muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

በመቀሌ ተከለከለ

በትግራይ ክልል "ሥርነቀል ለውጥ" ለማምጣት ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ በውናት፣ ሳልሳይ ወያነ እና ባያቶና ትግራይ ፓርቲ አማካኝነት ከጳጉሜ 2 እስከ 4 ባሉት ቀናት እንዲካሄድ ታቅዶ የነበው ሰልፍ በመቀሌ ተከለከለ ።

ኾኖም የመቀለ ከተማ አስተዳደር ትናንት ለሰልፉ አዘጋጆች በጻፈው ደብዳቤ፣ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄው ሕገመንግሥታዊ እንደሆነ ጠቅሶ ነገር ግን ለሰላማዊ ሰልፉ የጸጥታ ጥበቃ ማድረግ እንደማይችልና ሰልፉም እንደማይካሄድ ገልጧል።

የከተማዋ አስተዳደር ለሰላማዊ ሰልፉ የጸጥታ ጥበቃ ማድረግ እንደማይችል የገለጠው፣ ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራባቸው ወቅቶች የአዲስ ዓመትና የመስቀል በዓል ዋዜማ መኾናቸውን በመጥቀስና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እና የሥራ መደራረብ የሚበዛባቸው በመኾናቸው እንደኾነ በመጥቀስ ነው። (ዋዜማ)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

Johannesburg is burning
የደቡብ አፍሪቃ ትልቋ ዮሀንስበርግ መሀል ከተማ ከፍተኛ እሳት አደጋ አጋጥሟል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲስ ዜና ለሜትር ታክሲ አሽክርካሪዎች! ዋን ራይድ
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ልዩ አማራጭ ይዞ መጣላቸሁ!
ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በተጨማሪ በአካል ለመመዝገብ ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉስ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930858687/0944161718/0955161718/0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onepassenger
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል ከ183 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ገለጸ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ከሐምሌ ወር ጀምሮ ቢያንስ 183 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ ነሐሴ 22/2015 ባወጣው ሪፖርት፤ በአማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር እና በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተባብሶ መቀጠሉ እንዳሳሰበው ጠቅሷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለባለስልጣናቱ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል፣ የሰዓት እላፊ ገደብ ለመጣል እና ስብሰባዎችን ለመከልከል ሰፊ ስልጣን ሰጥቷቸዋል ነው ያለው።

በአስቸኳይ አዋጁ መሰረት በኢትዮጵያ ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸውንና ከታሰሩት መካከል "የፋኖ ደጋፊዎች ናቸው" ተብለው የሚገመቱት የአማራ ብሄር ተወላጆች በርካታ መሆናቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

እንዲሁም በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ የሚዘግቡ ቢያንስ ሦስት ጋዜጠኞች ከተያዘው ነሐሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለእስር መዳረጋቸውንና መሰረታዊ መገልገያዎች በሌላቸው እስር ቤቶች ዉስጥ እንደሚገኙ ነው የጠቆመው።

መንግሥት እየፈጸመ ያለውን የጅምላ እስር እንዲያቆም፣ የነጻነት ገደቦችን እንዲያነሳና ያለምክንያት የታሰሩት ኹሉ እንዲፈቱ የጠየቀው ተመድ፤ "መንግሥት ዓለም አቀፍ ሕጎችና ደንቦች መከበራቸውን ማረጋገጥ አለበት።" ሲል አሳስቧል።

እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩ መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጽህፈት ቤት የእስረኞች ማቆያ ቦታዎች ያለምንም ገደብ ክፍት እንዲደረጉ ጠይቋል።

አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩበት የፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ባለቤት (ቻይናዊ) እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአሁኑ ሰዓት ሲኤምሲ የሚገኘው ፀሐይ ሪልስቴት በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ቁጥሩ ያልታወቀ የዶላር ክምችት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ዘ-ሐበሻ ከፖሊስ ምንጮች ሰምቷል። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ይዘን እንቀርባለን።
የ ZeHabesha ዘገባ ነው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች

1፤ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ራሚዝ አልክባሮቭ በትግራይ ክልል ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። አልክባሮቭ ዛሬ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር የጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ በሚችሉበት፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና በክልሉ የተከሰተውን አንበጣ መንጋ መቆጣጠር በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ መወያየታቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት ገልጧል። አልክባሮቭና ልዑካን ቡድናቸው፣ የክልሉ የጦርነት ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን ማዕከላት ይጎበኛሉ ተብሏል።

2፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት ክልላዊ የሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ጉባዔ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል። የክልሉ መንግሥት የሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ጉባዔ ሥልጣንና ተግባራትን የሚወስን ረቂቅ አዋጅ ትናንት ማጽደቁን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። 114 አባላት ይኖሩታል የተባለው የሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ጉባዔ ዋና ሃላፊነቱ፣ በክልሉ በሚከሰቱ የጎሳ ግጭቶችና የልማት ሥራዎች ዙሪያ የክልሉን መንግሥት ማማከር እንደኾነ የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ረቂቅ አዋጁ፣ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ይጠበቅበታል።
ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሶማሌ ክልል ካቢኔ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ

የሶማሌ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 114 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 23፤ 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የጉባኤውን ስልጣን እና ኃላፊነት የሚዘረዝረውን አዋጅ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

የጉባኤው አባላት የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች ዋነኛ ስራቸው “የማማከር ስራ” መሆኑን የሶማሌ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። “በአንዳንድ አዳዲስ የሰፈራ ፕሮግራሞች ግጭት ስለሚከሰቱ፤ በግጭት ዙሪያ፣ በጎሳ ግጭት ዙሪያ፣ በልማት ዙሪያ የሚያማክሩን ይሆናል” ሲሉ የቢሮው ኃላፊው አስረድተዋል።

የጉባኤው አባላት በመሆን የሚመረጡት የሀገር ሽማግሌዎች የተለያዩ የጎሳ ማህበረሰብ ቅንርጫፎችን የሚወክሉ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አብዲቃድር፤ “ከአዋጁ መጽደቅ በኋላ በሚወጣ መመሪያ የአባላት ምርጫ በግልጽ የሚቀመጥ ይሆናል” ብለዋል። በዚህ መመሪያ መሰረት የሚመረጡት የጉባኤው አባላት በሚያደርጉት ስብሰባ፤ የጉባኤውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመርጡም አመልክተዋል። የጉባኤው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር በበኩላቸው፤ በአዋጁ በተቀመጠላቸው ስልጣን መሰረት “አስፈላጊ የሆኑ ሹመቶችን” እንደሚሰጡ የቢሮ ኃላፊው አክለዋል።

* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11934/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🌻🌻🌻ዳግም በማስታወ ዋጋ ተመልሰናል!

👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
🌻 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ አድርገናል። ከ CDC በ2. ኪ.ሜ  ርቀት ላይ የሚገኝ
65,395 ካሬ  ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር

📍  የቅድመ ክፍያ ቅናሸ  ከ30%-----100%  ለሚከፍሉ ደንበኞች (በካሬ ከ87,00ብር-----72,600 ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(እስከ 25%  የሚያተረፉበት )
የማስታወቂያ  ዋጋውን  ተጠቅመው ከ1,000,000  እስከ  3,076,000 ብር ያትርፉ!!!

🌻ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
ከ755 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ!!

ሊያመልጠዎ የማይገባ  ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ  የተንጣለለ መንደር በሠፊ የካሬ አማራጭ
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)15%=755ሺብር

▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ

▶ 132.እና 140.&144  ባለ ሁለት መኝታ
   
▶ 147 ,164&169 ባለ ሶስት መኝታ                 

ደስታዎ እዚህ ይጀምራል!!!
ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
      ለበለጠ መረጃ  
                 🌻🌻🌻+251906217873
                 🌻🌻 🌻+251918642895 /channel/Engineergashaw

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአፍሪካዊቷ ጋቦን ወታደሩ የምርጫ ውጤቱን አልቀበልም በማለት በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን መጥቷል።
አፍሪካን አለማረጋጋት አዲሱ ስትራቴጂ አካል ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ
=======#=======

ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል።

በዚህም፤ ላለፉት አራት ወራት በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሷል።

ሆኖም ግን የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት:-

1. ቤንዚን ----------ብር 74.85 በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ -----------ብር 76.34 በሊትር

3. ኬሮሲን ብር ------------76.34 በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---------ብር 68.58 በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ -----------62.22 በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ -----------61.07 በሊትር መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
/channel/addismaleda

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የፌዴራል መንግስትና የአማራ ክልል ፋኖ ግጭት ያሳሰባት አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ማይክ ሀመርን ወደ ኬንያና ኢትዮጵያ ላከች። ማይክ ሀመር ኢጋድን፣ የአፍሪካ ህብረትን እና የኢትዮጵያ መንግስትን ያናግራል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብራስልስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሲመክሩ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዐበይት ዜናዎች

1፤ 
ገንዘብ ሚንስቴር ለኢትዮጵያና ጅቡቲ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ማስፋፊያ የሚውል የ730 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራርሟል። ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ከጅቡቲ ጋር በሚያገናኘው መስመር ላይ የመንገድ ትይይዝና የሎጅስቲክ ዝውውርን ለማቀላጠፍ ያለመ ነው። በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ፣ ከመዒሶ እስከ ድሬዳዋ የመጓጓዣ ሰዓትንና ወጪን የሚቀንስና በርካታ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን ማስተናገድ የሚችል የ142 ኪሎ ሜትር መንገድ እንደሚገነባ ሚንስቴሩ ገልጧል። የገንዘብ ድጋፉ፣ በዚኹ መንገድ አቅራቢያ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጤና፣ ትምህርትና መጠጥ ውሃ ተደራሽነታቸውን ለማሻሻልና ከዋናው መንገድ ጋር የሚያገናኟቸውን መንገዶች ለመገንባት ጭምር ይውላል።

2፤
በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከትናንት እኩለ ሌሊት ጀምሮ መቋረጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠው፣ መኾኒ ከተማ ላይ ባጋጠመ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ብልሽት እንደኾነ ዘገባው በክልሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤትን በመጥቀስ አመልክቷል። ችግሩን ዛሬ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለመቅረፍ ተጨማሪ ባለሙያዎች ወደ መኾኒ እንደተላኩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ መናገሩንም ዘገባው ጠቅሷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በቀለ ገርባ ከኦፌኮ በመልቀቅ በአሜሪካ አገር ጥገኝነት መጠየቃቸውን አስታወቁ
=======#=======

ሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዜዳንት በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

በቀለ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት በቀለ፤ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠላቸው ጠቃሚ ስላልሆነ ራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ነው የተናገሩት።

በቀለ ገርባ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሦስት ወር ሆኗቸዋል።

ከእስር ከወጡ በኋላም ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ እንጂ በዚያው የመቅረት ዕቅድ እንዳልነበራቸው ጨምረው ተናግረዋል።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም " በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውንና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጽሕፈት ቤት ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚባልበት መልኩ ተዘግተዋል የሚሉት በቀለ፤ በዚህ ምክንያት በአገሪቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

" ውል ማዋዋል የምንጀምረው ረቡዕ ነው "

የ5ኛዉ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ግልጽ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል የሚጀመረው ከረቡዕ 24/12/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።

አሸናፊዎች ይህ ተረድተው ለመዋዋል የሚጠበቅባቸውን ሰነድ አሟልተው እንዲቀርቡ ማሳስቢያ ተላልፏል።

ለዉል ሲኬድ ምን ማሟላት ይገባል ?

1ኛ. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ሁለት ኮፒ
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN /
3ኛ. የጋብቻ ሁኔታን የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውን እና ሁለት ኮፒ
4ኛ. አራት/4/ ጉርድ ፎቶ
5ኛ. የዉጭ ሀገር ዜግነት ያለዉ ከሆነ ካለበት ሀገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሰጥ መታወቂያ እና ሙሉ የቤቱን ዋጋ 100% መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
Via Wasu Mohammed

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወንዶች ማራቶን አትሌት ልዑል ገ/ሥላሴ ለሀገራችን የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በውድድሩ ዩጋንዳዊው አትሌት ቪክቶር ኪፕላጋት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ለቸኮለ! ሐሙስ ነሃሴ 25/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ አውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭትና ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የሰላማዊ ሰዎች ሞት "እጅግ አሳስቦኛል" ሲል አዲስ ባወጣው አመግለጫ አስታውቋል። በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጀምሮ፣ "መጠነ ሰፊ የሰዎች እስር" እየተካሄደ እንደኾነ መረዳቱን የጠቀሰው ኅብረቱ፣ ሲቪሎች ከጥቃት እንዲጠበቁ፣ ግጭቱ እንዲቆምና ግጭት ውስጥ ባሉት ወገኖች መካከል ንግግር እንዲጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ኮሚሽንና አፍሪካ ኅብረት ያቀረቡትን ጥሪ እጋራለኹ ብሏል። ኅብረቱ፣ "ወደ ንግግር የሚያመራ ማናቸውንም ጥረት፣ እርቅ እና ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ" ለመደገፍ ዝግጁ መኾኑንም አስታውቋል።

2፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሹመዋል። የዩኒቨርስቲው የሥራ አመራር ቦርድ ደሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩን የቦርዱ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የሥራ አመራር ቦርዱ ወደፊት ለዩኒቨርስቲው አዲስ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ይሾማል።

3፤ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) አመራሮች ትናንት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ዝቅተኛ የሠራተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለካቢኔያቸው መመሪያ መስጠታቸውን የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለዋዜማ ተናግረዋል። ካሳሁን፣ በሌሎች የሠራተኛው አንገብጋቢ ጥያቄዎችና የሠራተኛውን ጥያቄዎች ለመመለስና መብቶቹን ለማስከበር መከናወን ባለባቸው አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደተደረገም ገልጸዋል። ኾኖም ውይይት የተደረገባቸውን ሌሎች አንገብጋቢ ጉዳዮች ካሳሁን ከመግለጥ ተቆጥበዋል። የሠራተኛ አዋጅ የሠራተኛና ሲቪክ ማኅበራትን ያካተተ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚወስን ቦርድ እንደሚቋቋም የደነገገ ሲኾን፣ ኢሠማኮም ቦርዱ እንዲቋቋም ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ ነበር።

4፤ ሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ስምሪት ዙሪያ የኢትዮጵያና ሊባኖስ መንግሥታት ቀደም ሲል የደረሱበትን ስምምነት አጽድቋል። የኹለትዮሽ ስምምነቱ፣ በሊባኖስ በተለያዩ የሥራ መስኮች ተቀጥረው የሚሠሩትንና ወደፊት የሚቀጠሩትን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብት ለማስከበር፣ ዜጎች ሊባኖስ ውስጥ የመብት ጥሰቶች ሲያጋጥሟቸው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ባግባቡ እንዲዳኙና የኢትዮጵያ መንግሥትም ለዜጎቹ አስፈላጊውን የሕግ ድጋፍ እንዲያደርግ የሚያስችል ነው። የሚንስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ስምምነቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቀው ልኳል።

5፤ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ "የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ" እንቋቁማለን ብለው ቀደም ሲል የተንቀሳቀሱ ሦስት ጳጳሳት በተናጥል የጳጳስነት ሹመት ሰጥተዋቸው የነበሩ ሰባት ግለሰቦችን ማክሰኞ'ለት ማሠሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ፖሊስ ያሠራቸው ግለሰቦች፣ የንቅናቄው አንቀሳቃሽ ሦስት ጳጳሳት በመንግሥት አቀራራቢነት በቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ስር ለመቀጠል ከቤተክርስቲያኗ ሲኖዶሱ ጋር የደረሱበትን ስምምነት ውድቅ ያደረጉ፣ ስምምነቱን ተከትሎ ሲኖዶሱ ለኦሮሚያ አሕጉረ ስብከቶች የሾማቸውን አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ያልተቀበሉና "የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ" ለማቋቋም አኹንም የሚንቀሳቀሱ እንደኾኑ ዘገባው ጠቅሷል።

6፤ "አኖኒመስ ሱዳን" የተሰኘው የኢንተርኔት መረጃ ጠላፊ ቡድን "ኤክስ"ን ወይም በቀድሞ ስያሜው ትዊተርን ማክሰኞ'ለት ለሰዓታት ጠልፎ ከቁጥጥር ውጭ አድርጎት እንደነበር ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ጠለፋውን ተከትሎ፣ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴው በበርካታ አገራት ለኹለት ሰዓታት ተቋርጦ እንደነበር ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ቡድኑ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ ጠለፋውን የፈጸመው፣ የ"ኤክስ" ኩባንያ ባለቤት ኤለን ማስክ "ስታርሊንክ" በተሰኘው ኢንተርኔት አቅራቢ ሳተላይቱ አማካኝነት በጦርነት ለምትታመሰው ሱዳን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያቀርብ ለማስገደድ እንደኾነ መግለጡን ቢቢሲ ዘግቧል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ እየገነነ የመጣው የኢንተርኔት መረጃ ጠላፊው "አኖኒመስ ሱዳን" ቡድን ትክክለኛ አድራሻውና ማንነቱ ግን እስካሁን በርግጠኝነት አይታወቅም።

ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦረዱም ዩኒቨርሲቲውን በሃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ፀሐይ ሪልስቴት እንደተከበበ ነው

ቻይናዊው የፀሐይ ሪልስቴት ባለቤት እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ማተም ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ በኋላ ግቢው በፌደራል ፓሊስ እና በፀጥታ ኃይሎች እንደተከበበ ነው።

ሲኤምሲ የሚገኘው ፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ከቀን ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል። ብርበራው ምሽቱም ላይ አጥሏል። እስካሁን በተደረገ ፍተሻ እስካሁን የተረጋገጠ 80 ሻንጣ ሙሉ ዶላር መገኘቱን በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። የሻንጣው ቁጥር ይጨምራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ይሰሩበት የነበረ የዶላር ማተሚያ እና ማቀናበሪያ ማሽን በግቢው ውስጥ ተገኝቶ በኢግዚቢትነት ተይዟል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የቻይና ዜጎች ወርቅ እና የከበሩ ድንጋዮች ከኢትዮጵያ በገፍ እያወጡ በህገወጥ ሲሸጡ መያዛቸው የሚታወስ ነው።

በፀሀይ ሪልሰቴት የዶላር ማተም ተግባር ላይም ሆነ በማእድን ዘረፋው ከተጠርጣሪዎቹ ጀርባ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉበት።

እንዲህ አይነቱ ወንጀል በሀገር ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት ከማወጅ የሚተናነስ አይደለም።
ዘሀበሻ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እግራቸውን ላከሟቸውና እንደገና መራመድ እንዲችሉ ላደረጓቸው የናሚቢያ ህክምና ባለሙያዎች ምስጋና አቀረቡ። በጋጠማቸው ወለምታ የእግራቸው አጥንት ተሰብሮ እንደነበር የገለጹት ቴዎድሮስ የናሚቢያዋ ዊንድሆክ ማእከላዊ ሆስፒታል ሰራተኞችን አመስግነዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#MakeSomeNoise የጋቦን መሪ የነበሩት አሊ ቦንጎ ባሰራጩት አጭር ቪድዮ "ወዳጆቼ... ታስሬያለሁ፣ ድምፅ አሰሙልኝ (make some noise)" ብለዋል።

ዌል... ምናልባት የአባታቸውን የ41 አመት ስልጣን የወረሱት አሊ ቦንጎ በቁም እስር ላይ ስላሉ ያላወቁት ነገር ቢኖር በርካታ ጋቦናውያን ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ በጎዳናዎች ላይ ወጥተው "የደስታ ድምፅ እያሰሙ" መሆኑን ነው።

በነገራችን ላይ የዛሬ አምስት አመት ገደማ ጋቦንን የመጎብኘት እድል አግኝቼ ነበር።

ከነዳጅ ምርት በሚገኝ ገንዘብ በአለም እጅግ ሀብታም ከሚባሉት ሀገራት ውስጥ የምትመደበው ጋቦን ህዝቧ ግን በከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል። በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ምስል በወቅቱ ያነሳሁት የፕሬዝደንቱ ቅንጡ ፅ/ቤት ሲሆን የቦንጎ ቤተሰብ በፈረንሳይ የበርካታ ቪላዎች እና ውድ ተሽከርካሪዎች ባለቤት ነው።
Via Elias Meseret

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲስ ዜና ለሜትር ታክሲ አሽክርካሪዎች! ዋን ራይድ
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ልዩ አማራጭ ይዞ መጣላቸሁ!
ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በተጨማሪ በአካል ለመመዝገብ ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉስ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930858687/0944161718/0955161718/0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onepassenger
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ፓስተሩ ኃጢያተኛ በረገጠው መሬት አልራመድም አለ🙉❗
በጊቱራይ፣ ኬንያ የሪቫይቫል ቤተ ክርስቲያንን ጆን ምዋንጊን የተባለ ፓስተር "የእግዚአብሔር አገልጋይ በኃጢአተኛ መሬት ላይ መሄድ ስለማይችል ሬንጅ ሮቨር 2023 ሞዴል እስኪገዙለት ድረስ ሁል ጊዜ ጉባኤው ተሸክመውኝ ይሄዳሉ " በማለት መሬት ሳይነካው በዚህ መልኩ እየተገለገለ ነው።
የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ለሕዝቡ አገልጋይ መሆን ሲገባቸው ህዝቡን እንዲህ ላለ ኃላ ቀርነት ዳርገውታል።
Via-adiss reporter

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በደብረማረቆስ ከተማ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረማረቆስ ከአርብ ነሐሴ 19/2015 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ በመከላከያ ሠራዊትና እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከመቶ በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አዲስ ማለዳ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከጤና ባለሙያዎች ሰምታለች።

ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የደብረማርቆስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል ሐኪም በከተማዋ ቦሌ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከመቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰው፤ የሟቾቹ አስክሬን ከኹለት ቀን በላይ ሳይነሳ መንገድ ላይ ወድቆ መታየቱን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

"በቦታው የወደቁትን አስከሬኖች፤ አንዳንድ ሰዎች ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኹሉንም እያነሱ ማሪያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በአካባቢ ቀብረዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰኞ ድረስ ያልተቀበሩም ነበሩ።" ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

በከተማው ለሦስት ቀናት በተደረገው ውጊያ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም፤ የትራንሰፖርት እና የሰው እንቅስቃሴ ባለመኖሩ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚወስዳቸው ጠፍቶ ሕይወታቸው ያለፉ ብዙዎች መሆናቸውንም ሐኪሟ ገልጸዋል።

የደብረማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አንዷለም ገረመው፤ ከአርብ ነሐሴ 19 እስከ ሰኞ ነሐሴ 22/2015 ድረስ 25 ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን በመጥቀስ፤ "ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ "በተኩስ ልውውጡ ቆስለው ወደ ሆስፒታል የገቡትና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች እድሜያቸው ከ17 እስከ 50 ዓመት የሆናቸውና ሰዎች ናቸው።" ካሉ በኋላ፤ በሆስፒታሉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ጠቁመዋል።

ዘገባው የአዲስ መለዳ ነው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዐበይት ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄዱ ግጭቶች በትንሹ 183 ሰዎች እንደተገደሉ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ከግጭቱ መቀስቀስና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ወዲህ የክልሉ ኹኔታ "በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል" ያለው ኮሚሽኑ፣ አዋጁን ተከትሎ የአማራ ብሄር ተወላጆች የሚበዙባቸው በፋኖ ደጋፊነት የተጠረጠሩ ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ታስረዋል ብሏል። ኮሚሽኑ፣ መንግሥት "የጅምላ እስር እንዲያቆም"፣ "በዘፈቀደ ያሠራቸውን እንዲፈታ"፣ የእስረኛ ማቆያ ቦታዎችን ለተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ክፍት እንዲያደርግም ጠይቋል።

2፤ የሳዑዲ ዓረቢያ ድንበር ጠባቂዎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መግደላቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ቀደም ብለው ያውቁ እንደነበር ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። አሜሪካ በግድያው ዙሪያ ዝምታን የመረጠችው፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር የተበላሸባትን ግንኙነት ለማደስና ሳዑዲ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድትጀምር ለማግባባት ስትል እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ግድያውን በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2022 ዓ፣ም አጋማሽ ከተመድ ባለሥልጣናት እንደሰሙ የጠቀሰው ዘገባው፣ የፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስዊድንና አውሮፓ ኅብረት ባለሥልጣናትም ያውቁ ነበር ብሏል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግድያውን እንደሰማን የሳዑዲ ባለሥልጣናትን በጉዳዩ ላይ አነጋግረናል ማለታቸውን ዘገባው ገልጧል።
ዋዜማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአቡሽ ዘለቀ አልበም በአዲስ አበባ እንደይሸጥ መከልከሉን አርቲስቱ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አሳወቀ።

የሚከተለው የአቡሽ ዘለቀ መልዕክት ነው 👇

"ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ! በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ።"

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዜና፡ ለሁለት ቀናት #በካይሮ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ተጠናቀቀ፤ ውይይቱ በቀጣይ ወር በአዲስ አበባ ይቀጥላል ተብሏል

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ነሃሴ 21 እና 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግብጽ ካይሮ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር መጠናቀቁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድነ መሪ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በማህበራዊ ሚዲያ ትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አሰታወቁ።

አምባሳደር ስለሺ በመልዕክታቸው በኢትዮጵያ፤ ግብጽና ሱዳን መካከል ስናደርግ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሁለት ቀናት የሶስትዮሽ የመጀመሪያ ሙሌት (ግድቡ በጥቂት አመታት ሙሉ ደረጃ እስኪደርስ) እና ውሃ አለቃቀቅ ድርድር ተጠናቋል ብለዋል፡፡

በበርካታ የስምምነት አንቀጾች ላይ ስምምነት ለመድረስ ውይይቱ በመስከረም ወር በአዲስ አበባ እንደሚቀጥል የጠቆሙት አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ወገን ውሃውን በቀጣይ ፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀምን በሚያረጋግጥ መልኩ እና በቀጣናው ትብብር እንዲጎለብት በሚያስችል መንገድ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 22፤ 2015 በነበረው የችሎት ውሎ ከቀድሞው የክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር በአንድ መዝገብ ከተከሰሱ ግለሰቦች መካከል 16 ተከሳሾችን በነጻ ማሰናበቱን የአቶ አብዲ ጠበቃ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የአቶ አብዲን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት፤ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ጉዳያቸው በችሎቱ እየታየ ካሉት 42 ተከሳሾች ውስጥ 26 የሚሆኑት በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል፤ የሶማሌ ክልልን ለስምንት ዓመት ያስተዳደሩት አቶ አብዲ መሐመድ ይገኙበታል። “አብዲ ኢሌ” በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዲከላከሉ የተበየነባቸው፤ “የጦር መሳሪያ ይዞ በማመጽ፣ ወይም የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀልን” ፈጽመዋል በሚል በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ዋና ክስ መሆኑን ጠበቃቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11927/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በጅግጅጋ ከተማ የ12 ዓመት ታዳጊን በቡድን አስገድደው በመድፈር ግድያ በመፈፀም የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጅግጅጋ ከተማ የ12 ዓመት ታዳጊ ላይ አስገድዶ መድፈር እና ግድያ በመፈፀም የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች የ12 አመት ታዳጊን በመድፈር እና በመግደል ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በተደረገው ምርመራም ታዳጊዋን መድፈራቸውንና መግደላቸውን ማመናቸውን ነው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው።

የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አብዲ አሊ በደረሰው አሰቃቂ ሁኔታ የተሰማቸውን ልባዊ ሃዘን የገለፁ ሲሆን ለሟች ቤተሰቦች እና ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ኮሚሽነሩ በመልእክታቸው ወንጀል ሰርቶ ማንም ሰው ከህግ ማምለጥ እንደማይቻል የጠቆሙ ሲሆን በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ጉዳይ በህግ ሂደት የሚታይ ይሆናል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን በመሆን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ላደረገው መረባረብ ያመሰገኑት ኮሚሽን ጀነራሉ ይህን አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ሀዘንን ሆን ብለው ባልተገባ መንገድ በመጠምዘዝና ተጠርጣሪዎቹ "የአንድ ብሄር ተወላጅ ናቸው" በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች ህብረተሰቡን ወደ አለመረጋጋት የሚያስገቡና ለግጭት የሚገፋፉ መረጃዎችን እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ይሁንና ህብረተሰቡ መረጃዎችን ከትክክለኛ የመንግስት አካላት እንጂ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መረጃን ከሚለቁ እና ውዥንብር ከሚፈጥሩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲርቅ ያሳሰቡ ሲሆን ፖሊስ በአንዲህ አይነት ተግባር ላይ በሚሳተፍ የትኛውም አካል ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድም ነው ያስጠነቀቁት።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እናመሰግናለን 🙏
የክቡር ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ ቤተሰቦች በፈረንሳይ ለጋሲዮን ነዋሪ ለወ/ሮ ትሁኔ እሸቱና ለአቶ ያደሣ ፈቃዱ 15 ቤተሰቦችን የፈራረሰ መኖሪያ ቤት ደረጃውን የጠበቀ የአድሳት ግንባታ አጠናቀው በዛሬው እለት አስረክበዋል እናመሰግናለን🙏
ነቢዩ ሲራክ-ነሐሴ 21/2015

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ለበዓለ ሲመት ሽመልስና አወል አርባ ፈገግ ሲሉ አዲሱ የአማር ክልል ፕሬዘዳንት የተሸበሩ ይመስላል
ሰላም ለሀገራችን 🙏

Читать полностью…
Subscribe to a channel