natnaelmekonnen21 | Unsorted

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

181663

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Subscribe to a channel

Natnael Mekonnen

ልዩ መረጃ‼️

ከትናት ጀምሮ አቡና ግንደበረት ሹንቄ የምባል ቦታ ላይ ኦነግ ሸኔ ሸዋና ኦነግ ሸኔ ወለጋ ለሁለት ተከፍለው እርስ በእርስ በመታኮስ ላይ ናቸው:: የአካባቢው ሰው በብዛት ከአካባቢው እየወጣ ሲሆን እስካሁን ድረስ በጃል ሰኚ እና ጃል መሮ የሚመራው ቡድን ለሁለት ተከፍሎ እርስ በእርስ መጨፋጨፉን ቀጥሏል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፕሮጀክቱ ከሚጠበቀው በላይ ውጤታማና ስኬታማ ሆኗል- አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ

የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ኡመር በ300 ሄክታር መሬት ላይ በቤር አኖ ወረዳ በምዕራብ ጎዴይ መስኖ ፕሮጀክት የሩዝ ሰብል ምርትን መስብሰብ ሥራ በይፋ አስጀምረዋል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕርግ አቶ አደን ፋራህ ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የሶማሌ ክልል ም/ኘሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኦስማን ፋራህ፣ የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል።

በሙከራ ደረጃ የተመረተው ሩዝ ውጤታማ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፥ እቅዱም ምርቱን በማስፋት ከውጭ ከሚመጣው ጋር ለመወዳደር እና የምግብ ዋስትናን በራስ መቻልን ለማሳደግ እቅድ ተይዟል።

ከዛሬ አምስት ወር በፊት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ በይፋ የተጀመረው ይሄው የሩዝ ተከላ በአምስት ወራት ውስጥ። ለውጤት በቅቶና ሙከራው ተሳክቶ ዛሬ የምርት መስብሰብ ፕሮግራሙ በይፋ ተጀምራል::

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ በስነስርአቱ ላይ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ከሚጠበቀው በላይ ውጤታማና ስኬታማ መሆኑን ጠቁመው ከለውጡ በፊት 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ብቻ ይገኝበት የነበረው የሶማሌ ክልል የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በተሰራው ሰፊ ሥራ በአሁኑ ወቅት የክልሉ ምርት ከ26 ሚሊዮን ኩንታል በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://youtu.be/eKlVt-80dGY?si=0MFjqfJ_a7ofjxRD

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮው ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ያዘ !

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላይ የአቪዬሽን አሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሐንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው፤ በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።በወቅቱ አየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፤ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

   

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚበቃውን ውሃ ይዞ የተረፈውን በዚህ መልኩ ለታችኛው ሀገራት በማስተነፈሻው በኩል እነሆ ብሎ ለቋል።

አሁን የአባይ ቁልፍ 🔐 መቶ በመቶ ኢትዮጵያ እጅ ገብቷል። እንደሁኔታው ይከፈታል ይዘጋል።

ቼበለው አባቱም ገዳይ
ቼበለው እናቱም ገዳይ
ቼበለው ድርድር አያውቅ
ቼበለው በሃገሩ ጉዳይ
ቼበለው አባይ የግሌን
ቼበለው ባልኩኝ ለጋራ
ቼበለው ካቃራት ምስር
ቼበለው ግፍም ሳትፈራ
ቼበለው የተቆጣ እንደሁ
ቼበለው ፍቅር ታግሶ
ቼበለው የሚባላ እሳት
ቼበለው ይሆናል ብሶ

ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ ደግሞ በአባይ.... ቴዲ አፍሮ 🔐

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ቦሌ ፍላሚንጎ ላይ አዲስ ታሪክ ኢትዩጵያ ውስጥ በእርዝመቱ 2ኛው ህንፃ

+251901978697
+251986687513

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል ባላቸው ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢፌፖሚ):-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል ባላቸው ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ።

ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር በመጣስ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ፡-
- በዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
- በአማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
- በናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
- በኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
- በይዲድያ ነጻነት አበበ እና
- በእሌኒ ክንፈ ተክለአብ በተባሉ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋል የቻሉት በሀገራችን ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም ያሉ የበረራ ባለሙያዎችን በማስገደድ በረራውን ለማስቀጠል በፈጠሩት አምባጓሮና ግርግር ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ የወንጀል ምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድኑ ተጠርጣሪዎቹ ላይ ከተመሠረተባቸው የወንጀል ክስ በተጨማሪ ከፀረ-ሰላም ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ጨምሮ ገልጿል።

በወቅቱ የአየር መንገዱ የደህንነት ኃይሎችና የበረራ ባለሙያዎች በትዕግስት ሁኔታውን ለማርገብ ቢማጸኗቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ አሻፈረን ማለታቸውንም በወንጀል ምርመራ መዝገቡ ተካቷል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ የበረራ ሕግና አሰራርን በመጣሳቸው እንዲሁም በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል በነገው ዕለት ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ፍርድ ቤት ፖሊስ እንደሚያቀርባቸው ታወቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የትግራይ ጊዜያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ሽምሹር አደረጉ።

ፕሬዜዳንቱ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ነሃሴ 14/2016 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ፤ ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን የሚገባቸው ጥቅም ተጠብቆላቸው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጡ አደራ በማለት ያሳስባል።

አዲሱ ተሿሚ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ኽርስቶስ ቀደም ሲል በዞኑ የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል። 

ወ/ሮ ሊያ ከቀናት በፊት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል።

ህወሓት ባካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያልሰጠው ፤ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን " ህጋዊ አይደለም " ያሉት ጉባኤ ካልተሳተፉት መካከል  ፦
- የምዕራባዊ
- የማእከላዊ
- የምስራቃዊ
- የደቡበዊ ዞኖች አስተዳዳሪዎች ይገኙበታል። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው የስልጣን ሹምሽር ያደረጉበት የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ኣስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተሸሙት ወ/ሮ ሊያ ካሳ የተኩት አምስተኛ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ የሚቃወሙ የዞን አስተዳዳሪ ናቸው።

በትግራይ ካሉ 7 የዞን አስተዳደሮች አምስቱ የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን አካሄድ በሚቃወሙ የሚመሩ ሲሆኑ ሁለት ዞኖች ማለትም የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በተካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት  ተኽላይ ገ/መድህን የመቐለ ከተማ ደግሞ በተካሄደው ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆኖው በተመረጡት ይትባረክ ኣማሃና ኤልያስ ካሕሳይ ዋናና ምክትል በመሆን በመመራት ላይ ይገኛሉ።

ቀሪዎቹ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን አካሄድ የሚደግፉ የሁለት ዞን አስተዳዳሪዎች በያዙት ሃላፊነት የቆዩ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። 

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከቀናት በፊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ ተናግረው ነበር።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ነበር ያሉት።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

AlemGenet Real Estate(AG)

በማስታወቂያ ዋጋ
በ 15% ቅድመ ክፍያ

☎️+251901978697
☎️
+251986687513

➣ የ አዲስ አበባ እምበርት በሆነችው
ፍላሚንጎ ዋና መንገድ ላይ  ከ  ባለ 1 መኝታ እስከ ፔንታ ሀውስ  ለሽያጭ ማቅረብ ብቻ አይደለም የቀሩን ቤቶች ውስን ናቸው ይፍጠኑ !

ቤተዎን ጥንቅቅ አድረገን ጨርሰን   ከአንድ አመት ባጠረ ጊዜ እናስረክበዎታለን

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251901978697
☎️
+251986687513

Telegram:- @Mulugeta31
Email
:- ymisganaw99@gmail.com

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ከሚሴ‼️

አማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በነበሩት አቶ አህመድ አሊ ላይ ጥይት ተኩሶ በመግደል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ ከትናንት በስቲያ መገደሉ ተሰምቷል።በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እጅ እንድሰጥ ቢጠየቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ደወይ ሀራዋ በተባለ አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ወዲያው ህይወቱ አልፏል ተብሏል።

ይሄ ልጅ ስሙ አህመድ ሼሁ ይባላል። ከአስተዳደሩ በፊት ታዋቂ ታዋቂ ሰዎችን እንደገደለ በአካባቢው ይነገራል።

በቅርቡም አንድትን እናት ኬሚሴ ላይ እንደገደለ ይነገራል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የጽንፈኛው ቡድን ዛሬ ከቀኑ 9:10 ላይ ባሕር ዳር ህዳሴ ቀበሌ አንድ ባጃጅ ላይ ፈንጂ ለማፈንዳት ሲዘጋጁ ፍንዳታው በራሳቸው እጅ ላይ እዛው ፈንድቷል።

በፍዳታው በሁለቱ የጥፋት ተልዕኮ ፈፃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶል፤ አንድ ተጠርጣሪ አብሮ ተይዟል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZGe3VdWdh/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሠራዊታችን ክፍሎችና የሰራዊቱ የክብር አባላት የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በአንድ ጀምበር በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ላይ የሰራዊቱ ክፍሎችም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
 
የምዕራብ ዕዝ ከነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የችግኝ ተከላውን አከናውኗል። ዕዙ ከ4.5 ሚሊየን በላይ ዛፍ መትከሉና እያደረገ ያለውም ክትትል ከሰላም ጠባቂነቱ ባለፈ በመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መሆኑን የኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ቸርነት ገልፀዋል። ዘገባው የሠማኸኝ ጥላሁን ነው።

የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሰራተኞች በላፍቶ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።

በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ታደሰ መኩሪያ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ የሰራዊታችን ህዝባዊነት መገለጫ መሆኑን አውስተው ጠቅላይ መምሪያው ከችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ባሻገር በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይም በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ዘገባው የማርታ ግርማ ነው።

በተያያዘም የጦላይ ከፍተኛ የባለሌላ ማዕረግተኞች ማሰልጠኛ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ሠልጣኞች ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብሩን ለማሣካት በጊቢ ውስጥ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል። ኃይለማሪያም ተሾመ እንደዘገበው።

የመከላከያ የክብር አባል አቶ ስዩም ተሾመ በበኩላቸው ከሰራዊታችን ጋር ይህን ሀገራዊ ሁነት መሳተፋቸው ትልቅ ክብር መሆኑን አውስተው መርሀ-ግብሩ ህዝብና ሰራዊታችንን ይበልጥ የሚያስተሳስር መሆኑን ገልፀዋል።

ሠራዊቱ በሚገኝባቸው ቦታዎች የተከሉት ለምግብነት የሚውሉና ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ችግኞችን ተንከባክበው ለውጤት እንዲበቁ አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉ በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉ የሠራዊቱና የሲቭል አመራሮችና በችግኝ ተከላው የተሳተፉ አባላት አረጋግጠዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሞቃዲሾ መሣሪያ ጭነው መጡ።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሁለት የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች (አንቶኖቮች) ወደ ሞቃዲሾ አደን አዴ አለም አቀፍ ኤርፖርት መጥተዋል። የመጡ ሲሆን

የጦር አውሮፕላኖቹ ክላሽ እና ስናይፐር የመሳሰሉ የጦር መሳሪያዎችን እንደዚሁም ተተኳሾችን ጭነው እንደመጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የመጡት የጦር መሳሪያዎች በ7 የጭነት ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ መከላከያ ሚኒስቴር መወሰዳቸውን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

12 የሚደርሱ የግብጽ የጦር መኮንኖች መሳሪያውን ይዘው የመጡ ሲሆን ምናልባትም ለሶማሊያ ወታደሮች ስልጠና ለመስጠት ሊቆዩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አለ።
አንዳንድ ምንጮች በገለጹት መሰረት አውሮፕላኖቹ ከላይ ከተገለጹት የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ የግንኙነት መሳሪያዎችንም ጭነው መጥተዋል።

በቀጣዮቹም ቀናት ተመሳሳይ በረራዎች እንደሚኖሩ፣ ወደ ሂራን ክልል ብለደወይን ከተማ እንደሚጓዙ መረጃዎች አመላክተዋል።

አብዛኞቹ የሶማሊያ ግዛቶች የግብጽን ጦር መግባት ገብነት እየተቃወሙ ናቸው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በእነ ዮሀንስ ዳንኤል ላይ የተጠየቀው የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ የግዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሀንስ ዳንኤል ላይ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለጳጉሜ 4 ቀን 2016ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

ከትላንት በስቲያ ፌዴራል ፖሊስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአሜሪካው አምባሳደር በትግራይ የፖለቲካ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ለመምከር ትናት መቀሌ ገብተዋል

በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የሆኑት ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ትኩረት ያደረገ የሶስት ቀን ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም #መቀለ መግባታቸውን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ አስታወቀ።

የአምባሳደሩ ጉብኝት በክልሉ የሚስተዋሉ “የፖለቲካ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት አስፈላጊነትን ለማጉላት” ያለመ ነው ሲል ኤምባሲው ገልጿል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ በማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ መሰረት አምባሳደር ማሲንጋ በትግራይ በሚቆዩባቸው ሶስት ቀናት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ እንደሚመክሩ፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማበረታታ ከሚመለከታቸው የክልሉ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተጠቁሟል።

በአሜሪካን መንግስት ድጋፍ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን፣ በተለይም በጾታዊ ጥቃቶች ሰለባ የሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች የሚደግፍ ፕሮጀክቶች እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል።

የአሜሪካን መንግስት ድጋፍ የሚያደርግባቸውን የቀድሞ የክልሉ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ስራዎችንም እንደሚጎበኙ ኤምባሲው አስታውቋል።

በመቀለ አሉላ አባነጋ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

   

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ቦሌ ፍላሚንጎ ላይ አዲስ ታሪክ ኢትዩጵያ ውስጥ በእርዝመቱ 2ኛው ህንፃ

+251901978697
+251986687513

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Thank you, Mr. President.

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZGe3wGVtJ/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ!

ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በ11 ወራት ውስጥ ለ3ተኛ ጊዜ ሴት መስሎ ሲንቀሳቀስ ተያዘ

በመስከረም ወር 2016ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሴት መስሎ፣እንደ ሴት ተኳኩሎ፣ ጡት ማስያዣ አድርጎ፣ የፈረስ ጸጉር ቀጥሎ፣ ያታለለው ወጣት በሌላ ስፍራ ለሶስተኛ ጊዜ መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከ11 ወራት በፊት ሴት በመምስል በዲማ ወረዳ ተቀጥሮ 2 ቀን ስራ እየሰራ እንዳለ በሰራተኞቹ ጥቆማ ተይዞ እንዲታሰር ቢደረግም ዳግም በተግባሩ ቀጥሎበት እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

በትክክለኛ መጠሪያ ስያሜው ቢንያም ከበደ በወቅቱ እንዲለቀቅ ቢደረግም ከእዚያ ድርጊት ስድስት ወራት በኋላ በመጋቢት ወር 2016ዓ.ም በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ሴት ነኝ ብሎ ህብረተሰቡን ሲያታልል ነበር ለ2ኛ ጊዜ ተይዞ እንዲታሰር የተደረገው።

በሁለቱ አከባቢዎች (በጋምቤላ ከተማ እና በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ) በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ የነበረው ወጣቱ ቢንያም በአሁኑ ወቅት ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ ሴት በመሆን ቀሚስ ለብሶ፣ ጡት ማስያዢያ አድር እና ዊግ በጭንቅላቱ አስሮ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

ግለሰቡ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቦታ እየቀያየር ድርጊቱን ሲፈፅም በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ላይ መያዙ ሶስተኛው እንዲሆን አድርጎታል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZGe3p7r57/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZGe3qyk3f/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የችግኝ ተከላ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል።

„ በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት የተከልናቸው ችግኞች ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ። „ ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ „ ባለፈው አመት ከተተከሉት ችግኞች 50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ ነበሩ። „ ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዋች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ልንደግፍ ይገባል „ ሲሉ ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ቦሌ ፍላሚንጎ ላይ አዲስ ታሪክ ኢትዩጵያ ውስጥ በእርዝመቱ 2ኛው ህንፃ

+251901978697
+251986687513

Читать полностью…
Subscribe to a channel