muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

A breakthrough in the Fight against HIV-AIDS
****
አዲሱ የኤች አይቪ መድሃኒት ውጤታማ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡

ኤች አይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ፡፡
ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነት ውስጥ የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት መረጋገጡ ታውቋል።
የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተውጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው።

በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች እየወሰዱ ይገኛሉ።
ከቼልሲ እና ዌስትሚኒስትር ሆስፒታል ጋር በመሆን የመድኃኒቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተደረገውን ሙከራ የመራው የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ጥናቱ በዓይነቱ ከዚህ ቀደም ከተሰሩ ጥናቶች ሰፊ መሆኑን ገልጿል።

ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2017 እስከ ሐምሌ 2020 ባሉት ጊዜያት እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ 157 የሥነ ተዋልዶ ጤና ተቋማት ላይ ተካሂዷል።
ይህ ጥናት ‘ፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፍላክሲስ (ፒአርኢፒ)’ የተባለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን መድኃኒቱ በኤችአይቪ የመያዝ ዕድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል።

በክሊኒክ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳመለከቱትም መድኃኒቱ 99 በመቶ ውጤታማ ነው።
የዩኬ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲ የመድኃኒቱ ውጤታማ መሆን የአገሪቷ መንግሥት በ2030 የኤችአይቪ ሥርጭትን ዜሮ ለማድረስ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳል ብሏል።

(via : Natnael Mekonnen)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከወላጆቻችን የወረስነውን ንብረት አላካፈልከኝም በማለት ወንዱምን የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በኢሊባቡር ዞን ከወላጆቻችን የወረሰውን ንብረት አላካፍልከኝም በማለት ወንድሙን ገድሎ የህዝብ መጸዳጃ ውስጥ ሊከት የነበረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ተከሳሽ ወላጆቻችን ያካፈሉንን ንብረት አላካፍል አለኝ በማለት ወንድሙን በስለት የተለያየ ቦታዎች መውጋቱን የኢሉባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሜ ሲሳይ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ተከሳሽ ባጫ የተባለው ግለሰብ ቂም ይዞ ታላቅ ወንዱሙ ላይ ድርጊቱን መፈጸሙ ተረጋግጧል ። ፖሊስ አስከሬኑን ካስመረመረ በኋላ ስርዓተ ቀብሩ እንዲፈፀም አድርጎ የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለዓቃቢ ህግ ልኳል።

ዓቃቢ ህግ የምርመራ መዝገቡን በጥልቀት በመመልከት እና ክስ በመመስረት ለኢሊባቡር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልኳል። ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ተመልክቶ ተከሳሽ ባጫ ያሲን ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሜ ሲሳይ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ቬሮኒካ አዳነ በህመም ምክንያት ዝግጅቶቿን ማቅረብ እንዳልቻለች አስታወቀች።

ቬሮኒካ አዳነ ዝግጅቶቿን በአሜሪካ በተለያዩ ከተማዎች ለማቅረብ አሜሪካ በቅርቡ መግባቷ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ባጋጠማት ህመም ምክንያት ዝግጅቷን በበቂ ሁኔታም ማቅረብ እንዳልቻለች በማህበራዊ ገጿ ላይ እንዲህ ስትል አስታውቃለች።

"NOVEMBER 25 ዳላስ ላይ ሾ እንዳለኝ አሳዉቄ ነበር; ፎቶ ላይ እንደምታዩት ከባድ ነገር ቢያጋጥመኝም ዳላስ ላይ የምትገኙ ቤተሰቦቼን ላለማስከፋት ቦታዉ ላይ ተገኝቼ ነበር; ለመዝፈን ብሞክርም ለመዝፈን አልቻልኩም ; ዳላስ የሚገኙ ኢትዮዽያዉያን እና ኤርትራዉያንም ቦታዉ ላይ መገኘቴን ብቻ ተረድተዉ መናገር ከምችለዉ በላይ ፍቅር እና ክብር ሰተዉኝ ቆንጆ ጊዜ አብረን አሳልፈናል; መጨረሻ ላይም የአቅሜን 6; 7 ዘፈን ተጫዉቼ ወርጃለዉ።

ዳላስ የምትገኙ ቤተሰቦቼ በድጋሚ ይቅርታ 🙏🏽

ስትል መልክቷን አስተላልፋለች።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ የማምረቻ ፋብሪካዎቹን አየዘጋ ነው ተባለ።

የሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር የማምረቻ ፋብሪካዎቹን መዝጋት የጀመረ ሲሆን ወደ 8ሺ የሚጠጉ ሰራተኞችን ከሥራ ውጪ ሊያደርግ እንደሚችል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ማንነታቸው ያልተጠቀሰ የውስጥ ምንጮች ነገሩኝ ብሎ ሪፖርተር እንደዘገበው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሞሃ ምርቶችን ለማምረት እጅግ አዳጋች ሁኔታ መፍጠሩ ሲጠቀስ የማምረቻ ማሽን መለዋወጫዎችን ጨምሮ ጠርሙሶች፣ ሣጥኖች እና የተለያዩ የጥሬ እቃ ግብአቶችን በምንዛሬ እጥረት ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንዳልተቻለ ተገልጿል።

ካለፈው አመት ጀምሮ በስምንቱም ፋብሪካዎች ላይ አዲስ ምርት የማምረት ሂደት ሙሉ በሙሉ መቆሙ የተገለፀ ሲሆን ፋብሪካው ገበያው ላይ ሲሸጡ የነበሩትን ምርቶች ክምችት (Store) ክፍል ውስጥ የነበሩ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ሞሃ ላለፉት አራት ወራት የደንበኞችን ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉ ሲገለፅ ፥ በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ የሚሸጡት የሞሃ ምርቶች ሀሰተኛ ወይም የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ በመሆኑ በጤና ላይ ስጋት ሊፈጥሩ እንደሚችል ተገልጿል።

በዚህ ችግር ምክንያት የሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ በርካታ ሰራተኞቹን ያሰናበተ ሲሆን ባለፈው አመት ከ8,000 በላይ ሰራተኞች ከስራ መሰናበታቸውንና በማኔጅመንት የስራ ድርሻ ላይ ያሉትም ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውና እንዲሰናበቱ መደረጉ ተጠቅሷል።

በቂ የማሳወቂያ ጊዜ አልተሰጠንም ወይም የተከፈለልን የስራ ስንብት ክፍያ በቂ አይደለም ያሉ የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንደስትሪ ሰራተኞች፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (CETU) መሄዳቸውም ተገልጿል።

ምንጭ

Credit : Reporter

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በባንኮች ላይ ዘረፋ የፈፀሙ የጥበቃ ሰራተኞችና ግብራበሮቻቸው ተቀጡ

በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እና በወጋገን ባንክ ላይ ዘረፋ የፈፀሙ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች እና ሰባት ግብራበሮቻቸው በእስራት ተቀጡ፡፡

አለሙ አሰፋ የተባለው ተከሳሽ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በከልቻ ቅርንጨፍ ውስጥ በጥበቃ ስራ ተቀጥሮ እያገለገለ ነበር፡፡

ተከሳሹ መስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም የምሽት ተረኛ የሆነው የስራ ባልደረባውን "ዛሬ እኔ ልሸፍንልህ አንተ ወደ ቤት ሂድ" ብሎ እንዲሄድ ካደረገ በኋላ ይርጋለም አድማሱ ከተባለው ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በፌሮ ብረት ካዝና በመስበር 2ሺህ 414 የአሜሪካ ዶላር እና ከ2 ሚሊዮን 280 ሺህ በላይ ብር ዘርፈው በበመውሰድ ተሰውረው ቆይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ገበየሁ ምስጋና የተባለ የወጋገን ባንክ የረር ቅርንጨፍ የጥበቃ ሠራተኛ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ በተፈፀመው ወንጀል ተሳትፎ ከነበረው ይርጋለም አድማሱ እና ከሌሎች አራት ግለሰቦች ጋር በመተባበር ሃምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመዋል፡፡

ተከሳሾቹ በዕለቱ በባንኩ የጥበቃ ስራ ላይ የነበረው ታሪኩ መንገሻ የተባለውን ግለሰብ እጅና እግሩን በማሰር የውንብድና ወንጀል ከፈፀሙበት በኋላ 419 ሺህ ብር ዘርፈው ወስደዋል፡፡

ፖሊስ የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት ከደረሰው በኋላ መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ በተለያየ ደረጃ ተጠያቂነት ያለባቸውን በአጠቃላይ ዘጠኝ ግለሰቦችን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ጭምር በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቄል ታግተዋል የሚል መረጃ እንደደረሰኝ ደወልኩላቸውና አነጋገርኳቸው። ''ሙከራ ተደርጓል። አሁን ግን ሰላም ነኝ። ማንነታቸውን የማላውቃቸው ሰዎች በመኖሪያ ቤቴ አከባቢ የሆነ ግርግር ፈጥረው ለመረበሽ ሞክረዋል። ምን እንደፈለጉ አላውቅም። አሁን የጸጥታ ሃይሎች መጥተው አረጋግተዋል። የሆነውን ነገር አጣርቼ እነግርሃለሁ'' አሉኝ።

ወደ ቅዱስ ሲኖዶሱም ደውዬ ነበር። እስከአሁን ምንም የሰሙት ነገር እንደሌለ ነገር ግን ጉዳዩን እንደሚያጣሩ አንድ አባት ገለጹልኝ። አቡነ ህዝቄል አንድ ከጠቆሙኝ ነገር የተረዳሁት ስርዓት አልበኝነት በአከባቢው መንገሱን ነው። የተደራጁ ሃይሎች የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለ ለማወቅ ችዬአለሁ። ከላይ አናት ሲነቅዝ ከታች የሚሆነው እንዲህ ነው!
Mesay Mekonnen

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሸኔና በመንግስት መካከል በታዛኒያ ሲደርግ የነበረው ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን አቶ ርድዋን ሁሴን በቲዊተር ገፃቸው አሳወቁ። ያልተስማሙት በየትኛው የድርድር ነጥቦች ላይ እንደሆነ አልገለፁም። ሸኔ የሽግግር መንግስት ይቋቋም፣ በኦሮሚያ እስካሁን የተደረጉ ግጭቶች በገለለተኛ አካል ተጣርቶ ተጠያቂነት ይስፈን፣ አዲስ አበባ አሁኑኑ ወደ ኦሮሚያ ክልል ትግባ፣ የኦሮምኛ ቋንቋ የፌዴራል መንግስት ቋንቋ ይሁን የሚሉ እንደሚገኙበት ሰሞኑን ሲጠቀስ መሰንበቱ ይታወሳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው የትጥቅ ውጊያ ምክንያት በሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮኖች የሚደርሱት ጥቃቶች አሳሳቢ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ጥቅምት 26 በዋደራ ወረዳ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሦስት መምህራንን ጨምሮ 7 ሰዎች፣ ጥቅምት 29 በምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋብር ከተማ በመነሃሪያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን የገለፀው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ በክልሉም ይሁን በሌሎች አካባቢዎች የቀጠሉ ያላቸው የመብት ጥሰቶችና የዘፈቀደ እሥሮች አሳሳቢነታቸው መጨመሩን አመልክቷል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ ይዘት ምን ይመስላል?

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል ግጭት ውስጥ ያሉት አካላት ሕገ ወጥ ካላቸው ጥቃቶች እንዲቆጠቡ እና በጦርነቱ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ሰላማዊ ሰዎችን ደህንነታቸውን እንዲጠብቁ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

በተለይ በሰሜን ምዕራብ አማራ እና ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች የዘፈቀደ እሥራትን ጨምሮ ቀጥሏል ያለው "የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የመብት ጥሰት በእጅጉ አሳሳቢ ነው" ሲል አስታውቋል።የድርጅቱ የሰብአዊ መብት ጽ/ ቤት በሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች እና ሌሎች ጥቃቶች በዚሁ ክልል አስከፊ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ጠቅሷል።በመንግስት ኃይሎች እየተወሰደ ባለው የድሮን ጥቃት ዋደራ ወረዳ የሚገኘኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ሦስት መምህራንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ስለመገደላቸው መግለጫው ያትታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጥንቃቄ ለወላጆች!

15 አመቱ ነው። ሳቢር ሬድዋን። አጋቾች ከቤት አባብለው አውጥተውት ካገቱት በኋላ ቤተሰቡን ከፍተኛ ብር ጠይቁ። ገዳዮቹ ገንዘብ እንኳን እስኪሰበሰብ አልጠበቁም። በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውት ሲያበቁ በሸገር - ጣዊል ሪልስቴት አካባቢ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ጥለውት ተሰውረዋል።

ሟች ተማሪ ሳቢር ሬድዋን ከአንዲት ሴት በተደጋጋሚ ስልክ ሲደወልለት እንደነበር። ደዋይዋ ደብዳቤ ልታደርስልኝ ስለምፈልግ ስልክህን ይዘህ ውጣ እንዳለችው ታውቋል፡፡ ሳቢር ስልክ ሳይዝ ደዋይዋ ወዳለችበት ቦታ መሄዱንና እዚያው መታገቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንዲህ አይነቱ ወንጀል ተስፋፍቶ የስራ እድል እስከመሆን ስለደረሰ ወላጆች ከባድ ጥንቃቄ ሊያርጉ ይገባል።
Zehabesha

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ ሃኪሞችን ለመቅጠር ቢፈልግም ተቀጣሪ በማጣቱ መሰረዙን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ 1ሺህ 1መቶ ሀኪሞችን ለመቅጠር ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ማስታወቂያ ቢያወጣም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ በጀቱን ወደ ሌላ ዘረፍ ማዛወሩን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ በሰኔ 2015 ላይ 1ሺህ 1መቶ ሀኪሞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ ቢሮዉ በጀቱን ለሌላ ጉዳይ ማዋሉን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ለ 2 ወራት ያክል ማስታወቂያዉን ክፍት ባደርግም ገበያ ላይ ተቀጣሪዎችን አላገኘሁም ብሏል ቢሮዉ፡፡

በየአንዳንዱ ጤና ተቋም ሀኪሞች መኖር ስላለባቸዉ ያንን ለማሟላት ማስታወቂያ ብናወጣም ሀኪሞችን ባለማግኘታችን በምትኩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን፣ አዋላጆችን እና ነርሶችን ለመቅጠር ተገደናል ነዉ ያሉት፡፡

ከዚህ በፊት ለመላዉ ኦሮሚያ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 72ሺህ ነበር ያሉት ሃላፊዉ አሁን ላይ ቁጥሩ ወደ 85ሺህ ከፍ ማለቱን ነግረዉናል፡፡

በተቻለን አቅም ማስታወቂያ አዉጥተን ገበያ ላይ የነበሩትን ለመዉሰድ ሞክረናል ነገርግን አሁንም የሀኪሞች ዕጥረት አለ ብለዋል፡፡

ማስታወቂያዉን አይተዉ የመጡትን እንቀጥራለን ፤ካልመጡ ግን ገበያዉ ላይ የሰዉ ሃይል እንደሌለ ነዉ የሚቆጠረዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሃላፊዉ በተጨማሪም ባለፈዉ ዓመት ሃኪሞችን ለመቅጠር ባወጣነዉ ማስታወቂያ ሀኪሞችን ማግኘት ስላልቻልን ወደ 7 መቶ አከባቢ የሚሆኑ የተለያዩ ባለሙያዎችን ቀጥረናል ሲሉም ነግረዉናል፡፡ (ኢትዮ ኤፍኤም)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሜሪካ የኢትዮጵያ ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱ አሳሰበች

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኔሊ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በስልክ ተወያይተዋል።

አብይ እና ብሊንከን ስ አማራና ኦሮሚያው ግጭት፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ፣ ስለ ትግራይ ሰላምና ቀጠናዊ ትብብር መነጋገራቸውን ውይይቱን አስመልክቶ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ብሊንከን የአማራና የኦሮሚያ ክልሉም ይሁን ሌሎች ግጭቶች በድርድርና ውይይት እንዲፈቱ ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተጠቁሟል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ትምህርትን በተመለከታ ባደረገዉ ጥናት 90% የሚሆኑት የአስር አመት ልጆች ማንበብ የማይችሉ ሲሆን ከአራተኛና አምስተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በትክክል ማንበብ የሚችሉት 1% ብቻ መሆናቸዉን አመልክቷል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"
"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘገባ ያሳያል።

ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ። በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።

በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘግቦታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ቀይባህር ጉዳይ ዝምታቸውን ሰበሩ❗❗
ኢሳይያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ ከአንድ የአረቢኛ ጊዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለምልልሳቸው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ስለቀይባህር ጉዳይ የሚከተለውን ብለዋል❗👇
ቀይባህርን የምንጋራ ሀገራት በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ነው የመለሱት።
የቀይባህር ዳርቻ ሀገራትን ሉዓላዊነት ለማስከበር እና የቀይባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ ከሆነ ከሌሎች ጣልቃ ገቦች ለመጠበቅ ያስችለናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ለሌሎች ሀገራትን ተጠቃሚነት በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ የቀይባህር ወደብን ለመጠቀም የሚፈልጉ ሌሎች ሀገራት በውይይት እና በምክክር ብቻ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰው ይህን ከማለም በፊት ግን በቀጠናው ያሉብንን የፀጥታ መደፍረስ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት ይኖርብናል ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
ለፈጣን ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join አድርጉ❗
ለሌሎች በመጋበዝ መረጃ እንዲያገኙ ያድርጉ(ከአክብሮት ጋር)👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በወልቂጤ ከተማ በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የ21 ዓመቷ ወጣት ራሳን አጠፋች።
#FastMereja
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን ማጥፋትዋ የዞኑ ፖሊስ ገለፀ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሶሬሳ ህንፃ ስር ከሚገኝ የግለሰብ ሞባይል ሴንተር ተቀጥራ የምትሰራዉ 21 ዓመቷ ወጣት መቅደስ መኮንን አራት የሞባይል ስልኮችን በ69 ሺህ ብር ለመግዛት ከፈቀዱ ሁለት ግለሰቦች የገዙበትን ክፍያ በሞባይል ባንኪንግ ሊያስተላልፉላት ትስማማና ገቢ የሚደረግበት አካዉንት ትሰጣቸዋለች።

ሁለቱ ግለሰቦች አካዉንቱን ተቀብለዉ ሞባይላቸዉን ከነካኩ በኋላ ስለመድረሱ ማረጋገጫ የሆነዉን ተጠናቋል (complete) የሚለዉን መልእክት ያሳይዋትና ሞባይላቸዉን ተረከበዉ ይሄዳሉ።

ወጣቷ አራት ሞባይል ስልክ የሸጠችበት ገንዘብ ገቢ መደረጉ ለማረጋገጥ ወደ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሄድ ስታረጋግጥ ገንዘቡ ገቢ አለመደረጉ ሲነገራት መታለሏን ታረጋግጣለች።

መጭበርበሯ ስታረጋግጥ እራሷን የምታጠፋበት መርዝ ገዝታ ወደ ቤቷ በማቅናት መርዝ ጠጥታ እራስዋን ስታ ተዝለፍልፋ ስትወድቅ በወጣትዋ አድራጎት የተደናገጡ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ህይወቷን ለማትረፍ ፈጥነዉ ወደ ሆስፒታል ቢያደርሷትም የጉዳት መጠኗ ከፍ ያለ ሆኖ ህይወቷ ወዲያዉኑ ማለፉ የጉራጌ ዞን ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አይደፈር መርሻ ገልፀዋል።

ወጣቷ በግለሰብ ሱቅ ተቀጥራ በመስራት ድህነቷን ለመርታት ነበር የምትፍጨረጨር የመኖርን ሚስጥር ገና በቅጡ ሳታጣጥም በሁለት ወንጀለኞቸ በተፈፀመባት መጭበርበር በእለተ ቅዳሜ ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም በ21 ዓመቷ ህይወቷ አልፏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የቦምብ ፍንዳታዎች በባሕር ዳር ከተማ

በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በተለያዩ አካባቢዎች የቦምብ ፍንዳታ መድረሱ ተሰማ ። የቦምብ ፍንዳታዎቹ ትናንት በተለይ ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 እና ቀበሌ 13 ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አካባቢ መድረሱ ተነግሯል ። በፍንዳታው በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም ተጠቁሟል ። በፍንዳታዎቹ ተማሪዎች መደናገጣቸው እና ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ቤት ለመውሰድ ሲሯሯጡ መታየታቸውን የባሕር ዳር ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ተናግሯል። ከፍንዳታው በኋላ ዛሬ በአንዳንድ ትምሕርት ቤቶች ፈተና ቢኖርም አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመሄዳቸውንም አክሎ ገልጿል ። ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ቀበሌ 14 አካባቢ በምሽት መጠጥ ቤቶች አካባቢ በተከታታይ ቀናት ፍንዳታዎች ነበሩ ተብሏል ። ሌሊቱን ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ ማር ዘነብ በተባለው ቀበሌ የተቀበረ ቦምብ ፈንድቶ ከፍተኛ ንዝረት መከሰቱንም ወኪላችን ገልጾልናል ።

DW

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ግንባታው ከ 50 % በላይ የደረሰ

☎️ +251986687513
☎️ +251987003603

በ 10 % ቅድመ ክፍያ

➢ ከ ወዳጅነት ፓርክ ጎን
➢ ከ CBE ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት
➢ ከ ኢትዮጵያ ፖስታ ጎን
➢ ከ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ጎን
➢ ከ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በ 1 Km ርቀት

👉 በሁሉም አቅጣጫ ተደራሽ የሆነ
የከተማችን ልብ ቦታ ላይ ያለ
እጅግ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር
በመሐል አዲስ አበባ ፍል ውሀ በተመጣጠነ ዋጋ ከ ባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ በማስታወቂያ ዋጋ ለሽያጭ ማቅረባችን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ።

👉 የ ቤተዎን ፊኒሽንግ አስጊጠው በማጠናቀቅ ይደሰቱ

ለበለጠ መረጃ
👇
☎️+251986687513
☎️+251916716110

WhatsApp:- +251916716110
Telegram :- @Girmagita
Email:- Yohannesmisganew5@gmail.com

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"ብዙ አክሲዮን ብገዛ ኖሮ!"

የሁሉም ባለአክሲዮኖቻችን ንግግር ነው

አያት አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም 51.3% ትርፍ ሲያተርፍ

የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የገዛ 513,000 ብር አትርፏል

የ 2 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የገዛ 1,026,000 ብር አትርፏል

የ 10 ሚሊዮን ብር የገዛ 5,130,000 ብር አትርፏል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2,500

በብር 250,000 ብር

ከፍተኛ የ 2 ሚሊዮን ብር

40% ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መክፈል ይችላሉ

በጊዜ ባለቤት ይሁኑ ፣ ብዙ ትርፍ ያግኙ

ለበለጠ መረጃ ፦ በ 0904607437 / 0919588894 ይደውሉ (ቀጥታ ወይም በዋትሳፕ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ለምግብነት እየቀረበ ነዉ በሚል ተሰራጭቷል በተባለው መረጃ ሳቢያ የዕለት ገበያቸዉ ከቀድሞ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ " ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ ከገበያዉ እንዲወጡ ሊያደርጋቸዉ እንደሚችል" ስጋታቸውን ለካፒታል ተናግረዋል ።

"አሁን እስከ 80 ሺህ ብር የተገዛው ሰንጋ በሬ ወደ ተጠቃሚዎች በሚቀርብ ጊዜ የአህያ ነዉ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እናስተናግዳለን" በዚህ ምክንያት ሳይሸጥ የሚያድርበት ቀናቶች በርካታ ናቸዉ" በማለት አስረድተዋል ።

ካፒታል ከገቢ አንፃር ምን ያህል አጣችሁ ? የሚል ጥያቄ ያቀረበላቸዉ ዮሐንስና በከረት የስጋ ሽያጭ ሉካንዳ ቤቶች እንደሚናገሩት " ከገቢ አንፃር ብቻ ሳይሆን በፊት ለገበያ የምናቀርበው ሁለት ሰንጋ ከብቶች በህጋዊ መንገድ በቄራ እርድ ተፈፅሞ ቢሆንም አሁን ግን አንዱን በትግል ነዉ የምንጨርሰዉ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚህ አኳያ ሲታይ ሁኔታዉ አሳሳቢ ነዉ የሚሉት ነጋዴዎቹ ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉ ማጣታቸዉን ገልፀው ከሃይማኖትም እንዲሁም ከስብዕና አንፃር ፀያፍ ነዉ ከባህላችንም አኳያ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ በማለት ድርጊቱን ኮንነዋል።

በመዲናዋ በህገወጥ እርድ እየተፈፀ ነዉ በሚለዉ ጉዳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያሳወቀዉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካልም እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት" ማሳወቁ ተሰምቷል።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አህዮች ቆዳቸዉ ተፈላጊ በመሆኑ ታርደው በአብዛኛው ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ውጭ በመላኩ ምክንያት በአህጉሪቱ የሚገኙ የአህዮች ቁጥር እየተመናመነ መሆኑን ካፒታል መዘገብ ይታወሳል።

ካፒታል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የድርድሩ አለመሳካትን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ሸኔ በማለት መንግስት የሚጠራው) መሪ ጃል መሮ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ጦሩን ይቀላቀላል ወይ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው። በተሰማው መረጃ መሰረት የአሜሪካ እና የኖርዌይ መንግስታት ለማደራደር ሲወስኑ ድርድሩ ካልተሳካ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ጦሩን እንደሚቀላቀል ዋስትና ስለሰጠው፣ የኢትዮጵያ መንግስትም ስለተስማማ ይመለሳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኬኒያ የ 12 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ከአለም ባንክ አግኝታለች። ኢትዮጵያ ላለባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ድጋፍ ብትጠይቅም ከጦርነት ባለመውጣቷ ይኸው ከጀርመን ባዶ እጃችንን የተመለስን ይመስላል። ፖለቲካን በመነጋገር ከመፍታት ወደ ሀይል እርምጃ መግባታችን ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀርመን ለቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ በተገኙበት ወቅት ተቃውሞ እንደደረሰባቸው የጀርመን ድምፅ ዶቾቬሌ ገለፀ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሶማሊያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኤርትራ አምባሳደር ሾመች።

ኤርትራ የሶማሊያ ምልምል ወታደሮችን የምታሰለጥን ሲሆን ይህ ሹመት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ያለበትን ጠንካራ ደረጃ የሚያመላክት ነው ተብሏል።

በሶማሊያ ላይ በማተኮር የሚሠሩ የህትመት ውጤቶች እንደዘገቡት ከሆነ ተሿሚው አምባሳደር ኦማር ኢድሪስ ይባላሉ። ዲፕሎማቱ ከዚህ ቀደም ሶማሊያን ወክለው በካታር በአምባሳደርነት አገልግለዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአገሪቱ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የሹመት ደብዳቤያቸውን ከተቀበሏቸው አስራ ዘጠኝ አምባሳደሮች መካከል አንዱ እኚሁ በሞቃዲሾ የተሾሙት ኢድሪስ መሆናቸውን የገለፀ ሲሆን በስነ ስርዓቱም ላይ አምባሳደሩ በታሪካዊ ሹመታቸው ከፍተኛ ክብር እንደተሰማቸው ገልፀዋል ብሏል። የቆየ መሠረት እና ረጅም ታሪክ አለው ያሉትን እና “ወንድማማቻዊ” ነው ብለው የገለፁትን በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በሚያንፀባርቅ መልኩ ጠንክረው እንደሚሰሩም አምባሳደሩ ተናግረዋል ብሏል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጫ። በሹመት ደብዳቤ የማቅረብ ስነ ስርዓቱ ላይ የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ እና የፕሬዚዳንታዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊው ኣሚን ሐሰን አብረው እንደተገኙ የመስሪያ ቤቱ ዘገባ ያሳያል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚዘገብ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃመድ ወደስልጣን ከመጡበት ካለፈው የፈረንጆች ዓመት አንስቶ ኤርትራን አራት ጊዜ ያህል ጎብኝተዋል።

ከአንድ ወር ገደማ በፊት አገሪቷን በጎበኙበት ጊዜ ሼክ መሃመድ ኤርትራ ያለምንም ክፍያ የአገራቸውን ጦር መልሶ በመገንባቱ ረገድ ከፍ ያለ ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገልፀው ትንሿን አገር አሞግሰው ነበር።


ኢትዮ ቲዩብ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል። የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርጓል።

በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤
2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤
3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10
• ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ)

4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ
• ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5
• ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000 - ብር 10
• ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000 - ብር 15
• ከብር 300,001 በላይ - ብር 20

5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡

• ከብር 50 በታች - ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500 - ብር 6.45
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 - ብር 7.60
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63
• ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተላለፈበት።
***
በታዳጊ ሜላት መሀመድ ላይ ጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር በመፈፀም የተከሰሰው አቶ ሳምሶን ሸኑ በዛሬው ዕለት (06/03/2016 ዓ.ም) የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተላልፎበታል።

Via:- መምህር እና ጠበቃ አበባየሁ ጌታ
Sheger Times Media

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሜሪካ በኢትዮጵያ አቋርጣው የነበረውን የምግብ እርዳታ ከመጪው ወር ጀምሮ ዳግም ልትጀምር መሆኑን አስታውቃለች

የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በሰኔ ወር ነበር የምግብ እርዳታ ከተቸገሩ ወገኖች ላይ ተሰርቋል በሚል እርዳታውን ያቋረጠው።

በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን፥ ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ማሳወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
https://am.al-ain.com/article/us-resume-food-aid-ethiopia

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮጵያን የባህር በር ያሳጣችው ህወሓት በባህርበር ጉዳይ ምን አቋም እንያዝ ብላ እየመከረች መሆኑ ተገለፀ። በቀጠናው እየተጠነሰሰ ባለው የስጋት ደመና ሚናችን ምን መሆን አለበት የሚለው ዋነኛ የውይይቱ አላማ ነው ተብሏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአገልግሎት ላይ ሳሉ በጥይት የተመቱትን አስተዳዳሪ በሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ !

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም በአገልግሎት ላይ ሳሉ በጥይት የተመቱትን መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ በሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ የቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ በደብሩ ለሁለት ቀን በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት የዓውደ ምህረት አገልግሎት ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ ነው ብፁዕነታቸው ለጥየቃ በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የተገኙት።

ብፁዕነታቸው ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እንደሚነጋገር ገልጸው ለአገልጋዮች ነገ ዋስትና እንዲኖራቸው መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በተፈጸመው ድርጊት የተደፈረችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት ብለዋል ብፁዕነታቸው አቡነ ሄኖክ ፤ ብፁዕነታቸው በሆስፒታሉ የሚገኙ ሌሎች ሕሙማንንም የጎበኙ ሲሆን ቡራኬ በመስጠት ሕሙማኑ ፈጥነው ያገግሙ ዘንድ ጸሎት አድርሰዋል።

ዘገባው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

እነ ጃል መሮ ለፖለቲካዊ መፍትሔ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

መንግሥት "ሸኔ" ብሎ በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ ለመፈለግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በእነ ጃል መሮ ድሪባ የሚመራው ታጣቂ ኃይሉ፣ ከመንግሥት ጋር እያደረገ ስላለው ድርድር አጭር መረጃ አውጥቷል።

በታንዛኒያ ደሬ ሰላም በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር፣ የሁለቱ ወገኖች ድርድር እንደቀጠለ ነው።

በዚህኛው ድርድር የታጣቂ ኃይሉ መሪ ጃል መሮና ምክትሉ ጃል ገመቹ አቦዬ እየታሰተፉ መሆኑ ተጠቁሟል።

የድርድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ ታጣቂ ኃይሉ መረጃ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በቀጠለው ድርድር መንግሥትን ወክለው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት ወታደራዊ አመራሮች፣ በተጨማሪ የፖለቲካ አመራሮች መጨመራቸው ተሰምቷል።

ድርድሩን ዘግይተው በትላንትናው ዕለት የተቀላቀሉት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ናቸው።

Via Andafta

Читать полностью…
Subscribe to a channel