muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች

1
ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል

2
አንዳርጋቸው ፅጌ ከሀገር መውጣታቸውን ገለፁ። በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ሁኔታ ለሀገር አስተዋፅኦ ለማድረግ ለደህንነት ሁኔታው እንማይመች ለመሳይ መኮንን አንከር ሚዲያ ገልፀዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በመጨረሻ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ስለተከሰተው ግጭት አቋሙን አሳወቀ።

ከጊዜያዊ መንግስቱ በተሰጠው መግለጫ የሚከተለው ይገኝበታል 👇

መከላከያ ሰራዊቱ በመውሰድ ላይ ያለውን እርምጃ ‘የህወሓት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለበት’ በሚል በሬ ወለደ ጩኸት እየደረሰባቸው ላለው ሽንፈት የትግራይን ህዝብ ሰበብ ለማድረግ  ሲዳክሩ ይሰማሉ። የፌዴራል መንግስት በነዚህ ሀይሎች ላይ እየወሰዳቸው ላሉ እርምጃዎች የትግራይም ሆነ የሌላ ወገን የተለየ ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለን አናምንም። ይሁንና ፀረ ሰላም አቋማቸውን  ለማራመድ እስኳሁን ሲረጩት የነበረውን መርዝ  አልበቃ ብሎ የትግራይን ህዝብ በትልቁ በትንሹ------ቋሚ ስራ አድርገውት ይገኛሉ። ይህ ዘመቻ ፍፁም አሸናፊ ሊሆን የማይችል፣ የፅንፈኝነትና የፀረ ሰላም መንገድን ለማረም  አያግዝም ብቻ ሳይሆን በህዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባውን ሰላማዊ ግንኙነት በእጅጉ የሚጎዳ ነው።
አሁንም ቢሆን የትግራይ ህዝብ ሁሉም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያለው ቁርጠኛ አቋም እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማፍረስ የሚቋምጡ ፅንፈኛ ሀይሎችና የቅርብም የሩቅም አጋሮቻቸውን -----ላይ የሚያደርጉትን ዘመቻ ለማክሸፍ ከፌዴራል መንግስት እስካሁን ድረስ እያደረግነው የመጣነውን አበረታች ግንኙነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር አቋሙን ግልፅ ማድረግ ይፈልጋል።

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር
07 ነሐሰ 2015 ዓ/ም

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

... በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክር ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ ይኖርበታል በሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊፀና የሚችለው ከአጠቃላይ የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በስድስተኛው ዙር ተመርጠው በምክር ቤቱ መቀመጫ ከያዙት 427 ተወካዮች መካከል 285 የሚሆኑት የድጋፍ ድምፅ ከሰጡ ነው። ከተጠቀሱት 427 ተመራጮች ውስጥ 142 የምክር ቤት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ከሰጡ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ ሊሆን ይችላል።

በምክር ቤቱ ወንበር ካገኙ አጠቃላይ 427 አባላት ወስጥ 410 የሚሆኑት በብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 125 ያህሉ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት የተወዳደሩና የክልሉን ሕዝብ የሚወክሉ ናቸው። ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ አምስት የሕዝብ ተወካዮች ሲኖሩ፣ በኢዜማ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ ሌሎች አራት የሕዝብ ተወካዮች እንደሚገኙም ይታወቃል።

(ሪፖርተር ጋዜጣ August 6, 2023)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአብን መግለጫ
የሚከተለውን ብሏል
👇
"በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚፈፀም ማንነት ተኮር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተስተዋለ መሆኑን ፖርቲያችን ተገንዝቧል። በዚህ ረገድ አዋጁን ተገን በማድረግ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ዘፈቀዳዊ የማንነት ተኮር ጅምላ እስራቶች እየተፈፀሙ መሆኑን፣ በዚህ መልኩ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ ወዳልታወቁ ቦታዎች ተወስደው መታሰራቸውን እንዲሁም ዛቻዎች፣ የቤት ብርበራዎች፣ አካላዊ ጥቃቶች እና ማንነት ተኮር ዘለፋዎች እየተፈጸሙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከምንም በላይ ማንነት ተኮር ጅምላ እስር እና የመብት ጥሰት፤

ጽንፈኛ የፖለቲካ አተያይ ያላቸው የህግ አስፈጻሚ ግለሰቦች አዋጁን ተገን አድርገው አማራዊ ማንነትን ወንጀል የማድረግ አካሄድ በአስቸኳይ እርምት ካልተወሰደበት የሚያስከትለው ዳፋ ከባድ እንደሚሆን በጥብቅ ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ፖርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው ሲሆን በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን አጠቃላይ ስጋት በሚመለከት ክትትል እያደረገ ሲሆን ተጨባጭ መረጃዎችም እየደረሱት ይገኛሉ።

የደረሱንን ጥቆማዎች ተከትሎ ባደረግነው ማጣራትም የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ምክንያት ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተዳረጉና በተለይም ለማንነት ተኮር እስራት እና ለቤት ውስጥ ፍተሻዎች መጋለጣቸውን ማረጋገጥ ችለናል።"

ብሏል።

የመብት ጥሰቶችን ለሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ለአለማቀፍ ዲፕሎማቶች አሳውቃለሁ ሲል አክሏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በቀረበው አስቸኳይ የሰላም ጥሪ መሰረት ከባለድርሻ አካለት ጋር ንግግር መጀመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተስፋፉ ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱ አስቸኳይ የሰላም ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

ኮሚሽኑ ባቀረበው አስቸኳይ የሰላም ጥሪ መሰረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር፣ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ሰላም ሁኔታ ንግግር መጀመሩን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ነሃሴ 2/2015 ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለመንግሥትና መንግሥትን ለሚፋለሙ የኃይሎች ባቀረበው ጥሪ የአገሪቱን ሕልውና የሚፈታተን ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#የጥንቃቄ_መልእክት!
የዋትስአፕና ፌስቡክ መልዕክቶችን የሚሰርቀው መተግበሪያ

የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ እና ፌስቡክ መልዕክቶችን ከሚሰርቀው መተግብሪያ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተመክሯል። የሳይበር ጥናት ተቋም ሳይፊርማ እንዳስታወቀው አዲሱ የአንድሮይድ ስልኮችን በተለየ እያጠቃ ያለው መተግበሪያ “ሴፍቻት” ይሰኛል።

“ሴፍቻት” እንደ ሌሎች መተግበሪያዎች ሁሉ የተለያዩ መረጃዎችን ለመውሰድ ፈቃዳችን ይጠይቅና ምንተፋውን ይጀምራል። ያለው የአል አይን ዘገባ ይህ መተግበሪያ በአሁኑ ወቅት ከፕሌይ ስቶር ቢወገድም በጫኑት ሰዎች ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ቀጥሏል ይላል ሳይፍሪማ።
የዋትስአፕ እና ፌስቡክ መልዕክት ልውውጣችን፣ የስልክ ቁጥሮች፣ የስልክ ንግግር ቅጂ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እየመነተፈም መተግበሪያውን ለስለላ አላማ ለገዙት ኩባንያዎች ያቀብላል።

“ሴፍቻት” የስልክ እና ኮምፒውተር መለያ ቁጥር (አይፒ አድራሻዎች)፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ የስማርት ስልኩን ሙሉ መረጃ እና ሌሎች ሚስጢራዊ መረጃዎችንም ይሰርቃል ነው የተባለው።

የሳይፍሪማ ተመራማሪዎች ሰዎች መተግበሪያውን እንዲጭኑ የሚያስተዋውቀው እንዴት ነው የሚለውን ያልጠቆሙ ሲሆን ይሁን እንጂ ምናልባትም ከተለያዩ ሀገራት መንግስታት ጋር በቅርበት ሊሰራ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል
የህንዱ “ባሃሙት” የተባለ የመረጃ መንታፊ ቡድን ኩባንያ ይህን መተግበሪያ መረጃን ከሚመነትፍ ቫይረስ ጋር ለተጠቃሚዎች እንዳቀረበው የሳይፍሪማ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን መተግበሪያው ከ2017 ጀምሮም የበርካታ የአንድሮይድ ስልኮች ተጠቃሚዎችን መረጃ ሲመነትፍ መቆየቱን ነው የሚገልጸው።

ባለፈው አመትም የአንድሮይድ ስልኮችን የሚሰልሉ ሀሰተኛ የቪፒኤን መተግበሪያዎችን ይሄው “ባሃሙት” የተባለው የመረጃ መንታፊ ቡድን ማሰራጨቱን ዴይሊ ሜል አስታውሷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አምስት ሀገራት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጸጥታ መደፍረስ አሳስቦናል አሉ

ሀገራቱ በጋራ በሰጡት መግለጫ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ዘላቂ መረጋጋት እንዲመጣ ድጋፉን ይቀጥላል ብለዋል።
ሀገራቱ፣ ዩኬ፣ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ አሜሪካ እና ኒውዝላን ናቸው።
አልኤይን የዘገበው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሳምሪ ቡድን በመተማ በኩል ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ
=======#=======

አርብ ነሐሴ 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ሳምሪ በመባል የሚጠራው የታጠቀ ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ፣ ሽንፋ እና ሹመት መንዶካ በተባሉ ቦታዎች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት መፈጸሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ጥቃት የፈጸመው ረቡዕ ነሐሴ 03/2015 ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ በሱዳን ድንበር የነበሩ የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከአካባቢው አለመኖራቸውን አረጋግጠው ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ተኩስ ከፍተዋል ነው ያሉት።

ታጣቂ ቡድኑ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደምቹ አጋጣሚ ተጠቅሞ ነው ጥቃት የሰነዘረው የተባለ ሲሆን፤ በወቅቱ ድንበር ሲጠብቁ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቋራ እና መተማ አካባቢ ለኹለት ሰዓታት ያህል ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ነበር ተብሏል።

ሆኖም የመከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች የተኩስ ልውውጥ ማድረግ በጀመሩ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ፤ የሳምሪ ቡድን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች የእርስ በእርስ ውጊያቸውን በማቆም ተባብረው ቡድኑን ወደመጣበት መመለሳቸውና የተወሰኑ የሳምሪ ቡድን አባላትንም እጅ እንዲሰጡ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/34757
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች
1፤
በአማራ ክልል የግጭት ቀጠና ኾነው የሰነበቱት ባሕርዳር፣ ጎንደርና ሌሎች ከተሞች ትናንት በመጠኑ ወደመረጋጋት ተመልሰዋል። በባሕርዳር እና ጎንደር ትናንት የተኩስ ድምጽ ሳይሰማ እንደዋለ የተለያዩ ዜና ምንጮች የከተሞቹን ነዋሪዎች ጠቅሰው ዘግበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ፣ ዛሬ ወደ ኮምቦልቻ በረራ እጀምራለኹ ብሏል። ባሕርዳርና ጎንደርን ጨምሮ በስድስት የክልሉ ከተሞች ከትናንት ጀምሮ የሰዓት እላፊና ሌሎች ገደቦች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ።

2፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ለደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ማኅበሩ ለጋሾች ለሰብዓዊ ቀውሱ የሚውል የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲኹም የደም ልገሳ እንዲያደርጉለት ጭምር ተማጽኗል። በግጭቱ ሳቢያ በክልሉ ምን ያህል ሰብዓዊ ቀውስ እንደተፈጠረ ዝርዝር መረጃ እንዳላገኘ የተናገረው ማኅበሩ፣ በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ሠራተኞቹ የደኅንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ 👌
በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም የስራ ዘርፍ በየዕለቱ የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበትን የቴሌግራም ቻናል ዛሬውኑ ይቀላቀሉ /Join
👇👇👇👇👇
/channel/ethiohulumsra
/channel/ethiohulumsra
/channel/ethiohulumsra

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሕገወጡን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደማይቀበል ገለጸ !

ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት በትግራይ ክልል የተፈጸመውን ሕገወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደማይቀበል የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ መምህር ዜናዊ ሀሸተ ለተ.ሚ.ማ ገለጹ።

መጋቤ ሐዲስ መምህር ዜናዊ ሀሸተ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ ለሀገረ ስብከታችሁ ኤጲስ ቆጶስ ሾመንላችኋል መባላቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸው ሀገረ ስብከቱን ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲመሩት ከመደበልን ሊቀ ጳጳስ ውጪ የምንቀበለው አካል አይኖርም ነው ያሉት።

ሾምን ያሉት እና ተሿሚ ነን የሚሉት ግለሰቦች በአንድ ወንበር ሁለት አገልጋይ ስለማይኖር ተሾምን ያሉት አካላት በሀገረ ስብከታችን ቦታ እንደሌላቸው ሊያውቁ ይገባል ሲሉም አክለዋል።

በተመሳሳይም ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሰላም ሀይሌ አምዴ ጋር ባደረግነው የስልክ ቆይታ በትግራይ ክልል የተፈጸመው ሕገወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በጣም እንዳሳዘናቸው፤ የሀገረ ስብከቱ አመራርም ሆነ ምዕመናን ሊቀበሉት እንደማይችሉም ገልጸዋል።

የሰሜኑ ክፍል የክርስትናው ምንጭ ሆኖ ሳለ የፖለቲከኞች ተላላኪ ሆነው ማየታችን በጣም የሚያሳዝነን ጉዳይ ነው ፤ ሀገረ ስብከቱም ከምዕመኑ ጋር ስብሰባን አካሂዶ ይሔን ጉዳይ ሊቀበሉ እንደማይችሉ በመወሰን መግለጫ ለማውጣት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ነው ዋና ጸሐፊው የገለጹት።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !

👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:

➤ በ 500,000 ብር ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ

➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ - 4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት

➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ

👉 ከወለድ ነፃ

#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል

ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513

👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ" በማለት ፌደራል ፓሊሶች እንደወሰዷት ቤተሰቦቿ ለዘሐበሻ ገለፁ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር እና የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ መልካሙ ሹምዬ ኮከብ በገዛ ፍቃዳቸው ከሀላፊነት ለቀቁ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !

👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:

➤ በ 500,000 ብር ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ

➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ - 4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት

➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ

👉 ከወለድ ነፃ

#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል

ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513

👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መርምሮ ውሳኔ ያሳልፋል
=======#=======

ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አርብ ሐምሌ 28/2015 ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ "በአማራ ክልል ለስድስት ወራት እንዲሁም "እንዳስፈላጊነቱ" በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ይተገበራል" ሲል ባስተላለፈው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015" ላይ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ፤ ችግሩ ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ በቀረበው ጥያቄ መሠረት፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ መወሰኑ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አጀንዳ በተመለከተ የጉዳዩን አሳሳቢነት አይቶና ተወያይቶ፤ በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲጠራ የወሰነ ሲሆን፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በአጀንዳነት እንዲቀርብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ከእረፍት የተጠራው ምክር ቤት በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው፤ በግጭት ውስጥ በሰነበተው የአማራ ክልል ለስድስት ወራት በታወጀውና "እንዳስፈላጊነቱ" በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ይተገበራል በተባለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ፤ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በምክር ቤት አባልነታቸው በቁጥጥር ሥር ያለመዋል ሕጋዊ መብታቸው ሳይነሳ፤ በቁጥጥር ሥር በሚገኙት የምክር ቤቱ አባል ያለመከሰስ መብት ጉዳይ ላይ የውይይት ሀሳብ ቀርቦ ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

➣ በኢትዮጵያ ብቸኛው ለገነባው ህንፃ ዋስትና የሚሰጥ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ምርጫ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁኑኑ ይቀላቀሉ !

👉 በመዲናችን አዲስ አበባ በተንጣለለ እና ለኑሮ አመች በሆነ ስፍራ ላይ እየተገነባ ያለ:

➤ በ 500,000 ብር ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ይሁኑ

➣ ከ 80 ካሬ- 216 ካሬ
➣ የንግድ ሱቆች ከ ግራውንድ - 4ኛ ፎቅ
➣ የግንባታ ደረጃ ከ 15%-100% የደረሰ
➣ የባንክ ብድር የተመቻቸለት

➣ ያለቀ ባለ ግቢ ቪላ አለ

👉 ከወለድ ነፃ

#ለገነባነው ህንፃ ዋስትና መስጠታችን ልዩ ያደርገናል

ለበለጠ መረጃ እና ለቢሮ ቀጠሮ
👇
☎️ +251987003603
+251986687513

👉WhatsApp +251916716110
👉Telegram: @Girmagita
👉 Email: Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአዲስ አበባ፣ ሸገር፣ ቢሾፍቱ እና ወልቂጤ ከተሞች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ እስር መኖሩ ተገለጸ
=======#=======

እሁድ ነሐሴ 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተዋቀረው ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ወልቂጤ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ብሔርን መሰረት ያደረገ የጅምላ እስር መኖሩን አዲስ ማለዳ በየከተሞቹ ካሉ ነዋሪዎች ቅሬታ ደርሷታል።

በመዲናዋ ኮተቤ፣ ሳሪስ፣ ቄራ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ሃና ማሪያም እና የተለያዩ ቦታዎች ላይ የጅምላ እስር መኖሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት ሐምሌ 28/2015 አዲስ አበባ ውስጥ ወንድሜ በድንገት ታስሮብኛል ያሉ አንዲት ሴት፤ "ልክ ሲይዙት 'ይዘውናል ግን የት እንደሚወስዱን አላወቅንም' ብሎ ነው ቴክስት ያደረገው። በአካባቢው የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ስንሄድ እዚህ የሉም ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ነው ያሉት አሉን። እዚያ ስንሄድም እዚህ ያሉት ሐሙስ ዕለት የተያዙት ናቸው አሉን። ከብዙ ልፋት በኋላ ኮተቤ አካካቢ ወንድይራድ ትምህርት ቤት መኖራቸውን አወቅን። ትምህርት ቤት ዉስጥ ስለሆነ ያሉት በየቀኑ ምግብ የምናደርሰው እኛ ነን።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የታሰሩ ሰዎች አልፎ አልፎ መለቀቅ ከፈለጉ ብር እንደሚጠየቁም ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ በተዋቀረው ሸገር ከተማ አስተዳደር እንዲሁ ማንነትን መሰረት ያደረግ እስር በስፋት እየተፈጸመ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሥሜ እንዳይጠቀስ ያሉ ግለሰብ በተለይ በሰበታ ከተማ በርካታ የአማራ ተወላጆች ታስረዋል ብለዋል።


/channel/addismaleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈጻሚነት ጊዜ “ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት ላልበለጠ ጊዜ ብቻ” እንዲሆን እንዲያደርግ እና የተፈጻሚነት ወሰኑንም በአማራ ክልል ብቻ እንዲገድብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ። በአዋጁ ለአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ “የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖችን እና መዋቅሮችን መልሶ ለማቋቋም” የተሰጠውን ስልጣን ፓርላማው እንዲሰርዝም ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ እነዚህን ጥያቄዎች ያቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ባለ 22 ገጽ የምክረ ሃሳብ ሰነድ ላይ ነው። ኢሰመኮ ይህንን ምክረ ሃሳብ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 6፤ 2015 ይፋ ያደረገው፤ የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ከነገ በስቲያ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሄድ መገለጹን ተከትሎ ነው።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም፤ የሰብአዊ መብቶች ስጋቶች እና የማሻሻያ ምክረ ሃሳቦች ባካተተበት ሰነድ ላይ በቅድሚያ ያነሳው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተወካዮች ምክር ቤት ያለመቅረቡን ጉዳይ ነው። የሚኒ/ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው ባለፈው ሳምንት ሐምሌ 28/15 ቢሆንም፤ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለእረፍት በመበተናቸው አዋጁ እስካሁን ለፓርላማ አልቀረበም።

አዋጁ ሳይጸድቅ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ተፈጻሚ መሆኑ፤ “የመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ለበርካታ ቀናት ያለ ምክር ቤቱ እይታ እና ቁጥጥር” እንዲቆይ ምክንያት እንደሆነ ኢሰመኮ በምክረ ሃሳቡ ላይ አመልክቷል። የተወካዮች ም/ቤት በመጪው ሰኞ በሚያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው አዋጁን የሚያጸድቀው ከሆነ፤ ድንጋጌው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን አፈጻጸም የተመለከተ ሪፖርት መንግስት ለፓርላማ እንዲያቀርብ እንዲደረግ ኮሚሽኑ ጠይቋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!!🤩
#Dmc real estate‼️
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
በለቡ መብራት ሀይል በመገንባት ላይ ያሉ ከ755,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!

ሊያመልጠዎ የማይገባ  ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።

📍15% ቅድመ ክፍያ(በካሬ 90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(#5% -10% discount includes)
             
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)

▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ

▶ 132.እና 140.&144  ባለ ሁለት መኝታ
   
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ

''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨‍🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአውሮፓ ህብረት በአማራ ክልል ያለው የግጭት ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል ዛሬ መግለጫ አውጥቷል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እንግሊዝ ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ ጠየቀች


በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ምድር በተለይም በኃይል ከያዘቻቸው የትግራይ አካባቢዎች እንድታስወጣ መጠየቃቸው ተገልጿል።

አምባሳደር ዳረን ዌልች ከትግራይ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት በግልጽ እንዳስቀመጠው ኤርትራ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ በተለይም ከትግራይ እንድታስወጣ የጠየቁ ሲሆን፤ ይህም እንዲሆን እንግሊዝ በጽኑ ትፈልጋለች ብለዋል።

የፕሪቶርያው ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተም አገራቸው እየተከታተለችው እንደምትገኝም ተናግረዋል።

በተጨማሪም አምባሳደሩ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት የፕሪቶርያውን ስምምነት አፈጻጸሙን የሚከታተለውን የአፍሪካ ኅብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና የተልዕኮ ማስከበር ቡድንን ለማገዝ የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የብሪታኒያ መንግሥት ልዑክ በትግራይ ጉብኝት እያካሄደ እንደሚገኝና ከክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ፕሬዘዳንቱ የኤርትራ መንግሥት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ እንቅፋት በመሆኑ የብሪታኒያ መንግሥት ለፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል።

በተያያዘ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በአፍሪካ ቀንድ እና ቀይባህር አከባቢ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ሳራህ ሞንትጎምሪ እና ሉዑካቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአፋር ክልል የተከሰተው አንበጣ የማሽላ በቆሎ ሰብሎችን ማውደሙ ተገለጸ
=======#=======

በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ የበቀለውን ሰብል በማወደሙ፤ አርሶ አደሮችን ደጋሚ አርሰው እየዘሩ መሆኑ ተገልጿል።

በአባላ ከተማ አስተዳደር የእርኩዚ ቀበሌ አስተዳዳሪ አሊ አብዱሩፍ፤ “የአንበጣው መንጋው መነሻውን ከቀይ ባህር አካባቢ በማድረግ ከሰኔ 15/2015 ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ በአካባቢው ውድመት እያሰከተለ ነው፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የአንበጣ መንጋው በክልሉ የሚገኙ 15 ወረዳዎችን ማዳረሱን ገልጸው፤ እርኩዚ በተባለ ቀበሌ ከ45 ሄክታር በላይ የበቆሎ እና ማሽላ ሰብልን ሙሉ ለሙሉ በማውደሙ አርሶ አደሮች ኹለተኛ አርሰው እየዘሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንበጣው የተከሰተው የደረሱ ሰብሎች በሚሰበሰቡበት እና ለኹለተኛ ዙር የእርሻ ሥራ በሚከናወንበት ወቅት በመሆኑ ከማሽላ እና በቆሎ ሰብል በተጨማሪ ለእንስሳቶች የሚሆኑ እጽዋቶችን እያወደመ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/34754

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቀውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው::

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሴቭ ዘ ችልድረን በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ሰብዓዊ ረድዔት በጊዜያዊነት ለማቆም መገደዱ ተገለፀ

የሕፃናት አድን ድርጅት(ሴቭ ዘ ቺልድርን) የሚዲያ ኮሚኒኬሽንና አድቮኬሲ ክፍል ሃላፊ ሕይወት እምሻው በክልሉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ‹‹ ተባብሶ በቀጠለው ግጭት ›› ምክንያት ‹‹ የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦቱን በጊዜያዊነት ለማቋም መገደዱን ›› አሻም ዘግቧል

ድርጅቱ ‹‹ በክልሉ ለሚገኙ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ህፃናትና ሌሎች ዜጎች እርዳታ ለማድረስ ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖር ›› በሚል ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ያወጣውን ጋዜጣዊ መግለጫ አስመልክቶ ከአሻም ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ሃላፊዋ ‹‹ በክልሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ከ580 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ›› አመልክተዋል፡፡

‹‹ ለተፈናቃዮቹ የተለያዩ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን ›› ገለፁት ሕይወት ‹‹ አሁን ላይ ግን በክልሉ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ በመተማ፣ በሰሜን ወሎ ባሉ ፕግራሞች እንዲሁም ከሰቆጣ ቢሮው ተነስቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሲቀርቡ የነበሩ የእርዳታ አይነቶች ለጊዜው ለማቆም መገደዱን ›› ነግረውናል፡፡

‹‹ ይህም በተለይ ከባለፈው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የተፈናቃይ ቁጥር ላለበትና የእለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከባድ መሆኑን ›› ጠቁመዋል፡፡

ሀላፊዋ አክለውም ‹‹ በሁሉም ወገን ያሉ የግጭቱ ተሳታፊ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ በምንም ዓይነት መንገድ መቋረጥ ስለሌለበት ለዚህ መተባበር እንዲኖርባቸው ›› አመልክተው ‹‹ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ሰራተኞችንም ከአደጋ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው ›› ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አሻም

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ተገለጸ
=======#=======

ሐሙስ ነሐሴ 4 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን ድንበርን መዝጋቷን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጣለች።

በአማራ ክልል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው የሚጠሩ ኃይሎች በይፋ ወደ ግጭት ከገቡበት ከሐምሌ 23/2015 ጀምሮ፤ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባትም ሆነ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን መውጣት መከልከሉ ነው የተገለጸው።

በሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት ተክትሎ በርካታ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ  የሚገቡት በመተማ በኩል መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ “ከሱዳን ገላባት በተባለ ቦታ አድርገው ወደ መተማ ወረዳ የሚያስገባውና የሚያስወጣው ድንበር በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡” ብለዋል፡፡

ድንበሩ እንዲዘጋ የተደረገው በጎንደር እና አካባቢው በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል እየተደረገ ያለውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ፤ በስደተኞች ሥም ችግር ፈጣሪዎች እንዳይገቡና እንዳይወጡ እንዲሁም መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደው ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንዳይደናቀፍ ታሰቦ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡

ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊ፤ የሱዳን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ በመተማ ድንበር በኩል ከ60 ሺሕ በላይ ስደተኞች የሱዳንን ቀውስ ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ጠቁመው፤ ከሐምሌ 23/2015 ወዲህ ግን ድንበሩ መዘጋቱንና ስደተኞችም እየገቡ አለመሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=>addismaleda.com/archives/34742

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር  ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል በተለይም ከአንድ ሳምንት በፊት አንስቶ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡

በሱዳን በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ በሚል በመተማ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሱዳናዊያን ዜጎች ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በጎንደር እና በባህርዳር ባሉ ሆቴሎች የቆዩ ሱዳናዊያን በምግብ እጥረት፣ ደህንነት እና ትራንስፖርት ችግር ገጥሞናልም ብለዋል፡፡
አልኤይን

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ባህር ዳር ሟቾችን ስትቀብር ዋለች
ብሏል የጀርመን ድምፅ

በውጊያው የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ዛሬ በተለያየ ቦታ መፈጸሙን የባህር ዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል። ከሞቾቹ አብዛኛዎቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት ብቻ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ያሏቸው ታራሚዎች ሲወጡ ማየታቸውንም ገልጸዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

2 ዐበይት ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈጻሚ ጠቅላይ ዕዝ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ ደብረብርሃን፣ ደብረማርቆስና ሸዋ ሮቢት ከተሞች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ነሃሴ 17 ድረስ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል። በሰዓት እላፊ ገደቡ መሠረት ከድንገተኛ ሕክምና አገልግሎትና ከጸጥታ ተቋማት ባልደረቦችና ተሽከርካሪዎች ውጭ፣ የሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ታግዷል። ዕዙ፣ በክልሉ ከተሞች "የአደባባይ ሰልፍ"፣ "ስብሰባ"፣ "መሰል እንቅስቃሴዎችን" እና ከጸጥታ ኃይሎች ውጪ "ጦር መሳሪያ ይዞ መዘዋወርን" ጭምር ከልክሏል። በስድስቱ ከተሞች "የባጃጅና ሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ" ያገደው ዕዙ፣ ከነገ ጀምሮ መደበኛ የአውሮፕላን በረራ፣ ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ ይጀምራሉ ብሏል። 

2፤ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈጻሚ ጠቅላይ ዕዝ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ ደብረብርሃን፣ ደብረማርቆስና ሸዋ ሮቢት ከተሞችና አካባቢያቸው የመሸገው ታጣቂ ቡድን "ጦር መሣሪያውን እንዲያስረክብ" እና "እጁን እንዲሰጥ" የተሰጠውን አማራጭ ባለመጠቀሙ "ርምጃ ተወስዶበታል" ሲል ማምሻውን አስታውቋል። ስድስቱ ከተሞች ከ"ጽንፈኛው" ቡድን ስጋት ነጻ ኾነዋል ያለው ዕዙ፣ የቡድኑ ታጣቂዎች ባንዳንድ አካባቢዎች ወደ "ቅርስ ቦታዎች"ና "የእምነት ተቋማት" ለመግባት እየሞከሩ መኾኑን ገልጧል። በአዲስ አበባ ብቻ 14 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ዕዙ ጠቅሷል።

ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና ሌሎች አስቸኳይ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ምክር ቤቱ ለሰኞ ስብሰባ ጠራ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በብሔራዊ ምርጫቦርድና ሌሎች አስቸኳይ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ የምክር ቤቱ አባላት ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓም እንዲሰበሰቡ ጥሪ አስተላለፈ።

ምክር ቤቱ አስቸኳይ አዋጁ በሕገመንግስቱ ድንጋጌ መሠረት ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ድጋፍ ካገኘ ሊያጸድቀው ይችላል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ላይ ባስተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ፣ አዋጁ እንደሁኔታው በመላው አገሪቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን ያስተላለፈው ድንጋጌ፣ ምናልባት በምክርቤቱ አባላት ጠንከር ያለ የሕግ ክርክር ሊያስነሳ እንደሚችል ይጠበቃል።

ሌላው የመከራከሪያ ሃሳብ፣ አዋጁ ያለመከሰስ መብት ያላቸው ተመራጮች ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።
ሌላው ምክርቤቱ ወሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ የሚጠበቀው በህመም ምክንያት ከኃላፊነታቸው በለቀቁት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምትክ ስለሚሾም ኃላፊ ጉዳይ ይሆል ተብሎ ይጠበቃል።

ሰሞኑን በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ) መሰረት ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 መደንገጉ ይታወሳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 2 (ሀ) እና (ለ) መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪችንን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ቢደነገግም ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡

ሪፖተር

Читать полностью…
Subscribe to a channel