መቀሌ ትናንት የወደድኳት ልጅ ከሌሎች ጋር ስትጨፍር አላስችልህ ብሎኝ ነው በማለት በአሸንዳ በዓል ማግስት ሲጨፍሩ በነበሩ ሰዎች ላይ ቦንብ በመወርወር አራት ሰዎችን ገድሎ ከሀያ በላይ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ያደረሰው ይህ ሰው ተይዟል
Читать полностью…የሴቶች ማራቶን ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል
ጎቲቶም ገብረስላሴ ፣ ፀሀይ ገመቹ ፣ አማኔ በሪሶ እና ያለምዘርፍ የኋላው ኢትዮጵያን ወክለው በመወዳደር ላይ ናቸው።
እስካሁን 1:30 ያህል የሮጡ ሲሆን ሁሉም አትሌቶቻችን ከመሪው ቡደን ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ለውጥ ተብዬው ከመጣ ስንተኛው ፕሬዝዳንት ነው በአማራ ክልል?
ገዱ ነበረ። ተነሳና አምባቸው ሆነ። ተገደለና ተመስገን ጥሩነህ መጣ። ከዚያ አገኘሁ ተሻገር ተሾመ። ተሻረ እና ይልቃል ከፋለ መጣ። ይልቃል ስደት አአ ሆኖ በላዩ ላይ አቶ አረጋ ከበደ መጥቷል። ከለውጡ በኋላ በኦሮሚያ ከለማ መገርሳ በኋላ ሽመልስ አብዲሳ ነው ያለው።
ሽመልስ ሳይነሳ ስንት ፕሬዘዳንት ተቀያየረ በአማራ ክልል?
መቐለ ውስጥ በአንድ መዝናኛ ስፍራ በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት አራት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 20 ቆሰሉ። ትናንት ሌሊት 8 ሰዓት ላይ በከተማዋ ሮማናት አደባባይ አካባቢ በሚገኝ አንድ የምሽት መዝናኛ ቤት ውስጥ የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት «በቀድሞ ታጋይ» የተፈፀመ መሆኑን ፖሊስ ያረጋገጠ ሲሆን ተጠርጣሪው ግን እስካሁን እንዳልተያዘ የመቐለ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በጥቃቱ ከቆሰሉት 20 ሰለባዎች መካከል አምስቱ በፅኑ መጎዳታቸውን ገልጿል።
የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ከአሸንዳ በዓል ጋር በተያያዘ በከተማዋ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል። ሆኖም በበዓሉ መዝጊያ ቀን ትናንት ግን በከተማዋ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ አሳዛኙ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል። ጥቃቱን የፈፀመው ግለሰብ ማንነቱ መለየቱን የገለፁት ኮማንደር ወልዳይ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና «በቁጥጥር ስር ለማዋልም» ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተናግረዋል።
ኤፍዋን በተባለ የእጅ ቦንብ ጥቃቱ መፈፀሙን ፖሊስ አረግጧል። የጥቃቱ አላማም «የግለሰቦች ጠብ» መሆኑ ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ገልፀዋል። መቐለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል 20 በቦንብ ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ መቀበሉን የሆስፒታሉ የድንገተኛ ሕክምና ክፍል ሠራተኛ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አምስቱ የጥቃቱ ሰለባዎችም ተገቢው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ማመልከታቸውን የመቐለው ዘጋቢያችን ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ በላከው ዜና ጠቅሷል።
DW Amharic
🌼🌼 ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼 🌼
⭐️ ከመገናኛ ወደ ኢንግሊዝ ኢንባሲ መንገድ ላይ 75% ግንባታው የተጠናቀቀ አፓርትመንት ይዘን ቀርበናል
👉በ30% ቅድሚያ ክፍያ ብቻ ቤትዎን ይግዙ
👉ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉ካርታ የተዘጋጀላቸው
👉በ6 ዙር ረጋ ብለው የሚከፍሉበት አማራጭ
👉በቂ የመኪና ማቆሚያ
👉ጂምናዚየም
👉በ4 ቱም ማዕዘን ከተማውን የሚያስቃኝ ሰፊ ሰገነት
👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
👉አስተማማኝ ጀነሬተር
👉የከርሰ ምድር ውሀ
📞ይደውሉ ከጠበቁት በላይ ሆኖ ያገኙታል
0964784722
በሸዋሮቢት ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ 17 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን ከተማ አሥተዳደሩ ገለጸ።
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሸዋሮቢት ከተማ ነሃሴ 17 ከሌሊቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ የእሳት አደጋው መድረሱን የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያዉ ኃላፊ ተክለየስ በለጠ በእሳት አደጋው ከ30 በላይ የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ለአሚኮ ገልጸዋል።
የደረሰው አደጋ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን አቶ ተክለየስ አብራርተዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኑርሁሴን ኢብራሂም የአደጋዉ ምክንያት እየተጣራ ነዉ ብለዋል፡፡
በአደጋዉ ተጎጅ የሆኑ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል፡፡
በሰዉ ሕይወትና አካል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አቶ ተክለየስ ገልፀዋል፡፡
በአደጋዉ ተጎጅ የሆኑ ወገኖችን ለመደገፍ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ዘጋቢ፦ ኤልያስ ፈጠነ
ለአትሌቶች የሚደረግ ምርጫ ወቅታዊ ብቃትን፣ ውጤት እና ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ ነው ፡- ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
*********************************
ኢትዮጵያን ለመወከል የሚደረገው የአትሌቶች ምርጫ የአትሌቶችን ወቅታዊ ብቃት፣ ውጤት እና በዋናነት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አስታወቀች።
በቡዳፔስቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 5000ሜ ማጣሪያ አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ከውድድር መቀነሱን ተከትሎ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ቅሬታ መቅረቡ ተገልጿል።
ይህን አስመልክቶ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጠችው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ውሳኔው ሲወሰን የአትሌቶችን ብቃት፣ ውጤት እና በዋናነት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ተናግራለች።
ከዚህ በፊት ውጤታማ ያደረጉ አሰራሮች አሁንም ተግባራዊ መደረጋቸውን እንደሚቀጥል የጠቀሰችው ፕሬዝዳንቷ፤ ከአትሌት ጥላሁን ኃይሌ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጉዳይም ውጤትን እና ወቅታዊ ብቃትን መሰረት አድርጎ የተወሰነ መሆኑን ተናግራለች።
የወንዶች 5000ሜ ማጣሪያ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች በተመለከተ የተወሰነው ውሳኔ ከአሰልጣኞች፣ ከአመራሮች እና ከስራ አስፈፃሚው የተውጣጣ ኮሚቴ የወሰነው ጉዳይ መሆኑንም ነው የገለፀችው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብዙ ታላላቅ ባለሙያዎች የሚገኙበት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሰዎችን ማውጣት የቻለ ተቋም ነው ያለችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ትክክለኛ ባልሆኑ መረጃዎች በተቋሙ ላይ የሚቀርቡ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው አስታውቃለች።
በይስሃቅ ታሪኩ
የዋግነሩ አዛዥ የቨግኒ ፕሪጎዢን ህይወቱ ሳያልፍ እንዳልቀረ ተገለጸ
የሩሲያው ቅጥረኛ ወታደራዊ ቡድን አዛዥ የቨግኒ ፕሪጎዥን ይጓዙበት የነበር አውሮፕላን ተከስክሷል የተባለ ሲሆን የአዛዡ ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ አርቲ ዘግቧል።
አዛዡ ከሌሎች መንገደኞች ጋር በመሆን በግል አውሮፕላን እየተጓዙ እያለ በተፈጠረ አደጋ የሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል።
ፕሪጎዢን ባሳለፍነው ሀምሌ በሩሲያ ጦር ላይ አምጸው የሀገር ክህደት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ነበር።
በኋላም ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በተደረገ ድርድር ክሱ ውድቅ ሲደረግ አዛዡም ወደ ቤላሩስ መኮብላቸው ይታወሳል።
በደራ ወረዳ 12 ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታግተው መወሰዳቸው ተነገረ
=======#=======
ረቡዕ ነሐሴ 17 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ 12 ያህል ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው ትናንት ነሐሴ 16/2015 ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የተባለ ሲሆን፤ ከታጋቾች አብዛኞቹ በአደአ መልኬ ቀበሌ በመልኬ ማርያም ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ሲፈፅሙ ቆይተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የነበሩ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
እገታው የተፈጸመባቸው ሰዎች ካህናት እንዲሁም የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ታጣቂዎቹ ያገቷቸውን ሰዎች በወረዳው በሚገኘው ባቡ ድሬ ቀበሌ እንደወሰዷቸውም ገልጸዋል።
ባለፈው አርብ ነሐሴ 12/2015 ኹለት የኦሮሞ ተወላጆች ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች ሬማ በምትባል ከተማ በመገደላቸው፤ የትናንቱ እገታ የዚያ አጻፋ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
በአካባቢው እየሆነ ያለው ሰዎችን በማንነታቸው ምክንያት የመግደል እና የማገት ተግባር የቂም እና የበቀል አዝማሚያ የሚታይበት መሆኑን በመግለጽም፤ “ይህም ለዘመናት ተጋብቶ እና ተዋልዶ በአብሮነት የኖረን ሕዝብ የሚያቃቃር ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ቦታው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ እንደመሆኑ ቀደም ሲል የኹለቱም ብሔር ተወላጆች ገበያ በጋራ ይገበያዩ እንደነበር የጠቀሱት ነዋሪዎቹ፤ በዚህ ወቅት ግን ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልልም ሆነ ከአማራ ወደ ኦሮሚያ ክልል ሄዶ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ነው የገለጹት።
በምስራቅ ጉራጌ ዞን 14 ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ
በቅርቡ በተዋቅረው ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ኃይል 14 የአካባቢው ነዋሪዎችን አግቶ በመውሰድ መግደሉን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ነሐሴ 13/2015 በኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በሚገኙ ዱግዳ፣ መቂ እና ጢያ ትክል ድንጋይ ተብለው በሚጠሩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ቦታዎች ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ሸኔ ‘ለመንግሥት አካላት መረጃ ትሰጣላችሁ’ በሚል 16 ሰዎችን በምሽት አግተው ከወሰዱ በኋላ፤ ኹለቱ ድብደባ ቢፈጸምባቸውም ‘ነጻ ናችሁ’ በሚል ሲለቀቁ፣ ቀሪዎቹ ተገድለዋል” ነው ያሉት።
“ከኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማፈናቀል መሬቱን የራሳቸው ለማድረግ ነው ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት፡፡”
ያሉት አንድ ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጽሙት ድብደባና ዘረፋ በኦሮሚያ ክልል ወሰን አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው እየተፈናቀሉ ነው ብለዋል።
በተለይም በኹለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ከሚኖረው ሕዝብ የክስታኔ ጉራጌ ብሔር ተወላጆች ዋነኛ የጥቃቱ ሰለባ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሶዶ ወረዳ በሚገቡበት ቦታ የሚገኙ በመሆናቸው የመጀመሪያዎቹ ተጠቂ መሆናቸው ተመላክቷል።
ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ቤት ምሽት በመግባት “ገንዘብ እና የጦር መሳሪያ አምጡ፣ ካላመጣችሁ ትገደላላችሁ፡፡” እያሉ እያሰቃዩ ነውም ተብሏል።
አዲስ ማለዳ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 16፤ 2015 በዋናው ቅጥር ግቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር ስር ያሉ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ የተዘጋጀው አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። የዚህን አዋጅ መውጣት ተከትሎም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ያስቻለው ደንብ፤ ከሶስት ሳምንት በፊት ሐምሌ 28፤ 2015 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በዛሬው መግለጫቸው፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]
🌼🌼 ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼 🌼
⭐️ ከመገናኛ ወደ ኢንግሊዝ ኢንባሲ መንገድ ላይ 75% ግንባታው የተጠናቀቀ አፓርትመንት ይዘን ቀርበናል
👉በ30% ቅድሚያ ክፍያ ብቻ ቤትዎን ይግዙ
👉ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉ካርታ የተዘጋጀላቸው
👉በ6 ዙር ረጋ ብለው የሚከፍሉበት አማራጭ
👉በቂ የመኪና ማቆሚያ
👉ጂምናዚየም
👉በ4 ቱም ማዕዘን ከተማውን የሚያስቃኝ ሰፊ ሰገነት
👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
👉አስተማማኝ ጀነሬተር
👉የከርሰ ምድር ውሀ
📞ይደውሉ ከጠበቁት በላይ ሆኖ ያገኙታል
0964784722
ሁለት ዜናዎች
1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ነፍጥ ያነገቡና በነፍጥ ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ የሚገኙ ቡድኖችን በአካል ለማነጋገር መወሰኑን አንደኛው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ለሪፖርተር ተናግረዋል። የኮሚሽኑ አባላት ነፍጥ አንግበው ጦርነት ውስጥ የሚገኙ አካላትን በአካል ለማነጋገር ሃላፊነት መከፋፈላቸውን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ ገልጸዋል። በአማራ ክልል ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ውጊያ ላይ የሚገኙትን የፋኖ ታጣቂዎችን በአካል የማነጋገሩ ኃላፊነት ለእሳቸው እንደተሰጠ ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልጸዋል።
2፤
አሜሪካና አውሮፓ ኅብረት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ለቀጠሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ በጋራ አማራጮችን እየፈተሹ መኾኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በተያዘው ሳምንት ወደ ብራስልስ ሲያቀኑ፣ ለግጭቶቹ ሰላማዊ መፍትሄ በማፈላለግ ግጭቶቹ በንግግር በሚፈቱበትና ሲቪሎችን ከጥቃት መከላከል በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ ከኅብረቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚመክሩ መግለጫው አመልክቷል። አሜሪካና ኅብረቱ፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሃት መካከል የተደረሰውን የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት አሜሪካና ኅብረቱ በጋራ መደገፍ በሚቀጥሉበትና በሰሜኑ ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማስፈን በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ ጭምር ሐመርና የኅብረቱ ባለሥልጣናት ይመክራሉ ተብሏል።
ዋዜማ
🌼🌼 ለአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽ🌼 🌼
⭐️ ከመገናኛ ወደ ኢንግሊዝ ኢንባሲ መንገድ ላይ 75% ግንባታው የተጠናቀቀ አፓርትመንት ይዘን ቀርበናል
👉በ30% ቅድሚያ ክፍያ ብቻ ቤትዎን ይግዙ
👉ባለ 3 መኝታ ቤቶች
👉ካርታ የተዘጋጀላቸው
👉በ6 ዙር ረጋ ብለው የሚከፍሉበት አማራጭ
👉በቂ የመኪና ማቆሚያ
👉ጂምናዚየም
👉በ4 ቱም ማዕዘን ከተማውን የሚያስቃኝ ሰፊ ሰገነት
👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
👉አስተማማኝ ጀነሬተር
👉የከርሰ ምድር ውሀ
📞ይደውሉ ከጠበቁት በላይ ሆኖ ያገኙታል
0964784722
ፒያሳ አራዳ ህንፃ ጋር ያሉ 42 ሱቆች በሁለት ቀናት ማስጠንቀቂያ እቃቸውን ይዘው እንዲወጡ አርብ ምሽት 12:00 ተነግሯቸው ትላንት ሌሊቱን አፍርሰውት አድረዋል::
Читать полностью…ኢትዮዽያውያን ሴት አትሌቶቻችን ዛሬም አኩርተውናል 🇪🇹🇪🇹
አማኒ በሪሶ ወርቅ 🇪🇹🇪🇹
ጎቲቶም ገ/ስላሴ ብር ጅግኖች 🇪🇹🇪🇹
ያለምዘርፍ የኋላው እና ፀሃይ ገመቹ ጀግኖች ናችሁ
እንኳን ደስ አለን
በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያልተመረመረ ጥሬ ስጋ የበሉ 80 የሚደርሱ ኢትዯጵያዊያን በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተው እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ገለፁ::
ምንጮቹ እንዳሉት በህገወጥ እርድ ስጋ ወደ ሆቴላቸው ያስገቡ እና ለደምበኞቻቸው ጥሬውን የሽጡ የምግብ ቤት ባለቤቶች ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተነግሯል::
ሆቲሉቹ በስም የሚታወቁ ቢሆንም ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ይፋ ከማድረግ ተቆጥበናል::
በጥሬ ስጋው ምክንያት ከታመሙት መካከል አንድ ሰው መሞቱም ይነገራል::
ጉዳዩ ያሳሰበው የቨርጂኒያ ግዛት መንግስት የህዝብን ጤና ለመጠበቅ ሲባል የተወሰኑ ሆቴሎች ለጊዜውእንዲዝጉ አድርጎ ጥብቅ ምርመራ እያደረገ ነው ተብሏል:
Zehabesha
የአማራ ክልል ምክርቤት በርካታ አባላት ሳይገኙ በዚህ መልክ እየተካሄደ ነው።
ኮረም መሙላቱ አጠራጣሪ ነው።
ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር ልትዘረጋ መሆኑ ተገለጸ
=======#=======
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን የባቡር መስመር በ13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ልትዘረጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡
ኬንያ የምትዘረጋው ይህ ፈጣን የባቡር መስመር በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን፤ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ ላሙ ወደብ በማድረግ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን እንደሚያገናኝ ብሉምበርግ ዘግቧል።
በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለው ይህ የባቡር መስመር በፈረንጆቹ 2025 ሥራ እንደሚጀመር እና 3 ሺሕ ከሎ ሜትር ወይም 1 ሺሕ 864 ማይል እንደሚረዝም ታውቋል፡፡
የባቡር መስመሩ መነሻውን ከህንድ ውቅያኖስ አድርጎ፣ በኬንያዋ ማዕከላዊ ከተማ ኦሲዮሎን በኩል፣ ናይሮቢን እና አዲስ አበባን በማገናኘት የመጨረሻም መዳረሻውን ደቡብ ሱዳን ጁባ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡
ይህ ፈጣን የባቡር መስመር “ኢትዮጵያ በአሰብ እና ምጽዋ እንዲሁም ጅቡቲ ወደቦች ላይ ያላትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው” የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉትም ተገልጿል፡፡
በዚሁ ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታ አማካኝነት ደቡብ ሱዳን ኹለተኛ ወደብ እንደሚኖራትም ተመላክቷል።
የባቡር መስመር ዝርጋታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠጥ በሚጀምርበት ወቅት፣ ከላሞ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ውል የፈጸመው ላፕሴት፣ በዓመት ከ29 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት እና 700 ሺሕ ተጓዦችን እንደሚያመላልስ አስታውቋል።
/channel/addismaleda
በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ፡፡
በ5ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሀጐስ ገ/ሕይወት እና በሪሁን አረጋዊ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡
“መቼ ፣ የት ፣ በምን እና እንዴት ” ...የሚለው እንጂ ይህ እንደሚሆን ያኔም ቢሆን ይገመታል ።
የሩሲያ የደህንነት ተቋም (KGB) እንኳን ሀገሪቷ ውስጥ ይቅርና እና አቅራቢያ ያሉ ሀገሮች ውስጥም ሩሲያን ከድቷል ብለው ያሰቡትን ግለሰብ አሳደው ይበቀሉታል ።
የKGB ሰላዮች እጅ ምን ያህል ረዥም እንደሆነ ማሳያው ጠንካራ የደህንነት ተቋም አለባቸው የሚባሉት አሜሪካና እንግሊዝ ውስጥ ሳይቀር የፈፀሙት ኦፕሬሽን (ተመርዘው የሞቱት ዜጎች ልብ ይለዋል ) የቅርብ ግዜ ዜና ነበር ።
የዚህ ሰውዬም (የዋግነር ጀነራል) ዕጣ ፈንታ ዛሬ የሆነውም ይህ ነው ።
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
#በመሃል_አዲስ አበባ ለቡ መብራት #ዋና_መንገድ ላይ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን
🌻በፈጣን የግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ
ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!! ከ755ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ 65,395 ካሬ ያረፈ የተንጣለለ መንደር።
📍15% ቅድመ ክፍያ
(በካሬ ከ72,604------90,756ብር ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️( -----25% discount )
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 132.እና 140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ
''ብልህ ሰው ዛሬን ዛሬ ይጠቀማል መልካም እድል!"
👨🚀ለበለጠ መረጃ ወይም ለቢሮ ቀጠሮ ለመያዝ
@Gashayie
+251918642895
+251906217873
/channel/Engineergashaw
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከEMS መልቀቁን ገለፀ።
#FastMereja
በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ ከኢሳት በመልቀቅ በርካታ ቦታ የተከፋፈሉት ጋዜጠኞቹ መሳይ መኮንን በመከተል ሲሳይ አጌና ከEMS መልቀቁን አሳውቋል። ይህን ብሏል…
«ከEMS ጋር የነበረኝ የአንድ ዓመት ተኩል ጉዞ ማብቃቱን ለEMS ባልደረቦቼ እና ለቦርዱ በዛሬው ዕለት አሳውቂያለሁ። EMS ላይ ለሳምንታት ባለመቅረቤ በተለያዩ መገናኛ መንገዶች ጥያቄ ላቀረባችሁ ወገኖች ለሁላችሁም በተናጠል ምላሽ መስጠት ያልቻልኩት ከአቅሜ በላይ በመሆኑ ስለነበር ይቅርታ እጠይቃለሁ። ዕረፍት ላይ መሆኔን የገለፅኩላችሁም በዕርግጥም ዕረፍትም ላይ ነበርኩ። በዕረፍት ግዜው ውስጥ ነገሮችን በመገምገም የኔ ከEMS መልቀቅ ለኔም ሆነ ለተቋሙ እንዲሁም ለመላው የEMS ባልደረቦች አስፈላጊ እንደሆነ ይበልጥ በማመኔ ከEMS ጋር ያለኝ ግኑኝነት ከነሐሴ16/2015 ጀምሮ ማብቃቱን እገልፃለሁ።»
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር እና በቅደመ ክፍያ ለመቀበል የሚከተለው አካሄድ ምን ይመስላል?
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚቀበልበት መንገድ “በጣም ተገድቦ” እንደነበር በዛሬው መግለጫቸው ያስታወሱት የተቋሙ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የራስ ገዝ ትግበራው በዚህ ረገድ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በየዓመቱ ሰባት ሺህ ገደማ አዳዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ከዩኒቨርስቲው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው የሚገቡት፤ ልክ እንደሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ሁሉ የትምህርት ሚኒስቴር በሚያደርገው ምደባ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ ገዝነትን መተግበር ከሚጀምርበት ከቀጣዩ 2016 የትምህርት ዘመን አንስቶ ግን የቅደመ ምረቃ ተማሪዎች የሚገቡበት ይህ አሰራር እንደሚቀር ፕሮፌሰር ጣሰው አስታውቀዋል።
“ከ2016 ጀምሮ ዩኒቨርስቲው የመቁረጫ ነጥቡን ያለፉ ተማሪዎችን አወዳድሮ፣ የዩኒቨርስቲ ተልዕኮዬን ያሳኩልኛል የሚላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ ያስተምራል” ሲሉ ፕሮፌሰር ጣሰው ዩኒቨርስቲው የሚከተለውን አዲስ አሰራር ገልጸዋል። አንጋፋው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚያወዳድረው፤ ዩኒቨርስቲውን ከመቀላቀላቸው በፊት በሚሰጥ የመግቢያ ፈተና መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማቲዮስ ኢንሰርሙ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ለመጪው አርብ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ በመጪው አርብ ነሐሴ 19፤ 2015 የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ለክልሉ ምክር ቤት አባላት ጥሪ የተላለፈው ትላንት ሰኞ ረፋድ መሆኑን ሁለት የምክር ቤቱ አባላት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የክልሉ ምክር ቤት አባላት ስብሰባው ከሚካሄድበት ዕለት አንድ ቀን በፊት በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም፤ የስብሰባው አጀንዳ እንዳልተገለጸላቸው አመልክተዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ምክር ቤት አባል “አስቸኳይ ስብሰባ ስለሆነ አጀንዳውን መናገር አልፈለጉም” ሲሉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።
ሆኖም እኙሁ የምክር ቤት አባል “ወቅታዊ የክልሉ ጉዳዮች”፤ የስብሰባው አጀንዳ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር “ከክልሉ መንግስት አቅም በላይ” በመሆኑ፤ የፌደራል መንግስት በክልሉ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ ይታወሳል። ከሐምሌ 28፤ 2015 ጀምሮ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ እንኳን አስፈላጊ ቢሆን፤ “አዋጁን ማውጣት የነበረበት የክልሉ ምክር ቤት ነው” የሚል ትችት ሲሰነዘር ቆይቷል።
* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11876/
የነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ,ም ዋና ዋና ዜናዎች፤
የቀድሞው የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ ከነአጃቢዎቻቸው ባለፈው ሐሙስ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ። ሆኖም ያሉበትን ማወቅ እንዳልቻሉ አመልክተዋል።
በክልሉ ከፍተኛ ውጊያ የነበረባቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬና ደንበጫ ከተሞች እየተረጋጉ እንደሆነ ነዋሪዎች ገለጹ። እንደነዋሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በየከተሞቹ የሚታዩ ሲሆን፤ በአንዳንድ የክልሉ ወረዳ ከተሞች ደግሞ የፋኖ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሳሉ።
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ ተሳትፈዋል ያላቸውን 25 አመራሮች እና ባለሙያዎች አሠረ። 10 ከፍተኛ አመራሮችንም ከኃላፊነት አነሳ።
የሳውድ አረቢያ የድንበር ጠባቂዎች በመቶዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ተሰዳጆችን መግደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አመለከተ።
የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ዘገባ ነው ☝
በአማራ ክልል ባለዉ ውጊያ ክልሉ ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው ያላቸውን ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች አሳወቀ❗❗
መንግስት ከስር የተዘረዘሩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ስለሆኑ ምንም አይነት ገንዘብ ዝውውር እንዳይፈፀም እገዳ ደብዳቤ ፅፏል።
ከእነዚህ ውስጥ!
▪ከሰሜን ሸዋ ወረዳዎች:-ሚዳ፣መርሃቤቴ፣ አለም ከተማ ፣እነዋሪ፣ መንዝ ቀያ፣ መንዝ ላሎ፣መንዝ፣ ማማ፣መንዝ ሞላሌ፣ መንዝ ጌራ፣ ሲያደብር፣ ዋዩ፣ እንሳሮ ፣ምረትና ጅሩ ወረዳዎች
▪ሰሜን ወሎ ወረዳዎች:- ግዳን ወረዳ ፣እስታይሽ፣ ቡግና እና ሙጃ ወረዳዎች
▪ከደቡብ ወሎ ወረዳዎች:- ወግዲ ወረዳ፣ ከለላ፣ መካነሰላም ፣ቦረና እና ዋድላ ደላንታ ወረዳ
▪ከምዕራብ ወሎ ወረዳዎች:- አማራ ሳይንት
▪ከደቡብ ጎንደር ወረዳዎች:- ደብረታቦር ከተማን ጨምሮ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች
▪ከጎጃም:- ሰሜን ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች
▪ማዕከላዊ ጎንደር ወረዳዎች:- ምዕራብ ደንብያ ወረዳ፣ጣቁሳ፣አለፋ፣ምስራቅ ደንብያ፣ሻውራ፣ቆላድባ ወረዳዎች
▪ከምዕራብ ጎንደር ወረዳዎች:- ቋራ ወረዳ
▪ከሰሜን ጎንደር ወረዳዎች:- ጃናሞራ ወረዳዎች ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ናቸው ብሏል። በእነዚህ ወረዳዎችም ምንም አይነት የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር የክልሉ ገንዘብ ቢሮ አግዷቸዋል።
ዛሬ አፍላ ውጊያ ያለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች❗ከስር ባለው ሊንክ ቴሌግራም ግቡ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ወደ አውሮፓ ማቅናታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ
=======#=======
ሰኞ ነሐሴ 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከነሐሴ 13 ጀምሮ እስከ 19/2015 ድረስ ወደ አውሮፓ በማቅናት፤ ከኅብረቱ አገራት ጋር በኢትዮጵያ ወቅትዊ ጉዳዮችና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በድረገጹ ባሰፈረው መረጃ፤ ማይክ ሀመር በስዊድን ስቶኮልም እና በቤልጂየም ብራስልስ በሚኖራቸው ቆይታ፤ በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ተዎካዮች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ አስታውቋል፡፡
በዚህም በቅድሚያ በስቶኮም ዓለም አቀፍ የውሃ ተቋም በተዘጋጀው የዓለም የውሃ ሳምንት መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ የተገለጸ ሲሆን፤ በመድረኩ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እንደሚመክሩ ተመላክቷል።
እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛው በቤልጂየም ብራስልስ በሚኖራቸዉ ቆይታ፤ ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ተዎካዮች ጋር ተገናኝተው ኅብረቱ እና አሜሪካ በኢትዮጵያ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ሰላማዊ ሰዎችን በመጠበቅ ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም አምባሳደሩ ከአዉሮፓ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር በጋራ በፕሪቶሪያ የተፈረመዉ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ፣ ፍትሕ እና ተጠያቂነትን በማስፈን ዙሪያም ከኢትዮጵያ አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
/channel/addismaleda
የየመን ድንበርን ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን ሂዩውማን ራይትስ ዎች ገለጸ
=======#=======
ሰኞ ነሐሴ 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩውማን ራይትስ ዎች እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ወር ድረስ፤ የየመን ድንበርን ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ነሐሴ 15/2015 ባወጣው የምርመራ ሪፖርት፤ “በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከየመን ለመሻገር ሲሞክሩ የሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል” ብሏል፡፡
መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ ኒውዮርክ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ተከራከሪው ድርጅት፤ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሕጻናት እና ሴቶች ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ስቃይ የሳዑዲ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጓል።
ድርጅቱ ከምስክሮች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ በሳተላይት ምስልና በቪዲዮ በታገዘው73 ገጽ ሪፖርት፤ “ግድያው ሰፊና ስልታዊ መሆኑን” ገልጿል፡፡
በዚህም እማኞች፤ “የሳዑዲ ወታደሮች ከባድ መሳሪያዎች በመጠቀም ድንበሩ ለማቋረጥ በሚሞክሩ ሰዎች ላይ ኹሉ ተኩስ እንደሚከፍቱና ጉዳት ደርሶባቸዉ ሕይወታቸዉ ያላለፈ ሰዎችንም እየፈለጉ ወደ ማጎሪያ ካምፕ እንደሚያስገቡ ነግረውኛል” ብሏል።
“የሳዑዲ ጦር፤ ድንበር ጠባቂዎችንና ምን አልባትም ሌሎች ልዩ ክፍሎችን ጨምሮ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመቶዎች ወይንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውንና በሕይወት የተረፉትንም ለእስር፣ ለእንግልት፣ አስገድዶ መድፈርና ለሌሎች ኢ ሰብዓዊ ተዳርገዋል” ሲልም በሪፖርቱ ገልጿል።
አዲስ ማለዳ