muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

በዚህ ሰዓት በጎንደር ዙሪያ 18 በሚባለው አከባቢ በመከላከያ ሰራዊትና በህዝቡ(ፋኖ) መሃል ውጊያ እየተካሄደ ነው። በአዘዞም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። ኢንተኔት ተዘግቷል። የስልክ መስመር ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው። በመከራ ሁለት ሰዎች ዘንድ ደውዬ ነገሮች ከበድ ያሉ እንደሆኑ ነግረውኛል። ትላንት ከአዘዞ አከባቢ የደረሰኝ መረጃ አገዛዙ ድሮን መጠቀሙን የሚያሳይ ነው። የዛሬው ውጊያ መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ሰሞኑን የደረሰውን ኪሳራ ለመበቀል በሙሉ ሃይሉ ከመጣው የአገዛዙ ጦር ጋር የሚደረግ እንደሆነም መረጃውን ያካፈሉኝ ሰዎች ገልጸውልኛል። ስለደረሰው ጉዳት ለጊዜው ማወቅ አልተቻለም።

በባህር ዳር ወደ ሞጣና ደብረማርቆስ የሚወስዱት መንገዶች በፋኖ ሃይል መዘጋቱንም አንድ አመራር አሁን ነገሮኛል። የተዘጋውን መንገድ ለማስከፈት 34 የሚሆኑ የአድማ በታኝ አባላት ተልከው መሳሪያቸውን አስረክበው ተመልሰዋል። ነገሮች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው። ከወለጋ ወደ ደብረማርቆስ አቅጣጫ በርካታ ቁጥር ያለው የአገዛዙ ሰራዊት በእግር እየገሰገሰ መሆኑንም ሰምቼአለሁ። በህዝባዊ የፋኖ ሃይል የተያዘችውን ደብረማርቆስን ኢላማ አድርጎ ለማስለቀቅ እንደሆነ ይገመታል።
via Mesay

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በፌስቡክ ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት

"የዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም እያሳሰብሁ፤ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።"

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

3 ዐበይት ዜናዎች

1፤
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ሚሊሻዎች በደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ታቦር አቅራቢያ ትናንትና ዛሬ ውጊያ ማካሄዳቸውን ሮይተርስ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የከተማዋን ሐኪምና ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል። ሐኪሙ፣ በጥይትና በከባድ መሳሪያ በከባድ ኹኔታ የቆሰሉ ሦስት ሰዎችና ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሌሎች 10 ሰዎች በከተማዋ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ ማግኘታቸውን እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ዜና ምንጩ፣ ውጊው ዛሬም እንደቀጠለ መኾኑን፣ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች መዘጋታቸውንና ቁስለኞች ከሆስፒታሉ የሚደርሱት በእግር ጉዞ መኾኑን ሐኪሙ ነግረውኛል ብሏል።

2፤
በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አካባቢ ዛሬም በመንግሥት ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውን ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮች ሰምታለች። ትናንትም በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ በፋኖ ታጣቂዎችና ከመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የዋዜማ ምንጮች ገልጸዋል። የስፔን ኢምባሲ፣ በከተማዋ የሚገኙ ስፔናዊያን ከቤታቸውና ሆቴላቸው እንዳይወጡ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፏል።

3፤
የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ መንግሥታቸው በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መኾኑን ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ይልቃል ውይይት የሚፈልጉ አካላት ነፍጣቸውን አስቀምጠው ለውይይት እንዲቀርቡ ጥሪ አድርገዋል። መከላከያ ሠራዊት በክልሉ እያካሄደ ያለው "የሕግ ማስከበር" እንቅስቃሴ መኾኑን ይልቃል በድጋሚ ገልጸዋል።
ዋዜማ ዘገባ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎ እና በጎጃም ከባድ አደጋ ለሀገር የሚፈጥር ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዘንድሮ የክረምት ትምህርት የለም ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በ21 የኤፈርት ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነ

በትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ስር የሚገኙ 21 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ። ድርጅቶቹን በጊዜያዊነት ሲያስተዳድር የቆየው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ኃላፊነትም እንዲሻር ፍርድ ቤቱ አዝዟል።

እነዚህን ተደራራቢ ትዕዛዞች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 21፤ 2015 የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው። የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ትዕዛዞቹን ያስተላለፈው፤ ፍትሕ ሚኒስቴር በኤፈርት ስር ያሉ ድርጅቶች ላይ የተሰጠው ዕግድ እና በጊዜያዊነት የማስተዳደር ኃላፊነት እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

በጦርነት እና በድርቅ የተጎዳውን የትግራይ ክልል ኢኮኖሚ መልሶ የማሻሻል ዓላማን ይዞ በ1987 ዓ.ም የተመሰረተው ኤፈርት፤ በኮንስትራክሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርና፣ ማዕድን እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በስሩ ሲያስተዳድር ቆይቷል። ሱር ኮንስትራክሽን፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ጉና ትሬዲንግ፣ መሰቦ ሲሚንቶ እና አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ በኤፈርት ስር ከሚተዳደሩ ግዙፍ ድርጅቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11572/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ይህች ምስኪን እህታችን ደቡብ ሱዳናዊት ናት

እሷ እና ባሏ ሲነጻፀሩ ባሏ ይጠቁራል (ጠይሜ ነው የሚላት)
እናላችሁ🤔የአብራኩን ክፋይ ሊስም ሲጠብቅ ሚስቱ የወለደቻቸው መንታ ህጻናቶች ነጭ ሆነው ብቅ ብለው አስደመሟቸው

እነዚህ ጥንዶች ሚስትየው "ወንድሜ" ባሏ ደግሞ "ወዳጄ" ብለው የሚጠሩት ነጭ እንግሊዛዊ ጎረቤት አላቸው🙌🏼ጉርብትናቸውን ሁሉም ይቀናበታል

የባል እና ሚስት ቤተሰቦች መጥተው እናትየውን "ምነው ልጆቹ ነፁ?" ሲሏት

👇🏾

“ባሌ ወተት አብዝቶ ይጠጣል! በቀን ሁለቴ እና ሶስቴ ነው የሚጠጣው:: ልጆቹ ነጭ የሆኑት ለዚያ ይመስለኛል" ብላለች

ውይ ወንድ ልጅ ግን🤦🏾

እሷ ፊት ባይጠጣስ ቆይ? ምናለበት ወተት ጭራሽ ባይጠጣስ?
Via Zemelak

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#በምስራቅ ጎጃም ዞን "ተማሪወች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ መኪና መገልበጡ ተነገረ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከእናርጅ እናውጋ ወረዳና ከደብረ ወርቅ ከተማ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የፈተና ጣቢያ ሲጓዙ አንበር ከተማ አካባቢ በተፈጠረ የትራፊክ አዳጋ ከአንድ ሠው መጠነኛ ጉዳት በስተቀር በሌሎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ከአነደድ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጸ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Via 👇
Join 👉 t.me/wasulife
https://bit.ly/3PYWA12
https://bit.ly/3PYWA12
https://bit.ly/3PYWA12
https://bit.ly/3PYWA12

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የገና በአልን በፈረንጆቹ አቆጣጠር እንድታከብር ከመንግስት የተሰጣትን ትእዛዝ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡ በትላንትናው እለት የዩክሬይን ፓርላማ የገና በአል የሚከበርበትን ቀን ወደዲሴምበር 25 የሚቀይረውን ህግ ያፀደቀ ሲሆን ህጉ ተፈፃሚ እንዲሆን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ፈርመውበት ነበር፡፡
ቀደም ሲል የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል የሆነው ገና የሚከበረው እንደኢትዮጵያና ሌሎች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ታህሳስ 29 እንደነበር ይታወቃል፡፡ ዘለንስኪ አዲሱን ህግ ያወጡት ከሩሲያ ባህል ለመላቀቅ በሚል መሆኑን መናገራቸውም ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ‹‹መጪውን የገና በአል የምናከብረው ከዚህ ቀደም በምናከብርበት እለት ይሆናል፡፡ በርካታ የእምነቱ ተከታይ ዩክሬናዊያን ስላሉ የእነሱም መብት ሊከበር ይገባል›› ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ፖለቲከኞች የገና በአልን ማክበሪያ ቀን መቀየር ከሩሲያ ባህል መራቅ ነው በሚል ያቀረቡትን ሀሳብ ትክክል ያልሆነና ባልተሟላ መረጃ የቀረበ ብለውታል፡፡ አባባላቸውን ሲያብራሩም ‹‹ታህሳስ 29 ቀን የገናን በአል ማክበር የሩሲያን ባህል መከተል አይደለም፡፡ ይልቁኑ የጥንታዊት ቅድስት እየሩሳሌምን የዘመን አቆጣጠር መከተል ነው፡፡ ሁሉም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአላት የሚከበሩት በዚህ የጁሊያን ካሌንደር ነው›› ብለዋል፡፡

