የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአዲስ አፍሪካዊ መንፈስ ተነስተን አዲስ ራዕይ ሰንቀን የአፍሪካን ሀይል፣ እድል እና እምቅ አቅም ለእድገት እናውል እያለ ነው። ይህን በፃፈበት ቲዊተር የለቀቀው ፎቶ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያሸበረቀ ነው። እኛ ወደ መንደር ስንወርድ አፍሪካውያን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አለማ እያሸበረቁበት አዲስ የተነሳሽነት መንፈስ እያደረጉት ይገኛሉ። #ሼር
የዊሊያም ሩቶ መልዕክት ከታች የተፃፈው ነው 👇
Owing to the emerging interaction of critical factors at various levels, it is inevitable to develop and articulate a new vision of African power and prospects in terms of opportunities, resources and potential.
ጉጂ ዞን በህዝብና በመከላከያ ከፍተኛ ፍጥጫ ተከስቷል። አመራሮቻችን ታስረዋል ይፈቱ የሚሉ የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ነገሌ መግቢያ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ በመያዝ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ምስራቅ ቦረና ተብሎ በተሰየመው አዲሰ መዋቅር በቦረና እና በጉጂ መካከል ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩ ይታወሳል።
ትናንተ ለሊት በደረሰው የጂጂጋው አዲሱ ታይዋን ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ ትልቅ እሳት አደጋ ነው የደረሰው።
በዚህ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ንብረት ወድሟል።
እስካሁን ቆስለው እየታከሙ ያሉ በርካታ ሰዎች ያሉ ቢሆንም የሞተ ሰው እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልተሰማም።
የሶማሌ ፖሊስ እሳት መከላከያ እሳቱን ለማጥፋትና ንብረት ለማሸሽ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርጉ ነበረ
የአከባቢው ነዋሪም እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆችን ንበረት ለማሸሽ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።
#ማስታወቂያ! እንዳያመልጣችሁ‼️
# DMC Real Estate‼️
የመጨረሻ ዙር ማስታወቂያ ዋጋ !!!
ለተወሰኑ ቤቶች ብቻ የተሠጠ፤ ታላቅ ቅናሽ ለቡ መብራት ላይ የሚገኝ፤ በ4ቱም አቅጣጫ ድንቅ እይታ ያለው
65,395 ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር
👉 ይህ የብልሆች የኢንቨስትመንት ምርጫ ነው።
👉ከ 52.6 ካሬ ጀምሮ እስከ 147 ካሬ አፓርታማዎችን ይዞ እየተገነባ ያለ!
👉ከ 20 ካሬ ጀምሮ Ground ላይ ለንግድ እሚሆኑ ሱቆችንም ይዟል
15% ቅድመ ክፍያ በ 710,100 ብር በመኪና ዋጋ የቤት ባለቤት ይሁኑ ለካሬ 90,000 ብር ከ ሁለተኛ ፎቅ ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ አፓርትመንቶችን እና ሱቅችን በሽያጭ ላይ መሆናችነን ስናበስረዎት በታላቅ ደስታ ነው።
❤ ልብ ይበሉ ይህ ዋጋ እሚቆየው ለትንሽ ቀናቶች ብቻ ስለሆነ ይፍጠኑ!
👉 Aluminum Formwork መጠቀማችን ልዩ ያደርገናል
DMC Real Estate
ዋና ቢሮ ለቡ
ለበለጠ መረጃ:-
+251918642895
+251906949686
ወይም
You can contact direct call or via Telegram , WhatsApp , Imo , Viber +251906217873
kefiegashaw12@gmail.com /channel/Engineergashaw
የብሪክስ ገንዘብ
በነሃሴ ወር በወርቅ የተደገፈ የብሪክስ ገንዘብ ይወጣል የሚል ዜና አለ። ከተጠበቀው ጊዜ ቀድሞ ነው የመጣው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ 30 የሚጠጉ አገሮች አባል ለመሆን ጠይቀዋል።
የብሪክስ ገንዘብ የዶላር ተፎካካሪ ነው የሚሆነው። አሜሪካ ከፍተኛ የጦር መሳሪያና ቴክኖሎጂ አምራችና ሻጭ አገር መሆንና አውሮፓና የአሜሪክ ወዳጅ የሆኑ አገሮች አሁንም ከዶላር ጋር ያላቸውን ግንኙነት በቀላሉ የሚያላቅቃቸው አለመሆኑ ዶላርን ደግፎ ያቆየዋል።
ነገግን የብሪክስ ገንዘብ በወርቅ መደገፉ ለብዙ ሶስተኛ ዓለም አገሮች በጣም አጓጊ ነው።
ዶላር የዓለም ገንዘብ ሲሆንና፣ ከወርቅ ጋር ያለው ግንኙነት ሲቋረጥ የሶስተኛ ዓለም አገሮችን መዝረፊያ መሳሪያ የሆነው። የዚህም ምክንያቱ የዶላር ያለጠያቂ መታተም ሲሆን እያንዳንዱ የታተመ ዶላር የሶስተኛ ዓለም አገሮች በገንዘብ መልክ ያስቀመጡት ተቀማጭም ይሁን በዶላር እየተገመተ የሚሸጡት ጥሬ እቃ ዋጋው እየወረደ እንዲሄድ ስላረገው ነው።
የመገበያያው ገንዘብ ወርቅ ከሆነ ግን ጥሬ እቃውን በወርቅ የሸጣ አገር ክወር ከሁለት ወር በኋላ ያ ወርቅ ዋጋው ስለማይረክስ አይጎዳም። ቢጨምር እንጂ።
የወርቅ ገንዘብነት በተለይ የሚጠቅመው ብድር የሚወስዱ አገሮችን ነው። ወርቅ በቀላሉ እንደ ዶላር የሚታተም ስላለሆነ ዋጋው በየጊዜው እየጨመረ ይሄዳል እንጂ እየቀነሰ አይሄድም።
አንድ አገር ፕሮጀክት ቀርጾ ብድር ቢወስድ በዋጋ ግሽበት ምክንያት የፕሮጀክቱ ዋጋ በጀቱን በጥሶ ይሄዳል የሚል ስጋት አይኖርም።
በዚህም ምክንያት አንድ ሰበብ ስለሚነሳ ሙስናውም ሊቀንስ ይችላል።
ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ትክክለኛ ስርዓትን በሚከተሉ አገሮች ነው።
Geleta Gamo
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች ቁጥር 60 ሺህ ደረሰ።
በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በፈጥና ደራሽ መካከል የተጀመረው ጦርነት አሁንም መቋጫ አላገኘም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሁለት ሰዓት ተኩል ገደማ የፈጀውን ማብራሪያቸውን ሲያሳርጉ፤ “ብተዋቸው ስለሚሻል አንዳንድ የተውኳቸው ጉዳዮች አሉ” ብለዋል። አብይ ምላሽ ሳይሰጡ ካለፏቸው ጥያቄዎች መካከል፤
√ መከላከያ ሰራዊቱ በአማራ ክልል እያደረገ ስላለው ወታደራዊ ዘመቻ
√ ስለዜጎች እገታ
“ከሸኔ ጋር የተጀመረው የሰላም ንግግር ሂደቱና ውጤቱ ምን ይመስላል?” በሚል በአቶ አኔሳ መልኮ የቀረበው አንዱ ነው።
ሌላኛው የፓርላማ አባል አቶ ብርሃኑ ሀንካራ ያነሱት እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት የሚመለከተው ጥያቄም በተመሳሳይ በአብይ ምላሽ አልተሰጠውም። የአቶ ብርሃኑ ጥያቄ፤ “በአሁኑ ጊዜ ከጎረቤት አገሮቻችን በተለይ ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት እንዴት ይታያል?” የሚል ነበር።
* * የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዛሬውን የፓርላማ ውሎ ዝርዝር ዘገባ በጽሁፍ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethiopiainsider.com/2023/11403/
ሹፌሩንና ረዳቱን በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን FSR መኪና ይዘው ከተሰወሩ ተጠርጣሪዎች አንዱ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር አባጀምበር ቀበሌ የጨረቃን ጎጥ ሲሆን ከገንዳ ውሃ ከተማ ወደ አዲስ አበባ አንድ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ሾፌርና ረዳቱን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሰኔ 28/2015 ዓም ሰዓቱ በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ ገድለው በመጣል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ፡፡
የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው ጥብቅ ክትትል ወንጀለኞቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ማሳደራቸው መረጃ ይደርሰዋል፡፡
ፖሊስ ወንጀለኞችን ክትትል በማድረግ ላይ እያለ ወንጀለኞቹ ሰኔ 29/2015 ዓም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ ህዝብና የጸጥታ አካላት ብርቱ ጥረት አንዱ ወንጀለኛ ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሲውል ሌሎች ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል፡፡
