ምሥጢረ ሥጋዌን በሞርያም ተራራ ይማር ዘንድ ይገባው ስለነበር ነው፡፡
ነገሩን አልን እንጂ አብርሃምስ ሁለቱን ምሥጢራት ብቻ በመማር ሳይወሰን በግዝረት ምሥጢረ ጥምቀትን ፣ በመልከ ጼዴቅ ምሥጢረ ቁርባንን ፣ በይስሐቅ ከሞት መዳን ደግሞ ምሥጢረ ትንሣኤን የተማረ ፣ ብሉይ ኪዳን ላይ ቁጭ ብሎ የሐዲሳት ጉባኤ ላይ የዋለ ፣ ምሥጢር ያደላደለ ሊቅ ነው፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ አብርሃም ወደ ተራራው ሲወጣ ሎሌዎቹን እዚህ ቆዩ ለምን አላቸው የሚለውን ‹‹የእግዚአብሔርን ልጅ ቀን ያይ ዘንድ ብቻውን ሊወጣ ስለወደደ ነው›› ብሎ ካብራራ በኋላ አብርሃም እንዴት የእግዚአብሔር ልጅ ቀን የተባለችዋን ዕለተ ዓርብ እንዳያት እንደዚህ ያብራራል፡-
‹‹ይስሐቅ ብቻውን ዕንጨቱን ተሸከመ ፤ ይስሐቅ በትከሻው ላይ ዕንጨትን መሸከሙ የጌታችን የክርስቶስ ዕፀ መስቀልን የመሸከሙ አምሳል ነው፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ከአገልጋዮች አንዱን ‹አንተ ዕንጨቱን ተሸከም ወደ ተራራውም ውጣ አድርሰህም ወደ ቦታህ ተመለስ› እንዴት አይለውም ነበር? ነገር ግን ይህን ያደርግ ዘንድ የጌታ ምሥጢር አላሰናበተችውም›› ይላል፡፡
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የሚሞትበትን የዕንጨት መስቀል ተሸክሞ ተራራ እንደ ወጣ ይስሐቅም የሚሠዋበትን ዕንጨት ተሸክሞ ወደ ተራራ ጫፍ ወጣ፡፡ ‹‹በእግዚአብሔር ልጅ የሞት መንገድ ንጹሕ ይስሐቅ ተጓዘ›› የአብርሃም ሎሌዎች አህያውን ይዘው ከተራራው በታች እንደቀሩ እንደ አህያ የሕግ ቀንበር መሸከም የለመዱ አይሁድና ተከታዮቻቸው ከተራራው ከቀራንዮ ምሥጢር የተለዩ ሆኑ፡፡ የሚያስደንቀው ጌታችን የተሰቀለበት ቀራንዮ ያለበት ተራራ አብርሃም ልጁን ሊሠዋ የወጣበት የሞርያ ተራራ ራሱ መሆኑ ነው፡፡ አብርሃም በዚያች ዕለት በልጁ በይስሐቅ ምሳሌነት የእግዚአብሔር ልጅ ቀን የተባለችዋን የመድኃኒትን ቀን ዕለተ ዓርብን ተመለከታት፡፡
ልጁ ይስሐቅ ዕንጨት ይዞ ሲወጣ ባየው ጊዜ ወልድን መስቀል ተሸክሞ አየው፡፡ ልጁ ይስሐቅ ‹አባቴ ሆይ የመሥዋዕቱ በግ የታለ?› ብሎ በመጠየቅ ራሱ መታረዱ እንዲቀርለት ወይም እንዲያልፍለት የሚያደርግ ጥያቄን ባቀረበለት ጊዜ ‹አባት ሆይ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ› ያለው የጌታ ቃል ለአብርሃም በምሳሌ ተገለጸለት፡፡ ስለዚህ አብርሃም የክርስቶስን ቀን አየ ፤ ደስም አለው፡፡
አብርሃም ልጁን ሊሠዋ ጫፍ ከወጣ በኋላ ፣ ይስሐቅም ዕንጨቱን ተሸክሞ ከደከመ በኋላ ይስሐቅ አልታረደም ፤ ቅዱስ አትናቴዎስ ‹‹የይስሐቅ ሞት ለዓለም ነጻነትን አይገዛም ፤ ነጻነታችን ሊሆን የሚችለው በእርሱ ቁስል ሁላችን በተፈወስነው በመድኃኒታችን ሞት ብቻ ነው›› ይላል፡፡
አብርሃም አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዛፉ ቅርጫፎች ታስረው አየ ፤ በይስሐቅ ፈንታም በጉን ሠዋው፡፡ አሁን አንድ ጥያቄ መጠየቃችን አይቀርም፡፡ አብርሃም የእግዚአብሔርን ልጅ ያየው ባልተሠዋው በልጁ በይስሐቅ ነው ወይንስ በተሠዋው በግ? ከሁለቱ የትኛው ነው የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው? ማለታችን አይቀርም፡፡ መልሱ ሁለቱም የክርስቶስ ምሳሌ ናቸው ፤ አብርሃምም በሁለቱም ክርስቶስን አይቶ ደስ ብሎታል፡፡ በይስሐቅ ውስጥ ክርስቶስን መስቀል እንደተሸከመ አየው፡፡
ከዛፍ ሐረግ ውስጥ እንደታሰረ በወጣው በግ በታተመ ድንግልና ከድንግሊቱ ተወልዶ የተገኘውን ሕጻኑን ክርስቶስ ፣ ቀንዶቹ በዛፍ ቅርንጫፍ በመታሰሩ ደግሞ በራሱ ላይ የእሾኽ አክሊል የደፋውንና በኋላም ዕፀ ሳቤቅ ከተባለው መስቀል ጋር የተቸነከረውን ክርስቶስን አየው፡፡ ይስሐቅና በጉ የክርስቶስ የአምላክነቱና የሰውነቱ ምሳሌ ሆኑ ፤ በበጉ መሞት የክርስቶስን በሥጋ መሞት ፤ በይስሐቅ አለመሞት ውስጥ ደግሞ የክርስቶስን በመለኮቱ የማይሞት መሆኑን አየ፡፡ ‹‹በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ›› (፩ጴጥ. ፫፥፲፰) ስለዚህ አብርሃም ጌታችን እንዳለው ዕለተ ዓርብን አይቶ ደስ አለው ፤ ሐሴትንም አደረገ፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አብርሃም ለያዘው ቢላም ሐዲስ ኪዳናዊ ትርጓሜ አግኝቶለታል፡፡ ‹‹እንጨቱን ሳይ መስቀሉን ቀድሜ አውቃለሁ ፣ የመሠዊያውን ተራራ ሳይ ጎልጎታን አውቃለሁ ፣ ቢላውን ሳይ ደግሞ ክርስቶስ ጎኑን የተወጋበትን ጦር አያለሁ›› ይላል፡፡ አብርሃም በዚህ ታሪክ መሠረት ልጁን በሕሊናው መሠዋቱ ምክንያት የእግዚአብሔር አብ ምሳሌ ሆነ፡፡ ሆኖም አብርሃም በልጁ ፈንታ የሠዋው በጉን ነበር፡፡ ከአብርሃም በኋላ የተነሣ ዮፍታሔ የተባለ መስፍን ደግሞ በግ ሊሠዋ ሲገባው በበግ ፈንታ ልጁን ሠውቷል፡፡ ‹እግዚአብሔር አብ ያደረገ
#አንደበቴም_ያውጣ
አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋር
አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ
አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣዖት እንድሰግድ ነገሥታት ቢያውጁም
ሁሉ ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድሀኔዓለም
አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋር
💚 💚
💛 💛
❤️ ❤️
የክርስቶስ ደም ዛሬም ሕያው ነው †
የክርስቶስ ደም እንደማንኛውም ሰው ዓይነት የሆነ የተራ ፍጡር ደም ሳይሆን መለኮት የተዋሐደው ሕያው ደም ነው።የክርስቶስ ደም አንድ ጊዜ ፈሶ የቀረ ደም ሳይሆን ዛሬም ድረስ ትኩስ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ሕያው ደም ነው።የክርስቶስ ደም ከፈሰሰ ሁለት ሺ ዓመት አለፈው የምንለው በሰው ሰውኛ አቆጣጠር ነው በእግዚአብሔር አቆጣጠር ግን ደሙ ከፈሰሰ ገና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ነው አንድ ሺህ ዓመት በፊቱ እንደ አንዲት ቀን ነች ተብሎ ተጽፏልና፤ ስለዚህም ደሙ ትኩስ ነው።ከተዋሐደው መለኮት የተነሳም ደሙ ዘለዓለማዊ ነው።መለኮት በባሕርይው በዘመናት የማይለወጥ፣ ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው።መለኮት የማያረጅና የማያፈጅ ነው።መለኮት የማይሻርና የማይለወጥ ነው።በደሙ በኩል የተገኘው የኃጢአት ሥርየትም ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው።መጽሐፍ እንደሚነግረን በዕለተ አርብ ለሰው ልጆች የኃጢአት ሥርየት የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ዛሬም ድረስ ላመነበት ሁሉ ሕያው መታረቂያ አድርጎ አቁሞታል።
ሮሜ 3 ፥23 " ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
24፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
25፤ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ #አቆመው ።"
በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለውን ትውልድ ሁሉ ከበደል ያነጻ፣ ከርኩሰት የቀደሰ፣ እርግማንን ሽሮ የልጅነትን ሥልጣን ያጎናጸፈ የነፍሳችን የድኅነት ዋስትና የተረጋገጠበት የክብር ዘውድ ነው።ይህ ደም ዛሬም በክርስቶስ ቤዛነትና መድኃኒትነት አምኖ ኢየሱስ አዳኜ ነው፣ኢየሱስ መድኃኒቴ ነው፣ኢየሱስ ስለ እኔ ኃጢአት ተላልፎ የተሰጠ ምትኬ፣ ቤዛዬ ነው ብሎ በእምነት ለተቀበለ ሁሉ በደሙ ኃይል ዛሬም የኃጢአት ሥርየትና ይቅርታን ሲሰጥ የሚኖር የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።ደሙ ስላለፈው አዳማዊ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዛሬውም መተላለፋችን ወደፊትም ለሚፈጸመው የትውልድ በደል ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ጊዜ ቀረቦ ለዘለዓለም መታረቂያ የሆነ ሕያው መስዋዕት ነው።ከክርስቶስ ደም ውጪ እግዚአብሔር ሰውን የሚታረቅበት የጽድቅ መንገድ የለም።ከክርስቶስ ደሙ ውጪ እግዚአብሔር የሚደሰትበት የድኅነት መስዋዕት የለም።ደሙ ዛሬም በኃጢአትና በዲያብሎስ ክፋት ሁሉ ላይ ኃይል አለው። የደሙን ኃይል አልፎ የሚወቅስ ኃጢአት የለም።የደሙን ጉልበት ጥሶም የሚወርድ መዓት የለም። ደሙ ከዲያብሎስ ወቀሳና ከመለኮት ቁጣ የምናመልጥበት ዋስትናችን ነው።
እግዚአብሔር እኛን የሚያየን በልጁ ደም በኩል ነውና ኃጢአታችንን ደሙ ይጋርደዋል።እግዚአብሔር የሚሰማው የደሙን ጩኽት ነውና የከሳሽ ጩኽት አድማጭ የለውም።ይህ ደም እግዚአብሔር ዓለሙን የታረቀበት ከመስዋዕቶች ሁሉ የላቀ መስዋዕት ነው።ይህ ደም እንደ ኦሪቱ መስዋዕት በየዓመቱ የሚታደስ ደም አይደለም አንድ ጊዜ ፈሶ ያረጀውን ሲያደስ የሚኖር ደም ነው እንጂ። ይህ ደም እንደ ጠቦቶችና ጊደሮች ደም በሰው ግምባር ላይ የሚረጭ ደም አይደለም በልባችን ላይ ታትሞ ነፍስና መንፈሳችንን ሲቀድስ የሚኖር ደም ነው እንጂ።
ማንም የበደለ፣በኃጢአትና በነውር የረከሰ ቢኖር በንስሐ ወደ ክርስቶስ ይቅረብ ይቅርታና ምሕረት ይበዛለታል ።ንስሐ ጸጸት ነው።ንስሐ ስላለፈ ኃጢአት ራስን በመውቀስ ዳግም ላለመበደል በቁርጥ ኅሊና ወስኖ በክርስቶስ ፊት ራስን ዝቅ ማድረግ ነው።ከኃጢአት ለመራቅ ከወሰንን በኋላ መልሰን በድፍረት ኃጢአት የወደቅን ከሆነ ግን የደሙን ዋጋ አክፋፍተናልና፣ ዳግም የመስቀሉን ውለታ ንቀን በሌላ በደል ክርስቶስን አሳዝነናልና በቅዱሳን ጸሎት እየታገዝን ዳግም ከውድቀታችን ተነስተን በፊቱ ቆመን ምሕረትን ልንጠይቅ ይገባል ደሙ ሕያው ነውና ሥርየት ይደረግልናል።የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ የሚያስፈልገን ለዚህ ነው የክርስቶስን የደም ውለታ በድፍረት ኃጢአት ስናክፋፋ ከክርስቶስ ጋር የምንታረቀው በንስሐ ውስጥ ሆነን በቅዱሳን ጸሎት በመታገዝ ነው።ሥርየትና ይቅርታ የሚሰጠን ግን ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል"1ዮሐ 1፥8 የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ ሊቀበለው የተገባ ነው።
መጽደቂያችን ደሙ ነው።የድኅነታችን ዋስትና ደሙ ነው።ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ በራችን ደሙ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ደሙ ክብር እንዲህ ብሏል "አኮ ዘንሰውዕ መስዋዕት ካልዐ ከመ ሊቀ ካህናት አላ ኪያሁ ንሰውዕ በጽድቅ" "ዛሬ የምንሰዋው መስዋዕት እንደ ኦሪቱ ሊቀ ካህናት ዓይነት መስዋዕት አይደለም ራሱን የዕለተ አርቡን መስዋዕት ነው እንጂ።" ብሏል ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ
"ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው።" ዮሐ 6፥54
አብ ሆይ በልጅህ ደም ልጆችህ አድርገኽናልና ክብር ለአንተ ይሁን።
ወልድ ሆይ በደምህ ወደ ሰማያዊት ቅድስተ ቅዱሳን አስገብተኽናልና አምልኮ ለአንተ ይሁን።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከደሙ ጋር ሕብረትን ፈጥረን ሕይወት ሆነኽናልና ውዳሴ ለአንተ ይሁን።
እባካችሁ ትውልድ የደሙን ዋጋ ይረዳ ዘንድ ለሌሎችም አካፍሉት።/ሼር/
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
ክፋትን_ከአንተ_አርቃት።
"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"
#ቅዱስ_ባስልዮስ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
✝ እግዚአብሔር_መፍራት
#ወደ_ፍቅር_መንገድ_ለመድረስ_የመጀመርያው_ፍርሃት_ነው።
• በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው በመጽሓፈ ምሳሌ ላይ " የጥበብ መጀመርያ #እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥…"(ምሳ9፡10) የሚል ቃል አለ፡፡ በዳዊት የመዝሙር መጽሓፍ ውስጥም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቃል አለ፥ መዝ 110 ፡10። ይህ እንዴት ነው የሚሆነው? በፍርሃትና በፍቅር መካከል ያለው ግንኝነት ምንድር ነው? ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ የውሐንስ ግን እንዲህ ይለናል፡- " በፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም . . ."1ኛ የሐ4 ፡18።
#መፍራት_ስትጀምሩ_ለእግዚአብሔር_ትታዘዛላችሁ_ትእዛዛቱንም_ትፈጽማላችሁ።
• ቢያንስ-ቢያንስ የእርሱን ቅጣት ትፈራላችሁ፥ አስፈሪው የፍርድ ቀን ትፈራላችሁ፥ ዘላለማዊ ስቃይ ትፈራላችሁ። የእርሱን ትእዛዛት የምትቀበሉ ከሆናችሁ ግን ለሕይወታችሁ ደስታንና ታላቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙራቱ ውስጥ ስለ #እግዚአብሔር ትእዛዛት ፥ ስለ ሥርዓቶቹና ስለ ሕግጋቱ እንዲህ እያለ ዘምሯል፡- " #የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።"፥ " #የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፡ ልብን ደስ ያሰኛል፥ . . ." ፥ " ሕፃናት ጠቢባን ያደርጋል።" ፥ "ከወርቅ እና ከክቡር እንቁ ይልቅ ይወደዳል ከማር ወለላም ይጣፍጣል፡፡" መዝ18፡ 7- 10። ከዚህ በተጨማሪ ዳዊት በረዥሙ መዝሙሩ ውስጥ እንዲህ ብሏል ፡- " ለባርያህ ተስፋ ያደረግኸውን ቃልህን አስብ፡፡ ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህቺ በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።"፥ "እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።" ፥ " እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።"፥ " የሥራህን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ ትእዛዛህ ግን እጅግ ሰፊ ነው፡፡"፥ " አቤቱ፡- ሕግህ እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።" መዝ 118 ።
#የእግዚአብሔር_ትእዛዛት_በመውደድ_መልካም_የሆነውን_እንወዳለን።
#መልካም_የሆነውን_በመውደድ_ወደ_እግዚአብሔር_ፍቅር_እንደርሳለን።
#ብጽዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
አጠር ያለ አስተማሪ መልዕክት
አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ እያለ
በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር
ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብ ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ
አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ
ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ,,,,,,,እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ
ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት
የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ አማረ
,,,,,,,, ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ ,,,,,, የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ ? አላቸው ,,,,, መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት
አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፈረስከው ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው አለአንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን
ያጣነውን የሰጠን እግዚአብሔርን አእምሯችን
ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን እግዚአብሔርን እንደ ቅዱሳን በእምነት መፅናትን ያድለን አሜን
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker
+++ የመነኩሴው ፈሊጥ +++
መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡ ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡
ከዐቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡ አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሓ ይዞር ነበር፡፡
በአንድ ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡ እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡
ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች እንዲህ ድክመታችን ታግሠው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን እንዛዝላ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለሁ፡፡
✝ በጸሎትሕይወት ውስጥ ለመኖር የሚፈልግ ሰው በየዕለቱ #ከቅድሳት_መጻሕፍት ላይ መመገብ አስፈላጊ ነገር ነው። መጽሓፍ ቅዱስ የምናጠናው #እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት መካከል መግባቱን ያፋጥነዋል። ከዚህ ሌላ እንዲህ ያለው ጥናት #ጸሎትን መቀጠል በማስቻሉ መልካም ነው። ከቅዱሳት መጽሓፍት በተለይም ከመዝሙራት መጽሓፍት በተጨማሪ በዕለቱ የሚታሰበው #የቅዱስ_ሰው ሕይወት እና ከአባቶች የሚገኝ የተመረጠ የምናኔ ጽሑፎች ለቀኑ ሽብርና ጭንቀት ሁነኛ መረጋጋትን ያድላሉ፥እኛንም እጃችንን #ለእግዚአብሔር እንድንሰጥ ያዘጋጁናል። እዚህ ላይ አስረግጠን ልንናገረው የምንፈልገው ነገር ቢኖር #እግዚአብሔር በቀን ውስጥ ከሚገኙት ሃያ አራት ሰአታት ውስጥ በጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የሚመለክ #አምላክ አለመሆኑን ነው። #እግዚአብሔር የሙሉውን ቀን #አምላክ ነው። እርሱም ለረዥም ጊዜ እኛን የሚያጅበን ከሆነ እኛ እርሱን ስንይዝ እንቅስቃሴዎቻችን በሙሉ ለተቀደሱት ሰአታት የዝግጅት ጊዜዎች ነው የሚሆኑት። የዚህ ግልባጩም እነዚህ የተቀደሱ #የጸሎት ሰአታት ለቀጣዩ ትግል የሚያጠነክሩን መሆናቸው ነው።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ (#ጸሎት_ንሰሓና_ተመስጦ በአያሌው ዘኢየሱስ ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው)
(.፬ የእግዚአብሔር ባሕርያት /ባሕርያቱ ለእግዚአብሔር/
በዚህ ርዕስ ሥር የምንመለከተው እግዚአብሔር ስለ ባሕርይው የሰው ልጅ እንዲያውቀው በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ከተገለጠው ጥቂቱን ነው፡፡ ከዚህ አልፎ ግን ሰው የፈጣሪውን ባሕርይ መርምሮ የሚደርስበት አእምሮ የሚገልጽበትም ቋንቋ አይኖረውም፡፡ ከዚህ በታች የምንመለከታቸውን የእግዚአብሔር ባሕርያት ናቸው ስንል ከሌላ ከማንም ያላገኛቸው ማንም ደግሞ ከእርሱ ሊወስዳቸው የማይቻለው የራሱ ገንዘቦቹ ናቸው ማለታችን ነው፡፡ ከዚህ ከባሕርይ ገንዘቡም ለፍጡር ቢሰጥ አንዲት ሻማ ብርሃንን ለሌሎች ሻማዎች ብትሰጥ የራሷ ብርሃን እንደማያልቅባት የእርሱም ገንዘቡ የማያልቅበት ነው፡፡
እግዚአብሔር በባሕርዩ፡-
፩. ዘላለማዊ /ሕያው/ ነው
እግዚአብሔር የሌለበት ጊዜ የለም፡፡ ፍጥረታትን ከመፈጠሩ በፊት በባሕርዩ የኖረ ነው፡፡ የሚታዩትና የማይታዩት ፍጥረታት ከእርሱ ተገኙ እንጂ እርሱን የፈጠረ/ያስገኘ ማስገኘትም የሚቻለው ሌላ ኃይል የለም፡፡እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ነበረ፡፡ የጊዜና የዘመን ፈጣሪንና ባለቤት እንጂ ዕለትና ጊዜ እርሱን አይቀድሙትም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ስለዚህ ምስክር ነው፡-
‹‹ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ›› /መዝ. ፹፱፥፪/
እግዚአብሔር በራሱ የነበረ ያለና የሚኖር ስለሆነ በጊዜ አይወሰንም ጊዜም እርሱን አይወስነውም፡፡ በባሕርይውም እርጅናና መለወጥ የለበትም፡፡
‹‹አቤቱ አንተ አስቀድመህ ምድርን መሠረትህ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው፡፡ እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ፡፡ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል እንደ መጎናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፣ ይለወጡማል፡፡ አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመትህም ከቶ አያልቅም››/መዝ. ፻፩፥፳፭-፳፯/
ከእግዚአብሔር በፊት የነበረ መጀመሪያ አልነበረም፡፡ ከእርሱም በኋላ የሚኖር መጨረሻ አይኖርም፡፡ እርሱ መጀመሪያና መጨረሻ ፊተኛና ኋለኛ ነው፡፡
‹‹የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እኔ ፊተኛ ነኝ እኔ ኋለኛ ነኝ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም፡፡›› /ኢሳ. ፵፬፥፮/
በተጨማሪም የሚከተሉት ጥቅሶች የእግዚአብሔርን ዘላለማዊነት ይገልጣሉ፡፡ /ራዕይ. ፩፥፲፰፤ ፩ኛ/፣ ጢሞ.፩፥፲፯፣ ዘፀ. ፫÷ ፲፬/
፪ኛ. ምሉዕ ነው
እግዚአብሔር የሌለበት/የማይኖርበት ቦታ የለም፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው በጊዜ እንደማይወሰን ሁሉ በቦታም አይወሰንም፤ በሁሉም ቦታ እርሱ አለ፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ሙሉ እንደሆነ ልበ አምላክ ዳዊት እንደዚህ ገልጾታል፡፡
‹‹ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፡፡ ወደ ጥልቁም ብወርድ አንተ በዚያ አለህ፡፡ እንደ ንስር ክንፍን ብወስድ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበር በዚያ እጅህ ትመራኛለች ቀኝህም ታኖረኛለች››/መዝ. ፻፴፰-፯-፲/
በነብዩ ኤርምያስም አድሮ እግዚአብሔር ምሉዓ ባሕርይነቱን ገልጧል፡፡
‹‹እኔ ቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም ይላል እግዚአብሔር ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ እኔ አላየውምን? ሰማይና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን ይላይ እግዚአብሔር›› /ኤር. ፳፫፥፳፫ እና ፳፬/
በተጨማሪም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተመልከት፡፡ /ኢሳ. ፰፥፩፤ መዝ. ፻፪፥፲፱፤ ኢሳ. ፮፥፫/
፫ኛ.ሁሉን ማድረግ የሚቻለው /ከሀሌ ኩሉ ነው/
እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚቻለው የሚሳነው የሌለ ነው፡፡ የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ የሚታየውም የማይታየውም ዓለም የችሎታው ውጤት ነው፡፡ ከተፈጠረው ፍጥረት አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለምና፡፡ /ዮሐ. ፩፥፫/ እግዚአብሔር ሁሉን ያለአማካሪና ረዳት ያስገኘ ስለሆነም ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው፣ ሁሉም በሥልጣኑ ሥር ነው፣ ሁሉን የመወሰን ስልጣን ያለውም እርሱ በቻ ነው፡፡ /ኢሳ. ፵፥፲፪-፲፯፣ ፵፫፥፲፫፤ ፵፬፥፯/
እርሱ ራሱ እግዚአብሔርም ከሣራ ጋር በአደረገው የቃል በቃል ንግግር ሁሉን ቻይነቱን ገልጧል፡፡ ‹‹በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን›› /ዘፍ. ፲፰፥፲፬
ጻድቁ ኢዮብም፡-
‹‹ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደሆንህ የሚሳንህም እንደሌለ አወቅሁ›› ብሏል፡፡/ኢዮ. ፵፪፥፪/ ተጨማሪ ጥቅሶች፡- /ሉቃ. ፲፰፥፳፯፤ ፩፥፴፯፤ መዝ. ፻፴፬፥፮/
፬ኛ. ቅዱስ ነው
እግዚአብሔር በባሕርይው ልዩ ክቡር ነው፡፡ ርኩሰት የማይስማማውም ፍጽም ንጽሕ ነው፡፡ እግዚብሔር የባሕርይ ገንዘቡ በሆነ በዚህ ቅድስናው ከማንም ጋር የማይነጻጸር የሚመስለውም የሌለ ነዉ፡፡
‹‹አቤቱ፡- በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማነው በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው ?››እንዲል፡፡ዘፀ ፲፭÷፲፩
የሳሙኤል እናት ሐናም ይህን የእግዚአብሔርን ልዩ ቅድስና እንዲህ ትገልጸዋለች፡፡ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና›› /፩ኛ ሳሙ. ፪፥፪/
ቅዱሳን መላእክትም ይህን የእግዚብሔርን ዘላለማዊ ቅዱስና በመግለጥ ያለማቋረጥ እንዲህ እያሉ ያመግኑታል፡፡ ‹‹ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የነበረውና ያለው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ›› /ራዕ. ፬፥፰/
ለዚህም ነው ቅዱስና ገናና ንጹሐ ባሕርይ እግዚአብሔር ሰውን በአርአያውና በምሳሌው በንጽሐ ባሕርይ ለክብር ስለፈጠረዉ የሰው ልጅ ከማንኛውም ርኩሰት ራሱን እንዲያነጻና በቅድስና እንዲኖር የታዘዘው፡፡ ‹‹የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እንዲሁ እናንተም በአካሄዳችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁሉ፡፡›› /፩ኛ ጴጥ. ፩፥፲፭/
ለግንዛቤ ያህል ከላይ ያሉትን ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት አነሳን እንጂ የእግዚአብሔር ባሕርያት እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡ አስቀድመን እንደተመለከትነው ፍጡር የፈጣሪውን ባሕርይ ሰፍሮ ቆጠሮ ዘርዝሮ የሚጨርሰው አይደለምና፡፡
፭ኛ. እግዚአብሔርን ማየትና ሙሉ ለሙሉ ማወቅ አለመቻሉ፡-
እግዚአብሔር በባህርይው ፍፁም መንፈስ ስለሆነ ሊታይና ሙሉ ለሙሉ ሊታወቅ አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን የሚመስል ከቶ ምንም ነገር የለም፡፡
ሐዋ 17÷29 “አምላክን በሰው ብልኀትና ሐሣብ የተቀረፀውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባም፡፡” ተብሎ እንደተፃፈ እግዚአብሔርን ማንም ያየው ሰው እንደሌለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አረጋግጦአል፡፡ ሉቃ 10÷22 “ውሱን የሆነው የሰው ዐይን ውሱንነት የሌለውን እግዚአብሔርን ማየት አይቻለውም፡፡ ፀሐይን እንኳ ትኩር ብለን በዐይናችን ለማየት የማንችል ከሆነ እንዴት አድርገን በባህሪው ፍፁም ረቂቂና ምሉዕ የሆነውን መለኮት ልናየው እንችላለን? መላዕክት እንኳን ከሰው በበለጠው ረቂቃን ሆነው ቢገኙም ረቂቁን (በባሕርዩ) የሆነው እግዚአብሔርን አይተውት አያውቁም፡፡ ነገር ግን ሰው እና መላዕክት እግዚአብሔርን በባሕርየ መለኮቱ አይተውት ባያውቁም አቅማቸው ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸውን ያህልና ሊረዱት በሚችሉበት ሁኔታ እግዚአብሔር ራሱን በዘፈቀደ በልዩ ልዩ ምሣሌዎች ይገልጽላቸዋል፡፡
ለምሣሌ ፡- ኢሣ 6÷2 “ሱራፌል ፊትህን ማየት አይቻለንም ብለው በክንፋቸው ፊታቸውን እንደሚሸፍኑ ተገልጿል፡፡”
ለሙሴ በእሳት ነበልባል መልክ ዘፀ 3
ለኢሳያስ በዘፍን ላይ ባለ ንጉሥ አምሳል ኢሳ 6
ለዳንኤል በራዕይ በሽማግሌ ዳን 7÷13-14
ለብርሃም በሦሥትነት እና አንድነት እንደ ሰው በሽማግሌ አምሳል ዘፍ 1÷9፡18 በመሆን ተገልጦላቸዋል፡፡
@menfesa_wimker
@menfesa_wimker