muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

ሁለት ቤተሰቦችን ያጨቃጨቀዉ ከሞት ተነሳ የተባለዉ ታዳጊ ጉዳይ እልባት ማግኘቱ ፖሊስ አስታወቀ

በስልጤ ሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከአራት አመት በፊት ሞቶ ተቀብሯል የተባለዉ ታዳጊ ባቂ ሲከማ መሀመድን ከመንገድ ላይ ያገኙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ለቤተሰቡ አስረክበዋል።

የታዳጊዉ ቤተሰቦችም ሟች ልጃቸዉ ባቂ ስለመሆኑ አንዳችም የሚያጠራጥር ነገር እንደሌለዉ አረጋግጠዉ ተደስተው ፈጣሪ ከሞተ በኋላ አስነስቶ ህያዉ አድርጎታል ሲሉ ታዳጊዉን ተቀብለዉ እንደወትሮዉ መንከባከብ መጀመራቸዉ ተነግሮ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ታዳጊ ጋር ሁለንተናዊ መመሳሰል ያለዉ አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ይሰጠን ሲሉ የመጡ ሲሆን በሁለቱ ቤተሰቦች መሀከል የይገባኛል ጥያቄ መነሳቱም ቀደም ሲል ተገልጿል።

አሁን የሁለቱ ቤተሰቦች የይገባኛል ክርክር መቋጫ ማግኘቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ ፣ዐቃቤህግና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ባደረጉት ማጣራት አብዲ ሄራቶ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች መሆኑ የሚያሳይ በእጅና በእግሩ የተነገሩ ልዩ ምልክቶችን መኖራቸዉ በማረጋገጥ ታዳጊዉ ጠፍቶብናል ለሚሉ ቤተሰቦች ተላልፎ መሰጠቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

ስለዚህ ከአራት አመት በፊት ሞቶ የተቀበረዉ ታዳጊ ከሞት አለመነሳቱ ህብረተሰቡ እንዲያዉቀዉ ሲል ፖሊስ አሳስቧል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት አገር ዓቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ጠየቀ

በኢትዮጵያ ግጭቶች የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባህል በመኖሩ ነው ያለው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት፤ አሁናዊ ቀውሶችን ለመፍታት አገር ዓቀፍ የሰላም መድረክ ሊመቻች ይገባል ሲል ጠይቋል።

ትናንት ጳጉሜ 1/2015 ህብረቱ 35 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሳተፉበት የፓናል ዉይይት ያካሄደ ሲሆን፤ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሌሎችም ቦታዎች ያሉ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የተገባደደው ዓመት ጥቅል ገጽታዎች መሆናቸውን አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዋና ዳይሬክተር ዳን ይርጋ በኹሉም የአገሪቱ ክፍሎች ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የሕግ የበላይነት አለመከበር አንጻር እጅግ አስቸጋሪ ዓመት መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለውም፤ እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ኹሉንም የማህበረሰብ አካላት የሚያሳትፍ አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ተመቻችቶ የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ እንዲሁም የረጅም ጊዜ ግጭትን የመከላከል፣ የመፍታት እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የሚጠናከሩበት አገራዊ ፍኖተ ካርታ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ነው የገለጹት።

"እንደ ሰብዓዊ መብት ተቋም ከሚመለከታቸው አካላት ትብብር ካለማግኘት ጀምሮ ሠራተኞቻችን ለእስር የተዳረጉበት እና ቢሯችን የተሰበረበት እንዲሁም ዛቻና ማስፈራሪያዎችን የተጋፈጥንበት ዓመት ነበር።" ሲሉም ተናግረዋል።

የስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሰረት አሊ በበኩላቸው፤ የግጭት ተሳታፊዎች፣ መንግሥት፣ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ሴቶች እንዲሁም ወጣቶች እኩል ተሳታፊ የሚሆኑበት መድረክ ማዘጋጀት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አዲስ ማለዳ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሳዛኝ ዜና !
ከሁለት ሳምንታት ፍለጋ በኋላ ፖሊስ የዮሐንስ ኪዳኔን አስክሬን በሳንፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ውሀ ላይ ተንሳፎ ማግኘቱን አስታውቋል😭😭😭😭
*******************************************************
ማክሰኞ ነሐሴ 29/2023 ቀን ከሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ ላይ በውሃ ውስጥ ምላሽ የማይሰጥ ሰው መታየቱን ጥቆማ ለመርማሪዎች ከደረሳቸው በኋላ አስክሬኑን ከውሀ ውስጥ ያወጡት ሲሆን የአስከሬን ምርመራው ውጤት አስከሬኑ የዮሐንስ ኪዳኔ መሆኑን አረጋግጧል።

የሞቱን መንስኤ ራስን ማጥፋት መሆኑን የማሪን ካውንቲ የሸሪፍ ጽህፈት ቤት ዛሬ ያስታወቀ ሲሆን የ22 አመቱ ወጣት የከባድ ጉልበት ጉዳት እና ውሀ ውስጥ መስጠም ለህይወቱ ማለፍ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ዮሐንስ በቅርቡ ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ ተመርቆ በታዋቂው ኔትፍሌክስ የሶፍትዌር ኢንጂነርነት ተቀጥሮ ለመስራት ከመጥፋቱ ሁለት ሳምንት በፊት ከኒውዮርክ መሄዱ ይታወቃል። ስልኮቹ እና የኪስ ቦርሳው ጎልደን ጌት ድልድይ አካባቢ ከጠፋ በኋላ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ለመጨረሻ ግዜ የታየው ከሁለት ሳምንታት በፊት በኡበር ታክሲ ሲሳፈር ነው።

በትልቅ ተስፋ እና ፅናት ሲያፈላልጉት ለነበሩት ቤተሰቦቹ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሸራተን አዲስ የሬማን ኮንሰርት መሰረዙን አስታወቀ።
በምትኩ ዝነኛ የአፍሮ ቢት ድምፃዊ እና ዲጄ ከ አፍሪካ ሀገራት እንንደሚያስመጣ አስታውቋል ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"አብዮት ልጆችዋን ትበላለች ያለው ማን ነበር?እናንተየ ምንአይነት ክፉ ጊዜ ነው የደረስነው? አባት እንዴት በልጁ ይጨክናል? ህወሓት ኪዳነ አመነ እስር ቤት አስገብተዋለች።
የባይቶና ፓርቲ መስራች ነው። በጦርነቱ ከህወሓት ጋር ተግሎአል።
ከአምስት ፓርቲዎች ጋር በመሆን የተቃውሞ ሰልፍ ጳጉሜ 2 ጠራ።

ህወሓት ተደናግጣ እያሰረች ነው። ወያኔ ህዝብ ጠልቷታል። ሰላማዊ ሰልፉ ከተፈቀደ ህዝብ ተገልብጦ ሊበላት ነዋ‼

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀ

ስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅ
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድርጅታችን ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ ስፖንሰር አጋር የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የስፓንሰርሺፕ አጋርነታችንን የሰረዝን መሆኑንና የፕሮግራሙ አጋር አለመሆናችንን እናሳውቃለን።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አማ (ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲስ ዜና ለሜትር ታክሲ አሽክርካሪዎች! ዋን ራይድ
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ልዩ አማራጭ ይዞ መጣላቸሁ!
ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር  በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት  አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽሎ  በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በተጨማሪ በአካል ለመመዝገብ   ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ  ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉስ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930858687/0944161718/0955161718/0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ  ትስስር ድረ ገጾቻችንን  ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onepassenger
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ደቡብ አፍሪካ ህዝብ ጭቅጭቅ ይዟለል። ወጣቱ ይጠይቃል...

ይህቺ ደቡብ አፍሪካዊት የማሜሌንዶ ሰንዳውንስ ተጫዋች የፊት ገፅታዋ ቁርጥ ሮናልዲንሆ ጎቾን ይመስላል::

አንዳንዶች "የDNA test ሁላ አያስፈልግም  የሱ ልጅ ናት" ይላሉ::🙂

ወጣቱ አሁንም ይጠይቃል😋... "ሮናልዲንሆ ሆይ; ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አሻራህ አርፏል ወይ?"😜

የልጅቷ እድሜ ይጣራ እንጂ 2009 ለኮንፌዴሬሺን ሮናልዲንሆ ደበቡ አፍሪካ ነበረ።

አስሉና ድረሱበት

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአፈ-ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ምሥጋና ክፍሌ አረፉ

የወ/ሮ ምሥጋና ክፍሌ አጭር የሕይወት ታሪክ

ወ/ሮ ምሥጋና ክፍሌ በሐምሌ ወር 1978 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ ከአባታቸው አቶ ክፍሌ ወ/ኢየሱስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘብይደሩ ዱሬሳ ተወለደች፡፡

ለቤተሰቧ አራተኛ ልጅ የሆነችው የያኔዋ ህፃን ምሥጋና የልጅነት እና ታዳጊነት ዕድሜዋን በNazareth School የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በመከታተል አሳልፋለች፡፡

በዚሁ የጨቅላነት ዕድሜዋ በዙሪያዋ ባሉ የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ብሎም በአብሮ አደጎቿ እና ቤተሰቧ መካከል በመልካም ሥነ- ምግባር የተመሰከረላትና ‘የልጅ አዋቂ’ ያስባላት በሳል ማንነት ገና ከማለዳው የተላበሰችው መለያዋ ነበር፡፡

በቀለም ትምህርቷ ከፊት ቀዳሚዎቹ ተርታ ትሰለፍ የነበረችው ምሥጋና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ባማረ ውጤት ታጅባ በማጠናቀቅና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በመሸጋገር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዋን፤ እንዲሁም በ public policy የሁለተኛ ዲግሪዋንም ከዚሁ ተቋም አግኝታለች፡፡

በትምህርቱ ዓለም የቀሰመችውንና በከፍተኛ ውጤት በመታጀብ ያጠናቀቀችውን ትምህርት ሀገሯንና ህዝቧን ወደምታገለግልበት ደረጃ መሸጋገር በብዙ ድርጅቶች ተፈላጊ ቢያደርጋትም ስትመርጥ መምረጥ የምታውቅበት በሳሏ ምሥጋና ለማህበረሰቡ ይበልጥ ልትጠቅም የምትችልባቸውን ድርጅቶች በመምረጥ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በፍጹም ትጋትና መሰጠት ሀገሯን አገልግላለች፡፡

ከነዚህም ውስጥ Advocates Africa, Christian Fellowship, World Vision Ethiopia, እና Irish Aid ከዋነኞቹ ተርታ የሚሰለፉት ናቸው::
Via Ethio News

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከሞት ተነሳ ስለተባለው ልጅ ከፖሊስ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ
#FastMereja
በሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከወትሮው በተለየ መልኩ የተሰማውን ነገር ለማጣራት እስከ ስፍራው የገባን ሲሆን አሁን የሚገኝበት ቤተሰብ ከአራት አመት በፊት ባቂ ሲከማ መሀመድ የተባለ ልጃቸው እንደሞተና በትላንትናው ዕለት መንገድ ላይ ሰው አንስቶ እንዳመጣላቸው ይናገራሉ።

በሌላ በኩል በሁሉም ነገሩ ተመሳሳይ የሆነ አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ የጠፋባቸው ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ሲሉ መጥተዋል።

ልጁ የመስማትም የመናገርም ችግር ያለበት በመሆኑ ነገሩን ያንዛዛው ቢሆንም የሁለቱ ቤተሰቦች በተገኙበት አስፈላጊው ሁሉ ውይይትና ምርመራ የሚደረግ ሲሆን የማይተማመኑ ከሆነም በህጋዊ መንገድ የDNA ምርመራ እንደሚደረግ የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

በመጨረሻም ፖሊስ ባስተላለፈው መልዕክት እስከዚያው ያልተጣሩ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ መልቀቁ አስፈላጊ ስላልሆነ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን ብሏል።

ልጁን ለማየት በርካታ ሰዎች በሞተር፣ በባጃጅ ወደ ቤተሰቡ እየጎረፉ እንደነበር ለፋስት መረጃ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ608 በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊያ 'በከባድ አውሎ ንፋስ ውስጥ አርፏል' የተባለው ስህተት ነው አለ።

አየር መንገዱ ይህን ያለው የአገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን የአየር መንገዱ የመንገደኞች አውሮፕላን ከባንግኮክ ተነስቶ በሆንግ ኮንግ በከባድ አውሎ ንፋስ ውስጥ ያረፈው ብቸኛ አውሮፕላን ነው በሚል ዘገባ ካወጡ በኋላ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጓዙ !

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬው ዕለት ለሐዋርያዊ ጉዞ ወደ ሰሜን አሜሪካ አቅንተዋል።

የቅዱስነታቸው የክብር አሸኛኘትም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክና በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፓርት ተደርጓል ፡፡

ቅዱስነታቸው ባሳለፍነው ዓመት በሰሜን አሜሪካ ተመሳሳይ ሐዋርያዊ ጉዞ ማከናወናቸው የሚታወስ ነው፡፡

© የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አየር መንገድ ትልቁ መርህ ጥንቃቄ ነው። ጀብደኝነት አያስሞግስም። የብዙዎችን ህይወት በእጁ ያለ አካል በሰው ህይወት አይቆምርም። ሌሎቹ ያልደፈሩትን መድፈር ጀግና አያሰኝም። የአየር መንገዳችን ከአደጋ ነፃ የመሆን ሪከርድ ጥንቃቄ ያስገኘው ነው። የፋና ዜና በአለማቀፍ አቬይሺን መርህ ውርደትን ማቆለጳጰስ ነው‼

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#መረጃ ኢቢሲ በተቋሙ ሰራተኞች ላይ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የ400 ሰራተኞቹ ሰነድ ፎርጂድ/ሀሰተኛ መሆኑን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

ይህ ሆኖ እያለ የተቋሙ ሀላፊዎች እርምጃ እንዳይወሰድ ይህን መረጃው እንደደበቁ፣ በጥቆማ አቅራቢዎች ላይም ዛቻ እና ማስፈራርያ እያደረሱ እንደኮነ ይህ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለጠቅላይ አቃቤ ህግ የፃፈው ደብዳቤ ያሳያል።
Via Elias meseret

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲስ ዜና ለሜትር ታክሲ አሽክርካሪዎች! ዋን ራይድ
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ልዩ አማራጭ ይዞ መጣላቸሁ!
ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በተጨማሪ በአካል ለመመዝገብ ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉስ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930858687/0944161718/0955161718/0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onepassenger
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አቶ ደመቀ መኮንን ሞቃዲሾ ገ
***


በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመጀመሪያው የኢትዮ-ሶማሊያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ላይ ለመሳተፍ የሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ ኤደን አዴ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳላህ አህመድ ጃማ እና በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ አቀባበል እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እሳት በሐረር 😢

በሐረር ከተማ ሸዋ በር አካባቢ በተለምዶ “ታይዋን”ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሌሊት 10 ሰዓት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አካባቢው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ እና ለብዙ ነዋሪዎች የገቢ ምንጭ ሆኖ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በእሳት አደጋው በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

መንግስት በአፋጣኝ የአደጋውን መንስኤ እና የደረሰውን የጉዳት መጠን በማጥናት ይፋ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡

በአካባቢው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከሕብረተሰቡ ጋር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡

የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት መጠን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ለነገ በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ትግራይ የሚገኙ የተቋዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ታስረዋል‼️

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለአዲስ ዓመት ባለ10 ነጥብ የሰላም ጥሪ አቀረቡ። የሰላም ጥሪውን ሙሉ ዝርዝር ይመልከቱ...

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ ሊደረጉ ከታቀዱ የምክክር መድረኮች ውስጥ አራቱ በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይካሄዱ መቅረታቸው ተገለጸ

በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ 50 ገደማ ከተሞች የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮችን በተመለከተ ግብዓት ሲያሰባስብ የቆየው የባለሙያዎች ቡድን፤ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት አራት የምክክር መድረኮችን ሳያካሄድ መቅረቱን አስታወቀ። የባለሙያዎች ቡድኑ ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነዱን በመጪው ዓመት ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ለማጠናቀቅ ማቀዱንም ገልጿል።

በአዳማ ከተማ የተጀመረው የምክክር መድረክ፤ 46 ከተሞችን አካልሎ በነሐሴ ወር መጀመሪያ በአዲግራት ከተማ በተካሄደ ውይይት መጠናቀቁን የባለሙያዎች ቡድኑ ዛሬ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ቡድኑ በአጠቃላይ ሊያካሄዳቸው አቅዷቸው የነበሩ የምክክር መድረኮች ብዛት 59 ቢሆኑም፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት አራት ያህሉን መሰረዙን የባለሙያዎች ቡድን አባል የሆኑት ዶ/ር ማርሸት ታደሰ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።

የባለሙያዎች ቡድኑ በዚህ ምክንያት ምክክር ማድረግ ያልቻለባቸው ከተሞች በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት ደምቢ ዶሎ እና ያቤሎ እንዲሁም በአማራ ክልል በሚገኙት ሰቆጣ እና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውን ዶ/ር ማርሸት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቀዋል። የባለሙያዎች ቡድኑ ከእነዚህ ከተሞች በተጨማሪ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች “የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው” ወልቃይት እና ሁመራ ከተሞች ሊያካሄድ አቅዶት የነበረውን ምክክርም ሳያከናውን ቀርቷል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11957/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !

#Ethiopia | እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !

ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!

ኩኩ ሰብስቤ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአርቲስት ሰላም ተስፋዬ መልዕክት

"እግዚአብሔር ሁሌም መሀሪ፣ ይቅርባይ፣ አዛኝ ነው። እሱን አምናቹ መቼም እንደማታፍሩ እኔ ምስክር ነኝ።
በዚህ ሰዓት በምንም ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላቹ። እኔ እርግጠኛ ሆኜ ምነግራቹ ሁሉንም ነገራቹ እሱ ላይ በእምነት ጣሉ አያሳፍራቹም።
ይሄን ነገር post ያረኩበት ምክንያት
- አንደኛ እግዚአቢሄር ይሄ ምስክርነት ስለሚገባው ነው።
- ሁለተኛ ሰው እሚያልፈበትን አናውቅም እና እርስ በርሳችን መልካም እንሁን።
- ሌላ ደሞ ሁሌ ምቾቴን፣ ደስታየን ብቻ ማሳየት ስለማልፈልግ እና ለብዙ ሰው ትምህርት ሊሆን ይችላል በሚል ነው ።
ከፈጣሪ ውጭ ማንምላይ እምነት አታድርጉ።
ይሄ የተፈጠረው ከ3 ወር በፊት ነው።
ለመመስከር ያበቃኝ እግዚአቢሄር የተመሰገነ ይሁን!"

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ጠየቀች።
******************************************************
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለውን ግለሰብ እና በተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ በላከችው ደብዳቤ ጠይቃለች።

በላከችው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ፣ በሃይማኖት አባቶቿ ፣ በምዕመናኗ እና የአምልኮ ቦታዎቿን ባንቋሸሹ እንዲሁም የሐሰተኛ ንግግር ባስተላለፉት በነፓስተር ዮናታን አክሊሉ ፣ በነቢይ ኢዩ ጩፋ ፣ በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን እና በክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን ላይ አቤቱታ አቅርባ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ሳለች ይህ እንደገጠማት ነው የገለጸችው።

በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለው ብላለች።

የተከሳሹ ድርጊት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን መልካም ስም የሚያጎድፍ ድርጊት በመሆኑ ፤ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ሰዎችን ለአመጽ እና ብጥብጥ የሚያነሳሳ በመሆኑ ፤ የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ያራከሰ በመሆኑ ፤ የምዕመናኑን ስሜት የሚነካ ፣ በሚያዋርድ እና ቤተክርስቲያንን በሚያናንቅ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑ በግለሰቡ እና በተባባሪዎቹም ላይ ጭምር ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሠርት ለአቃቤ ሕግም እንዲልክ ጠይቃለች።

ምንጭ ፦ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አቶ መኩሪያ መርሻዬ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት አቶ መኩሪያ መርሻዬን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አድርጎ ሾመ።

2ኛ ዙር 8 ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬ እለት በማካሄድ ላይ ያለው የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የሐዋሳ ከተማ አስተደር ከንቲባ ሆነው እንዲያገለግሉ በእጩነት የቀረቡትን አቶ መኩሪያ መርሻዬን ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ካንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ መኩሪያ መርሻዬ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ የፈፀሙ ሲሆን አዳዲስና ነባር የካቢኔ አባላትን ማቅረባቸው የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ዘግባል።

ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አዲስ ዜና ለሜትር ታክሲ አሽክርካሪዎች! ዋን ራይድ
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ልዩ አማራጭ ይዞ መጣላቸሁ!
ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በተጨማሪ በአካል ለመመዝገብ ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉስ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930858687/0944161718/0955161718/0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onepassenger
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሰበር
የውጪ ጣልቃ ገብነት እስከሌለ ድረስ ከፋኖ ጋር መንግስት ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን እንደተናገረ የሰራተኛ ማህበራት ፌዴሬሽን ሀላፊ ከጠቅላዩ ጋ ባደረጉት ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ለሪፖርተር ገለፁ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢሰመኮ የምክርቤት አባላትን ጨምሮ በአዋሽ አርባ የታሰሩ 53 ሰዎችን መጎብኘቱንገለፀ።
********
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የምዕራብ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የምክር ቤት አባላትና ጋዜጠኞችን ጨምሮ 53 ሰዎችን በትናንትናው እለት መጎብኘቱን ገልጿል።

ኢሰመኮ በሪፖርቱ "ታሳሪዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤ እንዲሁም ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤ እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ፤ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ/መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡" ብሏል።

ታሳሪዎቹ ወደ አዋሽ አርባ መውሰድ ያስፈለገበት ምክንያት በአዲስ አበባ ያለው የፌደራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ በመጣበቡ በመሆኑን ፖሊስ እንዳስረዳው የገለፀው የኢሰመኮ ሪፖርት ፖሊስ ታሳሪዎቹ አያያዝ ሰብአዊ መብትን ያከበረ መሆኑን፣ ህክምና እንደሚያገኙ ማደረጉን እና ቤተሰባቸውን እንዲያገኙ እንደሚያመቻች መግለጹን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ገልጿል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ግለሰቦች የትኛውንም ብሔርና ተቋም ባይወክሉም
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እምነት ተቋማትን ፣የሃይማኖት አባቶችን፣ ብሔርን መሠረት ያደረገ የጥላቻ ንግግሮች በሶሻል ሚዲያ ላይ እና በቲክቶክ ላይ መመልከታችን ግልጽ ነው።

ቀሲስ ታጋይ ታዷለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ

ይህ ከባድ ወንጀል ከመሆን አልፎም ሕዝብ ከሕዝብ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር የሚያጋጭ ተግባር ከመሆኑ አንጻር በአስቸኳይ እርምት ሊሰጠው እና በሕግ ሊጠየቁም ይገባል እላለሁ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አበው ይህንን ግልጽ የወጣን ድፍረት መልክ ማስያዝ ይገባልም እላለሁ::

ባለፉት ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በመግባት ከእምነቷ ውጭ የሆነ መዝሙር የዘመረችን ወጣት ልጅ በኋላም ባለማወቅ ለሰራችው ድፍረት ከልብ የሆነ ይቅርታን የጠየቀችውን እና ይቅርታም የተደረገላትን እህት መነሻ በማድረግ ሰሞኑን ደግሞ ለጊዜው ስድቡን መድገም የማልፈልገው "ልጅ ያሬድ" የተባለ ኮሜዲ በድፍረት ለተናገረው ስድብና ነውር በሕግ ሊጠየቅና ማን እንደላከውና በሀገሪቱ ብጥብጥና ሁከት ለመፍጠር ግጭት ቀስቃሽ ንግግሩ በሕግ ቁጥጥር ሥር ሊውልና ሊጠየቅ ይገባል።

ከዚህ ውጭ ምእመናን በፍጹም ጨዋነት የትኛውንም ብሔር እና ሀይማኖት በመጥቀስ መሰዳደብ የለብንም የተፈለገው አብሮነታችንን በመሸርሸር ወደ ጥላቻ እና ግጭት እንድንገባ በመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ። እኛ ሃይማኖተኞች በመሆናችን የሕግና የፍትህ መንገድ መከተል ይጠበቅብናል ።

ቀሲስ ታጋይ ታዷለ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

1. ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ወልዴ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

2. ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ ገ/መስቀል የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላ

3. ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ ገዳሙ የአብክመ ማረሚያ ቤቶች አገ/ኮሚሽን ኮሚሽነ

4. ዶ.ር እሸቱ የሱፍ አየለ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

5. ደጀኔ ልመንህ በዛብህ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

6. በሪሁን መንግሥቱ ከበደ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

7. ዳኛው በለጠ ጎኔ የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላ

8. ገደቤ ኃይሉ በላይ የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ

9.  ኮሚሽነር ውበቱ አለነ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ

10. ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ

11. ም/ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሎጀስቲክስ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኦሮሚኛ ድምፃዊ ጫላ ቡልቱሜ የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት ገለፀ
#FastMereja
የኦሮሚኛ ድምፃዊ ጫላ ቡልቱሜ ትናንት ምሽት ነሃሴ 25/2015 ዓም በአዲስ አበባ ቦሌ ቀነኒሳ ሆቴል በተደራጁ ሰዎች ግድያ ሙከራ ማምለጡን ገለፀ። በዚህ አመት ብቻ ከ15 ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት አርቲስቱ ገልፇል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel