በሀገር ውስጥ ሰው እንዳይፈናቀል በፅሁፍ ያሉ ህገመንግስታዊ ህጎች ብቻ በቂ ናቸው። ሌላ አዋጅ ገለመሌ አያስፈልግም። በአዋጅ ለማፈናቀል እየታቀደ ይመስላል።
Читать полностью…ሰበር ዜና!
ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ በወልድያ ከተማ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በከተማዋ በተለይ ፒያሳ ዳቦ ቤቱ አከባቢ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ አድማሱን እያሰፋ በአሬሮ፣ በመናኸሪያው ጀርባ፣ በቲንፋዝ እና በማረሚያ ቤቱ አከባቢ ከባድ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የከተማዋ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።
ምንጮቻችን አክለውም የተኩስ ልውውጡ በቡድን መሣሪያዎችም ጭምር የታገዘ ነው ያሉ ሲሆን፤ ነገር ግን ተኩሱ በማን እና በማን መካከል እንደሆነ ማረጋገጥ አልቻልንም ብለዋል።
ዘገባው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው!
የዚህ መኪና ባለቤት ዴንማርካዊ ነው
ከእለታት በአንዱ ቀን በጠዋት ከቤቱ ሲወጣ ይህች እርግብ የመኪናው መስታወት ላይ እንዲህ አድርጋ ጎጆዋን ሰርታ ያገኛታል
እንቁላል ደግሞ ጥላበታለች
የመኪናው ባለቤት ይህንን ሲመለከት ሊረብሻት አልፈለገም:: ይልቁንስ ለአንድ ወር ያህል መኪናውን አልነዳውም
👇🏾
“ጎጆዋን ሰርታ እንቁላሏን ለመፈልፈል የእኔን መኪና ከመረጠች ምርጫዋን ማክበር አለብኝ!"
ሰው ለመሆን ብዙ መንገዶች አሉ
ሰው ሁን !❤️🙌🏼
Via Zemelak Endrias
የትግራይ ቤተከርስቲያን አልመለሰም ብለው ዛሬ የጳጳሳት ማፅደቅ እንደሚጀምሩ አሳውቀዋል ።ቀጣይ የኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን ውሳኔ የትግራይ ቤተከርስቲያን ጳጳሳት ሹመት እንዲሻር እንዲወገዙ የሚያደረግ ውሳኔ ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን አባቶች በተደጋጋሚ የተማዕፅኖ "ኑ እንወያይ የሚል ጥሪ ለትግራይ አባቶች ቢያቀርቡም በራሳቸው ውሳኔ ይሁን በትግራይ በመንግሥት ወይም ብሄርተኞች ተፅዕኖ ደፍረው ያላቸውን ችግሮች ከመናገር ይልቅ ጭራሽ በራቸውን ዘግተው መሸሽን ነው የመረጡት።
ወዲ ሻምበል
በዛሬው ዕለት ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተበረከተላቸው። ላስሩት ትምህርት ቤቶች፣ ለማህበራዊ አገልግሎታቸው የተሰጠ ነው ተብሏል።
Читать полностью…ሳላዲን ሰዒድ ጫማ ሰቀለ
በተለያዩ ክለቦች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው ሳላዲን ሰዒድ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ከስኬታማ የአስራ አምስት ዓመታት በላይ የእግር ኳስ ህይወት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ጫማ መስቀሉን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
ሳላዲን ለእግር ኳስ ቤተሰቡ ያለውን ምስጋናም አቅርቧል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተ ሲሆን አምና በሲዳማ ቡና ቆይታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ልጃቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ አስመረቁ
*************
አቶ ደመቀ መኮንን በፌስቡክ ገጻቸው የሚከተለውን ብለዋል ፦
በመላው ሀገራችን በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የምረቃ በዓላቸውን ላካሄዱ እንዲሁም በዝግጅት ላይ ላሉ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ::
አንጋፋው እና ታላቁ ዩኒቨርሲቲያችን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው እለት የምረቃ በዓሉን አካሂዷል:: ለዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች በሙሉ ከብዙ ጥረት በኋላ ላሳካችሁት ግብ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ::
ተመራቂዎቹን ለዚህ ክብር ለማብቃት ወልዳችሁ ለፍታችሁ ያሳደጋችሁ ወላጆች እንዲሁም በርትታችሁ ያስተማራችሁ መምህራን እንኳን ፍሬያችሁን ለማየት አበቃችሁ::
እኔም በተማርኩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተምራ ከጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ በፋርማሲ የተመረቀችውን ልጄን ደስታ ለመካፈል ከቤተሰቦቼ ጋር በምረቃ በዓሉ በመታደሜ ደስታዬ ልዩ ነው::
ለተመራቂዎች በሙሉ ለፍሬያማ ህይወት ቸር የሆነው ሁሉ እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ ።
በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን፣ ሽሬ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ ከ210 ሺሕ በላይ የሚሆን የተፈናቃዮችን መጠለያ ጣቢያ ማውደሙን የዞኑ አስተዳደር ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ተክላይ ገብረመድኅን ከሐምሌ ወር መግቢያ ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ እጅግ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ሲጥል እንደነበር ገልጸው፣ በተለይ ከባለፈው ሰኞ ዕለት ጀምሮ የጣለው ከባድ ዝናብ የተፈናቃዮችን መጠለያ ማውደሙን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም በሽሬ ከተማ የሚገኙ 18 የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ነው የገለጹት።
በከተማው ካሉ ከ360 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ከስልሳ በመቶ በላይ የሚሆኑት በፕላስቲክ እና ሸራ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ እነዚህን የፕላስቲክ እና ሸራ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ማውደሙን ገልጸዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም ሰኞ ሐምሌ 10/2015 በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ሳቢያ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ተፈናቃዮች መሞታቸው እና የሴቷ አስከሬን እስካሁን አለመገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በአንድ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ቢያንስ ከ40 ሺሕ በላይ ሰዎች እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን፣ በጎርፍ አደጋው ምክንያት ጣቢያዎች ከወደሙ በኋላ፣አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ውጭ እንደሚያድሩ እንዲሁም ብርድ እና ውርጭ እየተፈራረቀባቸው እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
እንዲሁም የጣለው ከባድ ዝናብ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑም የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሞልተው ወደ ከተማው ነዋሪ ቤት ጭምር በመግባት በእንሰሳት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱም ተሰምቷል፡፡
በኢዮብ ተስፋዬ
አዲስ ማለዳ
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት
*******************************
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷል።
የክብር ዶክተሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላልች።
ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬቱ የተበረከተላት።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
ወረታ‼
በደቡብ ጎንደር ዞን የወረታ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኮማንደር መልኬ ጤናው ትናንት ምሽት ለጊዜው ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ተሰምቷል።ከቀናት በፊት የሸዋሮቢት አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ፣የደብረብርሃን ከተማ ፖሊስ አዛዥ በተመሳሳይ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ይታወሳል።
Via Wasu Mohammed
አንኮበር‼
የአንኮበር ወረዳ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ላቀው ጎሽሜ ትናንት ከቀኑ 6:30 አካባቢ የግል መኖሪያ ቤታቸውን በመዝጋት በሽጉጥ ራሳቸው አጥፍተዋል።የስራ ኃላፊው ራሳቸውን ለማጥፋት ያበቃቸው ጉዳይ የገንዘብ ጉድለት ተገኝቶባቸው ጫና ውስጥ በመግባታቸው እንደሆነ ተሰምቷል።
የጨው ግብር 300 ሚሊዮን ብር ለራሱ የሚውስደው ክልል ፕሬዝዳንት ራሱ ጥሩ ስው አደርግው ጠንካራ አመራሮች ከስልጣን እያናስ ያለው አፋር ክልል ፕሬዝዳንት የልቤነት ስራ ቢያይ ኑሮ ይሄ ወንድማችን አንኮበር ራሱን አያጠፍም ነበር
@WasuMohammed
ወዳጆቼ ይህን የዩቲዩብ ቻናል ልጋብዛችሁ… 🙏
✅
የገጠር ባህልና አኗኗር የሚቃኝት ሚዲያ = Tossa tube
👇
https://www.youtube.com/channel/UCl-8Z6RAkgpTkZpV3q8N63Q
✅
#Tossa_tube በአማራ ቴሌቪዢን የአርሶ አደሮች ወግ ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው የጋዜጠኛ ጀማል ሰይድ የዩቲዩብ ቻናል ነው።
✅ "Tossa tube" መገኛውን ደሴ ከተማ ላይ ያደረገ፣ የገጠሩን ማህበረሰብ ባህልና አኗኗር የሚያስቃኝ ቻናል ሲሆን የመዝናኛና ቁምነገር አዘል ዝግጅቶችን ያካተተም ነው።
✅ ቻናሉ የገጠር ልጆችን ተሰጥኦና ችሎታ ማጎልበት ላይም ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡
✅ ከዚህ በተጨማሪም የገጠር ለዛ የሬድዮ ፕሮግራም በ ጦሳ ቲዩብ ሚዲያ አዘጋጅነት በአማራ ኤፍ ኤም ደሴ 87.9 ዘወትር ቅዳሜ ከ10፡00-11፡00 ይቀርባል፡፡
⛔️ ቀጣዩን ሊንክ በመክፈት የዩቲዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
👇 https://www.youtube.com/channel/UCl-8Z6RAkgpTkZpV3q8N63Q
✅
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/gashaw.lene.7777/
ቲክቶክ-
tossa_tube" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tossa_tube?
ቴሌግራም-
/channel/tossatube
ኢንስታግራም- https://www.instagram.com/Embosa-tube/
# ፍ/ቤቱ በእነ ዶ/ር ወንዶሰን መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾችን ዋስትና ከለከለ‼
በእነ ዶ/ር ወንድወሰን መዝገብ ከተከሰሱ 51 ሰዎች ውስጥ ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይና መስከረም አበራን ጨምሮ 13 ተከሳሾች ዛሬ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ዋስትና ከለከለ።
በአማራ ክልል ከልዩ ሀይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታት ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ በአማራ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን ዛሬ ሐምሌ 12/2015 ዓ/ም ማለዳ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ዋስትና አልፈቅድም ያለ ሲሆን ወደ ወህኒ እንዲወርዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ሆኖም የዛሬው የችሎት ውሎ ሁሉም ተከሳሾችና የችሎቱ ታዳሚን ያሳዘነ በመሆኑ ችሎቱ እንዳበቃ የተቃውሞ ድምፅችና ጭብጨባ በአዳራሹ ይሰማ እንደነበር አሻራ አረጋግጧል። ፍ/ቤቱ ለተለዋጭ ቀጠሮ ሐምሌ 25/11 /2015 ተለዋጭ መስጠቱን አሻራ ሚዲያ በሰፊው የችሎት አዳራሽ መረጃ ለማግኘት ችሏል።
ተከሳሾቹም አቃቤ ህግ ያቀረበብንን ማስረጃ ባላዳመጥንበት ሁኔታ እንዴት መከላከል እንችላለን ሲሉ ጠይቀዋል።
በተለይም ማስረጃዎችን የላከው የደህንነት ተቋም ገለልተኛ ባልሆነበት ሁኔታና ቀድሞ በሽብርተኝነት ፈርጆን ሳለ መረጃዎቹን እንዳናይ መከልከሉ ተገቢ አይደለም በሚል ተቃውመዋል።
አቃቤ ህግ በተከሳሾቹ በኩል የቀረቡት የመብት ጥያቄዎች ትክክል መሆናቸውን አምኖ ወደ ማረሚያ ቤት ወርደው ሰፊ ጊዜ ማግኘት እንደሚችሉ ጥያቄ አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም ወደማረሚያ ቤት ይውረዱ ማለቱን ተከትሎ የፍትህ ስርዓቱ አጠያያቂ መሆኑ ብዙዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
በዛሬው ችሎት አዳራሽ የመብት የሟጋቾች ፣ ጋዜጠኞችና ቤተሰቦቻቸው ለመታደም ችለዋል።
የቤት ሽያጭ ዋጋ ታክስ ይፉ ሆነ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከዚህ ቀደም የቤት ግብይትን ዋጋ በተመለከተ ይቀርብ የነበረው የሽያጭ ውል ወቅቱን እና እውነታውን ያላገናዘበ እንዲሁም የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ይህንን መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የጥናት ቡድን በማቋቋም ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ አስጠንቶ ያጠናቀቀ ስለሆነ ይህንኑ ጥናት ከዚህ ቀደም ባለው መመሪያና አሰራር መሰረት ማለትም የካፒታል ክፍያን፣ የቴንብር ቀረጥ እና አሹራ ክፍያ ከጠቅላላ የቤቱ ዋጋ በፐርሰንት ተሰልቶ በጥናቱ መሰረት ይህ ደብዳቤ ወጪ ከሆነበት ቀን ሰኔ 8/2ዐ15 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንድታርጉ እያሳሰብን የተጠናውን ጥናት 3 ገፅ አባሪ ከዚህ መሽኛ ደብዳቤ ጋር ተልኳል።
ባለፉት 40 ዓመታት በዓለም ከተደረጉ ግጭቶች የሰሜኑ ጦርነት የከፋ መሆኑ ተገለጸ
ከፈረንጆቹ 1984 ወዲህ በዓለም ከተደረጉ ግጭቶች በሰሜን ኢትዮጵያ ለኹለት ዓመታት የተደረገው ጦርነት ከኹሉም የከፋ መሆኑ ተገልጿል።
መቀመጫውን በኖርዌይ ያደረገውና በሰላም ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ጥናቶችን የሚሰራው ተቋም፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረገው ጦርነት ከፈረንጆቹ 1984 ወዲህ እንደዓለም ከተደረጉ ግጭቶች መካከል የከፋ ነው ሲል አስነብቧል፡፡
ጥናቱ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በፖለቲካ ምክንያት በዓለም በተቀሰቀሱ ግጭቶች የ204 ሺሕ ሰዎች ሞት መመዝገቡን የገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ በዩክሬን እና ኢትዮጵያ የተመዘገበው ሞት 89 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጠቅሷል።
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የነበረው ግጭት የዓለምን ትኩረት የሳበ እና ከፍተኛ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ያገኘ ይሁን እንጂ፤ በኢትዮጵያ በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል የተደረገው ጦርነት እጅግ የከፋ እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ነው ሲል ጥናቱ አመላክቷል፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን እየተደረገ ባለው ጦርነት 81 ሺሕ 500 ሰዎች መሞታቸው ሲጠቀስ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ግን 100 ሺሕ 200 ሰዎች መሞታቸውን ነው የተገለጸው።
ጥናቱ አክሎም በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል በተለያዩ የአገሪቱ ቦታዎች እየተደረገ ያለው ውጊያ፤ በፈረንጆች 2022 በዓለም ከተደረጉ ሰባት አስከፊ ውጊያዎች አንዱ ነው ሲልም ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
/channel/addismaleda
🔥#መረጃ‼️
የወልድያ ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሠ በራሳቸው ፈቃድ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው ።
ምክንያታቸው ፋኖ ላይ የተጀመረውን ጥቃት በመቃወም ነው እየተባለ ነው።
ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰማም።
በዚህ ዜና ላይ ዝርዝሩን እናቀርባለን
በባሕርዳር ከተማ ወይዘሮ እቴአንች መንክርን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ ያቸውን ሁለት ሰዎች ተያዙ!!
በተላንትናው እለት በባሕርዳር ከተማ እጅግ አሳዛኝ በሆነ መንገድ ወይዘሮ እቴአንች መንክር ግድያ ተፈፅሞባቸዋል።
ወይዘሮ እቴአንቺ መንክር በከተማው ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሁሉ እናት እና በስራቸውም አርአያ የነበሩ ጠንካራ እናት ነበሩ።
ነገር ግን ቤታቸውን ሰብረው በመግባት ወይዘሮ እቴአንቺን በቢለዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኋላ በቤት ውስጥ ያሉ ንብሮቶችን በተለይም ወርቅን ጨምሮ የተለያዩ ጌጣጌጦችን ገንዘብ ና ሙባይል በመዝረፍ ይሰወራሉ።
ዛሬ ጠዋት ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ የባሕርዳር ከተማ ህዝብ ወ/ሮ እቴአንችን በደማቅ የቀብር ስርዓት የሸኛቸው ሲሆን ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዎችን በእንድ ቀን ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏል።
በወንጀሉ ቀጥታ ተሳታፊ ናቸው በማለት ፖሊስ በአጭር ጊዜ ክትትል በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሁለት ሰዎቾ ሲሆኑ አንደኛ ሐብታሙ አድጎ ሁለተኛ ብስራት ገበየሁ የተባሉ ናቸው።
የባሕርዳር ከተማ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ያሳየው ትጋትና ወንጀለኞችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋሉ የሚስመሰግነው ሲሆን ተገቢውን ቅጣት በፍርድ ሂደት እንዲቀበሉ ማድረግ ቀጣይ ተግባር ሊሆን ይገባል።
ለደረሰባቸው ሀዘን መላው ቤተሰቡንና ወዳጆችን መፅናናት እንመኛለን።
በመተከል ታጣቂዎች ከነ ጦር መሳሪያቸው ወደ ጫካ ተመለሱ
በመተከል ዞን በግልገል በለስ ከተማ ካምፕ ውስጥ የነበሩ ታጣቂዎች ከነጦር መሳሪያቸው ወደ ጫካ መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ተናገሩ። የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ከትጥቅ ትግል ተመለሱ የተባሉት ታጣቂዎች ለተሐድሶ እየተዘጋጁ ነበር። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪ እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ መመለሳቸው ከተሰማ በኋላ በአካባቢው ሥጋት ሰፍኗል።
ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በአማራ ክልል የሚዘምተው መንግስት ምነው እነዚህ ታጣቂዎችን ሳያስፈታ ቀረ?
የኢትዮጵያ ነገር ግራ የሚያጋባ ነው።
📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ
እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን
በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ
የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ
የቀሩን የካሬ አማራጮች፦
107 ካሬ
110 ካሬ
115 ካሬ
120 ካሬ
127 ካሬ
138 ካሬ
በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን
ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won
👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247
#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com
1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት መመዝገቡን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቀ
በዚህ አመት መገባደጃ ላይ ደግሞ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመዘገብ ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን ዩኒት ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝግባ በተለያዩ የምዝገባ ጣቢያዎች፤ በአንድነት ፓርክ እንዲሁም በባንኮች በተመረጡ ቅርንጫፎች ላይ እየተከናወነ ነው፡፡
በid.et ዌብ ሳይት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በየዕለቱ የግንዝቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ አቤኔዘር ተናግረዋል ።
የብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ስትራቴጂ ዋና አላማ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቅመው የተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ ማስቻል እንደሆነም ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት ።
ከባንኮች ጋር የዲጂታል መታወቂያን ማቀናጀት ተጀምሯል፤ እስካሁንም በ8 በተመረጡ የባንኮች ቅርንጫፎች ላይ የማቀናጀት ስራን እየተሰራ መሆኑንንም ገልፀዋል፡፡
ወደ ፊት ዲጂታል መታወቂያን ከፋይናንስ ሴክተር ጋር በማቀናጀት አንድ ሰው መታወቂያውን ተጠቅሞ ፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችል እየሰራን ነው ብለዋል ።
( EBC )
📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ
እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን
በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ
የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ
የቀሩን የካሬ አማራጮች፦
107 ካሬ
110 ካሬ
115 ካሬ
120 ካሬ
127 ካሬ
138 ካሬ
በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን
ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won
👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247
#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com
ተሰዷል!
ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኙ ቴዎድሮስ አስፋው በዛሬው ዕለት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ከሀገር ውጪ መሰደዱ ታውቋል።
📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ
እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን
በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ
የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ
የቀሩን የካሬ አማራጮች፦
107 ካሬ
110 ካሬ
115 ካሬ
120 ካሬ
127 ካሬ
138 ካሬ
በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን
ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won
👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247
#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com
አሉላ ሰለሞን ከአንድ ሰዓት በፊት ለፌስቡክ ጓደኞቹ በትግርኛ ያጋራውን ተስፋ መቁረጥ የታየበት መልእክት ተርጉመነዋል።
#ባለፈው ሁለት አመት ከዝያ በላይ የትግራይ ጆኖሳይድ የማጋለጥ ብልህነት ፡ ምንአልባት ለቀጣይ ለሚካሄደው ፍትሕና ተጠያቂነት ስኬቶች ለማምጣት የራሱ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ የተደረገበት የተጋሩ ዲያስፖራ ትግል ፡ አሁን በውጭ እና በውስጣዊ ሴራ (እርስ በራስ መናቆር ስም ማጥፋት ጨምሮ ) በጣም ላልተዋል ወይም ለዘላለም እንዳይነሳ ተደርጎ ተሰብሯል ።
via Wedi Shambel
የህዳሴ ግድቡ ብሔራዊ ተደራዳሪ መሪዎች የተስማሙበትን ማወቅ እንፈልጋለን ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁ
‹‹በአሳሪ ስምምነትና ከውኃ ልቀት ጋር የተያያዘ ስምምነት ውስጥ ዘለዓለማዊ የውኃ ልቀት ውስጥ ኢትዮጵያ የምትገባ ከሆነ፣ ከህዳሴ ግድብ በላይ የማልማት ዕድሏ ይዘጋል››፤ በማለት ‹‹በግድቡ ድርድር ላይ መሪዎች የተስማሙባቸው ነጥቦች ላይ በእኛ [በተደራዳሪዎች] በኩል ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ስለ ጉዳዩ ማወቅ አለብን ያሉት የህዳሴ ግድቡ ብሔራዊ ተደራዳሪና የኤክስፐርቶች ቡድን ዋና ሰብሳቢ ናቸው።
ስለጉዳዩ የተጠየቁት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሲመልሱ ‹‹አገሮቹ ተጨባጭ ወደሆነ ድርጊት እስኪገቡ መጠበቅ ያስፈልጋል። አሁን ጊዜው ገና ነው።›› ብለዋል
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ወቅታዊ ጉዳዮችና ስጋቶች ዙሪያ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ የህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ተደራዳሪና የኤክስፐርቶች ቡድን ዋና ሰብሳቢ ጌዲዮን አሁንም በድርድሩ ነጥቦች ላይ ወጥ አቋም መያዝ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን የግድብ ድርድርን በማፋጠን በአራት ወራት ለማጠናቀቅ በመሪዎች የተደረሰው ስምምነት ላይ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ተገናኝቶ የጋራ አቋም ሊይዝ እንደሚገባ፣ የተደራዳሪ ቡድኑ አባል ጌዲዮን አስፋው (ኢንጂነር) ገልፀዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በግብፅ ጉብኝት ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከግብፅ አቻቸው ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው የሁለቱ አገሮችን ግንኙነት በማስመልከት ከተወያዩ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ የህዳሴ ግድብ ድርድር በአራት ወራት እንዲጠናቀቅ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ
በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ። የተከሳሾችን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ በድረ ገጻቸው የጫኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን እንዲያወርዱም ፍርድ ቤቱ አዝዟል።
ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 12፤ 2015 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው። ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ትዕዛዞችን በሰጠበት ቅጽበት፤ ተከሳሾች በጭበጨባ የታጀበ መፈክር አሰምተዋል። የተከሳሾቹ መፈክር እና ጭብጨባ፤ የችሎት ውሎ ተጠናቅቆ ታዳሚዎች ከአዳራሽ ከወጡ በኋላም አላቋረጠም ነበር።
በተከሳሾች ጭብጨባ የተጠናቀቀው ችሎት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው፤ ጠበቆች ባቀረቡት የተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት እና ከዚህ በፊት የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈጻጸም ለመከታተል ነበር። የተከሳሾችን የዋስትና መብት በተመለከተ ከ20 ቀናት በፊት በነበረ የችሎት ውሎ በተደረገ ክርክር፤ ጠበቆች የደንበኞቻቸው የዋስትና ጉዳይ ሊታይ የሚገባው “የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ እና በህገ መንግስቱ እንጂ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ አይደለም” ሲሉ ተከራክረዋል።
* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11500/
የቀድሞ ሴት ፍቅረኛዬን አግብተህብኛል በሚል ግለሰቡን የገደለ ተጠርጣሪ መያዙን በኮንታ ዞን የጪዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በኮንታ ዞን የጭዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ፈለቀ ጣምሩ እንደገለፁት ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ማራቃ ጎዲ ቀበሌ በልዩ ስሙ ጎዲ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ፍቅረኛዬን አግብቶብኛል ያለውን ግለሰብ መኖሪያ ቤቱን ሰብሮ በመግባት የግል ተበዳይን በገጀራ ጭንቅላቱ ደጋግመው በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ ሲሆን የሟቹን ባለቤት ጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አስረድተዋል፡፡
እንደ ፖሊስ አዛዡ ገለፃ ግለሰቡ ወንጀሉን የፈፀመው እኔን ትተሸ ሌላ አግብተሻል በሚል ቂም በመያዝ ሌሎች ጓደኞቹንም ጭምር በማስተባበር መኖሪያ ቤቷን ሰብሮ በመግባት የቀድሞ ፍቅረኛውን ጭንቅላት በመቁረጥና ባለቤቷን ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአከባቢው መሰወራቸውንም ገልፀዋል፡፡
ተጎጂዋ ባሰማችው የይድረሱልኝ ድምፅ የአከባቢው ነዋሪዎችና ፖሊስ ደርሰው ወደ ህክምና ተወስዳ ህይወቷ መትረፉንና በአሁኑ ሰዓት በጅማ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት መሆኑንም አዛዡ ተናግረዋል፡፡
ዋና ሳጅን ፈለቀ አክለውም ወንጀሉን ያስተባበረው የቀድሞ ፍቅረኛዋ መምህር ጌታሁን ጌታቸው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን ከፈፀሙ በኃላ በአከባቢዉ ዉስጥ ተሸሽገው ቢቆዩም ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ቀሪውን አንድ ተጠርጣሪ ለመያዝ የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው የጪዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ የገለፁት ሲል የዘገበው የዞኑ ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ነው።
ደራሲና ፀሃፊ አሳዬ ደርቤ በ10ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈቷል።
ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሃይሎች ተይዞ የታሰረው ደራሲና ፀሃፊ አሳዬ ደርቤ በዋስትና ጉዳይ ክርክር ለማድረግ ትናንት ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ነበር።
ፍርድ ቤቱም አቃቢ ህግ በአሳዬ ላይ ያቀረበውን ክስ ከመረመረ በኋላ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማዳመጥ ተከሳሹ በ10,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ብይን ሰጥቷል።
አሳየ የዋስትና መብቱ ተከብሮለት በአሁን ሰአት ከእስር ተፈቶ ወደ ቤቱ ገብቷል ሲል አሻራ ሚዲያ ዘግቧል።