muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

ኢፈርት ከዚያ ሁሉ ትግልና መስዋዕትነት በኋላ ተመልሶ መጣ።
የኢትዮጵያ ነገር እንዲህ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች ዜናዎች

1፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምሥራቅ ጉራጌ ዞን የተሰኘ አዲስ የዞን መዋቅር ከነባሩ ጉራጌ ዞን ተነጥሎ እንዲዋቀር ዛሬ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። አኹን በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ስር የሚደራጁት ወረዳዎች፣ ከጉራጌ ዞን ተነጥለው አዲስ የዞን አስተዳደራዊ መዋቅር ለማቋቋም እንዲፈቀድላቸው ለረጅም ጊዜያት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ጉራጌ ዞን ራሱን የቻለ ክልል ኾኖ እንዲዋቀር በሙሉ ድምጽ ሲወስን፣ የ"ምሥራቅ ጉራጌ" ዞን መዋቅር ጥያቄ ሲያነሱ የነበሩት የተወሰኑ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ግን ያኔ ገና ባልተደራጀው "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ" ክልል ስር ለመዋቀር በተናጥል ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል። ምክር ቤቱ፣ የቀድሞዎቹ የጉራጌ ዞን ወረዳዎች ቀቤና እና ማረቆ ደሞ ልዩ ወረዳዎች ኾነው እንዲዋቀሩ ወስኖላቸዋል። በተመሳሳይ፣ በቀድሞው ደቡብ ክልል ስር ለረጅም ዓመታት ልዩ ወረዳ የነበረውን የም ልዩ ወረዳ ወደ ዞን መዋቅር ያሳደገ ሲኾን፣ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ስር የነበረው ጠምባሮ ወረዳ ደሞ ልዩ ወረዳ ኾኖ እንዲዋቀር ወስኗል። የልዩ ወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅሮች ቀጥታ ግንኙነታቸው ከክልል ምክር ቤቶች ጋር ነው።

2፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባዔ እንደሻው ጣሰውን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል። እንደሻው ቀደም ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነርና የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ምክትል ዳይሬክተር ኾነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ምክር ቤቱ በተመሳሳይ የቀድሞው ደቡብ ክልል አፈ ጉባዔ የነበሩትን ፋጤ ሰርመሎን አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧቸዋል። አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር ከፊል የክልሉ ካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ በዕጩነት አቅርበው አጸድቀዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ነው ተብሏል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ አዘጋጅቶ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በመሸጥ በከፍተኛ የማጭበረበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፦ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ አዘጋጅቶ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በመሸጥ በከፍተኛ የማጭበረበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው አድራሻው የማይታወቅ ሰለሞን ሙሉ ከውን በተባለ ግለሰብ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት በዚሁ መታወቂያ የንግድ ፍቃድ በማውጣት የማሽነሪዎች እና የመሣሪያዎች ኪራይና ሽያጭ የንግድ ዘርፍ ላይ ተመዝግቦ ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ ሳያደርግና የሸጠው እቃ ሳይኖር ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በ30 ቢሊዮን 152 ሚሊዮን 434 ሺህ 002 ብር ከ03 ሣንቲም በመሸጥ መሆኑ ታውቋል።

ግለሰቡ የማጭበርበር ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ለበርካታ ጊዜያት ተደብቆ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን አስታውቋል ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ኅብረተሰቡም ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ በአካል ቀርቦ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ተነስተው “በህግ እንዲጠየቁ” በሲዳማ ክልል ውሳኔ ተላለፈ

ላለፉት ሶስት ዓመታት ገደማ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በ“ብልሹ አሰራር” እና “አፈጻጸም ድክመት” ተገምግመው ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የሲዳማ ክልል ምንጮች ገለጹ። አቶ ጸጋዬ ከኃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ረቡዕ ነሐሴ 10፤ 2015 ከተደረገ ግምገማ በኋላ መሆኑን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

በሲዳማ ክልል ደረጃ ያሉ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም እየተገመገሙበት ያለው መድረክ መካሄድ የጀመረው፤ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ነሐሴ 7፤ 2015 ጀምሮ ነው። በዚህ መድረክ ላይ  የተሳተፉ አንድ ምንጭ፤ ከሀዋሳው ከንቲባ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ አመራሮች ላይ ግምገማ መደረጉን አመልክተዋል። ከእሁድ ጀምሮ የነበሩትን ግምገማዎች በአካል ተገኝተው የተሳተፉት አቶ ጸጋዬ፤ እርሳቸውን በሚመለከተው የትላንት ከሰዓቱ ግምገማ ግን አለመገኘታቸውን እኚሁ ምንጭ አክለዋል።

በትላንቱ ግምገማ ላይ አቶ ጸጋዬ  “ከፍተኛ ሙስና ውስጥ መግባታቸውን” የሚያመለክቱ፣ “በሰነዶች የተረጋገጡ” መረጃዎችን መቅረባቸውን በመድረኩ የተሳተፉ ሁለት የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ተናግረዋል። በዚሁ ግምገማ “ከፍተኛ ተመራጭ የነበረችው የሀዋሳ ከተማ ወደ ኋላ መሄዷ” መነሳቱን የጠቆሙት ምንጮች፤ የከተማዋ ከንቲባ “የአቅም ውስንነት ጭምር አለባቸው” መባሉን ጠቅሰዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11813/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደሚማሩበት ዩንቨርሲቲ መግባት አለመቻላቸው ተገለጸ
የኮሮና ቫይረስን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በታቀደላቸው ጊዜ ለመደበኛ ተማሪዎች ሳይሰጡ የቀሩ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ከተያዘው የነሐሴ ወር እስከ መጭው ሕዳር ወር እንዲጠናቀቁ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት፤ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን የጠሩ እና ማስተማር የጀመሩ ቢሆንም፤ በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ መግባት አለመቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ለአብነትም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ፣ ኹለተኛ እና ሦሰተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ነሐሴ 04 እና 05/2015 ተመዝግበው የኹለተኛ መንፈቅ ትምህርታቸውን ከነሐሴ 08/2015 ጀመሮ እንዲከታተሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎች ምዝገባ አካሂደው ትምህርት የጀመሩ ቢሆንም፤ ከአማራ ክልል ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን መግባት አልመቻላቸውን ዩንቨርሲቲው ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እምቤት በቀለ፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተዛነፈውን የትምህርት ካሌንደር የማስተካከያ ስትራቴጂ ለማካሄድ በተያዘው የክረምት ወር ተማሪዎችን ጠርተን ምዝገባችን አጠናቀን ትምህርት ጀምረናል ሲሉ ጠቀሰው፤ ሆኖም በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ከአማራ ክልል ይመጡ የነበሩ ተማሪዎች ሳይመጡ ቀርተዋል ብልዋል፡፡

በዚህም በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ከተረጋጋ እስከ አርብ ነሐሴ 12/2015 ደረስ ገብተው እንዲመዘገቡና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋልም ነው ያሉት።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ተማሪዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መምጣት ካልቻሉ ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል ሲሉ ተደምጠዋል።
addis maleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በምዕራብ ሸዋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላት 12 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ እና እልፈታ ወረዳዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ 12 ሰዎች መገደላቸውን አዲስ ማለዳ ከአካካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች።

የአገር መከላከያ ሠራዊት በዞኑ “ኦነግ ሸኔን አጠፋለሁ” በሚል በጀመረው ዘመቻ፤ ከነሐሴ 04/2015 ወዲህ 12 ሰዎችን መገደላቸውን እና አራት ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በወረዳው እሁድ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስፋት ሰፍረው እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ቆሪቸ ኮቲቻ እና በኬ ኦፉ በተባሉ ቀበሌዎች መንገድ ላይ ያገኙትን እና ወደ ነዋሪዎች ቤት በመግባት ግድያ መፈጸማቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የወረዳው ነዋሪ፤ "የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ በቆሪቸ ኮቲቻ ቀበሌ በአንድ መኖሪያ ቤት ከገቡ በኋላ ስምንት የቤተሰብ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት ስድስቱ ወዲያው ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድረገዋል።" ነው ያሉት።

"በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት እና “በኦነግ ሸኔ” ታጣቂዎች መካከል ምንም ዓይነት ውጊያ አልነበረም።" ያሉት ነዋሪው፤ "የጸጥታ አካላቱ ለምን ይህን እንዳደረጉ ግልጽ አይደለም" ብለዋል።

በዕለቱ በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሎች በዞኑ እልፈታ ወረዳ ስድስት ሰዎችን ገድለዋል የተባለ ሲሆን፤ ሟቾቹ የፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው አርሶ አደሮች መሆናቸው ተመላክቷል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ይህን አስመልክቶ ማክሰኞ ነሐሴ 09/2015 ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ዘግናኝ ግድያዎች እየተፈጸሙ ነው ብሏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊካሄድ ነው
⚫ የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም ለሳምንቱ መጨረሻ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቷል

በህዝበ ውሳኔ የተመሰረተው 12ኛው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ይፋዊ የምስረታ በዓሉን በሳምንቱ መጨረሻ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊያደርግ ነው። የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም በተመሳሳይ ቀናት አስቸኳይ ጉባኤ መጥራቱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በአርባ ምንጭ ከተማ የሚካሄደው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ምስረታ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኤደን ንጉሴ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከነገ በስቲያ አርብ ነሐሴ 12፤ 2015 በሚኖረው መርሃ ግብር፤ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤውን እንደሚያደርግ ኃላፊዋ አስረድተዋል።

በዚሁ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የአዲሱን ክልል ህገ መንግስቱን ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል። በማግስቱ ቅዳሜ ደግሞ 12ኛው የፌደሬሽኑ ክልል በይፋ የምስረታ ፕሮግራሙን እንደሚያካሄድ ኤደን ጠቁመዋል። የአዲሱ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የካቤኔ አባላትም በዚሁ ቀን ይሾማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዋ አክለዋል።  

በ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል ላይ “ተጋባዥ” እንግዶች እና የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሏል። ለዚሁ ስነ ስርዓት ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ የአርባ ምንጭ ከተማን የማጽዳት ክንውኖች ሲካሄዱ መዋላቸውን እና የ“እንኳን ደህና መጣችሁ” መልዕክት የያዙ ባነሮች ሲሰቀሉ መመልከታቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

* * ዝርዝሩን 👇 https://ethiopiainsider.com/2023/11803/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች መገደላቸው ተነገረ

በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ፣ ድብዳባ እና እስር እየተፈጸመ ስለመሆኑ ቢቢሲ ከእማኞች መስማቱን ዘግቧል።

በተመሳሳይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረሰ (ኦፌኮ) ፓርቲዎች ባወጡት መግለጫ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

ነዋሪዎች እንደሚሉት በዞኑ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተፈጽሟል ከተባሉ ግድያዎች መካከል አንዱ ጮቢ በተባለው ወረዳ የተፈጸመው የበርካታ ሰዎች ግድያ ይገኝበታል።

ይህ በጮቢ ወረዳ ነሐሴ 04/2015 ዓ.ም. በመከላከያ ሠራዊት አባላት በተፈጸም ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን በቦታው የነበሩት እና በጥይት ተመትተው በሕይወት የተረፉት አንድ የአይን እማኝ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዕለቱ ከቤተሰብ አባላት እና ከጎረቤት ጋር በቤት ውስጥ ቡና እየጠጡ ሳለ ድንገት አንድ ወታደር ወደ ቤት ገብቶ ተኩስ በመክፈት 6 ሰዎችን መግደሉን እና እርሳቸውን ጨምሮ ሁለት ሰው ማቁሰሉን ገልጸዋል።

ሕይወታቸው ያለፈው ስድስት ሰዎች እህታቸውን ጨምሮ ሁለቱ ሴቶች እንዲሁም ልጃቸውን ጨምሮ አራቱ ወንዶች መሆናቸውን የአይን እማኙ ተናግረዋል ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አንፆኪያ‼

ሰሜን ሸዋ ዞን የአንፅኪያ ገምዛ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ኮማንደር ደምሰው አነጋውረው በዛሬው እለት ከቀኑ 7:40 በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል።በወቅቱ ጥቃቱን ማን እንደፈፀመው እስካሁን አልታወቀም።
via Wasu

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከተበተኑ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላት መካከል፤ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን መቀላቀላቸውን የሰላም ሚኒስትሩ ገለጹ

በአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ማስገባት ስራ ከተጀመረ በኋላ 50 በመቶ የሚሆኑ የልዩ ኃይል አባላት “እንደተበተኑ” እና ከእነዚህ ውስጥ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን እንደተቀላቀሉ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ። በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት የተጀመረው፤ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ “ዘግናኝ የሚባል ጥቃት መክፈታቸውን” ተከትሎ እንደሆነም ገልጸዋል።

አቶ ብናልፍ ይህንን የተናገሩት፤ በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ትላንት ሰኞ ነሐሴ 8፤ 2015 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአ/አ ካፒታል ሆቴል በተደረገ ውይይት ላይ ነው። አቶ ብናልፍ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመሩት በዚህ ስብሰባ 16 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

በውይይቱ መጀመሪያ ላይ 30 ደቂቃ ገደማ ለሚጠጋ ጊዜ ማብራሪያ የሰጡት የሰላም ሚኒስትሩ፤ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ ጋር ውይይት ለማድረግ የታሰበው “ከመንግስት በተነሳ ሀሳብ” መሆኑን ለተወካዮቹ ተናግረዋል። አቶ ብናልፍ በዚሁ ማብራሪያቸው፤ መንግስት በአማራ ክልል ያጋጠመው ግጭት “ዝም ብሎ በድንገት የተፈጠረ” ነው የሚል እምነት እንደሌለው እና “በተለያዩ ጊዜ የሚነሱ እና እየተደመሩ የመጡ ችግሮች የፈጠሩት” እንደሆነ አስረድተዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
አቶ ዮሐንስ ቧያለው ባህርዳር ዛሬ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መያዙ ተሰምቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጠየቁ

የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል “ሁሉንም ኃይሎች” ያካተተ “ጊዜያዊ አስተዳደር” እንዲቋቋም ጠየቁ። አቶ ገዱ በአማራ ክልል ያለውን “ችግር በቅንነት ለመፍታት” ፖለቲካዊ ንግግር መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣውን “ለውጥ” ከመሩ ባለስልጣናት አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት፤ በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ከመጽደቁ በፊት ባስደመጡት አስተያየት ነው። የገዢው ብልጽግና ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ገዱ፤ ዛሬ በተካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙት፤ በአማራ ክልል ለተፈጠረው ችግር “በቅንነት” ሃሳባቸውን በማቅረብ “አስተዋጽኦ ለማበርከት” በማሰብ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአማራ ክልልን ለአምስት ዓመታት የመሩት አቶ ገዱ፤ በክልሉ በአሁኑ ወቅት ያለውን ችግር ለመፍታት መፍትሔው “የፖለቲካ ውይይት፤፡ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። “ይህን ችግር በቅንነት ለመፍታት ከተፈለገ መፍትሔው፤ እስካሁን በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሞከር ከርሞ ሀገርን ወደ ከፋ ጥፋት ያመራው ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውይይት ነው የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል አቶ ገዱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethiopiainsider.com/2023/11773/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#NewsAlert

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች "ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ግጭት እንዲያቆሙ" እና ችግሩን በውይይት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ዛሬ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኢሰመኮ፣ መንግሥት የጅምላ እስር ማካሄዱን እንዲያቆም፣ ኮሚሽኑና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ድርጅቶች ሲቪሎች በታጎሩባቸው ማዕከላት ክትትል እንዲያደርጉ እንዲፈቅድ፣ በዘፈቀደ ያሠራቸውን ሰዎች ባስቸኳይ እንዲፈታም ጠይቋል። አፍሪካ ኅብረት፣ ኢጋድና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖችን እንዲያደራድሩም ኢሰመኮ ጥሪ እድርጓል። በክልሉ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም እና ቡሬ እንዲኹም በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተሞች በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶችና የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች ሲቪሎች እንደተገደሉ ሪፖርቶች እንደደረሱት የጠቀሰው ኢሰመኮ፣ መንገዶችን የዘጉ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ሳይቀር እንደተገደሉ፣ ወህኒ ቤቶች ተሰብረው ታሳሪዎች እንዳመለጡ፣ የጦር መሳሪያዎች እንደተዘረፉ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እንደተገደሉና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የአማራ ብሄር ተወላጆች በጅምላ እንደታሠሩ መረዳቱንም ገልጧል። በክልሉ በመንግሥት ሃይሎችና በታጣቂዎች መካከል ውጊያው በትላልቅ ከተሞች ቢቆምም፣ በሌሎች የክልሉ በርካታ አካባቢዎች ግን አኹንም ድረስ መቀጠሉን ኢሰመኮ ጨምሮ አመልክቷል። [ዋዜማ]

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

18 ዓመት ፍርድ የተላለፈበት ወንጀለኛ ከማረሚያ ቤት ለኹለተኛ ጊዜ ሲያመልጥ እርምጃ ተወሰደበት
=======#=======

ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት 18 ዓመት ፍርደኛ የነበረው ተከሳሽ ዮሐንስ አበበ፤ ከማረሚያ ቤት ለኹለተኛ ጊዜ የማምለጥ ሙከራ ሲያደርግ በጸጥታ ሃይሎች እርምጃ እንደተወሰደበት ተገለጸ፡፡

በሸኮ ወረዳ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት 18 ዓመት ፍርድ የተፈረደበት ዮሐንስ አበበ፤ በ2010 ከቤንች ሸኮ ዞን ማረሚያ ተቋም አምልጦ ወደጫካ በመግባት ባለፉት አምስት ዓመታት የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈጽም መቆየቱ ተነግሯል፡፡

ግለሰቡ በወረዳው አይበራ ሳንቃ ቀበሌ ሕግ በማስከበር ላይ የነበሩ የልዩ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በመግደል የጦር መሳሪያ በመውሰድ፣ በግድያ፣ በዝርፊያና ንብረት በማውደም ተግባራትን ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን፤ ከማረሚያ ቤት ካመለጠ ከ5 ዓመታት በኋላ በባሳለፍነው ሳምንት ቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታውቆ ነበር።

ነገር ግን ግለሰቡ በድጋሚ ከማረሚያ ቤት ለማምለጥ ሲሞክር በጸጥታ ሃይሎች እርምጃ ተወስዶበት ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል።
/channel/addismaleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🌼ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼
👉🏽ለ ኢንቨሥትመንት ወይም ለመኖሪያ ምቹ በሆነው መሀል ከተማ ካሳንቺስ 80% የደረሠ ዘመናዊ አፖርትመንት
👉🏽4B+G+14
👉🏽ባለ ግቢ የመኖርያ አፓርትመንት
👉🏽ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉🏽በተለያዩ የካሬ አማራጮች
70m2 - 150m2 ካሬ ሜትር
👉🏽በ1 ዓመት ውስጥ የሚረከቡት
👉🏽ከ5 ሚልዮን ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ.🌻
ለበለጠ መረጃ
በ 0977191398 ይደውሉልን
Email =selamesayas@gmail.com
Telegram username=@selamssa
Viber & WhatsApp =0977191398

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አቶ ጥላሁን ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

ከዚህ ቀደም በነበራቸው የስራ ኃላፊነት የህዝብ አገልጋይ ሆነው የሰሩ ብቃት ያለው አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ መሆናቸውም በምክር ቤቱ ተብራርቷል።

በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ሳይበገሩ ኃላፊነታቸውን በብቃት ስለመወጣታቸውም ተጠቁሟል።

አቶ ጥላሁን ከበደ የህዝብን ድምጽ የሚያከብሩ፣በብዝሀነት የሚያምኑ ሁሉንም ህዝብ ያለ አድሎ ያገለገሉ እንደነበርም በምክር ቤቱ አባላት እውቅና ተሰጥቷቸዋልአቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ በዛሬ ውሎው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና አፈ ጉባኤ ሹመትን አጽድቋል፡፡

በዚህ መሰረትም አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ እንዳሻው ከቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ጋር የሕገ-መንግስት ርክክብ ማድረጋቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ፋጤ ስርሞሎን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ እና መነቴ ሙንዲኖን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

ምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳድሩን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል በምግብ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ ተገለጸ
=======#=======

አርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል የተከሰትውን ቀውስ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በምግብ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን አዲስ ማለዳ በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ባደረገችው ማጣራት አረጋግጣለች።

በክልሉ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት መንገድ መዘጋቱን ተከትሎ፤ ከአዲስ አበባና የተለያዩ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ማስገባት ባለመቻሉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉ ነው የተገለጸው።

ለአብነትም በክልሉ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደሴ፣ ደብረብረሃን እና ደብረማረቆስ ከተሞች ግጭት ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ሐምሌ እኩሌታ በፊት ጤፍ በኩንታል ከ8 እስክ 9 ሺሕ ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከ10 እስከ 11 ሺሕ ብር እየተሸጠ ይገኛል።

እንዲሁም ከ800 እስከ 900 መቶ ብር ሲሸጥ የነበረው አምስት ሊትር የምግብ ዘይት፤ በአሁኑ ወቅት ከ1 ሺሕ 200 እስከ 1 ሺሕ 300 ብር እየተሸጠ መሆኑን መረዳት ተችሏል።

ከተፈጠረው ክልላዊ ቀውስ በፊት በእነዚህ ከተሞች የዳቦ ዱቄት በኩንታል እስከ 750 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት ከአንድ ሺሕ እስከ 1 ሺሕ 200 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

በተለይ ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በክልሉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በመቋረጡ በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ተስተውሏል ነው የተባለው።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ=> addismaleda.com/archives/34879

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🌼ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼
👉🏽ለ ኢንቨሥትመንት ወይም ለመኖሪያ ምቹ በሆነው መሀል ከተማ ካሳንቺስ 80% የደረሠ ዘመናዊ አፖርትመንት
👉🏽4B+G+14
👉🏽ባለ ግቢ የመኖርያ አፓርትመንት
👉🏽ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉🏽በተለያዩ የካሬ አማራጮች
70m2 - 150m2 ካሬ ሜትር
👉🏽በ1 ዓመት ውስጥ የሚረከቡት
👉🏽ከ5 ሚልዮን ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ.🌻
ለበለጠ መረጃ
በ 0977191398 ይደውሉልን
Email =selamesayas@gmail.com
Telegram username=@selamssa
Viber & WhatsApp =0977191398

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🌼ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼
👉🏽ለ ኢንቨሥትመንት ወይም ለመኖሪያ ምቹ በሆነው መሀል ከተማ ካሳንቺስ 80% የደረሠ ዘመናዊ አፖርትመንት
👉🏽4B+G+14
👉🏽ባለ ግቢ የመኖርያ አፓርትመንት
👉🏽ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉🏽በተለያዩ የካሬ አማራጮች
70m2 - 150m2 ካሬ ሜትር
👉🏽በ1 ዓመት ውስጥ የሚረከቡት
👉🏽ከ5 ሚልዮን ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ.🌻
ለበለጠ መረጃ
በ 0977191398 ይደውሉልን
Email =selamesayas@gmail.com
Telegram username=@selamssa
Viber & WhatsApp =0977191398

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🌼ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼
👉🏽ለ ኢንቨሥትመንት ወይም ለመኖሪያ ምቹ በሆነው መሀል ከተማ ካሳንቺስ 80% የደረሠ ዘመናዊ አፖርትመንት
👉🏽4B+G+14
👉🏽ባለ ግቢ የመኖርያ አፓርትመንት
👉🏽ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉🏽በተለያዩ የካሬ አማራጮች
70m2 - 150m2 ካሬ ሜትር
👉🏽በ1 ዓመት ውስጥ የሚረከቡት
👉🏽ከ5 ሚልዮን ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ.🌻
ለበለጠ መረጃ
በ 0977191398 ይደውሉልን
Email =selamesayas@gmail.com
Telegram username=@selamssa
Viber & WhatsApp =0977191398

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች

1፤
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ኤም-ፔሳ የተሰኘውን የሞባይል ገንዘብ መገበያያ አገልግሎት ዛሬ በይፋ ጀምሯል። ኩባንያው የኤም-ፔሳ አገልግሎት መተግበሪያውን በአምስት ቋንቋዎች እንዳዘጋጀ ገልጧል። ኩባንያው ኤም-ፔሳን እንዲጀምር ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘው ከሦስት ወራት በፊት ነበር። የኤም-ፔሳ አገልግሎት፣ የኩባንያው ደንበኞች ገንዘብ ከሞባይል ወደ ሞባይል እንዲላላኩ፣ በሞባይል ግብይት እንዲያካሂዱ፣ ከውጭ አገር በሞባይል ገንዘብ እንዲቀበሉ፣ ገንዘብ ከሞባይል ወደ ባንክ ሒሳባቸው እንዲያስገቡና ከባንክ ወደ ሞባይል ገንዘብ እንዲልኩ ያስችላቸዋል። ደንበኞች በኤም-ፔሳቸው ማስቀመጥና ባንድ ቀን መገበያየት የሚችሉት የብር ጣሪያ ስንት እንደኾነ ኩባንያው አልጠቀሰም።

2፤
ከደቡብ ክልል በሕዝበ ውሳኔ የተገነጠለው አዲሱ "ደቡብ ኢትዮጵያ" ክልል ከነገ ወዲያ ዓርብ በአርባ ምንጭ ከተማ በይፋ ይመሠረታል። በመፍረስ ላይ ያለው የነባሩ ደቡብ ክልል ምክር ቤት በዕለቱ የመጨረሻውን ጉባኤ ያካሂዳል። ይህንኑ ተከትሎ የ"ደቡብ ኢትዮጵያ" ክልል መስራች ዞኖችንና ልዩ ወረዳዎችን በነባሩ ደቡብ ክልል ወክለው የቆዩ ተወካዮች በዕለቱ የአዲሱን ክልል ምክር ቤት ይመሠርታሉ፤ ምክር ቤቱም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ይሾማል። የጋሞ ዞን ማዕከል አርባ ምንጭ ለክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ ስትኾን፣ የወላይታዋ ሶዶ ደሞ የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መቀመጫ ትኾናለች። የክልሉ አስፈጻሚ ቢሮዎች መቀመጫቸው በስድስቱ ዞኖችና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ማዕከሎች ይከፋፈላል።
ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

«400 የEBC ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ይህን ስናጋልጥ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው"
#FastMereja

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በተቋሙ ሰራተኞች ላይ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ሰነድ ማረጋገጥ የ400 ሰራተኞች ሰነድ ሀስተኛ በመሆኑ የትምህርትና ስልጠና አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ቢያሳውቅም አመራሮቹ በጥቅም በመተሳሰር የህግ ተጠያቂነት እንዳይኖር መረጃ ስለመስወራቸው ሁለት ግለሰቦች ለፌዴራል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥቆማ ማቅረባቸውን ፋስት መረጃ የደረሰው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ምክንያት የድርጅቱ አመራሮች በጥቆማ አቅራቢዎች ላይ ከስራ ለማሰናበት ዛቻ እና ማስፈራራት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅስው የህግ ከለላ እንዲሰጣቸው በቀን 02/12/2015 ዓ.ም በፌዴራል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኩል የህግ ከለላ እንዲሰጣቸው ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ አቃቢ ህግን ጠይቀዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ወላሂ እናት ልጁ በትራፊክ ፖሊስ እንዲህ ተቀጥቅጦ  ስታለቅስ አይቼ ማለፍ አልቻልኩም😔😔😔

ለምን ትርፍ ሰው ጭነሀል በማለት የሰው ህይወት እስከማጥፋት መድረስ ማለት በጣም ከባድ ነው እሄ ለከተማችን ገፅታም ጥሩ አይደለም።
ድንገት ዛሬ ማታ 1:00 አንድ ሰዓት አከባቢ ኑር መስጂድ አደባባዩ ጎን ላይ የሆነ ሱቅ ቁጭ ባልንበት ድንገት የሰዎችን ጩሀት ሰማን። ከዛን እኛ የመኪና አደጋ መስሎን እየሮጥን አደባባዩ ጋር ስንጠጋ መሬት ላይ ተመቶ የወደቀ ሰው አየን። ሰዎች ዙሪያውን ከቦ ልጁ ሞተ እያሉ ያለቅሳሉ። እኛ እንደምንም ልጁን አንስተን በባጃጅ ሆስፒታል ወሰድነው ሀኪሞችም ተሯሩጠው ኦክስጅን ደቀኑለት። ግን አልሀምዱሊላህ ልጁ ከሞት ድኗል🙏🙏🙏

ትርፍ ከጫነ በህጉ መሰረት መቅጣት እንጂ የሰውን ልጅ ዝም ብሎ መደብደብ ህግን መጣስ ነው።
የሚመለከተው አካል እሄንን ድርጊት የፈፀመውን ትራፊክ ለህግ ማቅረብ አለበት!!
#INBOX
ከዘሐበሻ ቤተሰብ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!!🤩
#Dmc real estate‼️
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!!
በለቡ መብራት ሀይል በመገንባት ላይ ያሉ ከ755,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!

ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።

📍15% ቅድመ ክፍያ(በካሬ 90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(#5% -10% discount includes)

▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)

▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ

▶ 132.እና 140.&144 ባለ ሁለት መኝታ

▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ

''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨‍🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በወልቂጤ እየተደረገ ያለውን ማንነት ተኮር እስር እንዲቆም የአገር ሽማግሌዎች የመንግሥት አመራሮችን ጠየቁ
=======#=======

ማክሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነቸው ወልቂጤ ከቀናት በፊት የተጀመረው ማንነት ተኮር እስር እና አፈና እንዲቆም የከተማው የአገር ሽማግሌዎች እና የወጣት ተወካዮች የመንግሥት አመራሮችን መጠየቃቸውን አዲስ ማለዳ ከአገር ሽማግሌዎችና ከወጣት ተወካዮች ሰምታለች።

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአገር ሽማግሌ ትናንት ነሐሴ 08/2015 ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈ ቤት በማቅናት አሁን ላይ በከተማው እየተደረገ ያለው ማንነት ተኮር የጅምላ እስር እንዲቆም መጠየቃቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በከተማዋ ረዥም ዘመን ከኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ጋር ተጋብተው እና ተዋልደው እንደኖሩ በመግለጽ፤ በዚህ ሰዓት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየተደረገ ያለው እስር እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ለከንቲባው ማስረዳታቸውን አውስተዋል፡፡

ከአገር ሽማግሌዎቹ እና ከወጣቶቹ አቤቱታ የቀረበላቸው የከተማዋ ከንቲባ “ሁከት አቀናጅታችኋል” ተብለው የተወሰኑ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እንጂ በከተማው ማንነት ተኮር የጅምላ እስር መኖሩን መረጃው እንደሌላቸው ገልጸውልናል ነው ያሉት።
አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሐና ተረፈ ትባላለች፣ ነዋሪነቷ ሐዋሳ ከተማ ነበር፣ ሐና በሀዋሳ ሱቅ ከፍታ ከኢትዮጵያ ውጪ በመሄድ የተለያዩ የህፃናት እና የወንዶች ልብሶችን በማምጣት ትሸጣለች አሪፍ ኑሮ ነበር የምትኖረው።

በስራ ላይ እያለች አንድ ግለሰብ ባለትዳር እና የልጆች አባት ሲሆን በከተማውም ታዋቂ የነበረ ነው "የእኔ ካልሆንሽ ካላገባውሽ አጠፋሻለሁ፣ አንቺ ከእኔ ውጪ የማንም መሆን አትችይም" እያለ ይዝትባት እንደነበር ለፋስት መረጃ ገልፃለች። "እኔ ነገሩ እውነት አልመሰለኝም ነበር ነገሩ እየከረረ ሲመጣ ግን ለአቃቢ ህግ አማከርኩ" ትላለች፣ አቃቢ ህጉ "አሁን ብትከሺው በዋስትና ይፈታል ከዛ ሲወጣ ደግሞ ይገልሻል" ሲለኝ ዝም አልኩ ብላለች ሐና

አንድ ቀን ህዳር 3/2013 ዓም ማታ ወደ ሱቅ በመምጣት ጓደኛዋና ሱቅ ውስጥ የምትሰራ ሰራተኛዋ ባሉበት በጥይት ተኩሶ በመምታት እራሱንም ተኩሶ ይገድላል።

እሷ ከጥይት ናዳ ብትተርፍም እሱ ግን እራሱን አጥፍቷል

አሪፍ ስራ እየሰራች ጥሩ ኑሮ እየኖረች የነበረችው ሐና ወገቧ ላይ የመታት ጥይት እግሯ እንዳይንቀሳቀስ አደረጋት፣ ህክምና ለማድረግ ቤቷን ሸጣ የነበራትን ሀብት ሸጣ ውጪ ሀገፍ ባንኮክ በመሄድ ህክምና እየተከታተለች በነበረችበት ወቅት ሰርጀሪ አድርጊ ተብላ ገንዘብ በመጨረሷ ህክምናውን አቋርጣ ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች።

ሐና ከቀድሞ ትዳሯ ከተለያየች 13 አመት ሲሆን የ14 አመት ልጅ አላት፣ ልጇ ትምህርት ካቋረጠች ሶስት አመት ሆኗታል፣ ባቅም ማነስ ህክምና መከታተለች አልቻለችም አሁን አዲስ አበባ ነው የምትገኘው በዊልቸር ነች ድጋፍ ትፈልጋለች

«እስካሁን በራሴ ስታገል ነበር አሁን ስላልቻልኩ ነው ወደ ሚዲያ የወጣውት ከችግሬ አይበልጥም እኔ ህክምና አግኝቼ ልጄም ወደ ትምህርቷ እንድትመለስ የኢትዮጵያን ህዝብ እጠይቃለሁ"ብላለች

እሷን ለማግኘት
☎ 0900031507

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአንድ ሳምንት በፊት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ። አዋጁን 16 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት አስራ ሁለት አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ነሐሴ 8፣2015

በአማራ ክልል የታወጀውና ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ የሚቆይ እንዲሆን ተጠየቀ፡፡

ጥያቄውን ያቀረበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ነው፡፡

ኮሚሽኑ በአዋጁ ላይ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ እና ዝርዝር ምክረ ሀሳቦችን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ልኬያለሁ ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለይም በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎችን እንዲሁም ለመንግስት የተሰጠውን የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቶበታል፡፡

የአዋጁን ከባቢያዊ እና የጊዜ ተፈፃሚነት ወሰን በተመለከተና የህዝብ ተወካዮች እንዲሁም ዳኞችን ያለ ምክር ቤቱ ውሳኔ ያለ መከሰስ ልዩ መብትን ጨምሮ ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚጠይቅ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡

በዚሁ ሰነድም በክልሉ ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቀት ተወግዶ መደበኛ እንቅስቃሴው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን መንግስት በይፋ መግለፁን ጠቅሶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሳምንታት ቢበዛ ከ1 ወር ጊዜ የበለጠ እንዳይሆን ጠይቋል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ እየገቡ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
=======#=======

ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡

የወረዳው ነዋሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ወረዳው የገጠር ቀበሌዎች እየገቡ መሆናቸውን ገልጸው፤ ታጣቂዎቹ ከሰሞኑ በስፋት መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ስጋት እየፈጠረባቸው መሆኑንም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በወረዳው በተደጋጋሚ ባደረሱት ጥቃት በርካታ ዜጎች መገደላቸውንም ነዋሪዎቹ አስታውሰዋል።

በተጨማሪም በወረዳው የገጠር ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ታጣቂዎችን ሸሽት ወደ ወረዳዋ ከተማ ጉንዶ መስቀልና ወደሌሎች አካባቢዎች መሰደዳቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በወረዳው የገጠር ቀበሌ በሆኑ ባቡ ድሬ፣ ራቾና ድሬ መንቃታ አካባቢዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ነው የተነገረው።

ኦነግ ሸኔ ከኹለት ዓመት በፊት ጀምሮ ወደ ወረዳው በመግባት ዜጎችን በማገት ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ግድያና ማፈናቀል እያደረሰ ነው ተብሏል።

በተለይም የደራ ወረዳን ከሰላሌ ጋር የሚያገናኘውን የጀማን ድልድይ በመቆጣጠሩ የወረዳዋ ነዋሪዎች በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ መገደዳቸው ተገልጿል፡፡

የደራ ወረዳ ከአዲስ አበባ 2 መቶ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል።
/channel/addismaleda

Читать полностью…
Subscribe to a channel