ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ
***********************
አየር መንገዱ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።
መንገደኞችም በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከል (6787/+251116179900) በመደወል መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።
ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ ነሃሴ 3/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የቤንሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) የፓርቲውን ሊቀመንበር አብዱል ሰላም ሽንግልን ከሃላፊነት ማንሳቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ፓርቲው ሊቀመንበሩን ያገደው፣ ሊቀመንበሩ ከፓርቲው እውቅና ውጪ ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል በማለት እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። በስምምነቱ መሠረት፣ የክልሉ መንግሥት ለፓርቲው አመራሮች ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች የሃላፊነት ቦታዎችን ለመስጠት ተስማምቷል።
2፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ካሳ ተሻገር "አካልን ነጻ የማውጣት" አቤቱታቸውን ትናንት ለፍርድ ቤት እንዳቀረቡ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። ጠበቆች ክርስቲያን በፖሊስ እየተደበደቡ ተወስደው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ እንደታሠሩና ካሳ ተሻገርም በዚኹ ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ ማስረዳታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ጠበቆች፣ ፌደራል ፖሊስ "ያለመከሰስ መብታቸው" ያልተነሳባቸውን የኹለት ምክር ቤቶች አባላት በማሠር ሰብዓዊ መብታቸውን ጥሷን በማለት፣ ፍርድ ቤቱ የታሳሪዎቹን "አካልን ነጻ የማውጣት" መብት ያለ ቅድመ ኹኔታ እንዲያከብር መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ፖሊስ ለአቤቱታው ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አዟል ተብሏል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር በጠበቆቻቸው አማካኝነት “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታው የቀረበለት ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፤ የፌደራል ፖሊስ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጥ አዝዟል።
የአቶ ክርስቲያን እና ዶ/ር ካሳ ጠበቆች አቤቱታቸውን ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 2፤ 2015 ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ ያለመከሰስ መብት ያላቸው ደንበኞቻቸውን ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ “ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ ያቆያቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው። በጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ሰለሞን ገዛኸኝ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታ፤ በምክር ቤት የህዝብ ተወካዮቹ የተያዙበትን መንገድ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።
በአንድ ገጽ የተዘጋጀው ይህ አቤቱታ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ባለፈው ሳምንት አርብ ከመኖሪያ ቤታቸው “እየተደበደቡ ተይዘው” በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መታሰራቸውን አትቷል። ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በዚሁ ቀን ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው፤ በተመሳሳይ ቦታ ታስረው እንደሚገኙ በአቤቱታው ላይ ሰፍሯል። የፌደራል ፖሊስ ሁለቱንም ግለሰቦች የያዛቸው “ለጥያቄ እፈልጋቸዋለሁ” በሚል መሆኑንም በአቤቱታው ተመላክቷል።
* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11733/
በረራዎች ተሰርዘዋል!
*ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ መሆናቸውን ለክቡራን ደንበኞቹ ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጣችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን ትኬታችሁ ለአንድ ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቃችሁ ወደፊት በፈለጋችሁት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር የምትችሉ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆንላችሁ የምትፈልጉ ክቡራን ደንበኞቻችን አቅራቢያችሁ ወዳሉ የአየር መንገዱ የትኬት መሻጫ ቢሮዎች ወይንም የጉዞ ወኪሎቻችሁ በመቅረብ መስተናገድ እንደምትችሉ በትህትና እንገልጻለን፡፡
አየር መንገዱ በዚህ ረገድ ለሚፈጠረው መጉላላት ልባዊ ይቅርታውን ያቀርባል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገጻችንን (www.ethiopianairlines.com) ይጎብኙ!
ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም.
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !
👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:
➤ በ 500,000 ብር ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ
➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ - 4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት
➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ
👉 ከወለድ ነፃ
#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል
ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513
👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!!🤩
#Dmc real estate‼️
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
በለቡ መብራት ሀይል በመገንባት ላይ ያሉ ከ755,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።
📍15% ቅድመ ክፍያ(በካሬ 90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(#5% -10% discount includes)
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 132.እና 140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ
''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw
ሕ.ወ.ሓ.ት በሚል ስያሜ ፓርቲ ለመመሥረት በቀረበ የዕውቅና ጥያቄ ላይ ከፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት የተደረገው ክርክር ውሣኔ ያገኘ ሲሆን፤ ይህውም ፍርድ ቤቱ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቅድመ ዕውቅና ፍቃድ መጠየቃቸው፤ በተጠቀሰው ስያሜ የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን የሚያደናግር በመሆኑ፤ ቦርዱ ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበውን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ስሕተት አይደለም በሚል የቦርዱን ውሣኔ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል።
በክልሎች መካከል የሚኖረው የንብረት ክፍፍል የተፈጻሚነት ወሰን፤ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ጥያቄ አስነሳ
በነባሩ የደቡብ ክልል እና በአዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል መካከል የሚኖረውን የንብረት ክፍፍል በተመለከተ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በደቡብ ክልል ምክር ቤት አባላት ጥያቄ አስነሳ። የክልሉ ምክር ቤት አባላት ጥያቄውን ያነሱት፤ የንብረት ክፍፍሉ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ጭምር “ተፈጻሚ ይሆናል” በመባሉ ነው።
ለጥያቄዎች መነሻ የሆነውን የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 29፤ 2015 በተካሄደው የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ያቀረቡት፤ አዲሱን ክልል የሚያደራጀው ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ኑርዬ ሱሌ ናቸው። የውሳኔ ሃሳቡ፤ በነባሩ የደቡብ ክልል እና ዛሬ በይፋ ስልጣን በተረከበው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል መካከል የሚኖረውን አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ጉዳዮች የሚመሩበትን ስርዓት የያዘ ነው።
በስድስት ክፍሎች በተዘጋጀው የውሳኔ ሃሳብ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፤ የተፈጻሚነት ወሰንን የሚያትተው ይገኝበታል። በነባሩ እና በ12ኛነት ፌዴሬሽኑን በተቀላቀለው ክልል መካከል የሚነሳው የሃብት እና ዕዳ ክፍፍል፤ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆንም በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ሰፍሯል።
የቀድሞው ሲዳማ ዞን ከነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በመነጠል፤ በህዝበ ውሳኔ የራሱን ክልል የመሰረተው ከሶስት ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም ነበር። በነባሩ ክልል ስር የነበሩ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ተመሳሳይ አካሄድ በመከተል “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች” የተሰኘ 11ኛ ክልል ባለፈው ዓመት መመስረታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!!🤩
#Dmc real estate‼️
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
በለቡ መብራት ሀይል በመገንባት ላይ ያሉ ከ755,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።
📍15% ቅድመ ክፍያ(በካሬ 90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(#5% -10% discount includes)
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 132.እና 140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ
''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምን ምን ተግባራት ተከለከሉ?
