muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

የሱማሌያው ኘሬዝዳን ከጂቡቲ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን አየር ክልል ላለመጠቀም ወይም ለመሸሽ በሶማሌ ላንድ በኩል በማለፍቸው ሶማሌ ላንድ የአየር ክልሌ ተጥሷል በማለት ከሳለች

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶማሌላንድን ሉዓላዊ የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሰው በመግባት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የሶማሊላንድን የግዛት መብቶች በመጣስ እየተካሰሱ ነው።

ፎከር 70 5Y-KBX በሚል ስም የተመዘገበ እና በኬንያ አየር መንገድ ስካይዋርድ ኤክስፕረስ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ከሶስት ሰአት በፊት የሶማሌላንድን የአየር ክልል አልፎ ወደ ሞቃዲሾ ሲመለስ የኢትዮጵያን ግዛት በመሸሽ ነው።

ሶማሊያላንዳዊያን<< ይህ ያልተፈቀደ ወረራ አፋጣኝ እርምጃ ይጠይቃል። አየር መንገዱ ይህንን ጥሰት በማቀላጠፍ ቅጣት ሊጣልበት ይገባል፤ ወደፊትም የሶማሊያ ባለስልጣናት የሶማሌላንድን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ መታገድ አለባቸው። የሶማሌላንድ አየር ክልል ሉዓላዊ ነው፣ እና ማንኛውም ያልተፈቀደ አጠቃቀም የራስ ገዝ ግዛቷን እና አስተዳደርን የሚነካ ነው። ብለዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ካናል+ ኢትዮጵያ ስርጭቱን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን አስታወቀ።

#CanalPlus #Ethiopia

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በግሩፕ ለምትመጡ ቅናሽ አለ❗️

(ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት )

ሁሉንም ህጋዊ መረጃ ያሟላ ሪልስቴት

ቴምር ሪልስቴት

ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

👉ባለ 1 መኝታ 66 ካሬ ጀምሮ እስከ 142 ካሬ 3 መኝታ

👉 10% ቅድመ ክፍያ ከ 693,000 ብር እስከ 1,365,000 ብር

👉ቀሪውን 90% በ17 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

💥 30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ 0961770077
0908770077

ዋትሳፕ ሊንክ - https://wa.me/251961770077?text

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

ዛሬ ታህሣስ 20/2017 ዓ.ም ከሰአታት በፊት ረዘም ላሉ ሰከንዶች የቆየውና አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዋሽ ፈንታሌ ከማለዳው 12:58 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ ተመዝግቧል 10km ጥልቀትም እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ።

ሰሞኑን ተከታታይ ቀናት እየተከሰተ እንደሚገኝ ይታወቃል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ መሆኑንም ነው በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ለፋና ዲጂታል ያረጋገጡት፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለትም በዚሁ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን አውስተው÷ ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንከር ማለቱን አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም ገብረ እየሱስ እስራኤል ጥቃት እየፈጸመች በነበረችበት በየመኑ ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንደነበሩ ገለጹ። በጥቃቱ አንድ የአውሮፕላኑ ሰራተኛ ተጎድቷል።
"ከሁለት ሰዓታት በፊት፣ ከሰንዓ ለመብረር ወደ አውሮፕላኑ ልንሳፈር ስንል አየር ማረፊያው የአየር ጥቃት ተፈጸመበት" ብለዋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በ84 ኮሌጆች የሚማሩ ተማሪዎች፤ እስከ ጥር ወር መጀመሪያ ወደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት እንዲዘዋወሩ ትዕዛዝ ተሰጠ

የፌደራል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ 84 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እስከ መጪው ጥር ወር መጀመሪያ ድረስ ተማሪዎቻቸውን ፈቃድ ወዳላቸው ተቋማት እንዲያዘዋውሩ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ባለስልጣኑ ይህንን ትዕዛዝ የሰጠው፤ በድጋሚ ሳይመዘገቡ ለቀሩ እና በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን ለማቋረጥ ለወሰኑ ኮሌጆች ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባወጣው “አዲስ ስታንዳርድ” መሰረት፤ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቦ የነበረው ባለፈው መስከረም ወር መጀመሪያ ነበር።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀስ ማንኛውም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን ለመስሪያ ቤቱ የሰጠው በ2014 ዓ.ም. የተሻሻለው የባለስልጣኑ ማቋቋሚያ ደንብ ነው።

መስሪያ ቤቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ፈቃድ ወይም እድሳት የመሰረዝ ስልጣንም በዚሁ ደንብ አግኝቷል።

በዚሁ መሰረት 84 የሚሆኑ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት “ከከፍተኛ ትምህርት የፈቃድ ስርአት እንዲወጡ” የሚያደርጋቸውን ውሳኔ ባለስልጣኑ ከሁለት ሳምንት በፊት አስተላልፏል።

ዘጠኝ በሚሆኑ የትምህርት ተቋማት ላይም ተመሳሳይ ውሳኔ በቅርቡ እንደሚተላለፍ ከባለስልጣኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2024/14683/

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ድርጅችችን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በታህሳስ 14፣ 2017 በተጻፈና በ ታህሳስ 16 2017 ዓ/ም እጃችን በገባ ደብዳቤ መሰረት ከየትኛውም እንቅስቃሴ ታግዷል፡፡ ለበለጠ መረጃ የተያያዘውን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡

Our Organization, Ethiopian Human Rights Defenders Center has been suspended by the Authority of Civil Society Organizations (ACSO). We are following up on the matter and contacting the authority for further information. We are attaching our short statement on the matter for additional clarity.
አቶ ያሬድ የፃፉት ነው

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሐዱ ራዲዮና ቴሌቭዥን የፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ ቃለመጠይቅ ላለማስተላለፍ መወሰኑን የጣቢያው የቅርብ ምንጮች ለድሬቲዩብ ገልፀዋል።

አሐዱ ቃለመጠይቁን በኬንያ ናይሮቢ ተገኝቶ ከሰራ በኋላ እንደሚያስተላልፍም ማስታወቂያ ማስነገሩን አስታውሶ ሆኖም
አቶ ጀዋር ለቢቢሲ አማርኛ ተመሳሳይ ቃለመጠይቅ በመስጠቱ ምክንያት ለዚህ ውሳኔ እንዳበቃው ተጠቁሟል።

ከጣቢያው በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

አቶ ጀዋር መሐመድ ከሰዓታት በፊት በማኀበራዊ ድረገፁ ባሰፈረው ሐተታ ቃለመጠይቁ ሳይከለከል እንዳልቀረ በመጥቀስ ቃለመጠይቁን በአማራጭ ሚድያ ለመልቀቅ እንደሚገደድ ፅፏል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በግሩፕ ለምትመጡ ቅናሽ አለ❗️

(ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት )

ሁሉንም ህጋዊ መረጃ ያሟላ ሪልስቴት

ቴምር ሪልስቴት

ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

👉ባለ 1 መኝታ 66 ካሬ ጀምሮ እስከ 142 ካሬ 3 መኝታ

👉 10% ቅድመ ክፍያ ከ 693,000 ብር እስከ 1,365,000 ብር

👉ቀሪውን 90% በ17 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

💥 30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ 0961770077
0908770077

ዋትሳፕ ሊንክ - https://wa.me/251961770077?text

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

Crypto ወደፊት የመገበያያ ገንዘብ መሆኑ አይቀርም እየተባለ ነው‼️
አሁን ላይ ጥሩ ፕሮጀክት ነው የተባለው star project ሲኋን ካሁኑ ጀምራችሁ ብሰሩት ይመከራል፣ከስር በተቀመጠው ሊንክ start በማለት ሽልማት ያሸንፉ👇👇❗
/channel/Stars_MeBot/stars?startapp=473382500

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሶማሊያ አቻው ትናንት በሶማሊያ ዶሎ ከተማ በኢትዮጵያ ሀይሎች ጥቃት ተሰነዘረብኝ ያለውን መግለጫ አስተባበለ። ክስተቱ የተፈጠረው የአንካራ መግለጫን ያልደገፉ ሰላም የማይፈልጉ ሀይሎች የፈጠሩት ነው ብሏል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ ዛሬ ሰኞ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የዛሬው ምሽት ርዕደ መሬት፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአካባቢው ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ነው። ትላንት ለሊት 10 ሰዓት ከ13 ደቂቃ አካባቢ፤ ከአዋሽ ከተማ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር በመላው ዓለም የደረሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚመዘግቡ ተቋማት ያወጧቸው መረጃዎች አመልክተው ነበር።

የትላንት ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ የመዘገቡ እነዚሁ ተቋማት፤ መጠኑ መጠነኛ የሚባል እና በሬክተር ስኬል 4.6 የሚለካ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል። ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 14፤ 2017 ምሽት 4 ሰዓት ከ40 ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ በአዋሽ አካባቢ ከተመዘገበው ርዕደ መሬት ጋር በመጠን እኩል ነው።

በአፋር ክልል የሚገኘው የአዋሽ አካባቢ፤ ባለፈው መስከረም እና ጥቅምት ብቻ 10 የመሬት መንቀጥቀጦችን አስተናግዷል። በአካባቢው እስካሁን የተመዘገበው ከፍተኛ የርዕደ መሬት መጠን፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በመዲናዋ በስድስት ክፍለ ከተሞች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው፥ ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡

አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱ ተጠቁሟል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ ስድስት ክ/ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተመላክቷል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።

(መላኩ ገድፍ -ኤፍ ኤም ሲ)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የአሜሪካ ኤምባሲ በአማራ ክልል ያለው የረሀብ ሁኔታ አሳሳቢነቱን ገለፀ። በተለይ በሰሜን ወሎ ያለውን ከባድ መሆኑን ገልፇል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
🔴አንኳን ደስ አላችሁ 🔴

በ 2016 ዓ.ም 45% ትርፍ /Dividend/ አትርፈናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0942585355 ይደውሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

አሳዛኝ ዜና‼️
ዛሬ 20/04/2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አደጋ ከ60+ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ‼️
አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና ከ60+ የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ብለዋል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እንደሚችል የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል።
======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሹመት‼️

የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ምክትል አዛዥ የነበሩት እና በቅርቡ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈፀሙት አቶ ጃል ሰኚ ነጋሳ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ቢሮ ሐላፊ በመሆን በዛሬው መሾሙ ተዘግቧል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገሪቱ አየር ክልል ውስጥ የተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን ላይ ለደረሰው አሰቃቂ አደጋ ይቅርታ ጠየቁ።

የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭን ይቅርታ የጠየቁት ፑቲን “አሳዛኝ ክስተት” ያሉት የአውሮፕላን መከስከስ በመፈጠሩ እና በአደጋው ምክንያት ለጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎችም በቶሎ እንዲያገግሙ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ክሬምሊን ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ጥቃት በመፈጸም ላይ የነበሩ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ የሩሲያ አየር መከላከያ ጥቃቱን የመከላከል ስራ አየሰራ እንደነበር መግለጹን አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ይሁን እንጂ የአዘርባጃኑ አውሮፕላን በስህተት በሩሲያ የአየር መከላከያ ኃይል ተመትቶ ይሁን አይሁን ተገለጸ ነገር የለም።

62 መንገደኞችንና አምስት ሠራተኞችን ያሳፈረ የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ ባሳለፍነው ረቡዕ ተከስክሶ የ388 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምርጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቻናል ይቀላቀሉ! በፍጥነት ይማራሉ! 

If you Plan to pursue a scholarship, pharmacy license, or dental school in the USA or Canada? Taking the TOEFL test is mandatory, and the TOEFL ZONE is here to guide you. With expert preparation and personalized support, we’ll help you achieve the scores you need. Start your journey with us today!


👇👇👇Join👇👇👇

/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ሊጠናቀቅ ነው‼️
ይህ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ አምስት ቀን ነው የቀረው፣ከስር በተቀመጠው ሊንክ start በማለት የፈረንጆች 2025 ሽልማት ይውሰዱ❗👇👇
/channel/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=7nLeTc0P

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ የታገዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደረሰ 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” ያላቸውን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ አገደ። ባለስልጣኑ ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያገዳቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቁጥር አራት ደርሰዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁለቱን ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያገደው፤ ከትላንት ረቡዕ ታህሳስ 16፤ 2017 ጀምሮ እንደሆነ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ለድርጅቶቹ በትላንትናው ዕለት በላከው ደብዳቤ ለእግድ ያበቃቸውን ምክንያት ዘርዝሯል። 

ሁለቱም ድርጅቶች “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ” እና “ኃላፊነት በጎደለው መልኩ” በመንቀሳቀስ እንዲሁም “ገለልተኛ ባለመሆን” በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

እነዚህ ውንጀላዎች ባለፈው ሳምንት በድጋሚ እንዲታገዱ በተደረጉት፤ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች (LHR) በተባሉት ድርጅቶች ላይም በምክንያትነት ተጠቅሷል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14668/

@EthiopiaInsiderNews

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

“ማህበረሰቡ ለተደራረበ የግብር ጫና እየተጋለጠ ነው” የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንበረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በውይይቱ ላይ ሃሳበቸውን የገለጹት የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ ( ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የኤክሳይዝ ታክስ አሻሽለናል ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስም እንደዛው አሁን ደግሞ የንበረት ታክስ ይጠበቃል ይህ ደግም ህዝቡን ለተደራረበ የግብር ወጪ መዳረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ተደራራቢ በሆኑ የታክስ ማሻሻያዎች በስፋት የሚጎዳው መካከለኛውን እና ዝቅተኛውን የህበረተሰብ ክፍል ነው ብለዋል፡፡

ነጋዴው ማህበረሰብ ቢያንስ መቋቋም ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“በዚህም ማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እና መማረር እንዳይፈጥር ስጋት አለን” ሲሉም የምክር ቤቱ አባል በውይይቱ ላይ ሃሳባቸውን ግልጸዋል፡፡

“የንብረት አዋጁ ግብሩ የሚጣለው የተሻለ ገቢ ባለው ላይ ነው የሚጣለው ይላል ኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ ገቢስ ስንት ነው” ሲሉ የምክር ቤቱ አባል አንስተዋል፡፡

ውይይቱ እንደቀጠለ ሲሆን አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ግልጽ በሆነ መልኩ ህዝቡን ማወያየትም ይጠበቃል ሲሉም የምክርቤቱ አባላት ሃሳባቸውን እየሰጡ ይገኛል፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

Crypto ወደፊት የመገበያያ ገንዘብ መሆኑ አይቀርም እየተባለ ነው‼️
አሁን ላይ ጥሩ ፕሮጀክት ነው የተባለው star project ሲኋን ካሁኑ ጀምራችሁ ብሰሩት ይመከራል፣ከስር በተቀመጠው ሊንክ start በማለት ሽልማት ያሸንፉ👇👇❗
/channel/Stars_MeBot/stars?startapp=473382500

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

“ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱልን ስራ የማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን” የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አባል ማህበራት፡፡

“ይህንን ማድረግ ሳያስፈልግ መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን፡፡” ኢሰማኮ

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በመንግስት እንዲወሰንና ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው #ከፍተኛ_ግብር እንዲቀንስ መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ ባለመስጠቱ ከዚህ በኋላ ሰራተኞች ወደ ስራ ማቆም አድማና ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያመሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ይወክላሉ ከሚባሉት አባላቱ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት አድርጎት በነበረው ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አባላቱ ባወጡት የአቋም መግለጫ፤ እስካሁን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎቻችን በመንግስት ባለመመለሳቸው ከዚህ በኋላ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንገደዳለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አያሌው አህመድ ነግረውናል፡፡

#የኢትዮጵያ_ሰራተኞች ወኪል ተደርገው የሚታዩት እነዚህ የኮንፌደሬሽኑ አባላት በአቋም መግለጫቸው ያሰፈሩት ወደ ተግባር ከማስገባታቸው በፊት ኮንፌደሬሽኑ ምን ለማድረግ አስቧል? ላልናቸው አቶ አያሌው ሲመልሱ፤ ሰራተኞቹ ወደዚህ ተግባር ከመግባታቸው በፊት የኮንፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመንግስት ምላሽ ለማግኘት የራሱን ጥረት ያደርጋል ብለውናል፡፡



ኮንፌደሬሽኑ ከ2,300 በላይ ተቋማትን በስሩ የያዘ ነው፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምርጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቻናል ይቀላቀሉ! በፍጥነት ይማራሉ!
በብዙዎች የውጭ ትምህርት ስኮላርሺፕ እድል ያገኙ ተማሪዎች እጅግ የተመሰገነ 😍 በአሜሪካና ካናዳ ስኮላሺፕ አግኝተው የሄዱ ዘውትር ለወዳጆቻቸው የሚጦቁሙት ምርጥ የቴሌግራም ቻነል 👌

If you Plan to pursue a scholarship, pharmacy license, or dental school in the USA or Canada? Taking the TOEFL test is mandatory, and the TOEFL ZONE is here to guide you. With expert preparation and personalized support, we’ll help you achieve the scores you need. Start your journey with us today!

👇👇👇Join👇👇👇

/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከሶማሊያ መንግሥት በቀረበ ጥያቄ መሠረት ግብፅ በሰላም አስከባሪ ሚሽን ውስጥ ለመካተት ወስናለች" ሲሉ የውጭ ገዳይ ሚኒስትሩ ባድር አብድላቲ በጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ

በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0942585355 ይደውሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

​በ2018 ከተደረገው የትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን ውይይት በኋላ በኮሪያ ንፍቀ ክበብ የነበሩት የመረጋጋት ተስፋዎች በነው ጠፍተዋል፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ በአካባቢው የሚታየ ውጥረትም ዓለም እስካሁን ከተመለከታቸው ጦርቶች ሁሉ አጅግ የከፋውን ሊያስመለክት የሚችልበት እድል የሰፋ አድርጎታል፡፡ በአንድ በኩል በሰሜን ኮሪያም በሌላ በኩል በአሜሪካ የሚመራው ሀይል አየቀሬ ለሚመስለው ጦርነት ዝግጅቱን አጣጡፏል። ቀጣዩን የዩትዩብ ገፅ ስትከፍቱም አሜሪካን ቀለበት ውስጥ የከተቱትን የፒዮንግያን ሚሳኤሎች ጨምሮ የሁለቱን ሀይሎች ዝርዝር ወታደራዊ አቅም በተመለከተ አስገራሚ መረጃዎችን ታደምጣላችሁ። 
https://youtu.be/Aen73SjeOqo?si=QZUzXQeI7v-AeBv0

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የሐሙስ ምሽት የዋዜማ ዕለታዊ ዜና

1፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ የኢላሙ ቀበሌ አሥተዳዳሪ ክፍያለው ነጋሽ አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ትናንት በቢሯቸው አካባቢ በፈጸመው ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ሰምታለች። ከአሥተዳዳሪው ጋር የነበሩ በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ቆስለው ለሕክምና ወደ ፍቼ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በደገም ወረዳ ሐምቢሶ ከተማ አማጺ ቡድኑ ትናንት ሌሊት በፈጸመው ጥቃት አንድ የሚሊሻ አባል ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ሌሎች በርካቶች ታፍነው መወሰዳቸውን ዋዜማ ተረድታለች። በገርበ ጉራቻ ወረዳ ኩዩ ከተማም በተመሳሳይ ሰዓት ቡድኑ የአፈና ድርጊት መፈጸሙን ዋዜማ ተረድታለች። ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠረ ግድያና ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል።

2፤ ንግድ ባንኮች በየዓመቱ የሚሰጡት ብድር ዕድገት አኹን ካለበት 14 በመቶ ወደ 18 በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። ብሔራዊ ባንክ በ2015 ዓ፣ም ባንኮች የሚሰጡት ብድር ከ14 በመቶ እንዳበልጥ ገደብን አስቀምጦ ነበር። መንግሥት ባንኮች የሚሰጡትን ብድር ለመጨመር የወሰነው፣ ገደቡ ኢንቨስትመንትና ሥራ ፈጠራ እንዳይጎዳና የ8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት በማሰብ እንደሆነ ታውቋል። ባንኮች የሚሰጡትን የብድር ምጣኔ የሚጨምረው መመሪያ፣ በውይይት ከዳበረ በኋላ ሊተገበር እንደታቀደ አንድ የባንኩ ምንጭ ተናግረዋል። ዋዜማ ራዲዮ ያነጋገረቻቸው የኹለት ባንክ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ግን፣ ዋናው መፍትሄ መኾን ያለበት ባንኮች ለብድር በሚያውሉት ገንዘብ ላይ ያለውን ከፍተኛ ዕጥረት መፍታት ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

3፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የዓለማቀፍ ወንጀል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አምባሳደር ቤዝ ቫን ስካክ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የመብት ጥሰት የሚከሰሱ ባለሥልጣናትንና የሠራዊት አዛዦችን ከሥልጣን እንዲያነሳ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ምክር ለግሰዋል። ሃላፊዋ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭት እየቀጠለና የሲቪክ ምኅዳሩም በጠበበበት ኹኔታ የሽግግር ፍትህ መተግበር "አስቸጋሪ" ወይም "የማይቻል" እንደሚኾን ስጋታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቶቹን በመፍታት ኹሉን ዓቀፍ የሽግግር ፍትህ ለማካሄድ ምን ዓይነት ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደኾነ ይፋ እስኪያደርግ አሜሪካ እየጠበቀች መኾኗን የገለጡት ሃላፊዋ፣ አንዱ ትልቅ ርምጃ በቅድሚያ ጥሰት ፈጻሚዎችን ከመንግሥት ሃላፊነት ላይ ማንሳትና ለጥፋቶች በይፋ ዕውቅና መስጠት እንደኾነ ጠቁመዋል። ሃላፊዋ፣ መንግሥት በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በሠራዊቱ ውስጥ ያሉ ጥፋተኞችን ተጠያቂ አድርጌያለኹ ያለበት ሂደት ግልጽነት ይጎድለዋል በማለት ተችተዋል።

4፤ የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን፣ በትግራይ ክልል ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ5 ሺሕ 728 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ አስፈትቶ ከማኅበረሰቡ ጋር ማቀላቀሉን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኮሚሽኑ ወደ ተሃድሶ ማዕከል ያስገባቸው የቀድሞ ተዋጊዎች 6 ሺሕ 625 እንደኾኑ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ባኹኑ ወቅት ለ889 የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት የመቐለ እና የዕዳጋ ሐሙስ ማዕከላት እንደኾኑና በአደዋ አካባቢ የሚገኘው ሦስተኛውን ማዕከል ለሥልጠና ክፍት ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንደኾነ ተገልጧል። በየካቲት ወር መጨረሻ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺሕ የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ ይቀላቀሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።

5፤ የኦፌኮ አመራር ጃዋር ሞሐመድ፣ መንግሥት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል የሰላም ድርድርና ንግግር እንዳይመጣ ዋነኛ ጋሬጣ ኾኗል በማለት ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከሷል። የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ሰዎች "ራሳቸውን ብቻ ሳይኾን አገር ይዘው ሊወድቁ" እንደሚችሉ ያስጠነቀቀው ጃዋር፣ የአገሪቱ የመፈራረስ አደጋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሎ እንደሚያምንም ተናግሯል። ጃዋር በቀጣዩ ምርጫ ይሳተፍ እንደኾነ ለቀረበለት ጥያቄም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ባኹን ወቅት ምርጫ ቅንጦት እንደኾነ በመጥቀስ፣ ምርጫ ሊካሄድ የሚችለው መንግሥት የሚቆጣጠረው ቦታ ሲኖር እንደኾነ አስተያየቱን ሰጥቷል። ጃዋር በዚኹ ቃለ ምልልሱ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጅምሩም አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር ፍላጎት እንዳልነበራቸው አውቅ ነበር ብሏል።

6፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከመሠረተ ልማቶቹ የተሠረቁ ብረቶች መዳረሻቸው ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ናቸው በማለት መክሰሱን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ተቋሙ፣ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ለውስጥ መመሪያቸው ተገዥ እንዲኾኑና ከተቋሙ የተዘረፉ ብረቶቶችን መግዛት እንዲያቆሙ ጠይቋል። በኃይል መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ ባለፉት አምስት ዓመታት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሄዱን የጠቀሰው ተቋሙ፣ በ2015 እና 2016 በጀት ዓመቶች በመሠረተ ልማቶቹ ላይ በተፈጸሙ ሥርቆቶች 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንደከሠረ ገልጧል ተብሏል።

7፤ ሩሲያና ኢራን በሱዳኗ ፖርት ሱዳን ወደብ ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያዎችን ለማቋቋም ባለፉት ጥቂት ወራት ከአገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት ጋር ንግግር ሲያደርጉ እንደቆዩ ከምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶችና ከሱዳን የደኅንነት ባለሥልጣናት መስማቱን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘግቧል። ሩሲያ ቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያ እንድታቋቁም ከተፈቀደላት፣ በምላሹ የሱዳን ጦር ሠራዊትን በዘመናዊ የጸረ-ሚሳይል ቴክኖሎጂ ለማስታጠቅ ዝግጁ መኾኗን ገልጣ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። ኾኖም የሱዳን ባለሥልጣናት፣ ሩሲያና ኢራን ፖርት ሱዳን ላይ የባሕር ኃይል ጣቢያ እንዲገነቡ መፍቀድ፣ ከምዕራባውያን ኃያላን አገራት ጋር ያጋጨናል ብለው ስላሰቡ ሃሳቡን ለጊዜው አልተቀበሉትም ተብሏል። ሩሲያ እስካለፈው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወታደራዊ ድጋፍ ስታደርግ የነበረ ቢኾንም፣ ባኹኑ ወቅት ግን ወታደራዊ ድጋፎችንና የስለላ መረጃዎችን እየሰጠች የምትገኘው ለጦር ሠራዊቱ እንደኾነ የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel