በትግራይ ክልል በ27 ወረዳዎች አስከፊ ድርቅ መከሰቱ ተገለጸ
በትግራይ ክልል በሦስት ዞኖች በሚገኙ 27 ወረዳዎች እና ከ180 በላይ በሚሆኑ ቀበሌዎች ድርቅ መከሰቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚካኤለ ብሩክ፤ "በክልሉ በሦሰት ዞኖች በሚገኙ 27 ወረዳዎች እንዲሁም ከ180 በላይ ወረዳዎች ላይ አስከፊ ድርቅ በመከሰቱ ሰብሎች እየወደሙ ነው።" ብለዋል፡፡
"በክልሉ ምስራቃዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡባዊ አካባቢዎች በተያዘው የክረምት ወቅት ዝናብ ባለመዝነቡ ተዘርቶ የነበረ ሰብል በመውደሙ እና በርካታ ሄክታር መሬት ሳይዘራ በመቅረቱ አርሶአደሮች ችግር ላይ ወድቀዋል።" ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
ለአብነትም በምስራቃዊ የትግራይ ዞን ጨርጨር፣ ጸኣዳ አምባ፣ ጽራአወምበርታ እና ሌሎች አካባቢዎች ከ4 ሺሕ 400 ሄክታር መሬት በላይ ሰብል ወድሟል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በድርቅ ከተጠቁ ከ180 በላይ ቀበሌዎች ውስጥ ምንም ዓይነት ዘር ያልተዘራባቸው መኖራቸውን ጠቅሰው፤ "በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ጤፍ፣ ማሽላ እና ባቄላ ተዘርቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሁሉም ሰብል ወድሟል።" ነው ያሉት።
"በክልሉ በአጠቃላይ ምን ያክል ሄክታር መሬት እንደወደመ ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው።" ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "በድርቁ አማካኝነት ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶአደሮች በቀላል ዝናብ እና በአጭር ጊዜ ሊደረሱ የሚችሉ እንደ ሽንብራ፣ ገብስና የመሳሰሉ አዝረቶችን እየዘሩ ነው።" ብለዋል።
አክለውም፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የቤት እንስሳት መሞታቸውን ጠቁመው፤ በሕይወት ያሉትንም የተሻለ የዝናብ መጠን ወዳለባቸው አካባቢዎች የማሸሽ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ ማለዳ
በረታ ብረት የተጫነች ተሸከርካሪ ተያዘች
በመስከረም 14 2016 በደቡብ ምስራቅ ከየጭላ ወደ መቀሌ ከተማ ስትጓዝ የነበረችው አይሱዚ መኪና ከ 50 ኩንታል በላይ ያልተተኮሰ ወደ 120 የመድፍ ተተኳሽ የመኪና ባትሪም ጨምሮ ሌሎች ብረታብረት የጫነች በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውላለች ።
ምንጭ መሶቦ ትግርኛ
ሁለት ዜናዎች
1፤
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ በአስተዳደራዊ "ውስጣዊ ድክመት" ሳቢያ አሽቆልቁሏል ብሏል። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመኾኑን ገልጦ፣ የትግራይ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበት እንደሚገኝም ገልጧል። ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በቅርበት ስለመስራትና ተጨማሪ ፖለቲካዊ ውይይት በማድረግ አስፈላጊነት ዙሪያ ውይይት ማድረጉንም ጠቅሷል። በሰላማዊ ትግል፣ በፓርቲው ውስጣዊ ድክመትና በቀጣይ የፓርቲውና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይ ፕሮግራሞች ላይ ጭምር መወያየቱን ፓርቲው አመልክቷል።
2፤
ዕሁድ'ለት በጎንደር ከተማ በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ሚሊሻዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች እንደተገደሉ ወይም እንደቆሰሉ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ነዋሪዎች ቆስለው ሆስፒታል የገቡ ሰዎችን ወታደሮች ወዳልታወቀ ሥፍራ እንደወሰዷቸው መናገራቸውን የዘገበው ደሞ ቢቢሲ አማርኛ ነው። የፋኖ ታጣቂዎች ከከተማዋ ኹለት ፖሊስ ጣቢያዎች አባሎቻቸውን ጨምሮ "በመቶዎች የሚቆጠሩ" እስረኞችን አስፈትተናል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ትናንት እንደተቋረጠ መኾኑንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዝግ መኾናቸውን ዘገባው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ዋዜማ
ልጃቸውን ለሀገር ሰጥተው ማልቀሻ ቤት የሌላቸው እናት!
