muktarovichousmanova | Unsorted

Telegram-канал muktarovichousmanova - Muktarovich Ousmanova

71256

Ethiopia forever

Subscribe to a channel

Muktarovich Ousmanova

የሊቢያ ታጣቂዎች ያገቷት ኢትዮጵያዊቷ፣ነሒማ ጀማል፦
ከቢቢሲ የተመዘዘ፦

ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው።

* ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ኩፍራ በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።
ነሒማ በፎቶዎቹ እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች።

* የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል፤ 'ነሒማ ከስምንት ወራት በፊት ነበር ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ የተሰደደችው!' ስትል ለቢቢሲ ትናገራለች። "ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ይልኩልናል። ስትሰቃይ ያሳዩናል። የድምፅ መልዕክትም ልከውልናል። እህታችን 'ገንዘብ ላኩላቸው ካልሆነ ይገድሉኛል' ስትል ይሰማል።"

* ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ የተባለው በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም እንደሚለው የ20 ዓመቷ ነሒማ ጀማል ባለፈው ግንቦት ሊቢያ ከገባች ከቀናት በኋላ ነው በታጣቂዎቹ እጅ ውስጥ የገባችው። በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ስቃይ ሲደርስባት እና ስትደበደብ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ለቤተሰቦቿ ተልከዋል።

* ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እርዳታ ቢጠይቅም እስካሁን ድረስ ሊሞላላቸው አልቻለም። "ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል።"

* አጋቾቹ ለነሒማ ማስለቀቂያ የጠየቁት ገንዘብ 6 ሺህ ዶላር ነው። የነሒማ ቤተሰብ ይህን ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።

* ለነሒማ ቤተሰብ የተላኩ ቪዲዮዎች በርካታ ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ያሳያሉ።
ነሒማ እጅና እግሯ ተጠፍሮ፤ አፏ በጨርቅ ታፍኖ ትታያለች። ስቃይ ሲደርስባት እና ደም በደም ሆና የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና ፎቶዎችም አሉ።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ደብዳቤ ተላከላቸው

(መሠረት ሚድያ)- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫውቸን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡

ሪፖርተር የተመለከተውና ከአንድ ሳምንት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ድንበር ውስጥ ለሚያደርጓቸው ማናቸው እንቅስቃሴዎች ቅድመ ፈቃድ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡፡

በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች በተመለከተ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተቀመጠ የቅድሚያ ማሳወቂያ ፎርም ከሞሉ በኋላ መሆን እንዳለበት አመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተጻፈው ደብዳቤ ማስጠንቀቂያው ለሥራ ወይም ለግል ጉዳይ የሚጓዙትን እንደሆነ በግልጽ አያስረዳም፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ከዚህ ተመሳሳይ ድበዳቤ ተጽፎ የነበረ ቢሆንም፣ አንዳንድ ዲፕሎማቶች አሁንም ከፌዴራል መንግሥቱ ዕውቅና ውጭ ሲንቀሳቀሱ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከዓመት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ ክልሎች በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ብቻ በተሰጠው የውጭ ግንኙነት ሥራ ላይ እየተሳተፉ በመሆኑ ፓርላማው ማሳሰቢያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ በኢትዮጵያ አዋሽ አፋር አካባቢ በሬክተር መለኪያ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬ ረቡዕ፣ ጥር 8 ቀን 2025 በማለዳ፣ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3፡53 (9:53 በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር) ላይ በ10 ኪ.ሜ ጥልቀት ተከስቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ ትክክለኛ መጠን እና ጥልቀት በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ወይም ደቂቃዎች ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች መረጃውን ሲገመግሙ እና ስሌቶቻቸውን ሲያጠሩ ወይም ሌሎች ኤጀንሲዎች ሪፖርታቸውን ሲያወጡ ሊከለስ ይችላል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር በህዝብ ግፊት ስልጣናቸውን ለቀቁ

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሊበራል ፓርቲው መሪ ጀስቲን ትሩዱ ከስልጣናቸው መልቀቃቸውን ዛሬ አስታወቁ፡፡

አስር ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሀገሪቱን ያስተዳደሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከስልጣን መልቀቃቸውን ያስታወቁት ለቀናት የዘለቀውን የህዝቡን የስልጣን ልቀት ግፊት ተከትሎ ነው፡፡

የምግብ እና የቤት ዋጋ ንረትን ተከትሎ ከህዝቡ ከፍተኛ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው የነበሩት ትሩዱ፣ ከስልጣን እንዲወርዱ ለሳምንታት ግፊት ሲደረግባቸው ቢቆይም ጉዳዩን በዝምታ ሲያልፉ ቆይተዋል፡፡

የፋይናንስ ሚኒስትራቸውም ከሳምንታት በፊት በድንገት ከሥራቸው በፈቃዳቸው ለቅቀዋል፡፡

እኤኤ በ2015 የተካሄደውን የካናዳ ምርጫ ተከትሎ፣ የአገሪቱን የሊበራል እሴቶች በማስጠበቅ ሲሞካሹ የነበሩት ጠቅላይ ሚነስትር ትሩዶ፣ ዝናቸው ቀስ በቀስ እየተቀዛቀዘ መሄዱ ታውቋል፡፡ ውሳኔያቸው ካናዳ በከባድ የፖለቲካ ቀውስ መግባቷን እንደሚያመላክትም እየተነገረ ነው።

ዘገባው የታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ነው

#GazettePlus

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም ድካም ማረፍ በጣም አዝኜአለሁ። ነፍስ ይማር 😢

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ባህር ዳር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 6 ሰወች ብሎ ፋና ቢዘግብም ከ14 ሰው በላይ ህይወት አልፏል የሚል መረጃ ነው ያለን የአደጋው መንስኤ የህዝብ አባዱላ ከትራፊክ ለማምለጥ ያለ መስመሩ በመግባት ሲሮጥ በተቃራኒ መስመር ከሚመጣ ሲኖ ጋር በፈጠረው ግጭት ነው ::

በእኛ በአሽከርካሪዎች እንዝላልነት ከልክ ያለፈ ፍጥነት በህግ ጥሰት ብዛት ያለው ህዝብ ለሞት ንብረት ለውድመት ለአካል ጉድለት እየተዳረገ ይገኛል::

ይህ አሽከርካሪ ትርፍ ጭኖ ከሆነ ቅጣቱ 1500 ብር ብቻ ነው ይህንን ላለመቀጣት በፈጠረው ህግ ጥሰት ግን ፋና የ6 ሰዎችን ህይወት ቢልም ከ14 ሰወች በላይ ህይወት ለመጥፋት ለተቀሩት ለከፋ የአካል ጉዳት እና ለንብረት ውድመት ዳርጓል :: የሞት የጉዳት የውድመት ምክንያት ሆንዋል ::

ህዝብ ጭነን የምንከንፍ ህግ ጥሰን የምንክለፈለፍ ከዚህ የከፋ አደጋ ልንማር ይገባል :: በእኛ ቸልታ የሚቀጠፈው ህይወት ሊያሳስበት በእኛ እንዝላልነት የሚደርሰው የአካል ጉዳት ረፍት ሊነሳን በእኛ አለማስተዋል ለሚፈጠር ንብረት ውድመት ልንቆጭ ይገባል ::
የሹፌሮች አንደበት

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአዋሽ ፈንታሌ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙትን ወገኖች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ሊከሰት ከሚችለው አደጋ ለማዳን በሚካሄደው እንቅስቃሴ ላይ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች በስፋት እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል 🙏🏽

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በዛሬው እለት የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በሰሜን ሸዋ ግድያ ተፈፀመባቸው

(መሠረት ሚድያ)- በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዛሬ ጠዋት ገደማ ለስራ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል።

በተተኮሰባቸው ጥይት የሞቱት ግለሰቦች ለስራ ጉለሌ ወረዳ 3 ላይ ቆይተዉ ወደ ፍቼ ከተማ እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።

የዞኑ የውሃ ሀብት ቢሮ ሀላፊ፣ የመስኖና ተፋሰስ ሀላፊ፣ የቡሳ ጎንፋ ሀላፊ እንዲሁም አንድ የቀበሌ ሊቀንመበር እና ሹፌራቸው በአጠቃላይ አምስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ወይም መንግስት 'ኦነግ ሸኔ' በሚላቸው ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን በቅርብ ወራት በመንግስት ጦር እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት መሀል ከፍተኛ የሆነ ግጭት እያስተናገደ ይገኛል።

ከዚህ በፊት በአንፃራዊ ሰላሙ የሚታወቀው ይህ የሰላሌ አካባቢ አሁን ላይ ከፍተኛ እገታ፣ ግድያ እና ተያያዥ ጉዳቶችን በህዝቡ ላይ እያስከተለ እንደሆነ ይታወቃል።

መረጃን ከመሠረት!

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ...

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ በሬክተር ስኬል የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከታች የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

👉 በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ፦ ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሦሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡

👉 በቤት ውስጥ ከሆኑ፦ በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

👉 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ፦ የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሦሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሦሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ መክሯል፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
🔴አንኳን ደስ አላችሁ!!! 🔴

በ 2016 ዓ.ም 45% ትርፍ /Dividend/ አትርፈናል ::

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 450 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.2 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0942585355 ይደውሉ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምርጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቻናል ይቀላቀሉ! በፍጥነት ይማራሉ!
በርካቶችን ለውጭ ሀገር እስኮላርሺፕ ያበቃ ምርጥ ቻነል 👌
ወደ ቴሌግራሙ ገባ ብለው በቁጥር የተደገፈ ስኬቱን ይመልከቱ

If you Plan to pursue a scholarship, pharmacy license, or dental school in the USA or Canada? Taking the TOEFL test is mandatory, and the TOEFL ZONE is here to guide you. With expert preparation and personalized support, we’ll help you achieve the scores you need. Start your journey with us today!

👇👇👇Join👇👇👇

/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"ሪያሊቲ እውነት ነው "

✨️ከ 8 በላይ ፕሮጀክቶችን ካስረከበው ሪያሊቲ ሪል እስቴት ቤት ይግዙ ::
በከተማችን በተመረጡ  ቦታወች ላይ


👉በቦሌ ደንበል ባለ 2 እና 3 መኝታ
👉በሳር ቤት ከባለ 1 -ባለ 3 መኝታ


✨️ለ ገና 30% ቅናሽ ✨️
      ለበለጠ መረጃ
📞
09-01-97-86-97
📞
09-86-68-75-13
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#holiday #realestateethiopia #realityrealestate #discount #christmas #newyear

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ የመቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተጀመረ

አዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ ዛሬ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡

ቅድመ ሁኔታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ነው ከዛሬ ታሕሣሥ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ባንኮች ተግባራዊ መሆን የጀመረው፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።

ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምርጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቻናል ይቀላቀሉ! በፍጥነት ይማራሉ!

If you Plan to pursue a scholarship, pharmacy license, or dental school in the USA or Canada? Taking the TOEFL test is mandatory, and the TOEFL ZONE is here to guide you. With expert preparation and personalized support, we’ll help you achieve the scores you need. Start your journey with us today!

👇👇👇Join👇👇👇

/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ኢትዮ-ሸማች የተሰኘው ችግር ፈቺ የመሰረታዊ ሸቀጦች (ስኳርና ዘይት) ስርጭት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች መተግበር ሊጀምር ነው!

በወጣት የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች በልፅጎ የቀረበውና የሸማቹን ማህበረሰብ ችግር በዘላቂነት የሚቀርፈው ኢትዮ-ሸማች የተሰኘው የቁጥጥር መተግበሪያ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኩል በአራዳ ክፍለከተማ ንግድ ፅ/ቤት ስር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች መተግበር ጀምሯል። ስኳርና ዘይት መከዘን፣እያለ የለም ማለት፣ ጥቁር ገበያ፣ ሰው-ሰራሽ የዋጋ ውድነት... ወ.ዘ.ተ ሲስተሙ የሚገታቸው ሲሆኑ ለማህበረሰቡም የላቀ እፎይታን የሚያመጣ ይሆናል።

ኢትዮ-ሸማች በሀገራችን ከሚገኙ አያሌ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች መካከል ዋነኛ ከሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር MoU በመፈረም የተሟላ System Integration ሰርቶ ያቀረበ ሲሆን፤ 6 ወራት በወሰደ የሙከራ ትግበራው የዲጂታል ግብይቱን ውጤታማነት ማረጋገጥ ተችሏል። የቁጥጥር ሲስተሙ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ሲሆን ሸማች ህብረት ስራ ማህበራትም ሆኑ የDelivery ተቋማት የሚያካሂዷቸውን የግብዓት ስርጭቶች በፍትሃዊነትና በገለልተኝነት ለመቆጣጠር ያስችላል።

መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገባቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ግብዓቱ ለታለመላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በስርዓቱ እንዲደርስ፣ ሰው-ሰራሽ እጥረት እንዳይኖር ብሎም የገበያ መረጋጋት እንዲኖር ለማድረግ አቅዶ እየሰራ የሚገኘው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር (MOTRI), በቀጣይ ሲስተሙን ለማሳደግና ሀገር አቀፍ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል ተገቢውን ስራ መስራት ጀምሯል።

ለፓይለት ትግበራው መሳካት ማህበረሰቡና የአራዳ ክ/ከ ንግድ ፅ/ቤት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።በቀጣይም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማዎች እንዲሁም በሌሎች ከተሞችና በሀገር አቀፍ ደረጃ ትግበራው የሚቀጥል ይሆናል።

መንግስት የተለመውን ዲጂታላይዜሽን ከማሳካት አንፃር ይህ የቁጥጥር ቴክኖሎጂ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል። የሀገራችን የእድገት ሞተር የሆነው ንግድ ባንክም የዳሬ ቴክኖሎጂ ሁነኛ አጋር በመሆን የዲጂታል ትራንዛክሽኑን በሰፊው ያሳልጣል።

መንግስት ለወጣት ስራ ፈጣሪዎችና ስታርትአፕ በፖሊሲ ደረጃ የሚያደርገውን ሙሉ ድጋፍ በሚመለከት ይህ ፕሮጀክት አይነኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችል ነው።
App ያውርዱ 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.darie.shemach_mobile

https://youtu.be/KRg88mtucRg?si=mRsC0YQOGy28u_as
https://youtu.be/KRg88mtucRg?si=mRsC0YQOGy28u_as

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በ84 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ
ዳግም ምዝገባ እንዲያካሄዱ ጥሪ ቀርቦላቸው ምዝገባ ባላካሄዱ 84 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ÷ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት እንዲተገበር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል

በዳግም ምዝገባውም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የተሳሳተ ሰነድ ካላቸው እንዲያስተካክሉ አልያም የጎደለውን እንዲያሟሉ እድል ተሰጥቷቸው እንደነበርም ተናግረዋል

ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት ውስጥም 84 የሚሆኑት ዳግም ምዝገባ አለማድረጋቸውን ገልጸው ምዝገባ ያላከናወነ ተቋም በራሱ ፈቃድ ከመማር ማስተማር ስራው እንደወጣ ይቆጠራል ብለዋል ።

እነዚህ ተቋማትም ከመማር ማስተማር ስራው ሲወጡ የመውጫ ፎርም እንዲሞሉ የሁለት ሳምንት ጊዜ ገደብ እንደተሰጣቸውም የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል ።

አሁን ላይ አምስት ተቋማት ብቻ ይህንን ሂደት የጀመሩ ሲሆን÷ ወደዚህ ስራ ያልገቡ ቀሪ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ በፍታብሄር እና በወንጀል ህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል ፡፡

ተቋማቱ ከዚህ በኋላ በሰነድ የታገዘ ምዝገባ እንደማያደርጉ እና ዳግም ወደ መማር ማስተማር ስራው እንደማይመለሱም አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣይም ዘጠኝ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀው በተቋማቱ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት እስከ ጥር ወር 2017ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ ፈቃድ ወዳላቸው ተቋማት እንዲያዛውሩ ትዕዛዝ መሰጠቱንም አብራርተዋል ፡፡

በመሳፍንት እያዩ

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ምርጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቻናል ይቀላቀሉ! በፍጥነት ይማራሉ!
በርካቶችን ለውጭ ሀገር እስኮላርሺፕ ያበቃ ምርጥ ቻነል 👌
ወደ ቴሌግራሙ ገባ ብለው በቁጥር የተደገፈ ስኬቱን ይመልከቱ

If you Plan to pursue a scholarship, pharmacy license, or dental school in the USA or Canada? Taking the TOEFL test is mandatory, and the TOEFL ZONE is here to guide you. With expert preparation and personalized support, we’ll help you achieve the scores you need. Start your journey with us today!

👇👇👇Join👇👇👇

/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone
/channel/toeflzone

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

መስቀል አደባባይ ከሚገኘው ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስትያን አንስቶ በቤተመንግስት አድርጎ እስከ ፍል ውሃ ድረስ ሰልፍ

👇🏾

ይህ እንደ እባብ የተጠማዘዘው ሰልፍ የነዳጅ ሰልፍ ነው

ዛሬ ጠዋት ደግሞ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲዎች ጫካ ውስጥ ነዳጅ እንደጫኑ ተደብቀው ተያዙ የሚል ዜና አንብቤ ነበር

ለምን ተደበቁ? - የወሩ መጨረሻ በመሆኑ የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በማለት ህዝቡን ሊዘርፉ እየጠበቁ

👇🏾

አንዳንድ ነገሮቻችን ግን🤔

🙌🏼❤️
Via Zemelak Endreas

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን መረጃዎች አያይዟል

♻️የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንድታጠናቅቁ ብሏል።

♻️የ2017 የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ይዘት የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን እንደሚሆን ገልጿል።

♻️ እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጃ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጎ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

(መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1)

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

DW Amharic የታኅሳስ 26 ቀን 2017 የዓለም ዜና
• የመሬት መንቀጥቀጥ ካሰጋቸው በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ቀበሌዎች ከ14,000 በላይ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወራቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። ባለፉት 15 ገደማ ሰዓታት አምስት የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ የአውሮፓ እና የአሜሪካ የምርምር ተቋማት መዝግበዋል።
• ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ልጆች በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከትምህርት ቤት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት አሳየ። ግጭት፣ ብጥብጥ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እና መፈናቀል የኢትዮጵያን ልጆች ከትምህርት ያራቁ ዋንኛ ምክንያቶች ናቸው። በሪፖርቱ መሠረት በአማራ ክልል 4.4 ሚሊዮን፣ በኦሮሚያ ክልል 3.2 ሚሊዮን፤ በትግራይ ክልል 1.2 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ልጆች ትምህርት ቤት አይሔዱም።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ከሰም ስኳር ፋብሪካ 🥺 የመሬት መንቀትቀጡ ያደረሰው ጉዳት። አላህ በቃችሁ ይበለን 🙏

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ይህ በአፋር ክልል በዞን 3 በዱለሳ ወረዳ በሳገንቶ ቀበሌ እና አከባቢው የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው መተንፈሻ የሚመስል እሳት፥ ጭስና ውሃ የቀላቀለ ፍንዳታ ነው። ማህበረሰቡ ከአከባቢው ተፈናቅሏል፥ ወዴት መሄድ እንዳለበት እንኳን አይታወቅም! በተቻለን አቅም መተባበር እና ለዚህ ህዝብ መድረስ ያስፈልጋል።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

(ጥቅምት 20/2017 ዓ/ም በመሠረት ሚድያ ቀርቦ የነበረ ዜና)

በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ለ10 ሺህ ገደማ ሰዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ስጋት እንደሆነ ተጠቆመ

(መሠረት ሚድያ)- 'Gelology Hub' በሚል የሚታወቀው እሳተ ገሞራዎችን እና የመሬት እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ትንታኔ የሚያቀርበው ድርጅት እንዳለው በአለም ዙርያ ትኩረት የተነፈገው ይህ አደገኛ ክስተት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታን ሊያስከትል የመቻል እድሉ ከፍተኛ ነው።

በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች ይህ ተፈጥሮአዊ አደገኛ ክስተት ብዙ ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል የሚለው Geology Hub ይህን መረጃ ለህዝብ ማድረስ የፈለገው የሰው ህይወት ለማትረፍ ነው ብሏል።

ከመስከረም ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የቀለጠ አለት ክምችት እየታየ መሆኑን ገልጾ እስካሁን ከአደጋው አካባቢ 700 ገደማ ሰዎች እንዲነሱ መደረጉን ገልጿል።

በዚህ አደገኛ ስፍራ የሚገኙ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በአስቸኳይ ከስፍራው እንዲነሱ መደረግ እንዳለባቸው የሚገልፀው Gelology Hub ይህን ጉዳይ በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ለአሜሪካው የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ማሳወቁን ጨምሮ ጠቅሷል።

21 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው ይህ የእሳተ ገሞራ ግፊት በመካከለኛ ኢትዮጵያ አዋሽ አካባቢ እንቅስቃሴው እንደቀጠለ የታወቀ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በአካባቢው ያልነበሩ አዳዲስ ሙቅ ውሀዎች መፍለቅ መጀመራቸውም ታውቋል።

በአዋሽ ፈንታሌ እስከ 5 ነጥብ 1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቆ ነበር።

መረጃን ከመሠረት!

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በአሁን ከመሸ (በአዲስ አበባ አቆጣጠር) 2:29 አፋር ክልል አዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን ጅዖ ሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታውቋል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ እንደተሰማ ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ እየገለጹ ነው።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

ዛሬ ረፋድ 4፡43 ሰዓት ላይ በአራት ኪሎ አካባቢ የመሬት ንዝረት ተሰምቷል፡፡ ሰሞኑን በተከታታይ በአዋሽ እና ፈንታሌ አካባቢ በሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች የመሬት ንዝረት ሲከሰት ነበር፡፡ በተለይ ከትናንት በስቲያ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ብቻ 12 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትን በማነጋገር ተከታታይ መረጃዎችን እንደምንሰጥ ከወዲሁ እንጠቁማለን።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ስንት ሚሊዮን እንደደረሰ ተገለጸ
ወርልድ ፖፑሌሽን ዛሬ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ኢትዮጵያ በአለማችን ላይ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ካላቸው አስር አገራት መካከል አንዷ መሆኗን አስታውቋል፡፡ እንደሪፖርቱ ከአለማችን ላይ ከፍተኛ ህዝብ በመያዝ ግንባር ቀደም የሆነችው ህንድ ስትሆን አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ህዝብን ይዛለች፡፡

በሁለተኝነት ቻይና የምትከተል ሲሆን ሶስተኛ አሜሪካ ሆናለች፡፡ በመቀጠል ኢንዶኔዥያ፣ ፓኪስታን፣ ናይጄሪያ፣ ብራዚል፣ ባንግላዲሽና ሩሲያ በዝርዝሩ ላይ በቅደም ተከተል የተቀመጡ ሲሆን በአስረኛ ላይ ኢትዮጵያ ሰፍራለች፡፡

ይህ ሪፖርት እንዳለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ነው፡፡ በአጠቃላይ የአለም ህዝብ አሁን ላይ ከስምንት ቢሊዮን አልፏል ብሏል ሪፖርቱ፡፡

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

በሁለቱ የህወሓት ወገኖች ክፍፍል ውጥረት የትግራይ የፀጥታ ሀላፊዎች እነ ወዲ ወረደ ሰላማዊ ሰልፍ ከልክለው የነበረ ቢሆንም ዛሬ መቀሌ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። መቀሌ ለወራት ያለ ከንቲባ ነች።

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

"48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል

ነገሩ እየከፋ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ብቻ ከ21 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ "Zamyad" የተባለ መተግበሪያ ላይ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።

በዚህ መተግበሪያ መሰረት ዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት የተከሰተውን ጨምሮ ሁለት እጅግ አደገኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ትላንት 18 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የዛሬውን ከትላንቱ ጋር ስንደመር በአጠቃላይ 48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ መተግበሪያው ላይ ያለው መረጃ ያሳያል።

ኮሜንት ላይ ያስቀምጥኩትን ስክሪንሹት ተመለከቱ !

ፈጣሪ ይጠብቀን 🙏🙏

~ Nati Manaye

Читать полностью…

Muktarovich Ousmanova

🔴 በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከሌሊቱ 7:13 (01:13 am)፣ በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ መንቀጥቀት ተከሰተ።

በአካባቢው ሌሊት 7:ሰዓት ከ13 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.2 የደረሰ እንደሆነ የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል (The German Research Centre for Geosciences | GFZ) አስታውቋል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel