ሰበር ዜና
በታላቁ አንዋር መስጅድ በዛሬው እለት የተካሔደ ተቃውሞ ባይኖርሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይል ግን ወደ ህዝቡ ቀጥታ መሳርያ እየተኮሰ እንደሆነ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል። እስካሁን ቁጥራቸው በቅጡ ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎችም መጎዳታቸውን አብረው ገልጸውልናል። ጥቃቱ ወደ ሴቶች መስጅድም የዘለቀ ሲሆን ሴት ምዕመናኖች ላይም የጸጥታ አካሉ የጥይት እሩምታ መክፈቱን ለማወቅ ችለናል። ዝርዝሩን እየተከታተልን ሲሆን መረጃዎችን ወደናንተ የምናድርስ ይሆናል።
© ሀሩን ሚዲያ
#ከትልቅ_ሰው_ሪል_ስቴት
በመሀል ካዛንቺስ በሽያጭ ላይ ነን
50/50 #የባንክ_ብድር_ ዝቅተኛ ወለድ
ግንባታወች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የሚረከቡ ናቸው።
በአንድ ወለል ላይ አራት አባወራዎች ብቻ
ባለ 2 መኝታ ቤት
#169ካሬ
#171ካሬ
ባለ 3 መኝታ ቤት
#167ካሬ
#178ካሬ
ቅድመ ክፍያ #30%
~ሁሉም መኝታዎች የራሳቸውን መታጠቢያ ክፍል ያላቸው።
~ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች እንዲሁም የሰራተኛ መኝታን ያካተተ
~ባለ 2 ቤዝመንት ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
~የ24ሰአት የደህንነት ካሜራዎች
~የእስፖርት ማዘውተሪያ
~ግዙፍ የዉሀ ማጠራቀሚያ
~መጠባበቂያ ጄኔሬተር
~የ ቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
~ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማዘጋጃ የሚውል የተንጣለለ ሰገነት
በ 10 ወራት የሚጠናቀቅ
/channel/Realestateconsult12
ለበለጠ መረጃ
+251946404247
በሀገረ ሜክሲኮ በካጀሜ ወረዳ
ዩዋን ኤን የተባለው ግለሰብ ሀገር ሰላም ብሎ የድሮ ፎቶዎቹን እየገረበ ነው
ድንገት ሊዮኖራ የተባለችው ሚስቱ ስትመጣ ዩዋን አንድ ፎቶ እያየ ነበር
የእርሱ እና የሚስቱ ሊዮኖራ የቆየ ፎቶ ነበር የሚመለከተው - ሚስቱ ቀጭን እያለች ከእርሱ ጋር ፍቅር እየሰሩ የተነሱት ፎቶ ነበር
ሚስትየው ሊዮኖራ ወዲያውኑ ባሏ የሌላ ሰው ፎቶ እያየ መስሏት በያዘችው ቢላዋ 37 ጊዜ ወጋችው:: ፖሊስ ደርሶ ሰውዬውን ከሞት ያዳነው ሲሆን
ሚስትየውም
👇🏾
"ባሌ የእኔን ፎቶ የሚያይ አልመሰለኝም ነበር! ድሮ ቀጭን እያለሁኝ ምን እንደምመስል ተረስቶኛል:: ፎቶው የእኔ እንደሆነ እየነገረኝ እንኳ አላመንኩትም ነበር"
ትግሉ ከባድ ነው ወገን 🙄😝
"እንዲህ ያለ ትግል ነው የገጠመን" አለ መንጌ
ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ 25 ፎቅ ሕንጸ ሊገነባ ነው
=======#=======
ሐሙስ ግንቦት 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ወጋገን ባንክ በመቀሌ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
ሕንፃው የሚገነባው በትግራይ ክልል ዋና ከተማ በመቀሌ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም አቅራቢያ በ3,500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መሆኑን ትግራይ ቲቪ ዘግቧል።
ለባንኩ ሕንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት ትግራይ ክልላዊ መንግሥት ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ "ወጋገን ባንክ ለትግራይ መልሶ ግንባታ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይገባል" ሲሉ ማሳሰባቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
/channel/addismaleda
የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ልጅ ዲቦራ ማዲንጎ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃሽ!! የማዲንጎ ጓደኛ የሆነው ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ በዱባይ ተገኝቶ የደስታ ተካፋይ ሆኗል። «ወንድሜ ማድዬ በህይወት ኖሮ ይሄንን ቢያይ ምንኛ ደስ ይል ነበር ግን አልሆነም አምላክ ነብስህን በገነት ያኑርልኝ ወንድሜ ማዲይዬ የዲቦራ እናት ሮዚ እንዲህ በስርአት የታነፀች ጎበዝ ተማሪ እንድትሆን ላደረግሽው ውድ እናት ክብረት ይስጥልኝ» ብሏል ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ።
እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዲቦራ!!
ሰሞኑን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤሊያስ ወረዳ መልከአ አንድነት ገዳም አካባቢ በተለያዩ በተባሉ ምክንቶች በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና የህክምና ተቋማት አመለከቱ።
በግጭቱ በአንድ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የነበሩ ምዕመናን ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ200 በላይ በሚሆኑ የመንግስት የፀጥታ አካላት ላይም የአካል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡
በገዳሙ ከ600 በላይ ሰዎች ይኖሩ እንደነበረ የተናገሩ አንድ አስተያየት ሰጪ ከ95 ከመቶ በላይ ቆስለዋል፣ ተገድለዋል አሊያም ተበትነዋል ብለዋል።፡
ካለፈው ግንቦት 18 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ደገሎ ቀበሌ፣ ብሔረ ብፁዓን ሥላሴ መልከአ አንድነት ገዳም አካባቢ መነሻው በግልፅ ባልታወቀ ምክንያት በምዕመናንና በፀጥታ ኃይሉ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታዎቹ ምዕመናን በከባድ ጦር መሣሪያ በታገዘ ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉንና ሌሎቹ መበተናቸውን የዓይን እማኞች ለDW ተናግረዋል። ግጭቱ ለለተከታታይ 5 ቀናት ከተካሄደ በኋላ ትናንት እኩለ ቀን አካባቢ መቆሙን ተናግረዋል፡፡
አንድ የደብረኤሊያስ ሆስፒታል አስተያየት ሰጪ ሰሞኑን በነበረው ግጭት ከ200 በላይ የመንግስት የፀጥታ አካላት ቆስለው ወደ ሆስፒታሉ መድረሳቸውን ተናግረዋል ሲል ዓለምነው መኮንን ከባሕርዳር ዘግቧል፡፡ ከአካባቢው አስተዳደሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሰሞኑን በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ምንጭ: ዶቸ ቨለ
OPTIMUM PHYSIOTHERAPY SPECIALTY CLINIC
ወደ ኦፕቲመም ፊዚዮቴራፒ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ሲመጡ እነዚህን አገልግሎቶች ከዘመኑ ህክምና መሳሪያዎች እና ብቁ ባለሞያዎች ጋር በጥራት ያገኛሉ 👇
⏩ የጀርባ/ዲስክ ህመም
⏩ የአንገትና የትከሻ ህመም
⏩ የጉልበት፣ የዳሌ እና የእግር ህመም
⏩ የቁርጭምጭሚት እና የመገጣጠሚያ ህመም
⏩ የጡንቻ መድከም እና የፊት መጣመም
⏩ በእጅ/እግር ላይ ለሚደርስ ድንዛዜ
⏩ ከስትሮክ በኋላ ለሚደርስ የሰውነት መድከም
⏩ ከማንኛውም ቀዶ ጥገና በኋላ ለሚያስፈልግ ማገገም
⏩ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ለሚደርስ አካላዊ ጉዳት
⏩ ለህፃናት የእድገት ውስንነት እና የሰውነት ሚዛን ችግር
🌴 በአጠቃላይ ለማንኛውም የጡንቻ፣ የዲስክ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች የተሟላ ህክምና ያገኛሉ 👌
☀ ሌላም የምስራች አለን!
አዲስ በተከፈትነው ቤተል በሚገኘው ቅርንጫፋችን ከነበሩት አገልግሎቶች በተጨማሪ የዘመኑን ህክምና መሰረት ያደረገ የሐይድሮቴራፒ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል።
ለየት የሚያደርገን 👌
▶ ለድርጅቶች የዱቤ አገልግሎት እንሰጣለን
▶ የቤት ለቤት አገልግሎትም መስጠት ጀምረናል
አድራሻችን
ቁጥር አንድ
አዲስ አበባ፣ ለቡ ቫርኔሮ ሪል ስቴት ፊትለፊት
ኦሳክ ታወር
☎ 251118442096
℡ 251939290222
ቁጥር ሁለት
አዲስ አበባ ቤተል፣ አዲሱ መንገድ፣ የውሃ ታንከሩ ጎን
☎ 251901845797
☏ 251901863797
Websites
https://optimumphysiotherapy.com.et
Telegram
/channel/optimumphysiotherapyspecialty
Facebook
https://www.facebook.com/optimumphysioclinic?mibextid=ZbWKwL
የማንሰማው የለም‼ የቲማቲሙን እርሻ ወደ ስንዴ ካልቀየርክ እየተባለ ነው። 👆
https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
እዚህ ደረጃ ላይ ተደርሷል ።
**********************
በደቡብ ክልል ፣ ሀዲያ ዞን ሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአጠቃላይ ሰራተኞቹ የሚያዝያ ወር ደመወዝ ባለመክፈሉ ሰራተኞች ስራ አቁመዋል ። ይሁን እንጂ ሆስፒታሉ ሰራተኞቹ በአስቸኳይ ወደስራ ገበታቸው ካልተመለሱ " ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ እንደማይሆን አስታውቋል ።
.
ፎቶ ፦ Hakim
#ከትልቅ_ሰው_ሪል_ስቴት
በመሀል ካዛንቺስ በሽያጭ ላይ ነን
50/50 #የባንክ_ብድር_ ዝቅተኛ ወለድ
ግንባታወች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የሚረከቡ ናቸው።
በአንድ ወለል ላይ አራት አባወራዎች ብቻ
ባለ 2 መኝታ ቤት
#169ካሬ
#171ካሬ
ባለ 3 መኝታ ቤት
#167ካሬ
#178ካሬ
ቅድመ ክፍያ #30%
~ሁሉም መኝታዎች የራሳቸውን መታጠቢያ ክፍል ያላቸው።
~ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች እንዲሁም የሰራተኛ መኝታን ያካተተ
~ባለ 2 ቤዝመንት ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
~የ24ሰአት የደህንነት ካሜራዎች
~የእስፖርት ማዘውተሪያ
~ግዙፍ የዉሀ ማጠራቀሚያ
~መጠባበቂያ ጄኔሬተር
~የ ቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
~ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማዘጋጃ የሚውል የተንጣለለ ሰገነት
በ 10 ወራት የሚጠናቀቅ
/channel/Realestateconsult12
ለበለጠ መረጃ
+251946404247
በሸገር ሲቲ የመስጂድ ፈረሳው መቀጠሉ ተሰማ።
በከተማዋ አጃምባ የሚገኘው ቀርሳ (አቡዘር)መስጂድ በትላንትናው ዕለት መፍረሱ ተገልጿል።
"አፍራሽ ሀይሎቹ ዕልህ በሚመስል መልኩ መስጅዱን በዶዘር ሙሉ በሙሉ አውድመውታል" ሲሉ ነው የአይን እማኞቹ የገለፁት።
በፉሪ ክፍለ ከተማ ብቻ አሁን የፈረሰው መስጅዲ 13ኛው የፈረሰ መስጅዲ መሆኑን የሰበታ መጅሊስ ቦርድ አባል ተናግረዋል
የመጅሊሱ መሪ እንዲህ ብለውን ነበር በተናገሩ በሁለት ቀን ውስጥ ይህ ሆኗል
መጅሊሱን ለባለቤቶቹ መልሱ
ለወር በፊት ቻይና የሰነበቱት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፍወርቂ ዛሬ ወደ ራሺያ ሞስኮ አመርተዋል።
በቀጠናው ምዕራባውዊያን ፍጥጫ ኢትዮጵያ ወደ ምዕራቦቹ ዘንበል ያለች ሲሆን የኤርትራ ወደ ምስራቅ መሄድ አከባቢውን የፖለቲካ ውጥረት እንዳያባብስ ያሰጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰኑ ተቋማት አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት በውክልና አስተላልፎ ሊያሰራ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ መስሪያ ቤቶች፤ የተወሰኑ ስራዎቻቸውን በውክልና ለግል ተቋማት አስተላልፈው (outsource) ሊያሰሩ ነው። በዚህ አሰራር ምክንያት ከስራቸው የሚነሱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችን ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ለማዘዋወር እና “በሚፈልጉበት የስራ መስክ” እንዲሰማሩ ለመደገፍ መታሰቡም ተገልጿል።
አዲሱን አሰራር ተግባራዊ የማድረግ ሂደትን እየመራ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነው። በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ መስሪያ ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ የመከታተል ኃላፊነት ያለበት ይህ ቢሮ፤ አዳዲስ አሰራሮችን የመዘርጋት ስልጣንም በአዋጅ ተሰጥቶታል። ቢሮው የተወሰኑ የመንግስት ስራዎችን ወደ ግል ተቋማት የማስተላለፍ እቅዱን በተመለከተ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ መስሪያ ቤቶች ጋር ዛሬ ሰኞ ግንቦት 21፤ 2015 ዓ.ም ውይይት አድርጓል።
ይህንን አሰራር በቅድሚያ እንዲጀምሩ በጥናቱ የተለዩ የከተማ አስተዳደሩ አምስት መስሪያ ቤቶች እና ስድስት ሆስፒታሎች መሆናቸው በዛሬው ውይይት ላይ ተጠቅሷል። በቅድሚያ ወደ ተግባር ይገባሉ የተባሉት የንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ገቢዎች እንዲሁም የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮዎች እና የአሽከርካሪ፣ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ውስጥ ያሉት የካቲት 12፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ፣ ዘውዲቱ፣ ጋንዲ መታሰቢያ እና ራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሎች የተወሰኑ አገልግሎታቸውን ለግል አካላት ከሚያስተላልፉት ውስጥ ተመድበዋል።
ዝርዝር 👇 https://ethiopiainsider.com/2023/11062/
ብጹዕ አቡነ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኅሊና እስረኛው መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ በታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር፣ የአንቀጸ ብርሃን አንድምታ ትርጓሜ መጽሐፍ ደራሲ፣ የሞዓ ተዋሕዶ መሥራች፣ የወሎ ዩኒቨርስቲ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መሥራችና መምህር እንዲሁም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ (2ኛ ዲግሪ) ተማሪ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፌደራል ፖሊስ ልከዋል።
Читать полностью…የሐሙስ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤሊያስ ወረዳ በሥላሴ አንድነት ገዳምና አካባቢው ሰሞኑን ስለደረሰው የሰላም መድፍረስ ፣የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ከመንግስት ያፈነገጡና የታጠቁ” ያላቸው ሰዎች በገዳሙ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጡ እንደነበር አረጋግጫለሁ ብሏል። አንድ የገዳሙ አገልጋይ እንደሆኑ የሚናገሩ አባት ግን ከገዳሙ ሁለት ታጣቂዎች ውጪ መሣሪያ የታጠቀ ኃይል የለም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች የተኩስ አቁሙን ድርድር እንዲቀጥሉ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች። ሁለቱም ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከልባቸው የሚያከብሩ መሆኑን ግልጽ ካደረጉ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስና ሳዑዲ አረብያ የተቋረጠውን ድርድር እንደገና ለማስቀጠል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቃለች ።
ደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ከዚህ ቀደም የጣለባትን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ማራዘሙን ተቃወመች።በውሳኔ መሠረት ማዕቀቡ እስከ ሚቀጥለው ጎርጎሮሳዊው ግንቦት 31 ቀን፣ 2024 ድረስ ተራዝሟል።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4S5DQ?maca=amh-Facebook-dw
ሰበር ዜና
ጸጋ ነጻ ወጥታለች
ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መግባቱዋ ታውቋል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ተበዳይዋን ጥሎ ወደ ጫካ በመግባቱ በከፍተኛ ክትትል ውስጥ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃዎችን ከደቂቃዎች በኋላ እንደደረሰን እናቀርባለን።
Tare W Lemma
ራስ የጥበቃ አገልግሎት
ለድርጅትዎ ደህንነት 💪
ከተመሰረተ ጀምሮ በአስተማማኝነቱ የተመሰከረለት
"ራስ የጥበቃና ፅዳት አገልግሎት"ን ይተዋወቁ 🙏
ራስ የጥበቃ አገልግሎትን ምን ለየት ያደርገዋል?
በሚያቀርባቸው የጥበቃ ባለሞያዎች የሚከተሉት ዋነኛ ባህሪያት 👇
⏩ ከፍተኛ ሞያዊ ስነምግባር ያላቸው
⏩ ለደንበኛችን ደህንነት ከምንም ነገር ቅድሚያ የሚሰጡ
⏩ ታማኝነት፣ ትህትና፣ ንቃት እና ቅልጥፍናቸው በደንበኞቻችን የተመሰከረላቸው
⏩ "ደንበኛ ንጉሥ ነው፣ እኛ የንጉሦቻችን ደጀን ነን" በሚል አክብሮት ዝቅ በማለትና ታዛዥነትን በማሳየት ከደንበኞቻችን ሙገሳ ያስገኙልን መሆናቸው
👌 ልዩ ያደርጋቸዋል 👌
ራስ የጥብቃና የፅዳት አገልግሎት ሲመጡ
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
በስነስርዓታቸው እና ሞያዊ ሀላፊነት በመወጣት ተልዕኮአቸው 100% ሪከርድ ያላቸው የጥበቃ ባለሞያዎቻችን ያገኛሉ‼
👌 ራስ ጥበቃ! ታማኝ አገልጋይ 👌
ራስ የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት ኃ/ የተ/ የግ/ ማህበር
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ☎
+251 966 02 08 88,
+251 930 51 91 75
19 መምህራን ከሞቱበት የመኪና አደጋ ምንም ሳይሆን የተረፈው መምህር የአደጋው የመጨረሻ ቅጽበት ትውስታ
ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን የደረሰው አስከፊ የትራፊክ አደጋ የ19 የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችን ሕይወት ሲቀጥፍ በ18 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳትን አደርሷል።
የብዙዎችን ሕይወት ከቀጠፈው እና የአካል ጉዳትን ካስከተለው ከዚህ አደጋ ታዲያ ሁለት መምህራን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሕይወት መትረፍ ችለዋል።
ከእነዚህ መምህራን አንዱ ደግሞ ደስታ ሙላቱ ነው።
በአደጋው በተከሰተበት ጊዜ ያ ቅጽበት የሕይወቱ ፍጻሜ እንደሆነ አምኖ የነበረው መምህር ደስታ፤ ከአስከፊው አደጋ በሕይወት መትረፉን የፈጣሪ ተዓምር ነው ይላል።
ቅዳሜ 12/2015 ዓ.ም. ከ50 ያላነሱ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በማታው እና በሳምንቱ ማብቂያ ቀናት (ኤክስቴሽን) በሚሰጠው የትምህርት መርሃ ግብር በሻሸመኔ እና ዶዶላር ካምፓሶች ያሉ ተማሪዎችን ለማስተማር ንጋት 11፡30 ላይ ነበር ከሮቤ የተነሱት።
ይሁን እንጂ ሲጓዙበት የነበረው ተሸከርካሪ በምዕራብ አርሲ ዞን ውስጥ “ዎሻቲ” ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲደርስ መንገድ ስቶ ወደ ገደል ውስጥ ገብቷል።
በዚህም አሰቃቂ አደጋ የ19 የዩኒቨርሲቲው መምህራን ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል።
አደጋው ቅጽበት
“ዶዶላ ጠዋት 2፡30 ላይ ለመድረስ ከሮቤ ከተማ ንጋት 11፡30 ላይ ወጣን” የሚለው ደስታ ያሰቡት ሳይሳካ ከመንገድ መቅረታቸውን ያስታውሳል።
ምንም እንኳ ስለዚህ አስከፊ የትራፊክ አደጋ መንስዔ በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም፣ መምህር ደስታ ግን ሲጓዙበት የነበረው ተሸከርካሪ የቴክኒክ ችግር እንደነበረበት ይናገራል ለማንበብ፦https://bbc.in/3C2hJ26
በአማራ ክልል በአምሃራ ሳይንት ወረዳ ስብሰባ ሲያካሄዱ በነበሩ አመራሮች ላይ የቦምብ ጥቃት ሙከራ ተደረገ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምሃራ ሳይንት ወረዳ ስብሰባ በማካሄድ ላይ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ እና ቀበሌ አመራሮች ላይ ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 22፤ 2015 የቦምብ ጥቃት ሙከራ መደረጉ ተነገረ። በብልጽግና ፓርቲ የተዘጋጀን ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ሲሳተፉ የነበሩትን እነዚህን አመራሮች ኢላማ በማድረግ የተወረወረው ቦምብ ቢፈነዳም፤ በሰው ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የወረዳ አስተዳደሩ አስታውቋል።
በአምሃራ ሳይንት ወረዳ መቀመጫ በሆነችው አጅባር ከተማ ይካሄድ በነበረው በዚህ ስብሰባ ላይ ቦምብ የተወረወረው፤ ትላንት ከቀኑ አስር ሰዓት ተኩል ገደማ እንደሆነ የወረዳው የአስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፉ ቦጋለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ቦምቡ ስብሰባው ይካሄድበት በነበረው የአምሃራ ሳይንት ወረዳ ምክር ቤት አዳራሽ የውጪያኛው ክፍል ላይ ማረፉንም ኃላፊው አስረድተዋል።
“[ቦምቡ] ወደ አዳራሹ ለመግባት አንድ 50 ሴንቲ ሜትር ርቀት ነበር የቀረው። ተፈናጥሮ ግንቡን እና መስታወቱን መትቶታል” ያሉት አቶ ሰይፉ፤ ይህን ተከትሎ በተከሰተው ፍንዳታ የወረዳው ምክር ቤት አዳራሽ መስታወት መሰባበሩን እና የአጥሩ ቆርቆሮ መበጣጠሱን ገልጸዋል። በትላንቱ የጥቃት ሙከራ “በሰው ህይወትም ሆነ በሌላ አካል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም” ያሉት የወረዳው ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ሆኖም ግን ቦምቡ የአካባቢው አመራሮች ስብሰባ እያካሄዱ ባሉበት የተወረወረ በመሆኑ ኮንፍረንሱን “ታላሚ እና ታሳቢ ተደርጎ የተፈጸመ ነው” የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ https://ethiopiainsider.com/2023/11085/
ባህር ዳር አሁን!
ከባህር ዳር ከተማ ዙሪያ እና አካባቢው የተሰባሰቡ የአማራ ገበሬዎች በድጋሚ በአፈር ማዳበሪያ እጦት ምክንያት መሬታችን ጦም ሊያድር ነው ።እህል መዝራት አልቻልንም በማለት በአሁኑ ሰዐት በባህር ዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው ።
የጸጋ እና የጠላፊው ጥያቄ ምንድን ነው?
በሀዋሳ ከአንድ ሳምንት በፊት የተጠለፈችው ጸጋ በላቸው እስካሁን ያለችበት አልታወቀም።
ጸጋ በላቸው ከተጠለፈች ዘጠነኛ ቀን ቢሆናትም ድምጿን የሰማሁት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ይላል ወንድሟ ታምሩ።
“እኔን ነጻ ማውጣት አትፈልግም ወይ? እኔን ነጻ በሚያወጣ መልኩ ተደራደር” ብላኛለች፥ ይሁን እንጂ ለድርድር ከተቀመጥን ደግሞ እሷ በሰላም የምትወጣበትን ዋስትና አላገኘንም ባይ ነው።
ጠላፊው ግለሰብ ደግሞ ሽምግልና መቀመጥ ግዴታ መሆኑን ደጋግሞ መግለጹን ነው የሚናገረው።
ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ያንብቡ፣ https://am.al-ain.com/article/a-girl-abducted-hawasa-city
እወዳታለሁ፣ እጮኛዋን ማግባት የለባትም ብሎ የጠለፋት የሀዋሳ ከንቲባ ቦዲጋርድ፣ ወደ ልጅቷ ሽማግሌ ላከ ለመታረቅ።
አግቶ እኮ ነው ለመታረቅ የሚልከው። ሽምግልና ሂዱልኝ ካላቸው
ከሽማግሌዎቹ ውስጥ አንዱ የፖሊስ አዛዡ ነው አሉ።
መረጃው ከቤተሰቧ የተገኘ ነው።
የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል‼
የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ የወ/ሪት ፀጋ በላቸው ጠለፋ አስመልክተው የሰጡት መግለጫ
ከወ/ት ፀጋ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማኀበራዊ ሚድያዎች የተዘገበው አስነዋሪ ድርጊት ከተማ አስተዳደሩ ጥቆማ ከቀረበበት እለት ጀምሮ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እየተከታተለዉ እንደሚገኝ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አስታወቁ።
በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠረው ግለሰብ የልዩ ኃይል አባል የነበረና በመንግስትና ህዝብ የተሰጠውን ታላቅ ኃላፊነት በማይመጥን መልኩ የተጠረጠረበትን ወንጀል መፈጸሙን ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
በወንጀሉ ላይ ፖሊስ መረጃ ከደረሰዉ ግዜ ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከከተማችን ፖሊስ፣ ከሲዳማ ፖሊስና ከክልላችን ሰላምና ጸጥታ ጋር በመቀናጀት ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ 6 ሰዎችን ይዞ በማጣራት ላይ ብለዋል።
ተጠርጣዉ ግለሰብ ከከተማ ወጥቶ የተሰወረ በመሆኑ ከክልላችን የሰላምና ጸጥታ ቢሮና ከክልላችን ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በልዩ ትኩረት እየሰራን ያለን በመሆኑ ዉጤቱን ለህዝባችን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ ከንቲባው ገልፀዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ አያይዘውም የተፈጸመዉ የወንጀል ድርጊት ከከተማ አስተዳደሩም ሆነ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ምንም የማይገናኝና ፈጻሚ ግለሰብ ብቻ የሚጠየቅበት በመሆኑ መላው ህዝባችን ከዚህ ቀደም በተለመደው ወንጀልን በመከላከልና የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቁ ከጸጥታ አካሉ ጎን በመሆን የከተማችንን መልካም ስምና ገጽታ የሚያጎድፉ ድርጊቶችን የመጠበቅ ስራውን አጠናክሮ እንዲሰራ አሳስባለሁ ብለዋል።
ወንጀል ፈጻሚ ማንም ይሁን ማን በህግ ተጠያቂ እንዲሆን አበክረን እንሰራለን ማለታቸው የደረሰን ዜና ይጠቁማል።
High School ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማት ጀምረዋል።
ዛሬ ስልጤ ዞን ዳሎቻና ባሌ ዞን ሮቤ High School መስጂዴን አትንኩ ብሎዋል።
ግንቦት 22፣2015
መንግስት በፍራንኮ ቫሉታ ከውጪ እንዲገቡ የፈቀዳቸው ምርቶች ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው መጨመር አሣሣቢ ሆኗል ተባለ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርቶቹን በፍራንኮ ቫሉታ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ጋር ጋር በጌትፋም ሆቴል ውይይት አድርጓል።
ዘይት ፣ ስኳር ፤ ሩዝና የህፃናት ወተት በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች መሆናቸው ይታወሳል።
ምርቶቹ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በመፈቀዱ ባለፉት አስር ወራት ብቻ መንግስት በታክስ መልክ ማግኘት የነበረበትን ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አጥቷል ተብሏል።
ነገር ግን የምርቶቹ ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው ሲጨምር እንደሚታይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ተናግረዋል።
ጭማሪው እየታየ ያለዉ በአለም ላይ ዋጋቸው ቀንሶ ባለበት ወቅት ጭምር ነው ብለዋል።
ምርቶቹ ወደ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ስርጭታቸውም ላይ ብዙ ግልፅነት እንደሌለ ተነግሯል።
እንደ ማሣያም ዘንድሮ በአስር ወራት ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት 97 ሚሊየን ሊትር እንደሆነ ተጠቅሷል።
አምና በተመሣሣይ ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ግን ከአንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ነበር ተብሏል።
እንዲያም ሆኖ በገበያው ላይ የምርት አቅርቦት ችግር የለም ነው የተባለው።
ሁኔታው በስርጭቱ ላይ ችግር መኖሩን አመላካች እንደሆነ ተጠቅሷል።
አስመጪዎች በበኩላቸው በብርና ዶላር መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋት የምርቶቹ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
#ShegerWerewoch #Ethiopia #ፍራንኮ_ቫሉታ #የንግድና_ቀጣናዊ_ትስስር_ሚኒስቴር
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
በአዲሱ ሸገር ከተማ ቤት የማፍረሱ ሂደት 100ሺ አቤቱታዎች ቀርበውበታል ተባለ
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ዜጎችን በግዳጅ የማስነሳትና ቤቶችን የማፍረስ ሂደት 100ሺ ቅሬታዎች እንደቀረቡበት ተገለፀ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ መረጃው ያልተጣራና ከአንድ ወገን ብቻ የተገኘ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ “ህገወጥ ግንባታ” በሚል እየተካሄደ ካለው የቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ከአንድ መቶ ሺ በላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት ገልጿል፡፡
ተቋሙ በተያዘው በጀት አመት ከ133ሺ በላይ አቤቱታዎችን መቀበሉን ገልፆ፤ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ካለው የቤት ፈረሳ ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች እንደሆኑም አመልክቷል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ “ህገወጥ ግንባታ” ናቸው እያለ ለሚያፈርሳቸው የመኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች ምትክ ቦታ እንደማይሰጥና ለተፈናቃዮችም ጊዜያዊ መጠለያ እንዳልተዘጋጀላቸው የገለፀው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ይህ ሁኔታም ተቋሙን እጅግ እንዳሳሰበውና መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ አመልክቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በከተማው እየፈረሱ ያሉት ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተገነቡና የግንባታ ፈቃድ የሌላቸው ቤቶች መሆኑን ጠቁሞ፤ እርምጃው የህግ የበላይነትን ከማስከበር ጋር የተያያዘ ነው ብሏል፡፡
በህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተገለፀውና 100ሺ ቅሬታዎች ቀረቡበት የተባለው ጉዳይም ከእውነት የራቀ፣ ውይይት ያልተደረገበትና፣በአግባቡ ያልተጣራ እንዲሁም ከአንድ ወገን ብቻ በተገኘ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ሲል አስተዳደሩ አስተባብሏል፡፡
በሃዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኛ የሆነችው ፀጋ በላቸው በከተማው ከንቲባ ጠባቂ በሆነው የኃላው መብራቴ ታግታ ከተወሰደች ሰባት ቀናት መቆጠሩን ቤተሰቦቿ አሳውቀዋል።
ወጣቷ እጮኛ ያላት እንዲሁም በቅርብ ልትሞሸር የነበረች ስትሆን የሃዋሳ ከንቲባ ጠባቂ ጠልፎ ከመውሰድ ባለፈ ለቤተሰቦቿ በመደወል "ሽማግሌ እልካለሁ ተቀበሉ። እኔ የከንቲባው ጠባቂ ነኝ ምንም ልታመጡ አትችሉም" በማለት ዛቻና ማስፈራሪያ ጭምር ሰጥቶ ስልኮቹን አጠፋፍቶ ከተሰወረ ውሎ አድሯል።
ይህ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ አንድም የከተማዋን ገፅታ የሚያጎድፍ ሥራን ሠርቷል፣ አንድም የሴቶችን መብት በመተላለፍ ያለ ፍላጎት አስገድዶ አግቷል፣ አንድም የሥራ ኃላፊ ጠባቂ ሲኮን የወታደር ድስፕሊን አለ፤ ያን ድስፕሊን ተላልፎ የሚጠብቀውን ሰው ስልጣንን ተገን በማድረግ ዛቻና ማስፈራሪያ በተበዳይ ቤተሰብ ላይ ሰንዝራል።
የሆነው ሆኖ የሃዋሳ ፀጥታ ዘርፍ፣ የክልሉ ፀጥታ ዘርፍ፣ የደህንነት መ/ቤቱ፣ የከንቲባው ቢሮ እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች የአንዲት ሴት ለዛውም በከተማው የባንክ ሥራ የምትሠራ እና በከተማው የመንግስት ሥራ ኃላፊ ጠባቂ ሆኖ የሚያገለግል መጠለፏ እንዴት አላሳሰባቸውም? እንዴትስ ሰባት ቀን ሙሉ አንድ ሰው ለመያዝ ተሳናቸው? እውን ይህ ሰው ከእነሱ አቅም በላይ ሆኖ ጠፍቶ ነው ወይስ ችላ ብለውት? አዘለም አቀፈም ያው ተሸከመ ነው እንዳሉት የልጁ አስነዋሪ ተግባር ጠቅለል ሲደረግ የሚያስነቅፈው ማንን እንደሆነ ማሰቡ ተገቢ ነው።
ሴቶችየ በጊዜ ጠለፋ የሚባል ኃላቀር አስተሳሰብ የሚያስቡን ሞኝ ወንዶችን በፅኑ እናውግዝ! ወንዶችም ተባበሩን! ነገ ያንተ እህት፣ ልጅ ላለመጠለፋቸው ምን ዋስትና አለህ?
ሔቨን