ዜጎችን በቀጥታ የሚመለከቱት ከታች የተቀመጡት ናቸው 👇
ምስላዊ መረጃ፦ “የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ” በሚል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ተዘርዝረዋል። በአዋጁ መሰረት “ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ” የተከለከለ ነው።
በአማራ ክልል “የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር እንዲሁም የጸጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት” መከልከሉም በአዋጁ ላይ ሰፍሯል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን “እንቅስቃሴ” እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን “አላማ የሚቃረን እና የሚቃወም” ንግግር ወይም የቅስቀሳ በተመሳሳይ ክልከላ ተደርጎበታል።
ለታጣቂ ቡድኖች “በየትኛውም መንገድ” “የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ” መከልከሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ ላይ ተቀምጧል። ማንኛውንም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ “የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈጸም” እንደማይቻልም በአዋጁ ተደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ከአማራ ክልል በተጨማሪ እንዳስፈላጊነቱ “በየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ ተፈጻሚነት እንደሚኖረው” ተገለጸ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ወር ጸንቶ ይቆያልም ተብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Читать полностью…በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሞተርሳይክል እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጣለ
=======#=======
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ሐምሌ 28/2015 ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ እሮብ ነሃሴ 3/2015 እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ባሉት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሞተርሳይክል ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው ጠይቋል።
ቢሮው እገዳው የተጣለበትን ምክንያት ግልጽ ያላደረገ ሲሆን፤ እግዱን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።
/channel/addismaleda
በራያና ጠለምት ጉዳይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ሀሳብ በመቅረቡ የጠለምት ተወካዮች ስብሰባ ረግጠው ወጡ
=======#=======
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአማራ ክልል መንግሥት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 22/2015 በባህር ዳር ከተማ በተደረገ ስብሰባ ላይ በራያ እና ጠለምት አካባቢዎች የሚነሳው የማንነት ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እልባት እንዲያገኝ ሀሳብ ማቅረቡን ተከትሎ፤ ሀሳቡን አንቀበልም ያሉ የጠለምት ተወካዮች ስብሰባውን ረግጥው መውጣታቸውን አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች አረጋግጣለች።
ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት፤ “በስብሰባው ላይ “በጠለምት ሕዝበ ወሳኔ ይካሄዳል” እንዲሁም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት “ጠለምት እና አካባቢው በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ይተዳደራል” የሚል ሀሳብ በመቅረቡ ስብሰባውን ረግጠን ለመውጣት ተገደናል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/34659
__
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የበይነመረብ አገልግሎት ተቋረጠ
በክልሉ በመከላከያ እና ራሱን ፋኖ ብሎ በሚጠራው የታጠቀ ኃይል መካካል የሚደረገው ውጊያ በተለያዩ አካባቢዎች መስፋፋቱን ተከትሎ የበይነመረብ አገልግሎት መቋረጡን ካርድ አስታውቋል፡፡
የመብቶችና ዴሞክራሲ ማዕከል (ካርድ) በጉዳዩ ላይ ባወጣው መረጃ፣ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ ግጭቶችን እንደማያስቆም እና ዘላቂ ሰላም እንደማያሰፍን ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ግጭቱን ተከትሎ የዘጋውን የበይነ መረብ አግልገሎት እገዳው እንዲያነሳ ካርድ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በክልሉ የተከተው ግጭት አሰሳቢ መሆኑን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ፖለቲከኞች እየገለጹ ሲሆን፣ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ የክልሉ መንግሥት የሰላም ጥሪ እያቀረበ ባለበት ሁኔታ ግጭቱ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ መንግሥት እንደ ላሊበላ፣ ጎንደር፣ ወልዲያና ቆቦ በመሳሰሉ ግጭት ባለባቸው አካበቢዎች ከትላንት ምሽት ጀምሮ የበይነ መረብ አገልግሎት ላይ ገድብ ጥሏል፡፡ በኢትዮጵያ ግጭቶች በሚከሰቱበት ወቅት መሰል እግዶች የተለመዱ ሲሆን፣ ከከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ችግር ጋር በተያያዘ ለወራት ተገድቦ የቆየው የበይነበረም አገለግሎት የተለቀቀው በቅርቡ ነበረ።
የስነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ከተገልጋዮች በቀረበ ጥቆማ መሰረት ተጣርቶ በማስረጃ ጥፈተኛ መሆናቸው የተረጋገጡ 112 ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተጠያቂነት ስርዓትን ለማስፈን ከተገልጋዮች በቀረበ ጥቆማ መሰረት 133 ጥቆማዎችን ተቀብሎ በ112 አመራርና ሰራተኞች ላይ ከጹሑፍ ማስጠንቂያ እስከ ስንብት የሚደርስ አስተዳደርዊ እርምጃ ወስዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የዲሲፕሊን ችግር በታየባቸው 1060 ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተታድራዊ እርምጃዎችን የወሰደ ሲሆን በ288 ሠራተኞች ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ በ719 ሠራተኞች ላይ የደመወዝ/ገንዘብ ቅጣት፣ በ39 ሠራተኞች ላይ ስንብት፣ በ9 ሠራተኞች ላይ ከቦታ ማንሳት እና በ11 ሠራተኞች ላይ ባደረገው ማጣራት ነጻ ብሏቸዋል፡፡
ተቋሙ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችና ጥቆማዎችን ለመቀበል ከተዘረጉ የ905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከላት በተጨማሪ ደንበኞች ቅሬታቸውን ቀላልና ምቹ በሆነ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ዘመናዊ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ስርዓት ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ነሀሴ 3 ቀን 2015 ዓም
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!!🤩
#Dmc real estate‼️
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
በለቡ መብራት ሀይል በመገንባት ላይ ያሉ ከ755,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።
📍15% ቅድመ ክፍያ(በካሬ 90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(#5% -10% discount includes)
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 132.እና 140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ
''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw
በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ አለመቻሉ ተገለጸ
=======#=======
ማክሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ለተፈናቃዮች ተብሎ የመጣ የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁስ ቢኖርም፤ በከተማዋ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ለተፈናቃዮች ማድረስ አለመቻሉን ነው የጠቀሱት።
ተፈናቃዮች ክረምት በመሆኑ በቂ የእርዳታ አቅርቦት አለመኖሩን የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት 10 እና 15 ኩንታል እህል እንደሚያገኙ፣ አንዳንዴም ለኹለትና ሦስት ሳምንት ምንም ዓይነት እርዳታ የማይቀርብበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።
በከተማዋ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ሳይጨምር ከ23 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሦስት መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ የተባለ ሲሆን፤ ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ወቅት ከአራት ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሚኖሩበት ባቄሎ ካምፕ አጠገብ የከባድ የመሳሪያ ተኩስ መኖሩ ተጠቁሟል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/34706
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚስተዋለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።
አሁን ላይ የሚታዩት ግጭቶች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆሞ ሁሉም ጥያቄውን በውይይት ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በትናንትናው እለት አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ግጭት በፍጥነት የማይቆም ከሆነ ስራዎቹ ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ሰኞ ነሃሴ 1/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬም በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ሚሊሻዎች መካከል ግጭቶች ቀጥለው ውለዋል። በክልሉ ዋና ከተማ ባሕርዳር በተለይ ባለፈው ቅዳሜ ግጭት በነበረባቸው ቀበሌ 13 እና 14 እንዲኹም ከባሕርዳር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ግጭቶች ሲካሄዱ እንደዋሉ ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። በሰሜን ጎንደር ዞን በጎንደር ከተማና በዙሪያዋ እና በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረብርሃን ከተማ ዳርቻ በሚገኙ አካባቢዎችም በተመሳሳይ ግጭቶች እንደነበሩ ዋዜማ ያገኘቻቸው መረጃዎች አመልክተዋል።
2፤ በአማራ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ የኾነው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግርና ግጭት "በውይይት" እና "ድርድር" ሊፈታ የሚችልበት ኹኔታ ዝግ እንዳልኾነና ለዚኹም "ተከታታይ ጥረቶች" እንደሚደረጉ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ተቋሙ በክልሉ "ለዘረፋ የተደራጁ" ያላቸው ኃይሎች' መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲያቋርጡና ክልሉን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኙ አንዳንድ መንገዶች እንዲዘጉ በማድረግ፣ በክልሉ ሕዝብ ላይ "ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር" እየሞከሩ ነው ብሏል። "ከሽብር ቡድኖች"፣ "ከሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር" እና "ከሙስና" ጋር ግንኙነት ያላቸው ከ3 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙም ተቋሙ ገልጧል። በአማራ ክልል ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ስንት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ግን ተቋሙ አልጠቀሰም።
በአማራ ክልል ያለው ግጭት እና አለመረጋጋት፤ “በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት” ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ
በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ “የሰላም ጥረቶች እና ስምምነቶች” በክልሉም መደረግ የሚችልበት ዕድል እንዲፈለግ ዘጠኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠየቁ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ወቅት የጸጥታ አካላት “ያልተመጣጠነ ኃይል እንዳይጠቀሙ”፣ “ብሔርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች እና ጥቃቶች እንዳይስፋፉ” እንዲሁም የጅምላ እስሮች” እንዳይፈጸሙም ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።
ዘጠኙ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት፤ በአማራ ክልል የተከሰተው “ግጭት እና አለመረጋጋት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት” ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 1፤ 2015 ባቀረቡት ጥሪ ነው። ይህንን ጥሪ ካቀረቡት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር እና የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ይገኙበታል።
“ግጭቶችን የመከላከል እና ሰላም የማስፈን” ጥረት ጊዜ የማይሰጠው “አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እናምናለን” ያሉት ድርጅቶቹ፤ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት “እጅግ እንዳሳሰባቸው” በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ፤ “ግጭቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደዱ እና እየተስፋፉ” መሆኑን ያነሱ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት “ግጭቶችን ለማስቆም የሚወሰዱ እርምጃዎች የብዙሃንን ደህንነት፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እና ነጻነቶች አደጋ ላይ የማይጥሉ” መሆን አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
ሰለሁሉም ነገር እግዚያብሄር ይመስገን ሰላም ወጥተናል ዛሬ እኔ እና አርቲስት ቤዛዊት መስፍን።👇👇
አርቲስት ዳኜ ዋለ በፌስቡክ ገፁ ካጋራዉ የተወሰደ።
ዜና እስር‼
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ዋዜማ ሬዲዬ ዘግቧል።አቶ ክርስቲያን በህ/ተ/ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸው አለመነሳቱ ተሰምቷል።ፖሊስ ለምን እንዳሠራቸው ግን ለጊዜው አልታወቀም ሲል ዘገባ ጠቁሟል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ድምፃዊ ዳኜ ዋለ መታሰራቸው ተሰምቷል።
የዶቼቬሌ ዘገባ ነው ከታች ያለው 👇
በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ሁለት ቦታ ቦምብ ፈንድቷል። ፍንዳታው ስላደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ እንዳልወጣ የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እስቱድዮ ልንገባ ስንል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አሳውቆናል።
በአማራ ክልል ያለውን አሳሳቢ የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ አወጣ።
በመግለጫውም
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መቋረጡ ተሰማ
በዩንቨርስቲው አቅራቢያ በነበረው የተኩስ ልውውጥ አንድ ፈታኝ መምህር እና ሦስት ተማሪዎች መገደላቸው ተገልጿል።
በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በ“ፋኖ” ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለውን ውጊያ ተከትሎ፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ የሚገኘው የአስራ ኹለተኛ ክፍል የመልቀቅያ ፈተና መቋረጡን አዲስ ማለዳ አረጋግጫለሁ ብላለች።
ከሐምሌ 25/2015 ጀምሮ ለአራት ቀናት በአገሪቷ ውስጥ ባሉ ከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት መሰጠት የጀመረው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቅያ ፈተና፤ በጎንደር ከተማ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና የ“ፋኖ” ታጣቂዎች የሚያደርጉትን ከፍተኛ ውጊያ ተከትሎ በዩንቨርሲቲው ሲሰጥ የነበረው ፈተና በትናንትናው ዕለት መቋረጡን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
