በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ባለፈዉ ዕሁድ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰዉ ተገደለ፤ ቆሰለ፤ በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ። ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጅቡቲ በሚወስደዉ አዉራ መንገድ ዳር በምትገኘዉ «አዉራ ጎዳና» ተብላ በምትጠራዉ ከተማና አካባቢዋ በሐብትና በቦታ ይገባኛል ሰበብ የጊዜዉ ግጭት ይነሳል። ባለፈዉ ዕሁድ የተቀሰቀሰዉ ግን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከሚነሳዉ ግጭት የከፋና በከባድ መሳሪያ የታገዘ ዉጊያ እንደነበር የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።ለጠቡ መነሻ ነዋሪዎቹ የሚሰጡት አስተያየት እንዳሉበት አካባቢና እንደየጎሳቸዉ የሚቃረን ነዉ።አንዳዶቹ ነዋሪዎች ግጭቱ የተነሳዉ የፋኖ ታጣቂዎች «በአካባቢዉ የሠፈረዉን የኦሮሚያ ፖሊስ በማጥቃታቸዉ ነዉ» ይላሉ።ሌሎች ግን ባካባቢዉ የፋኖ ታጣቂ አለመኖሩን አስታዉቀዋል።ቀደም ሲል አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከአካባቢዉ ሲለቅ ሠራዊቱን ተክቶ አካባቢዉን የሚቆጣጠረዉ የኦሮሚያ ፖሊስ ነዉ።ግጭቱ የተደረገዉም «ባካባቢዉ አርሶ አደርና በኦሮሚያ ፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ነዉ» ባዮች ናቸዉ።
አስተያየት ሰጪዎቹ በግጭቱ መነሻና በተዋጊዎቹ ማንነት ላይ ልዩነት ቢኖራቸዉም በግጭቱ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ወደ መተሐራና ወለንጪቱ ከተማ መወሰዳቸዉን አስታዉቀዋል።በግጭቱ ከ2 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ መፈናቀሉ፣ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሐብትና ንብረት መዉደሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዳግም ባካባቢዉ በመስፈሩ ግጭቱ መብረዱንም ነዋሪዎቹ አስታዉቀዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ የኦሮሚያና የአማራ ክልል የወረዳና የዞን መስተዳድር ባለስልጣናትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም።
በጀርመን ሽቱትጋርድ ከተማ በኤርትራውያን የባሕል ፌስቲቫል፤ ኤርትራውያኑ እርስበእርስና ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ አምባጓሮ 26 ፖሊሶችን ጨምሮ በአስራዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ ሲል የጀርመን ድምፅ የሆነው ዶይቼ ቬለ ነው የዘገበው።
Читать полностью…🌼እንኳን አደረሳችሁ 🌼
👉በአዲሱ አመትየቤት ህልምዎት ይሳካል
በልዩ የአዲስ አመት ቅናሽ መንደር ይግዙ !
👉ኒው ሆፕ ሪል እስቴት (ኒው ሆፕ መንደር)
እጅግ ዘምኖ የሚያዘምን ቅንጡ መንደር
👉ለመኖሪያ ምቹ በሆነው ጀርመን አዳባባይ 80% የደረሱ አፓርትመንቶችን
በማይታመን ዋጋ ሽያጭ ላይ ነን
በካሬ 96500 ብር
ባለ ሁለት መኝታ 146.6 ካሬ
ባለ ሶስት መኝታ 164.5 ካሬ
ቅድሚያ ክፍያ 25%
* 5000m2 Green Area
* የመዋኛ ገንዳ
* የመሮጫ ትራክ
* ቢዝነስ ላውንጅ
* ቤተ_መፅሀፍት
* የልጆች ማቆያ...እና ሌሎችን ያካተተ ዘመናዊ መንደር
ለበለጠ መረጃ 📞 09 47 02 22 22
Telegram /channel/msilmarketing
የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ አደረገ! ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግም ተገልፇል።
Читать полностью…በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ውስጥ በጉዞ ላይ በነበሩ ዜጎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች እንደተገደሉ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ግድያውን በተመለከተ የዞኑ አስተዳደር የፀጥታ ቢሮ "ድርጊቱ የተፈፀመው ዲቾ ላይ ነው" ያለ ሲሆን ከአንገር ጉተን ወደ ጊዳ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃቱ ተፈፅሟል" ሲል ገልጿል። የፀጥታ ቢሮው አክሎ ድርጊቱን የፈፀሙት "የአማራ ፅንፈኛ ታጣቂዎች" ናቸው ብሏል።
ቢሮው አክሎም "በአካባቢው ጸጥታውን የሚያውኩ ታጣቂዎች አሉ። ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪ የሚጓዙ ሰዎችን በመንገድ ላይ በማስቆም ነው ድርጊቱን የፈፀሙት" ሲል ገልጿል።
በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለጊዳ አያና ሆስፒታል፣ ለወረዳው አስተዳደር ሀላፊ፣ ለወረዳው የፀጥታ ሀላፊ እንዲሁም ለኮሚኒኬሽን ቢሮ ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በስልክ ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።
የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዘገባ "ሀሰት ነው" በማለት አሳዛኝ ምላሽ ሰጥቷል። ስንት ሰው ሲሞት ነው "ብዙ" የሚባለው? የአንድ ዜጋ ህይወትም እኮ ዋጋ አለው።
እንዲህ አይነት አፀያፊ ወንጀል የሚፈፅሙ ወንጀለኞችን ሁላችንም ማውገዝ አለብን፣ ለሞቱት ወገኖቻችን ነፍስ ይማር።
Via BBC Afaan Oromoo & Tikvah
#Update ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በፍቼ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የኮንዶሚኒየም ሳይት ውስጥ በብዛት ታስረው ስለሚገኙ ሰዎች ትናንት ያቀረብኩት መረጃን ተከትሎ ትክክለኛውን ቦታ ብጠቅሰው ማጣራት እንደሚደረግ ከአንድ የፌደራል የመንግስት የስራ ሀላፊ እንዲሁም ከአንዳንድ ሚድያዎች እና አንድ ሌላ የሰብአዊ መብት ክትትል አድራጊ ድርጅት ጥያዌ ቀርቧል፣ መረጃው የተሳሳተ እንደሆነ የገመተ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚም ሊኖር ይችላል።
እናም ምናልባት መፍትሄ ከሆነ እና በመረጃው ዙርያ ግልፅነት እንዲኖር በሚል ቦታውን ለሁሉም ልጠቁም:
📍ቦታው ከአዲስ አበባ ወደ 112 ኪ/ሜ ገደማ በምትርቀው ፍቼ ከተማ ውስጥ አብዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው በምስሉ ላይ የሚታየው ኮንዶሚኒየም ነው። ኮንዶሚኒየሙን ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ይጠቀምበት እንደነበር የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
መረጃው ከማስረጃው ጋር ይህን ይመስላል።
ከዚህም አውጥተው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው "መረጃው የሀሰት ነው" እንደማይባል ተስፋ እያደረግኩ መልካሙን ሁሉ ታስረው ለሚገኙ ወገኖች እና የደረሱበትን እንኳን ሳያውቁ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንመኝ።
መልካም ቀን።
ኤሊያስ መሰረት የፃፈው 👆
አቶ ጎሹ እንዳላማው ወንድምአገኝ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።
የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዙር ምርጫ ፣11ኛ ዓመት፣ 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤው አቶ ጎሹ እንዳላማው ወንድምአገኝን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል።
አቶ ጎሹ እንዳላማው በወረዳና በክልል በባለሙያነትና በተቋም ዳይሬክተርነት፣ እንዲሁም በዞንና በክልል አመራርነት አገልግለዋል።
በትምህርት ዝግጅታቸውም በክልልና አካባቢ ልማት ጥናት የማስተርስ ዲግሪ እንዳላቸው ተገልጿል።
አዲሱ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባደረጉት ንግግር፤ ሕዝባችን ከገጠመው የሰላም እጦትና ቀውስ ለማውጣት በሰከነ ውይይትና ንግግር ለሰላም ተባብረን እንሠራለን ብለዋል።
በውቢቷ ከተማ ባሕር ዳር ሰላመዊ እንቅስቃሴ እንዲረጋገጥ በትጋት እንደሚሠሩም ነው የተናገሩት።
ባሕር ዳር ከተማ ተፈጥሮ ያደላትን ጸጋ በመጠቀም ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የነዋሪዎቿን ምቾትና ፍላጎት ለማሟላት እንሠራለን ነው ያሉት።
ኅብረተሰቡ የሚያነሳቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎች ፣ ዜጎችን የሚያማርሩ የመልካም አሥተዳደርና የልማት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶች ተጋግዞ ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠሩም አስገንዝበዋል።
በተፈጠረው ወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ችግር ዜጎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል። በአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ልዩነት ያለው አይኖርም ያሉት አቶ ጎሹ፤ ልዩነቱ የሚኖረው በመፍቻ መንገዱ ላይ ነው ይላሉ።
ከተማዋ ከገጠመው የሰላም አለመረጋጋት ወደ አስተማማኝ ሰለሟ እንድትመለስ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
ዜናው የአሚኮ ነው 👆
በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በፍቼ ከተማ ታስረው የሚገኙ ዜጎች!
የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እዝ ከሁለት ቀን በፊት ባወጣው መግለጫ በኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ሸዋ ሮቢት እና አዋሽ አርባ ባሉ ማቆያዎች ተይዘው ካሉ 764 ሰዎች ውጭ ሌላ "ማገቻ ካምፕ" እንደሌለው ገልፆ ነበር።
በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ከእነዚህ አምስት በስም ከተጠቀሱ ቦታዎች ውጪ በሸገር ከተማ አስተዳደር ስር እንዲሁም እንደ ፍቼ ባሉ አንዳንድ በኦሮሚያ ክልል ስር ባሉ ከተሞች ጭምር ተይዘው የሚገኙ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ።
በተለይ በፍቼ ከተማ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተይዘው የሚገኙት በአንድ ስሙን እንዳልጠቅሰው በተነገረኝ ሰፊ የኮንዶሚኒየም ሳይት ነው።
ቲክቫህ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን አናግሮ ዛሬ በሰራው አንድ ዘገባው እንዳረጋገጠውም በኦሮሚያ ክልል፣ በሸገር ከተማ፣ በማቆያና በፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች እንዳሉ ጠቅሷል።
እኔም የሚደርሱኝ ተደጋጋሚ ጥቆማዎች በገላን እና ቡራዩ ሰዎች ታስረውባቸው የሚገኙ ቦታዎች እንዳሉ፣ ከእነዚህም ውስጥ በርካቶች በኮሌራ ወረርሽኝ እንደተጠቁ እና የሰው ህይወት ጭምር እንዳለፈ ነው።
እውነታው ይኸው ነው።
Elias Meseret የዘገበው ነው 👆
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ‼️
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በአማራ ክልል ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በክልሉ በተቋቋሙት አራት ኮማንድ ፖስቶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ማዕከላት ላይ በተለያዩ ጊዜያት በአካል በመንቀሳቀስ በህግ ጥላ ሥር ስላሉ ተጠርጣሪዎች (እስረኞች) ሁኔታ ምልከታና ምርመራ አድርጓል።
ምልከታና ምርመራ ባደረገበት ወቅት ያያቸውን ጠቅላላ ሁኔታዎች ትናንት ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።
የመግለጫውም ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም
በ2015 ዓ/ም የነበረው የኢኮኖሚ ዘርፉ እውነታ:
- በ2015 መጀመርያ ላይ ከ5- 6 ሺህ ብር ሲሸጥ የነበረ ጤፍ አሁን ላይ እስከ 16 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው (ሶስት እጥፍ ገደማ)፣ ይህ የዋጋ ግሽበት በሌሎች ምግብ ነክ ምርቶች ላይም በስፋት ይታያል።
- ለአመታት በሁለት ዲጂት ሲቆጠር የቆየው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ባሳለፍነው አመት ወደ 5.3 ፐርሰንት ወርዷል።
- የፊስካል ልዩነቱ ከአመታዊ የምርት መጠን ጋር ሲነፃፀር በ4.2 ፐርሰንት ሰፍቷል፣ ይህም በአነስተኛ ሀገራዊ የገቢ መጠን እና በከፍተኛ የመከላከያ ወጪ የመጣ ነበር።
- የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለ1 ወር ብቻ ግብይቶችን መፈፀም ወደሚያስችልበት ደረጃ ወርዷል።
- የቱሪዝም ዘርፉ በነበሩ አለመረጋፋቶች እጅጉን የተጎዳ ሲሆን አንዳንድ የቱሪስት መስህ ስፍራዎች እንኳን ቱሪስት ሊቀበሉ የጦርነት ቀጠና ሆነው ቆይተዋል።
- የኢንደስትሪ ዘርፉ ለግብአት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎችን ለመግዛት የውጭ ምንዛሬ በማጣት crippled እየሆነ ይገኛል፣ አንዳንድ የውጭ ኩባንያዎች በራቸውን ዘግተው ሰራተኞቻቸውን አሰናብተዋል።
- ባለፈው አመት በኩታ ገጠም የስንዴ እርሻ በርካታ ምርት እንደተገኘ በመንግስት ተገልጿል፣ ይህ መልካም እምርታ ቢሆንም አሁንም እስከ 20.2 ሚልዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ ስለዚህ እነዚህ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የምርት ሂደት ይጠበቃል።
ሌላም፣ ሌላም... ስለዚህ ስለ ኢኮኖሚ ዘርፉ ስኬት ሲነገር ፈታኝ የሆኑ እነዚህ ጉዳዮችም መፍትሄ ይሻሉ እንጂ ሁሉም ነገር ላይ rosy picture በማቅረብ ማለፉ ጠቃሚ አይመስለኝም።
Source https://www.afdb.org/en/countries/east-africa/ethiopia
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማትና አሸናፊዎች።
1) በመምህርነት ዘርፍ፦ አዝማች ይርጋ ገብሬ፣
2) መንግስታዊ የስራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ፦ ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው፣
3) በንግድ ኢንዱስትሪና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ፦ ኩሪፍቱ ሪዞርት፣
4) በስዕል ኪነ ጥበብ ዘርፍ፦ ሰዓሊ ወርቁ ጎሹ፣
5) በበጎ አድራጎት ዘርፍ፦ እቴነሽ ወንድምአገኘሁ
6) በባህል፣ ቅርስ እና ቱሪዝም ዘርፍ፦ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣
7) በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ ፦ ጋዜጠኛ ኤፍሬም እንዳለ
8) በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ፦ ዶ/ር ሙሉዓለም ገሰሰ
9) በውጭ አገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘርፍ ፦ ዶ/ር አሰፋ ጀጃው
10) በልዩ ተሸላሚ ዘርፍ ፦ አቶ ከተማ ይፍሩ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
#Satellite2 የሚፈጀው 1 ትሪሊየን ብርም ሆነ አሁን ላይ አስፈላጊነቱ የብዙዎች መወያያ ርዕስ የሆነው "ጫካ ፕሮጀክት" ከሳተላይት ይህንን ይመስላል።
የሳተላይት ምስሉ እንደሚያሳየው የግንባታ ስፍራው 276,000 ገደማ ካሬ ላይ ያርፋል። በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ለሚደረጉ ድርጅቶች ተጨማሪ ቦታ ይሰጣል፣ እንዲሁም የሁለተኛ ዙር ማስፋፍያ ፕሮጀክት እንዲኖረው ጥናት በቅርቡ ይጀመራል።
ይህ ፕሮጀክት በተለይ በአሁን ወቅት አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ?
የኤሊያስ መሰረት መረጃ ነው ☝
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ባለማሳየቱ ከዚህ ቀደም የተላለፈው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ወስኛለሁ አሉ።
ፕሬዝዳንቱ ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት መስከረም 7/2014 ዓ.ም. በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ ጥሰቶችን ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።
በኢትዮጵያ ....የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ 2014 2015 & 2016
መስከረም 2014.....4000 ብር
መስከረም 2015......6500 ብር
መስከረም 2016......13,000 ብር።
የአማራ ክልል ሸዋ፣ ጎጃምና ጎንደር በግጭት ውስጥ ስላሉ
በ2017 የአንድ ኩንታል ስንት ሊሆን ነው?
የመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ አልጨመረም። የኑሮ ውድነቱ አላፈናፍን ብሏል።
መቼ ይሆን ሰላምና ፍቅር ነግሶ እንደሌሎች ሀገሮች እፎይ የምንለው?
#አሳዛኝ_ዜና_እረፍት 😭
ልብ ይሰብራል
ሆሳዕና እጅግ በጣም ጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ናት።
ዛሬ ከሆሣዕና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ለይ ቡኢ ከተማ በደረሰው ግጭት አሰቃቂ የመኪና አደጋ አገልጋይ ዮናስ ዱባለ የሆሳዕና እናት የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ የሆነው አብረውት ከነበሩት 2 ጓደኞቹ ጋር ህይወታቸውን አጥተዋል።
እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቡ፣ ለቤተክርስቲያን ምእመን፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ሕይወት አለፈ
=======#=======
ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ቅዳሜ መስከረም 5/2016 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 ላይ ከጉንዶ መስቀል ከተማ ወደ ቱቲ 53 በሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 (75263 ኦሮ) የሆነ ቅጥቅጥ የሕዝብ ማመላሻ ተሽከርካሪ፤ ባጋጠመዉ የመገልበጥ አደጋ የ15 ሰዎች ሕይወት ወዲያዉኑ ማለፉ ተሰምቷል።
በአደጋዉ ሕይወታቸዉን ያጡት 8 ወንዶች እና 7 ሴቶች ሲሆኑ፤ ሌሎች 4 ሰዎች በእጅግ ከባድ የተባለ ጉዳት ደርሶባቸው በጳዉሎስ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሚገኙ የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኢንስፔክተር ባዩሳ ደበላ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የአደጋዉ መንስኤ የተሽከርካሪዉ የቴክኒክ ብቃት ማነስ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
በተጨማሪም በ30 ሰዎች ላይ 18 ሴት እና 12 ወንዶች ከባድ የተባለ ጉዳት እንዲሁም በኹለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ነዉ የተባለዉ።
ተሽከርካሪዉ ዳገት በመዉጣት በነበረበት ወቅት ወደ ኋላ በመመለሱ አደጋዉ ማጋጠሙን የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል። በአደጋዉ አሽከርካሪዉ እና ረዳቱ ወዲያዉኑ ሕይወታቸዉ ማለፉንም አክለዋል።
በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሌሎች 30 ሰዎች በፍቼ እና ጉንዶመስቀል ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የደራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ባዩሳ ደበላ ጨምረዉ ተናግረዋል።
/channel/addismaleda
ትናንት ምሽት በሶማሊላንድና በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የምትገኘዋ ወጃሌ ከተማ ታይዋን በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ወደመ። የበርካቶች ሱቅ በእሳት እንዲህ ሆኗል 👇
Читать полностью…በአዲስ ዓመት አዲስ ዜና አዲስ ብስራት ለሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች!🌼
🌻 ዋን ራይድ🌻
በልዩነት የቀረበ የብዙዎችን ችግር ለመፍታት ብዙ ልዩ አማራጭ ይዞ እነሆ መጣላችሁ መጣልን!
🚘 ዋን ራይድ ማይሌን ጨረስኩ ብሎ መጨነቅን የሚያስቀር በወር አንዴ በሞሉት ጥቅል ያለገደብ መሥራት የሚችሉበት::
🚘 ተገልጋዮች በጋራ እንዲጓዙ (የጋራ ጉዞ) በማድረግ ደንበኞዎትን አስደስተው የተጨማሪ ገቢ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ይዞ መምጣቱን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው
በአካል ለመመዝገብ ደንበል ቦሌ ጋዜቦ አደባባይ ለቤንዝ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ከአቧሬ አደባባይ ጃምቦ ሪል ስቴት 5 ፎቅ አልያም ሃያ ሁለት ከአክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንጻ 1ኛ ፎቅ መጥተው በንጉሥ መስተንግዶ ተስተናግደው ይመለሳሉ፡፡ መረጃዎቾን ለመላክ በቴሌግራም: /channel/OneR9744
☎️ ለበለጠ መረጃ
📞0930858687
📞0944161718
📞0955161718
📞0966161718 ላይ ይደውሉ፡፡
የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/rideinone
Instagram: https://www.instagram.com/rideinone
Telegram Group: http://t.me/rideinone
መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!
𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.onerideet.onedriver
ዋን ራይድ
በአንድ ይጓዙ!!
ከጳጉሜን አስጎብኚና የጉዞ ወኪል አ.ማ
የኢሰመኮ ሪፖርት አገዛዙ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈጸሙን [crime against humanity] አረጋግጧል።
የኢሰመኮ መግለጫ ያረጋገጣቸው እውነቶች ፦
ከአማራ ክልል ውጪ ምክንያታቸው ያልታወቀ ማጎሪያ መኖሩን፣
በእነዚህ ማጎሪያዎች የጅምላ አፈሳ መፈጸሙን፣
በአፈሳው ታስረው የሚንገላቱ ንጹሀን መኖራቸው፣
በማጎሪያዎቹ መነሻው ያልታወቀ ወረሽኝ መከሰቱ፣
በወረሸኙ የሞቱ መኖራቸው፤ ተረጋግጧል።
ክትትል እየተደረገ ነው ፤ በወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች አሉ ብላለች ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማቸው (በኢሰመኮ የሰሜንና ማዕከላዊ ሪጅን የክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር)
🌼እንኳን አደረሳችሁ 🌼
👉በአዲሱ አመትየቤት ህልምዎት ይሳካል
በልዩ የአዲስ አመት ቅናሽ መንደር ይግዙ !
👉ኒው ሆፕ ሪል እስቴት (ኒው ሆፕ መንደር)
እጅግ ዘምኖ የሚያዘምን ቅንጡ መንደር
👉ለመኖሪያ ምቹ በሆነው ጀርመን አዳባባይ 80% የደረሱ አፓርትመንቶችን
በማይታመን ዋጋ ሽያጭ ላይ ነን
በካሬ 96500 ብር
ባለ ሁለት መኝታ 146.6 ካሬ
ባለ ሶስት መኝታ 164.5 ካሬ
ቅድሚያ ክፍያ 25%
* 5000m2 Green Area
* የመዋኛ ገንዳ
* የመሮጫ ትራክ
* ቢዝነስ ላውንጅ
* ቤተ_መፅሀፍት
* የልጆች ማቆያ...እና ሌሎችን ያካተተ ዘመናዊ መንደር
ለበለጠ መረጃ 📞 09 47 02 22 22
Telegram /channel/msilmarketing
የቅበት ከተማ ተፈናቃዮች ሮሮ
ከሥልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተፈናቅለው በእምነት ቦታዎች ተጠልለው የሚገኙ ከአንድ ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ላይ እንደሚገኙ ገለፁ ፡፡ተፈናቃቹ አካባቢያቸውን ለቀው ከወጡ በኋላ በተለይ ህጻናትና ሀረጋዊያን ለከፋ እንግልትና ሥቃይ መዳረጋቸውን ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል ፡፡የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በበኩሉ በዞኑ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ከሀገር ሽማግሌዎችና ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጋር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ያምሆኖ «አንዳንድ የክርስትና አባቶችና ተቋማት «ሃላፊነት የጎደላቸው ፣ በፍረጃ የተሞሉና ሁከት ቀስቃሽ የሆኑ» ያሏቸውን መግለጫዎችን ከማውጣት እንዲታቀቡ ሲል ያሳሰበው ምክር ቤቱ መንግሥት በየትኛውም እምነት ውስጥ የተሸሸጉ አጥፊዎችን በመለየት ህግ የማስከበር ሚናውን እንዲወጣም መጠየቃቸውን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ከሀዋሳ ዘግቧል።
ሰበር
ከባድ የመሬት ምንቀጥቀጥ ኤርትራ እና ትግራይ አከባቢ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ደርሶአል። የደረሰው የጉዳት መጠን አልታወቀም።
ቀጣይ ዜናዎችን እናጋራለን
የትግራይ ደቡባዊ ዞን ከፍተኛ አመራር በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።
ከፍተኛ አመራሩ አቶ ሳምሶን ተፈሪ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት መስከረም 1/2016 ዓ.ም ምሽት 3:30 መሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ጠቅሰዋል።
አቶ ሳምሶን ተፈሪ ከጥቅምት 21 / 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመታት የማይጨው ከተማ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል።
በተተኮሰባቸው ጥይት በሞት እስከተለዩበት ቀንና ሰአት ድረስ ደግሞ የትግራይ ደቡባዊ ዞን የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉት አቶ ሳምሶን ፤ ቀደም ሲል በክልሉ የተለያዩ የመንግስት የስራ እርከኖች መስራታቸው የምንጮቻችን መረጃ ያስረዳል ።
አቶ ሳምሶን ተፈሪ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ይህንን ዘገባ እስከተጠናቀረበት ግዜ ድረስ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።
በትግራይ ከተሞች ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እንደሚታይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሚመለከታቸው አካላት ጠቅሶ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
በሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 300 የሚጠጉ ሰዎች ሕይዎት አለፈ
በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ296 ሰዎች በላይ ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
6 ነጥብ 8 የሚለካው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ካደረሰው የሰው ሕይዎት መጥፋት ባሻገር እስካሁን 153 ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም ሕንፃዎች ፈርሰዋል፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የቴሌፎን ኔትዎርክ ለ10 ደቂቃዎች መጥፋቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት፥ ታዋቁ የቱሪስት መዳረሻ የሆነችውና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበችው ማራካሽ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባታል፡፡
ከማራካሽ ከተማ በስተደቡብ የሚገኙ አካባቢዎችም የጉዳቱ ሰለባ እንደሆኑም ተገልጿል።
ከትግራይ ክልል በቀን በአማካኝ ከ3 ሺሕ በላይ ወጣቶች ከክልሉ እንደሚወጡ ተጠቆመ
በትግራይ ክልል አሁን ባለው የክልሉ የጸጥታ ችግር እና የኑሮ ውድነት ምክንያት፤ በቀን በአማካኝ ከ3 ሺሕ በላይ ወጣቶች በስደት መልክ ከክልሉ እንደሚወጡ የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
የቀድሞው የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ አታክልቲ ኃይለሥላሴ፤ "ከሦስት ቀን በፊት ከአንዳንድ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ከሚያሰባስቡ ባለሙያዎች ባገኘሁት መረጃ፤ በቀን በአማካኝ ከ3 ሺሕ በላይ ወጣቶች ከክልሉ በስደት መልክ ወደ መሃል አገር፣ አረብ አገር በመሰደድ የደላላ መጫዎቻ እየሆኑ ነው።" ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቋቋመ ወዲህ የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱንም ነው የጠቀሱት።
"ወጣቶች ከክልሉ የሚወጡት፤ አሁን ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባለመቻሉ ነው።" ሲሉም ገልጸው፤ "አስተዳደሩ የክልሉን ሠላምና ጸጥታ እንዲያስከብር፣ የመንግሥትንና የግል ተቋማቶችን መልሶ በማቋቋም ሥራ እንዲያስጀምር ኃላፊነት ቢጣልበትም፣ ምንም ዓይነት ሥራ እየሰራ አይደለም።" ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
የክልሉ ነዋሪዎች በሰላም የመኖር መብታቸው ተነፍጓል ያሉት የቀድሞው ከንቲባ፣ "የሰብዓዊ ድጋፍ ማግኘት እንዳይችሉ በማድረግ ከተለያዩ ረጂ ድርጅቶች የመጣውን እርዳታ ከተራበ አፍ ላይ ቀምተው ለግል ጥቅማቸው አውለዋል፣ በዚህም ብዙ ሰዎች ለረሃብ፣ ለበሽታ እና ለሞት ተጋልጠዋል።" ብለዋል።
አክለውም፣ "የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እየሰራ ያለው ቴሌቪዥን ላይ ብቻ ነው።" ካሉ በኋላ፤ "በክልሉ ከዞን በታች ያሉ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ከዚህ በፊት የነበሩት የሕወሓት አመራሮች ናቸው።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አዲስ ማለዳ