ነገ ሰኛ ረመዷን አንድ ነው።
በሱዕድ ዐረቢያ ጨረቃ ታይታለች።
አልሐምዱሊላህ ሱምመ አልሐምዱሊላህ ረመዷን አድስ ህይወት አድስ ምዕራፍ፡፡
ረመዷን ሙባረክ!!!
=============
/channel/MenhajuAsselfiya1
/channel/MenhajuAsselfiya1
/channel/MenhajuAsselfiya1
==>> በዚህ ቻናል የሚሰጡ ደርሶች
1/سلم الوصول إلا علم الأُصول في التوحيد
2/أعلام السنة المنشورة
لاعتقاد الطائفة الناجية المنصورة
3/نظم القواعد الفقهية
በአቡ ዐብዲላሂ ያሲን ሙሐመድ
/channel/MenhajuAsselfiya1
/channel/MenhajuAsselfiya1
በዚህች ቻናል አዳድስ ደርሶች ይጀመራል፡
በሁሉም ፈኖች ደርሱን ገብተው መከታተል ይችላሉ!!
/channel/MenhajuAsselfiya1
በዚህች ቻናል አዳድስ ደርሶች ይጀመራል፡
በሁሉም ፈኖች ደርሱን ገብተው መከታተል ይችላሉ!!
/channel/MenhajuAsselfiya1
በዚህች ቻናል አዳድስ ደርሶች ይጀመራል፡
በሁሉም ፈኖች ደርሱን ገብተው መከታተል ይችላሉ!!
===========
አቡ ዐብዲላህ
ያሲን ሙሐመድ
ٰ 🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹 👈አበባውን
🌹🌹🌹🌹🌹 በመንካት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ብቻ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የሚያመጣው
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🍀
🌹🌹🌹🌹🌹 add 🌷
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿 🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
+add የሱና ቻናል_የሚለው_በመጫን በጣም_ጠቃሚ _ነገር ትገኛላችሁ
እንኳን ያንተ አይነቱ
ውሻ ቢባል ሽልማቱ
ጀግና ‘ሚባል ተሰብስቦ
ሊያከስማቸው ጥልቅ አስቦ
አንዴ ሲዘልፍ ሙሐመድን
ሌላ ግዜ ሊገላቸው ጦር ሰብስቦ አገር ቢያድን
አልሆን ብሎት አፈር በልቷል
ከነ ጀሌው ጉድጓድ ገብቷል !
የዛሬውም ከንቱ ውሻ …,
ምግባር ሆኖ ለከረፋው ማንነትህ
ባፍ ብትጮህ ብታላዝን እንዳባትህ …
በዋልጌ አምደበትህ እምነቱን አትገታም
አለም ቢደግፍህ በባዶ ራስ ቅልህ እኛን ከቶ አትረታም !!!
/channel/Muhammedsirage
ዘረኝነት ከራስ ጋር ሲያጣላ
~
ጊዜው ሃሰተኛው ሙሰይሊማ ነብይ ነኝ ብሎ ተነስቶ ከባድ ፈተና የቀሰቀሰበት ጊዜ ነው። ጦልሐ አነሚሪይ ሙሰይሊማን ፍለጋ ወደ የማማ ሄደ።
* ሲደርስ "ሙሰይሊማ የት ነው?" ብሎ ጠየቀ።
- "እረፍ! የአላህ መልእክተኛ በል" አሉት።
* "ሳላየውማ አልልም!" አለ።
ሙሰይሊማ ዘንድ ደረሰና
* "ሙሰይሊማ አንተ ነህ?" አለው።
- "አዎ" አለ።
* "ማነው የሚመጣህ?" አለው። "ወሕይ ይወርድልኛል" ይል ስለነበር እሱን ነው የሚጠይቀው።
- "ረሕማን ነው" አለ።
* "በብርሃን ወይስ በጨለማ?"
- "በጨለማ።"
* በዚህን ጊዜ ጦልሐ እንዲህ አለው፦ "አንተ ውሸታም እንደሆንክ፣ ሙሐመድ ደግሞ እውነተኛ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ቢሆንም ግን ከሙዶር ጎሳ እውነተኛ ይልቅ የረቢዐ ጎሳ ውሸታም እኛ ዘንድ የተወደደ ነው።"
ልብ በሉ! የሙዶር ጎሳ እውነተኛ ያለው ነብዩን ነው፣ ﷺ። የረቢዐው ቀጣፊ ያው ሙሰይሊማ ነው።
የጦልሐ መጨረሻ ምን ሆነ? የ0ቅረባ ጦርነት ጊዜ ከሙሰይሊማ ጎን ተሰልፎ ሲዋጋ ተገደለ።
[ታሪኽ አጦበሪይ፡ 3/286]
እና ምን ለማለት ነው? በዘር ጥላቻ ወይም በዘር ውግንና ሰበብ ከአላህ ጋር እየተጣላን፣ የኣኺራ ቤታችንን እያጨለምን እንዳይሆን ተገቢ ጥንቃቄ እናድርግ።
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር
እዉቀትን መፈለግ
የላኢላሃ ኢለሏህ ትርጉም ምንድን ነው ?!!!
ይደመጥ !!!!!
t.me/NABAWITUBE
/channel/Muhammedsirage
በአለባበሱ ተማርካለት
ጺሙን አይታው ተመችቷት
ለባል መርጣ አግብታው
ልቧን ሰብሮ የከዳው ብዙ ነው
_
የፈለገ ዓሊም ፣የፈለገ ዳዒያህ ፣የፈለገ ታዋቂ ሰው ቢሆን እሱም እንደማንኛውም የሰው ልጆች ሰው ነው ስህተትን ይሰራል።ከስህተት የጸዳን ሰው ማግኘት አይቻልም።
ግን እህቶች ብትሰሙኝ ትንሽ ነገር ልበላችሁ፦
ድነኛን ሰው የትዳር አጋር ከማድረግ ጉጉታችሁ የተነሳ ካልሆኑ ሰዎች ከመውደቃችሁ በፊት ( ከሆነ ወንድ ጋር ከመተዋወቃችሁ በፊት)፦
1) ስለ ሰውየው ምንነትና ማንነት በጥልቅ እወቁ አጣሩ
2) ስለ ድኑ አጣሩ፤ ቢያንስ አምስት አውቃት ሶላትን በወቅቱ ስለመስገዱ
3) ስለ ስነ ምግባሩ ( ባህሪው) ከቤተሰቡ ጋር ያለው ህይወትና ግንኙነት ፣ከቅርብ ወዳጆቹ ጋር ያለው ባህሪ ምን ይመስላል? የሚለውን መርምሩ
4) ማስተዳደር የሚችልበትን ሐብትና ገቢ እወቁ
5) ከሱስ የጸዳ መሆኑን ጠይቁ
5) በአለባበሱና በውበቱ ብቻ ከመማረካችሁ በፊት ከላይ ያልኳችሁን ቀድማችሁ እወቁ
ድነኛ ነው፣ጺሙን ያስረዝማል፣ሱሪውን ያሳጥራል ብለው በውጫዊ ገጽታው ብቻ ተማርከው ብዙ ወራትን ሳይቆዩ ፍች የሚፈጽሙ ቤታቸውን የሚያፈርሱ እህቶች እጅግ ብዙ ናቸው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከአላህ ቀደር በታች ስለ ሰውየው ባህሪ በደንብ ካለማወቅ የመጣ ነው።
✍ Ibnu Seid ወንድማችሁ
t.me/dinhhiwothnew
ግን ለምን በዚህ መጠን?
~
ሰው ግን ወላሂ በጣም የሚገርም ሆኗል። ቁም ነገር ላይ የመጨረሻ ዳተኛ ነው። የሌሎችን አጀንዳ ለመቀበል፣ እንቶ ፈንቶ ለማራገብ ግን አንደኛ!
* ወደ ተውሒድ የሚጣሩ፣ ከሺርክና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ ስራዎች ገበያ የላቸውም።
* ሰዎችን ከአክ 'ፍሮተ- ኃይሎች ለማትረፍ ያቅማቸውን ተፍ ተፍ የሚሉ ዱዓት ስራዎች ይሄ ነው የሚባል የሚያሰራጫቸው የለም።
* ስለ ኢስላማዊ አደቦች የሚሰጡ ትምህርቶች ቦታ የሚሰጣቸው የለም።
* ሌላው ቀርቶ የቤተሰብ የአፋልጉኝ ጥሪ እንኳ ሰሚ አጥቷልኮ። አላህን ማሰብ የለ! በሰው ጭንቀት መጨነቅ የለ! ነግ በኔ የለ! ምን አይነት ድንዛዜ ላይ ነው የደረስነው? እንዲያው ልጅ፣ መኪና፣... ጠፍቶባችሁ ተጨንቃችሁ "አፋልጉን" ያላችሁ እንኳ ጭንቀቱን አይታችሁታል። ምናለ እናንተ እንኳ ለየት ብትሉ?!
ከእንዲህ አይነቶቹ አሳሳቢ ጉዳዮች ይልቅ
- የሆኑ ዱዓቶች ላይ ፀያፍ ነገር ሲታይ ወይም ሲሰማ ያለ ምንም ጥንቃቄ ሁሉንም በጅምላ ለማጠልሸት የሚታየው ርብርብ የሚገርም ነው።
- ኦሮሞ ተሰደብ፣ አማራ ተወገዘ፣ ትግሬ ተነካ፣ ... ሲባል እጁንም ምላሱንም እሾህ አድርጎ ሁሉን በጅምላ ሊወጋ የሚዘምተው እልፍ ነው። አስመሳይ የዘር ነጋዴዎች!
- የወንዙ፣ የመንደሩ ወሬ ሲነሳለት ለእስክሳ የሚነሳውም ለጉድ ነው። ሐራም ነገር ሁሉ በዘር በብሄራችን ስም ሲቀርብ ልናወግዘው ቀርቶ ደጋፊ ሆነን እንሰለፋለን።
- በማይረቡ ጉዳዮች የአጀንዳ ፍርፋሪ ሲወረወርለት የሚያራግበውም መዓት ነው።
ብቻ ያሳዝናል!
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
#ኢኽላስ ማለት በአላህና በባሪያው መካከል ያለ መለይካው አውቆ ሊጽፈው የማይችል እና ሸይጧንም ሊያበላሸው የማይችል ሚስጥር ነው » جنيد رحمه الله تعالى
]مدارج السالكين ٢ / ٩٢]
t.me/dinhhiwothnew
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
~
ሐጅ የኢስላም ልዩ መስህብ የሚሰተዋልበት፣ ድንቅ የአላህ ተዐምር የሚታይበት፣ የተውሒድ ነፀብራቅ ጎልቶ የሚነግስበት፣ ባእድ አምልኮ ከፍ ባለ ድምፅ ባደባባይ የሚወገዝበት ድንቅ ስርአት ነው። ሴት ወንዱ፣ ነጭ ጥቁሩ፣ መሪው ተመሪው በተመሳሳይ ቦታ እኩል ለአላህ የሚሰለፍበት ትንግርት። ሐጅ - አምስተኛው የኢስላም ምሰሶ።
በሐጅ "በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትእዛዝ ተጣራ" ለሚለው የአላህ ጥሪ “ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ፣…” /አቤት ጌታችን ሆይ አቤት፣ አቤት ጥሪህን ተቀብለን መጥተናል/” እያሉ መልስ በመስጠት ሚሊዮኖች ይተማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ “ከአላህ ሀገራት ሁሉ ይበልጥ አላህ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ከአላህ ሀገራት ሁሉም እኔ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ህዝቦችሽ ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ አልወጣም ነበር” የሚለውን የነብዩን ﷺ የቁጭት ንግግር፣ አሜኬላ የበዛበት ህይወታቸውን ልበዎ በሀዘን እየተከፈለ ያስታውሳሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ አስራ አራት ክፍለ-ዘመናት ወደ ኋላ አጠንጥነው የተውሒድ ጮራ ሲፈነጥቅ በአይነ-ህሊናዎ ይመለከታሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የመካ ሙሽ - ሪኮችን ለከት የለሽ ጭካኔና የነዚያን ፈርጥ የሆኑ ሰሐቦች ከብረት የጠነከረ ፅናት እያሰቡ በትዝታ ይነጉዳሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የነ ቢላልን ስቃይ፣ የነ ሱመያን የጣር ድምፅ አይነዎ እንባ እያቀረረ በሰመመን ያያሉ። ልበዎ በቁጭት እየደማ ይሰማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የአላህ የመጀመሪያ ቤት አለ - የሙስሊሞች ቂብላ፣ ከአለም ሁሉ ምርጡ ቦታ፣ መካ።
إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِلْعَالَمِينَ (96) فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا
"በርግጥም ለሰው ዘር (መፀለያ) ሆኖ መጀመሪያ (ምድር ላይ) የተኖረው ቤት ያ በበካህ (በመካ) ያለው የተባረከና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ የሆነው ነው። በውስጡ (እንደ) የኢብራሒም መቆሚያ (ያሉ) ግልፅ የኾኑ ተዓምራቶች አልሉ። ወደ ውስጡ የገባም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል።" [ኣሊ ዒምራን፡ 96]
- መስጂደል ሐራም መጤው ካገሬው እኩል የሚሆንበት ተአምራዊ ቦታ። የተውሒድ ቦታ፣ የእዝነት ቦታ። የኢብራሂም፣ የሐጀር፣ የኢስማዒል ትዝታ።
- መስጂደል ሐራም በረከት የበዛበት፣ ሰላም የሰፈነበት፣ እዝነት የነገሰበት፣ ተውሒድ የፈነጠቀበት ቅዱስ ቦታ።
- መስጂደ ልሐራም ልቦች ዘወትር የሚናፍቁት፣ አይኖች አይተውት የማይጠግቡት፣ ያላዩት ሊያዩት የሚቋምጡት ድንቅ ቦታ።
- መስጂደል ሐራም! “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” የሚለው ሀገርኛ ብሂል ፉርሽ የሚሆንበት ልዩ መስህብ። ለካስ ይናፍቃል! ደካማ አዛውንቶች በሽተኞች ሳይቀሩ ህመም ድካማቸውን ረስተው፣ ስቃይ እንግልቱን ዘንግተው፣ ባላዩት ሀገር ናፍቆት ተብሰክስከው፣ እልፍ አእላፍ ማይሎችን አቋርጠው ይተማሉ።
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَنْ لَا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
"ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ “በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ሩኩዕ ሱጁድ ለሚያበዙት ንፁህ አድርግላቸው” (ባልነው ጊዜ አስታውስ)።" [አልሐጅ፡ 26]
ከዕባ፣ ሐጀረል አስወድ፣ መቃም ኢብራሂም፣ ሶፋና መርዋ፣ ሚና፣ ዐረፋ፣ ሙዝደሊፋ፣… የሙስሊሞችን ቀልብ የሚማርኩ ልዩ የዒባዳ አውድማዎች ናቸው። ተልቢያ፣ ጦዋፍ፣ ሶላት፣ ዱዐ፣ እርድ፣ የጠጠር ውርወራ፣… ለፈፀማቸው ቀርቶ ለተነገረው የሚያጓጉ ሐጅ ላይ የሚፈፀሙ፤ ተቅዋን የሚያላብሱ የዚያኛው ዓለም ስንቆች ናቸው። (ذَلِكَ وَمَنْ يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِنْ تَقْوَى الْقُلُوبِ)
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ አላህ አድሎት የተዋጣለት ሐጅ ያደረገ እናቱ ስትወልደው እንደነበረው እንደ ህፃንነቱ ከወንጀል ሙሉ በሙሉ እንደሚፀዳ ነው መልእክተኛው ﷺ ያመላከቱት። በሐጅ ልቦች በኢማን ይታደሳሉ፣ አማኞች ከወንድሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ደካሞች ይታገዛሉ፣ ሙስሊሞች ከቅዱሱ ስፋራ፣ ከበረሃው፣ ከሐጁ ስርአት፣ ከተዳሚው ሁኔታ፣ ከዚያ የሚሊዮኖች ስብሰባ ብዙ ተፈኩር ይወስዳሉ።
አላህ አድሎት የሐጅ ስነ-ስርኣት ላይ ለተካፈለ ሰው ልብሳቸው የበሰበሰ፣ ሰውነታቸው የኮሰሰ፣ ኑሮ ያጎሳቆላቸው ስንት አይነት ሰዎችን ከተለያዩ የአለም አፅናፋት ታድመው ይመለከታል። አንዳንዶቹ ለዘመናት አጠራቅመው ለዚህ ስኬት እንደበቁ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ። በተሽከርካሪ ወንበር የሚገፉ፣ በጀርባ የታዘሉ አዛውንቶችን ሲመለከቱ፣ አቅሙም ጤናውም ተሟልቶ ከሐጅ ስለቀረው ወገን በእጅጉ ያዝናሉ። ሐጅ የወጀበባችሁ ወገኖቼ ሆይ! ጤናን አቅምን ያደላችሁ ጌታ፣ ሐጅን ግዴታ አድርጎባችኋል። ወንድሞቼ እህቶቼ፣ አባቶቼ እናቶቼ ሆይ! ለአላማ እንደተፈጠራችሁ አትዘንጉ። የተሰጣችሁ ገንዘብ ያንን አላማ ማሳኪያ እንጂ መጎረሪያም መባከኛም አይደለም። ሐጁን ብትፈፅሙት ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። ወንጀላችሁ ይረግፋል፣ ልባችሁ ይፀዳል፤ የዒባዳ ወኔያችሁ ይነሳሳል። እመኑኝ አንዴ ቆርጣችሁ ከፈፀማችሁት በያመቱ ገና ጊዜው ሲቃረብ ነው ልባችሁ የሚቆመው። “ወዴት” እንዳትሉኝ። ወላሂ ስንቶች ናቸው ሐጅ አጠናቀው መካን ሲለቁ፣ በእንባ የሚታጠቡት! ባትፈፅሙትስ ማነው የሚጎዳው? በርግጠኝነት አላህ ምንም አይቀርበትም! መቼስ ከሚታረደው እርድ አይደርሰው ነገር! ያበላል እንጂ አይበላምና። ከፍጡር ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነውና።
وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
"ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው።" [ኣሊ ዒምራን: 97]
ዱዓቶች ሆይ ሰዎችን ቀስቅሱ። አላህ የጣለባችሁን ሀላፊነት አድርሱ። ተሳክቶላችሁ በናንተ ሰበብ አንድ ሰው ለሐጅ ቆርጦ ቢነሳ የሚኖራችሁን አጅር አስታውሱ። ወገን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ተመልከት። ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት ብዙ ሐጅ ያላደረጉትን ፍቀድ። ዘንድሮ ባይደርስ ለቀጣይ አስታውስ። "አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና።" [አዛሪያት፡ 55]
ባይሆን አደራ!
ለሐጅ ቆርጠው ከተነሱ፡- በሚገባ ይዘጋጁ። ስለሐጅ ይጠይቁ፣ ይወቁ፣ ያንብቡ፣ የሚያነቡትም ይያዙ። ከተቻለም ቀድሞ ሐጅ ያደረገ የዲን ግንዛቤ ያለው ሰው ጓደኛ ማድረገዎን አይርሱ።
"ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)" ይላሉ ነብዩ ﷺ።
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ
ኢነል ሐምደ
ወኒዕመተ
ለከ ወልሙልክ
ላሸሪከ ለክ!
.
ያ ረሕማኑ ቤትህን ለመጎብኘት አንተ ወፍቀን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 3/2006)
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ኒቃብ (አይነ ርግብ) መልበስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው
~
ብዙ ክርስቲያኖች የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ (በተለይም ኒቃብን) የዐረብ ባህል እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ። በመሰረቱ የፈረንጅ ባህል ተከትለው ሴቶች ሱሪ ከሚለብሱበት ባህል የዐረብ ባህል ቢሆን እንኳ ግብረ ገብነትን የሚጠቁመው አለባበስ የተሻለ ስርአት ያለው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ የማርያም ምስል ነው ብለው ክርስቲያኖች በሚገልፁት ምስል ላይ ያለው አለባበስ ሙስሊሞች ዘንድ እንጂ ክርስቲያኖች ዘንድ የለም። ለምን የሚለውን ክርስቲያኖች ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው።
ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ሙስሊሞች የሚያራምዷቸው መርሆዎች - ፊት መሸፈንን ጨምሮ - በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ሊያውቁ ይገባል። ብዙ ክርስቲያኖች ለመፅሀፋቸው ባይተዋር ስለሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እጠቅሳለሁ፦
1- በኢስላም በሴት የሚመሳሰል ወንድ እና በወንድ የምትመሳሰል ሴት የተረገሙ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]
2- ሴት ፀጉሯን እንድትሸፍን ኢስላም በጥብቅ ያዛል። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል? ይሄውና :- "ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]
3- ሴት ፊቷን መሸፈኗ በኢስላም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሐቅ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስስ የለም? በሚገባ አለ። ይሄውና፦
* "ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። ሎሌውም፦ እርሱ ጌታዬ ነው አላት እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ #ተከናነበች።" [ዘፍጥረት 24፣ 64- 65]
* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]
ልብ በሉ! አይነ ርግብ ማለት ኒቃብ ወይም የፊት መሸፈኛ ነው።
* "ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።" መሀልየ ዘሠለሞን 5፡6]
* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1]
ስለዚህ ሙስሊም ሴቶች እየተገበሩት ያሉት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን እውነት ነው ማለት ነው። ለምንድነው ታዲያ ይሄ ጉዳይ ክርስቲያኖችን የሚያበሳጨው? ከሙስሊም ሴቶች ጎን መቆም ሲገባ ጭራሽ ማንገላታትና ከትምህርት ገበታ ማራቅ ፈፅሞ የማይገባ ነውረኛ ተግባር ነው።
ደግሞም እወቁ! ብዙ ጭቆናዎች በሂደት እንደተቀየሩት ይሄም ያለ ጥርጥር ዛሬ ወይም ነገ ይቀየራል። ለትውልድ የሚቀረው የናንተ የጭቆና ታሪክ ነው። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስማችሁ እንዲቀር ነው የምትፈልጉት? ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።
* ባያያዝኩት ምስል ላይ ፊታቸውን ሸፍነው የሚታዩት ሙስሊሞች አይደሉም። ይልቁንም አይሁዶች ናቸው። የሙስሊም ሲሆን ሁሉ ነገር ለሚያስጨንቃቸው አካላት ማስታገሻ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ዛሬ ምሽት ረመዷን 27ኛው ለይል ላይ እንገኛል። ይህ ለይል ለይለተል ቀድር ይሆናል ተብሎ እጅግ ተስፋ የሚጣልበት ለይል ስለሆነ ለሊቱን በሶላት በዚክር በዱዓእ በእስቲግፋር ቁርኣን በመቅራት ልናሳልፈው ይገባል ።
ከምናደርገው ዱዓእ ውስጥ ነብያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) ያስተማሯትን ዱዓእ ቢሆን ጥሩ ነው
ይሄውም፦
اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني
አሏሁመ ኢነከ ዐፉውን ቱሒቡል'ዐፉወ ፋዕፉ ዐኒ
👇👇
ጌታዬ ሆይ ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ
🤘🤘
ማለት ነው ትርጉሙ
ይህን ማለት የማይችል በሚያውቀው ቋንቋ የፈለገውን ማለት ይችላል
እንበርታ ወንድሞቼና እህቶቼ
አሏህ ለይለተል ቀዲርን ይወፍቀን !!
t.me/dinhhiwothnew
ረመዷን የመጨረሻው ውስን ቀናቶች ውስጥ ነን ይህን ዱዓ እናብዛ
" اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني "
" አሏሁመ ኢነከ አፉውን ቱሂቡል ዓፍወ ፈዓፉወ ዐኒ "
አላህ ሆይ አተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ይቅር በለኝ!
t.me/Kunizewjeten2
አላህ ይሁነን!
~
አልኢማም አልአውዛዒይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
" 'የማያሙ፣ የማይመቀኙ እና የማይጠሉ ሰዎች የሚኖሩበት የሆነን ቤት መጎራበት እፈልጋለሁ' በማለት አንድን ሰው ጠየቅኩት።
ከዚያ ሰውየው ወደ መቃብር ወሰደኝና 'ይሄው እዚህ አሉልህ' አለኝ።"
📖 [ጃሚዑል ዑሉም ወልሒከም፡ 2/182]
Ibnu Munewor
=
* የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ٰ 🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹 👈አበባውን
🌹🌹🌹🌹🌹 በመንካት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ብቻ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የሚያመጣው
🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🍀
🌹🌹🌹🌹🌹 add 🌷
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿 🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
+add የሱና ቻናል_የሚለው_በመጫን በጣም_ጠቃሚ _ነገር ትገኛላችሁ
خرج أبو بكر رضي الله عنه صبيحة الإثنين 12 ربيع الأول سنة11هجري وقال: مات #رسول_الله_ﷺ فأظلمت الدنيا على المسلمين ،
فبماذا ستحتفلون !
t.me/Kunizewjeten2
የመውሊድን ቢድዓእነት ለማስረዳት ብሽሽቅ ውስጥ መግባት፣ይበልጥ ወደ ሽርክና ቢድዓእ ሊያስገባቸው የሚችል ቃላትን መጠቀም አግባብ አደለም።አላማችን ስህተት ላይ ያሉ ወንድምና እህቶቻችን ለመመለስ ከሆነ ቅድሚያ የምናስተምረውንና የምናስረዳውን ሰውዬ ሁኔታ ማወቅ ቢቀድም ጥሩ ነው። ለጥቅል አክባሪዎቹም ከሆነ ቅድሚያ ጥበብን ተጠቅሞ እውነታውን ማስተማርና ማድረስ ነው ከእኛ የሚጠበቀው።
ቢድዓእነቱ እንደት እንደሆነ ቀድሞ ሳያስተምሩ
« መውሊድ የሆዳሞች በዓል ነው» ዓይነት መልእክቶችን ማሰራጨት ሰዎችን ካሉበት መንገድ አይቀይራቸውም፤ እንዳውም በእልህ ተነሳስተው ጥፋታቸውን ይጨምራሉ። ስለሆነም ለሰዎች እንዘንና እውነታውን አቅማችን በፈቀደው ልክ እናስታውሳቸው፣እንምከራቸው !
« አንድ ሰው በአንተ ምክንያት ቢመራልህ ( እውነታውን አውቆ ቢከተል) ከቀይ ግመል የበለጠ ነው »የሚል መልእክት ከነብያችን ለዐልይ ቢን አቢ'ጧሊብ ተላልፏልና
ለሰዎች እውነታን ለማስረዳት እንትጋ !
✍Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
በሐቅ መንገድ እስከጸናህ ፈተና አይቀሬ ነው !!
ታሪክን ወደኋላ ብታገላብጥ የትኛውም ሰው ለአላህ ድን በሐቅ ላይ እስከቆመ ድረስ ችግር/ፈተና ያገኘዋል ።
__ __
قال ابن عثيمين رحمه الله:
فتش في التاريخ ، ما من إِنسان قَام لله - عز وجل - بحقٍّ إِلّا وجد أَذى.
شرح الكافية الشافية ٣ / ٢٧٠
___
የመጀመሪያዎቹ ፈተናን ቀማሾች የአላህ ነብያቶችና መልእክተኞች ናቸው። እውነተኞች ታማኞች አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች በመሆናቸው አማካኝነት ብዙ መከራዎችን ከህዝቦቻቸው ከቤተሰብና ከጎሳዎቻቸው አስተናግደዋል ቢሆንም ግን ከአቋማቸው ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። አንተም በሐቅ ላይ እስካለህና እስከጸናህ ድረስ እንደ ኢማንህ ልክ ፈተናን ማስተናገድህ አይቀሬ ነው በያዝከው ሐቅ ላይ ጽና !! ✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
ይቅርብህ!
~
ስለ ትግራይ ፖለቲካ ቢነሳ ትግሬ ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል። ስለ አማራ ፖለቲካ ቢወራ አማራው ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል። ስለ ኦሮሞ ፖለቲካ ቢወራ ኦሮሞው ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል።
ወንድሜ ሆይ! የፖለቲከኛ ድስኩር ተከትለህ ጥላቻ አትዝራ። በኣኺራ ታምን የለ? ለነሱ በስባሳ ፖለቲካ ብለህ ኣኺራህን አታጨልም። ዘረኝነት ውስጥ አትግባ።
ወንድሜ የነሱ ፖለቲካ ለድሃው ህዝብ ጠብ የሚያደርገው ላይኖር ህይወትን ያክል ውድ ነገር አትገብር። የኢኮኖሚውን ኪሳራ፣ ማህበራዊ ውጥንቅጡን፣ የህሊና ጠባሳውን ትተነው ይሄው ሚሊዮን የሚገመት ወጣት ረገፈ። እስኪ ከዚህ ሁሉ መአት በኋላ ዛሬ ላይ እንደ ህዝብ ያተረፍነውን ንገረኝ። እንዲሁ ካንድ መከራ ወደ ሌላ መከራ መገላበጥ ብቻ። የፈተና አዙሪት።
አሁንም በዱር በገደሉ ያለህ፣ "በለው ውገረው" የምትል ሁሉ እቅጩውን እወቀው! በሞትህ አትፀድቅም። ባንተ ሞት እናትህ ቤት ሃዘን እንጂ ደስታ አይገባም። ሌላው ቀርቶ የትግል አጋሮችህ ሳይቀሩ የፖለቲካው አሰላለፍ ሲቀየር "ቅዱስ" ሞትህን "አላማ ቢስ እልቂት" ብለው ያራክሱታል። እናትህ ያለ ልጅ፣ ልጆችህ ያለ አባት ቀርተው ሜዳ ላይ ሲወድቁ አታጋዮችህ በትልልቅ ሆቴሎች ውስኪ ይራጫሉ። እና ለማን ነው የምትሞተው?! እኮ ለምን?
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
የተጠናቀቁ ዱሩሶች ስብስብ!
------------------------------------
በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ተቀርተው ተጠናቀው የተለቀቁ ዱሩሶችን እነዚህን ሊንኮች በመጫን በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
1, "አድ'ዱሩሱል ሙሂማህ | الدروس المهمة"
/channel/SheikhMuhammedZain/762
2, "ኡሱሉ'ሱንናህ | أصول السنة"
/channel/SheikhMuhammedZain/755
3, "ሸርሑ ከሽፊ' ሹቡሀት | شرح كشف الشبهات"
/channel/SheikhMuhammedZain/970
4, "ሸርሑ መሳኢሊል ጃሂሊያህ | شرح مسائل الجاهلية"
/channel/SheikhMuhammedZain/994
5, "ሸርሑ ዐቂደቲ 'ጠሐዊያህ | شرح عقيدة الطحاوية"
/channel/SheikhMuhammedZain/775
6, "ኡሱሉን'ፊ ተፋሲር | أصول في التفسير"
/channel/SheikhMuhammedZain/912
7, "አር'ረሒቁል መኽቱም | الرحيق المختوم"
/channel/SheikhMuhammedZain/548
8, "ሙልሐቱል' ኢዕራብ | ملحة اﻹعراب"
/channel/SheikhMuhammedZain/150
9, "ከሽፉ'ኒቃብ | كشف النقاب"
/channel/SheikhMuhammedZain/662
10, "አል'ፈዎኪሁል ጀንያህ | الفواكه الجنية"
/channel/SheikhMuhammedZain/224
11، "አል'ፈዎኪሁል ጀንያህ | الفواكه الجنية"
/channel/SheikhMuhammedZain/1084
12, "ሙዘኪራ ፊ አሕካሚ አስ-ሲያም" | مذكرة في أحكام الصيام
/channel/SheikhMuhammedZain/1255
13, "ሸርሑ ኡሱሊ አስ-ሱና" | شرح أصول السنة
/channel/SheikhMuhammedZain/1281
14, "ደዓኢሙ ሚኒሃጂ ኑቡዋህ | دعائم منهاج النبوة" /channel/SheikhMuhammedZain/1310
📍የሸይኹን የተጠናቀቁ ዱሩሶችን ለማግኝት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ↓↓↓
/channel/SheikhMuhammedZain♦️የቴሌግራም አድራሻች
ንን ጆይን ያድርጉ፦https://t.me/joinchat/AAAAAEPAmExFhLDgAQXMeg
የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመሸጥ የሞትተዳደሩ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፣
በምትሸጡ ግዜ እውነተኞች ሁኑ ! ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለን ስልክ፣ ታብሌት ... በአዲስ ስም ፣ ባልሠራ ሒሳብ ከመሸጥ ታቀቡ ! አሏህን ፍሩ ! ላመኗችሁ ታማኞች ሁኑ! የዱንያ ሸቀጥን ፣ ጠፊ ገንዘብን ለመሰብሰብ ሲባል እምነታችሁንና ክብራችሁን ለአደጋ አታጋልጡ
በውሸትና በማጭበርበር የሚገኝ ገንዘብ ዕረፍትን የሚነሣ ከመሆኑ ጋር የፍርዱ ቀን ደግሞ ኪሣራን ያሸክማል .. አሏህ ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋልና ተጠንቀቁ ! አሏህን ፍሩ!
ኢማምነትና ኸጢብነት ሸሪዐዊ ሃላፊነቶች ናቸው። በሸሪዐዊ ሃላፊነት ላይ በአግባቡ አማናን መወጣት ይገባል። የራስን ፍላጎት ብቻ ከመከተል ይልቅ ሰፊውን ተገልጋይ ማሰብ ይገባል። ስላሰኘህ ብቻ ማስረዘም፣ ስለ ታከተህ ብቻ ማሳጠር ተገቢ አይደለም። ኢማም ወይም ኸጢብ የሆነ ሰው አቅመ ደካሞችን፣ ባለ ጉዳዮችን፣ ህመምተኞችን፣ አዛውንቶችን፣ ፀሐይ ወይም ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆችን ወይም አድማጮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት። ነብያችንኮ ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሰምተው እናቱ እንዳትረበሽ በሚል ሶላት ያሳጥሩ ነበር።
ልክ እንዲሁ በኸጢቦች የሚነሱ ርእሶችም ማህበረሰቡ ያለበትን ሁኔታ ወይም ወቅታዊ ጉዳዮችን የዘነጉ መሆን የለባቸውም። ረመዷን ላይ አብዛኛው ደዕዋ ስለ ረመዷን ነበር። ይሄ ጥሩ ነው። ነገር ግን በዘረኝነት ስንታመስ፣ በሱስ ስንወረር፣ ነጋዴው መሀል ማጭበርበርና መካካድ ሲንሰራፋ፣ መጨካከን ሲበዛ፣ ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ ... ዱዓቶችና ኸጢቦች ጭልጥ ብለው ሌላ አለም ውስጥ ሊሆኑ አይገባም። አስተማሪ ማለት ልክ እንደ ሃኪም ነው። ሃኪም የውስጥ ደዌ ለማከም የቆዳ መድሃኒት አይሰጥም። ልክ እንዲሁ ለወገኑ ተቆርቋሪ የሆነ ዳዒያህ ማለት ህዝቡ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እያየ ተገቢውን ህክምና የሚሰጥ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
የስድስቶን ፆም የምትፆሙ እህትና ወንድሞች
ሰኞና ሐሙስ አብረው ከገጠሙ የስድስቶንም የሰኞና የሐሙስን ሱና ፆሞች በጋራ ነይታችሁ ብትፆሙ የሁለቱንም አጅር ታገኛላችሁ ኢን'ሻ አሏህ !
http://t.me/dinhhiwothnew
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
ከረመዷን በፊት ወደነበርክበት አመፅና ወንጀል ለመመለስ በማኮብኮብ ላይ ያለህ ወንድሜ ሆይ ! አላህን ፍራ! የረመዳኑ ጌታ የተቀሩት ወራቶችም ጌታ ነው ... አሏህን ፍራ!
ፈጣሪህን በመፍራት የታዘዝከው በዚህ ወር ብቻ አይደለም ... ከፀያፍ ነገሮች መራቅ የእድሜ ልክ ግብ እንጂ የአንድ ወር አላማ አይደለም !
ሁሌም ለአላህ እጅ የሰጠህ ሙስሊም ለመሆን ታገል ...
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
/channel/Muhammedsirage
አሏህ ሙስሊሙን ማሕበረሰብ በተውሒድና በሱናህ አንድ እንዳደርገን ፣የዱንያ አኼራችን ህይወት እንዳምርልን፣ ወደ አኼራ ለቀደሙን አማኞች ከአሏህ ምህረትን፣ አገራችን ሰላም የሰፈነባት የተረጋጋች አገር እንድትሆን፣ ግ*ፈኞ*ች ፓለቲከኞች እና በዳ*ዮችም የእጃቸውን እንዳገኙ ... አላህን እንለምን !!
t.me/dinhhiwothnew
ቁርኣንን ያለ ጦሀራ (ያለ ውዱእ / ትጥበት) መንካት ይቻላልን?
~
ቁርኣንን ያለ ጦሀራ መንካት አይቻልም የሚለው የአራቱም የፊቅህ መዝሀቦች አቋም ነው። አልፎም ባጠቃላይ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። መረጃ የሚደግፈውም ይህንኑ ነው። ሁለት መረጃዎችን እጠቅሳለሁ:-
♻️ [መረጃ አንድ]:- ሐዲሣዊ ማስረጃ ♻️
ነብያችን ﷺ ወደ የመን በላኩት ደብዳቤ ላይ
أَنْ لَا يَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا طَاهِرٌ
"ቁርኣንን ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው" ሲሉ አሳስበዋል። [ሙወጦእ: 468] ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ "ሶሒሕ" ብለውታል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7780]
👉🏾 ብዥታ!
~
ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት ይቻላል የሚሉ ዓሊሞች ግን "የሐዲሡ መልእክት ሌላ ነው። 'ጦሀራ የሆነ እንጂ እንዳይነካው' ማለት 'ሙስሊም እንጂ እንዳይነካው' ማለት ነው" ይላሉ። ለዚህም "ሙስሊም አይንነጀስም" የሚለውን ሐዲሥ ያጣቅሳሉ።
ይሄ ግን - ወላሁ አዕለም - ልክ አይደለም። ይልቁንም መልእክቱ በቀጥታ ጦሀራ የሌለው ሰው እንዳይነካው ማለት ነው። የሐዲሡ ሌሎች ዘገባዎች ይህንን መልእክት ግልፅ ያደርጉልናል። ለምሳሌ:-
✅ 1ኛ፦ የዐብዱረዛቅ ዘገባ ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا يُمَسُّ الْقُرْآنُ إِلَّا على طُهْرٍ
"በጦሀራ ላይ ተሁኖ እንጂ ቁርኣን አይንነካም።" [አልሙሶነፍ: ቁ. 1328]
✅ 2ኛ:- የኢብኑል ሙንዚር ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
لَا تَمَسَّ الْقُرْآنَ إِلَّا على طَهورٍ
"በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣን እንዳትነካ።" [አልአውሰጥ፡ 2/103]
▶️ ልብ በሉ! ሙስሊሙን ሰው ነው "በጦሀራ ላይ ሆነህ እንጂ ቁርኣንን እንዳትነካ" ያሉት። ይህም ሐዲሡን "ሙስሊም ያልሆነ እንዳይነካው ማለት ነው" በማለት የተረጎሙት ልክ እንዳልሆኑ ያሳያል።
♻️ [መረጃ ሁለት]:- ቁርኣናዊ ማስረጃ ♻️
በቁርኣን ውስጥም እንዲህ የሚል መጥቷል:-
{ لَّا یَمَسُّهُۥۤ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ }
"የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም።" [አልዋቒዐህ፡ 79]
በርግጥ የዚች አንቀፅ ቀጥተኛ መልእክት ጥብቁን ሰሌዳ (ለውሐል መሕፉዝን) የሚገልፅ እንደሆነ አገባቡ ያሳያል። ይሁን እንጂ መልእክቱ ለቁርኣንም የሚውል እንደሆነ ጥቆማ አለው ይላሉ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [ሸርሑል ዑምደህ: 384]
ይህንን ሃሳብ የሚደግፍ አንድ የሶሐቢይ ንግግር ልጥቀስ። ሶሐቢዩ ሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ናቸው። ዐብዱረሕማን ብኑ የዚድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"ከሰልማን ጋር በሆነ ጉዳይ ላይ ነበርን። እሳቸው ጉዳያቸውን ለመፈፀም (ለመፀዳዳት) ሄደው ተመለሱ። 'ውዱእ አድርግማ የዐብደላህ አባት! ምናልባት ከቁርኣን ስለሆኑ አንቀፆች ልንጠይቅህ እንችላለን' አልናቸው። በዚህን ጊዜ (ሰልማን) እንዲህ አሉ፦
فَاسْأَلُوا، فَإِنِّي لَا أَمَسُّهُ، إِنَّهُ {لَا يَمَسُّهُ إِلَّا الْمُطَهَّرُونَ}
'ጠይቁ! እኔ አልነካውም። ነገሩ {የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም}።' "
ከዚያም "ጠየቅናቸው። ውዱእ ሳያደርጉ ቀሩልን" አሉ። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ ቁ. 1100]
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት ጦሀራ የሌለው ሰው ቁርኣንን ሊነካ አይገባም የሚለው የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ኢብኑ ዐብዲል በር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
أجمع فقهاء الأمصار الذين تدور عليهم الفتوى وعلى أصحابهم بأن المصحف لا يمسه إلا طاهر
"ጦሀራ ላይ የሆነ ካልሆነ በስተቀር ሙስሐፍ እንደማይንነካ ፈትዋ የሚቀርብላቸው የሙስሊም ሃገራት ሊቃውንት እና ባልደረቦቻቸው ወጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።" [አልኢስቲዝካር፡ 8/10] ከኢብኑ ሁበይራም በተመሳሳይ ኢጅማዕ እንዳለበት ተጠቅሷል። [አልኢፍሷሕ፡ 1/68]
ይሄ እንግዲህ እነሱ በሚያውቁት መጠን ነው። እንጂ ጥቂቶች ቢሆኑም የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቁ ተገኝተዋል። የሆነ ሆኖ ቁርኣንን ያለ ውዱእ መንካት አይቻልም የሚለው ከሶሐቦች ውስጥ ከ0ሊይ፣ ከሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ፣ ከኢብኑ ዑመር፣ ከሰልማኑል ፋሪሲይ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ተገኝቷል። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም ይላሉ ነወዊይ እና ኢብኑ ተይሚያህ - አላህ ይዘንላቸውና። [አልመጅሙዕ፡ 2/80] [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 21/266]
ይህንን ሃሳብ አስምሩበት። ከሶሐቦች ውስጥ እነዚህን የተቃረነ አይታወቅም። ስለዚህ ውዝግቡ የመጣው ከሶሓቦች በኋላ ነው ማለት ነው። አዋቂው አላህ ነው።
ማሳሰቢያ፦ ሞባይልና መሰል ዲቫይሶችን ተጠቅሞ መቅራት እዚህ ውስጥ አይገባም። እንዲሁም ትርጉምና የተፍሲር ኪታቦችም የሙስሐፍ ብይን የላቸውም። ስለዚህ ያለ ጦሀራ መንካት ይቻላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 21/1444፣ ሚያዚያ 04/2015)
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor