⭕️ትክክልም እኚህ ናቸው ሰለፎቻችን
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰የሙነወር ልጅ አሁን ከለበት የተምይዕ ሚንሓጅ በፊት የሙብተዲዖችን ስም ማንሳትን የሚጠላን ሰው በተመለከተ የሰለፎችን መንገድንና ግንዛቤያቸውን
ከላይ በፁሑፉ እንደሚታየው አድርጎ ፅፎ
በዚህ የሰለፎች ግንዛቤ ተዕሊቅ ሲያደርግ
ይሄ የተባለው ስማቸው እንዳይነሳ ስለሚፈልገው ነው ።
እራሱን ለነሱ ጠበቃ የደረገውንስ ምን እንበለው ?
ቢድዐቸውን ጥሜታቸውን ስለሚያሰራጨውስ ምን እንበል ?
ብሎ የሙመይዖችን የእንጀራ አባቶቻቸውን እኽዋኖችን ፈልጎበት በማሕበራዊ ሚዲያ ገፁ ለይ ሼር አድጎት ነበር
አሁን ተቅሪበን ከዘጠኝ አመት በኋላ ሟምቶ ተገለበጠና
በፊት ያምንበት የነበረውን ሚንሓጅ እርግፍ አድርጎ በመተው ለእነ አቶ ኢሊያስ እየተከላከለ ሰለፊዮችንና መሻይኾቻቸውን #ሀዳዲይ_ጎጠኞች ወዘተ እያለ በሚንሓጁና በባልቤቶቹ ለይ ይሳለቃል !
ንቃ ወንድሜ በሱፊዮች ዘንድ የሚታወቀው ሙሪድነት አሻሽለህ ይዘህ ለደዕዋው ጠላት አትሁን
የእነ ኢሊያስን ፣ የሙነወር ልጅን የሳደትን እነ የሌሎችንም ሙመይዖችን ሚንሓጅ ለማወቅ አርቆ መሄድ አይጠበቅብህም ቀላሉ መንገድ የድሮውንና የዛሬውን ሚንሓጃቸውን አቅርቦ ማነፃፀር ብቻ ነው
ይኔ ጥሜታቸው እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ይለይልሃል !
አዎ አሁንም በድጋሚ እኚህ ናቸው ሰለፎቻችን
ሀዳዲይ ጎጠኛው የተባልነው እነሱን በመከተላችን
✍ በአቡ ኑህ ሚስባህ ሙሐመድ
/channel/MisbahAsselefy
/channel/MisbahAsselefy
*قَالَ ابو حنيفَة* ‹‹ من قَالَ لَا اعرف رَبِّي فِي السَّمَاء اَوْ فِي الأَرْض فقد كفر وَكَذَا من قَالَ إِنَّه على الْعَرْش وَلَا ادري الْعَرْش
أَفِي السَّمَاء اَوْ فِي الأَرْض ».
*ኢማም አቡ ሀኒፋ እንዲህ ይላሉ፡*
*‹‹ጌታዬ በሰማይ ይሁን በምድር አላውቅም ያለ በእርግጥ ከፍሯል፤ እንዲሁም አላህ ከዓርሽ በላይ ነው ብሎ ዓርሽ ደግሞ ከሰማይ ይሁን ከመሬት አላውቅም ያለም እንዲሁ ከፍሯል፡፡›› ፊቅሁል አክበር 135*
*አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ብቻ ማረጋገጥ በቂ እንዳልሆነና ዐርሽ የት እንዳለ ማወቅም ግዴታ መሆኑን ከኢማም አቡ ሀኒፋ ንግግር እንረዳለን፡፡*
*قَالَ مَالِكٌ: ‹‹ اللهُ فِي السَّمَاءِ، وَعِلْمُهُ فِي كُلِّ مَكَانٍ لاَ يَخْلُو مِنْهُ شَيْءٌ.» سير أعلام النبلاء 8/101*
*ኢማም ማሊክ አንዲህ ብለዋል፡*
*‹‹አላህ ከሰማያት በላይ ነው፤ እውቀቱ ደግሞ በሁሉም ቦታ ላይ ነው ከእርሱም ምንም ነገር አይደበቅም፡፡›› አዕላሙ ኑበላእ 8/101*
*قال لْأَوْزَاعِيَّ: كُنَّا وَالتَّابِعُونَ مُتَوَافِرُونَ نَقُولُ: إِنَّ اللَّهَ فَوْقَ عَرْشِهِ، وَنُؤْمِنُ بِمَا وَرَدَتِ السُّنَّةُ بِهِ مِنْ صِفَاتِهِ جَلَّ وَعَلَا ». العرش للذهبي 2/223*
_ኢማም አል አውዛዒ(157 ዓ.ሂ) ብዙ ታቢዒዮች እያሉ እንዲህ እንል ነበርን፡_
_‹‹ አላህ ከዐርሹ በላይ ነው፤ በአላህ በህሪዎች ዙርያ በመጡት ሱናዎች(ሀዲሶች) እናምናለን፡፡››አል-ዐርሽ 2/223_
*أبو سعيد الدارمي:‹‹ فَاللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى فَوْقَ عَرْشِهِ، فَوْقَ سَمَوَاتِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ، فَمَنْ لَمْ يَعْرِفْهُ بِذَلِكَ لَمْ يَعْرِفْ إِلَهَهُ الَّذِي يَعْبُد›› الرد على الجهمية للدارمي 47*
_ኢማም አቡ ሰዒድ አድ-ዳሪሚ(280ዓ.ሂ)_
*‹‹በረከተ ሰፊ የሆነው አላህ ከዐርሹ በላይ ከሰማያት በላይ ነው፤ ከፉጠራኑ የፀዳ ነው(ባኢኑን ሚን ኸልቂሂ -* *በአላህ ዛት ላይ ከፉጡራኑ የሆነ ነገር የለም፤ ከፉጡራኑ ላይ ደግሞ የአላህ ዛት የለም፡፡) በዚሁ የማያውቀው የሚያመልከዉን አምላክ አላወቀም፡፡›› አር-ረዱ አላ ጀህሚያ 47*
*ابْنِ الْمُبَارَكِ‹‹ قَالَ: قِيلَ لَهُ: كَيْفَ نَعْرِفُ رَبَّنَا؟ قَالَ: «بِأَنَّهُ فَوْقَ السَّمَاءِ السَّابِعَةِ عَلَى الْعَرْشِ، بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ» الرد على الجهمية للدارمي 48*
_ኢብኑ ሙባረክ እንዲህ ብለዋል፡_
*‹‹ጌታችንን እንዴት እናውቀዋለን›› ተብለው ተጠየቁ እሳቸውም እንዲህ አሉ‹‹ እርሱ ከሰማያት ከዐርሹ በላይ መሆኑን እና ከፉጠራኑ የፀዳ መሆኑን(ባኢኑን ሚን ኸልቂሂ - በአላህ ዛት ላይ ከፉጡራኑ የሆነን ነገር የለም፤ ከፉጡራኑ ላይ ደግሞ የአላህ ዛት የለም፡፡) በዚህ ጌታችሁን ታውቁት አላቹህ፡፡›› አር-ረዱ አላ ጀህሚያ 48*
*وقال محمد بن إسحق بن خزيمة - الملقب بإمام الأئمة -: (من لم يقل بأن الله فوق سماواته، وأنه على عرشه بائن من خلقه وجب أن يستتاب، فإن تاب وإلا ضربت عنقه..) درء تعارض العقل والنقل6/264* ኢማም ኢብኑ ኹዘይማ(311__ ዓ.ሂ) እንዲህ ብለዋል
_‹‹ አላህ ከሰማያት በላይ ከዐርሹ ባላይ ነው ከፉጠራኑ የፀዳ ነው (ባኢኑን ሚን ኸልቂሂ - በአላህ ዛት ላይ ከፉጡራኑ የሆነን ነገር የለም፤ ከፉጡራኑ ላይ ደግሞ የአላህ ዛት የለም፡፡) የማይል ሰው ተውበት እንድያደርግ ይደረጋል ከተመለሰ(ጥሩ) ካልሆነ ግን ይገደላል፡፡››ደራኡ ተዐሩድ 6/264_
*مَالِكَ بْنَ دِينَار«اسْمَعُوا إِلَى قَوْلِ الصَّادِقِ مِنْ فَوْقِ عَرْشِهِ»حلية الأولياء وطبقات الأصفياء 2/358*
_ማሊክ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ብለዋል፡_
*‹‹ከዐርሹ በላይ(ሆኖ ያወረደዉን) የእውነተኛዉን ንግግር ስሙ፡፡››ሒልያቱል አውሊያእ 2/358*
*ابن بطة العكبري ‹‹ وَأَجْمَعَ الْمُسْلِمُونَ مِنَ الصَّحَابَةِ وَالتَّابِعِينَ، وَجَمِيعِ أَهْلِ الْعِلْمِ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ أَنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى عَلَى عَرْشِهِ، فَوْقَ سَمَاوَاتِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ، وَعِلْمُهُ مُحِيطٌ بِجَمِيعِ خَلْقِهِ ››الإبانة الكبرى لابن بطة 7/136*
_ኢብኑ በጣህ አል-ዐክበሪ(387ዓ.ሂ) እንዲህ ይላሉ፡_
_‹‹ሙስሊሞች ከሱሀቦች እና ታቢዒዮች፤ ከምእመናን የሆኑ ሁሉም የእውቀት ባለቤቶች ከጉድለት የጠራው አላህ ከሰማያት ከዐርሽ በላይ ሙሆኑን እና ከፉጡራኑ የፀዳ መሆኑን(ባኢኑን ሚን ኸልቂሂ - በአላህ ዛት ላይ ከፉጡራኑ የሆነን ነገር የለም፤ ከፉጡራኑ ላይ ደግሞ የአላህ ዛት የለም፡፡) ተስማምተዋል፡፡ እውቀቱ ሁሉም ፉጡራኑን ያካበበ ነው፡፡›› አል-ኢባና አልኩብራ 7/136_
/channel/+I24JPm3D99hkNmY0
/channel/+b9vHubxXvqtiZTU0
https://chat.whatsapp.com/I1xVRl4Yf6J9s1SIVZs3aV
https://chat.whatsapp.com/I1xVRl4Yf6J9s1SIVZs3aV
ከሞት ሁሉ አሳዛኝ ሞት በርካታ ሰዎችን አሳስቶ መሞት ነው!!
ሞት ለሁሉም አይቀርም ኢስላምን አጥፍቶ መሞት ግን ሁለተኛ ሞት ነው።
ጥፋት የተባለን ሁሉ ተሸክመው የሚሞቱ ሰዎችን ምንም እንደሌለባቸው እንዳውም የነበሩበት ቀና መንገድ እንደነበረ የሚያሰጋቡ ተከታዮችን አፍርቶ መሞት ሶስተኛ ሞት ነው።
አላህ ሆይ፦ ከባድ የሆነ ቅጣህን ለማንም አንመኝም በዲነል ኢስላም ላይ ሲጫዎቱ የነበሩ ሰዎች ገላግለን!!
በሰተመጨረሻም ተገላገልነው የሚለውን የደስታ ቃሌን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ
#አልሀምዱሊላህ_ተገላገልነው!!
~~~~~~~~~~~~~
ውድ በሆነው ሀይማኖታችን በኢስላም ላይ ሲጫዎትና ሲያላግጥ እንዲሁም ሲያወድም የነበረው ታላቁ ሰይጣናዊ ሰባኪ ዩሱፍ አልቀርዷዊይ ከዚህ አለም በሞት ተለየን (ተገላገልነው)
በዚህም ምክንያት ከሱ በኀላ የሚመጣውን የአላህን ርዳታ ከጃዮች ነን!!
قال أنس بن مالك رضي الله عنه :
إذا مات مُبتدع فإنه قد فُتح على الإسلام فتحٌ .
تاريخ بغداد ٤ / ٣٨
አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና ታላቁ ሰሀብይ አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላል
አንድ ሙብተድዕ ሲሞት ለኢስላም በር ይከፈታል (ኢስላም እርዳታ ያገኛል)
( ታሪክ አልበግዳድ 4/38)
ከዛ በፊት ነብያችን (ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም) እንዲህ በለዋል
عن أبي قتادة -رضي الله عنه قال: رسول الله صلى الله عليه وسلم
والعبد الفاجر يستريح منه العباد والبلاد، والشجر والدواب».
(صحيح البخاري 6512)
ከአቡ ቀታዳ ረዲየላሁ ዐንሁ የአላህ መልእክተኛ (ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም)
አንድ አመፀኛ ፋጅር የሆነ ባሪያ (ሲሞት) ከእርሱ፣ ሕዝቦች (የአላህ ባሮች) ሀገሮች፣ ዛፎች እንዲሁም እንሰሳዎች ያርፋሉ።
(ቡኻሪ 6512)
✍ አብዱረህማን ዑመር
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/100080014215983/posts/162785213065285/?app=fbl
ቴሌ ግራም
t.me/Abdurhman_oumer
t.me/Abdurhman_oumer
,
⭕️ አላህ አያዋርደን ነው ነገሩ
=======================
አንድ ከህንድ ሃገር ከመጣ ህንዳዊ ወይም የህንድ ዜጋ ካለው ሰው ጋር ስንጫወት እንዲህ ብሎ አጫወተኝ " እኛ ሃገር ህንድ ላይ ስራ ለመቀጠር በትንሹ ከአራት በላይ ድግሪ መያዝ አለብህ ዶክተሬት በጣም ርካሽ ነው ድግሪ ማስተር መያዝ በጣም ቃላል ነው አብዝሃኛው ማህበረሰብ የተማረ ነው " ብሎ አጫወተኝ እሺ ህንድ ሃገር ላይ የሙስሊሙ ብዛት ምን ያህል ይሆናል አልኩት በጣም ትንሽ ነው ወደ ሁለት መቶ ሚልዮን ይሆናል አለኝ ይህ ማለት የህንድ ህዝብ አስራ አምስት ፐርሰንት አከባቢ ነው የሚገርመው ግን ይህ ቁጥር የኢትዮጵያን ሙሉ ህዝብ ሁለት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው ። ይህ ቁጥር ከኢትዮጵያ አኳያ ብዙ ቁጥር ነው ከህንድ ህዝብ አኳያ ግን በጣም ትንሽ ነው ።
ወደ ጉዳዬ ሲገባ ህንድ ሃገር ላይ ስራ ለመያዝ በትንሹ ከአራት እስከ ስምንት ዲግሪ ማስተርስ PHD እና ሌላም መደርደር አለብህ ። ይህ ማለት እንግዲህ የህንድ ህዝብ ምን ያህል በዘመናዊ ትምህርት በስልጣኔ ጫፍ እንደደረሰ ነው የሚያሳየን ። ለዚህም ነው በሃገራችን ያሉ አብዝሃኛዎቹ ዩንቨርስቲዎች ከውጭ ሃገር ዜግነት ካላቸው መምህራን በብዛት ህንዶት የሆኑት ። ምናልባት በቅርብ ግዜ የሃገራችን መንግስት ሊያስወጣቸው ነው ወይም በሃገራችን ሌክቸሮች መማር አለባቸው የሚልን ህግ አውጥቷል የሚል ሰምቼ ነበር ይፅደቅ አይፅደቅ መረጃው ዬለኝም ። ብቻ የህንድ ህዝብ ምን ያህል በዘመናዊ ትምህርት ጫፍ እንደደረሰ ያሳየናል።
#የሚገርማችሁ ደሞ ድንቅ የሚላችሁ የህንድ ህዝብ ይህን ያህል በዘመናዊ ትምህርት ጫፍ ደረሰ የሚባለው ሰማኒያ ፐርሰንቱ የሚያመልከው ከብትን ነው አስምርልኝ ከብትን ያመልካል አንድ ነጥብ ሁለት ቢልየን (1.2Bilion) ህዝብ ከብትን ያመልካል !! በአንድ መረጃ እንዳየሁት ከሆነ ደሞ በቅርብ ግዜ በሃገረ ህንድ ከባድ ረብሻ ተነስቶ ነበር የረብሻውም ምክንያት ደሞ የከብት ስጋ አይበላ በሚል ዙሪያ ነው ። ከብት ጌታችን ነው የከብት ስጋ አይበላ ... ወላሂ ይህን ሳይ የአንድ ትልቅ ሻይኽ ንግግር ምንኛ አዕምሮዬን ነካው ሸይኽ ጀሚል ዘይኑ ፊርቀቱ ናጂያ ላይ እንዲህ ይላሉ :-
وأي إهانة للإنسان أكثر من أن يرى إلى يومنا هذا مئات الملايين من البشر في الهند يعبدون البقر التي خلقه الله للإنسان لتخدمه وهي الصحيحة ويأكلها وهي ذبيحة
ከዚህ በላይ ውርደት የት አለ ?
እስከግዜያችን ድርሰ በህንድ ሃገር በመቶ ሚልየኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች ጤነኛ እያለች እነሱን ልታገለግላቻው ታርዳ ስጋዋን እንዲበሏት የተፈጠረችላቸውን ላምን ያመልካሉ ከዚህ በላይ ውርደት የት አለ ??
ወላሂ ዬለም !!
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ባለ ግዜ ምንኛ ንግግሩ አማረ ?
وَمَن يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن مُّكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ ۩
አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡
👌 ነገሩ በተማረ አይደለም አላህ በመራው እና ባከበረው ነው ።
---------------------------------------------------
✍ ጅብሪል ሱልጣን
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
/channel/Jebrilsultan
◾️ዱአ ካደረክ በኋላ ፊትህን አታብስ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
☑️ ሸኽ አልባንይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። … (ዱአ ካደረጉ በኋላ) ፊትን ማበስ ትክክል አይደለም። በዚህ ዙሪያ (ማበስ እንደሚቻል) የተወሩ ሀዲሶች ሁሉ ደካማ ናቸው። ዶኢፍ አቢ ዳውድ (263) ና አሀዲስ አስሶሂሀ (59) ላይ እንዳረጋገጥኩት ከፊሉ ከከፊሉ የባሰ የደከሙ ጀዲሶች ናቸው።
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
አንዳንዱማ ዱአ ካደረገ በኋላ በእጆቹ ከፀጉሩ ጀምሮ ሁሉ የሰውነት አካሉ የሚያብስ አለ። ይህም መሰረት የሌለው ተግባር ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል።
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
ስለዚህ አንድ ሰው ዱዓ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ እጆቹ ወደ ቦታቸው ይመልሳቸዋል። ማበሱ ከረሱል ﷺ ያልተገኘ በመሆኑ አንድ ሰው ከዚህ ተግባር ሊቆጠብ ይገባዋል። ይህ ድርጊት ከፊል ዑለማዎች "ቢድዓ ነው" እስከ ማለት ደርሰዋል።
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
/channel/+emfwazn
/channel/+VgzWTJOEeEVkNDNk
መውሊድ
መውሊድ በማህበረሰቡ ላይ ያደረሰው ጉዳት ይህ ነው ተብሎ በቃላት የሚገለፅ አይደለም
ለምሳሌ ያክል፦
💥በሽርክ አማካኝነት በፈጣሪና ፍጡር መካከል ያለውን ሰንሰለት የበጠሰ
💥የተለያዩ የቢድዐ ተግባራት ህዝባችን እንዲላመድ በማድረግ ትንኝ ያረፈችበት ያክል እንኳን እንዳይሰማው እንዲደነዝዝ አድርጎታል
💥ወጣቱን በመውሊድ ላይ በሚሰባሰቡ ሰአት ከሴቶችጋ ኢኽቲላጥ እንዲፈጠርና ዝሙት እንዲስፋፋ እንዲሁም የጫትና መሰል ሱሶች ሰለባ አድርጎታል
💥የእናቶቻችንን መቀነት እያስፈታ መና ያስቀረ በዚሁ ገንዘብ በሽርክና ቢድኣ ገናና ለመሆን እንደ ፋይናነስ ምንጭነት በመጠቀም የደሀዎች ገንዘብ የሚበዘበዝበት
ታዲያ ሱፍዮችና መሰሎቻቸው ሀበሻ የቀናችው በመውሊድ ነው ይሉናል እረ እንዲያውም መውሊድንኮ የአሏህ መልእክተኛ ለጀማ ንጉስ ያዘዙበት የሆነ ተግባር ነው ብላው የሚሰቀጥጥ ንግግር ይናገራሉ
ዛሬ ላይ ለማክበር ሽርጉድ የሚባልልት መውሊድ በዚህ መልኩ በውሸት በተረት ተረት የተገነባ ጃሂሎች ብቻ አሚን ብለው የተቀበሉት ከንቱ ተግባር መሆኑን ጀማንጉስን ከአሏህ መልእክተኛ ለማገናኘት የሞከሩበት ድራማ ግልፅ የሆነ ማሳያ ነው
/channel/AbuSarahh
/channel/AbuSarahh
መውሊድን ዒድ አድርገው የያዙ ሰዎች ዒድ አላደረግነውም ምክንያቱም ዒድ የሚባለው ገላ መታጠብና በዒዱ ምክንያት ተለይቶ የሚሰገድ ሶላት ያለበት ነው ይላሉ።
ለመሆኑ የካፊሮች ዒድ ( በዓል)"ስ በዓል (ዒድ) አይባልምን??
ﻋﻦ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﺭﺿﻲ اﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ، ﻗﺎﻟﺖ: قال ﺭﺳﻮﻝ اﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ: «ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺑﻜﺮ، ﺇﻥ ﻟﻜﻞ ﻗﻮﻡ ﻋﻴﺪا ﻭﻫﺬا ﻋﻴﺪﻧﺎ»
صحيح البخاري 952 ومسلم (892)
ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሀ) እንዳስተላለፈችው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- አቡበክር ሆይ!
ለየሁሉም ህዝብ ዒድ አለው ይህ (ዒደል ፊጥር) የኛ ዒድ ነው
(ቡኻሪ 952) ሙስሊም (892)
ደግሞ ኮሜንት ሲሰጣቸው ሸሪዓዊይ ዒድኮ ነው የማንለው ይላሉ!! እኛምኮ ዒድ አድርጋችሁ ይዛችሁታል እንጅ፣ መረጃ የወረደበት ሸሪዓዊ ዒድማ ቢሆን እኛም እናከብረው ነበር!!
✍ አብዱረህማን ዑመር
/channel/Abdurhman_oumer/3318
✍️ወንድሜ ሆይ⁉️ ግዜህን ልክ እንደ ፈሳሽ ዉሃ አስባት!!
⏱══ ❁✿❁ ════ ❁✿❁ ═══⏲
ግዜ ማለት ልክ 🗑በዚህ ወንፊት ዉሃን እየጨመሩ ነገር ግን ወፊትነቱን ዘንግተውት ያ ውሃ ወፊቱ ወስጥ አለ ብሎ ተተማመኖ መቀመጡ ጉዳት ነው።አዬህ ግዜም እንደዚህ ነው ዛሬ ባለችህ ግዜ ተጠቃሚ ካልሆከ የዛሬዋ ቀንህ ታልፍና ነገን ትተካለች ቀናቶች በተቀየሩ ቁጥር የዱንያ ርዝቅህ እየቀነሰች ትመጣለች በነጋ በመሸ ቁጥሩ እድሜክም እንደዛው ይገፋል አቅም እያጣክ እያረጀክ
ብል በል ዛሬም ሌላ ትላንትም ሌላ ቀንህ ነው ይህን አትርሳ እውቀትን በመቅሰም ላይ በፍፁም አትዘነጋ እደርሳለሁኝ አትበል ምናልባትም በዱንያ ላይ የመኖርህ ቀንህ አልቃ እደርሳለሁኝ እያል ሞት ሊደርስብህ ይችላልና ያለችህን የአሁኗን ግዜህን በአግባቡ ተጠቅመህ ከሙከር ነገራቶች ርከህ እውቀትን ቅሰምባት ለነገው ቤትህ በዚች ባለችህ ሰከንድ ስራባት።
⏱ጊዜን መጣል ከሞት የበለጠ ነው ምክንያቱም ሞት ከሰዎች ይቆራርጥሀል
ነገር ግን ጊዜ መጣል ከአላህና ከመጨረሻው ሀገር ያቆራርጥሀል"⏱
🌹══ ❁✿❁ ════ ❁✿❁ ═══🌹
✍️ምክር ለሰለፊያ ወጣቶች📚
🌹══ ❁✿❁ ════ ❁✿❁ ═══🌹
/channel/+iZB43KRQxRs2Zjhk
ትልቁ ዓሊም አህመድ አነጅሚይ አሉ :
" እወቅ:ላ ኢላሀ ኢላ አላህ (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ያለ አካል እርሱ ከአላህ ውጭ ሌላን እየተማፀነ ከአላህ ውጭ ማንም ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ ማይችለውን ነገር ከእርሱ ጥቅም ያስገኛል ጉዳትም ይከላከላል ብሎ እየከጀለ ፤ ወይም ለእርሱ እየተሰለ ፤ ወይም በስሙ እያረደ ፤ ወይም ለጭንቁ እየጠራው ፤ ጥገኝነት እየጠየቀው ከሆነ ይህ አካል ትልቁን ሺርክ (ማጋራት) አሻርኳል ። በአላህ አንድነት ከሃዲ ነው። ምንም ያክል ቢሰግድ ፣ ቢፆም ፣ ሙስሊም እንደሆነ ቢሞግትም ፣ (ላ ኢላሀ ኢላ አላህ) እያለ በቀን ሰባ ሺ ጊዜ ቢደጋግምም። ከአላህ ውጭ በሚመለኩ ሁሉ እስከሚክድ ድረስ ይህ ንግግሩ ብቻውን በፍፁም አይጠቅመውምና።"
/channel/Menhaj_Alwadih
ኢብሊስ አንድትን ሱጁድ በመተው ሳቢያ ከጀነት ከተባረረ፤ ሶላትን ከናካቴው በመተው በቀን በቀላሉ 34 ሱጁዶችን የተወ ሰው እንደት ይሆን ይሆን⁉️
إبليس طرد من الجنة بسبب سجدة فكيف بالذي يترك في اليوم 34 سجدة؟
رب إجعلني مقيم الصلاة ومن ذريتي ربنا وتقبل دعاء!
@muslimskno
📌የአለባበስ የመዋዋብ ስርዓቶች
🔺ከተከለከሉ ልብሶች አለባበሶች መራቅ
↗️:ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ዱኒያ ላይ የሀር ልብስ የሚለብስ በአኼራ እጣፈንታ የሌለው ነው።
🔺✅ለሴት ግን የተፈቀደ ነው ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ወርቅና ሀር ለሴቶች የተፈቀደ ሲሆን ለወንዶች ግን ክልክል ነው።
📌♻️የወንድ ልብስ ለሴት የሴት ልብስ ለወንድ የተከለከለ ነው
↗️ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ከሴቶች ወንድን የሚመሳሰልና ከወንዶች ሴትን የሚመሳሰል አላህ ከእዝነቱ አባሯል።
📌♻️የሌላ ሀይማኖት ተከታዬችን አለባበስ መልበስ ክልክል ነው።ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ህዝቦችን የተመሳሰለ ከእነርሱ ነው።
✅🔺የወንድ ልብስ ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ ማድረግ
➖➖➖➖➖➖➖
↗️ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለምእንድህ ብለዋል፣
✅🔺 ከቁርጭምጭሚት በታች የወረደ ሽርጥ የእሳት ነው። በሌላም ሀድስ እንድህ ብለዋል ሽርጥህን ከቁርጭምጭሚት በታች የወረደ ሽርጥ የእሳት ነው። በሌላም ሀድስ እንድህ ብለዋል ሽርጥህን ከቁርጭምጭሚት እንዳታወርድ ይህ ከኩራት ነው አላህ አይወደውም።
✅🔺የሴት ልብስ ደግሞ ማስረዘም
➖➖➖➖➖➖
↗️ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ሴት ልጅ አንድ ስንዝር ልብሷን ወደታች ወረድ ማድረግ አለባት በሚሉ ሰዓት ኡሙ ሰለማ እንድህማ ከሆነ እግሯ ይገለጻል አለቻቸው። እሳቸውም ወዲያውኑ እንድህ አሉ በቃ አንድ ክንድ ያርዝሙ ከዚያ እንዳይጨምሩ።
✅🔺ልብስ ሲለበስ የሚከተለውን ዚክር ማለት
➖➖➖➖➖➖➖➖
ال حمد الله الزي كسبانى هذا(الثوب )ورزقنيه من غير حول منى ولاقوة
✅ይህን ልብስ ያለበሰኝና ያለ ብለሀትና ሀያሌ ሲሳይን የለገሰኝ አላህ ምስገና ይገባዋል።
✅🔺አድስ ልብስ ለለበሰ ሰው የሚደረግ ዱዓ
➖➖➖➖➖➖➖➖
<<البس جديدا وعش حميدا ومت شهيدا ويرزقك الله قرة عين في الدنيا والاَ خرة>
✅አድስ ልብስ ልበስ ምስጉን ሁነህ ኑር፣ሸሂድ ሁነህ ሙት ፣አላህ በዱኒያም በአኼራም የአይን ማረፊያ ይለግስህ።))
📌♻️ልብስ ሲለበስ በቀኝ ማስቀዳም
➖➖➖➖➖➖➖
✅አቡ ሑረይራ እንዳሉት ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ቀሚስ ሲለብሱ በቀኝ ቀኛቸው ይጀምሩ ነበር።
♻️ሲወለቅ ግራን ማስቀደም።
@muslimskno
ክብር ለኡለማዎቻችን
➬➬
በዚች ምድር ላይ ትልቅ ክብር የሚገባቸውና ሊንከበከቡ የሚገቡት ኡለማዎቻችን ናቸው። ኡለማዎች ከነብያት በዃላ የዚች ምድር አብሪ ብርሀን ናቸው። ነብያችንም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው የነብያት ወራሽ ብለው መስክረውላቸዋል።
يقول النبي ﷺ في حديثه
وَفضْلُ العَالِمِ عَلَى العَابِدِ كَفَضْلِ القَمَرِ عَلَى سَائِرِ الكَوَاكِبِ، وَإنَّ العُلَمَاءَ وَرَثَةُ الأنْبِيَاءِ، وَإنَّ الأنْبِيَاءَ لَمْ يَوَرِّثُوا دِينَارًا وَلا دِرْهَمًا وَإنَّمَا وَرَّثُوا العِلْمَ، فَمَنْ أَخَذَهُ أَخَذَ بحَظٍّ وَافِرٍ)). رواه أَبُو داود والترمذي.
''የኣሊም (የአዋቂ) ደረጃው በ አላሀን ተገዢ በሆነው ሰው ላይ ጨረቃ በከዋክብቶቾ ላይ እንዳለው ደረጃ ነው፤
ኡለማዎች የነብያቶች ወራሾች ናቸው።
ነብያቶች (ለኡመታቸው) ገንዘብም ሆነ ወርቅ አላወረሱም፤ (ነብያቶች) ያወረሱት እውቀትን ነው። (እውቀትን) የያዘው የፋፋ (የጎለበተ)የሆነን ነገርኔ ይዟል''።
✅ ከዚህ ሀዲስ አስተዋይ ልብ ላለው ብዙ ቁምነገሮችን መያዝ ይቻላል። በጥቂቱ
❶ ኡለማዎች የነብያቶች ምትክ እንደሆኑ
❷ ከኡለማዎች ጠጋ ብለን እውቀትን መቅሰም እንደሚገባን
❸ ሁሉም ነብያቶች አላህ ዘንድ የተከበሩና ትልቅ ደረጃ ሲኖራቸው የነሱ ምትክ የሆኑት ኡለማዎችም ደግሞ አላህ ዘንድ ደረጃ እንዳላቸው። ልናከብራቸውም ይገባል።
❹ እውቀትን መቅሰም እንዳለብን ም/ቱም ከኡለማዎች እውቀትን የያወ ሰው ትልቅን ነገር የያዘ መሆኑ
ከዚህም በላይ አለው ጥቆማ ለብልጦች በቂ ነው
እዚህ ጋር ኡለማ በሚለው የተፈለገበት ኡለማኡል አህሊ ሱነቲ ወልጀምዓዎችን ነው።
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦
يرفع الله الذين آمنوا منكم والذين أوتوا العلم درجات والله بما تعملون خبير
አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
[ ሱረቱ አል-ሙጀድላህ - 11 ]
የእውቀት ባልተቤቶች አላህ ደረጃቸውን ከፍ እንደሚያደርጋቸው ነግሮናል።
يا أخي الحبيب إشتغل نفسك للطلب علم من العلماء السنة قبل أن يرفع، ألم تسمع قول النبي ﷺ ما قاله،
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
((إنّ من أشراط الساعة أنْ يُرفع العلم، ويثبت الجهل، ويشرب الخمر، ويظهر الزنا)).
والمراد به قيل: مراده تعظيم العلم وتوقيره،
በጣም በሚያሳዝን መልኩ በአሁኑ ግዜ ከሱና ኡለማዎች ዘንድ ጠጋ ብሎ እንደመማር የሚሳደብና የሚዛለፍ አልታጡም። ረሱን ጣራ ላይ ከሰቀለ በዃላ ከሱ በላይ ዓሊም፣ፈቂህ እንደሌለ አድርጎ ያስብና ኡለማዎችን ሲዛለፍና ሲያሾፍ ትመለከተዋለሁ። والإياذ بالله عن ذالك
ከዚህ አስቀያሚ ተግባር ተቆጥበን ወደ አላህ እንመለስ። ኡለማዎቻችንን እናክብር እንከባከባቸው።
አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን
አቡ ፈውዛን 27/02/2014
➬➬
/channel/AbuFewzanAselefy
/channel/AbuFewzanAselefy
🌿🌿🌿ጥቆማ🌿🌿🌿
🖊 ስትናገር ለሌሎችንም ለመስማት ጆሮ ስጥ በሰው ለይም ድንበር አትለፍ፤
🖊በምትቆጣበት ጉዳይ ላይ ነጥብ ምረጥ ከቁጣህም ቶሎ ተመለስ፤
🖊ጠንካራ ሁን ስትወድቅ መነሳትንም ልመድ ፤
🖊ይቅር በል በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ያስከትላል፤
🖊 ባለህና በተሰጠህ ተደሰት የጎደለህን እየቆጠርክ ሰላምህን አትጣ፤
🖊አያውቅም እንዳትባል ብለህ ስለማታውቀው ነገር አታውራ፤
🖊ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነተኛ ለመሆን አትሞክር ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ፤
🖊 ከሰው ጋር ስትኖር ቂም ይዘህ አትቆይ ፤
🖊 ሌሎችን አትናቅ ፤ባስተሳሰብህ ሁሌም ከሌሎች የተሻልክ እንደሆንክ አታስብ።
@muslimskno
“በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
~ ~ ~~ ~ ~~~~ ~~~~~~~~~~
እጅግ ከሚገርሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ መጤ ለሆነው መውሊድ ቁርኣንና ሐዲሥ የሚያጣቅሱ ሰዎችን ማየት ነው። ይሄ የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያክል ለቁርኣንና ሐዲሥ ተገቢ ክብር የማይሰጡ፣ ሐያእ የቀለላቸው እንደሆኑ ነው። መውሊድ በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስኮ፦
* ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት በሶሐቦቹ፣ በታቢዒዮቹ፣ በአትባዑ ታቢዒን፣ በታላላቅ ቀደምት ኢማሞች፣ ይከበር ነበር።
* እናንተ እንደምትሉት በሙዞፈር እስከሚጀመር ስድስት ክ/ዘመን መቆየት ሳያስፈልገው በኸሊፋዎቹ ይፈፀም ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ በዚህ ቢድዐ ላይ ውዝግብ ባልተነሳ ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ነቃፊ ዑለማዎች ቀርቶ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዒራቂ፣ ተዝመንቲ፣… ያሉ የመውሊድ ደጋፊዎች ጭምር ቢድዐ ነው ብለው ባልደመደሙ ነበር። ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ የሚገኝ ጉዳይ “ቢድዐ ይባላልንዴ?!”
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ሶላሑዲን አል አዩቢ የባጢኒያ ሺዐዎችን ስርኣት ሲገረስስ በነሱ የተጀመረውን መውሊድም አብሮ ባላቋረጠው ነበር።
እነዚህን እውነታዎች ይዘን ከዚያም እነዚህ አካላት ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናሉ ብለው የሚጠቅሷቸውን የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ብንመለከት ስራቸው አይን ያወጣ ማምታት እንደሆነ እንደመድማለን። ምክንያቱም የሚጠቅሷቸው አንቀፆችና ሐዲሦች መውሊድን የሚጠቁሙ ቢሆኑ ኖሮ በዚያ እንቁ ዘመን ይከበር ነበርና። በዚያ ዘመን መውሊድ አለመከበሩ እነዚህ አታላዮች ለአንቀፆቹ የሚሰጧቸው ትርጓሜዎች የተሳሳቱ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው።
ባጭሩ ለነዚህ አካላት የምንሰጣቸው ጥቅል ምላሽ የትኛውም የቁርኣን አንቀፅ ወይም የሐዲሥ ትርጓሜ ዋጋ የሚኖረው የቀደምቶችን ግንዛቤ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ የነሱን ቃላት እየተጠቀመ አፈፃፀሙ ግን የነሱን አፈፃፀም ያልተከተለ ከሆነ የሰለፎችን ግንዛቤ አልተከተለም ማለት ነው። ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ ረሒመሁላህ ሱብኪ የተባሉት ሸይኽ የሆነችን የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፎች አንድም ባልቀደማቸው መልኩ በመፈሰራቸው የተነሳ ምላሽ ሲሰጧቸው እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“ይሄ ተቃዋሚ ይህቺን አንቀፅ የፈሰረበት መንገድ በርግጠኝነት ውድቅ ነው። ሐቅ ቢሆን ኖሮ (ቀደምቶቻችን) በእውቀትም፣ በተግባርም፣ በማመላከትም፣ በመምከርም ይቀድሙን ነበር። በየትኛውም አንቀፅ ወይም ሱና ላይ በሰለፎች ዘመን ያልነበረ፣ እነሱ ያላወቁትና ለህዝቡ ግልፅ ያላደረጉት የሆነን ትንታኔ መፍጠር አይቻልም። እንዲህ ማድረግ እነሱ በዚህ ላይ ሐቁን ዘንግተውና ከሱም አፈንግጠው ኖሮ ይሄ ዘግይቶ የመጣው ተቃዋሚ አግኝቶታል ማለት ነው።” [አሷሪሙል ሙንኪ፡ 247]
በነገራችን ላይ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣… ያሉ ዓሊሞች መውሊድ በሰለፎቹ ዘመን ያልነበረ ቢድዐ ነው ብለው በግልፅ ሲናገሩ ብዙ ጣጣ ጨርሰውልናል። ምክንያቱም ሰለፎች ለማያውቁት ዒባዳ ቁርኣንና ሐዲሥን ማጣቀስ ስህተት መሆኑ በቁርጥ የሚታወቅ ነውና።
ይህንን ከያዝን በኋላ ሱፍዮች ለመውሊድ ቢድዐ ጠንካራ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን የቁርኣን መልእክት እንመልከት፡-
{قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ} [يونس: 58]
{“በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሃብት በላጭ ነው” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 58]
እና በዚህ ውስጥ መውሊድን የሚደግፍ ምን መልእክት አለ? ብትሉ “በአላህ እዝነትና ችሮታ እንድንደሰት ታዘናል፤ ከእዝነቶችና ችሮታዎቹ ሁሉ በላጩ ደግሞ የነብዩ ﷺ መወለድ ነው። ስለዚህ መውሊዳቸውን ማክበር በዚች አንቀፅ ውስጥ ተካቷል” ይላሉ።
መልስ፡-
=====
አዎ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ችሮታውና እዝነቱ ሲባል ምንድነው የተፈለገው በሚለው ላይ “ቁርኣን”፣ “ዲን”፣ “ኢስላም”፣ “ኢማን”፣ “ከቁርኣን ሰዎች ማድረጉ”፣ “ሱናዎች”፣ “ጀነት” ወዘተ የሚሉ ተፍሲሮችን በቀዳሚነት ብናገኝም ነብያችንንም ﷺ የሚያካትት ይሆናል። ይህንን የሚጠቁም ተፍሲር ኢብኑል ጀውዚ፣ ሲዩጢና ኣሉሲ አስፍረዋል። በርግጥ ሶስቱም በቀዳሚነት ያሰፈሩት ይህንን አይደለም። ሱፍዮች ግን ቀዳሚዎቹን ጥለው እዚህ ላይ ነው የሚያነጣጥሩት። ቢሆንም ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። መልእክቱ ጠቅላይ ነውና እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ውጭ ባሉ የጌታችን ችሮታዎች ጭምር እንደሰታለን፣ እናመሰግነዋለንም። ነገር ግን፦
1. የአንቀጿ መልእክት በነብያችን ﷺ ላይ የተገደበ ባልሆነበት እንዲያውም ሌሎቹ ተፍሲሮች ቀዳሚ በሆኑበት ነጥሎ እሳቸውን ብቻ የታሰቡ አድርጎ ማቅረብ ማድበስበስ ነው።
2. በቁርኣን፣ በሐዲሥ፣ በኢስላም፣ በኢማን፣ ... ለመደሰት አመት መጠበቅ እንደማያስፈልገን ሁሉ በነብዩ ﷺ ለመደሰትም አመት መጠበቅ አያስፈልገንም። ይሄ ሱፍያዊ ተርቲብ ነው። አመት ጠብቆ ያልዘለለ ሰው በነብዩ ﷺ መልላክ አልተደሰተም ብሎ ማሰብም የለየለት ብልግና ነው።
3. የአንቀጿ መልእክት ሙሉ በሙሉ ነብዩን ﷺ የሚገልፅ ነው ቢባል እንኳን አመት ጠብቃችሁ መውሊድ አክብሩ የሚል ጭብጥ በቅርብም በሩቅም የለም። እነዚህ አካላት ግን ካልተጨፈረ ካልተዘለለ ደስታ ያለ አይመስላቸውም። በዚያ ላይ የልደት ቀናቸው በቁርጥ አለመታወቁን ጨምሩበት።
4. የአንቀጿ መልእክት ለመውሊድ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ ቀደምቶች እየተሰባሰቡ መውሊዳቸውን ያከብሩ ነበር። ይሄ ተግባር በዚያ ዘመን አለመፈፀሙ የቁርኣኑ መልእክት መውሊድን ፈፅሞ እንደማያካትት በቁርጥ ያስረዳል።
5. ሰለፎች መውሊድን ያላከበሩት ስላልተመቻቸው ነው የሚለውን ሱፍያዊ ማምታቻ ለጊዜው ብንቀበል እንኳ ሰለፎቻችን ከተፍሲሮቻቸው ያሰፍሩት ነበር። ልብ በሉ የመውሊድ አክባሪዎች ከዘመናት በኋላ መጥተው መልእክቱን ጠምዝዘው ለዚህ ቢድዐ እስከሚጠቀሙበት ድረስ ይህቺን አንቀፅ ለመውሊድ መረጃ ያደረገ አንድ እንኳን የለም። ሙልሀም እንደሆኑ ከተመሰከረላቸው ዑመር፣ ቁርኣንን እንደወረደ መቅራት የፈለገ ከሳቸው እንዲማር የተነገረላቸው ኢብኑ መስዑድ፣ ቱርጁማኑል ቁርኣን ከተባሉት ኢብኑ ዐባስ፣ ከቁርኣን ሰብሳቢው ዑስማንና ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ከነ ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ … የሙፈሲሮች ሸይኽ ከሚባሉት ከሙጃሂድ፣ ከነቀታዳ፣ ከነዶሓክ፣ ከነሻፊዒይ፣ ከነማሊክ፣.. እንዴት ተሰወረ? እነዚህ ሁሉ ያላወቁትን ነው ከዚያ በኋላ የመጣ ትውልድ የሚያውቀው?!
6. በነዚህ ሰዎች ስሌት ከተሄደ የሶሐቦችንም መውሊድ ማክበር ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ሶሐቦች አላህ ለኡማው ከዋላቸው ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። የነብዩ ﷺ ሚኒስትሮችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ነበሩ። ሶሐቦች ለዚህ ኡማ ባለውለታ ናቸው። ቁርኣኑም ሐዲሡም ያለነሱ ወደኛ መድረስ አይችልም ነበር። ስለዚህ አላህ ለኛ ከዋለልን ውለታዎች፣ ከትሩፋቱ፣ ከእዝነቱ ናቸው። አላህ ደግሞ በትሩፋቱና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ስለዚህ የእያንዳንዱ ሶሐባ መውሊድ መከበር አለበት። በተለይ ደግሞ ኹለፋኡ አርራሺዲን። ውለታቸውም ደረጃዎቻቸውም ከፍ ያለ ነውና። ኧረ እንዲያውም በአንቀጿ ውስጥ “ትሩፋቱ” ሲባል የተፈለገው ነብዩን ﷺ ለማለት ሲሆን “እዝነቱ” የሚለው ደግሞ “ዐሊይን ነው” የሚል ዘገባ ከኢብኑ ዐባስ እንደተላለፈ አልኸጢብ እና ኢብኑ ዐሳኪር ገልፀዋል። [ሩሑል መዓኒ፡ 6/133] ከነሱ ቀጥሎ የመጡት ታቢዒዮችም እንዲሁ እነሱስ ባይኖሩ
ይህ ጂላኒ የሚናገረው ቃል በቃል ሲተረጎም፦ (ሰለፍዮችን ሲያናንቅ ጀምሮታል ) ''ከ25 አመት በፊት አንድም ሰው በሰለፍያ ሥር ሁኖ የሚጓዝና እኔ ሰለፍይ ነኝ የሚል የለም ነበር ከሳዑዲ ከየመን ወይም ከደማጅ ካሴት እየሰሙ ነው የጀመሩት
እነሱ እኛ የምንፈልገውን አይፈልጉትም ልክ እንደገለፅከላችሁ እኛ የምንፈልገው በዚህ ሀገር ከሱና/ከኢስላም ተፃራሪዎች ጋር መቀራረብ ነው።
እነሱ ግን ከተፃራሪዎች ጋር ከመቀራረብ ተቃራኒዎች ናቸው።
እነሱ አይረዱም ይሄ ወንድማማች አያደርግም።
በነርሱ ላይ ታገሱ እነርሱ ወጣቶች ናቸው ይመለሳሉ
የነርሱ ሸይኽ ኢልያስ ሰላሳ ምክሮች ብሎ የለቀቀውን ሰምታችሁታል?? ሰላሳ ምክሮች ደርሷችኋል??
ማነው ሚሞሪ ያለው ከኔ ዘንድ አለ የምሰጠው? መዲና የሚኖረው ኢልያስ ሰሰላሳ ምክሮችን ሰጥቷቸዋል። እሱ ከዚህ ነገር ከልክሏቸዋል። እነሱም ሙብተድዕ ነው ማለት ጀምረውታል። ከአቋሙ ወርዶዋል ይሉታል። እሱም (ኢልያስ) ከአስር አመታት በፊት ይሄን አይልም ነበር
ነገር ግን አሁን ክፍተት አለ!! የሳዑዲ ዑለሞችም እየተመለሱ ሰለሆነ ይመለሳሉና ብዙም አያሳስባችሁ!!''
,,
አደገኛ የሆነው የጂላኒ ንግግር ከዚህ ላይ አለቀ!!
-------------
#እኔም_አልኩኝ፦ ሰለፍያ ልትጠፋ ማለት ነው? አላህ ይጠብቀን!!
ለሰለፍያ ጠበቃ መስለን በቃላት ከመዘመር ይልቅ ይሄው ሊያጠፏት ሲነሱ እኛም እንነሳ!!
የሱና ጠላቶች በዚህ መልክ እያጠመዱልን ነው። እኛ እዚህ ግባ በማይባል እልህ ውስጥ ገብተን በመነቋቆር፣ በየጊዜው ሌላ አጀንዳ እንፈጥራል__
#አላሁል_ሙስተዓን_!
✍ አብዱረህማን ዑመር
/channel/Abdurhman_oumer/3440
.
የሙስሊሙ ዓለም
=============>
✅ በአዋቂነታቸውና በታማኝነታቸው የመሰከረላቸው የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ዑለማዎች አላህ ይዘንላቸውና የሚከተለውን ብለዋል፦
↩️ أعظم مصيبة هي وفاة النبي ﷺ توفي النبيﷺ في المدينة يوم الإثنين الثاني عشر من ربيع الأول من السنة الحادية عشرة للهجرة. المصيبة هي أن المسلمين يحتفلون بمولده ﷺ في يوم وفاته.
📚فتاوی اللجنة الداٸمة ٣٨١/٤
➽ከመከራዎች ሁሉ ትልቁና ከባዱ መከራ የአላህ መልክተኛ ﷺ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ነው። የአላህም መልክተኛ ﷺ የሞቱት በረቢዑል አወል ወር ቀን 12 አስረ አንደኛው (11) ሂጅራ ወይም ሂጅራ ባደረጉ 11ኛው አመት ላይ ሰኞ ቀን ነው። አሁን ደግሞ ሙሲባ የሆነው ነገር ሙስሊሞች የመልክተኛውን ﷺ የልደት በዓል በሞቱበት ቀን ማክበራቸው ነው።
📚ፈታዋ አለጅና አዳኢማህ 4/381
🗒ማስታወሻ
↪️ ከላይ ከዑለማወቹ ንግግር እንደምንረዳው የአላህ መልክተኛን ﷺ ማጣት ከመከራዎች ሁሉ ትልቁ መከራ እንደሆነና መልክተኛውም ﷺ የሞቱት በረቢዑል አወል ወር 12ኛው ቀን ሂጅራ ባደረጉ 11ኛው አመት ላይ መሆኑን ነው። ነገር ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር ሙስሊሞች ነብያቸው ﷺ የሞቱበትን ቀን ማዘን ሲገባቸው በአልና መደሰቻ መጨፈሪያ አድርገው መያዛቸው ነው። ይህ የመውሊድ ሰዎች መውሊድ የሚያጋፍሩበት ቀን መልክተኛው ﷺ የሞቱበት እንጂ የተወለዱበት አይደለም። የተወለዱበት ቀንማ በውል አይታወቅም። ነገር ግን ቢታወቅም ኖሮ የተወለዱበትን ቀን ማክበር ስንጥር ታክል ማስረጃ ያልተገኘለት ቢድዐ ነው። በእውነቱ ይህ የኢስላም ጠላቶች ለኢስላም ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ሙስሊሞችን ከቀጥተኛው መንገድ እንዲከረበቱ ለማድረግ በሙስሊሞች ውስጥ ያስገቡት ከኢስላም ጋር የተኳረፈ እኩይ ድርጊት ነው። ሙስሊሞች ሆይ ከሀዲያኖች የነርሱን ሀይማኖት እስካልተከተላችሁ ድረስ ለናንተ መልካም ነገርን እንደማይመክሩ አውቃችሁ በጥንቃቄ ልትቆሙ ይገባል።ስለዚህም ይህ መውሊድ የሚሉት በዐል በኪታብ፣ በሱና በሰለፎች አሳር ውስጥ መሰረት የሌለው መሆኑን አውቃችሁ ልትርቁ፣ ሌሎችንም ልታርቁ ከአላህ ግዴታ ተጥሎባችኋል።
📝አቡ ጀዕፈር ሙሐመድ አሚን
➘➷➴𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨 ⬇️
/channel/Abujaefermuhamedamin
/channel/Abujaefermuhamedamin
لقد مات التكفيري المبتدع يوسف القرضاوي :
✍🏼 قال أنس بن مالك - رضي الله عنه - :
إذا مات مُبتدع فإنه قد فُتح على الإسلام فتحٌ .
📚 |[ المصدر: « تاريخ بغداد » (٤/٣٨٠) ]|
በቲክቶክ በፌስቡክ በተለያዩ ሚድያዎች ተገላልጠሽ የምትወጭዋ እህቴ ሆይ ??
የናንተ ሚያ ላይ ተገላልጦ እየወጡ መጨፈር ዲበር አልፎ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተሰራ ነዉ አሁን ደግሞ በነብያችን ﷺ አልፎ ዘለፋ ስድብ የተለያዬ ነገሮች እየተመለከትን ነዉ
የዚህ" ሁሉ መስኤ እናስተምራለን ብላቹሁ የምትወጡ ሴቶች ያለ እውቀት እየተናገራቹሁ ዲናችችንን ዝቅ እያደረጋቹሁ እያሰደባቹሁ እንደሆኑ እወቁ ብትሰተሪ ኑሮ ይሄ ሁሉ ባልመጣ ነበር.. ወንዶቹ ኡስታዞች አሉ እነሱ ወተዉ ማስተማር እየቻሉ የናንተ ሚድያ ላይ ወቶ መገላፈጥ አይገባኝም ዲን ፓለቲካ አይዴለም እኔ አንች እንደምናወራዉ አይዴለም ማንም ሰዉ ከስሜቱ አመጭቶ የምናገረው ነገር አይዴለም::
~~
እንዲህም እየገባቹሁ ዲናችን በማይፈቅደዉ እየገባቹሁ ጭራሽ እስልምናችን የማትወክሉ ጋጠወጥ ባለጌ ሴቶች አላችሁ ከካሀድያን ጋር የምትላላጡ ቢነግሯቹ የማትሰሙ ስሜታቹሁን ብቻ የምትከተሉ በጣም ዲበር አላፊዎች እስልምናችንን ዝቅ የምታዱርጉ ከካሀድያን ጋር አንድ ለመሆን ዲናችን የማይፈቅደዉን ነገር እያደረጋቹሁ በአላህ ላይ ዲበር እያለፋቹሁ እንድነታችን ይበልጣል የምትሉ አላቹሁ አላህ አንድ ነዉ አይወልድም አይወለድም ብሎ የሚያምን እና አምላክ ሶስት ነዉ ብሎ የሚያምን እንዴት አንድ ሊሆን ይችላል ፈፅሞ አንድ ሊሆን" አይችልም ::አይዴለም ከከሃድያን ካር
ሙስሊም ሁኖ ከሚያሻርከዉ ጋር ሼይኾቼ ደርሱልኝ ነብዬ ድረሱል ከሚለው ሰዉ ጋር እንኳ ፈፅሞ አንድ ልንሆን አንችልም::
ስለዚህ በናንተ እርካሽ ሴቶች ዲናችንን እያሰደባቹሁ ነዉ እባካችሁ ከሌላ እምነት ተከታይ ቤት ሂዳቹሁ ብዙ ነገሮች ትላላችሁ እናንተ በተናገራቹሁ ቁጥር ዲናችንን እያሰደባቹሁ ነዉ መልስ ስትሰጡ እንኳ ያለዉቀት ከመሬት ብድግ እያላቹሁ መልስ እየሰጣቹሁ ነዉ እስኪ ምን ታደርጋላችሁ እካፊሮቹ ግሩፕ ??
በአላህ ላይ ዲበር እያለፉ አንድነት ፈፅሞ የለም አንድ የሚያደርገን ሌላ ነገር አለ አዎ አለ በዲናችን ግን ፈፅሞ አንድ ልንሆን አንችም አሁንም ይሄን ለይተን የማናዉቅ ብዙ አለን
በየኮሜቱ ስር እየሄዳቹሁ ነገር የምትፈልጉ አላቹሁ ንጽጽር የሚሰሩ አሉ እዉቀት ያላቸዉ ኡስታዞች እነሱ ይወዬበት እሱን ለነሱ ተዉት
ከዛ ውጭ እኛ በየኮሜቱ ዉስጥ እየገባን ከካፊር ቤት እየሄድን ለምንድን ነዉ ዲናችንን የምናሰድበዉ???
እስኪ እንማር ቁጭ እንበልና መጀመሪያ " ተውሂድን እንወቅ ዛሬ ሊመመጣብን ጥያቄ እንኳ በተገቢዉ እየመለስን አይዴለም ተዉሂድን በደንብ እንወቅ በደንብ አለመማራችን ነዉ በተለያዬ ሶሻል ሚድያዎች እየገባን ጭራሽ ከእስልምና አስፈጥሮ የሚያሶጣ ንግግር እየተናገርን ያለነዉ ስንናገር በእዉቀት እንናገር
ኧረ ተዉ ልብ እንግዛ በናንተ ምክንያት ዲናችን በተነካ ቁጥር ውስጣችን እየደማ ነው
/channel/+emfwazn
/channel/+VgzWTJOEeEVkNDNk
አንብብ ወዳጄ!!!
قال يحيى بن معاذ رحمه الله:-
من سلك الطريق بلا دليل ضل.
التحف والظرف ( ٥/١)
🔷 የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ – ረሒመሁላሁ – የተባለ ታላቅ ዓሊም እንዲህ ይላል:–
"ያለ መሪ መንገድ የሄደ ሰው መንገድ ይሳሳታል።"
ﻗﺎﻝ اﻟﻘﺮظي – رحمه الله:-
"ليس ﺷﻲء ﺃﻗﺮ ﻟﻌﻴﻦ اﻟﻤﺆﻣﻦ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﺮﻯ ﺯﻭﺟﺘﻪ ﻭﺃﻭﻻده ﻣﻄﻴﻌﻴﻦ ﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ".
تفسير البغوي (٦/ ٩٩) .
↪️ ኢማሙል ቁርጡብይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል፦
"ለአንድ ሙእሚን ባለቤቱና ልጆቹ አላህን ሲታዘዙ ከማየት የበለጠ የአይኑ ማረፊያ የለውም።"
قال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله
"و النَّاس إذا تعاونوا على الإثم
و العدوان أبغض بعضهم بعضاً "
مجموع الفتاوى ( ١٢٨/١٥ ).
👉 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ – ረሒመሁላሁ – እንንዲህ ይላል፦
"ሰዎች በወንጀልና በጠላትነት ከተባበሩ ( መጨረሻው ) አንዱ ሌላውን ይጠላል።"
قال الإمام الشافعي – رحمه الله:-
"ينبغي للرجل أن يَتَوخَّى لصحبَتِه أهلَ الوفَاءِ والصّدقِ، كَمَا يتوَخَّى لوَدِيعَتِه أهل الثقة والأمانَة"
الانتقاء لابن عبد البر ص ( ٩٩ )
➡️ ኢማሙ አሽሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ሰው ለጓደኝነቱ እውነተኛና ቃል ኪዳኑን የሚሞላ መምረጥ አለበት። ለአደራው እውነተኛና ታማኝ እንደሚመርጠው ሁሉ።"عن أنس بن مالك - رضي الله عنه - قال : قال رسول الله - صلى الله عليه وسلم:-
«كلُّ بني آدم خَطَّاءٌ , وخيرُ الخَطَّائِينَ التوابون».
(رواه الترمذي وابن ماجه وأممد بسند حسن)
🔷 አነስ – ረዲየላሁ ዐንሁ – ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም — እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦
"የኣደም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው። ከተሳሳች ሁሉ በላጩ ከስህተቱ ተመላሽ ነው።"
http://t.me/bahruteka
🔷 ኢኽዋኖችና ፈትሕ መካ
የባጢል ሀይሎች ሁል ጊዜ ይዘውት የሚመጡት ባጢል ሰዎችን ለማሳሳት የሐቅ ልብስ ላዩን ያለብሱታል ። ውስጡ ስትገባ ሁሌም ባጢል ነው ። ይህን የሚያደርጉት ላዩም ውስጡም ባጢል ቢሆን ኖሮ ማንም አይሸወድላቸውም ነበር ። ምክንያቱም ባጢልነቱ ግልፅ ስለሚሆን ። ነገር ግን ከሩቅ ከሐቅ ጋር የሚያመሳስለው ነገር ሲኖር ላዩን እያየ ብዙ ሰው ይሸወዳል ። ይህ ነው የሹቡሃት ሚስጢሩ ( ከሀቅ ጋር መመሳሰሉ ) ።
ኢኽዋኖች ማህበረሰቡን ለማስተኛትና የጥመት አንጃዎች ባሉበት ዝም እንዲባሉ ቀብር ሲመለክ ፣ ሙታኖች ድረሱልን እርዱን ሲባሉ ፣ የአላህ ስምና ባህርይ ተዕጢል ሲደረግ ፣ ቁርኣን መኽሉቅ ነው የአላህ ቃል አይደለም ሲባል ፣ ኢማን አይጨምርም አይቀንስም ባለቤቶቹን እኩል ናቸው ተብሉ ሲሰበክ ፣ ሙስሊም መሪዎች በከባኢር ካፊር ሲባሉ ፣ ዝም በሉ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – ከተላኩበት ጊዜ አንስቶ መካ እስከ ከፈቱበት ጊዜ ድረስ ካዕባ ላይ የነበሩትን ጣኦታት አልነኩም ነበር ። የሚል ውዥንብር ይነዛሉ ።
መካ የተከፈተ ቀን ስልጣን በእጃቸው ሲገባ ጣኦታቱን አንኮታኩተው አጋሪያኖችን ወደ ተውሒድ እንዲገቡ አደረጉ ። ስለዚህ ሙስሊሞች ስልጣን እስከ ሚዙ ድረስ ዝም ማለትና አንድ መሆን አለባቸው ።
ሰለፍይ ፣ ጀህሚይ ፣ ቀደርይ ፣ ሙርጂዕይ ፣ ኻሪጂይ ፣ ሙእተዚልይ ፣ ሱፍይ ፣ አሽዓርይ ፣ ኢኽዋንይ ፣ ተብሊጝይ ፣ ሙመዪዕይ ማለት አያስፈልጋቸውም ።
ስልጣን ከያዙ በኋላ ሁሉንም በሀይል ወደ ሸሪዓ ወይም ቁርኣንና ሐዲስ እንዲመጡ ማድረግ ስለሚቻል ይላሉ !!!!! ።
ይህ ነው ማስታወቂያቸው ። ህዝበሙስሊሙን መሸንገያቸው ።
የሀገራችን ኢኽዋኖች በሚገርም መልኩ አሁንም ከመጅሊሱ ወንበር በኋላ የፈለገ መውሊድ ያክብር ፣ የፈለገ ጫት ይቃም ፣ ሱፍይ ፣ ሰለፍይ ፣ ኢኽዋንይ ማለት አያስፈልግም የአዩሁድ ፣ የክርስትናና እስልምና እምነቶች አንድ ለማድረግ እየተሰራ ነው !!! ። ካሉ በኋላ ፈትሕ መካን መረጃ ገርሞ ገርሞ የሚገርም ነው ።
ከዚህ የምንረዳው ህዝበ ሙስሊሙ እንዴት የፈለገ ሰው ወደ ፈለገበት እንደሚነዳው ነው ። ኢስላም ከሌሎች እምነቶች ለየት ከሚያደርጉት ዋና ነጥቦች አንዱ የእውቀት እምነት መሆኑና ሙስሊሞች በመረጃ የሚያምኑና የሚሰሩ ህዝቦች መሆናቸው ነው ።
ለዚህ ነበር ያ ብርቅዬ ትውልድ ዐለምን የገዛው ። ሁሉንም ያነበረከከው ። ታሪክ የማይሽረው ተአምር ሰርቶ ያለፈው ። ሲደክመው ዛፍ ስር በሚተኛ መሪ ምስራቅና ምእራብ ፣ ሰሜንና ደቡብን ያስደመመው ።
ዛሬ ኢኽዋኖች የምእራባዊያን ጩኸት ከመብረቅ በላይ እያስደነገጣቸው ስልጣን ላይ ሲወጡ ሸሪዓ ማቅም አይደለም አላማችን የሚለው የሆነው የመጀመሪያ መፈክራቸው ።
አላህን አስቆጥተው ፣ ህዝቡን አበሳጭተው ምእራቡን ማስደሰት ነው ስራቸው ።
↪️ ጥያቄ ለኢኽዋኖች :–
ይህ ማወናበጃችሁ የምራችሁን ነው ወይስ ሆን ብላችሁ ?
የአላህ መልእክተኛ እውነት መካ ላይ ከሽርክና ፣ ከሙሽሪክ ፣ እንዲሁም ከካፊር አላስጠነቀቁም ? መካ ላይ ላትና መናትን ፣ ሁበልና ዑዛን አይጠቅሙም አላሉምን ? ከመካ ከሀዲያኖች ተበሪ ( ራስን ማራቅ) አላደረጉምን ?
መዲና ላይ ከአይሁዶችና ነሳራዎች እንዲሁም ሙናፊቆች አላስጠነቀቁምን ? ሽርክና ቢዳዓን ፣ ሙሽሪክንና ሙብተዲዕን አላወገዙምን ? ይገርማል !!! ። ምን ታደርጉት ስሜት ልብን ያውራል ።
ለማንኛውም ሰዎች አንገታቸውን የሰጡለት ፣ የተሰደዱለት ፣ ክብርና ንብረታቸውን ከዛ በላይ አጥንትና ደማቸውን ዋጋ የከፈሉለትን እስልምና ከአይሁድና ነስራንያ ጋር አንድ ነው የሚልህን በስሜት የታወረ ኢኽዋንይ ሰምተህ እንዳትሸወድ ።
በሰለፍያ ስም የእነዚህን ደንባሮች ተልእኮ የሚያስፈፅሙትን ሙመዪዓዎች ብዥታ ጆሮ ከመስጠት በመቆጠብ ዐቂዳህን/ሽን ጠብቅ / ጠብቂ የሚለው መልእክቴ ነው ።
http://t.me/bahruteka
" ትርጉሙ ንገረኝ "
ቃሉ አልገባኝም ጆሮዬ ለምዶታል
እኔን ሲያዩኘ ወሀብይ ይሉኛል ፣
እስቲ ልጠይቅህ ቃሉን ያመጣከው
ትርጉም ለሚሰጥህ ቃሉን ለፈሰርከው፣
መንሀጀ ሰለፍይ ሱናን ለጥበቃው
ኒቃብ ለለበሰች ዲና ላፀናችው፣
ልብሱን ላሳጠረ ጺሙን ላስረዘመው
ወሀብይ ይባላል ዲኑን የጠበቀው፣
ንገረኝ በአላህ ይህ ቃል አልገባኝም
ሱና የማይጥምህ የደለብክ በሀራም፣
ባሉባልታ ዜማ ጊዜህ ምታጠፋ
ሸሪያ ምትበርዝ ቢዲዐ ምሰፋ፣
ወሀብይ ምድነው ትርጉሙ ንገረኝ፣
መንሀጀ ሰለፊ የኔ መንገዴ ነው
ለምን ትለኛለህ ቃሉማ ያንተነው፣
ዲንህ የቸረቸርክ ለሼሆች ለድንጋይ ፣
ሸሪዓ ማፅናቴ ቢዲአን መጥላቴ
አጥብቄ ስለ ያዝኩ ስላልሸጥኩ እምነቴ ፣
ካልከኝ ወሀብያ ለኔ ትርጉም የለው
ስሙ አስተካክለው ቃሉን ያመጣከው፣
በሱና የደመኩ የጠራሁ ሙስሊም ነኝ።
《 ከውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው ‼️》
ድንቅ ምክር ከታላቁ ኢትዮጵያዊ
ዓሊም አንደበት
🎙ከሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ
《ሰዎች የአህሉሱና ወልጀመዐን መንገድ ከመከተልና የዚህ ኡማህ ምርጥ ቀደምቶችን (ሰለፎች) አርኣያ ከማድረግ አንፃር ብዙ አይነት ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ በውስጡ አርኣያ አድርጎ የሚከተላቸው አለ። ማለት ከአቂዳህ (ከውስጣዊ እምነት) አንፃር ጤናማ ኢዕቲቃድ (እምነት) ይይዛሉ።ነገር ግን ውጫዊ ገፅታዎችን አስተካክሎ ማቆም ያቅታቸዋል።
ሱናን (የመልዕክተኛውን ፈለግ) በግልፅ አጥብቆ መያዝ ያቅታቸዋል የአህሉሱናንም ተግባር አይተገብሩም።
እንዲያውም በውጫዊ ተግባራቸው አህሉሱናን ከሚፃረሩ አካለት ጋር ይስማማሉ።ለምሳሌ እነርሱ በአቂዳቸው (በአቋማቸው) ሰለፊይ ነን ብለው የሚያምኑ ሆነው ነገር ግን በአደረጃጀት ፣ በተግባርና በእንቅስቃሴ ሌሎች ጀማዓዎችን (አንጃዎችን) ይስማማሉ።
ለዚህ እንደምክንያት የሚጠቀሙት ደግም ሰለፊዮችን ቀዝቃዛ ሰዎች ናቸው ፤ ንቅናቄያዊ አይደሉም ፤ ነሻጣ (ተነሳሽነት) የላቸውም በሚል ሙግት ነው። እንዲህም ይላሉ"እነርሱን በአቂዳ መመሳሰል በቂ ነው። ምክንያቱም እነርሱ በእምነታቸው የተረጋጉና የሚያጣጥሙ ናቸው አቂዳቸው ጤናማ ነውና "። ይህቺ በጣም ትልቅ ምስክርነት ናት።ነግር ግን እነርሱ በንቅናቄ ፣ በአደረጃጀትና በተነሳሽነት እንደሌሎች አይደሉም ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ራሳቸውን በአቂዳ ሰለፊይ በውጫዊ እንቅስቃሴና አደረጃጀት ደግሞ ንቅናቂያዊ እንደሆኑ ይሞግታሉ። ይህም ግልፅ ስህተት (ጥፋት) ነው።
ሰው ውስጡ ውጩን የሚፃረርና ውጩም ውስጡን የሚፃረር ከሆነ ይህች የኒፋቅ ምልክት ናት። ትክክለኛ የቀደምቶችን መንገድ ለመያዝ ውስጣዊ እምነትህ (አቂዳህ) ብቻ አይበቃም። ከሰለፎች መንገድ አንተ በተግባር እያጎደልክና በአፈፃፀም እየተፃረርካቸው ነው። የአቂዳህ ጤናማነት ወደ ተግባር ሊጠራህ የግድ ነው። በጥሩ ማዘዝ ፣ ከመጥፎ መከልከል ፣ ለአላህ ባሮች ተማኝነትና ፣ ለእርቅ መትጋት ይህ ነው ኢስላማዊ ተግባር። አንተ ግን ይህን ተግባር ሰዎችን እንደሚያሸሽ አና እንደሚበታትን አስበህ እንደ ሌሎቹ ጀመዓዎች ሰዎችን ለመቀላቀል (ለመደመር) እና ለማጃጃል ትሞክራለህ። ወይም ያለ ምንም ተግባር አመፅን በማደረጀት እንደ አርባዎቹ ትንቀሳቀሳለህ።የሆነ የተደራጀ ጀመዓ ስለሆነ ብቻ ያንን አደረጃጀት አጥብቀህ ትይዛለህ። ስለዚህ በህጋቸውና በእቅዳቸው መሰረት አየሰራህ ሰለፎችህን በተግባር መከተልህን ትተዋለህ። አንተም በአቂዳ እስከተከተልካቸው ድረስ በውጫዊ ተግባርህ ብትፃረራቸው እንደማይጎዳህ ትገምታለህ። ይህ የለየለት ስህተት ነው። የተሳሳት እይታም ነው።
በውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው። በውስጥ ከአቂዳ አንፃር፤ ከውጭ ደግሞ ከተግባር አንፃር ሰለፊይ ልትሆን የግድ ነው። ተግባርህ ግዴታ ነው።
ከዚህ በላይ ደግሞ ሌሎቹ አንጃዎች እንደሚያምኑት ኢስላማዊ ስራ በመከናወን ውስጥ ለመምከር ፣ ለማቅናት ፣ በጥሩ ለማዘዝ ፣ከመጥፎ ለመከልከል ፣ በቻልከው ልክ ለማስታረቅ መሞከር ለዚህ ዘመን የማይበጅ ነው ብለህ ካመንክ
(ነገሩ የከፋ ነው)። እነርሱ አንደሚያመካኙት ይህ ሰዎችን ያለያያልና ሰዎች በኢስላም ጥላ ስር ፤ በኢስላም ታፔላ (የማስታወቂያ ሰሌዳ) ስር ብቻ ያለተግባር መሰባሰባቸው የግድ ነው ብለህ ካመንክማ ይህች ቢደዓ ናት። የከፋችም ጥመት ናት።
ሰዎችንም ከእውነተኛው የኢስላም ግንዛቤ ማራቅ ነው። ሰዎችንም ማታለል (ማጭበርበር) ነው። ከዚያም ማህበረሰቡ ጃሂል (አላወቂ) እና ለንቅናቄ መሪዎች ጭፍን ተከታይ ሆኖ ይቀራል።ተጠንቀቅ !! አንተ በጤናማ አቋምና የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመረዳትና በመተግበር ላይ አላህ ያደለ አካል ሆይ : ተጠንቀቅ እራስህን እንዳትበታትን። ግማሽህን ከሰለፊዮች ጋር አድረገህ ሌላው ግመሽህን ደግሞ ከንቅናቄ ቡድኖች ጋር አታድርግ። ለመሆኑ ምንድነው ወደዚህ የሚገፋፋህ!?
ሙስሊም ግልፅ ሊሆን ግድ ነው። መልክን መቀያየር ፣ መተጣጠፍና መከረባበት ደግሞ ከኒፋቅ ምልክቶች ውስጥ ነው። ሙስሊም ውስጡና ውጩ ሁሉ አንድ አይነት ነው። አንደዚሁ ነው።
ነገር ግን ከዚህም ጋር ሸይኹል ኢስላም እንደሚናገረው " እነዚያ አህሉሱና ወልጀማዐህን በውስጣቸው የሚገጥሙና ውጫቸውን ደግሞ ማስተካከልና ማቅናት የማይችሉ እነርሱም ከሱና ተፃራሪዎች አደጋ ሰላም አይሆኑም።" ከእነርሱ ሰላም ለመሆን እየሞከርክ በሙጃመላህ ብትመሳሰላቸውም አንኳ ሰላም የለህም። አቂዳህን (አቋምህን) እስካወቁ ድረስ አንተ ሰላም አትሆንም።
ስለዚህ እራስህን ማከፋፈል ይቅርብህ።
ቀጥተኛው መስመር ላይ ፅና። ምክንያቱም አንተ በየትኛውም መልኩ (ከተንኮለቸው) ሰላም አትሆንምና።》
✍ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) ሀፊዘሁሏህ
በቀጥታ ከድምፃቸው ለማዳመጥ
/channel/AbuImranAselefy/3239
በአረብኛ ፅሁፉን ለማግኘት ↙️
/channel/AbuImranAselefy/3240
በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በድምፅ [ኦዲዮ] ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበትን ፋይል ለማግኘት
➴➴➴ 👇👇👇 ↙️↙️↙️
/channel/AbuImranAselefy/3246
➾ዒልምን(ዕውቀትን)በመፈለግ ላይ ኢኽላስ ሊረጋገጥ የሚችለው መቼ ነው?
▪️ዒልምን በመፈለግ ላይ ኢኽላስ ሊረጋገጥ የሚችለው ዒልም ፈላጊው አራት ነገሮችን ሲነይት(ሲያስብ)ነው።እነሱም ፦
1⃣➯ዒልምን በመማር ከራሱ ላይ መሃይምነትን ለማስወገድ ሲያስብ
2⃣ ➯ዒልምን ተምሮ ሌሎችን በማስተማር መሃይምነትን ከሌሎች ላይ ለማስወገድ ሲያስብ፣
3⃣➯ ዒልምን በመማር ዒልም ሳይጠፋ ህያው ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግን ሲያስብ፣
4⃣➯ ዒልምን ተምሮ በተማረው ዒልም ለመስራት ሲያስብ።
📚 من كتاب "تعظيم العِلم" بتصرف
◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
አላህ በሁሉም ስራችን ኢኽላስን ይስጠን 🤲
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:
«… ውሸትን አደራችሁን። ውሸት ወደ አመፅ ይመራል። አመፅ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል።»
[ቡኻሪይ: 6094
ሙስሊም: 2607]
" عليكم بالصدق! فإن الصدق يهدي إلى البر، وإن البر يهدي إلى الجنة، ولا يزال الرجل يصدق ويتحرى الصدق حتى يكتب عند الله صديقًا، وإياكم والكذب! فإن الكذب يهدي إلى الفجور، والفجور يهدي إلى النار"
📜የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች(ሸርጦች)
⚡️شروط لاإله إلا الله
7 ሰባት ናቸው
❶ ዕውቀት العلم፡- ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት እና ቃሉ ዉድቅ የሚያደርጋቸዉንና እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነው፡፡
❷ እርግጠኛነት(اليقين)፡- በአላህ ብቸኛ አምላክነት ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን ነው፡፡
❸ መቀበል(القبول)፡- የላኢላሀ ኢለላህን መልእክት (አላህን በብቸኝነት ማምለክን) ከልብ መቀበልና ለሌላ አካል የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው ነው፡፡ይህንን ያልተቀበለ ግን አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸው እንዲህ በማለት ከገለፃቸው ሙሽሪኮች መደዳ ይሰለፋል፡፡
❹ መታዘዝ(الإنقياد)፡- ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል ለሚያመላክታቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን ነው፡፡
❺ እውነተኝነት(الصدق)፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ እውነተኛ መሆን ማለት ነው፡፡
❻ መውደድ(المحبة)፡- ይህ ማለት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡
❼ ማጥራት (الإخلاص)፡- ይህም ማለት የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፡፡
እንዲሁም በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ ጥቅማጥቅሞችን ከመከጀል፣ ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ መጥራት አለበት፡፡
📜 ‹ሙሐመዱን ረሱሉላህ›የሚለው የምስክርነት ቃል ስድስት መስፈርቶች አሉት
① መሀመድ መልዕክተኛ መሆናቸውን ከልብ ማመን፡፡
② መልዕክተኛ መሆናቸውን በአንደበት መመስከር፡፡
③እርሳቸውን መከተል፡- ትዕዛዛቸዉን መተግበርና የከለከሏቸውን ነገሮች መራቅ፡፡
⑤ ከዚህ በፊት ተከስተው ስለማለፋቸውም ይሁን ወደፊት ስለመከሰታቸው
በመልእክተኛው የተነገሩ ነገሮችን እውነት መሆናቸውን አምኖ መቀበል፡፡
⑤ መልእክተኛውን ከእራስ፣ከገንዘብ፣ከልጆችና ከወላጆች አንዲሁም ከሰው ልጆች ሁሉ
አስበልጦ መውደድ፡፡ ይህም ፈለጋቸዉን በመከተል እና በመተግበር ይገለፃል፡፡
⑥የመልእክተኛውን ንግግር ከማንኛውም ሰው ንግግር ማስቀደምና በእርሳቸው ፈለግ (ሱና) መስራት ናቸው፡፡
👆👆👆እነዚህ ካልተሞሉ ሙሉ ምስክርነት አልሰጠንም፡፡
/channel/Abufurayhan
/channel/Abufurayhan
ይድረስ ለአህባሹ ወሂድ
➪➩➪➩➪➩➪➩➪
የአህባሹ ወሂድ የተደናበረ እይታየአህባሾችን ተግባር ወሂድ የተባለውን ግለሰብ ጨምሮ ላስተዋላቸው በግልፅ እስልምና ላይ እየቀለዱ እንደሆነ ይረዳል።
➽ ወሂድ የተናገረውን ሁሉ ለመዳሰስ ሳይሆን በተደናበረበት አጭር ሀሳብ ላይ ተመስርቼ ጥቂት ነገር ማስታወስ እፈልጋለሁ።
የተደናበረበት ድምፅ ↙️
/channel/AbuImranAselefy/3865
አህባሹ እንዲህ ይላል፦
➘➷➴➘➷➴➘➷"መውሊድን የጀመረው አልመሊኩ ሙዞፈር ነው። ሺዓዎች አይደሉም። ኢብኑ ከሲር ነው መናገር የያዘው የራሳችሁ ሸይኽ ማለት ነው። ታሪኩን እየነገራችሁ ነው። ታሪኩን እየነገራቸው ነው። መፅሃፉ ላይ ፅፎ! እነሱ ግን ታሪክ አይከተሉም። የሚናገሩት ከልቦለዳቸው የሚመነጨውን ነው። የኡለማዎችን መንገድ አንከተልም አሉ። የተከሰቱ ታሪኮችን አንከተልም ቁርአን አንከተልም እንቢ እውነቱን አንሰማም"
አሉ ይላሉ አህባሹ ወሂድ
ከአንደበቱ ለመስማት
➴➘➷➘➷➴
/channel/AbuImranAselefy/3865
✅ መልስ፦ በመጀመሪያ መውሊድን የጀመረው አልመሊኩ ሙዞፈር ነው የሚለውን ነጥብ በተመለከተ ትክክል አይደለም። ምክንያቱም የፋጢሚያ ሺዓዎች እንደጀመሩት የሚያሳዩ የሚያረጋግጡም ጭምር ማስረጃዎች አሉና። መውሊድን ሺዓዎች ጀመሩት የሚለው ስለደበራችሁ ሺዓዎች አልጀመሩትም መዞፈር ነው የጀመረው እያላችሁ ትናገራላችሁ ትቀጥፋላችሁ። ያም ሆነ ይህ መውሊድ በሰዎች የተጀመረ እንጂ በቁርአን በሀዲስ የሌለ አድስ ጅምር መሆኑን አምናችኋል። ወሂድ በራሱ እንደበት መውሊድን የጀመረው መዞፈር ነው ብሏል።
↪️ ሌላው "ኢብኑ ከሲር ነው መናገር የያዘው የራሳችሁ ሸይኽ ማለት ነው። ታሪኩን እየነገራችሁ ነው። ታሪኩን እየነገራቸው ነው። መፅሃፉ ላይ ፅፎ!"
በማለት አህባሹ ወሂድ ይናገራል
✅ መልስ፦ ኢብኑ ከሲር ረሂመሁሏህ ይህ ቀጣፊ እንደሚለው መውሊድን ሙዞፈር ጀመረው አላለም ኢብኑ ከሲር ያለው ሙዞፈር መውሊድ ያከብር ነበር የሚል መልዕክት ነው። እንጂ በማያሻማ ቃል ሙዞፈር መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ጀመረው አይልም። አለ ካላችሁ የአህባሾች ከሊቀ እስከ ደቂቅ ግልፅ ማስረጃ አንጡ ለማምጣት መቶ አመት እንሰጣቸዋለን።
የራሳችሁ ሸይኽ ነው ላልከው አዎ የራሳችን ሸይኽ ነው። የናንተን አያቶች ደግሞ በመረጃ ራስ ራሳቸውን ብሎ ያራቆታቸው ታላቅ አሊም ነው። እደግመዋለሁ እናንተን ራስ ራሳችሁን የሚል ለኛ ደግሞ አላህ ባገራለት ወደ መልካም ጠቁሞን ያለፈ ምሁር ነው አላህ ይዘንለት!
↪️ ሌላው ደግሞ አህባሹ እንዲህ ይላል፦ "እነሱ ግን ታሪክ አይከተሉም። የሚናገሩት ከልቦለዳቸው የሚመነጨውን ነው።"
ይላል
✅ መልስ፦ ታሪክ ትክክል ከሆነ እንከተላለን ግን እንደ ወሂድ ገልብጠን ሳይሆን በቀረበበት አቅጣጫ እንቀበላለን። ኢብኑ ከሲር መውሊድን ንጉስ ሙዞፈር ያከብር ነበር ብሎ ሲነግረን እኛም ሙዞፈር ያከብር ነበር ብለን እንቀበላለን እንጂ መውሊድን የጀመረው ሙዘፈር ነው በሚል ቀይረን ገልብጠን እንረዳም። ከልቦለዳቸው የሚመነጨውን የሚናገሩ ናቸው ላልከው የአህባሾችን መንጋ እና መሰሎቻቸውን ከሆነ ትክክል ነህ ምክንያቱም መውሊድ ይፈቀዳል ሲሉ ከልቦለድ ባመነጩት እንጂ በቁርአን በሀዲስ ያገኙት መረጃ ኖሮ አይደለም።
↪️ አህባሹ ወሂድ አሁንም እንዲህ ይላል፦ "የኡለማዎችን መንገድ አንከተልም አሉ። የተከሰቱ ታሪኮችን አንከተልም ቁርአን አንከተልም እንቢ እውነቱን አንሰማም"
አሉ
✅ መልስ፦ እኛ ኡለሞችን አንከተልም አላልንም። በእርግጥ ጫት እየቃሙ ለሌላውም እያቃሙ በሬ ወለዴ አይነት ውሸት እየተረኩ በአላህ ላይ እያጋሩ በነብያችን ﷺ ላይ ድንበር እያለፉ ማለትም መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ ብትን ያለውን ሰብሳቢ እያሉ አሮጌ በሬ አርዳችሁ ነብያችንን በአመት አንድ ጊዜ አስታውሱ ብለው የሚፎግሩ ሴት ወንድ በሰለዋት ስም ተደባልቆ በድቤ ድምፅ የሚያስጨፍሩና ሌሎችም መጥፎ ነገሮችን የሚሰሩ ኡለሞችን አንከተልም አንተ ኡለማ ስለምትላቸው እንጂ ኡለማ አይደሉም። ሲቀጥል ታሪኮችን አንከተልም አሉ ትላለህ እንጂ እኛ እንከተላለን መውሊድን ሺዓዎች እንደጀመሩት የሚያመለክት ታሪክ አለ ተቀብለናል። አንተ ነህ ያልተቀበልከው እንደውም በኢብኑ ከሲር ላይ ትቀጥፋለህ! ምክንያቱም ሺዓዎች አልጀመሩትም ብለህ ለማቅረብ ስለፈለክ ኢብኑ ከሲር ንጉሱ ያከብር ነበር ያለውን አንተ ጀምሮታል ብሏል ብለህ ዋሸህ አላህን ፍራ አትዋሽ እንዳንልህ አህባሽ ነህ ምን ይሻልህ ይሆን???
ቁርአንንማ እንከተላለን እንጂ ባንከተልማ እንደናንተው ለመውሊድ እንጨፍር ነበር ግን ቁርአን ላይ ስለሌለ ክልክል መሆኑን አውቀን ታቅበናል። በተቃራኒው እናንተ ናችሁ ቁርአን የማትከተሉት ምክንያቱም በቁርአን የሌለን ጨምራችኋል!!
➴➘➷↙️
በጣም አስገራሚው
ቀጥሎ እንዲህ ማለቱ ነው፦ "ስለዚህ መውሊድን አላህ አዞበታል እንደዚሁም ነብዩ ﷺ አዘውበታል"
አለ አህባሹ
ከአንደበቱ ለመስማት
➘➷➴➘➷➴
/channel/AbuImranAselefy/3865
✅ መልስ፦ ከላይ እንደተነጋገርነው ይህ ብልሹ ልጅ መውሊድ በሙዞፈር እንደተጀመረ አምኖ ሲናገር ነበር። ይህ ማለት መውሊድ የተጀመረው ነብያችን ﷺ ከሞቱ ከ6 መቶ አመታት አካባቢ ቡኃላ ነው። ምክንያቱም ሙዞፈር የሞተው በ630 ሂጅሪያ ነው። ጥሩ በዚህ ከተስማማን ታዲያ መውሊድን መዞፈር ከነብዩ ﷺ ቡኃላ ለአመታት ቆይቶ ሲጀምረው ወህይ መቶለት ነውን?
ምክንያቱም "መውሊድን አላህ አዞበታል።" ብለሃል
መውሊድን አላህ ያዘዘበት በንጉስ ሙዞፈር በኩል ከሆነ ጂብሪል መቶ ነግሮት ነውን?
ልብ በሉ አህባሾች አዎ ካላችሁ ከነብዩ ﷺ ቡኃላ ነብይ አለ እያላችሁ እንደሆነ ተረዱ አይደለም ካላችሁ መውሊድን አላህ አላዘዘበትምና ከመስራት ተቆጠቡ አህባሹ ወሂድም ብልሹ ውሸታም መሆኑን ተረዱ!!!
"እንደዚሁም ነብዩ ﷺ አዘውበታል
" ብለሃል ቀደም ሲል ደግሞ የተጀመረው በሙዞፈር እንደሆነ አስረድተኸን ነበር! ጥሩ ታዲያ ነብያችን ﷺ ሙዞፈርን መውሊድ ጀምር ብለው ያዘዙት በምን መልኩ ነው??? በድብቅ ለሱ እንዲደርሰው አድርገው ነው ልትሉ ይሆን? ይሄማ ግፍ ነው ለሶሃቦች ሳይናገሩ ደብቀው ለሙዞፈር እንደት ይናገራሉ???
ከቀብር ተነስተው መጥተው ጀምር አሉትን??? አደራ አህባሾች አዎ ብላችሁ እንዳታርፉ ለነገሩ አብደላህ አልሃረሪ መውሊድ ያከብር የነበረ ነው ሲሞት ከቀብሩ ወጥቶ በረረ ብሎ ይናገር የለ! ብትሉም አይደንቅም። ግን የኛ ነብይ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሸሪዓቸውን ለባልደረቦቻቸውን በሙሉ አስተላልፈው የሄዱ ነብይ እንጂ ከቀብር እየወጡ ይህንን ስሩ የሚሉ ነብይ አይደሉም ሶላትና ሰላምታ የመልክተኞች መቋጫ በሆኑት ነብዩ ሙሐመድ - ﷺ - በቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይስፈን፡፡
📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን
/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy
የሰኞ ፆም እና መውሊድ
===============
የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦
1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?!!
እናንተኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው።
2. እናንተኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት!!
ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። #አመትጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር አይደለም ወይ?
3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም!!
ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።
4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም!
የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። እስቲ የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላል? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?!! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን?
{يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ} [الحجرات: 1]
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው} [አልሑጁራት፡ 1]
ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782]
5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም!
ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ ቋንቋ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር።
6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም
በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና።
7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም!
በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ ፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም!! እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሑ ሙኽተሶሩል ኸሊል የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ?
ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም።
ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014)
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor