muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

ጌቾ ኣመረረ በቃ

የትግራይ ክልል የህወሓትና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሽኩቻ ወደ ሌላ ምዕራፍ ተሸጋገረ

እንግዲህ ወንጀለኞች ጉዳያቸው በኮሚቴ እንዲታይ ተወስኖ የነበረው ጉዳዩ በፀረ ሙስና ኮምሽን ትግራይ እንዲታይ ውሳኔ ኣስተላልፈዋል።
ጥሩ ጅምር ነው ተጠያቂነትማ ግድ ነው።
መረጃ ያላቹ ለኮምሹኑ ስጡ እየተባለ ነው።
🙏

ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን 🙏

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

መቀሌ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነች። ጌታቸው ረዳ ለህወሓት ቦታውን እንዲለቅ እነ ደብረፂኦን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ወጣቱ ከጌታቸው ረዳ ጎን ሲሆን የትግራይ አስተዳደር መዋቅርን የያዘው ህወሓት ቢሮክራሲውን ይዞ ጌታቸውን እያስጨነቀ ነው። እነ ደፂ ጦርነት አውጀው ወልቃይትን መያዝ ይፈልጋሉ። ጌታቸው ጦርነት ይበቃናል። በንግግርና በሌላ ዲፕሎማሲ ማስመለስ ይሻላል እያለ ነው። የትግራይ ህዝብ በህወሓት አመራር ተስፋ የቆረጠ ይመስላል። በሀዘን ላይ ያሉ ቤተሰቦች ከሀዘናቸው ሳያገግሙ ወደ ውጊያ መግባት እብደት ነው እያሉ ነው።
ጌታቸው ረዳ ከፌዴራል በተላከለት ሪፐብሉካን ጋርድ እየተጠበቀ ነው ተብሏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ከዓለም 142 አገራት 13ቱን ብቻ በመቅደም 129ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ፣ ፍትሕን የማግኘት ነፃነት፣ ሙስናን እና ጠቅላይ አምባገነንነት በዓለም ዙርያ ፈትሾ ዓመታዊ ልኬትን የያዘ ሪፖርት የሚያወጣው ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት፤ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ከዓለም 142 አገራት ውስጥ የ129ኛ ደረጃን መያዟን አስታውቋል።

ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት ጥቅምት 14/2016 ባወጣው ሪፖርት፤ የዚህ ዓመት የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ምዘና ውጤት ከአምናው ዝቅ በማለት 129ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ያስታወቀ ሲሆን፤ ከሰሐራ በታች ካሉ 34 የአፍሪካ አገራት ደግሞ አራት አገራትን ብቻ በመቅደም 30ኛ ደረጃ ላይ መቀመዘጡን ገልጿል።

በሪፖርቱ ርዋንዳ በአፍሪካ ካሉ 42 አገራት የተሻለ አፈጻጸመ በማስመዝገብ 1ኛ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን፤ ናሚቢያ እና ሞሪሺየስ 2ኛና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በተጨማሪም ሪፖርቱ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው18 አገራት ውስጥ ኢትዮጵያን 15ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች በሪፖርቱ ከተካተቱ አገራት አንፃር ዝቅ ያለ ውጤት ካስመዘገበችባቸው መስፈርቶች መካከል፤ የመንግሥት ግልፅነት፣ የመሠረታዊ መብቶች መከበር፣ የህግ እና ስርዓት መኖር እንዲሁም የመንግስትን ስልጣን የሚቆጣጠር ልጓም መበጀት የሚሉት ይገኙባቸዋል።

በሪፖርቱ ዴንማርክ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፤ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድንና ጀርመን እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ቬንዘዌላ፣ ካምቦዲያ፣ አፍጋኒስታን፣ ሃይቲና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊከ ኮንጎ ዝቀተኛ ደረጃን መያዛቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ጥናቱ በተከናወነባቸው አገራት የሕግ የበላይነት በ59 በመቶ መቀነሱን ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጅ ዛሬ ተቀብለዋል።

በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ዘርፍ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የአሜሪካ ዜጎች በሚሰጠው በዚህ ሽልማት 19 ሰዎች የተካተቱ ሲሆን የፐርዱ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባው ፕሮፌሰር ጋቢሳ አንዱ ሆነዋል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው። ግኝታቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ታምኖበታል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

Via White House/EPA

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢዜማ በመግለጫው ብልፅግና ፓርቲ የመንግስትና የህዝብን ንብረት ለፓርቲ እየተጠቀመ ነው ብሎ ከሰሰ
መግለጫው ከታች የሚመለከተው ነው 👇

"የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ ከሀገራዊ ምርጫው አንስቶ ባሉት ጊዜያት ጀምሮ እስካሁን ባሉት ሂደቶች መንግሥት እና ፓርቲን ደባልቆ በማየት የሀገርን ሀብት እየዘረፈ እና እያባከነ እንደሆነ ገልጸን እንደነበር ይታወሣል።

በተለይም ከመስከረም 29/2016 ዓ.ም. ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሣተፉበት 2ኛ ዙር ብሎ ፓርቲው ያዘጋጀው በመቶ ሚሊዮኖች ወጪ የተደረገበት መድረክ እንዲሁ ዜጎች ግብር ከፍለው ከተሠበሠበ የመንግሥት ኃብት ላይ መሆኑን ጠቅሰን ይህንን ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ተከታትለው ከሕግ አግባብ ውጪ የሕዝብ ሀብትን የዘረፈው የመንግሥት አካል ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ጉዳዩን በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቁም ጠይቀናል።

በዚህም መሠረት ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ላልናቸው አካላት ማጣራት እንዲያካሂዱ ከታች በምስሉ በተያያዙት ደብዳቤዎች ያሣወቅን ሲሆን እነዚሁ አካላት በሕዝብ እና በሕግ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እናሳስባለን።"

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

#እጅግ_አሳዛኝ!

👉የ4 አመቷ ህፃን ልደቷን ለማክበር በተጠመቀ ጠላ በርሜል ዉስጥ ገብታ ህይወቷ አለፈ።
***
እጅግ አሳዛኙና አስደንጋጩ ዜና የተሰማው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

መረጃው እንደሚለው በክልሉ ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ ቀበሌ ቁጥር ሁለት ነው የ4 አመቷ ታዳጊ ለልደቷ ማክበሪያ፣ እንግዳ መሸኛ ተብሎ በተጠመቀ የጠላ በርሜል ውስጥ ህይወቷ ማለፉ የተሰማው።

ህይወቷ ያለፈው ታዳጊ ወላጆቿ የህፃኗን የአራተኛ አመት ልደት ለማክበር ጠላ መጠመቁንና ለልደቷ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች በሚሰናዳበት ጥቅምት10 ቀን 2016 ከጠዋቱ 4: 00 ላይ አደጋው መግጠሙን የገለፁትየጊምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢ/ር መሰረት አደመ በወቅቱ እናት ማልዳ ጠላዉን እያጣራች ሳለ ህፃኗ ከመኝታ ተነስታ እናቷ ወደምትሰራበት ቦታ በመምጣት ወንበር ላይ ቆማ ወደ በርሜሉ ዝቅ ብላ እያየችነበር ያሉ ሲሆም እናት ወጣ ብላ እስክትመለስ ህፃኗ በበርሜል በተጠመቀው ጠላ ዉስጥ ገብታ ህይወቷ እንዳለፈ አስረድተዋል።

በሰአቱ ልጇን ያጣችው ወላጅ ብትጣራ ምላሽ በማጣቷ ወደ ስፍራዉ መጥታ ህፃኗን ከበርሜል ውስጥ ብታወጣትም ህይወቷ እንዳለፈ የገለፁት ኃላፊው የልደት ደስታዉ ወደለቅሶና ሀዘን መቀየሩንና ህፃኗ ለአራተኛ አመቷ ልደት የተገዛላትን ልብስና ጫማ ለብሳ ፣ ሻማ ለኩሳ በመንደሩ እኩዮቿ መልካም ልደት ሳትባል ፣ ለወዳጅ ዘመድ ጥሪ የተጠመቀዉ ጠላናዳቦ ፣እንጀራ እና ወጥ ለሀዘንተኛ ማስተዛዘኛ መዋሉንም ነው ከኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው።
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"መድሃኒትን ምግብ ከሚያደርጉ፣ ምግብን መድሃኒት ያድርጉ"❗

በምግብ ብቻ አዎ በምግብ ብቻ❗️

ስር የሰደዱ በሽታዎችን ማለትም የደም ግፊትን፣ ልብ ህመምን፣ ስኳር መጨመርን፣ስትሮክን፣ የውፍረት ችግርን (መጨመር/መቀነስ)፣ ኮሌስትሮል መጨመርን ፣ ሪህን በምግብ ማከም እንደሚቻል ያውቃሉ?

እንግዳውስ ወደ ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና ማዕከል ጎራ ይበሉ መፍትሄው በእጃችን ላይ ነው።

በዘርፉ ብዙ ምርምር በሰሩ ሀኪሞችና የስነ ምግብ ባለሙያዎች አገልግሎቱን ያገኛሉ።

መድሃኒት ከመጀመርዎ በፊት እኛን ያማክሩን። ያለምንም መድሃኒት ጤናዎ እንዲስተካከል እናደርጋለን። ከጀመሩም በምናዘጋጅላችሁ ጤናማ የአመጋገብ ስርአት ጤናዎ እንድስተካከል እና እንዴ ሁኔታው መድሃኒት እንዲያቆሙ እናግዞታለን።

ከነዚህ በተጨማሪ ለነፍሰ ጡር እና አጥቢ እናቶች፣ ለህፃናት፣ ለአረጋውያን እንድሁም ለአትሌቶች የጤናማ አመጋገብ ስርአትን ለብዙ አመታት በሰራናቸው ጥናት እና ባካበትነው ልምድ መሰረት እየሰጠን እንገኛለን።

በምግብ ብቻ ጤናዎን ማስተካከል ተቀዳሚ ስራችን ነው።

ሳይንሳዊ በሆነ አመጋገብ ጤናዎን ይጠብቁ።

ቫይታል የስነ ምግብ ህክምናና ጤና ማማከር

አድራሻ:- ጉርድ ሾላ፣ ሴንቼሪ ሞል አጠገብ ፣ጂ ኤንድ ቢ ሕንፃ፣ 3ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ:- በ 0910770777/0911596059 ይደውሉ።

Telegram: /channel/vitalnutritionaltherapy

Instagram: https://instagram.com/vital_nutritional_therapy?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61551789519221&mibextid=ZbWKwL

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እጅግ አስቸኳይ መረጃ
ረሀብ ገብቷል

ሰሜን ጎንደር ዞን፣ በየዳ ወረዳ ፣ ጠለምት ወረዳ ፣ ጃናሞራ ወረዳ እና ዋግ ኽምራ ዞን እነዲሆም ሌሎች ቀበሌዎች ህዝባችን በቸነፈር እየተገረፈ ነው።

ያልሰማ ይስማ የሰማ ላልሰማ የያሰማ

Yared Shumete በፌስቡክ ገፁ ያጋራን መረጃ ነው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በመዲናዋ “ፉድ ዞን” ሆቴል ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ከ1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

👉የእሳት አደጋው በሆቴሉ ስጋ መጥበሻ ላይ መነሳቱ ተነግሯል
=======#=======

አርብ ጥቅምት 9 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብራስ አካባቢ በሚገኘው “ፉድ ዞን” ሆቴል ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ከ1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት አደጋው የደረሰው ትላንት ጥቅምት 8 ቀን 2016 ከምሽቱ 4:40 ሰዓት ሲሆን፤ አደጋው በሆቴሉ ከምግብ ማብሰያ ክፍል ዉስጥ ከስጋ መጥበሻ ላይ የተነሳ እሳት እሳት ምክንያት መከሰቱን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሀያ አምስት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም ሂደት 1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የገለጹት ንጋቱ፤ 11 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን መቻሉን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን፤ አደጋዉን ለመቆጣጠርም 1:31 ሰዓት መፍጀቱን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ትላንት ከቀኑ 9:49 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፒኮክ መናፈሻ በደረሰዉ የእሳት አደጋ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአዲስ አበባ የክረምት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ የእሳት አደጋ እየተደጋገመ መምጣቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል። አሁን ያለው የአየር ጸባይ ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ አስተዋጽኦ ያለዉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከወትሮዉ የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ታታሪዎችን ማበረታታት ይልመድብን❗
የበርካቶች ምርጫ ስለሆነ ቻናሉን ለማታውቁት ልዩ ጥቆማ ነው‼️
✅እውነት ለመናገር መረጃ በፍጥነት እና በጥራት በማቅረብ ረገድ ሁላችሁም ሊኖራችሁ የሚገባ የቴሌግራም ቻናል ነው።
✅ በተመሳሳይ ስም እና ፕሮፋይል የተከፈቱ የውሸት አካውንቶች ስላሉ ተጠንቀቁ።
ከስር ባለው ሊንክ join ያድድጉት፣በእርግጠኝነት ያተርፋሉ👇👇👇👇
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኤርትራ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ የፕሬስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ መግለጫው ሲጠቃለል "ባላየ እለፉት ...... " ነው የሚለው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በደረሰው የእሳት አደጋ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በትላንትናው እለት ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:47 ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኮየ ፈጩ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ውድመት ሲደርስ በአንድ ሰዉ ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት በእሳት አደጋዉ አንድ ጋራዥ ከአምስት ተሽከርካሪዎች ጋር ፣ የብየዳ አገልግሎት መስጫ፣ጎሚስታና ግሮሰሪ ተቃጥለዋል።

በጋራዡ ለጥገና የገቡ ተሽከርካሪዎች ዉስጥ የነበረ ነዳጅ እና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች መኖራቸዉ እንዲሁም ጥሪዉ ዘግይቶ መድረሱ ለእሳት አደጋዉ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተነግሯል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ የቻሉ ሲሆን በዚህ ሂደት 32 ከብቶችንና ከፍተኛ ግምት ያለዉ እህል እንዲሁም መኖሪያ ቤቶችን ማዳን ስለመቻሉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ዘጠኝ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና አንድ የዉሀ ቦታ ከሀምሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷል።

የእሳት አደጋዉን በመቆጣጠር ስራ ላይ ከነበሩት ባለሞያዎች መካከል በአንድ የአደጋ መቆጣጠር ሰራተኛ ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።በሌላ በኩል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በግተራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ቅዳሜ ረፋድ 4:52 ሰዓት በተነሳ የእሳት አደጋ አንድ የመኖሪያ ቤት ሲቃጠል በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
(ዘገባው የብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ነው)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📍 ትርፋማነቱ የተረጋገጠ አዋጭ ኢንቨስትመንት እነሆ!

ዛይራይድ ዜጎች የዛይራይድ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ውስን አክስዮኖችን ለሽያጭ አቀረበ!

ለሽያጭ የቀረቡ ውስን የአክስዮኖች ግዚ ዋጋ መጠን

⚡️የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ነው

⚡️የትንሹ አክስዮን ግዢ ብዛት ለአሽከርካሪዎች 25 (ሃያ አምስት) አክስዮን ወይም ሃያ አምስት ሺህ (25፣000) ብር ሲሆን ለሌሎች ደግሞ 75 (ሰባ አምስት) አክስዮን ወይም ሰባ አምስት ሺህ (75፣000) ብር ነው፡፡
⚡️የትልቁ አክስዮን ግዢ መጠን ለሁሉም አክስዮን ገዢዎች 5000 (አምስት ሺህ) አክስዮን ወይም 5 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
⚡️ለማንኛውም የአክስዮን መጠን ግዢ ክፍያ በቅድሚያ (በአክስዮን ግዢ ወቅት) በአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0973023522 ይደዉሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📍 ትርፋማነቱ የተረጋገጠ አዋጭ ኢንቨስትመንት እነሆ!

ዛይራይድ ዜጎች የዛይራይድ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ውስን አክስዮኖችን ለሽያጭ አቀረበ!

ለሽያጭ የቀረቡ ውስን የአክስዮኖች ግዚ ዋጋ መጠን

⚡️የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ነው

⚡️የትንሹ አክስዮን ግዢ ብዛት ለአሽከርካሪዎች 25 (ሃያ አምስት) አክስዮን ወይም ሃያ አምስት ሺህ (25፣000) ብር ሲሆን ለሌሎች ደግሞ 75 (ሰባ አምስት) አክስዮን ወይም ሰባ አምስት ሺህ (75፣000) ብር ነው፡፡
⚡️የትልቁ አክስዮን ግዢ መጠን ለሁሉም አክስዮን ገዢዎች 5000 (አምስት ሺህ) አክስዮን ወይም 5 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
⚡️ለማንኛውም የአክስዮን መጠን ግዢ ክፍያ በቅድሚያ (በአክስዮን ግዢ ወቅት) በአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0973023522 ይደዉሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ ወንበረ ክብራቸው በሰላም ተመልሰዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

❗️ G+1 እና G+2 ቪላ ቤቶች በ አፓርታማ ዋጋ ከ 3.3 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔥 ድጋሚ የማይገኝ እድል ውስን ቪላዎች ነው የቀሩት

እንይ ሪልስቴት / ENYI Real Estate
👉ከ 18 ዓመት በላይ ልምድ ያለው
👉ከ 6 በላይ እህት ኩባንያዎች ያሉት ሲሚንቶ ፋብሪካን ጨምሮ
👉ከዚህ በፊት ቦሌ ቡልቡላ እና አለምገና ሮዝላንድ መንደር ከ 100 በላይ ቪላ ቤቶች እና ከ 400 በላይ አፓርታማዎች አስረክቧል

📍 አሁን ደግሞ በጀሞ 2 እየሰራን ያለውን G+1 እና G+2 ቪላ ቤቶች በ 30% ቅድመ ክፍያ በ 1 ዓመት ከ 6 ወር ልናስረክብ ሽያጭ ጀምረናል

👉G+2 127 ካሬ
ዋጋ - 13,200,000 ብር
ቅድመ ክፍያ - 3,960,000 ብር

👉G+1 120 ካሬ
ዋጋ - 11,000,000 ብር
ቅድመ ክፍያ - 3,300,000 ብር

አሁን ይደውሉ ፥ ሳይት ይጎብኙ ከዛ ይወስኑ
+251967770077

Telegram - /channel/Apartmentconsultant

Whatsapp - https://wa.me/251967770077?text

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኤርትራ በሚገኙ ሁለት የእስራኤል የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።

የኢራኑ Press TV እንደዘገበው የሚሳኤል ጥቃቶቹ አንድ ከፍተኛ የእስራኤል ወታደርን ገድሏል። አንደኛው ጥቃት በዳህላክ ደሴት የተፈፀመ ሲሆን ሌላኛው አምባ ሲኢር በሚባል እስራኤሎች መመልከቻ በተከሉበት ተራራ ላይ መሆኑ ተዘግቧል።

በዚህ ዙርያ እስካሁን በእስራኤልም ሆነ ጥቃቱን አድርሻለሁ ባለ አካል የተሰጠ መግለጫ የለም፣ ኤርትራ ጥቃት ደረሰ መባሉን አስተባብላለች።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት 6 የዞን ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን አነሱ
=======#=======

ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ 6 የዞን ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ማንሳታቸውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በዚህም ከስልጣን የተነሱት አመራሮች የምስራቅ፣ የደቡብ፣ የማእከላይ፣ የደቡብ ምስራቅ፣ የሰሜናዊ ምእራብ እና የምእራብ ዞን የሕዝብ ግንኙነት ጽህፈት ኃላፊዎች ናቸው።

ኃላፊዎቹ ከፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 14/2016 በተፃፈ ደብዳቤ በይፋ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አዲስ ማለዳ ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል፡፡

አመራሮቹ ከስልጣን ስለተነሱበትን ምክንያት ጽ/ቤቱ በግልጽ ያለው ነገር የለም፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኦሮሚያ በሚፈጸሙ እገታዎች ሕዝቡ እያማረረ ነው።
ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀው አስተያየታቸውን የሰጡን በምስራቅ ሸዋ ዞን የአደአ ወረዳ ጊጬ ጋራ-ባቦ ቀበሌ ነዋሪ በየሰበብ አስባቡ ተስፋፍቷል ያሉት የእገታ ተግባር አሁን አሁን የነዋሪዎች ዋነኛ ስጋት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አስተያየት ሰጪው በቅርቡ ከዚሁ ቀበሌ አንድ ሰው ተገድለው ሌሎች ሶስት በሌሊት ታግተው ተወስደው በነፍስ ወከፍ መቶ ሺህ ብር ከፍለው መውጣታቸውንም አመልክተዋል፡፡

ሌለው በምእራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አስተያየት ሰጪ በወረዳው ጃሎ ከሚባል አከባቢ በቅርቡ እንኳ በአንድ ሌሊት የተወሰዱ 10 ሰዎች ገደማ ከመቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊየን ተጠይቀው ከፍለው መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ዞን ደንዲ ከተባለ ወረዳ ቤተሰብ ደጋግሞ እንደታገተባቸው ገልጸው አስተያየታቸውን የሰጡን የጊንጪ ከተማ ነዋሪ የእገታ ተግባራቱ እየተለመደ በመምጣቱም የህብረተሰቡን የመንቀሳቀስ መብቱ አደጋ ውስጥ ከቶታል ብለዋል።

አያይዘውም “የታጠቁ አካላት ትንሽ መሸት ሲል ታጥቀው ወደ ሰው ቤት ይገባሉ፡፡ የሚወስዱት ከብት ወይም ሌላ ንብረት አይደለም፡፡ ከቤተሰብ አባላት አንዱን ይዘው ይሄዱና ትንሽ ቆይተው ስልክ በመደወል ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡ አንድ ሰው እስከ 500 ሺህ ብር ይጠየቃል፡፡” ሲሉ ለDW ተናግሯል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሰሜን ጎንደር በየዳ ጃናሞራ ጠለምት በድርቅ ምክንያት ረሀብ ገብቶ ህይወት እየረገፈ ነው። #ሼር

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
----------||----------
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ ወደ ህዋ የላከቻቸው ሳተላይቶች ስራ አቆሙ
#FastMereja
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሳይንሳዊ ስራዎችን ለመከወን ያግዟታል ተብለው ወደ ህዋ የመጠቁ ሁለቱ ሳተላይቶች ስራ አቁመዋል ተባለ። የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚወገዱበት ጊዜ ስለደረሰ ሌሎች ሳተላይቶች ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑ ተገልፇል።

አዲስ ሳታላይት አልምቶ ለማምጠቅም እየተሰራ መሆኑን የኢንኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ተናግሯል። ከዚህ ቀደም ወደ ሳተላይት የመጠቁት ምን ፋይዳ አስገኙ የሚለው እንዳልተገለፀ ነው ሸገር ሬዲዮ የዘገበው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የታሸገ ውሃ ላይ ምክንያቱ ያልተገለጸ ከፍተኛ የዋጋ ጨማሪ እየተስተዋለ ነው።

የውሃ አከፋፋዮች ወትሮ ይሸጡበት ከነበረው ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ይገኛሉ።

በሱቆች 25 ብር ይሸጥ የነበረው 2ሊትር ውሃ አሁን 30 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ሱቆች ከአከፋፋዮች 20ብር ይረከቡ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በ25 ብር እየተረከቡ እንዳሉ ነግረውናል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ይህንን ጉዳይ ለማረጋገጥ በየሱቆች ቅኝት አድርጎ እውነት መሆኑን አረጋግጧል።

በየሱቆች እየተዟዟሩ ውሀ የሚያከፋፍሉ ነጋዴዎች ለዋጋው ጭማሪ ግልጽ የሆነ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል።

አከፋፋዮች እንደተናገሩት ከሆነ ፋብሪካዎች እኛም ላይ ጭማሪ አድርገውብናል ብለዋል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ኢትዮ ኤፍ ኤም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን እስካሁን መረጃው እንደሌለው ገልጾ በቀጣይ መረጃዎችን አሰባስቤ ማብራሪያ እሰጥበታለሁ ብሎናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች

1፤
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ ኢትዮጵያ ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት እንድታወግዝ  በድጋሚ መጠየቁን ምክትል አምባሳደር ቶመር ባርላቪ ለቪኦኤ ተናግረዋል። ኢምባሲው ጥያቄውን ያቀረበው፣ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱ ረቡዕ'ለት ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ በእስራኤልና ፍልስጤማዊያኑ ግጭት ዙሪያ እስካኹን አቋሟን አልገለጠችም። የኢትዮጵያ ጎረቤቶች፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሊያና ኬንያ ግን በግጭቱ ዙሪያ መግለጫዎችን አውጥተዋል።

2፤
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋብሪካ ግብዓቶችን ለማግኘት ሲሉ በተቋሙ ንብረቶች ላይ ሥርቆት እንዲፈጸም የሚያበረታቱና  ከተቋሙ የተሠረቁ ቁሳቁሶችን የሚረከቡ የብረታ ብረት ፋብሪካዎችና ባለሃብቶች ሊፈተሹ ይገባል በማለት አሳስቧል። ተቋሙ፣ በአዲስ አበባና በዙሪያው በሚገኙ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈጸሙ ሥርቆቶች ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። በተያዘው በጀት ዓመት ሦስት ወራት ውስጥ 1 ሺህ 771 ብረቶች እንዲኹም 7 ሺህ 84 ብሎኖችና የብሎን ማሰሪያዎች እንደተሠረቁበትም ተቋሙ ገልጧል። በሦስት ወራት ብቻ በተፈጸመበት ሥርቆት ሳቢያ የተቋረጠውን የኃይል መጠን ሳይጨምር፣ ጉዳት የደረሰባቸው የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችን ለመጠገን 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጭ ማድረጉንም ተቋሙ አመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጸጥታ አካላት ሥርቆቱን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ምላሻቸው ፈጣን አለመኾኑ ችግሩን አባብሶታል በማለትም ሞ ቅሬታውን ገልጧል።

3፤
የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ ኤምፔሳ የተሰኘውን የሞባይል መገበያያና ገንዘብ መላላኪያ ዘዴ ዞ ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት መቆጣጠሩን አስታውቋል። ኩባንያው ኤምፔሳን የጠቀለለው፣ የብሪታኒያው ቮዳፎን ኩባንያ ይዞት የነበረውን ድርሻ በ1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ በመግዛት ነው። ኤምፔሳ፣ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የደንበኞችን ገንዘብ በቁጠባ መልክ ያስቀመጠና ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚካሄድበት ነው። ኤምፔሳ ኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎቱን በቅርቡ መጀመሩ ይታወሳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ብንሄድ ይሻለናል..... ብላ ፖስታ ራሷዋ ወሰደች

ተስፈኛዋ እህታችንን ዛሬ አጣናት! መንገድ ላይ ሆናችሁ እንዲህ አይነት መርዶ አይድረስባችሁ.. የእህታችን ናዝራዊት ነፍስ ይማርልን🙏

ከ2008 እስከ 2013 በጅማ የዩንቨርስቲ ትምህርታችን አብረን ተከታትለናል በአንድ ክፍል:: ዝም ሚሉዋችሁ ለብቻችሁ ሲያገኝዋችሁ በድንብ እስከ ጥጉ ሚያጫውታችሁ ሰው አለ አይደል ናዝሪ እንደዛው ነበርች.... ከመሞትዋ አንድ ቀን በፊት የፖስትችውን ከዘገየው ቡሃላ ነው ያየውት.... ለዚህ ሁሉ ነበር ያሁሉ ድካም ያሁሉ ልፋትሽ አይ እች ከንቱ ዓለም! ቅርብ ያሉ እየመሰሉ የራቁን የተጨነቁ ሚያማክራችው ያጡ ዓለም የጨለመባቸው ብዙ ሰዎች አሉ... የኛ ሰላምታ :እነሱን መፈለግ: ቢያንስ አንድ ተስፋ ይስጠችዋል አጠገባችን ያለውን ሰው ቢያንስ እንፈልግ እንፈላለግ መጥፎ ቀናት እንደሚያልፋ እናብስር 🙏🙏🙏

በሰላም ነፍስሽ ትረፍ 🙏
እግዚአብሔር ነፍስሽን ከቅዱሳኑ ጋር ያስርፋት ናዝሪ 🙏🙏
በያሬድ ብርሃኑ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

📍 ትርፋማነቱ የተረጋገጠ አዋጭ ኢንቨስትመንት እነሆ!

ዛይራይድ ዜጎች የዛይራይድ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ውስን አክስዮኖችን ለሽያጭ አቀረበ!

ለሽያጭ የቀረቡ ውስን የአክስዮኖች ግዚ ዋጋ መጠን

⚡️የአንድ አክስዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ነው

⚡️የትንሹ አክስዮን ግዢ ብዛት ለአሽከርካሪዎች 25 (ሃያ አምስት) አክስዮን ወይም ሃያ አምስት ሺህ (25፣000) ብር ሲሆን ለሌሎች ደግሞ 75 (ሰባ አምስት) አክስዮን ወይም ሰባ አምስት ሺህ (75፣000) ብር ነው፡፡
⚡️የትልቁ አክስዮን ግዢ መጠን ለሁሉም አክስዮን ገዢዎች 5000 (አምስት ሺህ) አክስዮን ወይም 5 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
⚡️ለማንኛውም የአክስዮን መጠን ግዢ ክፍያ በቅድሚያ (በአክስዮን ግዢ ወቅት) በአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0973023522 ይደዉሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት የተሰጠ መግለጫ

መንግስት የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው በመቻቻልና በአብሮነት እንዲኖሩ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ሂደት የህብረተሰቡን የተለያዩ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየፈታ ይገኛል።

በቀን 02/02/2016 ዓም በወልቂጤ ከተማ ተቀሰቀሰው አመጽ እንዲበርድ የጸጥታ ኃይላት በሆደ ሰፊነት ግጭቱ እንዲበርድ እና የሚደርሰው ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ለመቀነስ በኃላፊነት ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል።

በመሆኑም ከዛሬ ጥቅምት 03/2016 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ ተጥሏል።

በዚህ መሰረት የትኛው ተሽከርካሪ ማለትም ሞተር ዳይክል፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣ አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ከ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ስለሆነም ማንኛወረም ሰውም ሆነ ተሽከርካሪ ከተጣለው የሰዓት ገደብ ውጭ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ ለሚወሰደው እርምጃ ተጠያቂው ህለሰቦቹ እንደሚሆኑ ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ሰላማችን እንጠብቅ !!

ጥቅምት 03//2016
ወልቂጤ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

«ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን። ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል።»

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በትግራይ ክልል ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የሃዘን ቀን ታወጀ


በፌደራል መንግስሥቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ተካሂዶ በነበረው ጦርነት ወቅት ሕይወታቸው ያለፉ ተዋጊዎችን ለመዘከር በትግራይ ክልል ከዛሬ ጥቅምት 2 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ክልላዊ የሃዘን ቀን ታውጇል፡፡

ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚቆየው የሃዘን ቀን የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማ ለሰማዕታት መታሰቢያ እና ክብር ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ተገልጿል።

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው "የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን" ሥነ-ስርዓት ዛሬ ጥቅምት 2 በይፋ ታውጆ፤ ከጥቅምት 3 እስከ 5 ባሉት ሦስት ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ሥር ባሉ ኹሉም የክልሉ አካባቢዎች በጥብቅ ድስፒሊን እንደሚተገበር ተነግሯል፡፡

በእነዚህም ቀናት በክልሉ የሕክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት እንደማይቋረጥ የተገለጸ ሲሆን፤ የባንክ አገልግሎት ግን ጥቅምት 3 እና 5/2016 ለኹለት ቀን ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል።

የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ሥነ-ስርዓቱ ሕዝቡን በቀበሌ ደረጃ በማሰባሰብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚከናወን፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጸጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከዚህ ቀደም ባስተላለፉት መመሪያ አስታውቀዋል፡፡

ይህንንም የሚያስተባብሩ አራት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ሥራ መጀመራቸውን የገለጹት ጀነራል ታደሰ፤ ኮሚቴዎችም የሚድያና የማነሳሳት፣ የመርዶ፣ የሕግ እና የፋይናንስ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ኮሚቴዎቹ ሥነ-ስርዓቱ ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ የሚጥስ ደግሞ ከገንዘብ እስከ የእስራት ቅጣት እንዲጣልበት ለመከታተል ሃላፊነት የተሰጣቸው እንደሆኑ ገልጸዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯን በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ለድርቅ ለተጋለጡ ዜጎች ከውጭ የሚላክ ድጋፍ ሊቀንስ እንደሚችል ይህን ፅሁፍ ከበርካታ ወራት በፊት አጋርቼ ነበር።

ታድያ እንደ ሩስያ ያሉ ሀገራት ሰሞኑን በርካታ ሺህ ቶን ስንዴ ለህዝባቸው ለሚፈልጉ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት ልከዋል፣ ኢትዮጵያ ዝርዝሩ ውስጥ የለችም።

እውነታው ግን:

- በሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በድርቅ ምክንያት እስካሁን 32 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፣ ድርቅ ከከፋባቸው ወረዳዎችም እና አካባቢዎች ዜጎች ቄያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።

- በስፍራው የሚገኙ ምንጮች እንደነገሩኝ በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ረሀብ እጅግ የበረታባቻው ዜጎች ገበያ እየሄዱ መንገድ ላይ ሲወድቁ (collapse ሲያረጉ) ታይተዋል።

- በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ባጋጠመው የድርቅ አደጋ ከ100,000 በላይ ነዋሪዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል፣ ነዋሪዎቹም ሆነ እንስሳቱ ለከፍተኛ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና የከፋ እልቂት እንዳይከሰት ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ታድያ የሚበልጠው የተገኘው ድጋፍ አሰባስቦ ለተራቡ መስጠት ወይስ ለኤክስፖርት የሚተርፍ ስንዴ አምርተናል ብሎ ዜና መስራት?

አፄ ሀይለስላሴ በድርቅ ግዜ እንዲህ ሲያደርጉ ነበር፣ ደርግ እንደዚያ ሲያረግ ነበር ሲባል በታሪክ እንደሚወራው የአሁኑ አስተዳደርም ተወቃሽ ከመሆን ለመዳን አለም አቀፍ ድጋፍን አስተባብሮ ህዝቡን ከሞት ማትረፍ አለበት።

Photo: File
Via Elias Meseret

Читать полностью…
Subscribe to a channel