እኚህ እናት ከሦስት ወር በፊት የላስቲክ ቤታቸው በአፍራሽ ግብረሀይል ፈረሰባቸው፣ ልጃቸው ደግሞ ከሁለት አመት በፊት በነበረው ጦርነት ወቅት ወደ ውትድርና ገብቶ ተሰውቷል።
ታድያ እኚህ እናት አሁን የልጃቸውን ማለፍ ሰሙ፣ የአንድ ልጃቸውን ሞት ሲሰሙ ግን የሚያለቅሱበት ቤት እንኳን አልነበራቸውም። ደጋግ የፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ሰዎች ወረዳ 1 ጨፌ የሚባል አካባቢ ገነተ ማርያም እድር አጥር ግቢ ውስጥ ወስደዋቸው እዚያ ለቅሶ ተቀምጠዋል።
ልጃቸውን ለሀገር ሠጥተው ማልቀሻ እንኳን የሌላቸው እናት እኚህ ናቸው።
የቻላችሁ ሄዳችሁ እኚህን እናት ብታፅናኑ እንዲሁም የቻልነውን ያህል ርብርብ አርገን በቀጥታ በራሳቸው አካውንት እንዲረዱ የሚያውቋቸውን ሰዎች የባንክ ቁጥራቸውን እጠይቃለሁ።
ይህን እንደመስማት እና እንደማየት ዘግናኝ ነገር ይኖር ይሆን?
የልጃቸው ስም እና ፎቶ ቢኖረኝም የቤተሰብ ፈቃድ ስላልጠየቅኩ አላቀረብኩትም።
መልካም ምሽት።
Elias Meseret ያጋራው መልዕክት ነው።
ኸረ በቃችሁ በለን 😭 ያ ረቢ 🙏
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ
የፓርቲያችን ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ ትላንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው፡፡ በምን ምክንያት እንደተያዙም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ይህን መሰል ህግ እና ሥርዓት ያልተከተለ እርምጃም በፅኑ የምናወግዘው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ፓርቲያችን ጉዳዩን በጥንቃቄ እና በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ ለአባላት እና ደጋፊዎች እያሳወቀ የፓርቲያችን ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ኮሚቴ አቋቁሟል፤ እያንዳንዱን ሂደትም እየተከታተለ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
እናት ልጃቸውን ተከትለው ሄዱ ፤ ስቃያቸው አበቃ ። አረፉ
*********************************************
የዛሬ 3 ወር ገደማ ሶደሬ አካባቢ በሸኔ አባላት ታግቶ የተገደለው ሠዓሊ ሙሉጌታ ገ/ኪዳን እናት በመረረ ሀዘን ሲሰቃዩ ኖረው ትናንት አረፉ ። የቀብር ስነስርዓታቸው ዛሬ ከ5:00 - 6:00 ሰዓት ካራ ቆሬ መድሀኒዓለም ይፈጸማል ። በሠዓሊው ጓደኞች " አደዬ " እየተባሉ የሚጠሩት እናት ጓደኞቹን ባገኙ ቁጥር በእንባ እየታጠቡ " እኔስ መቼ ነው ልጄን የምከተለው ? ጥራኝ ልጄ " ሲሉ ይሰማሉ ። ሊጠይቋቸው የሚሄዱ ጓደኞቹ በሙሉ እስቸውን ማየት ሲያሳቅቃቸው ኖሯል ።
እናታችን ነፍስዎን ይማርልን ። አምላክ መላው ቤተሰቡን ያጽናናልን ።
🌻ለ2016 አ.ም እንኳን አደረሣችሁ እያልን ላለፉት 26 አመታት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማራው አንጋፍው ጃንቦ ሪልሥቴት በመሀል ከተማ ገርጂ ኢፔሬያል ሽያጭ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል 🌻
ይፍጠኑ ለመሥቀል ያወጣነው ቅናሽ ጥቂት ቀናቶች ነው የቀሩት እሥከ 500,000 birr ያትርፉ !!!
👌 ቅድመ ክፍያ = 20%
👌 ከ 90ካሬ - 314 ካሬ
👌2 መኝታ ቤት = 90ካሬ
91ካሬ
131ካሬ
👌3 መኝታ ቤት = 154ካሬ
153ካሬ
👌4 መኝታ ቤት (ፔንትሀውሥ)
231ካሬ
314ካሬ
👌የንግድ ሡቆችን ጨምሮ
👌የማሥረከቢያ ጊዜ = 2 አመት
👌 ቦታ የሚገኘዉ = ቦሌ ገቢዎች አካባቢ ወይም ኢቢኤሥ ሥቲድዮ አጠገብ & ግሎሪ ት/ቤት አጠገብ .
call = 0920401667
= 0977191398
telegram link= t.me/ selamconsultant
telegram username= selamssa
Email= selamesayas870@gmail.com
🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼
🌼የአዲስ አመት ብስራት ለቤት ፈለጊዎች
ከፓልም ሪል እስቴት
💧በመሀል ገርጂ እና ብስራተገብርኤል በመጠናቀቅ ላይ እና ግንባታ ላይ ያሉ
እጅግ ውብ አፓርትመንቶችን በቅናሽ ዋጋ
ሽያጭ ላይ ነን !
👉50/50 እስከ 20አመት የረጅምጊዜ አከፋፈል የተመቻቸላቸው
👉ቅድሚያ ክፍያ ከ 25% ጀምሮ
👉አሁኑኑ የኢንቨስመንት ተጠቃሚ ይሁኑ
ሳይታችን ይጎብኙ !
📞 09 47 02 22 22 ይደውሉ
ቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ
/channel/msilmarketing
የልዑል አለማየሁ የፀጉር ዘለላና፣ ከመቅደላ ተዘርፎ የተወሰደ ታቦት እና የተለያዩ የኢትዮጵያ ቅርሶች ለኢትዮጵያ ተመላሽ ተደረጉ።
©ቢቢሲ አማርኛ
🌻🌻🌻ዳግም በማስታወ ዋጋ ተመልሰናል!
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
🌻 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ አድርገናል። ከ CDC በ2. ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ
65,395 ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር
📍 የቅድመ ክፍያ ቅናሸ ከ30%-----100% ለሚከፍሉ ደንበኞች (በካሬ ከ87,00ብር-----73ሺ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(እስከ 25% የሚያተረፉበት )
የማስታወቂያ ዋጋውን ተጠቅመው ከ1,000,000 እስከ 3,897,000 ብር ያትርፉ!!!
🌻ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
ሊያመልጠዎ የማይገባ ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ የተንጣለለ መንደር በሠፊ የካሬ አማራጭ
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)15%=760ሺብር
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 122,132,140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 150,164,170&175 ባለ ሶስት መኝታ
ደስታዎ እዚህ ይጀምራል!!!
ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
DMC Real Estate- Joy Starts Here!
