#ኢኽላስ ማለት በአላህና በባሪያው መካከል ያለ መለይካው አውቆ ሊጽፈው የማይችል እና ሸይጧንም ሊያበላሸው የማይችል ሚስጥር ነው » جنيد رحمه الله تعالى
]مدارج السالكين ٢ / ٩٢]
t.me/dinhhiwothnew
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
~
ሐጅ የኢስላም ልዩ መስህብ የሚሰተዋልበት፣ ድንቅ የአላህ ተዐምር የሚታይበት፣ የተውሒድ ነፀብራቅ ጎልቶ የሚነግስበት፣ ባእድ አምልኮ ከፍ ባለ ድምፅ ባደባባይ የሚወገዝበት ድንቅ ስርአት ነው። ሴት ወንዱ፣ ነጭ ጥቁሩ፣ መሪው ተመሪው በተመሳሳይ ቦታ እኩል ለአላህ የሚሰለፍበት ትንግርት። ሐጅ - አምስተኛው የኢስላም ምሰሶ።
በሐጅ "በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትእዛዝ ተጣራ" ለሚለው የአላህ ጥሪ “ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ፣…” /አቤት ጌታችን ሆይ አቤት፣ አቤት ጥሪህን ተቀብለን መጥተናል/” እያሉ መልስ በመስጠት ሚሊዮኖች ይተማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ “ከአላህ ሀገራት ሁሉ ይበልጥ አላህ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ከአላህ ሀገራት ሁሉም እኔ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ህዝቦችሽ ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ አልወጣም ነበር” የሚለውን የነብዩን ﷺ የቁጭት ንግግር፣ አሜኬላ የበዛበት ህይወታቸውን ልበዎ በሀዘን እየተከፈለ ያስታውሳሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ አስራ አራት ክፍለ-ዘመናት ወደ ኋላ አጠንጥነው የተውሒድ ጮራ ሲፈነጥቅ በአይነ-ህሊናዎ ይመለከታሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የመካ ሙሽ - ሪኮችን ለከት የለሽ ጭካኔና የነዚያን ፈርጥ የሆኑ ሰሐቦች ከብረት የጠነከረ ፅናት እያሰቡ በትዝታ ይነጉዳሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የነ ቢላልን ስቃይ፣ የነ ሱመያን የጣር ድምፅ አይነዎ እንባ እያቀረረ በሰመመን ያያሉ። ልበዎ በቁጭት እየደማ ይሰማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የአላህ የመጀመሪያ ቤት አለ - የሙስሊሞች ቂብላ፣ ከአለም ሁሉ ምርጡ ቦታ፣ መካ።
إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِلْعَالَمِينَ (96) فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا
"በርግጥም ለሰው ዘር (መፀለያ) ሆኖ መጀመሪያ (ምድር ላይ) የተኖረው ቤት ያ በበካህ (በመካ) ያለው የተባረከና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ የሆነው ነው። በውስጡ (እንደ) የኢብራሒም መቆሚያ (ያሉ) ግልፅ የኾኑ ተዓምራቶች አልሉ። ወደ ውስጡ የገባም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል።" [ኣሊ ዒምራን፡ 96]
- መስጂደል ሐራም መጤው ካገሬው እኩል የሚሆንበት ተአምራዊ ቦታ። የተውሒድ ቦታ፣ የእዝነት ቦታ። የኢብራሂም፣ የሐጀር፣ የኢስማዒል ትዝታ።
- መስጂደል ሐራም በረከት የበዛበት፣ ሰላም የሰፈነበት፣ እዝነት የነገሰበት፣ ተውሒድ የፈነጠቀበት ቅዱስ ቦታ።
- መስጂደ ልሐራም ልቦች ዘወትር የሚናፍቁት፣ አይኖች አይተውት የማይጠግቡት፣ ያላዩት ሊያዩት የሚቋምጡት ድንቅ ቦታ።
- መስጂደል ሐራም! “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” የሚለው ሀገርኛ ብሂል ፉርሽ የሚሆንበት ልዩ መስህብ። ለካስ ይናፍቃል! ደካማ አዛውንቶች በሽተኞች ሳይቀሩ ህመም ድካማቸውን ረስተው፣ ስቃይ እንግልቱን ዘንግተው፣ ባላዩት ሀገር ናፍቆት ተብሰክስከው፣ እልፍ አእላፍ ማይሎችን አቋርጠው ይተማሉ።
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَنْ لَا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
"ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ “በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ሩኩዕ ሱጁድ ለሚያበዙት ንፁህ አድርግላቸው” (ባልነው ጊዜ አስታውስ)።" [አልሐጅ፡ 26]
ከዕባ፣ ሐጀረል አስወድ፣ መቃም ኢብራሂም፣ ሶፋና መርዋ፣ ሚና፣ ዐረፋ፣ ሙዝደሊፋ፣… የሙስሊሞችን ቀልብ የሚማርኩ ልዩ የዒባዳ አውድማዎች ናቸው። ተልቢያ፣ ጦዋፍ፣ ሶላት፣ ዱዐ፣ እርድ፣ የጠጠር ውርወራ፣… ለፈፀማቸው ቀርቶ ለተነገረው የሚያጓጉ ሐጅ ላይ የሚፈፀሙ፤ ተቅዋን የሚያላብሱ የዚያኛው ዓለም ስንቆች ናቸው። (ذَلِكَ وَمَنْ يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِنْ تَقْوَى الْقُلُوبِ)
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ አላህ አድሎት የተዋጣለት ሐጅ ያደረገ እናቱ ስትወልደው እንደነበረው እንደ ህፃንነቱ ከወንጀል ሙሉ በሙሉ እንደሚፀዳ ነው መልእክተኛው ﷺ ያመላከቱት። በሐጅ ልቦች በኢማን ይታደሳሉ፣ አማኞች ከወንድሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ደካሞች ይታገዛሉ፣ ሙስሊሞች ከቅዱሱ ስፋራ፣ ከበረሃው፣ ከሐጁ ስርአት፣ ከተዳሚው ሁኔታ፣ ከዚያ የሚሊዮኖች ስብሰባ ብዙ ተፈኩር ይወስዳሉ።
አላህ አድሎት የሐጅ ስነ-ስርኣት ላይ ለተካፈለ ሰው ልብሳቸው የበሰበሰ፣ ሰውነታቸው የኮሰሰ፣ ኑሮ ያጎሳቆላቸው ስንት አይነት ሰዎችን ከተለያዩ የአለም አፅናፋት ታድመው ይመለከታል። አንዳንዶቹ ለዘመናት አጠራቅመው ለዚህ ስኬት እንደበቁ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ። በተሽከርካሪ ወንበር የሚገፉ፣ በጀርባ የታዘሉ አዛውንቶችን ሲመለከቱ፣ አቅሙም ጤናውም ተሟልቶ ከሐጅ ስለቀረው ወገን በእጅጉ ያዝናሉ። ሐጅ የወጀበባችሁ ወገኖቼ ሆይ! ጤናን አቅምን ያደላችሁ ጌታ፣ ሐጅን ግዴታ አድርጎባችኋል። ወንድሞቼ እህቶቼ፣ አባቶቼ እናቶቼ ሆይ! ለአላማ እንደተፈጠራችሁ አትዘንጉ። የተሰጣችሁ ገንዘብ ያንን አላማ ማሳኪያ እንጂ መጎረሪያም መባከኛም አይደለም። ሐጁን ብትፈፅሙት ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። ወንጀላችሁ ይረግፋል፣ ልባችሁ ይፀዳል፤ የዒባዳ ወኔያችሁ ይነሳሳል። እመኑኝ አንዴ ቆርጣችሁ ከፈፀማችሁት በያመቱ ገና ጊዜው ሲቃረብ ነው ልባችሁ የሚቆመው። “ወዴት” እንዳትሉኝ። ወላሂ ስንቶች ናቸው ሐጅ አጠናቀው መካን ሲለቁ፣ በእንባ የሚታጠቡት! ባትፈፅሙትስ ማነው የሚጎዳው? በርግጠኝነት አላህ ምንም አይቀርበትም! መቼስ ከሚታረደው እርድ አይደርሰው ነገር! ያበላል እንጂ አይበላምና። ከፍጡር ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነውና።
وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
"ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው።" [ኣሊ ዒምራን: 97]
ዱዓቶች ሆይ ሰዎችን ቀስቅሱ። አላህ የጣለባችሁን ሀላፊነት አድርሱ። ተሳክቶላችሁ በናንተ ሰበብ አንድ ሰው ለሐጅ ቆርጦ ቢነሳ የሚኖራችሁን አጅር አስታውሱ። ወገን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ተመልከት። ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት ብዙ ሐጅ ያላደረጉትን ፍቀድ። ዘንድሮ ባይደርስ ለቀጣይ አስታውስ። "አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና።" [አዛሪያት፡ 55]
ባይሆን አደራ!
ለሐጅ ቆርጠው ከተነሱ፡- በሚገባ ይዘጋጁ። ስለሐጅ ይጠይቁ፣ ይወቁ፣ ያንብቡ፣ የሚያነቡትም ይያዙ። ከተቻለም ቀድሞ ሐጅ ያደረገ የዲን ግንዛቤ ያለው ሰው ጓደኛ ማድረገዎን አይርሱ።
"ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)" ይላሉ ነብዩ ﷺ።
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ
ኢነል ሐምደ
ወኒዕመተ
ለከ ወልሙልክ
ላሸሪከ ለክ!
