ምቹ መኖሪያ የደስተኛ ኑሮ አንዱ ምንጭ ነው!
የድርጅታችን ባለ 1 መኝታ 56.34 ካሬ አፓርታማ በሚጠናቀቅ ወቅት የሚኖረው የውስጥ ገፅታ ይህንን ይመስላል::
ክፍሎቹን እያዟዟሩ ለመመልከት ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://sofomer.com/hambra/2/index.htm
ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ አ.ማ.
“አብረን ሰርተን በጋራ እንደግ!”
አድራሻችን
ስልክ
0944307337
0944307338
የሽያጭ ቢሮ መገኛ
👉ቁ1 - ፒያሳ፣ ግሎባል ኢንሹራንስ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 49
👉ቁ2 - ቤተል፣ ለይላ የንግድ ማእከል 3ተኛ ፎቅ
ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ የካቲት 21/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ የፒያሳና አራት ኪሎ ነዋሪዎች ለልማት ከመኖሪያቸው እንደሚነሱ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። አስተዳደሩ ኹለቱን አካባቢዎች መልሶ በማልማትና ነዋሪዎችን በማስነሳት ዙሪያ ትናንት ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እንዳደረገ ገልጧል። ውይይቱ፣ በንግድ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ንግዳቸውን በሚቀጥሉበትና ሌሎች ነዋሪዎች በመልሶ ማልማቱ ዕቅድ በሚስተነገዱበት ኹኔታ ነበር ተብሏል። ነዋሪዎችን ለልማት የማንሳቱን ሂደት የሚከታትል ከአመራሩና ከነዋሪዎች የተውጣጣ ኮሚቴም እንደተዋቀረ ተገልጧል። በተለይ የፒያሳ ነዋሪዎች በሦስት ወራት ውስጥ አካባቢውን እንዲለቁ እንደተነገራቸው እንዳንድ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
2፤ በአፋር ክልል ማክሰኞ'ለት በክልሉ ነዋሪዎችና በኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች መካከል መጠነኛ ግጭት ተከስቶ እንደነበር ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። ግጭቱ የተከሰተው፣ በዞን 3፣ አሚባራ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ቀበሌ አካባቢ እንደኾነ ምንጮች ተናግረዋል። የግጭቱን መነሻ ለጊዜው እንዳላወቁ ምንጮች ገልጸዋል። በዞን 2 ደሞ፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ሠመራ ወደ አባላ ከተማ በሚወስደው መንገድ ላይ ከምግብ ዕርዳታ ሥርጭትና ከመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ፣ በነዋሪዎችና በክልሉ መንግሥት መካከል ትናንት ውጥረት እንደነበር ተነግሯል።
መንግስት ዘንድሮ በሀገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመፍታት 3.2 ቢልዮን ዶላር (ከ180 ቢልዮን ብር በላይ) ያስፈልገኛል ብሏል።
የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነሩ አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለለጋሾች ባቀረቡት እና ዛሬ በተመለከትኩት አንድ ሰነድ ላይ ይህ 3.2 ቢልዮን ዶላር አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 10.4 ሚልዮን ዜጎች ድጋፍ ይውላል ተብሏል።
"ይህን [የገንዘብ መጠን በማሳካት ረገድ] የሚጠብቀን ስራ እጅግ ሰፊ ነው" ያሉት ኃላፊው የሀገር ውስጥ ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ድጋፍ ፈላጊዎች አስከትሏል ብለዋል።
ይህን መረጃ ሳነብ የታወሰኝ ሀሳብ...
አለም ከጋዛ እስከ ዩክሬን፣ ከሱዳን እስከ አፍጋኒስታን ባሉ ቀውሶች ተወጥሮ ተይዟል፣ ሰብአዊ ድጋፎችም እየተመናመኑ መጥተዋል። ምናልባት ኤክስፖርት እያረግን ነው ያልነውን ስንዴ እና እየገነባናቸው ያሉ የመዝናኛ እና የቱሪስት መዳረሻ ሪዞርቶችን እና ፓርኮችን ለግዜው ገታ አድርገን ለዜጎች የተራበ እና የተጠማ ጉሮሮ ብንደርስ በምድርም፣ በሰማይም ደግ ስራ አይሆንም?
ዘገባው የኤሊያስ መሰረት ነው
አፖርትመንት ቤቶች በመሀል ልደታ በ ካሬ 75,000 ብር ብቻ።
ቅድመ ክፍያ ከ 15% ጀምሮ
ባለ 2 እና 3 መኝታ ቤቶች::
0987434409
የጋራ መገልገያዎች
ባለ 2 ቤዝመንት ሰፊ የመኪና ማቆሚያ ።
ግዙፍ የዉሀ ማጠራቀሚያ።
መጠባበቂያ ጄኔሬተር።
የ ቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)።
ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማዘጋጃ የሚውል የጋራ መሰብሰቢያ ።
የመጨረሻዉ ፎቅ ላይ ቴራስ ያላቸው።
በ ፍሎር 3 ቤቶች ።
0987434409 ይደዉሉ
+251987434409 WhatsApp and Telegram
https://call.whatsapp.com/voice/zsTX5fHKZLMtnQbgqFg6vN
ሚዛን አማን ድንገት በተነሳው እሳት የንብረት ውድማት ደርሷል‼
በሚዛን አማን ከተማ ህብረት ቀበሌ በተለምዶው ሀናን ካፌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
ዛሬ የካቲት 19/2016 ከንጋት ጀምሮ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሃናን ካፌን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ በርካታ ቁጥር ያሉት የንግድ ሱቆች መውደማቸው ታውቋል ።
የተከሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ሲያደርግ ማንጋቱን ነው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን
ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና እና በሙያው የሰለጠኑ የሰው ሀይል ባለመኖሩ እሳቱን መቆጣጠር እንዳልተቻለ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እሳቱ በቁጥጥር እየዋለ መሆኑን አቶ አብዱ ሙሃመድ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።
የአደጋው መንስኤና የደረሰ የውድመት መጠንም ገና አልታወቀም።
በዱከም በደረሰ የመኪና አደጋ 7 ሰዎች በላይ ወዲያው ሲሞቱ፣ 11 ሰዎች ላይ ከባድ ለህይወት የሚያሰጋ ጉዳት ደርሷል።
ያሳዝናል 😢
ትናንት ከአርባምንጭ እየተመለሱ የነበሩ የሀዋሳ የጤና ቡድን የግርኳስ አባላት በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በመኪና አደጋ በአመት ከ 5000 በላይ ዜጎቻችንን እንደምናጣ ጥናቶች ያሳያሉ። ዋናው ምክንያት ከተገቢ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ነው።
በእርጋታ እናሽከርክር
ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም እና ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር “ለጠላት ሚስጥር አሳልፈው ስለሰጡ” በሚል ከህወሓት ከማእከላይ ኮሚቴ እና ከአባልነት ማባረሩ ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል‼️
Читать полностью…ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ "ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብገቱ ገለጸ።
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።
ከየካቲት 12 ቀን 20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ " መነኩሴ "ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መንኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።
ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በኦነግ ሸኔ ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
በአግባቡ አላስተናገዳችሁኝም በማለት የምግብ ቤት ባለቤትን የገደለው የፀጥታ ኃይል በእስራት ተቀጣ
#FastMereja
በምዕራብ ሸዋ ዞን ቡርቃ ኤጄሬ አካባቢ በአይን ፍቅር የወደቀላት አስተናጋጅ በአግባቡ አላስተናገደችኝም በማለት የሬስቶራንቱን ባለቤት የገደለው የፀጥታ ኃይል አባል በእስራት ተቀጥቷል፡፡
ረዳት ሳጅን አያኖ ተረፈ የተባለው የምእራብ ሸዋ ዞን የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ፖሊስ አባል በተደጋጋሚ በሚያዘወትርበት ወንድማማቾች ባርና ሬስቶራንት 21 ዓመት የሆነ አስተናጋጅ ጋር በአይን ፍቅር ይዞት የነበረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወደ ሬስቶራንቱ ያመራው ይህው ደንበኛ ዘወትር የምታስናግደው እና የዓይን ፍቅር የያዘባት አስተናጋጅ በሌላ ስራ በመጠመዷ በቶሎ ልታስተናግደው አልቻለችም ፡፡ በዚኅም በመበሳጨት እንዴት ልብሴን እንኳን አክብረሽ አታስተናግጅኝም በማለት በጥፊ የመታት መሆኑን የኤጄሬ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር መሰረት ጉታ በተለይ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የብስራት ሬዲዮ ነው።
ጨፌ ኦሮሚያ የአቶ ታዬ ደንዳአን ያለመከሰስ መብት አነሳ
ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው 6ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባዔ የአቶ ታዬ ደንዳአን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
ታዬ ስለሰላም በመናገር፣ መንግስትን በመተቸቱ ጠቅላዩ ከሚኒስተርነት አውርደውታል። ጠቅላዩን በመተቸቱ በማግስቱ መታሰሩ ይታወሳል።
ጨፌው ያለመከሰስ መብታቸውን ሲያነሳ
ከሽብር ድርጊት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ነው በሚል ነው
በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ የመምህራን እጥረት ሊከሰት ይችላል የተባለ‼️
ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን 2016 (አዩዘሀበሻ)
በሀገሪቱ የመምህራን ብቃት ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የባሰ ጉዳይ ሊገጥመን እንደሚችል ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር ከትናንት በስተያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ማንሳቱን የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
ሚኒስቴሩ የመምህርነት ሙያውን የሚቀላቀለው ሰው በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተገልጿል። ምክር ቤቱ ይሄን ጉዳይ በአፅንኦት እንዲያው የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ብርሃኑ ነጋ አክለውም የመምህራን ጉዳይ የጥራት ብቻ ሳይሆን አሁን በቅርብ ባደረግነው ጥናት ያየነው በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የመምህራን እጥረት ይገጥመናል " ሲሉ ተደምጠዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት አስተማሪ ለመሆን የሚፈልገው የሰው መጠንም በእጅጉ መቀነሱን ገልፀዋል። ለዚህ እንደ አንድ ምክንያት የተነሳው የደመወዝ ክፍያው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ይሄን በተመለከተ ከሲቪል ሰርቪስ ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ሚኒስትሩ መጠቆማቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል(አዩዘሀበሻ)። ጥቆማ❗👇👇
👉በርካታ ተጨማሪ መረጃዎች አሉ፣ይህን የቴሌግራም ቻናል ከስር ባለው ሊንክ join በማደረግ እና ለሌሎች በመጋበዝ ይከታተላሉ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት ራሳቸውን ዕጩ አድርገው ካቀረቡበት ውድድር ትናንት ራሳቸውን አግለዋል። ኹለቱ አገሮች ከውድድሩ መውጣታቸውን ተከትሎ፣ ታንዛኒያ በድጋሚ ለአባልነት ተመርጣለች። የኅብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ ለኹለት ዓመታት የምክር ቤቱን አባላት ከምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና በስምምነት መምረጥ የሚችሉት ኹለት አገራትን ብቻ ነበር። በዚኹ መሠረት፣ ኡጋንዳ ሌላኛዋ አባል ኾና ተመርጣለች። ከ10ሩ አዳዲስ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤቱ አባላት መካከል፣ ግብጽ፣ አንጎላ፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ይገኙበታል።
2 የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ ሱማሊያና ኢትዮጵያ ቁርሾ ውስጥ ከገቡ ወዲህ፣ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ወደ ኢትዮጵያ ሲያቀኑ የአኹኑ የመጀመሪያቸው ይኾናል። ለኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔው ትናንት ከገቡት መሪዎች መካከል፣ የናይጀሪያ፣ የደቡብ ሱዳንና የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የኮሞሮሱ ፕሬዝዳንት እንዲኹም የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ይገኙበታል።
3፤ ሱማሊያና አሜሪካ በሱማሊያ ግዛት ውስጥ አምስት ወታደራዊ ጦር ሠፈሮችን ለመገንባት ትናንት ስምምነት ፈርመዋል። ጦር ሠፈሮቹ የሚቋቋሙት፣ በሞቃዲሾ እና በአራት ፌደራል ግዛቶች ውስጥ እንደኾነ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ጦር ሠፈሮቹ፣ አሜሪካ የምታሠለጥናቸውን "ደናብ" የተሰኙ የሱማሊያ የጸረ-ሽብር ልዩ ኮማንዶዎች አቅም ይበልጥ ለማጎልበት ያለሙ እንደኾኑ ተገልጧል። በስምምነቱ ፊርማ ላይ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድና በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ሞሊ ፊ ተገኝተዋል። [ዋዜማ]
ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ባጋጠመ የእሳት አደጋ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና አንድ ቤተክርስቲያን በቃጠሎው መውደማቸው ተሰምቷል
ትናንት የካቲት 6 ቀን 2016 ዓመት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት በቀድሞዉ አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የህንፃው አንደኛ እና ሁለተኛ ወለል በዉስጣቸዉ ከያዙት ንብረት ጋር ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት በህንጻዉ ላይ ሙሉ በሙሉ ወድመት ከደረሰባቸዉ መካከል በቅርቡ የተቋቋመው እና የሩቅ ምስራቅ ፊልሞችን በአማርኛ ትርጉም ለተመልካቾች ሲያቀርብ የነበረዉ ያ ቴሌቪዥን እና በፓስተር ዘነበች የሚመራው ቤተክርስትያን ይገኙበታል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 20 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ እና ስድስት የዉሀ ቦቴዎች እንዲሁም ሁለት አምቡላንሶች ከ108 የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ህንጻዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር በተደረገዉ ጥረት 105 የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ የዉሀና ፍሳሽና የመብራት ኃይል ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።
በእሳት አደጋዉ አንድ ሰዉ ላይ ቀላል ጉዳት ሲደርስ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 5:40 ሰዓት ፈጅቷል።
ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን
የፎቶ ዘገባ፦ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ጡረተኞች ዛሬ ሐሙስ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ፤ የ18 ወራት የጡረታ አበል ባለማግኘታቸው በአስከፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የጡረተኞችን ጉዳይ አጽንኦት ሰጥቶ ግዴታውን እንዲወጣ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
ቁጥራቸው 250 ገደማ የሚሆኑት ሰልፈኞች፤ መፈክሮችን፣ የትግራይ ክልል እና የፌደራል መንግስት ባንዲራዎችን አንግበው ዛሬ ረፋዱን በመቐለ ከተማ ጎዳናዎች ተዘዋውረዋል። ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፤ “መንግስት ለጡረተኞች ራሱ ያወጣውን አዋጅ እና ደንብ ያክብር”፣ “ባለውለታ ይከበራል እንጂ በረሃብ እና በበሽታ አይቀጣም” የሚሉት ይገኙበታል።
በመቐለ ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ የጡረተኛ ማህበራት የተውጣጡት ሰልፈኞች፤ ጥያቄያቸውን በመያዝ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽህፈት ቤት አምርተዋል። ሰልፈኞቹ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር የዘገየው ውዝፍ የጡረታ አበል እንዲከፈላቸው እና የጡረተኞች ቦርድ አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥያቄ አቅርበዋል። በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የግጭት ማቆም ስምምነትም በአስቸኳይ ሙሉ በመሉ ተግባራዊ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
የሰሜን ሪጅን ማህበራዊ ዋስትና እና የመንግስት ሰራተኞች ኤጀንሲ ለሰልፈኞቹ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፤ ጡረተኞች እስካሁን ያልተከፈላቸውን አበል እንዲያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
አንዳንድ ሰራተኞቹ ፎርጅድ ወይም እውቅና የሌለው የትምህርት ማስረጃ አላቸው የሚል መረጃ በቅርቡ የወጣበት ኢቢሲ መረጃውን ያወጣብኝ የቀድሞ ሰራተኞዬ "ተአማኒነቴ እንዲቀንስ አድርጓል" በማለት 10 ሚልዮን ብር ካሳ ይክፈለኝ ብሎ ከሷል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አቶ ወገን አበበ የተባለ ግለሰብ "የኢቢሲ 400 ሰራተኞች ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ነው ያላቸው" በማለት ስሜን አጥፍቷል፣ በዚህም ምክንያት የደረሰብኝን የ10 ሚልዮን ብር ኪሳራ ይክፈለኝ ብሎ ክስ እንደመሰረተ ከፍርድ ቤት ምንጮች፣ ከራሱ የኢቢሲ ሰራተኞች እንዲሁም ከአቶ ወገን ያገኘሁት መረጃ ያሳያል።
ለፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት፣ ኮልፌ ምድብ ፍትሀብሄር ችሎት መስከረም ወር 2016 ላይ የቀረበው እና የተመለከትኩት ይህ አቤቱታ እንደሚያትተው መረጃው የወጣበት ሰሞን የአዲስ አመት መዳረሻ ስለነበር ተቋሙ ማግኘት የሚገባውን ከፍተኛ ገቢ አቶ ወገን እንዲያጣ አድርገዋል ይላል።
ክሱ አክሎም "ተከሳሽ በፈጠሩት የስም ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት የከሳሽን መስሪያ ቤት ተአማኒነት ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ በመክተታቸው፣ ወቅቱም የበአል ሰሞን እንደመሆኑ ከብር አስር ሚልዮን በላይ የሚሆን ገቢ እንዲያጣ ምክንያት ሆነዋል" ይላል።
በዚህ ተመሳሳይ ጉዳይ ከዚህ በፊት በወንጀል ተከሰው፣ ኋላ ላይ ግን ነፃ ወጥተው የነበሩት አቶ ወገን አሁንም በህግ ፊት ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ነግረውኛል።
አቶ ወገን እና ሌላ አንድ ግለሰብ ለፌደራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአንዳንድ የኢቢሲ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛነት ማስረጃ ማስገባታቸው ታውቋል።
ኤሊያስ መሰረት
አማራ ክልል‼️
በአማራ ክልል ሸዋሮቢት ከተማ ዛሬ ከረፋዱ 5:40 አካባቢ ባጀጅ ተራ ተኩስ ነበር እንደነበር የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል። በተኩሱም 2የፖሊስ አባላት እና 1 የሰላም እና ደህንነት ሃላፊ ሲገደሉ የፖሊስ አዛዡ ክፉኛ ተመቶ ሪፈር ተብሏል ሲሉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል። በዚሁ ተኩስ 1 በተባራሪ ጥይት እግሩን የተመታ ሰውም አለ ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
👉በርካታ መረጃዎች አሉ፣ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራና የኦሮሚያ ተወካዮችን በተለያየ ቀን ካናገሩ በኋላ፣
ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ዛሬ አናግረዋል።
ዋናው አጀንዳ ስለ ሰላም ነው።
በጎጃም ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። በሸዋና ወለጋም ከሸኔ ጋር እንዲሁ ጦርነት እየተደረገ ነው።
ዛሬ እየተወያዪ ያሉት አንፃራዊ ሰላም ውስጥ ያሉ ናቸው።
ኦሮሞ፣ አማራና ትግራይ ነበሩ ስለ ሰላም በሚገባ መመከር ያለባቸው።
ጥቂት የብሄሮች ተወካዮችን በቤተመንግስት ማወያየት የሰላም ድርድር አይመስልም።
ሰላም ከተፈለገ
ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም እንደሚባለው፣
ግጭት ያለበት ህብረተሰብን ማወያየት፣ ከፋኖና ሸኔ ጋር ተቀምጦ መነጋገር ነው።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በባህር ዳር ከተማ ፈጽመዋቸዋል ያላቸው “ግድያዎች” “የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ ይችላሉ” አለ
ከተማ ፈጽሟቸዋል የተባሉ “ከህ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ “ተንሰራፍቷል” ያለው “የተጠያቂነት እጦት፤ “በዓለም አቀፍ ህግ ወንጀል የሆኑ ከባድ በደሎችን የሚፈጽሙ አካላትን የሚያደፋፍር ነው” ሲል ወንጅሏል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህን ያስታወቀው፤ ባለፉት ነሐሴ እና መስከረም ወራት በባህር ዳር ከተማ የተገደሉ 12 ሰዎችን በተመለከተ፤ ዛሬ ሰኞ የካቲት 18፤ 2016 ባወጣው አጭር ሪፖርት ነው። ዓለም አቀፉ ተቋም በዚሁ ሪፖርቱ በመጀመሪያ የዳሰሰው፤ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ አቡነ ሀራ እና ልደታ በሚባሉ አካባቢዎች የተፈጸመውን የስድስት ሰላማዊ ዜጎችን ግድያ ነው።
ስድስቱ የባ/ር ነዋሪዎች የተገደሉት፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት “በቅርብ በተተኮሱ ጥይቶች” መሆኑን አምነስቲ የዓይን እማኞችን እና የቤተሰብ አባላትን ዋቢ በማድረግ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ “ከህግ አግባብ አውጪ” ተገድለዋል ካላቸው “ሰላማዊ ዜጎች” መካከል፤ “በመኖሪያ ግቢያቸው እንጀራ እየጋገሩ ባሉበት በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተመቱ” የዓይን እማኞች የመስከሩላቸው ወ/ሮ ይታጠቁ አያሌው አንዷ ናቸው።
በዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፤ “በንግድ ስራ ይተዳደሩ ነበር” የተባሉት የ55 ዓመቱ አዛውንት አቶ አየነው ደፍረሽ እና ሁለት ልጆቻቸው ይገኙበታል። “እነዚህ ሶስት የቤተሰብ አባላት የተገደሉት፤ ከቤተክርስቲያን ወደቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ጎዳና ላይ በጥይት ተመተው ነው” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።
ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዶ/ር ካሳ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት አነሳ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 16፤ 2016 ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ፤ የየካ ምርጫ ክልል ተወካይ የሆኑትን የዶ/ር ካሳ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት አነሳ። የዶ/ር ካሳ የህግ ከለላ የተነሳው፤ “በአማራ ክልል ተደራጅቶ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ይንቀሳቀሳል” ከተባለ “ጸረ ሰላም ኃይል” ጋር “ትስስር ያላቸው” እና “ለቡድኑ መመሪያ ይሰጡ የነበረ በመሆኑ ነው” ተብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
የቅዳሜ ማለዳ የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች
1፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ የብሄረሰብ ዞን በመጓዝ ላይ የነበሩ ስምንት መምህራንን ሐሙስ'ለት "ጭካኔ በተሞላበት ኹኔታ ገድለዋል" በማለት በ"ኤክስ" ገጹ ላይ ባወጣው አጭር መግለጫ ከሷል። ስምንቱ መምህራን የተገደሉት ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ መኾኑን የገለጠው ቡድኑ፣ ግድያውን "በጥብቅ አወግዛለኹ" ብሏል። ቡድኑ ተገደሉ ያላቸውን መምህራን ስም አልጠቀሰም።
2፤ ኢሰመኮ፣ በኦሮሚያ ክልል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ኢመደበኛ የአማራ ታጣቂዎች በውጊያና ከውጊያ ዐውድ ውጭ በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን ማረጋገጡን አዲስ ባወጣው የኹለት ዓመታት የክትትል ሪፖርት አስታውቋል። ኢሰመኮ ይህን ያለው፣ በቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሲቪሎች ላይ ተፈጽመዋል ያላቸውን ከሕግ ውጭ የኾኑ ግድያዎች በማስመልከት ባወጣው ሪፖርት ነው። ኮሚሽኑ፣ ድርጊቶቹ “እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች” እና "የጦር ወንጀልን" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀልን" ሊያቋቁሙ እንደሚችሉ ገልጧል። በጥሰቶቹ ላይ "ፈጣን፣ ገለልተኛና የተሟላ" ምርመራ ሊደረግ፣ ተጠያቂነት ሊረጋገጥና ተጎጂዎች ሊካሱ እንደሚገባም ኢሰመኮ አሳስቧል።
3፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ረቡዕ'ለት በአራት መነኮሳትና አባቶች ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ ከምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር አመራሮች፣ ከዞኑ የጸጥታ ኃላፊዎችና ከገዳሙ ኃላፊዎች ጋር ትናንት ውይይት እንዳደረገች አስታውቃለች። በውይይቱ፣ የሟቾቹ አስክሬን በመንግሥት ጸጥታ አካላት ወደ ገዳሙ ተወስዶ ሥርዓተ ቀብራቸው እንዲፈጸምና መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ጸጥታ አካላት ገዳሙንና ገዳማዊያኑን በዘላቂነት እንዲጠብቁ ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ ቤተክርስቲያኗ ገልጣለች። የተወያዮቹ ግብረ ኃይል፣ ከዚኹ ውይይት ጀምሮ በተሠሩ ሥራዎች ዙሪያ ወደፊት ተገናኝቶ ለመምከር ቀጠሮ መያዙም ተገልጧል።
4፤ የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴና ማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን የሕወሃት ጠቅላላ ጉባዔ በኹለት ወራት ውስጥ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ፓርቲው አስታውቋል። ፓርቲው፣ የኹለቱ አካላት የጋራ መድረክ የጉባዔውን አጀንዳ መምረጣቸውንም ገልጧል። ፓርቲው ጨምሮም፣ በመጪው ሳምንት በክልል ደረጃ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባና ከዚያም በዞን፣ ወረዳና ጣቢያ ደረጃ የአመራር፣ የአባላትና የሕዝብ ተወካዮች መድረክ ለማካሄድ ከውሳኔ ተደርሷል ብሏል። ምርጫ ቦርድ ሕወሃትን ከሕጋዊ ፓርቲነት የሰረዘበት ውሳኔ ግን እስካኹን እንደጸና ነው።
5፤ በተመድ የሱማሊያ ቋሚ መልዕክተኛ፣ ኢትዮጵያ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ውስጥ ወታደር እንዳዋጣ ተሳታፊ አገር "አመኔታ አጥታለች" ሲል የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሰሞኑን ላቀረበበት ወቀሳ ምላሽ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የጠቀሳቸው ጉዳዮች፣ "አሳሳች" እና "እውነትነት የሌላቸው" እንደኾኑም የሱማሊያው መልዕክተኛ ገልጧል። የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የኢትዮጵያን "ግዛት የመጠቅለል" ሙከራ "ኹሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ነው" ማለቱ፣ "ኢትዮጵያ የሱማሊያን የግዛት አንድነት ለመጣስ የምትከተለውን የተሳሳተ ዕቅድ ያሳያል" በማለትም የሱማሊያው መልዕክተኛ ወቅሷል። የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ፣ የሱማሊያው ቋሚ መልዕክተኛ በተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቅርቡ ያሰሙትን ንግግር "ሐሰተኛ" በማለት መውቀሱ ይታወሳል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ምክር ቤት አባል የነበሩትን የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
Читать полностью…ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በቅጽል ስሙ ልጅ ያሬድ በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለ።
የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።
ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃውን አቅርቧል።
የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።
ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።
ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።
ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።
ሰበር‼️
"የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በ2024 የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዳይሳተፍ ለማደናቀፍ ያደረገውን ቀስቃሽ ሙከራ በፅኑ ያወግዛል ሲል መግለጫ ሰጥቷል‼️
ይህ ድርጊት ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ እና አለምአቀፍ ፕሮቶኮሎችን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የተመሰረቱትን የአፍሪካ ህብረት ወጎች ይጥሳል።
ይህ ባህሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ በመጣው የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳቱ ድርጊቶች ዝርዝር ውስጥ ይጨምራል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤትን የምታስተናግድ በመሆኗ፣ አመራሯ እና መንግስቷ ሁሉንም የአፍሪካ መሪዎች በእኩልነት የማስተናገድ ግዴታ አለባቸው። የአፍሪካ ህብረትን ማስተናገድ ለኢትዮጵያ ክብርም እድልም ነው። ነገር ግን መንግስቷ ይህንን ክብር እና ሃላፊነት አስፈላጊ በሆነው ጌጥ ካልጠበቀ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤቱን የሚገኝበትን ቦታ እንደገና መገምገም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
የኢትዮጵያን ያልተገባ ድርጊት ብንኮንንም የአፍሪካ ኅብረት ይህንን አፀያፊ ተግባር በሕብረቱ ፕሮቶኮሎች መሠረት በአስቸኳይ ተዓማኒ እና ገለልተኛ ምርመራ እንዲያደርግ እንጠይቃለን"ይላል(አዩዘሀበሻ)።
👉በርካታ ተጨማሪ መረጃዎች አሉ፣ይህን የቴሌግራም ቻናል ከስር ባለው ሊንክ join በማደረግ እና ለሌሎች በመጋበዝ ይከታተላሉ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አሁን አዲስ አበባ ሲገቡ የፋየናንስ ሚኒስሩ አቶ አህመድ ሺዴ ተቀብለዋቸዋል።
እንደ ደንቡ ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስሩ ነበረ መቀበል የነበረባቸው። በሁለቱ ሀገራተ መካከል በተፈጠረው ውዝግብና መቃቃር ይህ ክፍተት መፈጠሩ ነው የተሰማው።
ሀሰን ሼክ መሀመድ የግዛት አንድነቴ በኢትዮጵያ ተጥሶብኛል የሚል አቤተቱ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ታነሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
#መልካም ዜና ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
የመጨረሻ ዙር የማስታወቂያ ዋጋ !!!! ሊያመልጠዎ የማይገባ
በዘመናዊ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ የግንባታ ጥበብ የሚገነባ
#ለአፓርትመንት ፈላጊዎች ከ602ሺ ጀምሮ
#ከ 5% - 25% ቅናሽ እናደርጋለን።
#ቀድሞ ለመጣ ቤት መርጦ መግዛት ይችላል።
👉👉👉10% ቅድመ ክፍያ
👉👉👉5% እስከ አንድ ወር
✅ ከስትድዮ እስከ ባለ4መኝታ ድረስ
▶️ 56.6ካሬ እና 574ካሬ ስቱዲዮ(studio)
▶️ ከ77.7-98.1 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
▶️ 123.3-155.8 ባለ ሁለት መኝታ
▶️ 151.6- 181.8 ባለ ሶስት መኝታ
▶️ 177.1- 186.9 ባለ አራት መኝታ
❇️ለመኖርያ ምቹ እንዲሁም ውብ በሆነው በመሀል ለቡ መብራት ቅንጡ አፓርትመንቶችን ከዲምሲ ሪልስቴት ፡
❇️ከ27ዓመት በላይ በኮንስትራክሽን ላይ ልምድ ያካበተ ድርጅት
❇️አፍሪካ CDC 2ኪ.ሜ ርቀት፡ ቻድ ኢምባሲ አጠገብ 65,395 ካሬ ላይ ያረፈ ሂልሳይድ ሰፊ መንደር !!ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
❇️ ቢኖሩባቸው ለመኖርያ ምቹ ፣ ቢያከራዩዋቸው በዶላር ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙባቸው እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ቢገዙዋቸው በብዙ የሚያተርፉባቸው
⭐️ ለበለጠ መረጃ
☎️ 0910663740
ላይ አሁኑኑ ይደውሉልን።
0910663740
https://chat.whatsapp.com/CoNCCfdtAMh1Z6m2xKNvnz
/channel/+SNVtxqi2bHBlYWI0
#HousingMarket #ForSale #PropertyInvestment #RealEstateAgent #BuyAHome #SellYourHome #HomeOwnership #HouseHunters #CommercialRealEstate #RealEstateInvestor #HomeDecor #dmc #dmcrealestate