ለበለጠ መረጃ
🌻🌻🌻+251906217873
🌻🌻 🌻+251918642895 /channel/Engineergashaw
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአማርኛ ቋንቋ መሰጠት መጀመሩ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያ፣ ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡
ተማሪዎቹ በበኩላቸው አማርኛ ቋንቋ ከማወቅ በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ህዝቡን እና የኢትዮጵያን ባህል ማየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪ የአፍሪካ ቋንቋዎችን የመማር ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
ከአማርኛ በተጨማሪ በአፍሪካ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለው የስዋሂሊ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
#Update "ልጃቸውን ለሀገር ሰጥተው ማልቀሻ ቤት የሌላቸው እናት" የሚል አንድ መረጃ ከትናንት በስቲያ አጋርቼ ነበር።
እኚህ እናት በትናንትናው እለት ማረፊያ እንዲሆናቸው አንድ አነስተኛ የቀበሌ ቤት በወረዳ 1 አስተዳደር ተሰጥቷቸዋል፣ ሌላ የተሻለ ቤት ሲገኝ ወደፊት እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ችያለሁ።
ወ/ሮ አለሚቱ በቅርቡ የላስቲክ ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ አሁን ደግሞ የወታደር ልጃቸውን ማረፍ ሰምተው በፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ሰዎች ትብብር ወረዳ 1 ጨፌ የሚባል አካባቢ ገነተ ማርያም እድር አጥር ግቢ ውስጥ ለቅሶ ተቀምጠው እንደነበር መረጃ አቅርቤ ነበር።
የወረዳው አስተዳደር ላደረገው ፈጣን ድጋፍ የላቀ ምስጋና ይድረሳቸው።
እኚህ እናትን በቻልነው ሁላችንም እንደግፋቸው፣ ለማስጀመርያ እኔ 5,000 ብር አበረክታለሁ።
አለሚቱ ዱሜሳ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1000360017226
በስልክ ለማግኘት: 0938045370
ኤሊያስ መሰረት የፃፈው 👆
ADVERTISMENT
👬 ልዩ ጥቆማ‼️‼️
አዲስ አበባ ከተማ ላይ ምን መግዛት ይፈልጋሉ????
👉መኖርያ ቤት፣ ንግድ፣ ቤት
👉 እናም የተለያዩ ህንፃወች ሆቴል አፓርታማ ኮንዶሚኒየም ባዶ ቦታ፣ የፈለጉት ሁሉም ከእኛ ከልዩ ቃና የቤት ጭያጭና ኪራይ የኮሚሽን ስራ ጋር አለ
👍‼️ ያለምንም~ ድካም~ ገንዘቦ ን ~ወደ ~ንብረት !
ንብረቶን ~ወደ ~ገንዘብ ~ይቀይሩ !!
👍👉 ከስር ያለውን ሊንክ Join በማድረግ
👉 በቴሌግራም ቻናላችን ሁሉንም ይመልከቱ Join👇👇👇
/channel/Joni9971
/channel/Joni9971
/channel/Joni9971
ልዩ ቃና የቤት ጭያጭና ኪራይ የኮሚሽን ስራ
🌻🌻🌻
🌻🌻🌻 25% የበዓል ቅናሽ(4ቤት ለገዛ 1 ቤት በነጻ)!!!
👉መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
🌻 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ አድርገናል!!
📍 የቅድመ ክፍያ ቅናሸ ከ30%-----100% ለሚከፍሉ ደንበኞች (በካሬ ከ87,00ብር-----73ሺ) ለውስን ቤቶች ብቻ‼️(እስከ 25% የሚያተረፉበት )
የማስታወቂያ ዋጋውን ተጠቅመው ከ1,000,000 እስከ 4,000,000 ብር ያትርፉ!!!
🌻ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
ለኢንቨስትመንት ወይም ለመኖሪያዎ የተንጣለለ መንደር በሠፊ የካሬ አማራጭ
▶ 55.5 ካሬ ስቱዲዮ(studio)15%=760ሺብር
▶ 76.2 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶ 122,132,140.&144 ባለ ሁለት መኝታ
▶ 150,164,170&175 ባለ ሶስት መኝታ
181 ካሬ ባለ 4 መኝታ
ደስታዎ እዚህ ይጀምራል!!!
ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
DMC Real Estate- Joy Starts Here!
ለበለጠ መረጃ
🌻🌻🌻+251906217873
🌻🌻 🌻+251918642895 /channel/Engineergashaw
ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 1:05 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዪ ቦታዉ ሀጫሉ ጎዳና እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትራኮን ሪል እስቴት እየገነባ ባለዉ አፓርታማ 6ኛ ፎቅ ላይ የተነሳዉን እሳት ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነዉ።
እሳቱ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልበት ዕድል ማስቀረት ተችሏል። በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም ሲሉ አቶ ንጋቱ ማሞ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ለፋስት መረጃ ገልፇል።
መንግስት የሚመጣው በዓልን እንደ ስጋት ያየው ይመስላል። የሚከተለውን ውሳኔ ኣልፏል 👇
ለሞተር ብስክሌተኞች፣ ለባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ
በአዲስ አበባ የምትገኙ የሞተር ብስክሌተኞች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29/2016ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌትን፣ የባለ አራት እግርና የባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል፡፡
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው እየገለፀ፤ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው ያሳስባል፡፡
ለ25 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ሊሰጥ ነው
👉እስከ አሁን ለሦስት ሚሊዮን ዜጎች ተሰጥቷል
በ2016 ዓመተ ምህረት ማብቂያ ለ25 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ መርሐ ግብር አስታወቀ። እስከ አሁን ለሦስት ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ እንደተሰጠም ተገልጿል።
የብሔራዊ መታወቂያ መርሐ ግብር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መርሐ ግብሩ በ2014 ዓመተ ምህረት ምዝገባ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች ከ125 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ መሰጠት ተችሏል። በ2015 ማብቂያ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጥምረት በተሠሩ ሥራዎች ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ማድረግ ተችሏል።
(ኢ ፕ ድ)
መጣ መጣ ፓልም ሪል እስቴት መጥቷል
በወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ግሩፕ እና በባህራን ትሬድንግ እንታወቃለን
መሀል ብስራተ ገብርኤል ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ አጠገብ እና ገርጂ ቶቶት አጠገብ በመጠናቀቅ ላይ እና ግንባታ ላይ ያሉ እጅግ ውብ አፓርትመንቶች በማይታመን ዋጋ ሽያጭ ላይ ነን
አፓርትመንቶቻችን ዘመኑን የዋጁ ከመሆናቸው ባሻገር
እንደፍላጎትዎ ሁነው የተሰሩ ናቸው::
50/50 የረጅም ጊዜ የአከፋፈል ተመቻችቷል
አሁኑኑ 25% ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል የግልዎ ያድርጓቸው፡፡
ለበለጠ መረጃ ለሳይት ጉብኝት ይደውሉ
09 47 02 22 22
ቴሌግራማችንን ይጎብኙ
/channel/msilmarketing
ሼኹ የአባን ቤት አደሱላቸው
"ሸህ ሰኢድ መሀመድ" ቦሌ ቡልቡላ መንገድ ያለው የጃዕፋር መስጂድ ዋና አስተዳዳሪ ናቸው።
ምን አደረጉ መሠላችሁ………ቤታቸው ፈርሶ ዝናብና ጎርፍ እየገባ መተኛ እና መቀመጫ ያጡትን የአባን እቤት በጃዕፋር መስጂድ የሚሰግዱትን ሰዎች (ጀመዐ) በማስተባበር 33.000 ብር ወጪ በማድረግ ቤታቸውን አድሰው ፍራሽና ብርድልብስ ገዝተው እንዲህ ባማረ ሁኔታ ቀሪ እድሜያቸውን በሠላም እንዲኖሩ አድርገዋቸዋል።
ኢትዮጵያን ስንወድ፣ አብሮነታችንን ስንፈልግ፣ አንድነታችንን ስንሻ በምክንያት ነው!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Via Yednekachew
#አቦ የናንተ አይነት ሸህ እና አባቶችን ያብዛልን!
(የዛሬ አራት አመት በፊት የተፃፈ ነው 👆)
አንዳንድ በጎ ነገሮችን ደጋግመን ማስታወስ አለብን‼
በዐማራ ክልል በተስፋፋው ግጭት የንግድ እንቅስቃሴ እንደተዳከመ ነጋዴዎች መግለፃቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ዘግቧል።
መከራችን ገና ነው 😢
የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ተስፋ አምክኗል ሲሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
በዘመነ ኢሕአዴግ ለተፈጠሩ ስህተቶች ኹሉ ይቅርታ ጠይቆ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የብልጽግና ፓርቲ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ተስፋ አምክኗል ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።
“በአሁናዊ የአገራችን ኹኔታ የእልህ፣ የፉክክር እና የአሻጥር ፖለቲካ ብቸኛ የእውቀት መገለጫ፣ የሕዝብ ሰቆቃ፣ ስቃይ፣ እልቂት እና ሥር የሰደደ ድህነት ደግሞ ብቸኛ የስልጣን ማስጠበቂያ መንገዶች ሆነዋል፡፡” ሲሉም አክለዋል።
“ከሰሜኑ ጦርነት በቂ ትምህርት መውሰድ ያልቻለው የብልጽግና መንግሥት፤ ዛሬም የአገር ዳር ድንበርን ከወራሪ ጠላት ለመከላከል የተቋቋመን የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ሕዝብ ላይ በማሰማራት ታሪክ ይቅር የማይለው የወንድማማች ጦርነት በማካሄድ ላይ ነው፡፡” ብለዋል።
በጦርነቱ ሕጻናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን በአሰቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል፣ ሃብት ንብረታቸውም እየተዘረፈ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፤ “ሕዝባችን ሥር በሰደደ የኑሮ ውድነት እና በማያባራ ጦርነት ተጠምዶ በቀቢፀ-ተስፋ እያነባ ነው፡፡” በማለት አስገንዝበዋል።
“ኢትዮጵያ አገራችን ጥንታዊ የመንግሥት ሥርዓት እንዳላት አገር፤ መንግሥትና የመንግሥት ሥልጣን የጨበጡ ግለሰቦች በሕግ የበላይነት እና ተጠያቂነት ሊመሯት ይገባል፡፤” ሲሉም አሳስበዋል።
“ከዚህ ውጭ ቀጣዮን ትውልድ አገር አልባ አድርጎ ለማስረከብ መሞከር ከመቶ ሚሊየን የሚልቀውን ሕዝብ መናቅ፤ በቀጣይ እጣ ፈንታችንም ላይ መሣለቅ ነው፡፡” ብለዋል።
አዲስ ማለዳ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ እየተባባሰ መምጣቱን ማክሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፤ ባለፈው ሳምንት 400 የሚጠጉ አዳዲስ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች ወደ ኩመር የኮሌራ ሕክምና ማዕከል የገቡ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ መሰረት ከዚያ ቀደም ከነበረው ሳምንታዊ የኮሌራ ተጠቂዎች ጋር ሲነጻጸር በ50 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
የጤና ተቋማት ባለባቸው የምግብ እጥረት የተነሳ ሕሙማኑን ማቆየት እንዳልቻሉ የገለጸው ጽህፈት ቤቱ፤ ይህም የኮሌራ ወረርሽኙን እያባባሰ ነው ብሏል።
የኮሌራ ሕክምና ማዕከሉ በበኩሉ ችግሩን ለመቆጣጠር አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚሻም ገልጾ፤ ብዙ ሰው ማስተናገድ የሚችል በቂ የሰው ኃይል ባለመኖሩ ብዙዎች እየሞቱ ነው ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።
የዓለም ጤና ድረጅት የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው፤ በኢትዮጵያ ሰባት ክልሎች ከ20 ሺሕ በላይ የኮሌራ ተጠቂዎች አሉ።
ባለፈው ሳምንት የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ 10 ሺሕ ሱዳናዊያን ስደተኞች በተጠለሉበት ኩመር መጠለያ ጣቢያ፤ ዘጠኝ ሱዳናዊያን ስደተኞች በኮሌራ በሽታ እንደሞቱና 395 ሰዎች በበሽታው መታመማቸው መግለጹ ይታወሳል።
/channel/addismaleda
የብሔራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት የወይዘሮ ሲልቪያ ፓንክረስት የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ (ዶክተር አሉላ ፓንክረስት) በኢትዮጵያ ዙሪያ የአባታቸውን ፈለግ ተከትለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተማርና የምርምር ተግባር የበኩላቸውን አሻራ እያሳረፉ ይገኛሉ።
እኤአ 1868 በሮበርት ናፒየር የሚመራው ጦር ከመቅደላ በርካታ ቅርሶችን ዘርፎ መውሰዱ ይታወቃል። ከተዘረፉ የሀገራችን ቅርሶች መሀከል ታቦት እና ሌሎች ሁለት ቅርሶች በዩናይትድ ኪንግደም ዋና ከተማ ሎንዶን በሚደረግ ልዩ የርክክብ ስነስርአት ነገ እንደሚመለሱ ዶክተር አሉላ ለቢቢሲ መናገራቸው በዜና አውታሮች ተዘግቧል።
NB. የኢትዮጵያ ቅርስ የእኔም የትውልድም ውርስ ነው።
ዘፀዓት በትግርኛ ፅፎት ሌሎች ኢትዮጵያውን እንዲያውቁት ወደ አማርኛ መልሰነዋል።
#ከሶስት ቀናት በፊት የሶስት ልጆችዋ መርዶ የተነገራት እናት ከደቂቃዎች በኋላ እኔስ ምን አለኝ በማለት ራስዋ በገመድ አጥፍታለች። የስነ ስርአት ቀብርዋ በስንቃጣ አብነቃ የሚባል ቦታ እንደተፈፀመ አረጋግጫለሁ ። ይህቺ እናት የራስዋ እንደባይቃ በድንጋጤ ሓዘን በርትቶ ራስዋ አጥፍታለች ልብ የሚሰብር ነው።
ይህ በስነስርዓት ተነግሮ የሁሉም ብሔራዊ ሓዘን ታውጆ አጥኒ ኮሚቴ ተደርጎ ካልተነገረ የህዝብ ሓዘን ከባድ ይሆናል ።
መፅናናትን ለመላው የተሰው ቤተሰቦች
ህይወቱ እንደ እቃ የተጫወቱበት የቀለዱበት የትግራይ ወጣቶች መስዋዕትነት ህዝብ መበደል አልነበረባቸውም ። መስዋዕትነት እንዲህ ርካሽ ማድረግ አልነበረባቸውም ። ቢያንስ በስነስርዓት መናገር ነበረባቸው መድከም አልነበረባቸውም ። መርዶ ለመንገር ገንዘብ መክፈል አልነበረባቸውም ፤ በእውነት ነውር ነው ።
ዘለአለማዊ ክብር ለተሰዉት የትግራይ ሰማዕታት !!"
ይህ ታሪክ ልብ ይነካል። ጦርነት ክፉ ነው። ባህላዊ ጨዋታችን ነው ያሉት እነ አሉላ ሰለሞን በውጪ አለም እየተምነሸነሹ ነው። የፃድቃን ልጆች ውጪ ናቸው። አብዛኛው ወያኔ ዘመድ አዝማዱ ውጪ ነው። በጦርነት ሟቹ ግን የደሃ ልጅ ነው።
አሁንም የጦርነት አዙሪት ላይ ነን። ያሳዝናል 😭
🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼
🌼የአዲስ አመት ብስራት ለቤት ፈለጊዎች
ከፓልም ሪል እስቴት
💧በመሀል ገርጂ እና ብስራተገብርኤል በመጠናቀቅ ላይ እና ግንባታ ላይ ያሉ
እጅግ ውብ አፓርትመንቶችን በቅናሽ ዋጋ
ሽያጭ ላይ ነን !
👉50/50 እስከ 20አመት የረጅምጊዜ አከፋፈል የተመቻቸላቸው
👉ቅድሚያ ክፍያ ከ 25% ጀምሮ
👉አሁኑኑ የኢንቨስመንት ተጠቃሚ ይሁኑ
ሳይታችን ይጎብኙ !
📞 09 47 02 22 22 ይደውሉ
ቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ
/channel/msilmarketing