በዚህም ፈተና ላይ የነበሩ ተማሪዎች በተኩስ ልውውጡ ተደናግጠው ፈተና አቋርጠው መውጣታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ተማሪዎች ጠዋት ላይ የተሰጠውን ፈተና ተፈትነው የከሰዓቱን አቋርጠው መውጣታቸው ነው የተሰማው።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
እስከ ሀምሌ 29 ቀን ብቻ
##ሮያል ሪል እስቴት
#በመሃል_አዲስ አበባ
በጀርመን አደባባይ
#ዋና_መንገድ ላይ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን
🌻በፈጣን የግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ
ግንባታቸው 50% የደረሱ
የመጀመሪያ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 8000 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።
G+12 Apartment
በወለል 4
📍15% ቅድመ ክፍያ
የካሬ አማራጭ
▶ 125 ,128,130&136 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 150 &155ባለ ሶስት መኝታ
''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ 0929831836
0713128810
@Kidistgash
#Update
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ሦስት የምግብ አዘጋጆችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገለጸ
=======#=======
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አጋጥሞ የነበረውን የጤና እክል ምክንያቱ ምን እንደሆን ለማጣራት ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በዚህም ተማሪዎቹ በሚመገቡት ምግብ ላይ የመመረዝ አልያም የምግብ መበላሸት መኖሩን በሕክምና ከሚደረገው ምርመራ ጎን ለጎን፤ የክልሉ ፖሊስ ሦስት የምግብ አዘጋጆችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የሕክምናና የፖሊስ ምርመራው ሲጠናቀቅም ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም የክልሉ መንግሥት ገልጿል።
በጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ተፈታኝ ተማሪዎች የጤና እክል ገጥሟቸው፤ ትናንት ምሽት ከ1:30 ጀምሮ ወደ ጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፤ ተገቢው ሕክምና እየተደረገላቸው አብዛኞቹ አገግመው ወደ ፈተና ማዕከላቸው መመለሳቸው ተነግሯል፡፡
/channel/addismaleda
አልሸባብ በኬንያ የሽብር ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
=======#=======
የአልሸባብ የሽብር ቡድን ማክሰኞ ዕለት በኬንያ መወምበኒ በተባለ ሥፍራ በፈጸመው ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ እና ስድስት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው ባለ ደን ውስጥ ሆኖ በበርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ የመንግሥት ባለስልጣናት የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት ከመግለጽ ተቆጥበዋል ነው የተባለው፡፡
በአካባቢው የአሳ እርባታ መኖሩ ተከትሎ የሽብር ቡድኑ በተደጋጋሚ በሠራተኞች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዘርባቸው እና ማክሰኞ ጠዋት ከተፈጸመው ጥቃት በሥፍራው ያሉ ልዩ ኃይሎች እንዳዳኗቸው ዘኢስት አፍሪካ ዘግቧል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የአገር ውስጥ ካቢኔ ዋና ፀሀፊያቸው ሊሙ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን አሳ እርባታ በጎበኙ ከስድስት ቀናት በኋላ ነውም ተብሏል፡፡
የአልሸባብ አማፂ ቡድን በአካባቢው ጥቃት ሲያደርስ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የተነገረ ሲሆን፤ በትምህርት ቤቶች፣ በተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይም ተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚያደርስ ነው የተጠቆመው።
የአልሸባብ የሽብር ቡድን መሰረቱን በሶማሊያ አድርጎ በጎረቤት አገራት ጭምር የሽብር ጥቃት የሚያደርስ ሲሆን፤ ከወራት በፊትም በኢትዮጵያ ድንበር ተመሳሳይ ጥቃት ለመሰንዘር ሙከራ ማድረጉ ይታወሳል።
/channel/addismaleda
ወደ ላሊበላ እና ጎንደር ከተሞች የሚደረገው የአየር በረራ መቋረጡ ተገለጸ
=======#=======
ሐሙስ ሐምሌ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ወደ ላሊበላ የሚደረግ የአየር በረራ መቋረጡን የላሊበላ ኤርፖርት ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ምክንያት በዛሬው ዕለት ወደ ጎንደር የሚደረግ የአየር በረራ አለመኖሩን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።
ዛሬ ረፋድ ላይም በጎንደር አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ነው መረዳት የተቻለው።
የላሊበላ አየር ማረፊያ ሠራተኞች ወደ ላሊበላ በቀን ከሚደረጉ ኹለት በረራዎች የመጀመሪያው ማክሰኞ ሐምሌ 25/2015 ጠዋት ላይ መደረጉን ገልጸው፤ “ተጨማሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላሊበላ አየር ማረፊያ ሊገቡ ነው” የሚል ወሬ የሰሙ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ሥፍራው አቅንተው ጥበቃ ላይ ከነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ይህን ተከትሎም በኹለተኛው በረራ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ50 ላይ ላሊበላ ኤርፖርት ማረፍ የነበረበት የመንገደኞች አውሮፕላን ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር ሳያርፍ መመለሱን ገልጸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/3465