1 . ኪታቡ ተውሒድ1__76
t.me/IbnuMuneworcom/230
2.ሪያዱ ሷሊሂን 1__ 194
t.me/IbnuMuneworcom/317
3.ዶላሉ ጀማዐቲል አህባሽ 1_ 4
t.me/IbnuMuneworcom/161
4. አል አርበዑነ ነወዊያህ 1___ 50
t.me/IbnuMuneworcom/603
5 .ሽሩጡ ሶላት 1__7
t.me/IbnuMuneworcom/514
6.ሠላሠቱል_ኡሱል 1__11
t.me/IbnuMuneworcom/522
7. ሒስኑል ሙስሊም 1__22
t.me/IbnuMuneworcom/535
8. ላሚየቱ ብኒ ተይሚያህ 1_4
t.me/IbnuMuneworcom/559
9 .አል ቀዋዒዱል አርበዓ
t.me/IbnuMuneworcom/654
10 .ሓኢየቱ ብን አቢ ዳውድ
t.me/IbnuMuneworcom/657
11 . ሸርሑ ሱንና ሊል በርበሃሪ 1__37
t.me/IbnuMuneworcom/564
ሙሉ የድምፅ ፋይል ለማግኘት 👇
t.me/IbnuMuneworcom
ሸይኽ ኢብራሂም አልሙሐይሚድ እና ሰሞንኛው ግርግር
~
ሸይኽ ኢብራሂም አልሙሐይሚድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት በመዘዋወር በየገጠሩ በመግባት ደዕዋ በማድረግ፣ አቅመ ደካማ ሙስሊሞችን በመርዳት፣ መስጂዶችን በመገንባት የሚታወቁ ሸይኽ ናቸው። ሸይኽ ኢብራሂም ሰሞኑን ቂም ባረገዙ አካላት እየተብጠለጠሉ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በኢኽዋንና በኸ -ዋሪጅ ቡድን ቀድሞ የተያዘው ቂም በመኖሩ ነው። ያሁኑ መነሻ ሰበብ ብቻ ነው። ሸይኹ በሁለቱ አንጃዎች ላይ በጣም ከባድ ናቸው። በዚህ ዘመን በጂሃድ ስም የሚፈፀመውን የኸዋ -ሪጅ እንቅስቃሴ እርቃን ያስቀሩበት ኪታቦቻቸው ለዚህ ምስክር ናቸው።
ሰሞኑን ከሸይኽ ሳሊም አጦዊል ተገናኝተው ባስተማሩበት መድረክ ላይ ለቀረበላቸው አንድ ጥያቄ ምላሽ የሰጡበትን ቆርጠር በማቅረብ እያብጠለጠሏቸው ነው። በዚህ ውንጀላ ላይ ከታዋቂ ሰዎች እስከ ተራ ሰዎች ተካፍለውበታል። "የውመል ቂያማህ ስለሽንት ትጠየቃለህ። ሽንት ነጃሳ ስለመሆኑ፣ ነጃሳው ቢነካህ ስለማጽዳትህ ትጠየቃለህ። ስለፈለስጢን ግን አላህ በፍጹም አይጠይቅህም እያሉ ደዕዋ ያደርጋሉ" እያሉ በቡድንተኝነት ፈርጀዋቸዋል።
እነዚህ አካላት ራሳቸው በቡድንተኝነት የተለከፉ ናቸው። ለውንጀላ ያላቸው ጥማትም ነው ንግግር እየቆረጡ ያለ አውዱ እስከመተርጎም ያደረሳቸው። የሆነ ዓሊም "የጦሀራ ርዕስ በፊቅህ ኪታቦች መጀመሪያ ላይ እየተደረገ፣ የጂሃድ ርእስ መጨረሻ ላይ የሚደረገው ለምንድነው?" ተብሎ ሲጠየቅ ጦሀራ አስተካክሎ የማያደርገው ሁሉ እየተነሳ ስለ ጂሃድ እንዳይናገር ነው አለ። ዛሬም እያየን ያለነው ተጨባጭ ይሄ ነው። ይሄ ነው የሚባል ግንዛቤ የሌለው ጥራዝ ነጠቅ ሁሉ እየተነሳ ከሚዲያ በለቃቀመው እንቶ ፈንቶ ላይ ተመርኩዞ የሱና ዑለማኦችን ይዘረጥጣል። መሰረታዊ የዐቂዳ ጉዳይ ላይ የረባ ግንዛቤም ጥረትም የለውም። እንደ አሕ.ባሽ፣ ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ ተክ.ፊር፣ ሺ0 ያሉ አጥማሚ አንጃዎችን ጥሎ ሁሌ በሱና እንቅስቃሴ ላይ በተለየ አቃቂር በማውጣት ላይ የተጠመደበት ምክንያት ቢያንስ ከከፊሎቹ ጋር የሚጋራው በሽታ ስላለው ነው።
ሸይኽ ኢብራሂም "የጦሀራ እና ከሽንት የመጥራራትን ህግጋትን ካልተማርክ ቀብርህ ውስጥ ትቀጣለህ። ፈለስጢን ውስጥ የተከሰተውን ባታውቅ ግን አትቀጣም" ብለዋል። ጥያቄው ምን ነበር? በፍልስጤም ጉዳይ ቀድሞ በተከሰቱ ነገሮች ሳይማር አሁንም መስመር ስለለቀቀ ሰው ምን ትላላችሁ የሚል ነው። ንግግራቸው ዘለግ ያለ ነው። የጠላትን ዝርዝር ሴራ ማወቅ በጦለበተል ዒልም ግዴታ እንዳልሆነ ነው የጠቀሱት።
በዚህ ንግግር ውስጥ ምንድነው ስህተቱ? በስርአት ከሽንት የማይጥራራ ሰው በቀብር እንደሚቀጣ ግልፅ ሐዲሥ የመጣበት ጉዳይ ነው። ይሄ እያንዳንዱን ሙስሊም የሚመለከት ግዴታ ነው። የጠላትን ሴራ ማወቅስ በሁሉም ሙስሊም ላይ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው ወይ? በስሜት ከመጮህ ውጭ ማንም በዚህ ላይ መረጃ ማምጣት አይችልም። በፍልስጤምም ይሁን በሌሎች ሙስሊሞች ላይ ስለሚደርሰውና ስለ ጠላት ዝርዝር ሴራ በነፍስ ወከፍ ደረጃ ሳይሆን ከሙስሊሞች ውስጥ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ላይ ብቻ ነው ግዴታ የሚሆነው። ስለ መሰረታዊ የተክሊፍ ህግጋት የሚያውቅ ሰው ይሄ አይሰወረውም። የፖለቲካ ጉዳይ የሁሉም ሙስሊም ግዴታ እንዳልሆነ ሲበዛ ግልፅ ነው። "አይ በሁሉም ላይ ግዴታ ነው" የሚል ካለ የድፍን ዓለም ሙስሊሞችን ወንጀለኛ እያደረገ ነው።
አንድ ሰው በሆነ የዓለም ክፍል ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን ባለማወቁ ይቀጣል የሚል ካለ በድፍን ዓለም ሙስሊሞች ላይ እየደረሱ ያሉ በደሎችን ሁሉ ማወቅ ዋጂብ ነው እያለ ነው። ይሄ ከየት የመጣ ሙግት ነው? በቻይና የኢጉር ሙስሊሞች ላይ፣ በኢራን ሱኒዮች ላይ፣ ጋዛ ውስጥ በሐማስ ስለተጨፈጨፉ ሙስሊሞች፣ ወዘተ ምን ያህል ሰው ያውቃል? ይህንን ያላወቀ ሁሉ በቀብር ውስጥ ይቀጣል ልትሉ ነው? በኛ ሃገር ሙስሊሞች ላይ ስለሚደርሱ በደሎች የሌሎች ሃገራት ሙስሊሞች፣ ዑለማኦች ጭምር የሚያውቁ ቢኖሩ ከጥቂትም ያነሱ ናቸው። ይህንን ስላላወቁ ወንጀለኞች ናቸው ልትሉ ነው?
የነዚህ አካላት ተንኮል ግልፅ ነው። ፍላጎታቸው ሸይኽ ኢብራሂም የሙስሊሞችን ደም ጉዳይ ከጦሀራ ጉዳይ በታች አድርገው አራክሰዋል ለማለት ነው። ንግግራቸውን ቆርጠው ያቀረቡትም ሆነ ብለው እንዲህ አይነት ይዘት እንዲይዝ ነው። ሆነ ብለው ሙስሊሞችን ከመርዳት ግዴታ ጋር በማያያዝ ሸይኹ መርዳት አያስፈልግም እንዳሉ አድርገው እያቀረቡ ነው። ሙስሊሞችን መርዳት ዋጂብ ነው። ግን በማን ላይ? በሚችል ላይ እንጂ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ አይደለም። እነዚህ ከሳሾች ራሳቸው ለፍልስጤም ሙስሊሞች ያደረጉት እርዳታ የለምኮ። ያደረጉት በደማቸው መቆመር ነው። እንጂ ሸይኽ ኢብራሂም ሙስሊሞችን መርዳት አያስፈልግም አላሉም። እንዲያውም እዚያው ቦታ ላይ ኢስላምን በንግግርም ቢሆን እርዳ ብለዋል። እንዲያውም እዚያው ቦታ ላይ በፍልስጤም ሙስሊሞች ላይ በሚደርሰው የሚደሰት ካለ ኢማኑን ይፈትሽ ብለዋል።
ምናልባት በሌላ ተያያዥ ነጥብ ልመለስ እችላለሁ፣ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
/channel/DurusuLugetilArabia?livestream=914ab86942daca4634
ግቡ ሊጀመር ነው!!
/channel/DurusuLugetilArabia?livestream=914ab86942daca4634
/channel/DurusuLugetilArabia?livestream=914ab86942daca4634
/channel/DurusuLugetilArabia?livestream=914ab86942daca4634
የዓሹራን ፆም እንድንፆመው
አሏህ ከወፈቀን የዘንድሮው የዓሹራእ ዕለት የሚውለው ከነገ በኋላ ዕለተ ማክሰኞ ሐምሌ 09/2016 ነው።
ይህን ዕለት ማለትም የዓሹራእን አስረኛውን ቀን በፆም ማሳለፍ የአንድ ዓመት ወንጀልን ያስምራል።
ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንድህ ብለዋል
« የዓሹራእን ዕለት መፆም የአንድ ዓመት ወንጀልን ያስምራል፤
አስረኛውን ቀን ( ዓሹራእን )ብቻውን መፆም አይጠላም »
الفتاوى الكبر ى ٣٧٨/٥
መፆም የሚችል ዘጠነኛውን እና አስረኛውን ዕለት ቢፆም ይበልጥ ይወደድለታል። መፆም የማይችል ሰው ግን አስረኛውን ቀን ብቻ ቢፆም ጾሙ ትክክል ነው የአንድ ዓመት ወንጀሉም ይማርለታል ከተባለው ውስጥ ይካተታል።
አሏህ ለመፆም ይወፍቀን፣ተቀባይነትም ያለው ያድርግልን !
Ibnu Seid ✍
t.me/dinhhiwothnew
በሒጅራው አቆጣጠር ዛሬ
ዕለተ ቅዳሜ ሙሐረም 1/1/1446ዓ.ሂ.ነው
አድሱን ዓመት ምክንያት በማድረክ የምናከብረው ምንም ዓይነት በዓል ባይኖርም አሏህ ዓመቱን የሰላም የጤና የተቅዋ... እንዳደርግልን እንለምነዋለን !
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
ነገ ዙልሒጃህ ዘጠኝ የዓረፋህ ዕለት ነው። የነገውን ዕለት መፆም የሁለት ዓመት ወንጀልን ያስምራል።ስለዚህ አላህ ይወፍቀንና ለመፆም እንወስን።
ፆም ብቻ ሳይሆን ዱዓዎችም ተቀባይነት የሚያገኙበት ፣በቀኑ ክፍለ ጊዜም አሏህ ወደ ቅርቧ ሰማይ የሚወርድበት ታላቅ ዕለት ነው።በዚህ ዕለት የዱንያም የአኼራም ጉዳዮቻችንን ወደ ጌታችን የምናሰማበት የተከበረ ልዩ ቀን ነውና በቻልንው መጠን ጠንክረን በዒባዳህ እንድናሳልፍ። የምናውቅ ለማያውቁት በመተዋወስ በመልካም ነገር ላይ እንተባበር
አሏህ በመልካም ነገራቶች ላይ ያበርታን !
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew
እዚያ ጋ ሰው ይታየኛል!
~
"ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ … ሚዛን የሚደፋ
ለእውነት የሚቆም … ላገር የሚለፋ"
እላለሁ እንደ ሰው
ሆዴን ሆድ ሲብሰው።
"ሴት ይርመሰመሳል … ሚስት ነው የጠፋ"
እላለሁ አንዳንዴ
ወንዶችን ወክየ … ቆሜ ሳንቀላፋ።
"ወንድ ይተራመሳል … ግን ባሎች የታሉ?"
