في بداية عام 2023 !
لا أماني ولا تهاني .. فأنا مسلم ولست نصراني .. . وإذا تمنيت شيئا .. أطلبه من الله .. لا من 2023 !!
تعلموا التوحيد رحمكم الله ..
t.me/Kunizewjeten2
መልካሙን መልበስህ ፣ ያማረን ነገር መጠቀምህ ፣ የተዋበን ቤት መገንባትሀ የሚነወር አይደለም ።
እነዚህ ነገሮች ላይ ለመድረስ የተከለከሉ ነገሮችን መዳፈርና የዱንያ ነገርህን ለማድመቅ አኺራህን አደጋ ላይ መጣል ግን ነውር ነውና እናስብበት !!
አላህ ይምራን !
t.me/Muhammedsirage
🌹🌹الزواجُ عقدٌ بين قلبينِ، ووصلٌ بين نفسينِ، ومزجٌ بين رُوحينِ ، وفي الأخيرِ تقريبٌ بين جِسمينِ»
آثار البشير الإبراهيمي (3/297)
اللهم يسّر الزواج لكل عازب
t.me/Kunizewjeten2
#ሰለፊያ_ማለት ታላቁ የየመን ዓሊም ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲኢ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"ሰለፊያ ማለት አንድ ሰው ሲፈልግ የሚለብሰው ሳይፈልግ ደግሞ የሚያወልቀው ካባ አይደለም ፣ እንዲያውም ሰለፊያ ማለት፦ የአላህን መፅሐፍ እና የመልክተኛውን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱናህ በሰለፉ ሳሊሂን አረዳድ አጥብቆ መያዝ ማለት ነው።"
【ቱሕፈቱ አልሙጂብ አላ አስኢለቲ አለሓዲር ወልገሪብ】
t.me/Kunizewjeten2
ለሚያስተውሉ
~
ከዚህ በፊት ከየመን መርከዞች በጅምላ የሚያስጠነቅቅ የሸይኽ ዐብዱልሐሚድ አለተሚ ድምፅ መሰራጨቱ ይታወቃል። እንደ ፊዩሽ፣ መዕበር፣ መፍረቅ ሑበይሽ፣ ሑደይዳ፣ ... ያሉ የየመን የሱና መርከዞች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከመላው ዓለም ለሚሰባሰቡ ተማሪዎች የአይን ማረፊያዎች ናቸው። ስለሆነም እነዚህን የሱና ቀንዲሎች በመጥፎ መፈረጅ ሐቅ ካለመሆኑም ባሻገር ከሀገራችን ለዒልም ፍለጋ የሚጓዙ ወንድሞችን ማሰናከል ነው የሚሆነው። ይሄ ደግሞ ጉዳቱ ወደኛው የሚመለስ ነው።
ሰሞኑን ኢትዮጵያ መጥተው እያስተማሩ ካሉት ሸይኾች ውስጥ አንዱ የሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳ ሐፊዞሁላህ ለጊዜው መካ ቢኖሩም የሑደይዳው የሱና መርከዝ ኃላፊ ናቸው። ሌሎቹንም የየመን የሱና መርከዞች ያውቋቸዋል። ሰሞኑን ስለ ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ጅምላ ውንጀላ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
وجلست معه إلي الساعة الثانية بعد منتصف الليل وبينت له ما عليه دور الحديث السلفية في الديار اليمنية، وكان يستفسر عن بعض الإشكالات وأنا أجيب، ولله الحمد، حتى أظهر لي وفقه الله، أنه لم يكن عنده علم بهذه الأمور، والآن تبين له أمر دور الحديث السلفية في الديار اليمنية بوضوح، ولم يبق عنده أي إشكال
"ከሱ (ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ) ጋር እኩለ ሌሊት በኋላ አልፎ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ አብሬው በመቀመጥ በሃገረ የመን ያሉ የሐዲሥ ተቋማት ያሉበትን ግልፅ አድርጌለታለሁ። አንዳንድ ግርታዎች ግልፅ እንዲሆኑለት እየጠየቀም ምስጋና ለአላህ ይሁንና መልሼለታለሁ። አላህ መልካምን ያድለውና በነዚህ ጉዳዮች ላይ እውቀቱ እንዳልነበረው እስከሚያንፀባርቅልኝ ድረስ። አሁን ግን በሃገረ የመን ያሉ የሐዲሥ ተቋማት ጉዳዩ ፍንትው ብሎ ግልፅ ሆኖለታል። እናም ምንም ግርታ አልቀረውም።"
ምንጭ:- [በ4/5/1444 ሸይኹ ከሰጡት ምላሽ የተቀነጨበ]
ሸይኽ ባሙሳ የገለፁት ትልቅ ነገር ነው። ወጣቶችን በነዚህ ተቋማት ዒልም እንዳይፈልጉ እንቅፋት ከመሆን መምመለስ ዋጋው ቀላል አይደለም፣ የእውነት መመለስ ከሆነ። ነገር ግን ለሸይኽ ባሙሳ መምመለሳቸውን ያሳዩት ከወራት በፊት ከሆነ እስከ ዛሬ ድረስ ግልፅ እርምት መስጠት ይገባ ነበር። ምክንያቱም
1⃣ ይሄ ድምፅ በሰፊው ተሰራጭቷል።
2⃣ በነዚህ የየመን መርከዞች "የሰለፊያ ደዕዋ የለም" የሚሉ ሰዎች በተጨባጭ አሉ። አንዳንዶቹ በሚገርም ሁኔታ እዚያው የመን እየተማሩ ይህንን አቋማቸውን በማራመድ ለሌሎች የኢትዮጵያ ተማሪዎች ፈተና እስከመሆን ደርሰዋል። ቢያንስ ለነዚህ ሲባል እንኳ ከሸይኽ ባሙሳ ፊት ያመኑትን ጉዳይ ባደባባባይ በመናገርና ስህተታቸውን በግልፅ የሚያርም ድምፅ በመልቀቅ ውለታ ሊውሉ ይገባ ነበር። ግልፅ እርምት ባለመሰጠቱም ነው ይሄ የሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ድምፅ ሰሞኑን ለሸይኽ ረሻድ አልሑበይሺ ሲቀርብላቸው ጠንከር አድርገው ምላሽ የሰጡት። የሸይኽ ረሻድን ምላሽ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ:-
/channel/IbnuMunewor/3955
ምናልባት ከአንዳንዶቹ ሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳንና ሸይኽ ረሻድን መጎንተል እንዳይከተል እሰጋለሁ። ይህን የሚያደርግ ካለ ከራሱ አልፎ ስብስባቸውን ነው የሚጎዳው። ከውስጣቸው ዛሬም ከመሻይኾቹ ጋር የሚገናኝ አለና።
ከዚህም በተጨማሪ ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድርንና ሸይኽ ሱለይማን አሩሐይሊን የሚጎነትል ንግግር ሳይቀር ወጥቷል። የአንዳንድ ዓሊሞችን ንግግር በመንተራስ በክር አቡ ዘይድን እስከ መወረፍም ተደርሷል። ሸይኽ ረይስንና ሸይኽ ሐመደል ዐቲቅን "ሰለፊይነታቸው ደካማ ነው ብለዋል ሸይኽ ረቢዕ" የሚል ድምፅም አለ። የሚገርመው አንዳንዶቹ ይህንን ከሚሉ አካላት ጋር ተጣብቀው ረይስ ዘንድ ሌላ ሆነው እየቀረቡ ነው።
የሸይኽ ሙሐመድ አልኢማምን "አልኢባና" ኪታብ በማስተዋወቃችን የተነሳ በቢድዐ እስከመፈረጅ ድረስ ሲጓዙ እንደነበርም አይተናል። ይሄው ሰሞኑን ሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳ ሐፊዘሁላህ "የሸይኽ ሙሐመድ አልኢማምን አልኢባና ኪታብ - እኛ ዘንድ ያሉ አንዳንድ ሰባኪዎች እንደሚሉት - በተምይዕ የተሞላ ነው ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር።
هل قائل هذا القول أعلم من الشيخ عبد المحسن العباد وصالح السحيمي المثنين على الكتاب؟ إن قال نعم فأنا أسكت
"የዚህ ንግግር ባለቤት ኪታቡን ካደነቁት ከሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ እና ከሷሊሕ አሱሐይሚ በላይ አዋቂ ነውን? 'አዎ' ካለ እኔ ዝም እላለሁ" ብለው መልሰዋል።
የዓሊሞቹን አቋም በድፍረት ስህተት ነው ልትሉ ትችላላችሁ። ይሄ አይገርመንም። አልፋችሁ ኪታቡን አስተዋወቃችሁ ብላችሁ በቢድዐ ስትፈርጁ ግን ብሽሽቅ ከሚመስል፣ በአንድ ጉዳይ ሰው እየመረጣችሁ ከምትወርፉበት አካሄድ ወጥታችሁ የት እንዳላችሁ ቆም ብላችሁ ተመልከቱ። አላህን ፍሩና ለሰው ፈተና ከመሆን ተመለሱ።
ደግሞም {የሸይኽ ባሙሳ ንግግር ወደ ተምይዕ ለሚጣራ የጥመት ኪታብ የሚከላከል አሳሳች ንግግር ነው} የምትሉ ከሆነ እዚሁ እያሉ አናግሯቸው። ብዥታ ካለባችሁ ይገፈፍላችኋል። "ሸይኽ ባሙሳ አልገባቸውም" የምትሉ ከሆነም ቀርባችሁ አለን የምትሉትን "እውነት" አቅርቡና የሚሆነውን እንይ።
ሌላ ባለፈው በሕሩ ተካ "ከነሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳ ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው አቋም የቀየሩት" እያለ ስሜን ጠቅሶ ፅፎ ነበር። በጊዜው እኔ ከነሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳ ጋር በአካል ተገናኝቼ እንደማላውቅ በመጥቀስ ይሄ የበሕሩ ንግግር ውሸት እንደሆነ ገልጫለሁ። ይሄው ሰሞኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ በርከት ያለ ሰው በነበረበት "ሙነወር የታለ?" ብለው ከጠየቁ በኋላ ሲነገራቸው "ባለፈው ስንመጣ አላገኘንህም። በደረሰብህ የመኪና አደጋ ምክንያት ታመህ እንደነበር ሰምተናል" ብለው ተናግረዋል። አስባችሁም ይሁን ገምታችሁ ከመዋሸት እንድትቆጠቡ ነው ይህንን የማነሳው። ለማስተባበል የሚዳዳው ካለ ሌላ የውሸት በር ከመክፈቱ በፊት ከፈለገ ከሸይኹ ከራሳቸው ማስረገጥ ይችላል።
የመጨረሻ የማነሳው ነጥብ እነዚህ ወንድሞች {ለነ ሸይኽ ባሙሳ በኢማሙ አሕመድ መስጂድ እንዲያስተምሩ ማስፈቀዳቸው ያላቸውን ተናዙል ያሳያል} ዓይነት ክስ ሲያሰራጩ አይቻለሁ። ለዚህ ሁለት ምላሾችን እሰጣለሁ፦
1⃣ ሸይኾቹ ባለፈው ሲመጡም አሁንም በብዙ መስጂዶች ውስጥ ነው ያስተማሩት። ለምን ነጥላችሁ ይሄኛውን መስጂድ ጠቀሳችሁ? ከመጅሊስ ግቢ መስጂድ፣ ከአወሊያ፣ ከሙስዐብ፣ ... መስጂዶች ሁሉ ለምን ይሄኛው ተለየባችሁ? ምላሹን ለራሳችሁ።
2⃣ በሕሩ ተካ የሚያስተምረውኮ ዳውድ ያሲን ከሚያስተምርበት መስጂድ ነው። በዚህ ዓይነት መስጂድ ማስተማር የማይቻል ከሆነ ለምን በሕሩ ጥሎ አይወጣም? ከወራት በፊት ወራቤ በአንድ መስጂድ ውስጥ ደዕዋ ስናደርግም ተመሳሳይ ክስ ከሳችኋል። የሚገርመው ግን ቀደም ብሎ በዚያው መስጂድ ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያስተማረ መሆኑ ነው። እኛ ስንፈፅመው የመንሃጅ ችግር እናንተ ስታደርጉት ግን ፅድቅ የሚሆንበት ሂሳቡ ምን ይሆን? አላህን መፍራቱ ቢቀር ቢያንስ ሰው ይታዘበናል አትሉም?
በተረፈ የመን ላይ በየጊዜው በግራም በቀኝም ካሉ አካላት ውስጥ ከቀደመ አቋማቸው እየተመለሱ ያሉ ወገኖች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ይሄ እኛም ተስፋ እንድንሰንቅ ያደርገናል። ከሁሉም አቅጣጫ ካሉ ወገኖች ጋር አላህ በሱና ላይ እንዲሰበስበን እንመኛለን።
الشيخ رشاد الحبيشي -حفظه الله- يدافع عن مراكز أهل السنة في اليمن ويذب عن عرض مشايخها الكرام وينصح بالذهاب إليها لطلب العلم ويؤدب بعض الغلاة المحذرين منها من داخل إثيوبيا
Читать полностью…قال الإمام شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله:
من تعصّب لأهل بلدته ، أو مذهبه ، أو طريقته ، أو قرابته ، أو لأصدقائه دون غيرهم ؛ كانت فيه شعبة من #الجاهلية.
الفتاوى ٤٢٢/٢٨.
🎈السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ልቦች ኮምቦልቻን ያስባሉ።ፕሮግራሞች ይሻሻላሉ።ጋራ ሸንተረሩን አልፈውን ወንዙን ሸለቆውን ተሻግረው እግሮች ወደ ኮምቦልቻ ያመራሉ።አዎ" ወደ ኮምቦልቻ። ያመራሉ።
~~~~ምን አለ ያላችሁ እንደሁ፦
እነሆ በውቢቷ ከተማ በኮምቦልቻ ምድር በአይነታው ለይት ያለ የሆነ የኮርስ፣የሙሓደራ እና የተላይ የነሲሃ ፕሮግራሞች መዘጋጀቱን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።ከሀገር ውጪም ይሁን በሀገር ውስጥ ባሉ ዑለመኦች፣መሻይኾች እና ኡስታዞች ፣የተለያዩ ዱዓቶች የሚገኙነት ፕሮግራም ነው።ስለሆነም ወሰን ቀድመህ ፕሮግራምህን አመቻች።አለቀ።ኮርሱ ለተከታታይ 3ት ቀናት የሚሰጥ ስለሆነ ከርቅት የምትመጡ አካላቶች ከተቻለ አንድ ቀን ቀደም ብላችሁ ብትገኙ በጣም መልካም ይሆናል።ማደሪያ እንዳታስቡ። ልብስ ግን ቀለል ያሉ ለየግላችሁ የሌት ልብሶችን ብትይዙ ደስ ይለናል።ለምግብ እናዳታስቡ ቤት ያፈራውን እንበላለን።
ዋና ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ቀን በወርሃ ህዳር በእለት እሑድ ቀን (18/3/2015) ነው።በመሆኑም እናንተ ቀድማችሁ ቅዳሜ ከስኣት ለመግባት ሞክሩ ብለናል።
*በእለቱ ከሚገኙት ዑለማኦች መካከል መቀመጫቸውን በሀገረ ሳዑዲ ያደረጉ ዑለሞች…
1, የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላሂ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى
2,የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ رشاد الورد الحبيشي حفظه الله
3, የተከበሩት ሸይኽ ሙሳ አሕመድ አል ቀጧኒ
فضيلة الشيخ موسى بن أحمد القطاني العفري
*ከሀገረ ኢትዮጺያ ከተለያየ ቦታ የተውጣጡ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦
=>ከደሴ፦
~ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን
~ ሸይኽ ሙሐመድ ጘዛል
~ ሸይኽ ሃሰን ቃዲ
~ ሸይኽ ሙሀመድ አሚን
~ ኡስታዝ በድሩ
~ ሸይኽ አረቡ
~ ሸይኽ ኢሳ
~ ሸህ ሁሴን
=> ከኩታበር፦
~ ሸህ ሙጅተባ
~ ሸህ አደም ኩታበር
=>ከኮምቦልቻ
~ ሸይኽ አሕመድ አወቅ ከኮምቦልቻ
=>ከኬሚሴ፦
~ሸይኽ አቢ ዐማር አወል ቢን አሕመድ አል_ኬሚሴ
~ኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር ቢን አሕመድ አል_ኬሚሴ
=> ከአፋር፦
~ ኡስታዝ አቡ ሒዛም
*ሌሎችም ከአዲስ አበባም የሚተሙ እንቁ ኡስታዞች አሉ ለግዜዉ ስማቸውን ይቆያችሁ
ማንቂያ 1፦ወደ ፕሮግራሙ ስትመጡ ማስታወሻ ደብተር እና እስኪርብቶ ብትይዙ መልካም ነው።በተለይም ተማሪዎች።
ማንቂያ 2፦ማንኛቸውንም ሹብሃ መሳይ ችግር ፈጣሪ ጥያቄዎችን መጠየቅ ስልምትችሉ ከወድሁ ጥያቄያችሁን ማዘጋጅት እንደምትችሉ ልንጠቁማችሁ እንወዳለን።
ማንቂያ 3፦ ከሩቅ የምትመጡ ወንድሞች ቅዳሜ እንድትገቡ እናሳስባለን በቅርብ ያላቹህ እሁድ በጧት እንድትገኙ እናሳዉቃለን።
ማሳሰቢያ፦በአሏህ ፍቃድ መሻይኾቹ ቅዳሜ ከሰዓት ኮቻ ይገባሉ ቅዳሜ ከመግሪብ እስከ ኢሻ የሙሐደራ ፕሮግራም ይኖረናል። የእሁዱን ፕሮግራም በዝርዝር እናሳውቃለን።
በመቅረታችሁ ብቻ ሳይሆን በማርፈዳችሁም ትቆጫላችሁ።
http://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
http://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
የነገው ቀጠሮ
በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት
ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ
ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ
ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ
/channel/Muhammedsirage
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ታላቅ ዳዕዋና ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ
እነሆ በአሏህ ፍቃድ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ አንሷር መስጅድ የፊታች እሁድ ቀን 18/03/ 2015 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በታላላቅ ከውጭ በመጡ አሊሞችና የሃገራችን አሊሞች መሻኢኾች እና ኡስታዞች ታላቅ የዳዕዋ ፣ የፈትዋ እና የኮርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹሃል... በዕለቱ ብዙ ታዳሚ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
በእለቱ ከሚገኙ ከውጭ ሀገር ታላላቅ ኡለማዎች መሃል
1) የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላሂ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى
2) የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ رشاد الورد الحبيشي حفظه الله
3) የተከበሩት ሸይኽ ሙሳ አሕመድ አል ቀጧኒ
فضيلة الشيخ موسى احمد القطاني
እና ሌሎችም ውድ የሰለፊያ ኡስታዞች እና ወንድሞች ከ አፋር ከአዲስ አበባ ከደሴ ከኸሚሲይ እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች በአለሠህ ፍቃድ ይዘምታሉ።
በዕለቱ :-
✔️ የኮርስ ፕሮግራም ይካሄዳል
✔️ የደዕዋ ፕሮግራም ይካሄዳል
✔️ በመሻኢኮቻችን ነሲሃ ይደረጋል
✔️ የፈትዋ ፕሮግራም ይኖረናል
ማሳሰቢያ :- ማንኛውም ስለማንኛውም ነገር ሹብሃ ያለበትም አካል ጥሪ ሳይደረግለትም መምጣት ይችላል በራችን ክፍት ነው ።
👌 በቂ ምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል ... ከቅዳሜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ይህንን ውድ ፕሮግራም ለመታደም ወደ ኮምቦልቻ አንሷር መስጅድ እብድታመሩ ስንል ጋብዘናቹሃል።
ማሳሰቢያ
የሌሊት ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ የተመረጠ ነዉ።
አድራሻ :- ኢትዮጵያ ኮምቦልቻ ከተማ ሀሰና ሀገር ክፍል ከተማ ቀበሌ ሁዳዴ በርበሬ ወንዝ አድሱ ድልድይ ተሻግሮ ደዌ ሰፈር በአንሷር መስጅድ
t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
አንተኛው ባለ ፂም - አላህን ፍራ!!
በሱና ተጊጠህ ላይህ እጅግ አምሮ
ታማኝ ነው በማለት ዟሂርህ መስክሮ
ስራህ ተበላሽቶ ላይ ታች ስታምታታ
በውሸት መሃላ ሙግት ስትረታ
አንተንም ጠሉና ደጉን ጠረጠሩ
ባለፂሙን ሁሉ በክፉ አነወሩ !
የሱናውን መንገድ ባንተ ክፋት ራቁ
በሱናው ሰው ሁሉ ጥላቻን ሰነቁ
ኧረ አላህን ፍራ !!
ላይን አሳምሮ ስራህን ማከርፋት
ከባድ ነቀርሳ ነው ለዳዕዋም እንቅፋት !!
ደጎችን አታስንቅ - አታዘልፋቸው
ባልዋሉበት ሜዳ አንተ አታውላቸው
ኧረ አላህ ፍራ !
/channel/Muhammedsirage
ኳስ የዘመናችን ጣዖት
~
ዛሬ ላይ ኳስ ከተራ መዝናኛነት አልፏል።
* በአላህ መንገድ ላይ የማይወጣው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭ ይወጣበታል። ሚሊዮኖች እየተራቡ፣ በክህ -ደት ሰባኪዎች እየተጠለፉ ከግለሰቦች እስከ መንግስታት ለዚህ ቆሻሻ ነገር ግን የማይገመት ወጭ ያወጣሉ።
* ዘረኝነት ይንፀባረቅበታል።
* በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስካሪ መጠጥ ይተዋወቅበታል።
* የጭፈራና የዘፈን ድግስ ይቀርብበታል።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ግዴታ የሆነባቸውን ሶላት ያሳልፋሉ።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ጎረቤት ይበጠብጣሉ፣ የወላጅ ሐቅ ይጥሳሉ፣ እርስ በርስ ይጋጫሉ፣ ለሱ ሲሉ ይወዳሉ፣ ይጠላሉ።
* የመገናኛ አውታሮች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ጋዜጦችና መፅሔቶች፣ ግለሰቦች፣ በቤትም በውጭም፣ በየጎዳናው፣ በየ ካፌው፣ ቆመው ተቀምጠው፣ ... ለዲንም ይሁን ለዱንያ በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ከሚጮሁት እጅግ በላቀ ስለዚህ ርካሽ ነገር ሆኗል ውትወታቸው። እንዲያውም ቀላል የማይባሉ ጥራዝ ነጠቆች ስለ ኳስ መተንተንን የንቃት ማሳያ አድርገውታል። ስለ ኳስ አለማወቅን ፋራነት አድርገውታል። ከዚህ በላይ ምን ዝቅጠት አለ?!