መረጃው የምስራቅ ጎጃም ኮሙኒኬሽን ነው
By Fasil Yenealem
ስለ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ የፓርላማ ውሎ በዛሬው ዕለታዊ ዝግጅት ላይ በስፋት እንዳስሰዋለን። ነገር ግን ፈረንሳይ በተቃውሞው ወቅት ኢንተርኔት አግዳለች በማለት የእርሳቸውን አፈና ትክክለኛነት ለማስረገጥ የሰጡት መረጃ፣ እርሳቸውን "ከወዳጃቸው" ማክሮን ጋር የሚያቀያይማቸው ብቻ ሳይሆን፣ እንደ መሪም የአመኔታ ጥያቄ የሚያስነሳባቸው ይሆናል። የማይታወቁ አገሮችን ስም እየጠቀሱ ለፓርማው ወይም ለምስኪኑ ህዝብ መናገር ይቻላል ግን ስለአውሮፓ ሲናገሩ ቢያንስ፣ ትንሽም ቢሆን፣ መርጃዎችን ቆፈር ቆፈር ማድረግ ይጠቅማል። እርሳቸው ፌስቡክ አሉባልታ ያሰራጫል እያሉ በእየጊዜው ይከሱ የለም?
ለማንኛውም ፈረንሳይ ኢንተርኔት አፍናለች የሚለው መረጃ የሃሰት መረጃ (Fake News) AP እና ሌሎችም ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፓርላማ ውስጥ የተገኘው የፈረንሳይ አምባሳደር ንቆን አቤቱታ ላያቀርብ ይችል ይሆናል እንጅ፣ አንድ ጠንከር ያለ አገር መሪ እንዲህ ቢል አስተባብል ብለው እንደሚያፋጥጡት እርግጠኛ ነኝ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች መታወቂያ ካርድ እስከ አራት ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተሰማ
=======#=======
ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተዋቀረው ሸገር ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች መታወቂያ ካርድ በሕገወጥ መንገድ ከሦስት እስከ አራት ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።
ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ መመስረት ጀምሮ የመታወቂያ ሽያጭ ተግባር በብዙ አካላት በሰፊው ሲፈጸም እንደነበር ገልጸዋል፡፡
"አንድ ሰው መታወቂያውን ለማውጣት እስከ አራት ሺሕ ብር መክፈል አለበት" ካሉ በኋላም፤ "ክፍያውን ሳይፈም መታወቂያውን መውሰድ ግን የማይታሰብ ነው" ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
በሕጋዊ መንገድ መታወቂያ ለማውጣት የሚሄዱ ነዋሪዎች ለወራት መመላለስ ስለሚሰለቻቸው ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ከፍለው ለማውጣት ይገደዳሉም ነው የተባለው።
ሌላኛው ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በከተማ አስተዳደሩ የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ነዋሪ እንዲሁ፤ ለብዙ ዓመታት በዚያው አካባቢ የኖሩ ሰዎች መታወቂያውን ለማውጣጥ በተደጋጋሚ ወደ ክፍለ ከተማው አቅንተው ማግኘት ሳይችሉ፣ ከሌላ አካባቢ የመጡ ነዋሪዎች ግን የመክፈል አቅም ስላላቸው ብቻ በአንድ ቀን ውስጥ መታወቂያው እንደሚሰጣቸው ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል፡፡
ሕግን ባለተከተለ መንገድ የነዋሪነት መታወቂያው በገንዘብ የሚቸበቸበውም ደላሎችና የክፍለ ከተማ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች በመናበብ ነው የተባለ ሲሆን፤ ደላሎች ሰዎችን ላመጡበት እንዲሁም የክፍለ ከተማው ሠራተኞችም መታወቂያውን ለሠሩበት ከሚገኘው ገንዘብ ድርሻቸውን እንደሚወስዱ ነው የተገለጸው፡፡
በኢዮብ ተስፋዬ
/channel/addismaleda
ምርጫ ቦርድ፤ የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔን በድጋሚ ለመሰረዝ የሚያስገድዱ ችግሮች አጋጥመውት እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተናገሩ
ድጋሚ በተደረገው የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ ላይ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በድጋሚ “እንዲሰረዝ” የሚያስገድዱ ተግባራት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሲፈጸሙ እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተናገሩ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በህዝበ ውሳኔው ዕለት፤ ምርጫ ቦርድ “ሌላ ውሳኔ እንደሰጠ” አድርገው መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደነበርም አቶ ውብሸት ገልጸዋል።
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ይህንን ያሉት፤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28፤ 2015 በተካሄደ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው። አቶ ውብሸት በንባብ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ሪፖርት፤ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ ያለፋቸውን ሂደቶች፣ የተገኘውን ውጤት እንዲሁም ያጋጠሙትን ችግሮች ዘርዝረዋል።
በ26 ገጾች በተዘጋጀው በዚሁ ሪፖርት ውስጥ በችግርነት ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ፤ በወላይታ ዞን ተከስተው ነበር የተባሉ የህግ ጥሰቶች ይገኙበታል። በወላይታ ዞን ባለፈው ጥር ወር የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ እንዲሰረዝ ምክንያት የሆኑ የህግ ጥሰቶችን አጽንኦት ሰጥተው ያነሱት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 94 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12፤ 2015 በወላይታ ዞን በድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሲያካሄድም ችግሮች እንዳጋጠሙት አቶ ውብሸት በዛሬው ሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11382/
በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ
በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የኢቦላ ቫይረስ ተጠርጣሪዎች መገኘት እና ሞት መመዝገቡን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት እንዳለ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቃል።
በተለይ በሱዳን የተፈጠረውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ክልሉ በአጎራባች ወረዳዎች በኩል በከፈተኛ ሁኔታ ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ በሽታው ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል።
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብተሰብ ጤና ጣቢዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሱዳን ዳባላይ በምትባል ስፍራ ከ150 በላይ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እሱን ለማጣራት ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች አካላት አካላት ጋር በመሆን ጥናት እየተደረገ ይገኛል።(ብስራት ራድዮ)
ምክር ቤቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲዳራጅ ውሳኔ አሳለፈ።
**********
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት በዛሬው ቀጣይ ዉሎው የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተካተቱበት "የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል" በሚል ስያሜ አዲስ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባካሄዱት ሕዝበ ውሳኔ በአንድ ክልል የመደራጀት ፍላጎታቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በአንድ ክልል እንዲደራጁ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ወስኗል፡፡
"የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል"በሚል በአዲስ የተደራጁት በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጎፋ፣ በጌዲዮ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በኮንሶ ዞኖችና በደራሼ፣ በቡርጂ፣ በአማሮ፣ በኧሌና በባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው፡፡
ቀድሞ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ውስጥ የነበሩ የሀድያ፣ የሀላባ፣ የከምባታ ጠምበሮ፣ የስልጤ፣ የጉራጌ ዞኖችና የየም ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በነባሩ ክልል የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሏል።
እስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታን እንዲያስጠብቅ አሳሰበች
የኢትዮጵያ መንግሥት ኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነውን የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ማስጠበቅ አለበት ሲሉ፤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
የእስራኤል መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ነው ብሎ እንደሚያምንም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን ጉዳዩ የፖለቲካ ጥቅም ግጭት ያለበት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንዳለበት ነው ያስታወቁት።
ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በገዳምነት ይጠቀሙበትና ይኖሩበት እንደነበር የሚነገርለት በእስራኤል ጎለጎታ ተራራ ላይ የሚገኘው የዴር ሡልጣን ገዳም፤ በተለያየ ጊዜ የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳበታል፡፡
በተለይ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የባለቤትነት ጥያቄ ስታነሳ ቆይታለች፡፡ በተደጋጋሚም ገዳሙ ውዝግብና ግጭቶችን ያስተናግዳል፡፡
ይዞታዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ቢነገርም፤ ግብጻውያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ ቦታ ነዉ፡፡
አምባሳደር አለልኝ ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉና ከዚያ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
አዲስ ማለዳ
/channel/addismaleda
ትናንት በሬሜዲያል ፕሮግራም የተሰጡት ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
=======#=======
ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ትናንት ሰኔ 26/2015 በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት በጀመረው የ2014 የ12ኛ ክፍል ሬሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ሂደት ወቅት፤ ባጋጠሙ ችግሮች ምክንያት የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።
2) ቀደም ብሎ በኹሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 እንዲሰጥ።
3) በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው በዚህ መረጃ ትላንት ፈተናውን መሰጠት ከጀመረ በኃላ አጋጥመዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር ይፋ አላደረገም።
/channel/addismaleda
እነሆ የሶስተኛው የአለም ጦርነት ሊጀመር እጅግ ተቃርቧል
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ንጹሃን ዜጎችን በመፍጀት ታሪክ ያላቸውን የክላስተር ቦምቦችን ለዩክሬን ለመላክ ወሰኑ።
ፕሬዚዳንቱ “አስቸጋሪ” ያሉትን ይህንን ውሳኔ ደግፈው በጽኑ ተሟግተዋል።
ጂጂጋ ታይዋን የደረሰው የእሳት አደጋ የፈጠረው የንብረት ውድመት እጅግ አሰቃቂ ነው። ዛሬ ጠዋት በድሮን የተነሳው ይህ ምስል የውድመቱን መጠን ያሳያል።
የሶማሊላንድ የእሳት መከላከያ እሳት ማጥፋቱን ለማገዝ መጥተዋል። አምና በሶማሊላንድ በደረሰው የእሳት አደጋ ሶማሌክልል ልዩ ሀይልና እሳት መከላከል ብርጌድ እገዛ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 👇
/channel/MuktarovichOusmanova
ትናንት ማታ በጂጂጋ አዲሱ ታይዋን የገበያ ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል
የእሳቱ መነሻ ምክንያት እየተጣራ ይገኛል። አደጋው የደረሰው ውድቅት ሌሊት በመሆኑ ለማጥፋት አስቸጋሪ አድርጎታል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ንብረት ሊወድም ችላል።
ለተጨማሪ መረጃ እመለሳለሁ።
ቴሌግራሙን join ያድርጉ
ሁለት ዜናዎች
አንድ፣
ዓለም ዓቀፉ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) ዓለማቀፍ ረድኤት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያቋረጡትን የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ባስቸኳይ እንዲጀምሩ ተማጽኗል። ድርጅቱ ይህን ጥሪ ያደረገው፣ በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናት ኹኔታ "ከአጣዳፊ ደረጃ" ማለፉን የገለጠው ድርጅቱ፣ የምግብ እጥረቱ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥሪታቸውን እንዱሸጡ፣ በልመና እንዲሠማሩና የሕጻናትን ጉልበት በገቢ ምንጭነት እንዲጠቀሙ እያስገደዳቸው መኾኑን ጠቅሷል። ድርጅቱ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዕርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ባስቸኳይ እንዲፈልጉና የምግብ ዕርዳታ የሚጀመርባቸውን አካባቢዎች በቶሎ ላይተው እንዲያሳውቁ ጠይቋል።
ሁለት፣
የአማራ ክልላዊ መንግሥት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል ያሉ የማንነትና የወሰን ውዝግቦች በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈቱ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት ይህንኑ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩት፣ የክልሉ ኮምንኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ፣ የኹለቱ ክልሎች የግዛት ይገባኛል ውዝግብ በሕዝበ ውሳኔና በሕጋዊ አግባብ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበር ይታወሳል።
ዋዜማ
በአዳማ/ናዝሬት እየተካሄደ ያለው የህዝብና የቤት ቆጠራ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዳማ ከተማ ሕዝብ ቆጠራ ማካሄድ መጀመሩ "ግርታ" እና "ስጋት" እንደፈጠረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል። የመንግሥት መረጃ መዝጋቢዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የብሄር ማንነት፣ ሃይማኖት፣ የቤተሰብ ብዛት፣ ጾታና ሌሎች መረጃዎችን እየሰበሰቡ እንደኾነ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ ኮምንኬሽን ጽሕፈት ቤት ግን፣ መረጃዎቹን መሰብሰብ ያስፈለገው በቅርቡ በከፍተኛ ደረጃ የሰፋችውን ከተማ በአዲስ መልክ በክፍለ ከተማና ወረዳ ለማደራጀት መኾኑን ነግሮናል። የብሄር ማንነትን በቆጠራው ለምን ማካተት እንዳስፈለገ ዋዜማ ላቀረበችው ጥያቄ፣ ጽሕፈት ቤቱ የመረጃው መካተት "ምንም ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም" ብሏል።
በሸዋሮቢት ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ የተባለ የፖሊስ አባል በከተማ 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት ላይ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። የከተማው አስተዳደር የፀጥታ ኋላፊ የነበሩት አቶ አብዱ ሁሴን ከቀናት በፊት መገደላቸው ይታወሳል።
Читать полностью…የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች የሱዳን አየር ክልልን ማቋረጥ ትተዋል
#Ethiopia | በሱዳን በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት
ምክንያት ለደህነት ሲባል በሰሜን ከአውሮፖ አሜሪካ እና ካናዳ የሚነሱ በረራዎች በግብፅ ቀይ ባህር በሳውዲ አየር ክልል ኤርትራን አቋርጦ ይገባሉ።
ይህም ለተጨማሪ የበረራ ሰአት እና የነዳጅ ወጪ ይዳርጋል
ይህ የበረራ መስመር አንድ ሰአት ያህል ይጨምራል
የሰላም ዋጋ ብዙ ነው በምድራችን ሰላም ይስፈን።
Via ቃለየሱስ በቀለ
ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ዕድገት ከሰብ-ሰሀራ ሀገራት በቀዳሚነት እየገሰገሰች ነው መባሉን ተከትሎ (መረጃው ስህተት ነው)...በአማራ ክልል አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በስድስት ጤና ጣቢያዎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ፤ያልተከፈላቸው የስድስት ወር ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው በዛሬው ዕለት በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ ናቸው።
ያ ሁሉ የዕድገት ማብራሪያ ደመወዝ መክፈል ስላልቻለች ሀገር ነው ቢባል ማን ያምናል!
Dereje Habtewold
#ፓርላማ #FactCheck ዛሬ በፓርላማ የ IMF ዳታን መሰረት በማድረግ "ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት በኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም" ተብሏል።
እውነታውስ?
የ IMF ዳታ እንደሚያመለክተው ዘንድሮ (እ.አ.አ በ2023) ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ከሰሀራ በታች ያሉት የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል እነዚህ ናቸው:
1. ሴኔጋል- 8.3%
2. ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ- 6.3%
3. ርዋንዳ እና አይቬሪ ኮስት- 6.2%
4. ኢትዮጵያ እና ኒጀር- 6.1% ናቸው።
በቀጣዩ አመት (2024) ከፍ ያለ እድገት ያስመዘግባሉ የተባሉት ሀገራት ደግሞ:
1. ኒጀር- 13%
2. ሴኔጋል- 10.6%
3. ርዋንዳ- 7.5%
4. ሞዛምቢክ- 8.2%
5. አይቬሪ ኮስት- 6.6%
6. ኢትዮጵያ- 6.4% ናቸው።
ሪፖርቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል: https://www.imf.org/en/Publications/REO/SSA/Issues/2023/04/14/regional-economic-outlook-for-sub-saharan-africa-april-2023
ስለዚህ መረጃው የተሳሳተ ነው።
Via Ethiopia Check
"ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።" የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለ ጠ/ሚ አብይ ካነሷቸዉ ጉዳዮች መካከል
Via: ዳጉ ጆርናል
#ማስታወቂያ! እንዳያመልጣችሁ‼️
# DMC Real Estate‼️
የመጨረሻ ዙር ማስታወቂያ ዋጋ !!!
ለተወሰኑ ቤቶች ብቻ የተሠጠ፤ ታላቅ ቅናሽ ለቡ መብራት ላይ የሚገኝ፤ በ4ቱም አቅጣጫ ድንቅ እይታ ያለው
65,395 ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር
👉 ይህ የብልሆች የኢንቨስትመንት ምርጫ ነው።
👉ከ 52.6 ካሬ ጀምሮ እስከ 147 ካሬ አፓርታማዎችን ይዞ እየተገነባ ያለ!
👉ከ 20 ካሬ ጀምሮ Ground ላይ ለንግድ እሚሆኑ ሱቆችንም ይዟል
15% ቅድመ ክፍያ በ 710,100 ብር በመኪና ዋጋ የቤት ባለቤት ይሁኑ ለካሬ 90,000 ብር ከ ሁለተኛ ፎቅ ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ አፓርትመንቶችን እና ሱቅችን በሽያጭ ላይ መሆናችነን ስናበስረዎት በታላቅ ደስታ ነው።
❤ ልብ ይበሉ ይህ ዋጋ እሚቆየው ለትንሽ ቀናቶች ብቻ ስለሆነ ይፍጠኑ!
👉 Aluminum Formwork መጠቀማችን ልዩ ያደርገናል
DMC Real Estate
ዋና ቢሮ ለቡ
ለበለጠ መረጃ:-
+251918642895
+251906949686
ወይም
You can contact direct call or via Telegram , WhatsApp , Imo , Viber +251906217873
kefiegashaw12@gmail.com /channel/Engineergashaw
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ
=======#=======
ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አዲስ ማለዳ ከምክር ቤቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡
በመርሻ ጥሩነህ
/channel/addismaleda
#ትግራይ ክልል ህወሓት በምትባል አውሬ ምክንያት ባለፉት #ሶስት አመታት በነበረው ጦርነት እናቶች ልጆቻቼውንና #ባሎቻቸውን አጥተው በምታዩት መልክ ኑሮን ይገፋሉ። #ህወሓት ለትግራይ ህዝብም ጠላት ናት የምንለው በምክንያት ነው።
Читать полностью…የሸዋሮቢት ከተማ የጸጥታ ኃላፊ አብዱ ሁሴን ተገደሉ
=======#=======
ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን የሽዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ኃላፊ አብዱ ሁሴን ከሰዓታት በፊት መገደላቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።
ኃላፊው የተገደሉት በጥይት ሲሆን፤ ግድያውን የፈጸመው አካል ማንነት ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።
የኃላፊውን መገደል ተከትሎ የአካባቢው መንገድ በመከላከያ ሰራዊት መዘጋቱን የከተማ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
አዲስ ማለዳ ስለ ኃላፊው ግድያና በከተማዋ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፤ ፖሊስን ጨምሮ ለከተማዋ አመራሮች ስልክ ብትደውልም መረጃ መስጠት የሚችሉበት ሁኔታ ላይ አለመሆናቸውን በመግለጽ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ሽዋሮቢት የአካባቢው ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ የሚገደሉባት ከተማ ስትሆን፤ ከአመራሮች ግድያ በተጨማሪ በመንግሥት የጸጥታ ተቋማት ላይ ጥቃቶች ሲስነዘሩ ነበር።
አማራ ክልል በተለይ የፌደራል መንግሥት መከላከያ አሰማርቶ፤ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ፋኖ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ በየአካባቢው አመራሮች እየተገደሉ መሆኑ ይታወቃል።
በመርሻ ጥሩነህ
/channel/addismaleda
#በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ የደጋሰኝን ከተማ እና የአካባቢው አርሶ አደር የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እንደገጠማቸው አሳወቁ‼
በአማራ የአርሶ አደሮች የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ አቅርቦት ጥያቄ ቁጣ እያቀሰቀሰ ነው።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ማቻከል ወረዳ አርሶ አደሮች ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ይቅረብልን የሚል ጥያቄ የያዙት አርሶ አደሮች፣ መንግሥት ለጥያቄያችን ምላሽ ይስጠን እያሉ ነው።
ማዳበሪያ ከነጋዴ በ300 መቶ ብር ጭማሪ እየገዛን ነው። ምርጥ ዘርም ከ1500 እስከ 2000 ብር በአየር ላይ እየገዛን እና ለከፍተኛ ኪሳራ እየተጋለጥን ነው ብለዋል።
መንግሥት ለአርሶ አደሩ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።
ያነሱት ጥያቄ መሠረታዊ እና ጊዜ የማይሰጠው ጥያቄ ነው።