አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ የሱና እህት ወንድሞች አንድ መልካም ነገር ወደናንተ ይዘን ብቅ ብለናል ሶደቃተል ጃሪያ ሊሆንልን የሚችል እሱም" እንደሚታወቀው ሀገራችን በተለያዩ ገጠራማ ቦታዎች ላይ የኪታብና የቁርዓን እጥረት አለ" እና እነሱን ለመርዳት ኪታብና ቁርዓን ከዚህ አሰባስበን ልንልክ አስበን ግሩፕ ከፍተናል መርዳት የሚችል ወደ ግሩፑ ይቀላቀል ሊንኩንም ሼር አድርጉልን
በዋትስአፕ መቀላቀል ለምትፈልጉ
https://chat.whatsapp.com/LY3f45dnmXBF8t066U3piy
በቴሌግራም መቀላቀል ለምትፈልጉ
/channel/+tYk7-EuYycBmZDU0
አብደላ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ይላሉ:-
«ዘፈን ንፍቅናን በልብ ዉስጥ ይተክላል፤ ልክ ዉሃ ሳር እንደሚያበቅለዉ ሁሉ።»
t.me/Kunizewjeten2
الحمد لله مستراح منه وفات أكبر رأس من رؤوس الخوارج يوسف القرضاوي بعد كل الخراب الدي حل في بلدان المسلمين بسببه
Читать полностью…تعدد الزوجات مما ينبغي أن يفعله العبد إذا كان ذا قدرة مالية وبدنية وآمناً من الجور والميل.
فإن في كثرة النساء كثرة الأولاد، وكثرة الأمة، وتحصين فروج كثير من النساء الباقيات في البيوت، وهو من نعمة الله عز وجل.
ولولا أن الحكمة في تعدد الزوجات ما شرعه الله عز وجل ولا أذن فيه.
نعم إذا كان الإنسان قليل المال أو ضعيف البدن أو خائفاً ألا يعدل فهنا نقول: الأفضل أن تقتصر على ما عندك، وتسأل الله التوفيق.
{ الشيخ ابن عثيمين }
t.me/Kunizewjeten2 👇
تعدد الزّوجات برعاية الأرّز المفور ..
أطعمهم الروز يا رجل ولا تخاف
قال رسول اللهﷺ
"من حلف بغير الله فقد أشرك"
📚 صحيح أبي داود [٣٢٥١]
http://t.me/Menhaj_Salafiya
👆👆👆
#በአላህ ዲን ላይ መጽናት እና ለመጽናት ሰበብ የሚሆኑ ነጥቦች (ሙሉ ሙሐደራ)
🔶በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አባስ መስጂድ የተደረገ ሙሐደራ።
🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)
🌐 /channel/shakirsultan
ታላቁን የኡሱል አልፊቅህ ሊቅ እንተዋወቅ ፦
አስተማሪና አስገራሚ በሆኑ ፈትዋዎቻቸውና ትምህርቶቻቸው እንጠቀም!
الشيخ محمد علي فركوس
በርካታ ዑለሞች የመሠከሩለትን እንዲህ አይነቱን የሰፊ እውቀት ባለቤት አለማወቅ የመጠቀማችንን ክፍተት የሚያሠፋ ደስ የማይል ነገር ነው ። ሌሎችን በጭፍን በመከተልና በመደናበር በሱና ዑለሞች ላይ ነጋ ጠባ ለሚዘባርቀው ጀሮህን ከሠጠህ እንዲህ ዓይነቱ ታላቅ ዓለም ላትጠቀምበት ያመልጥሃል ። እየቆየህም ሌሎችን ብርቅ የሱና ዑለሞች በስራ ፈቶቹ ጥሪ ታጣላህ - ያልነካኩት የላቸውምና ።
( የተከላከልኩት ና እንድንጠቀምባቸው ም
የጠቆምኩት ከሱና ዑለሞች ብቻ ነው ! )
http://ferkous.com/home/
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ👇
t.me/Muhammedsirage
"ወንጀል ከሱና አያስወጣም " እየተባለ .. ውሸት ፣ ማጭበርበር እና ሌሎችም አስከፊ ወንጀሎች ዉስጥ በግዴለሽነት መነከር አሳፋሪ መባል የሚያንሰው ክፉ ና ፀያፍ ምግባር ነው .. ወቅታችን ላይ ደግሞ ይሄው ክፉ ደዌ ብዙዎችን አጥቅቷል ---- ወንጀል አይጎዳ ይመስል በቀጥታም ባይሆን ባዙሪት ቀላልነቱ ይሰበክ ይዟል - በአንዳንዶቻችን ...
ነብዩን እና ባልደረቦቻቸውን እከተላለሁ የሚል ግለሠብና ወገን ወንጀልን የሚመለከትበት አይን ኢርጃእን የተጎራበተ መሆኑ ወይም የተጎራበተ ሊሆን መቃረቡ ይሳዝናል ...
የአላህን፡ ህግጋቶች ማክበርና አግዝፎ መመልከት የተቅዋ እና የአላህን ቅጣት መጠንቀቅ መገለጫ ነው ...
وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ
የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች (ትእዛዦች ፣ ክልከላዎች ) የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦች የኾነች ጥንቃቄ ናት፡፡
ተቃራኒው እንዝላልነት የልብን መጥቆር አጉልቶ ይሳያል .....
ዓብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ሙእሚን ወንጀልን አግዝፎ እንደሚመለከት፣ ሙናፊቅ ግን እጅጉን አቅልሎና አሳንሶ እንደሚያየው ተናግረዋል .....
በወንጀሎች ላይ መዘውተር የከሃዲያን መገለጫ መሆኑንም ልንዘነጋ አይገባም ... አላህ እነሱን ሲገልፃቸው እንዲህ ይላል
وَكَانُوا يُصِرُّونَ عَلَى الْحِنثِ الْعَظِيمِ
(በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና )
ሌላው ነገር፦ ወንጀል (በተለይ የድብቅ ወንጀል ) መጨረሻን (አሟሟትን) ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነውና የዛሬውን ሱና ላይ መሆን ብቻ ሣይሆን የወንጀል ብዛት ሊያስከትል የሚችለውን መንሸራተትና ክፉ ውጤት እናስብ... አላህን እንፍራ ... ወደሱም እንመለስ ።
ጥፋትና ወንጀል ከሁላችንም ሊመነጭ የሚችል መሆኑን አልዘነጋሁም ። ከላይ በተጠቀሰው መጠን ወንጀል ላይ ቸልተኛ መሆን ግን እጅጉን አደገኛ ነው።
አላህ፡ ይመልሰን !
ቻናሉን ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። መልእክቱን ለሌሎች በማሰራጨት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።
t.me/Muhammedsirage
የኪታብ ጥቆማ #4
~~~
የሶሒሕ አልቡኻሪ ሸርሕ የሆነውን "ፈትሑል ባሪ" ኪታብ መግዛት ከፈለጉ አደራዎትን የሸይኽ ኢብኑ ባዝና የሸይኽ ዐብዱረሕማን ናሲር አልበራክ ‘ተዕሊቅ’ (የግርጌ ማስታወሻ) ያለበትን ቅጅ ይግዙ። ኪታቡ ውስጥ ባሉ ክፍተቶች ላይ እጅግ ወሳኝ የሆኑ እርምቶች ተሰጥተዋል። የበራክ እርምት እራሱን ችሎ በአንድ ጥራዝ ስለተዘጋጀ ፈልገው መግዛት ይችላሉ። "መክተበተ ሻሚላ" ውስጥም
تعليقات الشيخ البراك على المخالفات العقدية في فتح الباري
በሚል ምግኘት ይቻላል። ወይም ጉግል ላይ ይፈልጉት።
/channel/IbnuMunewor
ታዋቂ ግን ደካማ ሐዲሦች እና ታሪኮች
(ክፍል 2)
~~~
ያለንበት ወር የረጀብ ወር ነው። ከዚህ ወር ጋር የሚያያዙ በርካታ መሰረተ ቢስ ቅጥፈቶችና ደካማ ሐዲሦች አሉ። ወሩን ጠብቀው ብዙ ሰዎች ሲያሰራጯቸው ያጋጥማል። ይህንን የረጀብ አስመልክቶ ከተላለፉ መሰረተ ቢስ ዘገባዎች እና ደካማ ሐዲሦች ውስጥ ከፊሉን እንይ፡-
[1ኛ]፡-
رجب شهر الله وشعبان شهري ورمضان شهر أمتي
“ረጀብ የአላህ ወር ነው። ሸዕባን የኔ ወር ነው። ረመዷን ደግሞ የህዝቦቼ ወር ነው።” ሸይኹል አልባኒ - ረሒመሁላህ - ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [አዶዒፋህ፡ 4400]
[2ኛ]፡- ረጀብ ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
اللهم بارك لنا في رجب وشعبان، وبلغنا رمضان
“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን አድርሰን።” ነወዊይ በ“አዝካር”፣ ዘሀቢይ በ“ሚዛን” ደካማ እንደሆነ ብይን የሰጡ ሲሆን አልባኒም “ደካማ ነው” ብለዋል። [ዶዒፉል ጃሚዒ ሶጊር፡ 4395]
[3ኛ]፡-
فضل شهر رجب على الشهور كفضل القرآن على سائر الكلام
“የረጀብ ወር በሌሎች ወራት ላይ ያለው ብልጫ ቁርኣን በሌሎች ንግግሮች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” ኢብኑ ሐጀር “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው ብለዋል።
[4ኛ]፡-
خمس ليال لا ترد فيهن الدعوة أول ليلة من رجب، وليلة النصف من شعبان، وليلة الجمعة، وليلة الفطر، وليلة النحر
“አምስት ሌሊቶች በነሱ ውስጥ የተደረገ ዱዓእ አይመለስም። የመጀመሪያው የረጀብ ሌሊት፣ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት፣ የጁሙዐ ሌሊት፣ የዒደል ፊጥር ሌሊት እና የዒደል አድሓ ሌሊት ናቸው።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 1452] [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 2852]
[5ኛ]፡-
رجب شهر عظيم يضاعف الله فيه الحسنات، فمن صام يوما من رجب، فكأنما صام سنة، ومن صام منه سبعة أيام، غلقت عنه سبعة أبواب جهنم، ومن صام منه ثمانية أيام، فتحت له ثمانية أبواب الجنة، ومن صام منه عشرة أيام، لم يسأل الله شيئا إلا أعطاه إياه، …
“ረጀብ አላህ መልካም ምንዳዎችን የሚያነባብርበት ታላቅ ወር ነው። ከረጀብ አንድ ወር የፆመ ሰው አመት እንደፆመ ነው። ከሱ ሰባት ቀናትን የፆመ ሰባቱ የጀሀነም በሮች ይዘጉለታል። ከሱ ስምንት ቀናትን የፆመ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል። ከሱ አስር ቀናትን የፆመ አላህን የሆነ ነገር አይጠይቅም፣ እሱኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ፣ …” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 5413]
[6ኛ]፡-
إن في الجنة نهرا يقال له رجب ماؤه أشد بياضا من اللبن وأحلى من العسل من صام يوما من رجب سقاه الله من ذلك النهر
“በጀነት ውስጥ ረጀብ የሚባል ወንዝ አለ። ውሃው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ ነው። ከረጀብ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ ከዚያ ወንዝ ያጠጣዋል።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 1902]
[7ኛ]፡-
صوم أول يوم من رجب كفارة ثلاث سنين، والثاني كفارة سنتين، والثالث كفارة سنة، ثم كل يوم شهرا
“የረጀብን የመጀመሪያ ቀን መፆም የሶስት አመት ወንጀል ያብሳል። ሁለተኛው የሁለት አመት ያብሳል። ሶስተኛው ደግሞ የአመት ያብሳል። ከዚያም እያንዳንዱ ቀን የወር ነው።” አልባኒ ደካማ ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 3500፣ 5649]
[8ኛ]፡-
لا تغفلوا عن أول جمعة من رجب فإنها ليلة تسميها الملائكة الرغائب
“ከረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐ አትዘናጉ። እርሷ መላእክት ‘አረጋኢብ’ ብለው የሚጠሯት ሌሊት ነች።” ‘ሶላተ ረጋኢብን’ በተመለከተ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “እርሷን የፈጠረን ሰው አላህ ይርገመው! እርሷ አስቀያሚ ቢድዐ ነች!” [ሸርሑ ሙስሊም] በተጨማሪም እሷንና የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ሶላትን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡- “… ቢድዐና አስቀያሚ ፈጠራዎች ናቸው። በ‘ቁቱል ቁሉብ’፣ ‘ኢሕያእ ዑለሚዲን’ ኪታብ ውስጥ ስለተጠቀሱ ማንም እንዳይሸወድ። እነሱን በሚጠቁመው ሐዲሥም እንዲሁ (እንዳይሸወድ)። ምክንያቱም ሁሉም ውድቅ ነውና።…” [አልመጅሙዕ፡ 3/548]
[9ኛ]፡-
أن رسول الله -صلى الله عليه وسلم- لم يصم بعد رمضان إلا رجبًا وشعبان
“የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን በኋላ ረጀብንና ሸዕባንን እንጂ አልፆሙም።” ኢብኑ ሐጀር በጣም ደካማ ነው ብለውታል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 12]
[10ኛ]፡-
من صلى المغرب في أول ليلة من رجب ثم صلى بعدها عشرين ركعة يقرأ في كل ركعة بفاتحة الكتاب، وقل هو الله أحد مرة، ويسلم فيهن عشر تسليمات، أتدرون ما ثوابه؟ قال: حفظه الله في نفسه وأهله وماله وولده، وأجير من عذاب القبر، وجاز الصراط كالبرق بغير حساب ولا عذاب
“በረጀብ የመጀመሪያ ሌሊት መግሪብን ሰግዶ ከዚያም በእያዳንዷ ረከዐ ፋቲሐንና ቁል ሁላሁ አሐድን አንድ ጊዜ እየቀራ፣ በአስር ተስሊማት እያሰላመተ ሃያ ረከዐ የሰገደ ሰው ምንዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አላህ በነፍሱም፣ በቤተሰቡም፣ በገንዘቡም፣ በልጁም ይጠብቀዋል። ከቀብር ቅጣትም ይጠበቃል። ሲራጥንም ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት እንደ ብልጭታ ያቋርጧል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/123] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 20]
[11ኛ]፡-
من صام من رجب وصلى فيه أربع ركعات ... لم يمت حتى يرى مقعده من الجنة أو يُرى له
“ከረጀብ ፁሞ፣ በሱ ውስጥ አራት ረከዓዎችን የሰገደ ሰው … በጀነት ውስጥ መቀመጫውን ሳያይ ወይም ሳይታይለት አይሞትም።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/124] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 21]
[12ኛ]፡-
إن شهر رجب شهر عظيم، من صام منه يومًا كتب الله له صوم ألف سنة ...
“የረጀብ ወር ታላቅ ወር ነው። ከሱ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺ አመት ፆም ይመዘግብለታል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/206-207] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 26]
ከረጀብ ጋር የሚያያዙት ዘገባዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። እነዚህን ለምሳሌ ያክል ይዘን ሌሎቹንም ጭምር በሚመዝን የዓሊሞች ንግግር ልቋጭ:—
1/ አልሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፡- “የረጀብን ወር ልዩ ብልጫም፣ መፆሙን ወይም ከፊሉን በተለየ እንዲፆም፣ ወይም ከሱ ውስጥ የተገደበን ሌሊት በሶላት ማሳለፍን፣… የሚጠቁም ለማስረጃነት የሚበጅ ትክክለኛ ሐዲሥ አልተላለፈም።" [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 6 እና 8]
2/ አልሓፊዝ አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ በክር አዲመሽቂይ (691 ሂ.) ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ የረጀብን ፆም እና ከፊል ሌሊቶቹን መስገድን የሚጠቁም ሐዲሥ ውሸት፣ ቅጥፈት ነው።” [አልመናሩል ሙኒፍ፡ 1/96]
ሱና ሶላቶችን በቤት ውጥ መስገድ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንድህ ብለዋል
ሱና ሶላትን በቤት ውስጥ መስገድ ጥበቡ፦
¹) ለኢኽላስ የቀረበ ይሆናል
²) ከሪያህ የራቀ ይሆናል
³)ቤት መቃብር ከመምሰል ይወገዳል(ይወጣል)
⁴)ቤተሰቦችን ለሶላት ማነሳሳትና ሶላትን እንድወዱ ያደርጋል
ምንጭ፦ [ፈታዋ ኑሩን ዐለ`ደርብ 2፤8]
✍Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
እቃዎችን በመግዛት ላይ ተመስርቶ እጣ ለሚወጣላቸው ሰዎች የሚሰጡ “ ሽልማቶች”ን በተመለከተ ….
ዛሬ አንድ ማስታወቂያን ተመለከትኩ
“ እስከ ….. ድረስ ‘ ይህንን ይህንን ‘ ለሚገዙ ግለሰቦች ሽልማት አዘጋጅተናል “ የሚል
ማስታወቂያቸው በርእሱ ዙሪያ የተመለከትከኩትን የዑለማእ ንግግር እንዳስታወስ አደረገኝና ጥቂት ነገርን ማለት ፈለግኩ ….
ሸቀጥን በመግዛት ለባለ እጣዎች ብቻ የሚገኙ ሽልማቶችን በተመለከተ የተለያዩ ገፅታዎች አሉና የተለያዩ ብይኖች ይኖራሉ - ዑለማእ እንደሚሉት
ለዛሬ ሁለቱን ብቻ ላውሳ ፣
1ኛው ገፅታ ፣ ለባለ እጣዎች በታሰበው ሽልማት ምክንያት በሸቀጡ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጎ ከሆነ ( ለምሳሌ ሽልማቱ ከመዘጋጀቱ በፊት 100 ይሸጥ የነበረ እቃ ከሽልማቱ ወዲህ 110 ቢገባ ) ወደ እንዲህ አይነቱ ውል መግባት የተከለከለ ይሆናል ።
ምክንያቱም ተጨማሪ ገንዘብ እየተከፈለ ያለው የሽልማቱ ባለ እጣ ለመሆን ነውና ነገሩ ሎተሪ ብለው ከሚጠሩት ቁማር የተለየ እንዳልሆነ ዑለማእ ይገልፃሉ
2ኛው ገፅታ ባለ እጣ ለሚሏቸው የተዘጋጀን ሽልማት በማሰብ ብቻ የማይፈልጉትን እቃ መግዛት ሲሆን እንዲህ አይነቱ ቅርፅም እንደማይፈቀድ ዑለማእ ያስተምራሉ ።
ለምሳሌ “ የታሸጉ የልጆች ምግቦችን ለሚገዙ እስከ ጥቅምት የሚዘልቅ ሽልማት አለ - እጣው ለሚወጣላቸው “ ቢባል ፣ እነዚህን ሸቀጦች የመግዛት ልምድና ፍላጎት የሌላቸው ላጤዎች ሸቀጦቹን መግዛትና በሽልማቱ መጠቀም አይፈቀድላቸው - የቁማር ገፅታ አለበትና ።
ምክንያቱም ፣
እኒህ ግለሰቦች ገንዘቡን እየከፈሉ ያሉት ይኖራል የተባለውን ሽልማት በማሰብ እንጂ ለሸቀጡ እውነተኛ ፍላጎት ኖሯቸው አይደለም - ሸቀጡ ለነዚህ ሰዎች የመጀመሪ ግብ ሳይሆን ትርፍ ፍላጎት ነው - ሸልማቱ የመጀመሪያ ግብ ነው !
ለዚህማ ነው ሽልማት አለ ባይባል ኖሮ እቃውን ባልገዙት ነበር !
ሁለቱም የጠቀስኳቸው ገፅታዎች ከሎተሪ ቁማር እንደማይለዩ ዑለማእ ገልፀዋል ፣
አሏህ ያውቃል
እንጠንቀቅ
/channel/Muhammedsirage
ለወሎዬዎች
~
ዘረኝነት የብሄርና የጎሳ አመለካከት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። አካባቢን መሰረት ያደረገ አጉል መጎረር እና ሌሎችን ማናናቅም ዘረኝነት ነው። ሰው አገሩን፣ የትውልድ አካባቢውን ቢወድ ተፈጥሯዊ ነው ይሁን። ከዚያ አልፎ እራስን ልዩ እያደረጉ ማቅረብ ግን ፀያፍ አካሄድ ነው። እርግጥ ነው ማህበረሰቦች ከቦታ ቦታ አንፃራዊ በሆነ መልኩ የስነ ልቦና ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል። ይሄንን ከወሎ አንፃር እውነት ነው ብለን ብንቀበል እንኳ - ለሙግት ያህል ማለቴ ነው - "ሰው ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል"፣ "ኢትዮጵያ ስትሰለጥን ወሎን ትመስላለች" ማለት ምን ማለት ነው?! ከንቱ ጉራ!! እስኪ ብዙ ከማለት በፊት የላሊበላ ሙስሊሞችን ሁኔታ ተመልከቱ። እስኪ "የመቻቻል ተምሳሌት ነን" ከማለት በፊት የዳውንት ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲስተካከል ጩሁ።
በተረፈ የእምነት አጥር የማይከበርበት በወሎም ይሁን በሌላ፣ በአማራም ይሁን በኦሮሞ፣ ... ስም የሚቀነቀን ቡድንተኝነት ከኢስላም አንፃር ቆሻሻ አካሄድ ነው። ትኩረቴ እዚህ ላይ ነው። እስኪ አሁን ይሄ ምን ይባላል?
{እሷ የሸህ ልጅ ናት እኔ የመምሬ
ምን ያስጨንቀኛል ወሎ ተፈጥሬ?}
በአጭር ቃላት ብዙ ጥፋት! እንዲህ አይነት ኢስላማዊ እሴቶችን የሚጨፈልቁ በወሎ ስም የሚቀነቀኑ ብዙ ጉድፎች አሉ። አለማወቅ ልታፍርበት በሚገባ ጉዳይ እንድትጀነን ያደርግሃል። አካደሚ ያንቧተሩ፣ ቃላት የሚከሽኑ ነገር ግን ለሸሪዐ ህግጋት ደንታ የሌላቸው በሆኑ መሀይማን ፀሐፍት እንዳንሸወድ መጠንቀቅ ይገባል። ኢስላሙን ለሚያስቀድም ሰው ብቻ ነው መልእክቴ። "ወሎዬን እንዲህ ብለህ ..." እያልክ "የወሎ ጥላቻ" ክስ አንጠልጥለህ እንዳትመጣ ነው ይህን የምለው። የወጣሁበት ማህበረሰብ እንደመሆኑ እቆረቆርለታለሁ እንጂ አሉታዊ እይታ አልሰፍርለትም።
ብቻ ለወሎዬ ወገኖቼ አንድ መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናያቸው አብዛኞቹ የወሎ እሴት ስብከቶች በሸሪዐ ሚዛን ጤነኛ አይደሉም። ይሄ ሃገሪቱ እንዳጠቃላይ ያለችበት በሽታ ነፀብራቅ እንደሆነ ይገባኛል። በሉሲ የሚጎረር አፋር፣ ለኢሬቻ የሚሟገት ሙስሊም ኦሮሞ፣ ... ማየት የተለመደ ሆኗል። ሌላውም ጋር እንዲሁ ለኢስላማዊ እሴቶች እውቅና በሌላቸው የብሄር ትግሎች ውስጥ የሚንቦጫረቀው ብዙ ነው። ኢስላማዊ እሴቶችህን የማያከብር የአማራነት፣ የኦሮሞነት፣ የትግሬነት፣ የጉራጌነት፣ ... ትግል ምንድነው የሚሰራልህ? ምንም!
በነገራችን ላይ አንዳንዶች ሐዲሥ ብለው የሚያወሩት "አገርን መውደድ ከኢማን ነው" የሚለው አባባል ነጭ ውሸት ነው። እንዲህ የሚባል ሐዲሥ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የለም። መልክቱም በሌጣው ከታየ ስህተት ነው። አገርን መውደድ በራሱ ኢማን ተብሎ የሚገለፅ አይደለም። ሰው በተፈጥሮው በትውልድ ሃገሩ ልቡ ይንጠለጠላል። ሌላ ምክንያት እስከሌለ ይህ የሚፈቀድ እንጂ የሚነቀፍም፣ የሚወደስም አይደለም። እንደ ሁኔታው ደግሞ ወደኸይርም ወደ ሸርም ሊቀየር ይችላል። ስለዚህ በልክ መያዝ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ታዋቂ ግን ደካማ ሐዲሦች እና ታሪኮች
(ክፍል 3)
~
የዑሥማንን በግፈኞች መገደል ተከትሎ በኸሊፋው ዐሊይ እና በሙዓዊያ (ረዲየላሁ ዐንሁም) መካከል እስከ ደም መፋሰስ የደረሰ አለመግባባት እንደተከሰተ ይታወቃል። በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሚጠቀሰው የዐምር ብኑል ዓስ እና የአቡ ሙሳ አልአሽዐሪ የሽምግልና ሂደት ነው።
ከዚህ ሽምግልና ጋር በተያያዘ አንድ እውነተኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ዐምር ብኑል ዓስን በሴራ እና ቃል በማፍረስ የሚወነጅል ትርክት አለ። ይሄ ሃሰተኛ ውንጀላ በሰፊው በመሰራጨቱ የተነሳ ብዙ ሙስሊሞች ለዐምር ብኑል ዓስ ጥላቻ አርግዘዋል። ይሄ መስተካከል ያለበት ፀያፍ ጥፋት ነው። ታሪኩ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነው:-
ከሲፊን ጦርነት በኋላ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪን፣ ሙዓዊያ ደግሞ ዐምር ብኑል ዓስን ለሽምግልና ይመርጣሉ። ሁለቱ ሽማግሌዎችም ዐሊይንም ሙዓዊያንም ከሃላፊነታቸው ሊያወርዱ ይስማማሉ። ከዚያም አቡ ሙሳ አልአሽዐሪ ሚንበር ላይ በመውጣት "እኔ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ" ብለው ቀለበታቸውን ያወልቃሉ። ዐምር ብኑል ዓስ በተራቸው ተነሱና "እኔም እንዲሁ አቡ ሙሳ እንዳደረገውና ይህንን ቀለበቴን እንደማወልቀው ዐሊይን ከኸሊፋነቱ አውልቄዋለሁ። ሙዓዊያን ደግሞ ልክ ይህንን ቀለበቴን እንደማፀናው አፀናዋለሁ" አሉ። ይህንን ተከትሎ ጫጫታ በዛ። አቡ ሙሳ ተቆጥተው ወጡ። ወደ ዐሊይ ዘንድ ወደ ኩፋ ሳይሆን ወደ መካ ሄዱ። ዐምር ብኑል ዓስ ደግሞ ወደሻም ሙዓዊያ ዘንድ ሄዱ።
=
ይሄ ታሪክ:-
1ኛ፦ ከማስረጃ የተራቆተ ወፍ ዘራሽ የፈጠራ ወሬ (መውዱዕ) ነው። በዘገባው ውስጥ አቡ ሚኽነፍ የተሰኘ ውሸታም ሰው አለበት። ያለ ተጨባጭ መረጃ ደግሞ ሶሐባን ቀርቶ ተራ ሙስሊምም አይወነጀልም። ለተጨማሪ መረጃ እነዚህን ምንጮች ተመልከቱ፦ [አኑስሕ ወልኢርሻድ ኢላ ተርኪ ቂሶሲን ላ የሲሑ ለሃ ኢስናድ: 61] [አልመሸሁር ሚነ ዶዒፍ ወማ ዩግኒ ዐንሃ፡ 409]
2ኛ፦ ዐሊይ ኸሊፋ ናቸው። ኸሊፋ ደግሞ እንዲህ እንደዋዛ በአንድና በሁለት ሰው ፍላጎት ከስልጣኑ አይነሳም። ኺላፋ እንዲህ ቀልድ ነው እንዴ? ያ ሁሉ ቃል ኪዳን የተገባለት ሰው ነውንዴ በሁለት ሰዎች ውሳኔ የሚወርደው?
3ኛ፦ ደግሞም ሙዓዊያ ረዲየላሁ ዐንሁ በጊዜው ፈፅሞ "ኸሊፋ ነኝ" አላሉም። እሳቸው "እኔም ኸሊፋ ነኝ" ብለው ባልሞገቱበት እንዴት ነው "ዐምር ብኑል ዓስ የሙዓዊያን ኸሊፋነት አፅንቻለሁ" የሚሉት?
ከዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ጋር ያጣላቸው ኸሊፋነቱ ይገባኛል ብለው አይደለም። ይልቁንም ሙዓዊያ የዑሥማን ገዳዮች ተላልፈው ካልተሰጥጧቸው ለ0ሊይ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀራሉ። ዐሊይ ደግሞ ሙዓዊያን ከሻም አስተዳዳሪነታቸው ሊያነሷቸው ይፈልጋሉ። አቡ ሙስሊም አልኸውላኒይ ረሒመሁላህ ሙዓዊያ ዘንድ ገብቼ "አንተ ግን ዐሊይን በኸሊፋነቱ ላይ እየተቀናቀንከው ነው እንዴ? አንተ የሱ አቻ ነህ ወይ?" ብዬ ጠየቅኩት ይላሉ። "በጭራሽ ወላሂ! እኔ ዐሊይ በላጭና በጉዳዩም (በኸሊፋነቱ) ላይ የተገባ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን ዑሥማን በግፍ እንደተገደለ አታውቁም? እኔኮ የአጎቱ ልጅ ነኝ። ስለዚህ የሱን ደም ነው የምጠይቀው። ስለዚህ ዐሊይ ዘንድ ሂዱና የዑሥማንን ገዳዮች አሳልፎ እንዲሰጠኝ ንገሩት። ከዚያ በኋላ ለነገሮች እጅ እሰጥለታለሁ" አለ። ከዚያ ዐሊይ ዘንድ ሄደው ሲያናግሩ ገዳዮቹን አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። [ታሪኹል ኢስላም፡ 540]
ወደ ነጥቡ ስመለስ ዐምር ብኑል ዓስ በሴራ ዐሊይን ለማስወገድና ሙዓዊያን ለማንገስ ሰርተዋል የሚለው ወሬ የፈጠራ ታሪክ ነው። እንደ ፀሐይ ፍንትው ያለ መረጃ ሳንይዝ ሰሐቦችን ልንወነጅል አይገባም። ተጨባጭ ጥፋት ቢገኝ እንኳ ምላሳችንንም እጃችንንም ልንሰበስብ ግድ ይለናል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ሶሐቦቼን የተሳደበ የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁን” ብለዋል። [አሶሒሐህ: 5/446] ደግሞስ ለስንቱ ጠማማ የሚሟገት ትውልድ በየትኛው ሞራሉ ነው በውዱ ነብይ ﷺ ጓደኞች ላይ አፉን የሚከፍተው?!
እርግጥ ነው በጊዜው በነበረው ውዝግብ ላይ ከሙዓዊያ ይልቅ የዐሊይ ስብስብ ይበልጥ ባለሐቅ እንደሆኑ ብዙሃን ዑለማዎች መስክረዋል። ከመሆኑም ጋር እራሳችንን እዚያ ፊትና ውስጥ በማስገባት ያልተጣሩ ጉፋፊ ወሬዎች ላይ እየተመረኮዝን እራሳችንን አደጋ ላይ ከመጣል ልንጠነቀቅ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።
1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
/channel/IbnuMunewor/893
2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
/channel/IbnuMunewor/869
3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
/channel/IbnuMunewor/876
4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
/channel/IbnuMunewor/884
5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2227
6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
/channel/IbnuMunewor/2214
7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
/channel/IbnuMunewor/2261
8, ዓሹራን ለመውሊድ?
/channel/IbnuMunewor/2269
9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
/channel/IbnuMunewor/2294
10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
/channel/IbnuMunewor/882
11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
/channel/IbnuMunewor/2298
12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
/channel/IbnuMunewor/886
13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
/channel/IbnuMunewor/2234
14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
/channel/IbnuMunewor/898
15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2277
16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
/channel/IbnuMunewor/878
17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
/channel/IbnuMunewor/34
18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
/channel/IbnuMunewor/1624
19, መውሊድ ተከሽኖ
/channel/IbnuMunewor/2309
20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
/channel/IbnuMunewor/918
21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
/channel/IbnuMunewor/2302
የብስራት ዜና ለንፅፅር ተማሪዎች
ሱናህ የንፅፅር ትምህርት ቤት እራሱን ከኩፍር መከላከል እና ሌሎችን ወደ ኢስላም መጣራት የሚችል ማህበረሰብ የመገንባት አላማን አስቀምጦ
በአላህ ፍቃድ በንፅፅር ዙሪያ በ online ትምህርት ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሲገልፅ በደስታ ነው።
ስለሆነም ስለ ንፅፅር በኦላይን መማር ለምትፈልጉ ወንድም እህቶች ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ወደቻናላችን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።
/channel/sunnacomparative
Let's learn the Science and Art of Comparative Religion
ሱናህ የንፅፅር ት/ቤት።
مدرسة الإمام أحمد
ውስጥ እየተሠጠ ያለ ተከታታይ ደርስ
ضلال جماعة الأحباش
እዚህ ቻነል ላይ ይለቀቃል - በአላህ ፈቃድ ! ቻናሉን ሸር አርጉት 👇
t.me/Muhammedsirage
እ.ኤ.አ. በ 1258 የሞንጎላውያን ጦር ለማውራት የሚዘገንን እልቂት የበግዳድ ሙስሊሞች ላይ ከፈፀመ፣ የዐባሳውያን ኺላፋንም እስከ ወዲያኛው ካፈራረሰ በኋላ እርጥብ ደረቅ ሳይለይ ያገኘውን እየበላ ወደ ደማስቆ ሲገሰግስ የሆነውን አልኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይተርኩታል።
“ከኢስላማዊ ሸሪዐህ ውጭ ያለው የተታር ጦር ደማስቆን ሲያጠቃ ጊዜ ላኢላሀ ኢለላህ” የሚሉት ሙስሊሞች ወደ ሁሉን ቻዩ አላህ ከመሸሽ ይልቅ ‘አደጋን ያስወግዳሉ፣ ጉዳትን ያነሳሉ’ ብለው ወደሚያምኑባቸው ሰዎች መቃብር ነበር የወጡት። ከነዚህም ሰዎች ገጣሚያቸው እንዲህ ሲል ገጥሟል፡-
‘እናንት ተታርን የምትፈሩ
በአቡ ዑመር ቀብር ተጠለሉ።’
ወይም ደግሞ እንዲህ ይል ነበር፡-
‘በአቡ ዑመር ቀብር ተጠበቁ
ያተርፋችኋል ከጭንቁ።’
ይህኔ እንዲህ አልኳቸው፡ ‘እነዚህ እርዳታን የምትጠይቋቸው ሰዎች ከናንተው ጋር ጦርነቱ ውስጥ ቢገቡ ልክ የኡሑድ ጦርነት ላይ ሙስሊሞች እንደተሸነፉት ይሸነፋሉ።’ … በዚህም ሳቢያ የዲኑ ምሁራን እና አስተዋዮች በዚህ ጦርነት ጊዜ አልተዋጉም። ምክንያቱም አላህና መልእክተኛው ያዘዙበት የሆነው ሸሪዐዊ ጦርነት ስላልነበር፣ ክፋትና ጥፋት የሚከተለው በመሆኑ፣ በጦርነቱም የሚፈለገው ድል ባለመኖሩ ነው። እናም የዱንያም ይሁን የአኺራ ሽልማት አይገኝበትም።… ከዚህ በኋላ ሰዎችን ሃይማኖታቸውን አሸናፊና የላቀ ለሆነው አላህ እንዲያጠሩ፣ ከሱም ብቻ እንጂ እርዳታን እንዳይጠይቁ፣ ከዚህ ውጭ ቅርብ በሆነ መልአክም፣ በተላከ ነብይም እርዳታን እንዳይጠይቁ ማዘዝ ያዝን። ልክ የላቀው አላህ የበድር ጦርነት ጊዜ ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ መለሰላችሁ እንዳለው ማለት ነው። … ከዚያ በኋላ ሰዎች ሁኔታዎቻቸውን ሲያስተካክሉና በጌታቸው እርዳታ እውነት ብለው ሲያምኑ በጠላታቸው ላይ ረዳቸው። ተታሮች የዚህን ጊዜ የተሸነፉትን ያክል ቀድመው አልተሸነፉም። ምክንያቱም ቀድሞ ከነበረው በተለየ የላቀው አላህ ተውሒድ እና ለመልእክተኛው ታዛዥ መሆን በሚገባ ስለተረጋገጠ ነበር። የላቀው አላህ መልእክተኛውንና እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቷም ህይወት እንዲሁም ምስክሮች በሚቆምበት ቀን በርግጥም ይረዳል።” [አረድ ዐለል በክሪ፡ 2/732-738]
ዛሬም ችግሩ ከፍቶ ሙስሊሙ በዐቂዳህ ብክለት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይናጣል። ፍትህን በነፈጉት አንባገነኖች ይረገጣል። በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይታመሳል። ታዲያ ችግሩን የሚመለከቱ የተለያዩ አካላት እንደየአስተሳሰባቸው የተለያዩ የመፍተሔ አቅጣጫዎችን መርጠዋል። ከፊሉ ሙስሊሙን ካለበት ውርደት ለማውጣት ሁነኛው መፍተሄ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን ማፈርጠም ነው በሚል ጧት ማታ ለዚያ ይጥራል፣ ስለለዚያም ይደሰኩራል። ከፊሉ ሌሎች አጀንዳዎችን ከቁብም ሳይቆጥር ማህበራዊ ህይወትን ያቃና ዘንድ ሰርክ ደፋ ቀና ይላል። ሌላው የችግሩን ቀዳሚ ሰበብ ፖለቲካ አድርጎት ኖሮ የስልጣን ማማዎችን ለመቆናጠጥ ሳይቦዝን ይጭራል። ሌላው ደግሞ የችግሩ ምንጭ ከዘመናዊ ትምህርት መራቃችን ነው በሚል ያለ የሌለ ሃይሉን አስኮላ ላይ አድርጓል። እነዚህ “የመፍተሄ አቅጣጫዎች” ከፊሎቹ ቢሳኩም የሙስሊሙን ክብር የማያስመልሱ፣ ካለበት ምስቅልቅል ህይወት የማያወጡት ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከፊል እውነታ ቢይዙም ነገር ግን ባፈፃፀማቸው ግድፈት ምክንያት ይበልጥ የሙስሊሙን ስቃይ ጨምረውታል። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ።
በኢኮኖሚ መፈርጠም ከገባንበት ውጥንቅጥ ለመውጣት ዋስትና አይሆነንም። እንዳውም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም {ድህነትን አይደለም የምፈራላችሁ! ይልቁንም ሀብትን ለማግበስበስ የምታደርጉትን መሽቀዳደም ነው የምፈራላችሁ!} ይላሉ። [አስሶሒሐህ፡ 2216] ዛሬ ዱንያ ፊቷን ስታዞርላቸው ከዲን ፊታቸውን የሚያዞሩት ስንቶች ናቸው? ዘመናዊ ትምህርትም ብቻውን ከችግራችን አይታደገንም። እንዳውም በቅጡ ካልተያዘ፣ በከሃዲዎች ታሪክና ስልጣኔ ተማርከን የአስተሳሰብ ቅኝ ግዛት ስር ከወደቅን መማራችን ይበልጥ ለውድቀታችን ሰበብ ሊሆን ይችላል። ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም።” [አልኢቅቲዳእ፡ 217] ዛሬ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜያቸውን ትምህርት ላይ ፈጅተው ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጡት እምነት ላይ በተበከለ ህሊናቸው ሊፈርዱ የሚዳዳቸው ስንቶች ናቸው? የስልጣን ማማዎችን መቆናጠጥም በራሱ ሸሪዐዊ ፍትሕ በህዝብ ዘንድ እንዲሰፍን አያደርግም። ለምን ቢባል“ከተውሒድ በላይ ፍትህ፣ ከሺርክ በላይ በደል የለምና!!" [መዳሪጁስሳሊኪን፡ 3/336] ይልቅ ቀዳሚው የመፍተሄ አቅጣጫ የዐቂዳን ብክለት ማስወገድ ነው። እምነት ሲስተካከል ሌሎቹ ጉዳዮች መስመር ይይዛሉ። ተውሒድ በሌለበት የሙስሊሙ ልማትም፣ ብቃትም፣ ንቃትም ፍትሕም አይታሰብም።
ከ"ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ" መጽሐፍ የተወሰደ
/channel/IbnuMunewor
من أجمل ما ستسمعه من الشيخ العلّامة صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله ورعاه وأطال في عمره ..
t.me/Menhaj_Salafiya
قال ابن القيم رحمه الله:
أربعة تجلب الرزق :
قيام الليل
وكثرة الاستغفار بالأسحار
وتعاهد الصدقة
وذكر الله أول النهار وآخره.
زاد المعاد 378/4
t.me/Menhaj_Salafiya
ከ5440 በላይ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን የድምጽ ፋይሎች በዚህ ሊንክ ያገኑታል → bit.ly/24Sizol
____________________
جَمِيعُ أَشْرِطَةِ الشَّيْخِ /مُحَمَّدِ بْنُ صَالِحٍ
الْعَثِيمَيْنِ رَحِمَهُ اللَّهُ:
فِي .( ٥٤٤٦ ). شَرِيطًا
bit.ly/24Sizol
©منقول
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
ልብ በሉ! በዚህ ወር ውስጥ ፆምና ሶላት አይኑር ለማለት አይደለም። ወሩን ከሌሎቹ ወራት በተለየ መልኩ መያዝ አይገባም ነው አጠቃላይ ጭብጡ።
………………………………………………
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor
ሸይኽ ፈውዛን እንዲህ ብለዋል:—
"የረጀብ ወር እንደሌሎቹ ወራት ነው። ከሌሎቹ ወራት ተነጥሎ በዒባዳ አይለይም። ምክንያቱም ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላትም ይሁን፣ በፆምም ይሁን፣ በዑምራም ይሁን፣ በሌላም ይሁን እሱን መለየት አልተገኘምና።" [አልሙንተቃ ሚነል ፈታዋ: 1/222]
እራስን መመልከት~~~~~~
እየውልህ ወንድሜ! ህሊና አልባ በድን ማሽን አትሁን። የምትገባው ከራስህ እንጂ ከኡስታዝህ ቀብር አይደለም። ሲራጥን የምትሻገረው በራስህ ስራ መጠን እንጂ ኡስታዝህ እጅህን ይዞ አያሻግርህም። ያለ አስተርጓሚ ራቁትህን ከጌታህ ፊት ለምርመራ ስትቆምም ኡስታዝህ ከጎንህ አይቆምልህም። ይህንን ሁሉ የምልህ ማንንም በጭፍን እንዳትከተል ነው። በአሁኑ ሰዓት በየሰፈሩ ያሉ ሸይኾችና ኡስታዞች አብይ መታወቂያ ጭፍንነትን ሥራዬ ብለው የሚግቱ፣ ተማሪዎቻቸውን በጭፍንነት የሚኮተኩቱ መሆናቸው ነው። የወደዱትን በጭፍን እንድትወድላቸው፣ የጠሉትን በጭፍን እንትጠላላቸው እስከ ደም ጠብታ ይታገሉሃል። ቁርኣን፣ ሐዲሥ፣ የዑለማእ ንግግር ተንኮለኛ በሆነ መልኩ ከአውድ ውጭ እያገናኙ የሃሳብ ሽብር ይነዙብሃል። እዚህ ላይ "ለምሳሌ እነ እንትናን ብንወስድ… " ብዬ ባጣቅስ የእነ እንትና ጭፍራ ጦር ሰብቆ ይነሳል። ከነሱ ውጭ ያለው ደግሞ በአመዛኙ ይደግፋል። እውነት ለመናገር ግን ጣት መቀሰሩ ስለሚቀለን እንጂ ይሄ በሽታ ይብዛም ይነስም በየቤቱ ይገኛል። ችግራችን ግን አይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ጥለን ከሌሎች አይን ያለን ጉድፍ ነው የምንመለከተው። የሌሎችን ጥፋት ለማጋለጥ እንረባረባለን። እሺ የራሳችንንስ ማን ያርመው? ለማነው የምንተወው? ኧረ ልባችን ፈቃጅ ተመልካች አጣ!! ድባቡ የተበከለ ሆኖ መገሳሰፅ አልቻልንም። እኛም ለራሳችን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠንም። ግን እስከመቼ?
እና ወንድሜ ከማንም ጎጠኛ ቡድን ጋር ጭፍን ተሰላፊ አትሁን። ከዑለማእ ንግግር ውስጥ ከስሜቱ ጋር በሚገጥምለት መልኩ እየመረጠ የሚያቀርብ ሰው ስታይ በችኮላ እጅ አትስጥ። የትኛውም ቡድን ጋር የተሰለፈው ሁሉ ይህንን እያደረገ ነውና የሱ ከሌሎች በምን እንደሚለይ ረጋ ብለህ መርምር። የማይነቃነቅ ነባራዊ ሐቅ፣ የአህለ ሱና ዋና መታወቂያ አስመስሎ ያቀረበልህ ጉዳይ አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ያለው አቋም እሱ ካወራህ ተቃራኒ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህና ከስሜት ነፃ ሆነህ በሚገባ ፈትሽ። ደግሞ ቆም ብለህ ታዘባቸው። ብዙዎቹ ቡድናዊነት የሰበሰባቸው አካላት
— "እነ እከሌ ጠርዘኞች ናቸው፣ ድንበር አላፊዎች ናቸው" እያለ ከፍ አድርጎ ያስተጋባል። የሚያስከነዱ ጠርዘኞችን ግን አቅፎ ያሽሞነሙናል። ምክንያቱም እነዚህኞቹ እሱ ሲስል የሚስሉ፣ ሲያነጥስ የሚያነጥሱ የገደል ማሚቶዎች ናቸውና።
— "እነ እከሌ ጃሂሎች ናቸው" ይልሃል። በምንም መመዘኛ ከነሱ የማይሻሉ ሰዎችን ግን በትልልቅ መድረክ ላይ ያስተዋውቃል። ምክንያቱ አቋማቸው ከአቋሙ ስለገጠመለት ብቻ ነው።
— "እነ እከሌ አቋም የሌላቸው ወላዋዮች ናቸው" ያለህ ስብስብ በየክስተቱ ባደባባይ የሚዋልሉ ሰዎችን ከጎናቸው አሰልፈው ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም መመዘኛው ርካሹ ቡድናዊ ሚዛን እንጂ ኢኽላስ አይደለምና።
ወንድሜ ሆይ! አላህን አስበህ ስለምትሰራው ነገር የማንንም ጭብጨባ አትጠብቅ። የማንም ተቃውሞም አይጠፍህ። ይልቅ ውስጥህን አዳምጥ፣ ኢኽላስህን ፈትሽ። ያለ ኢኽላስ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ነው። ልፋትህም ከንቱ ድካም። በደዕዋህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሰፊው ህዝብ ይሁን። አትዘንጋ! ዛሬም አብዛኛው ወገናችን ከተውሒድ ግንዛቤ የራቀ ነው። ሺርክ ላይ የሚማቅቀው ብዙ ነው። ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ላይ እስከ አፍንጫው የተነከረው ቀላል አይደለም። ቀዳሚው ጥረትህ የዚህን ወገንህን ሸክም ለመቀነስ ይሁን። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ ገሸሽ በማድረግ ውሃ ቀጠነ፣ ከሰል ጠቆረ ብሎ ለሚነታረክ ጀርባህን ስጠው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አረፋ ነው።
በኢኽላስ እስከሰራህ ድረስ የማንም ጫጫታ ቅስምህን አይስበረው። ሰዎች እንቅፋት ሲያበዙ አንተ ፅናትህን ጨምር። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትበል።
የሌሎችን ጩኸት ሳታጣራ የምታስተጋባ በቀቀን አትሁን። በጭፍን አትደግፍ። በጭፍን አትንቀፍ። እወቅ! እውር ጥላቻና እውር ውዴታ ነገ ከአላህ ፊት ያሳፍርሃል። ማንንም በእውር ድንብር አትከተል። ጭፍን ወገንተኝነት በቃላት ቢያሸበርቅም፣ በሱና፞ ስም ቢቀርብም የተወገዘ ነው። የአሳማ ስጋ በወርቅ ሰሀን ስለቀረበ አሳማነቱ አይቀየርም። አሳማ አሳማ ነው። የመዝሀብ ሰዎች ዘንድ የምናውቀው ጭፍን ወገንተኝነት ተቀባብቶ ተከሽኖ በሱና፞ ዑለማዎች ስም ሲቀርብ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ አንዳንዶች በየሰፈሩ በየመንደሩ እየተቧደኑ ‘ወላእ’ እና ‘በራእ’ የሚቋጥሩባቸው አካላት መመደባቸው ነው።
ደግሞም በልክ እንሁን። በሌሎች ሃገራት ወይም አካባቢዎች ያየነውን ወይም የሰማነውን ኺላፍ ሁሉ ሰበብ እየፈለጉ እየጎተቱ ማምጣት ግልብነት ነው። ወላጆችህ ወገኖችህ በሺርክ እየተጨማለቁ አንተ በሸይኽ እንትናና በሸይኽ እከሌ መካከል ስለተፈጠረው ኺላፍ ጧት ማታ እያቦካህ በአካባቢህ ያሉ ዱዓቶችን ለመፈረጅ አድፍጠህ ብትጠባበቅ የፊትና ጥማትህን እንጂ ንቃትህን አያሳይም። በአካባቢህ ይሄ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ ሳይኖርህ እንዳቅማቸው እየደከሙ ያሉ አካላትን ትንሽዬ ጥረት አይኗን ለማጥፋት ጦር ብትሰብቅ ጥሬነትህን ብቻ ነው የሚያሳየው። ወንድሜ ከቻልክ አግዝ። ክፍተት ካየህ አርም። አቅሙ ከሌለህ ባላቸው አስመክር። በምትችለው ከጎናቸው ቁም። ለሰፈርህ ለአካባቢህ የደዕዋ እንቅስቃሴ አጋዥ እንጂ አፍራሽ አትሁን። ለደዕዋ እንቅፋት በመሆን ሌሎች እንዳይለወጡ መሰናክል አትፍጠር። ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገሮችን መጣል ፀያፍ ጥፋት ነው። ወደ ኣኺራ በሚወስደው የደዕዋ መንገድ ላይ እንቅፋት መጣል ግን እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። እንዲህ አይነቱን የወንጀል ሸክም የምትቋቋምበት ጫንቃው የለህምና ዛሬውኑ ሚናህን ለይ። ዛሬውኑ ለደዕዋ ያለህን አስተዋፅኦ ገምግም።
………………………………………………
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
/channel/IbnuMunewor