* በዚህ ቆሻሻ ነገር የተነሳ እጅግ በርካታ ወጣቶቻችን ከሃዲዎችን፣ የሉጥ ህዝቦችን ተግባር የሚፈፅሙ፣ ለሱ ጥብቅና የሚቆሙ ርካሽ ፍጡሮችን እንዲያደንቁ ሆነዋል። ደካማ ሰበብ እየደረደሩ ራሳቸውን አደንዝዘዋል።
* ከዚህ ሁሉ በኋላ አንዳንዶች ጂሃድ ሊያስመስሉት ሲዳዳቸው ይታያሉ። ኳስ በዚህ በመከራ በተከበበ ህዝብ ላይ የተከፈተ ወደን የተቀበልነው ጦርነት ነው።
ይሄ ሁሉ እውነታ በገሃድ ፈጦ የሚታይ ከመሆኑ ጋር ቢያንስ ሸሩን በመቀነስ ላይ እንኳ ዱዓቶች እየሰሩ አይደለም። የዱዓት ትልቁ በሽታ ሰፊው ህዝብ የወደቀባቸውን ጉዳዮች ለመጋፈጥ ወኔ ማጣት ነው። መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ (ዋቒዕ) መሸነፍ። አትጠራጠር ወንድሜ! ኳስ ከዘመናችን ብዙ ዓይነት ጣዖቶች ውስጥ አንዱ ጣዖት ሆኗል። አደራ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ለዚህ የቦዘኔዎች ስራ ብለን ሶላት ከወቅቱ የምናሳልፍ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። ለዚህ የጂላጂሎች ስራ ብሎ መስጂዶቻችንን ማራቆት የሚያሳፍር ጉዳይ ነው። ስለዚህ ነፍሲያችንን እንርገጥ። ተቅዋን እናስቀድም።
ማሳሰቢያ፦
- ያወራሁት ስለ ኳስ እንጂ ስለ ቀጠር አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ይልቅ የኢኽዋን ቁንጮዎችን ከሳዑዲ መሪዎች ጋር አነፃፅራለሁ። ባለስልጣናትን ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ማነፃፀሩ ልክ ባይሆንም የኢኽዋን የሃይማኖት ቁንጮዎች ከአንድ ብልሹ ባለስልጣን የማይሻሉ የጥመት መሪዎች ናቸው። በሃይማኖት ስም እኮ ነው ጥመታቸውን እየረጩ ያሉት!! እነዚህ የሳዑዲ ዑለማዎችን የሚያብጠለጥሉ ሳይሞቅ ፈላዎች እጅግ ሰቅጣጭ የሆኑ የቀርዷዊን ጥፋቶች በስሱ እንኳ ሲነቅፉ አይታችኋል? ፈፅሞ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
የወንጀላችን ግዝፈትና ብዛት ነጅሶን በተፈቀዱ ነገሮች እንኳን መደሰት በከሰመበት ዘመን የተከለከሉ ነገሮችን በመጠቀም ደስታን ለመሸመት ማሰብ ድንቁርና ነው ።
አላህ ይመልሰን
አሏህን በመፍራት እውነተኛ ደስታና እረፍት ይገኛል !
/channel/Muhammedsirage
#ምርጥ_ስጦታ_ለአጭበርባሪወች
የጂን ሸይጧን ሲሸንፍህ ይወሰውሳል የሰው
ሸይጧን ግን ሲሸነፍ ይዋሻል ኢብኑ ተይሚያህ
ረሂመሁላህ (አል ፈታዋ 22/608)
t.me/Kunizewjeten2
ወላሂ አሳዛኝ ግዜ ላይ ነው ያለነው በጣም አሳዛኝ ግዜ ላይ ነው ያለነው ሰው እንደ ፈለገ ነው የሚናገረው እንደ ፈለገ ነው የሚያየው እንደፈለገ ነው የሚፅፈው አላህን መፍራት የሚባለው ነገር በጣም እርቆናል ደግሞ እኮ በሽታህን ማወቅ አንድ ነገር ነው በሽታህን ማወቅ አንድ እርምጃ ነው አንዳንዱ የለየለት ልብ መድረቅ ውስጥ ሆኖ፣የሚያውቀውን የማይተገብር ሆኖነገር ግን እራሱን የተሻለ ሰው አድርጎ ያስባል አላህ ይጠብቀን ሰዎች ላይ ትንንሽ ነገሮች ይታዪታል እራሱ ለይ ያለ የገዘፈ ጥፋት ግን አይታየውም ትልልቅ ወንጀሎች ለይ ተዘፍዝፏል ይህ አይታየውም የሰዎች ትንንሽ ወንጀሎች ግን ጎልቶ ይታየዋል አላህ ይጠብቀን ።መቼ ነው ለመሆኑ ወንጀላችንን ማሰብ የምንጀምረው፣መቼ ነው ለመሆኑ ጥፋታችንን መቁጠር የምንጀምረው፣መቼ ነው ስለ እራሳችን ማሰብ ማውራት የምንጀምረው፣መቼ ነው ከወንጀል መውጣትን አላማ አድርገን የምንቀሳቀሰው መንቀሳቀስ የምንጀምረው: ነገሩ ቀልድ አይደለም የእሳት እና የጀነት ጉዳይ ነው እኮ ዛሬ ትንንሽ የሚመስሉ ነገሮች ይደፈራሉ ነገ እነዚህ ትንንሽ ነገሮች ትልልቅ ነገሮችን ያስከትላሉ እነዚህ ትልልቅ ነገሮች ደግሞ ክህደትን እና ኒፋቅን ሊያመጡ ይችላሉ።እስከ መቼ ነው የሚተኛው ለመሆኑ: እስከ መቼ ሀራም ነገር ላይ ተዘፍዝፈን፣እስከመቼ ሀራም ነገር ተመልክተህ፣እስከ መቼ እንደፈለክ ተናግረህ፣እስከ መቼ የፈለከውን ነገር ሰርተህ ፣እስከ መቼ......... ።ሰው እኮ ያጠፋል ግን እንዴት ጥፋትን መንገድ አድርጎ ይይዛል: ዘወትር ወደ ሀራም ነገር መመልከት መንገድ ተደርጎ ይያዛል፣እንዴት የማትላቀቀው በሽታ ተደርጎ ይያዛል: አንደፈለክ ስለ ሰው መናገር ፣ሀሜት፣የመሳሰለው ነገር እንዴት.... እነዚህ ነገራቶች አይደል ልብን እያደረቁ ያሉት..........
{كَلَّا ۖ بَلْ ۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا يَكْسِبُونَ}
{ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡}
የልቦቻችን ድርቀት መሰረቱኮ እንደፈለክ መናገር እንደፈለክ መስራት እና መዘለል ነው።ይህ ነገር ይብቃ ብሎ እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ነው።ለምሳሌ የምትጠቀምበት ሙባየል ያለ አግባብ ስራ ላይ እየዋለ ከሆነ መተው ነው የሚሻለው በተለይ በተለይ ይህ ቲክ ቶክ የሚባል ነገር ጥንቃቄው እራሱኮ ከየት ሊመጣ እንደሚችል አይታወቅም እንዴት አድርገህ ነው እንዲህ አይነቱን ፈተና የምትጠነቀቀው? በምንም መልኩ ልትጠነቀቀው አትችልም! ምናልባት እዚህ ቦታ ለይ ለመጠቀም ሳይሆን ለመጥቀም የሚገቡ ሰዎች እየታገሉ አላህ ይወፍቃቸው መጠቀም ፈልገህ ከሆነ ግን ይህ ቦታ አይጠቅምህም በእርግጠኝነት እናገረዋለው ።የአሁን ህፃናት ቲክ ቶክ ያውቃሉ በጣም ይገርማል ልጆች! ነጃሳ ነገር የተሰበሰበበት ሜዳ ሆኖ እያለ: እሺ አንዴ አጠፋህ ፣ሁለቴ አጠፋህ አይበቃምምምም ወይ ።እስከ መቼ አረ ይህ ነገር ከቀጠለ በጣም አደጋ ነው ኢስላምን ፣ኢማንን ማጣት እኮ አለ መጨረሻ: ኢብኑ ከሰሪ ያወሱት አንድ አስገራሚ ታሪክ አለ: አንድከአማኞች ጋር የነበረ ታጋይ መልካም ነገሮች የሚፈፅም ስዉዪ ነበር ነገር ግን ይህ ሰው በአንድ ወቅት ወደ አንዲት ሴት ይመለከታል ቆንጆም ሆና ሳበቼው ከዛም አንቺን በምን መልኮ ላገኝሽ እችላለው አላት ሴትዪዋ በእምነቷ ለይ የፀናች ነበረች እና ወደ እኔው እምነት ጠቅልለህ መግባት አለብህ አለችው ወደ እሷው እምነት ገባ በአንድ የሀራም እይታ. ከአመታት ቡሗላ ይህንን ሰው ያገኙትና ያሁሉ ቁርዓን ከልብህ ውስጥ ጠፋ ብለው በጠየቁት ጊዜ እንዳለቹት ቁርዓን አያዎቹ ጠፍተዋል ነገር ግን አንድ አንቀፅ ግን አልጠፋም ብሎ ይህን አያ አነበበ
رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ
እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡
አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን
በዛውም ላይ ያፅናን...........
🏻ሙሐመድ ሲራጅ መ/ኑር
/channel/MedrestuImamuAhmed
✅ታላቅ የሙሓደራ ፕሮግራም ✅✅
🔰ከሱዑዲያ በመጡ ታላላቅ የየመን መሻይኾች🔰
1. የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላህ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى
2. የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ رشاد الورد الحبيشي حفظه الله
የሙሓደራ 🕑: ዛሬ ቅዳሜ ከመጝሪብ አስከ ዒሻእ
የሙሓደራ ስፍራ: ቦሌ ሚካኤል በሚገኘው ጀዕፈር መስጂድ
ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ኡማውን ደዕዋ እንዲደርሰው ለማድረግ ለሌሎችም ያጋሩ
〰〰〰Share 〰〰〰Share
ውሸት አስነዋሪ ባህሪ ነው ። ውሸት የሙናፊቆች መለያ ነው ። ውሸት ማንነትን ከሚያረክሱ መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ነው ። ታላቁ ነብይ ውሸት ወደ ወንጀሎች እንደሚመራ ገልፀዋል ። ውሸትን የሚዳፈር ሰው ሌሎች ትልልቅ ወንጀሎች ውስጥም ሊነከር የቀረበ ነው ። ውሸትን የሚያበዛ ሰው አላህ ዘንድ “ ውሸታም” ተብሎ ይፃፋል !!!
ባጠቃላይ ውሸት የሰዎችን ታማኝነት የሚሰባብር ቆሻሻ ልማድ ነው ።
ዛሬ ዛሬማ ይኸው ሰባራ ባህሪ ወደ አላህ መንገድ እጣራለሁ የሚለው አንዳንዱ ደፋርም ላይ የሚታይ ሆኗል - እጅጉን ያሳዝናል !! ቀደምት ደጋጎችን እከተላለሁ እያለ የሚሞግተው አንዳንዱ ውሸትን ሲያበዛ ማየት እንግዳ መሆኑ ቀርቷል !!
ጀሌዎቹን ለመስቀል ሀሰትን እንደ ጠመንጃ ይጠቀምበታል ። በጠላትነት የፈረጃቸውን ለመገንደስ ባልዋሉበት ያውላል - ያሳዝናል !!!
ሁሉም አላህ ፊት ይቆማል !
አንተ በሰዎች ላይ የምትዋሽ ሆይ ! እያንዳንዱ ተገቢ ዋጋውን በሚያገኝበት ቀን የዋሸህባቸው ሰዎች ከመልካም ስራህ እንደሚወስዱ አለያም ከወንጀላቸው እንደምትሸከም አስታውስ !! አላህን ፍራ !!
አላህን ፍሪ !!
በርግጥ ነው ለቡድንተኝነት ትግላቸው ሆን ብለው ውሸትን እንደ መሳሪያ ከሚገለገሉበት ሰዎች ጋር “ አላህን ፍሩ “ ማለት የሚያግባባ ቋንቋ ላይሆን ይችላል ….. የተባለውን ሁሉ ሳያጣሩ በየዋህነት የሚያወሩትን ግን ይጠቅማል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ። አላህን እንፍራ !!
አላህ ከውሸት ይጠብቀን !!
/channel/Muhammedsirage
محاضرة جديدة؛
بعنوان: "لعن الله من ذبح لغير الله"
لفضيلة الشيخ رشاد الورد الحبيشي
-حفظه الله-
التاريخ، ۸ - جمادى الأولى ١٤٤٤هـ
ألقيت بمسجد سلسبيل في مدينة أديس أبابا [إثيوبيا]
/channel/Sunnah_Media/4463
الألباني: نشكو من الثورة التي ثارت بين أهل السنة، حيث أنه إذا ظهر فيهم من يظن أنه خالف أهل السنة في بعض المسائل، بدعوه ، وكان حسبهم أن يقولوا إنه أخطأ،ثم يقيموا الحجة عليه أما أن يزيدوا في الفرقة ، فهذا ليس من عادة #أهل_السنة_والجماعة
سلسلة الهدى والنور(٧٣٤) دقيقة ١٠:٢٢
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : فإذا تعذر إقامة الواجبات من #العلم و #الجهاد وغير ذلك إلا بمن فيه بدعة ، مضرتها دون مضرة ترك ذلك الواجب ؛ كان تحصيل مصلحة الواجب مع مفسدة مرجوحة ﺧﻴﺮًﺍ من العكس ، ولهذا كان الكلام في هذه المسائل فيه تفصيل .
[مجموع الفتاوى (٢٨/ ٢١٢)
የነገው ቀጠሮ
በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት
ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ
ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ
ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ
/channel/Muhammedsirage
ዛሬ በ አለም ባንክ ኢማም አሕመድ (ሜዳ) መስጂድ የተደረገው ሙሀደራ
የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላሂ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى
2. የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ رشاد الورد الحبيشي حفظه الله
ትርጉሙ በ አቡል አባሥ ናሥር ሙሀመድ
/channel/imamahmedonlinemdrsa?videochat=15e1bfed41441316e5
ሼር
رحمه الله وغفر له وأسكنه فسيح جناته ، وإنا لله وإنا إليه راجعون ،
ستكون الصلاة على الشيخ بعد صلاة العصر هذا اليوم في المسجد النبوي
ዘፈኖችን የስልክ መጥሪያ ማድረግ በየትኛውም ቦታ አይፈቀድም። መስጂድ ውስጥ ሲከሰት ደግሞ ይበልጥ የከፋ ሐራም ይሆናል። ምክንያቱም:-
* የመስጂድን ክብር መዳፈር ነው።
* ለሶላት የማይመጥን ነውረኛ ተግባር ነው። ሰው እንዴት ከጌታው ፊት ቆሞ ይሄ ይሆናል?!
* ሰጋጆችን መረበሽ አለበት።
* መላእክትን አዛ ማድረግ አለበት። መላእክት ሰዎች በሚፈተኑበት ነገር ይፈተናሉና።
ስለዚህ የስልካችንን መጥሪያ የማይረብሽ፣ ዘፈን ያልሆነ ጠቋሚ ድምፅ ልንመርጥ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
እነዚህ ናቸው ስለ ዑለማእ ክብር የሚደሰኩሩት
~
ሰሞኑን በሰዑዲ ዐረቢያ የሃሎዊን በዓል መከበሩን ተከትሎ የኢኽዋንና የአሕባሽን ጥምር ዘመቻ ስናይ ነበር። ከላይ ያያያዝኩት በዘመቻው ላይ ከፊት ረድፍ ከተሰለፉት ውስጥ ነው፡፡ ፅሑፉ በጥላቻና በድንቁርና የተለወሰ ነው። ነጥብ እየመዘዝኩ ምላሽ እሰጣለሁ፦
1- "ሳዑዲ የሚለው ስያሜ ከ1932 ጀምሮ የመጣ እንጂ ኢስላም ውስጥ የሌለ ቢድዓ እንደሆነና በነብያችን (ሰዐወ) ወቅት ስሟ ሒጃዝ እንደነበር ... " ይላል።
መልስ፦
ሀ. እንደምታዩት የሃገራትን ስያሜ ሱናና ቢድዐ እያለ ሊከፍል እየዳዳው ነው። ስለ ቢድዐ ያለው ግንዛቤ ይሄው ነው በቃ። ከአቅምህ በላይ ስለሆነ ጉዳይ ከመፈትፈት ይልቅ ቢያንስ የቢድዐን መሰረታዊ ግንዛቤ ብትለይ ይሻልህ ነበር።
ለ. "ሳዑዲ የሚለው ስያሜ ቢድዐ ነው" ሲል የቢድዐ አደጋ የሚያስጨንቀው አይመስልም? በየትኛው ቢድዐ ላይ ነው ስትዘምቱ የታያችሁት? በሺርክ የተጨማለቁ ድግሶችን አይደልንዴ በትንንሽ ነገር መለያየት የለብንም እያላችሁ የምትከላከሉት? የቀርዷዊ ዓለም አቀፍ ማህበርኮ ምክትሎቹ ሺዐና ኻሪ-ጂ ናቸው። እኮ እናንተም ስለ ቢድዐ?
ሐ. ደግሞም ሳዑዲ ማለት ለሒጃዝ የተሰጠ አቻ ስያሜ አይደለም። ከ1932 በፊትም በኋላም ሒጃዝ ሒጃዝ ነው። ሒጃዝ ከ0ረቢያ ልሳነ ምድር ውስጥ አንድ ክልል እንጂ ድፍን አካባቢውን የሚገልፅ አይደለም። ሒጃዝ በዛሬዋ ሰዑዲያ ምዕራባዊ ክፍል ያለው ግዛት ነው። ሰዑዲያ የሚለው ስያሜ ከዚህ ግዛት በብዙ እጥፍ የበዛ ነው። በሰዑድ ስም መሰየሙም በጥላቻ ስለተሞሉ እንጂ ይህን ያህል የሚያነጋግር አልነበረም። ሁሌ የምትዘምሩለት የኦቶማን ተርክ ኤምፓየር እኮ በመስራቹ ዑሥማን ጋዚ ስም ነው የተሰየመው። ለማንኛውም ስለምታወሩት ጉዳይ እንኳ ያለምንም የእውቀት እርሾ በባዶ አትፃፉ። ጥላቻ እውቀት አይሆንም።
2- "ስዑድ የአንድ አምባገነን ቤተሰብ ስም መሆኑ ልብ ይሏል" ይላል።
መልስ፦
ሀ- አዎ ይሄ ስያሜ ዛሬ ላለው ሃገር በመጠሪያነት የዋለው በመስራቹ ንጉስ ዐብዱልዐዚዝ ዘመን ነው፣ ረሒመሁላህ። ከነ ክፍተታቸው ጀግና ናቸው፣ የጀግና ቤተሰብ። ከየትኛውም ሀገርና ቡድን በተለየ ለተውሒድ፣ ለኢስላም ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከሃገራቸው አልፈው በመላው አለም ተውሒድን ለማሰራጨት እጅግ ብዙ ገንዘብ ያፈሳሉ። ጠላት ሳይቀር ይህን ተገንዝቦ "የሳዑዲ ፔትሮ ዶላር" እያለ እያላዘነ ነው። ከመላው አለም ወጣቶችን እየተቀበሉ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው ያስተምራሉ። ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ ኢስላማዊ ጉዳዮች፣ ደዕዋና ኢርሻድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ባለስልጣን መስሪያ ቤት፣ የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት፣ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ወዘተ ለኢስላም ምን ያክል ትኩረት እንደሚሰጡ ህያው ምስክር የሆኑ በመንግስት የሚመሩ የሀይማኖት ተቋማት ናቸው። እስኪ በየት ሀገር ነው የነሱን የሚያህሉ እንዲህ አይነት ተቋማት ያሉት?
ንጉስ አልፎ ሌላ ንጉስ በተተካ ቁጥር ደስ የማይል መላላት በየዘመኑ እያየን ነው። በዚህ ነገር ውስጣችን እጅጉን ይደማል። ከመሆኑም ጋር እነሱን በማብጠልጠል ላይ የተሰማሩት የኢኽዋንና የአሕባሽ አንጃዎች ከነሱ ሊሻሉ ነው? አመድ በዱቄት ይስቃል!
ለ- በተረፈ አምባገነን ስርአት ነው ስትሉ ምንድነው የምትፈልጉት? ዲሞክረሲ የለም ልትሉ ነው? እንኳንም አልኖረ። በኢስላም መመዘኛ ዲሞክረሲ ፈፅሞ ከአምባገነን ስርአት የተሻለ አይደለም። ደግሞስ ሰርክ የምትዘምሩለት የኦቶማን አስተዳደር የለየለት አምባገነን እንደነበር ማን በነገራችሁ?
3- "የቀብር አምልኮ (ሽርክ ከመሆኑ ጋር) ላይ ብቻ የሚጮኹና ቤተ-መንግስት ውስጥ ያሉ ህያው አምባገነኖችን ቀዳሽና አወዳሽ አላህ ላይ ያለምንም ስልጣን አሻራኪ የነበሩ፣ በባለስልጣናት ዙፋን አስጠባቂ ዓሊሞችና እስር ቤት ለዓመታት እንዲማቅቁ ተደርገው የሚሞቱ ዓሊሞች መሃል ያለውን ልዩነት ማስተዋል ያሻል።"
መልስ፦
ለትናንቱም ለዛሬውም ፅሑፌ ቀዳሚው መነሻዬ ይሄን መሰል እርኩስ ውንጀላ ነው። ደጋግሜ እንደገለፅኩት የነዚህ ነውረኛ አካላት ዋናው ማጠንጠኛ የሳዑዲ ስርአት አይደለም። የሳዑዲ ዑለማዎች እንጂ። እንደምታዩት ዑለማዎቹን ነው "አምባገነኖችን ቀዳሽና አወዳሽ አላህ ላይ ያለምንም ስልጣን አሻራኪ" እያለ የሚገልፀው። በዚህ መልኩ ቆሻሻቸውን ሲደፉ እያየ "ዑለማዎቹን ማን ነካ?" የሚል እንቅ -ልፋም አለ። ከዚህ በላይ ምን ይበላቸው?! እኮ እነ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐባድ፣ ... ናቸው አምባገነኖችን እያመለኩ በአላህ ላይ የሚያሻርኩት?! በኢስላም ታሪክ እንደዚህ የኢኽዋን ቡድን ባለጌና ነውረኛ መንጋዎችን የሰበሰበ መኖሩን እጠራጠራለሁ።
4- "ሸሪዓ ቁረጠው ፍለጠውና ቅፍደዳ አይደለም። እንደዚያ አለመሆኑን ሐረሞቻችን ላይ የተጠመጠው ይህ ቤተሰብ ህዝቡን አፍኖ ጥቂት ነፃነት ሲሰጠው በቀጥታ እንደታየው የሸይጣን አምላኪ ባልሆነ ነበር። ከዚህ ስርዓት ይልቅ ምዕራቡ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ስለ ሸሪዓ አብዝተው ይሰራሉ" ይላል።
መልስ፦
ተመልከቱ ይህንን የተሳከረ ትንታኔ! በመጀመሪያ ሃሎዊን ያከበሩት የሳዑዲን ህዝብ 1% አይሆኑም። እንዴት እነዚህን መነሻ አድርጎ ህዝብን በጅምላ "የሸይጣን አምላኪ" ብሎ ይገልፃል? ጥላቻ አውሮት እንጂ አሁን ይሄ ለህፃን የሚሰወር ጉዳይ ነው? ደግሞስ ተመሳሳይ ስሌት ተጠቅሞ የቱርክን ህዝብ "የሸይጣን አምላኪ" ብሎ ይገልፃል? እኮ ከሳዑዲ በበለጠ ምዕራቡ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ስለ ሸሪዓ አብዝተው ይሰራሉ? ምን የሚሉት ፍርደ ገምድልነት ነው? በዚህ ቅጣምባሩ በጠፋው ግንዛቤህ ነው ህዝብን ከህዝብ የምትመዝነው?
5- "ተስፋ አስቆራጭና የቂያማ ነገ መሆንን ብቻ ሳይሆን እንደ ኡማ ፈሳድና ጃሂሊያን ታግሎ ልክ እንደ ኳታር የኢስላምን መርሆች ዳግም ማምጣትን ማሰብም ከአንድ ሙስሊም የሚጠበቅ የድል ተስፈኝነት ምልክት ነው" ይላል።
መልስ፦
ሀ. ሳዑዲን ያብጠለጠለው ብእር ለኳታር የሚጨፍርበትን ምክንያት እናውቀዋለን። ይሄ አስመሳይ አካሄድ ከቁንጮዎቹ የተወሰደ ድግምት ነው። እንዲህ የንፍቅና አካሄድ እየሄዱ ነው ስለ ድል የሚዘምሩት። "እናያለን" አለ እውር!
ለ. አንዳንዶች "እንዴት ሳዑዲንና እነ ቱርክና ኳታርን ታወዳድራለህ?" ብላችኋል። መቼ ስራ ፈታሁና! የማይወዳደር ነገር ላይ ምን አደከመኝ?! "እና ከሳዑዲ ለመከላከል ለምን እነሱን ትጠቅሳለህ?" ነው ሎጂካችሁ። እያወዳደርኩ ቢሆን ስለ ቱርክ አንድ መፅሐፍ እፅፍ ነበር። የማላደርገው የሚይዝ ይዞኝ ነው። እውነቱን ለመናገር ክፉም አልመኝላቸውም። ስማቸውን የምጠቅሰው ሳዑዲን ለመተቸት የሚያነሱት ጥፋት ሁሉ በነዚህ ሃገራት ውስጥ በሰፊው ከመኖሩ ጋር በሳዑዲ ዑለማዎች ላይ የሚዘምቱት የኢኽዋን መንጋዎች የነዚህ ሃገራት ቀዳሽ አወዳሽ ስለሆኑ ነው። ስለሆነም የትችታቸው እውነተኛ መነሻ ለዲን መቆርቆር ሳይሆን ቡድናዊ ጥላቻ የወለደው እንደሆነ ለማሳየት ነው የምጠቅሰው። በዚያ ላይ እያወዳደሩ ያሉት ራሳቸው ናቸው። በልጁ ፅሑፍ ላይ ራሱ ማወዳደሩን ታያላችሁ።
ሳዑዲና ሃሎዊን
~
ሰሞኑን በሳዑዲ ሪያድ ውስጥ ሃሎዊን የሚያከብሩ ሰዎች መታየታቸውን ተከትሎ ጫጫታ እያየን ነው። የሳዑዲ መንግስት ላይ፣ ከዚያም በሱ በኩል አቆራርጦ ዑለማዎቹ ላይ፣ አሁን ካሉትም አልፎ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ላይ የሚዘምቱ ሰዎችን በተደጋጋሚ አይቻለሁ። የሆነ ነገር በለጠፍኩ ቁጥር ደጋግመው እየመጡ 'ኮሜንት' ላይ ብዙ ነገር የሚለቀልቁም ገጥመውኛል። "ስለዚህ ግን ትንፍሽ አትሉም" ይላሉ። ብዙዎቹ ከሁኔታቸው መውሊድን በማውገዛችን ቂም ያረገዙ እንደሆኑ ያስታውቃሉ።
ሃሎዊን ምንድነው?
-
የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ስመለከት ያገኘሁት እንዲህ የሚል ነው፦
Halloween "የሁሉም ቅዱሳን ቀን" ማለት ሲሆን በአብዛኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ ሃገራት የሚከበር በዓል ነው፡፡ የሚከበረውም በፈረንጆች October 31 ነው። ህፃናት የተለዩ አስፈሪ ልብሶችን በመልበስ በየቤቱ እየዞሩ ከረሜላና መሰል ነገሮችን ይጠይቃሉ።
ምንጭ፦ http://en.wiktionary.org/wiki/Halloween
መነሻው ኬልቲክ አካባቢ ቢሆንም አሜሪካ ከገባ በኋላ ወደሌሎች ሃገራት ተሰራጭቷል። ከህፃናት አልሮ በ"አዋቂዎችም" ይከበራል። የሰይጣን አምልኮ ነው እያሉ የፃፉ አይቻለሁ። ሊሆን ይችላል። እኔ ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም። በዓሉ መነሻው የጣዖታውያን ልማድ እንደሆነ፣ ከዚያም ከፊል ክርስቲያኖችና የሁዶች እንደሚያከብሩት፣ ከክርስቲያኖችና የሁዶች ውስጥ እራሱ አጥብቀው የሚያወግዙት እንዳሉ አንብቤያለሁ።
ሃሎዊን በኢስላም
~
በኢስላም የትኛውንም የጃሂሊያ (ኢስላማዊ ያልሆነ) ስርአት በዓል ማክበር አይፈቀድም። ነብያችን ﷺ የመዲና ሰዎች ሲያከብሯቸው የነበሩ የፋርስ ዞራስቲያኒዝም ሃይማኖት በዓላትን መከልከላቸው የሚታወቅ ነው። በተጨማሪም "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው" ብለዋል። [አቡ ዳውድ፡ 4031] ይሄ እጅግ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው።
ሃሎዊን በሳዑዲ
~
ሳዑዲ ውስጥ እስከ ቅርብ አመታት ድረስ የሃሎዊን በዓል አልነበረም። የሚፈልግ ስለሌለ ሳይሆን በመንግስት ስለተከለከለ ነበር። የክልከላውን መላላት ወይም መነሳትን ተከትሎ ግን - በአንድ ዌብሳይት ላይ እንዳየሁት - ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየተከበረ ነው። ይሄ በጣም ዘግናኝ ጥፋት ነው። ጥፋቱ በሳዑዲ ስለተፈፀመ የሚቀየር ብይን የለም። ማንም ለዚህ ወግኖ የሚከራከርም የለም። ከኖረም ባይፈፅመው እንኳ የጥፋቱ አካል ነው።
ለኢኽዋኖ - አሕባሽ መን-ጋዎች!
~
ለብዙኛ ጊዜ ደጋግሜ የምናገረው ነገር ቢኖር ሳዑዲ ውስጥ ከዚህም ውጭ ብዙ ጥፋቶች እንዳሉ እናውቃለን። አንዳንድ ቂላቂሎች እንደሚያስቡት ሳዑዲን ፍፁም አድርገን የምንስል አይደለንም።
ግን እናንተ የመጮሁንም የማስጨሁንም ሞራል ከየት አገኛችሁት? ምዬ እናገራለሁ ከአብዛኛቻችሁ ጩኸት ጀርባ ያለው ለኢስላም መቆርቆር አይደለም። የጩኸታችሁ ቀዳሚ መንስኤ ቡድናዊ ልዩነት ነው። ይሄ በዓል'ኮ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎ ጀምሮ ቱርክ ውስጥ ይከበራል? በዚህ መልኩ አስጩሃችሁት ታውቃላችሁ? ለምን? አንዱ ሳዑዲን በዚህ ሰበብ እያብጠለጠለ በለቀለቀበት ረዥም ፅሑፍ ውስጥ ኳታርን ሲያወድስ አይቻለሁ። እስኪ Halloween in Qatar ብለህ ጉግል ላይ ፈልግ። የእውነት ለዲን መቆርቆር ከሆነ ምክንያታችሁ ምነው ስለ ኳታር እስከዛሬ አልጮሃችሁም?! እነዚህ አካላት በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ፊት የሚያሳዩ፣ በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ስፍር የሚሰፍሩ፣ ሃይማኖትን ለፖለቲካዊ ንግድ የሚጠቀሙ ቆሻ - ሻ ፍጥረቶች ናቸው።
ሲጀመር የኢኽዋን አንጃ በምን መለኪያ ነው ከሳዑዲ መንግስት የሚሻለው? የቡድኑ መሪ ዑመር ቲልሚሳኒይ ገንዘብ እየከፈልኩ የፈረንጅ ዳንስ ተምሬያለሁ፣ ሲኒማ ለማየት ብዬ ሁለት ሶላቶችን በአንድ ላይ ጀምዕ እያደረግኩ እሰግድ ነበር አላለም? ቀርዷዊ ነፃነትን መተግበር ከሸሪዐ ይቀድማል አላለም? የቡድኑ መስራች ሐሰነል በናና ዩሱፍ አልቀረዳዊ በተጨባጭ ሐዲሥ የተረጋገጠውን የመህዲን መምጣት አላስተባበሉም? መውዱዲ የደጃልን መምጣት አላስተባበለም? ቱራቢ በርካታ መረጃዎችን ረግጦ የቀብር ቅጣት የሚባል የለም፣ ነኪርና ሙንከር የሚባል የለም አላለም? ነብያት መዕሱም አይደሉም አላለም? የዒሳን ዳግም መምጣት አላስተባበለም? ቀረዳዊና ሙርሲ የክህደት ቁንጮ ለሆኑ ጳጳሶች አላህ እንዲምራቸው ዱዓ አላደረጉም? ሰይድ ቁጥብ ከሶሐቦች አልፎ ነቢያትን አልጎነተለም? ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከኢስላም እያስወጣ አልፃፈም? ሰዕድ አልከታቲኒ በግብፅ ምርጫ ብናሸንፍ አስካሪ መጠጥ አንከለክልም፣ የብልግና ድረ ገፆችን አንዘጋም አላለም? እስኪ ምናችሁ ተሽሎ ነው ምላሳችሁን የምታሾሉት?
የእውነት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ተቆርቁራችሁ ከሆነ ይሄንን እያንሸዋረረ የሚያሳያችሁን ቡድናዊ መነፅር አሸቀንጥራችሁ ጣሉና በስርአት አስተምሩ። ኢስላም በሚያስተምረው መልኩ ከሃሎዊንም፣ ከቫሌንታይኑም፣ ከሳዑዲ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሃገራት ብሄራዊ በአላትም፣ ከኢሬቻም፣ ከገናም፣ ከመስቀልም ፣ ከመውሊድም፣ ወዘተ አስጠንቅቁ። ከፊሎቻችሁ'ኮ ለመስቀል ስታፀዱ እናውቃችኋለን! ከፊሎቻችሁኮ ኢሬቻን ለማውገዝ የምትሽኮረመሙ ናችሁ። ከሌሎቻችሁ'ኮ ሉሲን ተከትላችሁ ከሃገር ሃገር ስትዞሩ ነበር። የምን ማስመሰል ነው? እምቢ ብላችሁ ስለ ሳዑዲ ብቻ ከሆነ ማውራት የምትፈልጉት ቢያንስ በሌላ ሃገር የሌለ ጥፋት እየጠበቃችሁ ብትጮሁ ይሻላችኋል! ያለበለዚያ ግን ጧት ማታ ሙገሳ በምትሰፈሩላቸው ሃገራት ውስጥ ያለው ሲወጣ አስመሳይነታችሁ ይጋለጣል።
በርግጥ ለኛም ቢሆን የሳዑዲ ጥፋት ይለያል! ምክንያታችን ግን እንደናንተ የገነፈለ ጥላቻ አይደለም። አዎ ከሌሎቹ በበለጠ ሳዑዲ ላይ ይሄ መሆኑ ያመናል። ተሽለው መገኘት እንዳለባቸው ስለምናምን። ለሃገሪቱ ካለን መቆርቆር። የኢስላምና የሙስሊሞች ምልክት (symbol) በመሆኗ።
የአሕባሸና የኢኽዋን ጩኸት ግን "ከፍየሏ በላይ ነው።" የተጠራቀመ ቂም ስላላቸው አጋጣሚ እየጠበቁ ከሳዑዲ መንግስት አልፈው ዑለማዎች ላይ ዘመቻ ለመክፈት ነው አድብተው የሚጠብቁት። የሙዚቃ ኮንሰርት ሲካሄድ ልክ ዑለማዎቹ የፈቀዱ ይመስል እነሱም ላይ ጭምር ይዘምታሉ። ልክ በግልፅ ሙዚቃ የሚፈቅደውን ቀረዷዊን ሲያንቆለጳጵሱ እንደማናውቃቸው። ልክ ቱርክና ኳታር የሙዚቃ ድግስ፣ ከዚህም አልፎ ብዙ ነገር እንደሌለ። ይሄው በቅርቡ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ኳታር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ እየተዘጋጀ እንደሆነ አልጀዚራ እየዘገበ ነው። ሪያድ ሲሆን እንደምታወግዙት ደውሐ ሲሆን ታወግዙታላችሁ? አታደርጉትም። ምክንያቱም መስፈሪያችሁ የሚታወቅ ነው። حصانة إخوانية
.
ሁኔታችሁን እያየሁ ልመለስ እችላለሁ፣ ኢን ሻአ'ላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor