ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጥር ወር በአማራ ክልል መራዊ ከተማ የተፈጸመ “የጅምላ ግድያን” አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግስት ቸልተኛነት ለከፋ ጉዳት አጋላጭ ሆኗል በማለት ወቅሷል።
በአማራ ክልል ጥር 21 ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በነበረበት ዕለት ከ50 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን መረጃ አግኝቻለሁ ያለው የመብት ድርጅቱ፤ ከ20 የሚበልጡ አስክሬኖች በመንገድ ላይ ተጥለው የሚያሳይ የሳተላይት ምስል ዛሬ አጋርቷል።
“የኢትዮጵያ መንግስት ተአማኒነት ያለው ጥረት አለማድረጉ የተገደሉት ቤተሰቦች ፍትህ እንዳያገኙ፣ መሰል ወንጀሎች ለመከላከል እንዳይቻልና ለከፋ ጉዳት የሚያጋልጥ ሆኗል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ወቅሷል።
ከሦስት ሳምንታት በፊት የመራዊ ጥቃትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን ለኢትዮጵያ መንግስት መላኩን ያስታወቀው ድርጅቱ፤ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ እና እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግድያው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ለፋኖ የሚዋጉ ሰዎችን ቤት ለቤት በመፈለግ እንደወሰዱ እና አንዳንዶችን ደግሞ ያሉበትን እንዲጠቁሙ በማስገደድ ከቤት እየወሰዱ እንደገደሉ አመልክቷል።
ከአንድ ዓመት በፊት የመንግስታቱ ድርጅት መርማሪዎች ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየው ትግራይ ክልል ብቻ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከ48 በላይ “ትላልቅ” ግድያዎች ተፈጽመዋል።
ይኹን እንጂ ጥር 24 ቀን 2016 ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች በተመለከተ የፌደራል መንስግቱ “ተገቢውን እርምጃ በእርሱ በኩል” መውሰዱን እንዳስታወቀ አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር።
ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ “በጸጥታ አካላት” ከተያዘ በኋላ ነው የተገደለው- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት
ግድያው “ባልታወቁ ሰዎች” የተፈጸመ ነው- የኦሮሚያ ክልል መንግስት
ሚያዝያ 03 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ብሎ የሚጠራው ቡድን ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ በኩል ባወጣው መግለጫ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ ካረፉበት ሆቴል እኩለ ሌሊት ላይ “በጸጥታ አካላት” ከተወሰዱ በኋላ ተገድለዋል ሲል ገልጿል።
ኢሰመኮን ጨምሮ ሌሎችም የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ግድያ ነጻ ምርመራ እንዲድረግበት እየጠየቁ ሲሆን... ዝርዝሩን ከድረ ገጻችን https://addismaleda.com/archives/36451 ይመልከቱ
———
የአማራ ህዝብ ዛሬ ከጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ጎን መሆኑ ለማስመስከር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄደ ነው ተብሎ ይህ ፎቶ እየተዘዋወረ ነው። የአማራ ህዝብ የአብይ ዋነኛ ደጋፊ ነበረ። በሚልዮኖች ወጥቶ ደግፎአል። ዛሬ ይህችን የምታክል የመንደር ስብስብ ሰልፍ እንደ ድጋፍ መቁጠር በጣም የሚያስተዛዝብ ነው። መንግስት የአማራ ህዝብን ችግር እና ግጭት በስክነት በመመልከት ወደ ቀልቡ መመለስ አለበት።
Читать полностью…ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ገለጸች።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን ማስከተሉም አይዘነጋም።
ይህንን ተከትሎም ሶማሊያ የተለያዩ ዲፕሎማያው እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ሶማሊያ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር ያባረረች ሲሆን ለውሳኔው መነሻ የሆነው ደግሞ ከሶማሊላንድ ጋር ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ባደረገችው የወደብ ስምምነት ምክንያት ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችንም ዘግቻለሁ ብላለች።
አል ዐይን አማርኛ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢዩ ተድላ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
በተያያዘ ዜና የፑንትላንድ ገንዘብ ሚንስትር መሀመድ ፋራህ የመሩት ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉን ተናግረው ይህ የአዲስ አበባ ጉብኝት ከሰሞኑ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ ነው ሲሉ በዛሬው ሳምንታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባደረጉት የወደብ መግባቢያ ስምምነት ምክንያት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ሆኗል።
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
28ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን 2017-2021 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፉ የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታው እና የፊሲካል አቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲዘጋጅ ለማድረግ፤ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት ለማድረግ፤ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየት እና ለማመላከት የሚያገለግል ማዕቀፍ በመሆኑ ምክር ቤቱ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ የእኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የተደረጉ ለውጦችን በህግ ማእቀፉ ውስጥ ማስገባት በማስፈለጉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ጫና እንዳያርፍባቸው ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
//
#PMOEthiopia
በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ
በመኖሪያ ቤቶች የሚደረገው የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ላይ፤ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በክልሎች በሚቋቋም ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሰረት እንዲከናወን የሚያደርግ አዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ። የተቆጣጣሪ አካሉ “የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች” ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚጸና የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው። በስድስት ክፍሎች እና በሰላሳ ሁለት አንቀጾች የተዋቀረው አዋጁ፤ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ዋጋ፣ ውል የሚቋረጥባቸውን አካሄዶች፣ የተቆጣጣሪ አካል ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም የጥቆማ እና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።
“የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር” የሚመለከተው ይህ አዋጅ ከያዛቸው ድንጋጌዎች መካከል፤ “ነባር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን” የተመለከተው ይገኝበታል። “አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል፤ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት እንዲቋረጥ ካልተደረገ በስተቀር፤ በአግባቡ መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት” በአዲሱ አዋጅ ላይ ሰፍሯል።
ውሉ መመዝገብ እና መረጋገጥ ያለበት፤ በዛሬው ዕለት በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው “ተቆጣጣሪ አካል” በተሰየመ በ30 ቀናት ውስጥ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። ክልሎች የሚመሰረተው አካል፤ የውል ማረ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
😎😎😎
ፎቶ ገጭ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፎቶ ለቋል
ገንዘቤን ወስደው አልመለሱም
ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ለቋል
አሁንም ገንዘቤን ትመልሱ
እንደሆነ መልሱ ብሏል::
ፎቶአችሁ አለ እንዴ እስቲ ራሳችሁን
ፈልጉ
ሴቶቹ 👁️😮
መልሱ………..
📸 ፎቶ ገጭ
🏃🏾♂️😎
🌴🌴🌴
ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች የመረጃ አቦሸማኔ ልጠቀማችሁ❗❗
👉መረጃ ለማድረስ ቴሌግራም ተመራጭ እየሆነ ነው❗👇
ከአራቱም ማዕዘን በአቦሸማኔ ፍጥነት ጥርት ያሉ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን በየደቂቃው የምታገኙበት ነው። የትም ያልተሰሙ ብዙ መረጃዎችን ስለምታገኙ Join አድርጉና ቤተሰብ ሁኑ።
👉ቻናሉን ብዙ ሰው ስለሚከታተለው ምርትና አገልግሎታችሁንም ብታስተዋውቁ ትጠቀሙበታላችሁ።
👇ከስር ባለዉ ሊንክJoin አድርጉ👇
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
ፖሊስ እየወሰዳት ነው !
የመምህርቷን ፎቶ እዚህ ሰፈር እንዳየሁት የወሎ ወንድሜ Fisseha Melese ስልኳን አቀበለኝ እና ደወልኩላት። በወሎ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በተመራማሪነት 12 አመት መስራቷን ነገረችኝ ።
እኔ 👉 ለምን ደሞዝሽ ተቋረጠ ?
እሷ 👉በህመም ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ስራ ስላቋረጥኩ ።
እኔ👉 አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነሽ ?
እሷ 👉አሁን አንተ ስታናግረኝ ፖሊስ መለመን አትችይም ብሎ በመኪና ጭኖ እየወሰደኝ ነው ።መኪና ላይ ሁኘ ነው የማናግርህ።
እኔ 👉የት አካባቢ ነበርሽ ?
እሷ👉አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ነበርኩ ።
እኔ 👉ወደ የት ነው የሚወስዱሽ ?
እሷ 👉ወደ የት እንደሚወስዱኝ አላውቅም ።
ስልኩ ተቋረጠ ።
Via ተስፋዬ ወልደስላሴ
በመጪዉ እሁድ በሸገር ሲቲ የሚገኙ ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጡ በደብዳቤ እንዲሁም በየቤቱ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው ብለዋል።
መጪው መጋቢት 24 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ 6ኛ አመታቸውን ይይዛሉ።
ጥቆማ❗❗👇
👉ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት፣ከስር ባለው ሊንክ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ❗👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ
በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ኮሚሽኑ በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።
በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።
በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጫችን መዘገቡ ይታወሳል ።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች የመረጃ አቦሸማኔ ልጠቀማችሁ❗❗
👉መረጃ ለማድረስ ቴሌግራም ተመራጭ እየሆነ ነው❗👇
ከአራቱም ማዕዘን በአቦሸማኔ ፍጥነት ጥርት ያሉ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን በየደቂቃው የምታገኙበት ነው። የትም ያልተሰሙ ብዙ መረጃዎችን ስለምታገኙ Join አድርጉና ቤተሰብ ሁኑ።
👉ቻናሉን ብዙ ሰው ስለሚከታተለው ምርትና አገልግሎታችሁንም ብታስተዋውቁ ትጠቀሙበታላችሁ።
👇ከስር ባለዉ ሊንክJoin አድርጉ👇
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
/channel/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
በሞጆ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባትና የልጅ ህይወት አለፈ
በሞጆ ከተማ አስተዳደር ሉቦ መጋላ በተሰኘዉ አካባቢ በትናንትናው እለት ከቀኑ 6ሰዓት ገደማ በተከሰተ የእሳት አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በባጃጅ አሽከርካሪነት ስራ ላይ የተሰማራዉ አባት በቤቱ ዉስጥም ቤንዚን ይሸጥ ነበር ብለዉናል።
ከስራ ገብቶ በእረፍት ላይ የነበረዉ አባት አዲሱ ቢራ የ 37 አመት ጎልማሳ ሲሆን ልጅ አብርሃም አዲሱ የ3 አመት ህጻን ነበር። ለአደጋዉ መንስኤ የሆነዉ ሁለት ጄሪካን ቤንዚን በቤት ዉስጥ እንዳለ እናት ምግብ ለማብሰል ለሞከረችበት ወቅት እሳቱ መነሳቱን ነግረውናል።
አደጋዉ ካጋጠመ በኋላ የሶስት አመት ልጁን ለማዳን ወደ እሳት ዉስጥ ገብቷል የተባለዉ አባት እርሱም ሆነ ልጁ ከፍተኛ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በአዳማ ሃይለማርያም ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው በትናንትናው እለት ህወታቸዉ እንዳለፈ ማለፉን የሞጆ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ነጋሽ ለገሰ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በአደጋዉ እናት በሰዉነቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል የተባለ ሲሆን በህክምና ክትትል ላይ ትገኛለች ሲል ብስራት ሬዲዮ ነው የዘገበው።
📲 ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል 🤔?
አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ
/channel/sellphone2777
📞 0929008292
📩 inbox @bina27
📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
0921388158
ጊዮን ሆምስ የጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ አካል በመሃል ከተማ ሌላ ከተማ እየገነባ ይገኛል።
➷ወሎ ሰፈር መስቀል ፍላወር አጠገብ
👉50%የባንክ ብድር የተመቻቸለት
90% የተገነባ መንደር አፓርትመንቶች
በ10 % ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት
ይሁኑ
ባለ 1,መኝታ 96.5ካሬ
ባለ 2 መኝታ 168.9ካሬ
ባለ 3 መኝታ 205ካሬ
➷50 አመት በቢዝነሱ ዘርፍ ልምድ ያካበተው
በውስጡ ስምንት እህት ኩባንያዎችን የያዘ
ጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ
Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w" rel="nofollow">https://youtube.com/@Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግኑኝነት ከፍተኛ ሀላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ መገደላቸውን ኦሜን ዘገበ።
በተወለዱበት መቂ ከተማ ከሆቴል አውጥተው እንገደሏቸው መረጃ ደርሶኛል ብሏል።
ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው
ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል፣ 10 ተማሪዎች ደግሞ መታሰራቸው ተገልጿል።
እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ በፖሊስ የሐይል እርምጃ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።
ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተገደዱት በተለያዩ ችግሮች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከተገለፀላቸው በኃላ ነው።
ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ በነበሩበት ወቅትም ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ ፖሊስ ሰልፉን በሐይል መበተኑ ተማሪዎቹ አስረድተዋል።
Source: Deutsche Welle Amharic
ትዝታ ገረመው ስራ አገኘች፣ ተቀጥራለች።
#FastMereja
ትዝታ ገረመው አዲሱን ስራዋን በኢትዬጲያን ቢዝነስ ሪቪዊ (Ethiopian Business Review) የመረጃ ጥንቅር እና ምርምር ኦፊሰር (Data Researcher) ሆና ሚያዝያ 1 ሥራ ለመጀመር የቅጥር ደብዳቤ ዛሬ ተቀብላለች።
አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?
ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው። “የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።
“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ [ውሉ] ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል። “ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።
“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ከዚህ በተጨማሪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ፤ የአንድ ቤት ባለቤትነት “በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት” ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው “ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራይ በመስጠት ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ እንደሚቻል ማብራሪያው” ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
* * ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ
የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት (ሲኦፒ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ ያደረገው መንግሥት በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ገለጸ።
ኦፌኮ ከጠቅላዩ ጋ የተደረገውን ውይይት እንዲሳተፍ ቢጠየቅም ጥያቄውን አለመቀበሉን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ወስደው ያልመለሱትን ፎቶ የለቀቀበት ድረ ገጹ፤ ሰርቨሩ ትራፊኩን (የጎብኚዎችን ቁጥር) መሸከም አቀቶት ለመክፈት አልተቻለም።
ባንኩ እንዳለው ሃብትና ደንበኛ ብዛት የሰርቨር አቅሙ ይህን ያህል ብቻ መሆኑ አነጋጋሪ ያደርገዋል ተብሏል
ከመጋቢት 30 ጀምሮ ለሚኒባሶች የሚደረገው የነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቋረጥ ተገለጸ
ከዚህ ቀደም የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ባወጣው ዕቅድ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ቀስ በቀስም መንግስት በነዳጅ ምርት ላይ የሚያደርገዉ ድጎማ የማቋረጥ እቅድ እንዳለዉ ይታወቃል፡፡
በሚኒባስ ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገዉ መንግስት ድጎማን የማስቀረቱ አንዱ አቅድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም የድጎማ ስርአቱን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ማህበረሰቡን በሚገባ እያገለገሉ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሰልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖስ ወርቁ ከዚህ ቀደም 170ሺ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርአት ውጪ መደረጋቸዉን ተናግረዋል።
ተሽከርካሪዎቹ ነዳጅ ድጎማን በስርዓት ባለመጠቀማቸው ከድጎማው ውጪ እንዲደረጉ ምክንያት መሆኑ አመላክተዋል።
ከፊታችን መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጅምሮ በነዳጅ ድጎማው ስርአት የሀገር አቋራጭና የከተማ አውቶቢስ ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀው እነዚህም ተሽከርካሪዎችን እስከሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡
የመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ነው
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ "ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው" በማለት የሰራው ዘገባ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው
ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከስራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም፣ በማንኛውም ሁኔታ በተቋሙ ላይ ክስና አሉባልታ አላነሳችም።
በመቀጠል ወደ ዩኒቨርስቲው አንድ ኋላፊ ተደውሎ የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋና በሚስጥር ሊጠበቅላት የሚገባ የግል ጉዳይ "የዐዕምሮ ታማሚ ነች" በመቀጠልም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" እያለ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ ቋንቋዎችን እየተጠቀመ ተቋሙን ባልከሰሰችበት ሁኔታ የግለሰቧን ሚስጥሮች ሲያዝረከርክ ነበር
12 አመት ያገለገለችንና ስራ ማጣቷን ብቻ ገልፃ ትብብር የጠየቀችን ሴት በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" እና "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ መልዕክቶችን ለአደባባይ ማስተላለፍ የተፈለገው የትኛውን ሃገራዊ መልካችንን ለመከላከል ነው?
ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የወረደ ዘገባ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች መረን የቃላት አጠቃቀምና ባልተከሰሱበት ጉዳይ ራስን የመከላከል ጥድፊያ እጅግ የሚያሳዝን ነው
ይህች እህታችን የስራ ቦታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውና እንደተባለውም የዐዕምሮ ህመም ገጥሟቸው ከሆነ ለህመማቸው መነሻና መባባስ የሆኑ ምክንያቶች ከዩኒቨርስቲው የስራ ከባቢ የተወለደ ቢሆንስ? የሸሹት ለጤናቸው ቢሆንስ?
ምንጭ: ሙሉቃል
Fact Check ማለት አንድን አካል ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ግለሰቧን፣ የህክምና ማስረጃ ካላት እሱን፣ የትምህርት ማስረጃዎቿን፣ ዩኒቨርስቲውን... በማናገር መረጃዎችን አመሳክሮ የሚሰራ እንጂ ግለሰቦችን ለማጥቃት የሚከናወን ስራ አይደለም
አሊያስ መሰረት
የጅቡቲ ጎርፍ!...
በጅቡቲ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው እና በልበላ በተባለው አካባቢ ለሊቱን በጣለው ዶፍ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማስከተለሰ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።
የመንገዶቹ መጎደት በጂቡቲ ወደብ ደ ኢትዮጵያ በሚመጡ መኪኖች ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፣ ተብሏል።
የህወሓት ታጣቂዎች በራያ ህዝብ ላይ ከትናንት በስተያ ጠዋት የከፈተው ውጊያ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ በአማራ ሚልሻና በራያ ወጣቶች ቅንጅት አፃፋውን አግኝቶ አሁን ተረጋግቷል ብለዋል። ታጣቂዎቹ ሾልከው በገቡባቸው የራያ አከባቢዎች በተለይ ጨማሮ እና ኮስም በሚባሉ አካባቢዎች የህዝብን ንብረት እና የኮስም 1ኛ ትምሀርት ቤትን ዘርፈውና አውድመው ሄዷል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አንድ መስጊድ ለማቃጠል ሙከራ አድርገው በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል ብለዋል፣የቁርዓን ትምህርት ቤቶችን ግን አቃጥለዋቸዋል ብለዋል፣ያሳዝናል። በጦርነቱ ያ ሁሉ እልቂት ተፈፅሞ እንደገና ሌላ ፀብ መጫር ለትግራይ ህዝብ ይበጀዋል? ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።
አዩዘሀበሻ
ፎቶ:-ከቦታው
ጥቆማ❗❗👇
👉ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት፣ከስር ባለው ሊንክ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ❗👇👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
በአዳባ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ኤጀርሳ ቀበሌ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።
የምዕራብ አርሲ ዞን ትራፊክ ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ከማል አማን እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከጉብሳ ወደ አዳባ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ በመገልበጡ ነው።
በአደጋው ሹፌሩ፣ ረዳቱን እና ከላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።
በሁለት ሰዎች ላይም ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
📌 ላይመለስ ሄዷል | #ነፍስ_ኄር 💔 😢
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት ተሰምቷል ።
ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ፤ ለሀዋሳ ከተማና ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎቱን ሰጥቷል ።
በቅርቡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስርአተ-ጋብቻዉን የፈፀመው ተጨዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትዉልድ ቦታው አርባምንጭ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ህልፈተ ህይወቱ ተሰምቷል ።
የቀብር ስነስርዓቱም በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚፈፀም ታዉቋል ። ለቤተሰቦቹ ፣ ለቡድን አጋሮቹ ፣ ለአድናቂዎቹ እንዲሁም ለመላው የስፖርት አፍቃሪ መፅናናቱን ይስጥልን ።
[ አሟሟቱን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን '' #ራሱን_አጠፋ '' የሚለዉ ከሚወጡት መረጃዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው ]