* ሀልወተ እግዚአብሔር *
ሀልወተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው ። እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም የሚሉ አሉና ከሱ እንጀምር ። ታዲያ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል ? ቢሉ ። 1ኛ.በስነ ፍጥረት ይታወቃል ። ም/ቱም ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለና ። ስዕል ካለ ሰዓሊው አለ ፣ ቤት ካለ አናፂ አለ ፣ ሙዚቃ ካለ ሙዚቀኛው አለ ማለት ነው ። ስለዚህ በዚ መሰረት ስናየው ይሄ ሁሉ ስነ ፍጥረት አስገኚ አካል ወይም ፈጣሪ አለው ማለት ነው ። 2ኛ. የሰው ልጆች ዝንባሌ ነው ።ይህም ማለት ግማሹ ሙስሊም ፣ ግማሹ ቡዲስት ፣ ግማሹ ክርስቲያን ፣ ግማሹ ባዕድ አምልኮ አምላኪ የሆነው ነብሱ ከውስጥ የፈጠራት አካል እንዳለ ስለምትጮህ ነው ። ስለዚ ይህም አንዱ የፈጣሪ መኖር ማስረጃ ነው ። 3ኛ.የቀናትና የወቅቶች መፈራረቅ ነው ። ይህም ለምሳሌ መብራት ሲጠፉና ሲመጣ መብራት ሀይል የሚባል አካል እንዳለ እንደምንረዳው ሁሉ ፡ የቀንና የማታ የበጋና የክረምት መፈራረቅም አምላክ እንዳለ ማስረጃ ናቸው ። ፀሀይን በቀን ጨረቃን በማታ ያሰለጠነ ቀኑን ለሰራዊት ሌሊቱን ለአራዊት ያደረገ አምላክ መሆኑን እናውቅበታለን ።የስነ ፍጥረት አይነቱ ብዛቱ ድንቅ ነው ። 1ፀሀይ ሆና ለአለም ሁሉ እንድታበራ ማን አደረጋት ? የዛፎቹ አይነት አንዳንዱ ቅጠሉ ሰፊ አንዳንዱ ቅጠሉ ቀጭን ፣ የአእዋፏቱ አይነት ፣ የአሶችና የሌሎች ባህር ውስጥ ያሉ ነብሳት መኖር ፣ ስናይ ፈጣሪ እንዳለ እንረዳበታለን ። ለውቅያኖሶች ዳርቻዎቻቸውን የወሰነላቸው ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበቦች ያስጌጠ ስራው ድንቅ የሆነ አምላክ የመኖሩ ማስረጃ ናቸው ። ሸክላና ተሽከርካሪ ፣ መርከብና አየር በራሪ ፣ ድልድይና አስፓልት ፣ መኪናና ሌሎችም ሞተር ነክ ነገሮች ፣ ታሪካውያን ህንፆዎች ፣ የሚያስገርሙ ነገሮች ሁሉ ያለ ሰሪ ፣ አትክልትና አዝርዕት ያለ መሬትና ያለ ዘሪ ፣ ልጅ ያለ እናትና አባት እንደማይገኝ ሁሉ ግዑዛንና ግዙፉን ጥቃቅንና ረቂቃን ፍጥረት ሁሉ ያለ ፈጣሪ እንዳልተገኙ እናምናለን ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚታየው ከማይታየው እንደሆነ እናምናለን" እንጂ ዳዊት በመዝሙር 13:1 "ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል" እንዳለው አምላክ የለም አንልም
📖ኦሪት ዘፍጥረት 2፥1-3📖
1.“ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።”
#ሠራዊቶቻቸውም : - በውስጣቸው ያሉት ፍጥረታትንም ሁሉ ፈጥሮ ጨረሰ።
🌍 @yemetshaf_qdus_tinat 🌌
2.“እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።”
#ሰባተኛው_ቀን : - ብርሃንና ጨለማ የተለያዩበት ከስነ ፍጥረት የመጀመርያው ቀን(እሁድ) አንስተን አዳም እስከ ተፈጠረበት(አርብ) ያለውን የብርሃንና የጨለማ ዑደት(ዙር፣መፈራረቅ) ብንቆጥር 6ቀን ይሆናል ስለዚህ ሰባተኛዋ ቀን ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመርያዋ ሰንበት) በአይሁድ "sabbath" የምትባለዋ ናት።የመጀመርያዋ ሰንበት ወይም ቀዳሚት ሰንበት (በተለምዷዊ አጠራር ቅዳሜ) የመባልዋ ምክንያት #እሁድም ሁለተኛዋ ሰንበት(የክርስቲያን ሰንበት፣ሰንበት ዓባይ፣የጌታ ቀን) ተብላ ስለምትጠራ ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር ከመፍጠር ያረፈው በሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚት ሰንበት ላይ ነው።
⏩ @yemetshaf_qdus_tinat ⏪
#ዐረፈ : -በስድስቱ ቀናት ከፈጠራቸው ፍጥረታት ተጨማሪ መፍጠርን #አቆመ #ተወ ማለት ነው እንጂ ፈጣሪ ውጣ ውረድ ድካም የለበትም!!።ይህ ቃል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫም ነው። እንዴት? በሰባተኛይቱ ቀን ከስራው ሁሉ ዐረፈ ካለ በኋላ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አይልም አንድ የዕረፍት ቀን ላይ ነው።ፍጥረቱ የሆነው የሰው ልጅ ደግሞ ወደእርሱ እንዲመጣ(እርሱን እንዲያውቅ) በቃሉም እየኖረ እንዲያመልከው ከፈጣሪው ጋር ህብረት እንዲያደርግ ይፈልጋል።
📜 @yemetshaf_qdus_tinat 📜
እስራኤል ከግብፅ ሲወጡ ለአብርሃም ወደ ማለለት ምድር ይገቡና እርሱን እያመለኩ በመንፈሳዊ ሐሳብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖራቸው ነበረ ዓላማው ይህም ለዘለአለማዊው ከእግዚአብሔር ጋር የመኖርን ምሳሌ ነው።በእምነት ቃሉን ሰምተው እየታዘዙት መኖር በመንፈስ ዕረፍቱን መውረስ መካፈል ነው።ነገር ግን ከግብፅ የወጡት ቃሉን ሰምተው አላመኑም ባለመታዘዝ አሳዘኑት ፈጣሪም ከኔ ጋር አንድነት ዕድል ፈንታ የላቸውም አለ።
@yemetshaf_qdus_tinat
⚠️“ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤”— ዘኍልቁ 14፥23
⚠️መዝ94(95)፥10-11 “ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ።ወደ #ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።”
💠ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ዕረፍት በዕብራውያን መልእክቱ ሲያብራራው እንዲህ ይላል
👉“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር #በእምነት_ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።ስለ #ሰባተኛው_ቀን በአንድ ስፍራ፦ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤በዚህ ስፍራም ደግሞ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም።እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ #ዛሬ_ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ #በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ #አንድ_ቀን እንደ ገና ይቀጥራል(ይወስናል)።” ዕብ4፥1-7
🛐 @yemetshaf_qdus_tinat 🛐
3.“እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።”
#ባረከው_ቀደሰውም : - መልካም ነገር እንዲያስገኝ መልካም እንዲሆን መረቀው ለራሱም ለየው።
#በረከቱም እስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ መሪነት ከባርነት ወጥተው አምላካቸውን አውቀው ህግም በተሰጣቸው ጊዜ ከባርነት ወጥተው ብቻ ሳይሆን ከስጋ ስራም በእግዚአብሔር ስራና ዕረፍት ምሳሌ 6 ቀን ሰርተው በሰባተኛይቱ ቀን እንዲያርፉ ሲታዘዙ፤ከሰማይ ይዘንብላቸው የነበረው መና ለነገው ማሳደር አልተፈቀደላቸውም ለቀኑ በቅቷቸው ካደረ መናው ይበላሻል ለየቀኑም አዲስ የዘነበ ይበሉ ነበር በስድስተኛይቱ ቀን ግን ከዘነበው መና የሁለት ቀን ይሰበስቡና በሰባተኛይቱ ቀን መናም አይዘንብም ያደረውም አይበላሽም አርፈው ይመገቡት ነበር (ዘጸ16)።
📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
¹⁰ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
¹¹ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎
“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡
እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡
የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
"ፍትወት ያጠፍኦ ለሂሩት፤ ፍላጎት ቸርነትን ያጠፋል" (መጽሐፈ ገነት)
✨ፈተወ ማለት ፈለገ፣ ወደደ፣ ከጀለ፣ ተመኘ፣ ጎመጀ የሚሉ ፍካሪያት ያለው ቃል ነው። ነገሩ ክፉና ደግ የሚሆነው ግን በአስደራጊ፣ በአድራጊ፣ በአደራራጊ፣ በተደራጊ፣ በድርጊት ነው። ለምሳሌ፦ ፍላጎቱ፣ ምኞቱ፣ ውዴታው፣ እግዚአብሔርን ማየት ከሆነ አስመኝው ራሱ እግዚአብሔር ነው። ተመኝውም መልአክ ነው፣ አብርሃም ነው። መመኛው ሃይማኖት ነው ምኞቱም ሥላሴ፣ ድርጊቱም ጽድቅ ነው፣ ዋጋውም መገለጥ ነው። (አብርሃም አባታችሁ ቀኔን ሊያይ ተመኘ አይቶም ደስ አለው) "መላእክትን የሚያስመኛቸው" እንዲል።
አስመኚው ሰይጣን፣ መመኛው ልብ ጠዋይ፣ ክህደት፣ ፈቃደ ሥጋ፣ ፍቅረ ሢመት፣ ትካዘ ዓለም፣ ሀልዮ መንበር፣ ፍቅረ ዉሉድ፣ ብእሲት ወዘመድ፤ ምኞቱም ሹመት ብዕል ድሎት በጥቅሉ የዓለም የልዕልና ማማ ላይ መውጣት የሆነ ጊዜ ግን "እፎ መልዐ ሰይጣን ውስተ ልብከ፤ ሰይጣን በልብህ ስለምን ሞላ?" የሚያስብል ቅዱሳንን ወደ ታች የሚያስደምም ርኩሰት ይሆናል። የሐ.ሥራ ፭፥፬ እንዲህ ያለው ምኞት ነው ቸርነትን የሚያጠፋ የተባለው።
✨ሰው ሁሉ ቸርነትን አቡሃ ለምሕረት ከሆኑ ከሥላሴ ዘንድ ይሻል። ምሕረትን የሚያገኙ ደግሞ ምሕረትን የሚያደርጉ ናቸው። "ብፁዓን መሐርያን እስመ ሎሙኒ ይምሕርዎሙ፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ይማራሉና" እንዲል። ማቴ. ፭፥፯
ይህ ሳይሆን እነርሱ እየጨከኑ ምሕረት የሚፈልጉ ግን አስደራጊው ሰይጣን ምኞቱ ምሕረት ማድረጊያው ጭካኔ ስለሆነ ፍየል ምሥራቅ ምዝግዝግ ምዕራብ መሆኑ ነው። መድኃኒትን በመርዝ መጠጣት እድን ብሎ ቢጠጡት ማዳኑንስ ቀርቶ መግደሉ ይብስ። የሥላሴን ቸርነት እየፈለጉ መጨከንም ማስማሩ ቀርቶ ያስፈርዳል። ወዲህም ጭካኔ የዲያብሎስ ምሕረት የእግዚአብሔር ስለሆነ ከሰይጣን ተነስቶ ወደ እግዚአብሔር ከመቼ ዕለት ወዲህ ተደርሶ ያውቃል? "እምኀበ እግዚአብሔር ይጸንዕ ሑረቱ ለሰብእ የሰው መንገዱ ከእግዚአብሔር የሆነ እንደሆነ ይቀናል" ተብሎ ነውና የተጻፈው። መዝ. ፴፮፥፴፬
✨ወንድሞቼ ሆይ ሞሕረትን የምንፈልግ ከሆነ ምሕረት ይኑረን። ምሕረትንም ለማድረግ ፍላጎታችን እንጠብቅ። ፍላጎት ምሕረትን ይደመስሳልና። የቀደመው ጠላት ምሕረት አጥቶ የቀረው ምሕረት የለሽ ስለሆነ ነው። ምሕረት የለሽ ያደረገውም ፍላጎቱ ነው። የማይገባውን አምላክነት ተመኘ፤ በክህደት ተመኘ፤ ክፋ ፍላጎቱ በአምላኩ ላይስ እንኳ ጨክኖ አምላክ ነኝ አስባለው። ስለዚህ ምሕረት ያልተገባው ሆነ። ይሁዳ በጌታው ላይ ለመሸጥ ያስጨከነው ክፉ የገንዘብ ፍላጎቱ። ጸሐፍት ጌታን ለመስቀል እንጀራ አበርክተው ያበሏቸውን እጆች ለመቸንከር የጨከኑት ክብርና የሥልጣን ፍላጎት ነው። ሄሮድስ በእናታቸው ወተት ቤተልሔም እስክትነጣ፣ በሕጻናቱ ደም እስክትቀላ እነዚያን ሕጻናት ያረዳቸው ያለ ሽረት ከመግዛት ክፉ መጎምጀት ነው። ኮቲባ ለድንግል ለምን ውኃ አልሰጥም አለች? ቅናቷና ስስቷ ነው።
✨ዛሬም ደም የሚያስፈስስ እኔ ብቻ ልኑር ነው። በሚያለቅሱና እንባን ከማሩኝታ ጋር በሚያቀርቡ ዓይኖች ላይ የሚጨክኑ ሾተል የሚመዙ እጆች ደም የተቀባን እንጀራ መጥገብ የሚልጉ ክፋ ልቦች ያበቀሏቸው ናቸው። በትዳራቸው ላይ የሚደፍሩ ለትዳራቸው ምሕረት የሌላቸው "በቃ ይበተን" የሚሉ ክፉ ምኞት የሚገረኛቸው ናቸው። በርህርኂቷ እመቤት፣ በጽድልቷ ንግሥት፣ በወላዲተ አምላክ ጨክነው ከልባቸው አሰድደው የሚሰድቧት የዛሬ ሄሮድሶችም እኔ ልክበር ልበልጽግ ልብላ ከሚል ምቀኛ ልብ የሚወጣ አሳባቸው ነው። አባቶቻችን የሚገባን መመኘት ጠቢብነት ነው የማያገኙትን ሁሉ መመኘት ግን ምቀኝነት ነው ይላሉ። ሰው በድንግል ማርያም ቢቀና እኔም እኮ ከእርሷ ጋር እኩል ነኝ ቢል አምላክን መውለድ አይችልምና አጉል ምቀኝነት ሆኖ ይቀራል።
✨ሄሮድስ የማይተካከለውን እገላለሁ ብሎ ሕጻናትን እንደገደለ ዛሬም እመቤታችንን ከልባቸው አሰድደው በአእምሮ ሕጻናት የሆኑትን የቤተልሔም እርሷ ልጆችን በምንፍቅና ሾተል ያርዳሉ።
ሄሮድስ እመቤታችንን በእኩይ ፍላጎቱ በርኩስ ቅናቱ አሰድዶ ሞተ። ወዳጄ ቅናትና ምቀኝነት እናታችን ከልባችን አንዳያሰድብን እንጠንቀቅ። ስለረከሱ ሕልሞች ስለሚጣፍጡ የሐኬት እንቅልፎች ውዳሴዋን አቋርጠን የምሕረትን ጠል ያዘለችውን ደመና ከእኛ እንዳትሰደድ እንንቃ። ለሄሮድስ መሰለው እንጂ ርግቢቱስ ገላግልቷን ይዛ በበረሃ ጉያ ውስጥ መዐዛዋን እያወደች ነው። ስለ ክፉ ምኞታቸው ሰማይን ከነ ፀሐይዋ አሳድደው ለጨለሙ ሄሮድሶች ይብላኝ እንጂ እርሷስ በየገዳማቱ "ምስለ ወልድኪ ልዑል በዘባንኪ ኅዙል ጎየይኪ እፎ ድንግል ደወል እምደወል" እየተባለች ትወደሳለች። ብቻ ዘመዶቼ በአንድ በጎ ነገር ላይ "አይ ይቅርብኝ" የሚያስብል አሳብ በመጣ ጊዜ የሰይጣን እንደሆነ አስተውሉ። ለቅዱስ ምኞት ያብቃን!!!
(©መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡
እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡
ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"
(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)
ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ኹሉንም_ነገር_ለእግዚአብሔር_እንስጠው
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ወርቅን የሚያነጥር ሰው አንዲትን የወርቅ ቅንጣት ወደ እሳት ውስጥ ጨምሮ እጅግ ንጹህ እስክትኾን ድረስ ይጠብቃታል፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዚሁ ሰዎች እስኪነጹ፣ እስኪለወጡና ባገኛቸው ነገር ጥቅም እስኪያገኙ ድረስ ፈተና ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል፡፡ ይህ ደግሞ ከጥቅምም እጅግ ከፍ ያለ ጥቅም ነው፡፡
ስለዚህ ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም ተስፋ ሊቈርጥ አይገባውም፡፡ ያ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያኽል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኵሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንሔድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቈርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡
ይህን በማስመልከትም ጠቢቡ ሰው እንደዚህ ሲል መክሮናል፡- “ልጄ ሆይ! ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሔድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፤ ልብህን አቅና፤ ኹልጊዜ ታገሥ፤ አታወላውልም፤ በመከራ ብትጨነቅም አትጠራጠር” /ሲራ.2፥1-2/፡፡ “ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ስጠው፡፡” ለምን? እግዚአብሔር ከዚያ መከራ መቼ እኛን ማውጣት እንዳለበት ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ኹሉንም ለእርሱ ልንሰጥ፣ ዘወትር እርሱን ልናመሰግን፣ ኹሉንም ነገር - ጥቅምም ይኹን ቅጣት - በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም ቢኾን ለእኛ ረብሕ የሚኾን ነውና፡፡ አንድ ሐኪም፥ ሐኪም የሚባለው ታካሚውን ገላዉን ሲያጥበውና ሲመግበው እንዲሁም ደስ ወደሚያሰኝ ስፍራ ሲወስደው ብቻ አይደለም፤ በእርሱ (በታማሚው) ሰውነት ላይ የቀዶ ጥገና ምላጭና ቢላ ሲያሳርፍም ጭምር ሐኪም ነው፡፡ አባትም አባት የሚባለው ልጁን ሲንከባከብ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ልጁን ከቤት ሲያስወጣው፣ ሲገሥጸው፣ ሲገርፈውም ያው አባት ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ከሐኪሞችም በላይ ሰውን ወዳጅ እንደ ኾነ በማወቅ፥ ምን ዓይነት የሕክምና ዓይነት እንደሚሰጠን በጥልቀት አንጠይቅ፤ ወይም ደግሞ ለደረሰብን መከራ እርሱን ተጠያቂ አናድርግ፡፡ ከዚህ ይልቅ እርሱ የወደደውን ነገር - ቅጣትም ይኹን ቅጣት የሌለው ነገር - ብቻ ምንም ይኹን ምን በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፡፡ በየትኛውም መንገድም ቢኾን የእርሱ ፈቃድ እኛ እንድንድንና ከእርሱ ጋር አንድ እንድንኾን ነውና፡፡ የትኛው መንገድ ለእኛ እንደሚጠቅምም እርሱ ያውቋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የትኛው መንገድ ወደ እርሱ እንደሚመልሰው ያውቃል፡፡ ኹላችንም እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ልንድን እንደምንችል ያውቃል፡፡ በመኾኑም የሚመራን በዚህ እኛ በምንድንበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ወደየትኛውም መንገድ ቢወስደንም - ልክ እንደ መጻጉዑ - እርሱ እንደሚያዘ’ን ተከትለን መሔድ እንጂ ትልቁ ጉዳያችን በለስላሳና በቀላል አልያም ደግሞ በከባድና በሸካራ ጎዳና እንድንሔድ የሚያዘ’ንን ትእዛዝ መኾን የለበትም (ልንሔድበት የሚገባ’ው መንገድ እርሱ ስለሚያውቀው እንዲሁ መታዘዝ እንጂ የመንገዱን ከባድነት ወይም ቀላልነት የእኛ አጀንዳ ሊኾን አይገባውም፡፡)
(ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልእክታት)
ሚስትህን አትናቃት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡
እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡
በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡
‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”
“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡
ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡
ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክት እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡
አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡
ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡”
✝ አንድ ሰው እግዚአብሔር አስቀድሞ ካነጋገራቸው ሰዎች ጋር እንደተነጋገረ ከእኔ ጋር በቀጥታ አልተነጋገረም ታዲያ የእግዚአብሔርን በረከት እንዴት ልቀበል እችላለሁ ?ለዚህስ እርግጠኛ የምሆነው እንዴት ነው? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ።
ሰው የእግዚአብሔርን በረከት ትእዛዛቱን በመጠበቅ ሊቀበል እንደሚችል እርግጥ ነው ይህ የመታዘዘዝ በረከት ነውና ።
በረከትና ትእዛዛትን በመጠበቅ መካከል ያለው ግንኙነት በኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ በእግዚአብሔር እንዲህ ተረጋግጧል ፦ " የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል ።...አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ ። የሆድህ ፍሬ የምድርም ፍሬ የከብትህም ፍሬ የላምህም ርቢ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል ። አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ ። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል ።. .. እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል ። " [ዘዳ 28*1_8 ] ።
ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን አሥራት በማውጣት ላይ ያለው የእግዚአብሔር ትእዛዝና እርሱ ለሰው ገንዘብ ላይ ያለው መብት ነው ።
አንድ ሰው ገንዘቤ ለእኔ ሳይበቃኝ እንዴት ከዚያ ላይ አስራት ላወጣ እችላለሁ ብሎ በአድናቆት ሊጠይቅ ይችል ይሆናል ። እውነቱን ለመናገር ግን ያለ በረከት ከሚመጣው ጠቅላላ ገንዘብ ይልቅ ከአሥር አንድ የተቆረጠለት ገንዘብ ይበልጣል ። ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ታላላቅ የገንዘብ ገቢ ኖሮአቸው ምንም ሳይበቃቸው የምንመለከተው ገንዘባቸውን ስላላስባረኩ ነው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
*ምክረ አጋንንት*
በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ
ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።
# በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
# ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
# እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።
ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
# ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሄር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።።
+++ የመነኩሴው ፈሊጥ +++
መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡ ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡
ከዐቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡ አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሓ ይዞር ነበር፡፡
በአንድ ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡ እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡
ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች እንዲህ ድክመታችን ታግሠው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን እንዛዝላ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለሁ፡፡
ስም ሲወጣለት ምስጢረ ሥጋዌን ምስጢረ
ተዋህዶን፣ ሥጋዌን ለመግለጽ ነው፣ ስለዚህም ለመዳን የተሰጠን ምስጢር ምስጢረ
ተዋህዶ ነው፣ ምስጢረ ተዋህዶ ባይፈጸም ድህነት የለም፣ ለዚህ ነው ስሙ ልዩ ስም ነው፣
አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም የሆነው አጋንንት የሚፈሯት ተዋሕዶን ነው፣
ዲያብሎስ ድል የተነሣው በምስጢረ ተዋህዶ በምስጢረ ሥጋዌ ነውና፡፡
ምስጢረ ስላሴ ለእኛ ሳይገለጥ ኅቡዕ ይሁን እንጂ በፊትም ነበረ፣ ሌሎችም ምስጢራት
ከምስጢረ ሥጋዌ በኋላ የመጡ ናቸው ከምስጢር ሁሉ የሚበልጠው አስደናቂው ምስጢር
ምስጢረ ሥጋዌ ነው፣ ለምን ቢባል አምላክ ሰው የሆነበት ልዩና ረቂቅ ምስጢር ስለሆነ ነው
ለዚህም ነው ሊቃውንት እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው
የሆነበት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተወለደበት ምስጢር ይበልጣል ያሉት፡፡
‹‹መቼም እግዚአብሔርን ያየው አንድስኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ ተረከው
እንጂ›› ዩሐ 1፡18 እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እግዚአብሔርን አየነው ዳሰስነው
ነካነው ብለን የምንናገርበት ምስጢር ይህ የሥጋዌ ምስጢር ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማንም
አላየውም ነገር ግን በምስጢረ ስጋዌ የእኛን ሥጋ ለብሶ በማርያም ሥጋ ተዳሰሰ ታየ
ሲናገር ተሰማ አፉን ከፍቶ ሲያስተምር ታየ ይህንን ነው ማዳን የሚሉት ቅዱሳት መጻሕፍት
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ነው፣ አዳነን፣ እግዚአብሔር አዳነን ማለት ይህ ነው ይህ
የእግዚአብሔር ማዳን የሚተካ ነገር አይደለም ሌላ ፍጡር የሚጋራው ማዳን አይደለም
እግዚአብሔር በከሐሊነቱ በእግዚአብሔርነቱ የሚያደርገው ብቻ ነው ለምን አዳምን ከሲኦል
ግዛት ነፃ ማውጣት እንደገና በአዲስ ተፈጥሮ በሥጋ ተፈጥሮ መስራት የእግዚአብሔር ብቻ
ገንዘብ ስለሆነ፣ የተዘጋውን ገነት መክፈት የእግዚአብሔር ብቻ ገንዘቡ ስለሆነ ይህ ማዳን
የማይተካ ነው በቅዱሳን መላዕክት በቅዱሳን ጻድቃን በድንግል ማርያም ሊደረግ የማይቻል
ማዳን ነው ይህ ማዳን ደግሞ በዓለም ላይ በዘመናት መካከል የተደረገ ማዳን ነው
በቀራኒዮ አደባባይ ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ያደረገው ማዳን ነው፡፡
ሌላው ማዳን ሁሉ ከዚህ የሚገኝ በረከት ነው፣ ይህ የመጀመሪያው ማዳን ነው የቅዱሳን
ማዳን፣ በጸበል መዳን በእምነት መዳን፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ተሻሽቶ ተሳልሞ መዳን፣
በመስቀል መዳን የምንላቸው ሁሉ በዚህ መዳን ምክነያት የተገኙ ናቸው ይህን ማዳን
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ብለን ቅዱሳን መላዕክት ያድናሉ ስንል ልዩነት አለው ይህንን
አውቀን ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንናገረው ሉተራውያን ወይም መናፍቃኑ እንደሚሉት
ጠቅልለን አይደለም የምንናገረው፣ ምን ማለታችን እንደሆነ አውቀን ተረድተን ነው
የምንመሰክረው፡፡
ለምሣሌ (በመዝ 33፡7) ላይ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል
ያድናቸውማል›› የኢየሱስ ክርስቶስን ያድናል ያለው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ሥፍራ ደግሞ
ቅዱሳን መላዕክት ያድናሉ ይላል፣ ይህ ማለት መላዕክት አዳምን ከሲኦል አውጥተው ወደ
ገነት ይመልሱታል ማለት አይደለም ይህን ማድረግ ለፍጥረታት ስላልተቻለ ነቢዩ ዳዊትም
ሆነ ነቢዩ ኢሳይያስ እጅህን፣ ቀኝህን ከአርያም ላክ አድነንም ሰማዮችን ቀደህ ውረድ (መዝ
143፡5-7 ፣ ኢሳ 64፡1) በማለት ተናግረዋል፡፡
አዳምን ከወደቀበት የሚያነሣ ወደ ጥንት ክብሩ የሚመልስ አልተገኘም ነበርና
እግዚአብሔር ቀኙን ማዳኑን ጥበቡን አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው አዳምን
ለማዳን አበው የእንሰሳት በመስዋዕት፣ ነቢያት በጽድቃቸውና በለቅሶ በጸሎት እንዲያውም
ደማቸውን በማፍሰስ አጥንታቸውን በመከስከስ ሞክረዋል ግን ስላልቻሉ እንዲህ ነው
ያሉት ‹‹ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፣ በደላችን እንደ ነፋስ አፍገምግሞ
ወስዶናል›› ኢሳ 64፡5 ምክንያቱም የሰው ልጅ መዳን ወደ ጥንተ ተፈጥሮ መመለስ
በእነዚህ ቅዱሳን በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብ በሰሎሞን በዳዊት በነቢያቱ የሚሆን
አልነበረም የሚከፈል ካሣ ይጠይቅ ነበረ ስለዚህም ነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ
ራሱ ሊቀ ካህን፣ ራሱ በግ፣ ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ፣ በአንድ ጊዜ ሦስቱንም ሆኖ
መስዋዕት ሰውቶ፣ መስዋዕት ተቀብሎ፣ ራሱ ደግሞ መስዋዕት ሆኖ ድኅነትን ፈጸመልን፡፡
ይህንን ማዳን ማንም ሊያደርገው አይችልም፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን የተለየ ማዳን ነው የኦሪቱም ሊቀ ካህናት የሐዲሱም ሊቀ ካህናት
ሦስት ነገር ይፈልጋሉ ክህነት ይፈልጋሉ፣ መስዋዕት ይፈልጋሉ፣ መስዋዕትን የሚቀበላቸውም
ይፈልጋሉ፡፡ በሐዲስ ኪዳን በቤተመቅደስ ካህኑ በክህነቱ፣ መስዋዕቱን ኅብስቱንና ወይኑን
ያቀርባል፣ መስዋዕቱን የሚቀበል እግዚአብሔር ነው እርሱ ካህን ነው፣ መስዋዕቱ በግ ነው
መስዋዕቱን የሚቀበል እግዚአብሔር ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ልዩ ካህን ነው (ዕብ 8፡2) ምክንያቱም
ሊቀ ካህናቱ ሁሉ ሦስት ነገሮች (መስዋዕት፣ ክህነት፣ መስዋዕት ተቀባይ) ሲፈልጉ እርሱ
ግን አላስፈለገውም፡፡
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንደመሰከረ ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር››
የእግዚአብሔር በግ የተባለ መስዋዕቱ ራሱ ነው ፣ ሊቀ ካህን ነው መስዋዕቱን አቀረበ፣
እግዚአብሔር ነው መስዋዕቱን ተቀበለ (2ቆሮ 5፡16-21) ይህንን ነው የኢየሱስ ክርስቶስ
ማዳን በፍጡር ሊደረግ የማይችል ድህነት የምንለው
ነገር ግን አይሁድ ፈሪሳውያን ሰዱቃውያን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ የአብ
የባሕርይ ልጁ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መድኅኒት (አዳኝ) እንደሆነ አያምኑም ነበረና
ይሰናከሉበት ነበረና የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ደጋግመው በመጥራት ከማስተማራቸው
ባሻገር ‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› በማለት የተናገሩት፡፡ ‹‹ሰው ደግሞ የሰውን ልጅ
የእግዚአብሔርን ልጅ የአብ የባሕርይ ልጅ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ የከበረ እንደሆነ ካላመነ
አይድንምና››
‹‹ዮሐ 20፡31 ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ
አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል››
መጥምቀ ዮሐንስም ‹‹እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ
መስክሬአለሁ›› ዮሐ 1፡34 ነው ያለው ይህ ነው ምስክርነቱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ
መድኀኒት አዳኝ ፈዋሽ እንደሆነ የአብ የባሕርይ ልጅ እንደሆነ መመስከር፣ ምክንያቱም
አይሁድ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ ብለው ሊገድሉት ይፈልጉት ነበረና (ዮሐ 5፡
18) ስለዚህም መዳን በሌላ በማንም የለም በደላችን የተደመሰሰው፣ መርገማችን
የተሻረው ፣ አዳምና ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብራችን የተመለስነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን
ነው፡፡
፪ኛ. የመላዕክት ማዳን፣ የቅዱሳን ማዳን፣ የመስቀል ማዳን የፀበል ማዳን ፣ በመስቀልና
በእምነት በቅዱሳት መጻሕፍት በመተሻሸት መዳን የምንለው ነው::
ሀ/ የመላዕክት ማዳን
ከላይ ከፍ ብለን እንደጠቀስነው የመላዕክትን ማዳን በተመለከተ ቅዱስ ዳዊት
‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› (መዝ 33፡7)
ይላል መላዕክት ያድናሉ ብለን ስንል ምን ማለታችን ነው ብለን ብንጠይቅና ብንጠየቅ
የመላዕክት ማዳን የጸጋ ነው፡፡
በአጠቃላይ የመላዕክት ማዳን የምንለው ሦስት ነገሮችን ነው፡-
ጥበቃቸውን (መላዕክት በመጠበቅ ያድናሉ ይታደጋሉ)
‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቅህ ዘንድ መላዕክቱን ስለ አንተ ታዟል›› መዝ 90፡11 ‹‹ከክፉ
ነገር ሁሉ ያዳነኝ እርሱ እንዚህን ብላቴናዎች ይባርክ›› (ዘፍ 48፡16)
ማር ይስሐቅ የተናገረው ሰውነትን የመዝለፍ ሥርዓት
✝ወንድሜ ሰውነትህን ዘወትር ዝለፋት ከሥጋ የምትለዪበት የምታልፊበት ጊዜ ደርሷል በላት ባለሺበት በኋላ ጥለሺው በምትሄጂ ሥራ ዛሬ ለምን ደስ ይልሻል? እሱን በማየት ጥቂት ዘመን ተድላ ደስታ የምታደርጊበት ኋላ ብዙ ዘመን በምታጪው የቀደመ ሥራሽን እወቂ የሠራሺው ሥራ ምን እንደሆነ አስቢ ጽድቅም እንደሆነ ለኃጢአትም እንደሆነ ያለ ዘመንሽን ከማን ጋራ ፈጸምሺው ከጌታ ጋር ነው ወይስ ከሰይጣን ጋር ነው? በትሩፋትሽ ምንን ደስ አስኘሽ ጌታን ነው ወይስ ሰይጣን ነው? በጊዜ ምትሽ ሊዋሐድሽ የሚመጣው ማነው? በመንግሥተ ሰማይ ዐርፈሽ ትኖሪ ዘንድ በሥራሽ ደስ ያለው ማነው ለማን ብለሽ ደከምሽ ለማንስ ብለሽ መከራ ተቀበልሽ ለመንግስተ ሰማይ ብለሽ ነው? ደስ ብሎሽ ታገኚው ዘንድ አኳኋኑስ ምንድር ነው ነፍስሽ ከስጋሽ በተለየች ጊዜ በመንግሥተ ሰማይ ይዋሕድሽ ዘንድ ገንዘብ ያደረግሺው ምንድር ነው ምን ምግባር ነው በማናቸው እርሻ ሊያውሉሽ ተቃጠሩሽ በማመናችው መዓርግ ተቃጠሩሽ በባለ ሠላሳ ነው በባለ ስድሳ ነው ወይ በባለ መቶ ነው ነፍስሽ ከሥጋሽ የምትለይበት ፀሐይ እድሜሽ በገባ ጊዜ ዋጋሽን እሰጥሻለሁ ያለሽ ጌታ ነው ዲያብሎስ ነው?
ነፍሴ ሆይ ሰውነትሽን መርምሪ ዕዳሽ በማናቸው ቦታ እንደሆነ እወቂ መንግስተ ሰማይም እንደሆነ ገሃነምም እንደሆነ እወቂ ለሚያርሱ ሰዎች አሞጭ እሬት የሚያፈራ እርሻሽን ያረስሽ ትሆኚ ማለት በሚሰሩት ሰዎች ፍዳን ማለት የሚያመጣ የኃጢአትን ብትሰሪ እያዘንሽ እየተቆረቆርሽ አልቅሺ ለምኚ።✝
ምንጭ-:
"ዘዘወትር ውዳሴ አምላክ"
++ሰው እንጂ እግዚአብሔር አልረሳኝም+++
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ፅኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደኃ ፣የሚበላውን የሚቸገር ረሃብተኛ ፣ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርብ ሆኖ ይታዘብ የነበረው ወዳጁ እንዲህ አለው ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማስገኘት ካልቻለ የመጸለይህ ትርጉም ምንድር ነው? በቃ ፈጣሪህ አልሰማህም ማለት ነው!› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያሃ ምስኪን ክርስቲያን ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም! ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ ነግሮት ነበር፡፡ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን ይህ ሰው ረስቶኛል!!!›
ክርስቲያኖች ለምን አንዳንዶች ከዕለት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ እንጀራ ያጣሉ ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር አድልዎ ኖሮበት ነው አትሉም?! (ሐዋ 10፡34)፡፡ይህስ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙት ምንም የሌላቸውን በመርዳት እና በመመገብ በባሕርይው መግቦትን ገንዘብ ያደረገውን አምላክ በጸጋ እንዲመስሉትና በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡
ስለዚህ ‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዕለት እንጀራችን አትርፎ የሚሰጠን ይህን አምላካዊ አደራ እንድንወጣም ስለሚፈልግ እንደሆነ ብንረዳው እንዴት መታደል ነበር!!!
+ ጥቃቅኑን ቀበሮዎች አጥምዳችኹ ያዙልን+ (መኃ.፪ ፥ ፲፭)
ከጥቃቅኑ ኃጣውእ እንጠበቅ ዘንድ ከማር ይስሐቅ የተገኘ ድርሳን ይኽ ነው፦
"በዐቢያት ኃጣውእ እንዳትሰነካከል ከንዑሳት ኃጣውእ ተከልከል። ንዑሳት የሚላቸውም ማየት መስማት ያለመጠን መብላት መጠጣት ናቸው። . . . መብል መጠጥን ከመውደድኽ የተነሳ ንዑሳት ኃጣውእን ትሰበስባለኽ። ንዑሳት ኃጣውእን ከመውደድኽ የተነሳ ዐበይት ኃጣውእን ሰብስበኽ ትሠራለኽ። ኃጣውእንም ከመውደደኽ የተነሳ ፍዳን ትቀበላለኽ ትሰበስባለኽ። መብል መጠጥ ብናገኝ አፋችንን ከፍተን እግራችንን ዘርግተን ብንበላ ብንጠጣ ሰውነታችንን ወስኖ ገትቶ ማኖር አይቻለንምና" ይላል (፩) ። የሰው ልጅ ካየ ከሰማ ዘንድ ያለ ልክ ከበላ ከጠጣ ዘንድ የክፉ ኅሊናት የፍትወታት እኩያት መናኽሪያ ይኾናልና!
ዳግመኛም ይኼው አባት እንዲኽ ይለናል ፦ "ራሱን ከምክንያተ ኃጢአት ወድዶ ካላራቀ ፣ በግድ ወደ ኃጢአት ይሳባል። . . . ንዑሳት ኃጣውእ ይጎዱኛል የሚል ዐበይት ኃጣውእን ድል ይነሣል። ሳያስቸግረው በመከራ ጊዜ ብርሃን ጸጋን ያገኛል። 'ንዑሳት ኃጣውእ' ይጎዱኛል የሚል ሰውን ፣ ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር ሰኰና ኅሊናውን ይጠብቀዋል።" አለ። በመከራ ጊዜ ኹሉ ረድኤተ - እግዚአብሔር ትመጣለታለች። 'ንዑሳት ኃጣውእ ይጎዱኛል' የማይል ግን በዐበይት ኃጣውእ ድል ይ 'ነሣል። ፍጹም መከራ ይቀበላል" (፪) ይላል።
ዳግመኛም ይኼው አባት እንዲኽ ሲል ያክላል ፦ "ጎበኞችን ንዑሳት ኃጣውእን ተቀብለኽ ታጠፋቸው ዘንድ ፃር ትጋ። ሳያድጉ ሳያብቡ ሳያፈሩ ፈጽመው ሳይሰፉ። ንዑሳት ኃጣውእ ቢታሰቡኽ ኃጣውእን መቃወም ቸል አትበል። እንዲኽ ያልኾነ እንደኾነ ግን የተገዛ ባሯ ገል ደንጊያ አሸክመው እንዲያስኰበዅቡት በፊት በፊታቸው የሚያስኰበዅቡኽ ዐበይት ኃጣውእን ታገኛለኽ። አስቀድሞ ንዑሳት ኃጣውእን የተዋጋ ዐበይት ኃጣውእን ድል ይነሣል።" ይለናል። (፫)
ዲ/ን ዳዊት ሰሎሞን
-------------------
(፩) መጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ ፣ አንቀጽ ፩ (ምዕራፍ. ፬ (ገጽ ፲ ፣ ገጽ ፲፪ ፣ ምዕራፍ ፲፫ (ገጽ ፳፫)
(፪) ዝኒ ከማሁ ፣ አንቀጽ ፪ ፣ ምዕ. ፩ ፣ ገጽ ፳፰ ፣ ገጽ ፴፩
(፫) ዝኒ ከማሁ. አንቀጽ ፪ ፣ ምዕ.፪. ገጽ ፴፪
🔸
† ጋብቻና የሰው ጥንተ ተፈጥሮ - ፩ †
አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን ጋብቻ በገነት ውስጥ በነበረው የሰው ልጅ ሕይወት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳን ለወደቀው የሰው ልጅ ድጋፍ እንዲኾን እግዚአብሔር የመሠረተው ቢኾንም፥ ከውድቀት በፊት ግን አልነበረም፡፡ እንዲህም ማለታችን በገነት ውስጥ የነበረው ድንግልና አሁን ከምናውቀው ዓይነት ድንግልና እንደሚለይና እጅግ እንደሚልቅ ኹሉ፥ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነትም አሁን ከምናውቀው የባልና የሚስት አንድነት የሚለይና እጅግ የሚልቅ ነበር፡፡ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነት ምሥጢራዊ አንድነት ነው፡፡ ሔዋን ለአዳም ረዳት ኾና ስትሰ’ጠው፥ አሁን በጋብቻ ውስጥ የምናውቀውን ዓይነት ረዳትነት እንድትሰጠው አልነበረም፡፡ አሁን በምናውቀው ዓይነት ጋብቻ ውስጥ ሚስት ለባሏ ረዳት ከምትኾንባቸው ነገሮች ዋናው ነገር፥ ፍትወት ሲበረታበት በዝሙት እንዳይወድቅ ሸክሙን ማቅለል ነው፡፡ ባልም እንደዚሁ ለሚስቱ! በገነት ውስጥ ከውድቀት በፊት የነበረው የሔዋን ረዳትነት ግን እንደዚህ አልነበረም፡፡ የተሰጠችው እንድታወራው፣ እንድታጽናናው፣ እኩል ክብሩን እንድትጋራ፣ በኹለንተናዋ እርሱን እንድትመስል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በእንተ ድንግልና” በተባለ ተወዳጅ መጽሐፉ ይህን ሲያብራራውም እንዲህ ይላል፡-
“እግዚአብሔር ይህን ዓለም ለጥቅማችን ፈጥሮ ከፈጸመና ዝግጁ ካደረገ በኋላ፥ በመጨረሻ ይህ ዓለም ለእርሱ የተፈጠረለትን ሰውን ፈጠረ፡፡ ከተፈጠረ በኋላም የሰው ልጅ በገነት ኖረ፤ ለጋብቻ የሚኾን ምክንያትም አልነበረም፡፡ ሰው ረዳት ያስፈልገው ነበር፤ ወደ መኖርም መጣች (ተፈጠረች)፡፡ ያን ጊዜም ቢኾን [አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡ ከንጹህ ምንጭ ጽሩይ ወንዝ እንደሚፈልቅ፥ እነርሱም (አዳምና ሔዋንም) በገነት በድንግልና ውበት ተጽደልድለው ይኖሩ ነበር፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆም እንዲህ ይላል፡-
“ያን ጊዜ [አሁን የምናውቀው ዓይነት] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡”
ስለ ሰባቱ ሰማያት !
♡ጽርሐ አርያም ፦
ሰማየ ሰማያት ፣ ከሰማያት ሁሉ በላይ ያለች ሰማይ ናት ፤ ዳር ድንበሯ ከእግዚአብሔር
በቀር ማንም አያውቀውም፡፡
♡መንበረ ስብሐት ፦
አራት ቅርጽ ያላት ሲሆን ድንኳን ትመስላለች ፤ የምንኖርባትን ዓለም ታክላለች ። ሥላሴ
በፈለጉት መጠንና መልክ ለቅዱሳን ይገለጡባታል ። ሰባት የእሳት መጋረጃም አላት ።
ዘፍ ፳፰፡፲፪-፲፯
ኢሳ ፮፡፩-፪
♡ሰማይ ውዱድ ፦
ኪሩቤል የሚሸከሙት የሥላሴ ዙፋን ነው ።
ሕዝ ፲፡፲፱-፳
♡ኢዮር ፣ ራማ ፣ ኤረር ፦
እነዚህ ሦስቱ የመላእክት ከተሞች ሲሆኑ ከአድማስ እስከ አድማስ የተዘረጉ ናቸው ። ከላይ
ወደ ታች ፣ መጀመርያ ሰማይ ውዱድ ፤ ቀጥሎ ኢዮር ፣ ቀጥሎ ራማ፣ ቀጥሎ ኤረር የተያያዙ
ናቸው ። ስፋታቸውም እኩል ነው ።
♡ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ፦
አራት መዓዘን ፣ 12 በሮች አሏት ፡፡ በውስጧ የብርሃን ሳጥን የተቀረጸ ከሥላሴ ፀዳል
የተሣለባት ታቦት ዘዶር አለች ፡፡ ይህቺም የእመቤታችን ምሳሌ ናት ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፦
ዓይን ያላየው ፤ ጆሮ ያልሰማው ፣ በሰውም ልብ ያልታሰበ ፣ እግዚአብሔር ለሚወዱት
ያዘጋጃት ያላት ይህቺው ናት
፩ኛ ቆሮ ፪፡፱-፲ ። መጠኗም የተወሰነ ነው ።
ባለ ራእዩ ዮሐንስ አዲሲቱ ሰማይ ያላትም ይህቺው ናት
ራእ ፳፩፡፪-፫ በጕበኖቿ የ12ቱ ሐዋርያት ስም ፤ በመድረኮቿ የ12ቱ ነገደ እስራኤል ስም ፤
በአዕማዶቿ የጻድቃን የሰማዕታት ስም ተጽፎባታል
ራእ ፳፩፡፲፩-፲፭ ።
(ስነ ፍጥረት)
እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡
አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?
ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡
ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡
ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡
ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#አንጨነቅ
በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡
ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡
(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)
ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው። የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።"
📜(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)📜
‟መብረቅ ሲጮህ ሰው ሁሉ እንደሚደነግጥ የአንቺንም ስም ሲሰማ ዲያቢሎስ ይደነግጣል። አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ እረፍት አላገኘምና ነው። በአንቺ ታመመ በልችሽ መስቀል ተሰቃየ ስለሆንም ከፍጥረት ሁሉ አንቺን ይጠላል”።
(ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
ጌታችን ለወንበዴው <<በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ > የሚል ልመና እውነት እውነት እልሃለሁ ፤ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ብሎ ወዲያውኑ :መልስ ሰጠ በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ፧ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው ።
በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግስት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት ፡ከቁጣ የራቀ ምህረቱ የበዛው አምላክ :ክፉ ስራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል <የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል ስለዚህ ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ! ይህንን ምህረት ተስፋ አድርገን << ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንት በኃጢአት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ እያልን እንጸልያለን !
#ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሕማማት መጽሐፍ ገፅ 354)
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....
ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡
"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡
አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ለመዳን፣ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
+++ አንድ "ግዩር" እንዲኽ ይመክራል +++
(መጋቤ ወብሉይ ወሐዲስ ቀሲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ እንደጻፉት)
ስለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እንውደድ እንጅ ስለ ሰው ብለን እግዚአብሔርን መውደድ አይገባንም ። በእግዚአብሔር ፊት ሰውን መውደድህን ይገለጥልህ እንጅ በሰው ፊት የእግዚአብሔር ወዳጅ ለመምሰል ብለህ የምትኖ ር አትሁን ። ለሰዎች ብለህ እንደወደድከው ለሰዎች ብለህ ልትጠላው ትችላለህ እና።
......
የእግዚአብሔር ሰው መሆን ማለት እግዚአብሔርን መመገብ እንጅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም ። ለመዳን ብለህ እወቅ እንጅ በእውቀትህ የምትድን አይምሰልህ ። የማታውቀውን የምታውቀው ልትኖረው እንጅ እውቀቱ በክርስቶስ ቀኝ ሊያቆምህ አይምሰልህ ። በጎ ነገርን ያወቅሃት ዕለት ብቻ ደስ አይበልህ ፥ የሠራሃት ዕለት እንጅ ፥ በመሥራትህም አትመካ አልፈጸምካትምና ። ከእግዚአብሔር ያወቅሃትን መልካም ነገር ወዲያው ሥራት ፥ እየሠራሃት ያለችህን መልካም ነገር አትልቀቃት ። እየኖርክ ተማር እንጅ እየተማርክ ብቻ ዘመንህን እንዳትፈጽም ተጠንንቀቅ ። ያለ ዕውቀት ብትኖር ከፍርድ የምታመልጥ አይደለምና መቼም ቢሆን ከቤተክርስቲያን ጉባዔያት አትታጣ ፥ በማወቅህ ፍርድ አይቀርልህምና ያወቅኸውን ፈጥነህ ሥራ ።
.....
ቤተክርስቲያንን በኹለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት ዕወቃት ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት ። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን ፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ ። እሊህም ፦ ኪዳን ማስደረስ ፥ ማስቀደስ ና ንስሐ ገብቶ መቁረብ ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው ። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ ።
.....
በሕይወትህ ኹሉ ቤተክርስቲያናዊ ኹን ! ብቻየን ለፋሁበት ብለህ ገንዘብህን ብቻህን አትጨርሰው ። ከምታገኘው ሁሉ ለመድኀኔዓለም ድርሻ አስቀምጥ ። የለመነህን ሰው አትመርምረው ቢቻልህ ስጠው ባይቻልህ እዘንለት እንጅ ። ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አታብጅለት ። መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው ፥ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው ። እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲዖል ሰው ለመሆንህ ዋጋ እንዳለው እወቅ ። ይቆየን መልካም የሆነ እግዚአብሔር ለመልካም የሚሳብ መልካምን የሚያደርግ በመልካሞ የሚጸና በጎ ሕሊና ይስጠን!
አባ ገብረኪዳን
ሰኔ ፲፯ - ፳፻፲፪ ዓም
----------------
ማሳሰቢያ፦ "ግዩር" የሚለው ቃል "መጻተኛ ፣ ስደተኛ..." የሚል ትርጒም አለው። ነገር ግን አባታችን በምን አገባብ እንደተጠቀሙት እርሳቸውን መጠየቅ ሳያሻ አይቀርም
እግዚአብሔር ልጆቹ ይገስጻል።
#እግዚአብሔር_አምላክ_ልጆቹ_ይገስጻል_ጠላቶች_ግን_ይቀጣል።
እርሱ ለተወዳጁ ልጆቹ " የቀደመ ፍቅራችሁን ትታችኋል" በማለት ያለውን ጣፋጭ ግዜ ያስታውሳቸዋል። ወደ ቀደመውና ውደሚያውቀው ነገር ግን አሁን ወደ ቀነሰበት ወይም ወደ ጠፋበት ወደ መጀመርያው ፍቅሩ መመለስ የሚችለውን ሰው ይገስጸዋል። አብዛኛውን ጊዜ የሚገስጸው ሰው ግን ፍቅሩ የቀነሰበት ሰው ነው።
#እግዚአብሔር ይህን ፍቅር ይጠብቀዋል፡ትኩረትም ይሰጠዋል፡ምክንያቱም እርሱ ከምንም ነገር በላይ ልብን ይፈልጋልና። እርሱ ተራ ተግባራትን አይፈልግም። እርሱ ልባቸው ከእርሱ ርቆ ወደ እርሱ የሚጸልዩትን ሰዎች ይገስጻቸዋል። ስለሆነም እንዲህ ይላቸዋል ፡-" ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፥ . . ." ማቴ15፡8።
#እግዚአብሔር_የተዉት_ልጆቹን_ወይም_እርሱን_የሚያውቁትን_ሰዎች_ይገስጻችዋል።
ስለሆነም በነብዩ ኢሳይያስ የትንቢት መጽሓፍ ውስጥ እንዲህ ብሏቸዋል፡- " . . . ሰማያት ስሙ ምድርም አድምጪ ፥ ልጆችሽን ወለድሁ አሳደግሁም እነርሱም ዐመጹብኝ።"ኢሳ1፡2።
እርሱ የተንከባከበው የወይን ቦታውን ገስጾታል፥ስለዚህ ቦታው ሲናገርም እንዲህ ብሏል፡- "ለወይኔ ያላደርግሁለት፥ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስተማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?"ኢሳ 5፡4።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
(ፍቅር ከሚል መጽሓፋቸውበአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ ) ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።
‹ # መዳንም_በሌላ_በማንም_የለም
‹ # የሉተራዉያን_ስህተት_በሊቃውንት_አስተምህሮ_ሲገለጥ ››
®ራኢይ ፍቅረ ስላሴ
>>> መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም
ከሰማይ በታች ሌላ የለምና›› (ሐዋ 4፡6-12)
ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው በዕድሜ በጸጋና በመንፈሳዊ አገልግሎት በእግዚአብሔር
ቤት ውስጥ የሸመገለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሆን መጽንኢ (አጽናኝ)፣
መስተፈስሒ (አስደሳች)፣ መንጽሒ (የሚያነፃ)፣ መስተሰርይ (የሚያስተሰርይ)፣ እና ከሳቲ
(ገላጭ) የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ በዕለቱ በዙሪያው ተሰብስበው
ለነበሩት ለቤተ አይሁድ በ72 ቋንቋ ወንጌልን በመስበክ 3000 ነፍሳትን አሳመነ፡፡ በዘጠኝ
ሰዓትም ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ በቤተመቅደስ በር ላይ
ተቀምጦ ሲለምን የነበረውን አንድ አንካሳ ሰው ወደ እኛ ትኩር ብለህ ተመልከት ብሎ
በናዝሬት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ በማለት ፈወሰው፡
ነገር ግን በነጋው ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን የካህናት አለቆች (ሐናና ቀያፋ) ና የመቅደስ
አዘዦች በምን ኃይል ወይም በማን ስም ይህን አደረጋችሁ? ባሉት ጊዜ ነበር ‹‹እናንተ
በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው
ግንበኞች የናቁት የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው መዳንም በሌላ በማንም የለም
እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና›› (ሐዋ 4፡
6-12) በማለት የመለሰላቸው፡፡
በመሆኑም የዚህ ጽሁፍ መሠረታዊ ዓላማ ሉተራውያን ፕሮቴስታንትና ተረፈ አርዮሳውያን
‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› የሚለውን ጥቅስ እንደ መፈክር በመያዝ ዝም ብለን
‹‹ኢየሱስ›› በማለት ብቻ እንድናለን ፕሮሰስ አያስፈልግም በማለት የመዳንን ትርጉም
ባለመረዳት የቅዱሳንን፣ የመላዕክትን የመስቀልን፣ የዕምነትን፣ የፀበልንና ሌሎችን የመዳን
መንገዶችን በመቃወም የስህተት ትምህርት ሲያስተምሩ ይስተዋላሉና፣ ይህ የመናፍቃን
ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲመረመር ምን እንደሚመስል ለተዋህዶ ክርስቲያኖች
ማስተማርና በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ ትውልዱን ከስህተት ትምህርት ከጥርጥር መታደግ
ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ መዳንን በተመለከተ ያስተምረናል ነገር ግን መዳንን
በተመለከተ የእኛ የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ለሁሉም አንድ ዓይነት ቃል ነው
የሚጠቀመው ከዚህም የተነሣ ምስጢርን የማያስተውሉ ሰዎች መጻሕፍትን በትርጉም
ሳይሆን በጥሬ ንባብ ለመረዳት የሚሞክሩ ወገኖች በሁለት መልኩ ሲስቱ እናስተውላለን፡፡
ሀ/ የመጀመሪያዎች መዳንን ጠቅልለው ቅዱሳንንም፣ መላዕክትንም ኢየሱስ ክርስቶስንም
በተመለከተ የተናገረው ቃል አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው የሚመስላቸው ናቸው፡፡
ለ/ በሌላው መልኩ ደግሞ መላዕክት ቅዱሳን ያድናሉ ብለን ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ
እንደሚያድነው ዓይነት ማዳን ያለ የሚመስላቸው ወገኖችም አሉ፡፡
መዳን የሚለው ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በሦስት ዓይነት ፍቺ ወይም ትርጉም
አመስጥረን እናየዋለን:-
፩ኛ. የዓለም መድኃኒት የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ
የመጀመሪያውና ዋንኛው እግዚአብሔር አዳምንና ልጆቹን ከወደቁበት ውድቀት አንስቶ
ከጠፉበት ከባዘኑበት መልሶ ወደ ነበሩበት ክብር መመለስ ወይም ለመመለስ ያደረገው ጉዞ
ማዳን ይባላል፡፡ አዳም በዕለተ አርብ ወደ ተፈጠረበት ክብር መመለስ ከባርነት ታድጎ
ከሲኦል ነፃ አውጥቶ አዲስ አድርጎ መሥራቱ ማዳን ነው (2ቆሮ 5፡15)
ከዚህም የተነሣ ነው እግዚአብሔር አዳነን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳነን የባርነታችን ቀንበር
ሰበረ ከእስራታችን ፈታን የምንለው
‹‹ፊል 2፡8-11 በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ይገልፅልናል
የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ተወልዶ የውርደት ሞት (የመስቀል ሞት) ሞቶ እኛን አዳምና ልጆቹን
እንዴት እንደ አዳነን ነው የሚያስተምረው›› ‹‹በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ
ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር
ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ
ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው›› (ፊልጵ
2፡8-11)
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም ከስም ሁሉ የከበረ ስም መሆኑን ሐዋርያው ያስተምረናል
እንዲሁም ፍጥረት ሁሉ ይድንበት ዘንድ የተሰጠው ስም ይህ ስም እንደሆነም አስረግጦ
ይነግረናል፡፡
ሐዋርያው ይህን ያለበት ምክንያት እግዚአብሔር ኤልሻዳይ አዶናይ ኤል፣ አልፋና ኦሜጋ ፣
ፊተኛውና ኋለኛው ፣ ያህዌ የሚለው ስም አያድንም ማለቱ ነው? ይህ አይደለም የቅዱስ
ጳውሎስም ሆነ የሐዋርያት ሃሣብ::
እግዚአብሔር የሚለው ስም የእግዚአብሔርነቱ የአንድነቱ የሦስትነቱ ኅቡዕ ስም ነው
አዶናይ ፣ ኤል ፣ ያህዌ የሚሉት ስሞች ከሥጋዌ በፊት የተሰጡ ስሞች ናቸው ኤልሻዳይ፣
ፊተኛውና ኋለኛው፣ አልፋና ኦሜጋ የሚሉት ስሞች ከሀሊነቱን ሁሉንቻይነቱን ያለ የነበረ ወደ
ፊትም የሚኖር መሆኑን የሚገልጹ ከሥጋዌ በፊት የተሰጡ ስሞች ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ሰው ሆነ በተዋህዶ ከበረ ለማለት የተሰጠው ስም ኢየሱስ የሚለው ነው፣
ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ያስባለውም ይህ የተዋህዶ ምስጢር ነው፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ
የሚለው ስም ከስም ሁሉ የተለየ ስም ነው፡፡
ሚካኤል ገብርኤል ዑራኤል ብንል የፍጡር ስም ነው ምንም እንኳን የቅዱሳን መልዕክት
ስም ቢሆንም ሌሎችም አበበ፣ ተስፋዬ፣ አልማዝ ….. የተጻውአ መጠሪያ ስም ነው
እግዚአብሔር ስንል የፈጣሪ ብቻ ስም ነው፡፡
ኢየሱስ ስንል ግን ፍጡርና ፈጣሪ በተዋህዶ ያገኙት ስም ነው
የፍጡር ስም ለብቻ ነበረ የፈጣሪም ስም ለብቻ ነበረ ፈጣሪ ከፍጡር ጋር በተዋህዶ
በመክበር ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሲወለድ ግን ኢየሱስ
ክርስቶስ የሚለው ስም ተሰጠው ይህም በመሆኑ ይህ ስም የማይደገም ልዩ ስም ነው
እንደፍጡራን ስም በተለያየ ጊዜ የሚደገም አይደለም፡፡
ኢየሱስ የሚለው ስም ግን ምስጢረ ሥጋዌ ስለማይደገም ሌላ ጊዜ የሚደገም ስም
አይደለም አንዱና ዋንኛውም ምክንያት ይህ ነው ኢየሱስ የሚለው ከስም ሁሉ በላይ የሆነ
ስም ያሰኘው፡፡
ሌላው ምክንያት ሌሎችን ስሞች ግብሩን ተመልክተው የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ
ተመልክተው ሰዎች በዚያ ስም ሲጠሩት በሌላ መልኩ ስምህ ማን ነው ብለው
እነአብርሃም እነሙሴ ‹‹ማን ብየ ልንገራቸው ቢለው ሙሴ›› ፊተኛውና መጨረሻው ሁሉን
ቻይ (ኤልሻዳይ) የሆነው ብለህ ንገራቸው ነው ያለው፡፡
ኢየሱስ የሚለው ስም ግን በመላዕክት ተነግሮ በእናቱ በኩል የወጣ ‹‹ትፀንሻለሽ ወንድ
ልጅ ትወልጃለሽ አሕዛብን በባርነት በትር ይገዛል ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ይባላል
ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ›› (ሉቃ1 ፣ ኢሳ 9፡6)
እግዚአብሔር የተባለው በዚህ ዘመን ነው በዚህ ሰዓት ነው ልንለው አንችልም ኢየሱስ
ክርስቶስ የተባለበትን ዘመን የተባለበትን ሰዓትና ቦታ እናውቀዋለን በመሆኑም ኅቡዕ
የነበረው ዘመንና ጊዜያት ዕለትና ቀናት የማይቆጠሩለት ፣ በቦታና በጊዜ የማይወሰን ተወስኖ
ተወልዶ ኢየሱስ ስለተባለ ይህ ስም ልዩ ስም ነው እንድንበት ዘንድ የተሰጠ ስም ሲልም
ቃላቶቹን ኢየሱስ የሚለውን ብቻ ሳይሆን ይህንን የማዳንን ምስጢር የሚወክል ስም
የዳንበት ስም የተፈወስንበት ስም ስለሆነ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ስም አንድን ግብር
ይወክላልና ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ
ትህትናን ገንዘብ እናድርግ (አባ ህርያቆስ)
=====================
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ ወራት ( በሥጋ በተገለጠለት ዘመን) ስለ ትህትና ሲያስተምር እንዲህ ብሎዋል። " እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" (ሉቃ 18፥14)
ይህንን አምላካዊ ቃል ዋቢ በማድረግ ነው ታላቁ አባት አባ ህርያቆስ በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ ላይ '' ትዕቢትና መታጀርን ጌጥ አናድርግ ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ
'' ሲል የተናገረው።
አባ ዮሐንስ ሐጺርም ስለ ትህትና ሲናገር እንዲህ አለ “ዮሴፍን ማን ሸጠው?” ብሎ ጠየቀ፡፡ ከወንድሞች አንዱም “ወንድሞቹ ሸጡት” ብሎ መለሠለት፡፡
አረጋዊውም (አባ ዮሐንስም) “አይደለም፤ ትሕትናው ነው የሸጠው፡፡ ‘ወንድማቸው ነኝ’ ብሎ በመናገር እንዳይሸጥ ማድረግ ይችል ነበርና፡፡ ነገር ግን ዝምታን ስለመረጠ፤ ራሱን በትሕትናው ሸጠ፡፡ ይኸው የእርሱ ትሕትና ግን በግብጽ አለቃ አደረገው፡፡” በማለት ተናግሯል ።
" እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤" (ቆላ 3: 13)
ስለዚህ ወድ አንባቢያን ትዕቢት የዲያቢሎስ ስራ ነው! እኛ ደግሞ በጥምቀት ልጅነትን ያገኘን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ተገንዝበን ራሳችሁን የትህትና ሰው በማድረግ ትዕግስትን ገንዘብ እናድርግ።
" ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ።"
(መክ 10፥4)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን።
[ ትምህርቱን ለሌሎች ያጋሩ]
(#ኀጢአቷን_የምትጽፈው1ሴት )
አንዲት ሴት ነበረች ኀጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኀጢአት የሰከረ ለኀጢአትም ተገዚ የሆነች
ይቸ ሴት የተለያየ ኀጢአት የምሰራ ነት
ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ትሰርቃለች፣ ትገድላለች
በአል ትሽራለች፣ ትሰክራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ለብሷ ኀጢአት ነበር። ነገር ግን የምሰረውን ኀጢአቷን ሁሉ አየጻፈች ታስቀምጥ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን የጻፈችው ኀጢአትቷን ብታየው ስንክሳር አክሎ ተመለከተችው
ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚውሉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው።
የዚች ሴትም ኀጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችው ደነገጠችና ኀጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ ለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችው አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው
አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታየው ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኀጢአቷ ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኀጢአት ነበረች ሊሰሩአት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች
አባቴ ይችሳ አለችው አባ ባስልዮስም ይችን ኀጢአትሽንስ ማስተስረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነው ሂደሽ ለእርሱ ንገሪው አላት።አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኀጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገለጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነው።ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነው። እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶርያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱ ኤፍሬም ደረሰች።
አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም
ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ኀጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጅ ስትመላለስ ኀጢአቷ እንዲቀልላትም ነው። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪው እሱ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸው እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞው በህይወት አታገኝውም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈው ኀጢአትሽን ከአስከሬኑ ላይ ጣይው አላት እርሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቀያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኀጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስከሬኑ ላይ ጣለችው አስከሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኀጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች
ከዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች።
እንደ ዚች ሴት ኀጢአቱን የሚያስታውስ ማን ነው?
ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነው?
ስለኀጢአቱ በረሃ የተንከራተተ ማን ይሆን?
የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም ጨረሻ ያሳምርልን
ኀጢአቷን የደመሰሰ የሁላችንም ኀጢአት ይደምስስልን
አምላኬ ሆይ ያለ ንስሐ አትጥራኝ!
#ለንሰሐ_የሚሆን_ፍሬ_አድርጉ!
የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
ሥጋ ወደም
ዲያብሎስ እጅግ በጣም አብዝቶ ማራቅ የሚፈልገው ከምሥጢራት ሁሉ የበላይ ከሆነው “ከምሥጢረ ቁርባን” ነው፡፡ ምሥጢራት ሁሉ የሚደመደሙት በሥጋ ወደሙ ነው፡፡ መሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ንስሓ፣ ምሥጢረ ተክሊል የሚፈጸሙት በቁርባን ነው፡፡ ይህንን የሚያውቅ የውሸት አባት ዲያብሎስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል፡፡ አንተ ግን “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም” ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን አምናለሁና ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነሳውን ሥጋና ደም እመገባለሁ በለው፡፡ /ዮሐ6፥35/ የዘላለም ሕይወትን መውረስ እንደምትፈልግም አሳወቀው፡፡ “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል” /ዮሐ6፥41/ ስለዚህ ለዘላለም በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር ከሰማይ የወረደውን እንጀራ እበላለሁ ብለህ ጠላትህን አሳፍረው፡፡ ጠላት ግን በድፍረት እንድትቀርብ ሊፈትንህ ይችላል፡፡ የምትቀበለውን ሥጋና ደም የዕሩቅ ብእሲ ሥጋና ደም ነው ብሎ ሊያታልልህም ይሞክራል፡፡ አንተ ግን አትስማው የምቀበለው ሥጋና ደም በዕለተ አርብ የተቆረሰውና የፈሰሰውን ሥጋና ደም ነው በለው፡፡ ሥጋና ደሙም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው እንጅ ጠላት እንደሚለው መለኮት የተለየው አይደለም፡፡ ጠላት ውጊያውን አሁንም አያቆምም “ንስሓ ሳትገባ ሳትዘጋጅ ተቀበል” ይልሃል፡፡ እርሱን ከሰማኸው የይሁዳ እጣ ፈንታ አንተ ላይም ይደርሳል፡፡ ሳይዘጋጁ ከኃጢአት ሳይነጹ ቢቀበሉት ግሩም ፍዳን የሚያመጣ የሚባላ እሳት ነው፡፡ ይሁዳ በጸሎተ ሐሙስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ከቁርባኑ ሥርዓት ተካፋይ ነበረ፡፡ ነገር ግን በልቡ የነበረው ጌታን በ30 ብር የመሸጥ ኃጢአት እንደወጣ እንዲቀር አድርጎታል፡፡ /ማቴ26፥14-29/፣ /ማቴ27÷3-9/ ሥጋና ደሙ ግሩም ፍዳ የሚያመጣ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ በንጽሕና በትሕትና ንስሓ ገብቶ ሊቀበሉት ይገባል፡፡ በዚህ መልኩ ለሚቀበለው የዘላለም ሕይወትን የሚያወርስ ጥበብን የሚገልጽ ምሥጢርን ሁሉ የሚያድል ነው፡፡ ለዚህም ነው ካህኑ በቅዳሴ ሰዓት “ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብም ያለበት ቢኖር አይቅረብ እጄን ከአፍአዊ ደም ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ፡፡ ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጅ፡፡ በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ” ብሎ እጁን የሚታጠበው፡፡ ዲያቆኑም ተቀብሎ “ይህን የቄሱን ቃል ያቃለለ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ወይም በቤተክርስቲያን በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው በእርሱም እንደተነሣሣ ይወቅ ይረዳ ስለበረከት ፈንታ መርገምን ስለኃጢአት ሥርየት ፈንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል” ይላል፡፡ ይህ አዋጅ የሚታወጀው ከክርስቶስ ሥጋና ደም ርቀን እንድንቆም ወይም የበይ ተመልካቾች እንድንሆን ተፈልጎ ወይም ለማስፈራራት ተብሎ አይደለም ንስሓ ገብተን፣ የበደልነውን ይቅር ብለን፣ የቀማነውን መልሰን፣ ተዘጋጅተን በንጽህና ሆነን እንድንቀበል ነው እንጅ፡፡ በድፍረት በኃጢአት እንደተጨማለቁ ተዘሎ የሚበላና የሚጠጣ አይደለም ፍዳ መቅሰፍት ያመጣልና፡፡ ጠላት ግን ይህንን አዋጅ እያሳሰበና እንደተመቸው እየተረጎመ “ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የበቃህ አይደለህም” ብሎ ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል፡፡ የአዋጁ ዋና መልእክት ንስሓ ገብታችሁ፣ ከንስሓ አባታችሁ ጋር ጨርሳችሁ ቅረቡ የሚል ነው፡፡ በዚህ ድል ስትነሳው ደግሞ “አንተ ገና ወጣት ነህ ሽማግሌዎች እንኳን ሳይቆርቡ ያንተ ቁርባን ምንድን ነው” ይልሃል፡፡ አንተ ምክሩን አትቀበል “ሽማግሌዎች የራሳቸው ነፍስ ነው ያላችው እኔም እንደዚሁ የራሴ ነፍስ ነው ያለኝ ስለዚህ እነርሱ ስላልቆረቡ እኔ መቁረብ የለብኝም? በወጣትነት ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ ተባልኩ እንጅ ሽማግሌዎች የሚሠሩትን እያየህ እንደእነርሱ ሁን አልተባልኩም፡፡ በእርግጥ በጎ ሥራ ሲሠሩ ልመስላቸው ግድ ነው መጥፎ ሲሠሩ ግን ልመስላቸው አልሻም፡፡ እነርሱ የሚቆርቡበት የራሳቸው ጊዜ ሊኖራቸው ይችላል የእኔ ጊዜ ግን ዛሬ ብቻ ነው” ብለህ አሳፍረው፡፡ ይህን ሁሉ ብለህ ስታሸንፈው ደግሞ እንደለመደው ከንቱ ውዳሴን ይጨምርብሃል፡፡ ቆራቢ እንድትባል ብቻ መቁረብን ያለማምድሃል፡፡ ከዚያ በኋላ ልምድ ያደርግብህና ሳትዘጋጅ ንስሓ ሳትገባ በድፍረት መቅረብን ያለማምድሃል፡፡ ስለዚህ በጣም ጥንቃቄ ልታደርግ ያስፈልጋል፡፡ ሥጋና ደሙን ለመቀበል የግድ ንስሓ መግባት ከንስሓ አባት ጋር መወያየትን ይጠይቃል፡፡ የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ስትሻ የዘላለም ቅጣት እንዳይመጣብህ ተጠንቀቅ፡፡