የራሳችሁ ያልሆነን ብር የወሰዳችሁ ብሩን ለባንኩ መልሱ:-ጅማ ዩኒቨርስቲ‼️
የጅማ ዩኒቨርስቲ ባለፉት ቀናት የራሳችሁ ያልሆነ ገንዘብን ከንግድ ባንክ የወሰዳችሁ ተማሪዎች ሊስታችሁ ከንግድ ባንክ እየመጣ ስለሆነና በህግ ተጠያቂ ከመሆናችሁ በፊት አሁኑኑ የእናንተ ያልሆነውን ብር በየትኛውም የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ዛሬው አስገቡ ሲል ዩኒቨርስቲው አሳስቧል።
ዛሬ ጠዋት በዩኒቨርስቲው ውስጥ ከነበሩ የሌላ ባንክ ATM ብር ማውጣት ተከልክሎ ነበር ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
ጥቆማ❗❗👇
👉በዚህ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ❗👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞኛል አለ
በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።
አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ በመሆኑ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እየጠየቅን፣ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።
አሳዛኝ ዜና‼️
የምስራቅ ሸዋ #ወንጂ ከተማ ከባድ ሀዘን ላይ ናት‼️
ነገሩ አንዲህ ነው ከስድስት ቀናት በፊት ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው ይወሰዳል። አጋቾቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ እስከ 600,000 ይጠይቃሉ። የታጋች ቤተሰቦችም ብሩን አሰባስበው ለመክፈል ሲንቀሳቀሱ ብሩን እንዳይከፍሉ በፌደራል ተከለከሉ። አጋቾቹ ብሩ አለመከፈሉን ሲያውቁ የታገቱን ሰዎች ገድለው መንገድ ላይ ይጥሏቸዋል። ዛሬ ጠዋት የአምስት ሰው አስኬረን ወንጂ ከተማ ገብቷል።
አንድ የአዩዘሀበሻ ቤተሰብ እንደገለፀው ወንጂ ከባድ ሀዘን ውስጥ ናት ብሏል(አዩዘሀበሻ)።
👉ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ❗👇👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
አሜሪካ ቴክቶክን ዘጋች።
ቲክቶክ የዜጎቼን መረጃ እየወሰደ ለቻይና ይሰጣል
ዜጎቼ ጊዜያቸውን ቲርኪሚርኪ እንዲያሳልፉ እያደረገች ነው፣
እየተሰለልኩ ነው በሚለረ ነው ኮንግረሱ ውሳኔ ያሳለፈው።
የኢትዮጵያ ቲክቶኮሮች ገቢ ማግኛ መንገዳቸው ተዘጋ
ዩኒ ማኛ፣ ሞጣ
😂
ሰላም ልናገኝ ነው
ንግድ ባንክ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ማባረሩ ተሰምቷል
ባንኩ ከሰሞኑ ሀሰተኛ የትምህርት ሰነድ አቅርበዋል በሚል ከስራ ያባረራቸው ሰራተኞቹ ባለፈው አመት ንግድ ባንኩ ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተወዳድረው በማለፍ በስራ ላይ የነበሩ መሆናቸውን ዋዜማ ሬድዮ ዘግቧል።
ጠቅላዩ ከኦርቶዶክስ የሀይማኖት አባቶች ጋር መወያየታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አሳውቀዋል። ውይይቱ ምን እንደነበረ አልተገለፀም።
Читать полностью…የፎቶ ዘገባ፦ የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 2፤ 2016 “ስትራቴጂካዊ ግምገማ’’ ማካሄድ ጀመረ። የዛሬው ግምገማ፤ የሰላም ሂደቱ “ወሳኝ ሁኔታዎች” በተባሉት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎች እንዲበተኑ ማድረግ እና ከህብረተሰቡ ጋር መልሶ ማዋሃድ እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽን ገልጿል።
የዛሬውን ግምገማ በንግግር የከፈቱት የአፍሪካ ህብረት ሙሳ ፋኪ ማህማት ናቸው። በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ሲደረግ የነበረውን የሰላም ንግግር የመምራት ኃላፊነት ሲወጡ የቆዩት፤ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዛዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆም በግምገማው መክፈቻ ላይ ንግግር አሰምተዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በተመለከተችው የዛሬው መርሃ ግብር ዝርዝር፤ የፌደራል መንግስት፣ የህወሓት፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት እና የታዛቢዎች ተወካዮች በመክፈቻው ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።
የፌደራል መንግስትን በመወከል በዛሬው ግምገማ ከተኙት ውስጥ በቅርቡ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ሬድዋን ሁሴን፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ ይገኙበታል። በህወሓት በኩል የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ ምክትል ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ተገኝተዋል። ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ሰበር ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቢያንስ 40 አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ።
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቢያንስ 40 አመራሮችን ከኃላፊነት እንዳነሳ ብሪጅ ሚዲያ ሰምቷል።
የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ክፍ ለከተማ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የቢሮ ኃላፊዎች እና በሌሎች የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ያሉ እስከ አርባ 40 የሚሆኑ የስራ ኃላፊዎችን እንዳነሳ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።
ብሪጅ ሚዲያ
ቤተክርስቲያን ለመሳለም ከመኪና የወረደው ሹፌር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አለፈ!
በኦሮሚያ ክልል ወለንጪቲ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በር ላይ መኪናውን በማቆም ቸር መልሰኝ ከክፉ ጠብቀኝ መንገዱን ቀና አድርግልኝ ብሎ ለመፀለይ ከቤተክርስቲያኑ ሙድያ ነዋይ ገንዘብ ለማስገባት በማሰብ ቢወርድም በሽፍቶች እዛው ቤተክርስቲያን በር ላይ ሊገደል ችሏል።
ወየ ጉድ!!
በቀን በየካቲት 28/2016 ከቀኑ 9:30
በፊጋ ገብርኤል ኖህ ሪልስቴት ብሎክ J የተከሰተ ክስተት
የቤቱ ባለቤቶች ሀገር ሰላም ነው ብለው በመኖሪያ ቤታቸው ኖህ አፓርትመንታቸው በተቀመጡበት ዘው ብለው ቤታቸው የገቡት የፌድራል ፖሊስ በመምሰል መለዮውን ለብስው ሶስት በመሆን. በገመድ አስረውና ስለት በማውጣት ከሌባው ጀርባ በምታዩት ቢላ በማስፈራራት የተለያዩ ስልኮችና ገንዘብ በመዝረፍ ሊያመልጡ ሲሉ በአፓርታማ ውስጥ በሚኖሩ ነዋሪዎች ርብርብ ሁለቱ ሲያመልጡ አንዱ ተይዟል።
#Via_Inbox
Ahmed Habib Alzarkawi በፌስቡክ ያጋራው መረጃ
ቴሌግራም በሰዓታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዳዲስ ተጠቃሚዎች አገኘ።
ዓለም ላይ ለሰዓታት ፌስቡክ እና ኢንስታግራም መቋረጣቸውን ተከትሎ " ቴሌግራም "ን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መቀላቀላቸውን የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ገለጹ።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተቋረጡበት ባለፉት ሰአታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቴሌግራም ላይ ሲመዘገቡ እና ይዘቶችን ሲያጋሩ ቆይተዋል " ብለዋል።
" ቴሌግራም " ከእነዚህ አገልግሎቶች የበለጠ አስተማማኝ ነው ሲሉም አክለዋል።
" ምንም እንኳን ከሜታ አንድ ሺህ ጊዜ ያነሱ ቋሚ የሆኑ ሰራተኞች ቢኖሩንም በመተግበሪያው ላይ አዳዲስ ይዘቶችን ለማሻሻል እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማከል ፈጣኖች ነን " ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በ2023 ሙሉ ከዓመቱ 525,600 ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌግራምን አገልግሎት ማግኘት ያልተቻለው በአጠቃላይ ለ9 ደቂቃ ብቻ ነው " ያሉ ሲሆን " ይህም 99.999983% ቴሌግራም ስራ ላይ እንደነበር አመላካች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
እንዳላቸው ተናግረዋል።
የፌስቡክ አካውንታችን ከእጃችን ቢወጣ መመለሻው መንገድ ምንድን ነው?
ዳዎን ዲቴክተር የተባለ ድረ ገጽም በመላው ዓለም ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች ፌስቡክ አልሰራ አለ የሚሉ ሪፖርቶችን መቀበሉን አስታውቋል።
ትሪድስ የተሰኘው የትዊተር ተፎካካሪ የሜታ መተግበሪያም አገልግሎት እየሰጠ አይደለም።
የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ሜታ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ በሰጠው ማብራሪያ፤ “ኢንጂነሮቻችን ችግሩን በአፋጠኝ ለመቅረፍ እየሰሩ ነው” ብሏል።
የሜታ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኤንዲ ስቶን፤ በቀድሞ ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ገጽ ላይ፤ ኩባንያው በዓለም ዙሪያ ችግሩ እንዳጋጠመ መረዳቱን አስታውቀዋል።
ሜታ ኩባንያ በአሁኑ ጊዜ ቸግሩን ለመቅረፍ እየሰራ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ያለምንም ችግር እየሰራ ያለው የሜታ መተግበሪያ ዋትስአፕ ብቻ መሆኑን ዳውንዲቴክተር አስታውቋል።
ሜታ በ2021 ተመሳሳይ ችግር የገጠመው ሲሆን፥ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ለስአታት አልሰራ ማለታቸው ይታወሳል።
በስዊዲን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሰደር ዲፕሎማት መኪና ጠጥቶ በመንዳት የባቡር መንገድ ላይ ተቀርቅሮ ተገኝቷል።
ሀገርን የሚያዋርዱ እነዚህ ዲፕሎማቶች ሊጠየቁ ይገባል።
ሁለት መረጃዎች‼️
1.በአማራ ክልል ወልድያ ከተማ ትናንት ጠዋት የከተማው መዘጋጃ ቤት ሀላፊ መገደሉን ተከትሎ ዛሬም የባጃጂ እንቅስቃሴ እንደታገደ ሲሆን ሆርማት ቁርጥ ቤት ባለቤቱን ጨምሮ ጠቅላላ ሰራተኞቹ በሰዓቱ በዚያ አካባቢ የተገኙ መንገደኞች በአካባቢው ያሉ ባለሱቆች ታስረው እስካሁን ድረስ አልተፈቱም ብለዋል።
2. በቆቦ ከተማ የምሬ ወዳጆ 1ቤት የተቃጠለ ሲሆን አንደኛውን ቤት የሀገር ሽማግሌዎች ከመቃጠል ታድገውታል ተብሏል። ቤቱን ማን እንዳቃጠለው የታወቀ ነገር የለም(አዩዘሀበሻ)።
👉በርካታ መረጃዎች አሉ፣ፈጣን መረጃ ያግኙ፣join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
ንግድ ባንክን ምን አጋጠመው?
ከትናንት ለሊት ጀምሮ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየደረሱኝ ነበር፣ መልዕክቶቹም "በርካታ ሰዎች፣ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከንግድ ባንክ ከኤቲኤም እና ከኦንላይን ትራንስፈር በነፃ ገንዘብ ወስደዋል ወይም ትራንስፈር አርገዋል" የሚል ነው።
አንድ ተማሪ እንደጠቆመኝ "እኛ ጋር ጓደኞቻችን ከ100 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሰሩ አሉ። 435ሺ ብር የሰራ ተማሪ አለ በዛች ቅፅበት ምክንያቱም ለሊት ላይ ንግድ ባንክ የፃፍክለትን ብር ያወጣ ነበር። ይህ የሆነው ለሊት ከ6 ሰአት እስከ 9 ሰአት አከባቢ ነበር።"
ሌላ ተማሪ ሲያስረዳ "ለምሳሌ እኔ ጋር 500 ብር ቢኖረኝ ዝም ብዬ ወደ አንተ 50,000 ብር ፅፌ በሞባይል ባንክ ብልክ ዝም ብሎ ይልክ ነበር" ብሏል። ወደ ኢ-ብር የላኩት ልጆች ግን አካውንታቸው ወዲያው እንደታገደባቸው ታውቋል።
አንድ መምህር ደግሞ "እኔ በምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ለሊቱን ሙሉ በዛ ያለ ገንዘብ በኤቲኤምና በትራንስፈር ገንዘብ ሲያስተላልፉ እንደነበር ሰምቻለሁ። ይህም ነገር በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንደነበር ስለሰማሁ ጥቆማ ልስጥህ በሚል ነው የጻፍኩልክ" ብለዋል።
ይህን ተከትሎ ባንኩ "በሲስተም ችግር ምክንያት" አገልግሎቶቹ ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል ብሏል።
የባንኩን የስራ ሀላፊዎች በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም፣ ባንኩ ግን ምን እንደተከሰተ ዝርዝር መረጃ ለህዝብ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Elias Meseret
ከትግራይ ተወካዮች ከተባሉ ሰዎች ጋር ጠቅላዩ በቤተመንግስት ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ መከላከያ ሚኒስትሩና የጊዜያዊ መስተዳደሩ ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል።
የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት በፓርላማ ተነሳ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓርላማ አባል የሆኑትን የአቶ
ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሳ። ምክር ቤቱ የፓርላማ አባሉን የህግ ከለላ ያነሳው በሁለት ተቃውሞ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ ነው።
አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ስር የዋሉት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ባሳለፈበት ዕለት ሐምሌ 28፤ 2015 ነበር። ላለፉት ሰባት ወራት በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) የፓርላማ ተወካይ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው፤ የፍትህ ሚኒስቴር በፍርድ ቤት ክስ ሊመሰርትባቸው በመሆኑ ነው።
የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ በዛሬው ስብሰባ ለተገኙ 245 የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ፤ አቶ ክርስቲያን በጸረ- ሽብር እና በወንጀል ህግ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ "የሚያስከስስ ከባድ ወንጀል" በመፈጸም መጠርጠራቸውን ገልጸዋል። የፓርላማ አባሉ "ከጸረ- ሰላም ኃይሎች ጋር ትስስር በመፍጠር" በአማራ ክልል ቋሪት እና ደጋ ዳሞት አካባቢዎች "በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር መመሪያ መስጠታቸው" በምርመራ መዝገቡ መረጋገጡን ዶ/ር ጌዲዮን አስረድተዋል።
ጥቃቱ "የሰው ህይወት ያስከፈለ" እና "የንብረት ወድመት" ያስከተለ መሆኑንም የፍትህ ሚኒስትሩ አክለዋል። አቶ ክርስቲያን "መመሪያ ሰጥተውባቸዋል" ከተባለባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው ቋሪት፤ አብንን በመወከል ለፓርላማ መቀመጫ ተወዳድረው ያሸነፉበት ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ታክሎበታል]
ፓርላማው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት በነገው ዕለት ሊያነሳ ነው
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ፤ የአንድ የፓርላማ አባልን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው። ምክር ቤቱ በዚህ ስብሰባው፤ የተጓደሉ የምክር ቤት ጉዳዮች ማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለማሟላት የሚቀርብለትን የውሳኔ ሃሳብም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ልታገኝ ባሰበችው የባህር በር ምትክ ለሱማሊላንድ ልትሰጥ ያሰበችውን የሀገር እውቅና ለመተው እያሰበች እንደሆነ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ነው።
እኔም ከሰሞኑ በተካፈልኩበት አንድ የዲፕሎማቲክ አባላት መግለጫ ላይ ይህ ጉዳይ የተነሳ ሲሆን "አንድም ከአለም አቀፍ አጋሮች፣ ሀገራት እና ተቋሟት በተሰነዘረ አስተያየት እና በተደረገ ጫና...ሁለትም አሁናዊ አለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ክስተቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሱማሌላንድ እውቅና መስጠት የሚለው ሀሳብ እንደማያስኬድ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግንዛቤ እንደተወሰደ እናውቃለን" የሚል አስተያየት ተሰጥቷል።
በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የመግባብያ ስምምነቱ ተግባራዊ ቢሆን የሁቲ አማፅያንን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ መፍትሄ እንደሆነ ተደጋግሞ የተነሳ እንደነበር፣ ይህም ከዩናይትድ ኪንግደም አቋም ጋር ቢመሳሰልም ዩኬ ሀሳቧን ወደ መሬት ለማስረገጥ እንዳልቻለች ይጠቅሳሉ።
በሱማሌላንድ በኩል በዚህ ዙርያ እስካሁን አስተያየት ያልተሰጠ ሲሆን ከዚህ ቀደም ግን 'እውቅና ከሌለ ስምምነቱም የለም' (No recognition, no deal!) ብለው ደጋግመው ተደምጠው ነበር።
Image via Bloomberg
መረጃው የኤሊያስ መሰረት ነው 👆
የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሀርቫርድ የሚኒስትሮች አመራር ፕሮግራምን በዳይሬክተርነት መቀላቀላቸው ታውቋል
በኮቪድ ወቅት በሳል አመራር በመስጠት የሚታወቁት ዶ/ር ሊያ የሀርቫርድ የሚኒስትሮች አመራር ፕሮግራምን (Harvard Ministerial Leadership Program) በአሜሪካን ሀገር በሀላፊነት ደረጃ መቀላቀላቸው ታውቋል።
የዛሬ 12 አመት ገደማ የተቋቋመው ይህ ፕሮግራም በጤና፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት እና ሌሎች ዘርፎች ለአፍሪካ፣ ደቡብ-ምስራቅ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን እስካሁን ከ66 ሀገራት የተውጣጡ 262 ሚኒስትሮች ተሳትፈውበታል።
ዶ/ር ሊያ በሚኒስትርነት ወቅታቸው ከስራ ባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም እኔ በግሌ እስከማውቀው ከሚድያ ሰራተኞች ጋርም ተናበው በመስራት አርአያ የሆኑ ናቸው።
ይህን በግሌ ያጋጠመኝን ላንሳ. ኮቪድ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ የውጭ ተጓዦች በአስገዳጅ ሁኔታ ኳረንቲን በሚገቡበት ወቅት የሆነ ነው።
አንድ ምሽት (እኩለ ለሊት ገደማ) ማህበራዊ ገፆቼን የሚከታተል በግሌ ከማላወቅው ግለሰብ "አባቴ አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ኳረንቲን ገብቶ ይገኛል፣ የስኳር በሽተኛ ነው። ከፍተኛ ህመም እንደተሰማው ቅድም ነግሮኝ ነበር፣ መድሀኒት እንኳን የሚሰጠው የለም። ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስደውልልለት ስልኩ አይሰራም፣ ህይወቱ አልፎ ይሆን ብለን ተጨንቀናል" ብሎ መልዕክት ላከልኝ።
ሆቴሉን ጨምሮ ወደማውቃቸው ሰዎች ስደውል "ማንም ሰው ኳረንቲን መግባት አይችልም ተብለናል" የሚል ነበር።
በመጨረሻም መልዕክቱን ለዶ/ር ሊያ በለሊት ላኩላቸው። ወዲያውኑ ወደ ሆቴሉ አምቡላንስ አስልከው ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ፣ የግለሰቡ ህይወት ባይተርፍም የእርሳቸው ከፍ ያለ ትብብርን ግን አስታውሳለሁ።
ኤሊያስ መሰረት
የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በአንድ ቀን 20 ቢሊዮን ዶላር ማጣቱ ተገለጸ
የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በአንድ ቀን 20 ቢሊዮን ዶላር ማጣቱ ተገለጸ፡፡
በትናንትናው ዕለት በሜታ ኩባንያ ስር የነበሩት ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ኢንስታግራም ትሬድስ የተሰኙት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጠው ነበር፡፡
በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ላይ በገጠመው በዚህ እክል ምክንያት የሜታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ መቀነሱ ተገልጿል፡፡
በፌስቡክ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ከአገልግሎት ውጪ የሆነበት ዕለትም የትናንትናው ማለትም የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ሆኖ ተመዝግቧልም ተብሏል፡፡
በእነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ምክንያት በርካቶች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው እንደተጠለፈባቸው መደምደሚያ ላይ የደረሱ ሰዎች እና ተቋማትም ቀላል እንዳልነበር መናገራቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ መስተጓጎል ምክንያትም አንድ የሜታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ የ7 ነጥብ 7 ዶላር ዋጋ ቅናሽ እንዳሳየ ሲገለጽ በአጠቃላይ በአንድ ሰዓት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር አጥቷል ተብሏል፡፡
የሜታ ኩባንያ አጠቃላይ ሀብት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ከዋትስ አፕ ውጪ ያሉት ቀሪ መተግበሪያዎች አገልግሎታቸው ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጦ ነበር፡፡
የሜታ ኩባንያ መተግበሪያዎች በመላው ዓለም ያጋጠመ ቢሆንም በአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና ፣ ሜክሲኮ እና ግብጽ ብዙ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎት ውጪ ሆነው ነበር ተብሏል፡፡
ዘገባው የአል ዐይን ነው!!
የሂዩመን ራይትስዋች መግለጫ
የኢትዮጵያ መንግሥት የኦነግ ቃል አቀባይ ባቴ ኡርጌሳንና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞችን እያዋከበ ነው ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ።
ድርጅቱ «ማንም ሰው ከዘፈቀደ እስርና በቁጥጥር ስር ከመዋል የሚያመልጥ አይመስልም» ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ ከአስር ቀናት በፊት ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ ባቴ ኡርጌሳ እስከ ነገ በእስር እንደሚቆዩ አቃቤ ሕግ ማሳወቁን ገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲለቀቅ ጥሪ የተደረገለት ጋዜጠኛ ጋሌንዶ ከተያዘበት ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ባለፈው ሐሙስ ተለቆ ወደ ሀገሩ መሄዱን ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታዉቋል።
ይሁንና ከጋዜጠኛዉ ጋር አብረው የታሰሩት የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ባቴ ኡሮጌሳን ግን መንግሥት በአሸባሪነት ከፈረጀዉ ከኦሮሞ ነጻ አውጭ ጦር ጋር አላቸው በተባለው ግንኙነት ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አቃቤ ሕግ ባለፈው አርብ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ማሳወቁንና እስከ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ወደ ተያዙበት ቦታ መመለሰቸውን የመብት ተማጋቹ ድርጅት ጽፏል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የፓርላማ አባሉን አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ መንግሥትን የሚተቹ 5 ሌሎች ፖለቲከኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ያስታወሰው ሂዩመን ራይትስ ዋች እነዚህ የቅርብ ጊዜ እስሮች በኢትዮጵያ ማንም ሰው ከዘፈቀ እስርና በቁጥጥር ስር መዋል እንደማያመልጥ የሚያሳይ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ አጋሮችም እነዚህ «የተሳሳቱ» ያላቸውን እስሮች እንዲያወግዙና መንግሥት ሰላማዊ ጥያቄና እንቅስቃሴዎችን ለማስተናገድ ፈቃደኛ አለመሆኑን እንዲቃወሙ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢቢሲ አማርኛ ዛሬ የሰራውን "አየር መንገዱ በሶማልያ አየር ክልል መብረር አቆመ" የሚል ዘገባውን የተሳሳተ ነው ብሏል።
ግዜው ግን የመረጃ ነው፣ Flight Radar ላይ እንደሚታየው ሁሉም የአየር መንገዱ የመንገደኞች በረራዎች በጅቡቲ በኩል እየተከናወኑ ነው፣ ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት የነበረ የበረራ መስመር ነው።
ባይሆን የጭነት (ካርጎ) በረራዎች በሶማልያ የአየር ክልል መብረር አልቆሙም ቢል ይሻላል። አስተባብል ተብሎ ከላይ ተነግሮት ሊሆን ይችላል፣ እውነታው ግን ይኸው ነው።
#FactsFirst
ኤሊያስ መሰረት
ባህርዳር በአምስት አቅጣጫ መከላከያና ፋኖ ጦርነት እያደረጉ ነው።
ከተማው የከባድ መሳሪያ ድምፅ እየተናወጠ ነው።
ወደ ባህርዳር የሚካሄደው በረራ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል!
ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ዛሬ ማለዳ እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ 4 በረራዎች መደረግ ነበረባቸው፤ ነገር ግን እስከ አሁን ምንም አይነት በረራ አልተደረገም
1ኛ.12:50 ሰአት ET 294
2ኛ.1:10 ሰአት ET 126
3ኛ.1:35 ሰአት ET 194
4ኛ. 2:00 ሰአት ET 186
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም “ዳኛው ይነሱልኝ” ብሎ በመጠየቁ አንድ ሺሕ ብር እንዲቀጣ ተፈረደበት
ጋዜጠኛ ተመስን ደሳለኝ የቀረበበትን ይግባኝ ከሚመለከቱት ዳኞች መሃል የግራ ዳኛው አቶ መሐመድ አሕመድ ከዚህ ቀደም በዚሁ መዝገብ በሰጡት የተሳሳተ ትዕዛዝ ምክንያት “በቀጣይ ትክክለኛ ፍትሕን ሊሰጡኝ ስለማይችሉ ይነሱልኝ” ሲል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ በዛሬው ቀን ትእዛዝ ሰጥቶበታል፡፡
ተመስገን ቅሬታውን ያቀረበው ጥር 7 ሲሆን፤ ውሳኔ ለመስጠት ለጥር 28 ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁንና፣ በጥር 28ቱ ቀጠሮ እንዲነሱ “አቤቱታ የቀረበባቸው ዳኛ ስልጠና ላይ ስለሆኑ ውሳኔ አልሰጠንም” በሚል ለዛሬ የካቲት 21 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከችሎት እንዲነሱ ቅሬታ የቀረበባቸው ዳኛ “አልነሳም” ብለዋል፡፡
በዛሬው ቀጠሮም፣ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ሸምሱ ሲርጋጋ በንባብ ባሰሙት ትዕዛዝ “እንዲነሱ የተጠየቁት ዳኛ መልካም ስብዕና ያለቸው መሆኑን” በመጥቀስ ጥያቄውን ውድቅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ትእዛዝን በተመለከተ አስተያየቱን የገለጸው ጋዜጠኛ ተመስገን “የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እኔን ስጋት ላይ የጣለ ነው” ብሏል፡፡ ጋዜጠኛው ለዚህ ቅሬታው “መሰረታዊ ነው” ያለውንም ነጥብ አስቀምጧል፡፡ “ያቀረብኩት አቤቱታ፣ ዳኛው ከዚህ ቀደም በሰጡት ትዕዛዝ ዐቃቢ ሕግ ያልጠየቀውን ዳኝነት እንዲካተት አድርገው ከሳሽን ያለአግባብ በመጠቅማቸው፣ እኔን ጉዳት ላይ የሚጥል ትዕዛዝ መስጠታቸውን የተመለከተ ነው፡፡ ስለዚህም ፍርድ ቤቱ በቀረበለት ቅሬታ መሰረት ‹ዳኛው ስህተት ሠርተዋል ወይስ አልሠሩም?› ወይም ‹ከሳሽ ያለአግባብ ጠቅመዋል ወይስ አልጠቀሙም?› የሚለውን መመርመር ሲገባቸው፤ ይህን ዋንኛ ጉዳይ ወደጎን ብሎ የቀድሞ ስብእናቸውን መነሻ በማድረግ ቅሬታዬን ውድቅ መደረጉ እጅጉን አስደንግጦኛል፡፡” ብሏ