muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

ዐበይት ሁለት ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ "የታጠቁ ኃይሎች" ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በፈጠሩት ግጭት ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አዛዦች በምዕራብ ደንቢያ ወረዳ የሚገኘውን "የጎርጎራ ገበታ ለአገር" ፕሮጀክት ለመጎብኘት በተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ ታጣቂዎቹ "መንገድ በመዝጋታቸውና አናሳልፍም ብለው ትንኮሳ በማድረጋቸው" ግጭቱ እንደተፈጠረ ምክር ቤቱ ገልጧል። ግጭቱ በትክክል መቼና የት ቦታ ላይ እንደተፈጠረ፣ በግጭቱ ከኹለቱም ወገን ስንት ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ወይም ከመከላከያ ከፍተኛ አዛዦች መካከል የተገደሉ ስለመኖራቸው መግለጫው አልጠቀሰም።

2፤

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ከተማ አካባቢ ከ2 ሺህ 100 በላይ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መገኘቸውን ዛሬ ባወጣው አዲስ መረጃ አስታውቋል። 32 ሰዎች ከኮሌራ ጋር በተያያዘ እንደሞቱ ቢሮው አመልክቷል። በሽታው የመተማ አጎራባች በኾነችው ቋራ ወረዳ ከሚገኝ አንድ ጸበል በቅርቡ ተቀስቅሶ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ በርካታ የክልሉ ዞኖች መዛመቱን ቢሮው ጨምሮ ገልጧል። የበሽታው በፍጥነት መስፋፋት፣ በመተማ ወረዳ በስደተኞች ካምፖች በተጠለሉ ሱዳናዊያን ስደተኞች ላይ ጭምር ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ተብሏል።
ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በሀገርቀፍ ደረጃ ሊሰጥ ነው

ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በሀገርቀፍ ደረጃ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በሁሉም ፕሮግራሞች እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህንንም ወጥ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም እንዲቻል ለሁሉም የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተጻፈ ደብዳቤ መገለጹን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎቹ የ2016 ትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ማስታወቂያ በማዉጣትና በመመዝገብ እጩ ተማሪዎችን እስከ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲያሳዉቁ መልዕክት መተላለፉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በገዛ ፈቃዴ ከሀላፊነት ለቅቄያለሁ - ታምራት ሰለሞን የሸዋሮቢት ከተማ ብልፅግና ወጣት ሊግ ሀላፊ

ስለነበረን የአብሮነት ቆይታ በእጅጉ አመሰግናለሁ።

ቀደም ሲል በቆየሁባቸው ከቀበሌ እስከ ወረዳ በተሰጡኝ የተለያዩ ሃላፊነቶች ያለምንም ድካምና መሰልቸት የከተማዬን ህዝብና መንግስትን ለማገልገል አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ ሳደርግ ቆይቻለሁ።

ከቅርብ አመታት ወዲህ መንግስት እንደ መንግስት መስራት ያለበትን የቤት ስራዎች ወደጎን ትቶ፣ በተለያዩ የፖለቲካ አሻጥሮች የአማራን ህዝብ በየቦታው ሰላሙን አጥቶ እንዲኖር በማድረግ፣ ከኖረበት ዕርስቱና ከቀዬው በማፈናቀል፣ በማንነቱ ብቻ ተለይቶ እንዲገደል፣ በጅምላ እንዲቀበር በማድረግ አለ'ፍ ሲልም የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ አቅሙን ሚዛን በማሳጣት አማራ አንገቱን እንዲደፋ የሚደረገው "ግፍና በደል" ከጊዜ ወደጊዜ የሚቆም መስሎኝ ተስፋ በማድረግ በትዕግስት ስጠባበቅ ነበር...!!

ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ገዢው ፓርቲም ይሁን መንግስት ለህዝብ ፍላጎት ጆሮ ከመስጠት ይልቅ ከፍተኛ የሆነ እብሪት ውስጥ በመግባት፣ በ'ይዋጣል'ን የፖለቲካ አካሄድ ሀገሪቱ ወደለየለት ትርምስ ውስጥ እንድትገባ እያደረገው ባለው ያላሰለሰ ጥረት "ባለመስማማት" በገዛ ፈቃዴ ከሀላፊነት ለቅቄያለሁ።

ሰላም
ታምራት ሰለሞን
የሸዋሮቢት ከተማ ብልፅግና ወጣት ሊግ ሀላፊ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
*********************

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊዮን ዶላር (የ21.8 ቢሊዮን ብር) የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በበይነ መረብ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል።

የፋይናንስ ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትን እና ውጤታማነትን ለማሻሻል እና የሥርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን ከአገልግሎቱም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶች እና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ታውቋል።

የፋይናንስ ድጋፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋጋጥ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በተመረጡ ወረዳዎች የስርዓተ ምግብ አገልግሎትን በማጎልበት የህጻናት መቀንጨርን ለመከላከል እንደሚረዳ ታምኖበታል።

የገንዘብ ድጋፉ ጥራት ያለው የማህበራዊ አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ አስፈጻሚዎችና ባለሙያዎች ቴክኒካዊ የአቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ለሰው ሀብት ልማት ቅድሚያ የምትሰጥና ለተግበራዊነቱም የላቀ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች የምትገኝ ሲሆን እ.ኤ.አ ከጁላይ 25-26 / 2023 በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ለሚካሄደው ለሰው ሀብት ልማት የመሪዎች ጉባኤም ድጋፍና ቁርጠኝነቷን አረጋግጣለች።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የማይገባኝ ነገር የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቴሌቪዥን ግብር ሰብሳቢነትና የብሔራዊ ሎተሪ የሎተሪ እጣ ፍቃድ ሰጪነት ነው ።
ራሱ ተወዳዳሪ መሆን ያለበት ተቋም ገና ለገና የመንግሥት ስለሆነ ብቻ አወዳዳሪ ይሆናል ። መንግሥት መሆን ጥሩ ነው ። የመንግሥት ተወካዮች ( የሕዝብ ተብሎ የሚጠራው ) ም/ቤት በፍርደገምድልነት ከ50 ኪሎዋት በላይ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚጠቀም ሰው ቴሌቪዥን ቢኖረውም ባይኖረውም ለኢቴቪ በየወሩ 10 ብር ይከፍላል።

( 50 ዋት የሚጠቀም እንዴት " ቴሌቪዥን አለው ማለት ነው" ተብሎ እንደታሰበ ግልጽ ባይሆንም ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሕዝቡ የሚያስበው እንዲህ ነው ። በግሌ የማውቃቸው በምርጫቸው ቤታቸው ቴሌቪዥን የሌላቸው አንድ ሁለት ብቻ ያልሆኑ ሰዎች አውቃለሁ።
በምን ምክንያት ነው ቤቱ ቴሌቪዥን የሌለው ሰው የቴሌቪዥን ግብር እንዲከፍል የሚገደደው ? ቤቱ 4/5 ቴሌቪዥን በየክፍሉ ያለው ደግሞ አለ። እሱም ምንም ከሌለው እኩል ይከፍላል ማለት ነው። የእኛ " የሕዝብ ተወካዮች " እንዲህ ነው የሚያስቡት። በወር 10 ብር ከከፈልን በዓመት 120 ብር እንከፍላለን።" የቴሌቪዥን ግብር ክፍያ 100 % ጭማሪ ተደርጎበታል " ብሎ በግልጽ የነገረን የለም። ራሳችን ነን ያገኘነው ። በፍላጎት 60 ብር የሚከፍል ሲጠፋ በግዳጅ 120 ብር ማስከፈል መንግሥት የመሆን ጸጋ እንጂ ሌላ አይደለም።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከእነ ፋና፣ ኢቢኤስ፣ ባላገሩ ፣ ዋልታ ጋር ተፎካካሪ እንጂ እንዴት ነው ብቸኛው የቴሌቪዥን ግብር ሰብሳቢ የሆነው ? ብሔራዊ ሎተሪስ ራሱ የሎተሪ ጨዋታ አጫውቶ ብር የሚሰበስብና በገቢው የሚተዳደር ተቋም ሆኖ እንዴት ነው ለሎተሪ አጫዋቾች ፍቃድ ሰጪና ክፍያ ሰብሳቢ የሆነው ? ራሱ ብሔራዊ ሎተሪን የሚገዳደር የሎተሪ አጫዋች ቢመጣ " አልፈቅድም " ሊል ነው ወይስ ሊፈቅድ ?

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደዚህ ሰውዬ ለቃሉ ታማኝ፣ ቅን፣ ሀገር ወዳድ፣ ሐይማኖተኛ እና የተማረ ትምህርቱንም ለሀገሩ ልማትና ሰላም ያዋለ ሰው አይቼ አላውቅም። በፈጣሪ ተመልከቱ። የክልሉ አስተዳዳሪ ከሆነ ጀምሮ ሰላም አስከብሯል። በትምህርት ዘርፍ 576 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 79 ሁለተኛ ደራጃ ት/ቤቶች፣ 11 ቦርዲን ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል። በሚቀጥለው የበጀት አመት ለትምህርት 40% ያህል በጀቱን አሳድጓል። ሙስጠፌን አላህ ይጠብቀው 🙏

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

👌Great Arabian Mejlis👌

ግሬት አረቢያን መጅሊስ

√ ጥራታቸውን የጠበቁ

√ በተለያዩ ዲዛይኖችና ቀለማት

√ እንደየቤቱ ስፋትና ጥበት የተለያዩ ድንቅ መጅሊሶች

የተዘጋጀ ለሚወስድ 5 % ቅነሽ እና ነፃ ትራንስፖርት
በቤት ዲዛይን ላይ ሞያዊ እገዛ የሚያደርጉ ባለሙያዎች የታገዘ አገልግሎት እንሰጣለን

ይምጡ
ከዝቅተኛ 3500 ብር እስከ 21 ሺህ

በሜትር ድገሞ እስከ 12ሜትር ለሚደርስ የአረቢያን መጅሊስ አለን

ትራንስፖርት በነፃ

☞ ሊንኩን ይጫኑ
/channel/Greatarebian
ዉድ ደንበኞቻችን የፈለጉትን ዕቃ ለመዘዝም ሆና ለመጠየቅ በዚህ ስልክ ይጠቀሙ
0912612810/ 0973979790 / 0922336666
☞☞☞ አድራሻ ፦ አዲስአበባ /ግራር ኮንዶምኒየም
ይፃፉ @Greatarebei

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የETV የአገልግሎት ክፍያን ከመብራት ክፍያ ላይ ተደምሮ ሊሰበሰብ ነው! ይህ የሚሆነው ከ50 ኪሎ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የምትጠቀሙ ደንበኞች ላይ መሆኑ ተገልፇል። ከሰኔ ወር ጀምሮ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ በየወሩ 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ቢል ጋር ተዳምሮ እንዲዘጋጅ መደረጉ ተገልፇል።
#FastMereja

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በወልዲያ ከተማ በጸጥታ አካላትና በታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አምስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
=======#=======

ማክሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 ከምሽት ኹለት ሰዓት ገደማ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ የጸጥታ አካላት እና ንጹሃን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የምሽት ተረኛ በነበሩ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ መንገድ ዳር በቆሎ ስትጠብስ የነበረች የኹለት ልጆች እናት እና ኹለት ወጣቶች መገደላቸው ተጠቅሷል።

ለሰዓታት በቆየው የተኩስ ልውውጥ ከሟቾች ባለፈ የጸጥታ አካላት ላይም የአካል ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል።

የወልዲያ ከተማ ከንቲባ ዱባለ አብራሬ በጉዳዩ ላይ ለአዲስ ማለዳ በሰጡት ምላሽ፤ ዕሁድ ምሽት በከተማዋ በነበረው የተኩስ ልውውጥ አንዲት በቆሎ በመጥበስ የምትተዳደር የኹለት ሕጻናት እናት ሕይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ማለፉን ገልጸው፤ ተኩሱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በኋላ መረጋጋቱን አስታውቀዋል።

በተኩስ ልውውጡ ስለተገደሉት ሌሎች ሰዎችና የጸጥታ አካላት ለቀረበላቸው ጥያቄ “በጸጥታ አካላትና በንጹሃን ላይ ስለደረሰው ጉዳት በጸጥታ አካላት በኩል መግለጫ እንሰጣለን፡፡” ሲሉም ከንቲባው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
/channel/addismaleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !

👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:

➤ CMC ላይ በ15% ቅድመ ክፍያ ባለ ቤት ይሁኑ

➤ ቦሌ አትላስ ላይ በ 50% ቅድመ ክፍያ ቤተዎን በእጀዎ ያስገቡ

➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ-4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት

➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ

👉 ከወለድ ነፃ የአከፋፈል ስርአት አለ

#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል

ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513

👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጥቆማ‼️ የግድ ሊኖራቹ የሚገባ ቺናል

አሁን ላይ በቴሌግራሙ አለም አሉ ከሚባሉ የመረጃ አቅራቢዎች መሀከል የተለያዩ ወቅታዊ እና እውነተኛ መረጃዎችን በታማኝነትና በፍጥነት ፈልፍሎ የሚያቀርብ የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማቹ 👍

በጥቆማዬ ሙሉ በሙሉ እተማማናለሁ 👌"የመረጃ ቋት ቻናል ነው "በዚህ ሊንክ ግቡ 👉   /channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጉድ ሳይሳማ መስከረም አይጠባም

ለቲክ ቶክ ጊፍት ብሎ አለቀሰ ፤ አይኖቹ ማየት አቃታቸው።


ናይጄሪያዊው ቲክ ቶከር Tembu ebere 100 ስአት አለቅሳለሁ ብሎ በቲክ ቶክ live በመግባት ማለቅስ ጀመረ ።
ጊፍት የሚወርድለት ይህ ግለሰብ ማለቀሱን ለሳምንት ቀጥሎ
በመጨረሻ ጊፍትም በጊፍት የሚላክለት ገነዘብ ሰበሰበ ።
የጊኒስ ሪኮርድ ባለቤትም ሆነ ። ነገር ግን 100 ስእት ካለቀሰ በኃላ አሁን ላይ አይኖቹ በጣም ስላለቀሱ አብጠው ማየት ተሰኗቸዋል::

ጭራሽ እንዳይጠፉ በከፍተኛ የህክምና ክትትል ላይ ይገኛል!

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ 
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

            107 ካሬ

            110 ካሬ

             115 ካሬ

             120 ካሬ

             127 ካሬ

             138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won

👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354           
      +251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ለብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት 254 የምዝገባ ማዕከላት ወደ ሥራ እየገቡ መሆኑ ተነገረ

👉እስካሁን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገልጿል
=======#=======

በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ለመስጠት 254 የምዝገባ ማዕከላት ወደ ሥራ እየገቡ መሆናቸውን የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በዚህም ከ400 በላይ የመመዝገቢያ መሣሪያዎች መገዛታቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁንም 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ለመውሰድ መመዝገባቸውን ተነግሯል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዳይሬክተር ሄኖክ ጥላሁን፤ ብሔራዊ መታወቂያ በአገራዊ ፋይዳው የሚታወቅ በሌሎች አገሮች ተተግብሮ ትልቅ ለውጥ ያመጣ የዲጂታላይዜሽን ቁልፍ ሚና ያለው፤ የዲጂታል መታወቂያን የማዳረስ ሥራ ነው ያሉ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ 254 የምዝገባ ማዕከላት ወደ ሥራ እየገቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በክልሎች ደረጃ በተለይ በገቢዎች በኩል አዲስ አበባና ድሬዳዋን ከተሞች ጨምሮ በአገሪቱ ኹሉም ክልሎች 184 ማዕከላት ለመመዝገብ የሚያስችሉ ግብዓቶች እየተሟላላቸው ያሉና ወደ ምዝገባ በመግባት ሂደት ላይ ያሉ፤ እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ወደ ምዝገባ ግብዓቶች እየተሟላላቸው ያሉና ወደ ምዝገባ በመግባት ሂደት ላይ ያሉ፤ እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ወደ ምዝገባ የገቡ መኖራቸውን ሄኖክ ጠቅሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ በዘጠኝ ባንኮች በኩል ያሉ 68 የምዝገባ ማዕከላት እንዲሁም የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ኹለት ማዕከላት ያሉት ሲሆን፤ በአሁን ወቅት ኹሉም ወደ ሥራ መግባታቸውንም ገልጸዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላላው 254 ማዕከላት ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው እነችፎ ቡልቸድ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር ይጓዝ ከነበረ አውቶብስ ጋር በመጋጨቱ ወድያውኑ ከአይሱዙው 3 ሰው ከአውቶብሱ 2 ሰው በድምሩ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ ገልጸዋል ፡

መረጃው የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳዳር ነው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

👌Great Arabian Mejlis👌

ግሬት አረቢያን መጅሊስ

√ ጥራታቸውን የጠበቁ

√ በተለያዩ ዲዛይኖችና ቀለማት

√ እንደየቤቱ ስፋትና ጥበት የተለያዩ ድንቅ መጅሊሶች

የተዘጋጀ ለሚወስድ 5 % ቅነሽ እና ነፃ ትራንስፖርት
በቤት ዲዛይን ላይ ሞያዊ እገዛ የሚያደርጉ ባለሙያዎች የታገዘ አገልግሎት እንሰጣለን

ይምጡ
ከዝቅተኛ 3500 ብር እስከ 21 ሺህ

በሜትር ድገሞ እስከ 12ሜትር ለሚደርስ የአረቢያን መጅሊስ አለን

ትራንስፖርት በነፃ

☞ ሊንኩን ይጫኑ
/channel/Greatarebian
ዉድ ደንበኞቻችን የፈለጉትን ዕቃ ለመዘዝም ሆና ለመጠየቅ በዚህ ስልክ ይጠቀሙ
0912612810/ 0973979790 / 0922336666
☞☞☞ አድራሻ ፦ አዲስአበባ /ግራር ኮንዶምኒየም
ይፃፉ @Greatarebei

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሸዋሮቢት ከተማ መንገድ ተዘግቷል።ትናንት ምሽት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ጉዳት ስለደረሰ ነው በመከላከያ መንገዱ የተዘጋው ተብሏል።
Via Wasu Mohammed

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው ያለው አሉላ ሰለሞን ጌችን በጥበቃ እያገለገለው ይሆን? አሉላ አቋቋሙ ግን ወታደራዊ ጥበቃ ሳይሆን ባህላዊ ጥበቃ ይመስላል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

107 ካሬ

110 ካሬ

115 ካሬ

120 ካሬ

127 ካሬ

138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won

👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !

👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:

➤ CMC ላይ በ15% ቅድመ ክፍያ ባለ ቤት ይሁኑ

➤ ቦሌ አትላስ ላይ በ 50% ቅድመ ክፍያ ቤተዎን በእጀዎ ያስገቡ

➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ-4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት

➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ

👉 ከወለድ ነፃ የአከፋፈል ስርአት አለ

#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል

ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513

👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የርዕሰ መስተዳድሩ የጸጥታ አማካሪ ከስልጣናቸው ተነሱ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸውን እና የክልሉን ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ከስልጣናቸው አነሱ። ዶ/ር ይልቃል የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸውን ከኃላፊነት ያነሱት የተሰጣቸውን “ተግባር እና ኃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም” በሚል ነው።

ዶ/ር ይልቃል ሁለቱን ኃላፊዎች ከስልጣናቸው ያነሱት ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሐምሌ 17፤ 2015 በጻፉት ደብዳቤ ነው። በአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በምክትል ኃላፊነት ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ከፋለ እሱባለው እና የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ፤ ውሳኔውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

ከሰኞ ዕለት ጀምሮ ከአማካሪነታቸው የተነሱት አቶ ከፋለ፤ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ለአምስት ዓመት ገደማ ቆይተዋል። አቶ ከፋለ ይህንን ኃላፊነት ያገኙት በቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአመራርነት ጊዜ ሲሆን፤ የአሁኑን ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃልን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ክልሉን የመሩትን አምስት ርዕሰ መስተዳድሮች በአማካሪነት አገልግለዋል።

* ለዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11551/

@EthiopiaInsiderNews

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላ ያቃጠለችው ግለሰብ በሞት እንድትቀጣ ተፈረደ

በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ከታ ወረዳ ሁለት የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላ ያቃጠለችው ግለሰብ በሞት ፍርድ ተፈረደባት፡፡

የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የሁለት አመትና የአስራ ሁለት አመት የእንጀራ ልጆቿን ሆን ብላና ጨለማን ተገን አድርጋ በቀን 27/08/2015 ዓ.ም ከለሊቱ 5:00 ላይ በመጥረቢያ ቆራርጣ ገድላ ያቃጠለችው ወ/ሮ ነጋሴ ከበደ በሞት ፍርድ እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።

ተከሳሿ ወንጀሉን ፈጽማ ከሸሸችበት እለት አንስቶ በፓሊስ ስትፈለግ ከቆየች በኋላ ፓሊስ ባካሄደው ከፍተኛ ጥረት ግንቦት 1/2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውላ የፍርድ ሂደቷን ስትከታተል እንደቆየች ችሎቱ አስረድቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጥቆማ‼️

ወቅታዊ እና እውነተኛ የመረጃ እጦት ለጋጠማችሁ፣ የቱን ልመን? ብላችሁ ለተወዛገባችሁ ፣ እነሆ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ መረጃዎችን ካሉበት አጣርቶና ፈልፍሎ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ።መረጃዎቹ ለየት ያሉ ፈጣን እና እውነተኛ ናቸው።

በእርግጠኝነት በሀላፊነት የተሞላ መረጃን ያገኛሉ👌"በዚህ ሊንክ ግቡ 👉 /channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ ከ74ሺ በላይ ግለሰቦች የባንክ ሚስጥር ቁጥራቸው ተወስዶ ዘረፋ ተፋፅሞባቸዋል ተባለ::
#FastMereja
በ2ዐ15 ዓ.ም ብቻ ከሞባይል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ጋር ተያይዞ ከ74ሺ በላይ ግለሰቦችን የሚስጥር ቁጥር አጭበርብረው በመውሠድ ዘረፋ የሚፈፅሙ ሰዎች መበራከታቸውን የድርጊቱ ሠለባ የሆኑ ተጠቃሚዎች ተናግረዋል፡፡

አጭበርባሪዎቹ ከባንክ የደወሉ በማስመሠል የተለያዩ የተለያዩ የማሳመኛ መንገዶችን እንደሚጠቀሙ የወንጀሉ ሠለባ የሆኑ ደንበኞች ኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1 ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዢ አቶ ሠለሞን ደስታ ከባልደረባችን ከታደሰ አለብኝ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ባደረጉት ቆይታ በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር እና ወንጀል እንደሚፈፅም ተናግረዋል፡፡

በብሄራዊ ባንክ በኩል ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የሚፈፅም ወንጀሎችን ለመከላከል የፋይናንስ ተቋማትን መከታተል የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል፡፡

ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ሴኩሪቲ ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ዳዋ በበኩላቸው በማጭበርበር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች የባንክ ደንበኞችን መረጃ በተለያየ መንገድ እንደሚያገኙ ገልፀዋል፡፡

ቁጥሮችን በመገመት፣ አንዱ መንገድ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ መሲሳ አብዲሳ በዘርፉ እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎች መበራከታቸውን ገልፀው ደንበኞች መሠል ድርጊቶች ሲፈፀሙባቸው በ15 ቀን ውስጥ ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ዘግቦታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሞስኮ ዋናው እምብርት ላይ ፡ ሚገኘው፡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቢሮ ፡ በድሮን ተመታ።
የራሺያ መልስ ይከፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ዋለ
******************************

መነሻውን ጅቡቲ ወደብ፣ መዳረሻውን ወረታ ከተማ አድርጎ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ አሽከርካሪው ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ ተግባር ሲሰራ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ህገወጥ ድርጊቱ የተፈፀመው በባህርዳር ከተማ፣ ሰባታሚት ቀበሌ ሀምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን፤ በአሳቻ ሰዓት ከሌሊቱ 6:00 የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።

አብዛኛው ማዳበሪያ ሳይራገፍ ከነተሽከርካሪው መያዝ ቢቻልም ከ140 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለግለሰቦች በህገወጥ መንገድ መሰራጨቱን ፖሊስ ባደረገው ክትትል ደርሶበታል።

ፖሊስ ባደረገው የቤት ለቤት ፍተሻ ከተሽከርካሪው ተራግፎ በግለሰቦች ቤት የተከዘነ በርካታ የአፈር ማዳበሪያ ማግኘቱን አስታውቋል።

89 ኩንታል ማዳበሪያ በአንድ ግለሰብ ቤት ተከዝኖ የተገኘ ሲሆን፤ 24 ኩንታል ማዳበሪያ ደግሞ በሌላ ግለሰብ ቤት በአልጋ ስር እና በኩሽና ተከዝኖ መገኘቱ ተጠቅሷል።

አሽከርካሪው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሱዳን በደረሰ የአዉሮፕላን መከስከስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ
*************************

በፖርት ሱዳን የአየር ማረፊያ አንድ አንቶኖቭ አዉሮፕላን ተከስክሶ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በተከሰተው አደጋ ህይዎታቸዉን ካጡት መካከል አራቱ ወታደሮች መሆናቸዉም ተገልጿል።

በፖርት ሱዳን የአየር ማረፊያ ዛሬ ጠዋት ለደረሰዉ የአዉሮፕላን መከስከስ አደጋ መንስኤዉ የቴክኒክ ብልሽት መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል።

አንድ ህፃን ከአደጋዉ መትረፉንም የሀገሪቱ ጦር አስታዉቋል።

በሱዳን በቀጠለው ጦርነት ሳቢያ በሀገሪቱ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የአውሮፕላን ማረፊያ ፖርት ሱዳን ብቻ መሆኑም ተጠቅሷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ወደ አማራ ክልል ይገባል ከተባለው ውስጥ ገና ከ1.6 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ በላይ ይቀራል‼️
ወደ አማራ ክልል ይገባል ተብሎ በፌደራል መንግስቱ ግዢ ከተፈጸመበት ውስጥ አሁንም ድረስ ከ1.6 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ በላይ ወደ ክልሉ አልገባም።
የገበሬው የእርሻ ወቅት ደግሞ ቢበዛ ሁለት ሳምንታት ብቻ ይቀሩታል።
ከግብርና ቢሮ ምንጮቼ እንደሰማሁት ክልሉ በካርጎ ወደ ሶስት ከተሞች ይጓጓዙልኝ (ኮምቦልቻ፣ባህርዳር፣፣ ጎንደር) ብሎ በቃል ደረጃ የጠየቀ ቢሆንም የአውሮፕላን ማጓጓዙ ውድ ነው የሚል ምላሽ እንደለ ሰምቻለሁ።
Ethiopian shipping line ደግሞ ከጅቡቲ ወደ ኮምቦልቻ በደረቅ ጭነት ለማጓጓዝ አሽከርካሪዎች ለጥቅማጥቅም ሲባል በየመንገዶቹ ማጓተት እየበዛበት እንደሆነ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ።
ለምሳሌ አንድ የጭነት መኪና ከጅቡቲ ኮምቦልቻ ለመድረስ 3ቀናትና ባህርዳር ደግሞ 4ቀናት የሚጨርስበት ቢሆንም ባሁኑ ሰአት ግን ከ6-7 ቀናት እየፈጁ እንደሚመጡ ተነግሯል።
በዚህ ጉዳይ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል።
©አዩዘሀበሻ
♦የረፋድ መረጃዎች በዩቱብ ቻናላችን አሉ፣ከስር ባለው ሊንክ subscribe👇👇
https://youtu.be/laIrP8hMXwM
https://youtu.be/laIrP8hMXwM

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጌታቸው ረዳ ዴንቨር ያደረገው ንግግር

ትግራይ ላይ የተደረገው ጦርነት በ”design” የተደረገ ነው አማራን አፋር ከተደረገው እይወዳደርም

መከላከያ በወልቃይትና ራያ የአማራ አስተዳደር መዋቅሮችን የማፍረስ ግዳጅ ተሰጥቶት እየሰራ ነው ስራውን ጀምሯል In principle ፌደራል መንግስት ግዛቶቹን ለመመለስ ተስማምቷል

በብዙ እስር ሽዎች የሚቆጠር ሰራዊት አለን
Via Gizaw Legesse

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

107 ካሬ

110 ካሬ

115 ካሬ

120 ካሬ

127 ካሬ

138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won

👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354
+251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…
Subscribe to a channel