muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

የትግራይ አባቶች የኢትዮጵያ ሲኖዶስ በእነሱ ላይ ያወጣውን መግለጫ መልስ ከመስጠት ይልቅ አባ ሰረቀ ብርሃን ያሰራቸው አካል በአስቸኳይ እንዲለቃቸው አለበለዝያ ግን በመላ ትግራይ ህዝቡን አስተባብረን ሰልፍ እንወጣለን በማለት ይህንን ከስር ያለውን መግለጫ አውጥተዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በዋይት ሐውስ የተገኘውን ኮኬይን ማን እንዳስገባው አልታወቀም

ከአንድ ሳምንት በፊት፣ በዋይት ሐውስ ተገኝቷል፤ የተባለውን የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ አስመልክቶ ሲያደርግ የነበረውን ምርመራ እንዳጠናቀቀ፣ የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ አገልግሎት አስታውቋል።

“ሴክሬት ሰርቪስ” በመባል የሚታወቀው፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጥበቃ አገልግሎት ዛሬ እንዳስታወቀው፣ ጎብኚዎች ስልካቸውንና ሌሎችንም የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያቸው በሚያስቀምጡበት ሥፍራ የተገኘውን ኮኬይን፣ ማን ሊያመጣው እንደቻለ ለማወቅ ባደረገው ምርመራ፣ ከጥቅሉ ላይ የጣት አሻራ ለማግኘት አለመቻሉን፤ የተገኘውን የዘረ መል ናሙናንም፣ በወቅቱ ከነበሩት ጎብኚዎች ጋራ ለማነጻጸር በቂ እንዳልኾነ ገልጿል።

በመኾኑም፣ ኮኬይኑን ወደ ዋይት ሐውስ ማን ሊያመጣው እንደቻለ ሳይታወቅ መቅረቱን፣ የጥበቃ አገልግሎቱ አስታውቋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 9 ቀን በትግራይ ክልል ይደረጋል የተባለው ሕገ ወጥ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት" ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ እና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ

የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትናንትናው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ሐምሌ 9 ቀን በትግራይ ክልል ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 እና 38 የጣሰ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ፣ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊ አስተዳደር የሚጥስ አንድነቷን የሚጎዳ ፤ በጦርነቱ ሀብት ንብረቱ የወደመበትን እና እጅግ የተጎዳውን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ወስኗል።

በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ችግር በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉን የገለጸው ቅዱስ ሲኖዶሱ ተፈጠረ ለተባለው ችግር ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ አሳዛኝ ነው ብሏል።
ባለፈው ሰኞ ወደ በቅዱስነታቸው የተመራው የሰላም ልዑክ ወደ በመቀሌ ተጉዞ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቢሄድም ቤተ ክርስቲያኑ ተዘግቷል መቆየቱን የገለጸው ቅዱስ ሲኖዶሱ በትግራ ጊዜያዊ አስተዳደር ለልዑኩ ለተደረገው አቀባበል አመስግኗል።

በክልል ተከስቶ የነበረው ችግር በፌደራል መንግስቱ እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ አማካይነት የተፈታ ቢሆንም የሰላም ባለቤት የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማያቋርጥ መሆኑን ያስታወቀው ቅዱስ ሲኖዶሱ  ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ  የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ እንዲያስቆሙ ጭምር ጥሪውን አቅርቧል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትናንት ምሽት ካይሮ ገብተው ከፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጋር መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ግብጽ የሱዳን ጎረቤት አገራት መሪዎች በሱዳኑ ግጭት መፍትሄ ዙሪያ የሚያደርጉትን ጉባኤ ዛሬ የምታስተናግድ ሲኾን፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የደቡብ ሱዳኑ ሳልቫ ኪር ቀደም ብለው ካይሮ ገብተዋል።

ሱዳንም በውይይቱ ለመሳተፍ ዝግጁ መኾኗን ትናንት የገለጠች ሲኾን፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ጀኔራል አል ቡርሃን ይገኙ አይገኙ አልታወቀም።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዜና፡ አንድ እስራኤላዊ በጎንደር መታገቱን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በጎንደር ታግቶብኛል ሲል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ። እስራኤላዊው የታገተው ማስለቀቂያ ገንዘብ በፈለጉ ሀይሎች መሆኑም ተጠቁሟል።

ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሚገኙ መስሪያ ቤቱ ገልጿል። ታጋቹ እስራኤላዊ እድሜ በ70ዎቹ መሆኑን የጠቀሙት ዘገባዎች ወደ ጎንደር ያቀናው ከቀናት በፊት መሆኑን አስታውቀዋል።

ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን እና በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸውነ ዘገባዎቹ ጠቁመዋል። ለማስለቀቅ የተጠየቀው ገንዘብ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች እንደነበረ አና ቆየት ብሎ በተደረገ ውይይት ወደ ሺዎች መውረዱን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመላክተዋል። ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ ማለቱን ያስነበቡት ዘገባዎቹ ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም ይመስላል፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም ሲሉ እንደሚደመጡ አስታውቀዋል።
https://rb.gy/q2vgi

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ባንኮች በግድ ቦንድ እንዲገዙ ተገደዋል ይላል ሪፖርተር። በዚህም 25ቢ ብር መንግስት ሰብስቧል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢሰመኩ በኢትዮጵያ የሚያኩራራ የሰብዓዊ መብት መሻሻል የለም አለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በኢትዮጵያ የሚያኩራራ ለውጥ አለመኖሩን ተናገረ።

ኮሚሽኑ ሁለተኛውን አመታዊ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ሰዎችን አስገድዶ መሰወርን ጨምሮ፣ አዋራጅና ህገወጥ አያያዝ በሰዎች ላይ እንደሚፈጸም ገልጿል።

በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ይፈጸማሉ ያለው ኮሚሽኑ ግጭቶች በዋናነት ለሰብአዊ መብት ጥሰቶቹ መነሻ መሆናቸውን ተናግሯል። ኢሰመኮ በሪፖርቱ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ጊዜ ፍትህ ያስፈልጋል ብሏል። ኢሰመኮ በጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ማህበራዊ አንቂዎች ላይም ጥሰት ይፈጸማል ብሏል።

የትግራይ መቀሌ ቢሮውን መልሶ እያደራጀ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከትግራይ የሃይማኖት መሪዎች፣ ጀርባ ህወሓት እንዳለበት ቅንጣት ታክል እኔ አልጠራጠርም። ሆኖም ግን የህወሓት አክቲቪስቶች እንዲህ ብለው እየሰበኩ ነው ።" ከሃይማኖት አባቶቻችን የትግራይ የፖለቲካ መሪዎች ትምህርት መውሰድ አለባቸው ብለው ሊጃጅሉን ይፈልጋሉ። የእኔ ጥያቄ የሃይማኖት አባቶች የክልል መሪዎችና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባን ለመቀበል ይህንን ያክል ከተጉ ለምንድነው ፓትርያርኩና የልዑኳን ቡድኑ ለመቀበል ጉልበትና አቅም ያጡ ብቻ ሳይሆን ለምን ቤተክርስቲያን ዘግተው ተደበቁ??? መልሱ ቀላል ነው ህወሓት አልፈቀደም። ትግራይ አይደለም ሃይማኖት ትልቅ ተቋም ይቅርና ትዳርና ቤተሰብ በህወሓት ቁጥጥር ስር ነው።

ለዚህ ምሳሌ ለመስጠት የዓረና አባላት ህወሓትን የሚቃወሙ ከ150 በላይ ትዳር በህወሓት የቀጥታ ትእዛዝ ፈርሷል። አናፈርስም እምቢ ያሉ ወደ መሀል ሃገር በመሰደድ ትግራይን ለህወሓት ጥለው ወጥተዋል ይህንን ማንም ትግራዋይ ያውቃል። መቼ ይሄ ብቻ ባህር ተሻግረውም በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ትዳር አፋርሰዋል በሰሜን አሜሪካ የሚኖር የፌስቡክ ጓደኛየ ሕሉፍ ሚስቱ የፈታችው "የመለስ ዜናዊ ለቅሶ አልሄድክም ሃዘንም አልተሰማሕም በማለት የሁለት ልጆች እናት በባህር ተሻጋሪ ካድሬዎች ትዳርዋ እንዲፈርስ ተደርጓል።
ወዲ ሻምበል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች የቤቶችን ቁልፍ ሰብረው በመግባት ወረራ እየፈጸሙ ነው ተባለ

ማክሰኞ ሐምሌ 4 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ለባለእድለኞች በተላለፉ ቤቶች ውስጥ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ቁልፍ ሰብረው በመግባት ወረራ እየፈጸሙ መሆኑን የኮንዶሚኒየሙ ሕጋዊ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

በኮንዶሚኒየሙ የእጣ እድለኞች ሆነው ለባለቤቶች ቁልፍ ተላለፈው፤ ነገር ግን ተቆልፈው በተቀመጡ ቤቶች እና እስካሁን ለባለእድለኞች ባልተላለፉ ቤቶች ላይ የማይታወቁ ሰዎች ወረራ እየፈጸሙ ነው ተብሏል።

ይህን ድርጊት ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ የኮንዶሚኒየም የጥበቃ ሠራተኞች ላይም ዛቻ እና ማስፈራሪያ በማድረስ ሰዎቹ በኃይል እንደሚገቡ ነው የተገለጸው።

ነዋሪዎቹ አክለውም፤ “ተዘግቶ የተቀመጠን ቤት በኃይል ሰብረው ገብተው ወረራ ሲፈጽሙ አንድም የመንግሥት አካል ሊያሰቆማቸው የሞከረ የለም፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከመጋቢት 2015 ጀመሮ በኮንዶሚኒየሞቹ ላይ ከፍተኛ ወረራ እየተካሄደ መሆኑን በመጠቆምም፤ “ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ብናቀርብም መፍትሔ ሊገኝ አልቻለም፡፡” ብለዋል፡፡

በዚህም ወደ ኮንዶሚኒየሞቹ የሚገቡና የሚወጡ ሰዎችን ማንነት ማወቅ ባለመቻሉ ሕጋዊ ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ ከቷል ነው የተባለው።

አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኮንዶሚኒየሙ የጥበቃ ሠራተኛ በበኩላቸው፤ ማንነታቸውን መናገር የማይፈለጉ ሰዎች የተዘጉ ቤቶችን ቁልፍ በኃይል ሰብረው በመግባት እየኖሩበት ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

አክለውም ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱን በመጠቆም፤ ድርጊቱን ማሰቆም አለመቻሉን ገልጸዋል።
አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
በሶማሊያ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ የአውሮፕላን አደጋ አጋጥሟል። ብዙዎች ሙትና ቁስለኛ እንደሆነ ተዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃ እናደርሳለን

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የትግራይ ቴሌቪዥን ትናንት ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ መቀሌ ባቀኑበት ወቅት ምዕመናን ሰብስቦ በትግርኛ ቋንቋ የተሰራው ዘገባ አነጋጋሪ መሆኑ ተገለፀ‼

ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም

"ሰይጣንን ከሚያመልክ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ጋር ህብረት የለንም፣ከመንበረ ሰላማ ጎን ነን!'' - የትግራይ ተወላጅ ምእመናን
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋም በትግራይ ሕዝብ ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ሲሉ ወነጀሉ።
የተፈናቀሉ ወገኖች በተለይም የኢትዮጵያ ሲኖዶስ አባላትና አመራሮች በትግራይ ተወላጆች ላይ በደረሰው የዘር ማጥፋት ተግባር ላይ በግልጽ መሳተፋቸውን ገልጸዋል"ይላል ዘገባው።
አባቶችን የሚያንቋሽሽ የተለያዩ ፅሁፎችን በመያዝ አባቶችን ለማሸማቀቅ ሞክረዋል።

በተለይም አንድ ወጣት በትቢት አባቶችን በማንጓጠጥ የተናገረው ንግግር ብዙዎችን አሳዝኗል ።
“ኦርቶዶክስ የአማራ ናት” የሚል የተሳሳተ ትርክት ማስተላለፍ ስለተፈለገ እንጂ ጦር አዝምተው የወጓቸው እና ያስተባበሩባቸው ፖለቲከኞችን አበባ ጎንጉነው እና ምንጣፍ አንጥፈው ሲቀበሉ ፤ እጃቸው ላይ ከመስቀል ውጭ ይዘው የማያውቁ የኃይማኖት አባቶችን በር ዘግተውባቸዋል።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መልስ እንደምትሰጥ ይጠበቃል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል ባህርዳር ላይ የገበሬዎች ድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ እየበረታ ነው።
ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ባለመቅረቡ መዝራት አለመቻላቸውን በመጥቀስ እያማረሩ ይገኛሉ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ የውጭ አገር ገንዘብ እና አደገኛ ዕፅ ተያዘ
=======#======

ሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ የውጭ አገር ገንዘብና አደገኛ ዕጽ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለጸ።

መነሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አድርጎ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ ሊወጣ የነበረ 44 ሺሕ 440 ዩሮ፣ 11ሺሕ 850 የአሜሪካን ዶላር፣ 20 ሺሕ 480 ፖውንድ (GBP)፣ 3ሺሕ 700 ዲርሃም፣ 3መቶ የሲዊዝ ፍራንክ እና 1ሺሕ 700 የሳውዲ ሪያል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና የአየር መንገድ የሴኩሪቲ ሠራተኞች ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከውጭ አገር ተጠርጣሪዎች ጋር መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

በተመሳሳይ መነሻውን ብራዚል ሳኦፖሎ አድርጎ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ወደ ሌሎች አገሮች ሊተላለፍ የነበረ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ 17.90 ኪሎ ግራም ኮኬይን አደገኛ ዕፅ፤ የጸጥታ አካላቱ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ ከሦስት የውጭ ሀገር ዜጎች ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

በመሆኑም በመሰል የወንጀል ድርጊቶች የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖች በየትኛውም መንገድ ማምለጥ እንዳይችሉ የጸጥታ አካላቱ እየወሰዱ ያሉትን ሕጋዊ እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
/channel/addismaleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ አመሩ

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ አመሩ

የሰላም ልኡኩን በመምራት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ አባገዳዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተጉዘዋል።

በዕለቱም ብፁዕ አቡነ እርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጀና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተገኝተው ለቅዱስ ፓትርያርኩንና ለልኡካኑ ሽኝት አድርገዋል።

ኢኦተቤ ቴቪ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአዲስ አበባ ከተማ በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ሆኖ ሲፀድቅ ከ55 በመቶ በላይ ለካፒታል በጀት ሆኖአለወ።

ለስራ ማስኪያጃው በማነሱ የመንግስት ሰራተኛው አሳር የሚቀጥል ሲሆን ቢሮ ማሰማመሩ የሚቀጥል ይመስላል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ግብፅና ኢትዮጵያ የጋራ መግለጫ አወጡ።
በአራት ወራት ውስጥ የሶስተዮሽ ስምምነትን ለመፈራረም የተስማሙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሊት ወደ ሚቀጥለው አመት (2003/4) አመት ምህረት ለማዘግየት ተስማምታለች።
ይህም ማለት በዚህ ክረምት የህዳሴው ግድብ ውሃ አይይዝም።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአሮጊቷ ጸሎት

አንዲት ዕድሜ የበረከተላቸው ሴትዮ ጧት ማታ፣ ሌት ከቀን “ለንጉሥ እድሜ ስጥልኝ!” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ይህንም ነገር ከጊዜ ብዛት ንጉሡ ሰሙና ተደነቁ፡፡ የተደነቁበትም ምክንያት ሌላ ሳይሆን እራሳቸው ሃይለኛ ነበሩና እንዴት ለእኔ እድሜ የሚለምን ሰው ይገኛል በማለት ነው፡፡ ነዋሪዎችም “ንጉሥ ሆይ እርግጥ ያለ ጥርጥር አንዲት አሮጊት ለንጉሥ ዕድሜ ይለምናሉ።” ብለው ለንጉሡ አረጋገጡ፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ እኚያ አሮጊት ወዳሉበት ሄዱና ጠየቋቸው፡፡ “እኔ ክፉና ሃይለኛ ነኝ፡፡ ሰው ሁሉ ሞቴን እንጂ መኖሬን አይደፍግም፡፡ አንቺ በምን ምክንያት ነው ለእኔ እድሜ የምትለምኝው? ለመሆኑ እንደ እኔ አሳብ ቢሆን ሁሉም ይጠላኛል እንጂ ለእኔ እድሜ የሚጸልይ ይኖራል አላልኩም ነበር።” ብለው ቢናገሩ ፣ አሮጊቷ ”ንጉሥ ሆይ! በእኔ ዕድሜ ከአንተ ጋራ አራት ንጉሥ ማየቴ ነው፡፡ የፊተኛው ደግ ነበር፤ የኋለኛው ክፉ ሆነ፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ሦስተኛው የበለጠ ክፉ ሆነ፡፡ አንተ ደግሞ ከሁሉ የባስክ ክፉ ሆንክ፡፡ ስለዚህ ደግሞ ከአንተ የባሰ እንዳይመጣ ለአንተ ዕድሜ እለምናለሁ” ሲሉ መለሱላቸው ይባላል፡፡

የእኛ እናቶች ፣ በዕድሜ የገፉ ባልቴቶች ለ'ንጉሡ' ምን ብለው ይጸልዩ እንደሆን የሰማዩ አምላክ ነው የሚያውቀው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

107 ካሬ

110 ካሬ

115 ካሬ

120 ካሬ

127 ካሬ

138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won
👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሳዛኝ ዜና ከግብፅ 🇪🇬

ከትላንትና ወዲያ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ማዲ የሚባል ሰፈር ግብፃዊያን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ገድለውታል።

ኢትዮጵያዊዉ ስደተኛው ወንድማችን ሱቅ ከፍቶ የሚሰራ ሲሆን አንድ ግብፃዊ ሲጋራ ሊያስረክበው ይመጣል። በዛ ስአት እርስ በእርስ ያለመግባባት ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ግብፅዊዉም ይይሄዳል።

ኢትዮጵያዊዉ ወንድማችን ሰላም ነው ብሎ ሱቅ ስራውን እየሰራ እያለ ግን ግብፃዊዉ ብዙ ሰዎችን ሰብስቦ መጥቶ ጥቃት አድርሰውበታል።
ወገናችንም በደረሰበት ጥቃት ከዚህ ዓለም ተሰናብቷል::

በዚህም የተነሳ በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ሰልፍ ፍትህ ለወንድማችን እያሉ ይገኛል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ 
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

            107 ካሬ

            110 ካሬ

             115 ካሬ

             120 ካሬ

             127 ካሬ

             138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 @Tsion_won
👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354           
      +251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አባ ሠረቀ በቦሌ
+++++
(አደባባይ ሚዲያ)

ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጋለሞታ እያለ በመሳደብ የሚታወቁት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ በአሁን ሰዓት ከአውስትራልያ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይገኛሉ። ለማይቀረው ሕገ ወጥ ሹመት ወደ መቀሌ ትራንዚት ሊያደርጉ ተዘጋጅተዋል።

የመንበረ ሰላማ ሐሳብ ዋና አመንጪ እና አቀንቃኝ ናቸው። የዳያስጶራው ክንፍ ኾነው፣ ከውጭ ገንዘብ እየላኩ እንቅስቃሴውን ሲደግፉ ቆይተዋል። በቅርቡ እንኳ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በጸጋየ በርሄ ለሚዘወረው የመንበረ ሰላማ ተገንጣይ ቡድን ልከዋል። ምን ይሄ ብቻ "አማራ የሚባል የለም ይሉና መልሰው አማራ በደለን እያሉ ይጮኃሉ። ግን አባ ሰረቀብርሃን የረገሙዋትን ኢትዮጵያ መሬትዋን ሲረግጡ ምን ተስመቶት ይሆን? እንግዲህ መቀሌ ያላችሁ ከተደበቃችሁበት ውጡና አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቀባበል አድርጉላቸው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር ዜና

የትግራይ አባቶች

ሐምሌ 9/ 2015 ዓ/ም አክሱም ፅዮን ማርያም ላይ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚሾሙ ለክልሉ መንግሥት እና ሚድያዎች ጥሪ አስተላልፏል
እንግዲህ ዙሩ ከሯል ከአሁን በፊት ብሔር ብሔረሰቦች በሚል እርስ በእራሳቸው የተሿሿሙት መጨረሻው ምን እንደሆነ አይተነዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር በበርካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ፥ ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ያጋጠመውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው፡፡

ችግሩ እንደተቀረፈም የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቱ ወደነበረበት እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከሌለህ የለህም

ኢትዮጵያ 💔

* እናት የጠፋው ልጄ ከውጪ ይመጣ ይሆን

ወይንስ

* ሀብታም ሆኖ ይሆን እያለች ነው

ነገር ግን ልጇ በኑሮ ና በተለያዩ ምክንያት

ጎዳና መኖር ጀምሯል
የአእምሮ እክል አጋጥሞታል

አሁን እናት ና አባት መጀመሪያ ሲያዩት ደስ ብሏቸው ተቀበሉት

ከዛ ምንም እንደሌለው
ጎዳና እንደሚኖር ና ትንሽ የአእምሮ ችግር ያለበት መሆኑን ሲያውቁ ግን

* ፊታቸው ተለዋወጠ
* አረ ይሄ ልጃችን አይደለም
* አረ ይሄ ልጃችን አይሆንም
* አረ ይጣራ በህክምና ይታወቅልን

ማለት ጀመሩ

የጠበቁት ና ያገኙት ነገር አልጣጣም አላቸው

በቅርቡ በሚታወቀው በDNA ምርመራ መሰረት እናቱ ትሆን አትሆን የሚለው መልስ የሚያገኝ ሲሆን

እኛ ጉርሻዎች ከወዲሁ እናቱ እንዳትሆን ምኞታችን እንግለፃለን

ግን ኤፍሬም ሌላ መልካም የሆኑ ቤተሰቦች ይኖሩት ይሆን ?

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

©ጉርሻ ፔጅ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
----------------------------------------------------

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በክልል ትግራይ መቐለ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል ።

ትግራይ ቤተክህነት አባቶች ለይቅርታና እርቅ በራቸውን ዘግተው ፓትሪያኩን መመለሳቸው ብዙዎችን ማሳዘኑ የሚታወስ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የትግራይ ክልል ቤተክህነት የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቆ፣ ፓትሪያክ ቢልክም፣ ይቅርታው የረፈደ ነው በማለት እንዲህ የቤተክርስቲያንን በር በፓትሪያኩ ላይ ዘግተዋል።
ለታሪክ ይቀመጥ።

የሰሜን እዝን በማጥቃት ጦርነት የከፈተውን ወያኔ የተቃወመ አንድም የሀይማኖት አባት አልነበረም ከትግራይ።
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እንወርዳለን ሲሉ የተቃወመ አልነበረም።
ጅራፍ ገርፎ ይጮሀል ሆኖ ይህ አሳዛኝ ነገር ተከስቷል።
መዝግቦ ማለፍ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሶማሌ ሐገረ ስብከትና የምስራቅ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ በጅግጅጋ ከተማ የንግድ ማእከል ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ጉዳት ተመለከቱ።
*********
የሶማሌ ሐገረ ስብከትና የምስራቅ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ ከቀናት በፊት በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን የንግድ ማእከል ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል ።

ብፁዕነታቸው ዛሬ ከሰአት በሁዋላ ከሶማሌ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ከመላከ መዊ ቆሞስ አባ ፅጌ ደስታ ጋር በመሆን በንግድ ማእከሉ ላይ በድንገት የተከሰተው የእሳት አደጋ ላይ የደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው ተመልክተዋል ።

ብፁዕነታቸው አቡነ በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን በንግድ ማእከል ነጋዴዎች ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በጣም የሚያሳዝንና ጉዳቱ የሁላችንም ነው ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ የሶማሌ ክልል እና የጅግጅጋ ከተማ ሰላም የሰፈነበትና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነ ክልልና ከተማ በመሆኑ መላው የሀገሪቱና የክልሉ ህዝቦች አለን በማለት ተጎጂዎቹን ለመደገፍ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በእሳት አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የተቻለውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች የተናገሩት ብፁእነታቸው በሐገር ውስም ሆነ በውጪ ሐገራት ያሉ ኦርቶዶክሳውያንም ሆኑ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ወደ ቀደመ ኑሮዋቸው እንዲመለሱ የክልሉ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ሁሉ እንዲሳተፉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

የሶማሌ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መላከ መዊ ቆሞስ አባ ፅጌ ደስታ በበኩላቸው የደረሰው ጉዳት እንደ ማህበረሰብ ሁሉንም ያሳዘነ መሆኑን ጠቅሰው ጉዳት የደረሰባቸውን መደገፍ ይገባል ብለዋል።

መረጃው Somali Fast Info

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በፆታዊ ጥቃት የተማረሩ የመቀሌ ሴቶች ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው ነበር።
ወያኔ ሆዬ ካድሬዎቹን አስርጎ ሰልፉን Politicize አደረጋት !

ሴቶቹ ሰልፉን የጠሩት ስለሚደርስባቸው መጠነ ሰፊ ፆታዊ ጥቃት አቤቱታ ለማቅረብና ድምፃቸውን ለማሰማት ነበር።
ትግራይ ቲቪ ሆዬ የሰልፉን አላማ ገለል አድርጎ ፊት ለፊት የወያኔን መፈክር ገጭ አድርጎ ስለፕሪቶሪያ እያወራ ነው።
ቆይ እስኪ ....የፕሪቶሪያው መድረክ በትግራይ ሲፈፀሙ ስለቆዩትና አሁንም እየተፈፀሙ ባሉት ፆታዊ ጥቃቶች ዙሪያ አጀንዳ ይዞ መክሮበት ነበር ?

በጭራሸ

ጉዳዩ መድፈር የለመዱ ታጣቂዎች በመቀሌና በዙሪያዋ ሴቶችን መድፈር መቀጠላቸው ነው እናቶችን ሰላማዊ ሰልፍ ያስወጣው።

እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱ ሴቶች በግድ እንዲወልዱ ተደርገው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ካንፓስ ተኝተው እየታረሱ ነው።

ምክንያቱ በትግል የወደቁ የትግራይ ወጣቶችን ለመተካት የሚል ነው።

ወያኔ ግን ክፉ ነች።

የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ካልተገላገለ መጪው ዘመን ጨለማ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከ4ሺህ በላይ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መደረጉን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት የይቅርታ አሰጣጥ አዋጅና መመሪያን ያሟሉ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ተደርጓል ብለዋል የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ገረመው ገብረፃድቅ ለሕግ ፍትሕና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት።

በዚህም 4 ሺህ 401 ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ መኾናቸውን አንስተዋል። ከዚህ ውስጥ 4ሺህ 308 ወንዶች ሲኾኑ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

በክልሉ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በየማረሚያ ቤቱ ያሉ ታራሚዎች በፊዴራል ይቅርታ አወሳሰንና አሰጣጥ መመሪያ 966/2015 መሠረት በቀጣይ ይቅርታው ተጣርቶ ለፌዴራል ይቅርታ ቦርድ እንዲላክ ለማረሚያ ቤት መመሪያ መተላለፉንም ኀላፊው አቶ ገረመው ገልጸዋል።
አሚኮ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በፍርድቤት ሊከሰስ ነው!

ከሰሞኑ የአማርኛን የትምህርት ክፍልን እዘጋለሁ ብሎ በእነ ዶ/ር ንጉስ ታደሰ በኩል የእውር ድንብር ውሳኔ ያሳለፈው ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በፍርድቤት ክስ ሊመሰረትበት እንደሆነ ተሰምቷል።

ዩንቨርስቲው አማርኛ ቋንቋን ጨምሮ የባህል ማዕከሉን የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪክ ጥናት ማዕከልን፣ ታሪክንና ሌሎች 18 ዲፓርትመንቶችን እዘጋለሁ በማለት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲው ክስ ሊመሰረትበት መሆኑን እና በቅርቡ ፍርድቤት ሊቀርብ እንደሆነም ታውቋል።

ዝርዝር ትንታኔውን ይዘን እንመለሳለን
ብሏል መረጃ ቲቪ

Читать полностью…
Subscribe to a channel