.
ያ ረሕማኑ ቤትህን ለመጎብኘት አንተ ወፍቀን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 3/2006)
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ኒቃብ (አይነ ርግብ) መልበስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው
~
ብዙ ክርስቲያኖች የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ (በተለይም ኒቃብን) የዐረብ ባህል እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ። በመሰረቱ የፈረንጅ ባህል ተከትለው ሴቶች ሱሪ ከሚለብሱበት ባህል የዐረብ ባህል ቢሆን እንኳ ግብረ ገብነትን የሚጠቁመው አለባበስ የተሻለ ስርአት ያለው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ የማርያም ምስል ነው ብለው ክርስቲያኖች በሚገልፁት ምስል ላይ ያለው አለባበስ ሙስሊሞች ዘንድ እንጂ ክርስቲያኖች ዘንድ የለም። ለምን የሚለውን ክርስቲያኖች ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው።
ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ሙስሊሞች የሚያራምዷቸው መርሆዎች - ፊት መሸፈንን ጨምሮ - በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ሊያውቁ ይገባል። ብዙ ክርስቲያኖች ለመፅሀፋቸው ባይተዋር ስለሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እጠቅሳለሁ፦
1- በኢስላም በሴት የሚመሳሰል ወንድ እና በወንድ የምትመሳሰል ሴት የተረገሙ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]
2- ሴት ፀጉሯን እንድትሸፍን ኢስላም በጥብቅ ያዛል። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል? ይሄውና :- "ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]
3- ሴት ፊቷን መሸፈኗ በኢስላም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሐቅ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስስ የለም? በሚገባ አለ። ይሄውና፦
* "ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። ሎሌውም፦ እርሱ ጌታዬ ነው አላት እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ #ተከናነበች።" [ዘፍጥረት 24፣ 64- 65]
* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]
ልብ በሉ! አይነ ርግብ ማለት ኒቃብ ወይም የፊት መሸፈኛ ነው።
* "ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።" መሀልየ ዘሠለሞን 5፡6]
* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1]
ስለዚህ ሙስሊም ሴቶች እየተገበሩት ያሉት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን እውነት ነው ማለት ነው። ለምንድነው ታዲያ ይሄ ጉዳይ ክርስቲያኖችን የሚያበሳጨው? ከሙስሊም ሴቶች ጎን መቆም ሲገባ ጭራሽ ማንገላታትና ከትምህርት ገበታ ማራቅ ፈፅሞ የማይገባ ነውረኛ ተግባር ነው።
ደግሞም እወቁ! ብዙ ጭቆናዎች በሂደት እንደተቀየሩት ይሄም ያለ ጥርጥር ዛሬ ወይም ነገ ይቀየራል። ለትውልድ የሚቀረው የናንተ የጭቆና ታሪክ ነው። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስማችሁ እንዲቀር ነው የምትፈልጉት? ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።
* ባያያዝኩት ምስል ላይ ፊታቸውን ሸፍነው የሚታዩት ሙስሊሞች አይደሉም። ይልቁንም አይሁዶች ናቸው። የሙስሊም ሲሆን ሁሉ ነገር ለሚያስጨንቃቸው አካላት ማስታገሻ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ዛሬ ምሽት ረመዷን 27ኛው ለይል ላይ እንገኛል። ይህ ለይል ለይለተል ቀድር ይሆናል ተብሎ እጅግ ተስፋ የሚጣልበት ለይል ስለሆነ ለሊቱን በሶላት በዚክር በዱዓእ በእስቲግፋር ቁርኣን በመቅራት ልናሳልፈው ይገባል ።
ከምናደርገው ዱዓእ ውስጥ ነብያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) ያስተማሯትን ዱዓእ ቢሆን ጥሩ ነው
ይሄውም፦
اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني
አሏሁመ ኢነከ ዐፉውን ቱሒቡል'ዐፉወ ፋዕፉ ዐኒ
👇👇
ጌታዬ ሆይ ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ
🤘🤘
ማለት ነው ትርጉሙ
ይህን ማለት የማይችል በሚያውቀው ቋንቋ የፈለገውን ማለት ይችላል
እንበርታ ወንድሞቼና እህቶቼ
አሏህ ለይለተል ቀዲርን ይወፍቀን !!
t.me/dinhhiwothnew
ረመዷን የመጨረሻው ውስን ቀናቶች ውስጥ ነን ይህን ዱዓ እናብዛ
" اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني "
" አሏሁመ ኢነከ አፉውን ቱሂቡል ዓፍወ ፈዓፉወ ዐኒ "
አላህ ሆይ አተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ይቅር በለኝ!
t.me/Kunizewjeten2
ትርፋማዎቹ ውድ የረመዷን አስር ለሊቶች ዛሬ ምሽት ይጀመራሉ።
( ረመዷን 21ኛው ለይል !)
እነዚህ አስር ሌሊቶች ለይለቱል ቀዲር የምትገኝባቸው ሌሊቶች ናቸው ።አስር ሌሊቶቹን በዒባዳእ ያሳለፈ ለይለቱል ቀዲርን ያገኛል !
ሁላችንም ዛሬ ሌሊት ጀምረን በዒባዳእ ለማሳለፍ እንሞክር
አሏህ ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን !!
t.me/dinhhiwothnew
عجل فطرك على تمرات ثم صل المغرب ثم اكمل طعامك
قالت اللجنة الدائمة للبحوث العلمية والإفتاء :
السنة أن يبادر الصائم إلى الإفطار إذا تحقق من غروب الشمس ؛ لحديث : (لَا يَزَالُ النَّاسُ بِخَيْرٍ مَا عَجَّلُوا الْفِطْرَ)
والأكمل في حق الصائم أن يفطر على تمرات ثم يؤخر تناول الطعام إلى بعد صلاة المغرب ؛
حتى يجمع بين سنة تعجيل الفطر وصلا ة المغرب في أول وقتها في الجماعة ؛ اقتداء بالنبي صلى الله عليه وسلم .
فتاوى اللجنة الدائمة
t.me/Kunizewjeten2
"ፕራንከ በማድረግ የሚታወቀው ሶሀቢይ"
~
በዚህ መልኩ ርእስ ከሰጠ በኋላ የኑ0ይማን እና የሱወይቢጥን "ገጠመኝ" ማስረጃ አድርጎ የጠቀሰ ሰው አየሁ። የታሪኩን ጭብጥ ከፀሀፊው ልጥፍ ቀንጨብ አድርጌ ላቅርበው፦
{{ኑአይማን ሱወይቢጥን ምግብ ጠየቀው። አቡበክር ሳይመጣ አልሰጥህም አለው። በዚህን ግዜ ኑዐይማን ቆይ እሰራልሃለሁ ብሎት ወደ ሌሎች ነጋዴዎች ዘንድ በመሄድ "ባሪያ ትገዙኛላችሁ?" አላቸው። "አዎ በስንት እንግዛህ?" አሉት። "አይ ዋጋውማ ቀላል ነው ነገር ግን ባሪያው ጉድለት አለበት ጉድለቱን ሳልነግራችሁ አልሸጥላችሁም እስከነጉድለቱ ከገዛችሁኝ ነው የምሸጥላችሁ" አላቸው። "ጉድለቱ ምንድነው ?" ብለው ሲጠይቁት "ባሪያው ምላሱ ረጂም ነው ሁሌ ነጻ ሰው ነኝ ባሪያ አይደለሁም እያለ ይለፈልፋል" አላቸው። "ጉድለቱ ይህ ብቻ ከሆነ አብሽር እንገዛሃለን" አሉት። በ 10 ትናንሽ ግመሎች ተስማሙ። ግመሎችን ሰጥተውት እየነዳቸው ወደ ሱሀይቢጥ ጋር ነጋዴዎችን ይዟቸው መጣ። "ይሄው ባሪያው ውሰዱት" አላቸው። ሱሀይቢጥም "ኧረ ባሪያ አይደለሁም ነጻ ሰው ነኝ" ብሎ ቢጮህ "ዝም በል ይህ ነውር እንዳለብህ ቀድመን አውቀናል ዝም ብለህ ና" ብለው በገመድ አስረውት ወሰዱት።
አቡበክር ሲዲቅ ሲነገረው ስቆ ለነጋዴዎቹ ግመሎቹን መልሶላቸው ሱሀይቢጥን አስለቀቀው። ከጎዞ ሲመለሱ ለነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ኑአይማን ሱሀይቢጥ ላይ የሰራው ፕራንክ ሲነገራች እሳቸውም ሶሀቦቻቸውም ሳቁ ኑዐይማንን አልወቀሱትም።
ኑአይማን ሌሎችም በርካታ ፕራንኮች አሉት ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አይቃወሙትም ነበር ። }}
=
እንግዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ፕራንክ እየተባሉ ለሚለቀቁ ስራዎች ማስረጃ መሆኑ ነው። ሌላም ፀሐፊ ከዚህ በፊት ይህንንና ሌሎች ቂሳዎችን በተከታታይ ሲፅፍ አይቻለሁ።
ለማንኛውም በኢስላም እንዲሁ ኪታብ ውስጥ ስለተገኘ ብቻ አንድ ዘገባ ዝም ብሎ አይወስድም። ተቀባይነቱ ይፈተሻል። የዘርፉ ማለትም የሐዲሥ ሊቃውንት ደግሞ ምርቱን ከእንክርዳዱ አበጥረው እየለዩ አስቀምጠዋል። ወደ ተነሳንበት ዘገባ ስንመለስ የሐዲሥ ምሁራን ብይን ይህንን ይመስላል፦
1- አልቡሲሪይ "ይሄ ደካማ ሰነድ ነው" ብለዋል። [ሚስባሑ ዙጃጃህ: 4/115]
2- አልባኒይ ደካማ ነው ብለዋል። [ዶዒፍ ኢብኑ ማጀህ፡ 750]
3- ሹዐይብ አልአርናኡጥ ደካማ ነው ብለዋል። [ተኽሪጁ ሙሽኪሉል ኣሣር፡ 1620] [ ተኽሪጁል ሙስነድ፡ 26687]
ይልቁንም ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ
"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"
አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ እና አሕመድ የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
የተጠቀሰውንም ሆነ ሌሎች ከኑ0ይማን ጋር ጋር የተያያዙ ቀልዶች ሰነዳቸው ደካማ እንደሆኑ የሚጠቀም አጠር ያለ ዳሰሳ በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid04D6qPPXykD7WodZJ5eW3Pms9PkcQBhiVjvwbKAc59Vf1hXwWxSKSQVnZZerTXq47l&id=354099817993687&mibextid=Nif5oz?
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
የኢሞ ማስታወቂያ ላስቸገራችሁ
Setting ውስጥ በመግባት ከዚያም Functions የሚለውን በመክፈት " Voice club፣Friends of Friend & Explore "የሚሉትን በመዝጋት የኢሞን ማስታወቂያ መዝጋት(ማስቆም ትችላላችሁ)
✍ Ibnu Seid
የቢሮ “ አለቆቻቸውን “ አለቃየ ይላሉ …
ባሎቻቸው “ አለቃዎቻቸው “ ለምን አልሆኑም ?!!!
ምእራቡ አለም
ትዳር …..
ከደርስ የተቆረጠ አጭር ምክር
በሙሐመድሲራጅ ሙ ኑር
/channel/Muhammedsirage
ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~
ለሙስሊም ወንዶች ከነ ጭራሹ ሃይማኖት የሌላቸውን ሴቶች ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድላቸውም። ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ባጠቃላይ ማግባትም እንዲሁ የተፈቀደ አይደለም። ከዚህ ተለይቶ የሚወጣው እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት ብቻ ነው። ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ግን ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
.
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ ዝንባሌያችን ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
.
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግንኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ለቀጣይ ህይወት መሰናክል እንዳይሆን ያክል ብቻ ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል።
ቁርኣናችን ደግሞ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከታወቁት ጋር ብቻ ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።
ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው። ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ትዳር ፈፅመው ከዚያ ልጆቻቸው የከፈሩ ስንቶች ናቸው? አንዳንዶቹ እንደዋዛ ልጆቹ 18 አመት ሲሞላቸው ሃይማኖታቸውን ይመርጣሉ ይላሉ። ይሄን ሁሉ አመት ኢስላምን አልተማረም፣ ሶላት የለም፣... ። በዚያ ላይ ለልጆች ከአባቶች ይልቅ እናቶች የበለጠ የቀረቡ ናቸው። ጊዜው አይነቱ የበዛ የሞራል ዝቅጠት የተንሰራፋበት ነው። በነዚህና መሰል ምክንያቶች የተነሳ ልጆቹ ኢስላምን የመያዛቸው እድል የመነመነ ይሆናል። እንዲህ አይነት ከባቢ ባለበት ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይፈቀድም።
.
ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523]
እንዲያውም ኢስላም አላህን መፍራትና ግብረ ገብነት ያላቸውን ሴቶች እንዲያገቡ ነው ወንዶችን የሚያነሳሳው። ይህንን ህግ መጠበቅ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ለሚወለዱ ልጆችም፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም፣ ለኢስላምም ውለታ መዋል ነውና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
/channel/IbnuMunewor
قناة السنة سفينة نوح:
እኛ የእናታችን አይሻ አላህ ሰራዋን ይውደድላትና የእሷ ፋሽን ተከታይ ነን እንጅ የባጢሎችና ለዚና መንስኤ ለመሆን እራቁታቸውን በፒኪና ተገላልጠው ከሚሄዱት የነብስያቸውን ተከታይ ከሚገላለጡት የሸይጧን ተባባሪ አይደለንም አልሀምዱሊላህ
አዋቂና ብልህ ሰው ማለት ስጋዊ ፍላጎቱን እና ስሜታዊ ዝንባሌውን ተቆቁም ከምት በሁዋላ ላለው ህይወቱ የሰራ ሰው ነው ብለዋል ረሱል صلى الله عليه وسلم ለዛ ነው እህቴ ጊዜና ዘመን እንዳያታልሽ አንች የእውነት ደስተኛ ለመሆን ከፈለግሽ ተሸፋፈኒ ሱና የስኬት ውጤት ነው!!
/channel/Menhaj_Salafiya
الحل الأمثل للسعادة الزوجية عند الخصام مع الزوجة ...
للاشتراك في قناة التليجرام
╰➢ t.me/Kunizewjeten2
የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመሸጥ የሞትተዳደሩ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፣
በምትሸጡ ግዜ እውነተኞች ሁኑ ! ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለን ስልክ፣ ታብሌት ... በአዲስ ስም ፣ ባልሠራ ሒሳብ ከመሸጥ ታቀቡ ! አሏህን ፍሩ ! ላመኗችሁ ታማኞች ሁኑ! የዱንያ ሸቀጥን ፣ ጠፊ ገንዘብን ለመሰብሰብ ሲባል እምነታችሁንና ክብራችሁን ለአደጋ አታጋልጡ
በውሸትና በማጭበርበር የሚገኝ ገንዘብ ዕረፍትን የሚነሣ ከመሆኑ ጋር የፍርዱ ቀን ደግሞ ኪሣራን ያሸክማል .. አሏህ ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋልና ተጠንቀቁ ! አሏህን ፍሩ!
ኢማምነትና ኸጢብነት ሸሪዐዊ ሃላፊነቶች ናቸው። በሸሪዐዊ ሃላፊነት ላይ በአግባቡ አማናን መወጣት ይገባል። የራስን ፍላጎት ብቻ ከመከተል ይልቅ ሰፊውን ተገልጋይ ማሰብ ይገባል። ስላሰኘህ ብቻ ማስረዘም፣ ስለ ታከተህ ብቻ ማሳጠር ተገቢ አይደለም። ኢማም ወይም ኸጢብ የሆነ ሰው አቅመ ደካሞችን፣ ባለ ጉዳዮችን፣ ህመምተኞችን፣ አዛውንቶችን፣ ፀሐይ ወይም ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆችን ወይም አድማጮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት። ነብያችንኮ ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሰምተው እናቱ እንዳትረበሽ በሚል ሶላት ያሳጥሩ ነበር።
ልክ እንዲሁ በኸጢቦች የሚነሱ ርእሶችም ማህበረሰቡ ያለበትን ሁኔታ ወይም ወቅታዊ ጉዳዮችን የዘነጉ መሆን የለባቸውም። ረመዷን ላይ አብዛኛው ደዕዋ ስለ ረመዷን ነበር። ይሄ ጥሩ ነው። ነገር ግን በዘረኝነት ስንታመስ፣ በሱስ ስንወረር፣ ነጋዴው መሀል ማጭበርበርና መካካድ ሲንሰራፋ፣ መጨካከን ሲበዛ፣ ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ ... ዱዓቶችና ኸጢቦች ጭልጥ ብለው ሌላ አለም ውስጥ ሊሆኑ አይገባም። አስተማሪ ማለት ልክ እንደ ሃኪም ነው። ሃኪም የውስጥ ደዌ ለማከም የቆዳ መድሃኒት አይሰጥም። ልክ እንዲሁ ለወገኑ ተቆርቋሪ የሆነ ዳዒያህ ማለት ህዝቡ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እያየ ተገቢውን ህክምና የሚሰጥ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
የስድስቶን ፆም የምትፆሙ እህትና ወንድሞች
ሰኞና ሐሙስ አብረው ከገጠሙ የስድስቶንም የሰኞና የሐሙስን ሱና ፆሞች በጋራ ነይታችሁ ብትፆሙ የሁለቱንም አጅር ታገኛላችሁ ኢን'ሻ አሏህ !
http://t.me/dinhhiwothnew
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
ከረመዷን በፊት ወደነበርክበት አመፅና ወንጀል ለመመለስ በማኮብኮብ ላይ ያለህ ወንድሜ ሆይ ! አላህን ፍራ! የረመዳኑ ጌታ የተቀሩት ወራቶችም ጌታ ነው ... አሏህን ፍራ!
ፈጣሪህን በመፍራት የታዘዝከው በዚህ ወር ብቻ አይደለም ... ከፀያፍ ነገሮች መራቅ የእድሜ ልክ ግብ እንጂ የአንድ ወር አላማ አይደለም !
ሁሌም ለአላህ እጅ የሰጠህ ሙስሊም ለመሆን ታገል ...