እያሉ 'ሚጮሁ … እልፍ ሴቶች አሉ።
ሰው ሁሉ ሰው አድዳኝ … በሆነበት ምድር
ሰው ያልተገኘበት … አለን አንዳች ምስጢር።
ገባኝ ገባኝ
ለካስ ሰው "ነፍ" ነው … "ሰው" ከሰው ለለየ
ክፉን ብቻ ሳይሆን … ጥሩውንም ላየ።
ለካስ ሚስቶች አሉ … ባል ሆኖ ለመጣ
ሐያእ ለሚገባው … ላልሆነ ፈጣጣ።
ለካስ ባል በሽ ነው … ባልነት ለገባት
እራሷን ረስታ እንጂ … ዞራ የዞረባት።
ምልከታ ከራስ ይጀምር!
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 16/2011)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
የሶስቱ የሱና ኡስታዞች የድምፅ ፋይልን በቀላሉ ለማግኘት ተስፈንጣሪው በመንካት ወደ ግሩፑ በመቀላቀል እና #ሼር_ሸር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድወ ያካፍሉ!!
#የድምፅ_ፋይል👇
t.me/Sadatcom1
t.me/IbnuMuneworcom
t.me/Muhammedsiragecom
የአረበኛ ቋንቋ ደርስ
ዘወትር 8:00 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር
ከሰኞ እስከ ሃሙስ!
ኪታቡ በውስጡ ነህው እና ሶርፍን በዋናነት የሚያተምር ሆኖ
1/አዳድስ ቃላቶን (vocabulary words)
2/የማንበብ ክህሎትን(reading skills)
3/የመናገር ክህሎትን(speaking skills)
4/ የዐረበኛ ቋንቋ ሰዋሰው(Arabic language Grammars
5/ የመፃፍ ክህሎት (writting skill)
እነዚህን አምስት ጥቅሞችን ያስጠቅመናል።
ኪታቡ pdf ቢኖረውም ኪታቡን መግዛት ግደታ ነው።
ኪታቡን ይዞ የሚከታተል እና የማይከታተል በጭራሽ እኩል አይጠቀምም።
ማታ በኢትዪ 4:00 /10:00
በመሊክ ኻሊድ ዩኒቨርሲቲ የሸሪዓ ተማሪ
በዚህ አመት ተመራቂ በሆነው
ወንድም
ዐብዱረዛቅ ድሌቦ ኑሪ
በአድስ መልኩ ዛሬ ማታ ይጀመራል,,
በኔት ምክንያት ስለተቋርባችሁ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን
======================
/channel/+WoKpxQu3y3Q3YjI8
ተለቋል ኒዕማነቱን አውቀን አሏህ ዘንድ የማያስጠይቅን መልካም ስራ እንስራበት!!
ብዙ ነገሮችን ኒዕማነታቸውን የምናውቀው ሲወገዱ ብቻ ነው።
አልሐምዱሊላህ ዐላ ኩሊ ሃሊን!!
ኪታቡ በውስጡ ነህው እና ሶርፍን በዋናነት የሚያተምር ሆኖ
1/አዳድስ ቃላቶን (vocabulary words)
2/የማንበብ ክህሎትን(reading skills)
3/የመናገር ክህሎትን(speaking skills)
4/ የዐረበኛ ቋንቋ ሰዋሰው(Arabic language Grammars
5/ የመፃፍ ክህሎት (writting skill)
እነዚህን አምስት ጥቅሞችን ያስጠቅመናል።
ኪታቡ pdf ቢኖረውም ኪታቡን መግዛት ግደታ ነው።
ኪታቡን ይዞ የሚከታተል እና የማይከታተል በጭራሽ እኩል አይጠቀምም።
ማታ በኢትዪ 4:00 /10:00
======================
/channel/+WoKpxQu3y3Q3YjI8
ሐላል የትዳር አጋሬ ነው በሚል ምክንያት በክላሳችሁ ብቻ የምትፈጽሙትን ጉዳይ በኢሞም ይሁን በዋትሳፕ በሌሎችም ፕላትፎርሞች የምትልኩ እህቶች ጥፋትንና ውርዴትን በፍላጎታችሁ እንደፈጸማችሁ እወቁት
ዛሬ ሃላሌ ብለሽ ሐፍረተ ገላሽን የላክሽለት ወንድ ነገ ጠላትሽ ሁኖ ገንዘብሽን በመቶሺዎች እንድትልኪለት ፣ደም እንድታለቅሽ፣የአዕምሮ ታማሚ እንድትሆኝ ነው የሚያደርግሽ።
እናም በጊዜያዊ ፍቅር ብቻ መውደቅሽን ሳይሆን ፍፃሜው የት ሊጥልሽ እንደሚችል አርቀሽ መመልከትን አትርሽ
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew