ታላቁን የኡሱል አልፊቅህ ሊቅ እንተዋወቅ ፦
አስተማሪና አስገራሚ በሆኑ ፈትዋዎቻቸውና ትምህርቶቻቸው እንጠቀም!
الشيخ محمد علي فركوس
በርካታ ዑለሞች የመሠከሩለትን እንዲህ አይነቱን የሰፊ እውቀት ባለቤት አለማወቅ የመጠቀማችንን ክፍተት የሚያሠፋ ደስ የማይል ነገር ነው ። ሌሎችን በጭፍን በመከተልና በመደናበር በሱና ዑለሞች ላይ ነጋ ጠባ ለሚዘባርቀው ጀሮህን ከሠጠህ እንዲህ ዓይነቱ ታላቅ ዓለም ላትጠቀምበት ያመልጥሃል ። እየቆየህም ሌሎችን ብርቅ የሱና ዑለሞች በስራ ፈቶቹ ጥሪ ታጣላህ - ያልነካኩት የላቸውምና ።
( የተከላከልኩት ና እንድንጠቀምባቸው ም
የጠቆምኩት ከሱና ዑለሞች ብቻ ነው ! )
http://ferkous.com/home/
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ👇
t.me/Muhammedsirage
"ወንጀል ከሱና አያስወጣም " እየተባለ .. ውሸት ፣ ማጭበርበር እና ሌሎችም አስከፊ ወንጀሎች ዉስጥ በግዴለሽነት መነከር አሳፋሪ መባል የሚያንሰው ክፉ ና ፀያፍ ምግባር ነው .. ወቅታችን ላይ ደግሞ ይሄው ክፉ ደዌ ብዙዎችን አጥቅቷል ---- ወንጀል አይጎዳ ይመስል በቀጥታም ባይሆን ባዙሪት ቀላልነቱ ይሰበክ ይዟል - በአንዳንዶቻችን ...
ነብዩን እና ባልደረቦቻቸውን እከተላለሁ የሚል ግለሠብና ወገን ወንጀልን የሚመለከትበት አይን ኢርጃእን የተጎራበተ መሆኑ ወይም የተጎራበተ ሊሆን መቃረቡ ይሳዝናል ...
የአላህን፡ ህግጋቶች ማክበርና አግዝፎ መመልከት የተቅዋ እና የአላህን ቅጣት መጠንቀቅ መገለጫ ነው ...
وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ
የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች (ትእዛዦች ፣ ክልከላዎች ) የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦች የኾነች ጥንቃቄ ናት፡፡
ተቃራኒው እንዝላልነት የልብን መጥቆር አጉልቶ ይሳያል .....
ዓብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ሙእሚን ወንጀልን አግዝፎ እንደሚመለከት፣ ሙናፊቅ ግን እጅጉን አቅልሎና አሳንሶ እንደሚያየው ተናግረዋል .....
በወንጀሎች ላይ መዘውተር የከሃዲያን መገለጫ መሆኑንም ልንዘነጋ አይገባም ... አላህ እነሱን ሲገልፃቸው እንዲህ ይላል
وَكَانُوا يُصِرُّونَ عَلَى الْحِنثِ الْعَظِيمِ
(በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና )
ሌላው ነገር፦ ወንጀል (በተለይ የድብቅ ወንጀል ) መጨረሻን (አሟሟትን) ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነውና የዛሬውን ሱና ላይ መሆን ብቻ ሣይሆን የወንጀል ብዛት ሊያስከትል የሚችለውን መንሸራተትና ክፉ ውጤት እናስብ... አላህን እንፍራ ... ወደሱም እንመለስ ።
ጥፋትና ወንጀል ከሁላችንም ሊመነጭ የሚችል መሆኑን አልዘነጋሁም ። ከላይ በተጠቀሰው መጠን ወንጀል ላይ ቸልተኛ መሆን ግን እጅጉን አደገኛ ነው።
አላህ፡ ይመልሰን !
ቻናሉን ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። መልእክቱን ለሌሎች በማሰራጨት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።
t.me/Muhammedsirage
የኪታብ ጥቆማ #4
~~~
የሶሒሕ አልቡኻሪ ሸርሕ የሆነውን "ፈትሑል ባሪ" ኪታብ መግዛት ከፈለጉ አደራዎትን የሸይኽ ኢብኑ ባዝና የሸይኽ ዐብዱረሕማን ናሲር አልበራክ ‘ተዕሊቅ’ (የግርጌ ማስታወሻ) ያለበትን ቅጅ ይግዙ። ኪታቡ ውስጥ ባሉ ክፍተቶች ላይ እጅግ ወሳኝ የሆኑ እርምቶች ተሰጥተዋል። የበራክ እርምት እራሱን ችሎ በአንድ ጥራዝ ስለተዘጋጀ ፈልገው መግዛት ይችላሉ። "መክተበተ ሻሚላ" ውስጥም
تعليقات الشيخ البراك على المخالفات العقدية في فتح الباري
በሚል ምግኘት ይቻላል። ወይም ጉግል ላይ ይፈልጉት።
/channel/IbnuMunewor
ታዋቂ ግን ደካማ ሐዲሦች እና ታሪኮች
(ክፍል 2)
~~~
ያለንበት ወር የረጀብ ወር ነው። ከዚህ ወር ጋር የሚያያዙ በርካታ መሰረተ ቢስ ቅጥፈቶችና ደካማ ሐዲሦች አሉ። ወሩን ጠብቀው ብዙ ሰዎች ሲያሰራጯቸው ያጋጥማል። ይህንን የረጀብ አስመልክቶ ከተላለፉ መሰረተ ቢስ ዘገባዎች እና ደካማ ሐዲሦች ውስጥ ከፊሉን እንይ፡-
[1ኛ]፡-
رجب شهر الله وشعبان شهري ورمضان شهر أمتي
“ረጀብ የአላህ ወር ነው። ሸዕባን የኔ ወር ነው። ረመዷን ደግሞ የህዝቦቼ ወር ነው።” ሸይኹል አልባኒ - ረሒመሁላህ - ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [አዶዒፋህ፡ 4400]
[2ኛ]፡- ረጀብ ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
اللهم بارك لنا في رجب وشعبان، وبلغنا رمضان
“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን አድርሰን።” ነወዊይ በ“አዝካር”፣ ዘሀቢይ በ“ሚዛን” ደካማ እንደሆነ ብይን የሰጡ ሲሆን አልባኒም “ደካማ ነው” ብለዋል። [ዶዒፉል ጃሚዒ ሶጊር፡ 4395]
[3ኛ]፡-
فضل شهر رجب على الشهور كفضل القرآن على سائر الكلام
“የረጀብ ወር በሌሎች ወራት ላይ ያለው ብልጫ ቁርኣን በሌሎች ንግግሮች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” ኢብኑ ሐጀር “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው ብለዋል።
[4ኛ]፡-
خمس ليال لا ترد فيهن الدعوة أول ليلة من رجب، وليلة النصف من شعبان، وليلة الجمعة، وليلة الفطر، وليلة النحر
“አምስት ሌሊቶች በነሱ ውስጥ የተደረገ ዱዓእ አይመለስም። የመጀመሪያው የረጀብ ሌሊት፣ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት፣ የጁሙዐ ሌሊት፣ የዒደል ፊጥር ሌሊት እና የዒደል አድሓ ሌሊት ናቸው።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 1452] [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 2852]
[5ኛ]፡-
رجب شهر عظيم يضاعف الله فيه الحسنات، فمن صام يوما من رجب، فكأنما صام سنة، ومن صام منه سبعة أيام، غلقت عنه سبعة أبواب جهنم، ومن صام منه ثمانية أيام، فتحت له ثمانية أبواب الجنة، ومن صام منه عشرة أيام، لم يسأل الله شيئا إلا أعطاه إياه، …
“ረጀብ አላህ መልካም ምንዳዎችን የሚያነባብርበት ታላቅ ወር ነው። ከረጀብ አንድ ወር የፆመ ሰው አመት እንደፆመ ነው። ከሱ ሰባት ቀናትን የፆመ ሰባቱ የጀሀነም በሮች ይዘጉለታል። ከሱ ስምንት ቀናትን የፆመ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል። ከሱ አስር ቀናትን የፆመ አላህን የሆነ ነገር አይጠይቅም፣ እሱኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ፣ …” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 5413]
[6ኛ]፡-
إن في الجنة نهرا يقال له رجب ماؤه أشد بياضا من اللبن وأحلى من العسل من صام يوما من رجب سقاه الله من ذلك النهر
“በጀነት ውስጥ ረጀብ የሚባል ወንዝ አለ። ውሃው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ ነው። ከረጀብ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ ከዚያ ወንዝ ያጠጣዋል።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 1902]
[7ኛ]፡-
صوم أول يوم من رجب كفارة ثلاث سنين، والثاني كفارة سنتين، والثالث كفارة سنة، ثم كل يوم شهرا
“የረጀብን የመጀመሪያ ቀን መፆም የሶስት አመት ወንጀል ያብሳል። ሁለተኛው የሁለት አመት ያብሳል። ሶስተኛው ደግሞ የአመት ያብሳል። ከዚያም እያንዳንዱ ቀን የወር ነው።” አልባኒ ደካማ ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 3500፣ 5649]
[8ኛ]፡-
لا تغفلوا عن أول جمعة من رجب فإنها ليلة تسميها الملائكة الرغائب
“ከረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐ አትዘናጉ። እርሷ መላእክት ‘አረጋኢብ’ ብለው የሚጠሯት ሌሊት ነች።” ‘ሶላተ ረጋኢብን’ በተመለከተ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “እርሷን የፈጠረን ሰው አላህ ይርገመው! እርሷ አስቀያሚ ቢድዐ ነች!” [ሸርሑ ሙስሊም] በተጨማሪም እሷንና የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ሶላትን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡- “… ቢድዐና አስቀያሚ ፈጠራዎች ናቸው። በ‘ቁቱል ቁሉብ’፣ ‘ኢሕያእ ዑለሚዲን’ ኪታብ ውስጥ ስለተጠቀሱ ማንም እንዳይሸወድ። እነሱን በሚጠቁመው ሐዲሥም እንዲሁ (እንዳይሸወድ)። ምክንያቱም ሁሉም ውድቅ ነውና።…” [አልመጅሙዕ፡ 3/548]
[9ኛ]፡-
أن رسول الله -صلى الله عليه وسلم- لم يصم بعد رمضان إلا رجبًا وشعبان
“የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን በኋላ ረጀብንና ሸዕባንን እንጂ አልፆሙም።” ኢብኑ ሐጀር በጣም ደካማ ነው ብለውታል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 12]
[10ኛ]፡-
من صلى المغرب في أول ليلة من رجب ثم صلى بعدها عشرين ركعة يقرأ في كل ركعة بفاتحة الكتاب، وقل هو الله أحد مرة، ويسلم فيهن عشر تسليمات، أتدرون ما ثوابه؟ قال: حفظه الله في نفسه وأهله وماله وولده، وأجير من عذاب القبر، وجاز الصراط كالبرق بغير حساب ولا عذاب
“በረጀብ የመጀመሪያ ሌሊት መግሪብን ሰግዶ ከዚያም በእያዳንዷ ረከዐ ፋቲሐንና ቁል ሁላሁ አሐድን አንድ ጊዜ እየቀራ፣ በአስር ተስሊማት እያሰላመተ ሃያ ረከዐ የሰገደ ሰው ምንዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አላህ በነፍሱም፣ በቤተሰቡም፣ በገንዘቡም፣ በልጁም ይጠብቀዋል። ከቀብር ቅጣትም ይጠበቃል። ሲራጥንም ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት እንደ ብልጭታ ያቋርጧል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/123] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 20]
[11ኛ]፡-
من صام من رجب وصلى فيه أربع ركعات ... لم يمت حتى يرى مقعده من الجنة أو يُرى له
“ከረጀብ ፁሞ፣ በሱ ውስጥ አራት ረከዓዎችን የሰገደ ሰው … በጀነት ውስጥ መቀመጫውን ሳያይ ወይም ሳይታይለት አይሞትም።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/124] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 21]
[12ኛ]፡-
إن شهر رجب شهر عظيم، من صام منه يومًا كتب الله له صوم ألف سنة ...
“የረጀብ ወር ታላቅ ወር ነው። ከሱ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺ አመት ፆም ይመዘግብለታል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/206-207] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 26]
ከረጀብ ጋር የሚያያዙት ዘገባዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። እነዚህን ለምሳሌ ያክል ይዘን ሌሎቹንም ጭምር በሚመዝን የዓሊሞች ንግግር ልቋጭ:—
1/ አልሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፡- “የረጀብን ወር ልዩ ብልጫም፣ መፆሙን ወይም ከፊሉን በተለየ እንዲፆም፣ ወይም ከሱ ውስጥ የተገደበን ሌሊት በሶላት ማሳለፍን፣… የሚጠቁም ለማስረጃነት የሚበጅ ትክክለኛ ሐዲሥ አልተላለፈም።" [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 6 እና 8]
2/ አልሓፊዝ አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ በክር አዲመሽቂይ (691 ሂ.) ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ የረጀብን ፆም እና ከፊል ሌሊቶቹን መስገድን የሚጠቁም ሐዲሥ ውሸት፣ ቅጥፈት ነው።” [አልመናሩል ሙኒፍ፡ 1/96]
ሱና ሶላቶችን በቤት ውጥ መስገድ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንድህ ብለዋል
ሱና ሶላትን በቤት ውስጥ መስገድ ጥበቡ፦
¹) ለኢኽላስ የቀረበ ይሆናል
²) ከሪያህ የራቀ ይሆናል
³)ቤት መቃብር ከመምሰል ይወገዳል(ይወጣል)
⁴)ቤተሰቦችን ለሶላት ማነሳሳትና ሶላትን እንድወዱ ያደርጋል
ምንጭ፦ [ፈታዋ ኑሩን ዐለ`ደርብ 2፤8]
✍Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
አዛን እየተደረገ መስጂድ የገባ ሰው አዛኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሙአዚኑን በአዛኑ እየተከተለ መጠበቅ አለበት። እንጂ ቀጥታ ወደ "ተሒየ፞ተል መስጂድ" መግባት የለበትም።
የጁሙዐ አዛን ከሆነና ኸጢቡ ሚንበር ላይ ወጥቶ ከሆነ ግን አዛኑን መከተል ትቶ "ተሒየ፞ተል መስጂድ" ነው መስገድ ያለበት። ምክንያቱም ሙአዚኑን በአዛን መከተል "ሙስተሐብ" ነው፣ ግዴታ አይደለም። ኹጥባ ማዳመጥ ግን ግዴታ ነው። ስለዚህ ከ"ሙስተሐቡ" ይልቅ ለግዴታው ቅድሚያ መስጠት ይገባል።
/channel/IbnuMunewor
إذا غُلِبت فلا تقل انتصر العدو ولكن قل ...!
#التفريغ
رابط تحميل المقطع على التيليجرام 👇👇
/channel/ahmed19871111/2617
👉ሱሪን ማስረዘም እና ሱሪውን ያስረዘመ ግለሰብ ማኩረፍና ማግለል በሸሪዓ ዕይታ ።
ይህ ጥያቄ የቀረበው ለታላቁ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ ሲሆን ጥያቄውም እንደሚከተለው ነው።
"ጀዛከላሁ ኸይረን ያ ሸይኽ! ሱሪን ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች ይቆጠራልን? እሱን ማኩረፍና ማግለል እንዴት ይታያል?
መልስ ፦
⛔️"ሱሪን ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።
🔖ምክንያቱም የአላህ መልክተኛው ﷺ ሱሪ ያስረዘመ የአላህ ቅጣት እንደሚገባው ዝተው ተናግረዋል ።
◼️" የውመል ቂያማ እለት ሦስት ሰዎችን አያናግራቸውም፣ (ከወንጀላቸው) አያፀዳቸውም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
(ሰሀባቹም)፦ "ከሰሩ ተዋረዱም እነርሱ ማናቸው?" በማለት ጥያቄ አቀረቡ። መልክተኛውም፦"ሱሪውን የሚያስረዝም ፣ በስጦታው የሚመፃደቅ እና በውሸት መሐላ ሸቀጡ እንዲሸጠ ያደረገ ።"
📎(ከሐዲሱ እንደተገነዘብነው) ሱሪ ማስረዘም ከከባባድ ወንጀሎች የሚቆጠር ነው። ነገር ግን ማኩረፍ
ልጄ ሆይ ዕወቅ❗️
ማኩረፍ እና ማግለል መድሐኒት ነው ጠቅሞ ካገኘኸው ተጠቅመው ። ጥቅም ካላስገኘ አሊያም ይባስ 《በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ 》 አይነት ከሆነ ማኩረፍና ማግለል (እንደ መፍትሔ) አትጠቀመው።
ይህ ሱሪውን የሚያስረዝም ግለሰብ ካኩረፍነው በተግባሩ የሚያፍርና የሚቃና ከሆነ እና እንዲህም ካለ፦ "እንደ ሙሳ አሳሙሪይ ሠዎች መሐል ምሣሌ መሆን አልፈልግም "ሳሙሪይ ሰዎች እንዳይጠጉህ እና እንዳይቀርቡህ" ተብሎ እንደ ተረገመው መሆን አልፈልግም ብሎ ሱሪውን ከፍ ካደረገ ይሄኔ አኩርፈው።
ነገር ግን ስናገለው ይባስ ወንጀሉ የሚጨምር ፣ የሚጠላህ እና በልቡ ጥላቻ የሚቋጥርብህና ብሎም ሰዎችን ካነሳሳብህና ካሳመፀብህ ይህኔ አታግልለው አታኩርፈውም።
ይህ መርሕ ላንተ በቂ ነው፦
ማግለልና ማኩረፍ
መድሐኒት ነው ከፈየደ ተጠቀመው አሊያ ግን አትጠቀመው።
ምንጭ ፦
📚【ሲልሲለቱ ሊቃኣት አልባብ አልመፍቱሕ(200)】
🔈ፈትዋውን በድምፅ ማድመጥ የፈለገ ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫን፦
http://zadgroup.net/bnothemen/upload/ftawamp3/od_200_13.mp3
t.me/Menhaj_Salafiya
➢ በቡድንና በአጠቃላይ የተጠቀሱ ካሉ በነሱ ማመን።
ለምሳሌ፦ -> የጀነት ጠባቂዎች
-> የዓርሽ ተሸካሚዎች. . . .
-> በይተል መዕሙን 75 000 መላኢኮች እየገቡ ዒባዳ እንደሚያደርጉና አንድ ግዜ የደረሰው ደግሞ እንደማይደግም።
➢ በስም የተጠቀሱመላኢኮችን ካሉ በስማቸው ማመን። በነጠላ የተጠቀሰ መላኢካ ካለ በነጠላ ማመን። ስለ እያንዳንዳቸው የተጠቀሰ ባህሪ ካለ በዛ ማመን።
ለምሳሌ ፦ ጂብሪል
አላህ እንዲህ አለ፦
﴿النحل: ١٠٢﴾ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ
(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ (16: 102)
ጅብሪል 600 ክንፍ አለው አንዱ ክንፉ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አድምሱን ይሞላዋል።
ነብዩ ሙሀመድ(ሰለላ ዓለያሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ተናግረዋል ፦ ጅብሪል ስራው መልእክትን (ዋሒን) ከ አላህ ወደ ነብያት ማድረስ ነው።
አላህ እንዲህ አለ፦
﴿النحل: ١٠٢﴾ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ
(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ (16: 102)
➢ በቡድን (ባጠቃላይ) የተነገሩ ባህሪይ፣ ስራ ወይንም መገለጫ ከተነገረ ማመን።
ለምስሌ፦
አላህ እንዲህ አለ፦
الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴿فاطر: ١﴾
ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ (35: 1)
አላህ እንዲህ አለ፦
وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ ﴿الأنفال: ٥٠﴾
እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡ (8: 50)
አላህ እንዲህ አለ፦
جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِم مِّن كُلِّ بَابٍ سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ ﴿الرعد: ٢٣ - ٢٤﴾
(እርሷም) የመኖሪያ ገነቶች ናት፡፡ ይገቡባታል፡፡ ከአባቶቻቸውም፣ ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርያቸውም መልካም የሠራ ሰው (ይገባታል)፡፡ መላእክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ፡፡ «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡ (13: 23 - 24)
###
የቢድዓ ሰዎች ምልክቶች በሸይኽ ረስለን
በትርጉም የቀረበ ትምህርት
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://youtu.be/igieYyzlxlM
👇👇👇👇👇👇👇👇
ዝግጅቶቻችንን ለመከታተል
➷➘➷➘
√√√√√√√√√√√√√√√√√
👇👇👇👇
YOU TUBE SUBSCRIBE
https://youtube.com/channel/UC-xgCtuVRlQc8tPk7ElpPww
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👇👇👇👇
Facebook
http://fb.com/Ikhlasmedia1442
👇👇👇👇
Telegram
http://t.me/IkhlasMedia
من أجمل ما ستسمعه من الشيخ العلّامة صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله ورعاه وأطال في عمره ..
t.me/Menhaj_Salafiya
قال ابن القيم رحمه الله:
أربعة تجلب الرزق :
قيام الليل
وكثرة الاستغفار بالأسحار
وتعاهد الصدقة
وذكر الله أول النهار وآخره.
زاد المعاد 378/4
t.me/Menhaj_Salafiya
ከ5440 በላይ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን የድምጽ ፋይሎች በዚህ ሊንክ ያገኑታል → bit.ly/24Sizol
____________________
جَمِيعُ أَشْرِطَةِ الشَّيْخِ /مُحَمَّدِ بْنُ صَالِحٍ
الْعَثِيمَيْنِ رَحِمَهُ اللَّهُ:
فِي .( ٥٤٤٦ ). شَرِيطًا
bit.ly/24Sizol
©منقول
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
ልብ በሉ! በዚህ ወር ውስጥ ፆምና ሶላት አይኑር ለማለት አይደለም። ወሩን ከሌሎቹ ወራት በተለየ መልኩ መያዝ አይገባም ነው አጠቃላይ ጭብጡ።
………………………………………………
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor
ሸይኽ ፈውዛን እንዲህ ብለዋል:—
"የረጀብ ወር እንደሌሎቹ ወራት ነው። ከሌሎቹ ወራት ተነጥሎ በዒባዳ አይለይም። ምክንያቱም ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላትም ይሁን፣ በፆምም ይሁን፣ በዑምራም ይሁን፣ በሌላም ይሁን እሱን መለየት አልተገኘምና።" [አልሙንተቃ ሚነል ፈታዋ: 1/222]
እራስን መመልከት~~~~~~
እየውልህ ወንድሜ! ህሊና አልባ በድን ማሽን አትሁን። የምትገባው ከራስህ እንጂ ከኡስታዝህ ቀብር አይደለም። ሲራጥን የምትሻገረው በራስህ ስራ መጠን እንጂ ኡስታዝህ እጅህን ይዞ አያሻግርህም። ያለ አስተርጓሚ ራቁትህን ከጌታህ ፊት ለምርመራ ስትቆምም ኡስታዝህ ከጎንህ አይቆምልህም። ይህንን ሁሉ የምልህ ማንንም በጭፍን እንዳትከተል ነው። በአሁኑ ሰዓት በየሰፈሩ ያሉ ሸይኾችና ኡስታዞች አብይ መታወቂያ ጭፍንነትን ሥራዬ ብለው የሚግቱ፣ ተማሪዎቻቸውን በጭፍንነት የሚኮተኩቱ መሆናቸው ነው። የወደዱትን በጭፍን እንድትወድላቸው፣ የጠሉትን በጭፍን እንትጠላላቸው እስከ ደም ጠብታ ይታገሉሃል። ቁርኣን፣ ሐዲሥ፣ የዑለማእ ንግግር ተንኮለኛ በሆነ መልኩ ከአውድ ውጭ እያገናኙ የሃሳብ ሽብር ይነዙብሃል። እዚህ ላይ "ለምሳሌ እነ እንትናን ብንወስድ… " ብዬ ባጣቅስ የእነ እንትና ጭፍራ ጦር ሰብቆ ይነሳል። ከነሱ ውጭ ያለው ደግሞ በአመዛኙ ይደግፋል። እውነት ለመናገር ግን ጣት መቀሰሩ ስለሚቀለን እንጂ ይሄ በሽታ ይብዛም ይነስም በየቤቱ ይገኛል። ችግራችን ግን አይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ጥለን ከሌሎች አይን ያለን ጉድፍ ነው የምንመለከተው። የሌሎችን ጥፋት ለማጋለጥ እንረባረባለን። እሺ የራሳችንንስ ማን ያርመው? ለማነው የምንተወው? ኧረ ልባችን ፈቃጅ ተመልካች አጣ!! ድባቡ የተበከለ ሆኖ መገሳሰፅ አልቻልንም። እኛም ለራሳችን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠንም። ግን እስከመቼ?
እና ወንድሜ ከማንም ጎጠኛ ቡድን ጋር ጭፍን ተሰላፊ አትሁን። ከዑለማእ ንግግር ውስጥ ከስሜቱ ጋር በሚገጥምለት መልኩ እየመረጠ የሚያቀርብ ሰው ስታይ በችኮላ እጅ አትስጥ። የትኛውም ቡድን ጋር የተሰለፈው ሁሉ ይህንን እያደረገ ነውና የሱ ከሌሎች በምን እንደሚለይ ረጋ ብለህ መርምር። የማይነቃነቅ ነባራዊ ሐቅ፣ የአህለ ሱና ዋና መታወቂያ አስመስሎ ያቀረበልህ ጉዳይ አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ያለው አቋም እሱ ካወራህ ተቃራኒ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህና ከስሜት ነፃ ሆነህ በሚገባ ፈትሽ። ደግሞ ቆም ብለህ ታዘባቸው። ብዙዎቹ ቡድናዊነት የሰበሰባቸው አካላት
— "እነ እከሌ ጠርዘኞች ናቸው፣ ድንበር አላፊዎች ናቸው" እያለ ከፍ አድርጎ ያስተጋባል። የሚያስከነዱ ጠርዘኞችን ግን አቅፎ ያሽሞነሙናል። ምክንያቱም እነዚህኞቹ እሱ ሲስል የሚስሉ፣ ሲያነጥስ የሚያነጥሱ የገደል ማሚቶዎች ናቸውና።
— "እነ እከሌ ጃሂሎች ናቸው" ይልሃል። በምንም መመዘኛ ከነሱ የማይሻሉ ሰዎችን ግን በትልልቅ መድረክ ላይ ያስተዋውቃል። ምክንያቱ አቋማቸው ከአቋሙ ስለገጠመለት ብቻ ነው።
— "እነ እከሌ አቋም የሌላቸው ወላዋዮች ናቸው" ያለህ ስብስብ በየክስተቱ ባደባባይ የሚዋልሉ ሰዎችን ከጎናቸው አሰልፈው ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም መመዘኛው ርካሹ ቡድናዊ ሚዛን እንጂ ኢኽላስ አይደለምና።
ወንድሜ ሆይ! አላህን አስበህ ስለምትሰራው ነገር የማንንም ጭብጨባ አትጠብቅ። የማንም ተቃውሞም አይጠፍህ። ይልቅ ውስጥህን አዳምጥ፣ ኢኽላስህን ፈትሽ። ያለ ኢኽላስ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ነው። ልፋትህም ከንቱ ድካም። በደዕዋህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሰፊው ህዝብ ይሁን። አትዘንጋ! ዛሬም አብዛኛው ወገናችን ከተውሒድ ግንዛቤ የራቀ ነው። ሺርክ ላይ የሚማቅቀው ብዙ ነው። ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ላይ እስከ አፍንጫው የተነከረው ቀላል አይደለም። ቀዳሚው ጥረትህ የዚህን ወገንህን ሸክም ለመቀነስ ይሁን። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ ገሸሽ በማድረግ ውሃ ቀጠነ፣ ከሰል ጠቆረ ብሎ ለሚነታረክ ጀርባህን ስጠው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አረፋ ነው።
በኢኽላስ እስከሰራህ ድረስ የማንም ጫጫታ ቅስምህን አይስበረው። ሰዎች እንቅፋት ሲያበዙ አንተ ፅናትህን ጨምር። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትበል።
የሌሎችን ጩኸት ሳታጣራ የምታስተጋባ በቀቀን አትሁን። በጭፍን አትደግፍ። በጭፍን አትንቀፍ። እወቅ! እውር ጥላቻና እውር ውዴታ ነገ ከአላህ ፊት ያሳፍርሃል። ማንንም በእውር ድንብር አትከተል። ጭፍን ወገንተኝነት በቃላት ቢያሸበርቅም፣ በሱና፞ ስም ቢቀርብም የተወገዘ ነው። የአሳማ ስጋ በወርቅ ሰሀን ስለቀረበ አሳማነቱ አይቀየርም። አሳማ አሳማ ነው። የመዝሀብ ሰዎች ዘንድ የምናውቀው ጭፍን ወገንተኝነት ተቀባብቶ ተከሽኖ በሱና፞ ዑለማዎች ስም ሲቀርብ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ አንዳንዶች በየሰፈሩ በየመንደሩ እየተቧደኑ ‘ወላእ’ እና ‘በራእ’ የሚቋጥሩባቸው አካላት መመደባቸው ነው።
ደግሞም በልክ እንሁን። በሌሎች ሃገራት ወይም አካባቢዎች ያየነውን ወይም የሰማነውን ኺላፍ ሁሉ ሰበብ እየፈለጉ እየጎተቱ ማምጣት ግልብነት ነው። ወላጆችህ ወገኖችህ በሺርክ እየተጨማለቁ አንተ በሸይኽ እንትናና በሸይኽ እከሌ መካከል ስለተፈጠረው ኺላፍ ጧት ማታ እያቦካህ በአካባቢህ ያሉ ዱዓቶችን ለመፈረጅ አድፍጠህ ብትጠባበቅ የፊትና ጥማትህን እንጂ ንቃትህን አያሳይም። በአካባቢህ ይሄ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ ሳይኖርህ እንዳቅማቸው እየደከሙ ያሉ አካላትን ትንሽዬ ጥረት አይኗን ለማጥፋት ጦር ብትሰብቅ ጥሬነትህን ብቻ ነው የሚያሳየው። ወንድሜ ከቻልክ አግዝ። ክፍተት ካየህ አርም። አቅሙ ከሌለህ ባላቸው አስመክር። በምትችለው ከጎናቸው ቁም። ለሰፈርህ ለአካባቢህ የደዕዋ እንቅስቃሴ አጋዥ እንጂ አፍራሽ አትሁን። ለደዕዋ እንቅፋት በመሆን ሌሎች እንዳይለወጡ መሰናክል አትፍጠር። ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገሮችን መጣል ፀያፍ ጥፋት ነው። ወደ ኣኺራ በሚወስደው የደዕዋ መንገድ ላይ እንቅፋት መጣል ግን እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። እንዲህ አይነቱን የወንጀል ሸክም የምትቋቋምበት ጫንቃው የለህምና ዛሬውኑ ሚናህን ለይ። ዛሬውኑ ለደዕዋ ያለህን አስተዋፅኦ ገምግም።
………………………………………………
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor
ክርስቲያን ሴት ማግባት~~~~~~~~
ለሙስሊም ወንዶች እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ አካሄድ ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግኝኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። እርሱም በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል።
ቁርኣናችን ደግሞ ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከሚታወቁ የመፅሐፉ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።
ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው።
ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor
24ኛ ሓዲስ
الحديث الرابع والعشرون
🔴. تحريم الظلم
▫24ኛ ሓዲስ
🔴 የሓዲሱ ትርጉም
📌 በደል የተከለከለ መሆኑ።
📖. አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ:አላህ እንዲህ አለ “ እናንተ ባሮቼ ሆይ! እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመራሁት ሲቀር ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ። ስለዚህ ቀጥተኛ መንገድ እንድመራችሁ ለምኑኝ እመራችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመገብኩት ሲቀር ሁላችሁም ረሃብተኞች ናችሁ። እንድመግባቹህ ጠይቁኝ እመግባችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ ያለበስኩት ሲቀር ሁላችሁም እርቃናችሁ ናችሁ። እንዳለብሳቹህ ጠይቁኝ አለብሳችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ ቀንና ለሊት ትሳሳታላችሁ እኔ ደግሞ ወንጀሎችን ሁሉ እምራለሁ። ስለዚህ መሃርታን ጠይቁኝ እምራችኋለሁ። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተኮ እኔን የመጉዳት ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጉዳት አትችሉም ደግሞም እኔን የመጥቀም ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጥቀም አትችሉም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ጌታን ፈራሂ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይጨምርም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያቹህ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ወንጀለኛ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይቀንስም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ አንድ ሜዳ ላይ ቆመው ቢጠይቁኝና ሁሉንም የጠየቁኝን ብሰጣቸው፥ ይህ ስልጣኔ ላይ ልክ መርፌ ባህር ላይ ገብቶ ከባህሩ እንደሚያጎድለው ቢሆን እንጂ ምንም አያጎድልም። እናንተ ባሮቼ ሆይ!ስራችሁን ነው የምቆጥርላችሁ ከዛም በስራችሁ መሰረት እከፍላችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ ሌላን ነገር ያገኘ ግን ራሱን እንጂ ሌላን አይውቀስ።”
ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።
📝. ከሃያ አራተኛው ሓዲስ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
▫ • ይህ ሓዲስ ሓዲሰል ቁድስ (ነብያችን[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ከአላህ የዘገቡት ሓዲስ) እንደሆነ።
▫ • አላህ በጣም ፍትሃዊ እንደሆነና ማንንም እንደማይበድል።
▫ • በመካከላችን መበዳደል ክልክል እንደሆነ።
▫ • የሰው ልጅ አላህ ካልመራው ጥመትና መሃይምነት ውስጥ እንደሚሆን።
▫ • አላህን ቀጥተኛ መንገድ እንዲመራን መጠየቅ እንዳለብን።
▫ • ሁሉም ባርያዎች አላህ የመገባቸው ሲቀራ የተራቡ እንደሆኑ እና አላህ ያለበሳቸው ሲቀሩ እርቃን እንደሆኑ።
▫ • የሰው ልጆች ብዙ ወንጀል እንደሚሰሩ። ወንጀል መሃሪ ደግሞ አላህ ብቻ እንደሆነ። ስለዚህ አላህን ለወንጀላችን መሃርታ መጠየቅ እንዳለብን።
▫ • ወንጀል ምንም ቢበዛም ሰውየው መሃርታን ከጠየቀና ወደ አላህ ከተመለሰ አላህ ወንጀሉን እንደሚምር።
▫ • ወንጀለኛ ወደ አላህ ሳይመለስ ከሞተ በስራው ራሱን እንደሚወቅስ።
📕📗📘📙
ሼይኽ አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
ሰለፊያ ዳዕዋ ለሆነ ለአንድ ግለሰብ ወይንም ለሆነ ለአንድ አመለካከት (አስተያየት) ወገንተኝነትን አታውቅም። ሰለፊያ ዳዕዋ የምታውቀው ማስረጃን ብቻ ነው።
( ሲልሲለቱል ሁዳ ወን ኑር)
t.me/Menhaj_Salafiya
قال الشيخ الألباني رحمه الله:-
الدعوة السلفية لا تعرف التعصب لشخص معين ولا لرأي معين إنما الحجة والبرهان والدليل.
(سلسلة الهدى والنور)
t.me/Menhaj_Salafiya
#ሰላተል__ጀመዓ
ሰኢድ ኢብን ሙሰይብ እንዲህ ይላሉ፦ ከዛሬ አርባ አመት በፊት ጀምሮ ሰላት በጀመአ አምልጦኝ አያውቅም"
(ሒልየቱል አልውልያ (2/162)
t.me/Menhaj_Salafiya
ሸይክ አላማህ ኢብኑ ተይሚያ رحمَه الله እንድህ ይላሉ፦
#ሙስሊም ሁል ጊዜ ሱናን ህያው ለማድረግ እና ቢዳዓን ለመግደል ይሰራል።
( አል ፈታዋ 487.3)
t.me/Menhaj_Salafiya