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
/channel/Muhammedsirage
አሏህ ሙስሊሙን ማሕበረሰብ በተውሒድና በሱናህ አንድ እንዳደርገን ፣የዱንያ አኼራችን ህይወት እንዳምርልን፣ ወደ አኼራ ለቀደሙን አማኞች ከአሏህ ምህረትን፣ አገራችን ሰላም የሰፈነባት የተረጋጋች አገር እንድትሆን፣ ግ*ፈኞ*ች ፓለቲከኞች እና በዳ*ዮችም የእጃቸውን እንዳገኙ ... አላህን እንለምን !!
t.me/dinhhiwothnew
ቁርኣንን ያለ ጦሀራ (ያለ ውዱእ / ትጥበት) መንካት ይቻላልን?
~
ቁርኣንን ያለ ጦሀራ መንካት አይቻልም የሚለው የአራቱም የፊቅህ መዝሀቦች አቋም ነው። አልፎም ባጠቃላይ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። መረጃ የሚደግፈውም ይህንኑ ነው። ሁለት መረጃዎችን እጠቅሳለሁ:-
♻️ [መረጃ አንድ]:- ሐዲሣዊ ማስረጃ ♻️
ነብያችን ﷺ ወደ የመን በላኩት ደብዳቤ ላይ
أَنْ لَا يَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا طَاهِرٌ
"ቁርኣንን ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው" ሲሉ አሳስበዋል። [ሙወጦእ: 468] ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ "ሶሒሕ" ብለውታል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7780]
👉🏾 ብዥታ!
~
ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት ይቻላል የሚሉ ዓሊሞች ግን "የሐዲሡ መልእክት ሌላ ነው። 'ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው' ማለት 'ሙስሊም እንጂ እንዳይነካው' ማለት ነው" ይላሉ። ለዚህም "ሙስሊም አይንነጀስም" የሚለውን ሐዲሥ ያጣቅሳሉ።
ይሄ ግን - ወላሁ አዕለም - ልክ አይደለም። ይልቁንም መልእክቱ በቀጥታ ጦሀራ የሌለው ሰው እንዳይነካው ማለት ነው። የሐዲሡ ሌሎች ዘገባዎች ይህንን መልእክት ግልፅ ያደርጉልናል። ለምሳሌ:-
✅ 1ኛ፦ የዐብዱረዛቅ ዘገባ ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا يُمَسُّ الْقُرْآنُ إِلَّا على طُهْرٍ
"በጦሀራ ላይ ተሁኖ እንጂ ቁርኣን አይንነካም።" [አልሙሶነፍ: ቁ. 1328]
✅ 2ኛ:- የኢብኑል ሙንዚር ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا تَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا على طَهورٍ
"በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣን እንዳትነካ።" [አልአውሰጥ፡ 2/103]
▶️ ልብ በሉ! ሙስሊሙን ሰው ነው "በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣንን እንዳትነካ" ያሉት። ይህም ሐዲሡን "ሙስሊም ያልሆነ እንዳይነካው ማለት ነው" በማለት የተረጎሙት ልክ እንዳልሆኑ ያሳያል።
♻️ [መረጃ ሁለት]:- ቁርኣናዊ ማስረጃ ♻️
በቁርኣን ውስጥም እንዲህ የሚል መጥቷል:-
{ لَّا یَمَسُّهُۥۤ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ }
"የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም።" [አልዋቒዐህ፡ 79]
በርግጥ የዚች አንቀፅ ቀጥተኛ መልእክት ጥብቁን ሰሌዳ (ለውሐል መሕፉዝን) የሚገልፅ እንደሆነ አገባቡ ያሳያል። ይሁን እንጂ መልእክቱ ለቁርኣንም የሚውል እንደሆነ ጥቆማ አለው ይላሉ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [ሸርሑል ዑምደህ: 384]
ይህንን ሃሳብ የሚደግፍ አንድ የሶሐቢይ ንግግር ልጥቀስ። ሶሐቢዩ ሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ናቸው። ዐብዱረሕማን ብኑ የዚድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"ከሰልማን ጋር በሆነ ጉዳይ ላይ ነበርን። እሳቸው ጉዳያቸውን ለመፈፀም (ለመፀዳዳት) ሄደው ተመለሱ። 'ውዱእ አድርግማ የዐብደላህ አባት! ምናልባት ከቁርኣን ስለሆኑ አንቀፆች ልንጠይቅህ እንችላለን' አልናቸው። በዚህን ጊዜ (ሰልማን) እንዲህ አሉ፦
فَاسْأَلُوا، فَإِنِّي لَا أَمَسُّهُ، إِنَّهُ {لَا يَمَسُّهُ إِلَّا الْمُطَهَّرُونَ}
'ጠይቁ! እኔ አልነካውም። ነገሩ {የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም}።' "
ከዚያም "ጠየቅናቸው። ውዱእ ሳያደርጉ ቀሩልን" አሉ። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ ቁ. 1100]
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት ጦሀራ የሌለው ሰው ቁርኣንን ሊነካ አይገባም የሚለው የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ኢብኑ ዐብዲል በር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
أجمع فقهاء الأمصار الذين تدور عليهم الفتوى وعلى أصحابهم بأن المصحف لا يمسه إلا طاهر
"ጦሀራ ላይ የሆነ ካልሆነ በስተቀር ሙስሐፍ እንደማይንነካ ፈትዋ የሚቀርብላቸው የሙስሊም ሃገራት ሊቃውንት እና ባልደረቦቻቸው ወጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።" [አልኢስቲዝካር፡ 8/10] ከኢብኑ ሁበይራም በተመሳሳይ ኢጅማዕ እንዳለበት ተጠቅሷል። [አልኢፍሷሕ፡ 1/68]
ይሄ እንግዲህ እነሱ በሚያውቁት መጠን ነው። እንጂ ጥቂቶች ቢሆኑም የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቁ ተገኝተዋል። የሆነ ሆኖ ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት አይቻልም የሚለው ከሶሐቦች ውስጥ ከ0ሊይ፣ ከሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ፣ ከኢብኑ ዑመር፣ ከሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ተገኝቷል። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም ይላሉ ነወዊይ እና ኢብኑ ተይሚያህ - አላህ ይዘንላቸውና። [አልመጅሙዕ፡ 2/80] [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 21/266]
ይህንን ሃሳብ አስምሩበት። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም። ስለዚህ ውዝግቡ የመጣው ከሶሓቦች በኋላ ነው ማለት ነው። አዋቂው አላህ ነው።
ማሳሰቢያ፦ ሞባይልና መሰል ዲቫይሶችን ተጠቅሞ መቅራት እዚህ ውስጥ አይገባም። እንዲሁም ትርጉምና የተፍሲር ኪታቦችም የሙስሐፍ ብይን የላቸውም። ስለዚህ ያለ ጦሀራ መንካት ይቻላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 21/1444፣ ሚያዚያ 04/2015)
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ዱንያ ላይ የጌታውን ትዕዛዝ ያከበረ ፣ነፍስያውን ከሐራምና ከስሜቱ ያቀበ፣በተወረደለት ቁርኣንና ሐድስ መልካም ስራን የፈጸመ... ነገ አኼራ ላይ ዕድለኛና የተምቻቸ ህይወትን ይኖራል ።
ተጣሪው በሚጣራበት ጊዜ « እናንተ የጀነት ባለቤቶች ሆይ ! ከዚህ በኋላ ሞት የሚባል ሥቃይ የለባችሁም ዝንተ ዓለም ጀነት ውስጥ ዘውታሪዎች ናችሁ»
ለሚባልበት ዕለት አላህ የምንዘጋጅ ያድርገን !
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
የነገው ቀጠሮ
በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት
ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ
ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ
ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ
/channel/Muhammedsirage
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
~
በየሳምንቱ ዘወትር እሁድ አንፎ አካባቢ የሚሰጠው ደርስ ነገ እሁድ አይኖርም። ኢንተርኔት ደካማ ስለሆነ መልክቱን በምትችሉት መንገድ በማሰራጨት ተባበሩን።
አብኑል ቀይም ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :- " አላህን መታዘዝ ለአንድ የአላህ ባሪያ የሁሉ ነገር በረካ ያመጣል አላህን ማመፅ ( ወነንጀል ) ደግሞ የሁሉ ነገር በረካ ያጠፋል "
ጠሪቁል ሂጅረተይን ( 1/53 )
t.me/Kunizewjeten2
#أنت_الحرة
ﺍﻟﻮِﻻﻳﺔ ﻭﺍﻟﻘﻮﺍﻣﺔ ﻭﺍﻟﺤﺠﺎﺏ ﻭﺍﻟﻌَﻔﺎﻑ ﻟﻴﺲ ﻋﺮﻓًﺎ ﺍﺟﺘﻤﺎﻋﻴًّﺎ ﻭﻻ ﻣﻮﺭُﻭﺛًﺎ ﻗﺒﻠﻴًّﺎ ﻳﻘْﺒﻞ ﺍﻟﺘَّﻨﺎﺯُﻝ ﻭﺍﻟﻤﺴﺎﻭﻣﺔ؛ ﺇﻧّﻬﺎ ﺩﻳﺎﻧﺔ ﻧﺘﻘﺮّﺏ ﺑﻬﺎ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ رجلًا ﻭنساء.
t.me/Kunizewjeten2
🇸🇦اعرفوا لهذه الدولة قدرها🇸🇦
للشيخ محمد بن هادي المدخلي
التليجرام:
╰➢ t.me/Kunizewjeten2
انشر واشترك في قناتنا ويصلك الجديد