የዩክሬይንና ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ መፈጠሩና በመንግስት ጥርጣሬ ውስጥ መውደቁ ይታወቃል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከሳምንት በፊት በትግራይ መንበረ ሰላማ ለኤጲስ ቆጶስ ከመረጣቸው መካከል ሊቀ አእላፍ አባ እስቲፋኖስ ገ/ጊዮርጊስ በቀድሞው መጠሪያቸው አባ ፀጋይ በመኪና ተገጭተው ሆስፒታል ገብተዋል።

ባለፈው ሳምንት ጳጳስ ሆነው የተሾሙት አባ እስጢፋኖስ በመኪና ተገጭተው እስካሁን ከኮማ አልወጣም። ሰውዬው የ18 አመት ሴት ልጅ እንዳላቸው የልጅቷ እናት ነኝ ያለች ሴት የሰጠችው ኢንተርቪው በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ነበር።

ጥላሁን አረፈ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እንደ ብሔርተኛ ነውራም የለም "ልቀፍህ ብትለው እዘለኝ ይለሃል፣ልያዝህ ብትለው፣ጎትተኝ ይልሃል፣በቃ ዘወር በል ብትለው "ጥሎኝ ሄደ ብሎ ይቀውጠዋል። አሁን አንዱ የመንግስት ባለስልጣን ከመሬት ተነስቶ " በሚሊኒየም አዳራሽ አሸንዳ በዓል አይከበርም ቢል "እንዴት እንከለከላለን በደማችን እና በአጥንታችን የገነባናት ኢትዮጵያ እኛን ከልክላ ባለፈው ለኤርትራውያን የነፃነት በአላቸው ፈቅዳና አስጨፍራ ብለው ምድሩን ሰማይኑን ይቀውጡት ነበር።

አሁን እየሆነ ያለው ግን በጣም የሚገርምና የሚያሳፍር ነው። አሸንዳ በዓል በሚሊኒየም አዳራሽ ለማክበር ያዘጋጁ ሰዎች እንዳሉ ሰምተናል። ተዋቂዎች የጦርነት ዘፋኞች በአሸንዳ በዓል ለመዝፈን ተጋብዘዋል ይህንን የተመለከቱ በአገርና በውጭ የሚኖሩ ብሔርተኞች " እንዴት አዲስ አበባ ላይ ይከበራል? እኛ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል እየታገልን አሸንዳን እንዴት ሚሊኒየም አዳራሽ ይወሰዳል ሌላም አስነዋሪ ስድቦችን በማዝነብ አንዳንዶቹ ደግሞ "ከመንበረ ሰላማት እንማር ማንም እዚህ ሰው እዚህ አዳራሽ እንዳይገኝ በማለት (Boycott) እያሉ ነው።
ወዲ ሻምበል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በምስራቅ ወለጋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ጊምቢ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በፍጥነት ከመንገድ ወጥቶ በመገልበጡ ነው የደረሰው።

በአደጋው እስካሁን የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ትራፊክ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር በላቸው ቲኬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም በ46 ተሳፋሪዎች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።

በመላኩ ገድፍ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ራሺያ ለቡርኪናፋሶ፣ ዝምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ እና ኤርትራ 50,000 ቶን ነፃ ስንዴ ለመስጠት ቃል ስትገባ ኢትዮጵያን አላካተተችም። እርዳታው በቀዳሚነት ይገባት የነበረው ሀገራችን ኢትዮጵያ ነበረች።

ከዩክሬን ጋር ባለው ጦርነት ስንዴ ዩክሬን እንዳታወጣ ራሺያ ማገዷ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጋር ደውለው ስለ ስንዴው ጉዳይ መነጋገራቸው ይታወሳል።

ራሺያ በዚህ የተበሳጨች ይመስላል። ስለስንዴው እርዳታው መከለክሏ ጉዳይ ከኢትዮጵያ መንግስት የውጪ ፖሊሲ ወደ ምዕራብ ማድላቱ ራሺያን ሳያበሳጭ አልቀረም።

እንደሚታወሰው በሰሜኑ ጦርነት ራሺያ እና ቻይና ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸው በመጠቀም መንግስትን ከማዕቀብ መታደጋቸው ይታወሳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📌በ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት ይግዙ

እጅግ በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ አፓርታማዎችን

በረጅም ጊዜ ክፍያ 
ገዝተው ቋሚ ንብረትዎ ያድርጉ

የ60/40 የአከፋፈል አማራጫችንን ይጠቀሙ

የቀሩን የካሬ አማራጮች፦

            107 ካሬ

            110 ካሬ

             115 ካሬ

             120 ካሬ

             127 ካሬ

             138 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1 አፓርታማዎች አሉን

ለበለጠ መረጃ
👉 http://t.me/Tsion_won

👉 /channel/nvhfjnfdhnojbfedgjn
☎️ +251912287354           
      +251946404247

#Viber | #IMO | #WhatsApp | #Telegram
www.ayatsc.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ወጣት የኔወርቅ አበበን ዘርፈው ከባጃጅ በመወርወር ለሞት የዳረጓት ተጠርጣሪዎች በቁቁጥር ሥር ዋሉ

በሐረር ከተማ የኔ ወርቅ አበበን ዘርፈው ከባጃጅ በመወርወር ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረጉ ግለሰቦች በሙሉ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሀረሪ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጃቢር አሊዪ አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ እንደገለጹት መጋቢት 13/2015 በግምት ከምሽቱ 12:00 ላይ በሀረሪ ክልል ሽንኮር ወረዳ ሞቢል ተብሎ በሚጠራበት ስፍራ፤ ሟች የኔ ወርቅ አበበ የተባለችውን ከምትማርበት ሐረር መምህራን ኮሌጅ ወደ ቤት ስትመለስ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 4248 ሐረ- የሆነች ቲቪኤስ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ 1ኛ ሮቤል አህመድ (ዋና ንጥቅያ የፈጸመ) 2ኛ ዳግም ቴዎድሮስ አለማየው 3ኛ በቅፅል ሥሙ ኪያ ተብሎ የሚጠራ በጋራ በመሆን ሟችን ባጃጅ ውስጥ ካስገቧት በኋላ ቦርሳዋን ታግለው በመጠቅ ከባጃጁ ወርውረዋት ከመንገዱ በተቃራኒ በኩል ይጓዝ የነበረ ቅጥቅጥ ሀይሱዙ አውቶብስ ተሽከርካሪ ተገጭታ እንድትሞት አድርገዋል።

ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል ተሸሽገው እንዳሉ የሐረሪ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እና ምርመራ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራው ተጠናቆ ለዐቃቢ ህግ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በወቅቱ ሟችን የገጨ ቅጥቅጥ ሀይሱዙ አውቶብስ መኪና ምርመራው ተጠናቆ ለዐቃቢ ህግ መሠጠቱንም ገልጸዋል፡፡

የኔወርቅ አበበ በ2014 ከሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካውንቲንግና ፋይናንስ በዲፕሎማ ተመርቃ በቅርቡ በሐረር መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ትምህርቷን ለማሻሻል በዲግሪ መማር በጀመረችበት 3 ቀናት ውስጥ በከተማዋ የዝርፊያ ተግባር በሚፈፅሙ ሌቦች አማካኝነት የእጅ ስልኳንና ቦርሳዋን ተነጥቃ፣ ወደ አስፓልት ተገፍትራ በሞት መለየቷን በወቅቱ አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡
አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
እስከ ሀምሌ 29 ቀን ብቻ
##ሮያል ሪል እስቴት
#በመሃል_አዲስ አበባ
በጀርመን አደባባይ
#ዋና_መንገድ ላይ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን

🌻በፈጣን የግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ

ግንባታቸው 50% የደረሱ
የመጀመሪያ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!

ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 8000 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።

G+12 Apartment
በወለል 4
📍15% ቅድመ ክፍያ
የካሬ አማራጭ

▶ 125 ,128,130&136 ባለ ሁለት መኝታ

▶ 150 &155ባለ ሶስት መኝታ

''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨‍🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ 0929831836
0713128810
@Kidistgash

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ መኮንን የሚከተለውን መልዕክት በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል 👇

"በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መጥተዋል::
በመሰረቱ ብዙ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ግን ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ
1. የጥያቄዎችን መፍቻ መንገድ የሚያደናቅፍ
2. ያለንን የሚያሳጣ
3. በዘላቂነት ሊታዩ ይገባቸዋል የምንላቸውን ጉዳዮች እንዳይፈቱ የሚያወሳስብ አካሄድ ነው፡፡
'ሰላም ከሌለህ ሁሉን ታጣለህ' የሚባለውን እውነታ ከልብ በማጤን በአስተውሎት መጓዝ በሚገባን ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
በየዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እና ችግሮች ሲገጥሙ በጥበብ ተሻግረው ያሻገሩንን የአባቶቻችን ጥበብና አስተውሎት ማጥበቅ ይጠይቃል፡፡ የሀገር ሽማግሌ የጠፋበት፣ ታላቅ የሌለበት፣ መካሪ የሃይማኖት አባት የታጣበት ይመስል ሁላችንንም የሚያባላና የሚበላ አካሄድ ይስተዋላል፡፡
የዚህ መጨረሻ በግራም በቀኝም ከውጭም ከውስጥም ላሰፈሰፉ ኃይሎች ሰርግና ምላሽ ሆኖ አቅም የሚያሳጣ፣ ክብራችንን የሚጎዳ፣ ተጋላጭነታችንን የሚያሰፋ በአጠቃላይ ሁሉንም የሚያሳጣ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
ከለውጡ ብዙ የጠበቅናቸው ግን ደግሞ ምላሽ ያላገኘንባቸው ያላረኩንና ሌሎች ችግሮችና ስሜቶች ይኖራሉ፡፡
ለእነዚህ ጉዳዮች ቆም ብለን በማሰብ በሰላሙ መንገድ ዘላቂ መፍተሄ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም የሁሉም ዋስትና የሆነውን ህግና ሥርዓት በተሟላ መልኩ ማክበርና ማስከበር ይገባል፡፡ "

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በትግራይ የሚገኙ ብፁን አባቶች ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ቅዱስ ሲኖዶስ በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ

2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ተመልክቱ እነዚህ ሁለት ዜናዎች
አንዳኛው የጦርነት ዜና ነው።
ሁለተኛው የልማት ዜና ነው።
አይቃረንም?
ግራ የገባው ሀገር!

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ይህንን ምስኪን ላስተዋውቃችሁ እስኪ🙌🏼

👇🏾

ሙሳ ሴሞጎሮሬ ይባላል
ኡጋንዳዊ ሲሆን በኡጋንዳ ሀገር የአንድ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ነው

ይህ ምስኪን የህግ ሰው ኢሬኔ ሙቶኒዪ የምትብል የሴት ፍቅረኛ አለችው:: ኢሬኔ በኡጋንዳ የህግ ጥናት ማእከል የህግ ተማሪ ስትሆን ሀምሌ 29 ላይ የማጠቃለያ ፈተና ነበረባት

መቼም የዚህ ጾታ መከራ አያልቅም አይደል?🤗😝

ሙሳ ሶሞጎሮሬ ሹሩባ ተሰርቶ: ጡት መያዣ አድርጎ: ቀሚስ ለብሶ: ታኮ ጫማ አድርጎ እና ሜካፕ ተሰርቶ እንደ ሴት ቂን ቂን እያለ ለሴት ፍቅረኛው ፈተና ሊፈተን ይገባል

በፈተናው መሀል ግን ተነቃበት
የሴት ፍቅረኛው ኢሬኔን ጠንቅቆ የሚያውቅ አንድ መምህር (በመልክ ይሁን በሽታ ያወቃት አልታወቀም እስካሁን😝) ጥርጣሬውን ወደ ፍተሻ ሲቀይረው ሙሳ ሶሞጎሮሬ ሆኖ ተገኘ

የኡጋንዳ ፖሊስ በደቂቃዎች ውስጥ ሙሳን ከሴት ወደ ወንድ ቀይሮት በማጭበርበር እና ፎርጂድ ሙከራ ከሶት ፍርድ ቤት ገትሮታል
Via Zemelak Endreas

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ 18 ሾፌሮች መታገታቸውን ሰምተናል።
ዘሀበሻ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#ከስራ ተሰናበተ‼

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ዶ/ር ይልቃል ከፈለ “ኃላፊነትህን በአግባቡ አልተወጣህም” በሚል የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እንግዳው ጠገናውን አሰናብቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰሜ ወሎ ጉባላፍቶ

በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገብሬ ገበያው ትናንት ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ አልታወቀም።በአማራ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተበራክተዋል።ከአቶ ግርማ የሽጥላ ግድያ በኋላ የደብረብርሃን ፖሊስ አዛዥ፣የሸዋሮቢት አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ፣የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል ሃላፊ በተመሳሳይ ጥቃት ህይወታቸውን ካጡት የመንግስ የስራ ሃላፊዎች ተጠቃሽ ናቸው።
Via Wasu Mohammed

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ፑቲን ለዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ሂሊኮፕተር አበረከቱ፡፡

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ዘመናዊ ሂሊኮፕተር አበርክተዋል፡፡

በሩስያ እየተካሄደ በሚገኝው የሩስያ አፍሪካ ስብሰባ ላይ የተገኙት የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ከፑቲን ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ከአውሮፓ ህብረት እና ከአሜሪካ በርካታ ማዕቀቦች የተጣሉባቸው የዚምባብዌ ባለስልጣናት ከሩስያ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት እያጎለበቱ ይገኛሉ፡፡

ሩስያ የሚገኙት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩስያ ዚምባብዌ ወዳጅ ሀገር መሆኗ ማንም የሚያውቀው ነው ከንግዲህ ማንም ሊያበላሸው አይችልም ብለዋል፡፡

ከፑቲን የተበረከትላቸው ዘመናዊ ሂሊኮፕተር አስመልክተው እንደተናገሩትም ከወደጃችን የተበረከተልን ዘመናዊ ሂሊኮፕተር ለኛ ብዙ ትረርጉም አለው ብለዋል፡፡

በአውሮፓ እንደዚሁም በአሜሪካ የማዕቀብ ሰለባ የሆኑ ሃገራት መተባበር አለባቸው" ሲሉ ምናንጋግዋ ከሄሊኮፕተሩ ፊት ለፊት ቆመው ንግግር አድርገዋል፡፡(ኢትዮ ኤፍኤም)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዚህ ወዳጄን የዩቱብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ አረበኛ፣ ቻይነኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋን ይወቁ። በቀላል በሚስብ እና ለተመልካች በሚገባ አቀራረብ የውጪ ቋንቋዎችን ያስተምራል። አረብ ሀገር ለምትሄዱና አረብ ሀገር በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማራችሁ፣ ቻይነኛ እጅግ ተፈላጊ ቋንቋ በመሆኑ ለመማር የምትሹ፣ የአፍሪካ ሁነኛውን የዲፕሎማሲ ቋንቋ የሆነውን ፈረንሳይኛን በቀላሉ ለመልመድ የብርሃኑ ባይሌን ይህ የዩቱብ ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ! እኔ ሰብስክራይብ አድርጌ ፈረንሳይኛ እየተማርኩ ነው። ይህን ታታሪ ወጣት አበረታቱት 👌

https://youtube.com/watch?v=lzM4HmEmf8s&feature=share

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበር አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልጿል።

በባለስልጣኑ የከፍተኛ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ክትትል እና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው አድነው ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደተናገሩት፥ የመማር ማስተማር ስራው ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን አዲስ መመሪያ እና መስፈርት ተዘጋጅቷል።

የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የሚጠበቀውን ደረጃ እና ጥራት ማስጠበቅ ያስችላል የተባለው አዲስ መመሪያ እና መስፈርትም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።

በመመሪያው የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ በርካታ መለኪያዎች የተቀመጡ ሲሆን፥ አንዱ የመውጫ ፈተናን የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም እያንዳንዱ ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው በማንሳት ይህ ካልሆነ ግን የትምህርት ፕሮግራሙ ይሰረዛል ብለዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት 50 እና ከዛ በላይ ያመጡት 12 ሺህ 422 ወይም 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወቃል።

በዙፋን ካሳሁን

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጥቆማ‼️

ታታሪዎችን ማበረታታት ይልመድብን❗
የበርካቶች ምርጫ ስለሆነ ቻናሉን ለማታውቁት ልዩ ጥቆማ ነው‼️

መረጃ በፍጥነት እና በጥራት በማቅረብ ረገድ ሁላችሁም ሊኖራችሁ የሚገባ የቴሌግራም ቻናል ነው።

ከስር ባለው ሊንክ join ያድድጉት፣በእርግጠኝነት ያተርፋሉ👇👇👇👇
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk
/channel/+sx8GYG1oT3lmZmFk

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

" በጊዜ ገደቡ ምላሽ ካልሰጠ ወደ ክሥ እናመራለን " የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ቤቶቻቸው ለፈረሱባቸው ሰዎች አቤቱታዎች፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ተቋሙ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ ጋራ ተያይዞ፣ ከ100 ሺሕ በላይ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ፣ ከዚኽ ቀደም ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርመራ ዲሬክተር አቶ ቶሌራ በላይ፣ የከተማ አስተዳደሩ፥ ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ በደብዳቤ እንደተጠየቀ ገልጸዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፣ ጉዳዩ ወደ ክሥ እንደሚያመራ፣ የምርመራ ዲሬክተሩ አቶ ቶሌራ በላይ አመልክተዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የሸገር ከተማ አስተዳደር ያለው ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም ግን በሰጠው " ለእንባ ጠባቂ ተቋም 100 ሺሕ አቤቱታዎች መቅረባቸውን አላውቅም " ብሎ ነበር።

የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ፣ " ሕገ ወጥ ግንባታ " በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100 ሺሕ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ ማሳወቁ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ፣ እንባ ጠባቂ ተቋሙ፥ የሸገር ከተማ አስተዳደር ለአቤቱታ አቅራቢዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ፣ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ እንደጠየቀው ማስታወቁን ሬድዮ ጣቢያው አመልክቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

መንግሥት አርሶ አደሩ የጠየቀውን የአፈር ማዳበሪያ የማቅረብ አቅም የለኝም አለ

መንግሥት ክልሎች የአርሶ አደሩን ፍለጎት አጥንተው ያቀረቡትን የአፈር መዳበሪያ ፍላጎት የመመለስ አቅም እንደሌለው አስታውቋል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በዘንድሮው የመኸር ወቅት አጠቃላይ የኢትዮጵያ አርሶ አደር እንዲቀርብለት የተጠየቀው 20 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያው ቢሆንም የቀረበለት 10 ሚሊዮን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ አርሶ አደሩ የዘር ወቅት ሳያልፍ እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ አደባባይ ወጥቶ ቢጠይቅም፣ እሰካሁን ከተጠየቀው ግማሽ ብቻ ነው ለአገሪቱ አርሶ አደሮች የደረሰው፡፡

ክልሎች የአርሶ አደሩን ፍላጎት አጥንተው በየዓመቱ ለግብርና ሚኒስቴር የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ በዘነድሮው ዓመት የጠየቁት 20 ሚሊዮን ኩንታል ቢሆንም፣ የተገዛው 13.6 ሚሊዮን ኩንታል መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ክልሎች የጠየቁትን የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት፣ አገሪቱ የማቅረብ አቅም የላትም ብለዋል፡፡
በመጪው አመት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቀውስ ይፈጥራል ተብሏል።

በኢትዮጵያ የመኸር ወቅት አምራች በኾኑ አካባቢዎች፣ በዘንድሮው ወርኀ ክረምት፣ ማሳዎች ታርሰው ለዘር ዝግጁ ቢኾኑም፣ አብዛኞቹ በዘር እንዳልተሸፈኑ፣ የተባበሩት መንግሥት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(OCHA) ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በዘር በተሸፈነው የመሬት መጠን፣ በአማራ ክልል 50 በመቶ፣ በኦሮሚያ ክልል 80 በመቶ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 48 በመቶ፣ በደቡብ ክልል 50 በመቶ እና በትግራይ ክልል ደግሞ 30 በመቶው የታረሰ መሬት በሰብል መሸፈኑን ኦቻ ጠቁሟል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር 
በትግራይ ጌታቸው ረዳ በሌለበት የደብረፂዮን አንጃ ቡድን ሰልፍ በሚል ስበብ  የወታደራዊን ክንፍ ጠልፈው

ከፍተኛ አመፅ ላይ ናቸው። አንዳንዶች  መፈንቅለ መንግስት እያካሄዱ ነው ብለዋል። በአሁን ሰዓት ቁጥራቸው እስከ 6000 የሚገመት  የTDF  አባላት መቀለን ወራዋታል::

ጥያቄያቸው ብጣሽ ወረቀት ከ TDF መሰናበታችን አግባብ አይደለም ነው የሚሉት።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ55 ሺህ ታጋይ በላይ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ አድርጊያለሁ ማለቱ ይታወሳል።

ጌታቸው አሜሪካ ሲሆን የደብረፂኦን ሴራ እየሰራበት እንደሆነ እያተገመተ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel