#ከትልቅ_ሰው_ሪል_ስቴት
በመሀል ካዛንቺስ በሽያጭ ላይ ነን
50/50 #የባንክ_ብድር_ ዝቅተኛ ወለድ
ግንባታወች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የሚረከቡ ናቸው።
በአንድ ወለል ላይ አራት አባወራዎች ብቻ
ባለ 2 መኝታ ቤት
#169ካሬ
#171ካሬ
ባለ 3 መኝታ ቤት
#167ካሬ
#178ካሬ
ቅድመ ክፍያ #30%
~ሁሉም መኝታዎች የራሳቸውን መታጠቢያ ክፍል ያላቸው።
~ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች እንዲሁም የሰራተኛ መኝታን ያካተተ
~ባለ 2 ቤዝመንት ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
~የ24ሰአት የደህንነት ካሜራዎች
~የእስፖርት ማዘውተሪያ
~ግዙፍ የዉሀ ማጠራቀሚያ
~መጠባበቂያ ጄኔሬተር
~የ ቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
~ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማዘጋጃ የሚውል የተንጣለለ ሰገነት
በ 10 ወራት የሚጠናቀቅ
/channel/Realestateconsult12
ለበለጠ መረጃ
+251946404247
ውድ የፌስቡክ ወዳጆቼ
👌 እነሆ መፅሐፌን በዲጂታል 👌
"ሥራ አዳኝ" የተሠኘው ረጅም አመታት የደከምኩበት መፅሐፍ በወረቀት ለህትመት መብቃቱን ከዚህ ቀደም አሳውቄያችሁ እንደነበረ ይታወሳል። አሁን ደግሞ በቱባ ዲጂታል መፅሐፍት መሸጫ አፕሊኬሽን ልታገኙት እንደምትችሉ ስነግራችሁ ከፍተኛ ደስታ እየተሰማኝ ነው።
መፅሐፉ የሥራ አፈላለግ ዘመናዊና ሳይንሳዊ ጥበቦችን፣ ስልቶችን እና ስትራቴጂዎችን ለአዲስ ተመራቂ እና ሥራ በማደን ላይ ላሉ ሥራ–አጥ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የሚያስተዋውቅ መፅሐፍ ነው።
በዚህ መፅሐፍ ውስጥ:–
ስለ በሰው ሰው ሥራን የመፈለግ ጥበብ (networking)፣
ስለ ሲቪ፣
ስለ ሸኚ ደብዳቤ፣
ስለ ለቃለመጠየቅ የአለባበስ ህግጋት፣
ስለ ለቃለመጠይ ዝግጅት፣
ስለ በቃለመጠየቅ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች እና አሳማኝ ምላሽ የመስጠት ጥበቦች፣
ስለ ደሞዝን የመደራደር ብልሃት፣
ስለ ምርጥ ሠራተኛ የመሆን እና ሥራን በሥኬት ጀምሮ ወደ ከፍተኛ የሐላፊነት ቦታ የመሸጋገር ጥበብ
እና
ሌሎች ተፈትሸው ስኬታማ እንደሚያደርጉ የተረጋገጡ የሥራ አፈላለግ ሳይንሳዊ ጥበቦችን ለሥራ ፈላጊዎች ያስተዋውቃል።
በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የሥራ አፈላለግ መሰረታውያንን (The basics of job hunting) ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን፣ አዲስ ተመራቂዎች ከትምህርት አለም ወደ ሥራው አለም ለመሸጋገር በሚያድርጉት ትግል ውስጥ፣ ሊገጥማቸው የሚችልን እንቅፋቶች እንዴት በብልሃት ሊያልፉ እንደሚችሉ የሥነልቦና ምክሮችን ይለግሳል።
መፅሐፉን ለማግኘት በሚከተለው ሊንክ በቴሌ ብር መግዛት ይችላሉ 👇
https://tuba.et/
እነፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሰረት ጥያቄ ቀረበ።
ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
ይህ ክስ ያቀረቡት አሁንም በፓርቲው ውስጥ ያሉ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ናቸው።
በፕ/ር ብርሀኑ ነ ጋና በሌሎች 21 ግለሰቦች ላይ በኢዜማ 1ኛ ጠ/ጉባኤ ላይ ቀርቦ ያልፀደቀ የሀሰተ የመተዳደሪያ ደንብና የውጭ ኦዲተር ሪፖርት በጉባኤው ቀርቦ እንደፀደቀ በማስመሰል ለም/ቦርድ አቅርበው በተሳሳተ መንገድ ዕውቅና ለመውሰድ በመሞከራቸውና የቦርዱን ውሳኔ ለማሳሳት በመሞከራቸው በአገሪቷ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀፅ 375 እና 378 መሠረት የወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው ለምርጫ ቦርድ በአገሪቷ ሕግ መሠረት ጥያቄ ቀረበ።
ምርጫ ቦርድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በግለሰቦቹ ላይ ክስ የማይመሰርት ከሆነ የወንጀል ክሱን ከነሙሉ ማስረጃው ለሚመለከተው አካል በቀጥታ የሚቀርብ መሆኑን በደብዳቤው በግልፅ ተቀምጧል።
መስቀል አደባባይ ለመግባት ክፍያ?
መስቀል አደባባይ የህዝብ ነበረ። በነበር ሊቀር ይመስላል።
ለዘመናት ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በርካቶችም በድካም የዛለ ሰውነታቸውን ለማደስ ይጠቀሙበታል፡፡ ለዓይን ማራኪ በመሆኑ በርካታ ሰዎች ይዝናኑበታል፣ አረፍ ብለው ያወጉበት ነበር፡፡ መስቀል አደባባይ በየዓመቱ የመስቀል በዓል የሚከበርበት፣ የመንግሥት ትልልቅ ዝግጅቶች የሚከናወንበት፣ በተለይ በሰንበት በርካቶች የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትና የተለያዩ የሙዚቃ ትዕይንቶች በየወቅቱ የሚቀርቡበት የከተማዋ ስመ ጥር አደባባይ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ስነ ስርአት የሌለው ስርአት፣ ህዝብ ምን ያመጣል በሚል እብሪት ተነሳስቶ በህዝብ ስም በተለመነ ገንዘብ ካደሰው በኋላ "መስቀል አደባባይ ድንጋይ ላይ ለመቀመጥ ገንዘብ ክፈሉኝ" ይለን ጀመር።
ብልጽግና ሲሉን ህዝብን በስራና በትምህርት አበልጽገው ሀገርን አለም ወደ ደረሰበት የስልጣኔና የእድገት ደረጃ ያደርሳሉ ብለን ስናስብ እነሱ በአቋራጭ ደሀን በማጥፋት ሀብታምን ይበልጥ በማበልጸግ ተወጥረው አገኘናቸው። እንግዲህ እንዲያ ያሸበሸብንለት የህዝብ መንግስት ነው ያልነው "መንግስት" እዚህ ድረስ ሲሸጠን "ይበለን"ከማለት ሌላ ምን እንላለን?
የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ
ዋጋ ያለቀው ሳምሰንግ የእጅ ስልኩ ወደ ግድቡ ገብቶብኛል፣ ስልኩ በርካታ እጅግ አንገብጋቢ የመንግስት መረጃዎችን ይዟል በሚል ግድቡ እንዲመጠጥ አስደርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለስልጣኑ መጀመሪያ ላይ ስልኩን ለማስወጣት በአካባቢው ያሉ ዋናተኞችን ቢያሰማራም አለመገኘቱን ተከትሎ በውሃ መሳቢያ ፓምፕ የግድቡ ውሃ እንዲመጠጥ አስደርጓል ተብሏል።
ራጂሽ ቪሽዋስ የተባለው ይህ ባለስልጣን ስልኩን ለማግኘት ሲባል ባለሙያዎች የግድቡን ውሃ ለመምጠጥ እና ለማፍሰስ ሶስት ቀናት እንደፈጀባቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ስልክ ቢገኝም በውሃ ተሞልቶ የመስራቱ ነገር አጠራጣሪ ነው የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በህንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህን ተከትሎም የሐገሪቱ መንግስት ባለስልጣኑ በፈጸመው ድርጊት ስልጣኑን ያለ አግባበብ በመጠቀም ከስራ የታገደ ሲሆን ጉዳዩ አሁንም መነጋገሪያነቱን ቀጥሏል ተብሏል።
ለዚህ ባለስልጣን ሲባል እንዲመጠጥ እና እንዲባክን የተደረገው ውሃ ከስድስት ሺህ በላይ ሄክታር መሬት መስኖ የማልማት አቅም እንደነበረው ተገልጿል።
በሩዋንዳው የዘር ግጭት ከ2 ሺህ በላይ ግጭቱ ሸሽተው በቤተክርስቲያን የተጠለሉ ሰዎችን ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በገፍ አቃጥሎ ሲያበቃ በኋላ በዶዘር ቆፍሮ የቀበራቸው ወንጀለኛ Fulgence Kayishema ከዓመታት ክትትል በኋላ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ስር ውሎ ተይዞ ፍርድቤት ቀርቧል።
ይህ ነብሰ ገዳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስደተኛ ሆኖ ስሙ ቀይሮ ነበር የገባው። የአንድ እርሻ ዘበኛ ሆኖ ነበር ሲሰራ የነበረው። የሩዋንዳና የደቡብ አፍሪካ የጽታና ድህንነት ሰራተኞች ባደረጉት ክትትል በ2018 እሱ መሆኑ ካወቁ በኋላ ለተባበሩት መንግሥታት በማሳወቅ የስደተኝነት ማንነቱ ተፍቆ ዛሬ ፍርድቤት ቀርቧል።
PS: ትላንት በአማራ ህዝብ ላይ በኦሮሞ ክልል በተለይ ወለጋ ውስጥ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ገና አፉ እንደከፈተ ወንጀሎች ሳይቀጡ ከሞት የተረፈው ህዝባችን አሁንም ሜዳ ላይ ተበትኖ ይገኛል። ይህን የመሰለ የዘር ማጥፋት ጭካኔ የፈጸሙ ሰዎች ግን ዛሬ ባለ ጊዜ ሆነው ማለፍ ቢችሉም የነገ ዕጣ ፈንታቸው እንደዚህ ሰውዬ ከመሆን እንደማያልፍ ሊያውቁ ይገባል።
ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ዓለም ነገ የማን ጓደኛ እንደሚሆን አይታወቅምና ወንጀለኞች አንድ በአንድ መዝግበን እንያዝ።
Gran Chico
🏢🏢YAMLOC REAL ESTATE🏢🏢
📍ሰሚት 72 አፓርታማዎችን እየገነባ ይገኛል በ25% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ
📍ዳሎል ማደያ ጎን , ዋናው መንገድ ላይ
50/50 የባንክ ብድር
🛌ባለ 2 መኝታ
110ካሬ ሜትር
🛌ባለ 3 መኝታ
152 ካሬ ሜትር
60% የተገነባ
በአንድ አመት ከስድስት ወር የሚረከቡት
ዋጋ= 85,000.00 ብር/m2
ልዩነታችን
...ሰፊ የጋራ ቴራስ
🌷በኢትዮጵያ ብር ያለምንም ጭማሪ የሚከፍሉበት
💴ምቹ ና ቀላል የአከፋፈል ስርአት
🚘በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ
💴💴💴💴ለኢንቨስትመንት ፍለጎቶዎ በአጭር ጊዜ ትርፋማ የሚየደርጉ
ዘመናዊ አሳንሰር የተገጠመላቸዉ
ለመብራት መቆራረጥ አስተማማኝ ጀነሬተ
🏦💲ለ ዲያስፖራ እና ለ ''NGO'' ሰራተኞች በ አይነቱ ልዩ የሆነ የብድር አገልግሎት
ለሌሎች አማራጮች ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናላችን
ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑ
☎️ 0930903762
☎️ 0929831836
አለም አቀፍ ሚዲያዎች የብልፅግና መንግስት መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻውን እና የህዝቡን ተቃውሞ ለአለም እየዘገቡ ይገኛሉ::
ዓለም አቀፉ ሚዲያ አልጀዚራ ኢትዮጵያ «መስጅዶቻችንን አታፍርሱብን!» ያሉ ሰላማዊ ዜጎቿን መግ'ደሏን ዘግቧል።
ቢቢሲም እየፈረሱ ስላሉ መስጂዶች እና የሙስሊሙን ተቃውሞ ዘግቧል
#EthiopianMuslimsUnderAttack #JusticeForEthiopianMuslims #ReligiousFreedomInEthiopia #StopMosqueDemolition #SupportEthiopianMuslims #StandWithEthiopianMuslims
#ShegerCity
#IslamophobiaInEthiopia
#ከትልቅ_ሰው_ሪል_ስቴት
በመሀል ካዛንቺስ በሽያጭ ላይ ነን
#በመሃል_ካዛንችስ #ዋና_መንገድ ላይ
50/50 #የባንክ_ብድር_ ዝቅተኛ ወለድ
ግንባታወች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የሚረከቡ ናቸው።
በአንድ ወለል ላይ አራት አባወራዎች ብቻ
ባለ 2 መኝታ ቤት
#169ካሬ
#171ካሬ
ባለ 3 መኝታ ቤት
#167ካሬ
#178ካሬ
ቅድመ ክፍያ #30%
~ሁሉም መኝታዎች የራሳቸውን መታጠቢያ ክፍል ያላቸው።
~ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች እንዲሁም የሰራተኛ መኝታን ያካተተ
በ 10 ወራት የሚጠናቀቅ
/channel/Realestateconsult12
ለበለጠ መረጃ
+251946404247
ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ በፀጥታ አካላት በተወሰደዉ ያልተገባ እርምጃ የደረሰባቸዉን ወንድሞቻችን ሸይኽ ሱልጧን አማን(የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንት)፤ ኡስታዝ አህመዲ ጀበል፣ አቶ ካሊድ ሙሀመድ(የአዲስ አበባ መጅሊስ የፕሬዝደንት ጽ/ቤ/ኀ) ... በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተዉ ጎብኝተዋል።
Mujib Amino
በዛሬው እለትም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሰብ ሳቢነት ሁሉም የየክልሉ የመጅሊስ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ የተጠራ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ህወሓት ትጥቅ የማስረከብ ስንስርዓት ሲያካሂዱ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች ተከታትለዋል። በህወሓት በኩል ጀ/ ምግበይ በፌዴራል መንግስቱ በኩል ጄነራል ደርቤ መኩሪያ ርክክቡን አስፈፅመዋል።
በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት በአንድ ወር ውስጥ ይፈፀማል የተባለው ትጥቅ የማስፈታት ሂደት እስካሁን መቆየቱ ብዙዎች የፌደራል መንግስቱን ሲተቹ ነበረ። አሁንም ህወሐት የቀበራቸው መሰሪያዎችን አላስረከበም የሚል ጥርጣሬ የገባቸው ብዙዎች ናቸው።
የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች፤ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባዎቻቸውን ሊያካሄዱ ነው
የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች፤ ከመጪው ሰኞ ግንቦት 21 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ገደማ የሚቆዩ ስብሰባዎችን ሊያካሄዱ ነው። በሁለቱ ኮሚቴዎች መደበኛ ስብሰባዎች፤ ወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።
ከመጪው ሰኞ እስከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የሚቆዩት የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች መደበኛ ስብሰባዎች፤ የፓርቲው የስራ አፈጻጸም “በዋነኛነት የሚገመገምባቸው” እንደሆኑ የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ የሚደረጉት ስብሰባዎች በቅደም ተከተል የሚደረጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በቅድሚያ የሚደረገው የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሲሆን፤ ሰኞ ግንቦት 21፤ 2015 ተጀምሮ በማግስቱ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ስብሰባ መጠናቀቅ አንድ ቀን በኋላ የሚጀመረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 29 ድረስ እንደሚቀጥል አቶ አዲሱ ተናግረዋል።
* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11045/
#ከትልቅ_ሰው_ሪል_ስቴት
በመሀል ካዛንቺስ በሽያጭ ላይ ነን
#በመሃል_ካዛንችስ #ዋና_መንገድ ላይ
50/50 #የባንክ_ብድር_ ዝቅተኛ ወለድ
ግንባታወች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የሚረከቡ ናቸው።
በአንድ ወለል ላይ አራት አባወራዎች ብቻ
ባለ 2 መኝታ ቤት
#169ካሬ
#171ካሬ
ባለ 3 መኝታ ቤት
#167ካሬ
#178ካሬ
ቅድመ ክፍያ #30%
~ሁሉም መኝታዎች የራሳቸውን መታጠቢያ ክፍል ያላቸው።
~ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች እንዲሁም የሰራተኛ መኝታን ያካተተ
በ 10 ወራት የሚጠናቀቅ
/channel/Realestateconsult12
ለበለጠ መረጃ
+251946404247
🏢🏢YAMLOC REAL ESTATE🏢🏢
📍ሰሚት 72 አፓርታማዎችን እየገነባ ይገኛል በ25% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ
📍ዳሎል ማደያ ጎን , ዋናው መንገድ ላይ
50/50 የባንክ ብድር
🛌ባለ 2 መኝታ
110ካሬ ሜትር
🛌ባለ 3 መኝታ
152 ካሬ ሜትር
60% የተገነባ
በአንድ አመት ከስድስት ወር የሚረከቡት
ዋጋ= 85,000.00 ብር/m2
ልዩነታችን
...ሰፊ የጋራ ቴራስ
🌷በኢትዮጵያ ብር ያለምንም ጭማሪ የሚከፍሉበት
💴ምቹ ና ቀላል የአከፋፈል ስርአት
🚘በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ
💴💴💴💴ለኢንቨስትመንት ፍለጎቶዎ በአጭር ጊዜ ትርፋማ የሚየደርጉ
ዘመናዊ አሳንሰር የተገጠመላቸዉ
ለመብራት መቆራረጥ አስተማማኝ ጀነሬተ
🏦💲ለ ዲያስፖራ እና ለ ''NGO'' ሰራተኞች በ አይነቱ ልዩ የሆነ የብድር አገልግሎት
ለሌሎች አማራጮች ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናላችን
ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑ
☎️ 0930903762
☎️ 0929831836
በቅሎ ወለደች
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ አንዲት በቅሎ መውለዷ ተነግሯል፡፡
የበቅሎዋ ባለቤት አቶ ብርሃኑ ተምትሜ ÷ በ2014 በቅሎዋን እንደገዟት እና ለማጓጓዣ አገልግሎት ሲጠቀሙባት መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ነገር ግን የበቅሎዋ ሆድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን እንዳአስተዋሉ እና ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ላይ እንደወለደች አረጋግጠዋል፡፡
የበቅሎዋ መውለድ ክስተት እንዳስገረማቸው አንስተው÷ ውርንጭላው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
በባኮ ቲቤ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት የእንስሳት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ለማ አያላ÷በቅሎ ሲወልድ አይተው እንደማያውቁ እና ክስተቱ እንግዳ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡
ባለሙያው በቅሎ አትወልድም የሚለው እሳቤ በሳይንስ እና በባህላዊ መንገድ የታመነበት ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ከአንድ ሚሊየን በቅሎዎች አንዳቸው ሊወልዱ እንደሚችሉ መግለጻቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)
ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
=======#=======
ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።
በባለሥልጣኑ የተሽከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በድሉ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ አንዱ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ አንዱ ነው። ይህም ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል።
‹‹ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥናት በባለሥልጣኑ የሚመዘገበው የገንዘብ መጠን እና ለገቢዎች ቢሮ የሚቆረጠው ደረሰኝ ተመሳሳይ ያለመሆን ሁኔታዎች አሉ። በዚህም በተለይ የአዲስ ተሽከርካሪዎች ዋጋ የሚቆረጥበት ደረሰኝና ገዢዎች ለመኪናው የሚከፍሉት ዋጋ ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡›› ብለዋል።
በዚህም መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ግዥና ሽያጭ ማግኘት የሚገባውን የታክስ ገቢ እያገኘ አለመሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህንን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
‹‹ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ኹለት አይነት ሕገወጥ ተግባራት ይገጥሙታል›› ያሉት ኃላፊው፤ እነሱም ከክልል በዝውውር የሚመጡ መኪናዎች ላይ እና በተጭበረበረ ሰነድ የተመዘገቡ መኪናዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ 👇
/channel/addismaleda
ስትገፋ ፅና ወዳጄ‼
አሊሰን ፊሊክስ በተለያዩ የሩጫ ውድድሮችን በማሸነፍ ትልቅ ስም ያላት አሜሪካዊት የአጭርና መካከለኛ ርቀት ፈጣን ሯጭ ናት ።
ይህ ታዋቂነቷም ፡ እውቁን የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክን ስቦት የረጅም ጊዜ ውል አስፈርሟት ነበር ።
እና በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አሊሰን አረገዘች ።
ይህን የሰማው የረጅም ጊዜ ስፖንሰሯ ናይክ ፡ ከንግዲህ በባለፈው ውል መቀጠል አንችልም ። ከእርግዝናና ከወሊድ በኋላ እንደድሮው ልትሆኚ ስለማትችይ 70% ክፍያሽን እቀንሳለሁ አላት ። አሊሰን ይህ መሆን የለበትም ስትል ከናይክ ጋር ተከራከረች ።
ሆኖም ናይክ ይህን ቅሬታዋን ከመመለስ ይልቅ ቃል በቃል " Know your place and just run " ልክሽን ( ደረጃሽን አውቀሽ ትሮጭ እንደሁ ሩጭ ) በማለት በውሳኔው ፀና
አሊሰን ጥሩ እንደዛ ከሆነ ከናንተ ጋር ያለኝን ውል አቋርጣለሁ አለች ።
ናይክ በዚህ ተስማማ ውላቸው ተቋረጠ ።
አሊሰን ፊሊክስ የመጀመሪያ ሴት ልጇን ወለደች ።
እና ከሁለት አመት በኋላ ወደ ልምምድና ውድድሩ ተመለሰች ። ቦታሽን ደረጃሽን አውቀሽ ዝም ብለሽ ሩጪ ያላትን የናይክን ልብ ሰባሪ አባባል ወስዳም “I Know My Place " ( ደረጃዬንማ አውቃለሁ ) የሚል የድርጅት ሞቶ ያለው SAYSH የሚባል የራሷን ብራንድ ፈጥራ ፡ በራሷ ካምፓኒ የተመረተ ጫማ ለብሳ መሮጥ ጀመረች ።
እና በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው ኦሎምፒክ መድረክ ተሳትፋ 11 ሜዳልያዎችን ሰብስባ ብዙ ሜዳልያ በማግኘት ታሪክ ሰራች ።
.......
አሁን ላይ በአሊሰን ፊሊክስ ካምፓኒ የሚመረተው ይህ SAYSH የሚባለው ጫማ በ150 ዶላር የሚሸጥ ተቀባይነት ያለው ብራንድ ሆኗል ።
........
I Know My Place !
Thank you Wasihune Tesfaye for sharing
[ማስታወቂያ]
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ከፓስፖርት ጋር ለተያያዘ አገልግሎት ፈላጊዎች ኢምግሬሽን መሰለፍ ድሮ ቀረ ጊዜዎትን ይቆጥቡ
በ ቤትዎ ሆነዉ ቀጠሮ ያስይዙ።
✔️ፖስፖርት ለማሳደስ
✔️አዲስ ፖስፖርት ለ ማዉጣት
✔️ለ ጠፋ ፓስፖርት
✔️የ ስም እና የ እድሜ ቅያሪ አገልግሎት ከፈለጉ 0944311346
0900577529 ይደውሉ
1⃣4⃣3⃣PassportService
🇪🇹ዉድ ደንበኞቻችን
ቀደም ሲል እንሰጥ የነበረዉን የ ኦን-ላይን ፓስፖርት አገልግሎት በተቀላጠፈ መንገድ መስጠታችንን እየገለፅን፤በፋጥነት ይህንኑ እድል እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናሳዉቃለን።
🏁አዲስ አበባ
ክልል ላይ አገልግሎት የሚሰጡበት ቦታዎች
🏁ድሬዳዋ
🏁 አዳማ
🏁 ጅማ
🏁ባህርዳር
🏁ደሴ
🏁ጅጅጋ
🏁ሰመራ
🏁ሀዋሳ
በ 0900577529
0944311346 ይደዉሉ
Dear Clients⚡️⚡️⚡️
We are Very happy to inform you that,We are doing the online passport service appointment Efficiently,Hence We Sincerely Encourage all Of You to Seize this opportunity in the earliest possible time.
📞☎️ 0944311346
0900577529
በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና አስተዳዳራዊ ነፃነት በመስጠት፣ የራሳቸውን ሀብት እንዲያመነጩ የሚፈቅድ ሕግ ለመደንገግ የተዘጋጀው አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ሲፀድቅ፣ በርካታ የፓርላማ አባላት የፍትሐዊነት ጥያቄ እንዳያመጣ በሚል ሥጋት ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት፣ የቀረቡ ግብዓቶችን በማካተት እንዲፀድቅ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ ያቀረበው ረቂቅ፣ በአራት ተቃውሞና በ13 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡
ይሁን እንጂ የምክር ቤቱ አባላት አዋጁ ወደ ሥራ ሲገባ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ ምክንያት ከትምህርት ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሥጋታቸውን አሰምተዋል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) አዋጁ ከትምህርት ፍትሐዊ ተደራሽነት ጋር ሊያመጣ የሚችለውን አንድምታ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ከፍለው ለመማር የሚያስችል የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መደላድሎች አሉ ወይ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ መጀመርያ ማኅበራዊ መደላድሉን መፍጠር መቅደም አለበት ብለዋል፡፡
"በህግ ስም የደሀን ቤት እና የእምነት ተቋምን ማፍረስ ልክ አይደለም"
(አቶ ታዬ ደንደአ)
በዚህ አምስት አመታት ውስጥ አ.አ ዚርያ ያለውን የቱለማ ህዝብ መሬት በገበሬ ስም የዘረፈው.ማን እንደሆነ እናውቃለን። በሚልየን ዘርፎ ለሴት ገንዘብ የሚበትነው እና ውስኪ ሲገለብጥ የሚያድረውም ማን እንደሆነ እናውቃለን።
ህገ-ወጥ ግንባታን ማስቆም ጉልበት እና ንብረት ሳይባክን ነበር።መሬት ሲቸበቸብ ፣ቤት ሲሰራ በዝምታ ታልፎ እንዲሁም ውሃ እና መብራት ሰጥቶ የሀገር ሀብት ከፈሰሰ በኋላ በህግ ስም ተከልሎ የደሀን ቤት እና የእምነት ተቋማትን ማፍረስ አግባብ አይደለም።
Via Hanna R Waktolaa
«መጅሊስ ዝም ያለው ፈርቶ እንዳልሆነ መንግስት ሊገነዘብ ይገባል።»ክቡር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
መንግስት ውስጥ ያሉ ጠብ አጫሪ ኢስላም ጠል አካላቶች መኖራቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንት ክቡር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በዛሬዉ እለት የፌደራል መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የየክልሉ መጅሊስ ፕሬዝደንቶችና አመራሮች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ መግቢያ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል።
ቤታችን እስልምናችን ነው ያሉት ክቡር ፕሬዝደንቱ «መስጂዳችን ፈርሶ ሙስሊሙ ተገድሎ ሰሚ አጥተን እንሆ ችግሮች እየተባባሱ መጥተዋል» ሲሉ በምሬት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንት ክቡር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
«መንግስት መጅሊስ ዝም ያለው ፈርቶ እንዳልሆነ ሊገነዘብ ይገባል። አሁንም ቢሆን መስጂዶቻችን ሊተኩ ይገባል። ካልሆነ ግን እኛ እንጂ መስጂዳችን አይፈርስም »ብለዋል።
በንግግራቸዉ ላይ «ይህች ሀገር ያለ ሙስሊሞች መኖር አትችልም ፤ወደ ፊትም ያለ ሙስሊም ሀገር መኖር አይቻልም። ሙስሊም ሰላም ወዳድ ነው። የሰላም ዘብ ነው...» ሲሉ አብራርተዋል።
የትግራይ TDF ይባል የነበረው ታጣቂ በተቃውሞ ላይ ነው። ተቃውሞው በትግራይ ሽግግር መንግስት ላይ ነው። በጌታቸው ረዳ ላይ።
የተቃውሞው ምክንያት
ለትግራይ ብንታገልም ተረስተናል፣ ምንበላው የለንም፣ የቆሰሉ፣ አካላቸውን ያጡ ክራንችና ዊልቼር የላቸውም፣ የሽግግር መንግስቱ ክዶናል፣ ረስቶናል የሚል እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፤ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙም ተገልጿል።
ከአዲስ አበባ በ350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12፤ 2015 መሆኑን ተናግረዋል። ፋብሪካው ባለፈው 2014 ዓ.ም እና በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ጥቃቶችን ቢያስተናግድም፤ የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት “ከበድ ያለ” እንደሆነ ተነግሯል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ እና በስሩ ያለው የሸንኮራ አገዳ እርሻ፤ በአጠቃላይ በ67 ሺህ ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፈ ነው። የቀደሙት ጥቃቶች ይበልጥኑ ኢላማ የሚያደርጉት የፋብሪካው እርሻ ላይ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ረታ፤ ታጣቂዎቹ “የአገዳ እና የእርሻ ማሽነሪዎችን የማቃጠል” ድርጊት ይፈጽሙ እንደነበር ያስታውሳሉ። የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሚለየው፤ ታጣቂዎቹ ወደ ፋብሪካ ጭምር በመግባት ጥቃቶቹን በመፈጸማቸው እንደሆነ ያስረዳሉ።
የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጥቃቱን እንዲመረምር ያቋቋመው ግብረ ኃይል፤ በጥቃቱ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን ኃላፊው አስታውቀዋል። ሰኞ ዕለት ወደ አካባቢው የተሰማራው ይኸው ግብረ ኃይል፤ “እንደ ልብ ተዘዋውሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ” የደረሱ ሌሎች ጉዳቶችን እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ አለመቻሉንም ጠቅሰዋል።
ሰበር
አንዋር መስጊድ አዲስ አበባ በተቃውሞ ላይ የነበሩ ሙስሊሞችን ለመበተን የጥይት ተኩስ በመተኮሱ ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሯል።
ስክነት፣ ጥንቃቄና ለህይወት መጥፋት ምክንያት መሆን አያስፈልግም።
ጥንቃቄ፣ ጥንቃቄ ጥንቃቄ
የገንዘቦች ሁሉ ንጉስ የሆነው የዶላር የበላይነት እያበቃ ይሆን?
በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት 90 በመቶ የዓለማችን የውጭ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በአሜሪካ ዶላር መከናወኑን ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ ገልጿል፡፡
በዓለማችን ከተካሄደው አጠቃላይ ንግድ ውስጥ ከ6 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በአሜሪካ ዶላር የተካሄደ ሲሆን ይህም ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው ሆኖ መመዝገቡን አይኤምኤፍ አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ዶላር ለምን ይሄን ያህል ቅናሽ አሳየ? የሚለው ጉዳይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
የአርብ ወሬ።
በቻይና ዩኒቨርስቲዎች ለማስተማሪያነት የሚውሉ የአማርኛ መማሪያ መፅሐፍት ተመረቁ። በምረቃው ወቅት ቻይናዊያን ተማሪዎች በአማርኛ ግጥም አቅርበዋል።
#NewsAlert
ዋዜማ - የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሠፋን ጨምሮ ሰባት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት በገዛ ፍቃዳቸው ከፓርቲው አባልነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
ከኢዜማ አባልነታችን ለቀናል ያሉት፣ ከየሺዋስ በተጨማሪ ሀብታሙ ኪታባ፣ ዳንዔል ሺበሺ፣ ናንሲ ውድነህ፣ ጂአልጋው ጀመረ፣ ተክሌ በቀለ እና ኑሪ ሙደሲር ናቸው። ግለሰቦቹ፣ የፓርቲውን አካሄድ ለማስተካከል ለረጅም ጊዜ ያደረጉት ጥረት "በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ" ምክንያቶች እንዳልተሳካ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ተሰናባቾቹ ፖለቲከኞች፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ሕዝብንና ፓርቲዎችን አስተባብሮ በማታገል ፋንታ፣ "አገዛዙ እየፈጸመው ላለው አገር ዓቀፍ ግፍ ድጋፍ እየሰጠ" እና "የገዢውን ቡድን እሴቶችና ዓላማዎች እያራመደ" ይገኛል በማለት ከሰዋል።
የአቋም ልዩነቶች ላይ የአካሄድ ልዩነት ተጨምሮበት፣ "ትግላችን መስመር ስቶ ከፍተኛ የውስጠ ፓርቲ ትግል ውስጥ ለመቆየት" ተገደን ቆይተናል ያሉት ግለሰቦቹ፣ የኢዜማ የበላይ አመራር ቀስ በቀስ የፓርቲው አደረጃጀት "ነጻና አሳታፊ" እንዳይኾን አድርጎ ዘግቶታል በማለትም ወቅሰዋል።
ካሁን ቀደም፣ የፓርቲው ምክትል መሪ የነበሩት አንዷለም አራጌ እና የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ናትናኤል ፈለቀ ከፓርቲው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።
[ዋዜማ]