አዛን እየተደረገ መስጂድ የገባ ሰው አዛኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሙአዚኑን በአዛኑ እየተከተለ መጠበቅ አለበት። እንጂ ቀጥታ ወደ "ተሒየ፞ተል መስጂድ" መግባት የለበትም።
የጁሙዐ አዛን ከሆነና ኸጢቡ ሚንበር ላይ ወጥቶ ከሆነ ግን አዛኑን መከተል ትቶ "ተሒየ፞ተል መስጂድ" ነው መስገድ ያለበት። ምክንያቱም ሙአዚኑን በአዛን መከተል "ሙስተሐብ" ነው፣ ግዴታ አይደለም። ኹጥባ ማዳመጥ ግን ግዴታ ነው። ስለዚህ ከ"ሙስተሐቡ" ይልቅ ለግዴታው ቅድሚያ መስጠት ይገባል።
/channel/IbnuMunewor
إذا غُلِبت فلا تقل انتصر العدو ولكن قل ...!
#التفريغ
رابط تحميل المقطع على التيليجرام 👇👇
/channel/ahmed19871111/2617
👉ሱሪን ማስረዘም እና ሱሪውን ያስረዘመ ግለሰብ ማኩረፍና ማግለል በሸሪዓ ዕይታ ።
ይህ ጥያቄ የቀረበው ለታላቁ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ ሲሆን ጥያቄውም እንደሚከተለው ነው።
"ጀዛከላሁ ኸይረን ያ ሸይኽ! ሱሪን ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች ይቆጠራልን? እሱን ማኩረፍና ማግለል እንዴት ይታያል?
መልስ ፦
⛔️"ሱሪን ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።
🔖ምክንያቱም የአላህ መልክተኛው ﷺ ሱሪ ያስረዘመ የአላህ ቅጣት እንደሚገባው ዝተው ተናግረዋል ።
◼️" የውመል ቂያማ እለት ሦስት ሰዎችን አያናግራቸውም፣ (ከወንጀላቸው) አያፀዳቸውም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
(ሰሀባቹም)፦ "ከሰሩ ተዋረዱም እነርሱ ማናቸው?" በማለት ጥያቄ አቀረቡ። መልክተኛውም፦"ሱሪውን የሚያስረዝም ፣ በስጦታው የሚመፃደቅ እና በውሸት መሐላ ሸቀጡ እንዲሸጠ ያደረገ ።"
📎(ከሐዲሱ እንደተገነዘብነው) ሱሪ ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች የሚቆጠር ነው። ነገር ግን ማኩረፍ
ልጄ ሆይ ዕወቅ❗️
ማኩረፍ እና ማግለል መድሐኒት ነው ጠቅሞ ካገኘኸው ተጠቅመው ። ጥቅም ካላስገኘ አሊያም ይባስ 《በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ 》 አይነት ከሆነ ማኩረፍና ማግለል (እንደ መፍትሔ) አትጠቀመው።
ይህ ሱሪውን የሚያስረዝም ግለሰብ ካኩረፍነው በተግባሩ የሚያፍርና የሚቃና ከሆነ እና እንዲህም ካለ፦ "እንደ ሙሳ አሳሙሪይ ሠዎች መሐል ምሣሌ መሆን አልፈልግም "ሳሙሪይ ሰዎች እንዳይጠጉህ እና እንዳይቀርቡህ" ተብሎ እንደ ተረገመው መሆን አልፈልግም ብሎ ሱሪውን ከፍ ካደረገ ይሄኔ አኩርፈው።
ነገር ግን ስናገለው ይባስ ወንጀሉ የሚጨምር ፣ የሚጠላህ እና በልቡ ጥላቻ የሚቋጥርብህና ብሎም ሰዎችን ካነሳሳብህና ካሳመፀብህ ይህኔ አታግልለው አታኩርፈውም።
ይህ መርሕ ላንተ በቂ ነው፦
ማግለልና ማኩረፍ
መድሐኒት ነው ከፈየደ ተጠቀመው አሊያ ግን አትጠቀመው።
ምንጭ ፦
📚【ሲልሲለቱ ሊቃኣት አልባብ አልመፍቱሕ(200)】
🔈ፈትዋውን በድምፅ ማድመጥ የፈለገ ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫን፦
http://zadgroup.net/bnothemen/upload/ftawamp3/od_200_13.mp3
t.me/Menhaj_Salafiya
➢ በቡድንና በአጠቃላይ የተጠቀሱ ካሉ በነሱ ማመን።
ለምሳሌ፦ -> የጀነት ጠባቂዎች
-> የዓርሽ ተሸካሚዎች. . . .
-> በይተል መዕሙን 75 000 መላኢኮች እየገቡ ዒባዳ እንደሚያደርጉና አንድ ግዜ የደረሰው ደግሞ እንደማይደግም።
➢ በስም የተጠቀሱመላኢኮችን ካሉ በስማቸው ማመን። በነጠላ የተጠቀሰ መላኢካ ካለ በነጠላ ማመን። ስለ እያንዳንዳቸው የተጠቀሰ ባህሪ ካለ በዛ ማመን።
ለምሳሌ ፦ ጂብሪል
አላህ እንዲህ አለ፦
﴿النحل: ١٠٢﴾ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ
(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ (16: 102)
ጅብሪል 600 ክንፍ አለው አንዱ ክንፉ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አድምሱን ይሞላዋል።
ነብዩ ሙሀመድ(ሰለላ ዓለያሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ተናግረዋል ፦ ጅብሪል ስራው መልእክትን (ዋሒን) ከ አላህ ወደ ነብያት ማድረስ ነው።
አላህ እንዲህ አለ፦
﴿النحل: ١٠٢﴾ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ
(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ (16: 102)
➢ በቡድን (ባጠቃላይ) የተነገሩ ባህሪይ፣ ስራ ወይንም መገለጫ ከተነገረ ማመን።
ለምስሌ፦
አላህ እንዲህ አለ፦
الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴿فاطر: ١﴾
ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ (35: 1)
አላህ እንዲህ አለ፦
وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ ﴿الأنفال: ٥٠﴾
እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡ (8: 50)
አላህ እንዲህ አለ፦
جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِم مِّن كُلِّ بَابٍ سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ ﴿الرعد: ٢٣ - ٢٤﴾
(እርሷም) የመኖሪያ ገነቶች ናት፡፡ ይገቡባታል፡፡ ከአባቶቻቸውም፣ ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርያቸውም መልካም የሠራ ሰው (ይገባታል)፡፡ መላእክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ፡፡ «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡ (13: 23 - 24)
###
የቢድዓ ሰዎች ምልክቶች በሸይኽ ረስለን
በትርጉም የቀረበ ትምህርት
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://youtu.be/igieYyzlxlM
👇👇👇👇👇👇👇👇
ዝግጅቶቻችንን ለመከታተል
➷➘➷➘
√√√√√√√√√√√√√√√√√
👇👇👇👇
YOU TUBE SUBSCRIBE
https://youtube.com/channel/UC-xgCtuVRlQc8tPk7ElpPww
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👇👇👇👇
Facebook
http://fb.com/Ikhlasmedia1442
👇👇👇👇
Telegram
http://t.me/IkhlasMedia
ተቀርተው ያለቁ ድርሶችን ለማግኘት Join 👇
t.me/Sadatcom1
t.me/IbnuMuneworcom
t.me/Muhammedsiragecom
ግብሽን ወንድ(ባል) ብቻ አታድርጊ!
ሂይወት ማለት ባል ብቻ አይደለም
ትክክለኛ ሂይወት ማለት በአላህ ትዕዛዞች ላይ ቀጥ ማለት፡ ክልከላዎቹን ሁሉ መራቅ፡ ለሊትን ቁሞ መስገድ፣ነዋፍል የሆኑ ፆሞችን መፆም፣ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ለቤተሰብ መልካም መዋል፣ ቁርዓንን መሀፈዝ፣እዉቀትን መፈለግ፣ በቻሉት ያክል በሀቅ ኡማዉን ማገልገል፣ ሰደቃ መስጠት፣ምክር መስጠትም መቀበልም፣ በአኽላቅ በተዋበ ወደ ደዕዋ ጥሪ ማድረግ፣ መልካም ጓደኞችን መጎዳኘት፡ እነዚያ ወደ አላህ የሚያስታዉሱንን፣ በሀቅና በትዕግስት ላይ አደራ የሚሉንን፣ ኢስቲግፋር ተዉበት የእለትተ-ለት ተግባራችን ማድረግ ኢንሻ አላህ የመሳሰሉት
መልካም ስራዎችን ባጠቃላይ ………
እንጂ ሂይወትን አነጣጥረን ወንድ ብቻ ማድረግ የለብንም። ወይም እስከ ትዳር ብቻ
አላማችን ለዲናችን ብሎም ለቀብራችን ይሁን
ጥቂትም ቢሆን የዒልም ጭንቀት ይኑር በዉስጣችን
አላህ ይወፍቀን
أبو طلحة( كمال بن مكونن)
t.me/Menhaj_Salafiya
ሰዒድ ኢብኑ ዓሚር አድዱበዒ (208 ሂ.) ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ብለዋል፡-
الْجَهْمِيَّةُ أَشَرُّ قَوْلًا مِنَ الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى، قَدِ اجْتَمَعَتِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، وَأَهْلُ الْأَدْيَانِ أَنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى عَلَى الْعَرْشِ، وَقَالُوا هُمْ: لَيْسَ عَلَى الْعَرْشِ شَيْءٌ
“ጀህሚዮች ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ንግግራቸው የከፋ ነው። አይሁዶችነ፣ ክርስቲያኖች እና የሌሎችም ሃይማኖት ተከታዮች አላህ - ተባረከ ወተዓላ - ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ከሙስሊሞች ጋር ተስማምተዋል። እነዚህ (ጀህሚዮች) ግን ‘ከዐርሽ ላይ ምንም የለም’ አሉ።”
[ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፣ አልኢማም አልቡኻሪይ፡ 31]
ሀያእ ይኑረን በተለይ በአሁኑ ሰዓት አካዳሚ ቀመስ ሲያደርጉ መድረክ ሲለማምዶቸው መጀመሪያ እንዲገፉት ትልቅ ታርጌት የሚደረገው ሀእያ ነው በየመድረኩ ላይ ሁለነገሮን እያወዛወዘች ታወራልች በነብዩ ዘመን ይሄ አልነበርም ሀእያ ትልቅ ዋጋ ነበር ያልው!!
ወንድም ፦ Ibnu Munewor
t.me/Menhaj_Salafiya
ሸይክ አላማህ ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁላህ ) እንድህ ብለዋል ፦
ተውሒድ የእምነት መሰረት ነው !
አል ፈተዋ 230-20
t.me/Menhaj_Salafiya
በ ኢብኑ ሙነወር…✍
ስለ ማልታ መጠጥ
ማልታ ስለሚባለው መጠጥ ብይን የሚጠይቁ ሰዎች በዝተዋል። በእርግጥ እኔ ብይኑን አላውቅም። ተቀራራቢ በሆነ መጠጥ ላይ የተለያየ ይዘት ያላቸው ጥቂት የዑለማዎች ፈትዋ ባገኝም እንደራሴ እይታ በቂ ስላልመሰለኝ ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻልኩም። ብቻ ፋብሪካውን ከመንግስት በመግዛት ይህን መጠጥ የሚያመርተው ዲያጆ ኩባንያ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የአልኮል መጠጥ አከፋፋይ ነው። ለምሳሌ ያክል የሚከተሉት መጠጦች በዚህ ኩባንያ የሚመረቱ እንደሆኑ መረጃዎችን ሳስስ አግኝቻለሁ:–
① ጆኒ ዎከር፣
② ክራውን ሮያል፣
③ ጄብ፣
④ ቡኬነንስ፣
⑤ ዊንድሶርና ቡሽሚልስ ውስኪ፣
⑥ እስሚርኖፍ፣
⑦ ሰሮክ፣
⑧ ኬቴል ዋን ቮድካ፣
⑨ ቤይሊስ፣
①0 ካፒቴን ሞርጋን፣
①① ታንክሬይ
በኢትዮጵያ ደግሞ
① ሜታ ቢራ እና
② ጊነስ ናቸው።
ከእነዚህ በተጨማሪ ነው እንግዲህ ማልታ የተሰኘውን ከአልኮል "ነፃ ነው" የሚለውን መጠጥ በማምረት ማስተዋወቅ የጀመረው።
ሌሎች ነገሮችን ለጊዜው ይቅሩና
① የእውነት ማልታ ከአልኮል ነፃ ነው ወይ?
② ማንስ ተጨባጭ ጥናት አድርጎበታል?
③ ኩባንያው "ከአልኮል ነፃ" እያለ በሚለቀው ማስታወቂያ ምን ያክል ይታመናል?
④ አዘገጃጀቱስ ምን ያክል ጤናማ ነው?
⑤ ኩባንያው ማልታን የሚያመርተው ከሌሎች አስከሪ መጠጥ ንግድ ከሚያገኘው ገቢ ነው ወይስ ከሌላ?
⑥ የሚያዘጋጀው በአልኮል ምርቶቹ ትርፍ ከሆነ ሐራም በሆነ ገንዘብ የተዘጋጀን ምግብና መጠጥ አስገዳጅ ችግር በሌለበት መመገብ ብይኑ ምንድን ነው?
እነዚህና መሰል ጥያቄዎች በቂ መልስ የሚሹ ይመስለኛል። ፈትዋ እየሰጠሁ እንዳልሆነ ይሰመርልኝ። ሆኖም ግን እንደ ግል እይታ ቁርጥ ያለ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ብንርቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በሐዲሥ:
– "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደማያጠራጥርህ ሁን!!"
– "አሻሚ ነገሮች ላይ የወደቀ ሐራም ላይ ወድቋል" እንደተባለ ይታወስ።
በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ፈትዋ ያጋጠማችሁ ከስር ብታሰፍሩት ለብዙ ሰዎች ይጠቅማል ብየ አስባለሁ። ስለዚህ መጠጥ ተጨማሪ መረጃ ያላችሁ ከኖራችሁም እንዲሁ ማጣራት ለሚሹ ሰዎች ግብአት ይሆናልና ያላችሁን ብንለዋወጥ ደስ ይለኛል። ጀዛኩሙላሁ ኸይራ።
t.me/Menhaj_Salafiya
ክርስቲያን ሴት ማግባት~~~~~~~~
ለሙስሊም ወንዶች እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ አካሄድ ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግኝኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። እርሱም በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል።
ቁርኣናችን ደግሞ ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከሚታወቁ የመፅሐፉ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።
ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው።
ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor
24ኛ ሓዲስ
الحديث الرابع والعشرون
🔴. تحريم الظلم
▫24ኛ ሓዲስ
🔴 የሓዲሱ ትርጉም
📌 በደል የተከለከለ መሆኑ።
📖. አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ:አላህ እንዲህ አለ “ እናንተ ባሮቼ ሆይ! እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመራሁት ሲቀር ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ። ስለዚህ ቀጥተኛ መንገድ እንድመራችሁ ለምኑኝ እመራችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመገብኩት ሲቀር ሁላችሁም ረሃብተኞች ናችሁ። እንድመግባቹህ ጠይቁኝ እመግባችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ ያለበስኩት ሲቀር ሁላችሁም እርቃናችሁ ናችሁ። እንዳለብሳቹህ ጠይቁኝ አለብሳችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ ቀንና ለሊት ትሳሳታላችሁ እኔ ደግሞ ወንጀሎችን ሁሉ እምራለሁ። ስለዚህ መሃርታን ጠይቁኝ እምራችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተኮ እኔን የመጉዳት ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጉዳት አትችሉም ደግሞም እኔን የመጥቀም ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጥቀም አትችሉም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ጌታን ፈራሂ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይጨምርም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያቹህ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ወንጀለኛ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይቀንስም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ አንድ ሜዳ ላይ ቆመው ቢጠይቁኝና ሁሉንም የጠየቁኝን ብሰጣቸው፥ ይህ ስልጣኔ ላይ ልክ መርፌ ባህር ላይ ገብቶ ከባህሩ እንደሚያጎድለው ቢሆን እንጂ ምንም አያጎድልም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!ስራችሁን ነው የምቆጥርላችሁ ከዛም በስራችሁ መሰረት እከፍላችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ ሌላን ነገር ያገኘ ግን ራሱን እንጂ ሌላን አይውቀስ።”
ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።
📝. ከሃያ አራተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
▫ • ይህ ሓዲስ ሓዲሰል ቁድስ (ነብያችን[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ከአላህ የዘገቡት ሓዲስ) እንደሆነ።
▫ • አላህ በጣም ፍትሃዊ እንደሆነና ማንንም እንደማይበድል።
▫ • በመካከላችን መበዳደል ክልክል እንደሆነ።
▫ • የሰው ልጅ አላህ ካልመራው ጥመትና መሃይምነት ውስጥ እንደሚሆን።
▫ • አላህን ቀጥተኛ መንገድ እንዲመራን መጠየቅ እንዳለብን።
▫ • ሁሉም ባርያዎች አላህ የመገባቸው ሲቀራ የተራቡ እንደሆኑ እና አላህ ያለበሳቸው ሲቀሩ እርቃን እንደሆኑ።
▫ • የሰው ልጆች ብዙ ወንጀል እንደሚሰሩ። ወንጀል መሃሪ ደግሞ አላህ ብቻ እንደሆነ። ስለዚህ አላህን ለወንጀላችን መሃርታ መጠየቅ እንዳለብን።
▫ • ወንጀል ምንም ቢበዛም ሰውየው መሃርታን ከጠየቀና ወደ አላህ ከተመለሰ አላህ ወንጀሉን እንደሚምር።
▫ • ወንጀለኛ ወደ አላህ ሳይመለስ ከሞተ በስራው ራሱን እንደሚወቅስ።
📕📗📘📙
ሼይኽ አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
ሰለፊያ ዳዕዋ ለሆነ ለአንድ ግለሰብ ወይንም ለሆነ ለአንድ አመለካከት (አስተያየት) ወገንተኝነትን አታውቅም። ሰለፊያ ዳዕዋ የምታውቀው ማስረጃን ብቻ ነው።
( ሲልሲለቱል ሁዳ ወን ኑር)
t.me/Menhaj_Salafiya
قال الشيخ الألباني رحمه الله:-
الدعوة السلفية لا تعرف التعصب لشخص معين ولا لرأي معين إنما الحجة والبرهان والدليل.
(سلسلة الهدى والنور)
t.me/Menhaj_Salafiya
#ሰላተል__ጀመዓ
ሰኢድ ኢብን ሙሰይብ እንዲህ ይላሉ፦ ከዛሬ አርባ አመት በፊት ጀምሮ ሰላት በጀመአ አምልጦኝ አያውቅም"
(ሒልየቱል አልውልያ (2/162)
t.me/Menhaj_Salafiya
ሸይክ አላማህ ኢብኑ ተይሚያ رحمَه الله እንድህ ይላሉ፦
#ሙስሊም ሁል ጊዜ ሱናን ህያው ለማድረግ እና ቢዳዓን ለመግደል ይሰራል።
( አል ፈታዋ 487.3)
t.me/Menhaj_Salafiya
ወደ ሸሪዐዊ ህግጋት ስትጠራ ትእቢት አይያዝህ። ጥቅሙም ጉዳቱም አንተኑ የሚመለከት እንደሆነ አትዘንጋ። አላህ እንዲህ ይላል:–
(إِنْ أَحْسَنْتُمْ أَحْسَنْتُمْ لِأَنْفُسِكُمْ ۖ وَإِنْ أَسَأْتُمْ فَلَهَا )
[سورة اﻹسراء 7]
"መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡ መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፡፡" [አልኢስራእ: 7]
ወንድም ፦ Ibnu Munewor
t.me/Menhaj_Salafiya
🔹وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الْإِيمَانِ 🔹
🔶 «ልብ በይ ውዷ እህቴ» 🔶
« ሀያዕ ከሁላችንም የሚያስፈልገን ነገር ነው ። ጌታችንን አሏህ ሱብሀነ ወተአላ ማፈር አለብን ።
ሀያእ ካለን ነው ከወንጀል የምንርቀው ፣ ኸይር ነገር የምንሰራው፣ በተለይ "ሴቶች" ላይ ሀያእ በጣም ያስፈልጋል‼️
ካልተፈቀደላት ወንድ ጋር ዝም ብላ ማውራት የለባትም። ዝም ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ቻትን ማድረግ የለባትም።
ጉዳይ ካላት ጉዳይዋን ተናግራ ትውጣ, ሀጃ ካላት ሀጃዋን ተናግራ ትውጣ!! ከዚያ በኋላ ያለውን ጊዜዋን በኸይር ነገር ትጠቀም።
ሀያእ ከሌላትስ ከማንም ወንድ ጋር ታወራለች ፣ነገ ከዚያ ጋር ሀያእዋን እያጣች ትሄዳለች ሰዎች ዘንዳ ።
🔶 وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الْإِيمَانِ 🔶
📚 " ከሰላሰቱል ኡሱል ወአዲለቱሀ
ከሚለው ክፍል 23 ደርስ የተወሰደ ነው"
🎙በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ ሀፊዘሁሏህ
http://t.me/Tewjihat
ሀያእ ሊኖረን ይገባል ምን አገባኝ ስለሰው አይባልም! አንድ ሁለት ኪታብ እያቀራ በአሁኑ ሰአት ወጣቱ የሚናገሩት ያአራዳ ቋንቋ የሚባልው አንድ ሼይክ ፣ ዳዒ ፣ ኢማም ሁኖ ፀጉሩን እየፈተለ ዳዕዋ ቢያረግ አስቡት? ያሳፍራል አያሳፍርም ?? ድንገት እሱ ባያፍር የሚመለከቱት ሰዎች ያፍራሉ ቀና ብለው ሊያዩት !!
ወንድም ፦ Ibnu Munewor
t.me/Menhaj_Salafiya
100(መቶ)ብር #ለተውሂድ_መርከዝ
ተውሂድና ሱናን ወዳድ የሆነ አካል በሚችለው አቅሙ ወዳድነቱን በተግባር ያሳየን!!👇
የአካውንት ቁጥር
1000329889789
የአካውንት ባለቤት ስም
𝐉𝐞𝐦𝐚𝐥 𝐍𝐞𝐠𝐚𝐬𝐡 𝐀𝐧𝐝 𝐀𝐰𝐨𝐥 𝐒𝐡𝐞𝐦𝐬𝐞𝐝𝐢𝐧
ቅርጫፍ : 𝐓𝐞𝐪𝐰𝐚 𝐁𝐫𝐚𝐧𝐜𝐡
t.me/sunnacom
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:-"የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ለናንተ ልትጠቀሙባቸው የሚገቡ ጥሩ እድሎች ናቸው። ለተንኮለኞችና ለጥመት ሰባኪዎች እንዳትተዋቸው።"
(አሀምይየቱል ዐቂደቲ አስሶሒሐህ)
http://t.me/Menhaj_Salafiya