የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1,812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመውንና 849,896 መራጮች ድምፅ የሰጡበትን የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የውጤት ማዳመሩን ሥራ በዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሲያከናወን መቆየቱ ይታወቃል። በዛሬውም ዕለት ቦርዱ የውጤት የማመሳከሩንና የማዳመሩን ሥራ በማጠናቀቅ በዞን ደረጃ የጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።
ምርጫው በስድስቱ ዞኖች እና በአምስት ልዩ ወረዳዎች ስር እንደ ክልል በክላስተር መደራጀትን በመደገፍና ባለመደገፍ የተደረገ የህዝብ ውሳኔ ነው።
የወላይታ ዞን በክልልነት መደራጀት ላይ በርካቶች ህዝብ ውሳኔ እንዲደረግ ይፈልጉ ነበረ።
አሁን የክልሉ ህዝብ ውሳኔ በምስሉ እንደሚታየው በሆኗል።
በዓለም ጤና ከተማ 10ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ አንዲት የገጠር ወረዳ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች መገደላቸውን አሁን ዓለም ጤና ደውዬ አረጋግጬለሁ። የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው የሚበልጥ እንደሚሆን ገልጸውልኛል። ማንነትን መነሻ ያደረገውና በዋናነትም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ መከላከያ ደርሶ አከባቢውን ተቆጣጥሮታል። በቅርቡ እነዚህ የተገደሉትን ጨምሮ አብዛኞቹ የአከባቢው አርሶ አደሮች ለሚጠቀሙበት መሬት በያንዳንዳቸው 300ሺህ ብር ተጥሎባቸው ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በካሽ መክፈላቸውን ነግረውኛል። ከተገደሉት መሃል የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አባትና ሁለት ልጆቻቸው ይገኛሉ።
መሳይ መኮንን
ታዋቂው ሰዓሊ በጨካኞች እጅ ተገደለ🥲
ለማን አቤት እንበል!!!!!!!!
የሶስት ልጆች አባት የሆነው አመለሸጋው ሰዓሊ ሙልጌታ ገ/ኪዳን ህይወቱ በአሳዛኝ መልክ አለፈ!
=================================
(ይትባረክ ዋለልኝ)
"ይህንን መርዶ እንዴት ልመን? ከቀናቶች በፊት ስንት ጉዳዮችን ስንጨዋወት የነበረውን የአመለሸጋውንና የትሁቱን ወንድሜን ሞት ልቀበል? ዮናስ ታረቀኝ ደወለልኝና "ወንድማችን ሰዓሊ ሙልጌታ ገ/ኪዳን ሕይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፎል።"ብሎ ነገረኝ።ይህን መርዶ ማመን አቃተኝ።የሞቱን ምክንያት ስሰማ ደግሞ ሰውነቴ ሁሉ ነው በንዴት የተንቀጠቀጠው።ሐገር ሰላም ነው ብሎ እንደወጡ መቅረት።አዳማ ታግቶ ነው የተገደለው::የሶስት ልጆች አባት እና በሙያው ኢትዮጵያን በትላልቅ መድረክ ያስጠራና አለምን የዞረ ታላቁ ሰዓሊ ይሄው በአሳዛኝ ሁኔታ ተለየን።ገደሉት ያሳዝናል። ያማል። ያንገበግባል። ወይኔ ሙሌ። ይቆጫል! ያንገበግባል!! ወንድሜን እግዘብሔር ነፍስሕን በአጸደ ገነት ያኑር!"
ከላይ የሰፈረውን ፅሁፍ በፌስቡክ ሳነብ በጣም ነው ያዘንኩት። ሀገራችን እንዲህ የሰፈር ወሮበሎች መፈንጫ መሆኗ ያበሳጫል።
ሰው ወጥቶ የማይመለስባት ሀገር እየሆነች ነው። ሰው አፍነው ገንዘብ መጠየቅ። ገንዘቡ በባንክ አካውንት ይጠየቃል።
አይ ኢትዮጵያ 😭
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አምስት ዓመታት ከ31 ቢሊየን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ እንደገጠመው አስታወቀ
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አምስት ዓመታት ከ31 ቢሊየን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ እንደገጠመው የተቋሙ ዋና የፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ አየለ ተናገሩ። የኩባንያው ትርፍ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ12 በመቶ ወደ 22 በመቶ ቢደርስም፤ የዋጋ ንረት እና የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ እንደሚፈታተኑት አቶ አሰግድ ገልጸዋል።
የፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ይህን ያሉት፤ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች የኩባንያውን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ አርብ ሰኔ 16፤ 2015 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው። በዛሬው የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዋና አስራ አስፈጻሚዋ የሚመሩት ተቋም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘጠኝ ወራት 52.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን እና 103 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱን ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ስራ ያስጀመረው “ቴሌ ብር” የተሰኘው የተሰኘውን የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር ከ30.5 ሚሊዮን በላይ መድረሱንም አስታውቀዋል። በዚህ አገልግሎት ባለፈው ዘጠኝ ወራት ብቻ 394.7 ቢሊዮን ብር ዝውውር መፈጸሙንም ተናግረዋል።
በትርፋማነቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የተቋሙ ዋና የፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ፤ ተቋሙ ባለፉት አምስት ዓመታት ትርፋማ ቢሆንም “በርካታ ተግዳሮቶች” እንዳሉበት አመልክተዋል። “የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳው ኩባንያ” እንደሆነም አስረድተዋል።
ኢትዮፒያን ኢንሳይደር
ሩቅ እንዳይመስላቹህ ይህ ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሙከ ጡሪ ውጫሌ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ዞን ነው ኦነግ ከነ ሙሉ ትጥቁ በነፃነት የሚንቀሳቀሰው።
መከላከያ አማራ ክልል ዘመቻ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ሁኔታ እንቆቅልሺ ነው።
የታይታኒክ መርከብ ጦስ ቀጥሏል፡
ፈጣሪ የሰጣቸውን ንፁህ አየር ፡ እምቢ ልዩ ነገር እንይ ብለው የወሰኑ ቢሊየነሮች ፡ በፊልም ምናውቃትን ታይታኒክ መርከብን ቅሪት አካል ለመጎብኘት ብለው አትላንቲክ ውቂያኖስ ውስጥ ገብተው ሲጎበኙ፡ ፈጣሪ የሰጣቸውን ኦክስጂን ሳይሆን ፡ በገንዘባቸው በስልጣናቸው የተማመኑበትን ፡ 94 ሰአት ብቻ ሚቆይ ኦክስጂን ተማምነው ገብተው፡
ህምጥ ይግቡ ስምጥ አልታወቀም።
የቀበጡ ለት ....... እንደሚባለው
ሌቦች ተይዘዋል 👏
ዛሬ ከሰዓት ጦርሀይሎች አካባቢ ነው
እነዚህ :-
* በጣም የዘነጡ ና
* የሚገርም መኪና የያዙ
አንዲት ትልቅ ሴትዬን መኪናቸው ውስጥ አስገብተው
* ወርቃቸው ና
* ብራቸውን ሲዘርፏቸው
ሴትየዋ ጩሀት በማሰማታቸው በአካባቢው የነበሩት ወጣቶች ግልብጥ ብለው መጥተው እጅ ከፍንጅ ይዘዋቸዋል::
ወጣቶቹም ሌቦቹን ለፖሊስ ከማስረከባቸው በፊት በቪዲዮ ቴሌግራም ላይ አለላችሁ እልል አድርገው ቀጥቅጠዋቸዋል 👏
ሌባ ስታገኙ ነገ ሰለሚፈታ እንዲህ እልል አድርጎ ጭኑ ስር መገረፍ አለበት ባይ ነን sometimes
መረጃ የሰጠን ቸሩን እናመስግናለን
2 ቪዲዮን የጉርሻ ቴሌግራም ኮሜንት ላይ አለላችሁ
የተረገሙ ህብረተሰቡን እኮ ናላውን አዞሩት
ደሞ ምንም እኮ ሌባ አይመስሉም
በዱባ ሞት
ሌብነት ተፀይፉ
ጉርሻ የፌስቡክ ገፅ
የሰሜን እዝ ጦር "በ45 ደቂቃ ውስጥ በመብረቃዊ ጥቃት ከስራ ውጪ አደርግነው" ያሉት ሴኩቱሪ ጌታቸው በመቐለ በስማቸው ጎዳና ተሰይሟል።
በእውነቱ ለሴኩቱሬ አደባባይ መሰየም ያለብን ከህወሓት ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን (የትግራይ ህዝብን ጨምሮ) ነን።
ሴኩቱሬ በቴሌቭዥን ወጥቶ ጥቅምት 24 የሰሜን እዝን እንዴት እንዳጠቁት ባይነግረን ኖሮ ጉዳዩ ተድበስብሶ የት ህ* ነግን ተግባር አናውቀው ነበረ።
ለዚህም መመስገን አለበት።
የፌደራል መንግስት ለሚቀጥለው በጀት ዓመት በራያ እና አካባቢው ለሚገኙ መዋቅሮች የሚመድበው ድጎማ፤ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይተላለፍ የቀረበን ጥያቄ የደገፉ የ145 ሺህ ሰዎች ገደማ ፊርማ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀረበ። በአካባቢው የሚገኙ ሶስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደርን የተመለከተው ጥያቄ የቀረበለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤ ጉዳዩን ለመመልከት ቃል ገብቷል ተብሏል።
ይህንን ጥያቄ የሚደግፉ ሰዎችን ፊርማ አሰባስቦ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሰኔ 12፤ 2015 ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስረከበው፤ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ነው። ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ የቀረበው ይህ ጥያቄ፤ የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ስር የነበሩ አራት መዋቅሮችን የተመለከተ ነው።
እነዚህ መዋቅሮች በትግራይ ክልል ስራ በነበሩበት ወቅት “የማንነት ጥያቄ ይነሳባቸው” እንደነበር የጠቀሰው ደብዳቤው፤ ሆኖም የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ “ራሱን በራሱ ለማስተዳደር” መቻሉን አትቷል። ጥያቄውን ያቀረቡት አመልካቾች፤ የአካባቢው ህዝብ “ከፌደራል መንግስቱ ሊያገኝ ይገባ የነበረው በጀት” የሚላከው “በትግራይ ክልል በኩል ነው” በመባሉ ምክንያት እስካሁን የገንዘብ ድጎማ አለማግኘታቸውን ያስረዳል።
“ይህ አይነቱ አካሄድ ላይ ላዩን ሲታይ ከህጋዊነት ጋር የሚገናኝ ቢመስልም፤ በይዘት እና በውጤት ደረጃ ሲታይ ግን የአንድን ህዝብ መሰረታዊ ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ነው። [አካሄዱ] ነጻነትህን የምትመርጥ ከሆነ ምግብ፣ መጠጥ፣ ትምህርት፣ ህክምና፣ አጠቃላይ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው አገልግሎቶችን ማግኘት አትችልም እንደማለት ነው” ሲሉ አመልካቾቹ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
"በዚህ ሰዓትድምፅ የሌለበት ውጊያ ላይ ነን
እኝህ አባት ትናንት አቡነ መርሃ ክርስቶስ ይባላሉ በአዲግራት ከተማ በቅዱስ ሚካኤል በአል እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል
"የአዲግራት ህዝብ እንኳን አደረሰህ እያልኩ በቅርቡ ጊዜ ከ10 በላይ ጳጳሳት የምንሾም ስለሆነ ምእመናን ደስ እንዲላቸው ተናግረዋል ።
ሲቀጥሉ አስር ጳጳሳት መሾም ስንት ወጣ ውረድ አንዳለው ማወቅ ይገባል ያሉ ሲሆን፣ቢዚህ ሰዓት ድምፅ የሌለበት ውጊያ ነው የገባነው። እኛ የሚሳካልን እናንተ ከእኛ ጎን ስትሆኑ ብቻ ነው። በማሃላችን ያሉት ሊከፋፍሉ በሚሊዮን ገንዘብ አውጥተው የማያደርጉት ነገር የለም።ይሁን እንጂ የፈሰሰው ገንዘብ ይፍሰስ ያሳብነው ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም ።
ህዝበ ክርስቲያን ደግሜ ልንገራችሁ የሳብነው ግቡ እንዲመታ እባካችሁ አግዙን ራቁታችንን እንዳንቀር እያሉ እየለመኑ ያረፈዱ ሲሆን በመጨረሻም ንግግራቸው በፀሎት ጨርሰዋል ።
በዚያው ቀን ህወሓቶች ተገናኝተው ለሰማዕታት (1 ሚሊየን ብለው ነው እንደ ቀላሉ የሚናገሩት) የህሊና¡ ፀሎት በማድረግ ለቀጣይ ትግል የትግራይ ህዝብ እንዲዘጋጅ መፈክር አሰምተዋል።
የትግራይ ህዝብ መከራ በቅርብ ጊዜ የሚያልቅ አይመስልም። ሌላ ዙር ግጭት ጠመቃ ላይ ናቸው።
ቄሱም፣ ጳጳሱም፣ ሼኩም፣ መሪውም እንዴት ህዝብ ላይ ይፈርዳል?
ግፍ አደለም?
ልብ ሰባሪው ክስተት!!!
******
ዛሬ ረፋድ ላይ በቀብሪደሃር ከተማ 4 ንፁሃን የቀጠፈውን ግድያ በተመለከተ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ኃላፊው በ3 ወንድ እና በአንዲት ሴት ላይ ተኩስ በመክፈት ህይወታቸው እንዲቀጠፍ ያደረገውን ድርጊት እጅግ አሳዛኝ እና ልብ የሚሰብር ነው ብለውታል።
በቀብሪደሃር ከተማ ዛሬ ረፋድ ላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል እንደሆነ የተገለፀ ግለሰብ ቀበሌ 08 እየተባለ በሚታወቀው አከባቢ ተኩስ በመክፈት የቀበሌው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ማህሙድ ሀጂ ጠይብ፣ ወጣት በሽር ኢሻባል፣ ወጣት አህመድ አብዲ ያሬን እንዲሁም
ዘይነብ አብዲናስር የተባለች ወጣትን ህይወት በመቅጠፍ ተጨማሪ ሰዎችን ያቆሰለው ግለሰብ ራሱን ማጥፋቱ ነው የተጠቆመው።
የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ በተፈጠረው እጅግ አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ድርጊቱን በማጣራት ላይ መሆኑንና ምርመራውን ሲያጠናቅቅ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ምንጭ
Somali Fast Info
*ግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር በአዋጅ 985/2009 እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በወጡ ደንቦች የተቋቋመ ተቋም ነው። በዘርፉ ህጋዊ ሰውነት በመያዝ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ6 ዓመት በላይ የሆነው ሲሆን፣ለስራ መኪና ግዥ፤ለመካከለኛና ዝቅተኛ የስራ ዘርፎች መነሻና ማስፋፊያ የሚሆን ከ46 ሚሊዬን ብር በላይ ለአባላት ብድር ተደራሽ አድርጓል። ይምጡና አባል በመሆን ራስዎንና ቤተሰብዎን ተጠቃሚ ያድርጉ!!
ዓላማ
1, የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል በማዳበር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ፈቺ የሆነ የብድር አገልግሎት መስጠት፡፡
የአገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች
☑️ የአንድ ሼር (ዕጣ) ዋጋ ብር 1,000 ሆኖ አምስት ዕጣ እና ከዛ በላይ መግዛት የሚችል፤
☑️በተቋሙ ደንብ መሰረት በየወሩ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 በተሻለ ወለድ ለመቆጠብ ፈቃደኛ የሆነ፤
☑️ የአከፋፈል ሁኔታ በምዝገባ ወቅት አባሉ ሊገዛ የፈለገውን የዕጣ ብዛት 50% ሆኖ የመጀመሪያው ክፍያ በተከፈለ እስከ ሶስት ወር ቀሪው ክፍያ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
☑️ቁጠባ ከተጀመረ ከ15 ቀን ጀምሮ የቁጠባውን አራት እጥፍ ብድር ማግኘት ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ /channel/+PvdivOnnBTs1ZDQ8
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ አየር መንገዶች የተያዘባቸውን ገንዘብ መንግስት እንዲለቅ አሳስቧል።
ከማህበሩ ዛሬ የደረሰኝ መረጃ እንደሚጠቁመው አሁን ላይ ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ የውጪ አየር መንገዶች 95 ሚልዮን ዶላር ኢትዮጵያ ውስጥ ተይዞባቸዋል።
"ኢትዮጵያ (የአየር) ግንኙነት ችግር እንዳይገጥማት ይህ ገንዘብ በፍጥነት ሊለቀቅ ይገባል፣ ይህንን ማድረግ በአለም አቀፍ ስምምነቶች የተረጋገጠ ነው" ያለው ማህበሩ ኢትዮጵያ ከኮቪድ 19 በኋላ ከፍተኛ የአቪዬሽን እድገት እና ትርፋማነት እያስመዘገበች እንደሆነ ተጠቅሷል።
ማህበሩ አክሎም አየር መንገዶች ለሰጡት የበረራ አገልግሎት ያገኙትን ገንዘብ በውጭ ምንዛሬ እንዲያወጡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በብሄራዊ ባንክ አነስተኛ ትኩረት ተሰጥቷል።
"ይህ ትክክለኛ ያልሆነ መልእክት ያስተላልፋል፣ ኢትዮጵያ ትርፋማ ለሆነችነት ዘርፍ ያለባትን ሀላፊነት ልትወጣ ይገባል" ብሏል።
*በነገራችን ላይ፣
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጠው አገልግሎት በውጭ ሀገራት ገንዘብ ተይዞበት ለማስመለስ ጥረት ሲያደርግ እንጂ እኛ የሌሎችን ይዘን ብዙም ተሰምቶ አይታወቅም ነበር። ለምሳሌ ዘንድሮ ብቻ አየር መንገዱ በኤርትራ 2 ሚልዮን ዶላር፣ በናይጄርያ ደግሞ 80 ሚልዮን ዶላር ተይዞበት ይገኛል። ከፓርክ እና ቤተ መንግስት ግንባታዎች ይልቅ ዘንድሮ ብቻ 6.1 ቢልዮን ዶላር ለሀገሪቱ ላስገባ ዘርፍ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብዬ አስባለሁ።
ዘገባው የኤሊያስ መሰረት ነው
በወላይታ ዞን በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ፤ “በርካታ” መራጮች ስድስት ወራት ያልሞላው መታወቂያ ይዘው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በዛሬው ዕለት በድጋሚ ሲካሄድ በዋለው ህዝበ ውሳኔ፤ “በርከት ያሉት” መራጮች የያዙት መታወቂያ ከተሰጠ ስድስት ወር ያልሞላው ሆኖ መገኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። እነዚህ መራጮች በዞኑ ነዋሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ሌሎች አማራጮችን ተግባራዊ ማድረጉን ቦርዱ ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ይህንን ያለው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልልን ለመመስረት በወላይታ ዞን እየተደረገ ያለውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 12፤ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው። ምርጫ ቦርድ በዚሁ መግለጫው፤ በህዝበ ውሳኔው ከተሳተፉ ድምጽ ሰጪዎች ውስጥ “በርከት ያሉት” ቦርዱ መራጮችን ለመመዝገብ ያስቀመጠውን መስፈርት የማያሟሉ ናቸው ብሏል።
በ2012 ዓ.ም የወጣው የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ፤ “ማንኛውም ሰው በምርጫ ክልሉ ቢያንስ ስድስት ወር የኖረ ከሆነ በመራጭነት ሊመዘገብ ይችላል” ሲል ደንግጓል። በዛሬው ህዝበ ውሳኔ ላይ ድምጻቸውን ለመስጠት የወጡ “በርካታ” የዞኑ ነዋሪዎች የያዙት መታወቂያ፤ “ከተሰጣቸው ስድስት ወር ያልሞላው” ሆኖ መገኘቱን ምርጫ ቦርድ በመግለጫው አመልክቷል።
ቦርዱ ይህን ያረጋገጠው፤ ድምጽ ለመስጠት የሚመጡ ነዋሪዎችን ምዝገባ ለመፈጸም መታወቂያቸው በሚታይበት ጊዜ መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ከተቋሙ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት የድምጽ አሰጣጦች በተለየ ሁኔታ፤ በዛሬው ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ እና የድምጽ የመስጠት ሂደትን ያከናወነው በአንድ ቀን ነው።
Ethiopian Insider
*ግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር በአዋጅ 985/2009 እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በወጡ ደንቦች የተቋቋመ ተቋም ነው። በዘርፉ ህጋዊ ሰውነት በመያዝ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ6 ዓመት በላይ የሆነው ሲሆን፣ለስራ መኪና ግዥ፤ለመካከለኛና ዝቅተኛ የስራ ዘርፎች መነሻና ማስፋፊያ የሚሆን ከ46 ሚሊዬን ብር በላይ ለአባላት ብድር ተደራሽ አድርጓል። ይምጡና አባል በመሆን ራስዎንና ቤተሰብዎን ተጠቃሚ ያድርጉ!!
ዓላማ
1, የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል በማዳበር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ፈቺ የሆነ የብድር አገልግሎት መስጠት፡፡
የአገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች
☑️ የአንድ ሼር (ዕጣ) ዋጋ ብር 1,000 ሆኖ አምስት ዕጣ እና ከዛ በላይ መግዛት የሚችል፤
☑️በተቋሙ ደንብ መሰረት በየወሩ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 በተሻለ ወለድ ለመቆጠብ ፈቃደኛ የሆነ፤
☑️ የአከፋፈል ሁኔታ በምዝገባ ወቅት አባሉ ሊገዛ የፈለገውን የዕጣ ብዛት 50% ሆኖ የመጀመሪያው ክፍያ በተከፈለ እስከ ሶስት ወር ቀሪው ክፍያ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
☑️ቁጠባ ከተጀመረ ከ15 ቀን ጀምሮ የቁጠባውን አራት እጥፍ ብድር ማግኘት ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ /channel/+PvdivOnnBTs1ZDQ8
በአፍሪካ የመጀመሪያው የተሳካ ቀዶ ጥገና በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ተካሄደ
#Ethiopia | በአፍሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ የሚነገርለት የህጻናት ቆዶ ጥገና ባሳለፍነው ሳምንት በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የ12 ዓመት ታዳጊ ህፃን ላይ ተከስቶ የነበረውን ከቆሽት የሚነሳ የሆድ ዕጢ ከ10 ሰዓት በላይ የፈጀ whipple (ዊፕል) በሚባል የቀዶ ህክምና ዘዴ በልዩ ሁኔታ ዕጢውን በማስወገድ የተሳካ ቀዶ ህክምና ሊከናወን ችላል።
እስካሁን ባሉ መረጃዎች መሠረት ይህ ቀዶ ህክምና በአይነቱ ለየት ያለና በህፃናት የቀዶ ህክምና ታሪክ በሃገራችንም ሆነ በአፍሪካ ፈር ቀዳጅ ሆኗል።
የቀዶው ጥገና ህክምና የመሩት የህፃናት ቀዶ ጥገና እስፔሻሊስት ዶ/ር ወርቅዬ ጥጋቤ እና ለሙያ አጋሮቻቸው በሙሉ ከልብ እናመሠግናቸዋለን
እንኳንም ደስ አላችሁ !
(ጌች ሐበሻ)
# DMC Real Estate
የመጨረሻ ዙር ማስታወቂያ ዋጋ !!!
ለተወሰኑ ቤቶች ብቻ የተሠጠ፤ ታላቅ ቅናሽ ለቡ መብራት ላይ የሚገኝ፤ በ4ቱም አቅጣጫ ድንቅ እይታ ያለው
65,395 ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር
👉 ይህ የብልሆች የኢንቨስትመንት ምርጫ ነው።
👉ከ 52.6 ካሬ ጀምሮ እስከ 147 ካሬ አፓርታማዎችን ይዞ እየተገነባ ያለ!
👉ከ 20 ካሬ ጀምሮ Ground ላይ ለንግድ እሚሆኑ ሱቆችንም ይዟል
15% ቅድመ ክፍያ በ 710,100 ብር በመኪና ዋጋ የቤት ባለቤት ይሁኑ ለካሬ 90,000 ብር ከ ሁለተኛ ፎቅ ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ አፓርትመንቶችን እና ሱቅችን በሽያጭ ላይ መሆናችነን ስናበስረዎት በታላቅ ደስታ ነው።
❤ ልብ ይበሉ ይህ ዋጋ እሚቆየው ለትንሽ ቀናቶች ብቻ ስለሆነ ይፍጠኑ!
👉 Aluminum Formwork መጠቀማችን ልዩ ያደርገናል
DMC Real Estate
ዋና ቢሮ ለቡ
ለበለጠ መረጃ:-
+251918642895
+251906949686
ወይም
You can contact direct call or via Telegram , WhatsApp , Imo , Viber +251906217873
kefiegashaw12@gmail.com
ታይታኒክን ለማሰስ ባሕር የጠለቀችዉ ሰርጓጅ መርከብ ፈንድታ አምስቱም ተመራማሪዎች ሞቱ
ሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ 3,800 ሜትር ጥልቀት ውስጥ ሰጥማ ለአንድ ክፍለዘመን የቆየችውን ታይታኒክ ግዙፍ እና ዝነኛ መርከብን ለማሰስ አምስት ተሳፋሪዎችን ጭና ሰሜን አላንቲክ ውቅያኖስ የጠለቀችዉ በአነስተኛ የባሕር ሠርጓጅ መፈንዳትዋ ተሰማ።
የአምስቱ ተመራማሪ ቤተሰቦች ኃዘን ተቀምጠዋል። ይህ የተነገረዉ የባህር ሰርጓጅዋ ስባሪ ትናንት ሃሙስ ምሽት ላይ መገኘቱን ተከትሎ ተመራማሪዎቹ በህይወት እንደሌሉ መረጋገጡን ተከትሎ ነዉ።
ባለፈዉ እሁድ ወደ ሰባት ሜትር ርዝመት ያላት ሰርጓጅ መርከብ አምስት ተመራማሪዎችን አሳፍራ ሰሜን አላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ከጠለቀች ከ አንድ ሰአት ከ 45 ደቂቃ በኋላ ግንኙነቱ መቋረጡ ይታወቃል። ተመራማሪዎቹ ምናልባትም ወደ ዉቅያኖሱ እንደጠለቁ ህይወታቸዉ ሳያልፍ እንዳልቀረ ዘገባዎች አመልክተዋል።
ኦነግ የተመሰረተበትን 50ኛ አመት ሊያከብር ነው
የኦነግን 50ኛ አመት አከባበር በተመለከተ የተዋቀረው ኮሚቴ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል።
በአከባበር መርሀግብሩ ላይ ኦነግ ከተመሰረተ ጀምሮ ስላሳካው አላማ እና ስለገጠመው ተግዳሮት ይገመግማል ተብሏል።
ሰማዕታት ይዘከራሉ
ሌሎችም ፕሮግራሞች ይኖራሉ።
ታዛቢዎች ጥያቄ አላቸው።
ኦነግ ከተመሰረተ ጀምሮ አምስት እና ከዚያ በላይ ቦታ ተከፋፍሏል።
የትኛው ኦነግ ነው ሀቀኛ ኦነግ?
ሁለቱ የአለማችን የግዙፍ ኩባንያ ባለቤቶች ኤሎን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ የቦክስ ግጥሚያ ሊያካሂዱ ነዉ
የዓለማችን ግዙፍ የኩባንያ ባለቤቶች የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች የቦክስ ፍልሚያ ሊያካሂዱ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
የትዊተር ባለቤቱ ኤለን መስክ "up for a cage fight" with Mr Zuckerberg. በ ቲውተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
ይህን ሃሳብ የተቀበለ የሚመስለዉ የሜታ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ዙከርበርግ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ኤለን መስክ የጻፈዉን ሃሳብ screen shoot በማድረግ ‹‹ ቦታዉን አሳዉቀኝ›› ብሎታል፡፡
ኤለን መስክም በትዊተር ገጹ ‹‹ ቬጋስ ኦክታገን›› እንገናኝ ሲል የፍልሚያዉን ቦታ አስቀምጧል፡፡
መስክ በትዊተር ገጹ ላይ ‹‹ በተቀናቃኜ ሰዉነት ላይ ተኝቼ ተጋጣሚየን ምንም እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የምገታበት ዘ ዋልረስ የሚባል ምት አለኝ›› ሲል አስፍሯል፡፡
ዙከርበርግ የጂትሱ ልምምድ በተደጋጋሚ እንደሚያደርግ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የለጠፈ ሲሆን፣ ከ 6 ሳምንታት በፊትም የጂትሱ ዉድድር ማድረጉን እና የተለያዩ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉን ተናግሮ ነበር፡፡
📍ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ትልቅ ዕድል
⚡️አንደአከፋፈሉ ከ 14% - 35% ቅናሽ ያግኙ
ከ 70% በላይ የተጠናቀቁ አፓርታማዎችን በመግዛት ተ ጠቃሚ ይሁኑ!
ቀድመው በመምጣት ቤትዎን ይያዙ
የቀሩን የካሬ አማራጮች፦
107 ካሬ
110 ካሬ
115 ካሬ
120 ካሬ
127 ካሬ
138 ካሬ
በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን
ለበለጠ መረጃ ፦
⚡️ t.me/Tsion_won
⚡️ /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354 / +251904444670
ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የውጭ አገር ባንኮች ፈቃድ ሊሰጥ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
አምስት የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
አገር በቀል ባንኮች ከወዲሁ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እና ቀድሞ የነበራቸውን ስትራቴጂ መከለስ እንዳለባቸውም አሳስቧል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ተቋማት ዘርፍ ምክትል ገዥ አቶ ሠለሞን ደስታ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትን ከማጠናከር ጎን ለጎንም የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡
‹‹ሥራውን አሁን እያጠናቀቅን ነው፡፡ አዋጁን የመከለስ ሥራውንም እያጠናቀቅን ነው:: ከለጋሾች አንዳንድ ግብዓቶችን እየጠየቅን ነው:: በወራት ዕድሜ ለህዝብ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103108
ዘወትር ረቡዕ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ አሁን በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
--------------------
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ www.EthiopianReporterJobs.com
📍ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ትልቅ ዕድል
⚡️አንደአከፋፈሉ ከ 14% - 35% ቅናሽ ያግኙ
ከ 70% በላይ የተጠናቀቁ አፓርታማዎችን በመግዛት ተ ጠቃሚ ይሁኑ!
ቀድመው በመምጣት ቤትዎን ይያዙ
የቀሩን የካሬ አማራጮች፦
107 ካሬ
110 ካሬ
115 ካሬ
120 ካሬ
127 ካሬ
138 ካሬ
በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን
ለበለጠ መረጃ ፦
⚡️ t.me/Tsion_won
⚡️ /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354 / +251904444670
ሁለት ዜናዎች
1፤
ትናንት በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የተካሄደው የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ውጤት በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደረጃ ሲገለጥ መዋሉን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በሕዝበ ውሳኔው ድምጽ አሰጣጥ የተወሰኑ አነስተኛ ችግሮች ከማጋጠማቸው በስተቀር ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁን ትናንት ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ሕዝበ ውሳኔው፣ ወላይታ ዞን ከጌዲዖ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞና ጎፋ ዞኖች እና ከቡርጂ፣ አሌ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ጋር በጋራ አንድ ክልል ያቋቁም እንደኾነ የሚወስን ይኾናል።
2፤
የዓለም ምግብ ድርጅት ተረጂዎች የሚመረጡበት የቁጥጥር ሥርዓት ባግባቡ ከተዘረጋ የምግብ ዕርዳታ ሥርጭቱን በሐምሌ ኹለተኛ አጋማሽ በትግራይና በስደተኛ ጣቢያዎች እንደገና ሊቀጥል እንደሚችል መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል። የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቫለሪ ጓርኔሪ፣ በምግብ ዕርዳታ ተረጅዎች ምልመላ ላይ የአካባቢና የክልል ባለሥልጣናትን ተጽዕኖ መቀነስ እንደሚፈልግ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ድርጅቱ በተለይ በትግራይ ክልል በዕርዳታ የቁጥጥር ሥርዓቱ ላይ ችግር እንደነበረበት የድርጅቱ መርማሪዎች ማረጋገጣቸውን ሃላፊዋ መጥቀሳቸውን የገለጠው ዘገባው፣ ድርጅቱ ለተጠቀሱት ተረጂዎች ዕርዳታውን ለመቀጠል ከባለሥልጣናት ዋስትና ማግኘቱንና በሌሎች አካባቢዎችም በፍጥነት ዕርዳታ የመጀመር ተስፋ እንዳለው ሃላፊዋ ተናግረዋል ተብሏል።
ዋዜማ የዘገበችው
👉 የባንክ ብድር የተመቻቸለት
👉ቅንጡ G+1 ቪላ ቤቶች በአያት
👉 የካሬ አማራጮ
📌230ካሬ
📌270 ካሬ
📌331 ካሬ
⚡️የቀሩን ጥቂት ቤቶች በመሆናቸዉ መተዉ የግሎ ያድርጉ
/channel/Realestateconsult12
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ/አማካሪ
📞 ☎️ +251946404247
Direct call / Whatsapp or telegram
መንግሥት እንዲህ ነው ለሕዝብ የሚያስበው ? እሱ ከአቅም በላይ ክፍያ ሲጠይቅ የሚቻል ፣ ግለሰቦች ግን በራሳቸው ንብረት እንዳያዙ ማድረግ ምን ያህል ፍትሐዊ ነው ?
የዛሬ ዜና
እስከ ሰኔ 30 /2015 ዓ.ም ድረስ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ
ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ክትትል እንደደረሰበት ገልጿል::
የከተማ አስተዳደሩ አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ይታወሳል::
በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
ከሰኔ 30 በኋላስ ?
ጥያቄው እሱ ነው ። መንግሥት ድንገት ሕግ አውጥቶ ሕጉ ከመውጣቱ በፊት ያለውን ሁሉ " ክፈሉኝ " ብሎ ነዋሪው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበት ተበድሮና ተለቅቶ ጭምር ከፈለ ። መንግሥት በሁሉም አገልግሎቶቹ ላይ ያለርህራሄና የሕዝቡን የመክፈል አቅም ሳያገናዝብ እያስከፈለ ይገኛል ። አከራዮች ላይ ይህን መመሪያ ሲያወጣ በምን አግባብ ነው ? እኔም ራዜ ቤትን ከግለሰብ ተከራይተው ከሚኖሩ ዜጎች መሀል አንዱ ነኝ ። ኪራይ ጭማሪን ላበረታታ አይደለም ። ግን ደግሞ የተገቢነት ጉዳይ አለ ። መንግሥት የትኛውንም የዋጋ ንረት እየተቆጣጠረ አይደለም ። ጉልበቱ ለምን አከራዮች ላይ ብቻ ሆነ ? ሰኔ 30/15 ድረስ ይህ ሕግ ወጣ ። ከዚያስ ?
"ለማን ነው አቤት የምንለው?"
በታጣቂዎች የታጋቱ ሹፌሮች እና ረዳቶች ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።
ከቀናት በፊት ሹፌሮች እና ረዳቶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር እና በተቃራኒው ጉዞ ላይ የነበሩ አዳራቸውን " አሊዶሮ " ላይ ካደረጉ በኃለ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦች መግለፃቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱ በተፈፀመበት ዕለት መልዕክት ካደረሱት ተጨማሪ የታጋች ወዳጆችን ፣የሚያውቋቸውን እንዲሁም በዕለቱ ጉዞ ላይ ከነበሩ አባላት መልዕክት ተቀብሏል።
አንድ በዕለቱ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የነበረ የቤተሰባችን አባል ፤ ገብርጎራቻ 2 ሰዓት በደረሱበት ወቅት " አሊዶሮ " ላይ ወደ 14 መኪና ሹፌርና እርዳት መወሰዳቸውን እንደሰሙ ገልጿል። " ለ4 ሰዓታት ያህል ቁመን መከላከያ መቶ ነው መገዱ ተከፍቶ ወደ አ/አ የሄድነው " ሲል አስረድቷል።
አንድ የቤተሰባችን አባል " የኔም ጓደኝዬ ከታገቱት አንዱ ነው " ሲል ቃሉ ሰጥቶ ትላንት ለቤተሰቡ ተደውሎ " አንድ ሚሊዮን ብር ላኩ " መባሉንና ቤተሰብም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል
ሌላ የቤተሰባችን አባል " አሊደሮ " ላይ ከታገቱት መካከል ሁለቱ የቻግኒ ልጆች እንደሆኑና ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር መጠየቁን እንደሚያቅ ፤ ለቤተሰቦችም ይህንን ብር ካላመጡ " እንገላቸዋለን " የሚል ማስፈራሪያ መላኩን አስረድቷል። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በጭንቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።
እገታው በተፈፀመበት ዕለት መልዕክቱን የላከልን አንድ ወንድሙ መታገቱን ያመለከተ የቤተሰባችን አባልም፤ አጋቾቹ ደውለው " 1 ሚሊዮን ብር አምጡ እኛ እነሱን አንፈልግም " ማለታቸውን ገልጿል።
ሹፌሮች እና ረዳቶች መታገታቸው ከተነገረ ቀናት ቢያልፍም ከሚመላከታቸው የመንግሥት አካላት በኩል አንድም የተሰጠ ማብራሪያ የለም
ኢትዮ ቴሌኮም የ994 የጥሪ ማዕከል አገልግሎቱን ለውስን ደንበኞች ብቻ ክፍት እንዲሆን አደረገ
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ከጥሪ ማዕከል ሰራተኞች ጋር የሚገናኙበትን አገልግሎት፤ በከፊል የሚያስቀር አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። በአዲሱ አሰራር መሰረት ከድርጅቱ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች ጋር የሚገናኙ ተገልጋዮች፤ “የፕሪሚየም እና የተለዩ አገልግሎቶችን የሚፈልጉ” ተብለው የተለዩ ደንበኞች ብቻ እንደሚሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
መንግስታዊው የቴሌኮሚዩኒኬሽን አቅራቢ ድርጅት ከደንበኞቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ከሚሰጥባቸው አማራጮች ውስጥ አንዱ፤ ወደ ተቋሙ የጥሪ ማዕከል በ994 አጭር ቁጥር መወደል ነው። በዚህ ቁጥር ላይ የሚደውል ደንበኛ፤ በስልኩ ላይ በድምጽ የሚቀርብለትን አማራጮች በመከተል የሚፈልገውን የአገልግሎት አይነት እንዲያገኝ ይደረጋል። ደንበኞቹ ከተቋሙ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችም፤ በመስመር ላይ የሚጠብቁ የጥሪ ማዕከሉ ሰራተኞች ምላሽ ይሰጣሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለጥሪ ማዕከሉ ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ “የፒን ቁጥርን ከመርሳት፣ የጥሪ ዝርዝርን ከመጠየቅ እንዲሁም ስልክ ቁጥር ከማስከፈት እና ከማዘጋት” ጋር የተያያዙ መሆናቸውን የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች መስመሩን ለረጅም ጊዜ ይዘው የሚቆዩ መሆናቸው እና ቁጥራቸውም በርካታ መሆኑ፤ ሌሎች “መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚጠይቁ ሰዎች” ከጥሪ ማዕከሉ ሰራተኞች ጋር እንዳይገናኙ ማድረጉን አስረድተዋል።
* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11224/